Telegram Web Link
"ዘወትር ፍጹም ሰላምን እግዚአብሔር ይሰጣት ዘንድ እግዚአብሔርን ስለምትወድ ስለ ሀገራችን ኢትዮጵያ እንማልዳለን"

#በእንተ_ቅድሳት
Audio
መሠረተ እምነት በአንዲት ሀይማኖት

እምነት ምን ማለት ነው

ሀይማኖት ምን ማለት ነው

አዘጋጅና አሳታሚ :-ኢንጂነር ወንዴ ጫኔ

https://www.tg-me.com/Egizhaberanidinew
ካህኑ ለምን በእጁ ያሳልመናል?

የካህኑን እጅ መሳለም፦ አንዳንድ ሰዎች ካህኑ ለምን በእጁ ያሳልመናል ይላሉ። ነገርግን ሚስጢሩ ይሄ ነው የካህኑ እጅ እኮ እሳታዊያን የሆኑ መላዕክት መንካት የማይቻላቸውን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን የዳሰሰበት ነው።

በቅዳሴ ላይ ቅዱስ ሥጋውን መንካት የሚችለው ዋናው ካህን ብቻ ነው ፤ ሁለተኛው ካህን እንኳን መንካት አይችልም። ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን የዳሰሰበት ስለሆነም ካህኑ በእጁ ያሳልመናል እኛም የተቀደሰውን የጌታ ስጋና ደም የተዳሰሰበት እጅ እየተሳለምን የቅዳሴው በረከትና የአምላካችን ምህረት በእኛ ላይ እንዲሆን አሜን አሜን እንላለን።

ድንቅ መለኮታዊ ሚስጢር ማለት
እንዲህ ነው...

አንሥኡ እደዊክሙ ቀሳውስ ፦

ዲያቆኑ ይህን በሚልበት ጊዜ ንፍቁ ካህን ማሕፈዱን ከጻሕሉ ላይ ያነሳል ፤ ይህም የጌታ መልአክ የመቃብሩን ድንጋይ የማንከባለሉ ምሳሌ ነው። ከዚህ በኋላ ጌታችን በምሴተ ሐሙስ ሕብስቱን እንደያዘው ዋናው ካህንም ሕብስቱን ከፍ አድርጎ ይይዘዋል ፤ ይህም የጌታ ትንሣኤ ምሳሌ ነው።

እግዚኦ መሐርነ ክርስቶስ፦

በእግዚኦታ ላይ ካህኑ ሕብሥቱን ይበልጥ ከፍ አድርጎ ይይዘዋል ይህም የዕርገቱ ምሳሌ ነው። ከካህኑ ጋር ሆነን 41 ግዜ እግዚኦ መሐርነ ክርስቶስ እንላለን ፤ ይህም አርባው እግዚኦታ አይሁድ ጌታችንን 40 ግዜ እንገርፋለን ብለው እያዛቡ ብዙ ግዜ የመግረፋቸው ምሳሌ ሲሆን በመጨረሻ ካህኑ ብቻውን የሚላት እግዚኦታ ደግሞ የአዳምና የሔዋን የንስሃ ምሳሌ ነው። 12 ግዜ እግዚኦ መሐርነ ክርስቶስ ስንል ደግሞ ስለስምህ ብለህ ይቅር በለን ስንል ነው።“አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ” የሚለውን እያንዳንዱን ፊደል ስንቆጥር 12 ይሆናልና!!እንዲሁም 12ግዜ በእንተእግዚትነ ማርያም መሐርነ ክርስቶስ ስነንል ደግሞ ስለእናትህ ብለን ማረን ማለታችን ሲሆን*ቅድስት ድንግል ማርያም*የሚለውን እያንዳንዱን ፊደል ስንቆጥር 12 ይሆናልና ነው

ወንጌል፦

የመጀመሪያው መልዕክት ሲነበብ ዲያቆኑ ፊቱን ወደ ምዕራብ አዙሮ ያነባል; ሁለተኛው ዲያቆን ፊቱን ወደ ሰሜን አዙሮ ያነባል; ንፍቅ ካህን ወደ ደቡብ ዙሮ የሐዋርያት ሥራን ሲያነብ ዋናው ካህን ደግሞ ወደ ምሥራቅ ዙሮ ወንጌልን ያነባል ፤ ይህም ግሩም የሆነ ምሳሌ አለው፦ አንድም ወንጌል በአራቱም አቅጣጫ መሰበኩን ለመግለጽ ነው; አንድም ገነትን የሚያጠጡ 4 ወንዞች አሉ; ኤፍራጠስ ጤግሮስ ጊዮን [ዓባይ] እና ፊሶን ናቸው። ገነትን አጠጥተው ለምለም እንደሚያደርጓት ጌታችን የተጠማ ቢኖር የህይወትን ውሃ በነፃ ይጠጣና ይርካ እንዳለው ወንጌሉም እንዲሁ ያለመልማል ሲሉ ነው።

ቤተክርስቲያን ከጣራዋ እስከ መሬቷ ሁሉም ሥርዓቷ ያስተምራል ፤ ባህረ ጥበብ ቤተክርስቲያን እየተናገረች ታስተምራለች ሳትናገር ዝም ብላም ታስተምራለች!!

ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የሲኦል ደጆች አያናውጧትም
ቤተክርስቲያን አ..ት..ታ..ደ..ስ..ም!

ፀልዩ በእንተ ሰላም ቤተክርስቲያን አሐቲ ቅድስት ጉባኤ እንተ ሐዋርያት ርትዕት በኅበ እግዚአብሔር!

የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም እንማልዳለን! (መጽሐፈ ሚስጢር)

ለሌሎች እንዲዳረስ SHARE እና LIKE እንዲያደርጉ በሚጠፉትና በሚድኑት መሀል የክርስቶስ መአዛ በሆኑት በቅዱሳን ስም እንጠይቃለን!

ቤተክርስቲያን....
መሰረቷ ጉልላቷ እርሱ ነው
ሙሽራዋ መስቀል ላይ የሞተው
ዛሬም ነገም ያው ነው ለዘላለም
አትንገሩን አዲስ ጌታ የለም!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን-ይቆየን።
ጌታ ሆይ፥ ከአንተ የሆነውን ሰማያዊ ደስታ አትንፈገኝ።
ጌታ ሆይ፥ ከዘላለም ፍርድ አድነኝ።
ጌታ ሆይ፥ በአሳብም ሆነ በአእምሮ፥ በቃልም ሆነ በሥራ ብበድል ይቅር በለኝ።
ጌታ ሆይ፥ ከአላዋቂነት፥ ከዝንጉነት፥ ከፈሪነት፥ ከልብ ጥንካሬ አድነኝ።
ጌታ ሆይ፥ከማናቸውም ፈተና አድነኝ።
ጌታ ሆይ፥ ክፉ ምኞት ያጨለመውን ልቤን አብራልኝ።
ጌታ ሆይ፥ ሰው የሆንኩት እኔ በድያለሁ፥ ነገር ግን አንተ ባለጸጋው አምላክ፥ ምሕረት አድርግልኝ፤ የነፍሴን በሽታ ታውቃለህና።
ጌታ ሆይ፥ ቅዱሱ ስምህን አክብር ዘንድ ጸጋህ እንዲያግዘኝ ላክልኝ።
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፥ እኔን ባሪያህን በሕይወት መጽሐፍ ጻፈኝ፤ መልካም ፍጻሜ ስጠኝ።
ጌታዬ አምላኬ፥ በፊትህ ምንም መልካም ሥራ ባይኖረኝም፥ ከጸጋህ የተነሣ መልካም ጅማሬ አድለኝ።
ጌታ ሆይ፥ የጸጋህን ጠል በልቤ ላይ እርጨው፤ የሰማይና የምድር ጌታ፥ እኔን ኃጢአተኛውን አገልጋይህን በመንግሥትህ አስበኝ። አሜን።
Audio
መሠረተ እምነት በአንዲት ሀይማኖት

ሀይማኖት ምን ማለት ነው

አዕማድ ምን ማለት ነው

አዘጋጅና አሳታሚ :-ኢንጂነር ወንዴ ጫኔ

https://www.tg-me.com/Egizhaberanidinew
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ክርስቲናያን መንፈሳዊ ትምህርቶች እና ጽሁፎች ቻናል⛪️
Video
የተማፅኖ እርዳታ ጥሪ*

ስሜ እመቤት አበበ እባላለው እድሜዬ 16 ዓመት ሲሆን የ10ኛ ክፍል ተማሪ ነኝ። በገጠመኝ የልብ ህመም ምክንያት የልብ ህመም ምክንያት ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሪፈር የተፃፈልኝ ቢሆንም ሆስፒታሉ ደግሞ መሳሪያ የለንም አሉኝ። በግል ደግሞ ለመታከም 500000 ብር (አምስት መቶ ሺህ ብር) ያስፈልጋል አሉኝ። ህክምናው ደግሞ ቶሎ ካላደረግሁኝ ህይወት አስጊ ላይ ስለሆነብኝ ነው። ቤተሰቦቼ ያደርጉልኛል እንዳልል አባቴ በህይወት የለም እናቴ ደግሞ ጉሊት ሰርታ ነው የምንተዳደረው ስለሆነም ይህን ትምህርቴ ከግብ የማድረስ ምኞቴ እንድታሳኩልኝ አቅማችሁ የፈቀደውን እርዳታ እንድታደርጉልኝ በፈጣሪ ስም እማፀናችኋለው።
ለበለጠ መረጃ ፦0942328386/0911361490/0900192673
account no ፦ አቢሲኒያ ባንክ 112836101
                           ንግድ ባንክ 1000344731776
Audio
መሠረተ እምነት በአንዲት ሀይማኖት

ለምን ምስጢራትርተባለ

አዕማደ ምስጢራት ምን ምን ናቸው

ምስጢረ ሥላሴ

አዘጋጅና አሳታሚ :-ኢንጂነር ወንዴ ጫኔ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ክርስቲናያን መንፈሳዊ ትምህርቶች እና ጽሁፎች ቻናል⛪️
"ከኃጢአተኛው ድንኳን" ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
እንኳን አደረሳቹ የቸሩ መድኃኔዓለም አመታዊ ክብር በዓል ዋዜማ


\\\\   ከኃጢአተኛው ድንኳን////

ከኃጢአተኛው ድንኳን ቅዱሱ ቆመሃል
ልጅ ይት ነህ ብለህ እኔን ፈልገሃል
አንተ ሰላለህኝ ቀሎአል መከራዬ
ለእኔ ያደረከው ብዙ ነው ጌታዬ(2)

አዝ

እንኳንስ አረገህኝ ጌታዬ ሙሉ ሰው
እንዲህው ይህው ነው ልቤ ሚናፍቀው
የዘመናት ሽክም ቀረ ጉስቁልና
የጠፍው ድሬም አግኝተሃልና

አዝ
ባገኝህኝ ጊዜ ሸፍናኝ በለስዋ
ከፊትህ ያነበብኩት ፈጸሞ አይረሳ
ከዚህ የበለጠ ታያለህ የምትለኝ
አይንህ ይናገራል  እንደማትረሳኝ

አዝ
ምን አለኝ ብለህ ነው ደጃፌ የምትመታ
እኔ ደካማ ነኝ አንተ ቅዱስ ጌታ
ከእንግዲህ አላረስም ምንጣፌ በእንባ
መጡላይቴ ክፍተህ በምህረት ግባ

አዝ
እኔ እኮ አውቅሃለሁ ሁሉን ስታፈቅር
የአናብስት ጉርጓድ የሞት አዋጅ ስትሽር
እንዲህ እያለ ነው የሚቀኝው ውስጤ
ኢየሱስ ክርስቶስ ምግብና መጠጤ

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለ ወላዲቱ ድንግል ማርያም ወለ ክብር መሰቀሉ ይቆየን አሜን
Audio
ጥቅምት 27 ዝክረ ቅዱሳን

🎙 ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ🎙

(ጥቅምት 27-2012)

አባታችን መበኣ ፂኦን

👆🏽👆🏽👂🏽👂🏽
Audio
መሠረተ እምነት በአንዲት ሀይማኖት

የሥላሴ ሶስትነት

አዘጋጅና አሳታሚ :-ኢንጂነር ወንዴ ጫኔ
Audio
መሠረተ እምነት በአንዲት ሀይማኖት

ምስጢር ሥላሴ አንድነት እና ሶስትነት

አዘጋጅና አሳታሚ :-ኢንጂነር ወንዴ ጫኔ
Audio
መሠረተ እምነት በአንዲት ሀይማኖት

ምስጢር ሥላሴ አንድነት እና ሶስትነት

አዘጋጅና አሳታሚ :-ኢንጂነር ወንዴ ጫኔ
Audio
መሠረተ እምነት በአንዲት ሀይማኖት

ምስጢር ስጋዊ

አዘጋጅና አሳታሚ :-ኢንጂነር ወንዴ ጫኔ
Audio
መሠረተ እምነት  በአንዲት ሀይማኖት

ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ሰው ሆነ

አዘጋጅና አሳታሚ :-ኢንጂነር ወንዴ ጫኔ

https://www.tg-me.com/Egizhaberanidinew
Audio
መሠረተ እምነት  በአንዲት ሀይማኖት

ምሥጢረ ጥምቀት
ምሥጢረ ቁርባን
ምሥጢረ ሙታን ትርጉም የብሉይ ኪዳን ሐዲስ ኪዳን ማሰረጃ

አዘጋጅና አሳታሚ :-ኢንጂነር ወንዴ ጫኔ

https://www.tg-me.com/Egizhaberanidinew
Audio
መሠረተ እምነት  በአንዲት ሀይማኖት

አዕማደ ምስጢራት መሠረት ምንድን ነው

አዕማደ ምስጢርን ለምን ይጠቅማል

ሰባቱ ምስጢራተ ቤተክርስቲያን ለምን ሰባት ሆኑ

አዘጋጅና አሳታሚ :-ኢንጂነር ወንዴ ጫኔ
የሰማዕታት እና ካህናት የእነርሱ እምነት ጽናት ንቃት ተፈትኗል አንዳንድ ጊዜ ለቀናት ወይም ለወራት ይህ በቂ ጊዜ ነው ከዚህ በኃላ ወደ ገነት ይነጠቃሉ

አቡነ ሺኖዳ ሥልሣዊ እንደጻፉት
2024/09/30 19:31:15
Back to Top
HTML Embed Code: