Forwarded from Tewesta
💥 ለቤትዎ ለቢሮ እንዲሁም ለስጦታ የሚሆኑ የግድግዳ ምስሎች 💥
- የቤቶን ውበት በዕጅጉ የሚጨምሩ
- የፎቶ ጥራታቸው HD የሆኑ
- ጠንካራ ወጥ MDF እንጨት ላይ የሚሰሩ
- መወልወል በሚችል ማቴሪያል ላሚኔት የተደረጉ
- ለሳሎን ፣ ለመኝታ ቤት እንዲሁም ለቢሮ የሚሆኑ
- ለወዳጅ ዘመድ እንደ ስጦታነት የሚሆኑ
- በራሶ ፎቶ መሰራት የሚችሉ
1 ሜትር ከ 50 ሴሜ በ 90 ሴሜ = 3000 ብር
የግድግዳ ምስሎቹን አሁኑኑ በሚፈልጉት ዲዛይን ይዘዙን በ 2 ቀን ውስጥ ሰርተን ያሉበት ድረስ አምጥትን እንገጥማለን፡፡
ብዙዋች ወደውታል እርሶም ይሞክሩት
ለማዘዝ ከፈለጉ በቴሌግራም ያናግሩን
www.tg-me.com/natnaeladane
ወይም ይደውሉ
0922490744

💛አንድ ዓይነት አስተሳሰብ እንዲኖር ከመጠበቅ ድርቅና ይልቅ መልካም አስተሳሰብ እንዲበዛ የመመኘቱ የዋህነት የበለጠ ይጠቅመን ይመስለኛል... በዚያው ልክ 'ልዩነትን' ከምንገልጽበት ስድብ ይልቅ ግንዛቤያችንን የምናኖርበት ስልጡን መንገድ ለአብሮ መኖር ትልማችን ብዙ ያዋጣ ይሆናል
💙ያልተዋጠልህ ነገር እንዳለ ስትገልጽ ሌሎች ያጣጣሙትን እንዲተፉልህ እየጠየቅህ ከሆነ በጎ አይደለም... አንተ ስትለው ትክክል ሌሎች ሲሉት ስህተት የሚባል ነገርም ያስተዛዝባል ፣ ሁሉም ሰው ምንም የማለት ሰዋዊ ችሮታው ቢከበርለት እሻለሁ... "ዘንግህን ማወዛወዝ የምትችለው የሌሎችን አፍንጫ እስካልነካህ ድረስ ነው" የምትለው ደገኛ መርህ ብትጠበቅም ደስ ይለኛል... የማቻቻል ጉዳይ ነው.
❤️The common ground of our humanity is greater and more enduring than the differences that divide us. It is so, and it must be so, because we share the same fateful human condition. We are creatures of blood and bone, idealism and suffering. Though we differ across cultures and faiths, and though history has divided rich from poor, free from un-free, powerful from powerless, and race from race, we are still all branches on the same tree of humanity". ~ Nelson Mandela
💛በጣም የሚያሳስበኝ ግን የ Common Ground እጦት ነው... እንዴት ሰው የጋራ አካፋይ ያጣል?... ስለምንስ በጋራ የሚቆምለትን ነገር ይሰዋል?... በየታዛህ ብትሸጎጥም ጉርብትና የምታጠነክርበትን ፈለግ ትሰራለህ እኮ... የቀዬው ሳር፣ ወንዙ፣ መስኩ ሁላ ለከብቶችህ ብቻ አይደለም... ለከብቶቻቸውም መድኅን ነው... አንድ ዓይነት ሐይማኖት ባትከተሉ መንፈሳዊነት አንድነታችሁ ነው... አንድ ቋንቋ ባይኖራችሁ ሰው መሆን የጋራችሁ ነው... የተለያዩ የብሔር ስያሜዎች ብትይዙ ዜግነት ንብረታችሁ ነው... "ልዩነት" የማይቋጠርበት ገመድ የለም!!!
💜የእኔና ያንት ገዢ መሬት /common ground/ ሰውነት ይባላል፡፡
ህግ የምናወጣውም፤ ህግ የምንሽረውም እሱ ላይ ቆመን ነው፡፡ ክፋት፣ ደግነት፣ ትክክል፣ ስህተት፣ ተበዳይ፣ በዳይ የምንባባለውም እሱ ላይ ቆመን ነው፡፡ ወደድንም ጠላንም፤ ከሳንም፣ ወፈርንም ሁላችንም ሰው በሚባል ቁና እኩል ተሰፍረናል፡፡
❤️እስኪ እየሆነ ያለውን እንመርምር... የንፋሱን ከየት ወዴት እንፈትሽ... እያዋጣን ያለነውን ነገር እንጠይቅ... ምንም ከማለታችን በፊት ግን እንዲመጣ ለምንፈልገው በጎ ነገር ያለውን አስተዋጽዎ እንመዝን።
ውብ ቅዳሜ ❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanityBot

ሰዓት እላፊ!
🔥
አንዳንድ ነገሮች
①
“ሊነጋ ነው…”
በረጅሙ የጨለማ ዘመን ውስጥ ሊነጋ ነው ብለው የሰበኩን የተስፋ ነጋዴዎች ብዙ ናቸው። ይነጋ ይሆን ብለው የጓጉ ገበያተኞች በአይነትም በጠገራ ብርም ተስፋ ሲገዙ፣ በተስፋ ብርቱ ሰልፍ ተሰልፈው ከድቅድቅ ሲፋለሙ ባጅተው አልፈዋል።
ተስፋ ግን አሁንም ተፈላጊ ሸቀጥ ሆኖ ቀጥሏል። “ሊነጋ ነው” ይልሃል ጀምበሩ ደመቀ። “ሊነጋ ሲል ይጨልማል” ይልሃል ዘማሪው የአሁን ጨለማ አይርታህ ሲል። “በል በርታ ታጠቅ!” ይልሃል ሃይለ ቃል የሚያትት አፈ ቀላጢ ወቀሳጢ።
ድቅድቁ ግን አልተረታም። ነጋ ተብለን ነቅተን ነበር የዛሬ ሶስት አመት። ነጋልን እነሆ ደማቅ ጮራ ፈነጠቀ ብለን አረንጓዴ መስክና የሱፍ አበባ ልናይ ጓጉተን ተስፋ ሰነቅን። አይኖቻችንን በነጠላ ጫፍ አብሰን ብናይ ግን አይን ይወጋል ጨለማው። ከአይኖቻችን ቡኒ እዥ ፈሰሰ። ስንጨናበስ ከረምን። ተስፋ የጠበቁ አይኖች ዳፍንት ዳበረባቸው።
ተስፋ የሸጠልን ግን ከበረ።
ግድግዳዎቻችን ላይ “ሆፒንግ ኢዝ ሆፕለስ!”
②
አንዲት ታካሚ ለማነጋገር የተኛችበት ሄጄ ነበር። ሳይታወቀኝ ከሚገባው በላይ ተነጫነጭኩባት። እየወጣሁ ሳስበው የነበረው “ምን አድርጋኝ ነው እንዲህ የተቆናጠርኩባት?” ነበረ።
ሁሉም ሰው ይነጫነጫል ያለው። እኔም፣ ኮንሰልታንቱም፣ ሌሎች ሀኪሞችም ይቆናጠራሉ። ሆስፒታል ብቻ ሳይሆን ሁሉም ቦታ ነው። ሁሉም ሰው ነው። ምን ሆነን ነው?
ቀላል መልስ የለውም።
ወደቤቴ እያዘገምኩ እያሰብኩት ነበር።
ቀና መልስ የሚመልስ ሰው የለም። እንካ ስትለው ዓረፍተ ነገር፣ ሀይለ ቃል ይመልስልሃል ዘጠና ዘጠኝ።
መቼ ለት አንዱ ጀብራሬ መንገድ ላይ ያለምክንያት የአይን ቀለምህ አላማረኝም ብሎ ጥንብ እርኩሴን አወጣኝ። ደነቆርኩ ከስድቡ የተነሳ። ምን ሆነን ነው ይሄ ሁሉ tenderness አልኩ?
ቤቴ ስገባ አገኘሁት መልሱን።
አስቤዛ ስለመግዛት ማሰብ አለብኝ።
③
“Is your brain a vestigial organ?“
*insert Alfred Hitchcock's voice*
አንዱ በጥይት ጭንቅላቱን ተመትቶ መጥቶ የተጎዳውን አንጎሉን በቀዶ ህክምና ተወገደለትና ወደቤቱ ተመለሰ። debridement።
ከሳምንታት በኋላ በቀጠሮ ሲመጣ አስታማሚው “አሁንማ ተሽሎት ከበፊቱ የተሻለ ሰው ሆኗል” ብሎ ቀለደ።
አባባሉ አየር ላይ እየተንገዋለለች ቀረች።
“የተሻለ ሰው ሆኗል”፤ “አንጎሉ ጎድቶት ነበረንስ?” ፤“የማይጠቅም አንጎል ይዞ ይዞር ነበረን?”፤ “are we heading back to a fast track evolution where we don't need our frontal cortexes anymore?"
ባዮሎጂው ባያስኬድም አነዋወራችን ግን ይናገራል። የማንጠቀምበት የአንጎል ሸክም ግንባራችን ስር አለ።
አንቱ፥ ማጣፊያ አጥሮዎ ተቸግረዋል? እንኪያስ አንጎልዎን ያስቀንሱት። ህይወትዎን በተሻለ ያጣጥሙ።
④
“በሰማይ ላም አለኝ። በሬም ጭምር። ቤትና መኪናም። ድራፍት በማድጋ እጠጣለሁ፣ የተገኘውን ሁላ ፋክ አደርጋለሁ።”
— ወድቆ የተገኘ ዋሌት ውስጥ የነበረ ህልም።
📝yo Na
@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
@Nagayta

❤️አንዳንድ ውብ ልቦች ወደ ሕይወትህ ፍኖት ሲቀላቀሉ የቀድሞ አንተን አትሆንም... ትለያለህ... በጣም ትለያለህ!!
💎የሰው ሰውነቱ መታያው በልቡና ዉስጡ በሰነቀው ቅንነት ፣ ለሌላው በሚሰጠው እኩል ፍቅር ነው፡፡ይህ ልብ ውብ ነው፣ወበትንም በመላው ተፈጥሮ ላይ እነደከርቤ እጣን መአዛውን አግንኖ ያውዳል፡፡ይህ ውብ የደከመን ያበረታል፡፡ይህ ውብ ልብ ያዘነን ያፅናናል፣ይህ ውብ ልብ የወደቀን አንስቶ ያፀናል፡፡
❤️ይህ ውብ ልብ በኑሮ ዝሎ የመጣበትን ዓላማ የዘነጋን ወደተፈጠረበት ዓላማ ይመልሰዋል፡፡ይህ ውብ ልብ ካጋጠመህ የድሮውን ቀርቶ የቅድሙን አንተ አትሆንም፡፡ይህ ውብ ልብ ይቀይርሀል፡፡ቅየራውም ለመልካም ነውና ራስህንም ውብ ያደርግሀል፡፡
✍ደምስ ሰይፉ
ውብ አሁን!!❤️

❤️እናንት ሁላችሁም፣ አንድ ላይ፣ የሕይወት ዛፍ ናችሁ፡፡ እናም ራሳችሁን ከመከፋፈል ተጠበቁ፡፡ ፍሬን ከፍሬ፣ ቅጠልን ከቅጠል፣ ቅርንጫፍን ከቅርንጫፍ አታስበልጡ፡፡ ግንዱን ከሥሮቹ፣ ዛፉን ከእናት አፈሩ ለይታችሁ አትውደዱ፡፡ ይህ ደግሞ … በዕርግጥም … አንዱን ከሌላኛው አስበልጦ፣ ሲከፋም ለይቶ ስትወድዱ የምታደርጉት ነው፡፡
አዎን … እናንት ሁላችሁም … አንድ ላይ … የሕይወት ዛፍ ናችሁ፡፡
💛ሥራችሁም የትም ነው፡፡ ቅርንጫፍና ቅጠሎቻችሁም በሁሉም ስፍራ፣ ፍሬዎቻችሁም በሁሉም አፍ ውስጥ ! በዛ ዛፍ ላይ ያለው የትኛውም ፍሬ፣ የትኛውም ቅርንጫፍ ሆነ ቅጠል፣ የትኛውም ሥሮች ይሁን ፍሬ፣ የእናንተው ፍሬ፣ የእናንተው ቅጠልና ቅርንጫፍ፣ የእናንተው ሥር ነው፡፡
💚ዛፉ ጣፋጭና ባለማራኪ መዓዛ ፍሬ ሲቸራችሁ ብታዩ፣ ጠንካራ እና ፍፁም አረንጓዴ ሆኖ ብታገኙት … ሥሮቹን ወደመገበው የሕይወት ወለላ አስተውሉ፡፡
💙ፍቅር የሕይወት ወለላ ነው፡፡ ጥላቻ ደግሞ የሞት መግል፡፡ ፍቅር ግን ልክ እንደ ደም ሳይታጎልና ሳይገደብ በሕይወት ሥሮች ውስጥ ሊፈስስ ይገባዋል፡፡ የደም ፍሰት መገደብ በሽታ እንደሚሆነው ጥላቻም እንዲሁ የተገደበ ወይም የታፈነ ፍቅር ነው፡፡ የታፈነ ፍቅር መመረዝ ደግሞ ጠይውንም ተጠይውንም፣ ሁለቱንም ይመርዛል፡፡
❤️በሕይወት ዛፍ ላይ ያለች አንዲት ቢጫ ቅጠል ሌላም ሳትሆን ፍቅር የተነፈገች ቅጠል ነች፡፡ እናም ቢጫዋን ቅጠል አትውቀሷት፡፡ ተገንጥሎ የተዘነጠፈው ቅርንጫፍም ፍቅር የተራበ ቅርንጫፍ ነው፡፡ የተዘነጠፈውን ቅርንጫፍ አትርገሙት፡፡ መራራውም ፍሬ ቢሆን ሌላም ሳይሆን ጥላቻ የመረዘው ነውና አትኮንኑት፡፡ ይልቁንም የሕይወትን ወለላ፣ የፍቅርን በረከት ለጥቂቶች ብቻ አዝንቦ ለብዙዎች የነፈገውን፣ በዚህም ራሱን የካደውን፣ የታወረውን የራሳችሁን ተናዳፊ ልብ ውቀሱ፡፡
💙በልባችሁ ውስጥ የጥላቻ ዘር እስካለ ድረስ የፍቅርን ሐሴት አታውቋትም፡፡ የሕይወት ወለላን ለሁሉም መግባችሁ ለአንዲት ቅንጣት ነፍሳት ብትነፍጉ ያቺ የተነፈገችዋ ሕይወታችሁን ታመርረዋለች፡፡ የቱንም ወይንም ማንንም ስትወዱ እንደ እውነቱ ከሆነ የምትወዱት ራሳችሁን ነው፡፡ ስትጠሉም እንዲሁ ነው … የቱንም ወይንም ማንንም ብትጠሉ እንደ እውነቱ የምትጠሉት ራሳችሁን ነው፡፡
💛የምትወዱትና የምትጠሉት ልክ እንደ አንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ላይነጣጠሉ ተጣምረዋል፡፡ ለራሳችሁ ታማኝ ብትሆኑማ ኖሮ የምትወዱትንና የሚወድዳችሁን ከመውደዳችሁ በፊት የምትጠሉትንና የሚጠላችሁን ትወድዱ ነበር፣ፍቅር ቅንጦት አይደለም፡፡ ፍቅር መሰረታዊ ፍላጎት ነው፡፡ ከዳቦና ከውሃ፣ ከዓየርና ከብርሃን ይልቅ ፍቅር ያሻችኋል፡፡
❤️ማንም ቢሆን በማፍቀሩ አይኩራራ ይልቁንም ነፃ ሆናችሁ እንዲሁ በዘፈቀደ ዓየሩን ወደ ውስጥ እንደምትስቡትና እንደምታስወጡት ሁሉ ፍቅርንም እንዲሁ በነፃነት ልብም ሳትሉ ተንፍሱት…ፍቅርን ማንም ከፍ ሊያደርገው፣ ሊቀድሰው የሚችል የለም፡፡ ይልቁንም ለፍቅር የሚገባ የተቀደሰ ልብ ሲያገኝ ፍቅር ራሱ ያን ልብ ይቀድሰዋል እንጂ፡፡
💚ፍቅር አያበድርም፣ አያውስምም፡፡ ፍቅር አይሸጥም፣ አይገዛምም፡፡ ሲሰጥ ግን ሁሉንም ይሰጣል፡፡ ሲወስድም ሁሉንም ይወስዳል፡፡ መቀበሉ በራሱ መስጠት ነው፡፡ መስጠቱም እንዲሁ መቀበል፡፡ እናም፣ ለዛሬ እንዲሁ እንደሆነው ሁሉ ለነገም ለከነገወዲያም እንዲሁ ነው፡፡
❤️ራሱን ሳይሰስት ለባሕሩ የሚለግስ የትኛውም ወንዝ ዘወትር በባህሩ እንደሚሞላው ሁሉ እናንተም እንዲሁ ፍቅር መልሶ ይሞላችሁ ዘንድ ራሳችሁን አንጠፍጥፋችሁ ለፍቅር ተሰጡት፣አዎን … የባሕሩን ስጦታ ከባሕሩ የሚነፍግ ኩሬ መጨረሻው መበስበስም አይደል፡፡
በፍቅር … ትንሽ ወይም ትልቅ የሚሉት ነገር የለም፡፡ ፍቅርን መለካት፣ መመተር … ለፍቅር ደረጃ ማውጣት ስትጀምር፣ ፍቅር መራር ትዝታዎቹን አስታቅፎህ እብስ ብሎ ይጠፋል…
በፍቅር ዘንድ … ትላንት ወይም ዛሬ፣
ዛሬ ወይም ነገ…
እዚህ ወይም እዚያ ብሎ ነገር የለም፡፡
💚ሁሉም ወቅቶች የፍቅር ወቅቶች ናቸው፡፡ የትኛውም ቦታ ቢሆን ለፍቅር ቤተ መቅደስነት የተገባ ክቡር ነው፡፡ፍቅርን … ወሰንም ሆነ ዳር ድንበር፣ካቴናም ሆነ የተዘጋ በር አይገድበውም ፣ አዎን … ፍቅር ዓይናችሁን ሲያበራው … ያኔ … ሁሉም መልስ ፍቅር ዉስጥ እንደሚገኝ ትረዳላችሁ ፡፡
✍ግሩም ተበጀ
📖The Book of Mirdad

💡ከተለመደው ወጣ በሉ!
አብዛኛው ሰው ለገጠመኙ የሚሰጠውን ምላሽ አትከተሉ፡፡ ከተለመደው ወጣ በሉ! ለየት በሉ!
ድክም ሲላችሁ ተስፋ መቁረጥን ሳይሆን ማረፍን ልመዱ፡፡
ሰዎች ትተዋችሁ ሲሄዱ እነሱን ሲከታተሉ መጦዝን ሳይሆን ለብቻችሁ ጊዜን መውሰድን ልመዱ፡፡
🔆• ስሜታችሁ ሲረበሽ “ለምን ስሜቴ ተረበሸ” ብላችሁ የበለጠ መረበሽን ሳይሆን ተረጋግታችሁ መንስኤውንና መፍትሄውን ማግኘትን ልመዱ፣ ስትሳሳቱ ራስን መውቀስና በጸጸት ታስሮ መኖርን ሳይሆን ራስን ይቅር በማለትና ከሁኔታው ትምህርትን በማግኘት እንደገና መሞከርን ልመዱ፡፡
💡አብዛኛውን ግዜ ሰዎች የሚረበሹት በሚያጋጥማቸው ችግር እውነተኛ ባህሪ ሳይሆን ለችግሩ በሰጡት የስሜት ትርጉም የተነሳ ነው ። ዋናው ችግር በሕይወትህ የሚያጋጥምህ ችግር ሳይሆን ስለችግሩ የምትሰጠው ስሜት ነው ። በሕይወትህ የሚያጋጥሙህ ችግሮች ሁሉ እውነተኛ ክስተቶች አይደሉም ።
💎አብዛኞቹ የስሜትህ ሁኔታ ናቸው ። ትልቁ ችግር ከክስተቶቹ በመነሳት በራስህ ስሜት የምትፈጥራቸው ችግሮች ናቸው ። "
📍በሁኔታዎች አትወሰዱ! ከሁኔታዎች ውስጥ መልካም ነገርን መውጣት ልመዱ! ይለመዳል!
✍ዶ/ር እዮብ ማሞ
ውብ ቅዳሜ❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
@EthioHumanitybot

"ባለቤቴ ምጧ እንደመጣ ወደ ሆስፒታል አመራን ፣ ልጃችን እንደተወለደ ነርሷ የልጃችንን ፆታ ወንድ ወይም ሴት ናት ብላ ልትነግረን አልፈለገችም። ከዛ በኋላ የልጃችንን ፆታ ለምን ልትነግረን እንዳልፈለገች አጥብቄ ጠየቅኳት። ነርሷም "ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሆስፒታሉ ፆታን በተመለከተ ምንም አይነት መረጃ መስጠት እንደማንችል ስልጠና ተሰጥቶናል። የልጃቸውን ፆታ ይሄ ነው ብለህ ስትነግራቸው ሆስፒታሉን እና የጤና ባለሙያዎቹን በታላቅ ቁጣ በአንድ እግራቸው የሚያቆሙ ሞገደኛ ወላጆች አሉ " ብላ መለሰችልኝ። አሁን የገባኝ ነገር የምንኖርበት አለም የዕብደት ሆኗል!"
ሌላኛዋ አስተያየት ሰጪ የገጠማትን ጨመረች " በቅርቡ ወንድ ልጄን ስወልድ የሞላሁት የልደት ሰርተፍኬት ፎርም የፆታ ማሳወቂያ ሶስት አማራጮች ነበሩት። ወንድ_ ሴት__ እና ያልተወሰነ_.....! አስቡት የምንወልዳቸው ህፃናት በአንድ ጊዜ ወንድ ወይም ሴት ከመሆን የዘለለ ምርጫ ባይኖራቸውም ሶስተኛው አማራጭ የተተወው ህፃናቱ ሲያድጉ በራሳቸው ምርጫ ፆታቸውን እንዲመርጡ ታስቦ ነው"
እነዚህን አስተያየቶች What is a woman? ከሚለው የ Matt Walsh አስደናቂ ዘጋቢ ፊልም ስር ያስቀመጡት በሃገራቸው ስር ሰዶ በተንሰራፋው ፆታን ከመረዳት እስከ መቀየር በደረሰው ማህበረሰባዊ ጤንነታቸው ግራ የተጋቡ አሜሪካዊያን ወላጆች ናቸው።
የሶስት ሴት ልጆችና የአንድ ወንድ ልጅ አባት የሆነው ማት ዎሽ What is a Woman? ( ሴት ምንድናት?) የሚለውን ቀላል ጥያቄውን ይዞ ከአሜሪካ ጎዳናዎች አንስቶ ግዙፍ ዩኒቨርስቲዎቿን አስከሚመሩት ምሁራን " ሴት ምንድናት" እያለ ቢጠይቅም የሚያገኘው መልስ የራሱን ጤንነት እስኪጠራጠር ድረስ አስደንጋጭ ነበር።
ማት አንዲት ፆታዋን ቀይራ ወንድ ነኝ ከምትል ቆንጆ ጋር ቁጭ ብሎ "ሴት ምንድናት?" ብሎ ጠየቃት። ይህቺው ቆንጆ "እስኪ ሴቶቹን ጠይቃቸው። እኔኮ ሴት አይደለሁም" ትለዋለች። ወንዶቹም ከፆታቸው ተካክደው ሴት ሆነው ያወሩታል። ማት ለመሞገት ቢሞክርም ኋላ ቀር የዳይኖሰር ዘመን ሰው መስሎ ይታያቸዋል።
ማት በመንገድ የሚያገኛቸውን የተለያዩ ወጣቶችን ይጠይቃል " እኔ እንደምታዩኝ በእውነታው ወንድ ነኝ። እራሴን ሴት ነኝ ብዬ ብገልፅና ብቀርብ ምላሻችሁ ምንድነው?" ታዲያ ለዚህ ጥያቄ ከወጣቶቹ የሚያገኘው አብዛኛው መልስ " ምርጫህ ያንተ ነው። ሴት ነኝ ብትለኝም ችግር የለብኝም። ሁሉም ሰው ነኝ ብሎ የሚያምነውን ነው። ያን ያህል የሚያስጨንቀኝ ጉዳይ አይደለም " የሚል ነበር።
ማት ወደ ዩኒቨርስቲዎች አምርቶ በስነ ፆታ ማህበራዊና ቤተሰባዊ ጉዳዮች ጥርሳቸውን የነቀሉ አንቱ የተባሉ ምሁራንና ባለሙያዎችን በሴት ምንነት ፣ የፆታ ክፍፍልና ብየናችን በተፈጥሮ መሰረቶችና በእውነታው መመዘን እንዳለበት ቢሞግትም የአብዛኞቹ ትንተናና አረዳድ እንደሚከተለው ነው .... 'የሰው ልጆች ፆታቸው በመራቢያ አካላቸው ማለትም በብልቶቻቸው ምክንያት ሊወሰን እንደማይችልና ፆታቸውን በውስጣቸው ከሚሰማቸው ስሜት ተነስተው መምረጥ እንደሚችሉ በምርጫቸውም ላይ የዘረመል ተዋፅኦዋቸው ያለውን የምናልባት ድርሻ በመተንተን ይህም ማለት ሴት ወይም ሴትነት ጡት ስላንጠለጠለችና Vagina ስላላት የሚገኝ እንዳልሆነ ያስረዳሉ። ለወንዶችም ወሸላ ማንጠልጠላቸው ፆታቸውን ወንድ ነው ለማለት ብቁ አይደለም። ሴትም ሆነ ወንድ ፆታቸውን ውስጣቸው እንደሚሰማቸው ስሜት መምረጥና መቀየር መብታቸው እንደሆነ የአብዛኛው ምሁራንና ባለሙያዎች አቋም ነው።
ታዲያ ይህንን ፆታን በተመለከተ የተዛባው አመለካከት ፆታን በመበየን አላቆመም። ወንዶችን እንደፍላጎታቸው ሴት ለማድረግ ሴቶችንም ወደ ወንድነት ለመቀየር ሆስፒታሎች ተቋቁመው የፆታ ቅየራ gender transplant ይሰራላቸዋል። ወንዶች ቀዳዳ ያበጃሉ ሴቶችም ያንጀለጅላሉ። ፆታ መቀየሩ የሚያስከትለውን የሆርሞን መዛባት ለማስተካከል በፋብሪካ እንደ መድሃኒት የተመረቱ ሆርሞኖች የፆታ ቅየራውን ተከትለው ጥቅም ላይ ይውላሉ። ኢንዱስትሪው በቪሊየን ዶላሮች እየዘወረ ትውልዱ ከማይቀር የማንነት ቀውስ ውስጥ ይወድቃል።
ህፃናት በጨቅላ እድሜያቸውና ባልበሰለ አዕምሯቸው በዚህ ውዝግብ ውስጥ ገብተው በየ ሆስፒታሉ ፆታቸውን ለመቀየር ላይና ታች ይቀደዳሉ። አብዛኞቹ ፆታቸውን ያስነካኩ ወይም gender transplant ያሰሩ ህፃናት
ከሚገጥማቸው የማንነት ቀውስ የሚያወጣቸው አጥተው አብዛኞቹ ራሳቸውን ያጠፋሉ።
ማት በዚሁ ዘጋቢ ፊልም እንዳሳየን ፆታቸውን ወደ ሴትነት የቀየሩ ወንዶች በተለያዩ የስፖርት ውድድሮች ከሴቶች ጋር ሴት ነን ብለው እየተወዳደሩ ውድድሮችን ያሸንፋሉ። የካዱት ተፈጥሯዊ ማንነታቸውና ፆታቸው ውድድሩን ለማሸነፍ እንደረዳቸው ቢጠየቁም ማሸነፋቸው ከስራና ከጥረት ጋር እንጂ ከፆታ ጋር እንደማይገናኝ አጥብቀው ይሞግታሉ። በነሱ አለም ሴት ነኝ ያለ ሴት ወንድ ነኝ ያለም ወንድ ነው።
ፆታቸውን ያስቀየሩ ወይም ሴት ነን ብለው የሚያምኑ ወንዶች የሴቶች ሽንት ቤት ካልተጠቀምን ፣ ሴቶች የሚጠቀሙበት ስፓ ውስጥ ገብተን ካልታሸን በሚል የአደባባይ አንባጓሮ ይፈጥራሉ። አስቡት... ልብም በሉ አንድ ወንድ ወሸላውን እንጠልጥሎ ከሴቶች ጋር ካልሸናው ከሴቶች ጋር ካልታጠብኩ ይላል። በዚሁ ፆታቸውን በቀየሩ ሰዎች የሽንት ቤት አጠቃቀም ዙሪያ ከማት ጠንከር ያለ ጥያቄና ክርክር የገጠማቸው የኮንግረስ አባል ጥያቄውን ለመመለስ ከመጨነቃቸው የተነሳ ከፍተኛ ፍርሃት እየተነበባቸው ቃለ መጠይቁን እስከማቋረጥ ደርሰዋል። ከምሁራኑ እስከፖለቲከኞቹ የሚያስፈራቸው አንዳች ሃይል ምን እንደሆነ ግራ ያጋባል።
በዚህና መሰል ጉዳዮች ላይ ለተቃውሞ መንቀሳቀስና አጥብቆ መጠየቅ በኋላ ቀርነት አስፈርጆ የዳይኖሰር ዘመን ሰው ያስብላል። ሚዲያውም ሆነ ምሁራኑ በግላቸው ያመኑበት አቋም እንዳለ ሆኖ በጉዳዩ ላይ የሰላ ትችትን ማቅረብ ይፈራሉ።
በዚህ ሁሉ መከራ ውስጥ Hollywood Netflix እና ግዙፍ የፊልም ኢንዱስትሪዎች ፆታን መርጦ ስለመቀየርና የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻን በተመለከተ በፊልሞቻቸው ይሰብካሉ። በአሜሪካ ተደማጭነት ያላቸው ፖለቲከኞችና የህዝብ ተወካይ ሴናተሮች ወገባቸውን አስረው ፆታን መርጦ ስለመቀየር ያልተገደቡ መብቶች ይሞግታሉ።
ማት ቢጨንቀውና ሃገሩን አሜሪካን ቢጠራጠር ሴት ምንድናት የሚለውን ጥያቄውን ይዞ የኬንያ የገጠር መንደሮች ውስጥ ተገኘ። የማሳይ ጎሳ አባላትን አጊንቶ ሴት ምንድናት አላቸው? ማሳዮች የጠራ ተፈጥሮአዊ መልስ ነበራቸው "ሴት የምትወልድ ናት ፣ ሴት ጡት ያላት ፣ ሴት የመራቢያ አካል ያላት ወልዳ የምታጠባ ናት። ሴትና ወንድን ለመለየት አንቸገርም" አሉት። ማት ለማሳይ ጎሳ አባላት በሃገሩ ያለውን ፆታን የመረዳትና የመቀየር ዝብርቅርቅ አስረዳቸው። ማሳዮች ሳቁ ተገረሙም። ማት ወደ ማሳይ ሄደ እንጂ ወደ ሃገሬ ኢትዮጵያ ቢመጣ በመስቀለኛ ማማተብን ይለምድ ነበር።
ማት በስተመጨረሻ "ሴት ምንድናት?" ብሎ ጥያቄ ያቀረበላቸው ምሁር በትዕቢት ተሞልተው "ሚስትህን ጠይቃት" ባሉት መሰረት አለምን የዞረበትን ጥያቄ ይዞ ወደ ሚስቱ ተመልሷል።
ሚስቱ ምን ትመልስለት ይሆን ?
ዘጋቢ ፊልሙን ከማየት ብዙ መረዳትና መልሶች ያገኛሉ!
📝ሙሉቃል ቃል

💎በዚህ ምድር ላይ ሰው ሁሉ የዘራውን ያጭዳል። ይህ ህገ ተፈጥሮ ነው። በየትኛውም የዓለም ክፍል የሚሰራ ህግ ነው። እንደ ህገ-መንግስት በአንድ ሉአላዊ ሀገር ብቻ የተገደበ አይሆንም። በምድር ላይ ለሰራው ደግነት ይሁን ክፋት ብድራት መከፈሉ የማይቀር ይሆናል።በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የቻልከውን ያህል መልካም ውለታ ብትውል ብድራት ተከፋይ ትሆናለህ። ካለህ ላይ መስጠት ማለት ነው። … የምትሰጠው ነገር ባይኖርህ ጥሩ ፈገግታ ስጥ። ምናልባት ይህች ፈገግታ አንተ ባታውቅ እንጂ አንዲት የጨነቃት ነፍስ ትታደጋለች ።
💛ያንተ መልካም ስነምግባር ሌላውን ተመልካች ከተኛበት የመቀሰቀስ መግነጢሳዊ የስበት ኃይል እንዳላት አንተ አታውቅም ይሆናል። በዚህ ምድር ላይ የተዘራ ማንኛውም ነገር እንዲሁ ወድቆ የሚቀር ላይሆን ይችላል።
💫መልካም ገበሬ ለነፍሱም ለቤተሰቦቹም ብሎም ለሃገር ለህዝብ የሚተርፍ ዘር ዘርቶ ፍሬውን ይመግባል። በየትኛውም የህይወት ሜዳ ላይ የሚገኝ እያንዳንዱ ግለሰብ መልካም ገበሬ ለመሆን የሚያግደው የለም።
🔆ሁሌም በጎ በጎውን ማሰብ ስትለማመድ መልካም ገበሬ ትሆናለህ። ከራስህ አልፎ ተርፎ ለሌላው የሚጠቅም መልካም ሐሳብ ወደ ዓለም ብትልክ መልካምነት ዞሮ ይከፍልሃል። ብድራቱን ታገኛለህ። የጣልከው አልያም ያካፈልከው ሁሉ መልሶ ብድራቱን ይከፍልሃልም። …መልካም መሆን ኪሳራ ከሌለው ክፉ መሆን ምንም ትርፍ የለውም። … ወዲህም ባንተ ላይ እንዲሆንየማትፈልገውን ነገር በሌላው ላይ አታድርግ። …ፍቅር ትሻ እንደሆን ፥ ቀድመህ አንተ ፍቅር ስጥ። ያልሰጡትን ለማግኘት ማሰብ ፥ ስንዴ ዘርቶ የጤፍ ምርት እንደመጠበቅ እንዳይሆን። … ከመስተዋት የተሰራ ቤት ውስጥ የሚኖር ሰው ከቤቱ ሆኖ ወደ ውጭ ድንጋይ መወርወር የለበትም።
💡ጋን በጠጠር ይደገፋል እንዲሉ ፤ እያንዳንዱ ሰው በሌላው ህይወት በቀጥታም ይሆን በተዘዋዋሪ ተፅእኖ ማሳደሩ ህገ-ተፈጥሮ ነው።አይመለከተኝም፥ አይደርስብኝም የምትለው ነገር ላይሆን ይችላል። … ጉንፋን የያዘው ሰው አጠገብህ ተቀምጦ ቫዮረሱ አንተ ዘንድ እንዳይደርስ ለማድረግ አትችልም። በአንድም በሌላ መልክ ኢንተርአክሽን ይኖራል።
ውብ ምሽት❤️