Telegram Web Link
💞🌺💞🌺💞🇪🇹#ፍቅር ብቻ🇪🇹🌺💞🌺💞🌺

በህይወት ጉዞ ላይ አንዳንድ ያላሰብካቸው ነገሮች ሊያጋጥሙ ይችላሉ። ለሩጫህ መሰናክል ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ አንተ ግን ተስፋ አትቁረጥ! እንደውም ለሩጫህ ሀይልና ብርታት አድርገህ ቁጠራቸው።

ይሄን እውነት መተግበር ስትጀምር ምንም አይነት ነገሮች በህይወትህ ላይ ቢያጋጥሙህ የብርታት እንጂ ተስፋ የመቁረጥ ስሜትን ከህይወትህ ላይ ጠራርገህ ታጠፋለህ። ስለዚህ ነገር ሁሉ ለበጎ ነው ብለህ አስብ።

💞 #መልካም ቀን

@youthkiller
#አጭር_ታሪክ በ #



አንድ በጣሙን ደሃ የሆነ ሰው ከሚስቱ ጋር ይኖር ነበር፡፡ አንድ ቀን ሚስቱ ጸጉሯን የምታበጥርበት ማበጠሪያ እንዲገዛላት ጠየቀችው፡፡ ባል በጣም አዘነ፡፡ በኪሱ አንዳችም ገንዘብ ስለሌለው እያዘነ እንደማይችል ገለጸላት፡፡ ሌላው ይቅርና በቅርቡ ማሰሪያው ለተበጠሰበት የእጅ ሰዓቱ እንኳ ማሰሪያ መግዛት ስላልቻለ በኪሱ ይዞት እንደሚዞር ማሰሪያው የተበጠሰውን ሰዓት እያሳየ እንደማይችል ገለጸላት፡፡ ሚስትም ነገሩን ተወችው፡፡ ባል ወደ ሥራ ሲሄድ በአንድ የሰዓት መሸጫ በኩል ሲያልፍ ወደ መሸጫው ገብቶ ማሰሪያው የተበጠሰውን ሰዓት ሸጠ፡፡ ሌላ ሱቅ ገባ፡፡ ለሚስቱ በጣም የሚያምር ማበጠሪያ ገዛ፡፡
ምሽት ላይ ከስራ ወደ ቤት ሲመለስ ዋንኛ ዕቅዱ ለሚስቱ እንዴት ያንን የሚያምር ማበጠሪያ እንደሚሰጣት ነበር፡፡ ሚስቱን ሲያያት ግን ደነገጠ፡፡ ያ የሚያምረው ዘንፋላ ጸጉሯ በአጭሩ ተቆርጧል፡፡ ባለማመን እንደተዋጠ የገዛላትን ማበጠሪያ ከቦርሳው አውጥቶ ወደ እሷ ቀረብ ሲል አይኗ በእንባ እንደረጠበ በእጆቿ መሃል የያዘችውን ነገር ተመለከተ የሰዓት ማሰሪያ፡፡ ሰዓቱን ሸጦ ማበጠሪያ እንደገዛላት ሁሉ፣ ለካንስ እሷም ያን ዘንፋላ ጸጉሯን አስቆርጣ ሸጣ የሰዓት ማሰሪያ ገዝታለት ነበር፡፡
አንዳቸው ለሌላኛቸው የከፈሉት የፍቅር መስዋእትነት ሁለቱንም ከልብ አስለቀሳቸው 🇪🇹
#ፍቅር_ያሸንፋል

@youthkiller
ሰውየው አዲስ ውብ መኪና ገዝቶ ጥልቅ ደስታ ውስጥ ነው። በዚህ መሃል የ4 አመቷ ህፃን
ካቻ ቢቴ (መፍቻ) አነሳችና የመኪናውን ክፍል በመጫር ታበላሸዋለች።
ይህን ስታደርግ አባቷ እየሮጠ መጥቶ ገፍትሮ ጣላት በጣም ንዴት ውስጥ ስለነበር በያዘው
ነገር እጇን ሳያስበው በሀይል መታት።
°
ለስላሳ የህፃን እጇ ምቱን መቋቋም አልቻለምና ጉዳት ደረሰባት።
ሀኪም ቤት ስትሄድ ዶክተሩ ጣቶቿ ስብራት ስለደረሰባቸው እንዲቆረጡ ያደርል።
°
አባት ልጁን ሊያይ ወደተኛችበት ክፍል በሩን ከፍቶ ሲገባ ህፃኗ እንዲህ አለችው "አባዬ
ጣቶቼ ድጋሚ መቼ ነው የሚያድጉት?"
አባት ልቡ ተሰበረ። ምንም መልስ ሳይሰጣት ተመልሶ ወጣ። መኪናውን እስኪደክመው
ደበደበው። በስራው ተፀፀተ።
ድንገት ቁጭ ሲል ህፃኗ መኪናው ላይ የጫረችውን ተመለከተው።
ፅሁፉ እንዲህ ይል ነበር " I love my dad "(አባቴን እወደዋለሁ)
°
ንዴትም ፍቅርም ኃይለኛ ናቸው።ህይወታችን ጣፋጭና ውብ እንዲሆን ፍቅርን ልንመርጥ
ይገባል።
ነገራቶችን - መኪና፣ ቤት ፣ ወርቅ ፣ ገንዘብ ከሰዎች ልናስበልጥ አይገባም። በዚህ ዘመን
ሰዎች ሁሉ ቁሳዊ እየሆኑ ነው። ወንድም ወንድሙን ለንብረት ሲል ይገድላል። ይህ ጥልቅ
አለማወቅ ነው። ብርስ ተመልሶ ይገኛል። ወንድም ይገኛል? እናት ትተካለች አባት ይተካል?
ጓደኛ በወርቅ ይቀየራል? በፍፁም አይቀየርም!
°
ከላይ ታሪኩ ላይ እንዳየነው አባትየው መኪናውን በቀላሉ ማስጠገን ይችል ነበር። የህፃን
ልጁን ጣቶች ግን መመለስ አይችልም።
ወዳጆቻችንን ልንንከባከባቸው ይገባል። ወዳጅ ማለት ውድ ከሚለው ቃል የተያያዘ ነው።
ቤተሰቦቻችን ጓደኞቻችን ዘመዶቻችን ውድ ናቸው። አንዴ ካስቀየምናቸው መልሰን ላናገኛቸው
እንችላለን። የሀገሬ ሰው "በእጅ ያለ ወርቅ እንደ መዳብ ይቆጠራል" ይላል። ወዳጆቻችን
አጠገባችን ስላሉ ብቻ ርካሽ አድርገን ልናያቸው አይገባም!! @youthkiller
❤️ፍቅር❤️
ስታፈቅር አንተነትህን የነበረህን በሀሪ ትተክ አዲስ ሰው ትሆናለክ ያፈቀርከው ሰው እየቀለደብክ ምንም ሳይመስልክ ዝም ብለክ ማፍቀርህን ትቀጥላለክ ያፈቀርከው ደግሞ መልሶ ሲያፈቅርክ አንተ ደሞ ማፍቀርህን ትተክ እሱን ማምለክ ትጀምራለክ ግን ይሄ የሚሆነው ከስንት አንዴ ነው አፍቅረክ ስትጎዳ ምላሽክ መልሶ መጉዳት ሳይሆን መልሶ ማፍቀር ይሁን ይሄ ነው ትክክለኛ ፍቅር ከፈጣሪ የተሰጠን ፀጋና በሀሪ ከእኔነት ከግላዊነት ስሜት ወጥቶ ስለሰው መኖር

@youthkiller
ኔልሰን ማንዴላ ፕሬዝደንት ከሆኑ በኋላ አንድ እለት ከቅርብ ጠባቂዎቻቸው ጋር ለምን
በእግራችን ወጣ ብለን አንንሸራሸርም በዛው ምሳ እንበላለን ብለዋቸው ተያይዘው ወጡ።
አንድ ሞቅ ያለ ሰፈር ሲደርሱ ምግብ ቤት አግኝተው ከጠባቂዎቻቸው ጋር ገብተው እንዳዘዙ
ከፊት ለፊታቸው ያዘዘው ምግብ የዘገየበት አንድ ሰው ስላዩ "ጥሩትና ከእኛ ጋር
ይብላ"ብለው አንዱን ወታደር ላኩ።
ሰውየው መጥቶ አብሯቸው ተመገበ።
እየተመገበ ሳለ እጁ ይንቀጠቀጣል ጨርሶ ሲሄድ ከጠባቂ ወታደሮቹ መሃል አንዱ
"ማዴባ የቅድሙ ሰውዬ ህመምተኛ ነበርኮ እጁ ይንቀጠቀጥ ነበር"ይላቸዋል
"አይደለም!ድሮ የታሰርኩበት እስር ቤት ጠባቂ ዘበኛ ነበር።ብዙ ግዜ ተደብድቤ ከቶርች
ስመለስ ውሃ ስለሚጠማኝ ውሃ እንዲሰጡኝ በጩኽት ስጠይቅ ይሄ ሰው በምላሹ ይመጣና
ፊቴ ላይ ሽንቱን ይሸናል።አሁን የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዝደንት ሆኜ ሲያየኝ የምበቀለው መስሎት
ፈርቶ ነው"
ሀገር በመቻቻል እና በፍቅር እንጂ በቂም በቀል አትገነባም።
ደካሞች ይቅርታን አያውቋትም ይቅርታ የጠንካሮች መለያ ባህርይ ናትና! @youthkiller
ምርጥ__የአፍሪካዊያን__አባባሎች "
……" ያለ ሰዓቱ የሚጮኽ ዶሮ መንጋቱን ሳይሆን
መታረዱን ያውጃል!!" (ኢትዮጵያዊያን)
1 "በችግር ጊዜ ብልህ ሰው ድልድይ ሲገነባ፤ ሞኝ
ደግሞ ግድብ ይገድባል!" (ናይጄሪያዊያን)
2 "ሀብት ሲጠቀሙበት እያለቀ ይሄዳል፤ ትምህርት ግን
እየተጠቀሙበት በሄዱ ቁጥር እየጨመረ
ይሄዳል!" (ታንዛኒያውያን)
3 "እውነቱን ላለማየት ዓይናችንን የምንጨፍን ከሆነ
ልንማር የምንችለው ከአደጋ ይሆናል!" (ኬንያዊያን)
4 "ከማሸነፍ ይልቅ በመሸነፍ ወቅት ብዙ ትምህርት
ይገኛል!" (ጋቦናዊያን)
5 "ሞኝ ጨዋታውን በሚለምድበት ጊዜ ተጨዋቹ
ይበተናል!" (አሻንቲዎች/ጋና)
6 "ምክር ልክ እንደ-እንግዳ ነው። የሚቀበለው ካገኘ
ያድራል፤ የሚቀበለው ካጣ ግን የዚያኑ ቀን ተመልሶ
ይሄዳል!" (ኮንጎዎች)
7 " አዋቂዎች በበዙበት ቦታ የአዳማጭ ዕጥረት
አለ!!" (የስህዋሊ አባባል)
8፦ ……" በአንበጣዎች መካከል የሚደረግ ፀብ ለከብቶች
መዝናኛ ነው!!" (ቦትስዋናዊያን)
9፦ ……" ትልቅ ወንበር ብቻውን ንጉሥ ሊያደርግ
አይችልም!!" (ሱዳናዊያን)
10፦ ……" በረሮ ዶሮዎችን የመምራት ሃሣብ ካለው፤
ቀበሮን ጠባቂው አድርጎ መቅጠር
ይኖርበታል!!" (ሴራሊዮናዊያን)
11፦ ……" ቤተሰብ ልክ እንደ-ደን ነው። ከሩቅ ሲያዩት
ጥቅጥቅ ያለ ሲሆን፤ ሲገቡበት ግን እያንዳንዱ የየራሱ
ቦታ አለው!!" (ዛየራዊያን)
12፦ ……" የገንዘብ ስልት ከጦር ስልት
ይበልጣል!!" (ካሜሮናዊያን)
13፦ ……" ገንዘብ ማውራት ባይችልም፤ ውሸትን እውነት
የማድረግ አቅም ግን አለው!!" (ደ/አፍሪካዊያን)
14፦……" ከገንዘብ ውስጥ ስንወጣ አዋቂ እየሆንን
እንሄዳለን!!" (አይቮሪኮስታዊያን)
15፦ ……" እስኪያወራ ድረስ እያንዳንዱ ሰው ውብ እና
ቆንጆ ነው!!" (ዙምባቤዎች)

~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ፔጁን ሼር፣……@youthkiller
❤️❤️❤️❤️❤️
ፋቅር ማለት ውበት አይደለም
ፍቅር ማለት ጥቅም ፋለጋ አይደለም
ፍቅር ማለት ዝሙት ፍለጋ አይደለም
ፍቅር ማለት በደስታ ጊዜ መተቃቀፍ አይደለም
ፍቅር ማለት ስለወደደን መውደድ አይደለም
ፍቅር ማለት ስላከበረን ማክበር አይደለም
ፍቅር ማለት ስላገዘን አንተም ቀን ጠብቀህ
ብድር መመለስ አይደለም
ፍቅር ማለት ከማንነት የፀዳ
ፍቅር ማለት ከማዳላት የራቀ
ፍቅር ማለት ከመፍረድ እጅን ያወጣ
በመከራም፣በሀዘንም፣በጭንቀት ም፣በደስታም፣
መተሳሰብ፣መተጋገዝ፣መረዳዳት
አንተ ያላገኝሀውን ነገር ሌሎች እንዲያገኙ መመኘት
፣ ጠላትህን መውደድ፣ስለወንድምህ እራስህን አሳልፈ
መስጠት የወንድምህን በደል መሸከም ባንተ እንዲፈፀም
የማትፈልገውን፡በሌላ አለመፈፀም
ተመልሶ በራስህ መፈፀሙ አይቀርም እና

እንዲህ እንድንሆን አምላክ ይርዳን፡፡
@youthkiller
አስተማሪ ታሪክ። ይነበብ👇

ከእለታት አንድ ቀን አንዲት ወጣት በትዳሯ ተስፋ ትቆርጣለች ። ባሏንም ለመግደል ታስባለች። ማታውን ስታሰላስል ታድርና ጧት ላይ እንዴት ማንም ሰው በማይጠራጠረውና እርሷንም ወንጀለኛ በማያስደርጋት መልኩ መግደል እንደምትችል ለመመካከር እናቷ ጋር ትሄዳለች።እናቷም "ማንም በማይጠረጥረው መንገድ እንድትገይው እረዳሻለሁ። ግን አንቺም ማድረግ ያለብሽ ነገሮች አሉ።
1ኛ መጀመሪያ ከባልሽ ጋር መታረቅ አለብሽ። ምክንያቱም ከሞተ በኋላ በፊት ፀብ ካልነበረሽ ማንም አይጠረጥርሽም
2ኛ ራሰሽን መጠበቅና ለባልሽ ቆንጆ ሆነሽ መታየት አለብሽ
3ኛ ጥሩ እንክብካቤና አድናቆት ስጪው። ያሰብሽውን እንዳይጠረጥር ያደርገዋል።
4ኛ ትዕግስተኛ ሁኚ።ፍቅር ሰጪው። ቅናት ቀንሺ።የሚናገረውን ጆሮ ሰጥተሽ አዳምጪው።
እነዚህን ነገሮች ማድረግ ትችያለሽ?"ብላ ጠየቀቻት።እናቲቱ። "ምንም ችግር የለውም። እማ ብቻ እርሱን የምገድልበትን መንገድ ንገሪኝ።" አለች ልጅቷ።
"እንደዚያ ከሆነ ምን ማድረግ እንዳለብሽ እነግርሻለሁ። በደንብ አድምጪኝ።"አለች እናት።ልጅቷም በአትኩሮት መስማት ጀመረች።
"ይህንን መርዝ በምግቡ ውስጥ በየቀኑ ትንሽ ትንሽ ጨምሪ ቀስ በቀስ እያዳከመው ይገድለዋል።" አለቻት። ልጅቷም መርዙን ይዛ በደስታ ቤቷ ሄደች። በተነገራት መሰረትም ለባሏ መስጠት ጀመረች።
ከወር በኋላ እንደገና እያለቀሰች እናቷ ጋር መጣች። "እማ አሁን ባለቤቴን መግደል አልፈልግም።በጣም ተለውጧል። እንደያውም ለርሱ ያለኝ ፍቅር ከቀን ቀን እየጨመረ ነው።እባክሽ እማ መርዙ እንዳይገድለው ምን ላድርግ?ያለ እርሱ መኖር አልችልም። አለች ስቅስቅ ብላ እያለቀሰች።
እናትም "አይዞሽ ልጄ አታልቅሺ የሰጠሁሽ መርዝ አልነበረም።የደቀቀ ስኳር ነበር። በርግጥ መርዝ የነበርሽው አንቺ ነበርሽ። ያ ነበር ባለቤትሽን ቀስ በቀስ እየገደለው የነበረው። አየሽ አይደል ፍቅርና እንክብካቤ ስትሰጪው እንዴት አይነት መልካም ሰው እንደሆነ።ስለዚህ ከዚህ ተምረሽ ለባልሽ መልካም ሚስት ሁኚለት።"ብላ ነገረቻት።
የኔ እህት ወንድ ልጅ የፈለገ አረመኔ ቢመስል ልቡ ገራገር ነው በፍቅር ልታሸንፊው ትችያለሽ። መልካም ሚስት ሁኚለት። ፍቅር ሁሌም ያሸንፋል ሸር ላይክ እናድርግ ላላነበበቡ እንዲደርስባቸው❤️
@youthkiller
ምክር ለወዳጅ

👉🏾 ሁሉን ወሬ ላውራ አትበል ፣ የደበቁህን ምስጢር አታውጣጣ ፣ የሰማኽውን ወሬና የተገለጠልህን ምስጢር ምን መፍትሔ ሰጠኸውና ? ያየህውን ሥራ ሁሉ እሰራለሁ የሰማኸውን ትምህርት ሁሉ እማራለሁ አትበል ። ይህ የተሰወረው የቅንዓት ጠባይ ነውና ሁሉን ልያዝ ማለትም ዝንጉ አድረጎ እንዳያስቀርህ ሁሉም ውስጥ ልኑር አትበል ።

👉🏾 👉🏾 እወድሃለሁ ብለህ የምትናገረውን ቃል ውለታ አታድርገው ፣ መውደድህን የምትናገረው እንወድሃለን እንዲሉህ አይሁን ፣ ሠላም ያለው አፍቃሪ የራሱን ፍቅር ያለ ምክንያት መፈፀም የሚችል ብቻ እንደሆነ እወቅ ። መወደድህን ለመስማት አትጠብቅ ።

👉🏾 👉🏾 የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን እርዳቸው ።

👉🏾 👉🏾 ዛሬ የመዝራት ዘመንህ ነገ መከርህ ነውና በእምነት እውነትን ዝራ ፤ በምታውቀው ቦታ ላይ አገልጋይ በማታውቀው መልካም ተግባር ላይ ደጀን ሁን ፤ በቦታህ መምህር ያለቦታህ ተማሪ
ሁን ፤ ክብሩ እንዳይቀንስብህ ከዕቃ ትምክህት ፣ ከዕውቀት ሙግት ራቅ ።

👉🏾 👉🏾 ቆንጆዎች ቁንጅናቸው ሁሉን የሚተካ እየመሰላቸው ከዕውቀትና ከትሕትና ይርቃሉ ። ሁሉንም ሰው በመልካቸው የሚማርኩት ስለሚመስላቸው ኩሩና ተንኮለኞች ይሆናሉ ። አንተ ግን ቆንጆ ወዳጅን እንጂ ቆንጆ ቁመናን አትሻ ፤ ቆንጆ ትዳርን እንጂ ቆንጆ ሴትን አትመኝ ፤ የላይ ነገር ከንቱና ኀላፊ ነውና በሚፈርስ አካል ፣ ኑሮ በሚለውጠው መልክ አትደለል ።

👉🏾 👉🏾 ቂም አፍን የሚያመር ፣ ልብን የሚያነቅዝ ፣ ተግባርን የሚያልፈሰፍስ ነውና ለበደለህ ሰው ቅያሜህን ግለጥለት ፤ ቂመኝነት በክፉ መሸነፍ እንጂ ጀግንነት አይምሰልህ ።

መልካም ዕሁድ
@youthkiller
እራስክን ከማንም ጋር አታወዳድርው
የሁሉም መክሊቱ የተለያየ ነው እና
በሰው ሳይሆን በፈጣሪ ተደገፍ
እሱ አይጥልህምና
ውሻ 3 ቀን ብታበላው 3 አመት ያስታውስሀል
ሰው ግን 3 አመት ብታበላው በ3 ቀን ይርሳሀል
# ወዳጀ
እራስክን ከማንማ ጋር አታወዳድር፡፡ ይህን ባደረክ ጊዜ እራስክን በራስህ እንደሰደብክ
ቁጠረው፡፡
ቁልፍን ያለመክፈቻ ማንም እንደማይሰራ ሁሉ ፈጣሪም መፍትሄ የሌለው ችግር
እንዲገጥምን አይፈቅድም፡፡
ደስታህን ከራስህ ባራቅህ ጊዜ ሕይዎት በአንተ ላይ ትስቃለች፡፡ ደስተኛ በሆንክ ጊዜ
ሕይዎት ፈገግታዋን ትለግስሃለች፡፡ ሌሎች እንዲደሰቱ ምክንያት በሆንክ ጊዜ ግን ሕይዎት
የከበረ ሠላምታዋን ታቀርብልሃለች፡፡
ማንኛውም ስኬታማ ሰው ከበስተጀርባው አስቸጋሪ ታሪኮች እንዳሉት ሁሉ ማንኛውም
የችግር(አስቸጋሪ) ታሪክ መጠናቀቂያው ስኬት ይሆናል፡፡ ስለሆነም ችግሩን ተቀበልና
ለስኬት ተዘጋጅ፡፡
የሌሎችን ስህተት ለመተቸት በጣም ቀላል ነው፡፡ ከባዱ ነገር የእራስን ስህተት መረዳቱ
ላይ ነው፡፡
የተፈጠረልህ መልካም አጋጣሚ ባመለጠህ ጊዜ እዛው ባለህበት ቁመህ አይንህን
በእንባ አትሙላ፡፡ ቀጣዩንና የተሻለውን መልካም አጋጣሚ እንዳታይ ይከልልሃልና፡፡
ለችግር ፊትን ማዞር ችግሩን አይቀይረውም ችግሩን መጋፈጥ እንጅ፡፡ በሌሎች ቅሬታን
ከማሰማት እራስን ለውጦ ሠላምን መግዛት፡፡
ስህተት ስህተቱ በተፈጠረበት ወቅት ስሜትን ይጎዳል፡፡ ከዓመታት በኋላ የስህተቶች
ድምር የሚፈጥረውና ወደ ስኬት የሚያመራው ከስህተት መማር ተሞክሮ(ልምድ)
እንለዋለን፡፡
የቀለጠ ወርቅ ጌጣጌጥ እንደሚሆነው፣
አንተም በብዙ ችግር ባለፍክ ቁጥር አንተነትህ እያደገ መሆኑን አትርሳ፡፡ በመሆኑም ስትሸነፍ
ጠንካራ ስታሸንፍ የተረጋጋ ሁን፡፡
@youthkiller
መልካም_ሚስት
ብዙ አይነት እድለኛ ሰዎች ቢኖሩም ለኔ ግን #መልካም_ሚስት እንዳለችው ሰው የታደለ
የለም ። #ከላይ_የተፃፈች መልካም ሚስት ካለችህ በየትኛውም ሁኔታ ላይ ሁነህ እንኳ
# ሙሉ_ሰው ነህ ። የሂወት # ውጣ_ውረድ እና #ጉድለት ላንተ ምንም ናቸው ። ወጥተህ
እስክትገባ # በናፍቆት የምትጠብቅህ ከውጭ ስትመጣ ደሞ በስስት እያየች # ስቃ
የምትቀበልህ ሳታወራ # የምትረዳህ መልካም ሚስት ስትኖርህ # ችግርህ ድሎት ፣
# መድከምህ እረፍት፣ # መክሰርህ ትርፍ ፣ # ማጣትህ ማግኛት ፣ #ብሶትህ ደሞ ደስታ ነው
በቃ መልካም ሚስት ጎንህ ካለች ከቤት ውጭ ስቱል እንኳ የሚያጋጥሙህን # ጥሩ ያልሆኑ
አጋጣሚወችን በቅፅበት # ረስተህ ወደ አዲስ #የእፎይታ_ስሜት ውስጥ ለመግባት
# ፊቷን_ማየት ብቻ በቂህ ነው መልካም ሚስት በሂወትህ #ትልቅ_ዋጋ ከምሰጣቸው
ነገሮች ውስጥ አንዱ የሆነውን #ልጅ ትወልድልህና #አይንህን_ባይንህ ታሳይሀለች ፣ አለፍ
ሲል ደሞ የወለደችልህን ልጆች በመልካም ባህሪዎቿ እየኮተኮተች #በፍቅር አሳድጋ
ቤተሰባቸውን እና ማህበረሰቡን የሚያከብሩ # ለስምህ_መጠሪያ የሚሆኑ ጥሩ ልጆች
ባለቤት ታደርግሀለች፣ #ቤተሰቦችህን እና #ጓደኞችህን ስለምትወድልህ ከነሱ ጋር በቂ የሆነ
ሰአት ለመስጠትም ሆነ ማደረግ ያለብህን ለማድረግ ስለማትቸገረ የቤተሰብህን
# ሀቅ_በመጠበቅ በኩል አትዘናጋም ፣ # ማህበራዊ_ሂወት ላይ ያለህ ተሳትፎም
አይቆረፍድብህም እሷ ከምሰጥህ # ፍቅር እና # ደስታ በመነሳት በምትኩ አንተ የልጆችህን
እና የሷን ሀቅ ለመጠበቅ ብለህ በምታደርጋቸው # የመልካም_ነገር_ሩጫወች #ከፈጣሪህ
ዘንድ ትልቅ #ደረጃ ታሰጥሀለች።
መልካም ሚስት #የእናት_የአባትህን #የእህት_ወንድምህን ቦታ ሳይቀር ተክታ በመያዝ
ብቻዋን ሁና ነገር ግን #ባለ_ሙሉ_ቤተሰብ እንደሆንክ እንዲሰማህ ታደርግሀለች።
#መልካም_ሚስት_ካለችህ_ሁለም_ነገር_አለህ የመልካም ሚስት #ደረጃዋ በቀላሉ
ተዘርዝሮ የሚወራ እና ተቆጥሮ የሚያልቅ ነገር አይደለም ለዛም አይደል
#መልካም_ሚስት_ከፈጣሪ_ናት የሚባለው ። #ወንዶች መልካም "ባል" አድርጎን
መልካም ሚስት ይሰጠን ዘንድ #ሴቶች ደሞ "ሚስት" ብቻ ሳይሆን #መልካም_ሚስት
ሁናችሁ "መልካም ባል" ታገኙ ዘንድ ምኞቴ ነው።
#እናንተም_የምኞታችሁ_ይሳካላችሁ. @youthkiller
የህይወት ትርጉም

አንድን ነገር አንተ አትፈልገውም ማለት ነገሩ በራሱ መጥፎ ነው ማለት አይደለም። ነገሩ መጥፎ የሆነው ለአንተ ስሜት እንጂ በራሱ ባህሪ ምንም ነው። አንተ ስለነገሩ የሚሰማህ የነገሩን ባህሪ አያመላክትም። መኪና ሰው ስለገጨ መጥፎ ነው የሚል ስሜት ሊሰማህ ይችላል። ነገር ግን የመኪናው እውነታ ሌላ ነው። ስለዚህ አንተ ስለነገሩ በሚሰማህ መልኩ ሌሎችም እንደሰማቸው ማድረግ ተገቢነት የለውም። አንተ ስለነገሩ የሚሰማህ መጥፎ ስሜት አንተ የሚሰማህ የራስህ አመለካከት እንጂ የነገሩን የመጥፎነት ባህሪ አያመላክትም። ስለዚህ አንተ የሚሰማህን ስሜት ሌሎችም በተመሳሳይ መልኩ እንዲሰማቸው አትጠብቅ። በጋራ ሲኖር የህይወት ትርጉሙ ያለው በአንድ ነገር ላይ የሚፈጠር የስሜት ልዩነት በመሆኑ በማንኛውም ጉዳይ አንተ እንደሚሰማህ አንድ ስሜት መፍጠር አይቻልም።
በአለማችን ላይ ጥሩ እና መጥፎ የሚባል ነገር የለም። ልዩነቱ የመጣው ከነገሩ ተፈጥሯዊ ባህሪ ሳይሆን ሰዎች ከነገሩ ጋር በሚያደርጉት መስተጋብር በተፈጠረ የስሜት ልዩነት ነው።

የህይወት ትርጉም የአንፃራዊ ስሜት ውጤት ነው። እውነትን መስሎ የኖረ እንጂ ሆኖ የኖረ የለም። አንተ እግርህን ለመራመድ ብቻ ስለምትጠቀምበት ሌላው እግር ኳስ ስለተጫወተበት ስህተት ነው ማለት አይደለም። የአንተ የህይወት ትርጉም የአንተ ነው። የኔ ደሞ የራሴ ነው። ስለዚህ አንተ ስለነገሩ የሚሰማህን መጥፎ ስሜት ትክክል ነው ብለህ እንደምታምን ሁሉ ሌሎችም ስለነገሩ የሚሰማቸው መልካም ስሜት ለራሳቸው ትክክል ነው።

ሁሉ በአንዱ፣ አንዱም በሁሉ በመሆኑ በልዩነት ኖሮ በአንድነት መቆም ትልቁ የህይወት መርህ ነው!!
@youthkiller
በማግባት ውስጥ የሚገኙ ጠቀሜታዎች
1. ለወሲብ እርካታ
የሰዎች የወሲብ ግንኙነት እንደሚያምኑት እሴት የተለያየ ቢሆንም ከፍተኛ የሆነ የወሲብ
እርካታ የሚገኘው በጋብቻ በተጣመሩ ጥንዶች መካከል ሲፈጸም ነው፡፡ ሳይጋቡ ከሚፈጸም
ወሲብ ይልቅ በጋብቻ ግንኙነት ውስጥ የሚኖር የወሲብ እርካታ የበለጠ እንደሆነ ጥናቶች
ይጠቁማሉ፡፡ በዘላቂ የጋብቻ ግንኙነት ውስጥ የሚፈጸም ወሲብ ከስሜትም አልፎ
ሁለንተናዊ ህይወትን የማርካት ኃይል አለው፡፡ ምክንያቱም ወሲብ የግንኙነቱ መገለጫ
ተደርጎ ስለሚታሰብና በባልና ሚስት መካከልም የመተማመኑና የመተዋወቁም መጠን
ከፍተኛ በመሆኑ ነው፡፡ ይህ ማለት ግን ያገቡ ሰዎች ሁሉ መልካምና አርኪ የወሲብ ግንኙነት
ይኖራቸዋል ማለት አይደለም፡፡ መልካም ወሲብ ትምህርት፣ ክህሎት፣ መሰጠት፣
መተማመንና ግልጽነትን ስለሚጠይቅ በማግባት ብቻ የሚገኝ ውጤት አለመሆኑ መታወቅ
አለበት፡፡
2. ለሁለንተናዊ ጤና
ማግባት ለአካላዊና የስነ-ልቦናዊ ጤንነት አዎንታዊ አስተዋጽኦ አለው፡፡ በመልካም የጋብቻ
ግንኙነት ውስጥ በጥንዶች መካከል ሁሉ ነገር መደጋገፍ ስለሚኖር አንዱ ብቻውን
ከሚጨነቅ ለሌላው ጭንቀቱን ያጋራል፡፡ የጭንቀት መቀነስ ደግሞ ለስነ-ልቦና ጤንነት
እንዲሁም ሰውነት በሽታን መቋቋም የሚያስችል ኃይል እንዲኖረው ያግዛል፡፡ በጋብቻ
ግንኙነት ውስጥ ያሉ ጥንዶች ካላገቡ ሰዎች ይልቅ የሚኖራቸው የህይወት ዘይቤ ለምሳሌ
አመጋገብ ስርዓት ያለውና በጥንቃቄ የሚሠራ ይሆናል፡፡ በአብዛኛው እቤት የሚዘጋጅ ምግብ
በመሆኑ የምግቡን ዓይነትና አሠራር ለጤንነት በሚያመች መንገድ የማዘጋጀት ዕድላቸው
ከፍ ያለ ነው፡፡ ማግባት ሰዎች ስርዓት ያለው የህይወት ዘይቤ እንዲከተሉ ይረዳል፡፡ ያገቡ
ሰዎች ለአልኮል መጠጥና ለሌሎች ሱስ አምጪ ነገሮች የመጋለጣቸው ዕድል ካላገቡት
ሰዎች ያነሰ ነው፡፡ ያገቡ ሰዎች ከኃላፊነትና ተጠያቂነት የተነሣ ለአልኮል፣ ለሲጋራና ሌሎች
አደንዛዥ ዕፆች በቀላሉ የተጋለጡ አይሆኑም፡፡ ያገቡ ሰዎች ካላገቡ ሰዎች የበለጠ ረጅም
ዕድሜ ይኖራሉ፡፡ ያላገቡ ሰዎች ህይወታቸውን ለአደጋ የሚያጋልጡ ነገሮችን የማድረግ
ዕድላቸው ከፍ ያለ ነው፡፡ ስለዚህ ቶሎ ይሞታሉ፡፡
3. ልጆች ወልዶ ለማሳደግ
ሰዎች ሳያገቡ ልጆችን መውለድ እንደሚችሉ የታወቀ ነው፡፡ ሆኖም ሳያገቡ ልጆችን መውለድ
ቢቻልም ነጠላ ሆኖ ልጆችን ማሳደግ አስቸጋሪ ከመሆኑም በላይ በልጆቹ የስነ-ልቦና
ህይወት ላይ የሚኖረው ውጤት አሉታዊ ነው፡፡ ልጆች በሁለንተናዊ ህይወታቸው በመልካም
ሁኔታ ለማደግ ምቹ የሆነው አውድ አባትና እናት ተጋብተው በአንድ ላይ ሲኖሩ ነው፡፡
4. ሃብት ለማፍራት
አንዳንድ ሰዎች ሃብት ለማፍራት ሳያገቡ መኖር እንደሚሻል ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡ ይህ
ትክክል አይደለም፡፡ ሃብት ለማፍራት ማግባት የተሻለ ዕድል ይሰጣል፡፡ አንድ ሰው ለብቻው
ከሚሠራ ይልቅ ባልና ሚስት አንድ ላይ ሆነው ኃይላቸውን፣ ዕውቀታቸውን፣ ልምዳቸውን፣
ክህሎታቸውን አስተባብረው ቢሰሩ የበለጠ ውጤታማ መሆን ይችላሉ፡፡ ከአንድ አእምሮ
ሁለት አእምሮ የተሻለ ውጤት ይኖሯል፡፡ በእርግጥ በዓለም ላይ የታወቁ ሃብታም ሰዎችን
ስንመለከት ብዙዎቹ ያገቡና ትዳር ያላቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ማግባት ለብልጽግና አስተዋጽኦ
አለው፡፡ ከደመወዝም አንፃር ሲታይ ያገቡ ሰዎች ካላገቡ ሰዎች በላይ አማካይ ደመወዝ
እንደሚያገኙ በአንዳንድ ስፍራዎች የተደረጉ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡
5. ማኅበራዊ ከበሬታን ያስገኛል
በአብዛኛው ማግባት የተጋቢዎችን ማኅበራዊ ከበሬታ እንዲጨምር ያደርጋል፡፡ በኅብረተሰብ
ውስጥ ላገቡ ሰዎች የሚሰጥ አክብሮት ላለገቡ ሰዎች ከሚሰጠው ይበልጣል፡፡ ስለዚህ ያላገባችሁ በቶሎ መሰብሰብ ነው የሚያዋጣው share መረጋቹን አትርሱ @youthkiller
@youthkiller


ኔልሰን ማንዴላ ፕሬዝደንት ከሆኑ በኋላ አንድ ቀን ጠባቂዎቻቸውን ለምን በእግራችን ወጣ ብለን አንንሸራሸርም በዛው ምሳ እንበላለን ብለዋቸው ተያይዘው ወጡ።

አንድ ሞቅ ያለ ሰፈር ሲደርሱ ምግብ ቤት አግኝተው ከጠባቂዎቻቸው ጋር ገብተው እንዳዘዙ ከፊት ለፊታቸው ያዘዘው ምግብ የዘገየበት አንድ ሰው ስላዩ "ጥሩትና ከእኛ ጋር ይብላ"ብለው አንዱን ወታደር ላኩ።

ሰውየው መጥቶ አብሯቸው ተመገበ። ሰውዬው እየተመገበ እጁ ይንቀጠቀጥ ነበር። ጨርሶ ሲሄድ ከጠባቂ ወታደሮቹ መሃል አንዱ "ማዴባ የቅድሙ ሰውዬ ህመምተኛ ነው መሰለኝ ። እጁ ይንቀጠቀጥ ነበር"ይላቸዋል ማዴባም "አይደለም!ድሮ የታሰርኩበት እስር ቤት ጠባቂ ዘበኛ ነበር ። ብዙ ግዜ ተደብድቤ ከቶርች ስመለስ ውሃ ስለሚጠማኝ ውሃ እንዲሰጡኝ በጩኽት ስጠይቅ ይሄ ሰው በምላሹ ይመጣና ፊቴ ላይ ሽንቱን ይሸናብኝ ነበር" አሁን ፕሬዝደንት ሆኜ ሲያየኝ የምበቀለው መስሎት ፈርቶ ነው" ሀገር በመቻቻል እና በፍቅር እንጂ በቂም በቀል አትገነባም ።

ደካሞች ይቅርታን አያውቋትም !!!
ይቅርታ የጠንካሮች መለያ ባህርይ ናትና!

ቅን ሰው ከሆኑ ሼር ያድርጉ
ይቀላቀሉን
@youthkiller
አስተማሪ ታሪክ

ልብ ብለው ያንብቡ።

በጣም ሚዋደዱ ሁለት ፍቅረኞች ለመጋባት
ይወስናሉ፡፡ ቀለበት ሊያስሩ ጥቂት ወራት
ሲቀራቸዉ ልጅቱ የመኪና አደጋ ይደርስባት እና
ፊቷ ሙሉ በሙሉ ተበላሸ፡፡ "ቀሪ ሂወቴን መልከ-ጥፉ እና አስጠሊታ ሁኘ መኖሬ ግድሁኗል፡፡ ከእንግዲህ ላንተ የምገባ ሴት አደለሁም፡፡ ሌላ ቆንጆ ወጣት ሴት ፈልገህ አግባ፡፡" ብላ ለልጁ ፃፈችለት፡፡ ከጥቂት ቀናት በኋካ እንዲህ ሚል ደብባቤ ደረሳት "ዉዴ ማፈር ያለበት ሰዉ ካለ እኔ ነኝ ማፈር ያለብኝ፡፡ በአይን ህመም ምክንያት ማየት እንደማልችል ዶከረተር ነግሮኛል፡፡ እንዲህ ሁኘ የ ምታገቢኝ ከሆነ እኔ አንቺን ለማግባት እፈልጋለሁ፡፡" ወዲያዉ ተጋቡ፡፡ ልጁ ጭራሽ ማየት አይችልም ነበር፡፡

ለ 20 አመታት በፍቅር በደስታ በመተሳሰብ ኖሩ፡፡
እሷ የአይኑ ብርሃን ሁና እየመራችዉ ፍቅራቸዉ ፈክቶ በሃሴት ኖሩ፡፡ ከ20 አመት ቆይታ በኋላ ሴቷ በጠና ታመመች፡፡ በባዶ ጨለማ ትቸዉ ልሞት ነዉ ካለኔ ማን አለዉ እያለች ትጨነቅ ነበር፡፡ ሞት አይቀርምና ወደማይቀርበት አለም ሄደች፡፡ ሚስቱ የሞተችበት እለት ሰዉየዉ አይኑን ገልጦ ማየት ጀመረ፡፡ ሰዉ ሁሉ ተገረመ "አይነ ስዉር አልነበርኩም የተበላሸዉን ፊቴን አየብኝ ብላ እንዳትሳቀቅ ብየ ነዉ አይነ ስዉር መስየ የኖርኩት፡፡" አለ፡፡ የታሪኩ "ሞራል" እዉነተኛ ፍቅር አካላዊ ዉበትን ሳይሆን ሚመለከተዉ ዉስጣዊ ዉበትን ነዉ፡፡ ምክንያቱም እዉነተኛ ፍቅር በአይን ሳይሆን በልብ ነዉ ሚመለከተዉ፡፡


@youthkiller
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የፈቃድ ባርነት

የባርነትን ታሪክ ለሚያውቀው፤ ቢደበዝዝ እንኳን የማይጠፋ ቁስል ነው። እኔ እንኳን በዚህ ፅሁፍ ለማንሳት የፈለግኩት የጥቁሮችን የባርነት ታሪክ ሳይሆን፤ እኔ እና እናንተ ያለንበትን የፈቃድ ባርነት ልብ እንድንለው ስለፈለግኩኝ ነው። የኛ ባርነት፤ ጥቁሮቹ ላይ እንደተፈፀመው ያለፈቃድ የሆነ ግፍ ሳይሆን፤ በገዛ ፈቃዳችን የተዘፈቅንበት ባርነት ነው።

ጨቋኞቻችን ቢለያዩም እንኳን፤ አብዛኛዎቻችን የፈቃድ ባሪያዎች ሆነን፤ የምንፈልገውን ሳይሆን የማንፈልገውን ኑሮ እንኖራለን። ይህ ጥሪ የሃዘን፤ የጭንቀት፤ የፍርሃት፤ የቅናት፤ የስንፍና፤ የመጥፎ አስተሳሰብ፤ የሱስ ……..የፈቃድ ባሪያዎች ለሆንን ሁሉ…..የነፃነት አዋጅ አብረን እንድናውጅ የተደረገ ጥሪ ነው። ምን አልባት ባሪያ መሆናቸውን የማያውቁ ብዙ የፈቃድ ባሪያዎች ሞልተዋል።

የፈቃድ ባሪያዎች ነን ያልኩት፤ ሁሉም ሰው የመደሰት እና የሚፈልገውን ኑሮ የመኖር መብትም ሆነ አቅም አለው ብዬ ስለማስብ ነው። ችግር ፈተና እና ውድቀት እርግጥም የሚገጥሙን ውጊያዎች ናቸው። የፈቃድ ባሪያዎች የምንሆንላቸው ከጦርነቱ በኋላ ጦር ሜዳውን ለቀን መውጣት ሲሳነን ነው።

አይምሮዋችን ያለውን ሃይል ብዙዎቻችን አናውቀውም እንጂ፤ አለምን አሁን ያለችበት ቦታ እንድትደርስ ያደረጋት ምንም ሳይሆን የሰው ልጅ አይምሮ ነው። ይህንን ማድረግ የሚቻለው አይምሮ አንተን ከማትፈልገው ግንኙነት፤ ከምጠላው ስራ፤ ከሚጨቁንህ ሱስ፤ ከሚረብሽህ ጭንቀት ማስወጣት የማያስችል ይመስልሃል? አሁን ያለንበት ማንኛውም አይነት ባርነት……በፈቃዳችን የተዘፈቅንበት ነው። የነፃነት ካቴናችንን በጉያችን ይዘን የነፃነት ያለህ እያልን ይምንዞር ምስኪን ባሪያዎች ነን………ደስተኛ ሰዎች ደስተኛ ሆነው ተፈጥረው ሳይሆን፤ ያሉበትን ሁኔታ መለወጥ እንደሚችሉ በማመናቸው ነው።

የማትፈልገውን ነገር እያሰብክ ከመብከንከን ይልቅ፤ አትኩሮትህን መፍትሄው ላይ ብታደርግ ብዙ ነገሮችን መለወጥ ይቻልሃል። ዛሬም ወደፊትም ከባድ ነገሮች ያጋጥማሉ፤ ተፋለማቸው፤ አንዳንዴ ታሸንፋለህ፤ አንዳንዴ ትሸነፋለህ፤ ውጊያው ሲያበቃ ግን፤ ሽንፈትህን እያሰብክ የፈቃድ ባሪያ ከመሆን ይልቅ፤ ለሌላ ውጊያ እራስህን ለማዘጋጀት ጊዜ ውሰድ። እመን የምትፈልገውን ነገር ሁሉ ማግኘት ትችላለህ፤ በመጀመሪያ ግን ለህይወትህ ሃላፊነት ውሰድ። ጊዜህን እራስህ ላይ አጥፋ። አንብብ፤ ጆሮህን ከመጥፎ ዜናዎች አርቅ፤ እራስህን ይቻላል በሚል
መፈክር ለመኖር አስልጥነው። ይህንን ጥሪ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ሁሉ……..ከፈቃድ ባርነት ለመውጣት ነገ ሳይሆን ዛሬ እንንቃ!

@youthkiller
አእምሮህን እንደ አንድ የአትክልት ስፍራ ተመልከተው፡፡ አንድ የአትክልት ስፍራ የተለያዩ አትክልቶችን የሚያበቅለው ስለዘራህበት ብቻ አይደለም፡፡ ብትዘራበትም ባትዘራበትም አረምም ሆነ “ወፍ-ዘራሽ” ነገሮችን ማብቀሉ አይቀርም፡፡ ጥሩ ዘርን ከዘራህበት የዘራህበትን ጥሩ ዘር ያበቅላል፡፡ መጥፎ ዘር ከዘራህበትም እንዲሁ፡፡ ምንም ዘር ካልዘራህበት ደግሞ ይህንና ያንን ማብቀሉ አይቀርም፡፡ አእምሮህም እንዲሁ ነው፡፡ በገጠመኞችና በተለያዩ ሁኔታዎች የሚገቡ “ወፍ-ዘራሽ” ሃሳቦችን ማብቀሉ ካልቀረ፣ መልካም ነገርን እየዘራህበትና ጥሩ ጥሩውን እያሰብክ ጣፋጭ ሁኔታዎች መፍጠር ትችላለህ፡፡
በተፈጥሮአችን ወደ እኛ የምንስበውም ሆነ ራሳችንን ተስበን የምንገኝለት ሁኔታ ከአመለካከታችን ጋር ዝምድና አለው፡፡ ስለዚህም፣ ሰዎች ወደ እነሱ የሚስቡት የሚመኙትን ነገር አይደለም፤ የሆኑትን ነገር ነው እንጂ፡፡ ይህ ልንክደው የማንችል ሕግ ነው፡፡ ከጥቂት ገጠመኞች በስተቀር በጥቅሉ ስናየው ሰው አሁን ያለበት ቦታ የተገኘው በአጋጣሚ አይደለም፡፡ ባሰላሰላቸው ሃሳቦች፣ ባዳበረው እይታና በዚያ ተጽእኖ ምክንያት በወሰናቸው ውሳኔዎች ምክንያት ነው፡፡
ሰው በአመለካከቱ ወደመሆን ያመጣውን ሁኔታ ለማጥፋት ሲታገል የሚኖር ፍጡር ነው፡፡ “ሁኔታዬ መለወጥ አለበት” የሚል የማያቋርጥ ትግል ሲታገል ይታያል፡፡ ያንን ሁኔታ ወደመሆን ያመጣውን አመለካከቱንና እይታውን ግን መለወጥ አይፈልግም፡፡ ይህ ሁኔታውን ወደመኖር ያመጣው አመለካከቱ በውስጡ እንዳለ ላያስተውለው እንኳን ይችላል፡፡ አለማወቅ ግን ከውጤቱ እንዲያመልጥ ሊያደርገው አይችልም፡፡ አመለካከቱን ሳይለውጥ ሁኔታውን ለመለወጥ የሚያደርገው ጥረት ከንቱ ስለሆነ በሁኔታው እንደታሰረ ይኖራል፡፡ @youthkiller
አስተማሪ ታሪክ። ይነበብ👇

ከእለታት አንድ ቀን አንዲት ወጣት በትዳሯ ተስፋ ትቆርጣለች ። ባሏንም ለመግደል ታስባለች። ማታውን ስታሰላስል ታድርና ጧት ላይ እንዴት ማንም ሰው በማይጠራጠረውና እርሷንም ወንጀለኛ በማያስደርጋት መልኩ መግደል እንደምትችል ለመመካከር እናቷ ጋር ትሄዳለች።እናቷም "ማንም በማይጠረጥረው መንገድ እንድትገይው እረዳሻለሁ። ግን አንቺም ማድረግ ያለብሽ ነገሮች አሉ።
1ኛ መጀመሪያ ከባልሽ ጋር መታረቅ አለብሽ። ምክንያቱም ከሞተ በኋላ በፊት ፀብ ካልነበረሽ ማንም አይጠረጥርሽም
2ኛ ራሰሽን መጠበቅና ለባልሽ ቆንጆ ሆነሽ መታየት አለብሽ
3ኛ ጥሩ እንክብካቤና አድናቆት ስጪው። ያሰብሽውን እንዳይጠረጥር ያደርገዋል።
4ኛ ትዕግስተኛ ሁኚ።ፍቅር ሰጪው። ቅናት ቀንሺ።የሚናገረውን ጆሮ ሰጥተሽ አዳምጪው።
እነዚህን ነገሮች ማድረግ ትችያለሽ?"ብላ ጠየቀቻት።እናቲቱ። "ምንም ችግር የለውም። እማ ብቻ እርሱን የምገድልበትን መንገድ ንገሪኝ።" አለች ልጅቷ።
"እንደዚያ ከሆነ ምን ማድረግ እንዳለብሽ እነግርሻለሁ። በደንብ አድምጪኝ።"አለች እናት።ልጅቷም በአትኩሮት መስማት ጀመረች።
"ይህንን መርዝ በምግቡ ውስጥ በየቀኑ ትንሽ ትንሽ ጨምሪ ቀስ በቀስ እያዳከመው ይገድለዋል።" አለቻት። ልጅቷም መርዙን ይዛ በደስታ ቤቷ ሄደች። በተነገራት መሰረትም ለባሏ መስጠት ጀመረች።
ከወር በኋላ እንደገና እያለቀሰች እናቷ ጋር መጣች። "እማ አሁን ባለቤቴን መግደል አልፈልግም።በጣም ተለውጧል። እንደያውም ለርሱ ያለኝ ፍቅር ከቀን ቀን እየጨመረ ነው።እባክሽ እማ መርዙ እንዳይገድለው ምን ላድርግ?ያለ እርሱ መኖር አልችልም። አለች ስቅስቅ ብላ እያለቀሰች።
እናትም "አይዞሽ ልጄ አታልቅሺ የሰጠሁሽ መርዝ አልነበረም።የደቀቀ ስኳር ነበር። በርግጥ መርዝ የነበርሽው አንቺ ነበርሽ። ያ ነበር ባለቤትሽን ቀስ በቀስ እየገደለው የነበረው። አየሽ አይደል ፍቅርና እንክብካቤ ስትሰጪው እንዴት አይነት መልካም ሰው እንደሆነ።ስለዚህ ከዚህ ተምረሽ ለባልሽ መልካም ሚስት ሁኚለት።"ብላ ነገረቻት።
የኔ እህት ወንድ ልጅ የፈለገ አረመኔ ቢመስል ልቡ ገራገር ነው በፍቅር ልታሸንፊው ትችያለሽ። መልካም ሚስት ሁኚለት። ፍቅር ሁሌም ያሸንፋል ሸር ላይክ እናድርግ ላላነበበቡ እንዲደርስባቸው
@youthkiller
2024/09/22 04:51:28
Back to Top
HTML Embed Code: