Telegram Web Link
Audio
⛪️ #ፈታሔ ማኅፀን፣ከሣቴ ዕውራን
     ፈዋሴ ድውያብ ፣ሰዳዴ አጋንንት
#ቅዱስ_ሩፋኤል_ሊቀ_መላእክት
     ከመላእክት አለቆች ሦስተኛ
""በሰው  ቁስል የተሾመ ከክብሩ
ከመላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው""

    🍃በዲ/ን ጥበቡ ማሞ

  🌹መልካም ቆይታ አድምጡ 👂🥀


@yetwahdotemrtmaskemch
Audio
3.ድንገተኛ ወዳጅ እንደሱ አይሆንህምና የቀድሞ ወዳጅህን አትተወው። አዲስ ወዳጅ ጉሽ ጠጅ ነው ቢከርም ግን ደስ ብሎሀ ትጠጣዋለህ። እንዲጠፉ አታውቅምና የኃጥአን ብልጽግናቸው አያስቀናህ። የእግዚአብሔርን ሕግ የዘነጉ ሰዎች ተድላቸው አያስጐምጅህ እስኪሞቱ ድረስ እንዳይከብሩ አስብ።
ወንድሞቼ "እገሌ እኮ እንዲህ እንዲህ ዓይነት ኃጢአት ሠርቷል" ብላችሁ የምታሙትን ወንድማችሁ ከዚያ ኃጢአቱ ነጻ እንዲወጣ ትፈልጋላችሁን? እንግዲያስ ስለ ኃጢአቱ አልቅሱለት፤ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩለት፤ ለብቻ ወስዳችሁም ምከሩት እንጂ አትሙት። ሐዋርያው ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ክርስቲያኖች እንዲህ ብሎ ጽፎላቸው ነበር፡- "ነገር ግን ወዳጆች! እናንተን ልናንጻችሁ ሁሉን እንናገራለን። ስመጣ እንደምወደው ሳትሆኑ አገኛችሁ ይሆናል፤ እኔም እንደምትወዱት ሳልሆን ታገኙኝ ይሆናል ብዬ እፈራለሁና፡፡ ምናልባት ክርክር ቅንዓትም ቁጣም አድመኝነትም ሐሜትም ማሾክሾክም ኩራትም ሁከትም ይሆናሉ፡፡ እንደ ገና ስመጣ በእናንተ ዘንድ አምላኬ እንዲያዋርደኝ፥ አስቀድመውም ኃጢአት ከሠሩትና ስላደረጉት ርኵሰትና ዝሙት መዳራትም ንስሐ ካልገቡት ወገን ስለ ብዙዎች ምናልባት አዝናለሁ ብዬ እፈራለሁ" /2ቆሮ.12፥19-21/። ስለዚህ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ በትልቁ ደግሞ እንደ ጌታችን "ኃጢአተኛ ነው" የምትሉትን ወንድማችሁ ውደዱት፡፡ ለብቻው አድርጋችሁ ስትነግሩትም አመጣጣችሁ እርሱን ለመምከርና ለመገሰጽ ደግሞም ከኃጢአቱ እንዲመለስ እንጂ እርሱን ከመጥላታችሁ የተነሣ እንዳልሆነ አስረዱት፡፡ ስለዚህ በትክክል ካለበት ደዌ እርሱን መፈወስ ስትፈልጉ ወደ እርሱ መሄድን አትፍሩ፤ ጥፋቱን ለመንገርም አትፈሩ፡፡

ሐኪሞችን አይታችሁ ከሆነ አንድ አስቸጋሪ ታማሚን ለማከም መጀመርያ ቀስ ብለውና ጊዜ ወስደው ታማሚዉን ያሳምኑታል፤ ከዚያም መራሩን መድኃኒት ይሰጡታል፡፡ ታካሚውም በሽታው የሚድን ከሆነ ይፈወሳል፡፡ ሐኪሙን የሚያመሰግነው ግን ሲድን ነው፡፡ እናንተም እንደዚህ ሐኪም መሆን አለባችሁ፡፡ ከምታሙት ይልቅ የወንድማችሁን ቁስል የበለጠ እንዳይመረቅዝ ፈጥናችሁ ወደ ሐኪም ቤት (ወደ ቤተክርስቲያን) ውሰዱት። ከዚያም ሐኪም (ካህን) እንዲያየው አድርጉ፡፡ እንዲህ ስታደርጉ እናንተም ወንድማችሁም በእጅጉ ትጠቀማላችሁ፡፡ እውነተኛ ጦም ጦማችሁ ማለትም እንዲህና ይህን የመሰለ መልካም ምግባር ስታደርጉ ነው፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖

🌻 የ፳፻፲፭ (2015) ዓ/ም🌻

💠ዝክረ_ቅዱሳን በእግዚአብሔር ቸርነት ደረሰ፡፡ ተፈጸመ፡፡ 💠

✞ ዘአቅረብኩ ማኅሌተ . . . ✞

☞"ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ"
(አእላፍ ቅዱሳንን አዘክሬ ምስጋናን አቀረብኩልህ)

☞"እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ"
(እሊህ ቅዱሳንም ዘወትር አንተን ያገለገሉህ ናቸው)

☞"ለእለ አነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ"
(በድኅነቴ የማነብልህን መጽሐፍ /ምስጋና/ ተቀበል)

☞"እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ: እም እለ አብኡ ብዑላን ዘተርፈ"
(አንተ ብዙ ባለ ጠጐች ካገቡት ይልቅ የድሃዋን መበለት ስጦታን ተቀብለሃልና)

☞"ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባክያን"
(ቅዱሳን የሆናችሁ ነቢያት: ለማስተማር የተመረጣችሁ ሐዋርያት)

☞"ሰማዕታት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን"
(ሰማዕታት: ጻድቃን: ትጉሃን የሆናችሁ መላእክት)

☞"ደናግል ዓዲ ወመነኮሳት ሔራን"
(እናንተም ደናግል: ቸር የሃናችሁ መነኮሳት)

☞"ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን"
(ይህችን ጉባኤ /አንድነታችንን/ መባረክን ባርኩ)

☞"እስከ አረጋዊ ልሒቅ እምንዑስ ሕጻን"
(ስትባርኩም ከሕጻናቱ ጀምራችሁ እስከ ሽማግሌው ድረስ ይሁን)

☞"ለዘጸሐፎ በክርስታስ"
(በብራና: በወረቀት የጻፈውን)

☞"ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ"
(ሊያስደርስ በገንዘቡ ዋጅቶ ያጻፈውን)

☞"ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ"
(አምኖ ያነበበውን: ወደ ሌላ ልሳን የተረጐመውንም)

☞"ወለዘሰምዐ ቃሎ በዕዝነ መንፈስ"
(በዕዝነ ልቡና አምኖ የሰማውን)

☞"በጸሎተ እሙ ማርያም አራቂተ ኩሉ እምባዕስ"
(ከጠብ ከክርክር: ከመከራ ከችግር በምትሰውር በእናቱ በማርያም ጸሎት)

☞"ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ"
(ኢየሱስ ክርስቶስ ሁላችን አንድ ላይ ይማረን)

☞"ወይፈኑ ለነ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ"
(ቅዱስ መንፈሱንም ይላክልን)

☞"እምይእዜ ወእስከ ለዓለም አሜን"
(ከዛሬ ጀምሮ ለዘለዓለሙ አሜን)

✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞

ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር

https://www.tg-me.com/zikirekdusn
🌻🌻🌻"እንኳን አደረሳችሁ !"🌻🌻🌻

"በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል። የምድረ በዳ ተራሮች ይረካሉ ፥ ኮረብቶችም በደስታ ይታጠቃሉ። ማሰማርያዎች መንጎችን ለበሱ ፥ ሸለቆችም በእህል ተሸፈኑ ፤ በደስታ ይጮኻሉ ይዘምራሉም።"
[ መዝ.64፥11 ]

          🌻 2⃣0⃣1⃣7⃣🌻

እንኳን ከዘመነ ቅዱስ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ቅዱስ ማቴዎስ በሰላምና በጤና አሸጋገራቹ፡፡  ዘመኑን የንሰሃና የፍሬ ያድርግላቹሁ  ያድርግልን እንደ ቸርነቱ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላምን፣ ፍቅርን፣አንድነትን ይስጠን ያድለን አሜን ፫፡፡

🌼 የታመሙትን ፈውሶ፡፡
  🌼የወጡትን በሰላም መልሶ፡፡
🌼ያለቀሱትን እንባቸውን አብሶ፡፡
🌼የወደቁትን አንስቶ፡፡
🌼በግፍ የታሰሩትን ፈትቶ፡፡
🌼የሞቱትንም ነፍሳቸውን ይማርልን፡፡
      ቸሩን ዘመን ይስጠን አሜን ፡፡


   🌻መልካም አዲስ ዓመት🌻
Audio
⛪️ #ዘመኑ ለጽድቅ የምንበቃበትን
    ተግባር የምንፈጽምበት ይኹን።
#ኹላችንም ወደ እግዚአብሔር እንመለስ
#የቤተ ክርስቲያን ጸሎትና ውለታዋ••••
#ከአቅማችን በላይ የኾነውን ለአምላካችን
መተው /ማቴ• 17፥21:ዘዳ •28፥ 15~28/


    🍃በዲ/ን ጥበቡ ማሞ

  🌹መልካም ቆይታ አድምጡ 👂🥀


@yetwahdotemrtmaskemch
“ወውእቱ ይዌልጥ ዓመታተ ወመዋዕለ ወያነብር ነገሥተ ወይስዕር ወይሁቦሙ ጥበበ ለጠቢባን ወምክረ ለመካርያን”

“እርሱ ጊዜያትንና ዘመናትን ይለውጣል፤ ነገሥታትን ያስነሣል ፤ ነገሥታትንም ይሽራል ፤ ጥበብን ለጠቢባን ምክርን ለመካርያን (እውቀትንም ለአስተዋዮች) ይሰጣል ።” (ት.ዳን፪፥፳፩)


መስከረም 4

-ትምህርት በመጋቤ ምሥጢር ያሬድ ዘርዓ ቡሩክ

ለእለቱ የሚስማማ የተመረጡ ዜማዎች በየኔታ ልብሰ ወርቅ (የቅዳሴ መምህር )


መዝሙር  -በዘማሪ አቤል ብርሃኑ

የበገና መዝሙር -በዲያቆን ኢዮብ ጻድቁ



ግጥም እና
ሥነ ጹሑፍ  በማኅበሩ ልጆች

እና ሽልማት ያለው የጥያቄ እና መልስ ውድድር ተዘጋጅቷል

🌻🌻🌻🌻 መልካም በዓል

https://www.tg-me.com/felege_haymanot

https://www.tg-me.com/+zfynpJbtDPQyODU8
Audio
ሥር ሰዳችሁ እደጉ 
                                                  
Size:- 68.3MB
Length:-1:13:47
       
     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
http://www.tg-me.com/abagebrekidan
http://www.tg-me.com/abagebrekidan
Audio
ጥበብን ተከተላት መሥጢሯንም መርምር ሥራቷንም ጠብቅ። መስኮቷን የሚጐበኝ ባደባባይዎቿም ተቀምጦ የሚያዳምጥ። በቤቷም አጠገብ የሚኖር በዙሪያዋም የድንኳኑን ካስማ የሚተክል። ሰውነቱን በሥልጣኗ የምያስጠብቅ ባማረ ማደሪያዋም የሚኖር። ልጆቹንም በረድኤቷ የሚያስጠብቅ በዘጠኙም ሕገጋት ጸንቶ የሚኖር። በሷም ከመከራው የሚያርፍ በክብሯም ጸንቶ የሚኖር ሰው የተደነቀ ነው።
ኑ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ
Photo
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
መስከረም ፬ በዚህች እለት ከ ፲፪ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ የሆነ  ባለ ራዕይ የተባለ፤ የፍቅር ሐዋርያ ፣ጸጋና ደግነትን ሁሉ የተሰጠው፤ ገናናው የእግዚአብሔር ካህን ፤እንዴ ውድ ጌጥ በእግዚአብሔር ጣት ላይ የሚያበራ፤ ጹሁፎቹ ሁሉ ለመላው ዓለም እንዴ መለኮታዊ መብራት የሚያበሩ የሆኑ ሰባቱን የመስቀል ላይ ጩኸቶቹን የሰማ የጌታን መከራ ያየ ወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ በዓለ ልደቱን ቅድስት ቤተክርስቲያን ትዘክራለች ::

" በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው"
(ኤፌ ፪፥፳) እንዲል ቅዱስ ጳውሎስ

• የሚታየውን ንቀው ፣የማይታየውን ተዋግተው፤ ካሸነፉ የቤተክርስቲያን መሶሶ እና ግድግዳ ሆነው እንዴ እሳት ነደው፤ እንዴ ግንድ ተለብልበው፤ እንዴ ሰም ቀልጠው ካጸኗት አንዱ ይህ ሐዋርያ ቅዱስ ዮሐንስ ነው ::
•አስቀድሞ በአሳ አጥማጅነት ግብር ቡሃላ ከቅዱስ እንድርያስ ጋ የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት ደቀ መዝሙር የነበር ፤ቡሃላም መጥምቁ ዮሐንስ የዓለምን ኃጢያት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግዕ ብሎ ሲናገር ሰምተው ጌታን ከተከተሉት ከሁለቱ ደቀ መዛሙርት አንዱ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ነው ::

•አባቱ ቅዱስ ዘብድዮስ፣ እናቱ ቅድስት ማርያም ባውፍልያ፤ ታላቅ ወንድሙ ደግሞ ቁጥሩ ከአሥራ ሁለቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ የሆነው ፣ ቡሃላም በ፵፬ ዓ. ም ከ፲፪ቱ ደቀ መዛሙርት አስቀድሞ መጀመሪያ ሰማዕትነትን እዛው ኢየሩሳሌም የተቀበለ ቅዱስ ያዕቆብ ወልደ ዘብድዮስ ነው ::

•ዮሐንስ ማለት ርኅራኄ ወሣህል ማለት ነው ::በጸጋ ዘነሳእክሙ በጸጋ ሀቡ በከንቱ ዘነሳዕክሙ በከንቱ ሀቡ ባለው ጸንቶ ያስተምራልና ::

•አንድም ፍሥሐ ወሐሴት ማለት ነው ::ቅብዐ ትፍሥሕት መንፈስ ቅዱስን አሰጥቶ ዴስ ያሰኛልና ::
ከቡዙ መጠርያ ስሞቹ ጥቂቱ
•ወልደ ነጎድጕድ :-ውሉደ መንግሥት ወክህነት ሲል ነው ::የዘር ሐረጉ ከቤተ መንግሥት እና ከቤተ ክህነት ነውና ::
•ነባቤ መለኮት :-ንጽሐ ሥጋ ንጽሐ ነፍስ ንጽሐ ልቡና ተሰጥቶት ቀዳሚሁ ቃል ብሎ የምሥጢረ ሥላሴን አንድነት ሦስትነቱን አምልቶ አስፍቶ ስለተናገረ/ ተናግሯልና::
-ፈለገ ሃይማኖት
-ልዑለ ስብከት
-ንስር ሠራሪ
-ኮከበ ከዋክብት
-ዓምደ ብርኃን....
...
•ሶስቱ ወንጌላውያን ያስቀሩትን በማካተት ወንጌልን ጽፏል
•3ቱን መልዕክታት
•ራዕየ ዮሐንስን
•ድርሳነ ዑራኤልን
•በስሙ የሚጠራ መጽሐፈ ቅዳሴውን (አኰቴተ ቁርባን ዘቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጕድ )የጻፈው ይህው ሐዋርያ ነው

•  የተጠራው ገና በለጋነት እድሜው በ፳ ዓመቱ እንደነበር አባ ጀሮም(ይሩማሲስ ) ተናግሯል ::
•በታላቁ ንጉሥ ከተማ በኢየሩሳሌም በእስያስ በኤፌሶን እና በዛ ዙሪያ ባሉ ሀገሮች ሁሉ ዞሮ ሰብኳል ::

•ታኅሳስ    ፅንሰቱ
•መስከረም ፬ :-ልደቱ
•መስከረም ፳፱:- ወንጌሉን የጻፈበት
•መስከረም ፴ :-ከወንድሙ ጋ መጠራቱ
•ጥር    ፬ -ሞትን ሳይቀምስ የተሰወረበት
•ግንቦት ፲፮ :-የራዕዩን መጽሐፍ የጻፈበት በእስክንድርያ ሀገር በቅዳሴ ቤቱ የከበረበት ወደ ፍጥሞ ደሴት በንጉሡ ትዕዛዝ የተጋዘበት
•ሐምሌ ፳፯ በእስክንድርያ ቅዳሴ ቤቱ ብሎ ስንክሳር ያነሳዋል
ከጌታ ጎን ይቀመጥ የነበር "ዘረፈቀ ውስተ ኅጽኑ "፤ የፋሲካውን እራት ያዘጋጀ ፤ሙታንን ሲያነሳ፤ እውራንን ሲያበራ ፥የቃሉን ትምህርት ፥የእጁን ተአምራት የተመለከተ ፤የምስጢር ሐዋርያት ከሚባሉት አንዱ የሆነ ፤ወዳጅ በጠፋ ጊዜ የቁርጥ ቀን ወዳጅ ሆኖ የተገኘ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ፤ቅዱሳን ነቢያት እጅግ በለቅሶ እና በሐዘን ሆነው ሲሽዋት ሲፈልጕት የነበረችውን የሽቶዋን ቢልቃጥ፤ ሙዳየ አሚን በአደራነት የተቀበለ እነ ቅዱስ ዳዊት ማደርያው ወደት ነው እያሉ አርቀው ሲጣሩ የነበረውን የአምላክ ማደርያ ያይ ዘንድ የተመረጠ ፤መልካም መዓዛ ያለው ጽጌሬዳ ፥ድንግል ፥ታማኝ የጌታ ወዳጅ ነው ::
  (ዮሐንስ ፩፥፴፱)

ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ዮሐንስ ተማረ =>ከቅዱስ ዮሐንስ ቅዱስ ፖሊይካርፕ ተማረ =>ከቅዱስ ፖሊይካርፐስ ቅዱስ ሄሬኔዎስ ተማረ .....

እግዚአብሔር አምላክ ከሚወደው ደቀ መዝሙር በረከትን ይክፈለን ማስተዋልን ጥበብን ንጽሕናን ያድለን!

ምንጭ
-ገድለ ሐዋርያት
-ስንክሳር
-መጽሐፈ ቅዳሴ
-ትርጕሜ ወንጌል

መስከረም ፬/፩/፳፻፲፯🌻🌻


እንኳን አደረሳችሁ 🌹❤️

ዳግም የተለጠፈ
Audio
ነባቢ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ
የጌታችን ወዳጅ አቡቀለምሲስ
ከቤቴ ልትገባ ለእኔ ባይገባኝ
ከደጅህ የተጣልኩ ልጅህን አስበኝ

ዝማሬ መላእክት ያሰማልን 👏👏👏🌹🍃🍃🕊🕊🕊🌹🌹🌹🌹🌹🌻🌻🌻🌻
Audio
3.ቁጣው እንደ ቸርነቱ ብዛት መጠን ነው ሰውንም እንደ ሥራው ይከፍለዋል። ኃጢአተኛ ሰው ከመከራ አያመልጥም ደግ ሰውም የትዕግሥቱን ዋጋ አያአጣም። ምጽዋቱ ሁሉ ይቀርታን ያመጣል ሰውም እንደ ሥራው ዋጋውን ያገኛል። ኃጢአት ሠርተህ ከእግዚአብሔር አመልጣለሁ በሰማያትም የሚያገኘኝ የለም።
4. በብዙ አሕዛብም ዘንድ የሚያውቀኝ የለም። የሰውነቴስ ቁጥሯ ለዓለሙ ሁሉ ምንድነው አትበል። እነሆ ይህ ሰማይ ከሰማይም በላይ ያለ ሰማይ ከሰማይም በታች ያለ ውቅያኖስ ምድርም በመዓት በጐበኛቸው ጊዜ ይህ ሁሉ ያልፋል። ተራሮችም የምድርም መሠረት በመዓት ባያቸው ጊዜ ይንቀጠቀጣሉ ይነዋወጣሉ። ይህንንም ልብ አያስበውም የእግዚአብሔርን ሥራውን ማን ያውቃል ገናንቱንስ ጠንቅቆ ማን ያውቃል።
2024/09/21 02:49:59
Back to Top
HTML Embed Code: