Telegram Web Link
የቅዱስ ዮሐንስ ልዩ ጸጋ

ንጽሕና፣ ቅድስና፣ ድንግልና ነው። እንደ ዮሐንስ ስለ ንጽሕና የተነገረለት ሐዋርያ የለም። ቅዱስ ያሬድ ዮሐንስን ስለ ንጽሕናው ስለ ድንግልናው እንደሚከተለው ይገልጠዋል።

“ለትጉሓን ይኤምሮሙ እስመ ኅብረ ንጽሐ ምስሌሆሙ ዮሐንስ ክቡር ሰባኬ ወንጌል መምህር ወድንግል"

ወንጌልን የሚሰብክ ክቡር መምህር ድንግል ዮሐንስ መላእክትን ይመለከታቸዋል፤ በንጽሕና ከእነርሱ ጋር አንድ ሆኖአልና

አኃዊከ ሐዋርያት ያሌዕሉከ በክብር፣ ማኅበረ መላእክት ይኤምኁከ በፍቅር፣ ወንጌላዊ ዮሐንስ ይዌድሱከ ሐዋርያት በእንተ ሥነ ግብርከ፣ ወይትፌግዑ በጣዕመ ቃልከ፡ ይዌድሱከ መላእክት እስመ ኀበርከ ንጽሐ ምስሌሆሙ ዮሐንስ ድንግል ሰባኬ ወንጌል። ብሩህ ከመ ፀሐይ ጽዱል ከመ ባሕርይ

ወንጌላዊ ዮሐንስ ሆይ ወንድሞችህ ሐዋርያት በክብር ከፍ ያደርጉሃል፤ ማኅበረ መላእክትም በፍቅር ሰላም ይሉሃል። ስለ ሥነ ምግባርህም ሐዋርያት ያመሰግኑሃል፣ በቃልህም ጣዕም ደስ ይላቸዋል። መላእከትም ያመሰግኑሃል፡ በንጽሕና ከእነ እርሱ ጋር ተባብረሃልና። ወንጌልንም የምትሰብክ ዮሐንስ ሆይ እንደ ፀሐይ ብሩህ ነህ እንደ ዕንቍም ታንጸባርቃለህ።

ኀረየከ አብ ወአማኅፀነከ ኀበ ወልዱ። ኀረየከ ወልድ ወሰአመከ በአፉሁ። አፍቀረከ እምአርዳኢሁ ወአርፈቀከ በእንግድአሁ። ኀረየከ መንፈስ ቅዱስ ወረሰየከ ሰረገላሁ ትሩፈ ኩሉ ምግባር ዮሐንስ መልአክ ዘበምድር

አብ መርጦሃል፣ ለልጁም አደራ ሰጥቶሃል፣ ወልድም መርጠሃል በአፉም ስሞሃል፣ ከደቀመዛሙርቱም አብልጦ ወዶሃል፣ በደረቱም አስቀምጦሃል፣ መንፈስ ቅዱስም መርጦሃል ማደሪያውም አድርጎሃል። መንፈሳዊውን ሥራ ሁሉ አብዝተህ የምትሠራ ዮሐንስ ሆይ ምድራዊ መልአክ ነህ' ይለዋል/ ድጓ ገጽ 191-192 / (በዜማም ክበሩን ጥሩ አድርጎ ይገልጽለታል።
ከአራቱ ዓበይት ነቢያት አንዱ የሆነው ልዑለ ቃል ቅዱስ ኢሳያስ መስከረም ፮ በዚህች እለት ዕረፍቱን ቅድስት ቤተክርስቲያን ትዘክራለች::

ቅዱስ ኢሳያስ የስሙ ትርጉም መድኃኒት ማለት ነው
የአባቱ ስም አማቴ ይባላል

የሁለት ልጆች አባት የነበረ ሲሆን የልጆቹ ስም

1ኛው "ያሱብ "ትርጉሙ ቅሬታዎች ይመለሳሉ "

2ኛው "ማሔር ሻላል ሐሽ ባዥ " ትርጉሙ ምርኮ ፈጠነ ብዝበዛ ቸኮለ "ማለት ነው

ልዑለ ቃል ቅዱስ ኢሳያስ 66ምዕራፍ ያለው ትንቢት የጻፈ ሲሆን በመጨረሻ በቅዱስ ምናሴ ሰማዕትነት ተቀብሎ(በመጋዝ ተሰንጥቆ )ነው ያረፈው ::


        "ሰላም ለኢሳይያስ ነቢይ ወልደ አሞጽ ዘፈጸመ ገድሎ በሞሠርተ ዕፅ ደራሲ ትንቢተ እምነቢያት ልዑላተ"።

" በዕንጨት መጋዝ ተተርትሮ ገድሉን የፈጸመ ለሆነ ከታላላቆች (ከዐበይት) ነቢያት ይልቅ ትንቢትን ለጻፈ ለነቢዩ ለቅዱስ ኢሳይያስ ሰላምታ ይገባል።

(አባ ጊወርጊስ ዘጋስጫ )

እንኳን አደረሳችሁ አደረሰነ

መስከረም ፮/፩/፳፻፲፯ ዓ. ም 🌻🌼🌻🌻🕊️
New ብርሃን ይሁን ዛሬ Berhan Yihun Zare ዘማሪ ዘውዱ ጌታቸው
<unknown>
እውነት እና ሰላም ፍቅር ከሞላበት
አምላኬ በቤትህ ልኑር በረከት
የሚያምኑትን ከማያምኑ ወገኖች፤ የእግዚአብሔር የሆኑ ወገኖችን የእግዚአብሔር ካልሆኑት የሚለያቸው ጥበብ ይሄ ነው። ሰይጣን ገንዘቡን ወዳጅ ነው፤ ማንም ወገን ገንዘቡን ከያዘበት ከእርሱ አይርቅም ስለዚህ የእግዚአብሔር ወገን መሆን ከፈለግህ የሰይጣንን ገንዘቡን መልስለትና የእግዚአብሔር ልጆች የያዙትን ገንዘብ ገንዘብህ አድርግ። የሰይጣን ገንዘቡ ትዕቢት፣ ራስን ማግነን፣ ከንቱ መታበይ ሲሆኑ የእግዚአብሔር ልጆች ገንዘብ ትህትና ነው።

ብጽዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
(የሕይወት መዓዛ ከሚለው መጽሐፍ የተቀነጨበ )
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ::

ተቋርጦ የነበረውን ጥያቄ እና መልስ መርሐ ግብራችንን እንጀምራለን ::

1,ይህ ቅዱስ ገባሬ መንክራት /መንክራዊ/ (ድንቅ አድራጊ )የሚል ቅጽል ስም ካላቸው ቅዱሳን አንዱ ሲሆኑ ሐዋርያት ሰማዕት ጻድቅ ሊቅ በስም ደረጃ መንክራዊ ተብለው የሚጠሩት እርሳቸው ናቸው :: መቄት ወሎ ገዳማቸው ከአለት ፈልፍለው የሰሩት ገዳማቸው ጣራው ክፍት ነዉ ጸሐይ ይገባል ለአገልግሎት ጥላ ይዘው ያገለግላሉ ዝናብ ግን በፍጹም አይገባም ::እኒህ ቅዱስ ገበያ ተብላ በምትጠራ ስፍራ ገብረ መስቀል እና አመተ ማርያም ከሚባሉ ደጋግ ክርስቲያኖች የተወለዱ ሲሆን በልጅነታቸው የቤተክርስቲያንን ትምህርት ጠንቅቀው ተምረው አድገዋል :: ለምናኔያቸው ምክንያት የሆናቸው በዲቁና እያገለገሉ እያሉ ፍሕም ሲጭሩ እሳት በልታቸው ምድራዊ እሳት ይህንን ያክል ካቃጠለኝ የሰማያዊውማ እንዴት ሊያደርገኝ ነዉ ብለው መንነዋል ::የመነኮሱት ታላቁ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ያሉበት ደብረ ጎል (ጋስጫ )ሄደው መንኩሰዋል ::ሁለት ጊዜ መከራ ደርሶባቸዋል አንደኛው በአጼ ዓምደ ጽዮን ዘመን ከአቡነ በጸሎተ ሚካኤል ጋ  ሁለተኛው በአጼ ሰይፈ አርዕድ ዘመን ሰማዕትነትን በሁለት ነገሥታት እጂ የተቀበሉ ነሐሴ አምስት ተወልደው መስከረም 5 ያረፉ እኒህ ቅዱስ ማናቸው?

መልሱን በዚህ አስቀምጡልን ⤵️
https://www.tg-me.com/felege_haymanot
"ሰላም ለገብርኤል ለኤልሳቤጥ ዘአስተፍስሓ ቀዲሙ
ይመጽእ ቃል ለልዑል እምአርያሙ
ተፈስሒ ዘይብል ከመ ለማርያም እሙ
ዲዮስቆሮስ እስመ ነሥአኪ ውስተ ቤተ ሐዲስ ዓለሙ
ዐስበ ጥረሲሁ ውዱቅ ወንጹይ ጽሕሙ።"

"ሰላም ለኤልሳቤጥ ለሶፍያ ወለታ
ወለማርያም እኅታ
በውስተ ገዳም ነጺሮ ከመ ይእቲ ባሕቲታ
መንፈሰ ስምዖን ነቢይ ወመንፈሰ ዘካርያስ ምታ
እግዚአብሔር አዘዘ ይምጽኡ በሞታ።"

(ዐርኬ )


" ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት፥ በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች፡— አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው። የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?እነሆ፥ የሰላምታሽ ድምጽ በጆሮዬ በመጣ ጊዜ ፅንሱ በማኅፀኔ በደስታ ዘሎአልና። ከጌታ፤ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብፅዕት ናት።"
(ሉቃስ ፩፥፵፩-፵፭)


እንኳን ለቅድስት ኤልሳቤጥ, ለቅዱስ ዲዮስቆሮስ አበ ተዋሕዶ, ለቅዱስ ሳዊርያኖስ ዘገብሎን ዓመታዊ የእረፍት መታሰቢያ የቅድስት ሐና ልደቷ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን
Audio
#ንፉግ ሰው ልቡናውን ቅር እያለው ይሰጣል። ሰነፍም ይለገዳል አይመሰግንም። ሳትናገር አስቀድመህ ነገሩን ተረዳ በኃጢአት ሳትታመም ንስሐ ግባ። ሳይፈረድብህ ተዋረድ በመከራህም ጊዜ ይቅርታ ታገኛለህ። ሳትደክም ራስህን አዋርድ በበደልህም ጊዜ ተለማመጥ። ስእለትህን አታስቀር ፈጥነህ ስጥ ሳትሞትም ጽድቅን ሥራት። ሳትሳልም አስቀድመህ ስእለትህን አዘጋጅ እግዚአብሔርን እንደሚፈታተነው ሰው አትሁን። በተቈጣህም ጊዜ የምትሞትባትን ቀን አስባት ፍዳ የምትቀበልባትን ቀን አስበህ ንስሐ ገብተህ ተለማመጥ። በጠገብህበትም ወራት የተራብህበትን ወራት አስብ።
Audio
ክርስትናና ሚዲያ እንዴት? 
                                                  
Size:- 102.2MB
Length:-1:50:26
       
     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
http://www.tg-me.com/abagebrekidan
http://www.tg-me.com/abagebrekidan
የእግዚአብሔርን ፍርድ የሚያዘገየው የእኛ ተልካሻ በቀል ነዉ ::

(መምህር ሳሙኤል አስረስ )
ኑ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን :: ተቋርጦ የነበረውን ጥያቄ እና መልስ መርሐ ግብራችንን እንጀምራለን :: 1,ይህ ቅዱስ ገባሬ መንክራት /መንክራዊ/ (ድንቅ አድራጊ )የሚል ቅጽል ስም ካላቸው ቅዱሳን አንዱ ሲሆኑ ሐዋርያት ሰማዕት ጻድቅ ሊቅ በስም ደረጃ መንክራዊ ተብለው የሚጠሩት እርሳቸው ናቸው :: መቄት ወሎ ገዳማቸው ከአለት ፈልፍለው የሰሩት ገዳማቸው ጣራው ክፍት ነዉ ጸሐይ…
መልሱ አቡነ አሮን መንክራዊ ዘመቄት ናቸው ::

ጥያቄ ቁጥር ፪


እኒህ  ኢትዮጵያዊ ጻድቅ ንጉሥ የአጼ ዮሐንስ 2ኛ (የባለ አንድ እጅ )ልጅ ናቸው ::አባታቸው አጼ ዮሐንስ 2ኛ  በስተ እርጅናቸው ለአንድ ዓመት አሻንጉሊት ንጉሥ ሆነው ከቆዩ ቡሃላ በነገሡ  በ 1ዓመታቸው አርፈው ልጃቸው ኃያል ሰገድ ተብለው ተሹመዋል በ1763 ዓ/ም ገና በ15 ዓመታቸው በአባታቸው ዙፋን ላይ ተቀምጠው በጎንደር ዘመን ለሰባት ዓመት ሃገርን ሲያስተዳድሩ የነበር ሲሆን በአጭር ጊዜ የንግሥና ዘመናቸው ቡዙ አብያተ ክርስቲያናት አሳንጸዋል ጥቂት የማይባሉም አብያተ ክርስቲያናት አሳድሰዋል:: ዘመኑ በስዑል ሚካኤል የስልጣን ጥመኝነት ምክንያት ዘመነ መሳፍንት እገባ እገባ ዘመነ ነገሥት እወጣ እወጣ እያለ  ነበር :: በውስጥ በሰቅ ወገባቸውን ታጥቀው ዙፋን ላይ ተቀምጠው ሲፈርዱ ይውላሉ  ማታ ማታ ደግሞ በጸሎት በስግደት ሲተጉ ያድራሉ :: በእንዲህ እያሉ መንግሥታቸውን ትተው ዋልድባ ገዳም ገብተው ለ1ዓመት ከ6ወር (6 ወርም ይላል )ቆይተው መስከረም 7 ቀን አርፈዋል :: ስማቸው ሲጠራ መናኔ መንግሥት ተብሎ ተቀጽሎ የሚጠራ እኒህ ደገኛ ንጉሥ ማናቸው?!

መልሱን በዚህ ሊንክ አስቀምጡልን
https://www.tg-me.com/felege_haymanot
ኑ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ
መልሱ አቡነ አሮን መንክራዊ ዘመቄት ናቸው :: ጥያቄ ቁጥር ፪ እኒህ  ኢትዮጵያዊ ጻድቅ ንጉሥ የአጼ ዮሐንስ 2ኛ (የባለ አንድ እጅ )ልጅ ናቸው ::አባታቸው አጼ ዮሐንስ 2ኛ  በስተ እርጅናቸው ለአንድ ዓመት አሻንጉሊት ንጉሥ ሆነው ከቆዩ ቡሃላ በነገሡ  በ 1ዓመታቸው አርፈው ልጃቸው ኃያል ሰገድ ተብለው ተሹመዋል በ1763 ዓ/ም ገና በ15 ዓመታቸው በአባታቸው ዙፋን ላይ ተቀምጠው በጎንደር ዘመን ለሰባት…
መናኔ መንግሥት ተክለ ሃይማኖት ናቸው

ቃለሕይወትን ያሰማልን በትክክል ተመልሷል ::

ጥያቄ ቁጥር 3

ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ወደ ጋግራን ደሴት በንጉሡ ትእዛዝ ሲደድ አብሮት ወደ ጋግራን ተሰዶ የነበር እና ቡሃላ በእስክንድርያ ሰማዕትነት ትቀበላለህ ብሎት ወደ እስክንድርያ ሄዶ ኩላሊቱን ረግጠውት ገድሉን ፈጽሟል, ሲቀድስ ሁል ጊዜ ጌታን ከመላእክቶቹ ጋር ያየው ነበር, ከብቃቱ የተነሳ የሰው ሁሉ ኃጢያት በግንባራቸው ላይ ይታየው ነበር ይህ ጳጳስ እና ሰማዕት ማነው?

ሀ, ታላቁ መቃርስ
ለ, ቅዱስ መቃርስ ዘእስክንድርያ(ሊቀ ጳጳስ )
ሐ, ቅዱስ መቃርስ ዘሀገረ ቃው
መ, ቅዱስ መቃርስ ቆቅ በሊታው
Audio
በጎ ዘመን 2017 
                                                  
መዝሙረ ዳዊት 33

11፤ልጆቼ፡ኑ፥ስሙኝ፤እግዚአብሔርን፡መፍራት፡አስተምራችዃለኹ።
12፤ሕይወትን፡የሚፈቅድ፡ሰው፡ማን፡ነው፧በጎንም፡ዘመን፡ለማየት፡የሚወድ፟፧
13፤አንደበትኽን፡ከክፉ፡ከልክል፥ከንፈሮችኽም፡ሽንገላን፡እንዳይናገሩ።
14፤ከክፉ፡ሽሽ፡መልካምንም፡አድርግ፤ሰላምን፡ሻ፥ተከተላትም።
       
     በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
http://www.tg-me.com/abagebrekidan
http://www.tg-me.com/abagebrekidan
Audio
ባንደበቱ ያልሳተ ሰው የተደነቀ ነው። ቁጣ ሳይበዛ ወዳጅህን ተቈጣው ጥበብ ሁሉ ሕጉን የምታሠራ ስለ ሆነች ጥበብ ሁሉ እግዚአብሔርን መፍራት ነውና። ስለእግዚአብሔር ሕግ ብለህ የጸናች ቁጣን አሳልፋት ጥበብ ሁሉ ሕጉን ታስጠብቀዋለችና። ጥበብ ሁሉ እግዚአብሔርን መፍራት ነው። ክፉ ነገርን የሚያስተምር ጥበብ የለም።
ኑ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ
መናኔ መንግሥት ተክለ ሃይማኖት ናቸው ቃለሕይወትን ያሰማልን በትክክል ተመልሷል :: ጥያቄ ቁጥር 3 ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ወደ ጋግራን ደሴት በንጉሡ ትእዛዝ ሲደድ አብሮት ወደ ጋግራን ተሰዶ የነበር እና ቡሃላ በእስክንድርያ ሰማዕትነት ትቀበላለህ ብሎት ወደ እስክንድርያ ሄዶ ኩላሊቱን ረግጠውት ገድሉን ፈጽሟል, ሲቀድስ ሁል ጊዜ ጌታን ከመላእክቶቹ ጋር ያየው ነበር, ከብቃቱ የተነሳ የሰው ሁሉ ኃጢያት በግንባራቸው…
ቃለሕይወትን ያሰማልን

ንጉሠ ነገሥት ተክለ ሃይማኖት 2ኛ ናቸው


ጥያቄ ቁጥር 4

እኒህ ቅዱስ አባት በ308 ዓ. ም ተወልደው የግሪክ አቴናን ፍልስፍናና ጥበብ ጠንቅቀው የተማሩ ናቸው፡፡ምግባር ሃይማኖታቸው የሰመረ፣ ትሩፋት ተጋድሏቸው የቀና ነው፡፡ብሉይን ከሐዲስም አጠናቀው ተምረዋል፡፡ወላጆቻቸው ያወረሷቸውን እጅግ የተትረፈረፈ ንብረት ሸጠውና ለጦም አዳሪዎች መጽውተው ለድኆች ማደሪያና ለእንግዶች ማሪፊያ ቤት ሠርተው ነዳያንን ይንከባከቡ ጀመር፡፡ይህንንም የጽድቅ ሥራቸውን የሮሜው ጻድቁ ንጉሥ አኖሬዎስ ሲሰማ እጅግ ደስ ተደስቶ አስመጥቶ ከእርሱ ጋር በቤተ መንግሥቱ አማካሪና አባቱ አድርጎ አኖራቸው፡፡ከንጉሡም ጋር አብረው ሁልጊዜ ወደ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ ሌሊቱን በሙሉ ለጸሎት ቆመው ያድራሉ፡ጻድቁ የገብላው አገር ንጉሥ ሴት ልጁን ሰይጣን ይዟት ሳለ ደብዳቤ በመጻፍ ልከው በልጅቷ ላይ ያደረውን ሰይጣን በደብዳቤአቸው ብቻ አስወጥተውታል፡፡እኒህ አባት ደብዳቤ በመጻፍ ብቻ በሀገር ላይ የመጣ የጠላትንም ጦር
እያሸበሩ ድል ያደርጉ ነበር፡፡ አበው እንደሚነግሩን በዚያን ጊዜ በቁስጥንጥንያ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ, በሶርያ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ, በግብጽም እንዲሁ በጸሎት የተጉ አበው ስለ ነበሩ ሰይጣን መንገድ ለመንገድ እያለቀሰ ይታይ ነበር ይባላል :: ይህ አባት ጥንተ ሃገሩ ኤላ, ሃገረ ስብከቱ ገብላ , ምናኔ ሃገሩ ደግሞ አስቀሎና ናት :: ከብዙ ተጋድሎ ቡሃላ በ100 ዓመቱ 408 ዓ. ም መስከረም 7 ቀን አርፏል ማነው?

ሀ, ቅዱስ ሳዊሮስ ዘእስሙናይ

ለ ቅዱስ ሳዊርያኖስ ዘገብሎን

ሐ, ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ

መ, ቅዱስ ቴዎፍሎስ ዘአንጾኪያ
ኑ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ
ቃለሕይወትን ያሰማልን ንጉሠ ነገሥት ተክለ ሃይማኖት 2ኛ ናቸው ጥያቄ ቁጥር 4 እኒህ ቅዱስ አባት በ308 ዓ. ም ተወልደው የግሪክ አቴናን ፍልስፍናና ጥበብ ጠንቅቀው የተማሩ ናቸው፡፡ምግባር ሃይማኖታቸው የሰመረ፣ ትሩፋት ተጋድሏቸው የቀና ነው፡፡ብሉይን ከሐዲስም አጠናቀው ተምረዋል፡፡ወላጆቻቸው ያወረሷቸውን እጅግ የተትረፈረፈ ንብረት ሸጠውና ለጦም አዳሪዎች መጽውተው ለድኆች ማደሪያና ለእንግዶች…
ቃለሕይወትን ያሰማልን በትክክል ተመልሷል

ቅዱስ ሳዊርያኖስ ዘገብሎን ነዉ ::በረከቱ ይደርብን ::


ጥያቄ ቁጥር 5,


በእምነት ከማትመስላት አይሁዳዊት ቤት አገልጋይ ሆና ስትኖር እምነቷን ልታስቀይራት ብዙ ሞክራ አልሳካ ቢላት አሰሪዋ የገደለቻት በሃማኖቷ ጸንታ እምነቷን ጠብቃ ሰማዕትነትን የተቀበለች ይህች ቅድስት እናት ማናት?


https://www.tg-me.com/felege_haymanot
ኑ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ
ቃለሕይወትን ያሰማልን በትክክል ተመልሷል ቅዱስ ሳዊርያኖስ ዘገብሎን ነዉ ::በረከቱ ይደርብን :: ጥያቄ ቁጥር 5, በእምነት ከማትመስላት አይሁዳዊት ቤት አገልጋይ ሆና ስትኖር እምነቷን ልታስቀይራት ብዙ ሞክራ አልሳካ ቢላት አሰሪዋ የገደለቻት በሃማኖቷ ጸንታ እምነቷን ጠብቃ ሰማዕትነትን የተቀበለች ይህች ቅድስት እናት ማናት? https://www.tg-me.com/felege_haymanot
ቃለሕይወትን ያሰማልን በትክክል ተመልሷል

ቅድስት መጥሮንያ ናት ::በረከቷ ይደርብን ::

ጥያቄ ቁጥር 6

ይህችንም ቅድስት እናት ሌላ ሰው አስገድዶ ከባሏ ለያትና ከባሏ ጋር የነበራትን አንድነት አበላሸ። ያን ጊዜም ታላቅ ኀዘን በማዘን ተጸጸተች፣ መሪር ልቅሶንም አለቀሰች። በኋላም ልክ እንደ ቅድስት እንባ መሪና የወንድ ልብስ ለብሳ ስሟን ቴዎድሮስ ብላ መንኲሳ በጽኑዕ ገድል መጋደል ጀመረች። በዚህም ገድሏ የቀና ሰይጣን ተንኮል አበጀባት። በዚያ አካባቢ የምትኖር አንዲትን ብላቴና ከአንድ ሰው ጋር አመነዘረችና ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደች። ይህንም ቤተሰቦቿ ሲያዩ ማነው እንዲህ ያደረገሽ ቢሏት በዚያ ገዳም ያለው አባ ቴዎድሮስ ነው አለች ። እነርሱም ልክ እንደሰሙ ወደ አበምኔቱ ኼደው ልጁን ሰጡትና ኾነ የተባለውን ኹሉ ነገሩት። አበምኔቱም ቅድስቲቱ አስጠርቶ ለምን እንዲህ አደረግህ ብሎ ተቆጣት (ሴት መኾኗን አያውቅምና በወንድ ነው የጠራት) ፣ እርሷም አባቴ ማረኝ፣ ስቻለሁ ብላ ከእግሩ ወደቀች። አበ ምኔቱም ተቆጥቶ ልጁን ሰጣትና ከገዳሙ አስወጥተዋት ለሰባት ዓመታት ልጁን እያሳደገች ከአጋንንትም የሚደርስባትን ጽኑዕ ጸብዕ ኹሉ ታግሣ ቆየች። ኋላም ወደ ገዳሙ ከመለሷት ከጥቂት ጊዜ በኋላ መስከረም 11 ቀን አርፋለች ይህች ቅድስት እናት ማናት?!

ዕለተ እረፍታቸውን የምንጠቁመው ሁላችንም ስንክሳር እንዲናነብ ነዉ
Forwarded from 🟢ናታኒም ፖሮሞሽን🟢
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከ15 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል


የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

10+10×0+10=???
2024/09/21 00:18:11
Back to Top
HTML Embed Code: