Telegram Web Link
​​🌺የራስህን ኑሮ ኑር! | ሁሉንም አታገኝም!🌺

አንዳንድ ጊዜ አጠገብህ ያሉ ሰዎች የሚፈልጉትን በቀላሉ ሲያገኙና በትምህርት🎓፣ በሥራ💼 በትዳር💍... ቶሎ ስኬትን ሲጨብጡ ታያለህ። አንተ ግን አንድ ቦታ ቆመሃል። ወቅቱ የእነርሱ ነውና ከመቅናት ይልቅ ባገኙት ስኬት የደስታቸው ተካፋይ ሁን። ለእነርሱ ያደረገ አምላክ ላንተም እንደሚያደርግልህ እመን። ይሀውልህ፤ የማንጎ ዛፍ የቡርቱካን🍊 ዛፍ ከርሱ ወቅት ቀድሞ ምርትን ስለሚሰጥ አይጨነቅም። ሆቴል ውስጥ ያለ ምግብ🍔 ተቀምጬ ብታየኝ ልታዝንልኝ አይገባም፣ ያዘዝኩት እስኪደርስ እየጠበኩ ነውና።

ስኬት፣ በወቅት የሚታጨድ መኸር ነው። ወቅትህ ሲሆን ምንም ነገር ከመንገድህ ሊቆም አይችልም። የአንበሳ በዝግታ መራመድ ስንፍናን ወይንም ድካምን አያመለክትም፤ ያለመውን አደን በእጁ ለማስገባት እርምጃውን እያሰላ እንጂ። የሰዎች ፈጥነው መራመድ አያውክህ። በቃ! የራስህን ኑሮ ኑር!፤ ፈጣሪህን ታመን። ልብ በል፤ ቤትህን በፍጥነት ሠርተህ መጨረስህ ሳይሆን ንፋስና ጎርፍን መቋቋም የሚችል ጠንካራ አድርገህ መሥራትህ ነው ቁምነገሩ። በሰዎች ደስታ ደስ ይበልህ። የእውቀት ሰውና ጠንካራ ሠራተኛም ሁን!

ደግሞ ሁሉንም አታገኝም!

አንተ የተሳፈርክበት አውሮፕላን መሬት ሲያርፍ፣ ከዛ መሬት የሚነሣ አውሮፕላን አለ፤ ሌሎች ደግሞ ለመነሳት በሂደት ላይ ይገኛሉ። ሁሉም መዳረሻቸው የተለያየ ነው፤ ምናልባትም ወዳንተ መነሻ ሊሆን ይችላል። አየህ ህይወት እንዲ ናት፤ "ደረስኩ" ብለህ ስታስብ ሌሎች ያንን ሥፍራ "ጥለው" ሲነሱ ታገኛቸዋለህ። አንዳንዶቹ አንተ ወደ ተነሳህበት፣ ሌሎቹም ወደ ሌላ።

በልጅ ማጣት ምክንያት ቀን ማታ የሚያለቅሱ ሰዎች እንዳሉ በልጆቻቸው ምክንያት ቀንና ማታ የሚያለቅሱ ሰዎች አሉ። ባለማግባታቸው የሚጨነቁ ሰዎች እንደገጠሙኝ ሁሉ በማግባታቸው የሚጨነቁም ሰዎች ገጥመውኛል። በሥራ እጥረት ምክንያት የታመሙ እንዳሉ በሥራ ብዛት ምክንያት የሚታመሙ አሉ። ልጆቻቸው ፈተና ላይ ጥሩ ውጤት እንዲያመጡላቸው የሚጨነቁ እንዳሉ፣ ልጆቻቸው ጥሩ ትምህርት ቤት እንዲገቡላቸው የሚጨነቁ አሉ።

ህይወት እንዲህ ነው፤ በቃ! ሁሉንም የኛ ልናደርግ አንችልም!፣ ንፋስን አባሮ እንደመያዝ ነውና። ሁሉንም ነገር የራስህ እንዲሆን ከመድከም ይልቅ ባለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን ሞክር። ከአንዱ ምእራፍ ወደ ሌላው ምእራፍ እንደሚያሸጋግርህም ፈጣሪህን ታመን። ሁልጊዜም በአምላክህ ደስ ይበልህ! በእምነትም ኑር. Share&join us @youthkiller @youthkiller @youthkiller
በህይወቴ ከተማርኩት ነገር ውስጥ አንደኛው ለሰዎች መልካም ነገር ብታደርግ ለመልካምነትህ ከሰዎች ዘንድ ምላሽ መጠበቅ ሊጎዳ እንደሚችል ነው።

❖✿አንዳንዱ መልካም ስታደርግ ሞኝ እንደሆንክ ሊቆጥርህ ይችላል።

❖✿አንዳንዱ ደግሞ ከእሱ የሆነ ነገር ፈልገህ የምታደርግለት ይመስለዋል።

፠=ሌላኛው ደግሞ ከምስጋና ይልቅ ጠላትህ ሊሆን ይችላል።

=፠እናም እልሀለሁ ለመልካምነትህ
ከሰዎች ምላሽን አትጠብቅ!

፠=ባገኘኸው አጋጣሚ ሁሉ ምላሹ
ምንም ይሁን ምን መልካምነት አብሮህ ይሁን! ፈጣሪህ ይከፍልሀልና. Share&join us @youthkiller. @youthkiller
የንባብ ቅምሻ

📖📜📜📜📖

ከ3000 ሺህ በላይ ዕድሜ ባላት በሀገራችን ኢትዮጵያ ህዝብ ውስጥ ብዙም ከቁብ የማይቆጠሩ በግሪክ ታሪክ እና ትውፊት ውስጥ ግን በብዛት የሚዘመርላቸው እና የሚወደሱ ብዙ አማልክት ነበሩ ።

ታላቁ የግሪክ ባለ ቅኔና ገጣሚ ሰው ሆሜር በዘመኑ ድንቅ ስራዎችን ጥሎ ያለፈ ሲሆን ከስራዎቹ ውስጥ ስለ ግሪክ አፈ-ታሪክ ባሰፈረበት 'ኦሊያድ' መፅሀፉ ውስጥ ስለ አማልክቱ በሰፊው አብራርቶታል ።

📖📖📖

በግሪክ አፈ-ታሪክ "ዜውስ" ማለት የግሪክ ትልቁ የመንፈስ አምላክ ሲሆን እርሱም ከዕለታት በአንዱ ቀን ሊድ ከምትባል አንዲት ወጣት ጋር ሌሊት በህልሙ ወሲባዊ ግኑኝነት ያደርጋል በዚያው ለሊትም ሄለን የምትባል አንዲት የዓለም ቆንጆ ተፀንሳ ታድራለች ።

ሄለንም ተወልዳ ካደገች በኅላ በውበቷ በዓለም ነገስታት ላይ ትልቅ ተፅዕኖ የምትፈጥር እና የምታንበረክክ ድንቅ ሴት ትሆናለች ።

📖📖📖

በታሪኩ ውስጥ በሄለን ውበትና ፍቅር የተነሳ በርካታ ነገስታት እንዲሁም ገበሬዎችን ጨምሮ ራሳቸውን እስከመሳት ይደርሱ እንደነበር ተፅፎ እናገኛለን ።

ሆሜር ምሳሌ ጠቅሶ ሲያስረዳም የግሪክ ገበሬዎች በውበት ስበቷ ኅያልነት እና ፍቅሯ ከመፍዘዛቸው የተነሳ በእርሻቸው ላይ ጨው ይዘሩ እንደነበር ይነግረናል ።

📖📖📖

በሄለን ፍቅርና ውበት የተነሳ ሁለት የዓለማችን ታላላቅ ነገስታት መካከል አንድ ትልቅ ጦርነት ሊነሳ ቻለ ይኸውም በታሪክ "የትሮይ ጦርነት" በመባል እስካሁን ይጠራል ።

ይህ ጦርነት ስለ ሄለን ከታካሄዱ ታላቅና ጀብደኛ ጦርነቶች መካከል አንዱና ዋነኛው ሲሆን ሄለን አግብታ ትኖር ከነበረችበት ከስፓርታ ንጉስ ሜሎስ በትሮይ ንጉስ ልጅ ልዑል ፖሪስ ተጠልፋ ወደ ትሮይ ከተማ ስትወሰድ የስፓርታው ንጉስ ንጉስ በትሮይ ላይ ባደረገው የጦር ዘመቻ በሁለቱም ወገን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወታደር እና ህዝብ ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል ።

📖📖📖

ነገር ግን በዚህ ጦርነት ወቅት ላይ አንድ ስመ ገናና የነበረ የግሪክ ጦረኛንም ጀብድ ታሪክ እናገኛለን

ጦረኛውም አርኪለስ ሲባል ከአማልክት ልዩ ኅይል የተሞላበት የዜውስ ስርወ-ዝርያ የነበረው እንዲሁም በቀላሉ ሊሞት የማይችል ጀግና እንደነበር ታሪኩ ያስቀምጣል

አርኪለስ ከኅይለኝነቱ እና የአማልክ ስርወ-ዝርያ የተነሳ በጦር ቢወጉትም ሆነ በጎራዴ ቢከፍሉት እንዳልሞተ እና በመጨረሻ ቁርጭምጭሚቱ ላይ በተወረወረ ቀስት ሊሞት እንደቻለ ታሪኩ ያስረዳል

የዜውስ የሄለን እና የአርኪለስ ታሪክ አሁን ካለንበት ዘመን ጭምር ጠባሳውን ከትውልድ ትውልድ እየተላለፈ እንደመጣ የሆሊውድ ፊልሞችን ማየት ብቻ ይበቃናል ።

📜📜📜

ምንጭ 📖 እርካብና መንበር 📖 መጽሐፍ
ደራሲ ዶ/ር ዓብይ አህመድ(ዲራአዝ) share&join us @youthkiller @youthkiller @youthkiller
ኮፒ ከ#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

ሕይወት ስትፈልግ የምትኖርበት፤ ሳትፈልግ ዘግተኸው የምትወጣው ቤት አይደለም። ፈለክም አልፈለግክም፣ ደከመህም በረታህም፣ ወደክም ተነሳህም፣ ወደድከውም ጠላሀውም፣ የመኖር ግዴታ ተጥሎብሀል።

ስለዚህ እንዴት ልኑረው በየትና በምን መንገድ ላስኪደው ብለህ በጥልቀት ስለራስህ ማሰብና የሕይወት መንገድህን በሚገባ የመስራት ኃላፊነት አለብህ።

ፈጣሪ አንተን በራሱ ምስል ሰርቶሀል። አንተ ደግሞ ሕይወትህን በሚመጥንህ መንገድ የመስራት ኃላፊነት ተሰጥቶሀል።

የህይወት መንገድህ ከሰማይ እንዲወርድልህ የምትጠብቀው መና አይደለም። አንተ ራስህ በራስህ መንገድ የምትሰራው ሥዕል ነው።

በየቀኑ የምትስለውን ስዕል አስተውለህ፣ አቅደህ፣ አልመህ ከእነሙሉ ልብህ፣ ህሊናህ እና ፍቃድህ ሆነህ ሣለው። ያኔ ውጤቱም ያማረ ሥዕሉም የሠመረ ይሆናል።

ያለፈው አልፏልና በትላንትናህ መፀፀት አቁመህ ከእንግዲህ የእያንዳንዷ ቀን ውሳኔህና ድርጊትህ፣ ተደምራ ነውና የሕይወት ስኬትን የምታጎናፅፍህ ለዕለት ተዕለት ውሳኔህና ተግባርህ ትልቅ ዋጋና አትኩሮት ስጥ።

የባከኑ ሰዓቶች ተደምረው የባከነ ሕይወት እንዳያጎናፅፉህ የሚባክን ሰዓት አይኑርህ!!!

@youthkiller @youthkiller
የለውጥ ሁሉ መነሻው ፣ የአስተሳሰብ ለውጥ መሆኑን አትዘንጋ ፣
ከየትኛውም ውሳኔ በፊት እውቀትን አስቀድም ፣ እውቀትህን ለማዳበር ፣
ሁሉንም ዓይነት፣ የእውቀት መንገድ ተጠቀም ። ከንግግርም ሆነ ከተግባር በፊት ዕውቀት ቀዳሚ ነው"! @youthkiller @youthkiller @youthkiller
ምሁራን ስለ ጊዜ ምን አሉ...

🗒🗒📜🗒🗒

🕰 " መቶ አመት የምትኖር መስለህ ስራ ነገ የምትሞት መስለህ ጸልይ ። "
/ ቤንጃሚን /

🕰 " አንድን ነገር ለመቀዳጀት ያለው ሃይል ጊዜ ብቻ ነው ። "
/ ሄላሪየር ቤሎክ /

🕰 " የሰነፎች የጊዜ መለኪያ ሰዓት ሲሆን ትጉሃን ግን በስራ ይቆጥራሉ ። "
/ ዊልያም ብሌክ /

🕰 " የዛሬዋ አንድ ቀን ከሚመጣው ሁለት ቀን ትበልጣለች እና በስራ ተርጉማት ። "
/ አብርሃም ሊንከን /

🕰 " በሕይወትህ ውስጥ ያለፉትን ሳይሆን በዓመታት ውስጥ የሚያልፈውን ሕይወትህን ነው መቁጠር ያለብህ ። "
/ ኮድሌ ስፒሽን /

🕰 " ጥሩም ይሁን መጥፎ ብቸኛው ጊዜ አሁን የያዝነው ነው ። "
/ በች ዋይልድ /

🗒🗒🗒

ምንጭ 📰 ንግስት መጽሔት 📰

📖 ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል

@youthkiller @youthkiller @youthkiller
!!! እራስህን ስታውቅ እምታደርጋቸው ድርጊቶች…

🏆1⃣ ለራስህ ፍቅር ይኖርሀል

🏆2⃣ ለራስህ ጥሩ ግምት ትሰጣለህ

🏆3⃣ ራስህን ታምናለህ

🏆4⃣ መቀየር እማትችላቸውን አምነህ ትቀበላለህ

🏆5⃣ ራስህን ታውቃለህ

🏆6⃣ ራስህን ታሳድጋለህ

🏆7⃣ ራስህን መንከባከብ ትጀምራለህ

🏆8⃣ ስራህን ለሌሎች ታጋራለህ


@youthkiller
@youthkiller
ከአንዱ ጋር እያወራን ነዉ

እሱ፣ "በናትህ ቻናልህ ላይ የአፋልጉኝ ማስታወቂያ ለጥፍልኝ"

እኔ፣ "ምን ጠፍቶብህ ነዉ?"

እሱ፣ "መፅሐፍ ገዝቼ ስመጣ የት እንደጣልኩ ረሳሁት"

እኔ፣ "ምን የሚል መፅሐፍ ነዉ?"

እሱ፣ "የመርሳት ችግርን ለማስወገድ የሚረዱ 10 ነጥቦች"

እኔ፣ "😂😂😂😂😂 አይጠቅምህም ተወዉ በቃ!"

እሱ፣ "ምኑ?"

እኔ፣ "መፅሐፉ ነዋ"

እሱ፣ "የምን መፅሐፍ?"

ሀ ሀ ሀ

ሼር ይደረግ! ሌሎችንም ወደ ቻናላችን ለመቀላቀል
@youthkiller
@youthkiller
🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ🙏

አትኩሮትህን በሌለህ ነገር ላይ ሳይሆን ባለህ ነገር ላይ አድርገው። ደስተኛ ለመሆን ሁሉም ነገር ሊኖርህ አይገባም። በደንብ ካስተዋልከው አሁን ያለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን በቂ ነው። ምክንያቱም አንተ ያለህን የሚመኙ ምስኪኖች ብዙ ናቸውና።

🙌መልካም አዳር የነገ ሰው ይበለን!!! @youthkiller
አንድ ወጣት ልጅ ታክሲ ውስጥ ተቀምጦ እያለ አንዲት አዛውንት እናት ወደ ታክሲው ቀርብ ብለው ለሹፌሩ እባክህ ልጄ በእጄ የነበረኝን ገንዘብ ሌባ ሰርቆብኝ ነው እዚህ አከባቢ ማንም ሊረዳኝ የሚችል ሰው የለኝም እባክህን እቤት ሄጄ እከፍላለው ውሰደኝ አሉት ሹፌሩም ይቅርታ ይሄን ማድረግ አልችልም ሂሳብ በቅድሚያ ነው የምንቀበለው አላቸው

ታክሲ ውስጥ የነበረ ድሃ ልጅ አዛውቱን ለመርዳት አስቦም ግን በኪሱ ውስጥ ያለው 50 ብር ብቻ ነው እራት የሚባላበት ብር ነው ስለዚህ ጨነቀው
ትንሽ አሰበና መጽሐፈ ቅዱስ ውስጥ<< ስጡ ይሰጣችኃል>> የሚል ጥቅስ ትዝ አለዉ
ከዛም ስለ እራቱ ማሰብ ትቶ እናቴ እኔ እከፍላለሁ ግቡ አላቸው
እዛውንቱዋም ልጄ እግዚአብሔር መልካም ነገር ይስጥህ አሉትና ታክሲ ውስጥ ገብተ አብረው ሄዱ
ከዛም ልጄ አንዴ እንደሆነ ተቸገረሃል እባክህ ይሄንን ፕላስቲክ እቤት አድርስልኝ አቅም የለኝም አሉት ልጁም ችግር የለም ብሎ እቃውን ይዞላቸው ወደ አዛውንቷ ቤት ሄዱ እቤት ሲደርሱ ያየውን ማመን አልቻለም እኚህ አዛውንት በጣም ሀብታም ናቸው ነገር ግን ልጆች የላትም እቤት ገብቶ አብሮ እራት በሉ አዛውንቷም ልጄ ለኔ ልጅም ዘመድም የለኝም እስክሞት ከኔ ጋር ሁን እኔንም እርዳኝ አንተም ከእንግዲህ አትቸገርም አሉት ልጁም ሀብታም ሆነ የሁሉም ንብረት ወራሽ ሆነ
@youthkiller
የአዕምሮ ምግቦች

ማንበብ የሰውን ልጅ የአዕምሮ ጡንቻ በማዳበር ለነገሮች ሁሉ ያለንን መረዳት በየጊዜው እንደሚያሳድገው የተረዳ ሰው ከማንበብ ሊቆጠብ አይችልም፡፡ የሰው ልጅ አካለ ሥጋ (Physical Body) ጡንቻዎች በስፖርታዊ እንቅስቃሴና በተመጣጣኝ ምግብ ሊዳብሩና ማራኪ ቅርጽ ሊይዙ ይችሉ ይሆናል፡፡ ጤንነታቸውም በነዚህና በሌሎች የህክምና መንገዶች ሊጠበቁ ይችላሉ፡፡ የአዕምሮ ጡንቻ የሚዳብረውና ጤናው የሚጠበቀው ግን በንባብና በመሳሰሉት የአዕምሮ ምግቦች ነው፡፡ እና የአዕምሮው ጡንቻ እንዳይዳብርና የመረዳት አቅሙ እንዳያድግ የሚፈልግ ማነው? በእውነት ሰው ይሄንን ከተረዳ ለማንበብ ይሰንፋል ብዬ አላምንም፡፡
የሰው ልጅ አንባቢ ሲሆን ሀሳቡ ይሰበሰባል፡፡ አስተውሎቱ ይጨምራል፡፡
@youthkiller👍👍👍
ሳይኮሎጂ | ለራሳችን መንገር የሌለብን 4 ነገሮች
የተለያዩ ችግሮች ውስጥ የምታልፉበት አጋጣሚ
ሊኖር ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ለችግሮቹም ራሣችሁን
ተጠያቂ ታደርጉ ይሆናል፡፡ በየትኛውም አይነት ሁኔታ
ውስጥ ብትሆኑም ግን ደካማነታችሁን የሚያጎሉና
ከሠዎች በታች ሆናችሁ እንድትታዩ የሚያደርጉ ቃላትን
መጠቀም የለባችሁም በማለት የሥነ-ልቦና ምሁራን
ይመክራሉ፡፡ እነኚህ ቃላት አስተሳሰባችን ላይ አሉታዊ
ተፅእኖ የመፍጠር አቅማቸው ከፍተኛ ነው፡ ፡ ለራሳችን
የምንናገራቸው አሉታዊ ቃላት ከፍተኛ ጉዳት
እንዳላቸው ከሕይወት ልምዴ ተገንዝቤያለሁ የሚሉት
የሥነ-ልቦና ባለሙያው ማይክ ቡንድራንት በተለይ
የሚከተሉትን ቃላት ለራሳችሁ ፈፅሞ መንገር
የለባችሁም ይላሉ፡፡
የማልረባ ነኝ
ይህ በራስ መተማመናችሁን በቀጥታ የሚገድል
አነጋገር ነው፡፡ የማትረቡ ወይም አንዳች ዋጋ
የሌላችሁ መሆኑን ለራሳችሁ መንገር አሉታዊ
አስተሳሰብ በአእምሯችሁ እንዲሰርፅ የማድረግ ኃይል
ስላለው ቃሉን መጠቀም ተገቢ አይደለም፡፡
2. አልችልም
አንዳንድ ነገሮችን በምትፈልጉት ደረጃ መስራት
የማትችሉባቸው ሁኔታዎች በሚፈጠሩበት ጊዜ
አቅማችሁን ልትጠራጠሩ ትችላላችሁ፡ ፡ የምታደርጉት
ነገር ጥቅም እንደ ሌለው ለራሳችሁ መንገር ለሥራ
ያላችሁን የተነሳሽነት ስሜት ይቀንሠዋል፤ አቅማችሁን
ያሣጣችኋል፡፡ ይህ አነጋገር እውነታውን ከመግለፅ
በላይ ራሳችሁን መልሶ የማጥቃት አቅም አለው፡፡
አንድ ነገር ከመሥራታችሁ በፊት እወድቃለሁ/
አይሣካልኝም ከማለት ይልቅ ደጋግሞ በመሞከር
ለውጤት መብቃት እንደምትችሉ ማመን አለባችሁ፡፡
3. ሠዎች አይወዱኝም
ሠዎች አይወዱኝም የሚለውን ስሜት በአእምሯችን
ማስረፅ ሌሎች ከእኛ የተሻሉ እንደሆኑ እንድናስብና
ለራሳችን ጥረት ተገቢ ውጤት እንዳንሠጥ
ያደርገናል፡፡ በሌሎች ያለመወደድ ስሜት ከተሠማን
ደግሞ ለራሳችን የምንሠጠው ክብርም ይቀንሳል::
4. ለውጥ ማምጣት አልችልም
አንድን ነገር ለመለወጥ አቅማችሁ ካልፈቀደ
ራሣችሁን አታስገድዱት፡፡ ፍፁም መሆንንም
ከራሣችሁ አትጠብቁ፡፡ በተለያዩ ርዕሠ ጉዳዮች ላይ
የምትሠጧቸው ሀሳቦች የራሳቸው አዎንታዊ ተፅእኖ
አላቸው፡፡ ስለዚህ ‹ለውጥ ማምጣት አልችልም››
የሚለው ቃል ለራሳችሁ መንገር ከሌለባችሁ አሉታዊ
ቃላት መካከል አንዱ ነው፡፡
በአጠቃላይ ስሜታችሁን የሚጎዱ እንዲህ ዓይነት
ቃላትንና አነጋገሮችን መጠቀም ትታችሁ
አንደበታችሁን በመጠበቅ በየዕለቱ ለምታከናውኗቸው
ተግባራት ትኩረት በመስጠት ውጤታማ መሆን
ትችላላችሁ፡፡share &join us@youthkiller @youthkiller @youthkiller
ምንጭ፡- Psychcentral.com
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የለውጥ ሁሉ መነሻው ፣ የአስተሳሰብ ለውጥ መሆኑን አትዘንጋ ፣
ከየትኛውም ውሳኔ በፊት እውቀትን አስቀድም ፣ እውቀትህን ለማዳበር ፣
ሁሉንም ዓይነት፣ የእውቀት መንገድ ተጠቀም ። ከንግግርም ሆነ ከተግባር በፊት ዕውቀት ቀዳሚ ነው"! @youthkiller @youthkiller @youthkiller
ይ መ ለ ከ ተ ኛ ል…
ይ መ ለ ከ ት ካ ል…
ይ መ ለ ከ ት ሻ ል…
ይ መ ለ ከ ታ ች ኃ ል …
ይ መ ለ ከ ተ ና ል…

. ''ወጣት-ነክ ስህተቶች''

🌿አንድ ሰዉ በህይወት በኖረባቸዉ አመታቶቹ በርካታዉን ስህተት የሚሰራዉ በልጅነቱ እንደሆነ ግልፅ ነዉ። ከዚያ በመቀጠል በርካታ ስህተት የሚሰራባቸዉ አመታት የወጣትነት አመታት ናቸዉ። የወጣትነት ስህተት በመጠኑ ያለመብሰል ስህተት ቢገኝበትም በአብዛኛዉ የድፍረትና ''የቅብጠት'' ስህተት ነዉ።

🌿የአዋቂነት ስህተት ግን በአብዛኛዉ ካለፈዉ ስህተት ያለመማርና ለማደግ ፈቃደኝነትን የማጣት ስህተት ሊሆን ይችላል።

🌿መንደርደርያ እንዲያገኙ የሚረዷቸዉ የስህተት አይነቶች፦

1. የእዉቀት ዓለም
የኃላ ኃላ እንዳትፀፀት የትምህርትን ጉዳይ በምንም አትለዉጠዉ። አለማወቅ ጨለማ ነዉ። አለማወቅ ኃላቀርነት ነዉ።




2. የአቻዎች ዓለም
የኃላ ኃላ እንዳትፀፀት የእድሜ አቻዎችህ የተለያዩ ከመስመር የሚያወጡ ነገሮችን እንድታደርግ ሲጋብዙህ ፡ በእነሱ ግፊት ተነሳስተህ ወይም ከቡድናቸዉ እንዳያገሉህ ብለህ ራስህን አትሽጥ።




3. የተቀባይነት ዓለም
ቤተሰብህ ፡ የቅርብ ጓደኞችህ ፡ ፍቅረኛህ ስለገፉህና ስላልተቀበሉህ ስህተቶች የመሆናቸዉ እዉነታ በመራራ ዉሳኔህ ም/ት ከሚመጣ የወደፊት ፀፀት አያድንህም።




4. የፍቅር ዓለም
መስመሩን ካልጠበቀ ፡ ልቅ ከሆነና በኪዳን ካልታሰረ የእግረ-መንገድ ወሲብ ራስህን ካልገታህ የዚህን አይነቱን የሕይወት ዘይቤ የለመዱ ሰዎች ከወደቁበት አዘቅት አንተም አታመልጥም።




5. የስሜት ዓለም
አንተ ስሜትህን የምትመራበት እንጂ ስሜትህ አንተን የሚመራበት ሕይወት አያስፈልግህም። ምግባረ ብልሹ የወሲብ ምስሎቾና ፊልሞች {pornograph} አንድ ጊዜ ስሜትህን ከተቆጣጠሩት ዲሲፕሊን ያለዉን የሙያና የስራ ፡ እንዲሁም የፍቅርና የቤተሰባዊ ሕይወት እንዳትመራ ጠንቅ ይሆንብሃል።




ፅሁፉ የተወሰደበት ከገፅ 138 - 140

ርዕስ - የህይወት ፀፀቶች
ደራሲ - ዶር. ኢዮብ ማሞ
የገፅ ብዛት - 160 ገፆች
ዋጋ - 81 ብር

እኔ በዚሁ አበቃዉ🙏

ስለዚህ ገዝታችሁ አንብቡ

መፅሀፉ ግን ይቀጥላል…… share&join us @youthkiller @youthkiller @youthkiller
በጣም አስተማሪ ታሪክ
.
አንድ በጣም ሌባ እና ብዙ ሴቶችን ደፍሮ የታሰረ ወጣት ነበረ ። ከእስር እንደተፈታ ወደ አያቶቹ ቤት ለጥየቃ እየተጓዘ እያለ ይመሽበትና ሰው ቤት ለማደር ፈልጎ የኣንድን ሰው ቤት ያንኳኳል ሰውየው ሲከፍት ልጁ እባካቹ ተጓዥ መንገደኛ ነኝ እንድታሳድሩኝ ስል በፈጣሪ ስም እለምናልው ሲል ጠየቀ ሰውየው በለሰለሰ ድምፅ ይቅርታ አምኜ ላሳድርህ አልችልም ሴት ልጅ አለችኝ ይለውና በሩን ይዘጋል ።ሁለተኛውም ቤት ሄዶ ጠየቀው ተመሳሳይ መልስ ሰጠው እና በሩን ዘጋ። ሶስተኛው ቤት አንኳኩቶ ሲጠይቅ ግባ ብለው አስገብተው እራት አበሉት ልጁ ማሰብ ጀመረ ወንድ ልጅ ቢኖራቸው ነው ብሎ አሰበ ግን ወደ ማደሪያው ሲሄድ ቆንጂዬ ሴት ልጅ ተኝታለች። ሰውየው ያረገውን ኮፍያ አውልቆ መሃላቸው ላይ አስቀምጦ ማንም ወደ ማንም እንዳይጠጋ አለና ልጁን አምንሀለው ብሎ ኩራዙን አጥፍቶላቸው ይተኛሉ። ልጁ በመደነቅ ምንም ሳያቀኝ አንዴት አመነኝ ብሎ እንቅልፍ ሳይወስደው አደረ በጠዋት ሊሄድ ሲወጣ ምግብ ቋጥረው ሰጡት። ልጁ ከግቢው እንደወጣ ልጂትዋ በረንዳ ላይ ሆና ስታየው ተመለከተ ። ገብቶ ሰላም እንዳይላት በሩ ተዘግቷል አጥሩ ላይ ሆኖ ቆይ መጥቼ ሰላም ልበልሽ ሲል
ልጂቱ ያባቴን ኮፍያ ያልዘለልክ ልጅ አሁን አጥር ልትዘል ነው ብላ አሾፈችበትና ሄዳ በሩን ከፈተችለት። ልጁም ፀጉርዋን እየዳበሰ እምነት ትልቅ እስር ቤት ነው እምነትን ስትቀበይ መንቀሳቀስ አትችይም እኔ ብዙ ጊዜ ታስሬ አቃለው ግን ምንም አይመስለኝም የእምነት እስር ቤት ግን ከምንም በላይ ትልቅ ነው አላት ይባላል። እና አምነሀት ወይም አምነሺው ከጎዳሽ አትበሳጪ(ጭ) የጎዳህ ሰው እድሜ ልክ ፀፀት ይሆንበታል።
👇 Join us👇

@youthkiller @youthkiller
@youthkiller
ምክር


"በህይወትህ ትእግስተኛ መሆን ከቻልክ የምትፈልጋቸው ነገሮች በሙሉ ግዜያቸውን እየጠበቁ ወዳንተ ይመጣሉ፡፡
በፍቅር አለም ውስጥም ትልቁን ዋጋ ሚያስከፍለው ትእግስት ነው፡፡ መታገስ ይከብዳል፡፡ ያ' ግዜ ሲያልፍ ግን ምንፈልገውን እናገኛለን፡፡መራራውን ግዜ አልፈህ ጣፋጩን ፍሬ ትበላ ዘንድ ታጋሽ ሁን፡፡ ትእግስተኞች ከ ጉልበተኞች ይበልጣሉ፡፡"

💐መልካም አዳር
ፍቅር ማለት ማስመሰል አይደለም።

ፍቅር ማለት ስለወደደህ ብቻ
የምትወደውም አይደለም።

ፍቅር ማለት በደስታ ግዜህ ጠብቆ የሚቀርብህ አይደለም።

ፍቅር ማለት ሀዘንህን ብቻ የሚመለከት አይደለም።

ፍቅር ማለት በይሉንታ የሚታሰር አይደለም።

ፍቅር ማለት አንተነትህን ባወቀህ ልክ የሚተችህ አይደለም።

ፍቅር ማለት ለብቸኝነት የሚዳርግህ አይደለም።

ፍቅር ማለት ሲቸገርህ የሚርቅህ አይደለም።
ፍቅር ማለት የክብር ጉዳይም አይደለም።

💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕
#ፍቅር_እውነተኛ_ስሜት_ነዉ የሌሎችን #ስሜት_ሳይሆን_የራስህን #ስሜት_የምታዳምጥበት_ልብህን_ከፍተህ #የምታስቀምጥበት_በደስታው_ደምቀህ_በሀዘኑ_መፍትሄ_የምትሻበት_ዛሬን_ኑረህ_ነገን_የምታልምበት_ኣዲስ_ነገር-የምታይበት
💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕

#እውነተኛ_ፍቅር ሁሌም ቃሉ ትክክል ነው ሽንገላን አያውቅም፤ችግር ፤ስህተትህን በትግስት እያለፈ መልካም ነገርን ያስተምራል።መሆን ምን ማለት አእንደሆነ እየኖረ ያሳየሀል።።።።፣
አይበግረውም
የማይቇረጥ ፣ችግር የማይፈታው ፣አንደበታዊ ያልሆነ፣ ማስመሰል የሌለበት ፍቅር ይስጠን።፣፣፣፣አሜን


@youthkiller
e
Dr. Mehret Debebe —ምህረት ደበበ
# ስብዕናህን_ፈትሽ
ጭንቀት ውስጥ የሚከትህንና የማይከትህን ነገሮች ለይተህ በመረዳት ራስህን ጠብቅ፡፡
ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ ጭንቀትን ለመቀነስ ቴክኒኮችን ማወቅና አስተሳሰብን
መለወጥ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህም በሥልጠናና በባለሙያ የካውንሰሊንግ አገልግሎት ሊገኝ
ይችላል፡፡
ለዛሬ ሁለት ቴክኒኮችን ብቻ እንመልከት(በርካታ ቴክኒኮች እንዳሉ መገንዘብ ያስፈልጋል)፡-
አንደኛው በእንግሊዝኛው ምህፃረ ቃል # ABCDE ተብሎ የሚጠቀሰው ነው፡፡
ይህ ቴክኒክ አልበርት ኤሊስ (Albert Ellis) በተባሉ የስነልቦና ባለሙያ የተገኘ ዘዴ ነው፡፡
አልበርት ኤሊስ ሰዎች ወደ ጭንቀት የሚገቡት አግባብ ያልሆነ አስተሳሰቦችና እምነቶች
(Irrational beliefs and thoughts) ሲጠናወቷቸው ነው ብለው ያምናል::
ለምሳሌ ሰው ሁሉ ይጠላኛል፣ ሰው ሁሉ ይወደኛል፣ ከሰው ሁሉ ተቀባይነትን ማግኘት
አለብኝ፤ በምሰራው ስራ ሁሉ መሳሳት የለብኝም ወዘተ የሚሉ እምነቶችና አስተሳሰቦች
ለጭንቀት እንደሚዳርጉ ያሰምሩበታል።
እኚህ ሰው እንደሚሉት አሉታዊ ነገሮችን አጋኖ ማየት (Awfulising) ፤ ጥቁርና ነጭ እሳቤ
(Black and White thinking) (ይህ እንግዲህ አንድን ነገር ጥሩ ወይም መጥፎ ብሎ
መመደብና በውስጡ ሊኖር የሚችለውን የተወሰነውን ጥሩ ነገር አለማየት ነው)፣ጠቅላይ
እሳቤ (Over generalizing)-
ሁልጊዜ፣ሁሉም ሰው፣ በፍፁም ወዘተ የሚሉ ቃላትንና ሃሳቦችን መጠቀም፤ የማይመለከተንን
ነገር ከራሳችን ጋር አቆራኝቶ ማየት (Personalizing)፤ በሁኔታዎች ውስጥ አሉታዊን ነገር
ብቻ መርጦ
ማየት(Filtering)፣ ይህንን አስቦ ነው ብሎ ያለምንም ማስረጃ ድምዳሜ ላይ መድረስ
(Mind reading)፣ሰዎችን መተቸትና መውቀስ (Blaming)፣ለራስ ስያሜ መስጠት
ለምሳሌ ደካማ ነኝ፤ዋጋ ቢስ ነኝ ወዘተ ማለት (Labeling) አግባብ ላልሆኑ አስተሳሰቦች
ምክኒያት ናቸው ይሉናል፡፡
የ ABCDE ቴክኒክን ተንትነን ለማየት እንሞክር
# Antecedent (Activating event, Stimulus)፡ ይህ ማለት ጭንቀትን የሚቀሰቅሰው
ሁኔታ ወይም ነገር ነው(ተንኳሽ እንበለው)፡፡
ይህ ተንኳሽ የኛን ምላሽ (Response) ይጠይቃል። ለምሳሌ ከስንት አንድ ቀን ቀጠሮ
ብናረፍድ ጭንቀት ሊፈጠርብን ይችላል፡፡ በዚህ ምሳሌ መሰረት ጭንቀትን የሚፈጥርብን
ጉዳይ ማርፈዳችን ነው ማለት ነው፡፡
# Belief_our_cognition_about_the_situation ፡- ይህ እንግዲህ ስለ ተንኳሹ ያለን
ሃሳብና እምነት ነው፡፡ ለምሳሌ ማርፈዴ ያለኝን ተቀባይነት ያሳጣዋል፣ በምንም አይነት
ምክኒያት ቢሆን ማርፈድ አሳማኝ አይደለም ወዘተ የሚል እምነት ማለት ነው፡፡
# Consequences - the way that we feel and behave፡ ይህ ውጤት ነው -
ጭንቀታችን፡፡ ይህ ምን ባህሪ ይፈጥራል? ቶሎ ለመድረስ አላግባብ ጣልቃ እየገባን
መኪናችንን መንዳትን፣ በእጃችንም በአንደበታችንም የተንቀረፈፈ የመሰለንን ሾፌር
መስደብ፣መቆጣት፤ ከአስፋልት ወጥቶ በእግረኛ መንገድ መንዳት ወዘተ ማለት ነው፡፡
እዚህ ላይ አልበረት ኤሊስ ይሞግታሉ “ያስጨነቀን ማርፈዳችን ነው ወይስ ስለ ማረፈድ ያለን
አስተሳሰብና እምነት ነው?” አሳቸው እንደሚሉት፤ ውጤቱን የፈጠረው ማርፈዳችን
(stimuls ) ሳይሆን ስለ ማርፈድ ያለን አስተሳሰብና እምነት ነው ባይ ናቸው፡፡
Dispute is the process of challenging the way we think about situations:
ይኸኛው አስተሳሰባችንን የምንሞግትበት ዘዴ ነው። እሳቸው አግባብነት የሌለውን
አስተሳሰብና እምነት መሞገት ያስፈልጋል ይላሉ፡፡
ለምሳሌ ከላይ የጠቀስነውን ማርፈድ ብንወስድ እምነታችንን ስንሞግተው እንደሚከተለው
ይሆናል፡፡ “ ብዙ ጊዜ በሰዓቱ የምገኝና ቀጠሮ አክባሪ የሆንኩ ሰው ነኝ፡፡
አንድ ዛሬን ባረፍድ ተቀባይነቴን አያሳጣም”፣ “ለማርፈዴ ምክኒያት የሆነኝ የትራፊክ
መጨናነቅና ያልጠበቅሁት የመንገዶች መዘጋጋት ነው፡፡ ስለዚህ በቂ ምክኒያት ሊሆን
ይችላል፡፡
” እነዚህን ምክኒያቶች በማሰብ ነባሩን ሃሳብ መሞገት እንደሚገባ ይጠቁማሉ፤ አልበርት
ኤሊስ፡፡
# Effect : ይሄ አዲሱ ውጤት ነው።
አስተሳሰባችንን ከሞገትነውና በአዲስ አስተሳሰብ ከተካነው በኋላ የሚፈጠር ባህሪ ነው፡፡
የላይኛውን ምሳሌ ብንከተል ተረጋግቶ መንዳት፤ ተራ መጠበቅ፤ በተፈቀደው አስፋልት
መንዳት ወዘተ ማለት ነው፡፡ በነገራችን ላይ ሃሳብ ስሜታችን እና ባህሪያችን ላይ ተፅእኖ
ይፈጥራል፡፡
በሁለተኛ ደረጃ #የሶቅራጠስን_ቴክኒክ እንመልከት፡- የጥንቱ የግሪክ ፈላስፋ ሶቅራጠስ
አስጨናቂ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ የሚጠይቃቸውን የሚከተሉትን አምስት ጥያቄዎች መጠየቅ
ይጠቅማል፡፡
ተጨባጩ ነገር ምንድነው? ስለዚህ ነገር ያለኝ የኔስ የግል እሳቤ?
የግል እሳቤዬን የሚደግፍ ማስረጃ አለ?
የግል እሳቤዬን የሚቃረን ማስረጃስ?
የአስተሳሰብ ስህተት ፈፅሜያለሁ?
ስለ ተፈጠረው (ስለ ተጨባጩ) ሁኔታ ምን ማሰብ አለብኝ? ነገሩ የግል እሳቤን
የሚያጠናክር ማስረጃ ካለው(ተ.ቁ 2.2) ለችግሩ መላ መፈለግ ያስፈልጋል። ከእምነቴ
ተቃራኒ ከሆነ(ተ.ቁ 2.3) መጨነቅ ለማያስፈልገው ነገር ጊዜዬን እያባከንኩ ወይም
ለጭንቀት ውጤቶች ራሴን እየዳረግሁ ነው ማለት ነው፡፡
የሶቅራጠስ ቴክኒክ
የነገሮችን ወይም የሁኔታዎችን ተፅእኖ የምንፈትሽበትና የእርግጠኝነት ምላሽን
የምንፈልግበት ነው፡፡ በነገራችን ላይ ዴል ካርኒጊ፤ አብዛኛው ሰው የሚጨነቀው ገና
ባልደረሰብት ችግር ነው የሚል አስተሳሰብ ነበረው።
በመጨረሻም እንድ ማወቅ የሚገባን ነገር አለ፡- እንዳንድ ነገሮችንና ሁኔታዎችን መቆጣጠር
እንችላለን። ይህንን ፅሁፍ ማዘጋጀትና አለማዘጋጀት በኔ ቁጥጥር ስር ነው፡፡ ከፈለግሁኝ
አዘጋጀዋለሁ ካልፈለግሁኝ አላዘጋጀውም፡፡ ስለ ፈለግሁኝ አዘጋጀሁት፡፡ በአንዳንድ ነገሮች
ወይም ሁኔታዎች ደግሞ ተፅእኖ መፍጠር እንችላለን ነገር ግን ልንቆጣጠራቸው አንችልም፡፡
ለምሳሌ በቡድን በሚሰሩ ስራዎች እርስዎ የሚያምኑበትን ነገር ተግባራዊ እንዲሆን የስራ
አመራሩን ተፅኖ ሊፈጥሩበት ይችላሉ እንጂ ውሳኔውን በግልዎ ሊቆጣጠሩት አይችሉም።
አንዳንድ ነገሮችን ደግሞ መቆጣጠርም ሆነ ተፅእኖ መፍጠር አይቻልም። ስለዚህ ሁኔታውን
መቀበል ወይም በሁኔታው ውስጥ ውጤታማ ሆኖ ለመኖር መወሰን ነው የሚጠበቅብዎ፡፡
ለምሳሌ የእርስዎ የቅርብ ሰው በሞት ቢለይ ወይም ፈፅሞ እርስዎን ላለማግኘት ወስኖ
ከእርስዎ መለየት ቢቆርጥ የሚቀይሩት ጉዳይ ስላልሆነ መቀበል እንዲሁም በተፈጠረው
ሁኔታ ውስጥ ራስን አዘጋጅቶ መኖር ያስፈልጋል።
አብዛኛው ሰው መቆጣጠር የሚገባውን ነገር ለሌሎች ተፅእኖ አሳልፎ ሲሰጥ ወይም
ተቀብሎ ሲኖር፣ ወይም ተፅእኖ ማሳደር የሚገባውን ነገር ለመቆጣጠር ወይም በቸልተኛነት
ሲቀበለው እና ራስን አዘጋጅቶ መኖር የሚገባውን ወይም መቀበል ያለበትን ሁኔታና ነገር
ለመቆጣጠር ወይም ተፅእኖ ለማሳደር ሲሞክር የጭንቀት ሰለባ የመሆኑ ዕድል የሰፋ ነው።
ይህንን በአጭሩ ለማስታወስ በእንግሊዝኛው ምህፃረ ቃል CIA-Control-Influence-
Accept/Adapt to ብሎ መያዝ ይጠቅማል፡፡
አንዳንዱን ነገር Control እናደርጋልን፤ አንዳንዱን influence ነው የምናደርገውን አንዳንዱን
ደግሞ Accept/Adapt to ነው ማድረግ የሚገባን፡፡ @youthkiller
አእምሮህን እንደ አንድ የአትክልት ስፍራ ተመልከተው፡፡ አንድ የአትክልት ስፍራ የተለያዩ አትክልቶችን የሚያበቅለው ስለዘራህበት ብቻ አይደለም፡፡ ብትዘራበትም ባትዘራበትም አረምም ሆነ “ወፍ-ዘራሽ” ነገሮችን ማብቀሉ አይቀርም፡፡ ጥሩ ዘርን ከዘራህበት የዘራህበትን ጥሩ ዘር ያበቅላል፡፡ መጥፎ ዘር ከዘራህበትም እንዲሁ፡፡ ምንም ዘር ካልዘራህበት ደግሞ ይህንና ያንን ማብቀሉ አይቀርም፡፡ አእምሮህም እንዲሁ ነው፡፡ በገጠመኞችና በተለያዩ ሁኔታዎች የሚገቡ “ወፍ-ዘራሽ” ሃሳቦችን ማብቀሉ ካልቀረ፣ መልካም ነገርን እየዘራህበትና ጥሩ ጥሩውን እያሰብክ ጣፋጭ ሁኔታዎች መፍጠር ትችላለህ፡፡
በተፈጥሮአችን ወደ እኛ የምንስበውም ሆነ ራሳችንን ተስበን የምንገኝለት ሁኔታ ከአመለካከታችን ጋር ዝምድና አለው፡፡ ስለዚህም፣ ሰዎች ወደ እነሱ የሚስቡት የሚመኙትን ነገር አይደለም፤ የሆኑትን ነገር ነው እንጂ፡፡ ይህ ልንክደው የማንችል ሕግ ነው፡፡ ከጥቂት ገጠመኞች በስተቀር በጥቅሉ ስናየው ሰው አሁን ያለበት ቦታ የተገኘው በአጋጣሚ አይደለም፡፡ ባሰላሰላቸው ሃሳቦች፣ ባዳበረው እይታና በዚያ ተጽእኖ ምክንያት በወሰናቸው ውሳኔዎች ምክንያት ነው፡፡
ሰው በአመለካከቱ ወደመሆን ያመጣውን ሁኔታ ለማጥፋት ሲታገል የሚኖር ፍጡር ነው፡፡ “ሁኔታዬ መለወጥ አለበት” የሚል የማያቋርጥ ትግል ሲታገል ይታያል፡፡ ያንን ሁኔታ ወደመሆን ያመጣውን አመለካከቱንና እይታውን ግን መለወጥ አይፈልግም፡፡ ይህ ሁኔታውን ወደመኖር ያመጣው አመለካከቱ በውስጡ እንዳለ ላያስተውለው እንኳን ይችላል፡፡ አለማወቅ ግን ከውጤቱ እንዲያመልጥ ሊያደርገው አይችልም፡፡ አመለካከቱን ሳይለውጥ ሁኔታውን ለመለወጥ የሚያደርገው ጥረት ከንቱ ስለሆነ በሁኔታው እንደታሰረ ይኖራል፡፡ @youthkiller
2024/09/22 02:27:49
Back to Top
HTML Embed Code: