Telegram Web Link
👆👆👆👆👆👆👆👆
Teleprompter ምንድነው?

ብዙ ጊዜ የሀገር መሪዎች ህዝብ በተሰበሰባቸው ትላልቅ መድረኮች ላይ ንግግር ሲያደርጉ ከፊታቸው በቀኝ እና በግራ በኩል መስታወት የሚመስሉ ነገሮች ቆመው እናያለን በተለይም ባደጉት ሀገራት የተለመደ ነው።

ብዙዎቻችን የጥይት መከላከያ እየመሰለን ስንሸወድ የከረምንም አንጠፋም😁😁። እውነታው ግን Teleprompter ተብሎ የሚጠራ መሳሪያ ሲሆን ዋናው ስራውም ተናጋሪው ከዛ ላይ እየተመለከተ እንዲያነብ የሚያግዝ መሳሪያ ነው።
እንዴት ይሰራል?

የኮምፒዩተር እስክሪኑ ከቆመው መስታወት ትይዩ መሬቱ ላይ ተደብቆ ይቀመጣል(ለበለጠ ፎቶውን በመመልከት ይረዱ) መስታውቱም ከስክሪኑ ላይ Reflect በማድረግ ጽሁፉን ወደ መስታውቱ ያስተላልፈዋል።

በአድማጩ በኩል ምንም የሚታይ ነገር አይኖርም ነገር ግን ተናጋሪው በቀኝ እና በግራ በኩል አድማጩን የሚያይ እየመሰለ ከመስታወቱ ላይ ያነበዋል። ተናጋሪውም የተዘጋጀበትን ጉዳይ በጥሩ ሁኔታ እንዲያቀርብ ያስችለዋል።

የጽሁፉን ፍጥነት የሚቆጣጠር ባለሞያ ከጀርባ በመሆን ከተናጋሪው ፍጥነት ጋር እየተናበበ ያነበበውን ክፍል ያሳልፍለታል።

ከሰሞኑ በሀገራችንም ጠቅላይሚኒስትሩ ቢሮ መግባቱ እየተነገረ ሲሆን የጠቅላያችንን ንግግር ከዚህ በላይ የተዋበ ያደርገዋል ተብሎ ይጠበቃል
# የማትናደፍ_ንብ_ከፈለክ_ከዝንብ_ጋር_ተጋባ "
(በዲ/ን ዳንኤል ክብረት)
ትዳር ከንብ ጋር መኖር ነው ። ለማሩ ስንል ንድፊያውን መታገሥ ፡፡ ቆይተህ
ደግሞ ንድፊያውን መልመድ ፡፡ ገበሬ ቀፎ ሰቅሎ ንብ ሲያንብ ፣ ንብ
እንደምትናደፍ ሳያውቅ ቀርቶ አይደለም ፡፡ የማትናደፍ ንብ ከፈለገ በየደጁ ቆሻሻ
ፍለጋ የምትጓዘው ዝንብ ነበረችለት ፡፡ ዝንብ ምን ጠባይዋ ሸጋ ቢሆን ፤ ጠብ
የሚላት ግን ሌላ ነገር ነው ፡፡
ይህን ያውቃል ገበሬው ፡፡ እያወቀም ንብ ያንባል ፡፡ ማነብ ብቻ ሳይሆን ከንብ ጋር
እንዴት መኖር እንደሚቻልም ያውቃል ፡፡ ንብ ትናደፋለች ፤ ግን እንዳትናደፍ
ማድረግም ይችላል ፡፡ የምትወደውና የማትወደው ሽታ አለ ፡፡ ስትቀርብህ ምን
ማድረግና ምን አለማድረግ እንዳለብህ ገበሬው ያውቃል ፡፡
በሀገራችን ንብ አትገደልም ፡፡ ነውር ነው ፡፡ ብትነድፍም አትገደልም ፡፡ የንቧን
ማር ለመውሰድም ንቧን ገድሎ ፣ አጥፍቶ ፣ ጎድቶ ወይም አሰቃይቶ ሳይሆን
በጭስ ራሱን እየተከላከለ ፣ ፊቱን በጨርቅ ሸፍኖ ፣ ወደ ንቧ ቀፎ ገብቶ ነው
ማሩን የሚቆርጠው ፡፡ ንቧም ሳትጎዳ ፣ ማሩም ሳይጠፋ ፣ እርሷም ሳትናደፍ ፡፡
ትዳርም እንዲህ ነው ፡፡ አኗኗሩን ነው ማወቅ ፤ የንቧን ንድፊያ የመቀነሻውን
መንገድ ነው ማወቅ ፣ የማሩን አቆራረጥ መንገድ ነው ማወቅ ፡፡ ደግሞም‘ኮ
አስገራሚው ገበሬው የሚከባከበው ይህቺኑ የምትናደፈውን ንብ መሆኑ ነው ፡፡
የምትቀስመው አበባ ትፈልጋለች ፣ ንጹሕ አካባቢ ትፈልጋለች ፣ ከጉንዳንና
ከአውሬ ነጻ የሆነ ቀፎ ትፈልጋለች ፡፡ ግን ትናደፋለች ፡፡ ደግሞም ማር ትሰጣለች
፡፡
ትዳር አስደሳች ነገር ብቻ ሳይሆን አስመራሪ ፣ አስጠሊታ ፣ ጨጓራ አንዳጅ ፣ ልብ
አቃጣይም ክፍል አለው ፡፡ ይናደፋል ፡፡ ግን ደግሞ ክብካቤም ይፈልጋል ፡፡ ንጹሕ
ልብ ፣ ታማኝ ኅሊና ፣ ቻይ አንጀት ፣ ታጋሽ ሆድ ፣ ጠቢብ አእምሮ ፣ አሳላፊ ልቡና
ይፈልጋል ። ለምን ቢሉ ? ማር ይሰጣልና ታገሱ ።
ሰናይ ቀን. @youthkiller
ፍቅር ማለት ማስመሰል አይደለም።

ፍቅር ማለት ስለወደደህ ብቻ
የምትወደውም አይደለም።

ፍቅር ማለት በደስታ ግዜህ ጠብቆ የሚቀርብህ አይደለም።

ፍቅር ማለት ሀዘንህን ብቻ የሚመለከት አይደለም።

ፍቅር ማለት በይሉንታ የሚታሰር አይደለም።

ፍቅር ማለት አንተነትህን ባወቀህ ልክ የሚተችህ አይደለም።

ፍቅር ማለት ለብቸኝነት የሚዳርግህ አይደለም።

ፍቅር ማለት ሲቸገርህ የሚርቅህ አይደለም።
ፍቅር ማለት የክብር ጉዳይም አይደለም።

💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕
#ፍቅር_እውነተኛ_ስሜት_ነዉ የሌሎችን #ስሜት_ሳይሆን_የራስህን #ስሜት_የምታዳምጥበት_ልብህን_ከፍተህ #የምታስቀምጥበት_በደስታው_ደምቀህ_በሀዘኑ_መፍትሄ_የምትሻበት_ዛሬን_ኑረህ_ነገን_የምታልምበት_ኣዲስ_ነገር-የምታይበት
💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕

#እውነተኛ_ፍቅር ሁሌም ቃሉ ትክክል ነው ሽንገላን አያውቅም፤ችግር ፤ስህተትህን በትግስት እያለፈ መልካም ነገርን ያስተምራል።መሆን ምን ማለት አእንደሆነ እየኖረ ያሳየሀል።።።።፣
አይበግረውም
የማይቇረጥ ፣ችግር የማይፈታው ፣አንደበታዊ ያልሆነ፣ ማስመሰል የሌለበት ፍቅር ይስጠን።፣፣፣፣አሜን


@youthkiller
Forwarded from ወጣቱ ና ሙዱ (Some Body)
የአዕምሮ ምግቦች

ማንበብ የሰውን ልጅ የአዕምሮ ጡንቻ በማዳበር ለነገሮች ሁሉ ያለንን መረዳት በየጊዜው እንደሚያሳድገው የተረዳ ሰው ከማንበብ ሊቆጠብ አይችልም፡፡ የሰው ልጅ አካለ ሥጋ (Physical Body) ጡንቻዎች በስፖርታዊ እንቅስቃሴና በተመጣጣኝ ምግብ ሊዳብሩና ማራኪ ቅርጽ ሊይዙ ይችሉ ይሆናል፡፡ ጤንነታቸውም በነዚህና በሌሎች የህክምና መንገዶች ሊጠበቁ ይችላሉ፡፡ የአዕምሮ ጡንቻ የሚዳብረውና ጤናው የሚጠበቀው ግን በንባብና በመሳሰሉት የአዕምሮ ምግቦች ነው፡፡ እና የአዕምሮው ጡንቻ እንዳይዳብርና የመረዳት አቅሙ እንዳያድግ የሚፈልግ ማነው? በእውነት ሰው ይሄንን ከተረዳ ለማንበብ ይሰንፋል ብዬ አላምንም፡፡
የሰው ልጅ አንባቢ ሲሆን ሀሳቡ ይሰበሰባል፡፡ አስተውሎቱ ይጨምራል፡፡
@youthkiller👍👍👍
🎡🌹🎡🌹🎡🌹
🎡
🎡🌹🎡🌹
🎡
🎡🌹🎡🌹🎡🌹


🌺🌺🌺🌺
🌺
🌺
🌺
🌺
🌺
🌺🌺🌺🌺


🎡🌹🎡🌹🎡
🎡 🎡
🌹 🌹
🌹 🌹
🎡 🎡
🎡🌹🎡🌹🎡


🌻🌻 🌻🌻
🌻 🌻 🌻 🌻
🌻 🌻 🌻 🌻
🌻 🌻 🌻
🌻 🌻
🌻 🌻


🌹 🌹
🌹 🌹
🌹 🌹
🌹 🌹
🌹 🌹
🌹 🌹
🌹 🌹🌹

🌻🌻🌻🌻🌻
🌻 🌻
🌻 🌻
🌻 🌻
🌻🌻🌻🌻🌻
🌻 🌻
🌻 🌻
🌻 🌻
🌻🌻🌻🌻🌻


🌻
🌻 🌻
🌻 🌻
🌻🌻🌻🌻
🌻 🌻
🌻 🌻
🌻 🌻


🌻 🌻 🌻 🌻
🌻 🌻
🌻 🌻
🌻 🌻 🌻
🌻 🌻
🌻 🌻
🌻 🌻


🌻
🌻 🌻
🌻 🌻
🌻🌻🌻🌻
🌻 🌻
🌻 🌻
🌻 🌻

🌹 🌹
🌹 🌹
🌹 🌹
🌹 🌹
🌹🌹
🌹 🌹
🌹 🌹
🌹 🌹
🌹 🌹


@youthkiller
እንኳን ለ1440ኛው የዒድ አል-ፈጥር
በዓል በሰላም አደረሳችሁ ! 🎊



#ዒዱኩም\_ሙባረክ! 😍

💐 @youthkiller💐
🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን

ሁለት ሴቶች አንድን ወንድ በFacebook ይተዋወቁና ከረዥም ጊዜ ቡኃለ ለመገናኘት ቀጠሮ ይይዛሉ። ታድያ ይህ ሰው ውጭ አገር ይኖር ስለነበር ሁለቱም ሴቶች ምንም እንኳን ጏደኛሞች ቢሆኑም የጥቅም ነገር ነውና ለኔ ነው ለኔ ነው እያሉ መጣላት ይጀምራሉ።

ሰውየውም ሁለቱንም ባንዴ ቀጥሮ ወደሱ እንዲሄዱ ያደርጋል። ሴቶቹ ታድያ ሁለቱም ብሃሪያቸው እጅግ የተለያየ ነበር። ኣንደኛዋ መልካምና ከአፏ የእግዚአብሔር ቃል የማይጠፋ ጥሩ እምትባል ኣይነት ናት። አንደኛዋ ደግሞ በተቃራኒው ችኩልና እራስ ወዳድነት የሚያጠቃት አይነት ሴት ናት። ይህ ሰው ወደ ቀጠራቸው ቦታ ተያይዘው ሲደርሱ ግን የጠበቃቸው ነገር አስደንጋጭ ሆነ።

ያ ለኔ ለኔ ሲሉት የነበረው ሰው አካል ጉዳተኛ ሆኖ አገኙት። ዊልቸር ላይ ተቀምጦ "እንኳን ደህና መጣችሁ" ብሎ ደስ በሚል ፈገግታ ቢቀበላቸውም እነሱ ግን ፊታቸው ክስል ብሎ "እንዴት አርገን እናምልጥ" እሚል ስሜት ውስጥ ነው የገቡት። እንደምንም ሰላምታ ከተለዋወጡ ቡኃላ "እንግዲህ ይህን ያክል ከተዋወቅን ወደ ዋናው ቁም ነገር እንግባ" አላቸውና ብቻ ብቻቸውን ማውራት እንደሚፈልግ ነግሮ አንዳቸው ውጭ እንዲቆዩ ጠየቃቸው።

ችኩሏ ሴት ፈጠን አለችና "እኔ እወጣለሁ አውሩ"ብላ ተነስታ ወጣች። ሰውየውም ለመልካሟ ልጅ የጋብቻ ጥያቄ አቀረበላት ልጅቷም በጣም በተደናገጠ ስሜት ማውራቷን ቀጠለች። እንዲህም አለችው "እስከ ዛሬ ድረስ በፍቅር ክንፍ ብየልህ ነበር፤ ዛሬ ሌሊት ግን እግዚአብሔር ተገለጠልኝ፣መንገዴንም እንዳስተካክል ነገረኝ" እያለች ከመፅሐፍ ቅዱስ እያጣቀሰች ብዙ አውራች። እሱም ተስፋ ባለመቁረጥ ለማግባባት ሞከረ እሷ ግን "እኔ አልሆንህም ሌላ ፈልግ" አለችው። እሽ ብሎ "ሌላኛዋን ጥሪልኝ"አላት።

ችኩሏ ልጅ ገባችና እሚላትን በጥሞና ስታዳምጥ ከቆየች በኀላ "ጥያቄህን ተቀብየዋለሁ። ማን ያውቃል ፈጣሪ ይፈውስህ ይሆናል፣ እኔ ሙሉ አካል አለኝ አያለሁ፤ እሰማለሁ፤ እንቀሳቀሳለሁ። ይህ የሆነው ደግሞ በ እግዚአብሔር ፍቃድ ነው። አንተም እግዚአብሔር ፈቅዶ ትፈወስ ይሆናል። ስለዚህ አገባሃለሁ" አለችው። ደስ ብሎት "በቃ እሽ ጏደኛሽን እንሸኛት" ብሎ በዊልቸር እየተገፋ ወደ ውጭ ወጣ።

ያቺ መልካም አንደበት ያላትና ልቧ ግን የጎደፈ ሴት ለመሄድ እጅግ ቸኩላለች። ችኩሏና ልታገባው የወሰነችው ሴት እየገፋችው መልካም መሳይዋ ልጅጋ ደረሱ። እንዲህም አላት "በ እግዚአብሔር ቃል ተሞልተሻል። ግን ተግባርሽ እንደ ንግግርሽ አይደለም። ይሄን እውቀትሽን ተጠቀሚበት"። አላትና ልታገባው ወደ ወሰነችው ሴትም ዘወር በማለት "አንቺን ደግሞ ሰርፕራይዝ አረግሻለሁ"። ካለ ቡኅላ ከተቀመጠበት ዊልቸር ብድግ ብሎ በመቆም ምንም አይነት የጤና ችግር እንደሌለበት አሳያቸው። አስመሳይዋም በህፍረት አንገቷን ደፍታ "መልካም ጋብቻ ያርግላችሁ"።ብላ ውልቅ አለች።

"ጥቅም ለማግኘት መልካም ነገሮችን ማድረግ መልካምነት ሳይሆን አስመሳይነት ነው"።

🙌መልካም ቀን ቸር ያውለን🙌

@youthkiller
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💎💎💎@youthkiller 💎💎💎:
🔵በምክንያት አትታሰር❗️
❗️
ለውድቀታችን ብዙ ምክንያቶችን መስጠት ለምደናል። ወደ ኃላ ለቀረንበት፤ የፈለግነውን ሳይሆን ያልፍለግነውን ለመሆናችን፤ምክንያቱን ብንጠይቅ፤ እጅግ ብዙ ነገሮችን ለመደርደር
እንችላለን። ግን ሁሌም ምክንያቶች በኖሩን ቁጥር፤ ውድቀታችንን በጸጋ ለመቀበል ዝግጁ ነን ማለት ነው ፤ እንደዛ ማለት ብቻም ሳይሆን ለወደፊቱ ውድቀታችንም ዝግጁ ያደርገናል::

ህልም ካለህ እና ህልምህ ለህይወትህ ትልቅ ትርጉም ካለው፤
ከባዶ ማንነት ወጥትህ፤ ትርጉም ያለው ማንነት እዲኖርህ
ከፈለግክ ምክንያት መስጠትህን አቁም። ሁላችንም ለውደቀታችን ማስተባበያ የሚሆን ብዙ ምክንያቶችን ማቅረብ
እንችላለን…..በገዛ ህይወታችን ሃላፊነት ስለሚጎድለን፤
እራሳችንን እንዳንለውጥ ምክንያቶቻችን አስረው ይይዙናል::
ስኬታማ ሰዎች ግን ለውድቀታቸው ምክንያትን መስጥት የማይወዱ ሰዎች ናቸው። ስኬታማ ስል ገንዘብን ወይም የሃብት ክምችትን ብቻ እንደ ስኬት መለኪያ ቆጥሬው አይደለም። ስኬት
በራሳችን መመዘኛ የሚለካ ነው።አንድ የሚያስማማን ነገር ግን
ስኬታማ ሰዎች፤ የመረጡትን ኑሮ መኖር የቻሉ ናቸው። ልባቸው የወደደውን፤ ለህይወታቸው ትርጉም የሚሰጠውን መንገድ የተከተሉ፤ ብርሃናቸው ከራሳቸው አልፎ ለሰው የሚያበሩ ሰዎች
ናቸው::

በዘልማድ ኑሮ ውስጥ ተዘፍቀን፤ ማህበረሰቡ ባወጣልን
መስፈርት፤ አካባቢያችን ባሰመረልን መስመር፤ ችሎታችንን
ገድበን እስከመቼ እንኖራለን? ህልሞቻችንን ሌሎች ማየት
ስለተሳናቸው ብቻ ቅዠት እየመሰለን፤ እውን የሚሆኑ ብዙ ህልሞችን እስከመቼ እናጨልማለን? አላማችንን እንደራሳችን አድርጎ የሚመለከትልን ሰው ስላጣን፤ አላማችንን በተስፋ መቁረጥ ጉድጓድ ውስጥ ቆፍረን ቀበርነው። ችሎታችንን ሰው እንዲነግረን ስንጠብቅ፤ አቅም እና ችሎንታችንን፤ እንደቅጠል ጠወለጉብን:: እራሳችንን የሚመስል ከሰው መሃል ፈልገን ስላጣን፤ ሰውን ለመምስል ሙግት ጀመርን። ሌሎችን መስለን ተራ ሆንን፤ ስራችን የሌላውን መስሎ ተራ ሆነ። መመሳሰል ህይወታችንን የሚያቀልን መሰለንና፤ እኛነታችንን እረስተን ተመሳሰልን፤ ያኔ ልዩነታችን ሞተ፤ ከልዩነታችን ጋር እኛነታችን አብሮ ሞተ፤ከኛነታችን ጋር ህልማች ሞተ። የገዛ ውበታችን ጠፋ ምክንያቱም
ውበት በልዩነት ውስጥ የሚንጸባረቅ ነበርና::

ስንቶቻችን የምንወደውን ስራ አየሰራን ነው? ትርጉም የሚሰጠን ኑሮ፤ ለመኖር ምክንያት የሚሆን እሴት ያለን ስንቶቻችን ነን? አብዛኛዎቻችን ችግራችንን ለምደነዋል፤ ውድቀታችንን ተቅብለነዋል፤ ስለምንኖረው ኑሮ ምንም አይነት ነገር የማድረግ አቅም የሌለን ይመስለናል፤ ህይወታችንን የሚለውጥ ሰው ወይም አጋጣሚ እስኪመጣ እንጠብቃለን፤ በዛ መሃል ውስጣችን ቀስ በቀስ ይሞታል።
ብዙዎች የሚያውቁት ጥቂቶች ግን የሚኖሩበት እውነታ ግን ይህ
ነው።ለህይወትህ ሃላፊነት ከወሰድክ እና መሆን የምትፈልገውን ከወሰንክ በዚህ ምድር ላይ ካንተ በቀር ከጉዞህ የሚያስቀርህ ማንም የለም። እርግጥ ነው መንገድህ ሁሉ አልጋ በአልጋ አይሆንልህም፤ ብዙ ችግር ያጋጥመሃል ምክንያቱም የስኬት
መንገድ ቀላል ቢሆን ኖሮ ሁሉም ይሳካለት ነበር። ግን ከባድ
ነው…….መንገድህ ሊያቀልልህ የሚችለው አንድ ሚስጥር አለ
እሱም ህይውትህን ለመቀየር ምን ያህል ትፈልጋለህ?
ናፖሊዮን ሂል አንድ ሰው ስኬታማ እንዲሆን የሚያስችለውን
ሚስጢር እንዲህ ይናግረዋል “ሰዎች አሸናፊ እንዲሆኑ
ሊኖራቸው የሚገባ ባህሪ አለ እሱም ፤ የሚፈልጉትን ነገር
በእርግጠኝነት ማወቅ፤ መወሰን እና ውሳኒያቸውን በተግባር
ለማዋል የሚያስችላቸው ከፍተኛ ፍላጎት ማዳበር።” እኒዚህ
ሶስት ነገሮች አንድ ላይ ሲዋሃዱ ህይወታችንን ወደፈለግንበት
አቅጣጫ እንድንመራ የሚያስችለንን መሪ ጨበጥን ማለት ነው።

ብዙዎቻችን በህይወታችንየምንፈልገውን ነገር አናውቅም፤ብናውቅ እንኳን መወሰኑ ይከብደናል። ለምን?ለመለወጥ ስለምንፈራ? ዛሬ ያለንበትን ቦታ ስለለመድነውና መጪውን
ስለማናውቅ?ሌሎች አይሳካም አይሆንም ስላሉን? አቅማችንን
ማንም ነግሮን ስለማያውቅ? ወይስ ውድቀትን ፈርተን?ሁላችንም ምክንያቶች አሉን፤ እኒህ ምክንያቶች ደግሞ ባለንበት
ቦታ እንድንቀር የሚቸነክሩን ሚስማሮች ናቸው። ለውድቀትህምክንያት እስከሰጠህ ድረስ…ካሰብክበት አትደርስም ምክንያቱም ፤ የመለወጥ ፍርሃትህ ሌላ ምክንያት መፍጥር አያቆምምና።ከዚህ አለም ስትሄድ በምን መታወስ ትፈልጋለህ? ዳግም
በማታገኛት አንዴ በተሰጠችህ በዚህች አጭር ህይወት ምን ማድረግን ትመርጣለህ? መለወጥ የምትፈልገው ምንድን ነው?የምትፈልገውን እና የሚያስደስትህን ስራ መስራት?መልካምቤተሰብ መመስረት? መማር? ከሱስ መላቀቅ? የጀመርከውን
ስራ መጨረስ? ለምትወዳቸው ሰዎች መኖር? ወይስ ምን?
የራስህን ህልም መኖር ካቃተህ የሌላውን ሰው ህልም እውን
ለማድረግ ስትለፋ እንደምትኖር እመን፤ አይ የራሴን ህልም
ማሳካቱን እመርጣለው ካልክ ደግሞ፤ ሶስቱን ነገሮች አስታውስ፤
♦️ የምትፈልገውን ነገር እወቅ
♦️ወስን
♦️ለመለወጥ ፍላጎት ይኑርህ። ከምንም በላይ ምክንያት መስጠትህን አቁም።ሁሉም ስዎች ትልቅ እንዳይሆኑ እንቅፋት ሊሆኑባቸው የሚችሉ ብዙ ምክንያቶች አሏቸው። ልዩነቱ ደካሞች በምክንያት ታስረው፤ከአቅማቸው በታች ሲኖሩ፤ ጠንካሮች ግን ችግሮቻቸው እና እንቅፋቶቻቸውን የውድቀት ምክንያት ከማድረግ ይልቅ፤
እራሳቸውን ይበልጥ ያጠነክሩበታል………ከመንገዳቸው የሚያቆማቸው ምንም ነገር የለም፤ ማንም ከአላማቸው
አይገዝፍባቸውምና::ያንተስ አላማ ምን ያህል ግዙፍ ነው?
(ምንጭ:-አሻራየ)

@youthkiller
Forwarded from እንማማር (Yidnekachew Girma)
እንማማር:
መልካምነት የሚመሰገን ተግባር ብቻ ሳይሆን
የመልካም አድራጊውን ሰው እድሜ እንዲጨምር
ሊያደርግ እንደሚችል ኢቮሉሽን ኤንድ ሂውማን
ቢሄቪየር በተባለ የሳይንስ መጽሔት ላይ የወጣ ጥናት
ውጤት ይፋ አድርጓል፡፡
እንደ ጥናቱ ግኝት ከሆነ ቢያንስ አልፎ አልፎ ለሰዎች
የሚራሩና ድጋፍ የሚያደርጉ ሰዎች በመልካምነታቸው
የሚያገኙት ምርቃት ሰምሮላቸውን ሳይሆን አይቀርም
በጎ ተግባር ከማያከናውኑ ይልቅ እድሚያቸው
እንደሚልቅ ነው የተነገረው፡፡
ጥንቱ የተካሄደው እድሜያቸው ከ70 እስከ 103
የእድሜ ክልል ባሉ 500 አረጋዊያን ላይ ነው
ተብሏል፡፡
በጥናቱ መሠረት አያት የሆኑ አረጋዊያን አልፎ አልፎ
የልጅ ልጃቸውን ሲንከባከቡ እንደዚሁም ለልጆች
እንክብካቤ የማያደርጉ ግን ደግሞ በማህበራዊ
መስተጋብራቸው በበጎ ተግባር የተሰማሩ ሰዎች
በጥናቱ ተካተዋል፡፡
በጥናቱ የተካፈሉት ሰዎችም ለ20 ዓመታት በዘርፉ
ተመራማሪዎች ክትትል ሲደረግባቸው የቆየ እንደሆነም
ተገልጿል፡፡
ለልጅ ልጆቻቸው እንክብካቤ የሚያደርጉ አያት
አረጋዊያን እንዲሁም ልጆቻቸውን የሚደግፉ
እማወራና አባወራዎች ጥናቱ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ
ለ10 ዓመታት በህይወት መቆየት ችለዋል ነው
የተባለው፡፡
በአንፃሩ ይህን መሰሉን እንክብካቤና ሰናይ ተግባር
ያልፈፀሙ ግማሽ ያህሉ የጥናቱ ተሳታፊዎች ጥንቱ
ከተጀመረ ከ5 ዓመት በኋላ ህይወታቸው እንዳለፈ
ተመልክቷል፡፡
ከቤተሰባቸው ውጪ ለሌሎች ሰዎች ሰናይ ምግባር
የሚያከውኑ ሰዎች ይህን ከማያደርጉ ሰዎች ይልቅ
ህይወታቸው እንደጨመረ በጥናቱ ተረጋግጧል፡፡
በመሆኑም በአቅሪያቢያቸው ለሚገኙ ሰዎች መልካም
ተግባር የሰሩ ሰዎች ግማሾቹ ጥናቱ ከተጀመረ በኋላ
ለ7 ዓመት በህይወት መቆየት ችለዋል፡፡
ይሁንና ይህን መሰሉን ተግባር ያላከናወኑ ሰዎች
ደግሞ ጥናቱ ከተጀመረ በኋላ ለ4 ዓመት ብቻ ነበር
በህይወት መቆየት የቻሉት፡፡
እንደ ጥናቱ ተመራማሪዎች ከሆነ በመልካምነትና
በጤና በረከት ብቻ ሳይሆን በሰናይ ምግባርና በሞት
ምጣኔ መካከል ግንኙነት እንዳለ ጠቅሰዋል፡፡
ጥናቱ ሌሎችን መርዳት እድሜ በእርግጠኝነት
እንደሚጨምር ምንም ማረጋገጫ ባይሰጥም በጎ
ምግባር የሚገኘው የመንፈስ እርካታ አሉታዊ
ስሜቶችን ለማጥፋት እንደሚጠቅም የዘርፉ
ተመራማሪዎች ያምናሉ፡፡
በዘርፉ ላይ ተጨማሪ ጥናት ያስፈልጋል የሚሉት
ተመራማሪዎቹ መልካምነትና ሰዎችን መርዳት ግን
በአመዛኙ ለጤና መጠበቅና ለረጅም እድሜ ፍቱን
መድሃኒት ነው ባይ ናቸው፡፡
ምንጭ፦ታይም
በጊዜያዊ ስሜቶች (“ሙዶችህ”) አትታለል

ሰው በተፈጥሮው መልካም ገጠመኝ ሲደርስለትና በጣም በጋለና ግሩም በሆነ ስሜት (“ሙድ”) ውስጥ ሲሆን ከዚያ ቀን ጀምሮ ልብህን የሚያሳዝን ምንም ነገር እንማይገጥመው የማሰብ ዝንባሌ አለው፡፡ በተቃራኒውም በአንዳንድ ክፉ ገጠመኞች ምክንያት በጣም በወደቀ “ሙድ” ስሜት ውስጥ ራሳችንን ስናገኘው ከዚያ ሁኔታ የመውጫ ጭላንጭሉ አይታየንም፡፡ ይህ ከጊዜው “ሙድ” የተነሳ የሚመጣ “የቋሚነት” ስሜት በውሳኔአችን ላይ ጣልቃ ይገባና የኋላ ኋላ የምንጸጸትባቸውን ውሳኔዎች እንድንወስን ይገፋፉናል፡፡

ለምሳሌ፣ ይከፈለትልኛል ብለህ የጠበከው የእድል በር ባልጠበከው መንገድ ቢዘጋና የወደቀ “ሙድ” ውስጥ ብትሆን፣ ኑሮ ሊያስጠላህና የተለያዩ ውሳኔዎችን እንድትወስን ሊገፋፋህ ይችላል፡፡ “ሙዱን” ግን ማሳለፍ የግድ ነው፡፡ አየህ፣ በክፉም ሆነ በጥሩ የጠለቀ ስሜት ውስጥ ስትሆን አእምሮህ ለሕይወትህ የሚጠቅምህንና የማይጠቅምህን ነገር የማመዛዘኑ ሁኔታ ይወርዳል፡፡ እነዚህ የ“ሙድ” ውጣውረዶች ግን እየመጡ የሚሄዱ እንደሆኑና፣ እውነታ ብቻ ዘላቂ እንደሆነ በማሰብ አይኖችህን እውነታው ላይ ጣል - የማያልፍ ነገር የለምና፡፡

“የስሜት ብልህነት” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ
🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት ናችሁ🙏

በአንድ ወቅት አንድ ወጣት ብዙ እንጨቶችን ተሸክሞ በጫካ ውስጥ ያቋርጣል፡፡ ትንሽ እንደተጓዘ አንድ ትልቅ ሰው ተርቦ ተመለከተ፤ ልቡ በጣም አዘነ፤ ምግብ ሊሰጠው ፈለገ ነገር ግን ለእራሱም የሚበላው የለውም ነበር፡፡ እናም ምንም ሳያደርግለት መንገዱን ቀጠለ፡፡

አሁንም ከትንሽ መንገድ በኀላ አንድ አጋዘን በውሃ ጥም ሲሰቃይ ተመለከተ፤ ወጣቱ አሁንም ልቡ አዘነ፤ ውሃ ሊያጠጣው ወደደ ነገር ግን ለእራሱ የሚጠጣውም ውሃ አልነበረውምና ምንም ማድረግ ሳይችል መንገዱን ቀጠለ፡፡

አሁንም ትንሽ ከተጓዘ በኀላ የሆነ ቱሪስት ካምፕ ለመስራት ፈልጎ እንጨት ሲፈልግ ተመለከተው፤ በዚህ ወቅት ወጣቱ ለቱሪስቱ የሚያስፈልገውን ያህል እንጨት ሰጠው፡፡ ቱሪስቱም ለወጣቱ ከሰነቀው ምግብና ውሃ አካፈለው፡፡ በዚህ ወቅት ወጣቱ ወደ ተራበው ሰው ተመልሶ ቱሪስቱ ከሰጠው ምግብ አካፈለው፤ ወደ አጋዘኑ ተመልሶ ከውሃው አጠጣው፡፡

በሌላ ቀን ወጣቱ ተንሸራቶ ገደል ይገባል፤ በጣም ታመመ በዙሪያው ግን አንድም የሚረዳው ሰው አልነበረም፤ ድንገት ግን በሌላ ቀን ምግብ ያበላው ሰውዬ ሲያልፍ ወጣቱን ተመለከተና ከገባበት ገደል ጎትቶ አወጣው፤ ነገር ግን ብዙ ቦታ ተጋግጧል፡፡ በዚህ ወቅት ውሃ ያጠጣው አጋዘን ወደ ጫካው በመግባት ለመድኀኒትነት የሚጠቅመውን ዕፅ አመጣለት፡፡ ከእዛን ቀን በኀላ ወጣቱ ፣ ትልቁ ሰው እና አጋዘኑ በደስታ ይኖሩ ጀመር፡፡

⭕️እርዳታ የሚፈልግ ሰው ስንመለከት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንርዳ፤ አንድ ቀን እኛም የሰዎችን እርዳታ የምንፈልግበት ሁኔታ ይፈጠራል፤ የዛኔ መልካምነታችን መልሶ ይከፍለናል፡፡

🙌መልካም ምሽት🙌

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@youthkiller
Forwarded from ወጣቱ ና ሙዱ (Gizachew Nega)
🏃🏃🏃‍♀🏃‍♀
ወጣትነት

🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣

ወጣትነት ፋሽን ተከታይ ዘናጭ ተሽቀርቃሪ መሆን ማለት አይደለም! ወጣትነት ራስን በሱሶች ማጠር ማለት አይደለም! ወጣትነት በምክንያታዊነት ሳይሆን በስሜታዊነት እየተነዱ ራስንና ሌላውን አደጋ ውስጥ መዝፈቅ ማለት አይደለም! ወጣትነት ብዙ ጃንቦ የጠጣ ጀግና ማን ነው መባባል ማለት አይደለም! ወጣትነት ብረት ገፍቶ ደረትን ማሳበጥ ማለት አይደለም! ወጣትነት ሺሻ ቤት ተቀምጦ ጭስ ማቡነን ማለት አይደለም!

ወጣትነት በወሲብ ሱስ ከዚህም ከዚያችም ጋር በዝሙት ተወጥሮ መልከስከስ ማለት አይደለም! ወጣትነት በጥላቻ እና በዘረኝነት ተሞልቶ መታወር፣ መደባደብ እና መነታረክ ማለት አይደለም! ወጣትነት ተመልሶ የማይመጣውን ተፈጥሮ የሰጠችንን ታላቅ ሃይል በማይረባው ነገር ጊዜን ማቃጠል ማለት አይደለም! ወጣትነት ግዜያዊ ስሜትን ብቻ እያዳመጡ እንደፈረስ ጋሪ መነዳት ብቻ አይደለም! ወጣትነት በሀሜት፣ በአሉባልታ፣ በወሬ ሱስ፣ በአቃቂር፣ በተንኳሽነት፣ በቧልት መሞላት ማለት አይደለም!

ወጣትነት ይሄንንም ያንንም ይቺንም ያቺንም መጀንጀን መጀናጀን ማጀናጀን ማለት አይደለም! ወጣትነት በባዶ ጭንቅላት ምርጥ አልባሳትን ለብሶ እየተጀነኑ በባዶ ኩራት ተወጥሮ መሬትን ለመርገጥ እየተጸየፉ መራመድ ማለት አይደለም! ወጣትነት በግዴለሽነት፣ በተስፋ መቁረጥ፣ ከነፈሰው ጋር መንፈስ ማለት አይደለም! ወጣትነት በራስ ወዳድነት መንፈስ መወጠር እና እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ማለት አይደለም! ወጣትነት በማይረባው በቀበሌኛው አመለካከት መታጠር ማለት አይደለም! ወጣትነት ቁንጫ የምታክል እውቀት በመያዝ ይቺ እውቀት ብቻ ትበቃኛለች እያሉ አጉል መመጻደቅ ማለት አይደለም...

ወጣትነት ባህር ነው ። ወጣትነት ውቂያኖስ ነው ። ወጣትነት አድማሰ ሰፊነት ነው ። ወጣትነት እውቀትን ለማስፋት የምንጋደልበት ሰአት ነው ። ወጣትነት በማስተዋል ብርሃን መሞላት ነው ። ወጣትነት ችግር ፈጣሪነት ሳይሆን ችግር ፈቺነት ነው ። ወጣትነት በዘረኝነት ተሞልቶ አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ ወላይታ...ቅብርጥሶ እየተባባሉ ቡድን በመስራት ስለ ቀበሌኛ አስተሳሰብ መስበክ ሳይሆን ወጣትነት ስለ ኢትዮጵያዊነት ከተቻለም አለም አቀፋዊ እይታን ማስፋት ነው ።

ወጣትነት ፍቅርን እና አንድነትን መስበክ ነው ። ወጣትነት በዝሙት ባህር መንቦራጨቅ ሳይሆን ስሜትን የመግዛት ጥበብ ማዳበር መቻል ነው ። ወጣትነት ብርሃን ነው ። ወጣትነት ተስፋ አለመቁረጥ ነው ። ወጣትነት በቀናነት መሞላት ነው! ወጣትነት እስከመጨረሻው ጠብታ ህልምን ለማሳካት መፍጨርጨር ነው ። ወጣትነት ማንበብ ነው ። ወጣትነት መጠየቅ ነው ። ወጣትነት ስለዓለም፣ ስለ ህይወት፣ ስለ ጥበብ፣ ስለ እውቀት ብዙ ለማወቅ መጠማት ነው ። ወጣትነት ለሌሎች መኖር ነው ። ወጣትነት ለአገሬ ምን ልስራላት ብሎ ራስን መጠየቅ ነው ። ወጣትነት ስለነገ ትልቅ ህልም እና እቅድ መሰነቅ ነው ። ወጣትነት እሳት ነው ። ወጣትነት ቤንዚል ነው ። ወጣትነት ቅጠል ነው ። ወጣትነት ጤዛ ነው ። ወጣትነት ታክሲ ነው ። ወጣትነት ምርጫ ነው ። ወጣትነት በባህር ላይ ያለች ጀልባ መሆን ነው ። ወጣትነት የመቶ ሜትር ሩጫ ያህል ነው ። ወጣትነት ውስጥን ፈተናን ለማለፍ ማጀገን ነው ። ወጣትነት ከፍርሃት፣ አልችልም እና አይሳካልኝም የሚለውን እስር በጣጥሶ ማለፍ ነው ። ወጣትነት ለአንዳች ስኬት በኩራት እና በሞራል መራመድ ነው ... ።


ምንጭ ፦ " ኤጭ...! " መጽሐፍ ከገጽ 170-172 የተቀነጨበ
ደራሲ ፦ አዘርግ

👇👇👇👇
Join us @youthkiller

ለአስተያየትዎ
👇👇👇👇
@gzeman
ፍቅር ፈራን
"ፈራን"
ፍቅርን ፈራን መቀራረብ ፈራን
እንዳልተዛመድን እንዳልተዋለድን
ፈርተን መዋደድን ጉርብትናን ናድን
እኛነትን ትተን እኔነትን ለመድን
"ፈራን"
ፍቅርን ፈራን ጥላቻን ሰራን ብቸኝነት ጠራን
በጋራ ቤታችን አጥር ድንበር ሰራን
"ናቅን"
በልዩነት ደምቀን ያልኖርን ያህል አንድም ቀን
እልህ ተናነቅን
"ናቅን"
መቻቻልን ናቅን ለፀብ አሟሟቅን
ለአመፅ ስንነሳ ለሰላም ወደቅን
አገር ስትቃጠል ከዳር ሆነን ሞቅን
"ጠላን"
መወያየት ጠላን መነጋገር ጠላን
መደማመጥ ጠፍቶ መነቋቆር በዝቶ
መናናቅ በርክቶ
መመካከርን ስንረሳ መከባበርን ስንረሳ
እጃችን በወንድማችን ላይ ዱላ አነሳ
የቃየል ምቀኝነት በልባችን ላይ ነግሳ
"ራቅን"
የተስፋ ሻማችን ተለኩሶ
ወጋገኑ መታየት ሲጀምር አድማሱን ጥሶ
እኛ ግን ራቅን ብሩህ ነገን ራቅን
ዛሬን ተጣበቅን ትላንትን ናፈቅን

#ደራሲ → ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን

ሼር @youthkiller
~~~~~~~~~~~~~
የኔ ልጅ አሁን አንተ ትልቅ ሰው ነህ። ነገ ሌላ እናት ታገኛለህ አዲስ ሰው ምግብህን ያበስላል ምስጢርህን ይካፋላል። እኔ ከእንግዲህ ይህንን አላደርግም ...አዲሷን እናትህን ውደዳት። እሰከመጨረሻው በእጆቿ ላይ ከመተኛትህ በፊት ምክሬን ልስጥህ!
አንድ ቀን ከአባትህ ጋር እየተነጋገርን ነበር ...በጣም በስሜት ሆነን እንጯጯህ ነበር ...በቁጣ ስሜት ውስጥ ሆነን ሳላ እኔ በድንገት "አንተ የማትረባ" ስለው በጣም ተሸማቀቀ። ወደ እኔ እየተመለከተ "እንዴት እንደሱ ትያለሽ?" ሲለኝ ቀበል አድርጌ "አዎ አንተ የማትረባ ሞኝ እብድ!" ብዬ ያለ የሌለውን የስድብ ናዳ አወረድኩበት። ታድያ እሱ ምን እንዳደረገ ታውቃለህ? እሲቲ ገምት? ሊደበድበኝ ይችል ነበር ግን እጆቹን ሳያነሳ ምንም ሳይለኝ መዝግያውን አላትሞ ወጥቶ ሄደ።
ልጄ አባትህ ቢመታኝና ፊቴን ቢያበላሸው አንተ ዛሬ በተበላሸው ፊቴ ታዝንብኝና ታፍርብኝ ነበር። እሱንም እንደ አባት አትቆጥረውም ሁሌ ታዝንበት ነበር። የምትኮራበት አባት አይሆንህም ነበር።
ልጄ ሚስትህን እንዳትመታት! ብትሰድብህም ብታዋርድህም ከአጠገቧ ለግዜው ዞር በል። ኋላ ላይ ነገሮች ይስተካከላሉ። እንግዲህ ሚስትህ ስታበሳጭህ ይህንን የእኔን ታሪክ አስታውስ!
ካቋረጥኩበት ልቀጥል ...ልክ ብቻዬን ትቶኝ እንደሄደ ስለሰደብኩት በጣም ፀፀተኝ ...ታድያ የተጣላን ቀን ምሽት አንድ አልጋ ላይ አብረን አደርን። በሚቀጥለው ቀን ማድረግ የሚገባኝን ሁሉ አድርጌ ይቅርታ ጠየኩት። እርሱም ተቀበለኝ ...ታድያ የዛን ቀን ምን አደረኩ መሰለህ የሚወደውን ምግብ አዘጋጅቼ ስሰጠው ደስ እያለው በላ። ካዛ ቀን በኋላ ከአፌ ክፉ ቃል አልወጣኝም ለእሱ ያለኝ ክብር እስር እጥፍ እየጨመረ መጣ።
አንድ በጣም አስፈላጊ ነገር ማድርግ ያለብህ ነገር አለ። ሚስትህን በደንብ አድምጣት ...ጋሻና መከታ ሁናት ...በጭንቅ ግዜ ከጎኗ ሁን። ጓደኞችህ ቢጠሉዋትም ያንተ ንግስት እንደሆነች አሳያቸው። ታውቃለህ አጎትህ አይወደኝም ነበር ...አባትህ ግን ስለኔ ያለውን አሳምኖት ሃሳቡን አስለውጦት እኔን ይደግፈኝ ነበር።
ልጄ! ...አንድ ቀን አባትህ 3 ሰዎች ወደ ቤት ጋብዘ። አንደኛው የስራ አለቃው ሲሆን ሁለቱ ጓደኞቹ ነበሩ ...ምግብ አብስዬ ሁሉን አሟልቼ ካቀረብኩ በኋላ አንድ ነገር ረሳሁ ...ጨው አልጨመርኩም ነበር። በጣም አፈርኩኝ! አባትህ ወድያው ምግቡን እንደቀመሰ ወደኔ ተመልክቶ ወደ እነሱ ዞር አለና "በጤና እክል ምክንያት ከወር በፊት ምግብ ውስጥ ጨው እንዳትጨምር አዝዣት ነበር!" ብሎ ሲስቅ ሁሉም ሳቁና እባክሽ ጨው ስጭን ብለው ሁሉም እንደፍጌጎታቸው ጨምረው ተመገቡ።
እንግዶችም በሄዱ ጊዜ ተንበርክኮ "ጌታ ሆይ ስለዋሁ ይቅር በለኝ!" አለ።
ሚስትህ ልክ እንደ ህፃን ናት ...አንዳንዴ ምን ማለት ወይም ማድረግ እንዳለባት አታውቅ ይሆናል ...ነገር ግን ተነስተህ ስለ እሷ ስትል ተናገርላት።
ልጄ! ...ስለ ግብረስጋ ግኑኝነት ልንገርህ ...ወሲብ ጥሩ ነገር ነው። ሚስትህ በወሲብ የምትደሰተው ካንተ በላይ ከሆነ አይግረምህ። ታውቃለህ አንዳንድ ቀን እኔን በጣም ያስፈልገኛል ...እሱ ግን እስከዚህም ይሆናል። ሌላ ግዜ ደግሞ እሱን በጣም ያስፈልገዋል ...እኔ ግን እስከዚህም እሆናለው...አንድ ማውቅ ያለብህ ነገር ...እራስ ወዳድ አትሁን አንደኛው ሌላኛውን መረዳት አለበት።
አስቸጋሪ ግዜያት ይመሉ። አባትህን ለመደገፍ ስል ሁለት ቦታ ስራ እሰራ ነበር ...ታድያ አንድ ቀን ምሽት በጣም ደክሞኝ ወደ መኝታ ሳመራ እሱ በጣም ተነቃቅቶ ጠበቀኝ ...ግን አልተቃወምኩም። ቢደክመኝም ፍላጎት እንዳለው ሰው ሆንኩለት ...ነገር ግን እንደጠበቀው ስላልሆንኩለት ፊቴን አይቶ በመረዳት "ምን ሆነሻል?" አለኝ "ምንም" አልኩት። ከዚያ ስለተረዳኝ እቅፍ አድርጎ የመኝታ ታሪኮችን/bed time story/ እየነገረኝ እንቅልፍ ወሰደኝ ... ወሲብ የሁለት ሰው የእዕምሮና የአካል ዝግጁነትን ይጠይቃል። አንዳንዴ ሚስትህን በደንብ ተመልከታትና ተረዳት።
ልጄ! ...ከሚስትህ ጋር የትም መሄድ ልማድ አድርገው። ከስራህ ውጭ ሰትሆን ከሚስትህ ጋር አሳልፍ አንድ ሰው ከሚስትህ ውጭ ብቻህን ቤቱ እንድትመጣ ከጋበዘህ ተጠንቀቅ ...ብልህ ሁን።
እኔን እንደምትወደኝ ችግሮችህን እንደምትነግረኝ አውቃለው። አሁን ግን ይህ ሁኔታ ተቀይሮአል። ከነገ በኋላ ሚስትህ ሁሉንም ነገር ማወቅ አለባት። ከእሷ ጋር ስትጋጭ ወድያው ወደኔ አትሩጥ ...ለአንድ ወይም ለሁለት ቀን ታገሳት። ከዚያ ነገሩ ጋብ ሲል ተነጋገሩ ...ፀልዩበት ...ስለ እሷ ለሌላ ሰው ለማንም አትናገር።
በመጨረሻም በየወሩ ከሚስትህ ጋር እየመጣችው ጠይቁኝ ...ጥሩ ትዳር እንደሚኖርህ ተስፋ አደርጋለው። አንተ ምርጥ ልጄ ነህ! እግዚአብሔር ይባርክህ ወደ ፈጣሪ ፀልይ ...ሁሌም የእርሱን እርዳታ ፈልግ!!” (ልጅ ሃሚ)
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ማንም ትሁን ምን እናት እናት ነች! …ዛሬ ላለን ማንነት በምንም የማይተካ ዋጋ ከፍላለችና ክብር ይገባታል! @youthkiller

ረጅም_እድሜ_ለልጆቻቸው_ስኬት_ዋጋ_ለከፈሉ_እናቶች !
ልብ በል ....

በህይወትህ አሸናፊ እንዳትሆን የሚያደርጉህን ነጥቦች ለያቸዉ በምንም መለኪያ ከአሸናፊነት የሚያግድህን ክስተት ሁሉ ቦታ አትስጠዉ አሸናፊ እስክትሆን አትድከም ወይም አትስነፍ፤ ደከመኝ በማለት ለራስህ ስንፍና አታስተምረዉ ።

በምድር ባለህ ቆይታ አሸናፊነትህ የሚወሰነዉ እስከዕለተ ሞትህ በምትከዉናቸዉ መልካም ስራዎችህ መሆኑን አስተዉል ።

ስኬት ስጋዊ ድሎት (የገንዘብ ክምር) ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ አቋምህም የላቀ በመሆኑ የሚገለጽ ጥምር ድል መሆኑን አስምረህ ተነስ ።

ስራህን ለመጀመር ነገ የሚለዉን ቃል ከአፍህም ከልብህም አስወግድ ዛሬ ላይ የምታደርገዉን ብቻ ወስንና ፈጽም ።

ሼር @youthkiller
አስተሳሰብን መቆጣጠር

አስተሳሰብን መቆጣጠር ማለት ወደ እኔ የሚመጣውን ወይም በውስጤ የሚፈጠረውን ሃሳብ በማጣራት ማስተናገድ ማለት ነው፡፡ አስተሳሰባችንን ሳንለውጥ ሕይወታችንንም ሆነ ሁኔታችንን መለወጥ አንችልም፡፡ ይህ የሚሆንበት ምክንያት የሁሉ ነገር መጀመሪያ አስተሳሰብ ስለሆነና አስተሳሰባችን የማንነታችን “ወፍጮ” በመሆኑ ነው፡፡ በመጀመሪያ አንድ ሃሳብ ወደ አእምሮአችን ይገባል፡፡ በመቀጠልም ይህ ሃሳብ በውስጣችን ይብላላና በንግግርና በተግባር መገለጥ ይጀምራል፡፡ ይህ ተግባር ወደ ልማድ ከተለወጠ በኋላ ፍጻሜአችንን የመለወጥና የመቅረጽ ጉልበት ይኖረዋል፡፡ ይህ ሃሳብ ጤናማም ሆነ ጤና ቢስ ሂደቱ ያው አንድ ነው፡፡

ጤና ቢስ አመለካከቶችን ለማስወጣት መውሰድ የምትችላቸው እርምጃዎች፡-

1. በሕይወትህ የምታሰላስላቸውን ሃሳቦች ለይተህ እወቅ፡፡

ለማንነትህና ለሕይወትህ አላማ የሚመጥኑ ሃሳቦች ምን እንደሆኑ ለይተህ ማወቅ አለብህ፡፡ ይህንን ለይተህ ስታውቅ በሃሳቦች መካከል መለየትንና የትኛውን ማስተናገድ እንዳለብህ ጥርት ባለ መልኩ እንድታውቅ ይረዳሃል፡፡

2. ጤና ቢስ አስተሳሰቦችን አታስተናግዳቸው፡፡

የመጣ ሃሳብ ሁሉ በአእምሮህ ስፍራ ማግኘት የለበትም፡፡ ለጤናማ አመለካከትህና ላስቀመጥከው የሕይወት ከፍታና ደረጃ የማይመጥነውን ተራ ሃሳብ በመጣበት ፍጥነት እንዲወጣ ተቃወመው፡፡ ይህንንም ልምምድ የዘወትር አድረገው፡፡

3. ጤና ቢሱን አስተሳሰብ በጤናማ አስተሳሰብ ቀይር፡፡

ከዚህ በፊት በውስጥህ ያስተናገድካቸውን ጤና ቢስ ሃሳቦች መልካምና ስኬታማ በሆኑ ጤናማ ሃሳቦች መለወጥ መጀመር አለብህ፡፡ ከአእምሮህ ክፉውን ሃሳብ አስወጥተህ በጤናማው ካልተካኸው ሌላ ሃሳብ መሙላቱ አይቀርም ፡፡

ምንጭ = ዶ/ር ኢዮብ ማሞ
ሼር @youthkiller
​​"ለፍቅር መስዋእትነት ቃል~ኪዳን ሳይሆን ታማኝነት ነው!"

የፍቅር ህይወት በተሞክሮ ውስጥ የምናልፍበትና በሂደት የምናዳብረው ክህሎት ነው፡፡ እንደ ሰው በፍቅር ግንኙነት ውስጥ መፈጸም የማይገባንና የፍቅር አጋራችንን ስሜት ሊጎዱ የሚችሉ ስህተቶችን ልንፈጽም እንችላለን፡፡ የፍቅር ግኑኝነታችን ጤናማ ሆኖ እንዳይቀጥል የሚያደርጉና ቀጣይነቱን እንድንጠይቅ የሚያስገድዱን ስህተቶችም ይኖራሉ፡፡

የሚከተሉት 5 ስህተቶች በፍቅር ግንኙነት ላይ አዳጋ ሊያስከትሉ ከሚችሉ ጉዳዮች ውስጥ ይካተታሉ፡፡

1."ምልዑነትን መጠበቅ (Expecting Perfection )!"

ብዙዎቻችን ወደ ፍቅር ግንኙነት የምንገባው ፍቅረኛችን ውብ እንደሆነ/ች እና በሁሉም ነገር ደግሞ ብቁ እንደሆኑ አድርገን አስበን ነው፡፡ በጊዜ ሂደት ውስጥ የፍቅር አጋራችን ጉደለቶች መታየት ሲጀምሩ ያንን ሰው አስበነው ወደ ነበረው ምልዑነት ለመቀየር ግርግር መፍጠር እንጀምራለን፡፡ ሰዎች ደግሞ በባህሪያቸው በማንነታቸው እንዳሉ ተቀባይነት እንዲያገኙ እንጂ “የመቀየር አለብህ/አለብሽ ” ግፊት ብዙም ምቾት አይሰጣቸውም፡፡ ለዚህ መፍትሄው የፍቅር አጋርዎን አሁን ባለበት ሁኔታ ሳያቅማሙ መቀበል፤ ሁሉም ሰው (እራስዎን ጨምሮ) ጉድለቶች እንዳሉበት መረዳትና የፍቅረኛችንን ክፍተቶች እኛ መሙላት የምንችልበት መንገድ ካለ መሞከር የተሻለ ነው፡፡

2."መወስለት (Cheating)!"

ፍቅር በመርህ ደረጃ የሁለት ተቀራኒ ፆታዎች የአካልና የመንፈስ ውህደትን ይጠይቃል፡፡ ከፍቅረኛችን አሻግረን ሌላ ይምናይ ከሆነ፤ይባስ ብሎም ከሌላ ተቃራኒ ፆታ ጋር የስሜት ትስስር መፍጠር ወይም ወሲብ መፈጸም የፍቅር ግንኙነትን በፍጥነት ከሚገድሉ ጉዳዮች አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ስህተት ውስጥ የገቡ ከሆነ ማድረግ የሚገባዎት የፈጸሙትን ስህተት ለፍቅረኛዎ ነግሮ፤ በቀጣይ መደረግ ስለሚገባው ጉዳይ መወያየት ነው፡፡ ውስልትናን ከፍቅር ጓደኛ ደብቆ ማቆየት ቢቻልም በግንኙነታችን ላይ ተጽዕኖውን በተለያየ መንገድ ስለሚያሳርፍ ፍቅራችንን ይገድለዋል፡፡

3."ማኩረፍ (Silent treatment)!"

በፍቅር ግንኙነት ውስጥአለመግባባቶችና ጸቦች ይከሰታሉ፡፡ፍቅርን ጠብቀው
ከሚያቆዩ ምሰሶዎች አንዱ ግልጽ ውይይት ነው፡፡ ንዴታችን እስኪበርድልን ጠብቀን በአልተግባባንበት ጉዳይ ላይ መነጋገር ወደተሻለ መንገድ ይመራናል፡፡
በተቃራኒው ያልተወያየንባቸው
አለመግባባቶች በውስጣችን በተጠራቀሙቁጥር፤ ግንኙነታችን በየጊዜው ይረበሻል፡፡

4."ውሸት (Lying )!"

የፍቅር ግንኙነትን ጤናማነት ጠብቀው ከሚያቆዩ ነገሮች አንዱ ሀቀኝነት ነው፡፡ማንኛውንም ጉዳይ ለፍቅረኛችን/ የትዳር አጋራችን በግልጽ የመናገር ልምድ ሲኖረን ግንኙነታችን ይጠነክራል፡፡ ነገር ግን ጓደኛችን በሆነ ጉዳይ ላይ ስንዋሽ ከያዘን/ከያዘችን በቀጣይ ለመታመን ዋስትና የለንም::ስለዚህ በተቻለ መጠን እውነቱን ብቻ የመነጋገር ልምድን ማካበት ይኖርብናል፡፡ከዚህም በተጨማሪ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በዝርዝር የመወያየት ባህል ቢኖረን ግንኙነታችን ይጠነክራል፡:ከፍቅር አጋራችን ደብቀን የምንይዛቸው ጉዳዮች ካሉ በጊዜ ሂደት ግንኙነታችንን ሊያሻክሩ ይችላሉ፡፡

5."ቂም መቋጠር (Holding a grudge)!"

ማንም ሰው ከስህተት የጸዳ አይደለም፡፡ ከዚህ በፊት የተሰሩ ስህተቶችንና ይቅርታ የተጠየቀባቸውን ጉዳዮች ሁልጊዜ እንደ አዲስ እያነሱ ፍቅረኛን መውቀስ፦አንቺኮ ከዚህ በፊትም እንዲህ አድርገሽኛል፤አንተኮ ባለፈውም እንዲህ በድለኸኛል እየተባባልን የምንነታረክ ከሆነ ፍቅራችንን ውሃ እያስበላነው ነው፡፡ከቂምና በቀል ያልጸዳ ግንኙነት መሰረቱ ጽኑ አይሆንም፡፡ ስለዚህ በተቻለ መጠን ያለፉ ስህተቶቸን በይቅርታ መርሳት፤ ወደፊት ደግመው እንዳይከሰቱ ደግሞ መፍትሄ መቀየስ ያሻል፡፡

የፍቅር አምላክ ንጹሕ ፍቅር ይስጣችሁ"



Share .......@youthkiller
በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት ዕለት ተዕለት በሚኖራችሁ ህይወት ውስጥ ሁሉም ነገር አስጠልቷችሁ ምንም ለማድረግ ወኔና ፍላጎቱ ጠፍቷችሁ መነሳሳት ከእናንት ርቆ ያውቃል? እንግዲያውስ ህይወትን በኃይልና በመነሳሳት መንፈስ እንደገና ለመጀመር እነኚህን ነጥቦች ይተግብሯቸው፡፡

1. የህይወትን ዓላማ ማወቅ፡- እያንዳንዳችን ወደዚህች ምድር የመጣነው ያለ ዓላማና ምንክንያት ስላልሆነ ለእኛ በህይወት መኖር ለራስና ለሌሎች የሚያበረክተው ጥቅም ስላለው በህይወት የመኖራችንን ዓላማ ጠንቅቀን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

2. ጊዜን በአግባቡ መጠቀም፡- ለሰው ልጅ በነፃ ከተሰጠው የተፈጥሮ ሃብት ውስጥ ጊዜ ነው፡፡ ማድረግ የምንፈልገውንና መሆን የምንመኘውን በጊዜ ቀመር ማስቀመጥ ወደ ምንፈልገው የዕድገት ደረጃ ይመራናል፡፡ ጊዜ ሰይፍ ነው ይቆርጣል ያቆስላል ፤ ጊዜ መድኃኒት ነው ከውድቀት ያነሳል፡፡ “ጊዜን ስሩበት እንጂ አይስራባችሁ!”

3. ተስፋ፡- ዛሬ በእጃችን መዳፍ ውስጥ ናት የስኬትንና የውድቀትን ካርድ ልንመዛባት እንችላለን፡፡ ዛሬ ባይሳካ ነገ ደግሞ ሌላ ቀን ነው ፤ ህይወት ሎተሪ ናትና ደጋግመን መሞከር ያስፈልጋል፡፡ የተሻለ ነገን ለማሰብ ተስፋ ትልቅ ስንቅ ነው፡፡

4. ውድቀትን አለመፍራት፡- ብዙዮች ጠንክረው ላመስራታቸውና ህይወትን በተሻለ መልኩ ላለመኖራቸው ትልቁ ምንክንያት ውድቀትን መፍራት ነው፡፡ ነገር ግን ሰዎች ወድቀው በተነሱ ቁጥር ጠንካራ መንፈስን እንደሚላበሱ ጥርጥር የለውም፡፡ ገና ለገና ባይሳካልኝና ብወድቅ እሳ ብሎ ከመጨነቅ ተፋልሞ ወድቆ መነሳት ይሻላል፡፡

5. በዕቅድ መመራት፡- ህይወት ዝብርቅር እንድትል ከሚያደርጉ ነገሮች ውስጥ አንዱ በዕቅድ አለመመራት ነው፡፡ በዕቅድ መመራታችን በህይወታችን ውስጥ ያሳካናቸውንና ያላሳካናቸውን ነገሮች እንድናውቅ ስለሚረዳን ምን ማድረግ እንዳለብን አቅጣጫ ያሳየናል፡፡

6. አወንታዊ አስተሳሰብ፡- በአሉታዊ አስተሳሰብ ጫና ውስጥ ያሉ ሰዎች የመስራትና የመነሳሳት ስሜታቸው ቀዝቃዛ ነው፡፡ ከብርሃን ይልቅ ጨለማው ቀድሞ ስለሚታያቸው ስልቹዎች ናቸው፡፡ መልካም ማሰብ ወደ መልካም ይመራል ድርጊት ከተጨመረበት፡፡

7. ፍላጎትን መቀነስ፡- መስራትና መሆን የምንፈልጋቸው ነገሮች በበዙ ቁጥር አንድ ነገር ላይ አእምሮአችንንና ጊዜአችንን አሳርፈን መስራት ስለማንችል በምኞት ብዛት ራዕይአችን፤ ጊዜአችንና ጉልበታቸን በከንቱ ይባክናል፡፡

8. ትዕግስት፡- የአንድን ነገር ውጤትና ለውጥ በቅጽበታዊ ጊዜ ውስጥ መፈለግ መነሳሳትን ይገድባል፡፡ በትዕግስት የሚጠባበቁና የሚጥሩ ከሆነ ቢዘገይ እንጂ መድረስ ያለባችሁ ቦታ ከመድረስ የሚያግዳችሁ የለም፡፡

9. ዛሬውኑ መጀመር፡- ስራዎቻችንንና ዕቅዶቻችንን ለማሳካት ከነገ ከመጀመር ይልቅ ከአሁኗ ደቂቃ መጀመር ትልቅ ጥቅም አለው፡፡ የነገን ለነገ በመተው የዛሬን በትንሽ በትንሹ መጀመር ወደ ትልቁ ደረጃ ይመራናል፡፡

10. ስራችንን በደስታ መጀመር፡- ውስጣዊ ስሜቶቻችንን ለስኬቶቻችን ትልቅ አስተዋጽኦ ስለሚኖራቸው የምንሰራውን ስራ መውደድ ይጠበቅብናል፡፡ የማንወደው ስራ ቢሆን እንኳን የምንወደውን ስራ እስክናገኝ የአሁኑን ስራችንን መውደድ አለብን።


JOIN us @youthkiller
#እህቴ_ሆይ: የትዳር💍 ምርጫሽን ስትመርጭ ብር ያለው፣ ቆንጆ የሆነ ተክለ ስውነቱ ያማር፣ወይም ሀብታም ፣የተማረ ድልቅቅ አርጎ የሚያኖርሽ ትፈልጊ ይሆናል አትሳሳች።
#ትዳር በሀብት ብዛት የማትወሰን #በመልክ ማማር የማትመካ ድንቅ #የህይወት_መንገድ ናት ።።
#እህቴ: መልኩ ሳይሆን ቆንጆ ልብ ቆንጆ የሆነውን፣ ልብሱ ሳይሆን ንፁህ ልቡ ንፁህ የሆነውን የህይወት አጋርሸን ከፈለግሸ የምትወጂውን ወንድ ከማንም ጋር አታወዳድሪው ሀይማኖቱን አክብሪና ፈጣሪውን የሚፈራ ባል እንዲሰጥሽ አስተምሪው በትዳርሽ ደስታ እንዲኖርሽ ከፈለግሽ ህይወትሽን ከማንም ጋር አታወዳድሪው ባልሽ ማለት የአባትሽ ምትክ ማለት ነው። #ተንከባከቢው እንጂ አትጨቃጨቂው ወንድ ባልሽ የደስታ ምንጭሽ ነው ከእቅፉ ውስጥ ገብተሽ ሌላ አለም ውስጥ የገባሸ እስኪመስልሽ የሚያስደስትሽ ባልሽ ነው። ያንችባል ላንች ውብና ቆንጆ ንጉስሽ ነው ። አክብሪው በደካማጎኑ ገብተሽ አበርችው ሀይል ሁኚው አጠንክሪው። ከተሳሳተ አስርጂው ደስታን ስጪው ብርታት ሁኚው ያኔ #የህይወት ጣእሙን ታውቂያለሽና ፈጣሪውን የሚፈራ ትዳሩን ያከብራልና።

#ወንዶች_ሆይ: መልክ ትዳር አይሆንም የተስተካከ ተክለ ሰውነቷ ቤትህን አያቆመውም፣ያትልቅ #መቀመጫዋ ለቤትህ #ሶፍ አይሆንህም ልብ በል ትዳር ማለት የህይወትን ጣዕም የምታውቅበት የምትደጋገፍበት በሳል የምትሆንበት አባት የምትሆንበት ከብቸኛነት ወተህ ሁለተኛ እናት የምታገኛበት፣ሀሳብህን የምትጋራልህ፣ መፍትሄ የምስጥህ የህይወትህ ማጣፈጫ ደስታን የምሰጥህ ሴት ከፈለክ መልኳን ሳይሆን ከአስተሳሰቧ፣ከአለባበሷ ሳይሆን ከፈጣሪ ፈሪነቷ፣ ልብ ብለህ እያት #በአሁኑ_ ፈጣሪዋን የምትፈራ ሴት ማገኛት መታደል ነውና። መልኳን ሳይሆን ለአንተ ያላትን አመለካከት አስብ ለዘላለም አብሮህ የሚኖረው ልቧ❤️ ላይ ያለው ላንተ ያላት ፍቅር እንጂ መልኳ አይደለም ወንድሜ ሆይ ለህይወትህ ስኬትን ከፈለክ አይንህ ሳይሆን ልብህ ያርፈባትን ሴት አግባ አይን ቀለዋጭ ነው ብዙ ያምርዋልና ልብህን አዳምጥ። ያንተሚስት ላንተ ብቻ ቆንጆና ውብ ናት ያንተ ሚስት ላንተ ንግስት👑 ናት ወንድሜ ሆይ ሚስትህን ከማንም ጋር አተወዳድራት እራስን ሆኖ መኖር ጥበብ ነው እንደራስ መኖር ብስለት ነው። ህይወትህን ከማንምጋር አተወዳድር (ትዳርህን) እንደራስህ ሆነክ ከኖርክ እራስህን ከማንም ጋር ሳይሆን ከራስህ ጋር ካወዳደርከው በህይወትህ ደስተኛ ነው የምትሆነ።
#መልክ_ትዳር_አይሆንም ጎጆን አያቆምም ፈጣሪዋን ፈሪ ትዳሯን አክባሪ ታዛዥ ሚስት ከፈለክ አንተም ፈጣሪህን ፈሪ ሁን ፈጣሪን የሚፈራ ፍቅርን ያውቃልና: ለሁላችንም ፈጣሪውን የሚፈራ የተባርከና የተቀደሰ
#ፍቅርና_ትዳር_ይስጠን
"#አምላክ_ያገናኛውን_ማንም_አይለየውም"።
Join us @youthkillet
2024/09/21 22:45:21
Back to Top
HTML Embed Code: