Telegram Web Link
Audio
መሠረተ እምነት  በአንዲት ሀይማኖት

ሰባቱ ምስጢራት ለምን ሰባት ሆኑ
ምን ምን ናቸው በሰባት የተወሰኑት

አዘጋጅና አሳታሚ :-ኢንጂነር ወንዴ ጫኔ
Audio
መሠረተ እምነት  በአንዲት ሀይማኖት

ምስጢር ጥምቀት ምንድነው አዲስ ኪዳን ብሎይ ኪዳን

አዘጋጅና አሳታሚ :-ኢንጂነር ወንዴ ጫኔ
Audio
👏👏👏👏👏👏🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻ልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልል
Audio
መሠረተ እምነት  በአንዲት ሀይማኖት

ጌታችን መቼ የት ተጠመቀ

ጥምቀት ለምን አሰፈለገ

ጥምቀት ለምን በወኃ እንጠመቃሐለ

አዘጋጅና አሳታሚ :-ኢንጂነር ወንዴ ጫኔ
Audio
መሠረተ እምነት  በአንዲት ሀይማኖት

ምስጢረ ቁርባን ምንድነው

በብሉይ ኪዳን የምሥጢሰ ቁርባን ምሳሌዎች

የፋሲካው በግ

አዘጋጅና አሳታሚ :-ኢንጂነር ወንዴ ጫኔ
ቅዳሴ

“የመላዕክትን እንጀራ ሰው በላ”


+ የመላዕክት እንጀራ፦ ክቡር ዳዊት በገናውን እየደረደረ
እንዲህ አለ፦
“የመላዕክትን እንጀራ ሰው በላ” የመላዕክት እንጀራ ምን
ይሆን? መላዕክት ምግቡ የላቸውም ፤ ምግባቸው
ምስጋና ምስጋናቸውም ምግብ ነው; ረፍታቸው ምስጋና
ምስጋናቸውም ረፍታቸው ነው። የሚያርፉበት የሰከንድ
ሽራፊ የላቸውም 24 ሰዓትም ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ
እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ።
እኛም በቅዳሴው እንደ መላዕክቱ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ
እያልን እግዚአብሔርን ስለምናመሰግን
//"የመላዕክትን ምግብ ስለተመገብን" //
ልበ አምላክ ዳዊት በገናውን እየደረደረ “የመላዕክትን
እንጀራ ሰው በላ” ብሎ ዘመረ!!!መዝ77 (78):25
+ በየሳምንቱ የምናየው ግሩም የሆነ የቅዳሴ ሥርዓት
እነሆ ለበረከት፦
“ቅዳሴ ዘመላዕክት”
ቅዳሴን ማን ጀመረው? የቅዳሴን ሥርዓት ለመጀመሪያ
ግዜ የጀመሩት የሰማይ መላዕክት ናቸው ፤ በትንቢተ
ኢሳያስ ምዕራፍ 6 ላይ መላዕክቱ “ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ”
እያሉ እግዚአብሔርን እንዳመሰገኑት። ይህን ዜማ
በቅዳሴ ላይ እንደምናስታውሰው የታመነ ነው። ሥርዓተ
ሰማይ በምድር ተሰርቶ በሰማይ ባለችው ቤተመቅደስ
ያለው ሥርዓት በምድር ባለችው ቤተመቅደስም እንዲሆን
እግዚአብሔር ፈቅዶ የሠራዊት ጌታ ልዑል
እግዚአብሔርን እናመሰግናለን።
በምድርም ለመጀመሪያ ግዜ የቅዳሴን ዜማ ያዜሙት
መላዕክት ናቸው፦ ጌታችን በኤፍራታ በቤተልሔም
በተወለደ ግዜ መላዕክቱ ከእረኞቹ ጋር ሆነው “ሥብሐት
ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ስምረቱ
ለሰብ” ብለው እንደዘመሩት። እኛም በቅዳሴው ላይ
የምናመሰግነው ይህንን የመላዕክቱን ምስጋና ነው ፤
መላዕክቱ በቤተልሔም የዘመሩትን እኛም በቤተመቅደሱ
ዘመርን!!!
ከቤተልሔም ወደ ቤተመቅደስ፦ በሃገራችን ንፍቁ ዲያቆን
ሕብስቱን ተሸክሞ ዋናው ዲያቆን ደግሞ ወይኑን በፅዋ
ይዞ ከቤተልሔም ወደ ቤተመቅደስ ይሄዳሉ። ቤተልሔም
ያለችው በምሥራቅ ነው ፤ ቤተመቅደስ ደግሞ የቀራንዮ
ምሳሌ ናት; አንድም ጌታ ከገሊላ ወደ ኢየሩሳሌም
የመሄዱ ምሳሌ ነው።
መንፈስ ቅዱስ ከሰማየ ሰማያት የሚወርድባት ናት፦
ቅዳሴ ሲጀመር ካህኑ “ይህች ቀን ምን ያህል የምታስፈራ
ናት መንፈስ ቅዱስ ከሰማየ ሰማያት የሚወርድባት ናት”
ይላል። ንጉስ እንኳን ሲመጣ ምን ያህል ዝግጅት
ይደረጋል? እኛም ታላቅ ዝግጅት እንድናደርግ ካህኑ ይህን
ያውጃል።
+ በቅዳሴ የምንገለገልባቸው ንዋያተ ቅድሳት ፤
• ማሕፈዳት፦ ማሕፈዳት ማለት ሥጋ ወደሙ
የሚሸፈንበት ነው ፤ አንድም እመቤታችን ጌታን ወልዳ
በጨርቅ የመጠቅለልዋ ምሳሌ ነው፤ አንድም ዮሴፍና
ኒቆዲሞስ ጌታን የገነዙበት የመግነዙ ምሳሌ ነው።
• ጻሕል፦ የሕብስቱ ማስቀመጫ ሲሆን አንድም በማህፀነ
ድንግል ማርያም ይመሰላል፤ አንድም ጌታችን
የተወለደበት የግርግም ምሳሌ ነው፤ አንድም የመቃብሩ
ምሳሌ ነው። ወይኑን ደግሞ ዲያቆኑ በጽዋዕ ይይዘዋል።
//ጽዋዕ ፤ ዕርፈ መስቀል//
• ዕርፈ መስቀል፦ ዲያቆኑ የጌታችንን ክቡር ደም
ለምእመናን የሚያቀብልበት እንደ ማንኪያ የመሰለ
ቢሆንም የሚጠራው ግን እርፈ መስቀል ተብሎ ነው፤
ይህም የራሱ ምክንያት አለው; እርፈ መስቀል ክርስቶስ
ስለእኛ ጎኑን በተወጋበት ጦር ይመሰላል ፤ ለንጊኖስ
የተባለው ወታደር የጌታችንን ጎን በጦር በሚወጋበት ግዜ
በቅዱስ ደሙ በመቀደሱ ከንዋየ ቅድሳት አንዱ ነው።
+++ “ለምፄን ተመልክተህ አምላኬ አትጣለኝ” ትንቢተ
ኢሳያስ ምዕራፍ 6 ላይ ኢሳያስ ለምፅ ነበረበት; መልአኩ
መቶ በጉጠት ከእሳቱ ፍም ከንፈሮቹን ዳሰሰው; ኢሳያስም
ከለምፁ ነፃ፤ መልአኩ የካህናት የዲያቆናት ምሳሌ ነው;
ጉጠቱ የእርፈ መስቀል ምሳሌ ነው; የእሣቱ ፍም የሥጋ
ወደሙ ምሳሌ ሲሆን ለምፅ ደግሞ የሃጢአት ምሳሌ
ነው። እንዴት ነው የእሣት ፍም ከንፈርን ሲዳስስ
የሚፈውሰው ቢሉ ለምፅ የሃጢአት ምሳሌ ነው ብለናል;
የእሣቱ ፍም ደግሞ የሥጋ ወደሙ ምሳሌ ነው ብለናል ፤
ኢሳያስ ከለምፁ እንደነፃ ሁሉ ሥጋ ወደሙም እንደዚሁ
ያነፃል ሲለን ነው።
[1ኛ ዩሐንስ 1:7]
+++ ጥላ፦ በቅዳሴ ላይ ወንጌል ሲነበብ ጥላ ይዘረጋል
፤ ፀሐይ የለም ዝናብ የለም ለምንድን ነው ቢሉ ምሳሌው
እንዲህ ነው፦ ክቡር ዳዊት “አቤቱ በክንፎችህ ጥላ
ከልለኝ” ያለው ምሳሌ ነው ፤ አንድም እስራኤልዊያን
የበረሐው ፀሐይ እንዳያደክማቸው የደመናው ምሳሌ ነው
፤ አንድም በመገናኛ ድንኳኑና ሰለሞን ባሰራው
ቤተመቅደስ የሞላው የደመና ምሳሌ ነው።
+++ ጧፍ ፦ ካህኑ ወንጌል ሲያነብ ጧፍ ይይዛል;
አልጨለመ ብርሐን አለ ለምንድን ነው ቢሉ ክቡር ዳዊት
“ሕግህ ለእግሬ መብራት ለመንገዴም ብርሐን ነው”
ስለሚል ነው። (መዝ 118:105) ወንጌሉ ነውና
የሚነበበው ወንጌሉም ለእግራችን መብራት
ለመንገዳችንም ብርሃን ስለሆነ ነው። በቤተክርስቲያን
ውስጥ በብዛት ሻማ አለ; ይህም እግዚአብሔር
በባሕርይው ብርሐን ስለሆነ ነው ፤ ሻማው እየቀለጠ
ብርሃን ይሰጣል ይህም ቅዱሳኑ ስለቤተክርስቲያን
እንደሻማ እየቀለጡ ለዓለም ብርሐን የመሆናቸው ምሳሌ
ነው።
+++ የዲያቆናት ምሳሌነታቸው፦ ከካህኑ ፊት መብራት
የያዘው ዲያቆን የመጥምቁ ዩሐንስ ምሳሌ ነው፤ “ብርሃኑ
እሱ እንጂ እኔ አይደለሁም የዓለምን ሃጢዓት
የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ እንዳለ” መስቀል
ተሸክሞ ከካህኑ በሗላ የሚከተለው ዲያቆን ደግሞ
የቀዳሜ ሰማዕት የዲያቆን እስጢፋኖስ ምሳሌ ነው፤
ከጌታ ቀጥሎ “አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና
ይቅር በላቸው እንዳለ”
ቤተክርስቲያን ከጣራዋ እስከ መሬቷ ሁሉም ሥርዓቷ
ያስተምራል ፤ ባህረ ጥበብ ቤተክርስቲያን እየተናገረች
ታስተምራለች ሳትናገር ዝም ብላም ታስተምራለችና!!!
ላዕካነ ሚስጢር ዲያቆናት
+++ ተንሥኡ ለፀሎት፦ በቅዳሴ ግዜ ለምን በየግዜው
ተንሥኡ ይባላል ቢሉ; ማነው ሃሳቡ ሳይሰረቅ
እስከመጨረሻው የሚያስቀድሰው? ስለዚህም በሃሳባችን
ሄድ ካልን መለስ እንድንል ነው; አንድም ግሩም ምሳሌ
ስላለው ነው፦
አዳም ለፍጥረቱ ተንሥኡ ለፀሎት አላቸው ፍጥረቱም
እግዚኦ ተሣሃለነ አሉ
ጌታም በሲኦል ያሉትን ነፍሳት ሠላም ለኩልክሙ አላቸው
እነሱም ምስለ መንፈስከ ብለው
ከሲኦል ጨለማ ብርሃንን አዩ።
ካህኑ እኮ ሰላም ለኩልክሙ ሲል ጌታችን በተዘጋ ደጅ
ለሐዋርያቱ ሰላም ለናንተ ይሁን ያላቸውን ነው ፤ እኛም
ቅዳሴውን ስንመልስ ይህን እያሰብን መሆን ይኖርበታል።
+++ ስገዱ ለእግዚአብሔር ፦ ዲያቆኑ ስገዱ
ለእግዚአብሔር በፍርሐት ሲል እንሰግዳለን ይህም ክቡር
ዳዊት “በቅድስናው ስፍራ ለእግዚአብሔር ስገዱ”
እንዳለው ነው; መዝ28:2 አንድም ጠቢቡ ሰለሞን
ቤተመቅደሱን ሰርቶ ከፈጸመ በሗላ ለረጅም ሰዓት
ተንበርክኮ መጸለዩን ያስታውሰናል። 1ኛ ነገስት 6:54
+++ ኦ ምልዕተ ፀጋ፦ በቅዳሴ ላይ ለእያንዳንዱ ፍጥረት
የተወሰነ ጸጋ እንደተሰጠው በዜማ እንለዋለን፦ ለሚካኤል
ምህረት ተሰጠው ለገብርኤልም ማብሰር; ለሙሴ ህግ
ለአሮንም ክህነት … ለእመቤታችን ግን ፀጋ
አልተከፈለባትም “ተፈሥሂ ፍሥህት ኦ ምልዕተ ፀጋ”
ብለን በቅዳሴው የምናመሰግናትም ምልዕተ ፀጋ
ስለሆነች ነው።
እሣታዊያን የሆኑ መላዕክት የእሳቱን ፍም የሚነኩት
በጉጠት ነበር እመቤታችን ግን እሳቱን ወልዳ እሳቱን
ታቀፈችው!!! ፤ ስለዚህም ኦ ምልዕተ ፀጋ እያልን
እንዘምራለን እናመሰግናታለንም። የእመቤታችን ፍቅርማ
መቼ በቀላሉ… በንግግር ይፈጸምና?!!!
+++ ምስባክ፦ ምስባክ የብሉይ ኪዳን የተስፋው ምሳሌ
ነው ፤ ነቡያቱ የተነበዩት; አምላክ ሰው የሆነበት; ትንቢቱ
ሁሉ የመፈጸሙ ምሳሌ ነው። ምስባኩን የሚያነበው
ዲያቆን ደግሞ የነብያቱ ምሳሌ ነው ማለት ነው።
ምስባኩ ሁል ግዜ ከዳዊት መዝሙር የሚሆንበት
ምክንያት ነብያቱ የተሰጣቸው ጸጋ የተወሰነ ነበር፤ ክቡር
ዳዊት ግን የክርስቶስን ከልደቱ እስከ ዕርገቱ ያለው ጸጋ
ስለተሰጠውና ለዜማ ስለሚያመች ነው።
+++ ወንጌል፦ የመጀመሪያው መልዕክት ሲነበብ ዲያቆኑ
ፊቱን ወደ ምዕራብ አዙሮ ያነባል; ሁለተኛው ዲያቆን
ፊቱን ወደ ሰሜን አዙሮ ያነባል; ንፍቅ ካህን ወደ ደቡብ
ዙሮ የሐዋርያት ሥራን ሲያነብ ዋናው ካህን ደግሞ ወደ
ምሥራቅ ዙሮ ወንጌልን ያነባል ፤ ይህም ግሩም የሆነ
ምሳሌ አለው፦ አንድም ወንጌል በአራቱም አቅጣጫ
መሰበኩን ለመግለጽ ነው; አንድም ገነትን የሚያጠጡ 4
ወንዞች አሉ; ኤፍራጠስ ጤግሮስ ጊዮን [ዓባይ] እና ፊሶን
ናቸው።
ገነትን አጠጥተው ለምለም እንደሚያደርጓት ጌታችን
የተጠማ ቢኖር የህይወትን ውሃ በነፃ ይጠጣና ይርካ
እንዳለው ወንጌሉም እንዲሁ ያለመልማል ሲሉ ነው።
! “ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ በቅዳሴ” !
ገባሬ ሠናዩ ካህን ወይም ዋናው ካህን ዘአወፈየኒ
አወፈይኩከ /የሰጠኸኝን ሰጠሁህ/ ብሎ ወንጌሉን
ለንፍቅ ካህን ወይም ለሁለተኛው ካህን ይሰጠዋል ፤
ሁለተኛው ካህንም ለዲያቆኑ ይሰጠዋል; ይህ ነው
ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ Apostolic Succession
የሚባለው; ዋናው ካህን የጌታ ምሳሌ ሲሆን ሁለተኛው
ካህን ደግሞ የቅ/ጴጥሮስ ምሳሌ ነው፤ ዲያቆኑም
የምዕመናን ሁሉ ምሳሌ ነው ማለት ነው!!
ወርቅ የሆኑት አባቶቻችን ምስጢርን ከተግባር ጋር
አወረሱን
“ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ”
+++ ወንጌል መሳለም፦ ወንጌሉን ሁላችንም
የምንሳለምበት ምክንያት የመለኮት ቃል ነው እንከን
የለውም እናምናለን ስንል ነው; አንድም ኦሪት 622 ህግ
አላት; ሁሉም ህግ በፍቅር ይታሰራልና እኛም
የተሰባሰብነው በወንጌሉ መሰረት በፍቅር ነው አንድ ነን
ስንል ነው።
+++ የካህናቱ ሥብሐት ምሳሌ፦ ካህናቱ ሥብሐት ለአብ
ሥብሐት ለወልድ ሥብሐት ለመንፈስ ቅዱስ እያሉ
ይዞራሉ፤ ይህም እስራኤላዊያን የኢያሪኮን ግንብ 7 ቀን
ዞረው በሰባተኛው ቀን 7 ግዜ ሲዞሩ የኢያሪኮ ግንብ
የመፍረሱ ምሳሌ ነው። ካህኑ ዕጣን እያጠነ ህዝቡን
ይዞራል ይህም እስራኤላዊያንን ከጠላታቸው
እንደጠበካቸው ሕዝቡንም ከጠላት ዲያቢሎስ ጠብቅ
ሲል ነው። ካህኑ ዕጣን በሚያጥንበት ግዜ የምንጸልየው
ጸሎት ከዕጣኑ ጋር ወደ እግዚአብሔር ያርጋል፦
“የዕጣኑ ጢስም ከቅዱሳኑ ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ ወደ
እግዚአብሔር ፊት ዐረገ” ራዕ 8:4
+++ ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ፦ ዲያቆኑ ወደ ምሥራቅ
ተመልከቱ ይላል ፤ ሕዝቅኤል በትንቢቱ እንዲህ አንዳለ፦
“በምሥራቅ የተዘጋ ጀጅ አየሁ; ይህች በር ተዘግታ
ትኖራለች እንጂ አትከፈትም፤ ሰውም አይገባባትም ፤
የእስራኤል ቅዱስ ሳይከፍት ገብቶ ሳይከፍት ወቶባታልና”
ሕዝቅኤል 44:1
ምሥራቅ እመቤታችን ናት ፤ መናፍቃኑ ግን ይህማ
ስለቤተመቅደስ የተነገረ ነው ይላሉ; ተዘግቶ የሚኖር
ቤተመቅደስ አለ እንዴ? ሰውም የማይገባበት ቤተመቅደስ
የለም፤ ይህማ ስለእመቤታችን የተተነበየ ነው።
ከምሥራቅ ፀሐይ እንደሚወጣ ከምስራቋ እመቤታችን
ፀሐይ ጌታ ተወልዷልና አንድም ይህች በር ተዘግታ
ትኖራለች እንጂ አትከፈትም አለ; ድንግል በክልኤት ናትና;
በሥጋም በነፍስም ድንግል ናትና ፤ ቅድመ ፀኒስ ወሊድ
ድንግል ፤ ግዜ ፀኒስ ወሊድ ድንግል ፤ ድህረ ፀኒስ
ወሊድ ድንግል ናትና; ወትረ ግዜ ድንግል ናትና ሲል
ነው። አንድም ሰውም አይገባባትም አለ አንድያ ልጇን
ብቻ ወልዳለችና። የእመቤታችን ክብርማ መቼ ተነገረና?
የእመቤታችን ፍቅርማ መቼ ተነግሮ ይፈጸምና? ስለፍቅሯ
ለመዘመር ለመቃኘት…ሞከሩ ግን መቼ የእናቴ ፍቅር
በቀላሉ ይነገርና? መቼ እንዲህ በቀላሉ?
+++አንሥኡ እደዊክሙ ቀሳውስ ፦ ዲያቆኑ ይህን
በሚልበት ግዜ ንፍቁ ካህን ማሕፈዱን ከጻሕሉ ላይ
ያነሳል ፤ ይህም የጌታ መልአክ የመቃብሩን ድንጋይ
የማንከባለሉ ምሳሌ ነው። ከዚህ በሗላ ጌታችን በምሴተ
ሐሙስ ሕብስቱን እንደያዘው ዋናው ካህንም ሕብስቱን
ከፍ አድርጎ ይይዘዋል ፤ ይህም የጌታ ትንሣኤ ምሳሌ
ነው።
+++እግዚኦ መሐርነ ክርስቶስ፦ በእግዚኦታ ላይ ካህኑ
ሕብሥቱን ይበልጥ ከፍ አድርጎ ይይዘዋል ይህም
የዕርገቱ ምሳሌ ነው። ከካህኑ ጋር ሆነን 41 ግዜ እግዚኦ
መሐርነ ክርስቶስ እንላለን ፤ ይህም አርባው እግዚኦታ
አይሁድ ጌታችንን 40 ግዜ እንገርፋለን ብለው እያዛቡ
ብዙ ግዜ የመግረፋቸው ምሳሌ ሲሆን በመጨረሻ ካህኑ
ብቻውን የሚላት እግዚኦታ ደግሞ የአዳምና የሔዋን
የንስሃ ምሳሌ ነው። 12 ግዜ እግዚኦ መሐርነ ክርስቶስ
ስንል ደግሞ ስለስምህ ብለህ ይቅር በለን ስንል ነው።
“አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ” የሚለውን እያንዳንዱን
ፊደል ስንቆጥር 12 ይሆናልና!!!
+++በእግዚኦት ላይ የሚሰማው ቃጭል፦ በእግዚኦት
ላይ የሚሰማው ቃጭል የእመቤታችን የቅድስት ድንግል
ማርያም በቀራንዮ ልጇን ፊት ለፊት በመስቀል ላይ
እያየችው ያዘነችው ሃዘን ያለቀሰችው ልቅሶ ምሳሌ ነው።
አረጋዊው ስምኦን
ወላኪሰ ይበውእ ውስጠ ልብኪ /በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል
እንዳላት/ ሉቃስ 2:35
ይህ ሃዘን ከባድ ነውና ፤ መላእክት ባያጽናኗት ኖሮ ሃዘኑ
ለሞት ባበቃት ነበር ይላል!!! ታላቅ ሃዘን ነበርና; በነፍስሽ
ሰይፍ ያልፋል የተባለውም ይህ ከባድ ሃዘን ነው።
+++ በካህኑ እጅ መሳለም፦ አንዳንድ ሰዎች ካህኑ
ለምን በእጁ ያሳልመናል ይላሉ። የካህኑ እጅ እኮ
እሳታዊያን የሆኑ መላዕክት መንካት የማይቻላቸውን ቅዱስ
ሥጋውን ክቡር ደሙን የዳሰሰበት ነው። በቅዳሴ ላይ
ቅዱስ ሥጋውን መንካት የሚችለው ዋናው ካህን ብቻ
ነው ፤ ሁለተኛው ካህን እንኳን መንካት አይችልም።
ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን የዳሰሰበት ስለሆነም ካህኑ
በእጁ ያሳልመናል።
መንጠላኦት/ መጋረጃ/፦
መጋረጃው ከተጋረደ በሗላ በውጪ ያሉት ንፍቅ ካህንና
ዲያቆን የነብያቱ ምሳሌ ሲሆኑ ከውጭ የሚሆንበት
ምክንያት በነብያቱ ዘመን የጥል ግድግዳ የነበረበት ዘመን
በመሆኑ ነው። በውስጥ ያሉት ዋናው ካህንና ዲያቆን
ደግሞ የሐዋርያት ምሳሌ ናቸው ይህም የጥል ግድግዳ
ፈርሶ ጌታችን ከሐዋርያቱ ጋር በቅርብ በመሆኑ ነው።
በመቀጠል ዲያቆኑ ቀሳውስ ደጆቹን ክፈቱ ይላል ፤
ይህም ለአናጉንስጢሱ ነው። አናጉንስጢስ ማለት
ድምጻቸውን ከፍ አድርገው መጻሃፍትን የሚያነቡና
መብራት በመያዝ የሚያገለግሉ ረድዕ ናቸው።
አናጉንስጢሱ መጋረጃውን ይከፍታል ከዛም በነብያቱ
የተመሰሉት ካህናት በሐዋርያት ከተመሰሉት ካህናት ጋር
ይገናኛሉ። ነብያትና ካህናቱ አንድ የሆኑባት ማን ናት?
ሙሴ ኤልያስና ቅ/ጴጥሮስ የተገናኙባት የታቦር ተራራ
ናት ፤ ቤተክርስቲያንም በታቦር ተራራ ስለምትመሰል ይህ
ውብ ሥርዓት በቤተክርስቲያናችን አለ!!!
ወርቅ የሆኑት አባቶቻችን ምስጢርን ከተግባር ጋር
አወረሱን
“ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ”
+ የአምላካችን ቅዱስ ሥጋው ወክቡር ደሙ፦
ቅዱስ ሥጋው ወክቡር ደሙን በምሴተ ሐሙስ በማርቆስ
እናት በማርያም ባውፍልያ ቤት በላይኛው ፎቅ ጌታ
ለሐዋርያቱ እንዲህ ብሎ ሰጣቸው፦
“ይህ ሥጋዬ ነው እንኩ ብሉ፤ ይህ ደሜ ነው እንኩ
ጠጡ። ሉቃስ 22:19
ሥጋዬን ይመስላል መታሰቢያ ነው አላለም ፤ ጌታ
ለሐዋርያቱ ምን አላቸው? ሶበ ትገብርዎ ለዝንቱ ተዝካር
ዚያዬ ግበሩ /ይህንን በምታደርጉበት ግዜ መታሰቢያዬን
አድርጉ አላቸው። ጌታችን መታሰቢያዬን አድርጉ ሲለን
ምን ማለት ይሆን?
ሥጋ ወደሙን በምትቀበሉበት ግዜ መካራዬን እያሰባቹ;
የቀራንዮ የጎሎጎታ ፍቅሬን እያሰባቹ ተቀበሉ ሲለን ነው
እንጂ እንደ መናፍቃኑ ሃሳብ አይደለም። ቅ/ጳውሎስ
መናፍቃኑን እንዲህ ይላቸዋል “ሳይገባው ሥጋ ወደሙን
የተቀበለ በምህረት ፈንታ ፍርድ ይሆንበታል” 1ኛቆሮ.
11:29 ፤ የቆሮንቶስ ሰዎች በድፍረት እንደመናፍቃን
ስለቀረቡ ብዙዎች ሞቱ፤ ሰው ምግብ በልቶ አይሞትም
ይህ ግን ሥጋ ወደሙ ስለሆነና በድፍረት ስለቀረቡ
ሞቱ!!! 1ኛቆሮ. 11:29-32 እኛስ እንደቸርነትህ ነው
እንጂ እንደበደላችን አይሁን እያልን እንድንቀርብ
የእግዚአብሔር ፈቃዱ ይሁን፤ አሜን። ታላቁ ሐዋርያ ቅ/
ጳውሎስ መታሰቢያ ነው ለሚሉት መናፍቃን በድፍረት
አትቅረቡ ይላቸዋል። ካህኑ እጁን እየታጠበ “ሳይገባው
ሥጋ ወደሙን የተቀበለ በምህረት ፈንታ ፍርድ
ይሆንበታል; ንስሃ ገብታቹ ቅረቡ” የሚለውም ይህን
የታላቁን ሐዋርያ መልዕክት ነው። 1ኛቆሮ. 11:29
// አዕይነተ እግዚአብሔር ካህናት የቅ/ጳውሎስ
መልዕክትን እየተናገሩ //
ቅ/ጳውሎስ ደገመና እንዲህ አለ፦ “ይህን ህብስት
በምትበሉበት ይህንንም ጽዋ በምትጠጡበት ግዜ ሁሉ
ጌታችን እስከሚመጣባት ቀን ድረስ ሞቱን
ትናገራላቹ”1ኛቆሮ. 11:26 እኛም ከሐዋርያው ተቀብለን
ጌታም የቀራንዮ ፍቅሬንና መከራዬን አስቡ ያለንን
እያሰብን በቅዳሴው ላይ እንዲህ አልን፦
ንዜኑ ሞተከ እግዚኦ… / ክቡር ሞትህን እንናገራለን
እናስባለንም እንላለን/
ቅዳሴውና ወንጌሉ እርስ በእስርሳቸው በግሩም ሁኔታ
ይናበባሉና።
“ሥጋ ወደሙ”
የዓለምን ሁሉ ሃጢዓት ያስተሰርያል ዩሐንስ ወንጌል 1:29
1ኛ ዩሐ 2:2 ማቴ 26:26
ሥጋዬን የበላ ደሜንም የጠጣ የዘለዓለም ህይወት አለው
ዩሐንስ 6:54
ሥጋዬን የበላ ደሜንም የጠጣ እኔ በሱ እኖራለሁ ዩሐንስ
6:56
ከቅዱሳን ህብረት ያስቆጥረናል
ከሃጢአት ያነጻናል 1ኛቆሮ 10:16 1ኛ ዩሐ 1:7
// ሁሉን ቻይ ጌታ አምላክ ሆይ ሥራህ ታላቅና ግሩም
ነው!!!//
[ራዕ 15:3]
ለተጠየቀው ጥያቄ ከነ ማብራሪያ መልስ ነው ንፍቅ ካህን የሚለው ጥያቄ ⤴️
Audio
መሠረተ እምነት  በአንዲት ሀይማኖት

መና ዘጸአት 16÷33

የቅዱስ ቁርባን ጥቅሞች

በቅዱስ ቁርባን የሚታይ ጸጋ

አዘጋጅና አሳታሚ :-ኢንጂነር ወንዴ ጫኔ
Audio
መሠረተ እምነት  በአንዲት ሀይማኖት

ለመቁረብ ቅድመ ዝግጁቶች

ሜሮን የምንድነው

ቅብዓ ሜሮን አገልግሎት ?

አዘጋጅና አሳታሚ :-ኢንጂነር ወንዴ ጫኔ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ክርስቲናያን መንፈሳዊ ትምህርቶች እና ጽሁፎች ቻናል⛪️
Photo
🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔
ጥንቃቄ ለመላው ኦርቶዶክሳዊ❗️
#ሁሉም ኦርቶዶክስ_ሼር ሼር ሼር_ያድርግ!!!

🔔 የቀበሌ መታወቂያ ጉዳይ ❗️

💥 ታግዶ የቆየው የመታወቂያ እድሳት ከዚህ ከህዳር ወር ጀምሮ መሰጠት የተጀመረ መሆኑን ተከትሎ መታወቂያ ለማሳደስ የሚሄዱ የከተማዋ ነዋሪዎች ከታች የምትመለከቱትን ፎርም አስቀድመው እንዲሞሉ በመደረግ ላይ ይገኛል።

💥 በሚሞላው ፎርም ላይ ከተካተቱት መጠይቆች አንደኛው " ሃይማኖት " የሚለው ነው። አብዛኛው ኦርቶዶክሳዊ ባለማስተዋልና ትኩረት ባለመስጠት በዚህ መጠይቅ ሥር "ክርስቲያን" የሚለውን መጠሪያ መጠቀም ልምድ አድርጎት ይታያል።

💥 ሆኖም በዚህ ወቅት እንደ ወል ስም እያገለገለ በሚገኘው ስም መጠቀም ከኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ቁጥር ጋር ተያይዞ በቀጣይ ትልቅ ፈተና ይዞ የሚመጣ መሆኑን በማስተዋል ሃይማኖት በሚለው መጠይቅ ሥር " #ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ " የሚለውን የሃይማኖታችንን መጠሪያ ለይቶ በአግባቡ መሙላት ይገባዋል።

💥 በክርስትና ስም የሚጠቀሙ ሌሎች የሃይማኖት ድርጅቶች በመኖራቸውና ይህም የኦርቶዶክሳውያን ቁጥር የተዛባና የተሳሳተ እንዲሆን ያደርጋል።

💥 በአሁኑ ወቅት እየተስተዋለ እንዳለው ኦርቶዶክሳውያን ከሀገሪቱ ፖለቲካዊ ፤ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች እየተገፉና እየተገለሉ እንዲሄዱ በማድረግ ቁጥራቸውን በማዛባትና ዝቅ አድርጎ በማሳየት ፍላጎታቸውን ለማሳካት ለሚፈልጉ አካላት ምቹ ሁኔታ መፍጠር አይገባም።

💥 በተለይም በዕድሜ የገፉና የቀለም ትምህርት ያልቆጠሩ ወገኖቻችንን በማሳወቅ " #ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ" የሚለውን የሃይማኖታችንን መጠሪያ በአግባቡ እንዲሞሉ ማድረግ ከእያንዳንዱ ኦርቶዶክሳዊ የሚጠበቅ ተግባር ነው።
Audio
በደብር ሰላም ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን በአርብ ሃገር በኪዌት

ቆሞስ አባ በርናባስ በእውነት ቃለ ህይወት ያሰማልን
Audio
መሠረተ እምነት  በአንዲት ሀይማኖት

ቅብዓ ሜሮን በሐዲስ ከዳን

ሜሮን አገልግሎት

ቅብዓ ሜሮን አፈፃፀም እንዴት ነው

አዘጋጅና አሳታሚ :-ኢንጂነር ወንዴ ጫኔ
Audio
Easy Voice Recorder
*ከክፍ ነገር ኹሉ የአዳነኝ መልአክ እርሱ እነዚኽን ብላቴኖች ይባርክ*
*(ኦሪት ዘፍጥረት ፵፰÷፲፯)*
በመጋቤ ሐዲስ ቀሲስ አበበ
ለመምህራችን ቃለ ሕይወት ያሰማልን
*ማኅበረ ተዋሕዶ ዘኦርቶዶክስ*
ደቂቃዉ *//46፥51//*
*Ke Kfu Neger Hulu Yeadanegne Melak Ersu Enezihn Blatanoch Yibark*
*(Orite Ze Ftret 48÷16)*
Be Megabe Hadis Kesis Abebe
Lemehrachn Kale Hiywet Yasemaln
*MAHBERE TEWAHDO ZE ORTHODOX*
👆👂👂👈
https://youtube.com/channel/UCSzRc-X36uAdN5vIJ6MPwlQ
*የዩቲዩብ ቻናል👆*
2024/09/30 21:31:53
Back to Top
HTML Embed Code: