Telegram Web Link
Audio
የኖኅ ዘመን

Size:-43.5MB
Length:-2:04:47

   በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
👉 ሴት በወር አበባዋ ጊዜ መጸለይ ትችላለች?
👉 ግለ አውናን / ሴጋ /ማስተርቤሽን/ የፈጸመ ሰው ተክሊል ማግባት ይችላልን?
👉 በሱባኤ ወቅት ህልመ ሌሊት (ዝንየት) ቢመታን ምን እናደርጋለን?
👉 ሕልመ ሌሊት በራሱ ኃጢአት ነውን?
👉 ሕልመ ሌሊት በምን ይከሰታል?
👉 ከዝሙት አጋንንት እና ከዝንየት በተጨማሪ በሕልመ ሌሊት የሚፈትነን አጋንንት የትኛው ነው?
👉 የሕልመ ሌሊት መፍትሔ ምንድን ነው?

ለእነዚህ ሁሉ መልስ ለማግኘት ይቀላቀሉ
Channel link
@tewahdo_haymanotea
#ትዕቢት የነበረንን መልካም ምግባር ሁሉ የሚያሳምም ደግሞም የሚገድል ክፋ ደዌ ነው፡፡
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
እግዚአብሔር ሰዎችን ኹሉ ሲፈጥራቸው በመንፈሳዊ ማንነታቸው እኩል አድርጎ ነው፡፡ እንዲህም ስለ ኾነ እያንዳንዱ ሰው በጎም ኾነ ክፉ ግብር ለመሥራት እኩል ዝንባሌ አለው፡፡ እግዚአብሔርን ለመታዘዝም ኾነ ላለመታዘዝ እኩል የመምረጥ ዕድል አለው፡፡ ከዚህ ውጪ በኾነ ነገር ግን ሰው ኹሉ እኩል አይደለም፡፡ አንዳንዱ እጅግ አስተዋይ ነው፤ ሌላው ደግሞ ደከም ያለ ነው፡፡ አንዳንዱ በሰውነቱ ብርቱና ጤናማ ነው፤ ሌላው ደግሞ ደካማና ሕመም የሚበዛበት ነው፡፡ አንዳንዱ ሰው መልከ መልካምና ማራኪ ነው፤ ሌላው ደግሞ አይደለም፡፡

ይህ ኹሉ ቢኾንም ግን በኾነ ነገር ስጦታው ያለው ሰው ስጦታው የሌለውን ሌላውን ሰው ሊንቀው አይገባም፡፡ እግዚአብሔር እንዲህ ለእያንዳንዳችን የተለያየ ስጦታን የሰጠን አንዳችን አንዳችንን እንድንጠቅም ነውና፡፡ እግዚአብሔር እያንዳንዳችን ከሌላው ወንድማችን የምንፈልገው ጥቅም እንዲኖር ያደረገው በመካከላችን መጠላላትና መለያየት እንዳይኖር ነው፤ እንድንፋቀርና አንድ እንድንኾን አስቦ ነውና፡፡

ስለዚህ ወዳጄ ሆይ! ወንድምህ ከአንተ ይልቅ አስተዋይና ዐዋቂ፥ ብርቱም ቢኾን በዚህ ቅር አይበልህ፡፡ ከዚህ ይልቅ እግዚአብሔርን አመስግን፤ ከወንድምህ አስተዋይነትና ዐዋቂነት ብርታትም ትጠቀማለህና፡፡ በዚህ ብቻ ሳታቆምም ራስህን፡- “ስጦታዬ ምንድን ነው? ወንድሜን እኅቴን በምን ልጠቅም እችላለሁ?” ብለህ ጠይቅ፡፡ ይህን ጥያቄ በትክክል ስትመልስ፥ እንደ መለስከው ምላሽም ስትተገብር በአንድ መልኩ በሚበልጥህ ሰው ቅር መሰኘትህን፥ በሌላ መልኩ ደግሞ የምትበልጠውን ሌላውን ወንድምህን መናቅህን ታቆማለህ፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
"የተሳሳተ እምነት ይዘን መልካም ሕይወት ብንኖር ምንም ጥቅም የለውም፡፡ ልክ እንደዛውም ቀጥተኛ ሃይማኖት ይዘን የኃጢአት ኑሮ ብንኖር ምንም ፋይዳ የለውም፡፡ እምነት ብቻ ለመዳን በቂ አይምሰለን ንጹሕ ሕይወትም አስፈላጊና ወሳኝ ነው፡፡"

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ እንዲህ አሉ፦ ማንም ቢሰድብህ ስለ መሰደብህ ሳይሆን ስለ ሰደበህ ሰው አስብ። ያ ሰው ወንድምህ ነው። በፍቅር የተሞላህ መንፈሳዊ ሰው እንደመሆንህ መጠን አንተን በመስደብ ኃጢአት ላደረገው ወንድምህ ምን ልታደርግለት እንደምትችል ታስብ ዘንድ ይገባሃል። በእርግጥ አንተን የተሳደበበት ስድብ በድኅነቱ መግቢያ ላይ ቆሞ ይከለክለውና በዚሁ ሳቢያ ውድ ነፍሱ ወደ ሲዖል ትወርድ ዘንድ አትሻም። በመሆኑም ያንን ኃጢአት ቆጥሮ እንዳይቀጣው ይልቁንም ይቅር እንዲለው እግዚአብሔርን ትጠይቅለታለህ ከዚህ በተጨማሪም እግዚአብሔር አምላክ እንዲህ ካለው ኃጢአት እንዲያወጣውና ዳግመኛ አንተን ሆነ ሌሎችን በመስደብ እንዳይበድል ልትጸልይለት ይገባል።

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
"ስለታሙ የሐሜት ጥርስህ የሚያርፈው በወንድምህ ሥጋ ላይ ሳይሆን ነፍስ ላይ ነው፡፡.በዚህም ጥርስህ ወንድምህን በእጅጉ ትጎዳዋለህ፡፡ እንዲህ በማድረግህ አንተም እርሱንም ሌሎችንም ብዙ ሺህ ጊዜ ትጎዳቸዋለህ፡፡ በሐሜትህ አንተን የሚሰማህ ባልንጀራህ የሐሜት ተባባሪ ይሆናል፡፡ በዚህም ምክንያት እርሱንም በደለኛ ታደርገዋለህ፡፡ እርሱም በእርሱ ላይ ከነገሠበት ኃጢአት የተነሣ ለሌላ ለወዳጁ ምን መርጦ ማውራት እንዳለበት ሳያውቅ ከሐሜተኞች ጎራ ይቀላቀላል፡፡ እንዲህ ዓይነት ሰው ጻድቅ ልንለው እንችላለንን? እንዲህ ዓይነት ሰው በመጦሙ ትልቅ የጽድቅ ሥራን እንደፈጸመ ቆጥሮ ይኩራራል፡፡ ሰዎችን ወደ ኃጢአት እየመራ ትልቅ ሥራን እንደሠራ ሰው ራሱን በከንቱ ያስኮፍሳል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን ሊታይ የሚገባው ትልቁ ቁም ነገር ስለቤተክርስቲያን ጥቅም ሲባል የእንዲህ ዓይነቱን ሰው ንግግር ከመስማት መከልከል እንደሚገባ ነው፡፡ ምክንያቱም የዚህ ሐሜተኛ ወሬ እርሱን ብቻ ኃጢአተኛ የሚያሰኝ ጉዳይ ሳይሆን ቤተክርስቲያንንም ጭምር የሚያሰድብ ነውና፡፡

ስለዚህ በጦም ሰዓታችሁ ጊዜም ይሁን አይሁን ሦስት ነገሮችን በሕሊናችሁ ትይዙ ዘንድ እመክራችኋለሁ፡-
እነርሱም....
✟ ክፉ ከመናገር መከልከልን፣
✟ ማንንም ሰው እንደጠላት ከማየት መቆጠብንና
✟ እንደልምድ አድርጋችሁ ከያዛችሁት መሐላ ትርቁ ዘንድ እመክራቸኋለሁ፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
«ወዳጄ ሆይ! እግዚአብሔር ነዳያንን የሚልክልህ መስጠትን እንድትለማመድ ነው፡፡ ዛሬ በነዳያኑ አድሮ የሚለምንህ ለኋለኛይቱ ቀን ስንቅ እንዲያስቀምጥልህ ወድዶ ነው፡፡ ታድያ ንጉሥ ወደ ቤቱ መጥቶ የሚያባርር ሰው እንደምን ያለ ጎስቋላ ሰው ነው? እንግዲያውስ ነዳያንን ስታይ ወደ አንተ የመጣው ንጉሠ ሰማይ ወምድር ክርስቶስ እንጂ ሰው አይደለምና አትግፋው፡፡ በረከትህንም ከቤትህ አውጥተህ አትሸኘው፡፡»

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
“እኔ ክርስቲያን ነኝ፡፡ ለሚጠይቁት እንደዚህ ብሎ የሚመልስ ሰው በአንድ ጊዜ በኹሉም ነገሮቹ ላይ ማወጁ ነው፡፡ ሀገሩ የት እንደ ኾነ፣ ሥራው ምን እንደ ኾነ፣ ቤተሰቡ እነማን እንደ ኾኑ መመስከሩ ነው፡፡ ክርስቲያን የሰማያዊት ኢየሩሳሌም ነዋሪ እንጂ በምድር ላይ ካሉት ከተሞች የአንዲቱም አይደለምና፡፡”

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Audio
እግዚአብሔር በመጨረሻ ይመጣል

Size:-26MB
Length:-1:14:41

   በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
የአራቱ ኪሩቤልን ስም ቅዱስ ያሬድ እንዲህ ይላቸዋል
፩) ባራማራ
፪) እግረማጣ
፫) ሱርትዮን
፬) መሊጦን
ይላቸዋል። ሃይማኖተ አበው ላይ ስለዚህ ኪሩቤል ሲናገር መናብርት ነባብያን ይላቸዋል። የሚናገሩ መናብርት ይላቸዋል። ከሱራፌል ነገድና ከኪሩቤል ነገድ ሁለት ሁለት ተመርጠው በጠቅላላው አራት ኪሩቤል አሉ። እንደገና በኢዮር ከሚገኙት አርባ ነገዶች አሥሩ ነገድ ኪሩቤል ይባላል።

ሰአሉ ለነ ኀበ እግዚአብሔር ጸባዖት___ቅ. ያሬድ
(ኪሩቤል ሆይ ወደአሸናፊ እግዚአብሔር ለምኑልን)
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
የ፸፪ቱ አርድእት ስም (ምንጭ:-መጽሐፈ ግንዘት)
#፲፪ቱ ሐዋርያት #፬ቱ ወንጌላውያንና ስያሜያቸው
፩) እስጢፋኖስ
፪) ጢሞቴዎስ
፫) ሲላስ
፬) በርናባስ
፭) ቲቶ
፮) ፊልሞና
፯) ቀሌምንጦስ
፰) ዘኬዎስ
፱) ቆርኔሌዎስ
፲) ቴዎፍሎስ
፲፩) ኤውዴዎስ
፲፪) አግናጥዮስ
፲፫) ጳውሎስ
፲፬) አርንያኖስ
፲፭) ማልኮስ
፲፮) ኤሌኖስ
፲፯) አርሳጢስ
፲፰) አስትራትዮስ
፲፱) አርስጦስ
፳) ጋይዮስ
፳፩) አድማጥስ
፳፪) ሉኪዮስ
፳፫) ዲዮናስዮስ
፳፬) መርአንዮስ
፳፭) አርክቦንዮስ
፳፮) አናሲሞስ
፳፯) ከርሳጊስ
፳፰) አኪላስ
፳፱) ሉቃስ
፴) ዮሴፍ
፴፩) ኒቆዲሞስ
፴፪) ያዕቆብ እኁሁ ለእግዚእነ
፴፫) ብርኮሮስ
፴፬) ንኪትስ
፴፭) ቀርስጶስ
፴፮) ክርስቶፎሮስ
፴፯) ፊልጶስ
፴፰) ጰርኮሮስ
፴፱) ኒቃሮና
፵) ጢሞና
፵፩) ጰርሚና
፵፪) ኒቆላዎስ
፵፫) ማርቆስ
፵፬) ሮፎስ
፵፭) እለእስክንድሮስ
፵፮) አንሞስ
፵፯) ስልዋኖስ
፵፰) ሰንቲኖስ
፵፱) ኢዮስጦስ
፶) አክዩቁ
፶፩) አፍሮዲጡ
፶፪) ገማልኤል
፶፫) እንድራኒቆስ
፶፬) አናንያ
፶፭) ጵርስቅላ
፶፮) አቂላ
፶፯) ኤጴንጤስ
፶፰) ዩልያል
፶፱) ጰልያጦስ
፷) መርማራያን
፷፩) ኬፋ
፷፪) ዑርባኖስ
፷፫) ሰጠክን
፷፬) አጤሌን
፷፭) አክሌምንጦስ
፷፮) ሄሮድያኖስ
፷፯) ጥርፌና
፷፰) ጠሪፌስ
፷፱) አስከሪጦስ
፸) ሉቅዮስ
፸፩) ሱሲ
፸፪) ጴጥሮስ
ናቸው። ቅዱስ ጳውሎስ ፲፬ቱን መልእክታት የጻፈው ከ፸፪ቱ አርድእት ውስጥ አይደለም። ከዚህ የተጠቀሰው ሌላ ጳውሎስ ሊሆን ይችላል። ሌሎችም በኋላ የተነሡ ስም ቢኖር ሞክሼ ሊሆን ስለሚችል በደንብ ማየቱ የተሻለ ነው።
#፲፪ቱ #ሐዋርያትና የሚከበሩበት ቀን
፩) መስከረም ፩_በርተሎሜዎስ
፪) ጥቅምት ፲፪_ማቴዎስ
፫) ህዳር ፳/፲፯____ፊልጶስ
፬) ታኅሣሥ ፬_እንድርያስ
፭) ጥር ፬___ዮሐንስ
፮) የካቲት ፲_ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ
፯) መጋቢት ፲____ማትያስ
፰) ሚያዝያ ፲፯____ያዕቆብ ወልደ ዘብዴዎስ
፱) ግንቦት ፳፯_ቶማስ
፲) ሐምሌ ፪___ታዴዎስ
፲፩) ሐምሌ ፭_ጴጥሮስ
፲፪) ሐምሌ ፲_ናትናኤል
አራቱ ወንጌላውያን ከነምሳሌያቸው ደግሞ እንደሚከተለው ቀርበዋል።
#ወንጌላውያን
፩) ዘብእሲ ማቴዎስ__ጌታ ከዳዊት ዘር መወለዱን ስለሚገልጽ ዘብእሲ ተባለ።

፪) ዘአንበሳ ማርቆስ__አንበሳ ላምን ሰባብሮ እንደሚበባ ማርቆስም በግብጽ አውራጃዎች ያሉ ጣዖታትን አስተምሮ አጥፍቷልና ዘአንበሳ አለ።

፫) ዘላሕም ሉቃስ__ለጠፋው ልጅ ፍሪዳ መታረዱን አውስቶ ይጽፋልና ዘላሕም አለው።

፬) ዘንስር ዮሐንስ__ንስር ከፍ ብሎ እንደሚበር ዮሐንስም ከፍ ብሎ ምሥጢረ መለኮትን ይናገራልና ዘንስር አለው።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#የቀበሮ #ፍርድ
ክቡር ዶክተር ከበደ ሚካኤል በአንድ መጽሐፋቸው በግጥም መልኩ ያስቀመጡት ድንቅ ነገር አለ። ይኽውም በአንድ ወቅት በእንስሳት እና በአራዊት ዓለም ታላቅ መከራ ይደርሳል። እና አራዊቱ እንስሳቱ ይሰበሰቡና ይህ ሁሉ የሆነው በኃጢአታችን ምክንያት ስለሆነ ንስሓ እንግባና ፈጣሪ ምሕረቱን ያውርድልን ይባባላሉ። ከዚያ ሁሉም መናዘዝ ይጀምራሉ። አንበሳ ሲናዘዝ "አንድ ወጣት ልጅ ላም እየነዳ ሳለ አንድ ቀን ላሚቱንም ሰውየውንም በልቻቸዋለሁ" ይላል። ይህን ጊዜ ቀበሮ የተከበሩ አንበሳ ያ ልጅ በእርስዎ በመባላቱ እንዲያውም እድለኛ ነው። እርስዎ ያጠፉት ምንም ዓይነት ጥፋት የለም ብላ ትናገራለች። እንዲህ እንዲህ እያሉ ሁሉም ከተናዘዙ በኋላ መጨረሻ ላይ አህያ መናዘዝ ጀመረች። እኔ አንድ ቀን ጌታዬ ጭኖኝ ወደ ገበያ ስሔድ ባለቤቱ ሳያየኝ ከሰው ማሳ አንድ ጉራሽ የሚሆን ሣር በልቻለሁ ትላለች። ይህን ጊዜ ቀበሮ አህያን "አንች አመዳም ለካ ይህ ሁሉ ግፍ የደረሰብን በአንቺ ምክንያት ነው" አለቻትና ሁሉም ተረባርበው በሏት ይላሉ።

ቀበሮዎች ፍርዳቸው እንዲህ ነው። በገንዘብ በጉልበት በሥልጣን ከእነርሱ የሚበልጥ ሰው ከመጣ ቢሳሳትም እንደ ጽድቅ ይቆጥሩለታል። የሰው ልጅ አእምሮ እስካለው ድረስ ውንብድናን በእኩልነት መቃወም አለበት። አድሏዊነት የትንንሽ ሰዎች ሥራ ነው። የሁላችንም መመሪያ እውነት ነው መሆን ያለበት። እውነት ደግሞ እግዚአብሔር ነው። አንዳንዶችን ዘረኝነት አውሯቸው የእነርሱ ዘር የመሰላቸው ሲያጠፋ ዝም ይላሉ። የሌላ ነው ብለው ያሰቡት ሲያጠፋ የእውነት ሰዎች መስለው ዓይናቸውን በጨው አጥበው ይመጣሉ። [እትየ ስመኝ ለማያውቁሽ ታጠኝ]

መፍትሔ የሌለው ችግር የለም። መፍትሔውን ለማምጣት ግን በችግሩ ዙሪያ ያለን እይታ ተቀራራቢ መሆን አለበት። የቤተክርስቲያን ራስ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በእርሱ ሕግ ከተመራን በቀላሉ ችግሮችን መፍታት እንችላለን። ከቀበሮ ፍርድ መውጣት ይገባል። እውነት፣ ቀኖና፣ ዶግማ፣ አስተምህሮ እንዲዳኙ እድል ይሰጣቸው።
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
"እንዲህ [ጳጳስ] ሆነህ ከማይህ ተገንዘህ ወደ መቃብር ሲያወርዱህ ባይ እወዳለሁ" እናት የምትወደው ልጇን
===+===+++======++++===+====+===

መቃርዮስ (ሃይ.አበ.98) ሊቀጳጳሳት ዘእስክንድርያ፡፡ብሉይ ሐዲስ ሲማር አደገ ከእርሱ አስቀድሞ የነበረው ሊቀጳጳስ አረፈ፡፡ከዚያ እርሱ ተሾመ በተሾመ ጊዜ ተሾምሁ የምስራች ብሎ ለእናቱ ላከ፡፡

ለመልእክተኞች የማትመልስላቸው ሆነች፡፡የእናቴ ነገር እኔን እንጂ ካልመጣ ብላ ነው ብሎ ልብሰ መዓርጉን ለብሶ ማኅበሩን አስከትሎ ሄደ፡፡ መጣ ብለው ነገሯት ከቤት የማትወጣ ሆነ፡፡

ከዚያ ልጅሽኮ ነኝ አላወቅሽኝም አላት። "አንተ አላወቅህም እንጂ እኔስ አውቄሀለሁ እንዲህ ሁነህ ከማይህ ተገንዘህ ወደ መቃብር ሲያወርዱህ ባይ እወዳለሁ" አለችው። "ከዚህ አስቀድሞ በራስህ ኃጢአት ይፈረድብህ ነበር ከእንግዲህ ወዲህ ግን በሕዝቡ ኃጢአትም ይፈረድብሀል" አለቸው፡፡

እርሱም ይህ ተግሳጽ ሁኖት እስከጊዜ ሞቱ ከማስተማር ሳያርፍ ኖሯል፡፡ [የአሁን መነኮሳት ደግሞ ጵጵስና ሳንሾም ከምንቀር ተገንዘን ብንቀበር ይሻላል የሚሉ ይመስላል።

ምንጭ፦ ሃይማኖተ አበው አንድምታ ትርጓሜ

© በትረማርያም አበባው
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
👉 ሴት በወር አበባዋ ጊዜ መጸለይ ትችላለች?
👉​​ ግለ አውናን / ሴጋ /ማስተርቤሽን/ የፈጸመ ሰው ተክሊል ማግባት ይችላልን?
👉 በሱባኤ ወቅት ህልመ ሌሊት (ዝንየት) ቢመታን ምን እናደርጋለን?
👉 ሕልመ ሌሊት በራሱ ኃጢአት ነውን?
👉 ሕልመ ሌሊት በምን ይከሰታል?
👉 ከዝሙት አጋንንት እና ከዝንየት በተጨማሪ በሕልመ ሌሊት የሚፈትነን አጋንንት የትኛው ነው?
👉 የሕልመ ሌሊት መፍትሔ ምንድን ነው?

ለእነዚህ ሁሉ መልስ ለማግኘት ይቀላቀሉ
Channel link
@tewahdo_haymanotea
#ተስዓቱ #ቅዱሳን
፩) አባ አረጋዊ
፪) አባ ሊቃኖስ
፫) አባ ይምአታ
፬) አባ ጽሕማ
፭) አባ ጉባ
፮) አባ አፍጼ
፯) አባ ጰንጠሌዎን
፰) አባ አሌፍ
፱) አባ ገሪማ (አባ ይስሐቅ?)

በቤተክርስቲያን አስተምህሮ ዘረኝነት በጣም የተጠላ ተግባር ነው። ስለሆነም ጻድቃንን የትም ይወለዱ በየትኛውም ዘመን ይነሡ በእኩልነት እንወዳቸዋለን። ተስዓቱ ቅዱሳን ከውጭ ሀገር መጥተው ለኢትዮጵያ ቅድስት ቤተክርስቲያን ትልቅ ውለታ የዋሉላት አባቶቻችን ናቸው።

© በትረማርያም አበባው
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በተለየ ያዘነችባቸው ፭ቱ ኃዘናት የሚከተሉት ናቸው።
፩) ስምዖን ጌታን እንደሚሰቅሉት በተነበየ ጊዜ
፪) በቤተመቅደስ ሦስት ቀን ፈልጋ ባጣችው ጊዜ
፫) ልጇን ጌታን እጁን አስረው አይሁድ ሲገርፉት
፬) ልጇ ኢየሱስ በሽፍቶች መካከል ሲሰቀል
፭) ጌታን በሥጋው በመቃብር ሲቀብሩት
ጌታም እነዚህን አምስቱን ኀዘናት አስቦ አቡነ ዘበሰማያት የሚለውን እምረዋለሁ። መንግሥቴንም አወርሰዋለሁ ብሏታል።

ተገቢ ኀዘን እና ተገቢ ያልሆነ ኀዘን አለ ሞተ ወልደ እግዚአብሔርን ግፍዐ ሰማእታትን እያሰቡ ማልቀስ በደልን እያሰቡ በንስሓ ማልቀስ ዋጋ ያለው ልቅሶ ነው። ሥጋዊ ነገር አጣሁ ብሎ ማልቀስ ግን አይገባም።

© በትረማርያም አበባው@
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት የተሰጠ መግለጫ፤
*******

ሐምሌ ፲፯ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም አዲስ አበባ
"""""""""""""""""""""""""""""""""""""""

1. በክልል ትግራይ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት በክልሉ ከሚገኙት አህጉረ ስብከት ጋር ተቋርጦ የነበረውን መዋቅራዊ ግንኙነት ችግር በውይይት እንዲፈታ ቅዱስ ሲኖዶስ ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪና ልዑካኑን በአካል ልኮ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ባለበት ወቅት በክልሉ የሚገኙ ብፁዓን አባቶች ሕገ ቤተ ክርስቲያንንና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ ቅዱስ ፓትርያርኩ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ተብለው በሚጠሩበት በማዕከላዊ ትግራይ ዞን አክሱም ሀገረ ስብከት በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ሐምሌ 15 እና 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በተከናወነ ሕገ ወጥ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት መፈጸሙን በመገናኛ ብዙኃን ለማወቅ ችለናል፡፡ በመሆኑም በዚህ የዶግማና የቀኖና ጥሰት ተግባር የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በእጅጉ አዝኗል፡፡

2. በመሆኑም የተከሰተው የዶግማ፣ የቀኖና እና አስተዳደራዊ ጥሰት አስመልክቶ ተወያይቶ ተገቢውን ለመወሰን ለሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥሪ ተላልፏል፡፡

3. የስብሰባው ቀን ሊራዘም የቻለው በውጭው ክፍለ ዓለማት ያሉት ሊቃነ ጳጳሳት መገኘት ስላለባቸው የጉዞ ቀኑ እንዳያጥር እና በሀገር ውስጥ የሚገኙትም ሊቃነ ጳጳሳት ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ምክንያት ለአገልግሎት ወደ አህጉረ ስብከታቸው የሄዱ በመሆኑ ለመመለሻ የሚያስፈልገውን ጊዜ ታሳቢ በማድረግ ነው፡፡

4. በየደረጃ ያሉ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የሥራ ኃላፊዎች እና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ምዕመናን ከአሁን ቀደም በቤተ ክርስቲያናችን ላይ በደረሰው ፈተና በሐዘንና በጸሎት ከቤተ ክርስቲያናችን ጎን በመቆም ላሳያችሁት ጽናት እያመሰገንን አሁንም በደረሰው ፈተና እንዳሁን ቀደሙ ሁሉ በሐዘንና በጸሎት ከቤተ ክርስቲያናችን ጎን ጸንታችሁ እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

5. በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በጉዳዩ ላይ ተወያይቶ ተገቢውን ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ በትግዕስት እንድትጠብቁ እናሳስባለን፡፡

6. ምንም እንኳን ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በሙሉ ጥሪው በደብዳቤ የተላለፈ ቢሆንም የመልእክቱ በፍጥነት መድረስ ካለው ስጋት አንጻር የችግሩን ተደጋጋሚነትና አሳሳቢነት ከግምት ውስጥ በማስገባት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭው ክፍለ ዓለማት የምትገኙ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በሙሉ እስከ ሐምሌ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ተጠቃላችሁ ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ እንድትመጡ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡


7. ሁሉም የቤተ ክርስቲያናችን ሚዲያዎችና ሌሎች መገናኛ ብዙኃን ይህን መልዕክት ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን መልእክቱን በማስተላለፍ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ በቤተ ክርስቲያናችን ስም እንጠይቃለን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ሐምሌ 17 ቀን 2015 ዓ.ም.
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
2024/09/23 18:28:58
Back to Top
HTML Embed Code: