Telegram Web Link
የፍቅር ጥቅሶች 💖 pinned «​​♥️ ፈተና ♥️ ክፍል አንድ       ✿ አጠር  ያለ የፍቅር ታሪክ ✿ ቅድስት እባላለሁ አሳዛኝ የፍቅር ታሪኬን ላጫውታችሁ ወደድኩ እኔ የምኖረው ከእናቴና ከታናናሽ ወንድሞቼ ጋር ነው ታድያ ገና የአስረኛ ክፍል አጠናቅቄ ውጤት ቀርቶብኝ የግል ለመማር እያቀድኩ ሳለ ጎረቤታችን ኢሳያስ የሚሰራበት የግል ድርጅት ውስጥ ሰአት ተቆጣጣሪ እንደሚፈልጉ ሰማሁ ትምህርት አስጠልቶኝም ስለነበር ስራውን አነጋግሬአቸው…»
​​♥️ ፈተና ♥️

ክፍል ሁለት

      ✿ አጠር  ያለ የፍቅር ታሪክ ✿

እንደዛ በፍቅር ክንፍ ያልኩለት ወንድ በከዋክብት ፊት የገባውን ቃል እረስቶ በጠራራ ፀሀይ ከሌላ ሴት ሲወዳጅ ማየት ለኔ ሞት ነበር ያስመኘኝ ... መንገድ ላይ እናቷ እንደጠፋችባት ህፃን እንባዬ መንታ መንታ እየወረደ እጓዛለው ይሄን ሁኔታዬን የተመለከተ ወጣት ወደኔ ተጠግቶ እጁን ለሰላምታ ዘረጋልኝ ቀና ብዬ ሳላየው እንኳ ትቼው መንገዴን ቀጠልኩ ይሄኔ ክንዴን ያዝ አደረገኝ ንዴት
መላ አካላቴን ሲወረኝ ይሰማኛል መንጭቄው ልሄድ ስል ተረጋጊ
የኔ ቆንጆ አለ የድምፁ እርጋታ የእውነትም ያረጋጋል እርምጃዬን ገታ አድርጌ ቆም አልኩ ቀና ብዬ ስመለከተው ፈገግታን ለገሰኝ ቆንጆ አይባልም ግን ወንዳወንድ ነው አብሬው ብሆን የልኡልን ክህደት የምረሳ መሰለኝ ልጁም በድጋሚ አይዞሽ እሺ ተረጋጊ አለኝ እኔም እሺታን
ለመግለጅ አይኖቹን እያየው እራሴን ነቀነኩ ጀምበር እያዘቀዘቀች
ነው ከመርካቶ ወደ አብነት በእግራችን መራመድ ጀመርን ዝምታችንን ለማፍረስ ይሁን ባላውቅም ናትናኤል እባላለሁ ናቲ
ብለሽ ልትጠሪኝ ትችያለሽ አለኝ እኔም ሀዘኔን ለመርሳት እየጣርኩ ቅድስት እባላለሁ አለኝ እሱም እሺ ኪዲ በጣም ታምሪያለሽ ይህን ታውቂ ነበር አለኝ ...እእእ አልኩ እንደመሽኮርመም እያረገኝ ..እ... አይ አታውቂም ነበር ማለት ነው ዛሬ ልንገርሽ በተለይ አይኖችሽ
ውብ ናቸው አልቅሰሽባቸው እንኳ ውበታቸውን መሸሸግ አልቻሉም
አለኝ ... ይሄኔ ሉሌ ትዝ አለኝ በድጋሚ ተረበሽኩ እናም ስለተፈጠረው ሁሉ አጫወትኩት... ናቲ ጥሩ ልጅ ይመስላል ልኡል ምናልባትም አኔ ባሰብኩት
መንገድ ላይሆን ይችላል አብሯት የቆመው የሚለውን እንዳስብ
መከረኝ ... እየውልሽ ኪዲ ቆንጆ አንቺ ገና ህፃን ነሽ ስለዚህ በቀላሉ መሸነፍና እጅ መስጠት የለብሽም በዛ ላይ እናትሽ አንቺን ያልሆነ ቦታ ልታይሽ እንደማትፈልግ አትርሺ ... ነገ ይህን
ፍቅረኛሽን አጊኝተሽ ለምን እንዲ እንዳረገ ጠይቂው ወይምኮ ይህች ልጅ እህቱ ልትሆን ትችላለች አለኝ ከተል አርጎም አሁን ወደቤትሽ ግቢ አጉል ሰአት ለሴት ልጅ ጥሩ አይደለም አለኝ...
በጣም ገርሞኝ አየሁት ከዛም ወደቤቴ ገባሁ ለሊቱን ሙሉ ስለ ልኡል ሳስብ ነጋ አምላኬ እንደናቲ አፍ ባረገልኝና ምናለ እፎይ ባልኩ ምናለ ፍቅሬን ለሌላ ባላጋራብኝ ስል ተመኘው ልክ ሲነጋ
ስራ ፍለጋ በሚል ሰበብ ወጣሁ ከዛም ቀጥታ የልኡል ሰፈር ሄድኩ ሉሌ ስራ ገብቶ እንደሆን ለማረጋገጥ ብዙም ሰአት አልፈጀምኝም ነበር ሄጄ እሱ ሲደብረው ተቀምጦ ሲጋራውን እያጨሰ በጭሱ
የሚመሰጥበት ቦታ ተቀመጥኩ... ድንገት ባይምሮዬ የጎሳዬ ዘፈን ይመላለስ ጀመር... "ሸጋ ልጅ ባ^ሳቤ
ድንገት ልቤ ገብታ ትመላለሳለች
ቀን ማታ ቀን ማታ(2)"
ይሄኔ ከሩቅ ትላንት ከልኡል ጋር ያየኋትን ሴት ተመለከትኩ ጊዜ
ሳላጠፋ እየሮጥኩ ወሷ ሄድኩ ልጅቷ ነብሰ ጡር ናት ሆዷን አይቼ
እርጉዝ ነሽ ምነው ጥላ ሳትይዢ በዚ ፀሀይ አልኳት የምፀት የሚመስል ፈገግታ በትንሹ ፈገግ ብላ ፀሀይ የታል አለች እኔም የማወራው አጥቼ በመዘባረቄ እንደ ማፈር ብዬ እባክሽ ስለ ልኡል
ልጠይቅሽ ብዬ ነው አልኳት እሷም በቅፅበት ፊቷልውጥውጥ ብሎ እንደ መቆጣት አረጋትና መልሳ አይኗ እምባ አቀረረ ... እኔም ግራ ገብቶኝ ሁኔታዋን እከታተል ጀመር ከዛም አየት አርጋኝ
አንቺንም አስረገዘሽ አለች ቃሉ ድንገት ሆኖብኝ አንደበቴ ተሳሰረ
ሰማይ ምድሩ ዞረብኝ

ይቀጥላል



       🥀💞SHARE AND JOIN💞🥀
           💚
@yefeker_tiksoche💚
           ❤️
@yefeker_tiksoche❤️

💛...........🍃🌸🍃............💛
​​♥️ ፈተና ♥️

ክፍል ሶስት

      ✿ አጠር  ያለ የፍቅር ታሪክ ✿

ከደቂቃዎች ቡሃላ እራሴን አንዲት ጠበብ ያለች ቤት ውስጥ ልብሴ በውሃ በስብሶ አገኘሁት ወድያው ያቺን እርጉዝ ሴት አየሁ ይሄኔ ነቃሽ ብላ ወደኔ ተጠጋች ፈራኋት ምን ልትለኝ ይሆን ስል
አሰብኩ.... አይዞሽ አለችኝ ይሄኔ ነበር ቅድም ያለችው ትዝ ያለኝ መናገር ተሳነኝ እንባዬ እየወረደ አንደበቴን አሰረው ቆይ ልኡል ምንሽ ነው አለችኝ ከዛም ከተቀመጥኩበት ብድግ ብዬ ልብሴን
እየጨመኩ ምኔም አልኳት እኔ እንደዛ ያልኳት ምክንያት አለኝ... አባቴ እናቴን በፍቅር አማሎ እንድታፈቅረው ካደረጋት ቡሃላ እናቴ በሱ ሙሉ ለሙሉ ተማምና ነበር እኔን ያርገዘችለት ሆኖም
የኋላኋላ ሌላ ልጅና የሞቀ ትዳር እንዳለው ሰማች እናም እናቴ
ሁሌም እራሷን ከሱ ሸሽጋ የሱን ትዳር ላለመበጥበጥ አባቴን ሳላውቀው አደኩ ... ለዛም ነው ልኡሌ ምኔም አይደለም ያልኩት ለዛም ነው እያፈቀርኩት ዋሸኝ ያላልኩት ልጅቷም ከብዙ ዝምታ ቡሃላ በቃ መሸብሽ ሂጂ እራስሽን ስትስቺ ደንግጬ ነው እቤቴ
ያስገባሁሽ አለችኝ እኔም ደና እደሪ እንኳ ሳልል ወጥቼ ሄድኩ ... ወጥቼ መንገድ ላይ ስሄድ እቃ የጠፋብኝ እመስል ነበር በቀኝና በግራ እንዲሁም ወደኋላዬ እየዞርኩ ትላንት ተስፋ የሰጠኝን ናቲን
ማግኘት ፈልጌአለው ልክ ትላንት እጄን የያዘኝ ቦታ ስደርስ ቆምኩ ኪዲዬ የሚል ድምፅ ስሰማ በቀጥታ ዞርኩ ናቲ ለመሆኑ ምንም አልተጠራጠርኩም እሱን ሳይ እምባዬ ያለገደብ ይወርድ ጀመር
እሩጬ ተጠመጠምኩበት እሱም አቀፎ አባበለኝና ያረጋጋኝ ጀመር ከቆይታ ቡሃላ ምን ትፈልጊያለሽ አለኝ እንባዬን እየጠራረኩ እራሴን መርሳት እፈልጋለሁ አልኩት ኮስተር ብሎ አልገባኝም አለኝ
በቃ መጠጣት እፈልጋለው ከቻልክ ቀውጢ ቤት ውሰደኝ አልኩት
እሱ ግን አመነታ የኔ ቆንጆ ይሄ አይጠቅምሽም ገናኮ 18 እንኳ
አልሞላሽም ተረጋጊ እንጂ አለኝ ይሄኔ ከከዳኝ ልኡል በላይ እሱ
አበሳጨኝ ሁለተኛ እንዳትከተለኝ ሌላ ፍላጎቴን የሚያሟላ አላጣም ብዬ ትቼው ስሄድ እሩጦ ያዘኝና ... እሺ እንዳልሽ አለኝ ይሄኔ ደስ ብሎኝ ፈገግ አልኩ... እኔ በሀሳቤ ልኡልንና ያረገዘችውን ሴት እያሰብኩ ፒያሳ አካባቢ የሚገኝ ባር ውስጥ ተቀመጥን ቤቱ ውስጥ ለስለስ ያለ ሙዚቃ ተከፍቷል ሰው እየተነሳ ይወዛወዛል እኔም ከልኡሌ ጋር
ያሳለፍኩትን እያሰብኩ በትዝታ እዋኛለሁ ናቲም በሀሳብ ተውጧል በመሀላችን እረጅም ሰአት ዝምታ ሰፈነ ... ይሄኔ ሳላስበው ታውቂያለሽ እኔ የማፈቅራት ልጅ ነበረች ያየሁሽ ቀን ለፍቅር
ስታለቅሺ እሷን ነበር የመሰልሽኝ በጣም ታፈቅረኝ ነበር ግን ምን ዋጋ አለው ድንገት ቤተሰቦቿ ለማታውቀው ሰው ድረው እንግሊዝ ሀገር ላኳት አለ የሆነ የሀዘን ድባብ ፊቱ ላይ ይታያል አሳዘነኝ...
ቆይቶ ትዝ የሚለኝ ሁለታችንም ስሜታችንን ለመርሳት ስንጨፍር
ነበር ከዛ የሆነውን አላስታውስም ስነቃ እንደ አንድ ሰው ተጣብቀን
ተኝተናል በድንጋጤ አላበኝ

ይቀጥላል


  🥀💕SHARE AND JOIN💕🥀
      💚
@yefeker_tiksoche💚
      ❤️
@yefeker_tiksoche❤️

    💚...........🍃🌸🍃............❤️
​​♥️ ፈተና ♥️

ክፍል አራት

      ✿ አጠር  ያለ የፍቅር ታሪክ ✿

ውጪ እንኳን ላድር አምሽቼ የማላውቅ ልጅ ዛሬ ሊያውም ከማላፈቅረው ወንድ ጋር ተኝቻለሁ ግን ምን ልበል ልናደድ ወይስ ደስ ልሰኝ ምንም አላውቅም ቀስ ብዬ የለበስኩትን ልብስ አየሁት
እናም እንደለበስኩት ነው እኔ ከማንም ወንድ ጋር ተኝቼ አላውቅም ያም ማለት ድንግል ነኝ ግን ምንም አይነት ደም አይታየኝም ግራ ገባኝ ወንድ ልጅ ነው አብሬው እስከመተኛት ደርሼ ምንም
አላረግንም ማለት አይታሰብም ... ነቅቶ የተፈጠረውን እስኪነግረኝ ጓጓው ...
እኔ በጭንቀት ተጣጥፌ ወንበር ላይ ተቀምጬ እንዳቀረቀርኩ ነቃ
በስስት ተመለከተኝ አይኖቼ እምባ አቀረሩ አንድ ጥያቄ እንዳለኝ ያወቀ ይመስል ለመናገር ጉሮሮውን ጠራረገ ከዛም ትላልቅ አይኖቹን በሁለት እጆቹ ያሻቸው ጀመር ሲነቃ ደፍርሰው ከነበረው
በላይ ደፈረሱ ደና አደርሽልኝ ቆንጆ አለ ይሄኔ ያላባት ያሳደገችኝ እናቴ ሳልነግራት አድሬ ምን ያህል እንደምትጨነቅ እና ሉሌ ከሌላ ወንድ ጋር መማገጤን ሲያውቅ ምን ሊለኝ እንደሚችል አስቤ
እራሴን ጠላሁት የማረባ ሴት መሆኔ ታወቀኝ ...ዝምታዬ ያስፈራው ናቲ ከተኛበት አልጋ ወርዶ ከተቀመጥኩበት
ወንበር ላይ አንስቶ አልጋው ላይ በጀርባዬ አስተኛኝ የልብ ምቴ
ጨመረ ግን ካንደበቴ ቃል አሎጣም ... ክንዱን አንተርሶኝ ከጎኔ ተኛ ... ደንግጠሻል? አለኝ አይ አልደነገጥኩም አልኩት እሺ ማታ ምን እንደተፈጠረ ታስታውሻለሽ ሲል ጠየቀኝ አ...ይ አልኩ እሺ እነግርሻለሁ ሲል ቀጥሎ የሚለውን ለመስማት ካንገቴ ቀና አልኩ
ከዛም እ...እኔ ማወቅ የምፈልገው አንድ ነገር ነው እናም ወሲብ ፈፅመናል? ብዬ ጠየኩት ከት ብሎ ሳቀ ይበልጥ ግራ ገባኝ ...ዝም ብዬ ተመለከትኩት ልክ ስቆ ሲጨርስ ... በፍፁም አለኝ ኮራ
ብሎ አላመንኩትም ... ብፈልግ እንኳ ሰክረሽ አላደርግም አለኝ ይሄኔ በልቤ ፈጣሪን አመሰገንኩ...ከዛ ቀን ቡሃላ እኔም ዱርዬ የምባል አይነት ሴት ሆንኩ መጠጥ እጠጣለው ሺሻ ቤት ቤቴ አርጌዋለው ታድያ እናቴም በኔ ማዘኗን
ቀጥላለች ናቲ በርግጥም ብዙ ግዜ መክሮኛል ከሱ ጋር ስሆን
መጠጥ እንኳ ብዙ አይፈቅድልኝም ሺሻም ፈፅሞ አላጨስም ግን
ከሱጋ የምሆነው ውስን ጊዜአቶችን ነው ምክንያቱም እሱ ስራ
አለው... በዚ መልኩ ወራት አለፉ እናም ከዛ በላይ ክብሬን ማስጠበቅ
አልቻልኩም ከናቲ ጋር አንሶላ ተጋፈፍን ... ይሄኔ ከዚ ቡሃላ ፍቅር የለም ብዬ አመንኩ እናም ስራ ፈልጌ ተቀጠርኩ ግን እቤት
የምገባው ከምሽቱ 4፡00 ቡሃላ ነው ማንም ሰው ሲመክረኝ ያናደኛል ናቲ ፍቅረኛዬ ይሁን ወንድማዊ ጓደኛዬ ምኑንም አላውቀው ግን አብረን ማደር አዘወተርን ... ፍቅረኛ እይዛለው 3ወር ሳይሞላ እጣላዋለሁ ሌላ ፍቅረኛ
እይዛለው ከዛም ከሱጋም እፋታለው ህይወቴ በዚ መልኩ እየቀጠለ ልክ ባመቴ ልኡል ደወለ ስልኩን ሳየው የደነገጥኩት መደንገጥ አሁን ድረስ ትዝ ይለኛል ግን አላነሳሁለትም የሚገርመው ግን ስራ ቦታዬን አፈላልጎ መጣ ሳየው የማደርገው ጠፋኝ ፍቅር እንዳዲስ አገረሸብኝ ግን ህይወቴ የተበላሸው በሱ
ስለነበር ዳግም መጎዳት አልፈለኩም ግን ሊተወኝ አልቻለም ደጋግሞ ይቅርታ ጠየቀኝ አንድ ቀን ከስራ ስወጣ ልኡል ከእናቱ ጋር እየጠበቀኝ አገኘሁት
ደንግጬ ቆምኩ እናቱም የኔ ቆንጆ ደሞ ስታምር ብለው ይስሙኝ ጀመር ግራ ገብቶኝ ዝም አልኩ ልጄን ከአጉል ሱስ አወጣሽልኝ የጠፋውን ልጄን መለስሽልኝ እደጊልኝ አሉኝ አይናቸው የደስታ
እምባ አቅርሮ... እኔ በሱ ምክንያት ህይወቴ ተመሰቃቅሎ እናቴ
በኔ ሀሌም ታዝናለች ልኡሌ ደግሞ በኔ ተለውጧል ግን እንዴት ቢያፈቅረኝ ኖሮ ሌላ ሴት እንዳለው አይደብቀኝም ነበር ይሄን ያህል ግዜም አይጠፋም ነበር... ወደኋላ ተመልሼ ሳስብ እንባዬ
ይምዘብ ጀመር ከዛም
እናትና ልጅ በቆሙበት ትቻቸው ሮጥኩ...

ይቀጥላል



           🥀💕SHARE AND JOIN💕🥀
              💚
@yefeker_tiksoche 💚
              ❤️
@yefeker_tiksoche❤️

           💛...........🍃🌸🍃............💛
​​♥️ ፈተና ♥️

ክፍል አምስት

   ✿ አጠር  ያለ የፍቅር ታሪክ ✿

እኔና ሉሌ እረጅም ሰአት ተጨቃጨቅን ከዛ የዛን ቀን ስለመሸብኝ
ትቼው ሄድኩ በሁለተኛው ቀን ስራ ልገባ ታክሲ ስጠብቅ ልኡል
መጣ ይሄኔ ከልኡል አርግዣለው ስላለችኝ ልጅ ነገርኩት
በመጀመርያ አላመነኝም ነበር ከዛ ግን የተፈጠረውን በሙሉ
ነገርኩት የእውነቱን ተናዶ ፊቱ ተለዋወጠ ቀይ ፊቱ ሚጥሚጣ
መሰለ እገላታለው አለኝና በቆምኩበት ትቶኝ ሄደ ... ግራ
ስለገባኝ ምንም አልመለስኩለትም ... ቀጥታ ወደስራዬ ሄድኩ ...
ቀኑን ሙሉ ስለልኡል ሳስብ ዋልኩ ለምን እንደዛ ሆነ ምናልባት
ልጅቷ ዋሽታኝ ይሆን? ግን ለምን ብላ ደግሞም አብረው
አይቻቸዋለው ... ብቻ ከራሴ ጋር ስሟገት ዋልኩ በጭንቀት
እራሴ ሊፈነዳ ደረሰ በርግጥ ከበፊቱ አሁን ደና ነኝ ማለትም
ማምሸትና ባመሸሁበት ማደር ትቻለው እድሜ ለሱሬ ከኔ ምንም
ምላሽ ሳይጠብቅ ከልቡ ይወደኛል ይንከባከበኛል ... ያ ደግሞ
እኔን ከመጥፎ ጎዳና መልሶኛል እማዬም እፎይ ብላ በኔ ደስተኛ
ሁናለች ስለዚህ ምንም ሆነ ምን ዳግም ልኡልን አልቀርብም
ሲቀጥል ደግሞ ምንምኳ መጠጥ ጭንቀቴን ቢያስረሳኝም
አልጠጣም ይህ በንዲህ እንዳለ ማታ ላይ ከስራ ስወጣ ብቻዬን ነበርኩ ሱሬ ስራ አመሻለው ስላለኝ ብቻዬን ወደቤት መሄድ ጀመርኩ ይሄኔ ልኡል ሁሌም እንደሚያረገው ውጪ ይጠብቀኝ ነበር ዛሬ ግን ለየት የሚያረገው ሉሌ ከልጁ እናት ጋር ነው ሳያቸው ሊነግሩኝ የሚፈልጉት ነገር እንዳለ ገባኝ ከዛም ወደኔ ሲመጡ ቆሜ
ጠበኳቸው ልጅቷ ታለቅሳለች ለምን እንደምታለቅስ ባይገባኝም
ዝም ብዬ መከታተል ጀመርኩ በይ ንገሪያታ አላት ለመስማት
ብዙም አልጓጓው ይሄኔ አንዱ የልኡል ጓደኛ መጣ ሁላችንንም
ሰላም ካለን ቡሃላ ቅድስቴ እሷ ህይወት ትባላለች የልጄ እናት ነች
አለኝ ... ከት ብዬ ሳኩና የተሻለ ድራማ የላቹም አልኩት ...
3ቱም በየተራ እኔን ለማሳመን ማውራት ጀመሩ ማንንም
አልሰማም በቃ የኔና ያንተ ግንኙነት አብቅቷል ብዬ ትቻቸው
ሄድኩ ይሄኔ ልጅቷ ሮጥ ብላ ያዘችኝና እባክሽ ይቅርታ አርጊልኝ እናም ልኡል ያፈቅርሻል ፍቅራቹን ቀጥሉ አለች በጣም ስለተናደድኩ
በጥፊ መታኋትና ያኔ ምን ብለሽኝ ነበር አንቺ ምን አይነት ሰው ነሽ
ሁለተኛ ብትደርሺብኝ እገልሻለሁ ብያት ጥያት ሄድኩ

የመጨረሻው ክፍል በቅርብ ቀን ይቀጥላል                      
  🥀💕SHARE AND JOIN💕💕
      💚
@yefeker_tiksoche❤️
      ❤️
@yefeker_tiksoche 💚
​​♥️ ፈተና ♥️

ክፍል ስድስት

    ✿ አጠር  ያለ የፍቅር ታሪክ ✿

የመጨረሻው ክፍል

ልኡልን ከዛ ቡሃላ ለረጅም ግዜ ሳላገኘው ቆየው በመሃል አክስቴ
ደቡብ አፍሪካ ወስዳኝ እዛ ለአንድ አመት ቆየሁ ይሄኔ ነበር
በደምብ የተራራቅነው ከሱራፌል ጋርም እንደመጀመርያው መሆን
አልቻልንም በስልክ ብቻ ሲሆን ግንኙነታችን ፍቅር ቀዘቀዘ እኔ ችላ
ስለው እሱም እኔን ለመርሳት ሌላ ሴት መተዋወቅ ጀመረ ...
ከአንድ አመት ቡሃላ ወደ ሀገሬ ስመለስ የመጀመርያው ባህሪዬ
ጠፋ አዲስ ሰው ሆንኩኝ ወንድ ልጅን በፍቅር መቅረብ አቆምኩ
ሱሬም እንዳዲስ ሲያገኘኝ ፍቅር አገርሽቶበት ኖሮ አንዳዲስ
እንጀምር የሚል ሀሳብ አቀረበልኝ እኔ ግን ከልኡል ቡሃላ ወንድ
ልጅን ማመን ከበደኝ ማፍቀር ፈራሁ እናም እራሴን ከዚ አግልዬ
ህልሜን ማሳካትና ስራዬን ባግባቡ እየሰራሁ መኖር ጀምሬአለው
እናም ሱሬን የራሱን ህይወት እንዲጀምር ነገርኩት...በዚ ሁሉ
መሀል ግን ልኡል ያለበትን ፈፅሞ አላውቅም አጋጣሚ እንኳ
አይቼው አላውቅም ... በርግጥ ሉሌ ልጁ የሱ አለመሆኑን
አረጋግጫለው ግን የይቅርታ ልብ አጣሁ ያኔ ስለተጎዳሁ ልኡልን
ደግሜ በፍቅር ማሰብ አቃተኝ...
ይህ በንዲህ እንዳለ አንድ ቀን ከስራ ወጥቼ ወደ ቤት ለመግባት
ብቻዬን ወክ አደርጋለሁ ሰአቱ ጨለምለም ብሏል እኔም የጆሮ
ማዳመጫዬን በጆሮዬ ሰክቼ ማንንም ላለመስማት ይመስል
ድምፁን ከፍ አድርጌ የታምራት ደስታን "ከዚያ ሰፈር " የሚለውን
ዜማ አዳምጣለሁ
ምን ሊያምርብኝ ብዬ
ሳትኖሪ ከጎኔ
ደሞስ ምን ሊጠቅመኝ
ያንን ሰፈር አየዋለሁ ባይኔ
.
ይቅር ይቅር
እንኳን ሌላው አንቺ ቀርተሻል"
.
እያለ በሚያምር ድምፁ በሚያምር ዜማ ያዜማል እሱ ዘፈን ሁሌም
ትዝታዬን ይቀሰቅስብኛል ከልኡል ጋር ያለፍናቸውን ግዚያቶች
ያስታውሰኛል በዚ መሃል አንድ ሰው ከኋላ ጎንተል አረገኝ ወንዶች
ያው በተለምዶ ለከፋ ደስ ስለሚላቸው አንዱ ወንድ ነክቶኝ
ይሆናል በሚል በንዴት ምን ላርግህ አይነት አስተያየት ዞር ብዬ
ሳይ ልኡል ነው አይኔን አላመንኩም ግን እውነትም ሉሌ ነበር ምን እንደማወራ ግራ ገባኝ በጣም ተጎሳቁሏል አሳዘነኝ በኔ ብዙ ስቃይ እንዳሳለፈ ይባስ ብሎም እኔን ለመርሳት በህገወጥ መንገድ
ከሀገር ሲወጣ ሊቢያ ላይ ተይዘው እንደተመለሰ ነገረኝ ለነ ብሎ ያደረጋቸውን የሳለፋቸውን
ፈተናዎች ከእግሬ ስር ተደፍቶ ይቅርታ አድርጊልኝ ብሎኝ ሲለምነኝ በጣም ነበር ያዛዘነኝ
ግን ይቅርታ ለማድረግ አልቻልኩም እሱን እንደ ጥፋተኛ አድርጌው እሱ ግን ምንም ነገር
ብለው ከእግሬ ስር ተንበርክኮ አውነትሽን ነው አሁን ያለፈው አልፎል ከአሁን በኀላ ግን
አዲስ ህይወት መጀመር አለብን እስካሁን ላደረኩብሽ በደል እክስሻለው እያለ እያለቀሰ
መቀባጠር ጀመረ ከእግሬ ስር እንዲነሳ አደረኩትና አንተ ምን ስለሆንክ ነው በህይወቴውስጥ እየገባ የምታስቸግረኝ ብዬው አንድ ነገር ነገርኩት እኔ አንተን ብዬ እስካልመጣው ድረስ አትምጣብኝ ብዬው ጉንጩን ሳም አደረኩትና ጥዬም እሮጥኩ....
ከዛም ለሊቱን በሙሉ ስለሱ ሳስብ ስላደርኩኝ መሰለኝ ከነጋ በኀላ ስላሳዘነኝ ብቻ መገናኘት
ጀመርን እሱ አሁንም ከኔጋር በፍቅር ቢቀጥል ይመርጣል እናም እሺ ብለሽኝ ፍቅር ከሰጠሽኝ ወደ ጥሩ መንገድ መጓዝ እጀምራለው እንደቀድሞ ተው ያልሽኝን እተዋለሁ አለኝ ...
እኔ ግን አሁንም ልኡልን በፍቅር መቅረብ አልፈልግም ያሳዝነኛል
ካለበት ሁኔታ ባወጣው ደስ ይለኛል ግን ደግሞ እሱ በፍቅር
እንድንቀጥል ብቻ ነው የሚፈልገው እኔ ግን አልቻልኩም
ሱራፌልንም ባላፈቅረውም ምን እንደማደርግ ግራ ገብቶኝ ይሄው
መሀል ላይ ቀርቼ የማን እንደምሆን ግራ መጋባት ጀመርኩ እናም እኔ ልዑሌን በጣም ነው
የምወደው ግን እሱን አምኖ ለመቀበል ከብዶኛል ሱሬ ደስ የሚልና አዛዛኝ ሰው ነው ግን
እሱ ይወደኛል እኔ እኔም እወደዋለው ግን ለማን መሆን እዳለብኝ እየለፈፈፍኩኝ ከቤቴ
ወጣው ወዴት እንደምሄድ ግን አላውቅም ግን እግሬ ወዳመራኝ መንገድ ብዙ ጎዳናዎች
ከተጓዝኩ በኀላ እራሴን መቆጣጠር አቅቶኝ ወደኩ ግን ግን የሚያነሳኝ ሰው ጠፋ
ምክንያቱም ከቤት ስወጣ የረባ ልብስ እና ጫማ ስላላደረኩኝ የጎዳና ተዳዳሪዎች አድርጎ
ስላሰቡኝ ምሽት አካባቢ ሲሆን ከወየኩበት ነቃውኝ ነገር ግን ያለወበት የት እንደሆነ
ስላላወኩኝ አገር ምድሩ ነበር የዞረብኝ በጣም እርቦኝ ስለነበር ምግብ ፍለጋ ወደ ጥጋጥግ
ፍርፋሪ መፈለግ ጀመርኩ ግን ላገኝ አልቻልኩም ወደፊት ብዙ እርምጃዎችን
እንደተራመድኩኝ በጥግ በኩል በፌስታል የተከለለ ቤት ውስጥ ስገባ ሰው የሌለውም
ስለሆነ በፌስታል የተቆጣጠሩትን ነገሮችን አንድ በአንድ እየፈታው ሳይ የሚበላ ምግብ ግን
ላገኝ አልቻልኩም ከትንሽ ደቂቃ በኀላ ኮቴ ሰማውኝ በድንጋጤ ዘልዬ ስወጣ ውስጥ ይኖር
የነበረው ሰውዬ እጄን አድርጎ አትፍሪ ብሎን የሚበላ ሰቶኝ ውስጥ ገብቼ እንድተኛ ነግሮኝ
ጥሎኝ ሄደ በንጋታው ከዛ ውስጥ ወጥቼ ብር ምናምን ለምኜ ባገኘውት ብር ወደ
ማለውቀው ቦታ ተሠድጄ መኖር ጀመርኩ

ተፈጸመ።
  🥀💕SHARE AND JOIN💕🥀
           💚
@yefeker_tiksoche ❤️
           ❤️
@yefeker_tiksoche 💚
❣️ :¨·.·¨: ❣️
         ❤️ ያሜናዳብ ♥️
         ┈┈••◉❖◉●••┈

               💢ክፍል1

❣️እውነትኛ የፍቅር ታሪክ❣️
በጣም ገራሚ እና አስተማሪ የሆነ የፍቅር ታሪክ ነው ሼር💌 ማድረግ አትርሱ

ትዙ እባላለሁ ተወልጄ ያደኩት በባህርዳር ከተማ ነው ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ ገጠመኝ አለው የአንዱ ህይወት ለአንዱ አስተማሪ ነው ከእኔ ህይወት ትማራላቹ ብዬ አስባለሁ አንደ ማንም ኢትዮጲያው
በስፈር ፍቅር ነው ያደኩት ግን ከሆነ ግዜ በኋላ አሜርካ የሚባል በሽታ ታጋባብኝ በዚች ምድር ላይ እንደ እኔ አሜርካ ለመሄድ የሚፈልግ አለ ብዬ አላስብም ሲበዛ እልኸኛ ነኝ ግቢያችን በጣም ሰፊ
ነው ሚከራይ ዶርሞችም አሉን እናቴ እኔን ወደ ውጭ ለመላክ ያልቆፈረችው ጉድ ጓድ የለም ግን ምን ያደርጋል ይታደሉታል
እንጂ አይታገሉትም በዚህ መሀል ነው እንግዲህ ጆን ወደ ህይወቴ የመጣ
የመጣው እቤት ሊከራይ ነበረ በደላላ ነው የመጣው 8 የሚከራይ ቤቶች አሉን ሁሉም ፅዳቱን የጠበቀ ነው ብዙዋቸ እቤቱ ላይ ብዙ የቆዩ ናቸው ልክ እንደ ቤተሰብ ነን አምስቱ ተከራዮች ባለ ትዳር ሲሆን ሶስቱ ወንደ ላጤ ነበሩ እንዱ ግን
በስራ ምክንያት ዝውውር ወደ አ/አ
ስሄድ ነው እንግዲህ ቤቱን ለጆን ያከራየነው ከገባ ሶስት ሳምንት ሁኖታል እኔ ግን የሚገርነው አንድም ቀን አይቼው አላውቅም ጥዋት ይወጣል ማታ ይገባል እናቴ ቀንም እኮ ይመጣል ትለኛለች አክስቴ ደግሞ እንዴት እንደ ተመቸኝ አጠይቂኝ ትለኛለች እኔም በርግጥ ዙረታም ነኝ መቀመጥ የሚባል አልውድም በዚህ መሀል ነው
እንግዲህ ከገባ ወር ሞልቶት የቤት ክራይ ሊከፍል ማታ ላይ እቤቱን አንኳኳ ቡና እየጠጣን ነበረ አቤት አለች እናቴ ደህና ዋላቹ ማዘር እያለ ገባ ቀልቤ ግፍፍ ነው ያለው ሲጀመር እንደዚህ አይነት ወንድ አይቼ አላውቅም ሁሉን ሰላም ሲል እኔ ግን ፈዝዤ ሰላም አላልኩትም ይቅርታ ጥዋት ወጥቼ ማታ እየገባሁ አልገናኝ አልን እኮ ሲል እንዴ ልጄ ስራም
አይደል ቆይ ምን አዲስ ወሬ አለ ስለ ወንድምህ አለችው ያው በቀደም የነገርኩሽ ጓደኛውን ስልኩን አግቼ ዛሬ ደውዬለት ነበረ ነገ ለንገናኝ ተቀጣጥረናል አለ እኔ ግን አይኔን ከአይኑ ላይ አልነቀልኩም ቡና እየጠጣ ቀና ሲል አይን ለአይን ተጋጨን እኔ አይደለም እንደዚህ አይነት ወንድ ይቅርና የለበሰውን ልብስ እንኳ ገበያ ላይ አይቼው አላውቅም ለናቴ የቤት ኪራይ ሶቶ ብዙም ሳይቆይ ወጣ ሲሄድ ልቤ አብሮ እሱ ጋር ሄዴ ምን እንደተፈጠረ እንኳን አላቅም ማታ ምንም ሳልተኛ አደርኩ በጣም ገርሞኛል በቃ ሁሉ ነገሩ ተመችቶኛል እሱን ለማዬት ብዬ በጧት ተነሳሁ እናቴ የኔ በጧት መነሳት ሳይገርማት አልቀረም በረንዳ ላይ ቁጭ ብዬ ብዙ ሰአት ተቀመጥኩ ግን አልወጣ አለ ወቶ ይሆን አልኩ በልቤ ሶስት ሰዓት ሲሆን ጓዴኞቼ ቤት መጡና ይዘውኝ ወጡ እነሱ ጋር ቆየሁ ግን ጆን ከውስጤ አልወጣ አለኝ እስከማዬው ቸኩያለሁ በጊዜ ወዴ ቤት መግባት አለብኝ ብዬ 10 ሰዓት ላይ ተመልስኩ እናቴ ቤት የለችም አክስቴ ናት ያለችው ስታዬኝ እሩጣ ወዴኔ መጣች ማታ ምን አባሽ ሁነሽ ነው እንዴዛ ልጁ ላይ ያፈጠጥሽበት አለችኝ እየሳቀች እኔም ሳቄ መጣብኝ ልጁ ግን እንዴት ነው ተመቸሽ አይደል አለችኝ ነገሮች ቶሎ ነው የሚገባት እንዳትፎግረኝ ብዬ ያው ብዙም አይደል አልኳት እና ለዛ ነው ጧት በረንዳ ላይ ቁጭ ብለሽ ያረፈድሽው ባክሽ ገብቶኛል ብለ ሳቀችብኝ እኔም እንዴማፈር ብዬ ቀርቀር ብዬ ሳኩ ሻወር ወስጄ ቢጃማዬን ለብሼ በረንዳ ላይ አንድ መፀሀፍ ይዤ ቁጭ አልኩ ልክ 11 ሰዓት
ላይ የግቢያችን በር ሲከፈት የልቤ ምት ጨመረ ጆን ነው ገና ጫማውን ሳየው አንገቴን ዴፍቼ መፀሀፌን አየሁት መፀሀፉ ያነበኛል እንጂ አላነበውም ጆን ቀጥ ብሎ ወዴኔ መጣ .....

✎ ክፍል ሁለት ይቀጥላል....
💚 @yefeker_tiksoche ❤️
💙 @yefeker_tiksoche💙
​​ ​​           
             :¨·.·¨:
              ያሜናዳብ ♥️
         ┈┈••◉❖◉●••┈🌺

               💢ክፍል 2⃣

እውነትኛ የፍቅር ታሪክ


መፀሀፉ ያነበኛል እንጂ አላነበውም ጆን ቀጥ ብሎ ወዴኔ መጣ ቀስ ብዬ ቀና አልኩ ትዙ አለኝ በቃ እስከ ዛሬ ማንም ሰው ስሜን ሲጠራኝ ዴንግጬ አላቅም እሱ ሲጠራኝ ግን ከተቀመጥኩበት አስነሳኝ ደህና ዋልሽ ብሎ ሰላም አለኝ የእጁ ልስላሴ ለጉድ ነው ከምንም በላይ የገረመኝ ዴሞ
#Boss የሚባል ሽቶ ነው የተቀባው ሽቶው አይደለም ኢትዮጲያ ውስጥ ይቅርና አሜሪካ ውስጥም እራሱ ውድ ነው ታድያ እሱ ማነው አልኩ በልቤ በሀሳብ ውስጥ እያለሁ እጄ ላይ ያለውን መፀሀፍ ተቀበለኝ በቃ ብዙ ወንዶች ጋር እቀራረባለሁ እንዴ ጆን ግርማ ሞገሱ ብቻ የሚያስፈራ ወንድ አጋጥሞኝ አያቅም ውስጤ በፍርሀት እየተንቀጠቀጠ ነው ስትጨርሺ ስጭኝና አነባዋለሁ ብሎ ተናግሮ ሳይጨርስ ውሰደው አልኩት
እህ ሳትጨርሸው አለኝ አንብቤዋለሁ እየዴገምኩት ነው ብዬ ሰጠሁት፡፡ እሺ አመሰግናለሁ ብሎኝ ወዴ ክላሱ ገባ፡፡ አብርው ብገባ ዴስታውን አልችለውም ነበር፡፡ ወዴ ክላሱ ገብቶ በሩን ዘጋና መልሶ ከፈቶ ትዙ ማዘር አለች አለኝ
አሁን ትመጣለች አልኩት እሺ ብሎ መልሶ በሩን ዘጋው፡፡ ለነገሮች ሁሉ ረጋ ያለ ነው፡፡ በዛላይ የገረመኝ ነገር ቢኖር ምንም ነገር ይሁን ካልተጠየቀ በቀር አያወራም፡፡ በዚህ መሀል ግን እኔ ያላሰብኩበት ነገር ውስጥ ገባሁ
በርግጥ ስለ ግል ህይወቱ ምንም ባላውቅም እኔ ግን ስሜቴን ብቻ ማዳመጥ ተያይዣዋለሁ በዚህ መሀል ስለ እሱ ለኳዴኛዬ እነግራታለሁ ግን እንዴወዴድኩት እንድታቅብኝ ስለ
ማልፈልግ ብዙም ለእሱ ያለኝን ስሜት አልነግራትም ሁሌም እሁድ እቤት መዋል አልወድም ነበር ዛሬ ግን ጆን በሁድ ቀን ከደጀ ሰላም ብኋላ እኔ ቤት ነው የምውለው ሲል በስልክ ሲያወራ ሰምቻዋለሁ እኔም አልወጣም አልኩ፡፡ ኤልሲ ዴውላ ካልወጣን አለችኝ ግን በቃ ድርቅ አልኩባት፡፡እሺ በቃ ቤት ልመጣ ነው ስትለኝ በጣም ዴስ አለኝ እናቴም ከዴጄ ሰላም እንዴ ተመለሰች በረንዳ ላይ ቡና ተፈላ እና እናቴ ጆንን ጥሩት አለች፡፡
እኛ ቤት ሁሉም ተከራዮች ምንም ነገር ይሁን አይጠሩም ልክ እንዴ ቤታቸው ነው
የሚገቡት የሚወጡት አክስቴ ጆንን ልጠራው ወዴ ክላሱ ስትሄድ ልቤ ይመታ ጀመር፡፡ በመሀል ኤልሲ መጣች እናቴ ከጓዴኞቼ ሁሉ ኤልሲን በጣም ነው የምትወዳት ጨዋታዋ በጣም ዴስ ይላል በዛው ልክ ምላሷ ግን አይደለም ወንድን ልጂ ድንጋይን ዳቦ ነው ብላ ማንንም ማሳመን ትችላለች፡፡ መታ አጠገቤ ተቀመጠች ከትንሽ ዴቂቃ ብኋላ ጆን
መጣ ቁምጣ ነበር የለበሰው እውነት ለመናገር አካበድሽ እንዳትሉኝ እንጂ ሁሉም ነገሩ ልዩ ነው፡፡ኤልሲ ጆንን ስታዬው እንዴ መርበትበት ስትል ቡናውን እጇ ላይ በትንሹ ደፋችው ቶሎ ብላ ወዴ ቤት ገባችና እሩጣ ሂዳ ክላሴ ጋባች፡፡ እኔም ተከተልኳት፡፡ ከዛ አጭር ጥያቄ ልጠይቅሽ አለችኝ እሺ ጠይቂኝ አልኳት ይሄንን ልጂ ወዴሽዋል ወይስ…ብላ አቆመች አንቺ ያምሻል እኔና እነሱ እኮ
ምንም አይነት ግንኙነት የለንም አልኳት
እሺ የሆነ ነገር በይኝ እኔ ወድጄዋለሁ አለችኝ እውነቱን ለመናገር የሆነ ነገር የነጠቀችኝ መሰለኝ በቃ ውስጤ እርር አለ፡፡ ክላሴ ውስጥ አንዴዬ ትነሳለች አንድዬ ትቀመጣለች በቃ የምትሆነው ነው ያሳጣት እኔማ እነግረዋለሁ አለችኝ አንቺ አብዴሻል እንዴ ማንነቱን የማታቂውን በቅፅበት ያየሽውን
ሰው ከመሬት ተነስተሽ እንዴት እንዴዚህ ታብጂለታለሽ አልኳት፡፡ ትዙ ምንም አትበይኝ ካሰብሽልኝ ሂጂና ንገሪልኝ አለችኝ፡፡ ምን!? አልኳት ዴንግጬ
ወዶ ነው የሀገሬ ሰው አታምጣው ስለው አምጦ ቆለለው ያለው ወይ ካልሆነ ብላ
እንዴ ማጉረምረም አለች እዚህ ጋ ፈራሁ ፊት ለፊት መፋጠጡን ትችልበታለች ትንሽ
በቀልቧ ብትሆን ብዬ እሺ ምን ልበልልሽ ስላት እንዴውም ተይው እኔው እራሴ ብላ
ሳትጨርስ ከክላሴ ወጣች……

✎ ክፍል ሶስት(3) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
💚@yefeker_tiksoche 💜
💙@yefeker_tiksoche ❤️
​​​​                :¨·.·¨:
             
ያሜናዳብ ♥️
         ┈┈••◉❖◉●••┈
   💢
ክፍል 3

እንዴውም ተይው እኔው እራሴ ብላ ሳትጨርስ ከክላሴ ወጣች ደንግጬ ተከትያት ወጣሁ ኤልሲ ያሰበችውን ነገር ከማድረግ ወዴ ኋላ አትልም እንዴምንም ብዬ በሩ ጋ ስዴርስ እጇን ያዝኳት እህህ… አለች ፈገግ እንደ ማለት ብላ እሺ ልቀቂኝ ልቀመጥበት ብላ ሂዳ አጠገቡ ተቀመጠች ነገሮቿ ሁሉ ምንም አላመሩኝም ጆን ፊት ለፊቴ ነበር የተቀመጠው እሷ ታወራው ጀመር ሁሉም እያወራ ነው፡፡ አክስቴ አጠገቤ ተቀምጣ ታወራኛለች እኔ ግን አንዲም አልሰማኋትም ልቤ እነ ኤልሲ ጋ ነው በመሀል አክስቴ እንዴዛ ነው ስትለኝ
እሺ አልኳት፡፡ ሷቋን እንዴት ትቻለው እንዴ ምን ሰምተሽ ነው እሺ የምትይኝ አለችኝ፡፡ሳቅ ብዬ የሰማሁትን ሰምቼ አልኳት ላለመበላት ብዬ እናቴ ጆንን ስለ ወንድምህ ምን አድስ ነገር አለ አለችው አገኘሁት እኮ ሲላት እናቴ ድንግጥ አለች ግን ያው ባለፈው እንዴነገርኩሽ እሱ ያለበት ሁኔታ ያው እንዴ ትናቱ ነው
ሲላት ያው የበፊቱ ነገር በውስጡ ላይ ስላለ ይሆናል አትናዴድበት ልብ እስኪ ገዛ ነው አለችው እስቲ ይሁና አለ በረጂሙ እየተነፈሰ ኤልሲ በቃ አስቃ ልትገለኝ ነው አይን፡፡ አይኑ ውስጥ ልትገባ ምንም አልቀራትም፡፡ የዛን ቀን እንዴምንም ብለን አሳለፍነው እናቴ ጆንን እንዴ ወዴድኩት ሳትጠረጥር አልቀረችም እኔ ሁሌም.እቤት አልቀመጥም ነበር ጆንን ካየሁ ቀን ጀምሮ ግን ለአንድ ሰዓት ያህል እንኳን ውጭ መቆዬት አስጠልቶኛል በዚህ ባህሪዬ ዴግሞ አይዴለም እናቴ ለተከራዮቻችን እንኳን ግርምት ፈጥሮባቸዋል፡፡ እኔ ግን ይሄ ነገር ከቀን ቀን ሌላ ነገር ውስጥ እየከተተኝ ነው እናቴ ያለውን ነገር በግልፅ ጠየቀችኝ ግን ምን ብዬ ልንገራት ጨነቀኝ  እናቴን ምንም ነገር ይሁን ዋሽቻት አላቅም ዋሸኋት ብል እንኳን ቁርስ በልተሻል? ስትለኝ ሳልበላ አዎ በልቻለሁ እላታለሁ እሱንም ቶሎ ከቤት መውጣት ከፈለኩኝ ከዚህ የዘለለ ግን እናቴን ዋሽቻት አላቅም አሁን ግን ወገቤን ያዘችኝ የምላት ጠፋኝ ተይው በቃ አትጨነቂ አለችኝ እና ግን ዴጋግመሽ አስቢበት አለችኝ ውስጤ ጥብብ አለኝ የምለው አጣሁ ጆን ደሞ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀረበኝ መጣ ግን ግልፀኝነቱ ይገርማል ከነገረኝ ነገር ውስጥ ግን ስለ ወንድሙ የነገረኝ ነገር ነው ባ/ዳር ድረስ ለወንድሙ ብሎ እንፈመጣ ሲነግረኝ በጣም ነው የገረመኝ ለወንድሙ እንዴት ይሄንን ያህል መስዋዕትነት ሊከፍል ይችላል አልኩ በልቤ ጆን ከንግግሮቹ ብኋላ ዝምታን ያበዛል ስለ ወንድሙ ከተወለደበት ቀን ጀምሮ እስካሁን ያለውን ነገር ሲነግረኝ እንባዬን እንዴት ልቻለው ጆን ከወንድሙ ጋር በእናት ይለያያሉ በጣም የገረመኝ ወንድሙ ጆንን በጣም ብዙ በደል በድሎታል ታድያ ጆን እንዴት ያንን ሁሉ በደል ይቅር ብሎ እዚህ ድረስ መቶ ወንድሙን ይፈልገዋል? የሚል ጥያቄ ፈጠረብኝ ምን አይነት ልብ ቢኖረው ነው? አልኩ በልቤ የወንድሙን ፎቶ ሲያሳዬኝ ዴርቄ ቀረሁ...ከአንድ አመት በፊት ነበር ፌቨን የምትባል ጓዴኛዬ ጋር የተለያዩት ፌቨን የጆንን ወንድም በጣም ነበር የምትወዴው ግን ምክኒያቱን በማናቀው ምክኒያት ነበር የተለያዩት በዛ ላይ በጣም የገረመኝ ጆን ጋር እንኳንስ የአንድ አባት ልጂ ይቅርና ዘመድ እራሱ አይመስሉም::

ጆን ቢነኩት እንኳት የሚቆሽሽ ነው የሚመስለው ወንድሙ ግን ወዙን የተሰረቀ ነው የሚመስለው ግን ሀብታም ነገር ነው ቆይ ትዙ ግን ምን አስዴነገጠሽ ስታይው? አለኝ የት እንዴማውቀው ነገርኩት ፌቨን የምትባል ጓዴኛዬ ፍቅረኛው እንደነበረች አሁን ግን እንደተለያዩ ነገረኝ ከደስታ ብዛት
አቀፈኝ ግራ ገባኝ አሁን ፌቨን የት ነው ያለችው አለኝ አክስቷ ጋር ሀዋሳ እንዳለች
ነገርኩት በቃ ደስታው ይሄ ነው አይባልም

መጣላታቸው ነው ያስደሰተህ? ወይስ ምንድን ነው? ያስደሰተህ አልገባኝም? አልኩት ሁሉንም ነገር እነግርሻለሁ ብሎ ወደ ክላሱ ፈጠን ብሎ ገባ ሁኔታው ግራ አጋባኝ ተመልሶ መጣ እና ማዘር ትቆያለች እንዴ ሲለኝ አሁን ትመጣለች ግን ጆን ለምንድን ነው ወንድምህ የዚህን ያህል የሚሸሽህ? አልኩት በቃ ሲፈጥረው ለራሱ ጥቅም ካልሆነ በቀር ሰው መቅረብ አይወድም አለኝ ታድያ እሱ
አንተን ካልፈለገህ ለምን አተወውም? አልኩት ሁለተኛ እንድህ እንዳትይኝ አለኝ! ደነገጥኩ ጆን ወንድሙን እንዴ አይኑ ብሌን ነው የሚያዬው እኔማኮ አንተ ይሄንን ያህል እየፈለከው እሱ ካልፈለገህ ብዬ ነው አልኩት ምንም መልስ ሳይሰጠኝ ወዴ ክላሱ ሄደ እኔም ምን አልባት ስለሚወደው ይሆናል በሱ
ዙሪያ ምንም ነገር እንዲወራ የማይፈልገው አልኩኝ በእንድህ እንዳለ እናቴ እንደመጣች ድምጿን ሰምቶ ወጣ ማዘር ብሎ ጠራትና ወደ እሱ ሄዴች......


✎ ክፍል አራት(4) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
ፍትህ ፍትህ ፍትህ !

የ7 አመት ታዳጊ ሴት ልጅን ደፍሮ ከጨረሰ በኃላ አንቆ የገደላት ሲሆን የፈፀመዉ አፀያፊ ተግባር እንዳይታወቅበት በምላጭ እግሯን ቢቆራርጣትም በመጨረሻም ያደረገዉ የቆሻሻ ተግባር ተጋልጧል...

የ25 አመት እስራት የተፈረደበት ሲሆን ለዚህ ቆሻሻ የሆነ ሰዉዬ ግን የሞት ፍርድም ሲያንስበት ነዉ ! 😭

#የፍቅር ጥቅሶች በህጻኗ ላይ በተፈጠረው የግፍ ግድያ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል።

𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚|| @yefeker_tiksoche
𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚|| @yefeker_tiksoche
ሳትኖር ለሞተችው አሳዛኟ ህጻን ላይ በአሰቃቂ ሁኔታ ጥቃት የፈጸመው ወንጀለኛ ላይ ቅጣቱ በቂ እንዳልሆነ እና የተሻለ ፍርድ እንዲፈረድ እየተሰበሰበ ያለውን petition ከታች ባለው ሊንክ እየገባቹ ድምፅ መስጠት ትችላላቹ 👇

https://www.change.org/p/justice-for-heaven-and-her-mother?recruited_by_id=94947080-5cca-11ef-af3a-c38f3884f55d&utm_source=share_petition&utm_campaign=psf_combo_share_initial&utm_term=signature_receipt&utm_medium=copylink

ፍትህ ለሄቨን !
#ያሜናዳብ

ክፍል 4

በእንድህ እንዳለ እናቴ እንዴመጣች
ድምጿን ሰምቶ ወጣ ማዘር ብሎ ጠራትና ወዴ እሱ ሄዴች ምን እንዴ ሚያወሩ አላቅም ብዙ ካወሩ ብኋላ ጆን ተመልሶ ወዴ ክላሱ ገባ ምንም አልገባኝም እናቴ መጣችና አንዴዬ ጆን ጋር ሀዋሳ አብረሽው ሂጂ እና የጓዴኛሽን ጉዳይ ጨርሽለት አለችኝ በቃ ከዴስታዬ ብዛት በቃ መጫህ ብቻ ነው የቀረኝ ቆይ እኔ ምንድን ነው የምሰራው? አልኳት እንዴ መግዴርዴር ብዬ ጆን ወንድሙ የሆነውን ለማወቅ ግዴታ ፌቨንን ማግኘት አለበት አለችኝ ካልሽ እሺ አልኳት ጆን ከሰዓት ወደ አ/አ በረራ እንደ ምናደርግ ነገረኝ እውነት ለመናገር ከእሱ ጋር መሆኔ ደስታው ከቃል በላይ ሆነብኝ ሻወር ምናምን ወስጄ ጨረስኩ እሱም ሁሉን ጨርሶ ወጣ እና ፌቨን ሀዋሳ መሆኗን
አረጋግጭልኝ አለኝ በተደጋጋሚ ስዴውልላት አታነሳም እኔ እና ጆን ወደ ባ/ዳር ኤርፖርት እየሄድን እያለ ፌቨን ደወለችልኝ እና ሳይለት አድርጋ እንደተኛች ነገረችኝ ሀዋሳ እንዳለች ስጠይቃት አዎ እዛ ነኝ ግን ለምን ጠየቅሽኝ? ስትለኝ እየመጣሁ ነው አልኳት በጣም ደስ አላት እና ስደርስ እደውልልሻለሁ ብያት ስልኩን ዘጋሁት ጆንም መኖሯን ሲያውቅ በጣም ተደሰተ እውነት ለመናገር ጆንን አይደለም ሴት ወንድም ጭምር ነው ከላይ እስከ ታች የሚያየው እኔም እራሱ እሱ ጋር በመሆኔ ብቻ የሆነ ደስታ እና ኩራት ተሰማኝ ልክ አ/አ እንደ ደረስን አንዷ መታ ጆን ላይ ጥምጥም አለችበት...

  አሁን ምን ይሉታል የሰው ሰው ላይ መለጠፍ? አልኩ በልቤ አጥብቃ ሰላም አለችው እንዴት ነህ? ሰላም ነህ? መቼ መተህ ነው? በቃ በሰላምታ አዋከበችው አሁን በቅርብ ነው የመጣሁት ብሎ ደበስበስ አድርጎ ሊያልፍ ሲል ታድያ መቼ ነው የምትመለሰው? ስትለው በቅርቡ እመለሳለሁ አንቺ ከዬት እየመጣሽ ነው? ወይስ እየሄድሽ? ሲላት እኔማ ከእስታፑል ትራንዚስት አድርጌ ነው አለችው ነው በቃ አለሁ እንገናኛለን ብሏት ተለያዩ እዚህ ጋ ደነገጥኩ ጆን ከዬት ነው የመጣው? ወዴትስ ነው የሚመለሰው? ልቤ ፍርሀት ፍርሀት አለኝ ብቻ ምንም ጥያቄ መጠየኩ አልፈለኩም በኦላይን ትኬት ስለቆረጠ አልቆየንም ልክ ሀዋሳ እንደገባን ሀይሌ ሪዞርት አልጋ ያዝን
አንድ ክላስ ሆኖ ደብል አልጋ ያለው ነበር የያዝነው ፌቨንን ደውዬ ጠራኋት ብዙም ሳትቆይ መጣች ጆንን ስታዬው ትንሽ አይኗን ጣለችበት ፌቨን በጣም ወፍራለች በፊት ቀጫጫ ነበረች መቼም ሴቶች ስንባል በውስጣችን ስላዬነው ሰው አቋም ማውራት እንወዳለን ሰዓቱ ወዴ 11 ሰዓት አካባቢ ስለ ነበር መክሰስ አብረን በላን እና የሀዋሳ ጎዳናዎች ላይ
ወክ ወጣን ጆን መሀላችን ላይ ነው እውነት ለመናገር እኛ እሱ ጋር ስንታይ ተለጣፊ ነገር ነው የምንመስለው
የሚያዬን መንገዴኛ ፊት ለፊት ማየት አልበቃው ብሎ አልፎ ዞሮ ያየናል
የጆን ቀልድ ፌቨንን ጥርሷን አላስከደናትም በጣም ሳቂታ ናት ጆንም ቢሆን ተጎዘጎዘባት እየመሸ ሲሄድ ፌቨን ወደ ቤት መሄድ አለብኝ ስትል ጆን እራት ካልበላሽ አላት መሄድ አለብኝ ስትል ግድ ካልበላን አላት ቅርብ ሰዓት አይደል መክሰስ የበላነው እንደጠገብኩ ነኝ በዛ ላይ አክስቴ እቤት ደለችም ስትል እሺ ብለን በኩንትራት ባጃጂ ሰዴድናት ጆን ዛሬ እንድህ ከተግባባን ነገ ደሞ የበለጠ እንቀራረባለን አለኝ አዎ ልጂቷ ባህሪዋ አስቸጋሪ አይደለም አልኩት እሱ ጋር በዚህ ሰአት መሆኔ በጣም ደስ ብሎኛል አየሩ ቀዝቃዛ ቢሆንም ፍቅር ስለ ሸተተኝ ግን ቅዝቃዜውን እረስቼዋለሁ ደጋግሜ በመዳፌ እጆቼን ሳሽ ስላዬኝ ጃኬቱን
አውልቆ አለበሰኝ፡፡ የምሆነው አጣሁ አመሰግናለሁ ብዬ ደስታዬን በውስጤ እንደምንም ቻልኩት የያዝነው ሆቴል ስንደርስ ቀጥታ ወደ ሩም ገባሁ እሱም ትንሽ ቆይቶ ተከትሎኝ መጣ የእውነት ለመናገር ባሌ በሆነ ብዬ ተመኘሁ ነይ እራት እንብላ ሲለኝ የቅድሙ እንዳለ ነው ይለፈኝ አልኩት እሺ እኔ እበላለሁ ነይ አብረሽኝ ሁኚ እስከምበላ አለኝ አግኝቼ ነው ብዬ አብሬው ሄድኩኝ ሆቴሉ ይሄ ነው ከሚባለው በላይ ትልቅ ነው በዛው ልክ ይሄ ነው የማይባል ሰው አለ ለካስ ቅድም እኔ ወደ ሩም ስገባ እሱ ወደ ኋላ የቀረው ወንበር እየያዘ ነበር አልኩ በልቤ አስተናጋጁ ልክ እንዳየን ወፈኛ መጣና የተያዘውን ወንበር አሳየን ብዙ ሰው እያየን ነው እኔ የሰው አይን በጣም እፈራለሁ ግን እንዴምንም እራሴን አረጋጋሁ
በተለይ ጆን ወንበር ስቦ ልክ እንዴ ፍቅረኛው ሲያስቀምጠኝ የሆነ ነገር ውስጤ ላይ ተሰማኝ የሚገርመው ነገር……

✎ ክፍል አምስት(5) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
​​​​           
            #ያሜናዳብ
#ክፍል 5

እውነተኛ የፍቅር ታሪክ


ብዙ ሰው እያየን ነው አይን በጣም እፈራለሁ ግን እንደ ምንም ራሴን አረጋጋሁ በተለይ ጆን ወንበር ስቦ ልክ እንደ ፍቅረኛው ሲያስቀምጠኝ የሆነ
ነገር ውስጤ ላይ ተሰማኝ የሚገርመው…
እና በጣም ያሸማቀቀኝ ነገር ቢኖር ፍቅረኛዋ ጋርቁጭ ብላ ስጠቅሰው አይን በአይን አየኋት ከምንም በላይ ያናደደኝ መጥቀሷ ሳይሆን ፍቅረኛዋ ጋር ቁጭ ብላ ይሄን ማሰቧ ትንሽ ውስጤ ላይ ንዴት ነገር ፈጠረብኝ ትዙ ምነው ችግር አለ አለኝ እረ የለም አልኩ ፈገግ ብዬ ፊትሽ ላይ ጥሩ ስሜት አይታይም ሲል እሷ
ናት አልኩ አንገቴን እንደ መድፋት ብዬ ሳቄን መጦኝ እእእ ምንም ማድረግ አይቻልም መቻል ነው አለ እየሳቀ አልበላም ያልኩትንስ አንድ በአንድ በላሁ በዛ ላይ ጫዋታው በትንታ ገሎኝ ነበረ ልክ እንደኛ የተቀመጡ ሁሉ ሰረቅ እያደረጉ ያዩናል እኔም በልቤ ይታደሉታል
እንጂ እይታገሉትም እያልኩ ጫወታችንን ቀጠልን የጠጣሁት መጠጥ ግን በጣም ራሴን ያዘኝ ለካስ ስልፈው የነበረው ቮድካ ነው እኔ በስም እንጂ ቮድካን የት አውቄው እንደ ምንም ብዬ ልነሳ ስል ራሴን ሊያዞረኝ ፈለገ ቀስ ብዬ ራሴን አረጋግቼ ተነሳሁ ክፍል እንደ ደረስኩ አልጋው ላይ ተዘረርኩ ጆን በሁኔታዬ ይስቃል መጠጥ ነገር አትሞክሪም
እንዴ ብዙም እኮ አልጠጣሽም በትንሹ ደፍቶሽ ነበር አለ እየሳቀ እረ ተውኝ ባክህ ይሄንንም እኔ ሁኜ ነው አልኩ ብርድ ልብስ ውስጥ ገብተሽ ተኚ ብሎ ወጣ ወዴት እንደ ሄደ አላውቅም በቃ አልጋው ላይ ራሴን እንኳ ማንሳት አቃተኝ ቆይቶ ሲመጣ እንደ ነበርኩ አገኘኝ በጉልበቱ አልጋው ላይ እንደ መደገፍ አለና ወገቤን እና ጭኔ ይዞ ወደ ላይ አስጠጋኝ በህይወቴ ለመጀምርያ ግዜ ነው ወንድ ልጅ እንደዚህ ሲይዘኝ በቃ ውሀ ሆንኩ ወደ ላይ አስጠጋኝና ጫማዬን አውልቆልኝ
።አስተኛኝ ድንጋጤም አለ ደስታም አለ ብቻ ካስተኛኝ በኋላ ንቅንቅ አላልኩም እሱ ከራሱ አልጋ ላይ ተኛ ጥዋት ስነሳ በጣም ራሴን አመመኝ ጆንን አልጋው ላይ ሳየው የለም ሻወር ቤት ውስጥ እየታጠበ ይሆናል አልኩ ድምፅ ስሰማ ግዜ
ትንሽ ቆይቶ ከሻወር ቤት ሲወጣ ደረቱን ሳይ ልቤ ድንግጥ አለ አንደ ግጥም ትዝ አለኝ ደረትህ ሰፊ ነው እንደ ንጉስ አልጋ ጎንህ ተሸጉጬ ዘላለም አይንጋ እያልኩ እንዳላዜምልህ እንዳልቀኝልህ በልቤ ነው እንጂ መቼ የኔ ሆንክና አለች በለግጥሟ
የእውነት በቃ ተመኘሁት ኧረ አይንሽ ንቀይ አለኝ አፍሬ አንገቴን ደፋሁ ሳቀብኝ ተነሺ ሻወር ግቢና ቶሎ እናግኛት አለኝ እኔም ጨራርሼ እንደ ወጣሁ ክላስ ድረስ ቁርስ መጣልን ሴትን ልጅ በፍቅር ነው ሚንከባከብ ምን ማድረግ አይቻልም ያልክ አንተ ነህ እያልኩ በልቤ እኔም ሚያደርግልኝን ሁሉ መቀበል ጀመርኩ ልክ ረፋዱ ላይ ፌቨንን አገኘናት አምሮባታል ሰላም ስትለኝ ጠጋ ብዬ በጆሮዋ ኧረ ሚስ ሀዋሳ ሆንሽብኝ አልኳት በጣም ሳቀች መጨረሻ ላይ ጆን ያለውን ነገር ነገራት ፊቷ ተለዋወጠ እኔ ወሬያቸው ምንም አልገባ አለኝ ያን ታክል አመት በቤተሰብ ፍቅር ሲሰቃይ የት ነበራቹ
አለች ፊቷን አጥቁራ ሁሌም ቢሆን ወንድሜ ራሱን ጥፋተኛ ማድረግ አይወድም አላት በቃ ብዙ ተጨቃጨቁ
ዛሬም ድረስ እንደዚህ ትወደዋለች እንዴ አልኩ በልቤ እሺ እውነቱን ልንገርሽ እናቱ ለእኔ እንጀራ እናት ናት ሲል ደነገጠች ታድያ እሱ እስከ ዛሬ ድረስ እኮ የአባቴን ልጅ በደልኩት እያለ እኮ ነው ራሱን የሚወቅስ አለች ጆን አንገቱን ደፋ ቆይ ቆይ አንተ ዘንድ አባትህ የሰጠህ ደብበዳቤ አለ እንዴ አለችው ጆን
በድንጋጤ አዋ አላት ከግዜ በኋላ አንድ ሊያደርገን የሚችል ቢኖር ያደብዳቤ
ነው ብሎ ነግሮኛል አለች ጆን ተነስቶ ሁለት እጆቿን ሳመው ደነገጠች እጅህ ላይ አለ አሁን አለችው የለም ግን ደብዳቤው ያለው እኮ texas ነው አለ
ልቤ ለሁለት ስንጥቅ አለ.....


✎ ክፍል አምስት(6) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
#ያሜናዳብ

#ክፍል 6

እጅህ ላይ አለ አሁን አለችው የለም ግን ደብዳቤው ያለው እኮ texas ነው አለ
ልቤ ለሁለት ስንጥቅ አለ የፈራሁት ደረሰ ልቤ ደንግጧል ምክንያቱም ጆን ውጭ ሀገር እንደ ሚኖር ብጠረጥርም እርግጠኛ አልነበርኩም አሁን ግን
ከአንደበቱ ሰማሁ አሜርካ ማለት ለእኔ ከምንም በላይ ነው እስትፋንሴ እስኪ መስል ድረስ ነው የተመኘሁት ፌቨንን ምሳ ጋብዘናት ምናምን መጨረሻ ላይ
ተሰናብተናት ቀጥታ ወደ ባ/ዳር በረራ አለ ተብሎ ሀዋሳ ኤርፖርት ውስጥ ነን እኔ ትኬቱን መቼ ነው የቆረጠ እላለሁ ግን እሱ በኦንላይን ኢንተርኔት ጨርሶታል በዚህ መሀል ወደ ባ/ዳር እንደ ገባን እሱ ኩንትራት የያዘው ሹፌር ነበር እየጠበቀን ነው እኔ ግራ የገባኝ መቼ ደውሎ እንደ ጠራው ነው ትኬት ሲቆርጥ አልጋ ሲይዝ
በቃ ብዙ ነገሮችን ሲያደርግ አላየውም ግን ተደርጎ አየዋለሁ እቤት እንደ ደረስን አክስቴን ሰላም ብሏት ወደ ክፍሉ ሄደ እናቴ ቤት የለችም ክላሴ ውስጥ ተኝቼ ሁሉም ነገር እየገረመኝ ነው በቃ እሱ ጋር በአንድ ቀን ውስጥ ይሄን ታክል ስንቀራረብ ከምንም በላይ ነው ደስ ያለኝ
ቢጃማ ለብሼ ኤድፎኔን ሰክቼ በረንዳ ላይ ቁጫ አልኩ እሱም ጃኬት ነገር ደርቦ ወጣ ስንተያይ ፈገግ አለ ትዙ ሻይ ቡና አለኝ አመስግናለሁ አልኩ ግድ የለም እንደ ትናቱ አትሆኚም አለኝ ሳቄን
ለቀኩት ይዘህልኝ ና አልኩ እረ ባክሽ ከፈልግሽ አትመጪም ብሎ ነይ ቶሎ
ነው ምመለስ ብሎ ወጣ የእውነት ለመናገር ልቤ አብሮት ወጣ በቃ አስጠላኝ ከእሱ ለደቂቃም ቢሆን
መለየትን አልፈልግም በፍቅር እንደ ወደኩ አውቂያለሁ ግን በቃ ምሆነው አጣሁኝ እስኪ መጣ ብዬ ተኛሁኝ ከደቂቃዋች በኋላ እናቴ መጣች ስታየኝ ደስ አላት
የሄዳቹበት ጉዳይ ተሰካላቹ አለች አዋ አልኳት እና ጆን የት ሄደ አለች አሁን
ቅርብ ሰአት ነው የወጣ እልኳት ሀሳቤ ጆን ላይ ነው ብቻ በቃ አላውቅም ትንሽ ጋደም እንዳልኩ እንቅልፍ ይዞኝ ሄደ ለራት ነው ያስነሱኝ ወጥቼ የጆንን ክላስ ሳየው መብራቱ በርቷል በቃ የእውነት ለመናገር በሰአታት ውስጥ ናፍቆኛል ቀጥ ብዬ ወደ ክፍሉ ሄድኩ ሳንኳኳ አቤት አለ ገርበብ አድርጎ ነበር የዘጋው ገባሁኝ እንደ ልማዱ ቁምጣ ለብሶ ወንበሩ ላይ እግሩን ዘርግቶ ለፕቶፑን ይነካካል ትዙዬ አለኝ እቤቱ ግቢያችን አልመስለኝ አለ ሲበዛ በጣም ይስባል ብዙ ዕቃ የለውም ግን ያሉት
የዕቃዋች አቀማመጥ በጣም ልዩ ነው አክስቴ ከውጭ ስትጠራኝ ሰምቼ ወጣሁ ወደ ላይ ቤት ስሄድ ቡና ተፈልቷል
አክስቴ ጆንን ጠራችው ሆነ ብዬ ወደ ውስጥ ገባሁና ጆን ሲመጣ ጠብቄ እራቴን ይዤ ወጣሁ ጆን ጋር ቁጭ አልኩ
እኔ እልበላም አለ ማን ብላ አለህ አልኩ ሳቀብኝ እናቴ ከውስጥ ስትመጣ አንቺ ብላ አትይውም ምን ሆንሽ አለችኝ
አልበላ አለኝ አልኳት የግዱን በላ በቃ እያጎረሰኝ ነው የጨረሰ ነገውን ጆን አ/አ ልሂድ አንድ መጨረስ ያለብኝ ጉዳይ አለ ሁለት ቀን በኋላ እመለሳለሁ ሲለኝ ወገቤ ቁምጥ አለ…


ይቀጥላል....__ ! ! !


✎ ክፍል ሰባት(7) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
​​​​           
             :¨·.·¨:
                ያሜናዳብ
         ┈┈••◉❖◉●••┈🌺

               💢ክፍል 7⃣

💢እውነትኛ የፍቅር ታሪክ💢
°
°
°
ጆን አ/አ ልሂድ አንድ መጨረስ ያለብኝ ጉዳይ አለ ሁለት ቀን በኋላ እመለሳለሁ ሲለኝ ወገቤ ቁምጥ አለ በቃ ምለው ሁላ ጠፋኝ እንደ ምንም ብዬ እሺ ዛሬ እኔ ጋር
ዋል አልኩት ትንሽ ካቅማማ በኋላ እሺ በቃ ግን ማታ ላይ እሄዳለሁ አለኝ ደስ ብሎኝ እሺ አልኩ በቃ ጆን ካየሁበት ቀን ጀምሬ ብዙ ጓደኞቼ ጋር ተላያይቻለሁ ድሮ ያሉበት ድረስ እሄድ ነበረ እሱ ከመጣ በኋላ ግን አይደለም እነሱ ዘንድ ልሄድ ይቅርና ፈልገውኝ ራሱ አጡኝ ድንገት
ስደውልላቸው ዛሬ ከየት ትዝ አልንሽ
ወይስ ምንድ ነው ጉድ ኤልሲ የነገረችን ነገር እውነት ነው እንዴ አሉ ሙድ እየያዙብኝ እሱን ተውትና የት ነው ያላቹ ስላቸው አዶቭ ካፌ ነን አሉ ጆንን ይዤው ሄድኩ ልክ እንደ ደረስን ሲያዩን ጓደኞቼ ጆንን ሲያዩ ሁሉም ፀጥ አሉ በቃ ግርምትም አለ ብቻ ስሜታቸውን ለመግለፅ ትንሽ አንገራገራቸው ሁሎችንም አስተዋወኩት እናቴ ሰደውልልኝ ከነሱ ትንሽ ራቅ አልኩኝ ትንሽ ቆይቼ ስመለስ ጆን በሳቅ ሊገላቸው ነው ከምንም በላይ ደግሞ ደንግጬ የቆምኩ አመለ ምትባል ጓደኛችን ስትስቅ ሳያት ነው በህይወቴ አንድም ቀን አይደለም ስትስቅ ፈገግ ስትል እንኳ አይቻት አላውቅም ይሄ ልጅ ምን አስነካት አልኩኝ እኔ ብቻ አደለም እነሱም አስገርሟቸዋል ምንም አይነት ቀልድ አያስቃትም ብቻ የዛሬው ሁኔታዋ በጣም ተለየብኝ በዚህ መሀል ኤልሲ ከሩቅ ስትመጣ አየኋት ልክ ጆንን ስታይ ቆመች በቃ እንደ ምናምን
አደረጋት በኮሪደሩ ጥግ ይዛ መጣችና በጆን ጀርባ ሂዳ ግጥም አድርጋ ጉንጩን ሳመችው የእውነት ለመናገር በጥፊ ብላት ደስታዬን አልችለውም አንቺ ውልብልብ አላት ብናደድም ሳቄን ግን
አልቻልኩም በዚህ መሀል አጠገቤ የተቀመጠች ጓደኛዬ ወደ ጆሮዬ ጠጋ ብላ ዘንድሮ በለስ ቀንቶሻል ደግሞ ስትፈዢ አስበይው አሉሽ አለችኝ አሳቀችኝ የእውነት በቃ ወደ ውሰጤ ተመለከትኩ ልቤ ያለ እሱ ባዶ ሁና አገኘኋት ብቻ ፈጣሪ ይርዳኝ ምን ብዬ እንደ ምነግረው ሳስብ እንኳ ይጨንቀኛል ቀኑን ሙሉ እኛ ጋር ዋለ ጓደኞቼ የማይጠይቁት ጉድ የለም እሱም ለመመለስ ደከመኝ አይልም በዛ ላይ በቃ ጆን ማለት ልዩ ሰው ነው አብረን ውለን ልክ ቤት እንደ ገባን ትንሽ ሻንጣ ነገር ይዞ ወጣ እኔስ ምሆነው አጣሁኝ ጩሂ ጩሂ አለኝ ግን አትሂድ
ማለት አልችልም እናቴ በስተ ጀርባ ነበርች ቻው ብሏት ወጣ የክላሱን ቁልፍ ሰጠኝና ነገ እንድታፀጂው አለ እየሳቀ በይ ቻው ሲለኝ እንባዬ ሲተናነቀኝ ይታወቀኛል በሩ ዘንድ ደርሶ ተመልሶ ሲመጣ እንባዬ ይፈሳል እንቺ ያምሻል እንዴ ሁለት ቀን እንጂ ሁለት አመት እኮ አላልኩም ብሎኝ ግንባሬን ስሞኝ ሄደ ኡፍ ምን አለ የወዱት ሰው ለደቂቃ ባይለዩት አልኩ በልቤ ክላሴ ገብቼ ተኛሁ በቃ ከዛን ቀን በኋላ ጆን በጣም ነበር የናፈቀኝ ሁለት ቀን ሞላ ግን አልመጣም እኔስ ምሆነው አጣሁኝ ትዝ ሲለኝ የክላሱን ቁልፍ ሰጦኛል ቁልፉን ፈልጌ አግቼ እንደ ምንም ሩጬ ክላሱ ገባሁ ቦርሳ ውስጥ ያለውን ሹራብ ሳወጣው ምንም ነፍስ የለኝም በቃ እንደ
እስትፋንስ አፍንጫዬ ጭምቅ አደረኩት ውስጤ ግን እኮ በስንቱ ታዝቦኛል በቃ ጠረኑ ወደ ውስጤ ሲገባ ፈጣሪ የሚያውቀው በቃ እኔ ጋር ያለ መሰለኝ ጆን ይመጣል ብዬ ዛሬ ነገ ብልም የለም ሳምንት ሆነው ሳይመጣ....




✎ ክፍል ስምንት(8) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
:¨·.·¨:
                ያሜናዳብ
         ┈┈••◉❖◉●••┈🌺

               💢ክፍል 8

💢እውነትኛ የፍቅር ታሪክ💢


በቃ ጠረኑ ወደ ውስጤ ሲገባ ፈጣሪ የሚያውቀው በቃ እኔ ጋር ያለ መሰለኝ ጆን ይመጣል ብዬ ዛሬ ነገ ብልም የለም ሳምንት ሆነው ሳይመጣ....እብድ ሆንኩ በራሴ ያዘንኩኝ እናቴን ምንም ስትለኝ እሺ ምላትን ዛሬ ግን እሷ ጋር ጭቅጭቅ ሆነ ስራዬ በቃ ያለ እሱ መኖር እንደ ማልችል ውስጤ አምኖ ተቀብሏል ያፈቀሩትን ሰው በቀላል እንዴት ከውስጥ በቀላል ማውጣት ይቻላል የደረሰበት ነው ጉዳትቱን የሚያውቀው ኤልሲ እንደ ምወደው አውቃለች በቃ ልታፅናናኝም ብትሞክርም ውስጤ ግን ይሄ ነው ለማለት ይከብዶኛል ግን ግፍ ይሆን አልኩ በልቤ ስንት ወንድ እንዳል ለመነኝ ዛሬ እኔ በተራዬ እለምናለሁ ለምኜም አላገኘሁ ሁሌም በአንድ ነገር አምናለሁ ግዜ ሁለት ነው አንድ ለእኔ አንድ በእኔ ለእኔ ሲሆን ሰው ላይ ኮራሁ በእኔ ሲሆን
ግን እኔ ራሴ ለመንኩ በዚህ እንዳለ ሁለት ሳምንት አለፈው እናቴ ግን የሆነ የምታውቀው ነገር እንዳለ ልቤ ይጠረጥራል በቃ ሁሌም አትጨነቂ ይመጣል ነው ምትለኝ ከሁለት ሳምንት በኋላ ጓደኞቼ እቤት መጡ ጆን ከሄደ በኋላ ከግቢ አልወጣሁም በግድ ይዘውኝ ወጡ ሁሌም ወደ ምንዝናናበት ባህር ዳርቻ ሄድነ በቃ ሁሌም ወደ ዚህ ቦታ ስመጣ ውስጤ እረፍት ያገኝ ይመስለኛል ብቻ ውስጤን በጣም ደስ ይለዋል በዚህ መሀል ጓደኞቼ አንድ ልጅ አስተዋወቁኝ ሊያወራኝ ዳር ዳር ይላል ከአድናቆት ጀመረ እኔ በህይወቴ ሰው ሲክበኝ አልወድም ስለ ራሱ ሳልጠይቀው
ይለፈልፍ ጀመረ ጓደኞቼ ከእኔ ትንሽ ራቅ ብለዋል ውሀው ውስጥ ይሮጣል እኔ ደግሞ ሁሌም ባህር ውስጥ እግሬን ነክሬ
መቀመጥ እወዳለሁ አጠገቤ ቁጭ ብሎ እያወራ ነው ግን ረስቼዋለሁ ምን አልከኝ ስለው የት ሄድሽ አለኝ ፈገግ እያለ ይባስ በነፃ ሀሳብ በትንሽ ትዝታ በብዙ ፍቅር ሸኘኝ ጆንን ከፊቴ አመጣው ካልተጠየቅ የማያወራው አንቺ በሎ እጄን ነካ አደረገኝ ከሀሳቤ ቀሰቀሰኝ እና ባንክ ቤት ነው ምሰራው እልሻለው አለ ፈገግ እያለ
በምን እንደ ጀመረው ራሱ አላውቅም በዚህ መሀል ብዙም ባይሆን ድብርቴ ለቀቀኝ በሳምንቱ ሁሉም ልደቴን ሊያከብሩልኝ መጡ የእውነት ለመናገር በየ አመቱ ልደቴን ሳከብር ከምንም በላይ
ደስተኛ ሁኜ ነው ዘንድሮ ግን ወደ ህይወቴ መጦ ሳላስበው በሄደ ሰው ትንሽ ተከፍቷል ባለፈው ያስተዋወቁኝ ልጅም
መጧል ነገሩ ትንሽ ግራ ቢገባኝም ምንም አላልኩም ሁሉም ያመጣልኝን ስጦታ ይሰጡኛል የዛሬ አመት ከማልረሳ ውስጥ ኤልሲ በጣም ትልቅ ካርቶን ውስጥ አንድ ደስታ ከረሜላ አድርጋ ሰጣኛለች ክርቶኑን
ላየው ግን ሌላ ነገር ነው የሚያስመስለው ከሁሉም ጓደኞቼ በላይ እሷ የምትሰጠኝ ነገር ይነስም ይብዛም ምንም ይሁን ብቻ
ያጓጓኛል በዚህ መሀል ሁሉም ከሰጠኝ በኋላ የእሷን እየጠበኩ እያለ ትንሽ የተጠቀለለ ነገር በእጇ ይዛ መጣች አይንሽን ክደኚ አለችኝ ልክ እንደ ከደንኩ ከሰከንዶች በኋላ የሆነ ጠረን አፍንጫዬን
አወደው አሁን ለመጨሁ ትንሽ ቀረኝ በቃ ውስጤ በሰከንድ ውስጥ ልቤ የሆነ ስሜት ሲሰማኝ ይታወቀኛል ሁሉም ዝም አለ አይንሽን ግለጪ ስትለኝ ቀስ ብዬ
አይኔን ስገልጠው.......

✎ ክፍል ዘጠኝ(9) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
:¨·.·¨:
                ያሜናዳብ
         ┈┈••◉❖◉●••┈🌺

               💢ክፍል 9

💢እውነትኛ የፍቅር ታሪክ💢
ልቤ የሆነ ስሜት ሲሰማኝ ይታወቀኛል ሁሉም ዝም አለ አይንሽን ግለጪ ስትለኝ ቀስ ብዬ አይኔን ስገልጠው ባለፈው ያስተዋወቁኝ ልጅ ፊቴ ላይ ተደቅኗል ነገሩ ግራ ገባኝ ትዙ ወድጄሻለሁ እባክሽን አብረን እንሁን አለኝ አንቺም በብቸኝነት ነው ያለሽው እኔም እንዳንቺው አለኝ በጥፊ ብለው ደስ ባለኝ ነበር እንደ ምንም ራሴን አረጋግቼ እኔ እኮ የራሴ የምወደው እና የማፈቅረው ሰው አለ በዛ ላይ እኔ እና አንተ የተዋወቅ ነው ትናት ነው አልኩት ምንም አለለኝም እንደዛም እያወራሁት
አፍንጫዬን ያወደኝ ጠረን አሁንም አፍንጫዬ ላይ ነው በዚ መሀል የሙዚቃውን ድምፅ ከፍ አደረጉት ሁሉም በየ ራሱ ጥሩ ሙድ ላይ ነው ኤልሲ ከውጭ ስልክ ስታወራ ቆይታ ወደ
ውጭ እንድወጣ በእጇ ምልክት ጠራችኝ
ስሄድ አናግሪው ይፈልግሻል አለችኝ ማነው ልላት ስል ስልኩን ሰጣኝ ዘላ ገባች ደጋግሜ ሄሎ ስል ዝም ነው መልስ የለም ተናድጄ ስልኩን ልዘጋ ስል ትዙ አለኝ ጆን ነው እጄ ስልኩን ለመያዝ ከበደው ማውራው ጠፋኝ ደህና ነሽ ግን አለኝ ምን አድርጌ ነው ግን አልኩት
ጫጫት ነገር አለ እስቲ ትንሽ ተንቀሳቀሺ አለኝ ሩጬ ክላሴ ገባሁ እንኳን ተወለድሽልን አለ በቃ የእውነት ለመናገር ከምንም በላይ ደስ አለኝ እንባዬ ይፈሳል የተወሰነ አወራሁትና ማታ እደውልልሻለሁ ወደ ፕሮግራምሽ ተመለሺ አለኝ ደስታው እጥፍ ሆነልኝ በቃ ጆንን ካገኘሁ በኋላ ያዩኝ ራሱ ምን አገኘሽ እስኪሉኝ ደስ አለኝ
ቀኑን ደስ በሚል ሁኔታ አሳለፍን ግን ሚገርመ ው ቀን ላይ አፍንጫዬን ያወደው መአዛ አስካሁን አልተረሳኝም ማታ ለይ ጆን ደውሎልኝ ብዙ አወራን በቃ የልደቴን ቀን ተከፋሁ ብዬ ነበር ግን ጭራሽ ተስምቶኝ የማያውቅ አይነት ስሜት ተሰማኝ ልደቴን በዚም በዚያም ብዬ አሳለፍኩ ለጆን ግን ከዛን ቀን በኋላ በተደጋጋሚ ብደውልለት ስልኩ አይሰራም በቃ ከአይኔ ከተለየ አርባ አምስት ቀን ሞላው እኔ ግን ለሰከንድ ከውስጤ አላወጣሁትም ብቻ ቀናት ተቆጠሩ እኔም በመሀል ሁሉም ነገር
አስጠላኝ በቃ አምላኬን አማረርኩ ምን ብበድል ነው ብዬ አለቀስኩ ሁሉም ነገር ግራ ገባኝ ሰው የወደዱት ከአይን በራቀ ቁጥር ይረሳል ይባላል ታድያ ምነው የኔ በረታብኝ ተቃራኒ ሆነብኝ እቤት ማንንም ማውራት አስጠላኝ ልክ ጆን ጋር በተለያየን ሁለተኛ ወሩ በቃ ቀኑ ትዝ ሲለኝ እንደ ማበድ አደረገኝ ጥዋት ላይ ክለሴን ዘግቼ ማንም እንዳይጠይቀኝ ብዬ ተኛሁ ቢቆፍ ቁፍ ቢለምኑኝ አልሰማ አልኩ እንባዬ እስኪ ደርቅ አለቀስኩ ቀኑን ሙሉ ክላሴን ዘግቼ ወደ ማታ ላይ አክስቴ በቃ አለቀሰችብኝ አትልፊ ሂጂ አልኳት ልክ ከምሽቱ ሁለት ሰአት ላይ ከቀኑ በተለየ በሩ ተንኳኳ ዝም አልኩ አሁንም ተንኳኳ ዝም አልኩ እረ ትዙ ምንሼ ነው አለኝ የጆን ድምፅ ነው በመብረቅ የተመታሁ
መሰለኝ በቃ ለመናገርም ከበደኝ እንደዛ ተኝቼ የዋልኩትን ከአልጋዬ ላይ ተስፈንጥሬ ተነሳሁ ቀስ ብዬ በሩን ስከፍተው ጆን ከፊቴ ላይ ቁሟል ዘልዬ ተጠመጠምኩበት በቃ በጣም ደስ አለኝ ደረቱ ላይ ማስቲሽ ሆንኩበት በይ ልብስ ቀይሪና እራት ልጋብዝሽ አለኝ ብቻ ደነግጫለሁ እሺ ብዬ እስክ ቀይር በጓሮ እናቴ ዘንድ ሂዶ እግሯ ስር ቁጭ ብሎ
ያወራል በቃ እሱ ካለ ግቢው ሰላም አለው ተያይዘን ወጣን በጣም ነበር ደስ ያለኝ እራት ጋብዞኝ ትንሽ መጠጥ ነገር ጠጥቼ ለው ብያለሁ በተላይ ስጠጣ ሁሌም ይስቅብኛል ምናለ የሱን ሳቅ
ለማየት ስል ሁሌም በሰከርኩ እላለሁ በውስጤ ልክ ወደ አራት ሰአት አከባቢ ተመለስን ጆን ሰላም እደሪ ብሎ ወደ ክፍሉ ገባ እኔ ግን ንፋስ እንዲ ልቀበል ብዬ በረንዳ ላይ ቁጭ አልኩ ሰአቱ እየሄደ ነው ልክ ሳስነጥስ ጆን ወጣ ምነው ምን ሆንሽ ብሎ ወደ እኔ መጣ አጠገቤ ቁጭ አለ እረ ተነሽና ግቢ አለኝ መልስ አልሰጠሁትም ብቻ በስስት አይኑን ነው የማየው አንቺን እኮ ነው ምልሽ አለኝ ፈገግ ብዬ ሳመኝና ልግባ አልኩት እረ ድፍረት ሚስቴ እንዳሰማሽ አለኝ ቆሌዬን ሳይሆን ቆዳዬን ነው ግፍፍ ያለ ምን ማለት ፈልጎ ነው እንዴ እኔስ አልኩ
በልቤ ማወራው ጠፋኝ ምነው ደነገጥሽ አለኝ.....


✎ ክፍል አስር(10) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
:¨·.·¨:
                ያሜናዳብ
         ┈┈••◉❖◉●••┈🌺

               💢ክፍል 10

💢እውነትኛ የፍቅር ታሪክ💢

ምን ማለት ፈልጎ ነው እንዴ እኔስ አልኩ
በልቤ ማወራው ጠፋኝ ምነው ደነገጥሽ አለኝ ልክ ከምሽቱ ሁለት ሰአት ላይ ከቀኑ በተለየ በሩ ተንኳኳ ዝም አልኩ አሁንም ተንኳኳ ዝም አልኩ እረ ትዙ ምንሼ ነው አለኝ የጆን ድምፅ ነው በመብረቅ የተመታሁ መሰለኝ በቃ ለመናገርም ከበደኝ
በልቤ ማወራው ጠፋኝ ምነው ደነገጥሽ አለኝ ራሴን አለመሳቴም እኔ ሁኜ ስለው ስቆ ስቀልድሽ ነው ብሎ ግንባሬን ሳመኝና ከተቀመጥኩበት አስነሳኝና ወደ ቤት
አስገባኝ እኔም ልቤ ቅር እያለኝ ገባሁ ግን በቃ ማታውን አልተኛሁም ሚስቴ ያለው ነገር ሲከነክነኝ አደረ ወደ ጥዋት አከባቢ እንቅልፍ ጣለኝ ወደ አምስት ሰአት ላይ ተነሳሁ ልክ እንደ ነቃው ወደ ጆን ክላስ ነበር የሄድኩ ግን ዝግ ነው ቅር አለኝ አክስቴ ካኋላ እያየችኝ ነበር ሳቀችብኝ ፎንቃ ይሉሻል ይሄን ነው አለች እየሳቀችብኝ እኔም ሳቄ አመለጠኝ ቀን ላይ ደውዬለት ትንሽ ስራ ይዤ ነው እንደ ጨረስኩ እመጣለሁ አለኝ እኔም ቀኑን ሙሉ ስጠብቀው ዋልኩ ማታ ላይ እቤት እራት አብረን በላን ልክ በዚህ መሀል ከሳምንት በኋላ ነገ አንድ ማስተዋውቅሽ ሰው አለ አለኝ ደስ ይለኛል አልኩ ነገውን ልክ ወደ ማታ አከባቢ ደውሎ ግራንድ ሚባል ሆቴል ጠራኝ እኔም ለባብሼ ሄድኩ ሆቴሉ እንደ ደረስኩ እንግዳ ማረፍያ ክፍል ውስጥ ሁኜ ደወልኩለት እንደ መጣ ይዞኝ ወደ ላይ ወጣ ቦታው በጣም የሚያምር ግራፊክስ አለው የሆነች ልጅ ጀርባዋን ሰጣ ተቀምጣለች ልዩ አላት ወዬ ብላ ዞር አለች እረ በፈጣሪ አልኩ በልቤ ደነገጥኩ በጣም ቆንጆ ልጅ ናት ይሄ ነገር እንዴት ነው አልኩ በልቤ
የዘር ነው ወይስ ተፈላልገው ነው የተገናኙ አልኩ ትዙ ያልኩሸ እሷ ነው ሲላት የምርህን ነው ብላ ተነስታ ሳመችኝ እኔም ውስጤ ትንሽ ደስ አለኝ ሁሌም የማያውቁን ሰዋች ስለ እኛ በተነገራቸው መጠን ነው በህሊናቸው ሊስሉን የሚችሉት ጫዋታዋ ደስ ይላል ልክ እንደ
ስሟ ልጅቱም ልዩ ናት ከሰአታት በኋላ እራት በልተን ጆን ወደ መታጠብያ ክፍል ሲሄድ እንድ ጓደኛዋ መጣች አንቺ እንቅልፋም ተነሳሽ አለቻት ሰላም ብላኝ ቁጭ አለች ከእንቅልፏ እንደ ተነሳች ያስታውቅባታል ፍቅር የት ሄደ አለች አለ ይመጣል አለቻት ግራ ገባኝ ማንን ነው
ፍቅር ብላ የጠራችው እልኩ በውስጤ ጆን እንደ መጣ ፍቅር አለችው ቲቲ ተነሳሽ አላት እናቴ ድረሽ አልኩ እንዴት እንደዛ ብላ ትጠራዋለች ፍቅረኛዋ ቢሆን እንጂ ብዬ በቃ ተረበሽኩ ስልኬ ሚሴጅ
ሲገባልኝ አይቼ ከወንበሩ ላይ አነሳሁት እረ አትናደጂ ትዙሻ ይላል ጆን ነው ቀና ብዬ ሳያው ጠቀሰኝ በቅፅበት ያሁሉ ንዴቴ ጠፋ ሰዓቱ እየመሸ ስሄድ ጆን እኛ እንሂድ ሲል.....

✎ ክፍል አስራ አንድ(11) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
2024/09/21 12:35:55
Back to Top
HTML Embed Code: