Telegram Web Link
በዓለ ቅዱስ ሚካኤል በሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በድምቀት እየተከበረ ይገኛል !!!
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
በየዓመቱ ሰኔ 12 ቀን 2012 ዓ.ም የሚከበረው የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል በዓል በሻሰመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በድምቀት እየተከበረ ይገኛል። ከትናንት ጀምሮ በዋዜማ እና በምሽቱ ሥርዓተ ማኅሌት ጭምር እየተከበረ የሚገኘው የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በዛሬው እለት በቅዱሴ ፣ በስብከተ ወንጌልና በሥርዓተ ማኅሌት በልዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓት እንደሚከበር ይታወቃል።

ሆኖም በአሁኑ ሰዓት የሥርዓተ ማኅሌቱ ፍፃሜ ሆኖ ታቦተ ህጉ ዑደት እያደረገ የሚገኝ ሲሆን በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና በሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች አማካይነት ያሬዳዊ ምስጋና ቀርቦ ሌሎች መርኃግብሮች እንደሚከናወኑ ይጠበቃል። በበዓሉ ላይ የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ፣ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ብርሃኑ ወ/ዮሐንስን ጨምሮ የሀገረ ስብከቱ የየመምሪያው ኃላፊዎች የአድባራት አስተዳዳሪዎችና በርካታ ምዕመናን መገኘታቸው ተጠቁሟል
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን።

#ሰው_ሆይ_አስተውል

የምናስተውል ካለን መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ
ይለናል።

🌿❤️~ : በሚሞት ስጋችሁ ሐጢያት አይንገስ
ብልቶቻችሁን የፅድቅ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ (ሮሜ 6፥12-14)

🌿❤️~ : ከሴት ጋር አለመገናኘት መልካም ነው ካልተቻለ ዝሙትን ለመከላከል በአንድ ይፅና ከዚህ ውጭ ጉዞ ወደ እሳት ነው (1ኛ ቆሮ 7፥1)

🌿❤️~ : ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱ ያፈርሰዋል ቤተ መቅደሱም እናንተው ናችሁ (1ኛ ቆሮ 3፥17)
ስንቶቻችን ነን የእግዚአብሔር ቤተ መቅደሶች እንደሆንን የምናውቀው?

🌿❤️~ : ሴቶች በሚገባ ልብስ ከእረፍትና ራሳቸውን ከመግዛት ጋር ሰውነታቸውን ይሸፍኑ (1 ኛ ጢሞ 2፥9)

🌿❤️~ : የወንድ ልብስ የለበሰች ሴት በአምላክ ዘንድ…የተጠላች ናት (ዘዳ 22፥5; ዘፀ 39፥28)

🌿❤️~ : ፀጉሯን ሳትሸፍን የምትፀልይ ሴት እራሷን ያዋረደች ናት(1ኛ ቆሮ 11፥5)

🌿❤️~ :…የወይን ጠጅ ከሚጠጣ ጋር አትቀመጥ (ምሳ 23፥20)

🌿❤️~ : ዘፈን የሰነፎች ዜማ ነው (መክ 7፥5)

🌿❤️~ : በዛም አጋንንት ይዘፍናሉ (ኢሳ 13፥21)

ስንቶቻችን ነን እነዚህን የእግዚአብሔርን ቃላት እየጠበቅን ያለነው?

#ሠምተን_ለመለወጥ_ያብቃን_የተግባ_ሰው_ይበለን።


#ወስብሐሃት _ለእግዚአብሔር!!
የሽንኩሩ ቅዱስ ሚካኤል የአደረገው ታምር
#በዘመነ_ኮረና🙏🙏
ዓለም አትችልምና በሽታውን ፈርታ ቤቷን ዘግታለች ቤተክርስቲያን ግን የሚያቅታት የለምና ሁሌም በሯ ክፍት ነው።
አጥማቂው ካህና መጋቢ ብሉይ መልዕከ ምክሩ ታዳጊው ቁጥራቸው ከባለቤቱ ከእግዚያብሔር ውጪ የማይቆጠሩ እልፍ አእላፋት የሆኑ እሳታዊያን መላዕክት የሊቃናት የአናብርታት የብርሃናት ተብለው በነገዳት ሁሉ የተከፈሉትም ጭምር አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል ነው።
ሕዝበ እስራኤልን ሌሊት በብርሃን ቀኑን በደመና እየመራ ባህር ከፍሎ ያሻገረ አፎሚያን ከዲያብሎስ ወጥመድ ያስመለጠ ባህራንን ከሞት የታደገ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል ዛሬም በእኛ ዘመን ድንቅ ስራ አደረገ ።
ከደረቅ አለት ላይ ፀበሉን ባፈለቀበት ያለ አጥማቂ ካህን ራሱ አጥማቂ ሆኖ በዮርዳኖስ በተሰየመ ፀበሉ የሽንኩሩ ቅዱስ ሚካኤል ያደረገው ታምር ይህ ነው፦
አንዲት እህታችን በማዕፀን ልጅ ፀንሳ ሳለ በመውለጃዎ ሰዓት በፀና ታማ አልጋ ላይ ወደቀች ቤተሰቧ እጅግ ተጨነቀ በዚህ ክፉ ዘመን ሰው ታሞ የማይጠየቅበት ቢሞትም በክብር በማይቀበርበት ጊዜ መሆኑ በራሱ ትልቅ ጭንቀት ውስጥ ከቷቸዋል።
ልጇንም እንደምንም ብላ ወለደች ነገር ግን ያልታሰበ ችግር ገጠማት አንገቷ ታጠፈ እግሯም የማይሰራ ፓራላይዝ ሆነ የተወለደውም ልጅ ማጥባት አልቻለችም በእናት እና በልጇ ላይ የሞት ድባብ አዣበበባቸው አኪም አገላብጦ ቢያያትም ምንም መፍትሔ እንደሌለው ገለፀላቸው ቢጨንቃቸው ቢጠባቸው ልጅቷን ይዘው ለፀበል ሽንኩሩ ቅዱስ ሚካኤል ፀበል አመጧት ቤተሰቡ በሙሉ ከእርሷ ጋር ለማስታመም ፍቃደኛ አልነበረም ።
ሁሉም በፀበል ቦታ ላይ ጥለዋት ወደ ቤታቸው ሊሄዱ ወሰኑ የሚያድንሽ አምላክሽ ይርዳሽ ብለው እርሷን ወደ መጠመቂያው የፀበል ቤት ለጥምቀት አስገብተው ተጠምቃ እስክትወጣ ዘንድ አስታማሚ ለመቅጠር ከፀበልተኛ ጋራ የገንዘብ ድርድር ማድረግ ጀመሩ በመጨረሻም በ1500 ብር እንዲከፈላቸው የሚያስጠምቋት ፀበልተኞች ጠየቁ ቤተሰቡም ከራሳቸው አውርደው ጥለዋት ለመሄድ ስለፈለጉ እሺ አሉ ቆየት ብለው ግን ፀበልተኞቹ ልጅቷ ሰውነቷ ከበድ ስለሚል ትንሽ ገንዘብ ጨምሩልኝ እያሉ ቤተሰቧን ድጋሚ ጠየቁ።
ቤተሰቦቿም በገንዘብ ሲደራደሩ ሕመምተኛዋ ባታውቅም አኪሟ ቅዱስ ሚካኤል ግን ያይ ይሰማ ነበር በገንዘብ ሲጨቃጨቁም ሲነታረኩም የሽንኩሩ ሚካኤል የድሆች አባት ይሰማቸውም ያደምጣቸውም ነበር።
ጭራሽ ለመዳን እረጅም ቀን እንደምትፈጅ ማመላለሱ አሰልቺም እንደሆነ እያወጓቸው እያለ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤልን ግን ስራውን ይሰራ ነበር እንዲው ሲጯጯው እንዳለ ከፀበል ቤቱ ውስጥ አንዲት ሴት በእልልታ እየጨወች መጣች ይቺም ሴት ቀድመው በገንዘብ የሚደራደሩባት ቤተሰቦቿም ጥለዋት ሊሄዱ የወሰኑባት ራሷ ነበረች የመጣችው ። ሽባነቷን ተርትሮ የተጣመመውን አንገቷን ወደ ቀድሞ ቦታ መልሶ በፍፁም ጤንነት በአንድ ቀን ፀበል ፈወሳት።
ጥለዋት ሊሄዱ በነበሩት የሚደራደሩትም ፀበልተኞች ፊት የሽንኩሩ ቅዱስ ሚካኤል በክብር በሞገስ በጤንነት አቁሞ አሳያቸው።
ገንዘቡንም አስመለሰ እህታችንም ራርብ ሊገለው ከእናቱም እቅፍ ገና ከማዕፀን እንደወጣ የተለየውን ሕፃን ታጠባው ዘንድ ቅዱስ ሚካኤል ከፊት እየመራት ከቤተሰቦቿ ጋር ወደ ቤቷ መለሳት።
የቅዱስ ሚካኤል ጥበቃ አይለየን
ይህቺ ፀጉሯን ተተኩሳ ቻፕስቲኳን ተቀብታ ማይኳን ጨብጣ እምታዩአት አርቲስት ወይም ዘፋኝ እንዳትመስላችሁ
የሴት ነብይት ናት በ ፌስቡክና በ ዩቲዩብም live ታስተላልፋለች
እንግዲህ ይሄን ያህል የመፅሀፍ ቅዱስን ህግ እየጣሱ እራሳቸውን እየሾሙ ህዝብን እያሳቱ ነው።
ሴት ልጅ በአደባባይ እንኳን ልትሰብክ ልትጠይቅ አልተፈቀደላትም።
መፅሀፍ ቅዱስ ስለ ሴት ልጅ እንዲህ ይላል
ሴቶች በማኅበር ዝም ይበሉ፤ ሕግ ደግሞ እንደሚል እንዲገዙ እንጂ እንዲናገሩ አልተፈቀደላቸውምና።
፤ ለሴት በማኅበር መካከል መናገር ነውር ነውና፥ ምንም ሊማሩ ቢወዱ በቤታቸው ባሎቻቸውን ይጠይቁ።
፤ ማንም ነቢይ ወይም መንፈሳዊ የሆነ ቢመስለው ይህች የጻፍሁላችሁ የጌታ ትእዛዝ እንደ ሆነች ይወቅ፤
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕ. 14 ቁ34-37
ራስዋን ሳትሸፍን ግን የምትጸልይ ወይም ትንቢት የምትናገር ሴት ሁሉ ራስዋን ታዋርዳለች፤ እንደ ተላጨች ያህል አንድ ነውና።
፤ ሴትም ራስዋን ባትሸፍን ጠጉርዋን ደግሞ ትቆረጥ፤ ለሴት ግን ጠጉርዋን መቆረጥ ወይም መላጨት የሚያሳፍር ከሆነ ራስዋን ትሸፍን።
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕ.11 ቁ5-6
💎የቅድስት ድንግል ማርያም ልጆች
Photo
ሼር ፖስት ላይክ ታግ አርጉት🙏
#ይህ ድንቅ ተአምር ሼር በማድረግ
ይህ የምታዩት በአንድ የሱቅ መደብር ውስጥ እሳት ተነስቶ ቤቱ ውስጥ ያሉትን ነገሮች እንዳለ ሲወድም መጽሐፍ ቅዱሳችን ምንም ነገር ሳንሆን ሌላው ነገር አመድ ሲሆን መጽሐፍ ቅዱሳችን አንዲትም እሳት ሳይነካው እንደ ምታዩት ተገኝቷል ከዚህ በላይ ተአምር ከየት ይምጣ።

በቴሌግራም መቀላቀል የምትፈልጉ Join አርጉ
https://www.tg-me.com/yemariyam2121
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምን ማለት ነው ?

► @Orthodox_Tewahdo_bot
➖➖➖➖➖➖
1 ኦርቶዶክስ የሚለው ስም ከየት የመጣ ነው?
2 ተዋህዶ የሚለውስ ከየት የመጣ ነው?
3 ክርስትያን ማለትስ ምን ማለት ነው???

1 ኦርቶዶክስ የሚለው ስም ከየት የመጣ ነው?
ኦርቶዶክስ ማለት ቃሉ የግሪክ ሲሆን አማርኛው
ትርጉሙ እውነተኛ፤ቀጥተኛ መንገድ የሆነች ሃይማኖት
ማለት ነው፡፡
ቀጥተኛዋ መንገድ ጠይቁ በእርሷም ላይ ሂዱ
ለነብሳቹሁም እረፍት ታገኛላቹሁ፡፡[ኤር 6÷16]
ነብዩ ኤርምያስ እንዳለው እዚህ ላይ እንግዲህ ቀጥተኛ
ማለት ኦርቶዶክስ ማለት ሲሆን መንገድ ማለት ደግሞ
ሃይማኖት ማለት ነው፡፡
ኢየሱስም ክርስቶስም አለ እኔ መንገድ እውነት
ሕይወት ነኝ ብልዋል፡፡[ዮሐ 14÷6]
ይህ ማለቱም የሃይማኖት መሰረታ ቹሁ እኔ ነኝ ማለቱ
ነው፡፡
ከሰማያዊው ጥሪ ተከፋዮች የሆናቹሁ ቅዱሳን ወንድሞች
ሆይ የሃይማኖታችንን ሊቀ ካህን የሆነውን ኢየሱስ
ክርስቶስን ተመልከቱ፡፡[ዕብ 3÷1]
ስለዚህ ኦርቶዶክስ ማለት ይህ ነው፡፡

2 ተዋህዶ ማለትስ ከየት የመጣ ነው?
ተዋህዶ ማለት ተዋሃደ ከሚለው የግእዝ ግስ
የተወሰደ ሲሆን ትርጉሙ አንድ ሆነ መለኮትና ስጋ አንድ
ሆነ ማለት ነው፡፡ ከሁለት አካል አንድ አካል ፤ከሁለት
ባህሪ አንድ በህሪ ሆነ ማለት ነው በሌላ አካሄድ ደግሞ
ተዋሃደ ማለት መለኮት ስጋ ለበሰ ከድንግል ማርያም
ከስጋዋ ስጋ ከነብሷ ነብስ ነሳ ማለታችን ነው፡፡
ይህም ደግሞ ግልፅ የሆነ እውነት ነው፡፡
በጀመርያ ቃል ነበረ ፤ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ
ነበረ፤ቃልም እግዚአብሔር ነበረ፡፡[ዮሐ 1÷1]
ቃልም ስጋ ሆነ፤ፀጋንና እውነትን ተመልቶ በእኛ አደረ
እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡[ዮሐ1÷14]
ስለዚህ ተዋህዶ ስንል ቃል ስጋ ለበሰ ማለታችን ነው፡፡
በበለጠ ደግሞ ብርሃናዊው የሆነ የዓለም ብርሃን
ቅዱስ ጳውሎስ ቃል በቃል ተዋህዶ የሚለው ፅፎልናል፡፡
ክርስቶስ እርሱ ሰላማችን ተውና፤ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ
የተነገረለት በራሱ አዲስ ሰውን ይፈጥር ዘንድ ሰላምም
አደረገ፡፡[ኤፌ 2÷14-15]
ስለዚ ተዋህዶ ማለትም ይህን ይመስላል፡፡

3 ክርስቲያን የሚለውስ ከየት የመጣ ነው?
ክርስትያን ማለት ከክርስቶስ ስም የተወሰደ ሲሆን
ክርስቶስ ተከታዮች፤አማኞች ማለት ነው፡፡
ክርስቶስ አምላክ ነው፤ጌታ ነው፤ፈጣሪ ነው፤ፈራጅ ነው
ብለን የምናምን ክርስትያን ተብለን እንጠራለን፡፡
የክርስቶስ ሐዋርያትም በአንጾክያ ምክንያት ክርስቲያን
ተባሉ፡፡[ሐዋ 11÷26]
በትዕቢት ተነፍቶ በዲያብሎስ ፍርድ
እንዳይወድቅ፤ሰው ሁሉ አዲስ ክርስቲያን አይሁን፡፡
[1ኛ ጢሞ 3÷16]
ክርስቲያን እንደሚሆን ግን መከራን ቢቀበል ስለዚህ ስም
እግዚአብሔርን ያመስግን እንጂ አይፈር፡፡
[1ኛ ጴጥ 4÷16]
ስለዚህ ሁሉም ከመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተነሳ ነው፡፡
ኦርቶዶክስ ነው ሃይማኖቴ ስን ቀጥተኛ ናት
ሃይማኖታችን እያልን ነው፡፡
=>የተዋህዶ ልጆች ነን ስንልም የክርስቶስ ልጆች ነን
እያልን ነው፡፡
=>ክርስቲያን ነን ስንልም ክርስቶስን የምናመልክ
የምናምን ክርስቲያን ነን፡፡
ማለታችን ነው፡፡
ሌላው እምነት ፤ሃይማኖት ግን ጴንጤ ፤ፕሮቴስንት
፤ካቶሊክ፤ጆባዊስትን ክርስቲያን ነን ቢሉም እነዚህ
የመሳሰሉ ግን ከጥንትም ያልነበረ ስም አዲስ ድርጂት
ነው በመፅሐፍ ቅዱስም አንድም ቦታ ላይ የለም፡፡
ከግዜ ቡሃላ ከኦርቶዶክስ ወጥተው ወደ ምንፍቅና
የተመሩ ድርጅቶች ናቸው፡፡
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ግን ከጥንት የነበረች የነብያት
የሃዋርያት የቅዱሳን ሰማዕታት ሃይማኖት ናት ፡፡አሁን እስከ
ልጅ ልጅ ለዘላለም ትኖራለች፡፡

አንድ ጌታ እንዲት ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር አሜን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር

ይቆየን
@yemariyam2121
Audio
⛪ #ኦርቶዶክሳዊ_ቤተሰብ

🎙መጋቢ አእላፍ ቀሲስ ፋሲል ታደሰ🎙

♥ጋብቻዬን እንዴት የተቀደሰ ላድርገው

👉🏾ከጋብቻ በፊት ስለ ጋብቻ ማወቅ

👉🏾የቅድስና ህይወትን በተግባር መኖር

👉🏾በንስሃ መንከባከብ
👂👂👂👂🌺🌺🌺👏🏻
+ የተሠጠህን ቁጠር +

ሔዋን ከዕባብ ጋር እየተነጋገረች ነው:: የመጀመሪያ ጥፋትዋ ካለደረጃዋ ወርዳ ከዕባብ ጋር ወዳጅነት መጀመርዋ ሳይሆን አይቀርም:: ዕባብ ደግሞ የስይጣን አንደበት ነበረ::

ሰይጣን እንዲህ አላት :- በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ አዝዞአልን? አላት።
ልብ አድርጉ እግዚአብሔር "ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ" አላለም:: የከለከለው አንዲት ዛፍ ነው:: ሰይጣን ግን ሁሉን ተከልክላችሁዋል? ብሎ እንዳላዋቂ ጠየቀ:: ሰይጣን በመጽሐፍ ቅዱስ ንግግሩን የከፈተው በውሸት ነበረ::

ዓላማው ከሔዋን መረጃ ለማግኘት አልነበረም:: ሔዋን እስከዛሬ ያላሰበችውን ማሳሰብ ነበር:: ብሉ ተብሎ ከተሠጣቸው ብዙ ሺህ ዛፍ ይልቅ የተከለከሉትን አንዲት ዛፍ አሳይቶአት ሔደ:: ከዚያች ደቂቃ ጀምሮ ስላልተሠጣት ማሰብ ጀምራ ደስታዋን አጣች:: የተከለከለችውን በልታ የተሠጣትን ብዙ ሥጦታ ከነሠጪው አጣች::

ወዳጄ የቀደመው እባብ ዛሬም መርዙን ይረጫል

በሕይወታችን ከተሠጠን ብዙ ነገር ይልቅ ያልተሠጠንን ጥቂት ነገር እናስባለን:: ገንዘብ እንደሌለህ እያሰብክ ጤና እንዳለህ ትረሳለህ:: ጫማ እንደሌለህ እያሰብክ እግር እንዳለህ ትረሳለህ:: አልጋ እንደሌለህ እያሰብክ እንቅልፍ እንዳለህ ትረሳለህ::
ስለዚህ ውስጥህ ያለውን የዕባቡን ድምፅ አትስማ ከሌለህ ይልቅ ያለህ ይበልጣልና የተሠጠህን ቁጠር::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሰኔ 13 2012 ዓ ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ከታች INSTANT VIEW የሚለውን ተጭነው ያንብቡ!

⤵️
https://telegra.ph/ነገረ-ክርስቶስ-01-08

@yemariyam2121

https://www.tg-me.com/Rediyemariyam/ነገረ-ክርስቶስ-01-08
++ የማኅጸን ውስጥ ሸንጎ +++
መንትያ ሕጻናት በእናታቸው ማኅጸን ውስጥ ተጸንሰው እየኖሩ ነው፡፡ አንደኛው ሕጻን ሌላኛውን ጠየቀው ‹‹ከማኅጸን ከወጣን በኋላ ሕይወት አለ ብለህ ታምናለህ?››
@Eortodox
ሌላኛው መለሰ ፡- ‹‹እንዴታ! ከማኅጸን ከወጣን በኋላማ የሆነ ሕይወት ሳይኖር አይቀርም፡፡ ምናልባት አሁን ማኅጸን ውስጥ የምንቆየው ለዛኛው ሕይወት ራሳችንን እያዘጋጀን ሊሆን ይችላል፡፡›› አለው፡፡
@Eortodox
‹‹የማይመስል ነገር!!›› አለ የመጀመሪያው ሕጻን፡፡ ‹‹ከማኅጸን ከወጣን በኋላ ሕይወት የሚባል ነገር የለም! እስቲ አስበው ከማኅጸን ውጪ የሚኖረው ምን ዓይነት ሕይወት ነው?›› አለ እየሳቀ፡፡
ሁለተኛው መለሰለት ‹‹እኔም አላውቀውም ግን እዚህ ካለው የተሻለ ብርሃን እዚያ ያለ ይመስለኛል፡፡ ምናልባት በዚያኛው ሕይወት በእግራችን ለመሔድ ፣ በአፋችን ለመጉረስ የምንችል ይመስለኛል፡፡ ምናልባት አሁን ልንረዳቸው የማንችላቸው ሌሎች ስሜቶችም ሊኖሩን ይችሉ ይሆናል፡፡››
የመጀመሪያው ሕጻን በብስጭት ቀጠለ ‹‹ይኼ ቅዠት ነው፡፡ በእግር መሔድ የማይቻል ነገር ነው፡፡ ጭራሽ በአፍ መጉረስ? የማይሆን ነገር ታወራለህ እንዴ?! ምግብ የምንበላውንና የሚያስፈልገንን ነገር የምናገኘው በእትብታችን በኩል ነው፡፡ እትብታችን ደግሞ በጣም አጭር ነው፡፡ ከማኅጸን ከወጡ በኋላ ሕይወት አለ የሚለው ነገር አሳማኝ አይደለም፡፡››
ሁለተኛው ሕጻን ግን ውትወታውን ቀጠለ ‹‹እኔ ግን የሆነ ነገር የሚኖር ይመስለኛል፡፡ ምናልባት ማኅጸን ውስጥ ካለው ነገር የተለየ ነገር የሚኖር ይመስለኛል፡፡ ምናልባትም እትብትም ላያስፈልገን ይችል ይሆናል፡፡››

የመጀመሪያው ሕጻን ግን አልተረታም ‹‹አይዋጥልኝም! እሺ የምትለውን ልቀበልህና እንዳልከው ከማኅጸን ውጪ ሕይወት ካለ እዚያ ደርሶ የተመለሰ ሰው ለምን አናገኝም? ከማኅጸን መውጣት የሕይወት መጨረሻ ነው፡፡ ከማኅጸን ከወጣን በኋላ በጨለማ ውስጥ በዝምታ ከመጣል በስተቀር ምንም ነገር የለም፡፡ ወዴትም አንሔድም!››

‹‹በእርግጥ ምንም አላውቅም›› ቀጠለ ሁለተኛው ሕጻን ‹‹ነገር ግን ከማኅጸን ከወጣን በኋላ እናታችንን እናገኛለን፡፡ እስዋ ትንከባከበናለች፡፡››

‹‹እናት? በእናት መኖር ከልብህ ታምናለህ ማለት ነው? በጣም የሚያስቅ ነገር ነው!!! እሺ እናት ካለች አሁን የት ነው ያለችው?
ሁለተኛው ቀበል አድርጎ ‹‹እናታችንማ በዙሪያችን አለች፡፡ በእርስዋ ተከብበን ነው ያለነው፡፡ የተገኘነው ከእርስዋ ነው፡፡ የምንኖረውም በእርስዋ ውስጥ ነው፡፡ ያለ እርስዋ ያለንበት የማኅጸን ውስጥ ዓለም ሊኖር አይችልም፡፡›› አለው፡፡

‹‹አላየኋትማ! የት አለች? ስለዚህ አለች የሚለው ነገር አሳማኝ አይደለም!›› አለ የመጀመሪያው ሕጻን
ሁለተኛው ሕጻን ግን ይህን አለ ‹‹በማኅጸን ውስጥ ስትኖር አንዳንድ ጊዜ በዝምታ ውስጥ ሆነህ በጥሞና የምታዳምጥ ከሆነ የእናትህን መኖር ትገነዘባለህ ፤ በፍቅር የተሞላ ድምጽዋን ከላይ ሆኖ ሲጠራህ ትሰማዋለህ›› ብሎ ክርክሩን ቋጨው፡፡
ይህች ዓለም እንደ ማኅጸን ናት ፤ የዚህ ዓለም ኑሮ ለወዲያኛው ኑሮ የምንዘጋጅበት አጭር ጊዜ ነው፡፡ ብዙዎች ለማመን ቢቸገሩም ከሞት በኋላ ዘላለማዊ ሕይወት አለ ፤ በጥሞና በተመስጦ ከፈለግነው የዓለም መጋቢና ሠራዒ አምላክ ልዑል እግዚአብሔርም አለ፡፡ የምንሞትበት ቀን ከጠባቡ ወደ ሰፊው የምንሔድበት ለዘላለም ሕይወት የምንወለድበት የልደታችን ቀን ነው፡፡

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

#ይቀላቀሉ 👇👇
➽ @yemariyam2121
➽ @yemariyam2121
➽ @yemariyam2121
🔴 #ዋሻ_ቅዱስ_ሚካኤል
🔴 #የየካ_ደብረ_ሣህል_ቅዱስ_ሚካኤል_ቤተክርስቲያን
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
📌 ዋሻ ሚካኤል ( Washa Mickael ) ከአዲስ አበባ በስተምስራቅ በኩል የካ ከፍለ ከተማ ውስጥ ያለ ጥንታዊ እና በከፊል ወጥ ከሆነ ዓለት ተፈልፍሎ የተሰራ ቤተ-ክርስቲያን ነው:: አዲስ አበባ ከሚገኘው የእንግሊዝ ኢምባሲ በስተጀርባ ቲንሽ ራቅ ብሎ በሚገኘው ከፍታማ ቦታ ላይ ይገኛል:: ቤተክርስቲያኑ የላሊበላ ውቅር ቤተክርስቲያን አይነት ስልት የያዘ ነበር። ምንም እንኳ የህንጻው አወቃቀር ባልታወቀ ምክንያት ሳይጠናቀቅ የቀረ ቢሆንም ስራው ቢገባደድ ኑሮ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት የአለት ውቅር ቤተክርስቲያኖች በትልቅነቱ ሁለተኛ ይሆን እንደነበር ተመራማሪዎች ይዘግባሉ ( ታላቁ የላሊበላ መድሃኒ ዓለም ነው ) ። ከትውፊት አንጻር ፣ ቤተክርስቲያኑ የተሰራው በዓፄ አፅብሐትዕዛዝ እ.ኤ.አ በ380 ዓ.ም. ነው። ታሪክ አጥኝው ኤ.ኤፍ.ማቲው ግን ቤተክርስቲያኑ ከላሊበላ ዘመን በኋላና ከግራኝ መነሳት በፊት እንደተመሰረተ ያስረዳል። የቤተክርስቲያኑ ስራ መቋረጥም አካባቢው በግራኝ በመወረሩ እንደሆነ ያስረዳል።
​​"ጽድቅ እንደ ላሊበላ እድሜ እንደ ማቱሳላ ይስጥህ" ይላል ደጉ ያገሬ ሰው!

ቅዱስ ላሊበላ ጌታችን ባሳየውና ባዘዘው መሠረት አብያተ ክርስቲያናቱን አንጾ ከጨረሰ በኋላ በቀኙ 10 ኪሎ በግራው 10 ኪሎ የሚመዝን የዓለት ድንጋይ ተሸክሞ ለ7 ዓመት ሲጾም ሲጸልይ ከኖረ በኋላ ጌታችን ተገልጦለት እንዲህ የሚል እጅግ አስገራሚ ቃልኪዳን ሰጠው፦

‹‹…ወደ ደጅህ የመጡት ሁሉ አስራት ይሁኑልህ፣ አንተ ከገባህበትም ይግቡ፣ አንተንም ከ12ቱ ሐዋርያት ጋር በፍርድ ቀን 13ኛ አደርግሃለሁ፡፡ ያነጽካቸውን ቤተ መቅደሶች የተሳለመውን ኢየሩሳሌምን እንደተሳለመ አደርግለታለሁ፤ መታሰቢያህን ያደረገውን፣ ገድልህን የጻፈውን ያጻፈውን፣ በዚህ ቦታ ላይ መጥቶ አማልደኝ ያለውን፣ በአማላጅነትህ የተማጸነውን ሁሉ እስከ 15 ትውልድ ምሬልሃለሁ።››

ዳግመኛም ጌታችን ለቅዱስ ላሊበላ ከገባለት ልዩ ቃልኪዳን ውስጥ አንዱ እንዲህ የሚል ነው፦

‹‹...ይህን የሚያስደንቅ ሥራ በእጁ ስለገለጥክለት ስለ ባሪያህ ስለ ቅዱስ ላሊበላ ብለህ ይቅር በለኝ›

እያለ የሚጸልየውን በዚያ ጊዜ እኔ ጸሎቱን እሰማዋለሁ፡፡ ከሕፃንነቱ ጀምሮ የሠራውን ኃጢአት ሁሉ አስተሠርይለታለሁ፤ ከማኅፀነ ዮርዳኖስ እንደ እንደተወለደባት ቀን የነፃ አደርገዋለሁ፡፡ የዕዳ ደብዳቤውንም በእጅህ ትቀደው ዘንድ ለአንተ እሠጥሃለሁ፤ ዕድሜውንም በምድር ላይ አረዝምለታለሁ፤ ቤቱንና ንብረቱን ሁሉ እባርክለታለሁ፤ በተንኮል የሚከራከረው ቢኖር ድል እንዳይነሣው አሠለጥነዋለሁ፤ እግሮቹ እየተመላለሰ ወደ ቤተክርስቲያን የገሠገሠ ሁሉ በኢየሩሳሌም ሰማያዊት በኤዶም ገነት ውስጥ እንዲመላለስ አደርገዋለሁ፤ መባዕ የሚያገባ ሁሉ ጥቂትም ቢሆን ብዙም ቢሆን በእጅህ ከምሠራው ከቤተ መቅደሴ የሚያመጣውን መባዕ ሁሉ ቀኝ እጄን ዘርግቼ ከእጁ ፈጽሜ እቀበለዋለሁ፡፡

ከዕጣንም ወገን በየአይነቱ ያገባ ቢኖር እንደሰው ልማድ ሥጋዬን እንደቀባበት እንደ ኒቆዲሞስ ሽቱ እቀበለዋለሁ፣ በቢታንያ እንደቀባችኝ እንደ ማርያም እንተ ዕፍረት ሽቱ መዓዛውን አሸትለታለሁ፤ ስለ ማርያም እንተ ዕፍረት እስከ ዓለም ዳርቻ ሁሉ የመንግሥቴ ወንጌል በተሰበከበት ስሟን ይጠሩ ዘንድ እንዳዘዝኩ ሁሉ ትጉሃን በሚሆኑ በሰማያውያን መላእክት ከተሞች ስሙን ይጠሩት ዘንድ አዛለሁ፡፡ ››

‹‹ለሌሎቹ ጻድቃን ከዚህ ዓለም በሞት በሚለዩበት ወቅት በፍጹም ልቡናቸው እንደሚገባ ያገለገሉኝን ዋጋቸውን ሰጠኋቸው፣ ለአንተ ግን በሞት የምትለይበት ጊዜ ሳይደርስ በሕይወትህ ሳለህ ኪዳንን ሰጠሁህ፡፡ ማደሪያህ ከጳውሎስና ከጴጥሮስ ጋር ይሆናል፡፡ አቀማመጥህ በቀኜ ነው፣ ደቀ መዛሙርቴን በ12 ወንበር ተቀምጣችሁ በ12ቱ ነገደ እስራኤል ትፈርዳላችሁ እንዳልኳቸው አንተም ወንበርህ ከወንበራቸው አያንስም፤ ብርሃንህ ከብርሃናቸው፣ ክብርህ ከክብራቸው አያንስም፤ ኪዳንህም ከሰጠኋቸው ኪዳን አያንስም፤ ርስትህ ዕድል ፈንታህ ከእነርሱ ጋር ነው፡፡ የሰጠሁህን ቃልኪዳንና ገድልህን የሚያቃልል ሁሉ ዕድል ፈንታው ከአንተ ጋር አይሁን፣ ርስት ጉልቱም ከአንተ ርስት ጉልት አይገኝም፤ የጸናሁልህን ቃልኪዳን የማያምን ያ ሰው እኔን ክርስቶስን እግዚአብሔር አይደለም እሩቅ ብእሲ ነው እንጂ እንደሚለኝ ሰው ይሁን፡፡

መጽሐፍህን ሰምቶ የተቀበለ ሁሉ የመንግሥቴን ወንጌል እንደተቀበለ ይሁን፤ አንተን ያከበረ እኔን እንዳከበረ ይሁን፡፡ ደቀ መዛሙርቴን እናንተን የሰማ እኔን የሰማ ነው፣ እናንተን የካደ እኔን የካደ ነው እንዳልኳቸው አሁንም አንተን የሰማ ቃልኪዳንህንም ያመነ እኔን ጌታህን የሰማ ነው እልሃለሁ፡፡

መከራህንና ቃልኪዳንህን የካደ ሰው ቢኖር እኔ በምድር የተቀበልኩትን መከራ እንደ ካደ ሰው ነው፡፡ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች በጸሎትህ ኃይል የታመኑ ሁሉ ማደሪያቸው ከአንተ ጋር ይሁን፤ ለቤተክርስቲያኖችህ አምኃ የሰጠ ቢኖር እንደ ደሜ ፍሳሽ እንደ ሥጋዬ ቁራሽ አድርጌ እቀበለዋለሁ፡፡››

ጽድቅ እንደ ላሊበላ እድሜ እንደ ማቱሳላ ያድለን።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን! እኛንም በአማላጅነታቸው የምንታመን ሁላችንን የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን እና የቅዱስ ላሊበላን በረከታቸውን ያድለን በጸሎታቸው ይማረን አሜን!!!

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @yemariyam2121💚
💛 @yemariyam2121💛
❤️ @yemariyam2121 ❤
💠 #አስደናቂ

ላልይበላ ንጉሥ፣
ላልይበ ቅዱስ፣
ላልይበላ ምስጢር፣ ላስታ ምድር ቅኔ፣
ህብረ ቃሉ ገብቶት፣ ወርቁ ጠፋ ከአይኔ፣
ሰሙ እየቀለጠ፣ ያስገባል ምናኔ
ዋሻው ሁሉ ድብቅ፣ ምድር ሙሉ ቅኔ
አንዱንም ላልፈታሁ፣ ላልተረዳሁ ዋ‘ኔ!!


#ሟር
___

#share #Join
https:/www.tg-me.com/yemariyam2121
Audio
Zemarit seblewengel
"ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀገር ናት"🇪🇹
ድንቅ መዝሙር
💒⛪️
@yemariyam2121
2025/02/23 23:20:57
Back to Top
HTML Embed Code: