Telegram Web Link
💕የድሀ ልጅ ፍቅር
ክፍል1⃣8⃣
#በእዉነተኛ_የህይወት_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ

ስለ ሜላቴ ስጨነቅ አምሽቼ የግዴን እንቅልፍ ወሰደኝ እኩለ ሌሊት ላይ የስልክ ጥሪ ቀሰቀሰኝ... በድንጋጤ ተነስቼ ተቀመጥኩ ስልኩን ሳየው የእናቴ ስልክ ነው.. ደነገጥኩ እጄ እየተንቀጠቀጠ አነሳሁት.... ስልኩን እንዳነሳሁት የሰማሁት ድምፅ በጣም ያስደስት ነበር ... የህፃን ልጅ ድምፅ! እያለቀሰ በቃ ደስ የሚል ድምፅ! ሰማሁ!...እንዴት ደስ ይላል በጌታ...
ልጄ አለችኝ እናቴ በደስታ እያነባች!... እማ ምን ምንድነው የሰማሁት? እኔም ወግ ደርሶኝ አባት ልሆን ነው?ልጄ ነው? አልኳት። ጥያቄዬን አከታተልኩት... እንባዬ ግን በደስታ ብዛት ይፈስ ነበር... ልጄ የወንድ ልጅ አባት ሆነሀል! አለችኝ እናቴ... ኦ አምላኬ ተመስገን አልኩ... እማ ሜላቴስ እንዴት ናት ? አልኩ ስቃይዋን እያሰብኩት... ደህና ናት ልጄ አትጨነቅ በሰላም ተገላግላለች አለችኝ ደስ አለኝ ...ግን ድምፆን መስማት እፈለግሁ... እማ ሜላቴን ላናግራት አልኳት... ጠዋት ታወራታለህ አሁን ትንሽ ደክሟት ተኝታለች አለችኝ.. እሽ ብዬ ስልኩን ዘጋሁት....
የሰላም የደስታ ሌሊት ሳልተኛ በደስታ ቁጭ ብዬ ነጋ ..ጠዋት ተነስቼ ቁርሴን በልቼ ወደ ትምህርት ከመሄዴ በፊት ሜላቴን ማናገር ፈለግሁና እናቴጋ ደወልኩ... ስልኩን ሜላት ነበርች ያነሳችው.. ወዬ ውዴ ስትለኝ በጣም ተደሰትኩ.. የኔ እናት ደህና ነሽ አይደል? አልኳት ደህና ነኝ ውዴ አትጨነቅ እሽ አለችኝ... የኔ ውድ የኔ ፍቅር አመስግናለሁ! ስላት.. ለምን ውዴ? አለችኝ ...ለዚህ ለአባትነት ክብር አበቃሽኝ አይደል አልኳት ውዴ እኔም ደስ ብሎኛል .. ምስጋና አያስፈልገውም አፈቅርህ የለ አለችኝ እሽ አልኳትና ትምህርት እንዳይረፍድብኝ ስልኩን ዘግቼ ወደ ክፍሌ ገባሁ....
ትምህርቴን በደስታ ተምሬ ጨረስኩ.. ከክፍል መልስም ስራ ቦታ በደስታ ዋልኩኝ,ማታ ጏደኞቼ የሜላትን መውለድ ነግሬያቸው ስለነበር ፕሮግራም አዘጋጅተው ና ሲሉ እነሱጋ ሄድኩ....ደስ የሚል ምሽት በደስታ አመሸን... እኔም ሜላቴን ደውዬላት አወራን ... ነገ ከሆስፒታል እንደምትወጣ ነገረችኝ በቃ ፈፁም ደስተኛ ነኝ,.ልጄን የማቅፍበትን ቀን እየናፈቅሁ ነው .....
ሜላቴ ጋ ደውዬ እያወራን የልጃችን ስም ማን እንዲሆን እንደምፈልግ ጠየቀችኝ እኔ ከድሮው የልጄ ስም ቅድስ ቢሆን ደስ ይለኛል እሷ ደግሞ ናትናኤል እንዲሆን እንደምትፈልግ ደጋግማ ነግራኛለች,... የመጀመርያ ልጄን ናታኒኤል ነው የምለው ትለኝ ነበር ከበፊትም እኔም ልቃወማት አልፈለግሁም....እና ለምን ስም አውጣ እንዳለችኝ አልገባኝም ,.የኔ ውድ "ቅዱስ ቢኒያም"ቢባል ደስ አይልም አልኳት,... "ናትናኤል ቢኒያምስ" አለችኝ...የኔ ፍቅር ስም አያጣላንም ያልሽው ይሁን አልኳት እሽ አለችኝ.....
ሜላቴ ከቤተስቦቿ ቤት ወጥታ ከእናቴ ጋር አሪፍ ቤት ተከራይተው መኖር ጀምረዋል ልጄ በሁለት እናቶቼ እጅ መሆኑን ሳስብ እጅግ እደሰታለው...ሁለቱም ለእኔ የፍቅር መምህሮቼ .በህይወት የመኖር ሚስጥሬ ናቸው...ስለዚህ ልጄ በእነሱ እጅ ስለሆነ ፍቅር ተምሮ እንደሚያድግ ሳስብ ደስታ ይሰማኛል.....
ሰአታት ቀናትን ቀናት ወራትን እየተኩ የልጄ ስደስተኛ ወር ሊሆነው ነው..እኔ ግን እስካሁን አቅፌው ለመሳም አልታደልኩም..ግን ሲናፍቀኝ በእስካይፕ ስለማየው ትንሽ ይሻላል ,ሜላቴ የእኔ መራቅ የእሷ ብቻዋን መሆን ትንሽ የጎዳት ይመስላል...
ሜላቴ ከስታለች በቃ ጥሩ ስሜት እንደሌላት ይገባኛል የልጃችን ስደስተኛ ወር ሊከበር ነው እያለች ደጋግማ ትነግረኛለች ...ግን ምን ላድርግ ,የኔ ፈቅር ትንሽ ነው የቀረኝ በቅርቡ እመጣለው እሽ በጣም እኮ ናፍቃችሁኛል እያልኩ አፀናናታለው ብዙ ባይዋጥላትም እሽ ማለት አልሰለቻትም,.. የሷ እንደዚህ መሆን እኔንም በጣም ጎድቶኛል,ለብዙ አመታት ብቻዋን እንድትሆን ፈርጄባታለው ልረዳት ይገባል ,...ግን ምን ማድረግ እችላለው .. በቃ በተስፋ መኖርን መርጫለው.....
ከትምህርት መልስ ስራ ውዬ እቤት ገብቼ እራቴን ሰርቼ በላሁና ጋደም አልኩ እያሰብኩ እያለ .የልጃችን ስድስተኛ ወር ነገ መሆኑ ትዝ አለኝ ,ተንደርድሬ ሜላቴ ጋ ደወልኩ.. ሰላም ተባባልን...የኔ ውድ አልኳት ወዬ አለችኝ.ነገ የቤቢ ስደስተኛ ልደት ነው አይደል አልኳት አዎ ውዴ አስታወስክ አይደል አለችኝ አዎ አልኳት,.. በቃ ነገ እረፍት ስለሆንኩ እኔም በ(Skype) ደውዬ አብሬያችሁ አከብራለው እሽ አልኳት እሽ ደስ ይለኛል አለችኝ.....ስልኩ ተዘጋ... ሜላቴ የልጃችንን ስም ማን እንዳለችው ልትነግረኝ አልፈለገችም እኔ በቃ መቼም እሷ በምትፈልገው ስም ነው የምትጠራው ብዬ ስላሰብኩ ደጋግሜም መጠየቅ አልፈለግሁም.... የልደት ፕሮግራሙ ተጀምሮ እኔ በስልክ እብሪያቸው ማክበር ...ጀመርኩ...ድንገት ሜላት የኔ ፍቅር ቆይ ወደዚህ እንዳታይ አለችኝ እሽ ብያት ፊቴን አዞርኩ... መለስ ስል የሚገም ያልጠበቅሁትን ነገር አሳየችኝ.......
ይ.....ቀጥላል
   ‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
​​የድሀ ፍቅር❣️
ክፍል 1⃣9⃣

#በእዉነተኛ_የህይወት_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ

የልጃችንን ልደት አብሪያቸው ማክበር ባልችልም በስልክ ተደዋውለን እብሬያቸው ማክበር ጀመርኩ .በቃ የሜላት እህቶች እና እናቷ አብረው እናቴ ቤት ተሰብስበው እያከበሩ ነው,.እኔም አብሪያቸው የሆንኩ ያክል ተሰማኝ,በ(Skype ) ስለነበር የምናወራው,ሁለም ነገር ይታየኛል ሜላቴ ጠጋ አለችና ቆይ ውዴ ወደዚህ አትይ አለችኝ እሽ አልኳት.
ከደቂቃዎች በኃላ ሜላት ውዴ አለችኝ ዞር ብዬ ሳይ ከፊት ለፊቴ ትልቅዬ ኬክ አየሁ ,አያምርም አለችኝ ያምራል ውዴ አልኳት በደንብ እየው አለችኝ ስልኩን አስጠግታ አሳየችኝ .. የሚገርም ነገር የልጃችን ስም"ቅዱስ ቢኒያም"ይላል እንዴ የኔ ፍቅር ቅዱስ አልሽው አልኳት አወ ,ባይሆን ሁለተኛ ስንወልድ ናታኒኤል ,እንለዋለን አለችኝ በጣም ደስ አለኝ ዋውው የኔ ፍቅር አመሰግናለው አልኳት....
አብረን አክብረን ኬኩ ከተቆረሰ በኃላ ቻው ብያቸው ስልኩ ተዘጋ እኔም ወደ ጏደኞቼ ጋር ሄድኩ ከእነሱ ጋር ዞር ዞር ስንል አመሸን,ደስ ስላለኝ እራት ጋብዣቸው ተለያየን.የልጄ ስም ቅዱስ ሆኗል .ተመስገን እግዚአብሄር ያሳድግልኝ ..ሜላቴንም ይጠብቅልኝ ...
ቀኑ እየነጎደ ቅዱሴም እያደገ እኔም የትምህርት ጊዜየን ወደ ማጠናቀቅ እየተዳረስኩ ነው.ሜላቴ አትመጣም ወይ ጥያቄን ተያይዘዋለች ሁሌ ስልክ ባወራን ቁጥር መቼ ነው የምትመጣ ሳትለኝ ስልኩ ተዘግቶ አያውቅም.ወራቶች ናቸው የቀሩኝ ትንሽ ጊዜ ብቻ እሽ የኔ ፍቅር እላታለው...ባይዋጥላትም እሽ ትለኝና ስልኩ ይዘጋል....
በፊት በፊት እኔ እንኳን ካልደወልኩ ሜሴጅ ካልፃፍኩ ሜላት ፀፋ ታስታውሰኝ ነበር አሁን ግን ሁሉም ነገር ተቀይሯል ስደውል ብቻ ነው የምታወራኝ.ለምን አትደውይልኝም ስላት ይቅርታ ስራ ይዜ በቃ ብዙ ምክንያቶችን ትነግረኛለች እኔም እሽ ከማለት ውጪ ምንም አማራጭ አልነበረኝም የሜላቴ መቀየር አሳስቦኛል.
ሁሉም ነገር ተቀይሯል በቃ የትላንት ድህነታችን ታሪክ ሆኖ ዛሬ አሪፍ ህይወት ላይ ነን ግን የሜላት ነገር አሳስቦኛል ወደ ሀገሬ ለመግባት ሁለት ወር ብቻ ነው የቀረኝ ይሄንን እንኳን ነግሪያት ብዙም ደስተኛ አላደረጋትም.አንዳንዴ ልክ ልትመጣ ሰአታት ሲቀሩህ ልመጣ ነው በለኝ እንጂ ወራት ሳምንታት አትበለኝ ብላ ትቆጣለች .አንዳንዴ ታለቅሳለች.ግራ ግብት ሲለኝ እናቴ ጋ እደውላለው እናቴ ግን ምንም እንዳልተፈጠረና .አንዳንዴ ግን መዝናናት እፈልጋለው ቢያንስ ልጄን ይዜ ከቤት መውጣት እፈልጋለው እያለች ስታማርር እስማታለው አለችኝ እናቴ....
ሜላቴ ይሄ ስሜት ስለተሰማት ይሆናል የምትቆጣና የምታለቅሰው ብዬ አሰብኩ,ግን መሄጃዬ ስለደረስ ,ዝም እላታለው ,ልጅህ አስቸግሮኛል ቻው ብላ ስልኩን ስትዘጋው ቢከፋኝም ዝምታን መርጫለው በእሷም አይፈረድም .3 አመት ዮኒቨርሲቲ,3 አመት ለትምህርት አወስትራሊያ.6 አመት ሙሉ ብቻዋን መሆኗ ጎድቷት ይሆናል ብዬ ስለማስብ ዝምታን መርጫለው...
የናፈቅሁትን ሀገር የናፈቅሁትን ቤተሰብ የናፈቅሁትን ነገር ሁሉ ላገኝው ወራቶች አልፈው ቀናቶች ቀናቶች አልፈው ሰአታት ቀርተውታል,በቃ ጏደኛቼ ትንሽ እዚህ ስራና ሂድ ለመሄድ አትቸኩል ሲሉኝ እኔ ግን መሄድን መርጬ ወደ ናፈቅሁት ቤተሰብ መቀላቀልን ወስኜ ለመሄድ ዝግጅቴን አጠናቀቄ በመጠባበቅ ላይ ነኝ .ስልክ ደውዬ ለቤተስብ ልመጣ እንደሆነ ተናገርኩ ጏደኞቼን ተሰናብቼ መንገዴን አቀናሁ......

ይቀጥላል......
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
​​የድሀ ፍቅር❣️
ክፍል 2⃣0⃣

#በእዉነተኛ_የህይወት_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ


በናፍቆት የሚንከራተቱ አይኖቼን ይዜ ወደ ናፈቁ ቤተሰቦቼ
ለመሄድ ጉዞ ጀመርኩ ,ልጄን,
እናቴን ,ወንድሜን,ፍቅሬ ,ለማየት በጣም
ጏጎቻለው.የበረራው ሰአት ደርሶ .በረራ ጀመርን
.ብዙ ነገሮችን እያሰብኩ መድረስ አይቀር በሰላም ደረስን
ከፕሌን ወርጄ ዕቃዎቼን ይዜ
ወደ ውጪ ወጣሁ የናፈቁኝን ቤተሰቦቼን ለማግኝት በአይኔ
መፈለግ ጀመርኩ ,
ትንሽ መቆም ስለነበረብኝ ቆምኩ ድንገት አባቢ የሚል
የህፃን ልጅ ድምፅ ስማሁ ዞር
ዞር ብዬ መፈለግ ጀመርኩ ከሰሞች መሀከል ሜላቴ
ቅዱስን ታቅፋ እጃቸውን
ሲያውለበሉብ አየኃቸው.ሰውነቴን ኤሌክትሪክ የነዘረኝ
ያክል ውርር ስትያደርገኝ ታወቀኝ
,ተንደርድሬ ሄጄ አቀፍካቸው ወንድሜ እናቴ ልጄ ፍቅሬ
ሁሉንም ሳገኝ የደስታ እንባ
አነባሁ ሁላችንም ተቃቅፈን ተላቀስን ለ 3 አመት ያጣሁትን
የቤተስብ የልጅ ፍቅር
መልሼ አገኝሁት ...
የፍቅር የደስታ እንባ ተራጭተን ወደ ቤት አመራን ልጄ
ቅዱስ እኔ ላይ ተጠምጥሞ
የሚላቀቅ አይመስልም ,ስለእኔ ጥሩ ጥሩ ነገር እየነገሩ
ነው ያሳደጉት በዛ ላይ ሁሌም
ስደውል አወራዋለው በጣም እንደምወደው ሁሌም
ስለምነግረው በቃ የናፈቀውን
ናፍቆት እኔ ላይ ጥምጥም በማለት እየተወጣ ነው,እቤት
ስንደርስ በጣም ደስ አለኝ
,ከጠበቅሁት በላይ አሪፍ ኑሮ እየኖሩ ነው .ሁሉ ነገር
ተሟልቶላቸዋል .ይበልጥ
ተደሰትኩ......
ከቤተሰቦቼ ጋር ሆኜ የደስታ ጊዜ ማሳለፍ ጀመርኩ ሁሉም
ነገር መልካም እየሆነ መጣ
ሜላቴም መነጫነጫንም ሆነ መቆጣቷን ትታለች ደስተኛ
ነች .ልጃችንን በሳምንት አንድ
ቀን እሁድ ዘና ለማለት ከፈለጉ ከከተማ ውጪ ካልሆነም
አሪፍ መናፈሻ ሄደን ትንሽ
እንዝናናለን ያ ነው መሰለኝ ሜላትን ደስተኛ አድርጏታል
...እኔም የራሴን ስራ ለመጀመር
በዝግጅት ላይ ነኝ ,እናቴ ስራ ስለሌላት ቅዱስት
መንከባከብ ሆኗል ስራዋ .ታናሽ
ወንድሜ በጣም ጎበዝና ጠንካራ ተማሪ ሆኗል .በቃ ከእኔ
በላይ ጎበዝ ተማሪ ሆኗል
በጣም በሱ ደስተኛ ነኝ...
ህይወት እንደ አዲስ እየተቀየረ ነው ሁላችንም እንደ አዲስ
ህይወት የምንጀምር ነው
የሚመስለው በተለይ እኔ ,ለእኔ ሁሉም ነገር አዲስ ነው
የራሴን ስራ መስራት መጀመሬ
አስደስቶኛል.ሜላቴም ስራዋን በደንብ እየስራች ነው ,ልጄ
መዋለ ህፃናት ገብቷል .እናቴ
ሄዳ ታመጣዋለች እሷው ስትንከባከበው ትውላለች....
ሁሉም ነገር እየተቀየር $ገንዘብ እየመጣ በስራ
መወጥር ሲጀመር ፀባይም እየተቀየረ
መጣ!! እኔ ፍፁም እናቴንና ወንድሜን ትቼ ለብቻዬ ቤት
ተከራይቼ የመኖር አላማዬም
ፍላጎትም ኖሮ አያውቅም ሜላት ግን ,ብር ስላለን
የራሳችን ቤት የራሳችን ህይወት
እንዲኖረን እፈልጋለው ማለትን ተያይዘዋለች . # ገንዘብ
ሲበረክት ፍቅር ይላላል!!
የሚባለው እውነት ነው.በእኔ ላይ እየደረስ እያየሁት ነው
.በቃ ሜላትም ንግግሯ ሁሉ
ገንዘብ ሆኗል,
እኔ የማስበው ስለ ፍቅራችን እንጂ ስለ አለን ገንዘብ
አውርቼ አላውቅም ምክንያቱም
ያገናኝን ፍቅር እንጂ ገንዘብ አይደለም ለሜላት ደግሞ
ገንዘብ ማግኝት ብርቋ አይደለም!
የሀብታም ልጅ ነጮችን ,እኔ ነኝ እንጂ የድሀ ልጅ ገንዘብ
ማግኝት ብርቅ የሆነብኝ ,ግን
ገንዘብ ማግኝታችን በፍፁም ፍቅራችንን ያላላዋል ብዬ
አስቤ አላውቅም እንዲያውም
እንደሚጠነክር ነበር የማስበው ግን
አልተሳካልኝም,.ሜላት ድሮ የሴት ጏደኞች
አልነበሯትም አሁን ግን ብዙ ጏደኞች አፍርታለች,ከእነሱ
ጋር ነው ውሎዋ ምሳም
እራትም ውጪ ትበላለች ,ለሁለታችን ጊዜ መስጠት
አቁማለች በቃ ግራ ግብት ብሎኛል
ሁሌ መሸማቀቅ ስልችት ብሎኛል ቀድሜ ስራ ጨርሼ
እቤት ስገባ እሷ ግን አምሽታ
ትመጣለች ,ሁኔታዋ አስፈርቶኛል......

ይቀጥላል......
   ‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
​​የድሀ ፍቅር❣️
ክፍል 2⃣1⃣

#በእዉነተኛ_የህይወት_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ



እኔና ሜላት በቃላት አለመግባባት ከመነጋገር ዝም መባባልን ከጀመርን ቀናቶች ተቆጥረዋል እሷም ማምሸቱን ውጪ መብላት መጠጣቱን አዘውትራበታለች እየሄድንበት ያለው መንገድ በጣም መሰዋዕት ሊያስከፍለን እንደሚችል አሰብኩ ሜላቴንም ለማናገር ወሰንኩ .ለልጃችን እንዲሁን ለእናቴና ለወንድሜ ስል እነሱ ፊት ምንም ነገር ተናግሪያት አላውቅም በተለይ ለልጄ,...
ጠዋት ስራ ከመሄዴ በፊት ቅዱሴን ትምህርት ቤት አድርሼው በዛው ወደ ስራ ገባሁ የሻይ ሰአት ጠብቄ ሜላት ጋ ደወልኩ ..ማታ አብረን እራት እንድንበላ እንደምፈልግ ነገርኳት ደስተኛ አልነበረችም ግን እሽ አለችኝ,ማታ ምን ብያት እንደምንነጋገር እያሰብኩ ዋልኩ በቃ ግልፅ በግልፅ መነጋገር እንዳለብን አሰብኩ ,እንደዛ ካልሆነ ትዳራችን አደጋ ላይ ነው,....
ከስራ እንደወጣሁ እቤት ሄጄ ልብሴን ቀይሬ ወደ ሜላት መስሪያ ቤት ሄድኩና እሷን ይዤ ወደ አንድ ሆቴል እራታችንን እንድንበላ ገባ ያቺ ፍልቅልቋ ሜላት ሳትሆን ሌላ የማላውቃት ሜላት አጠገቤ ያለቺ መሰለኝ ነገረ ስራዋ ሁሉ በሀይለ ቃል የተሞላ ነው የምናገረውን ነገር በቀጥተኛ ሳይሆን በተዘዋዋሪ እየተረጎመች ትቆጣኛለች,ለደቂቃዎች ዝም ተባባልን ይገርማል ያልጠበቅሁት ነገር አጋጠመኝ.....
ዝምታውን ለመስበር ምን ማድረግ እንዳለብኝ ማሰላሰል ጀመርኩ እስኪ በድሮ ትዝታ ልጀምር ብዬ ,.ሜላቴ ታስታውሻለሽ ድሮ ከአመታት በፊት ካፌ ስንገባ እንዳልሸማቀቅ አንተ ክፈል ብለሽ ቅድሚያ የምትሰጪኝ ብር .ብዬ ፈገግ አልኩ.ሜላቴ ግን ፊቷን ቅይርይር አስርጋ የትላንትን ትዝታ ልታመጣና ልታስታውሰኝ ነው እራት እንብላ ያልከኝ አለች ....አፈጠጠችብኝ...እኔም ተርበተበትኩ ,..አ አ አ ስል ገና ልናገር አሁን አብረን እራት እንድንበላ ከፈለግህ ዝም በል አለችኝ ,እሽ ብዬ ዝም አልኩ....
በዝምታ የታጀበ እራት በላን ግን አሁንም አላስቻለኝም ,ሜላቴ ላናግርሽና ልንነጋገር ስለፈለግሁ ነው እዚህ እራት እንድንበላ የጠየቅሁሽ አልኳት ,መነጋገር እንችላለን አይደል አልኳት እንደጥያቄ አድርጌ አወ አለችኝ,.ምን መሰለሽ ሜላቴ ከትንሽ ቀናቶች ጀምሮ ጥሩ አይደለሽም ሙሉ ለሙሉ ተቀይረሽብኛል ሌላው ቢቀር የምትወጂውንና የምትሳሺለትን ቅዱስን በስርዓቱ ማጫወት ትተሻል ለምን ግን አልኳት አይናይኗን እያየሁ....
ሜላቴ በረጅሙ ተንፍሳ አየህ ብላ ጀመረች እኔ ለፍቅራችን የቻልኩትን ሁሉ አድርጌ እዚህ አድርሼዋለው አንተ ግን እየናድከው እያፈረስከው ነው .አለችኝ .ደነገጥኩ ምን አደረግሁ እናቴ ምን አጥፍቼ ነው አልኳት ...ቢያንስ ላንተ ስል የከፈልኩትን መሰዋዕትነት ልታስታውስ ይገባህ ነበር ,አለችኝ ተወሳሰበብኝ እንዴይ አልገባኝም ምን ለማለት ፈልገሽ ነው አልኳት .....
እየውልህ እኔ ከዚህ በኃላ መጨናነቅ አልፈልግም በሰላም ለብቻዬ የራሴ ቤትና የራሴ ህይወት እንዲኖረኝ እፈልጋለው...አየህ የእኔ እህት ሁለት ወልዳ በሰላም እየኖረች ነው እኔ ግን አለችኝ ,ደነገጥኩ ,,ምን አጎደልኩብሽ ,ላደረግሽልኝ ነገር ሁሉ ውለታሽን ለመክፈል እየሞከርኩ ነው የምችለውን ሁሉ አደርጋለው አልኳት ,እሽ የምትችለውን ሁሉ ማድረግ ከቻልክና የትላንት ፍቅራችን እንዲመለስ ከፈለግህ እናትህንና ወንድምህን ትተህ ለብቻችን መኖር እንድንችል አድርግ ...አሁን ወደ ቤት እንሂድ ብላ ሂሳብ ልትከፍል ቦርሳዋን አነሳች ቆይ እኔ እከፍላለው ስላት ...ችግር የለውም መክፈል ልማዴ ነው ብላ ቀልቤን ግፍፍ አደረገችው ........

ይቀጥላል......
   ‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
​​የድሀ ፍቅር❣️
ክፍል 2⃣2⃣

#በእዉነተኛ_የህይወት_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ


እኔና ሜላት አብረን አምሽተን እሷም የእኔን ቀልብ ስትገፍና ስታስደነግጠኝ አምሽታ ሂሳብ ከፈለች ...ምንም አላልኩም አንዳንዴ ብዙ ከመናገር ብዙ ማዳመጥ ይባል የለ,... ለዛ ነበር ዝም ያልኩት,እቤት ገብተን እራት ስለበላን ወደ መኝታ ክፍላችን ተኛን ቅዱሴ ተኝቶ ነበር የደረስነው ምክንያቱም አምሽተን ስለደረስን.....
በዚህ ሁኔታ እስከመቼ መቀጠል እንዳለብን ባለውቅም ብቻ ስራ ስለበዛብኝ መጣደፍ ጀመርኩ.....በእኔና በሜላት መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት እኔቴ በፈፁም እንድታውቅ አልፈለግሁም ስለዚህ እናቴ ፊት እኔና ሜላት ሰላማዊ እንሆናለን....ታናሽ ወንድሜ ግን አንድ ቀን ስንጨቃጨቅና እናቴን ተለይተን መኖር እንዳለብን ስትነግረኝ ስምቷታል ... እናቴን ማስጨነቅ ስላልፈለገ ብቻ ዝምታን መርጧል.....
እኔም ከስራ እቤት ከቤቴ ስራ እንጂ ሌላ የትም ቦታ አልሄድም ልጄን ሳጫውት ማምሸት እመርጣለው ...ለነገሩ የስራ ባልደርቦቼ እንኳን እንዝናና ሲሉኝ ደስታኛ አልሆንም.... እናቴ ሜላት የት ነው የምታመሸው ብላ ስትጠይቀኝ...ሰበብ እየፈጠርኩ እዋሻታለው .አንዳንዴ ቤተስብ ጋ እህቷ ጋ ከጏደኞቿ ጋ ስራ ቦታ ....ብቻ ያልዋሸሁበት መንገድ የለም ...
አንድ ቀን እንደተለመደው ቀድሜ ገብቼ ቀኑ ገብረኤል ስለነበር .እናቴ ብና አፍልታ ቤቱን አድምቃ ሜላትን መጠበቅ ጀመርን እንጠጣ ቡናውን ስላት ሜላት ሳትመጣ አይሆንም አለችኝ.....ጨነቀኝ መሽ ሲመሽ እናቴ ተስፋ ቆረጠች ቡናውን እኛው ጠጣንም...ቡናው ልክ ሲያከትም ሜላት መጣች ...እናቴ ሜላቴ ጠብቀንሽ ስትቆይብን ጠጣነው ይቅርታ አለቻት....
ሜላት ግን ትንሽ ጠጥታም ስለነበር ስደብቀው የከረምኩትን በመሀከላችን የተፈጠረውን አለመግባባት ምንም ሳታስቀር ለእናቴ ዘረገፈችላት ...ቀልቤ ተገፈፈ ወንድሜ ሁሉንም ያውቅ ስለነበረ ምንም አላለም እናቴን ወደ መኝታ ክፍል ይዟት ሄደ ...ሜላትን ምን እንደምላት ግራ ገባኝ ትቻት ክፍላችን ገብቼ ጥቅልል ብዬ ተኛሁ ...እንባም ተናንቆኛል ..እናቴ ለመጀመርያ ጊዜ አንገቷን ስትደፋ አየኃት ...በድህነቷ የምትኮራ ማዘን የማትወድ ባላት የምትደሰት ለሰዎች ብርታት የነበረችው እናቴ በሜላት ከልክ ያለፈ አነጋገር አንገቷን ስትደፋ ሳይ ልቤ ተሰበረ በጣም አዘንኩ ...ግን በቃላት ሜላትን ማስከፋት ስላልፈለግሁ ጥቅልል ብሎ መተኛትን ምርጫዬ አደረግሁ....
ጠዋት ከመኝታዬ ስነሳ ሜላት ተኚታለች ዝም ብዬ ልብሴን ለብሼ ወደ ሳሎህ ሄድኩ ማንም ሰው የለም እናቴ ክፍል ስገባ እናቴ ተኝታለች ደህና አደርሽ ብዬ ግንባሯን ስይምኳት ግን የተኛች ስላስመሰለች ዝም አለችኝ ወንድሜ የለም ... ወደ ቅዱስ መኝታ ክፍል ስሄድ ቅዱስ የለም ወንድሜ ትምህርት ቤት ሊያደርሰው ሄዷል....ከቤት ልወጣ ስጣደፍ በስልኬ ሜሴጅ ደረሰኝ ወንድሜ ነበር ላናግርህ እፈልጋለው ከቤት ከወጣህ የት እንገናኝ?ይል ነበር ደወልኩለት ...ቦታ ተቀጣጥረን ወደ ስራ ከመግባቴ በፊት እንዳገኝው ወደ ተቀጣጠርንበት ካፌ አመራሁ....
ቀድሞኝ ደርሶ ስለነበር የተቁመጠበትን በምልክት ነግሮኝ አገኝሁት ....ከቤት ለመጀመርያ ጊዜ ቁርስ ሳልበላ ወጣሁ ....ጠዋት ጠዋት የእናቴ ጉርሻ ሱስ ሆኖብኛል ግን ዛሬ ሳልጎርስም ቅርስም ሳልበላ ከቤት ወጣሁ... ቁርስ አዘዝንና እስከሚደርስልን ድረስ ...ወንድሜ ለምን እንደፈለገኝ መነጋገር ጀመርን ...ወንድሜ ሁሉንም ነገር ቀድሞ እንደሚያው ነገረኝ ቀልቤ ተገፈፈ ...እንዴት እንዳወቀና እስከዛሬም ዝም ያለው ቤት እየፈለገ ስለነበር ነገረኝ...አሁን ግን አታስብ ቤት አግንቻለው አለኝ.....
ቁርሳችን ደርሶ ቀረበልን ግራ ገባኝ እናቴ ሳታጎርሰኝ ቀድሜ ጎርሼ አላውቅም .ወንድሜ ልማዴን ስለሚያውቅ .እንካ ጉርስ እናቴ ከእንግዲህ የለችም ልመደው ብሎ አጎረሰኝ .ጉርሻውን ጎርሼ መብላት ጀመርኩ.... ቆይ ግን እስከዛሬ ቢያንስ ለእኔ እንዴት አትነግረኝም አልኩት ላጨናንቅህ ስለማልፈልግ ነው አለኝ ....አሁን ምንም እንዳትጨናነቅ አንተና ሚስትህ ሜላት በሰላም ትኖራላችሁ እኛም ስትናፍቅርን መጥተን እንጠይቃችኃለን አለኝ.....
ከስደት ተመልሼ ከቤተሰቤ ተደባለቅሁ ስል ድጋሚ ሌላ ጣጣ ይገርማል,....እኔና ወንድሜ ተነጋገርን ብር እስከዛሬ ለታክሲ ለትምህርት ቤት በቃ ለተለያዩ ነገሮች እያልክ የምትሰጠኝን አጠራቅሜ የ 3 ወር ቤት ኪራይ ከፍያለው አለኝ ደነገጥሁ ለምን አልኩት ችግር የለውም ከፈለግሁ ደግሜ እጠይቅሀለው አለኝ,... እሽ ብዬው እንኡም ወደ ስራ መግባት ስለነበረብኝ ወደ ስራ ሄድኩ..ስራ ከመድረሴ በፊት ለወንድሜ በባንክ አካወንቱ ብር አስገባሁለት,....ከዛም ወደ ስራ ሄድኩ.....
ስራ ቦታ ስራ በዝቶብኝ እየተጣደፍኩ ሜላት ደወለች,ሰላም አልኳትና ልታናግረኝ የምትፈልገው ነገር አንዳለ ስትነግረኝ ከስርይ በኃላ ብያት ስልኩን ዘጋሁት ..ስደክም ውዬ ማታ ወደ ቤት ልሄድ ስል ወንድሜ ደወለልኝ ስራ ቦታ በር ላይ ከቅዱስ ጋ እየጠበቅንህ ነው ና አለኝ እሽ ብዬ ወጣሁ ስላም አልኳቸውና ወደ ቤት እንሂድ ስለው እሽ እናንተ ሂዱ እኔ እዚህ ሰው ቀጥሪያለው ብሎኝ ወንድሜ ሄደ,..እኔና ቅዱስ እየተጫወትን ወደ ቤት ሄድን ,.. እቤት ስደርስ ያጋጠመኝ ነገር ግን ያልጠበቅሁት ነገር ነበር........

ይቀጥላል.........
‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
​​የድሀ ፍቅር❣️
ክፍል 2⃣3⃣

#በእዉነተኛ_የህይወት_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ


እኔና ቅዱስ ወደ ቤት ተመለስን እቤት ስደርስ ያጋጠመኝ ነገር ግን ያልጠበቅሁት ነገር ነበር ...እናቴ እራት ሰርታ ጠረቤዛው ላይ አስቀምጣ በትንሽዬ ወረቀት ይቅርታ ልጄ,,ብላ ፀፉልኝ አገኝሁት በጣም ደነገጥኩ,...እናቴ ክፍል ተንደርድሬ ስገባ የእናቴም የወንድሜም ልብስ የለም,.እናቴ ቤቱን ትታ ሄዳለች ...በጣም ተበሳጨሁ እንባ ተናነቀኝ ቅዱስ ዝም ብሎ ቆሞ ያየኛል .....

በዛው ቅፅበት ሜላት መጣች ቤቱ እርጭ ብሏል ግራ ገባት የደነገጠች ትመስላለች ደህና ዋላችሁ አለች...ካጎነበርኩበት እንባዬን ጠርጌ ቀና በማለት ሰልይምታ ሰጠኃት ...ውዱሴም ማሚ ብሎ ሄዶ ተጠመጠመባት አቅፋ ሳመችው ...እንዴት በጊዜ እንደመጣች ገርሞኛል ግን ልጠይቃት አልፈለግሁም ..እንዳቀተቀርኩ ዝም አልኳት...

ሜላት ዝምታው ስለጨነቃት ምን እንደተፈጠረ ጠየቀችኝ እኔ ሳልሆን ቅዱስ እቴቴ ሌላ ቤት ሄደች..ስትናፍቀኝ መጥቼ አይሀለው ስናፍቅህ ና እሽ ብላኝ ሄደች አላት....እኔ ምንም አልተነፈስኩም..ሜላት ደነገጠች ..ትላንት ለተናገርኳቸው ነገር ይቅርታ ልጠይቃቸው ነበር በጊዜ የመጣሁ በጣም አዝናለው አለች,.ምንም ሳልላት ተነስቼ መኝታ ክፍላችን ገባሁ... ልብሴን ቀይሬ እናቴ መኝታ ላይ ጋደም አልኩ,...

ቅዱስ አባቢ ተነሳ እርቦኛል እራታችንን እንብላ አለኝ ....እንቢ ማለት ስላልፈለግሁ ተነስቼ ወደ ምግብ ጠረቤዛው ሄድኩ የቤቱ ቅዝቃዜ በጣም ያስፈራል ለመጀመርያ ጊዜ ነው እንደዚህ ቅዝቅዝ አለ ቤት ውስጥ ስናመሽ ሜላትም ጨንቋታል እንዳታንይግረኝ ምን ትበለኝ ዝም እንዳትል ዝም ማለት አልቻለችም...እሽ ግን የት ነው የሄዱት እኛ እንውጣ እንጂ መቼ እነሱ ይውጥ አልኩ አለች..... ልጎእስ በእጄ የጠቀለልኩትን ትቼ ምንም ሳልል ከመቀመጫዬ ተነስቼ እጄን ታጠብኩና ደህና እደሩ ብዬ እናቴ ክፍል ገብቼ ተኛሁ.....
ሜላት የምትይዘው የምትጨብጠው ጠፍቷታል ቅዱስም አባቢ ካንተ ጋር መተኛት እፈልጋለው ብሎኝ አጠገቤ መጥቶ ተኛ,.....ሜላት የበላንበትን አንስታ ክፍላችን ገብታ ተኛች,በአይኔ እንቅልፍ ሳይዞር ነጋ ....እናቴ ጋ ያልደወልኩት ምንም የምለው ነገር ስለሌለኝ ነበር ምክንያቱም እናቴ ቅር ብሏታል ስለዚህ ደውዬ ምንም አልላትም... ዝም ብዬ አደርኩ,ጠዋት ከመኝታዬ ተነስቼ ቅዱስን አስነስቼ ልብሳችንን ቀያይረን ልንወጣ ስንል ሜላት ነቃች ...

ወዴት ልትሄዱ ነው ቁርስ ልስራ ስትል አይ ተይው ውጪ እንበላለን ስራ እንዳይረፍድብሽ ብያት .ቅዱስን ይዝኡ ወጥይሁ...ወንድሜ ጋ ደውዬ የቤታቸውን አድራሻ ተቀብዬ እናቴ ጋ ሄድኩ..እናቴ ጋ ደርሰን ገና እናቴን ሳያት ቅዱስ ከመኪናው ወርዶ እየሮጠ እቴቴ ቁርስ ደርሷል እርቦኛል አላት ,...ና ልጄ ቁርስ ደርሷል ብላ እኔን ሰላም ብላኝ ወደ ውስጥ ገባን ....እናቴን ሳያት እንባ ተናንቆኛል ግን በፍፁም ማልቀስ አልፈለግሁም ምክንያቱም እናቴ ሳለቅስ ማየት እንደማትወድ ስለማውቅ.....

እናቴ የፊቷ ፈገግታ ምንም አልቀነሰ ...ገብተን የተዘጋጀውን ቁርስ በላን ወንድሜ ጎበዝ ነው ቤቱን አሟልቶታል,...ቁርስ በልተን ቅዱስን ይዜ ልወጣ ስል ሜላት ደወለች.ቅዱስ ከትምህርት ሲወጣ እኔ አወጣዋለው አለችኝ እሽ ብያት ቅዱስን ትምህርት ቤት አስገብቼ እኔም ወደ ስራዬ ገባሁ,..ስራዬን እንደምንም ስሰራ ዋልኩኝ .....ማታም ወደ ቤት ሄድኩ እቤት ስደርስ ግን ማንም ሰው አልነበረም......

ይቀጥላል..........
  ‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
​​የድሀ ፍቅር❣️
ክፍል 2⃣4⃣

#በእዉነተኛ_የህይወት_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ


ከስራ አምሽቼ እናቴ ጋ ሄጄ ማምሸት እያማረኝ ሜላቴ ቀድማኝ ከገባች ትናደድብኛለች ብዬ ቅር እያለኝ ወደ ቤት ሄድኩኝ ,...እቤት ስገባ ግን ማንም ሰው የለም ...ቤቱ ጠዋት ትቼው እንደወጣሁት ነው ምንም የተቀየረ ነገር የለውም,...እናቴ ክፍል ስገባ የተኛንበት አልተስተካከለም,..ልብሳችንን አነሳስቼ መኝታውን አነጠፍኩት....
ወደ እኔና ሜላት ክፍልም ስገባ አልተነጠፈም የቀየረችውን ልብስ እንኳን አላነሳችውም... እሱንም አስተካከልኩ ስልኬ ቻርጅ ስላልነበረው እሱን እያደረግሁ ቤቱን ማስተካከል ጀመርኩ.... ማታ እራት የተበላበት ሰአን አልታጠበም,...ብቻ በአጠቃላይ ቤቱ በጣም ያስጠላል ያስፈራል... እሪ ብዬ ብጮህ ደስ ይለኝ ነበር ግን አልችልም.....
ስራውን ሰርቼ ጨረስኩ እራት መስራት ፈለግሁ ግን ቅድሚያ ሜላት ጋ ልደውል ብዬ ስልኬን ከፈትኩት ሜላት ደውላ ነበር ግን ባትሪ ዘግቶብኝ ስለሆነ አላየሁትም ...መልሼ ደወልኩ አታነሳም ትንሽ ልጠብቅ አልኩ ....ግን ማንም የመጣ ሰው አልነበረም ...በጣም ተበሳጨሁ ተናደድኩ ግን በቃ ትዕግስት ይኑርህ እያለች ነው እያቴ ያሳደገችኝ.....
ጠብቄ ጠብቄ ሰው ሳይመጣ የሜላት ስልክ አልነሳ ሲለኝ እናቴ ጋ ደወልኩ ሰላም አልኳት እቤት ማንም እንደሌለ ነገርኳት እራት ቀርቧል ና አለችኝ ...ተነስቼ እናቴ ጋ ሄድኩ .... እናቴ ጋ እራት በልቼ ትንሽ ተጫውቼ ወደ ቤት ተመለስኩ ... እቤት ስመለስ ሜላት ተኝታ አገኝኃት ቅዱስም ተኝቷል .....
ወደ ሜላት ተጠግቼ ሜላት አልኳት ምን ላድርግህ ?አለችኝ በጣም ደነገጥሁ....ስልክ ስደውልልሽ አታነሽም ስጠብቃችሁ ስትቀሩብኝ እናቴ ጋ ሄድኩ አልኳት ...አሪፍ ነው ደክሞኛል ማረፍ እፈልጋለው አለች....ሜላት እየጠየቅሁሽ ነው ስደውልልሽ ስልክ አታነሽም ለምንድነው? አልኳት....
ሜላት በጣም በመቆጣት ከመኝታዋ ተነስታ ቁጭ አለችና በመጀመርያ ስደውል ለምን አላነሳህም አለችኝ.... ስልኬ ባትሪ ዘግቶ ነበር እንደከፈትኩ ስደውልልሽ አታነሺም ሲጨንቀኝ እናቴ ጋር ሄድኩ አልኳት.... አሪፍ ነው እኔም ስልኬን መኪና ውስጥ እርስቼው ስለነበር ነው አሁን ደክሞኛል ደህና እደር ብላኝ ትታኝ ተኛች.....
ነገሩን ላለማክረር ብዬ እኔም ዝም አልኩ ልብሴን ቀይሬ ተኛሁ .....ጠዋት ስነሳ ሜላት ተኝታ ነበር እስከዛሬ እናቴ ነበረች በጠዋት ተነስታ ቁርስ ሰርታ ቅዱስን አልብሳ እኛን የምትቀሰቅሰን አሁን ግን ያ የለም..... እኔም ተነስቼ ቅዱስን ቀስቅሼ ሜላትን ቀሰቀስኳት .... ቅዱስን ልብሱን አልብሼው እኔም ለበስኩ ...ድንገት ቅዱስ አባቢ አባቢ እንደ ትላንትናው እነ እቴቴ ጋ ቁርስ እንበላለን አለኝ?.....
በጣም ደነገጥኩ ሜላት አፈጠጠችብኝ ... አይ ቅዱሴ ዛሬ ማሚ የሰራችውን ቁርስ ነው የምንበላው እሽ አልኩትና ወደ መኝታ ክፍል ገባሁ...ሜላት ተከትላኝ መጣች ...ትላንት በጠዋት ልጄን ይዘህ የሄድከው የት ነው አለችኝ ... እናቴ ጋ.. አልኳት ...በጣም ተበሳጨች ግን እናቴን እንደምወዳት ስለምታውቅ ምንም ማለት አልፈለገችም ነበር.....
ሜላት ቁርስ እስከምትሰራ እኔ መኝታችንን አነጠፍኩ የሚስተካከለእን አስተካከልኩ ...ቁርስ ደርሶ በልተን ቅዱስን ይዜ ወደ ትምህርት ቤት ሄድኩ በዛውስራዬ ገባሁ ....ስራ ውዬ ቅዱስን ወንድሜ ከትምህርት ቤት አውጥቶት ስለነበር ቅዱስን ላመጣ ሄድኩ ...በዛውም እራት ሳትበላ አትሄድም በለውኝ እራት በልቼ ወደ ቤት ሄድኩ .... እቤት ስንደርስ ሜላት እራት አዘጋጅታ ጠበቀችን ቅዱስ ጠግቧል እኔም ጠግቤያለው ግን በቃኝ ማለት ስላልፈለግሁ ቁጭ አልኩ..... ቅዱስ ወደ መኝታ ክፍል ሲገባ .. ሜላት በጣም ተቆጥታ ከዚህ በኃላ አንዱን ቤት ምረጥ እሺ ወይ እዚህ ወይ እናትህ ቤት ... ስትል ድንገት ቅዱስ መኝታ ቤት በር ላይ ሆኖ ሲሰማ አየሁት........

ይቀጥላል......

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
​​የድሀ ፍቅር❣️
ክፍል 2⃣5⃣

#በእዉነተኛ_የህይወት_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ

ሜላት የቅዱስን መኝታ ክፍል መግባት ተከትላ .ከእናትህ ቤትና ከእዚህ ቤት አንዱን ምረጥ ብላ ስትጮህብኝ ቅዱሴ የመኝታ ቤት በር ላይ ቆሞ ይሰማ ነበረ ...ሳየው ደነገጥኩ ...ሜላትም አየችው .ቅዱሴ ወደ መኝታ ክፍል ገብቶ ቁጭ አለ ተከትዬው ገባሁ .ሊያናግረኝ አልፈለገም... ሜላትም መጣች .እሷንም መልስ ሊሰጣት አልፈለገም....
ቅዱስ አኩርፏል ስንጨቃጨቅ አይቶን አያውቅም ሜላትም ስሜቷን መቆጣጠር አቅቷት ስለነበር በደንብ ተቆጥታ ነበር የተናገረችኝ...መቼም የእናቴን ቤት መተው አልችልም እናቴ ናትና ...የሚስቴንም ቤት አልችልም ሚስቴ የልጄ እናት ናትና ከዛም በላይ አሁን ላለሁበት ትልቅ መሰዋአትነት ከፍላለችና ብቻ ግራ ገብቶኛል ምን እንደማደረግ አላውቅም....
እኔና ሜላት ከቀን ወደ ቀን ጭቅጭቃችን እየባሰ ቅዱስም እናቴጋ መዋል ማደረን ከመረጠ ሰነባበትን .. ቅዱስ ወደ ቤት እንሂድ ሲባል እናቴ እግር ላይ ተጠምጥሞ አልሄድም ይላል..ግራ ገብቶኛል ፍቅራችን እየተናደ እየተሸረሸረ ከመጣ ቀናቶች አለፉ...የተፈጠረውን እየተፈጠረ ያለውን ለእናቴ እነግራታለው....
ሜላት ሁሉን ነገር እርስት አድርጋው ጠጥታ አምሽታ ትመጣለች በጣም ሰለቸኝ በቃ ከአቅሜ በላይ ሆነችብኝ ምን ላድርጋት... ብመክራት ባስመክራትa ምንም ልትስተካከል አልቻለችም ...አንድ ቀን አምሽታ በጣም ሰክራ መጣች ያን ቀን ግን በጣም በሽቄ ስለነበር በቃ እኔ ከዚህ በኃላ እኔና አንቺ አብረን መሆን አንችልም እናቴ ጋ እሄዳለው አልኳትና እናቴ ክፍል አድሬ ጠዋት ሻንጣዬን አዘጋጅቼ ወደ እናቴ ቤት ሄድኩ.....
የእኔና የሜላትን እንደዚህ መሆን ሰው ሲሰማው እጅግ ልገረምበት ይችላል እንዳንድ ሰዎች ገንዘብ ሲበረክት ፍቅር ይጨምራል ይላሉ ግን ውሽት ነው ገንዘብ ሲበረክት ፍቅር ይጠፋል....እኔና ሜላት በድህነቴ የነበረን ፍቅር እጅ በጣም ደስ ይል ነበር ገንዘብ ስናፈራ ብር ወደኛ ሲመጣ ግን ፍቅራችን ተሸረሸረ ...ልጃችንን እንኳን በፍቅር ማሳደግ አቅቶን ሁለታችንም በተለያየ መንገድ መጎዝ ጀመርን....
ብዙውን ጊዜ ቅዱስ እናቴ ጋ ነው የሚውለው ሜላትም ስትፈልግ ትወስደውና አሷ ጋ አድሮ ውሎ ይመጣል ... እኔና ሜላት አንድ ነገር ተነጋግረናል ከቤት ሰወጣ ...መጠጧን ትታ ወደራሷ ተመልሳ ...ትዳራችንን ለመቀጠልም ሆነ ለመፋታት እንደምንወስን ነገር ግን በዚህ ሁኔታ ምንም ነገር መወሰን እንደማልችል ነግሪያት ነበር ...
ሜላት ሁሉንም ነገር አየችው ለሳምንታት ያክል እኔ እየተደበቅሁ እያየኃት እሷ እንዳታየኝ እየተጠነቀቅሁ ስከታተላት ከረምክ ..በጣም ተጎሳቁላለች የሚገርመው የያዘቻቸው ጏደኞች እልም ያሉ ጠጪዎች ናቸው አብዛኞቹ እንደ ሹገር ማሚ ነገር ይሰራሉ ..የተረፍት ደግሞ አግብተው የፈቱ ናቸው...ከእነሱ ጋር ሆና ነው እንደዚህ ቅይርይር ያለችብኝ ...
አንድ ቀን ማታ ከሰራ ስትወጣ ተከትያት ሄድኩኝ ሆቴል ውስጥ ስትገባ አብሪያት ገባሁ ...በጣም በብዛት ተሰብስበው ወደ ሚጠጡ ሴቶች ተደባልቃ ቁጭ አለች ...ብርጮቆ አምጥተው ቀዱላት ..በአንድ ትንፋሽ ጭልጥ አድርጋ ጠጣችው አጠጣጧ ያስፈራል ...ሳትሰክር ማናገር ስለነበረብኝ ...ተጠጋኃቸው ስታየኝ ደነገጠች ሁሉንም ሰላም አመሻችሁ አልኳቸው ...እዚህ ምን ትሰራለህ ብላ አፈጠጠችብኝ...ምንም አልሰራም መቼም መጠጥ እንደማልጠጣ ታውቂያለሽ ግን አንዳንድ ነገሮችን አንቺ ያላወቅሻቸውን ላሳውቅሽ ብዬ ነው አልኳት....ሴቶቹ ግራ ተጋቡ እሷም አይኗን አፈጠጠችብኝ.....

ይቀጥላል ......

      
    
💞የድሀ ልጅ ፍቅር
ክፍል 2⃣6⃣

የመጨረሻ ክፍል🔚

#በእዉነተኛ_የህይወት_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ

ሜላትን ከስራ ስትወጣ ጠብቄ ተከትያት ሄድኩ ሆቴል ውስጥ ከሴቶቹጋ ተደባልቃ ስትጠጣ ወደ እሷ ተጠግቼ ሰላም ካልኳቸው በኃላ ...የሜላት በቁጣ እኔን ማየት የሴቶቹን ማፍጠጥ ሳይ የመጣሁበትን መናገር ጀመርኩ...
ሁሉም ዝምታን መርጠዋል ያጨሳሉ ይጠጣሉ...ሜላት በእውነት ብትዝናኚ ምንም አይመስለኝም ግን ከማን ጋ እየተዝናናሽ እንደሆነ አላወቅሽም አልኳት ...ምን ማለት ነው አለችኝ? ስለ ሴቶቹ ምንነት በደንብ ነገርኳት ሴቶቹ ደነገጡም ተናደዱ ምን አገባህ አሉኝ...ግን እኔ ሚስቴን ከእነሱ መንጋጋ ውስጥ ማውጣት ስለነበረብኝ ሁሉንም ምን እንደሚሰሩ ነግሪያት እሷም ከእነሱ ጋር ከቀጠለች ትዳራችን እንደሚያበቃለት ነግሪያት ደህና እደሩ ብዬ ወደ እናቴ ቤት ሄድኩ....
ሜላት እንደዛ ካልኳት በኃላ ወደ ቤቷ ተመልሳ ነገሮችን እንዴት ማስተካከል እንዳለባት እንደምታስብ እርግጠኛ ነበርኩ...ምክንያቱም ሳታውቅ ዝም ብላ ነበር ጏደኛ ያደረገቻቸው..... በሳምንቱ ስራ ውዬ ድክም ብሎኝ ወደ ቤት እየተመለስኩ እያለ ስልክ ተደወለልኝ አነሳሁት ሜላት ታማለች እቤት ቶሎ ድረስ የሚል ድምፅ አሰምተውኝ ስልኩ ተዘጋ...በጣም ደነገጥኩ ወደ እናቴ ቤት መሄዴን ትቼ ወደ እኛ ቤት በፍጥነት መንዳት ጀመርኩ ብዙ ነገር እያሰብኩ ነበር......
እቤት ደርሼ በሩን ከፍቼ ስገባ ግን የጠበቀኝ ነገር ሌላ ነበር የሜላት ቤተሰቦች እናቴ ቅዱስ ወንድሜ በአንድ ላይ ተሰብስበው አገኝኃቸው ..ሜላቴስ አልኳቸው ..ሜላት ከመኝታ ክፍል ወጣች ..ጉልበቴ ላይ ወድቃ ይቅርታ ጠየቀችኝ ..በዛውም የ 3 ወር ነፍሰጡር እንደሆነች ነገረችኝ ይቅርታዋን ተቀበልኩ እናቴንም ይቅርታ ጠየቀች ...
እናቴ ምንም እንኳን ይቅርታዋን ብትቀበል ተመልሳ ግን አብራን መኖር እንደማትችል ነገረችን እሽ አልን ምክንያቱም ድጋሚ ሌላ ፀብ እንዲፈጠር ስላልፈለግሁ ነበር በእናቴ ሀሳብ የተስማማሁት ...በጣም ደስ የሚል ምሽት አመሸን ፍቅራችን ወደ ድሮው ተመለሰ ...ቅዱስን የምትንከባከብ ሞግዚት ፈልገን አመጣን ..ስራ ከስራ እቤት መዝናናት ስንፈልግም አብረን ቤተሰብ መጠየቅ ብንፈልግም አብረን ..በቃ ሁሉም ድርጊታችን አንድ ላይ በመመካከር የተሞላ ሆነ.....
ቅዱሴም እጅግ በጣም ደስተኛ ሆነ ሌላ ልጅ እህት ሊወለድ እንደሆነ ስላወቀ እሱም ደስተኛ ነው ፍቅራችን ወደ በፊቱ ተመልሶ ቤታችን የደስታ ቤት ሆኗል ...ፍቅር መጣላት መኮራረፍ ..በቃላት አለመግባባት..ሊኖረው ይችላል ግን ከሁሉም በላይ ትዕግስት ይጠይቃል ..ከሁሉም በላይ ግን ""ፍቅር ያሸንፋል"

ተፈፀመ🔚

ፍቅር በገንዘብ ወይም በጌጣጌጥ ልንገዛው አንችልም ፍቅርን መግዛት የምንችለው በፍቅር ብቻ ነው ..ፍቅር ይበልጥ የሚጥመው በድህነት ሲሆን ነው."ድሀ ሲሰራ እንጂ ሲያፈቅር አያምርበትም""የሚባለው ሙሉ ለሙሉ ውሸት ነው እንዲያውም ድሀ ሲያፈቅር በጣም ነው የሚያምርበት "" ፍቅር ያሸንፋል"" ሁላችንንም የፍቅር ሰው ያድርገን ..ስለተከታተላችሁኝ አመሰግናለው በሌላ ታሪክ እስከምንገናኝ መልካም ቆይታ
.💗  ልቤ ብቻ ፅኑ   💗

ድሮ ድሮ ድሮ... ድንጋይ ዳቦ እያለ
ሰማይ እንደ ጣሪያ ሳይርቅ ዝቅ እንዳለ
ዶሮም እንዳሞራ መብረር እየቻለ
ታስታውሺ ነበር?  እወድሽ ነበረ

   ታዲያ ምን ያደርጋል ሁሉም ተቀየረ
   ድንጋይ ዳቦ ትቶ ድንጋይ ሆኖ ቀረ
   ሰማይ አፈንግጦ እንደዚህ ከፍ አለ
   ዶሮም መብረር ትቶ መራመድ ጀመረ
   ልቤ ግን ልብ ነው ያኔ እንደነበረ
   በዘመኑ ሙሉ ሲያፈቅርሽ የኖረ፡፡♥️
አንድ አንብቤ የወደድኩት ታሪክ አለ። አጭር ነው ይለቀቅ ወይስ.???

ይለቀቅ👍
ይቅር👎
ተሳቀ እን
           ክፍል አንድ💚

.
"እማ" ትላለች አፏን በደንብ ያልፈታችው ህፃን ጀርባዋን ሰጥታ ወደ ውጪ እየተመለከተች የቆመችውን እናቷን እያየች። እናቷ ከታላቅ እህቷ ጋር ያወራሉ።
እናትየው ለመውጣት የተዘጋጀች ልጃቸውን እየተመለከቱ መናገር ጀመሩ።
"እና በቃ መውጣትሽ ነው? ምሳሽን ግን በደንብ በልተሻል?"
"ኧረ በደንብ በልቻለሁ። በቃ ልሂድ ደህና ዋይ።" 
"ማን ጋ ነው ግን የምትሄጂው?"
"ቤቲን ላገኛት ነው።"
የቤቱን የውጪ በር ከፍታ ወጣች። እናትየው ከኋላቸው "እማ" እያለች የምትነጫነጨው ልጃቸውን ከምንጣፉ ላይ አንስተው አቀፏት።
.
በሩን ዘግታ ከወጣች በኋላ ወደ ፊቷ የተንሸራተተባትን ሻሿን የእጅ ቦርሳዋን ወደ ብብቷ አስገብታ ይዛ አስተካከለች። የወጣትነት የመጀመሪያው የፍካት ድባብ አብቦባታል። የሚያሳሳ የሰውነት ቅርፅ ፣ ሳሙኝ ሳሙኝ የሚል ከንፈር ሌላም ሌላም ብዙ የወጣትነት ፣ የመድረስ ምልክቶች ተንቆጥቁጠውባታል። ሀያት ከህፃንነቷ አንስቶ የምትጠራበት ስም ነው። ሀዩና ፣ ሀዩ ፣ ሀዩዬ እያሉ ያቆላምጧታል። ሀያት መልኳ የቀይ ዳማ ተብሎ የሚገለፅ አይነት ነው። መልኳ የተጋነነ ውበት ባይኖረውም ለክፉ የሚሰጥ አይነት አይደለም። የተጋነነ ውበት ያላቸውን የምንሰይምበት ቃል እንቸገራለን ብለን ባንሰጋ ቆንጆ ናት ልንላት እንችል ነበር።  የጠመጠመችው ሻሽ የሀብሀብ የውስጡን ቀለም ይመስላል። በእነርሱ አጠራር "ፒች" የሚባል የቀለም አይነት ያለው ነው። ቀሚሷ ከሻሿ ጋር ተመሳሳይ ቀለም አለው።  ከላይ  እጀ ሙሉ ሸሚዝ ለብሳለች። ዛሬ ቅዳሜ ነው። እንደ ሀያት ላሉ ከሰኞ እስከ አርብ ያለውን ጊዜ በትምህርት ለሚያሳልፉ ተማሪዎች ውድ እና ተናፋቂ የእረፍት ቀን ነው። ከቤቷ ወጥታ ጥቂት በእግሯ ከተራመደች በኋላ ተክለሀይማኖት አደባባይ ደረሰች። ከተክለሀይማኖት የሜክሲኮ ታክሲ ይዛ ቅዳሜን አብረው ፏ ሊሉ ወደተቀጣጠረቻት ጓደኛዋ ቤቲ ተስፈነጠረች።
.
ቤቲ ከሀያት ቀደም ብላ ሜክሲኮ ከተቀጣጠሩበት ካፌ ተገኝታለች። ዳለቻ ቀለም ያለው ቱታ ሱሪ ፣ በከፊል ገላዋን አሳልፎ የሚያሳይ ስስ ጥቁር ሹራብ ለብሳለች። ከላይ ደግሞ ኮፍያ ደፍታለች። ቤቲ ፈታ ለቀቅ ያለች ልጅ ናት። ደስታን የምታድን አይነት።
ሀያት ከካፌው እንደደረሰች ሰላም ተባብለው ወደ ሞቀ ጨዋታ ገቡ። ሁለቱም የአስራሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው። የሚማሩት በከተማዋ ውስጥ ታዋቂ ከሚባሉ የግል ትምህርት ቤቶች በአንዱ ነው።  ጨዋታ እየደራ ሰዓቱ እየገፋ ሲመጣ ቤቲ ለሀዩ አንድ ሀሳብ አቀረበች።
"ሀዩ ዛሬ እኮ ከኤርሚ ጋር ቀጠሮ አለን። እሱም ከጀለሱ ጋር ስለሚከሰት አብረን ብንሄድስ?"
"ኧረ አይመሽብኝም?"
"ኧረ የምን መምሸት ነው? አግኝተናቸው ትንሽ ተጨዋውተን ላሽ እንላለን።"
ሀያት በሀሳቡ ተስማማች። ቤቲ ኤርሚያስ ጋር ደውላ ያሉበትን ቦታ ነገረችው። ሰዓቱ ወደ ዘጠኝ ሰዓት ተኩል ተጠግቷል።
.
ቤቲ  በርካታ ጊዜ የፍቅር ጓደኛ ይዛለች። መመቻቸት ሲደባበሩ ደግሞ ላሽ መባባል የፍቅቅሮሽ ህይወቷ መመሪያ ነው። ሀዩ ከዚህ ቀደም ረቢቅ የሚባል ፍቅረኛ ነበራት። ከሱ ጋር አብረው እያሉ የአፍላነት እሳታቸው ከንፈር ለከንፈር እስከመጎራረስ አዝልቋቸዋል። የቤቲ እንኳ በርካታ ስለሆኑ እና በጉዳዩ ላይም ዘልቃ ስለሄደችበት "ለሷ" ብርቅ የሚባል አይነት አይደለም። ኤርሚ ባለጊዜዋ ነው። ጊዜ ለፍቅረኝነት የመረጠላት። ሙድ ለሙድ ገጥመዋል። ተመቻችተዋል።
.
ኤርሚ የካፌው በር ላይ ሲደርስ ደወለላቸውና ከካፌው ወጡ። የካፌው በር ላይ አንድ ብርማ ኤክስኪዩቲቭ ቆማለች። ኤርሚያስ ከጋቢና ወረደና ቤቲን እና ሀዩን ሰላም ብሏቸው ቤቲን ይዞ ከኋላ ገባ። ሀያት የነገሮች ሂደት በመራት መልኩ ጋቢና ገባች። መኪናውን የያዘው የኤርሚያስ ጓደኛ ነው። ኢስማኢል ይባላል። ነጭ ጂንስ ሱሪ እና ነጭ እጀ ሙሉ ስስ ሹራብ ለብሷል። ከላዩ ላይ እጀ ጉርድ ጃኬት ደርቦበታል። ኤርሚያስ ጂንስ ቁምጣ ለብሷል። ከላይ የደረቱን ቅርፅ አጉልቶ በሚያሳይ ጥቁር እጀ ጉርድ ቲሸርት ተወጣጥሯል። 
የመኪናው ሬዲዮ መንዙማ ያጫውታል። ቤቲ የመንዙማውን አንዱን ቃል ይዛ አብራ እያለች ትጨፍራለች። ጭንቅላቷን በድቤው ሪትም ልክ እየወዘወዘች ትቀውጠዋለች።  ኤርሚም አብሯት እጁን እያወዛወዘ ይጨፍራል። እስማኢል የስልኩን ካሜራ ከፍቶ ጭፈራቸውን ይቀርፃል። ሀያት እየሳቀች ትመለከታለች።
ኢስማኢል የመኪናው ሬዲዮ ላይ ጣቱን አሳርፎ መንዙማውን አሳለፈው። እንግሊዘኛ ዘፈን ላይ ሆነ። ቤቲ መቀመጫዋን ከወገቧ ጋር በስልት እያሾረች ሁለት እጆቿን ዘርግታ ትደንሳለች። ተሳሳቁ ፣ ፈገጉ።
እስማኢል እጆቹን የመኪናው መሪ ላይ እንዳደረገ ሀያትን በአይኑ ሰርቆ አያት። ከዚያም ወደ ኋላ ዞሮ ወደ ኤርሚ ተመለከተ።
"እ ኤርሚ ወዴት ልንዳው?"
"ወደ ሳር ቤት ንዳው፣ ወደ ዶዲ"
መኪናዋ ወደ ሳር ቤት ተወነጨፈች። አራት የዘመኑን እሳቶች ይዛ። ሁለት የደረሱ ፈታኝ ሴትነቶችን አንከብክባ ፣ ከዶዲ ሬስቶራንት በር ላይ ቆመች።
.
ኢስማኢል ከመኪናው ወርዶ አጎንብሶ ወደ ውስጥ ሲመለከት ኤርሚ እና ቤቲ መኪናው ውስጥ መቆየት እንደሚፈልጉና ከሀዩ ጋር መኪናውን እንዲለቁላቸው ጠየቋቸው። ሀያት የመኪናውን በር ከፍታ ወረደች። ያደረገችው ቋቋ ጫማ ነው። ልቧ ከወትሮው በተለየ ይመታል። የኢስማኢል ወንዳወንድነት ገና እንዳየችው ቀልቧን አጥፍቶታል። እየተራመዱ ወደ ሬስቶራንቱ ሲገቡ ጫማዋ ደንቀፍቀፍ አደረጋት። እስማኢል ሊደግፋት በሚመስል መልኩ እጇን ያዛት። የባሰ የልቧ ምት ተዘበራረቀባት። አተነፋፈሷ ተስተጓጎለ። እጇን መያዙን ያልወደደች ለመምሰል ኮስተር ለማለት ሞከረች። ከንቱ ሙከራ ፣ በልቧ የተፎረሸ ቀሽም ሙከራ። ሬስቶራንቱ ውስጥ ገብተው ወደ ፎቁ ወጥተው ተቀመጡ። ትንሽ እንደቆዩ አስተናጋጅ መጣ። መታዘዝ ባይፈልጉም ለመቀመጥ ሲሉ ሁለቱም ጁስ አዘዙ። የመጀመሪያ ቀን እንደመገናኘታቸው ብዙ ጠለቅ ያለ ወሬ አያወሩም። ስለ ትምህርቷ ፣ ስለ ስራው ብቻ ፤ ወሬው ከዚህ አይዘልም። እስማኢል ከሀያ ሁለት ዓመት አይዘልም። እሷ ደግሞ ገና አስራስምንት አመት አልሞላትም።
"ዎክ ብናደርግስ እዚህ ከምንቀመጥ?" አለ ኢስማኢል።
ትንሽ ተግደረደረችና "እሺ" አለች።
ከመቀመጫቸው ተነስተው ከሬስቶራንቱ ግቢ ወጡ። መኪናው ውስጥ ኤርሚና ቤቲ በስሜት ግለት ታፍነው የስሜታቸውን እሳት በመዳፎቻቸውና በከንሮቻቸው እየተነፈሱት ነው።
ኢስማኢልና ሀያት አስፓልቱን ተሻገሩ። አካባቢው ላይ በክፍት ብረት የታጠረ ግቢ አለ። የሜድሮክ ግቢ ነው። የአጥሩ ዙሪያ የድንጋይ መቀመጫ አለ። ኢስማኢል ተመቻችቶ ተቀመጠ። ቀና ብሎ ሲመለከታት እሷም ተቀመጠች። እንደምንም ራሱን አደፋፍሮ ክንዱን ከአንገቷ ላይ አሳረፈ። አቀፋት። አካባቢው ላይ ሰው አይበዛም። አንዳንድ ሰዎች በመንገዱ ላይ ሲራመዱ ይታያል። ሀያት እና ኢስማኢል አንድ ድንጋይ ላይ ለሁለት ተቀምጠዋል። በመካከላቸው ምንም አይነት ክፍተት የለም። ደግሞ ኢስማኢል ክንዱን ዘርግቶ አቅፏታል። ከሩቅ ለሚያያቸው የቆዩ ፍቅረኞች እንጂ ዛሬ የተገናኙ ፤ ከዚህ ቀደም የማይተዋወቁ አይነት ሰዎች አይመስሉም።  
የሀያት ልብ ሰላሙን አጥቷል። ከኢስማኢል ደረት የሚፈልቀው የሽቶው ጠረን ፣ ልቧ የቀለጠለት ወንዳወንድ የሰውነት ቅርጹ ፣ የሚያምረው የፊቱ ገፅታ ፣ ምናልባትም ኤክስኪዩቲቭ መኪናውም ትንሽ ገፅታውን ሳያጎላው አይቀርም ፤ እነዚህ ሁሉ ተደማምረው እጅ አሰጥተዋታል። አሁንም እንዳቀፋት ናት ፤ እየተንሾካሾኩ.....

ይቀጥላል
🌹🌹🌹🌹❤️የተሳቀ እንባ❤️🌹🌹🌹🌹
         ክፍል ሁለት
.
ሀያት መኝታ ክፍሏ ተቀምጣ ስልኳን እያየች በማመንታት ስሜት ውስጥ ትዋልላለች። ደፈረችና ደወለችለት።
"ሄሎ ኢስማኢል"
"ወዬ ማር"
"ቤት ደረስክ?"
"አልደረስኩም ፣ እየነዳሁ ነው ቤት ስገባ እደውልልሻለሁ"
"እሺ ችግር የለውም"
ሀያት ልቧ ኢስማኢልን አምልኮታል። ለመጀመሪያ ጊዜ ሳመችው ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ደወለችለት። መውደዷን የሴትነት ሀፍረቷ እንዲከልልላት አልፈቀደችለትም።
ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ሞልቶ ጥቂት ደቂቃዎች እንደተቆጠሩ ኢስማኢል ደወለ። ሀዩ ህፃኗን ወደ ሳሎን ወስዳ ለእናቷ ካስረከበች በኋላ መኝታ ክፍሏን ቆልፋ ስልኩን አነሳችው። 
"ሀዩዬ ወድጄሻለሁ"
"እኔም ደስ ብለኸኛል"
"ምኔን ወደድሽው ግን?"
"አለ አይደል ሁሉ ነገርህ ደስ ይላል"
እንግዲህ መዋደዳቸውን የተገላለፁት ከተገናኙ አራት ሰዓት ሳይሞላቸው ነው። በስልክ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ላይ ማውራት የጀመሩ ንጋት አስራአንድ ሰዓት ድረስ አላቋረጡም። እንቅልፍ የለ ፣ ካርዱ አያልቅ ፣ የባጡን የቆጡን እያወረዱ ሲነጋገሩ ሰዓቱ ነጎደ። ሁለቱም ስለደካከሙ ስሜት ባለዘባቸው ቃላት ተሰነባብተው ስልኩ ተዘጋ። ለዘጠኝ ሰዓታት ያለማቋረጥ ስልክ ማውራት ምናልባት እብደት ሊመስል ይችላል። በሰዓቱ እነርሱ ግን አንድ ሰዓት ታክልም ያወሩ አልመሰላቸውም።
.
የሀያት አባት በጣም ሀይለኛ ናቸው። ሀያት ውጪ ማምሸት የምትፈራበት ዋናው ምክንያትም የአባቷን ቁጣ ፍራቻ ነው።
ሀያት ከእንቅልፏ ስትባንን ፀሀይ ትንሽ ወደ ምዕራብ ተዘንብላ ነበር። እኩለ ቀን አልፎ ስምንት ሰዓት ሆኗል። ስልኳን ስትመለከት ሁለት ሚስድኮል አላት። ኢስማኢል ነበር። ደወለችለት።
"ሀሎ ኢስሚ"
"የኔ ፍቅር ተነሳሽ?"
"አዎ አሁን ተነሳሁ"
"እኔ አሁን ስራ ገብቻለሁ። በቃ ማታ እንገናኛለን።"
ሰፈሯ መጥቶ ሊያገኛት ተስማሙ። ኢስማኢል የአባቱ ድርጅት ውስጥ ነው የሚሰራው። ለቤተሰቡ ደግሞ የመጀመሪያ ልጅ ነው። ሀያት  ፈገግታው አይኗ ላይ ውል እያለባት ፍዝዝ ትላለች። በሀያ አራት ሰዓት ውስጥ ብዙ ነገሯ ቅይርይር ብሏል። አስራ ሁለት ሰዓት ገደማ ሲደርስ ኢስማኢል ሰፈር መጥቶ አገኛት። ትንሽ አውርተው በብዛት ተሳስመው ተለያዩ።
ወደ ቤት ስትመለስ ልቧ የሚሰማውን የፍቅር ስሜት ወረቀት ላይ ልትዘረግፈው ግጥም መፃፍ ጀመረች። ብዙ ሰዎች የፍቅር ስሜት ሲሰማቸው አሊያም ልባቸው ሲሰበር ግጥም መፃፍ ይቀናቸዋል። ግጥሙን ፅፋ ስትጨርስ የወረቀቱ ዙሪያ ላይ በቀይ እስክሪፕቶ ትናንሽ ልብ ቅርጾች ሳለች። ግጥሙን ለራሷ ጮክ ብላ አነበበችው።
"ለትንግርት የሳለህ ፣ ወንድነት ነህ ለኔ፣
አንተ በቅተኸኛል ፣ ሌላ ወንድ ለምኔ?
ንገስ ይገባሀል ፣ ዙፋንህ ነው ልቤ፣
ያሻህን እዘዘኝ ፣ አጎነብሳለሁ ከፊትህ ቀርቤ።
የኔ ህልም አንተ ነህ ፣ ምርኮህ መሆን ክብሬ፣
ያሳየኝ ነገዬን ፣ በፈካ ጨረቃ ፣ ካንተው ተሞሽሬ።
ወንድነት ነህ አንተ፣ ሚዛን የለም ሌላ፣
ተፈጥሮ ያላቀችህ ፣ ትለካለህ እንጂ አትልለካም ብላ።"
ግጥሙን አንብባ ስትጨርስ ወረቀቱን ወደ ደረቷ ወስዳ እቅፍ አደረገችው።
.
ዛሬ ሰኞ ነው። ሀዩ የትምህርት ቤቷ ግቢ ውስጥ ከቤቲ እና ሳሚያ ከምትባል ጓደኛዋ ጋር ተቀምጠው ያወራሉ። ሀያት ከኢስማኢል ጋር የደረሱበትን ሁኔታ በተመለከተ አጠር ያለ ሪፖርት አቀረበች። ተደውሎ ወደ መማሪያ ክፍል ከገቡ በኋላ ሀያት መምህሩ የሚያስተምረውን ማዳመጥ ትታ ስለ ኢስማኢል ታስባለች። ፈገግታው እና ወንዳወንድነቱ አይኗ ላይ ድቅን ይላል።
ከከሰዓት ወደ ቤት ለመሄድ ከትምህርት ቤቷ ግቢ ስትወጣ ኢስማኢል የትምህርት ቤታቸው በር ፊትለፊት መኪናውን አቁሞ እየጠበቃት ነበር። ትናንት የተገናኙ አይመስሉም። አመት እንደተነፋፈቁ ተቃቅፈው ሰላም ተባባሉ። መኪናው ውስጥ ገብታ ቦርሳዋን ኋላ ወንበር ላይ አስቀመጠች። ኢስማኢል ወደ ሳር ቤት መኪናውን ነዳው። መኪናው ውስጥ የጥላሁን ገሰሰ ዘፈን ተከፍቷል። ኢስማኢል ፊቱን ወደ ሀያት አዙሮ ከጥላሁን እኩል አብሮ እየጮኸ ያንጎራጉርላት ጀመረ።
"ፍቅርሽ ነው የጎዳኝ ፣ ፍቅርሽ ነው የጎዳኝ ፣ ፍቅርሽ ነው የጎዳኝ!
በልቼ እንዳልበላሁ ፣ ጠጥቼ እንዳልጠጣሁ ፣
ያረገኝ ፍቅርሽ ነው ፣ መች አጣሁ መች አጣሁ።
ከሰው ተራ አውጥቶ ያረገኝ ብቸኛ ፣ አውቃለሁ ፍቅርሽ ነው ፣ ይሄ መዘዘኛ ፣ ይሄ መዘዘኛ።
ነጭናጫ ያረገኝ ፣ ተቆጪ በቶሎ፣
ያው ያንቺው ፍቅር ነው ፣ ሌላ ማን ተብሎ ፣ሌላ ማን ተብሎ?" እያለ አይን አይኗን እያየ እያንጎራጎረላት በየመሀሉ እጇን ጭምቅ አድርጎ እየያዛት ሳር ቤት ደረሱ። ከሩሚ በርገር በር ላይ መኪናቸውን አቁመው ወደ ውስጥ ዘለቁ። ሀዩ አይኑ ላይ ፍዝዝ እንዳለች እሱም ከእቅፉ ሸጉጧት ከከንፈራቸው ፉት እየተባባሉ ያዘዙትን በርገር ይጠብቃሉ። ዛሬ ሀያት እና ኢስማኢል ከተዋወቁ ሶስተኛ ቀናቸው ነው። በመካከላቸው መተፋፈር የለም። በፍፁም ሶስት ቀን ብቻ ያሳለፉ ጥንዶች አይመስሉም። ለእነርሱ ቀናት በሙሉ መፋቀሪያ ፣ ምሽት ሁሉ መነፋፈቂያ ሆኗል። ተመቻችተዋል።
.
ኢስማኢል ሳምንቱን ሙሉ ሀያት ከትምህርት ስትወጣ እየጠበቀ አጫውቶ ወደ ቤቷ ይሸኛታል። ቀናት ቆጥረው የተገናኙበትን ሳምንት አብረው በመዋል ሊያሳልፉት ተቃጠሩ። ገና በጠዋቱ ሊገናኙ ፣ ቀናቸውን ሊሰጣጡ ተስማሙ።
ሀያት ቤተሰቦቿን ጓደኞቿ ጋር እንደምትውል ነግራ ማሳመን ነበረባት። እናቷ የሚወዷትን ልጃቸውን "መልካም ቀን" ብለው ስመው ተሰናበቷት። ከጓደኞቿ ጋር ትጫወት ብለው ፣ ስመው ሸኟት።  እርሳቸው ልጃቸው ከወንድ ጋር ለመዋል ብላ ትዋሸኛለች ብለው አያስቡም። ለሳቸው ልጃቸው ጨዋ ናት። ደግሞ በዛ ላይ የአባቷ ቁጣም በደንብ እንደገራት ያስባሉ። ግን ልጅ እናቷ እንዳሰቡት ከቤቲ እና ከሳሚያ ጋር ለመዋል አልነበረም የወጣችው። ይልቁንስ ወድጄዋለሁ ካለችው ሰው ጋር ጊዜዋን ልታሳልፍ ነው።
.
ኢስማኢል መኪናውን እያሽከረከረ ወደ ሱሉልታ ሄዱ። ሱሉልታ ያያ ቪሌጅ ሲደርሱ የምሳ ሰዓት ደርሶ ነበር። መኪናቸውን የመናፈሻው መኪና ማቆሚያ ውስጥ አቁመው ወደ ውስጥ ገቡ። ቦታው በጣም ውብ ነው። መናፈሻው ውስጥ ያለ የሳር ቤት ውስጥ ተቀመጡና ምሳቸውን በሉ። ከዚያም መሟዘዝ ጀመሩ። ልጅ ልጅ መሆን። መጃጃል። ፍቅር የሚባለው ስሜት ትንሽ ከምክንያታዊነት አውጥቶ ለደቂቃዎች አነስተኛ እብደት ውስጥ ይከታል መሰል። ምሳ ከበሉበት የሳር ጎጆ ወጥተው ሳሩ ላይ ተቀመጡ። ቦታው ደስ የሚል አየር አለው። ኢስማኢል ሁለት እግሩን ወደ ፊትለፊቱ ዘርግቶ ተቀመጠ። ሀዩ ከኢስማኢል እግሮች መካከል እግሯን እሱ በዘረጋበት አቅጣጫ ዘርግታ፤ ወገቧን ደረቱ ላይ አስደግፋ ተቀመጠች። አንገቷን ወደ ኋላ አስተኝታ አይን አይኑን ታየዋለች። ሳማት ፣ በደንብ ሳማት። እግሮቿን ሰብስባ ወደ ደረቱ በደንብ ተጠጋች። አንገቱን ይዛ ትስመዋለች። በዚህ ሰዓት ምድር ላይ ከነሱ ወዲያ ሰው ያለም አይመስላቸውም። ሲሳሳሙ ፣ ሲላላሱ ፣ ከምክንያታዊነት አለም ወጡ። ኢስማኢል እየሳማት በስሜት ሳግ የታፈነ ንግግር ያሰማል።
"እንተኛ? እ? ልሞትብሽ እኮ ነው። እ ሀዩዬ? ኣህ ሀዩ ሞትኩ እኮ፣ ቆንጂት እንተኛ የኔ ማር"
ሀያት ያለችበት የስሜት ንዳድ ውስጥ ሆና የስሜት ሲቃው ያስረገዘውን ንግግሩን ታደምጣለች። ከዚህ በፊት ከወንድ ጋር ተኝታ አታውቅም። በፍፁም። ጥያቄውን ችላ ልትለው ሞከረች። ኢስማኢል ግን ከልመና የሚበገር አልሆነም።
"የኔ ውድ ትወጂኝ የለ? ማሬ ልሞትብሽ ነው እኮ ፣ እሺ በይኝ እንተኛ"....

ይቀጥላል....
🌹🌹🌹🌹❤️የተሳቀ እንባ❤️🌹🌹🌹🌹
         ክፍል ሁለት
.
ሀያት መኝታ ክፍሏ ተቀምጣ ስልኳን እያየች በማመንታት ስሜት ውስጥ ትዋልላለች። ደፈረችና ደወለችለት።
"ሄሎ ኢስማኢል"
"ወዬ ማር"
"ቤት ደረስክ?"
"አልደረስኩም ፣ እየነዳሁ ነው ቤት ስገባ እደውልልሻለሁ"
"እሺ ችግር የለውም"
ሀያት ልቧ ኢስማኢልን አምልኮታል። ለመጀመሪያ ጊዜ ሳመችው ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ደወለችለት። መውደዷን የሴትነት ሀፍረቷ እንዲከልልላት አልፈቀደችለትም።
ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ሞልቶ ጥቂት ደቂቃዎች እንደተቆጠሩ ኢስማኢል ደወለ። ሀዩ ህፃኗን ወደ ሳሎን ወስዳ ለእናቷ ካስረከበች በኋላ መኝታ ክፍሏን ቆልፋ ስልኩን አነሳችው። 
"ሀዩዬ ወድጄሻለሁ"
"እኔም ደስ ብለኸኛል"
"ምኔን ወደድሽው ግን?"
"አለ አይደል ሁሉ ነገርህ ደስ ይላል"
እንግዲህ መዋደዳቸውን የተገላለፁት ከተገናኙ አራት ሰዓት ሳይሞላቸው ነው። በስልክ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ላይ ማውራት የጀመሩ ንጋት አስራአንድ ሰዓት ድረስ አላቋረጡም። እንቅልፍ የለ ፣ ካርዱ አያልቅ ፣ የባጡን የቆጡን እያወረዱ ሲነጋገሩ ሰዓቱ ነጎደ። ሁለቱም ስለደካከሙ ስሜት ባለዘባቸው ቃላት ተሰነባብተው ስልኩ ተዘጋ። ለዘጠኝ ሰዓታት ያለማቋረጥ ስልክ ማውራት ምናልባት እብደት ሊመስል ይችላል። በሰዓቱ እነርሱ ግን አንድ ሰዓት ታክልም ያወሩ አልመሰላቸውም።
.
የሀያት አባት በጣም ሀይለኛ ናቸው። ሀያት ውጪ ማምሸት የምትፈራበት ዋናው ምክንያትም የአባቷን ቁጣ ፍራቻ ነው።
ሀያት ከእንቅልፏ ስትባንን ፀሀይ ትንሽ ወደ ምዕራብ ተዘንብላ ነበር። እኩለ ቀን አልፎ ስምንት ሰዓት ሆኗል። ስልኳን ስትመለከት ሁለት ሚስድኮል አላት። ኢስማኢል ነበር። ደወለችለት።
"ሀሎ ኢስሚ"
"የኔ ፍቅር ተነሳሽ?"
"አዎ አሁን ተነሳሁ"
"እኔ አሁን ስራ ገብቻለሁ። በቃ ማታ እንገናኛለን።"
ሰፈሯ መጥቶ ሊያገኛት ተስማሙ። ኢስማኢል የአባቱ ድርጅት ውስጥ ነው የሚሰራው። ለቤተሰቡ ደግሞ የመጀመሪያ ልጅ ነው። ሀያት  ፈገግታው አይኗ ላይ ውል እያለባት ፍዝዝ ትላለች። በሀያ አራት ሰዓት ውስጥ ብዙ ነገሯ ቅይርይር ብሏል። አስራ ሁለት ሰዓት ገደማ ሲደርስ ኢስማኢል ሰፈር መጥቶ አገኛት። ትንሽ አውርተው በብዛት ተሳስመው ተለያዩ።
ወደ ቤት ስትመለስ ልቧ የሚሰማውን የፍቅር ስሜት ወረቀት ላይ ልትዘረግፈው ግጥም መፃፍ ጀመረች። ብዙ ሰዎች የፍቅር ስሜት ሲሰማቸው አሊያም ልባቸው ሲሰበር ግጥም መፃፍ ይቀናቸዋል። ግጥሙን ፅፋ ስትጨርስ የወረቀቱ ዙሪያ ላይ በቀይ እስክሪፕቶ ትናንሽ ልብ ቅርጾች ሳለች። ግጥሙን ለራሷ ጮክ ብላ አነበበችው።
"ለትንግርት የሳለህ ፣ ወንድነት ነህ ለኔ፣
አንተ በቅተኸኛል ፣ ሌላ ወንድ ለምኔ?
ንገስ ይገባሀል ፣ ዙፋንህ ነው ልቤ፣
ያሻህን እዘዘኝ ፣ አጎነብሳለሁ ከፊትህ ቀርቤ።
የኔ ህልም አንተ ነህ ፣ ምርኮህ መሆን ክብሬ፣
ያሳየኝ ነገዬን ፣ በፈካ ጨረቃ ፣ ካንተው ተሞሽሬ።
ወንድነት ነህ አንተ፣ ሚዛን የለም ሌላ፣
ተፈጥሮ ያላቀችህ ፣ ትለካለህ እንጂ አትልለካም ብላ።"
ግጥሙን አንብባ ስትጨርስ ወረቀቱን ወደ ደረቷ ወስዳ እቅፍ አደረገችው።
.
ዛሬ ሰኞ ነው። ሀዩ የትምህርት ቤቷ ግቢ ውስጥ ከቤቲ እና ሳሚያ ከምትባል ጓደኛዋ ጋር ተቀምጠው ያወራሉ። ሀያት ከኢስማኢል ጋር የደረሱበትን ሁኔታ በተመለከተ አጠር ያለ ሪፖርት አቀረበች። ተደውሎ ወደ መማሪያ ክፍል ከገቡ በኋላ ሀያት መምህሩ የሚያስተምረውን ማዳመጥ ትታ ስለ ኢስማኢል ታስባለች። ፈገግታው እና ወንዳወንድነቱ አይኗ ላይ ድቅን ይላል።
ከከሰዓት ወደ ቤት ለመሄድ ከትምህርት ቤቷ ግቢ ስትወጣ ኢስማኢል የትምህርት ቤታቸው በር ፊትለፊት መኪናውን አቁሞ እየጠበቃት ነበር። ትናንት የተገናኙ አይመስሉም። አመት እንደተነፋፈቁ ተቃቅፈው ሰላም ተባባሉ። መኪናው ውስጥ ገብታ ቦርሳዋን ኋላ ወንበር ላይ አስቀመጠች። ኢስማኢል ወደ ሳር ቤት መኪናውን ነዳው። መኪናው ውስጥ የጥላሁን ገሰሰ ዘፈን ተከፍቷል። ኢስማኢል ፊቱን ወደ ሀያት አዙሮ ከጥላሁን እኩል አብሮ እየጮኸ ያንጎራጉርላት ጀመረ።
"ፍቅርሽ ነው የጎዳኝ ፣ ፍቅርሽ ነው የጎዳኝ ፣ ፍቅርሽ ነው የጎዳኝ!
በልቼ እንዳልበላሁ ፣ ጠጥቼ እንዳልጠጣሁ ፣
ያረገኝ ፍቅርሽ ነው ፣ መች አጣሁ መች አጣሁ።
ከሰው ተራ አውጥቶ ያረገኝ ብቸኛ ፣ አውቃለሁ ፍቅርሽ ነው ፣ ይሄ መዘዘኛ ፣ ይሄ መዘዘኛ።
ነጭናጫ ያረገኝ ፣ ተቆጪ በቶሎ፣
ያው ያንቺው ፍቅር ነው ፣ ሌላ ማን ተብሎ ፣ሌላ ማን ተብሎ?" እያለ አይን አይኗን እያየ እያንጎራጎረላት በየመሀሉ እጇን ጭምቅ አድርጎ እየያዛት ሳር ቤት ደረሱ። ከሩሚ በርገር በር ላይ መኪናቸውን አቁመው ወደ ውስጥ ዘለቁ። ሀዩ አይኑ ላይ ፍዝዝ እንዳለች እሱም ከእቅፉ ሸጉጧት ከከንፈራቸው ፉት እየተባባሉ ያዘዙትን በርገር ይጠብቃሉ። ዛሬ ሀያት እና ኢስማኢል ከተዋወቁ ሶስተኛ ቀናቸው ነው። በመካከላቸው መተፋፈር የለም። በፍፁም ሶስት ቀን ብቻ ያሳለፉ ጥንዶች አይመስሉም። ለእነርሱ ቀናት በሙሉ መፋቀሪያ ፣ ምሽት ሁሉ መነፋፈቂያ ሆኗል። ተመቻችተዋል።
.
ኢስማኢል ሳምንቱን ሙሉ ሀያት ከትምህርት ስትወጣ እየጠበቀ አጫውቶ ወደ ቤቷ ይሸኛታል። ቀናት ቆጥረው የተገናኙበትን ሳምንት አብረው በመዋል ሊያሳልፉት ተቃጠሩ። ገና በጠዋቱ ሊገናኙ ፣ ቀናቸውን ሊሰጣጡ ተስማሙ።
ሀያት ቤተሰቦቿን ጓደኞቿ ጋር እንደምትውል ነግራ ማሳመን ነበረባት። እናቷ የሚወዷትን ልጃቸውን "መልካም ቀን" ብለው ስመው ተሰናበቷት። ከጓደኞቿ ጋር ትጫወት ብለው ፣ ስመው ሸኟት።  እርሳቸው ልጃቸው ከወንድ ጋር ለመዋል ብላ ትዋሸኛለች ብለው አያስቡም። ለሳቸው ልጃቸው ጨዋ ናት። ደግሞ በዛ ላይ የአባቷ ቁጣም በደንብ እንደገራት ያስባሉ። ግን ልጅ እናቷ እንዳሰቡት ከቤቲ እና ከሳሚያ ጋር ለመዋል አልነበረም የወጣችው። ይልቁንስ ወድጄዋለሁ ካለችው ሰው ጋር ጊዜዋን ልታሳልፍ ነው።
.
ኢስማኢል መኪናውን እያሽከረከረ ወደ ሱሉልታ ሄዱ። ሱሉልታ ያያ ቪሌጅ ሲደርሱ የምሳ ሰዓት ደርሶ ነበር። መኪናቸውን የመናፈሻው መኪና ማቆሚያ ውስጥ አቁመው ወደ ውስጥ ገቡ። ቦታው በጣም ውብ ነው። መናፈሻው ውስጥ ያለ የሳር ቤት ውስጥ ተቀመጡና ምሳቸውን በሉ። ከዚያም መሟዘዝ ጀመሩ። ልጅ ልጅ መሆን። መጃጃል። ፍቅር የሚባለው ስሜት ትንሽ ከምክንያታዊነት አውጥቶ ለደቂቃዎች አነስተኛ እብደት ውስጥ ይከታል መሰል። ምሳ ከበሉበት የሳር ጎጆ ወጥተው ሳሩ ላይ ተቀመጡ። ቦታው ደስ የሚል አየር አለው። ኢስማኢል ሁለት እግሩን ወደ ፊትለፊቱ ዘርግቶ ተቀመጠ። ሀዩ ከኢስማኢል እግሮች መካከል እግሯን እሱ በዘረጋበት አቅጣጫ ዘርግታ፤ ወገቧን ደረቱ ላይ አስደግፋ ተቀመጠች። አንገቷን ወደ ኋላ አስተኝታ አይን አይኑን ታየዋለች። ሳማት ፣ በደንብ ሳማት። እግሮቿን ሰብስባ ወደ ደረቱ በደንብ ተጠጋች። አንገቱን ይዛ ትስመዋለች። በዚህ ሰዓት ምድር ላይ ከነሱ ወዲያ ሰው ያለም አይመስላቸውም። ሲሳሳሙ ፣ ሲላላሱ ፣ ከምክንያታዊነት አለም ወጡ። ኢስማኢል እየሳማት በስሜት ሳግ የታፈነ ንግግር ያሰማል።
"እንተኛ? እ? ልሞትብሽ እኮ ነው። እ ሀዩዬ? ኣህ ሀዩ ሞትኩ እኮ፣ ቆንጂት እንተኛ የኔ ማር"
ሀያት ያለችበት የስሜት ንዳድ ውስጥ ሆና የስሜት ሲቃው ያስረገዘውን ንግግሩን ታደምጣለች። ከዚህ በፊት ከወንድ ጋር ተኝታ አታውቅም። በፍፁም። ጥያቄውን ችላ ልትለው ሞከረች። ኢስማኢል ግን ከልመና የሚበገር አልሆነም።
"የኔ ውድ ትወጂኝ የለ? ማሬ ልሞትብሽ ነው እኮ ፣ እሺ በይኝ እንተኛ"....

ይቀጥላል....
🥀ከ ክፍል ሁለት የቀጠለ

ሀያት በእንቢታዋ ለመፅናት ብትሞክርም ኢስማኢልን ማሸነፍ አልቻለችም። ገና ከመጀመሪያ እይታዋ ጀምራ ራሷን አሳልፋ ሰጥታዋለች። ዛሬ ምላሷ እንቢ ቢለውም ልቧ ሊያስከፋው አልፈለገም። "ደሞ ብደብረውስ?" የሚል ስጋት ተፈታትኗታል።
አንገቱ ስር እንደተወሸቀች "እሺ በቃ" አለችው አንገቷ ስር የሚያላዝነውን ኢስማኢልን። እንዲያ ያለ ኩሩ ወንድ እንዲህ አንገቷ ስር ሲያላዝን በጣም ይቀፋል። እሱ ራሱ ተቀርጾ ቢያየው የሚቀፈው ይመስለኛል። ግን ስሜት የጥም እንጂ የምክንያታዊነት ጉዳይ አይደለም። ትንሽ ከስሜታቸው ቀዝቀዝ ለማለት ሞከሩና ተነስተው መኪናቸውን ወዳቆሙበት ቦታ ሄዱ። መኪናው ውስጥ ሲገቡ ኢስማኢል ከመኪናው ቴፕ የሚካኤል በላይነህን ሙዚቃ ከፈተ። ከዘፋኙ እኩል እየጮኸ ፣ እጆቿን በእጁ እየጨመቀ ከያያ ቪሌጅ አቅራቢያ ያለ አንድ ሆቴል በር ላይ ቆመ። ሆቴሉ ባለ አራት ኮከብ ሆቴል ነው። ወግ ላለው ጫጉላ መልካም ቦታ ይመስላል። ኢስማኢል ቀድሟት ከመኪናው ወርዶ ወደ ሆቴሉ የእንግዳ መቀበያ ገባ። ተከተለችው። የክፍሉን ቁልፍ እጁ ላይ እንደያዘ ወደ ፎቅ ወጣ። ሀያት እየተከተለችው ነው። ልቧ በፍርሀት ይርዳል። "አሁን አባዬ ቢሰማ ምን ይል ይሆን?" እያለች ታስባለች። ግን ከአባቷ ንዴት ይልቅ የኢስማኢል ኩርፊያ አስግቷታል። ተከተለችው። የክፍሉን በር ከፍቶ እንድትገባ አስቀደማት። ገባች።  ክፍሉ በጣም ያምራል። አልጋው በነጭ አልጋ ልብስ ተሸፍኗል። ከአልጋው አለፍ ብሎ ሁለት ሶፋ ወንበሮች አሉ። የክፍሉ መስኮት የውጪውን ገፅታ በደንብ ያስቃኛል።
.
ኢስማኢል የሀያትን እጅ ጥብቅ አድርጎ ይዞ ወደ ደረቱ አስጠጋት። ከአልጋው እግርጌ አጠገብ ቆመዋል። ከንፈሩን ወደ ከንፈሯ አስጠግቶ ሳማት ፣ ሳማት ፣ ነከሳት።
ብዙውን ጊዜ የህይወታችን መስመር የሚቀየርበትን ጊዜ አናውቅም። ማፍቀር ተብሎ የሚዘመርለትን ጉዳይ አብጠርጥረን በምክንያታዊ አይን መመልከት ይሳነናል።  ሀያት ከአባቷ ቁጥጥር እና ከእናቷ ስስት አንፃር ሲታይ እንደዚህ ከወንድ ጋር  መኝታ ቤት ውስጥ ትቆማለች ተብሎ አይታሰብ ይሆናል። ግን እንቢ ማለት በቁጥጥር እና በመንሰፍሰፍ ብቻ ሊመጣ የሚችል ጥበብ አይደለም። ግልፅነት የተሞላበት ውይይት ያስፈልገዋል። ጠንካራ የራስ መተማመን መገንባትን ይጠይቃል።
.
ሀያት እና ኢስማኢል ከአልጋው እግርጌ ቆመው ይሳሳማሉ። ይነካከሳሉ። አሁን ኢስማኢል የሀያትን ልብስ ማውለቅ ጀምሯል።
.
ይቀጥላል...
የተሳቀ እንባ


ክፍል ሶስት
.
ኢስማኢል እጁን ወደ ሀያት ቀሚስ ሰዶ ከሰውነቷ አወረደው። የክፍሉ መብራት ቦግ ብሎ በርቷል። የአምፖሉ ማቀፊያ ከሆቴሉ ግርማ ሞገስ ጋር የገጠመ ነው። ፀጥ ያለው መኝታ ክፍሉ ከፍ ያለ የትንፋሽ መቆራረጥ ድምፅ ማስደመጥ ጀምሯል። አሁን ደግሞ እንደጩኸት ያለ የስሜት ሲቃ ይሰማል። ኢስማኢል በሚቆራረጥ ድምፅ "እወ ድሻ ለ ሁ፣ እ ወድ ሻ ለሁ" እያለ ከእግሮቿ መካከል ወደ ፊት ወደ ኋላ ይመላለሳል። የሀያት ጩኸት እያየለ ነው።  ከአልጋው በስተጀርባዋ ተዘርራ የክፍሉን ጣሪያ እያየች እጆቿን ለመታገል በሚመስል አይነት ከእጆቹ ጋር ታፋትጋለች። ያመልጣት ይመስል እግሮቿን አጠላልፋቸዋለች። ብዙ ጩኸት ፣ ብዙ ሲቃ ፣ ብዙ "እ ወድ ሻለ ሁ" ተደመጠ። ነጩ አልጋልብስ በተቀላ ክብር ደም በሰበሰ። ክብሯ ከኢስማኢል ጭን መሀል ተሰዋ።  ድንግልናዋን ፣ እሷነቷን ካወቀችው ገና ሳምንት እንኳ በቅጡ ላልሞላው ለኢስማኢል አስረከበችው። የስሜት ትንቅንቁ ሲያባራ ተፋፈሩ። ኢስማኢል በጣም ደንግጧል። በፍፁም ድንግል አልመሰለችውም ነበር። ዝም እንደተባባሉ ፣ እንደተፋፈሩ ተያይዘው ከሆቴሉ ወጡ። መኪናዋ ከሱሉልታ እስከ አዲስአበባዋ ተክለሀይማኖት ድረስ ስትዘልቅ ምንም አልተነጋገሩም። ምንም። የመኪናው ቴፕ ሁለቱም የሚወዱትን የጥላሁንን "ፍቅርሽ ነው የጎዳኝ" የሚለውን ሙዚቃ ታንቆረቁራለች።  እንደተፋፈሩ ፣ ዝም እንደተባባሉ ተክለሀይማኖት ደረሱ። ቻው ሳትለው ከመኪናው ወረደች። ከራሷ ጋር ትልቅ ጭቅጭቅ ውስጥ ገብታለች። "እንዴት ሳምንት ለማውቀው ሰው ክብሬን ሰዋሁት?" "አባባ ቢሰማ ምን ይል ይሆን?" እያለች መልሳቸው ግራ የሚያጋቧትን ጥያቄዎች ራሷን ትጠይቃለች።
.
ቤት እንደገባች ከማንም ጋር ሳትነጋገር ወደ መኝታ ክፍሏ ገብታ በሩን ቆለፈችው። ልቧ መረጋጋት ተስኖታል። በጣም ፈርታለች። ኢስማኢል ደወለ ፣ አይታ ተወችው። እየደጋገመ ይደውላል ፣ አታነሳም። መደጋገሙ ሲበረታ ስልኩን አነሳችው። ኢስማኢል የቅድሙ ፍርሀቱ ሳይለቀው በለዘቡ ቃላት ያወራታል።
"የኔ ቆንጆ ፣ መቼም አልተውሽም እሺ ፣ መቼም"
"እሺ"
"ከማንም በላይ እወድሻለሁ እሺ ፣ የኔ ፍቅር"
"እሺ"
እሺ ከማለት በዘለለ ምንም አታወራም። የሆነው ነገር ሁሉ ግራ አጋብቷታል። ወንዳወንድነቱን የምታመልክለት ኢስማኢል እግሮቿ መሀከል ወደ ፊት እና ወደ ኋላ እየተመላለሰ ሲያላዝን ቅፍፍ ብሏታል። እንደዛ በእርጋታ የምታወራው እሷ ፣ በጀርባዋ ተንጋላ የሚደብር አይነት ጩኸት ስትጮህ ለራሷም ቀፏታል። በዚሁ ስሜት ውስጥ እንዳለች የአልጋው ኮመዲኖ ላይ የተቀመጠውን ማስታወሻ ደብተር አንስታ ባለ ሁለት ስንኝ ግጥም ሞነጨረች። ዜማውን ለመገምገም ጮክ ብላ አነበበችው።
"የምትሞቺለትን ፣ ዛሬ ቀመስኩት፣
ከፊሉ ደስታ ነው ፣ አብላጫው ውርደት።" 
የተሰማትን ስሜት ከወረቀት ጋር አዋደደችው። ይህን የዛሬውን ታሪኳን ማንም ባይሰማ ደስ ይላታል። የመኝታ ክፍሏ በር ተሞነጨረ። ታናሽ እህቷ ገና ለወሬ ባልጠናው አንደበቷ "አዩ ፣ አዩ" እያለች ከተዘጋው የመኝታ ቤቷ በር ጋ ትታገላለች። ሀያት ከአልጋዋ ተነስታ በሩን ከፈተችና ከመሬቱ ላይ አንስታ አቅፋት ወደ ውስጥ አስገባቻት። አልጋው ላይ አስቀምጣ ጣቶቿን እያማታች ለማጫወት ሞከረች። አባቷ ወደ ክፍሏ መጡ። ሀያት በጣም ደነገጠች። "እዚህ ተቀምጠሽ ነው እንዴ የምትፈለጊው? በይ ልጅቷ ሳትሸና አልቀረችም ፓምፐርሱን ቀይሪላት። ደሞ ልጅቷ የት ሄደች?"
"አሁን ወጣች ፣ የት እንደሄደች አላወቅኩም።"
ሀያት በድንጋጤ ሆና መለሰች እንጂ ሰራተኛቸው ወደ ቤት ስትገባም አልነበረችም። አባቷ ፊቷን አይቶ የዋለችበትን ሁኔታ የሚረዳ መስሏት ተቁነጠነጠች። አባቷ ግን ወዲያው ወደ ሳሎን ተመለሱ።
.
የተፈጠረውን ነገር ለማን መተንፈስ እንደምትችል ታውጠነጥናለች። ለቤቲ ልትነግራት ስልኳን አነሳችና ቅፍፍ ሲላት መልሳ አስቀመጠችው። ስለ ኢስማኢል አሰበች። የሷ እንደሆነ ስታስብ በጣም ደስ አላት። ወደ ፌስቡክ አካውንቷ ገባችና የፌስቡክ ስሟ በቅንፍ ውስጥ "እስሚዝ ህይወቴ" የሚል ፅሁፍ እንዲጨምር አደረገች። ፕሮፋይል ፒክቸሯን በኢስማኢል ፎቶ ቀየረችው። ማንም ምንም ቢል ግድ አይሰጣትም። ቤተሰቦቿ ከማህበራዊ ሚዲያ የራቁ ስለሆኑ አይመለከቱትም። ውዷ መሆኑን አወጀች። ፈገግታው እየናፈቃት ፣ ሁሌም የሷ ብቻ እንዲሆን ተመኘች።
.
ሀያት ከገባችበት የመፍዘዝ አለም ካገገመች በኋላ ኢስማኢልን ደውላ አወራችው። ኢስማኢል በጣም ደንግጦ ስለነበር እየደጋገመ ላይለያት ይምላል።
በነጋታው ቁርስ ይዞላት ወደ ሰፈራቸው መጣ። ቁርስ እሱ መኪና ውስጥ አብረው በሉ። አዲስ የተጋቡ ጥንዶች ይመስላሉ። ሲጎራረሱ ፣ ሲጎሻሸሙ ፣ አይን ለአይን በፍቅር ሲተያዩ ፍቅራቸውን ቤተሰብ ተቀብሎ ያወጀው ይመስላል። ግን አይደለም። የማህበረሰቡ እሴት በሚፈልገው መልኩ በጋብቻ አልተሳሰሩም።
.
ጊዜው እየገፋ ሀዩ እና ኢስማኢል ከተዋወቁ ሶስተኛ ሳምንታቸው ደረሰ። በዚህ መካከል የሱሉልታውን ትንቅንቅ አንዴ ሀዋሳ ሀይሌ ሪዞርት ውስጥ ደግመውታል። ዛሬ ሀዩ ለየት ያለ ስሜት ተሰምቷታል። እንደማቅለሽለሽ ያለ ስሜት ሲፈታተናት ከትምህርት ቤት ቀርታ ወደ ክሊኒክ ሄደች። ለሀኪሟ ስሜቷን ካስረዳቻት በኋላ ምርመራ ተደረገላት። ሀያት በነዛ ትንቅንቆች ምክንያት አርግዛ ነበር።  ማመን በጣም ከበዳት። በዘርፉ ብዙም ልምድ ስለሌላት የወሊድ መቆጣጠሪያ መንገዶችን በአግባቡ አልተጠቀመችም ነበር። በጣም ፈርታለች። የተረገዘው ህፃን ገና ከሶስት ሳምንት አልዘለለም። ሀዩ ምን ማድረግ እንዳለባት በጣም ግራ ገብቷታል። ለኢስማኢል ደወለችለት።
"ወዬ ፍቅር"
"ውዴ ዛሬ ክሊኒክ ሄጄ ነበር"
"ምነው ቆንጂት አመመሽ እንዴ?"
"እንደዛ ነገር ነበር ግን ስመረመር"
"ስትመረመሪ ምን?"
"ስመረመርማ አርግዘሻል ተባልኩ"
ኢስማኢል በጣም ደነገጠ። በጣም። ከሰዓት በኋላ ለመገናኘት ተቀጣጠሩ። እናቷ ልጃቸው ከትምህርት መቅረቷ በጣም አሳስቧቸዋል። አመመኝ ስላለች የምትወደውን ምግብ ሰርተው ደስ ሊያሰኟት እየሞከሩ ነው። በመሀል ወደ መኝታ ቤቷ መጥተው ክሊኒክ ምን እንዳሏት ጠየቋት።
"ምን አሉሽ ሀዩዬ? መድሀኒት አዘዙ?"
"መድሀኒት አልሰጡኝም። ማስታገሻ ብለው መርፌ ወጉኝ።"
"በሽታው እንዲህ ነው ብለው አልነገሩሽም?"
"የጨጓራሽ ስሜት ነው ነው የሚሉት"
ሀያት ጨጓራዋን ሌላ ጊዜም ያማት ስለነበር ቆንጆ ማሳበቢያ ሆኗታል። መርፌ የሚባል አልተወጋችም። ግን መዋሸት ነበረባት። የተፈጠረውን እናቷ ቢያውቁ ሰው አይሆኑም። አባቷ ቢያውቁ ደግሞ እሳቸውም እሷም በህይወት አይኖሩም። 
.
ከከሰዓት በኋላ ከኢስማኢል ጋር ተገናኙ። ሀዩ በጣም ፈርታለች። ከመኪናው ቴፕ ዛሬም "ፍቅርሽ ነው የጎዳኝ" የሚለው የጥላሁን ሙዚቃ ይንቆረቆራል። መኪናውን ወደ ዶዲ ነዳው። ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ተገናኙበት ቦታ! ዶዲ ሲደርሱ በአውራጣቱ የቅንድቧን ፀጉር እያሻሸ አይኖቿ ውስጥ ቀልጦ ማውራት ጀመረ።
"ሀዩ ምንድነው የሚሻለን?"
ሀያት ዝም ብላ ታየዋለች። አብረው መኖር አይጀምሩ ነገር ገና ከአባቱ ድጋፍ ነፃ ሆኖ በራሱ አልቆመም። ግራ ግብት ብሎት ሲፈዝ እሷ መናገር ጀመረች።
"ኢስማኢል በቃ ላስወርደው!"
"ምን?"
"በቃ ላስወርደው ታዲያ ምን አማራጭ አለን?"
"ማስወረድማ በፍፁም አይታሰብም!"
"ማርገዜ ተሰምቶ ቤተሰቦቼ ከሚዋረዱ ሞቴን እመርጣለሁ። በፍፁም እንደዚህ ያለ ውርደት ውስጥ መግባት አልፈልግም።"
"ልጁን ማስወረድማ .
ይቀጥላል....
አንቺ አልቃሻ……ዛሬም ታለቅሻለሽ
ህይወት ከበደኝ🥺
ሰው መረረኝ😩
ብቸኛ ነኝ😣
ብለሽ ዛሬም ታለቅሻለሽ አይደል
እንዳይመስልሽ ግን ……ጠንካራ እኮ ነሽ አንቺ
የኔ ጀግና 💪
ስንት ነገር አልፈሽ ነው እዚ የደረሽው? አስታውሺ እስኪ ያሳለፍሻቸውን መጥፎ ጊዜያቶች ምን ያክል ዋጋ እንደከልሽላቸው …ግን ዛሬም ቆመሻል ……
ከ ክፍል ሶስት(3) የቀጠለ

ቃላቱ ምክንያታዊነት አጡበት። ልጁ ይወለድ ከተባለ ለሀያት እና ለቤተሰቦቿ ትልቅ ቅሌት ነው።ሳይፈልግ በሀሳቧ ተስማማ። በነጋታው በአዲስ አበባ ውስጥ የተረገዙ ህፃናትን በመግደል ታዋቂ ወደ ሆነ ሰማያዊ በነጭ ክሊኒክ ሄዱ። ዛሬ ያሉበትን ቦታ ሁለቱም እንቆምበታለን ብለው አስበው አያውቁም። ከሰዓታት በኋላ ህፃኑ ማህፀኗ ውስጥ በብረት እየተቆራረጠ እንዲወጣ ተደረገላት። አንድ ምንም ያላጠፋ ህፃን ፣ አንድም ሰውን ያልበደለ ታዳጊ ፤ ገና ወደ ምድር ሳይመጣ ከምድር ክፋት ያዘለ ብረት ወደ ተሸሸገሸት አለም ሾልኮ ሄዶ ቆራረጠው። አንድ የተከበረ ከሀጢአት የፀዳ ሰው ሞተ።
.
ከክሊኒኩ ወጥተው ወደ ቤቷ ሊያደርሳት መንገድ ጀመሩ። መኪናው የተበላሸ አስፓልት ጋር ደርሳ ገጭ ባለች ቁጥር ሀያት የሚያሳዝን የስቃይ ድምፅ ታሰማለች። መኪናው ገጭ ባለ ቁጥር ኢስማኢል ነብሱ ከስጋው ልትነጠል ትደርሳለች። እጆቿን ጭምቅ ያደርጋታል። አንዴ መኪናው ገጭ ሲል ሀያት በጣም አመማት ፣ የሚያሳዝን የስቃይ ድምፅ አሰማች። ኢስማኢል ከአይኑ እንባ ወረደ። ህመሟ አመመው። ወንድነቱ ተረታ፤ አለቀሰ።
.
ሀያት ሲቆይ ህመሙ እየቀነሰ ፣ እየቀነሰ ሄዶ ተሻላት። ልጇን እንዳስወረደች ስታስብ በጣም ትፀፀታለች። ኢስማኢል ሲያደርግላት የነበረው እንክብካቤ አቅሏን ነስቷታል። በጣም አሳዝኗታል። ሲያለቅስ የነበረውን ስሜት እያስታወሰች ፈገግ ትላለች። ኢስማኢልን እያሰበች አንድ ግጥም ሞነጨረች። ሁሌም እንደምታደርገው ለራሷ በሚሰማ ድምፅ አነበበችው።
"ይሁን ያልከው ሆኗል ፣ እሰዋለሁ ላንተ፣
ምንም እችላለሁ ፣ አንተን ካስደሰተ።
ተዪኝ ግን እንዳትል ፣ እንዴት እችላለሁ?
አሊያም ደስ እንዲልህ ፣ ኑሬ አልችልምና እሞትልሀለሁ።"
.
ሀያት እና ኢስማኢል የአፍላ እድሜ ፍቅቅሮሻቸውን ቀጠሉ። የሳምንቱ የመጨረሻውን ቀናት ማለትም ቅዳሜን አሊያም እሁድን ከከተማ ወጣ ይላሉ። አንዳንዴ እነዚያ ትንቅንቆች ይደገማሉ። ኢስማኢል የሚይዘው ብር ሲታይ ገና ሀያ ሶስት አመት ያልሞላው አይመስልም። የሷም ሰውነት ሲታይ ገና አስራ ስምንት አመት አልሞላትም ቢባል ማንም አያምንም። በጣም ትልቅ ይመስላሉ። ስለምንም ስለማንም ማሰብ አይፈልጉም። እነሱ ብቻ ፣ አዎ እነሱ ብቻ የምድር ጌጦች ናቸው። ለነሱ!
.
ይቀጥላል...
የተሳቀ እንባ

ክፍል አራት

የመጨረሻው ክፍል
.
ሀያት እና ኢስማኢል ከተገናኙ ሶስት ወራት ተቆጠሩ። ሀያት ከሱ ጋር ያሳለፈቻቸውን ጊዜያት በቅደም ተከተል ተናገሪ ብትባል ያለአንዳች መዛነፍ መተረክ የሚያስችል ቆንጆ የትዝታ መዝገብ አላት። እሱን ስታስብ ሁሌም ደስታ ትዝ ይላታል። ዛሬ በጠዋቱ ደወለችለት። የሳምንቱ የእረፍት ቀን ስለሆነ ዛሬም እንደሁሌው እንገናኛለን በሚል ተስፋ! ኢስማኢል ግን ዛሬ በፍፁም እንደማይመቸው ነገራት። በስራ ተወጥሯል በሚል ሀሳብ መልካም ቀን ተመኝታለት ስልኩን ዘጋችው። ማታውን ይደውላል ብላ ብትጠብቅም አልደወለም።
ሀያት ታናሽ እህቷን ስታጫውት ፣ ከእናቷ ጋር ማዕድቤት ጉድ ጉድ ስትል ነበር የዋለችው። አባቷ ወደ ቤት ሲገቡ ሳሎን ላይ የወደቀ አንድ ወረቀት አግኝተው ማንበብ ጀመሩ። የፈተና ወረቀት ነበር። ሀያት ህፃኗን ለማባበል አስይዛት የነበረ ነው። አምስት ከሀያ ያገኘችበት ፈተና ነበር። አባቷ በጣም ደነገጡ። ተቆጡ። ፈተናዋን ስራዬ ብለው አይተው ባያውቁም ዛሬ በድንገት ባዩት ውጤት ተበሳጩ። ከልጃቸው እንደዚህ ያለ ውጤት ጠብቀው አያውቁም ነበር።
.
ቤቲ እና ኤርሚያስ ያሳለፏቸውን የመመቻቸት ጊዜዎች ጨርሰው ላሽ ተባብለዋል። ቤቲ ሄኖክ የሚባል ተረኛ ፍቅረኛ ይዛለች። ትንሽ የተረጋጋ ማንነት የላትም። ኤርሚያስም አዲስ ሴት ጠብሷል። ሁሉም ነገር በቤቲ እና በኤርሚያስ ህይወት ውስጥ እቃቃ ነው። ዛሬ ተጀምሮ ነገ ይፈርሳል። ጊዜያዊ ጥምን ማርካት የሁለቱም የህይወት መስመር ነው። በእነርሱ ህይወት ውስጥ ሀይማኖት ፣ ባህል ፣ ስነ ምግባር የሚባሉ ነገሮች ብዙም ቦታ የላቸውም።
.
ቀናት እየገፉ ሄዱ። ኢስማኢል እንደ ድሮው ከሀያት ጋር አይገናኝም። እያለ እያለ ደግሞ ስልክ መደወልም አቆመ። ሀያት በጣም ተረብሻለች። ውዷን ምን እንደነካባት ግራ ገብቷታል። ስትደውል ያወራታል ፣ ወሬው ግን እንደሌላ ጊዜው ብዙም ጣዕም የለውም። ቀናት እየገፉ ሲመጡ ስልክ ስትደውልለት አለማንሳት ጀመረ። ትናንት አብረው ብዙ ነገሮችን አድርገዋል። ከሁሉም የሚከብደው ክብሯን አሳልፋ ሰጥታዋለች። በእርሱ ምክንያት ምንም የማያውቅ ህፃን አስወርዳለች። ሀያት ሁሉ ነገር ጨለመባት። እንባዋ ታረቃት። ሁሌ ማልቀስ ስራዋ ሆነ። ኢስማኢል ከድቶኛል ብላ ለማሰብ አትፈልግም። አንዳንዴ ብቻዋን ክፍሏ ውስጥ ትቆምና ከስልኳ ስክሪን ላይ ፎቶውን እያየች "ምን ነካብኝ የኔ ንጉስ? ምን ነካብኝ?" እያለች ተንሰቅስቃ ታለቅሳለች። የተፈጠረውን ነገር ለሳሚያ እና ቤቲ ነገረቻቸው። እነርሱ ግን ኮራ እንድትልበት ከመምከር በዘለለ ምንም ሊፈይዱላት አልቻሉም።
ልቧ ሊቆርጥለት አልቻለም። ኢስማኢል መጥፎ ሰው አይደለም ብላ ትሞግታለች። ዛሬም ትንሰፈሰፍለታለች።
.
አንድ ቅዳሜ ጠዋቱን ሀያት ታናሽ እህቷን ሱመያን አልጋዋ ላይ አስቀምጣት በሩን ቆለፈችው። ህፃኗ ገና ንግግር የመረዳት ደረጃ ላይ አልደረሰችም። ሀያት እየተንሰቀሰቀች ከኢስማኢል ጋር ያሳለፈችውን ጊዜ ለህፃኗ ተረከችላት።
"ሱሚ እድግ ስትዪ ወንዶች እወድሻለሁ  ቢሉሽ አትመኛቸው እሺ!" እንባዋ ሳጓን ያጠነክረውና ከመናገር ይገታታል። ራሷን ለመቆጣጠር ትሞክርና ንግግሯን ትቀጥላለች።
"ሱሚ እነሱ የስሜት ጥማቸውን ሊያረኩብሽ ፣ ሊለማመዱብሽ ነው እሺ መቼም እወድሻለሁ ሲሉሽ አትመኚ! ይኸው እኔን እንኳ ክብሬን የሰጠሁት ኢስማኢል ፍቅርሽ ነው የጎዳኝ ሲለኝ እንዳልነበር ዛሬ ለሽታ እንኳ ራቀኝ።"
ህመሙ ቢወጣልኝ ብላ ንግግሯን ለማትረዳት ህፃን ትዘረግፈዋለች። ለቅሶዋ እጅጉን በረታ እየተንሰቀሰቀች " ሱሚ እድግ ስትዪ ካላገባሽው ወንድ ጋር እንዳትሳሳሚ እሺ ፣ ከተሳሳምሽ አብረን እንተኛ ይልሻል ፣ አብረሽው ከተኛሽ ደግሞ ክብርሽን ታጪያለሽ ፣ ክብርሽን ካጣሽ ደግሞ ይንቅሻል። ወንድ አትውደጂ እሺ ሱሚዬ" ለቅሶዋ እየጠና ሲመጣ ሱሚ አብራት እየጮኸች ማልቀስ ጀመረች። ሀያት ፊቷ በእንባ ታጥቧል። ሱሚን አባበለቻትና መሀል ጣቷን ከአውራ ጣቷ እያማታች ልታጫውታት ሞከረች።
.
ሀያት ስታኮርፍ ኢስማኢል አንገቷ ስር ይነክሳት ነበር። አንዳንዴ ደግሞ ሳቂ ይላትና ስትስቅ ጥርሷን ይስማት ነበር። ዛሬ እነዛ ሁሉ ፍቅር ይመስሉ የነበሩ ቀናት እንደጠወለገ አበባ ውበታቸውን ተነጥቀዋል። ስልኳን አንስታ ሰሞኑን የጀመረችውን አንድ ልብወለድ ቴሌግራም ላይ ማንበብ ጀመረች። አርዕስቱ "የማይፋቅ ስህተት" ይላል። በምታነበው ታሪክ ውስጥ ያለችው ፌቨን የምትባለው ገፀ ባህሪ የደረሰባትን ህመም  ከራሷ ህመም ጋር አመሳሰለችው። ፀሀፊውን ብታናግረው ደስ አላት። ከልብወለዱ አርዕስት ስር ያለውን ስሜን ፌስቡክ ላይ አስሳ አካውንቴን አገኘችው። መልዕክት ስታስቀምጥልኝ ፌስቡክ ላይ ብዙም ስለማልቆይ በቴሌግራም እንድታወራኝ ዩዘርኔሜን ላኩላት። ሁሉንም ታሪኳን አጫወተችኝ። ከእኔ ጋር የተዋወቅንበት ቅፅበት ይኸው ነው። ሁሌም የተሰማትን ትልክልኛለች እኔም በቻልኩት አማክራታለሁ።
.
ቀናት ከሄዱ በኋላ እሁድ ማታውን ኢስማኢል ደወለላት። የሚናገረው ተመሳሳይ ነገር ነው። "ጊዜ እፈልጋለሁ ፣ ራሴን ልወቅ" ነበር ቃሉ። ራሱን ከማወቁ በፊት ነበር የተኛት ማለት ነው? ቀናት ሲሄዱ ኢስማኢል የሀያት ጓደኛ እንደሆኑ የማያውቃቸው ጓደኞቿ ፎቶ ስር ኮመንት መስጠት አበዛ።  አሁንም የሀያት ምኞት ልቡ አደብ ገዝቶ የድሮው ኢስማኢል ቢሆንላት ነው። የፈጣሪዋን ትዕዛዝ መጋፋቷን ራሷም አትዘነጋውም። ታሪኳን በፃፈችልኝ ቁጥር ጌታችን እንዲምረን ዱዓ አድርግልን ትላለች። ከሁሉም የገረመኝ ደግሞ ምህረቱን ለእሷ ብቻ ሳይሆን ለእርሱም መመኘቷ ነበር። ዛሬም ትወደዋለች። ዛሬም ታፈቅረዋለች።
.
የተወለደችበት ጥር ሀያ ስድስት ቀን ሲደርስ እኔ ቤት መኝታ ክፍል ውስጥ ተኝቼ በስልኬ ማስታወሻ ላይ የዚህን ፅሁፍ ክፍል አንድን እየፃፍኩ ነበር። ታሪኳን ለማስታወስ የላከችልኝን ድምጾች ሳደምጥ "አስራ ስምንት አመቴን ጥር ሀያ ስድስት ነው የምይዘው" ያለችበትን ሰማሁና ሊሰማት የሚችለውን ህመም እያሰብኩ "ዛሬ 18+ ሆንሽ አይደል?" የሚል መልዕክት ላኩላት። ዛሬ የተወለደችበት ቀን እንደሆነ ማሰብ እንዳልፈለገች በሚያሳብቅ ሁኔታ "አዎ" ብቻ ብላ መለሰችልኝ። ምናልባትም እያለቀሰች ይሆናል።
ወደ ማታ ላይ ኢስማኢል ደውሎላት "ሀፒ በርዝደይ" እንዳላት ነገረችኝ። እንደድሮው ቢሆን በሚገርም ትዕይንት ሊያከብሩት ይችሉ ይሆናል። ግን የነበሩበት የፍቅር ግንኙነት ምንም አይነት ህጋዊ ድጋፍ ስለሌለው እንደእቃቃ ሆ ተብሎ ተመስርቶ ሆ ተብሎ ፈረሰ።
.
ዛሬም ብዙ ሰዎች ታሪኳን ሲሰሙ "ይህቺ ሴት ናት እንዴ? ደሞ ራሷ ስማው!" "ቲሽ እንዴት አብራው ትተኛለች? ባለጌ!" እያሉ ሊወቅሷት ይሞክራሉ። አዎን ትናንትም እሷ እንደዚህ ያሉ ተመሳሳይ ታሪኮችን ብትሰማ ልትል የምትችለው ይኼን ሊሆን ይችላል። ግን ዛሬም ብዙ አፍላ ወጣቶች ከሚወዷቸው ቤተሰቦቻቸው ፣ ከሚሳሱላቸው ወላጆቻቸው ፊት የእሳቱ እድሜ ወላፈን ዞር ሲያደርጋቸው ያደጉ እየመሰላቸው አንሶላ መጋፈፍ ጀምረዋል። ሊያስከፍለው የሚችለውን ዋጋ ግን ለማሰብ አልቻሉም።
.
በሰዓቱ ታሪኳን ስታጫውተኝ በፈተና የተጨናነቅኩበት ጊዜ ስለነበር ወዲያው ልፅፈው አልቻልኩም ነበር። ስለ ታሪኳ ሳስብ ሁሉንም እውነት ፣ ሁሉንም እሳት ያለምንም ሽሽግ ልፅፈው ለራሴ ቃል ገባሁ። ሁሉንም እውነት ፣ የመኝታ ክፍሉን ትንቅንቅ ሳይቀር በግልፅ አማርኛ ፅፌዋለሁ። ይህ ማስተዋል ለሚችሉ ወጣቶች ሁሉንም የህይወት ጎን ተመልክተው የነገሩን መልካምነት አሊ
​​♥️ ፈተና ♥️

ክፍል አንድ

      ✿ አጠር  ያለ የፍቅር ታሪክ ✿

ቅድስት እባላለሁ አሳዛኝ የፍቅር ታሪኬን ላጫውታችሁ ወደድኩ እኔ የምኖረው ከእናቴና ከታናናሽ ወንድሞቼ ጋር ነው ታድያ ገና የአስረኛ ክፍል አጠናቅቄ ውጤት ቀርቶብኝ የግል ለመማር
እያቀድኩ ሳለ ጎረቤታችን ኢሳያስ የሚሰራበት የግል ድርጅት ውስጥ
ሰአት ተቆጣጣሪ እንደሚፈልጉ ሰማሁ ትምህርት አስጠልቶኝም ስለነበር ስራውን አነጋግሬአቸው ጀመርኩ
ስራ ቦታው የራሱ የሆነ የማይረሳ ትዝታ አለው ፈርኒቸር ቤት ነበር እናም ሰራተኞቹ እርስ በርስ ያላቸው ድጋፍ ያስቀናል ... ይሄኔ ነበር ልኡልን እዛው ሲሰራ ያየሁት ታድያ ልኡልን ድንገት ላየው እንጨት ሲፈቀፍቅ የሚውል አይመስልም በጣም ያምራል ቀላ ብሎ እረዘም ሲል ትናንሽ አይኖቹ እንደጨረቃ ያበራሉ ፈገግታው
ልብ ይሰርቃል ... ይገርማል በዛ እድሜዬ ማፍቀር ቀርቶ ስለፍቅር ማሰብ ከባድ ነበር ይሁንና ለልኡል ፍቅር ይሁን አድናቆት የማላውቀው ስሜት አለኝ ... ግን ልኡል ላይ አይኔ አረፈ ...በስራው ጎበዝና ታታሪ ነው። ታድያ አንድ ቀን ምሳ በልቼ ፀሀይ መሞቅ ጀመርኩ ይሄኔ ልኡልና ጓደኛው እያወሩ መጡ ሁሌም ቢሆን ሳየው ደስ ይለኛል እኔ መቆም ካለብኝ ቦታ እሱን ለማየት እሱ የሚሰራበት ቦታ ድረስ እሄድ ነበር ታድያ ዛሬ ለኔ አዲስና አስደሳች ቀን ነበር ልኡሌ
ከጓደኛው ጋር ሲገባ በአይኑ አወራኝ አላመንኩም በፈገግታ መለስኩለት ... ከዛን ቀን ቡሃላ ከእይኖቻችን ባለፈ የተመጠኑ ቃላቶችን መጠቀም ጀመርን ቀናቶች በሄዱ ቁጥር መግባባታችን
እየጨመረ ሄደ ... አንድ ቀን ከስራ ስወጣ ብቻዬን ነበር የምሄደው ሁሌም
ከጎረቤታችን ኢሳያስ ጋር ስለምሄድ ብቻዬን መሄዴ ለኔ የመጀመርያ ነበር ብቻዬን የምሄድበት ምክንያት ደግሞ ኢሳያስ ስራ ባለመግባቱ ነበር ... ታድያ ይሄን ያየው ልኡል በደስተኛ ፊት
ልሸኝሽ አለኝ እኔም ምላሼን በፈገግታ አጅቤ በአዎንታ እራሴን ነቀነኩ... ከዛ ቀን ቡሃላ ኢሳያስን እየተደበኩ ልኡል ይሸኘኝ ቀጠለ ... በጥቂት ቀን ውስጥ ተግባባን ... ልኡልን ወደድኩት እሱም ወደደኝ ማንም ማንንም ሳይጠይቅ ፍቅር
ተጀመረ አሁን ላይ ሆኜ ሳስበው የብስራት ሙዚቃ ቃልበቃል  ሚለው ዘፈን ያኔ ቢኖር እላለው ምክንያቱም አንድ የሚላት አዝማች አለች ማሀል ላይ
"እንደኔ በሆነ ፍቅሯ እያልኩኝ ልቤን ሳስጨንቅ አረግሽኝ በሀሴት ጥልቅልቅ
ያብሮነት ጥጉ በጊዚያት ካይን አልፎ ልብን ሲላመድ እንዲ ነው ለካ መዋደድ"
ይላል ታድያ ዘፈኑ ለኛ የተዘፈነ እስኪመስለኝ ድረስ አሁን ስሰማው
ያን ህይወት ያስታውሰኛል አንድ ቀን ልኡል ሰፈር ድረስ ሸኝቶኝ ልክ ስደርስ ቆመን ማውራት ጀመርን ሰአቱ ሳናስበው መሽቶ ጨለምለም እያለ ነው ሰማዩ በከዋክብት ደምቋል ይሄኔ በሚያማምሩት ከዋክብት ስም ላይከዳኝ ላልከዳው ቃል ተገባባን ለመጀመርያ ግዜ ከንፈሬን ሊስመኝ ተጠጋኝ የዛን ቀን ነበር እንደሚያጨስ ያወኩት ... እውነት ለመናገር ሲጋራ የሚያጨስ ሰው ባጠገቡ ማለፍ እንኳ በጣም ይቀፈኝ ነበር ልኡሌን ግን ሳልፀየፍ ሳምኩት እውነትም ፍቅር ይዞኛል ... ልኡል በጣም እንደሚወደኝ ያወኩት ማጨስ ማቆም እንዳለበት ስነግረው በሀሳቤ ተስማማ እናም ለአመታት የነከሰውን ሲጋራ
ለማቆም 1 አለ ለማቆም ቅድምያ መቀነስ ነበረበት ይሄን ሲያደርግ ደግሞ ከፍተኛ እራስ ምታት ያመዋል ከዛም ስራ ይቀራል ይሄ ደግሞ እኔን ያስከፋኝ ጀምሯል... ስራ ሲቀር አንገናኝም
አጭሰህ ደግሞ ላይህ አልፈልግም እንኳን ልስምህ ብዬዋለው... ልኡሌ ማጨስ ለማቆም ሲጥር በመሀላችን ክፍተት ይፈጠር ጀመር... በዛ መሀል እኔም ስራ አቆምኩኝ ... የኔ ስራ ማቆም ደግሞ ይበልጥ አራራቀን ይሄኔ ልኡል መደወል ቀነሰ እኔ ስደውልለትም አያነሳም በጣም ከፋኝ ይናፍቀኝ ጀመር
ለኔ ብሎ ብዙ አጉል ሱሶችን የተወልኝ ልኡል ዛሬ ራቀኝ እኔም ቀን በቀን ማልቀስ ቀጠልኩ በዚ መልኩ ቀናት ተቆጠሩ እኔም ቢያንስ አይኑን ልየው ብዬ ወደሱ ሰፈር ሄድኩ እዛው አካባቢ
የሚቀመጥበትን ስፍራ አውቀው ስለነበር ወደዛ ሄድኩ ስደርስ ግን ያልጠበኩት ነገር ነበር ያየሁት ልኡሌ ከሌላ ሴት ጋር ... የእውነቴን ያበድኩ መሰለኝ እንባዬ እየዘነበ ብቻዬን እያወራሁ ተመለስኩ ወደቤት ግን መግባት አስጠላኝ

ይቀጥላል

SHARE AND JOIN
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche

💛...........🍃🌸🍃............💛
2024/09/21 14:33:16
Back to Top
HTML Embed Code: