Telegram Web Link
Audio
ምን እንደምመርጥ አላውቅም 
                                                  
Size:- 17.8MB
Length:-51:06
       
     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
- የሕይወት ዛፍ -

|ጃንደረባው ሚዲያ | መስከረም 2016 ዓ.ም.|
✍🏽 ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ

እግዚአብሔር በምድር ላይ ለማየት ደስ የሚያሰኙ፣ ለመብላት መልካም የሆኑ ዛፎችን ማብቀሉን ቅዱስ መጽሐፍ ይነግረናል፤ ከእነዚህ ዛፎች መካከል አንዱ የሕይወት ዛፍ ነው። ዘፍ 2፥9 ገነትን የሚያጠጡ አራቱ አፍላጋት ኤፌሶን፣ ግዮን፣ ጤግሮስ፣ ኤፍራጥስ የሚመነጩት ከዚህ የሕይወት ዛፍ ሥር ነው። ስለዚህ የሕይወት ዛፍ በነገረ ክርስቶስ ያለውን ጥልቅ አስተምህሮ በሌላ ጊዜ የምናነሣው ሆኖ ለዛሬ ግን ልነግራችሁ የወደድሁት በሰዎች መካከል ስለሚገኘው የሕይወት ዛፍ ነው።

ለቅድስና ራሳቸውን የሚያተጉ ሰዎች ወደ እግዚአብሔር ገነት ከመወሰዳቸው በፊት ልቡናቸው ተድላ ደስታ የሚፈስባትን ገነት ትሆናለች። አረጋዊ መንፈሳዊ የተባለው ሊቅ “ልቡሰ ለባህታዊ ገነተ ተድላ ይዕቲ፤ የባህታዊ ልቡ ተድላ ደስታ የሚገኝባት ገነት ናት” ብሎ የተናገረውም ስለዚህ ነው። የጻድቅ ሰው ልቡ ገነት፣ አንደበቱም የሕይወት ዛፍ ናት። የማስተዋል መንፈስ የተሰጠው ሰው ሰሎሞን በገነት መካከል ስላለው ሳይሆን በሰዎች ዘንድ ስላለው የሕይወት ዛፍ እንዲህ ሲል ይናገራል። “መፈውስ ልሳን ዕፀ ሕይወት ውእቱ፤ ፈዋሽ ምላስ የሕይወት ዛፍ ናት” ምሳ 15፥4 ይላል።
ዛሬ በገነት መካከል ካለው የሕይወት ዛፍ ይልቅ የሚያስፈልገን ሰሎሞን የተናገረለት የሕይወት ዛፍ ነው። ያኛውማ ከዚህ በኋላ እንዳንፈልገው በክርስቶስ ተተክቷል። ፍሬውን በልተነው የዘለዓለም ሕይወትን የምናገኝበት እውነተኛው የሕይወት ዛፍ ሁልጊዜ በፊታችን እንደተሰቀለ ሆኖ የተሳለው ክርስቶስ ነው። እሁን ለምድራችን ምን ያስፈልጋታል ካላችሁኝ ልቡ ገነት፣ አንደበቱም የሕይወት ዛፍ የሆነችለት ሰው ነው። አራቱ አፍላጋት የተባሉት አራቱ ወንጌላውያን ዙረው የሚያጠጡት ልቡ ገነት የሆነችለት አንደበቱም የሕይወትን ዛፍ የምትመስልለት ይህ ሰው ዛሬ ከወዴት ይገኛል?
ተፈጥሯችንን በእግዚአብሔር ቃል ብንጠብቀው እንዴት ያለ ድንቅ ስጦታ መሰላችሁ? ክርስትና ገነትን በመሻት ተጀምሮ ገነትን ወደ መሆን ማደግ የሚያስችል ሕይወት ነው። ፈውስን የሚሻ ሰው ፈዋሽ የሚሆንባት፣ ምድራዊው ሰው ሰማያዊ ምሥጢር የሚያይባት፣ ደካማው ሰው ኃይልን በሚሰጠው በክርስቶስ ሁሉን የሚችልባት ድንቅ ሕይወት ናት ክርስትና። ቅዱስ ጳውሎስ ለራሱ ፈውስን የሚሻ ድውየ ሥጋ ነው 2ቆሮ 12፥7 ለሌሎቹ ግን በሄደበት ቦታ ሁሉ ፈውስን የሚሰጥ የሕይወት ዛፍ ነው። ቅዱሳን ሐዋርያት በቃላቸው ተናግረው በእጃቸው ዳሰው ከዚያም አልፎ በልብሳቸውና በጥላቸው የፈወሷቸው ድውያን ብዙ ናቸው። ከዚያ ይልቅ በአንደበታቸው የፈወሷቸው ምዕመናን ይበዛሉ። ዓለምን ዙረው ካስተማሩበት ጊዜ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ትምህርታቸውን የስሙ ሁሉ ወደ ዘለዓለም ሕይወት ይደርሳሉ።

መልካሙን የምሥራች የሚናገሩ እውነተኛውን ቃል የሚያወሩ አንደበቶች ሁሉ ዛሬ በምድራችን ላይ የበቀሉ የሕይወት ዛፎች ናቸው። ልቡን ከኃጢአት የሚጠብቃት ሰው ለአዳም የተሰጠችውን ገነትን ያደርጋታል። አንደበቱንም ሀሰትን ከመናገር የሚከለክላት የሕይወትን ዛፍ ያስመስላታል። ለሚሰሟት ሁሉ ፈውስን የምትሰጥ እንደዚህ ያለች አንደበት እንድትኖረን ሀሰትና ቁጣን፣ ፌዝና ቧልትን የመሳሰሉ ነገሮችን ሁሉ ከቶውኑ ወደ አፋችን ማስገባት አይገባንም። ቅዱስ ዳዊት “አቤቱ ለአፌ ጠባቂ አኑር የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ” መዝ 141፥3 ብሎ የጸለየው እንዳገኙ መናገር አንደበትን የሚያረክስ ስለሆነ ነው። እንዳገኙ መናገር እንዳገኙ ከመብላትና ከመጠጣት ይልቅ ሰውን የሚጎዳ ልማድ ነው።
ከአንደበታችን በሚወጣው ነገር እግዚአብሔር ሌሎችን የሚፈውስበት ከሆነ አንደበታችንን መጠበቅ ይገባናል ማለት ነው።

አንተ ሰው! እግዚአብሔር ገነትን ባንተ በኩል ሊገልጣት ይፈልጋል፤ አንደበትህም ለብዙዎች ፈውስ ትሆን ዘንድ የሕይወት ዛፍ ሊያደርጋት ይቻለዋል። ራስህን አዘጋጅ እግዚአብሔር ባንተ ልሳን ሊፈውሳቸው የተዘጋጁ ሕሙማን በዙሪያህ መሰብሰባቸውን አትርሳ። እንደዚያ የመቄዶንያ ሰው እርዳታህን ፈልገው የሚጠባበቁ ሰዎች መኖራቸውን አስብ ሥራ 16፥9 አንዲት የሰማርያ ሴት በተናገረችው ነገር ብዙዎች በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ማመናቸውን በመጽሐፍ ተመልከት ዮሐ 4፥39 የተናገረችው ብዙ አይደለም እሷ ስለክርስቶስ ብዙ ትናገር ዘንድ ጴጥሮስን ወይም ጳውሎስን አላደረጋትማ! ቃሉን በሙላት እንደሚናገሩ ሐዋርያት የማስተማር ጸጋን አልሰጣትማ! “ያደረግሁትን ሁሉ ነገረኝ” ብቻ ነው ያለቻቸው። ነገር ግ ን ብዙ ሣምራውያን በክርስቶስ አመኑ። ከሁሉ ይልቅ የሚገርመው ትምህርትና ተአምራት ከጀመረባት ከገሊላ ሰዎች በልጠው በእነርሱ ዘንድ እንዲኖር መለመናቸው ነው።

የሕይወት ዛፍ የሆነች ምላስ ማለት ይህች አይደለቸምን? ብዙዎችን ከሞት ወደ ሕይወት ያሻገረች። አንደበታቸው የሕይወት ዛፍ የሆነችላቸው ሰዎች ብዙ ተናግረው ሳይሆን አንድ ቃልም ቢናገሩ በቂ ነው። የሕይወት ዛፍ የሚያፈራው ፍሬ አንዱ በቂ ነውና። ብዙ መናገር ባትችልም የተናገርሃት አንዷ ቃል ትፈውሳለች ። አከናውነህ መናገር ባይሆንልህም እንደምንም ብለህ ከአንደበትህ ያወጣሃት ቃል እሷ መድኃኒት ትሆናለች ሙሴ ዲዳና ምላሰ ጸያፍ እንደነበረ አስብ እንጅ። አሮን ደግሞ ደኅና አድርጎ እንደሚናገርም አትርሳ ነገር ግን እስራኤልን ለሞት የሰጣቸው የሙሴ ቃል ሳይሆን የአሮን ነው ዘፀ 32፥2

“ፈዋሽ ምላስ የሕይወት ዛፍ ናት” ለሰዎች ፈውስ የማይሆን ቃል አትናገር፤ አንደበትህ የሕይወት ዛፍ ትሆንልህ ዘንድ አስቀድመህ ልብህን እንደ ገነት በእግዚአብሔር ቃል የለመለመች መልካም ሥፍራ አድርጋ፤ የሕይወት ዛፍ ከገነት ውጭ በሌላ ሥፍራ አትገኝምና። ከዚህ የሚበልጥ ጸጋ ከወዴት ታገኛለህ? በምድር ሳለህ ልብህን ገነት አንደበትህን የሕይወት ዛፍ ካደረገልህ ሌላ ምን ትሻለህ?

ማስታወሻ :- ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ የአራቱ ጉባኤያት መምህርና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት የሊቃውንት ጉባኤ ሰብሳቢ ሲሆን የመጻሕፍት ደራሲም ናቸው:: ሊቅ ሊቃውንት የጃንደረባው ሚዲያ ዐምደኛ ሲሆኑ ጽሑፎቻቸው ዘወትር ሰኞ የሚነበቡ ይሆናል::

የሕይወት-ዛፍ
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
"ሰማዕትነት ስር ነው፡፡ ክርስቲያኖች ደግሞ ከዚኽ ስር የሚያቆጠቁጡ ምርጥ ዘሮች ናቸው፡፡ ብዙ ዛፍ የሚያቆጠቁጥበት ስር በለም አፈር ስለሚሸፈን አይታይም፡፡ ከዚያ በሚያቆጠቁጡ ዛፎች ግን ስሩ እንዴት እንደተመቸው ይታወቃል፡፡ ሰማዕታትም በግዙፉ ዓይናችን እንደምን ያለ አክሊል ሽልማት እንደተቀበሉ አይታየንም፡፡ ፍሬያቸው ግን እነርሱን መስለው እነርሱን አኽለው በሚጋደሉ ምርጥ ዘሮች ይታወቃል፡፡

ሰማዕታት አክብሩን ብለው አይናገሩም፡፡ ነገር ግን በክርስቲያኖች ልብ የሚዘሩት ፍሬ ምእመናንን በፍቅር ያስገድዳል፡፡ እነርሱን እንዲመስሉ ያሳስባል፡፡

ሰማዕታት እንደ ፍቅረኛ ናቸው፡፡ አንድ ሰው የፍቅረኛውን ስም በየአጋጣሚው ያነሣል፡፡ በዓይነ ሕሊናው ያስባል፡፡ በተለያየ መልኩ ያያል፡፡ ሰማዕታትም ለክርስቲያኖች እንደዚያ ናቸው፡፡ እጅግ የተወደዱና በፍጹም ከሕሊና የማይጠፉ ተወዳጆች ናቸው፡፡ የልጆቻችንን ስም በነርሱ ስም የምንሰይመው፣ ሥዕላቸውን ሥለን የምንተሻሸው የምንስመው ለሰማዕታቱ ያለንን ጥልቅ ፍቅር የምንገልጽበት መንገድ ስለኾነ ነው፡፡"

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ በረከት አይለየን!
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
ስርዓተ ማህሌት ዘካልዕ ጽጌ በዓለ አብርሃ ወአጽብሐ ነገስተ ኢትዮጵያ ወዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ
🍀🍀
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለአፉክሙ ዘማዕፆሁ ሰላም፤ጽጌያቲሁ ሥላሴ ለተዋሕዶ ገዳም፤መንገለ አሐዱ አምላክ ንዋየ መጻኢ ዓለም፤ወልጡ አምልኮትየ በጸጋክሙ ፍጹም፤እምአምልኮ ጣዖት ግሉፍ አሐዱ ድርህም።

ዚቅ፦
ለሥሉስ ቅዱስ ጥዑም ቃሎም፤ናርዶስ ጸገየ ዉስተ አፍሆሙ፤

ማኅሌተ ጽጌ
በከመ ይቤ መጽሐፍ ማዕከለ ፈጣሪ ወፍጡራን፤ለዕረፍት ዘኮንኪ ትእምርተ(ጽላተ) ኪዳን፤ሰንበተ ሰንበታት ማርያም ዕለተ ብርሃን፤ብኪ ይትፌስሑ ዘገነተ ጽጌ ጻድቃን፤ወብኪ ይወጽኡ ኃጥአን እምደይን፡፡

ወረብ
በከመ ይቤ መጽሐፍ ማዕከለ ፈጣሪ ወፍጡራን ለዕረፍት ዘኮንኪ ትእምርተ ኪዳን/፪/
ብኪ ይትፌስሑ ዘገነተ ጽጌ ጻድቃን ብርሃን ዕለተ ብርሃን/፪/

ዚቅ
ሰንበቶሙ ይእቲ ለጻድቃን ትፍሥሕት፤ሰንበቶሙ ይእቲ ለኃጥአን ዕረፍት፤ኅቡረ ንትፈሳሕ ዮም በዛቲ ዕለት፡፡

ማህሌተ ጽጌ፦
ፄነወኒ ተአምርኪ ሶበ ይነፍሑ ነፋሳት፤ ከመ ጼና ገነት ዘይፄኑ እምርኁቅ ፍኖት፤ መዓዛ አፈዋት ማርያም ወጽጌ መንግሥት ቡርክት፤  ጽጌ ጽጌ ዘሰሎሞን ወዳዊት፤ጽጌ ጽጌ ጽጌ አሮን ዘክህነት

ወረብ
ጽጌ ጽጌ ዘሰሎሞን ወዳዊት/፪/
መዓዛ አፈዋት ማርያም መዓዛ አፈዋት ወጽጌ መንግሥት ቡርክት/፪/

ዚቅ
ሠርፀ መንግስት ዘእምሥርወ ዕሤይ ወጽጌ ንጽሕት ዘእምጕንደ ዳዊት፤ወብኪ ይትሜዓዙ ኲሎሙ ቅዱሳን

ማኅሌተ ጽጌ
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፤ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፤ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ።

ወረብ፦
ንዒ ርግብየ ንዒ ርግብየ ምስለ ሚካኤል/፪/
ወንዒ ሰናይትየ ወንዒ ሰናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ/፪/

ዚቅ
ንዒ ኀቤየ እንቲአየ ሠናይት ንባብኪ አዳም መዓዛ አፉሃ ከመ ኮል ትሁብ ሰላመ ለነገሥት ለአሕዛብ ወለበሐውርት

ዓዲ ዚቅ
ወትወፅዕ እምግበበ አናብስት እምታዕካ ዘነገሥት እምቅድመ ሃይማኖት ንዒ ርግብየ ሠናይት ኵለንታኪ ሠናይት አልብኪ ነውር ወኢምንትኒ ላዕሌኪ ንዒ ርግብየ ሠናይት ንዒ ርግብየ ሠናይት

ማኅሌተ ጽጌ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቄ ባሕርይ ዘይኀቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤አንቲ ኩሎ ታሰግዲ ሎቱ ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ።

ወረብ፦
ክበበ ጌራ ወርቅ ዘየሐቱ እምዕንቈ ባሕርይ/፪/
ማርያም አክሊለ ጽጌ ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ/፪/

ዚቅ፦
በወርቅ ወበዕንቍ ወበከርከዴን፤ሥርጉት ሥርጉት በስብሐት፤ወነገሥት ይትቀነዩ ለኪ፤ትርሢተ መንግሥቱ አንቲ መድኃኒቶሙ ለነገሥት

ሰቆቃወ ድንግል
እፎ ጐየይኪ እምፍርሃተ ቀትል እምገጽ ሄሮድስ ቍንጽል፤ ወለተ አናብስት ግሩማን እለ ይጥኅሩ በኃይል፤ኢፈቀድኪዮ በምድር ለመንግሥተ ዓለም ወብዕል፤ እስመ ልማዱ ትሕትና ለፍሬ ከርሥኪ ልዑል፤ከማሁ ግዕዝኪ በምግባር ወቃል

ወረብ-
ወለተ ግሩማን አናብስት ግሩማን እለ ይጥኅሩ/፪/
እፎ ጐየይኪ ጐየይኪ  እምገጽ ሄሮድስ/፪/
ዚቅ፦
ሃሌ ሉያ እምሊባኖስ ትወፅእ መርዓት፤ ወትወፅእ እም ግበበ አናብስት እምታዕካ ዘነገሥት ከመ ፍህሶ ቀይህ ከናፍሪሃ፤ መዓዛ አፉሃ ከመ ኮል

መዝሙር፦
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ
ኪነ ጥበቡ መንክር ወእፁብ፤ኪነ ጥበቡ መንክር ወእፁብ ለዘሀሎ መልእልተ አርያም።አርአየ ምሕረቶ በላዕሌነ።ዘከለሎ ለሰማይ በከዋክብት ብሩህ። አርአየ ምሕረቶ በላዕሌነ ወለምድርኒ አሠርገዋ በጽጌያት ንፁህ። አርአየ ምሕረቶ በላዕሌነ ወሠርዓ ሰንበተ ለነባረ ያዕርፉ ባቲ። አርአየ ምሕረቶ በላዕሌ:ማ- መዓዛሆሙ ለቅዱሳን ከመ ፅጌ ደንጎላት ዘውስተ ቆላት። ጸገዩ ቀንሞስ ምስለ ናርዶስ።

አመላለስ፦
መዓዛሆሙ ለቅዱሳን ከመ ፅጌ ደንጎላት ዘውስተ ቆላት/፪/
ጸገዩ ቀንሞስ ምስለ ናርዶስ/፬/

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ማርያም ሆይ የሐናን ወተት እየጠባሽ ወደ ቤተ መቅደስ በገባሽ ጊዜ ያገኘሽ ብቸኝነት ያሳዝነኛል፤ ዳግመኛም በደመና የሚመላለስ ደመናን የሚረግጥ የእሳት አበባ ፋኑኤል ከጓደኞቹ መላእክት ጋር መናን እየመገበሽ በንጽሕና የማደግሽ ተአምር ደስ ያሰኘኛል፡፡
••
" አባ ጽጌ ድንግል "
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
#እንኳን #ለአቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ_በዓል_በሰላምና_በጤና_አደረሳችሁ፡፡
ጥቅምት 5 በዓለ ዕረፋቱ ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ

ጻድቁ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍታቸው መጋቢት 5 ቀን ነው ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው ፍትሃ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላል የሀዘን ወቅት ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍጹም ሀዘን እንጂ ስለዚህም ወደ ጥቅምት 5 ቀን ተዛውሮ እንዲከበር የመጋቢት 27 ስቅለት ደግሞ ጥቅምት 27 ቀን እንዲከበር ተደረገ፤ ከዚያን ጊዜ አንስቶ ይህ ስርዓት ሆነ ይህንንም ስርዓት አባቶታችን ሰሩልን

አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (አቦ፥ አቡዬ)፤
* እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ብርሃነ ዓለም የኾኑ፤
* እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጸጋንና ክብርን የተሞሉ፤
* ኰከበ ገዳም፥ መናኔ ዓለም፥ ምድራዊ መልአክ፤
* ስማቸውን ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ያወጣላቸው፤
* በአክናፈ መባርቅት ተጭነው የሚጓዙ፤
* 60 አናብስትና 60አናብርት ይታዘዙላቸው የነበሩ፤ የእግራቸው ትቢያ ለአራዊቶቹ ምግብ የኾነላቸው፤
* ለብዙ አእላፍ ቅዱሳን ወላዴ የኾኑና በረከትን የሰጡ ታላቅ አባት (ለአብነትም፤ ለቅዱስ #ላሊበላ፥ ለአቡነ #ሳሙኤል ዘዋልድባ፥ ለአባ #አንበስ ዘደብረ ሐዘሎ፥ ለአባ ብንያም ዘግብፅ)

፠፠፠ #ምድረ_ከብድ_፤ /ዝ_ምድር_ክቡድ_ውእቱ_/ ፤ #ዝቋላ (#ዝ_ቆላ)

ምድረ ከብድ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ለመጀመሪያ ጊዜ ያረፉባት ቦታ ናት፤ ቀጥሎ ወደ ደብር ቅዱስ #ዝቋላ (#ዝ_ቆላ) ለጸሎት ሂደው ለሃገራችን ኢትዮጵያና ለዓለማችን ምሕረትና በረከትን ከአምላካችን ለ100 ዓመታት በባሕር ውስጥ ሆነው ለምነዋል፤
*ወደ ምድረ ከብድ ተመልሰው ለ7 ዓመታት ጸልየዋል፤ ቊራም በሰይጣን ተመስሎ መጥቶ ዓይናቸውም ቢያጠፋውም ከ7 ሱባዔያት በኋላ ሊቀ መላእክት ሚካኤልና ገብርኤል ዓይናቸውን መልሰውላቸዋል፡፡
*ወደ ዝቋላ በመመለስም አጋንንትም ከምድረ ዝቋላ አጥፍተዋል፤

፠ እንደገና ወደ ምድረ ከብድ ተመልሰው በነበሩበት ጊዜ ታላላቆቹና በአንበሳ ዘባን ላይ የሚሄዱት #አቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ#አባ_አንበስ_ዘደብረ_ሐዘሎ_አፋር)፣ #አባ_ብንያም_ዘግብፅ ከአባታችን ቡራኬ ለመቀበል መጡ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ተሰውረው ነበርና፤ የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ አናብስት የ3ቱን አባቶች አናብስት በሉባቸው፤ በ7ኛው ቀን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ተገልጠው የኾነውን ነገር በማየት የተበሉትን አናብስት እንዲመልሱ የራሳቸውን አናብስት አዘዟቸው መልሰውም እንደነበሩ በተዓምራት አስነስተው ሰጧቸው፤ በደመና ጠቅሰው ቅዱስ ፋኑኤል 3ት ሰማያዊ ኅብስትና 3ት ጽዋዕ ይዞ ለእንግዶቻቸው ይዘው ሠረገላ በሚባለው ዋሻ አመጡላቸውና ሰጥተው ሸኟቸው፤ እነዚህን ቅዱሳን በሸኙ በ7ኛው ቀን ወደ ተለያዩ ሃገራት ሄደው አስተምረዋል፡፡

፠ እድሜያቸው ረዥም እንደመሆኑ፤ ቅዱሱ ንጉሥ አፄ ላሊበላን ጨምሮ ሌሎችም ቅዱሳን ወደ ርሳቸው እየመጡ በረከትን ተቀብለዋል፡፡
#በግብፅ_300_ዓመታት_#በኢትዮጵያ_ምድር_ላይ_262_ዓመታት (በዋነኛነት #በምድረ_ከብድና_በዝቋላ_ ቢኖሩም ሌሎችም የመሠረቷቸውና የኖሩባቸው ገዳማት አሉ፤ ለአብነትም ደቡብ ወሎ የሚገኘውን #ገዘዛ_አቦን_ መጥቀስ ይቻላል)
፠ በድምሩ 562 ዓመታት ከኖሩ በኋላ በንጉሥ ሕዝብናኝ(እንድርያስ) ዘመነ መንግሥት፤ መጋቢት 5 ቀን ቅዳሜ ለእሑድ አጥቢያ ብዙ ቃል ኪዳንን ጌታችን ሰጣቸው፥ 12 አክሊላትንም አቀዳጃቸው፤ የነበሩባት ምድረ ከብድ ገዳም ግን ራደች፥
ተንቀጠቀጠች፥ በብርሃንም ተጥለቀለች፤ ዝቅ እያለችም መንሸራተት ጀመረች፤ ጌታችንም አንቺ መሬት ሆይ ጽኚ ይህንን ኹሉ ስለቻልሽ ምድር ክቡድ /ኋላ ምድረ ከብድ/ ተብለሽ ተጠሪ አላት፤ የጻድቁም ነፍስ ከሥጋቸው ከሌሊቱ 6 ሰዓት ተለየች፡፡
፠ ይህችውም ምድረ ከብድ ጻድቁ የኖሩባትና የቀደሱባት፥ የመሠረቷትና ያነፅዋት፣ ሠራዊተ መላአክት የከተሙባት፣ ታላላቅ አበው መጥተው በረከት ከአባታችን የተቀበሉባት፣ አርምሞና ጸጥታ የማይለያት፤ አጸዷና ቅጥሯ ልቡናን የሚመስጥ፤
ከአ.አ 125 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ናት፡፡

አምላከ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤት፥ በረከትን ይክፈለን፡፡
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
ስርአተ ዋዜማ ዘጥቅምት ገብረ መንፈስ ቅዱስ
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
በ ፩ -
ሃሌ ሉያ እንተ አጽናዕኮሙ ለአድባር በኃይልከ፤ወቅኦታን እሙንቱ በኃይል፤ዝንቱሰ ብእሲ መምህርነ፤አባ፤ጸሊ በእንቲአነ

ምልጣን፦
ዝንቱሰ ብእሲ መምህርነ፤አባ ጸሊ በእንቲአነ፤አባ ጸሊ በእንቲአነ

አመላለስ፦
አባ ጸሊ በእንቲአነ/፪/
አባ ጸሊ ጸሊ በእንቲአነ/፬/

ለእግዚአብሔር ምድር በምላህ፦
አባ ጸሊ በእንቲአነ፤ ጸሎትከ ወትረ ይብጽሐነ፤ አባ ጸሊ በእንቲአነ።

እግዚአብሔር ነግሠ፦
ጼና አልባሢሁ አባ መባእ ጽዮን ስሂን ገነት ከመ ይርአይ ዘሜላት ዘወረደ ውስተ ገነት ከመ ይርአይ ስነ ፅጌያት

ይትባረክ፦
ኪያከ መሠረት አንተ ብነ፤ አባ ጸሊ በእንቲአነ፤ እስመ ጸሎተ ጻድቅ ይሰምዕ እግዚአብሔር

ሰላም፦
ድምፀ ወተሠብከ ውስተ አለም ዜና ምግባሩ ትሩፍ ለአረጋዊ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ኮከብ ገዳም ፤ድምፀ ወተሠብከ ውስተ አለም ፀጉያን እሙንቱ እምፅጌ ሮማን ወቀ ይሐን እምከላ ገዳም ፤ ድምፀ ወተሠብከ ውስተ አለም ደቂቁ ሔራን ልኡላን ክቡር ወስያ፤ድምፀ ወተሠብከ ውስተ አለም እንዘ የአርግ መስዋዕት ሰላም ድምፀ ወተሠብከ ውስተ አለም፤ድምፀ ወተሠብከ ውስተ አለም

አመላለስ፦
ድምፀ ወተሠብከ ውስተ አለም/፪/
ድምፀ ወተሠብከ ውስተ አለም/፬/
@EotcLibilery @EotcLibilery
@EotcLibilery
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
ሥርዓተ ማኅሌት ዘጥቅምት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለሕፅንክሙ ምርፋቀ ጻድቃን አግብርቲሁ፤ ማያተ ኢያሱ ሥላሴ እለ ትውኅዙ እምሕሊናሁ፤ እንዘ በአፍአሁ አንትሙ ወአንትሙ በውሣጤሁ፤ ኢነጸረ ኀበ ሐይመት ከመ አብርሃም አቡሁ፤ ወመስኮተ ነቢይ ዳንኤል ኢፈቀደ ያርኁ

ዚቅ
በአፍአኒ አንትሙ፣ ወበውሣጤኒ አንትሙ፤ በገዳምኒ አንትሙ፤ ብርሃኑ ለዓለም (ለኢያሱ) አንትሙ።

መልክአ ሚካኤል
ሰላም ለሕፅንከ እንተ በዲቤሁ ሕቁፍ፤ ጸሎተ ቅዱሳን ውኩፍ፤ ሚካኤል ክቡር መስፍነ ትጉሃን አእላፍ፤ ለረዲኦትየ ከመ ዘይሠርር ዖፍ፤ እንዘ ትሠርር ነዓ በ፪ኤ አክናፍ።

ዚቅ
ከመ መዓዛ ቅዱሳን፤ ውስተ አብያተ ክርስቲያን፤ ይሰምዖሙ ጸሎቶሙ ለንጹሐን ከመ መዓዛ ቅዱሳን።

ዘጣዕሙ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።

ዚቅ
እስመ ርእየ ሕማማ ለዓመቱ፤ ወገብረ ኃይለ በመዝራዕቱ፤ መዝገቡ ለቃል ጽጌ እንተ ኢትትነገፍ መድኃኒተ ሕዝብ፤ መዓዛሆሙ ለቅዱሳን።

መልክአ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘኆኅያቲሁ ቅሩጽ፤ ኀበ ዓምደ ብርሃን ጽዱል ወአኮ ዘዕፅ፤ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ኃያል ሠዋቄ ትንቱናን እምዳኅፅ፤ ለዝክረ ስምከ ሠናየ ዜና ወድምፅ፤ ትሴብሕ ኢትዮጵያ ወትዜምር ግብፅ።

ዚቅ
ኮከብ ብሩህ ዘሠረቀ እምአቅሌስያ፤ ቤተ ክርስቲያን ዘንሰምያ፤ ኮኖሙ አበ ለሰብአ ግብፅ ወኢትዮጵያ፤ አማን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሐዋርያ

ወረብ
ኮከብ ብሩህ ዘሠረቀ እምአቅሌስያ ቤተ ክርስቲያን ዘንሰምያ/፪/
ኮኖሙ አበ ለሰብአ ግብፅ ወኢትዮጵያ አማን በአማን ሐዋርያ/፪

ዓዲ (ወይም)
ዚቅ
ፃማ ቅዱሳን ዲቤሁ አዕረፈ፤ አፈዋተ ወንጌል ጸገየ ዘልፈ፤ አባ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሃይማኖተ ተአጽፈ፤ ኀበ ዓምደ ወርቅ ስሙ ተጽሕፈ።

መልክአ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ሰላም ለጒርኤከ ኅሩመ መብልዕ ዘኮነ፤ ወእስከ ስቴ ማይ መነነ፤ ሶበ ረድኤተከ ርእዩ ወኪዳነከ እሙነ፤ ይቤሉከ ኲሉ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አቡነ፤ በኪዳንከ አሥራተ ንሥአነ።

ወረብ
አሥራተ ንሥአነ አሥራተ ንሥአነ/፪/
ገብረ መንፈስ ቅዱስ አሥራተ ንሥአነ/፪/

ዚቅ
በመንግሥተ ሰማያት ይነግሥ ምስሌከ፤ ኃጥእ ዘገብረ ተዝካረከ፤ ወጸውዓ ስመከ እንዘ ይብል አምላከ ተካየድከ፤ በእንተዝ ንሥአነ ለሕዝብከ፤ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አሥራተ በኪዳንከ።

መልክአ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ሰላም ለአዕጋሪከ እለ ኢሖራ በፍናዊሃ፤ ለዛቲ ዓለም ዘዕበድ ጥበባቲሃ፤ ለኢትዮጵያ ምድርነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሐዋርያሃ፤ ውስተ ገፀ ኲሉ ደወላ ዜና ነገርከ በዝኃ፤ ወእስከ ጽንፋ ለምድር ነቢብከ በጽሐ።

ዚቅ
ዝንቱሰ ብእሲ መምህርነ፤ ዘተፈነወ ውስተ ምድርነ፤ ይክሥት ብርሃነ ይፈውስ ዱያነ፤ ሐዋርያ ዘኮነ ወተሰምዓ ዜናሁ፤ ውስተ ኲሉ ምድር።

ወረብ
ዝንቱሰ ገብረ ሕይወት ተፈነወ ውስተ ምድርነ/፪/
ይክሥት ብርሃነ ይፈውስ ዱያነ ሐዋርያ ሐዋርያ ዘኮነ/፪/

ሰቆቃወ ድንግል
እስከ ማእዜኑ እግዝእትየ ማርያም ውስተ ምድረ ነኪር ትሔልዊ፤ሀገረኪ ናሁ ገሊላ እትዊ፤ለወልድኪ ሕፃን ዘስሙ ናዝራዊ፤ለክብረ ቅዱሳን በከመይቤ ኦዝያን ዜናዊ፤እምግብጽ ይጼውዖ አቡሁ ራማዊ።

ወረብ
በከመይቤ"ኦዝያን"(፪) ለክብረ ቅዱሳን/2/
እምግብጽ ይጼውዖ ለወልድኪ አቡሁ ራማዊ አቡ/2/

ዚቅ
ትንቢተ ኢሳይያስ ዘተብህለ እምግብፅ ጸዋዕክዎ ለወልድየ ለክብረ ቅዱሳን ጸዋዕ

ማኅሌተ ጽጌ
እምደቂቀ ሕዝብኪ አነ እንዘ ነዳይ ወአባሲ፤ በብዕለ ዚአኪ ድንግል እትሜካሕ ከመ ነጋሢ፤ወበጽድቅኪ እትፌሣሕ አርአያ ጻድቅ ብእሲ፤እስመ ብየ ተአምርኪ ጌጋየ ኃጥአን ደምሳሲ፤ወመዝገበ ብዕል ጽጌኪ ለኲሉ ዘይሴሲ

ዚቅ
ማርያምሰ ረከብኪ ሞገሰ በኀበ እግዚአብሔር፤ወአነሂ እትፌሣሕ በእንቲአኪ፤እስመ ረከብኩ እምዉስተ ደቂቅኪ እለ የሐዉር በትእዛዝየ፤አምኂ አምኂ፤አምኂ ደቂቀ እኅትኪ ኅሪት።

  ምልጣን
ኮከብ ብሩህ ዘሠረቀ እምአቅሌስያ፤ ቤተ ክርስቲያን ዘንሰምያ፤ ኮኖሙ አበ ለሰብአ ግብፅ ወኢትዮጵያ፤ አማን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሐዋርያ።

አመላለስ
አማን በአማን/፬/
ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሐዋርያ/፬/

እስመ ለዓለም
ንጉሥኪ ጽዮን አሠርገዋ ለምድር በጽጌያት፤ወለሰማይኒ በከዋክብት፤ውእቱ ክብሮሙ ለቅዱሳን፤ብርሃኖሙ ለመሐይምናን፤ዘየአምር እምቅድመ ሕሊና፤ዘይሔሊ ልብ አርአየ ኃይሎ፤በላዕሌነ ወጸገወነ ሠናይቶ።
@EotcLibilery @EotcLibilery @EotcLibilery


 
Audio
ምልክት ወዳለው ሰው አትቅረቡ 
                                                  
Size:- 28.1MB
Length:-1:20:44
       
     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Forwarded from Quality move bot
ተዋህዶ ሀይማኖቴ ነው ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ መረዳት መጻህፍትን ማንበብ እፈልጋለው የየእለቱን ስንክሳር ማንበብ እፈልጋለው ያለ ሁሉ ሊቀላቀላቀላቸው ሚገባ ድንቅ ኦርቶዶክሳዊ ቻናል 3 ቻናሎች
👇 ከታች Join በሉ
2024/09/24 22:17:52
Back to Top
HTML Embed Code: