Telegram Web Link
"ዲያብሎስ ልጅነታችንን እናቆሽሽ ዘንድ በእኛ ላይ የሚተናኰለው ተንኰል በጣም ተደጋጋሚና ኃይለኛ ነው፡፡ ስለዚህ ይህን መንቻካ የዲያብሎስን ደባ ድል እንነሣ ዘንድ ዘወትር ንቁዎችና ጠንቃቆች ልንኾን ይገባናል፡፡ እኛ ይህን ማድረግ ሳንችል ቀርተን እጅግ ጥቂት መግቢያ ቀዳዳ የምንተውለት ከኾነ ግን እርሱ ጥቂቷን ቀዳዳ ሰፊ በር ያደርጋታል፡፡ እንዲህ አድርጎም ኃይሉን ኹሉ ተጠቅሞ ወደ እኛ ይገባል፡፡

ስለዚህ ስለ ድኅነታችን የሚገደን ከኾነ እንደዚህ ጥቂትና ቀልድ በሚመስሉ ነገሮች እንኳን አንዘናጋ፤ እርሱ የሚንቀውና ጥቂት የሚለው ኃጢአት የለምና፡፡ እኛ ጥቃቅን የምንላቸውን ነገሮች መነሻ አድርጎ ልጅነታችንን የምናቆሽሽበትን ታላላቅ ኃጢአቶችን እንድንሠራ አድርጎ እጅግ ይተጋልና፡፡"

ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Forwarded from የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ ("የአምር አቡክሙ ሰማያዊ ዘትፈቅዱ ዘእንበለ ትስአልዎ።" ማቴ. ፮፡፰)
መወድስ
●ከዊነ ምንትኑ ይኄይስ እም ከዊነ ሰብእ ከዊነ ዝእብኑ ወሚመ ከዊነ የዋህ በግዕ፥
●ባሕቱ ይኄይስ ከዊነ ተኵላ ሐቅል ኅቡእ፥
●በትምይንቱ ወበጽልሑቱ እም ተኵላ ገዳም እስመ ብእሰ ሰብእ፥
●ዘበኍልቈ ጸጕሩ ኀጣውኢሁ ወእምዘ የሐነክስ ሰብእ ተኵላ ገዳማት ይረትዕ፥
●ዝሰ ከመ ሀሎ ይዘንጋዕ፥
●ሶበ እንዘ ይብለነ ሐዋርያ መብልዕ ኢይበቍዕ፥ (፩ ቆሮ. ፰፡፰)
●በምልኡ ዓለም ለመብልዕ፥
●ላዕለ የዐርግ ወላዕለ ይወፅእ።

👉እም ኀበ መምህር ያሬድ ዘርአ-ቡሩክ
👉፳፻፬ ዓ.ም
👉ባሕር ዳር ሽንብጥ ፈለገ ፀሓይ ቅዱስ ሚካኤል ገዳም

የዩቲዩብ ድሕረ ገጽ👇
https://www.youtube.com/@yaredzera-buruktube8843

የፌስቡክ ገጽ👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=100063724038968&mibextid=ZbWKwL

የፌስቡክ ገጽ👇
https://www.facebook.com/Yared.ZeraBuruk?mibextid=ZbWKwL

👉የቴሌግራም ቻናል
https://www.tg-me.com/yaredzer

👉ለሌላውም እንዲደርስ share ያድርጉት!!!
Forwarded from የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ ("የአምር አቡክሙ ሰማያዊ ዘትፈቅዱ ዘእንበለ ትስአልዎ።" ማቴ. ፮፡፰)
"...ሰው ያለ ሕግ ሥራ በእምነት እንዲጸድቅ እንቆጥራለንና..." ሮሜ. 3:28

#ሰው_በእምነት_ብቻ_ይጸድቃልን?
በመ/ር ያሬድ ዘርአ-ቡሩክ = አዲስ አበባ

👉በ16ኛው መቶ ክ/ዘ ለተፈበረኩት ፕሮቴስታንታውያን የተሰጠ የማያዳግም አጥጋቢ መልስ ● Share ይደረግ!

ክፍል ፩. እምነት

ሰው በእምነት ብቻ በጭራሽ ሊድንም ሆነ ሊጸድቅ አይችልም። አንድ ሰው መዳንን ወርሶ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት በትንሹ የሚከተሉት ሰባት መሥፈርቶች ያስፈልጉታል፦ ማመን፣ መጠመቅ፣ መቍረብ፣ መመስከር፣ ሕግን መጠበቅ፣ ሥራን መሥራት እና መጋደል። እነዚህም ሥርዐታት ሳይሆኑ በቀጥታ ከመዳን ጋር የተያያዙ ለመዳን መሟላት ያለባቸው ቀደምት መሣፍርት ናቸው።

እምነት፦ መስማትን፣ ማዳመጥንና ማየትን ተከትሎ የሚመጣ ነው። በቅዱስ መጽሐፍም "እምነት ከመስማት ነው፥ መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።" (ሮሜ. 10:17) ተብሏል። ማንኛውም ሰው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት በሥላሴ አንድነትና ሦስትነት፣ በእግዚአብሔር ወልድ ነገረ ሥጋዌ፣ በቅዱሳን መላእክትና ሰዎች ምልጃና ጸሎት ሊያምን ይገባል። በምሥጢረ ሥላሴም ማመን እንዲገባ "እኔ በአብ እንዳለሁ፥ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ፤ ባይሆንስ ስለ ራሱ ስለ ሥራው እመኑኝ።" (ዮሐ. 14:11፤ 10:38፤ 14:1) ተብሏል። ቅዱስ ጳውሎስም በዕብራውያን መልእክቱ ላይ 3:12 "ወንድሞች ሆይ፥ ምናልባት ሕያው እግዚአብሔርን የሚያስክዳችሁ ክፉና የማያምን ልብ ከእናንተ በአንዳችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ።" በማለት በሕያው እግዚአብሔር (ሥላሴ) የማያምን ልብ እንዳይኖር ያስጠነቅቃል።

ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን በተመለከተም፦ "በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።" (ዮሐ. 3: 36) ተብሏል። ዳግመኛም "በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን በነፍሱ ምስክር አለው፤ በእግዚአብሔር የማያምን እግዚአብሔር ስለ ልጁ የመሰከረውን ምስክር ስላላመነ ሐሰተኛ አድርጎታል።" (1ኛ ዮሐ. 5: 10) ተብሎ ተተንትኖ ተቀምጧል።

አንድ የወህኒ ቤት ጠባቂም መዳን የሚቻልበትን ፈልጎ በጠየቀ ጊዜ ቅዱስ ጳውሎስና ቅዱስ ሲላስ "በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን፥ አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ።" በማለት መልሰውለታል። ሐዋ. 16:3። በቅዱሳንም ተራዳኢነት መታመን ለመዳን ምክንያት እንደ ሆነ "በአምላካችሁ በእግዚአብሔር እመኑ፥ ትጸኑማላችሁ፤ #በነቢያቱም እመኑ፥ ነገሩም ይሰላላችኋል።" (2ኛ ዜና. 20:20) ተብሎ ተጽፏል።

እምነት፦ ሕግ ያለው፥ በሕግ የሚጓዙበት ቀጥተኛ መሥመር ነው። ቅዱስ ጳውሎስም "ትምክሕት እንግዲህ ወዴት ነው? እርሱ ቀርቶአል። በየትኛው ሕግ ነው? በሥራ ሕግ ነውን? አይደለም፥ #በእምነት_ሕግ ነው እንጂ።" (ሮሜ. 3:27) በማለት እምነት በሕግ የሚመላሱበት እንጂ በጋጠወጥነት ሥርዐት አልባና ስድ ተሁኖ የሚከተሉት እንዳልሆነ እንቅጩን ቃል ተናግሯል።

እምነት በሥራ ካልታገዘ እምነት ብቻውን በድን ነው። ቅዱስ ያዕቆብ 2:17 "ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው።" ሲል ጽፏል። እምነትና ሥራ ድርና ማግ ሆነው ሳይነጣጠሉ በሰዎች ሕይወት ላይ መሰፋት አለባቸው። ቅዱስ ያዕቆብም በዐጭር አገላለጽ "ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደ ሆነ እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው።" ያዕ. 2:26 በማለት በእምነት ብቻ እንጸድቃለን ለሚሉ ከንቱዎች የማያዳግም ልብ አርስ መልስ ሰጥቷል።

በእምነት ብቻ መዳን የሚገኝ ቢሆን ኖሮም ከሉተራውያን እጅግ በተሻለ ደረጃ በእግዚአብሔር ፍጹም እምነት ያላቸው አጋንንት ቀድመው መዳንን ይወርሱ ነበር። ነገር ግን በእምነት ብቻ እንዲሁ በቀላሉ መዳንን ማግኘት የሚቻል አይደለም። የመናፍቃን መዶሻ ቅዱስ ያዕቆብ "እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ #አጋንንት ደግሞ #ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል።" (ያዕ. 2:19) በማለት የአጋንንትን እምነት ገልጦ ነገር መጽደቅ እንደማይቻላቸው ጽፏል።

ቅዱስ ጳውሎስም በሮሜ መልእክቱ 3:28 "...ሰው ያለ ሕግ ሥራ በእምነት እንዲጸድቅ እንቆጥራለንና..." ብሎ መናገሩ በሕግ ሥራ ብቻ እንጸድቃለን ይሉ ለነበሩ፥ በሮም ተሰደው ይኖሩ ለነበሩ አይሁድ በሕግ ሥራ ብቻ መጽደቅ እንደማይቻል አስረግጦ ሲያስገነዝባቸው ነው።

የሕግ ሥራ ብሎ የገለጠውም ግዝረትን ነው። ገና ከመጀመሪያው ሲጀምርም "እንግዲህ የአይሁዳዊ ብልጫው ምንድር ነው? ወይስ የመገረዝ ጥቅሙ ምንድር ነው? በሁሉ ነገር ብዙ ነው።" ይልና "እግዚአብሔር የአይሁድ ብቻ አምላክ ነውን? የአሕዛብስ ደግሞ አምላክ አይደለምን? አዎን፥ የተገረዘን ስለ እምነት ያልተገረዘንም በእምነት የሚያጸድቅ አምላክ አንድ ስለ ሆነ የአሕዛብ ደግሞ አምላክ ነው።" ሮሜ. 3:1፣ 29-30 በማለት ያብራራል።

በመቀጠልም "እንግዲህ ሕግን በእምነት እንሽራለንን? አይደለም፤ ሕግን እናጸናለን እንጂ።" ሮሜ. 3:31 በማለት ማንኛውም አማኝ ሕግን እንዲከተል በአጽንዖት ያስገነዝባል።

አስተዋይ ልቡና ያለው ሰው በሮሜ. መልእክቱ 4:1-15 ላይ ቅዱስ ጳውሎስ የጻፈውን፥ የሚከተለውን እንደ ፀሐይ የሚያበራ ግልጽ ዐሳብ በቀላሉ አንብቦ መረዳት ይችላል፦

<<እንግዲህ በሥጋ አባታችን የሆነ አብርሃም ምን አገኘ እንላለን? አብርሃም በሥራ ጸድቆ ቢሆን የሚመካበት አለውና፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ዘንድ አይደለም። መጽሐፍስ ምን አለ? አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት። ለሚሠራ ደመወዝ እንደ ዕዳ ነው እንጂ እንደ ጸጋ አይቈጠርለትም፤ ነገር ግን ለማይሠራ፥ ኃጢአተኛውንም በሚያጸድቅ ለሚያምን ሰው እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቈጠርለታል። እንደዚህ ዳዊት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ሥራ ጽድቅን ስለሚቈጥርለት ስለ ሰው ብፅዕና ይናገራል እንዲህ ሲል። ዐመፃቸው የተሰረየላቸው ኀጢአታቸውም የተከደነላቸው ብፁዓን ናቸው፤ ጌታ ኀጢአቱን የማይቈጥርበት ሰው ብፁዕ ነው።

እንግዲህ ይህ ብፅዕና ስለ መገረዝ ተነገረ? ወይስ ደግሞ ስለ አለመገረዝ? እምነቱ ለአብርሃም ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት እንላለንና። እንዴት ተቈጠረለት? ተገርዞ ሳለ ነውን? ወይስ ሳይገረዝ? ተገርዞስ አይደለም፥ ሳይገረዝ ነበር እንጂ። ሳይገረዝም በነበረው እምነት ያገኘው የጽድቅ ማኅተም የሆነ የመገረዝን ምልክት ተቀበለ፤ ይህም እነርሱ ደግሞ ጻድቃን ሆነው ይቆጠሩ ዘንድ ሳይገረዙ ለሚያምኑ ሁሉ አባት እንዲሆን ነው፥ ለተገረዙትም አባት እንዲሆን ነው፤ ይኸውም ለተገረዙት ብቻ አይደለም ነገር ግን አባታችን አብርሃም ሳይገረዝ የነበረውን የእምነቱን ፍለጋ ደግሞ ለሚከተሉ ነው። የዓለምም ወራሽ እንዲሆን ለአብርሃምና ለዘሩ የተሰጠው የተስፋ ቃል በእምነት ጽድቅ ነው እንጂ በሕግ አይደለም። ከሕግ የሆኑትስ ወራሾች ከሆኑ እምነት ከንቱ ሆኖአል የተስፋውም ቃል ተሽሮአል።>>
‹‹ተስፋ ለሕይወታችን አስፈላጊ ነገር ነው:: ሰው ተስፋ ካጣ ሁሉንም ነገር ያጣል። ተስፋ ያጣ ሰው ደግሞ በጭንቀት፣ በስቃይ፣ ግራ በመጋባት፣ ዓላማ በሌለው ጥበቃና በዛለ መንፈስ ውስጥ የወደቀ ስለሚሆን ሰይጣን በመዳፎቹ ውስጥ አስገብቶ መጫወቻ ያደርገዋል፡፡ ይህ በመሆኑም ወደ ተስፋ መቁረጥ የሚመራው ሰይጣን ነው እንላለን፡፡ ይሁን እንጂ የእግዚአብሔር ልጆች ምን ጊዜም ተስፋ ስላላቸው በማንኛውም ሰዓት የሚኖሩት በተስፋ ነው፡፡

በማንኛውም ሰዓት የሚኖሩት በተስፋ ነው፡፡ በመከራ ጊዜ ተስፋ አላቸው፤ ነገሮች ሲወሳሰቡ ተስፋ አላቸው፤ ከዚህ በተጨማሪ እግዚአብሔር የዘገየ በሚመስልበት ጊዜና ነገሮች ሁሉ ጨለማ በሚመስሉበት ጊዜም ተስፋ ይኖራቸዋል፡፡››

(ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ)
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ተወዳጆች ሆይ! እስኪ ልጠይቃችሁ፦ አንድ ሰው የተጣራ ወርቅ ልሰጣችሁ እመጣለሁና የኾነ ቦታ ላይ ጠብቁኝ ቢላችሁ ምን ታደርጋላችሁ? ወደዚያ ቦታ ለመሔድ አስፈላጊ ነው የምትሉትን ኹሉ አታደርጉምን? ቀኑን ሙሉም ቢኾን ቁጭ ብላችሁ አትጠብቁምን?

እግዚአብሔር እሰጣችኋለሁ ያላችሁ ግን አንዲት ወይም ዐሥር ወይም ሃያ ወይም መቶ ወይም አንድ ሺሕ ቅንጣት ወርቅ አይደለም፤ ወይም ምድርን ኹሉ አይደለም፡፡ ከዚህ ኹሉ የምትበልጠው መንግሥተ ሰማያት እንጂ፡፡ ከዚህ የሚበልጥ ስጦታ ታዲያ ምን አለ? ይህንን ስጦታ ለማግኘት የማይደክሙ ሰዎችስ እንደምን ያሉ ምስኪናን ናቸው?

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

#ይቀላቀሉ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
አንድን በክፉ ምግባር የተያዘን ሰው ወደ መልካም ነገር ልትመልሰው ብትወድድ መጀመርያ ሰላሙን እንዲያገኝ አድርገው፡፡ በፍቅር ቃል ከፍ ከፍ አድርገው። እንዲህ ያለን ሰው ከክፉ ስራው እንዲመለስ ለማድረግ ከዚህ የተሻለ ዘዴ የለምና። ሰው በተግባር የሚያደርገው ፍቅር ሰዎችን የመለወጥ ፍጹም ሀይል አለውና።

ቀጥለህ በፍቅር አንድ ሁለት ቃልን ንገረው፣ በቁጣ አትንገረው። በእርሱ ላይ አንዳች የጠላትነት ስሜት አታሳይ። ፍቅር ሰዎችን ለመለወጥ መንገዱን እርሱ ያውቅበታል። ብቻ እንተ እድሉን ስጠው። የፍቅር ሰውም ሁን።

(መክስምያኖስ ባህታዊ ዘሶርያ - የበረሃ ፈርጦች)

"ከእውነት የራቀ ማንኛውም ሰው ከእግዚአብሔር መንፈስ የራቀ ነው፡ ከእውነት የተለየም ማንኛውም ሰው ከእግዚአብሔር የተለየ ነው።"

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

"የሥልጣን ፍቅርን ያኽል ቤተ ክርስቲያንን የሚከፍላት ጽኑ ደዌ  የለም።"
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

“እኔ ክርስቲያን ነኝ፡፡ ለሚጠይቁት እንደዚህ ብሎ የሚመልስ ሰው በአንድ ጊዜ በኹሉም ነገሮቹ ላይ ማወጁ ነው፡፡ ሀገሩ የት እንደ ኾነ፣ ሥራው ምን እንደ ኾነ፣ ቤተሰቡ እነማን እንደ ኾኑ መመስከሩ ነው፡፡ ክርስቲያን የሰማያዊት ኢየሩሳሌም ነዋሪ እንጂ በምድር ላይ ካሉት ከተሞች የአንዲቱም አይደለምና፡፡
                •➢ ሼር // SHARE

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
👉 ሴት በወር አበባዋ ጊዜ መጸለይ ትችላለች?
👉​​ ግለ አውናን / ሴጋ /ማስተርቤሽን/ የፈጸመ ሰው ተክሊል ማግባት ይችላልን?
👉 በሱባኤ ወቅት ህልመ ሌሊት (ዝንየት) ቢመታን ምን እናደርጋለን?
👉 ሕልመ ሌሊት በራሱ ኃጢአት ነውን?
👉 ሕልመ ሌሊት በምን ይከሰታል?
👉 ከዝሙት አጋንንት እና ከዝንየት በተጨማሪ በሕልመ ሌሊት የሚፈትነን አጋንንት የትኛው ነው?
👉 የሕልመ ሌሊት መፍትሔ ምንድን ነው?

ለእነዚህ ሁሉ መልስ ለማግኘት ይቀላቀሉ
Channel link
@tewahdo_haymanotea
++++ ያልተተከሉ ዛፎች +++


አንድ ሩስያዊ የቴዎሎጂ መምህር የተናገሩትን አዝናኝ ወግ ሐበሻዊ ቀለም ሠጥቼ እንዲህ ልተርከው :-

ባልና ሚስት ከተጋቡ ጥቂት ዓመታት ቢያልፋቸውም ልጅ ግን አልወለዱም ነበር:: ወደ አንድ አባት ይሔዱና እባክዎን ልጅ እንዲሠጠን ይጸልዩልን ይሏቸዋል:: አባም ችግሩን ሰምተው የሚከተለውን ምክር ሠጡ

“እዚያ ተራራ ላይ ያለችው ገዳም ትታያችኁዋለች?" አሉአቸው
"አዎ አየናት" አሉ ባልና ሚስቱ
"ነገ በጠዋት እህል ሳትቀምሱ ሒዱና ገዳሙ ውስጥ የወይራ ዛፍ ተክላችሁ ልጅ ሥጠን ብላችሁ ስእለት ተሳሉ"

ባልና ሚስት በማግሥቱ ወደ ገዳሙ ሔደው የወይራ ዛፉን ተከሉ:: ይህ በሆነ በጥቂት ቀናት ልዩነት ውስጥ አባ ወደ ሌላ ሀገረ ስብከት ተመድበው ከዚያች ትንሽ የገጠር ከተማ ተሰናብተው ሔዱ::

ከሃያ ዓመታት ቆይታ በኁዋላ በአንድ አጋጣሚ አባ ወደዚያች ከተማ ተመልሰው መጡ:: ትንሹ ከተማ ትልቅ ሆኖ ብዙ ነገር ተለውጦ ጠበቃቸው:: የመጡበትን ጉዳይ ከፈጸሙ በኁዋላ የእነዚያ ባልና ሚስት ነገር ትዝ አላቸው:: በከተማው መቀየር ትንሽ ቢቸገሩም ቤቱን ፈልገው አገኙትና በር አንኳኩ::

አንድ የሚያምር ሕፃን የታቀፈች ሴት በሩን ከፈተች:: መካኒቱ ሴት ነበረች:: ከታቀፈችው ልጅ ሌላ እግርዋን ተጠምጥመው የያዙ ሁለት ሕጻናት አባን ሽቅብ እያዩ ይቁለጨለጫሉ:: መስቀል አሳልመው ወደ ውስጥ ሲዘልቁ ሶፋ ላይ ቁጭ ብለው ቴሌቪዥን የሚመለከቱ አራት ሕጻናት ተደርድረዋል::

ታላቆቻቸው የሚሆኑ ሁለት ልጆች ደግሞ ጠረጴዛው ላይ ቁጭ ብለው ያጠናሉ:: ይህ እንግዲህ ቡና የምታፈላውን ሴት ልጅና በሕፃን ልጅ አልጋ ላይ የተኛውን አራስ ልጅ ሳይጨምር ነው::

አባ በደስታም በመደነቅም ፈዝዘው ቀሩ::
"እንኩዋን ለዚህ አበቃችሁ ልጄ" አሏት በደስታ
"በእርስዎ ጸሎት ነው አባታችን" አለች እናት
"ለመሆኑ ባለቤትሽ የት ነው?" አሉ በጉጉት
እናት አንገትዋን ደፋች አባ ደነገጡ
"ምነው ሰላም አይደለም?" አሉ በስጋት
"ኸረ ሰላም ነው ... በጠዋት ወደዛች ተራራ ላይ ወዳለችው ገዳም ሔዶአል" አለች እያፈረች
"ምነው? ለምን ጉዳይ ሔደ?"
"ያኔ የተከልነውን የወይራ ዛፍ ሊቆርጥ"

✍🏽 ✍🏽 ✍🏽. ✍🏽. ✍🏽 ✍🏽 ✍🏽

ሊቁ ተርቱሊያን "የሰማዕታት ደም የክርስቲያኖች ዘር ነው" ብሎ ነበር:: "ክርስቲያን መግደል ክርስቲያን እንዲበቅል መዝራት ነው" እንደማለት ነው:: ከዚያ ውጪ ደግሞ ሌላው የክርስቲያን ዘር መውለድ ነው:: ብዙ ምእመናን የመውለድን ጸጋ ተጎናጽፈው ከመውለድ ይሸሻሉ::

ድሆች ሆነው እንኩዋን በፈጣሪ መግቦት አምነው የሚወልዱ እንዳሉ ሁሉ የኢኮኖሚ አቅም እያላቸው የተማሩ በመሆናቸው መውለድን እንደ ኁዋላ ቀርነት ቆጥረው ከመውለድ ወደ ኁዋላ የሚሉም ብዙዎች ናቸው::

ከላይ እንዳየነው ሰው ያህል እንኩዋን ሳይወልዱ ዛፍ ቆረጣ የሚሮጡ ብዙዎች ናቸው:: የሚወልደውን ኸረ በቃህ በቃሽ እያሉ የሚተቹ "ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሉ ሲባል ብቻህን ልትሞላ ነው እንዴ?" ብለው በወለዱ የሚዘብቱ አሉ::

መውለድ ጸጋ በረከት ነው:: የልጅን ጣዕምና ጸጋ የወለዱ ሁሉ ያውቃሉ:: ልጅ መውለድ የወላጆችን መንፈሳዊ ሕይወት ሳይቀር ከፍ ያደርጋል:: ልጅ ፊት አይወራም ሲባል ከሚተው ክፉ ወሬ ጀምሮ አርኣያ ለመሆን ሲባል ከሚደረግ ጥረት ድረስ ልጅ መውለድ ትልቅ በረከት ነው::

ለቤተ ክርስቲያን ደግሞ የልጆች መብዛት በረከት ነው:: አንድ አባትም "በሕፃናት የለቅሶ ጩኸት የማትረበሽ ቤተ ክርስቲያን የነገ ተስፋ የሌላት ቤተ ክርስቲያን ናት" ብለዋል:: ሕፃናት የሚበዙባት ቤተ ክርስቲያን ግን ነገ እንደምትኖር ያረጋገጠች ቤተ ክርስቲያን ናት።

ክርስቲያኖች ሆይ ውለዱ!

(በመምህር ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
"እንኳን አንተ እኔም አልገባሁም"
"እንኳን አንተ እኔም አልገባሁም"

ይህን ባየሁ ጊዜ አንድ ያነበብኩት ታሪክ ትዝ አለኝ። ታሪኩ እንዲህ ነው።

ሰውየው ናይጄሪያዊ ነው። በሃይማኖቱም የምስራቅ ኦርቶዶክሳዊት እምነት ተከታይ ነው። ቀን በንግድ ሥራ የሚተዳደር ታታሪም ሠራተኛ ነበር። ከዚህ በላይ መንፈሳዊም ሰው ስለሆነ ሰንበተ ክርስቲያንን ከእግዚአብሔር ውጪ ለማንም አይሰጥም ነበር።

ከሰኞ እስከ አርብ የንግድ ሥራውን ያከናውንና፤ ቀዳሚትን ለተለያዩ ማኅበራዊ ጉዳዮች ይጠቀማታል። እሁድን ግን በማለዳ ተነስቶ ያስቀድሳል። ሲዘጋጅ ሥጋ አምላክ ይቀበላል። ሕይወቱን የሚመራው እንዲህ ባለ መንገድ ነው።

ታዲያ አንድ ቀን ሀገሩ የሚሸጠውን ዕቃ ለመጫን ወደ ምዕራባውያኑ ሀገር ይጓዝና አንድ የሚያርፍበት ሆቴል ከተከራየ በኋላ የገበያውን ሁኔታ ለማጥናት ሲዘዋወር፤ አንድ ቤተ መቅደስ ያይና ተደስቶ፤ "በቃ እሁድ አይባክንብኝም። በማለዳ ተነስቼ መጥቼ አስቀድሳለሁ" ብሎ ከራሱ ጋር ቀጠሮ ይይዛል።

ቀኑ ደርሶ ለራሱ ቃል እንደገባው በማለዳ ተነስቶ ወደ ተመለከተው መቅደስ ይገሰግሳል። ሲደርስ ግን እንግዳ ነገር ይገጥመዋል። መቅደሱ በር ላይ የነበረው ዘበኛ "አትገባም" ይለዋል። "ለምን መቅደስ አይደለም?" ብሎ ሲጠይቀው፤ ሰውየው መልሶ "አዎ መቅደስ ነው ነገር ግን ጥቁር አይገባበትም" ብሎ ይመልስለታል።

ይህ አፍሪካዊ ነጋዴ በመልሱ ተደንቆ "ኧረ ግድ የለህም ለጥቁር ሌላ አምላክ የለውም። አንተን ነጭ አድርጎ የእኔን አጥቁሮ የፈጠረ እግዚአብሔርም የለም። እኔ የጠቆርኩት ፀሐይ በሚበረታበት አካባቢ ከሠሃራ በታች ስለምኖር ነው።" ብሎ አስረዳው።

ዘበኛውም በመልሱ በመደነቅ "ኦው እስከ ዛሬ ድረስ የነጭ አፈጣጠር የተለየ አድርጌ አስብ ነበር። ይህን እውነት ነግረህ ምልከታዬን ስላቃናኸው አመሰግናለሁ። ግን አትገባም።" ይለዋል። ይህ ምስኪን አፍሪካዊ ቀጠል አድርጎ "እውነቱ ከገባህ አንተ ልታገኘው ከተዘጋጀህለት አምላክ እኔን ለምን ትለየኛለህ?" ሲለው፦ ዘበኛው በማዘን "የነገርኸኝ እውነት የገባኝ እኔን እንጂ አለቆቼን አይደለምና፤ አዝናለሁ። አለቆቼ ለምን ጥቁር አስገባህ ብለው እኔን መጠየቃቸው አይቀርምና አታድክመኝ።" ብሎ በሩን ዘጋበት።

ይህ አምላኩን የፈለገና እሁድ እንዳይባክንበት የተጨነቀ ምስኪን፥ "ባያስገቡኝ እንኳ ሲቀድሱ ከውጪ ኾኜ ልስማ" ብሎ ጆሮውን ከመቅደሱ ግድግዳ ቢያስጠጋ ድምፅ ወደ ውጪ የማያስተጋባ ግድግዳ ነበር።

ባለመስማቱና ሰው ሀገር በመኾኑ በእግሩ በርከክ ብሎ ስቅስቅ እያለ አለቀሰ። ይህን ጊዜ የናፈቀው አምላክ አዘነለትና ድካም ቢጤ እንዲሰማው አድርጎ እንቅልፍ እንዲጥለው አደረገ። ከዚያም በሕልም ታየውና ምን ኾኖ እንደሚያለቅስ ጠየቀው።

እርሱም ሰው ሀገር በመኾኑና መቅደስ በመከልከሉ እንደኾነ መለሰለት። ያን ጊዜ በሕልም የታየው አምላኩ፦ "ባለመግባትህ አታልቅስ። እንኳን አንተ እኔም አልገባሁም።" ብሎ መለሰለት።

መቅደስን መቅደስ የሚያሰኘውን ታላቁን መቅደስ አውጥቶ ጥሎ፤ በመቅደስ የሚጠሩት አምላክ አይገኝም።

በመጋቤ ሃይማኖት ተስፋዬ ሞሲሳ
Audio
የኃጢአተኞች መንገድ ትጠፋለች

Size:-23.3MB
Length:-1:06:59

   በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#ለሲኖዶሳዊ_ልዕልና_መከበር_የምእመናን_ድርሻ_አስፈላጊ_ነው!

ክፍል ፩

ሐምሌ ፲፩፤ ፳፻፲፭ ዓመተ ምሕረት

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ቤተ ክርስቲያን የመልካም አስተዳደር ችግሮች እና የቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና አለመከበር እንዲሁም በርካታ ምእመናን በቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ ጉዳዮች ባይታዋር የሆኑበት፣ ቤተ ክርስቲያኗን ለካህናቱና ጳጳሳቱ ብቻ እየተው የመጡበት ሁኔታ ይታያል፡፡

ቅድስት ቤተ ክርስትያንን ፖለቲከኞች፣ አማሳኞች፣ ምንደኞች አገልጋዮች እንዲሁም የውስጥም ሆነ የውጭ ጠላቶቿ አጀንዳ ሲያደርጓት፣ ባልዋለችበት ሲያውሏት፣ የማይገልጻትን ጥላሸት ሲቀቧት፣ ታሪኳን ሲሰርዙ፣ ሲደልዙ፣ የፕሮፖጋንዳ ሰለባ ሲያደርጓት፣ በባሰ ሁኔታ ኵላዊትነቷን፣ ዓለማቀፋዊነቷን ወደ ጎን በማለት በርካሽ የጎሳ ከረጢት ሊከቷት ሲሞክሩ እያዩ ዝም ማለታቸው ነው፡፡

ስለዚህ ቤተ ክርስቲያኗ ክብሯ ተጠብቆ ሲኖዶሳዊ ልዕልና እንዲከበርና በአገልግሎቷና በአስተዳደርዋ ሁለንተናዊ ለውጥ እንዲመጣ የምእመናን ተሳትፎ ያስፈልጋል፡፡

ይህ ጽሑፍ ስለ ቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና የምእመናንን ግንዛቤ ለማሳደግ ታስቦ የቀረበ ነው፡፡

፩.፩. ቅዱስ ሲኖዶስ ማለት ምን ማለት ነው?
ሲኖዶስ ቃሉ የጽርዕ ቋንቋ ሲሆን ትርጉሙም ስብሰባ (ጉባኤ) ማለት ነው፡፡ አንድ/ቃለ ዓዋዲ፣ ሀብታችንና ሥርዓቱ/ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት/
ቤተ ክርስቲያናችን በሕግና በሥርዓት እንድትመራ ልዩ ልዩ መመሪያዎች ተሰጥተዋታል፡፡ የመመሪያው ባለቤትም ራሱ መሥራቿ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ነው፡፡ ‹‹በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቋት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው እና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ›› በማለት አደራ የሰጣቸው የሐዋርያት ተከታዮች የሆኑ ሊቃነ ጳጳሳትን ነው፡፡ (፪ኛ የሐዋ.ሥራ ፳፥፳፰) የጳጳሳቱ አንድነት ጉባኤ /ስብስብ /ደግሞ ሲኖዶስ ይባላል፡፡

፩.፪. የቅዱስ ሲኖዶስ ታሪካዊ አመጣጥ፡-

በብዙ ታሪኮች ላይ እንደ መጀመሪያ ሲኖዶስ ጉባኤ ተመዝግቦ የሚገኘው በ፶ ዓ.ም በኢየሩሳሌም የተደረገውን ጉባኤ ነው፡፡ ጉባኤውም በሐዋርያት የተደረገ ስብሰባ ሲሆን መሪውም የኢየሩሳሌሙ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ያዕቆብ እንደነበረና የስብሰባው ምክንያትም ከአይሁድ ወደ ክርስትና የመጡት እና ከአሕዛብ በመጡት መካከል በነበረው አለመግባባት ላይ ለመምከር ነበር፡፡ (የሐዋ.ሥራ ፩፥፲፭) ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በርካታ ስብሰባዎች ተደርገዋል፤ በርካታ ሥርዓቶች እና ሕግጋት ለቤተ ክርስቲያን ተደንግገውበታል፡፡ በዚህም ሲኖዶስ እየተባሉ የሚጠሩ እና እስካሁን ቤተ ክርስቲያን የምትመራባቸው ሕጎች ወጥተውበታል፡፡ በኋላም በብዙ ዓለም አቀፍ ጉባኤያት /ኒቅያ፣ ቍስጥንጥንያ፣ ኤፌሶን ወዘተ/ ዳብረውና ጸንተው የተላለፉ ውሳኔዎች አሉ፡፡ ፍትሐ ነገሥት ዋናውና ትልቁ ሲሆን በርካታ የሐዋርያት ሲኖዶስ ውሳኔዎችና ሌሎች ሕጎችን ይዟል፡፡

፩.፫. የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ተግባርና ኃላፊነት ፡-

ቅዱስ ሲኖዶስ ከላይ እንደተገለጸው በዓመት ሁለት ጊዜ እየተሰበሰቡ የቤተ ክርስቲያንን ጉዳይ አጀንዳ አድርገው እንዲወያዩ ሥርዓት ተሠርቷል፡፡ (ፍ/መ. ፭፥፻፷፭) ይህም ሥርዓት እስካሁን ቀጥሏል፡፡ የስብሰባውም ምክንያት
✍️ ሃይማኖትን ለማጽናት፣ ምግባርን ለማቅናት
✍️ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለማስፋት፣ ምእመናንን ለማብዛት
✍️ መናፍቃንን /ከሐድያንን ለመለየት፣ ሕግንና ሥርዓትን ለማውጣት ብሎም ለማስፈጸም
✍️ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሁለንተናዊ አንድነት ለማጽናትና ሁለንተናዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ መብቷን ለማስከበር አስተምህሮዋን ለማስፋት እና ለማስቀጥል የሚደረጉ ስብሰባዎች ሲኖዶስ እየተባሉ ይጠራሉ፡፡

ምክንያቱም ተሰብሳቢዎቹ ‹‹አደራ ጥብቅ ሰማይ ሩቅ›› እንዲሉ አበው አደራቸውን ለመወጣት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን መጠበቅ፣ ለመንጋው መራራትና ለራሳቸው መጠንቀቅ የተሰጣቸው አደራ ነውና፡፡ (የሐዋ. ሥራ ፳፥፳፰) ዋጋቸውንም በሰማይ ይቀበሉ ዘንድ፡፡ አንድም መክሊታቸውን ቀብረው ክፉ አገልጋይ (ማቴ.፳፭፥፳፬) ተብለው እንዳይፈረድባቸው ተግተው በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ይሠራሉ፡፡

፩.፬. የቅዱስ ሲኖዶስ የክብሩ/የልዕልናውና መገለጫ፡-
ቅዱስ ሲኖዶስ ክብሩ ከፍ ያለ ነው፤ ልዕልናውም እጅግ ታላቅ ነው፤ ቅዱስም ነው፤ ቅድስናው፣ ልዕልናው ክብሩ እንዲሁ አይደለም፤ ምክንያቱም

ሀ. መሪው ሰብሳቢው መንፈስ ቅዱስ ስለሆነ ነው፡፡
ሲሰበሰቡና ሲወስኑ መንፈስ ቅዱስን መሪ ሰብሳቢ አጋዥ አድርገው ስለሆነ ነው፡፡ አርዮስን ለማውገዝ ሃይማኖት ለማጽናት በኒቅያ /የቤተ ክርስቲያን ታሪከ፣ ሃይማኖተ አበው/ የተሰበሰቡ ፫፻፲፰ ሊቃውንትም ጌታ አብሯቸው እንደሚሰበሰብ እንደ ነበር የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ያስረዳል፡፡

ለ. የሐዋርያት ወራሴ መንበር ስለሆነ
‹‹እናንተን የተቀበለ እኔን መቀበሉ ነው ያላቸው የሐዋርያት ተከታዮች ናቸው፤ ሊቃነ ጳጳሳት በክርስቲያኖች ላይ ያላቸው ሹመት ሙሴ በእስራኤል ላይ እንደነበረው ምስፍና ያለ ነው›› ተብሎ ተደንግጓል፡፡ (ፍ/መ/፬፣፶፬ እና ፶፭/

ሐ. ለቅድስና የሚያበቃ ሕግና ሥርዓት ስለሚወጣበት ነው፡፡
ሥጋዊ ያይደለ መንፈሳዊ፣ ምድራዊ ያይደለ ሰማያዊ ሥርዓት የሚሠራበትና ሕግ የሚደነገግበት ስለሆነ ነው፡፡

መ. በቅድስናቸው፣ በንጽሕናቸው ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጠባቂነት የተመረጡ ስለሚሰበሰቡበት
ለቅድስና በምታበቃ ክህነት የተሾሙ፣ ሹመታቸው/መመረጣቸው ከሰው ሳይሆን ከእግዚአብሔር የሆነ፣ እኛና መንፈስ ቅዱስ ብለው የሚወስኑ፣ ጥብቅናቸው ለቤተ ክርስቲያን የሆኑ ብፁዓን አበው የሚሰበሰቡበት ስለሆነ ቅዱስ ነው፡፡

ሠ. ሃይማኖት እምነት የሚጸናበት ጉባኤ ስለሆነ
የሃይማኖት አንድነት የሚጸናበት፣ ክሕደት፣ ጥርጥር፣ የሚወገዱበት፣ አጋንንትና ውሉደ አጋንንት የሚገሠፁበት እና የቅዱሳን ቅድስና የሚነገርበት/የሚወሰንበት/ ስለሆነ ነው፡፡ ስለዚህ ቅዱስ ሲኖዶስ ስንል ቅድስናው የሚመነጨው ከሰው ሳይሆን ከራሱ ሁሉን ከሚቀድስ መንፈስ ቅዱስ ስለሆነ ክቡር፣ ቅዱስና ልዑል ነው፡፡

፩.፭. የልዕልናው መገለጫ የውሳኔዎቹ መፈጸም ነው፡፡
ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው ሲኖዶስ ክቡር ነው፤ ቅዱስ ነው፤ መሪውም መንፈስ ቅዱስ ነው፤ የክብሩ መገለጫ የልዕልናው መታያ መሆን ያለበት በመንፈስ ቅዱስ በብፁዓን አባቶች የተወሰነ ውሳኔ ሁሉ ሲከበር እና ሲተገበር ነው፡፡

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ለብዙ ሺህ ዓመታት ጸንታ የቆየችው ወርቃማውን ሥርዓቷን ጠብቃ ለትውልዱ ሁሉ ኩራት የጥበብ፣ የዕውቀት ሥጋዊ ወመንፈሳዊ ቤት፣ የመልካም ሰብእና ማእከል ሆና የዘለቀችው የማይናወጽ ሲኖዶሳዊ ሥርዓት በመጠበቁ በመከበሩ ውሳኔዋ በመፈጸሙ ነው፡፡ በርግጥ አንዳዶች በሊቃውንት ጉባኤ ስትመራ እንደኖረችናየሲኖዶሳዊ ታሪኳ ከ፶ ዓመት ያልዘለዘለ መሆኑን ይሞግታሉ፡፡ (አቡነ ሳሙኤል) ቢሆንም በሐዋርያት ሲኖደስ የምንተዳደር፣ ‹‹ማርቆስ አባታችን እስክንድርያ እናታችን›› ብለን የኖርን ሲኖዶስ አልነበረንም ማለት ተገቢ አይደለም፡፡ ስለሆነም፡-

✍️ የሕግና ሥርዓት ምንጭ፣ የቤተ ክርስቲያን ጠበቃና ዳኛ
✍️ የጾታ ምእመናን ባላደራ፣ የሐዋርያት ወራሴ መንበር የሆነ
✍️ የምሥጢራት ባለቤት፣ የክህነት መገኛ ወዘተ የሆነው
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ቅዱስ ሲኖዶስ ክብሩ ልዕልናው ካልተከበረ ውሳኔው ካልተፈጸመ ህልውናው ጥያቄ ውስጥ ይገባል፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቀርቶ ሀገርና ትውልድ አደጋ ላይ ይወድቃሉ፡፡ ምክንያቱም ሕግ ሁሉ ከሰው ከሆነ ሕገ ሰብእ መሆኑ ይቀርና ሕገ አራዊት ይሆናልና፡፡ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ መገለጫዋ መሪዋ የሕግ ሁሉ ምንጭ ሲኖዶሷ ነውና፡፡

ቸር ይግጠመን!

ይቆየን!
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ አብርሃም በትግራይ ክልል ለሚገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ ሊቃውንትና ምዕመናን ኦርቶዶክሳውያን በሙሉ የሰላምና የአንድነት ጥሪ አቀረቡ።
(EOTC TV//ኢኦተቤ ቴቪ / ሐምሌ ፲፫ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም )
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ችግሮች በተለይም በትግራይ ክልል ባሉ አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳትና ሊቃውንት ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን እና ከሕግ ውጭ በሆነ መልኩ " ኤጲስ ቆጶሳትን " እንሾማለን በማለት እየተደረገ ያለው ዝግጅት አስመልክቶ እንዲቆምና የውይይት መድረኮች ተመቻችተው ችግሮችን በሰላማዊና የቤተ ክርስቲያንን አንድነት በጠበቀ መልኩ ለመፍታት በቦታው ካሉ ሊቃነ ጳጳሳት ጀምሮ ለሊቃውንት ኦቶዶክሳውያንና ለሌሎች እምነት ተከታዮች እንዲሁም ለፌደራልና ለክልሉ መንግሥት የሰላምና የአንድነት ጥሪ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አቅርበዋል።
ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ አብርሃም መገለጫቸው ጉዳዮቹን ለማጥራትና ሁሉም አካል ወደልቡ እንዲመለስ ያለመ መሆኑን በመግለጽ መልእክታቸውን ማስተላለፍ የቀጠሉ ሲሆን በሰሜኑ ኢትዮጵያ በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት በሞቱ የተጎዱና ከቀያቸው በተፈናቀሉ በአጠቃላይ በደረሰው መከራና ሞት እጅግ ማዘናቸው ገልጸዋል። ይሁን እንጂ ጉዳዮች እዚህ ከመድረሳቸው በፊት በሰዓቱ አባቶች ከግል ጀምሮ እስከ ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ድረስ የተደረጉ ሰላማዊ ተግባራት እንደነበሩ አብራርተዋል።

ቤተ ክርስቲያን ጉዳዩን በትኩረት ከማየቷ በተጨማሪ "በችግሩ ወቅት በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጊዜ የሀገር ሰላምን በተመለከተ በያዘው አጀንዳ በተወያያበት ሰዓት ከብፁዓን አባቶች የተወጣጣ የሰላም ኮሚቴ ተዋቅሮ ችግሩ እንዲፈታ የሰላም አየር እንዲነፍስ በሚባልበት ወቅትም በአሁኑ ሰዓት በትግራይ ክልል አህጉረ ስብከት ከሚገኙት ሊቃነ ጳጳሳት መካከል "እኛ ጋር ሰላም ነው ችግር ወዳለበት አካባቢ ሂዱ" የሚል ምላሽ እንደሰጡ ኦርቶዶክሳውያን ሊያውቁ ይገባል ብለዋል።
ከዚህ ይልቅ ችግር በችግር አይወገድምና እንደጥፋትም ከሆነ የጋራ እንጂ ራስን ንጹሕ አድርጎ ሌላውን እንደበደለኛ መቁጠር ተገቢነት እንደሌለው ገልጸዋል።
አያይዘው ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ሊቃውንት በጎጥ በጎሳ በቋንቋና በብሔር በሌላ ምድራዊ ሐሳብ ሳትከፋፈሉ ለሰማያዊ መንግሥት ዓላማ ያለውን መልካም ተግባር በማድረግ አደራችሁን እንዲወጡ በማለት አሳስበዋል።

ቀጥለው ለኦርቶዶክሳውያን በሙሉ ባስተላላፉት መልእክት ትናንት እናት ቤተ ክርስቲያን የገጠማትን ከፍተኛ ችግር በእስከ መሥዋዕትነት በደረሰ ሁለንተናዊ ራስን መስጠት የበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንደተወጣችሁ ሁሉ ዛሬም ቤተ ክርስቲያን አንድነቷን ጠብቃ ለመሄድ በምታደርገው የእውነት መንገድ ከምንም በላይ ክርስቶስ በገዛ ደሙ ፈሳሽነት ለመሠረታት ሐዋርያዊት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ክብር በመሸነፍ ለአንድነቷና ለሰላሟ በጸሎት በሐሳብና በተግባር በተገለጠ ሕይወት እንዲቆሙ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ከዚሁ ጋር በልዩ ልዩ ሃይማኖት ላሉ ኢትዮጵያውያን በሙሉ መልዕክታቸውን የቀጠሉት ብፁዕነታቸው የቤተ ክርስቲያን አንድነት እንድትጠበቅ ከዚህ በፊት ያደረጋችሁትን መልካም አስተዋጽኦ ዛሬም ጥንታዊት እና ባለውለታ ቤተ ክርስቲያን አንድነቷና ሰላሟ ተጠብቆ እንዲቀጥል የበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንድትወጡ እንጠይቃለን በማለት መልእከታቸውን አድርሰዋል።
የኢፌዴሪ መንግሥት ትናንት ተፈጥሮ በነበረው የቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጥሰት ችግር በውይይትና በምክክር በከፍተኛ ኃላፊነት እንዲፈታ ማድረጉን ያስታወሱት ብፁዕነታቸው አሁንም በትግራይ ክልል ባሉ የአህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳትና ሊቃውንት እየተከተሉት ያለውን መፍትሔ የማይሆነውን ችግር በማስቆምና ሰላማዊ የውይይት መድረኮችን በማመቻቸት የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ እምነታችን ነው ብለዋል።
ይህ ካልሆነ ግን ይላሉ ብፁዕነታቸው "በታሪክ የቤተ ክርስቲያንን አንድነትን ማን ከፋፈለ ሲባል የፌደራልና የክልሉ መንግሥት" የሚል የታሪክ ተወቃሽ ሆኖ በታሪክ የሚመዘገብ ይሆናል። ስለሆነም ይህን በትግራይ ክልል ይፈጸማል የሚለውን ከቀኖና ቤተ ክርስቲያንና ሕገወጥ የሆነ ሹመት እንዲቆም ብሎም ችግሮች በውይይት እንዲፈቱ በማመቻቸት ታሪካዊ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ ቤተ ክርስቲያን ታሳስባለች ብለዋል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ለትልቁ ጉልበትና ቅዱስ ትዕዛዝ "ለይቅርታ" ራሱን በማስገዛት መንጋው እንዳይበተን ይፋዊ ይቅርታ ከመጠየቅ አልፎ የቤተ ክርስቲያናችን ቅዱስ ሲኖዶስ ርዕሰ መንበር ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእስ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በመሩት የሰላም ልዑክ ወደ መቐለ አቅንቶ ችግርን በውይይትና በሰላማዊ መንገድ ተወቃቅሶ ለመፍታት ቢሞከርም አለመሳካቱ አስታውሰው ጉዳዩ እጅግ እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል።

በመጨረሻም የባለውለታዋ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አንድነት የሚያሳስበው ሰላሟ የሚናፍቀው ሁሉም አካል ከትልቁ ጉልበት ጸሎት ጀምሮ የሚቻለውን አበርክቶት እንዲወጣ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ አብርሃም አሳስበዋል።
EOTC TV
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
2024/09/23 20:16:01
Back to Top
HTML Embed Code: