Telegram Web Link
💌🌹🕊

➥ፍቅር የራሱ የሆነ ውበትና ዜማ አለው
ያፈቀረ እንጂ ማንም የማይሰማውღ
💕.............🍃🌹🍃..............🍃

⇘ፍቅር እንደ ጦርነት ነው፤ ለመጀመር
ቀላል ነው፤ ግን ለመጨረስ በጣም
አስቸጋሪ ነው።

    ❝ዓይኖቼን ጨፍኜ አንቺን አስባለሁ፤
      ዓይኖቼን ገልጨ አንቺን አስባለሁ፤    
         አንቺም እያሰብሽኝ እንደሆነ
             ማወቅ እፈልጋለሁ።❞

     ➦አምነህ ልብህን ለሰጠኸው ከዛም
     በከዳህ ሰው ላይ ፈፅሞ እንዳታዝን፤
     ምክንያቱም ሰውየው አንተን ሳይሆን
     እራሱን ነውና የከዳው፡:

@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche

⇘ፍቅር ምን እንደሆነ ስታውቅ ነው
ለዋጋው መስዋዕት የምትከፍለው።
          
            #share
Forwarded from 🇪🇹ETHIO AIRDROP (Mame 🕊)
ቴሌግራም ልክ እንደ ቲክቶክ ብዙዎችን ባለሀብት ሊያደርግ ነው በተጨማሪም ቴሌግራምን ተወዳጅ ሊያደርጉት ከሚችሉ ነገሮች አንዱ ይህ ነው 🤩

አሱም MAJOR Telegram Stars ይሰኛል

እንደሚታወቀው TikTok በፈጠረው የቲክቶክ ኮይን ጊፍት አማካኝነት ብዙዎቹ ህይወታቸውን እንዲቀይሩ ረድቷል።

ቴሌግራምም የቲክቶክን ፈለግ በመከተል አዲስ Telegram Stars የተሰኘ Gift Coin አምጥቷል ይህም የቴሌግራም ክሬተሮች የተሰጣቸውን ጊፊት ወደ ገንዘብ መቀየር እንዲችሉ ተደርጓል

ቴሌግራምም ይህንን ነገር ለማስተዋወቅ Major በተሰኘ Airdrop መሰል ነገል መጥቷል ይህም ሰው invite በማድረግ በቀላሉ የቴሌግራም Star Coin መስራት እንድችሉ ያደርጋል።

በተጨማሪም Verify የሆነ Airdrop ነው ከመጣም 5 ቀን አልሆነውም ይህንንም በደንብ የሰራ ሰው የTON ሽልማት እንዳለው አሳውቀዋል

1 ሰው invite ስታደርጉ 15 star ታገኛላቹ




ይህንን እንደ ኤርድሮፕ እንዳትቆጥሩት ሊስት ብሎ ነገር የለውም ትክክለኛ ገንዘብ ነው ስለዚህ Guys አሁኑኑ ጀምሩት💥👇🏻

https://www.tg-me.com/major/start?startapp=815892887
https://www.tg-me.com/major/start?startapp=815892887
https://www.tg-me.com/major/start?startapp=815892887
​​​​​​            💊🔮አፈቅርሻለው💍

      አንድ ልዩ ሴት አለች👸ስለ እውነት ለመናገር በጣም ነው የምታሳሳኝ😍በእውነት  በጣም እኮ ነው ማፈቅራትግን እሷን ማጣት በጣም ያስፈራኛል😩ስለሷ አጠይቁኝ ልገልፃት አልችልም💓ለማለት አይደለም ከ ልቤ ነው
           🌺🌺
መልኳን ነው??? በጣም ቆንጆ ናት😍ልዕልት👰ስብዕናዋን👸የምርም ሴት ናት👸በጣም መልካም አስተዋይ ሴት ናት ፍቅሯ ልዩ ነው😍
 
የኔ ውድ በጣም አፈቅርሻለው
ይቅርታ አጥፍትሀል አላጠፋህም አትበይኝ ብቻ ይቅርታ ፍቅር💓
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
           
   #ሼር

         
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
💔🥺#_አደራ_ሼር_አድርጉ🙏
😘ያበደው ፍቅሬ😘

ክፍል 1⃣

ትቼው ልሄድ ነው። በቃ ልሄድ ነው የመጨረሻ ውሳኔዬን ወስኛለሁ የምሄደው እንደ ሌላው ጊዜ ጥላቻንና ክህደትን ሽሽት አይደለም...  ፍቅርን እንጂ።
እናም በሀሳብ እየዋዠኩ ደብዳቤ ልፅፍለት ወሰንኩ ቢያንስ ምክንያቴን ማሳወቅ አለብኝ አይደል... ደግሞ ጠፋች ብሎ ሀገር ምድሩን ነው የሚያምሰው...

መፃፍ ጀመርኩ

አንዳንዴ ልቋቋመው ከምችለው በላይ ይሆንብኛል። ፍቅርህ፣ ስስትህ፣ እንክብካቤህ፣ አንተን ትተህ ለኔ ደስታ መድከምህ፣ ከቃላት ጋጋታ ይልቅ በተግባር የምታሳየኝ መውደድህ በአጠቃላይ ሁሉም ነገርህን መቋቋም ያቅተኛል።

ሰው እንዴት ይህን ያክል ሰውን ሊወድ ይችላል እንዴትስ ሁሉ ነገሩ ፍቅር ብቻ ይሆናል ፍቅር... ፍቅር... አሁንም ፍቅር.... አንተጋ ያለው ፍቅር ብቻ ነው እኔጋ ደግሞ....

ከዚህ በላይ መቀጠል አልቻልኩም በሀሳብ ወደ ተገናኘንበት ጊዜ ጋለብኩ....

ከምናምን አመት በፊት በክህደት የተሰበረ ልቤ ላይ ትኩስ ሀዘን ተደምሮበት ግራ ቀኜን ሳላይ እግሬ ወደመራኝ ስጓዝ ሲጥጥ ብሎ እግሬ ስር የቆመ መኪና ከሀሳቤ አነቃኝ... አልደነገጥኩም እንደውም ተናደድኩ ለምን ፍሬኑን ያዘው? ለምን አልገጨኝም? ብሽቅ... የማይገኝ እድል አስመለጠኝ.... ይህን ሁሉ የማስበው ከመኪናው ወርዶ በአካባቢው ከነበሩ ሰዎች ጋር የስድብ ናዳ ሲያወርድብኝ ነው። "ያምሻል.... እያዬሽ አትሄጂም..... መሀል አስፓልት ላይ ምን ትሰሪያለሽ...... እብድ ነሽ..... ጦስ ውስጥ ከታው ነበር........." አይገርምም አንድ እንኳን ችግሬን ለማወቅ የፈለገ ምን ሆና መሀል አስፓልት ላይ ተገኘች ያለ ሰው የለም.... አስመሳይ ብቻ።

እጄን ይዘው ወደዳር ወስደውኝ የጀመሩትን ስድብ ያዘንቡብኝ ጀመር... ለትንሽ ሰከንድ አየሁዋቸው... ሳላስበው ቃል ከአፌ ወጣ 'ዞር በሉልኝ አስመሳዮች' ያልኳቸው አላስደነገጠኝም ምክንያቱም ይሉኝታም ሆነ ሀፍረት ከኔ በእጥፍ እርቀዋል... ይሉኝታ የተሰጠው ለሰው ነው እኔ ደግሞ ከሰውነት ደረጃ በትንሹ ወርጃለው.....  ምናልባትም እንደማስበው አልወረድኩ ይሆናል ግን በቃ ለኔ የሚሰማኝ ያ ነው......
በበረሀ ላይ ያለ እህል ውሀ የተጣልኩ..... ሙቀት ሀሩሩ ያነደደኝ..... ከአካላቴ አብዛኛውን በከሀዲዎች የተነጠኩ.... ለመኖር ተስፋ ለመሞት አቅምና ወኔ የሌላት ፍጡር እንደሆንኩ ይሰማኛል። አዎ ለመሞትም እኮ አቅም እና ወኔ  ያስፈልጋል.... ወኔ ቢኖረኝማ ይህን ጊዜ ሙት አመቴ አልፎ ነበር።
ስልችት፣ ድክም፣ ልፍስፍስ እላለሁ...
ማሰብ ያደክመኛል...
መብላት መጠጣት ይሰለቸኛል...
ስሜን ጠርተውኝ እንኳን 'አቤት' ማለት ትልቅ ተራራን የመግፋት ያክል ይሆንብኛል።

የልብ ስብራት ብቻ ሳይሆን  ከአካል ክፍሎቼ እያንዳንዳቸው ስብርብር እንክትክት እንዳሉ ይሰማኛል። በቃ ዝምምምም ብሎ መኖር ከነኝህ ጊዜያቶች በአንዱ ነው እንግዲህ ከዚህ ሰው ጋር የተገናኘሁት....


በቆሙበት ትቻቸው እየሄድኩ ነው ከኋላዬ የራቀ ድምፃቸው ይሰማኛል..." ያማታል መ ሰ ለ ኝ..." እኔ ግን እየሄድኩ ነው...  ከቤት ስወጣ ማንም ያየኝ የለም ለነገሩ ማን ሊያየኝ ይችላል... እንደሚሰበር እንቁላል የሚንከባከቡኝን ሁሉ አጥቻለው..... እየሄድኩ ነው....መነሻዬን አስታውሳለሁ መድረሻዬን ግን እንጃ.....

ይቀጥላል....

✎ ክፍል 2 ይቀጥላል....  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
━━━━━━━━ ✦

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
Forwarded from 🇪🇹ETHIO AIRDROP (Mame 🕊)
ROCKY RABIT ይባላል BINANCE SQUARE ላይ ARTICLE እየተፆፈለት ያለ ከ HAMSTER KOMBAT የተሻለ PROFIT ያስገኛል ተብሎ የሚጠበቅ አሪፍ POROJECT ነው

በዚህ LINK ግቡ :-
https://www.tg-me.com/rocky_rabbit_bot/play?startapp=frId815892887

SATRT በሉት
TAP TAP በማድረግ ብዙ POINT ሰብስቡ
EARN SECTION ውስጥ በመግባት ሁሉንም TASK COMPLET አድርጉ
ሰው INVITE አድርጉ
🔥Mine ውስጥ ገብታችሁ  Upgrade በማረግ PROFIT PER HOUR አሳድጉ

በተማጨማሪም በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ እንደሚባለው ልክ እንደ PRETON እዚህ ቦት ላይ 1 ሰው ስትጋብዙ 0.001 TON COIN ታገኛላችሁ ትንሽ ቢሆንም ለ GAS FEE ይጠቅማችኋል በዋነኝነት ግን RABBIT COIN መሰብሰቡ ላይ FOCUS አድርጉ 🫡



ትኩስና በየጊዜው የሚለቀቁ ምርጥ መረጃዎችን ለማግኘት የቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ
👇

@ethioRebiairdrop
@ethioRebiairdrop
😘ያበደው ፍቅሬ😘

ክፍል 2⃣

ከቤት ስወጣ ማንም ያየኝ የለም ለነገሩ ማን ሊያየኝ ይችላል... እንደሚሰበር እንቁላል የሚንከባከቡኝን ሁሉ አጥቻለው..... እየሄድኩ ነው....መነሻዬን አስታውሳለሁ መድረሻዬን ግን እንጃ.....

ማሰብና ማስታወስ ቢደክመኝም አይምሮዬ ወደማልፈልገው ጊዜ ሽምጥ ጋለበ.... ወደዛ የሁሉም ነገር ጅማሬ የመከራዬ ሀ ወደሆነው ጊዜ....
........
........
በአንድ አነስተኛ የገጠር ከተማ ውስጥ ከእናቴ ጋር ነበር የምኖረው። አባቴን ገና በልጅነቴ ነው በካንሰር በሽታ ያጣሁት። የልጅነት ጊዜዬን እንደማንኛውም ልጅ በጨዋታ እና በሳቅ ነው ያሳለፍኩት። ምንም እንኳን በቤታችን ብዙ የጎደሉ ነገሮች ቢኖሩም እናቴ ለኔ ደስታ አብዝታ ትደክማለች።

ፓስቲ እና ጠላ በመሸጥ ለኔም ሆነ ለሷ የሚያስፈልጉንን ነገሮች ታሟላለች። ሁል ጊዜም ባይሆንም ችግር እና ረሀብ አልፎ አልፎ ቤታችንን ያንኳኳል፤
እናቴን ሲያማት.....
.....
......

በዛን ሰዓት ምን እንደሆነ ባይገባኝም እናቴን አልፎ አልፎ  ከበድ ባለ ሁኔታ ያማት ነበር። አንዴ አሟት ከተኛች ሳምንት እና ከዛ በላይ ያስተኛታል። ሀኪም ቤት እንድትሄድ ደጋግሜ ብጨቀጭቃትም የሁል ጊዜም መልሷ አይሆንም ነው፤ ብያት ብያት እምቢ ስትለኝ በሚያማት ሰዓት ከአጠገቧ ሳልለይ እንከባከባት ነበር።
....
......

ከእለታት በአንዱ ቀን ከትምህርት ቤት ስመለስ በራችንን ተዘግቶ አገኘሁት.... እናቴ በዚህ ሰዓት የጠላ ጣሳዎቿን ደርድራ ፓስቲዋን በርንዳ ላይ እየጠበሰች  መገኘት ነበረባት....
.....
በሩን ከፍቼ ወደ ውስጥ ስገባ የሽቦ አልጋዋ ላይ እጥፍጥፍ ብላ ተኝታ አገኘኋት

"እማ ምን ሆነሽ ነው አመመሽ እንዴ?' እጄን ግንባሯ ላይ አድርጌ ትኩሳቷን አየሁ.... በጣም ግላለች

'እማዬ አተኩሶሻል እኮ እባክሽ ዛሬ እምቢ አትበይኝ ሆስፒታል እንሂድ' ከወገቧ ቀና ለማለት ስትሞክር አገዝኳትና ትራሱን ከጀርባዋ አስደገፍኳት....
.....
"አይሆንም ልጄ.... ደግሞ ልሂድ ብልስ በምን ገንዘብ .... ይልቅ መድሀኒት አልቆብኛል ሂጂና ግዢልኝ፤ ይህን ወረቀት ስታሳያቸው ይሰጡሻል...." የሆነች ትንሽዬ ወረቀት ከእጅ ቦርሳዋ ውስጥ አውጥታ ከብር ጋር ሰጠችኝ....
......
..
" በይ ታዲያ መጀመሪያ መክሰስሽን ብይና ነው የምትሄጂው" እሺ ብያት ዩኒፎርሜን ቀይሬ ምግብ አቀረብኩና እምቢ ብትለኝም በግድ እያጎረስኳት ትንሽ አብራኝ በላች።
....
....
ከተማችን ያለው  አንድ የመንግስት ፋርማሲ ብቻ ነው። እሱም ለሰፈራችን ራቅ ስለሚል በሩጫ መሄድ ይጠበቅብኛል። የእናቴን ጉንጭ ስሜና ቶሎ እንደምመለስ ነግሪያት እየሮጥኩ ከቤት ወጣሁ
....
....
ነፋሻማው አየር ቀሚሴን ወደላይ እያነሳው እኔም እንዳይገልጠኝ ለመከላከል እየሞከርኩ እየሮጥኩ እያለ አንድ ሰው ስሜን የጠራኝ መሰለኝ። ድጋሚ
" ሚጣ" አለኝ ማነው የጠራኝ ብዬ  ዞር ስል ሸክም ከአጠገቡ ያስቀመጠ ጎረምሳ ልጅ እጁን አውለበለበልኝ። አቅጣጫዬን ቀይሬ በፍጥነት አጠገቡ ደረስኩና
' አቤት የሚያሸክምህ አጥተህ ነው አልኩት' ከሁኔታው ሳየው ምኑም የኛን ከተማ ሰው አይመስልም ምናልባት ከሌላ ቦታ ለስራ መጥቶ ይሆናል ብዬ መላ ምቴን አስቀመጥኩ።
...
...
ያልገባኝን ፈገግታ ከለገሰኝ በኋላ "አዎ ሚጣዬ እስኪ አሸክሚኝ"  አለኝ።
'የምችለው አይመስለኝም ግን እሺ ልሞክር' አልኩትና ጎነበስ ብዬ ሸክሙን ያዝ አደርኩና ቀና ብዬ አየሁት የማይገባኝን አስተያዬት እያየኝ ነው።
'ምነው መሸከም አትፈልግም እኔ እቸኩላለሁ ለእናቴ መድኃኒቱን መግዛት አለብኝ' አልኩት ቆጣ ብዬ

"አይ እንደዛ አይደለም ይሄን አንቺም ለማሸከም ይከብድሻል እኔም እንጃ የምችለው አይመስለኝም... ውስጥ አነስ ያለ ሌላ ሸክም አለ እንደውም እሱን አሸክሚኝ አይዞሽ አትቆይም" ምላሼን ሳይጠብቅ ፊቱን አዙሮ  በጭቃ እየተሰራ ወዳለ ጅምር ቤት ገባ። ዘግዬት ብዬ ተከተልኩትና ወደ ውስጥ ስገባ ዘሎ በጥፊ ደረገመብኝ። ተንደርድሬ መሬቱ ላይ ተደፋሁ.... ለመጮህ አፌን እንደከፈትኩ ፀጉሬን ይዞ አፌ ውስጥ ጨርቅ ጠቀጠቀብኝ።
.....
.....
በመንፈራገጥ እና በድብደባ በዛለ ሰውነቴ ላይ  ከላዬ ሆኖ በስሜት ይጨፍራል....
......
ከባድ የሆነ የህመም ስሜት ይሰማኛል........
ቀስ በቀስ በእንባ የራሰው አይኔ መከደን ጀመረ......
ከላዬ ላይ ያለው ሰው ምስል ወደ ብዙ ሰውነት ተቀየረ.......
ከዛ ደግሞ ድብዝዝ እያለ መጣ...... በስተመጨረሻም ድርግም ብሎ ጠፋ..........
........
ጨለማ

ይቀጥላል....

@ethioRebiairdrop
@ethioRebiairdrop
ከወደዳችሁት
Forwarded from 🇪🇹ETHIO AIRDROP (Mame 🕊)
4-3-3 Pay 🥳

1. ከ1ኛ እስከ 10ኛ - ለእያንዳንዱ 1,000 ብር
2. ከ11ኛ እስከ 50ኛ - ለእያንዳንዱ 500 ብር

👉 ውድድሩ ዛሬ ተጀምሮ ቅዳሜ ይጠናቀቃል ፤ ውድድሩም የሚሆነው 4-3-3 Pay ቦትን Start ብሎ ማስጀመር ከዛም ቻናሎች ተቀላቅሎ ሰዎችን መጋበዝ ፤ የጋበዛቿቸውም ሰዎቹም እነዛን ቻናሎች እና  ቦቱን መቀላቀል ነው

👉 ብዙ የጋበዙ ከ1-50 ደረጃ ሁሉም ሰው ማየት የሚችል ሲሆን ፤ ከ50 ደረጃ ቡሃላ ያለውን ሰውዬው ያለውን ነጥብ እና ያስገባውን ሰው ከ50ዎቹ በማስተያየት እነሱ ላይ ለመድረስ አድ ማድረግ ይችላል ።

👉 ይሄ ሽልማት በየጊዜው የሚያድግ ሲሆን በየወሩ ከ150ሺ ብር በላይ 4-3-3 ለተከታዮቹ የሚያከፋፍል ይሆናል ።

👉 በተጨማሪም የ4-3-3 Pay የኮሚዩኒቲ ቻናልን በመቀላቀል በቀጣይነት በቻናላቸን ለሚሰጡ የተለያዩ ተጨማሪ ሌሎች ሽልማቶች ተሳታፊ መሆን ትችላላቹ ።

👉 ቦቱ በየ 1 ሰአት ልዩነት ደረጃ Update ያደርጋል ።

መጀመሪያ 5ቱንም ቻናሎች ጆይን ማለታችሁን አርጋግጡ !

ለመጀመር 👇 https://www.tg-me.com/Habesha_433_cashbot?start=r0697389427
😘ያበደው ፍቅሬ😘

ክፍል 3⃣

ከምን ያክል ሰዓት በኋላ እንደሆነ አላውቅም....  ራሴን እዛ ጅምር የጭቃ  ቤት ውስጥ ተኝቼ አገኘሁት። እንደምንም እየተንገዳገድኩ ከቤቱ ውስጥ ወጣሁ... ልብሴ በደም ተነክሯል፣ የሚሰማኝ የህመም ጥዝጣዜ ራሴን ሊያስተኝ ደርሷል ግን እንደምንም ተቋቁሜ ለመራመድ ሞከርኩ።
.....
.....

ብርሀን ለጨለማ ቦታዋን ብታስረክብም ደማቋ የምሽት ጨረቃ አካባቢውን በብርሀን ሞልታዋለች....

በቀስታ እየተራመድኩ ወደ መንገዱ ወጣሁ። አሁንም ደሜ አልቆመም በቀስታ ከጭኔ ላይ ሲወርድ ይሰማኛል። ከሩቅ ነጠላ ለብሶ የሚመጣ ሰው አየሁ  አንደበቴን ከፍቼ ለመጣራት መከርኩ ግን በምጥ የወጡት ቃላቶች  እንኳን ለሌላ ለኔም የሚሰሙ አልነበሩም።
......
......

ያለኝ አማራጭ ወደሚመጣበት አቅጣጫ ተራምጄ እንዲያየኝ ማድረግ ነው። እየቀረብኩት ስመጣ ቄስ እንደሆኑ ተረዳሁ.... አጠገባቸው ለመድረስ ትንሽ ሲቀረኝ ጉልበቴ ተብረከረከ፣ አቅሜ ተሟጠጠ፣ አጠገቤ መጥተው ያዙኝና

" ምነው የኔ ልጅ ችግር አለ ምን ሆነሽ ነው?" ድምፃቸው ከሩቅ የሆነ ያክል ይሰማኛል ። ልቤን ስልብ የሚያደርግ ህመም ተሰማኝ ከዛ በኋላ አላስታውስም
......
......

"ልጄ የኔ ስስት.... ምን አድርገውብኝ ነው? እባክሽ ተነሽ ሚጣዬ ተነሽልኝ..... የኔ ብቸኛ ልጅ...  ያላንቺ ማን አለኝ.... ትተሽኝ እንዳትሄጂ.... ተስፋዬ.... ነገን የማይብሽ.... " አይኔን ሳልገልጥ የሰማኋቸው የእናቴ በሳግና በለቅሶ የታጀቡ ቃላቶች ናቸው... ከዛ ከባዱ ጨለማ ይውጠኛል።
ትንሽ ትንሽ ዙሪያዬ እየተፈጠረ ያለውን ነገር ባውቅም አይኔን ለመክፈት ወሰድ መለስ የሚያደርገኝን ጨለማ እና የተጫነኝ ከባድ ነገር መታገል ግድ ሆኖብኛል።
.....
....

"አሁንስ አልነቃችም አይደል" አለ የሆነ ጎርናና ድምፅ

" አልነቃችም ኢንስፔክተር ልጄን እንደዚህ ያደረገውን ሰው አገኛችሁት?" እማዬ ናት

" አይ... ወይዘሮ ወይንሸት አላገኘነውም እሱን ለመያዝ የልጆት ቃል ያስፈልገናል" የበር መዘጋት ድምፅ ተሰማኝ እኔም ወደዛው ጨለማ የሄድኩ መሰለኝ.... እንቅልፍ
.....
.....

ዛሬ የተሻለ ጥንካሬ ይሰማኛል። ልክ አይኔን ስግልጥ እናቴን አጠገቤ አየኋት የአልጋውን ጠርዝ ተደግፋ እንቅልፍ ወስዷታል። እጄን አንቀሳቅሼ ፊቷን ስዳስሳት ተነሳች... ወዲያው እልልታዋን አቀለጠችው።

"ልጄ ነቃሽልኝ የኔ ስስት.... ተመስገን ልጄ ነቃች" ዶክተሩ ምርመራ እስከሚያደርግልኝ ውጪ እንድትቆይና ነገራትና አንዳንድ ህክምናዎች ካደረገልኝ በኋላ

"ፖሊስ መጥቶ ቃልሽን ይወስዳል... እንደዚ ያደረገሽ አውሬ እንዲያዝ ከፈለግሽ ምንም ሳትፈሪ ሁሉንም ለመናገር ሞክሪ.... ደግሞ አይዞሽ በሚያስፈልግሽ ሁሉ ከአጠገብሽ አለን..." ብሎኝ ክፍሉን ለቆ እንደወጣ ሁለት ፖሊሶች ተከታትለው ገቡ።
....
.....

ከ አንድ ወር በኋላ
የሰፈር ሰው ሰምቶ ስለነበር ግማሹ ሲያዝን ግማሹ ደግሞ የራሱን መላምት ማስቀመጥ ጀመረ።
"ፈልጋ ነው እንጂ ሳትፈልግ ማን ሊነካት..." በነገር የምትታወቀው ብርቄ

"ኧረ ተይ እንደዚህማ አትበይ እናቷ እኮ መድሀኒት ቤት ልካት ስትሄድ አግኝቷት ነው አሉ"  የእናቴ ጓደኛ አየለች

"ኡኡቴ እና ምን ልትልልሽ ኖሯል ልጄ ከኔ ተደብቃ ወንድ ፍለጋ ሄደች ትበልልሽ እናቷ እኮ ነች። ደግሞስ ከመች ጀምሮ ነው ሚጣን መድሀኒት ማስገዛት የጀመረችው...."

ከዚህም የባሱ ብዙ ሽሙጥና ስድቦችን በተቃራኒውም ብዙ አይዞሽ በርቺ የሚሉ ቃላቶችን እሰማለሁ። ለኔ ግን ከአስር አይዞሽ አንድ ምናባሽ ልቤን ያርደው ነበር። ጭምትና በትንሽ ነገር የምበረግግ ፈሪ ሆንኩ።

እኔ እምቢ ብልም በእናቴ ጉትጎታ ወደትምህርት ቤት ሄድኩ። እዛም የባሰው ነገር ጠበቀኝ አንድም ሊቀርበኝ የሚፈልግ ልጅ የለም ሁለም ራቅ ራቅ ብለው በዩኒፎርማቸው ኮሌታ አፋቸውን ሸፍነው ይንሾካሾካሉ።

ሁሉም ነገር ሊያሳብደኝ ደረሰ የሚያውቁኝ እንደማያውቁኝ ሲሆኑብኝ ጓደኞቼ እኔን ለመቅረብ ሲፈሩ ማየት አሳመመኝ። ምንም ሳልል ቦርሳዬን ይዤ ከትምህርት ቤት ወጣሁ። አረማመዴ ሁላ የእልህ ነበር። ቤት ስደርስ እማዬን አሻሮ እየቆላች አገኘኋት...

" ከዚህ ከተማ አስወጪኝ... እማ ለምን እልም ያለ ገጠር አይሆንም ሄጄ የከብት እረኛም ቢሆን እሆናለሁ ብቻ ከዚህ አርቂኝ ' እግሯ ላይ ተደፍቼ እየተንሰቀሰኩ ለመንኳት

"ችግርሽ ሳይገባኝ ቀርቶ መሰለሽ እኔም ወሬው ሰልችቶኛል የኛ ሰፈር ሰው እንኳን ይቺን አግኝቶ.... እህ.. መች አጣሁት... ግን የፖሊሶቹ ምርመራ አልቆ ያን እርኩስ ሰው ታስሮ ሳላይ ከዚህ ንቅንቅ አልልም። ያኔ እውነቱ ሲታወቅ አንቺም ቢሆን አንገትሽን ቀና አድርገሽ ትሄጃለሽ" እንባዬን ጠራርጋ እና አባብላ ብዙ መከረችኝ ምክሮቿም ብርታት ሆኑኝ።
....
.....

ምንም እንኳን በተኛሁበት መበርገጌ የምጥ እንቅልፍ መተኛቴ ባይቀርልኝም የሰፈሩ ሰው ግን ቀስ በቀስ ወሬውን እየረሳው ጓደኞቼም " ነይ እንጫወት" እያሉ መምጣት ጀመሩ።

ትምህርት ቤትም ተማሪዎቹ እንደድሯቸው ሆኑልኝ እኔ ግን እንደድሮዬ መሆን አቃተኝ ትምህርት ስማር በሀሳብ ጭልጥ ብዬ እሄዳለሁ... ወንድ አስተማሪ ሲገባልን እሱም ልክ እንደዛ ሰው አውሬ እንደሆነ አስብና እጠላዋለሁ ከመምህሩ እኩል የሚያስተምረውም ትምህርት ያስጠላኛል። እንዳዛ እንደዛ እያለ የእናቷ " ሚጣ" እኔ 'ሩት በዛብህ' ከማንነቴ ተፈናቅዬ እንዳልነበርኩ ሆንኩ። ሰው ሲያየኝ እንደበፊቱ ብመስልም ውስጤ የተረበሸ ከተማ ሆነ።
....
.....

ከአራት ወር የፓሊሶች ምርመራ እና ድካም በኋላ ውጤቱ ፍሬ አልባ መሆኑን ለእናቴ ነገሯት.... ደፋሪዬ ደብዛውም የለም። እኔ በነገርኳቸው ትንሽ ምልክት ብቻ እሱን ለማግኘት መሞከር እንደሚከብዳቸው ስለገባኝ አላዘንኩባቸውም።
....
....

ከእለታት በአንደኛው እሁድ
ፀጉሬን ከታጠብኩ በኋላ ገላዬን ልታጠብ የበርሜል ጉራጅ ላይ ቁጭ ብዬ ሙቅ ውኋዬን እስከምታመጣ እናቴን እየጠበኩ ነው። ውሃው መጣና እኔ ከፊቴ እናቴ ደግሞ ከጀርባዬ እያጠበችኝ
"እስኪ እጅሽን ዞር አድትጊ አሁን በዚህ ጭራሮ እጅሽ አሽተሽው ነው የሚጠራው..." ሁሌም እናቴ ከፊት ለፊቴ ልታጥበኝ ስትል የምትለው ነገር ነው። ልማዴ ስለሆነ እኔም አልቃወማትም እጄን ከፍ አድርጌላት እያጠበችኝ ድንገት  የያዘችውን ውሃ የያዘ ጆግ ለቀቀችው። በርሜል ውስጥ ስለወደቀ ከስር ያለው ውሃ ተፈናጥሮ አለበሰኝ።

'እንዴ እማ ምን ሆነሽ ነው ታጥቤ ታጥቤ' ተነጫነጭኩና ጆጉን አንስቼ ውሃ ልቀዳ ስል

"ቆይ ቆይ ቆይ እስኪ አንዴ ቁሚ" አለችኝ። ቀና ብዬ ሳያት ደንግጣለች

'እማዬ ምን ሆነሻል' አልኳት

"ወሬውን ትተሽ ያልኩሽን አድርጊ" ብላኝ እየተርበተበተች እጄን ይዛ አቆመችኝና ፍጥጥ ብላ ሆድ ሆዴን ካዬች በኋላ

"ልጄ" አለችኝ በሚያሳዝን ቅላፄ

'ወዬ እማ ለምን ነው እንደዚህ የምታይኝ'

"ሆድሽ" ጎንበስ ብዬ አየሁት እኔንም አስደነገጠኝ

'አብጦ ነው እማ? ወይስ እንደ ምንትዋብ ቁዝር ልሆን ነው' አልኳት።

ይቀጥላል
@ethioRebiairdrop
@ethioRebiairdrop
@ethioRebiairdrop
ከወደዳችሁት ❤️
😘ያበደው ፍቅሬ😘

ክፍል 4️⃣

"አቤት ሩት" አለኝ ዶክተሩ ካቀረቀረበት ቀና ብሎ ካየኝ በኋላ

'ማስወረድ እፈልጋለሁ' አልኩት

"ምን" የሚል ድምፅ ስምቼ ስዞር እናቴ ከኋላዬ ቆማለች።

"ምንድነው የምታወሪው እ... ማን ፈቅዶልሽ ነው የምታስወርጂው.... ምን ስልጣንስ ኖሮሽ ነው የእግዜርን ፍጡር የምትገይው......" ወደኔ የበለጠ እየተጠጋች የቁጣ ናዳ አወረደችብኝ። እናቴ በአካባቢው እያለች ከአንደበቴ ይህንን ቃል ማውጣት አልነበረብኝም።
.......
......
ከውርጃ ጋር ተያይዞ በጣም መጥፎ ትዝታ አለባት።  ልጅ እያለሁ ትርሲት የምትባል  የዘመዳችን ልጅ አብራን ትኖር ነበር።  ታናሽም ታላቅም ስለሌለኝ እንደ እህቴ ነበር የማያት እሷም ሲበዛ ታቀብጠኝ ነበር። በትምህርቷ በጣም ጎበዝ ነበረች። ታዲያ ከጊዜ በኋላ ውጤቷ እያሽቆለቆለ መጣ። መምህሮቿ ቤታችን ድረስ መጥተው እናቴን አናገሯት እማዬ ደነገጠች..... ትርሱ ከሄደችበት ስትመለስ ቁጭ አድርጋ አወራቻት መከረቻት ግን ለውጥ አልነበረውም የባሰ ትምህርት ቤት እያለች ሌላ ቦታ እንደምትውል ተደረሰባት.... እናቴ ይህን ስትሰማ በጣም ተቆጣቻት።
......
የሆነኛው ቀን ላይ መልዕክተኛ መጥቶ ትርሲት ታማ ሆስፒታል መግባቷን ነገሩን እናቴ እየሮጠች ሄደች። ወደቤት ይዛ የተመለሰችው ግን አስከሬን ነበር።
.......
........
ትንሽ ካደኩ በኋላ እናቴን ጠይቄ እንደተረዳሁት ከሆነ ትርሲት ከአንድ የከተማችን ነጋዴ ጋር የፍቅር ግንኙነት ትጀምራለች። ሁሉ ነገሯን ትታ ነበር ክንፍ ያለችለት .... ግንኙነታቸው በሱ ጎትጓችነት ወደ አልጋ ላይ ጨዋታ ይሸጋገራል.... በዚህ መሀልም ትርሲት አረገዘች። ማርገዟን ስታውቅ ሁሉንም ነገር ዘርዝራ ለጓደኛዋ ከነገረቻት በኋላ ምክሯን ጠየቀቻት
"ስለሚወድሽ ያገባሻል እንዳረገዝሽለት ንገሪው" አለቻት።

በማግስቱ ወደ ፊት የሚኖራቸውን የደስታ ህይወት እያሰበች በፈገግታ የደመቀ ፊቷን ይዛ ወደ ነጋዴው ፍቅረኛዋ ጋ ሄደች። እንዳረገዘችለት ስትነግረው

" ከማናባሽ አርግዘሽ መጥተሽ ነው አረገዝኩልህ የምትይው" አላት።
ከሱ ውጪ ወንድ እንደማታውቅ ያውቃል ግን ሊሰማት አልፈለገም። ትርሲት ለሱ የሆነ ሰዓት ላይ ተጠቅሞባት እንደሚጥላት እቃ ነበረች።
አይንሽን ማዬት አልፈልግም ከነ ዲቃላሽ ገደል ግቢ ብሎ አባረራት..... ለሳምንታት ተስፋ ሳይቆርጡ እሷም ጓደኛዋም ለመኑት.... ጭራሽ አይኑን ወደ ጓደኛዋ ማዞር ጀመረ ነገሩ ሲገባቸው እሱን እርግፍ አድርገው ትተው ሌላ መፍትሄ መፈለግ ጀመሩ እናም ማስወረድ በሚለው ተስማሙ። የትርሲት ጓደኛ ቤተሰቦቿ ወደገጠሩ ስለሚርቁ ቤት ተከራይተውላት ነው ትምህርቷን የምትማረው.... እናም ለእቅዳቸው ተስማሚ የሷ ቤት ስለሆነ ትርሲት እማዬን ለፈተና ለማጥናት ጓደኛዬ ጋር ልደር ብላ አስፈቀደቻት። እማዬም ምናልባት አብረው ሲያጠኑ ውጤቷ ይሻሻላል ብላ ስላሰበች አልተቃወመቻትም።
.......
.....
ጓደኛዋ ቤተሰቦቿ ካሉበት ገጠር ለውርጃ ይጠቀሙታል ያለችውን መድኃኒት ሰጠቻት እናም ግጥም አድርጋ ጠጣችው። ለትንሽ ጊዜ ሁሉም ሰላም ነበር ሌሊት ላይ ግን ከበድ ባለ ሁኔታ ደም ይፈሳት ጀመር። ልጁ እየወረደ ነው ብለው ስላሰቡ የሚሆነውን በዝምታ ጠበቁ..... ከሰአታት በኋላ ግን ትርሲት እየደከመች መጣች። ጓደኛዋ የአከራዮቿን ቤት አንኳኩታ እርዳታ ጠየቀች እናም ወደ ሆስፒታል ተወሰደች ግን አርፍደው ነበር። ትርሲት ብዙም ሳትቆይ አሸለበች ።
...................
..................
አይደለም እኔ  ልጇ ማንም ላሶርድ ቢላት ኡ ኡ እንደምትል አላጣሁትም ግን.......

"እማዬ በዘመናዊ መንገድ እኮ ነው በሀኪም" አልኳት

"አይሆንም ብያለሁ አይሆንም..." ጮኸችብኝ.... ንግግራችንን ሲሰማ የነበረው ዶክተር ተነስቶ አጠገባችን መጣና አረጋግቶ ወንበር ላይ ካስቀመጠን በኋላ

"ሩት ከማስወረድ ውጪ ሌላ አማራጭ የለም ብለሽ ታስቢያለሽ" አለኝ።

"አዎ ዶክተር መማር እፈልጋለሁ በዛ ላይ የሰው መሳቂያ ነው የምሆነው.... ማንም ተደፍራ ወለደች የሚለኝ የለም...." ንግግሬን ሳግ አቋረጠኝ

"እርሶስ ወይዘሮ ወይንሸት ምን ይላሉ"

"እኔ ቆሜ እያለሁ ልጄን ለሞት አሳልፌ አልሰጣትም በፍፁም አይሆንም" እርግጠኝነት በተሞላበት መንፈስ ተናገረች።
......
"እኔም የእናንተን ሀሳብ ልስማ ብዬ እንጂ ፅንሱ ሶስት ወር አልፎታል በዛ ላይ ልጅ ነሽ ከማስወረዱ ብትወልጂው ይሻላል ለሱም ቢሆን እድሜሽ ገና ስለሆነ ያላቋረጠ የህክምና ድጋፍ ያስፈልግሻል......" ይሄን እና የመሳሰሉትን ሲያወራ እናቴ 'እህ' እያለች አንገቷን እየነቀነቀች ትሰማዋለች።

ትቻቸው በሀሳብ ነጎድኩ ከዛስ አልኩ ለራሴ...... ከዛስ ትምህርቴ ሊቀር..... የሰፈር ሰው መጠቋቆሚያ ልሆን...... ከዛስ እ...... የወደፊት እጣ ፋንታዬስ.... እዚሁ የተወለድኩበት ሀገር በናቴ እግር ተተክቼ ፓስቲ እና ጠላ ስሸጥ ልጄን ለማሳደግ ደፋ ቀና ስል በህሊናዬ ሳልኩ።
....
"አይሆንም" አልኩ ቃል አውጥቼ.... ያልኩት መልሶ አስደነገጠኝ

"ምኑ ነው የማይሆነው ሚጣዬ.... ዶክተር ያለውን ሰምተሻል አይደል እንደዛ እናደርጋ...." ዶክተር! ዶክተር ምንድነው ያለው?...... ምንም ይበል ምን አገባኝ። ዶክተር እኮ ህልሙ ይሁንም አይሁንም ዶክተር ሆኗል አይደል.... ደግሞ እሱ ምን አለበት በሰው ቁስል ላይ እንጨት መስደድ ለሱ ቀላል ነው.... "ውለጂው" አለ አይደል? መውለዴ የሚያሳጣኝ ነገር ግን ግድም አይሰጠው.... ይቺ የአስራ ሶስት አመት ልጅ ከምታስወርድ ትውለድ ሲል ይቺ የአስራ ሶስት አመቷ ሩት ህልሟን ትቅበረው ማለቱ እንደሆነ አልገባውም።

''ወለድኩ ማለት ህልሜ ሁላ ይቀበራል" አልኩት የመጨረሻ እድሌን ልሞክር ብዬ

"አንቺ ከምትቀበሪ ህልምሽ ቢቀበር አይሻልም" አለችኝ እናቴ.... ምንም ሳልናገር ቢሮውን ለቅቄ ወጣሁና ወደቤት መንገድ ጀመርኩ እማዬ ከኋላዬ ደረሰችብኝ። ምንም ሳንነጋገር ጎን ለጎን ትንሽ ከሄድን በኋላ

"እስኪ ሚጣዬ ሆድሽን ሸፈን አድርጊው" ብላ የለበስኩትን ፎጣ ስባ ሆዴን አለበሰችው.....
..........
እና ሁሉም ነገር እንደዚህ ሊቀጥል ነው? አይሆንም! እናቴም እኔም አንገታችንን ከምንደፋ የሆነ ሀሳብ በውስጤ መጣልኝ። እንደማደርገው እርግጠኛ ሆንኩ.....

ይቀጥላል....

@ethioRebiairdrop
@ethioRebiairdrop
@ethioRebiairdrop
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
ከወደዳችሁት ❤️
የፍቅር ጥቅሶች 💖 pinned «😘ያበደው ፍቅሬ😘 ክፍል 4️⃣ "አቤት ሩት" አለኝ ዶክተሩ ካቀረቀረበት ቀና ብሎ ካየኝ በኋላ 'ማስወረድ እፈልጋለሁ' አልኩት "ምን" የሚል ድምፅ ስምቼ ስዞር እናቴ ከኋላዬ ቆማለች። "ምንድነው የምታወሪው እ... ማን ፈቅዶልሽ ነው የምታስወርጂው.... ምን ስልጣንስ ኖሮሽ ነው የእግዜርን ፍጡር የምትገይው......" ወደኔ የበለጠ እየተጠጋች የቁጣ ናዳ አወረደችብኝ። እናቴ በአካባቢው እያለች ከአንደበቴ…»
😘 ያበደው ፍቅሬ 😘

ክፍል 5⃣

እና ሁሉም ነገር እንደዚህ ሊቀጥል ነው? አይሆንም! እናቴም እኔም አንገታችንን ከምንደፋ የሆነ ሀሳብ በውስጤ መጣልኝ። እንደማደርገው እርግጠኛ ሆንኩ....
ቤት እንደደረስን ቁጭ አድርጋ የምክር ናዳ አወረደችብኝ ግን አንዱንም ከልቤ ሆኜ አልሰማኋትም..... እንዴት እንደማደርገው እቅድ እያወጣሁ ነበር።
*°°°°°°°°•••••°°•••••••°
........
ሁሌም ማክሰኞ ቀን እናቴ ገበያ ትሄዳለች። ያሰብኩትን ለማድረግ ከዚህ ቀን ውጪ የተመቸ እንደሌለ አውቃለሁ ስለዚህ ማክሰኞን መጠበቅ አለብኝ።
....
.....
የምጥ ቀን እሁድ አለፈና ሰኞ መጣ.... ብርድ ልብሴን ክንብንብ ብዬ የተኛሁ መሰልኩ።  እማዬ ቤት ውስጥ ውዲህ ወዲያ ስትል እንቅስቃሴዋ ይሰማኛል። አጠገቤ መጣችና
"አንቺ ሚጣ.... ሚጣዬ..... ሚጣ" ብላ ጠራችኝ። ባልሰማ ዝም ብያት የተኛሁ እንዲመስል ጣርኩ ምክንያቱም ከዚህ በኋላ ትምህርት ቤት መሄድ በጓደኞቼ እና በሌሎች ተማሪዎች መዋረድ አልፈልግም።

እኛ ላለንበት ማህበረሰብ ይሄ ከባድ ነገር ነው። መደፈሬን የሚያውቀው ሳይቀር
"የወይንሸት ልጅ ዲቃላ አረገዘች.... ድሮም ሴት ያሳደገው" ብለው እኔን ብቻ ሳይሆን ብርቱዋን እናቴንም ጭምር ነው የሚሰብሩብኝ

"አንቺ ሚጣ... ተነሽ እንቅልፍ እንዳልወሰደሽ አውቃለሁ..." አለችኝ። ምንም ማምለጫ የለኝም ፊቴን ቀስ ብዬ ገለጥኩና አጠገቤ የቆመችውን ድንቅ ሴት ከታች ወደላይ አየኋት..... እምዬን.... እናቴን። ጎንበስ ብላ በስስት  እያየችኝ ነው። ከተኛሁበት ቀና ብዬ ቁጭ እንዳልኩ አጠገቤ መጣችና ጥምጥም ብላ አቀፈችኝ።

"ልጄ የኔ ስስት.... አለሜ እኮ አንቺ ብቻ ነሽ.... በዚህ እድሜሽ እንደዚ ስብር አትበይብኝ። ምን ያክል እንደሚያም ካንቺ በላይ ይገባኛል። ህመምሽ ካንቺ የበለጠ እኔን ያመኛል። ነገር ግን ቁጭ ብለን በእንባ እና ያለፈውን መራር ጊዜ በማሰብ ነጋችንን አናጨልመውም ልጄ ትማሪያለሽ ልክ እንደምትመኝው ዶክተር ትሆኛለሽ..."

"እማ እኔ ትምህርት ቤት አልሄድም" እንባዬ ከአይኔ ክልብስ አለ። እየተንሰቀሰኩ አለቅስ ጀመር።
"አይ እንግዲህ የምን ለቅሶ ነው" አለችኝ ቆጣ ብላ ይሄን ቁጣዋን አውቀዋለው ምናባሽ.... የታባሽ..... የሚባለው አይነት ቁጣ አይደለም። ቃሏ እና ፊቷ ላይ "መፍትሄ አለው" ከሚል መልዕክት ጋር ነው የምትናገረው። ለቅሶዬን አቁሜ የምትለውን ለመስማት ተመቻቸሁ።

"ልብ ብለሽ ስሚኝ የኔ ልጅ...."
በሚገባኝ ቋንቋ አስረዳችኝ።

****•••••••••፨፨፨፨•°°°••••••°°°°°

ሙሉ  ለሙሉ ነው ሀሳቤን ያስቀየረችኝ የኔ እቅድ የነበረው ገበያ ስትሄድልኝ የገዛሁትን የአይጥ መርዝ ጠጥቼ ይህችን አለም መሰናበት ነበር። ንቁዋ እናቴ ግን እቅዴን ሁሉ ቀድማ ደረሰችበት። አዲሱን እቅዷን ከነገረችኝ በኋላ እንዲህ አለችኝ።

"  ያቀድሽውን ሁሉ ደርሼበታለሁ ሚጣ.... መርዝ ልትጠጭ ነበር አይደል" ክው ብዬ ነው የደነገጥኩት
........
.......

"እንዴት ሆኖ ከኔና ባለሱቁ ውጪ እኮ መግዛቴን የሚያውቅ አልነበረም" አልኳት ምን ያክል እንደምትደነግጥና ልታዝንብኝ እንደምትችል እያሰብኩ... ፊት ለፊቴ ያለችው ሴት ግን ፍፁም መረጋጋት ነው የሚታይባት

"ባለሱቁ ባንዴ ሶስት ስትገዢው  ተጠራጥሮ ነው። በመንገድ ሳልፍ ጠርቶ የነገረኝ አልዋሽሽም እንደሰማሁ ምድር ነበር የከዳችኝ... ቶሎ ብዬ ቤት ሰመጣ በረንዳ ቁጭ ብለሽ አገኘሁሽ ያኔ ወደቤት ገብቼ ከደበቅሽበት ፈልጌ አገኘሁትና ወሰድኩት....."

"ይቅርታ እማዬ ሁሉም ነገር ጨለመብኝ ከኔ ብሶ አንቺም አንገትሽን ደፋሽ..."

"ይገባኛል ሚጣዬ አሁን ስለ እቅዱ ምን ትያለሽ...." ብላ ሀሳቤን ጠየቀችኝ። እናቴ ለኔ እንዲህ ናት አስፈላጊ ያለችው ነገር ላይ ምን ታስቢያለሽ ብላ ታማክረኛለች። ምንም እንኳን ከልቤ ባልሰማት............
..........ወይም እሷ እያወራች ለጨዋታ ጓደኞቼ ሲጠሩኝ ሳላስጨርሳት ሮጬ ብሄድ..........
....... ወይም ደግሞ የልጅ ሀሳቤን ነግሪያት ሆዷን ይዛ ፍርፍር ብላ ብትስቅ... እናቴ ልጅ ናት ብላ ልትነግረኝ እንደሚገባ ያሰበችውን ለኔ ከመንገር ወደ ኋላ አትልም። በሀሳብ ጭልጥ ብዬ ስሄድባት

" ምን ትያለሽ እያልኩሽ ነው ሚጣዬ" አለችኝ ዘልዬ ጥምጥም አልኩባትና

"እጅግ በጣም ምርጥ ሀሳብ ነው ቶሎ ብለን እናድርገው አልኳት

"ኦ ኦ ልጄ እስከምትወልጂ ድረስ እንደፈለግሽ መዝለልና መንፈራገጥ የለም። በይ አሁን ተነሽ ቁርስ እንብላና ያልኩሽን እናደርጋለን።

ለብቻዬ ሌላ ጀንበር የወጣችልኝ መሰለኝ ...... ብሩህ ተስፋ.....



ይቀጥላል......

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
ከወደዳችሁት ❤️
😘 ያበደው ፍቅሬ😘

ክፍል 6⃣

የተሳፈርንበትን አውቶብስ መስኮት በትንሹ ከፈትኩት፤ በመስኮቱ የሚገባው ቀዝቃዛ አየር ከነፋስ ጋር ተቀላቅሎ በጆሮዬ ላይ ቢያፏጭም ምቾት አልነሳኝም። በመስታወት ውስጥ አሻግሬ ሰማዩን ስመለከት ፀሀይ ደም የተነከረ ሸማ መስላ ከወደ ምስራቅ ብቅ ማለት ጀምራለች። በፎቶግራፍ መቅረት ያለበት ድንቅ የተፈጥሮ ውበት። አይኔን እድማሱ ላይ ሰክቼ በራሴ ከቀናት በፊት የነበረውን ነገር ማስታወስ ጀመርኩኝ።
................

ልክ እንደዛ ስብር እንክትክት ብዬ በነበረበት ሰዓት...... ራሴን ላጠፋ ጫፍ በደረስኩበት ሰዓት..... ሀሳቤን አስቀይሮ በደስታ ያስፈነጠዘኝ የእናቴ እቅድ ይህ ነበር።

" ሁሉም ሰው የሚያውቀው የአባትሽ ወንድም አጎትሽ ያለው አዲስ አበባ እንደሆነ......." አላስጨረስኳትም

"አዎ ግን የሱ እዛ መሆን ለምን ይጠቅመናል"

"እዛ የምንሄደው እሱ አንቺን ለማስተማር ጠርቶሽ እኔ ደግሞ ካንቺ አልለይም ብዬ ነው አሉ.... ይህን ለሚጠይቀን ሁሉ እንነግራለን"

"እሺ ግን መቼም አጎቴ ጋ እንሂድ አትይኝም አይደል" አይን አይኗን እያየሁ ጠየኳት

"ለጊዜው የምናርፈው እሱ ጋር ነው ታላንትና ማታ ሱቅ ሄጄ ደውዬለት ነበር ባይዋጥለትም ሁሉንም በዝርዝር ነግሬዋለሁ"

"ምን እያልሽ ነው እማ... የወንድሜ ልጅ ብሎ አንድ ቀን እንኳን ዞር ብሎ ላላየኝ.... አንቺን ሳይቀር ወንድሙን እንደገደልሽበት ለሚቆጥረው.... ለሚጠላን ሰው ነገርሽው"
አልኳት ያልጠበኩት ነገር ነው

"አዎ እኔም አንቺም ይህን ተፅዕኖ መቋቋም አንችልም። ይሁን ብንል እንኳን የኔ ችግር የለውም አንቺ ግን ይከብድሻል ለህክምና ክትትሉም ሆነ ለትምህርትሽ አዲስ አበባ ይሻልሻል...."

"ግን እዛ ሄደንስ ምን ሰርተን እንዴት ሆነን ልንኖር..." ግራ ግብት አለኝ

" እሱ እያሳስብሽ እኔ እናትሽ ላንቺ አላንስም አንቺንም ልጅሽንም ማኖር አይከብደኝም ዳገት ወጥቼም ሆነ ቁልቁለት ወርጄ ህልምሽን እንድታሳኪ አደርግሻለሁ። ታዲያ ለዚህ ያንቺ ጥንካሬ ወሳኝ ነው። በይ አሁን ለጠየቀሽ ሁሉ ካልኩት ውጪ እንዳትናገሪ  ነገሮችን ላስተካክልና በጥቂት ቀን ውስጥ እንሄዳለን።

ከሀሳቤ ስመለስ እናቴን ዞር ብዬ አየኋት ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ውስጥ ናት።
መስኮቱን ተደግፌ አይኔን አድማሱ ላይ ተከልኩ

፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧**፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

ከኔ አካል ቅጥነት ጋር ሲነፃፀር ሆዴ ትልቅ ሆኖ ላየው ይሰቀጥጣል። ምጤ መቶ ሆስፒታል ገብቻለሁ
"አይዞሽ በርቺ..... ግፊ.... አይዞሽ እንደሱ..... በርቺ..... ግፊ" ብዙ ጊዜ ደጋግመው ቢሉኝም ያለኝን አቅም አሟጥጬ ባምጥም ልጄ ሊወለድ አልቻለም። እኔ ግን እቅት ድክም አለኝ የሚሉት በሰመመን ይሰማኛል...

"የልብ ምቷ በጣም እየወረደ ነው ባስቸኳይ ዶክተር ፋሲልን ጥሪ" ልሞት ነው ማለት ነው። የሰዎች መሯሯጥ ድምፅ ተሰማኝ ትንሽ ቆየት ብሎ

"በአስቸኳይ ወደ ቀዶ ጥገና ክፍል አስገቧት ይህቺን የምታክል ትንሽ ልጅ እንዴት በምጥ እንድትወልድ ታደርጋላችሁ..."

"ይቅርታ ዶክተር ፋሲል እናቷ ልትፈቅድልን አልቻለችም"
በሆስፒታል አልጋ እየገፉኝ እየወሰዱኝ እያለ አይኔን ለመግለጥ ሞከርኩ እናቴን በጭላንጭል አየሁዋት የአልጋውን ጠርዝ ይዛ በለቅሶ እየተከተለችን ነው የሆነ ክፍል አስገቡኝና በሩን ዘጉት ለመጨረሻ ጊዜ የሰማሁት የእናቴ ድምፅ

"ልጄን አድኑልኝ.....ልጄን"

እርስ በርሳቸው ሲነጋገሩ ይሰማኛል
"ከሁለት አንዳቸው አይተርፉም ካልፈጠንን ግን ልጅቷንም በሆዷ ያለውንም ነው የምናጣው... ፍጠኑ.... "

በጭንቅ ግራ ቀኝ ስወዛወዝ ከፊት ለፊቴ ያለው የተሳፋሪ ወንበር ላይ ተደፋሁ። ግንባሬን የመታኝ ወንበር ካለሁበት አስፈሪ ህልም ቀሰቀሰኝ.....ተመስገን በህይወት አለሁ።

እጄን ሰድጄ ሆዴን ዳበስኩት አሁንም ያቺ ትንሽዬ እብጠት ነው ያለችው።

ረዳቱ ጮክ ብሎ"ለምሳ ሀያ ደቂቃ ከዚህ በላይ መቆዬት አይቻልም" እለ። እናቴን ዞር ብዬ ሳያት ወደኋላ ለጠጥ ብላ ተኝታለች። እሷም እንደኔ አስፈሪ ህልም እያየች ይሆን? ትከሻዋን ይዤ ወዝወዝ ሳደርጋት ነቃች።

አውቶብሳችን ሲቆም  ወርደን ምሳ በልተን እና የሚያስፈልገንን ሸማምተን ተመለስን። ከኔ በላይ እናቴ ፊት ላይ የማየው ተስፋ እና ደስታ አቅሌን ሊያስተኝ ደርሷል። ወንበሩ ላይ እንደተቀመጠን አንገቴን ወደሷ ስባ እቅፍ አደረገችኝ..... ልብ ሰርስሮ የሚገባውን የእናት ጠረኗን አሸተትኩት። "አሁን ማን ሊያቆመኝ ይችላል" አልኩ በውስጤ.... ከፊቴ ደጀን ሆና ወኔ ብርታት የምትሰጠኝ.... ሀዘኔ ከኔ በላይ የሚያሳዝናት በደስታዬ የምትደሰት ችግሮቼን ቀድማ የምትጋፈጥልኝ እናት እያለችኝ..... እኮ ማን

፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧***፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

ከወራት በኋላ

አጎቴ ያሰብኩትን ያክል አልጨከነብንም። የራሳችንን ቤት ተከራይተን እስክንወጣ አንድ ክፍል ቤትና ምግባችንን ሰጥቶን ነበር። እኛም ብዙ ጊዜ ሳናስቸግረው ገጠር ያለውን የአባቴ ቤተሰብ ማለትም የአያቶቼ ውርስ የሆነውን የእርሻ መሬት ብዙ አመት መከራዬት ለፈለገ ሰው አከራየንውና ጥሩ ገንዘብ አገኘን። እማዬ ጊዜ ሳታጠፋ ነው በብሩ ከጀበና ቡና ጋር  ጠዋት ቂንጬ ጨጨብሳ እና አንዳንድ ለቁርስ የሚሆኑ ምግቦችን ማታ ደግሞ ድንች  እየቀቀለች ፔንቸራ መሸጥ የጀመረችው። በጥቂት ጊዜ ውስጥ ብዙ ደንበኞችን ማፍራት ቻለች። ስራው ትርፋማ እየሆነ ሲመጣ የራሳችን ቤት ተከራይተን ከአጎቴ ቤት በሰላም ወጣን።

፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧****፧፧፧፧፧፧፧፧፧•፧፧፧፧፧፧፧

በቀጫጫ እና ባልጠነከረ ሰውነቴ ላይ የሆዴ ትልቅነት ሲታይ ልክ በህልሜ እንዳየሁት ያስፈራል "አምላክ ሆይ ህልሜን እውን አታድርግብኝ" በልቤ ፀለይኩ

በምጥ መውለድ አትችልም ተብሎ ስለተወሰነ በቀዶ ጥገና ልጄን ወለድኩ። እነሱ ባይሉም እንኳን በምጥ አልወልድም ብዬ ኡ ኡ ነበር የምለው። ህልሜማ እውን አይሆንም

ሆዴ ውስጥ እያለ እንደ እንቅፋት እያሰብኩ እጠላው የነበረን ልጅ አምጥተው ክንዴ ላይ ሲያስቀምጡልኝ ስፍስፍ የሚያደርግ ስሜት ተሰማኝ። ሴት ልጅ ናት እናቴ ሀዘናችንን የምንረሳብሽ ስትል ስሟን ምናሴ አለቻት።
፨፨፨፨፨፨

ልጄ ትንሽ ጠንከር ስትልልኝ ትምህርቴን ካቆምኩበት ሰባተኛ ክፍል ቀጠልኩ። ቀናት ሳምንታትን ሳምንታት ወራትን ወራትም አመታትን እየወለዱ የአስራ ሁለተኛ ክፍል(የዩንቨርስቲ መግቢያ) ፈተናን ተፈተንኩ።

ልጄም ልክ እንደ እኔ እሳት የላሰች ጎበዝ ተማሪ ሆናልኛለች። ከሷ ጋር ስሆን ቦርቄ ያልጨረስኩት ልጅነቴ ይመጣብኛል እና ሁሌም ቢሆን ከልጄ ጋር ልጅ ነኝ። ያለፈኝን ህይወት በሷ እየካስኩ እንዳለሁ ይሰማኛል።

ነሀሴ መጨረሻ ላይ ውጤት መጣ ተባለና አየን ጥሩ ውጤት ነው ያመጣሁት ግን ሩቅ ሀገር ነው የመደቡኝ ጎንደር ዩንቨርስቲ በምፈልገው ዲፓርትመንት(ህክምና)

እናቴን እና ልጄን ትቼ  እንዴት ችዬ ይህን ያክል እርቃለሁ..

ይቀጥላል....



ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
ከወደዳችሁት ❤️
😘 ያበደው ፍቅሬ😘


ክፍል 7⃣


ነሀሴ መጨረሻ ላይ ውጤት መጣ ተባለና አየን ጥሩ ውጤት ነው ያመጣሁት ግን ሩቅ ሀገር ነው የመደቡኝ ጎንደር ዩንቨርስቲ በምፈልገው ዲፓርትመንት(ህክምና)

እናቴን እና ልጄን ትቼ  እንዴት ችዬ ይህን ያክል እርቃለሁ.. ትምህርቴን መተው እናቴን እንደመቅበር ነው። ሁላችንም ቢከብደንም ግዴታ ሄጄ መማር አለብኝ።
.....
.....
ስራ ቦታዋ ሄጄ ለእናቴ ስነግራት እልልታዋን አቀለጠችው። ደንበኞቿ ምን እንደተፈጠረ ሲጠይቁኝ ነገርኳቸው እንኳን ደስ ያለሽ እያሉ እናቴን አቀፏት.....   ከሁኔታቸው እኔ ሳልሆን እናቴ ውጤት የመጣላት ነበር የሚመስለው....
......
......

ቤት ውስጥ ጎረቤቶቻችንና አንዳንድ የእናቴ ወዳጆች በተገኙበት መጠነኛ የሽኝት ዝግጅት ተደረገልኝ። ልለያት እንደሆነ ያላወቀችው ልጄም ከኔ እኩል ፍንድቅድቅ ብላለች። እንግዶች በልተው ማዕዱ ከፍ ካለ በኋላ እናቴ ወደ መሀል ወጣችና
"አንዴ ፀጥታ...." ብላ ጨብጨብ ስታደርግ ሁሉም ሰው ባንዴ ዝምምም አለ።

"በህይወቴ እንደዛሬ የተደሰትኩበት ቀን የለም ... ልጄ ዩንቨርስቲ ገባችልኝ። ይሄ ከምንም በላይ ትልቁ ህልሜ ነው። እዛ ሄዳ በስኬት እንደምትመለስ እተማመንባታለሁ። ትልቅ ነገርም ባይሆን ይሄን ስጦታ በእናንተ ፊት እሰጣታለሁ"  ወደኔ መጥታ ጉንጬን አገላብጣ ከሳመችኝ በኋላ የተጠቀለለውን ስጦታ ሰጠችኝና"ክፈቺው..." አለችኝ። የተጠቀለለበትን ወረቀት ስከፍተው ሞባይል ከነ ቻርጀሩ ብቅ አለ። አላመንኩም እናቴ ለኔ የእጅ ስልክ ገዛችልኝ... በዚያን ጊዜ አብዛኛው ሰው ባለ ሞባይል እየሆነ ቢሆንም እኔ ይኖረኛል ብዬ ግን አላሰብኩም ነበር።

"አመሰግናለሁ እናቴ.... ደግሞ ቃል እገባልሻለሁ... አኮራሻለሁ"

"እተማመንብሻለሁ የኔ ጀግና.... ሳትሳቀቂ በናፈቅሺን ሰዓት መደወል ብቻ ነው...."ወደ ደረቷ ወስዳ ጥብቅ አድርጋ አቀፈችኝ። ይሄን እቅፍ እኮ ስወደው..............
ቃል ባትናገር እንኳን በእቅፏ ብቻ ብዙ መልዕክት የምታስተላልፍልኝ ይመስለኛል።
"በርቺ....
ባንቺ እተማመናለሁ....
እኔ አለሁልሽ...
እወድሻለሁ......." ብቻ ስታቅፈኝ ከዚህም በላይ ብዙ የምትለኝ ይመስለኛል።
..............

የምወዳት ልጄን እና እናቴን ተሰናብቼ ወደ አፄ ፋሲል ሀገር ጥንታዊቷ ጎንደር ተጓዝኩ ።
..........

ምዝገባ እና ሌሎች ፕሮሰሶች አልቀው ትምህርት የምንጀምርበት ቀን ደረሰ...... የመጀመሪያ ቀን እንደመሆኑ አብዛኛው ተማሪ ቀድሞ ክፍል ተገኝቷል ከነኛ መሀል አንዷ እኔ ነኝ።
.....
ከደቂቃዎች በኋላ
"ይሄ ሸበላ ብቻ እንዳይሆን የሚያስተምረን" ከኋላዬ ያለችው ልጅ ወደ ጆሮዬ ተጠግታ አንሾካሾከችልኝ። ከንግግሯ እኩል ቀና ብዬ ወደ ፊት ለፊቴ አየሁ..... " ዋው ውበት ..... ዋው ቁመና.... ዋው ደረት...." ብዙ ዋው የሚያስብሉ ነገሮችን ያሟላ ሸበላ ሰው.....
......
"እሺ ዛሬ ብዙም የምንማረው ነገር አይኖረንም እርስ በርሳችን እንተዋወቅና ኮርስ አውትላይን እሰጣችኋለሁ...... እምም ከፊት ልጀምር ስምሽን አስተዋውቂን እስኪ...." ምኑ ነው ምን አለ እስከምረጋጋ እንኳን ሌላ ሰው ቢጠይቅ

"ሩት በዛብህ እባላለሁ የመጣሁት ከአዲስ አበባ" ጣቱን ከኔ ቀጥሎ ወዳለችው ልጅ ጠቆመ

"መቅደስ ገዛህኝ..... ከሀዋሳ
ተፈሪ ይልማ...... ከደሴ
አብሳላት አበበ.... ከአዳማ
የትናዬት ዘመረ..... ከአዲስ አበባ......" ሁሉም ስማቸውን እና የመጡበትን ከተማ ተናገሩ ሁላችንንም ከሰማ በኋላ

" የኔ ስም ደግሞ ዮናታን ይባላል የ...." ከዚህ በኋላ ያለውን አልሰማሁትም .... ዮናታን.... ዮኒ ስሙ ደስ ይላል መልኩም ደስ ይላል። ሳላውቀው ስለሱ ብዙ አሰብኩ.... እጄ ላይ ያረፈ ወረቀት ከሀሳቤ አነቃኝ

"ያልኩትን ሰምተሽኛል ሩት" ድንብርብሬ ወቶ አይን አይኑን አየው ጀመር እሱም ትንሽ ካየኝ በኋላ

" ተወካይ እስክትመርጡ ድረስ አንቺ ተወካይ ሆነሽ እነኝህን ወረቀቶች ለሁሉም አዳርሺ...." መልሴን ሳይጠብቅ ክፍሉን ለቆ ወጣ።   እንዴ ቆይ ደግሞ ስሜን እንዴት ባንዴ ያዘው..... ይገርማል
........
.....

" እና እኔንም አፈዘዘኝ እያልሽኝ ነው" አለችኝ ከፊት ለፊቴ መጥታ

"ይቅርታ እህቴ ምን......"

."ቅድም አልሰማሽኝም የትናየት.... የትናዬት ነው ስሜ"

"እሺ የትናዬት የምትይው አልገባኝም"

"ቀስ ብሎ ይገባሻል ለማንኛውም የራሴን ልውሰድ." አንዱን ወረቀት አንስታ እየተቆናጠረች ከክፍሉ ወጣች።

"ወይ አምላኬ ስንት አይነት ሰው አለ" ብዬ ስዞር ሁሉም አፍጠው የሚያዩኝ እኔን ነው።


ይቀጥላል....


ቻናላችንን ይቀላቀሉ
         ┏━ 🦋 ━━━━ 🦋 ━┓
       @yefeker_tiksoche
       @yefeker_tiksoche
       @yefeker_tiksoche
         ┗━ 🦋 ━━━━ 🦋
ከወደዳችሁት ❤️
ከሰው አትጠብቅ !

ለችግርህ ጊዜ የራቁህ ለስኬትህ ዙሪያህን ቢከቡህ አትደነቅ፤ በከባዱ ጊዜህ ትዝም ያላልከቸው በምርጡ ጊዜ ፍቅር በፍቅር ቢሆኑ እንዳይገርምህ።

የዛሬም ሺ አመት ሰዎች እንደዚህ ነበሩ፤ ዛሬም ነገም እንዲህ ናቸው። ስለዚህ ከሰው ምንም አጠብቅ! ከፈጣሪህ ቀጥሎ ራስህን እመነው! ራስን እንደመጠራጠር ህልም ገዳይ ነገር የለም!
ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች የጀመርነዉን ታሪክ በፈተና ምክኒያት ተቁዋርጦ ስለነበር ዘሬ ማታ ከቆመበት እንጀምራለን🙏🙏🙏
😘 ያበደው ፍቅሬ 😘


ክፍል 8⃣

ህይወት ልክ በምኞታችን  ውስጥ  እንዳሰብናት ቀላልና ጣፋጭ አይደለችም።  ልንመራት ያወጣነውን እቅድ አስጥላ በራሷ ምህዋር ላይ ታሽከረክረናለች። እምቢ ብለን ብናስቸግራት እንኳን ወይ ከራሳችን እቅድ ወይም ሽክርክሪቱ ከሚያመጣው ነገር ሳንቋደስ ሜዳ ላይ እንቀራለን።

ዩንቨርስቲ መግባትን ሳስብ የሚታየኝ ጠንክሮ መማርና መማር ብቻ ነበር። ግቢ ውስጥ ሆኜ ከትምህርቴ የበለጠ ቦታ እሰጠዋለሁ ብዬ የማስበው ምንም ነገር አልነበረም። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለሁ የሆነ ሰው መጥቶ ይህን ጥያቄ ቢጠይቀኝ በመጠየቁ ልናደድበት እችል ነበር። ዛሬ ግን ያን እምነቴን የትላንት እቅዴን ሊያከሽፍ የሚችል ፍቅር ያዘኝ። ያውም ውድድር የበዛበት ፍቅር.....
አብሬው ልሁን ብዬ ባስብ እንኳን ከሱ እኔን አለማፍቀር ውጪ ከደርዘን በላይ ሴቶች ጋር መጋፈጥ ይኖርብኛል..... ያውም እኔ የማውቃቸው ብቻ።

ያለኝ አማራጭ አንድ ብቻ ነው ቢከብደኝም ስሜቴን አምቄ መያዝ እና በሰላም ትምህርቴን መቀጠል።  ምንም ሳይተነፍሱ ሁሉንም  በልብ መያዝ ከምንም በላይ ህመም ነው.... በተለይ ደግሞ ፍቅር ሲሆን...

ብዙ ጊዜ ይሄን አስባለሁ ለእናቴ ይሄ አይገባትም አይደል? ... ስኬቴን ለምትናፍቅ እናቴ ስል ከመጋፈጥ ይልቅ መሸሽን መርጫለሁ። የምሸሽበት ምክንያት ዋናው ቁም ነገሩ እኮ ማፍቀሬ አይደለም ፍቅር በየትኛውም ጊዜ እና ሁኔታ ውስጥ ሊከሰት የሚችል ስሜት ነው። ችግሩ ለዚህ ፍቅር ስል ብፋለም ለትምህርት የሚሆን ነፃ አይምሮ ላገኝ እችላለው ወይ?  የበለጠው ችግር ደግሞ ያፈቀርኩት ሰው ሁሉንም ቀማሽ መሆኑ ነው።
፧፧፧፧፧፧ ፧፧፧፧፧፧፧ ፧፧፧፧፧ ፨፨፨፨ ፨፨፨፨

ከዛን ቀን ጀምሮ ማለትም ከመጀመሪያ የትምህርት ቀናችን ጀምሮ በዮኒ ፍቅር ተለክፊያለሁ። ፍቅር እንደያዘኝ እንኳን እያወኩ ላለማመን ከራሴ ጋር ለወራት ተከራክሪያለሁ። የትናዬት በየቀኑ እኔን ማስበርገግ ስራዬ ብላ ከያዘች ቆይታለች። በተለይ ዮናታን አስተምሮን ሲወጣ ወይ ከጎኔ ናት ወይም ከፊት ለፊቴ.... እልፍ ጊዜ እኮ አብረው አይቻቸዋለሁ... ብዙ ጊዜ ቢሮው ስትገባ ያዩዋት ነግረውኛል...... እኔ ደግሞ በተቃራኒው ከሱ ጋር የሚያገናኘን ድልድይ ሁላ ላፈርስ የምሞክር ሰው ነኝ። ለምን ይሄን ያክል የቤት ስራ እንደሆንኩባት አላውቅም። አሁን ግን መሮኛል ፀብ ላለመፍጠር እያልኩ እንደፈሪ መታየት መሮኛል።

ዛሬም እንደለመደችው ከጥሩ ትወና ጋር የአሽሙር ንግግሯን ተናግራኝ ከክፍሉ ወጣች። ብሽቅ ብዬ ወረቀቶቼን ሰብስቤ ተከትያት እየወጣሁ እያለ አንድ ሰው ከኋላዬ ያዘኝ። ዞር ስል ቢኒ ነው ከተማሪዎች ሁሉ የተለየው ዝምተኛ ልጅ።

"አቤት ቢኒ" አልኩት ኮስተር ብዬ... ግንባሬን አይቶ እጁን ከክንዴ ላይ አነሳ እና

"ይቅርታ ሩት.... ጣልቃ ልገባ ፈልጌ አይደለም ግን እኔ የታየኝን አንድ ነገር ልበልሽ..."

"ምን"

"የትናየት ካንቺ የምትፈልገው ይህንን ነው... ማለትም ፀብ.... ከሷ የተሻልኩ ነኝ ብለሽ ካሰብሽ እቅዷን ቀድመሽ አክሽፊባት...."

"ማለት..... እንዴት አድርጌ"

"እኔ አግዝሻለሁ..." እንስማማ አይነት እጁን ዘረጋልኝ። ሳላወላውል ጨበጥኩት.... ተገኝቶ ነው ይቺን የሰው ቆንጥር ከአጠገቤ የሚያርቅልኝ

፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
ወደ መነሻ

አስታወሳችሁ መነሻዬን እንጂ መድረሻዬን ሳላውቅ እግሬ ወደመራኝ እየሄድኩ ነው ብያችሁ ነበር። አዎ መንገዴን አላቋረጥኩም።  ከእርምጃዬ እኩል ትዝታዬ በልቤ ውስጥ ይፈሳል በአይምሮዬም ውስጥ ይመላለሳል።

ከተማውን ሙሉ ለሙሉ መልቀቄን ያስተዋልኩት ከፊት ለፊቴ ያለው ሰፊ የግጦሽ ሜዳ ላይ የእረኛዎችን ድምፅ ስሰማ ነው።

ድንገት እኔን አልፎ ሲጥጥ ብሎ የቆመ መኪና ከሀሳቤ አንቅቶ አስበረገገኝ። ቅድም ሳይገጨኝ ያለፈው መኪና.... ከውስጡ አንድ ሰው ወረደና ወደኔ መጣ። በድንጋጤ ደርቄ ነው የቀረሁት

"ሩት በዚህ መልኩ አገኝሻለሁ ብዬ አልጠበኩም ነበር" አጠገቤ መጥቶ ክንዴን ያዘኝ ልክ እንደመጀመሪያው ቀን ልዩነቱ ያኔ ከኋላ አሁን ግን ከፊት ለፊት መሆኑ ነው

"ቅድም አንተ ነበርክ"

"አዎ ግን አንቺ መሆንሽን ለመለየት ጊዜ ወሰደብኝ ሩቴ በጣም ተጎሳቁለሻል  አንቺ እንደሆንሽ ያወኩት "ዞር በሉልኝ አስማሳዮች" ብለሽ ስትናገሪ በሰማውት ድምፅሽ ነው አረማመድሽ ደግሞ አረጋገጠለኝ። እናም ተከተልኩሽ.... የምትሄጅበትን መድረሻሽን ለማወቅ ተከተልኩሽ ግን እንደማየው.......

"ቢኒ እኔ...." ቃላቶቼ አፌ ላይ ተንገዋለሉ። ወደራሱ አስጠግቶ እቅፍ አደረገኝ።

"እሽሽሽሽሽሽሽ ይገባኛል ምንም አታስረጂኝ"

በህይወት መንገድ ላይ ለሁለተኛ ጊዜ ተገናኘን..... እኔና ቢኒ


ይቀጥላል....
         ┏━ 🦋 ━━━━ 🦋 ━┓
       🥀@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
         ┗━ 🦋 ━━━━ 🦋
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
ከወደዳችሁት ❤️
😘 ያበደው ፍቅሬ 😘


ክፍል 9⃣
አንዳንዶች ለወደዱት ብቻ ጥሩ ይሆናሉ.... አንዳንዶች ደግሞ እንዲሁ በተፈጥሯቸው ጥሩነትን ይታደሉታል። ቢኒ እንደዛ ነው መልካምነትን የታደለ ጥሩ ልብ ያለው ልጅ ነው። ድሀ ወይም ሀብታም፣ ክርስቲያን  ሙስሊም ወይም ሌላ እምነት፣ ቆንጆ ወይም መልከ ጥፉ፣ ቢኒ ጋር መስፈርት አይደሉም። ለሁሉም እኩል ፍቅርና እንክብካቤ ሲሰጥ ታዩታላችሁ..... ግቢ ውስጥም ሆነ ከተማ ውስጥ ያሉ የበጎ አድራጎት ስራዎች አያመልጡትም.....

"ቢኒዬ ግን እርግጠኛ ነህ እዚህ ብሆን አረብሽህም.." እረጅም ሰዓት ተጨቃጭቀን እስከፈለኩ ድረስ ቤቱ እንድኖር ከነገረኝ በኋላ ሀሳቡን ቢቀይር ብዬ ጠየኩት

አጠገቤ መጣና ቁጭ አለ.... እጆቹን ልኮ ሁለት እጆቼን ያዘና አይን አይኔን እያዬ "ሩቴ አንቺ ጓደኛዬ ነሽ... ጓደኝነት ውስጥ ደግሞ እኔ የሚባል ነገር የለም በተለይ እኔ ካንቺ እኔን ላስቀድም አልችልም ምክንያቱም......" ከንፈሮቹ ተንቀጠቀጡ።

"ምክንያቱም ምን ቢኒዬ" እጄን ለቆ ተነሳና ጀርባውን ሰቶኝ ከመስኮት ዳር ቆመ።

"ሩት ጊዜ የነገሮች ጌታ ነው ብዬ አምናለሁ... እናም ሁሉም በጊዜው ሲሆን ደስ ይላል። አሁን ከኔ ምክንያት በላይ ያንቺ ሁኔታዎች ናቸው መስተካከል ያለባቸው...." ክትክት ብዬ ሳቅሁ... የእብደት ሳቅ
ከሳቄ በኋላ

" እስኪ ንገረኝ ምኑን ነው የምታስተካክለው.... እናቴን ልጄን ወይስ ከሀዲው ባሌን ማንን መልሰህ ልታመጣልኝ የምትችል ይመስልሀል..." ድጋሚ አመመኝ... መቋቋም አቃተኝ... በሁለት እጄ ጭንቅላቴን ጥፍንግ አድርጌ ያዝኩት። የሆነ ሽክርክሪት ውስጥ እንዳለሁ ይሰማኛል ዥውውውውውውውው.... ሳቅ ከዛ ደግሞ ዝምምምምታ.... ከዛ ደግሞ ሌላ ሳቅ.... ይሄኛው አለም የተሻለ ይመስለኛል።

የሆነ ሰው አፌ ውስጥ የሆነ ነገር ለማስገባት ታገለኝ አልከለከልኩትም ዋጥኩት ከዛ ሁሉም ነገር ፀጥ አለ።

ምን ሰዓት እንደተኛሁ ባላውቅም ራሴን ጋቢ ለብሼ ሶፋ ላይ ተኝቼ አገኘሁት። ቀና ብዬ ተስተካክዬ ቁጭ ስል ቢኒን ከእግሬ ስር ቁጭ ብሎ መፅሀፍ ቅዱስ ሲያነብ አየሁት።

"ይቅርታ ቢኒ ረበሽኩህ መሰለኝ.." መፅሀፍ ቅዱሱን ዘግቶ ከሳመ በኋላ የኔንም ግንባር ነካ አደረገበትና ተነስቶ አስቀምጦ ተመለሰ።

"ሁለተኛ እንደዚህ እንዳትይኝ ማስቸገር ገለመሌ የሚባል ታሪክ የለም ያራቅሺኝ ነው የሚመስለኝ..."

"እሺ በቃ አይለመደኝም..... ይልቅ እስኪ ንገረኝ የውጪ ቆይታህ እንዴት ነበር የተመለስከውስ መች ነው"

"ቆይታዬን በደፈናው ጥሩ ነበር ልበልሽ መሰለኝ። የተመለስኩት ሁለት ወር አካባቢ ሆነኝ ግን ቀጥታ ቤተሰብ ጋር ክፍለ ሀገር ነው የሄድኩት ከተመለስኩ ገና ሳምንትም አልሞላኝ"

"እና ለምን ልትፈልገኝ ወደ ቤት አልመጣህም..." ክፍት ነው ያለኝ ምንም እንኳን የሱን ስም ሲሰማ ባሌ ቢናደድም ቢኒ ላጣው የማልፈልገው ጓደኛዬ ነው እና እንዴት...

"ወዳንቺ ጋር እየመጣሁ እያለ እኮ ነው መኪና ውስጥ የገባሽብኝ"

"ኦ እሺ እንደዛ ከሆነ"

"አልተዋጠልሽም አይደል ሩቴ ብዙ ጊዜ እንዳልደወልኩልሽ አውቃ..." አቋረጥኩት

"ምን ብዙ ጊዜ ትላለህ ከሄድክ ጀምሮ ሁለቴ ብቻ እኮ ነው የደወልከው.... እናም አልዋሽህም ተቀይሜሀለሁ"

"ምክንያቴን ስታውቂ እንደምትረጂኝ ስለማውቅ ችግር የለውም.... የሆነ ነገር መብላት አለብን ምን ትፈልጊያለሽ..." አለኝ ወደ ኪቺን እየገባ

"ፍላጎትሽን አትናገሪም ካለዛ ዱባ ወጥ ነው የምሰራው ሀ ሀ ሀ" ሽርጡን አገልድሞ ብቅ አለ

" ዱባ ስራና ሶስት ቀን ውጪ አሳድሬ ነው የማበላህ.... አንተ ደግሞ ሼፍ መስለህ የለም እንዴ"

"ነይ አሁን ተነሺ ቢያንስ ዱባውን እንኳን በመክተፍ አግዢኝ" ከስሙ ጭምር እንደምጠላው ስለሚያውቅ እኮ ነው ...ዱባን....

"ሀ ሀ ሀ አንተ እብድ ትቀልድብኛለህ አ" ከረጅም ጊዜ በኋላ ሳቅሁ
......


፨፨፨ ፨፨፨፨ ፨፨፨፨
ጎንደር ዩንቨርስቲ ሁለተኛ አመት

"ቢኒ ዮናታንን እወደዋለሁ ከዚህ በላይ መቋቋም አልችልም እናም እነግረዋለሁ"

"ሩት ዮናታንን ታውቂዋለሽ.... እሺ አለሽ እንበል ከዛ እነኝህን ሁሉ ሴቶች ትቶ ካንቺ ጋር ብቻ የሚሆን ይመስልሻል"

"አላውቅም ግን እድሌን ልሞክር.."

"ተይ ሩት ይቅርብሽ"

"አይሆንም ቢኒ እድሌን እሞክራለሁ" ይሄን ሁሉ የምንጨቃጨቀው ዮናታን የሚያመሽበት ጭፈራ ቤት በር ላይ ሆነን ነው። ወደ ውስጥ ገባሁ... አይኔን ዞር ዞር እያደረኩ ፈለኩት ጥግ ሶፋ ላይ ከአንዲት ሴት ጋር የተሰፋ ያክል ተጣብቋል.... በደንብ ቀረብኳቸው... አንገቱ ስር ስማው ቀና ስትል አይን ለአይን ተገጣጠምን... የትናዬት....

ደንዝዤ አንደቆምኩ የሆነ ሰው እጅ ትከሻዬ ላይ አረፈ "የኔ ቆንጆ በዛኛው በኩል ቦታ አግኝቻለሁ.... እንሂድ አይደል"  ውጪ ቆይ አላልኩትም ነበር.... ቢሆንም ግን ወሳኝ ሰዓት ላይ ነው የደረሰው።

"አየሽ አይደል በራስሽ ላይ ምን እያመጣሽ እንደሆነ"

"ሲጀመር እሱን ብቻውን አገኘዋለሁ ብዬ ማሰቤ ነው የኔ ጥፋት..." እርር ድብን ብሽቅቅቅ ብያለሁ እኮ

ይቀጥላል....
#Share
          ┏━ 🦋 ━━━━ 🦋 ━┓
       @yefeker_tiksoche
       @yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
         ┗━ 🦋 ━━━━ 🦋
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
ከወደዳችሁት ❤️
😘 ያበደው ፍቅሬ 😘


ክፍል 1⃣0⃣

"አረጋጊው እንጂ ውዷ ጉበትሽን መትፋት አማረሽ እንዴ"

"ተወኝ ባክህ ልጠጣበ" ከነ ጠርሙሱ አንስቼ ለመጠጣት ስሞክር ከእጄ ቀማኝና

"ነይ በቃ እንሂድ ግቢ ይዘጋል" አለኝ

"የትም አልሄድም ተወኝ"

"ይሄንን ነው መፍራት... ኧረ ሩት በፈጠረሽ..." ጠርሙሱን ተቀብዬው እየተንገዳገድኩ እነሱ ወዳሉበት ቦታ ሄድኩ....

፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ፧፧፧፧፧

"ሩት ሩት አንቺ ሩት" የእናቴ ድምፅ መሰለኝ.... እየጠራችኝ ነው።

"አቤት እማ መጣሁ" ብዬ ከተኛሁበት ለመነሳት ስሞክር ሀይለኛ ራስ ምታት አናቴን ይዞ እየፈለጠኝ ነው። ጭንቅላቴን በሁለት እጄ ጥፍንግ አድርጌ ይዤው ከቆየሁ በኋላ አይኔን በደንብ ከፍቼ ሳይ ያለሁት እናቴ ቤት አይደለም....

ከፊት ለፊቴ ቢኒ ተቀምጦ የማደርገውን ነገር ያያል።

"ኡፍፍፍፍ የት ነው ያለሁት ምን ተፈጥሮ ነው.... ቆይ እማዬ የጠራችኝ አልመሰለኝም.."

"ባክሽ እኔ ነኝ የጠራሁሽ ክፍል ልቀቁ እየተባልን ነው ተነሺ..." ቢኒ እንደዚህ አውርቶኝ አያውቅም....

"ምንድነው ቢኒ ችግር አለ እየተነጫነጭክ እኮ ነው ምነው ማታ አስቀየምኩህ እንዴ.... ማታ.......... ቆይ ቆይ እንዴት ወደዚህ ልመጣ ቻልኩ? ማነው ያመጣኝ? ማለት ምን ተፈጥሮ ነው?..." የጥያቄ መአት አከታተልኩበት

"በመጀመሪያ ተነሽና ታጠቢ ከዛ ወደ ግቢ እንመለስና ዶርም ገብተሽ እረፍት አድርጊ ከዛ ተገናኝተን ጥያቄዎችሽን እመልስልሻለሁ እስከዛው ትዝ የሚልሽ ነገር ካለ ራስሽ ጥያቄሽን መመለስ ትችያለሽ" እንዴ ምንድነው ጉዱ ቢኒ እንደዚ ከረር ብሎ አይቼው አላውቅም ጭራሽ የማላውቀው ሰው ነው የሆነብኝ። ተጨማሪ ጥያቄ ሳልጠይቅ ጭንቅላቴን ደግፌ እየተጎተትኩ መታጠቢያ ቤት ገባሁ።
ሰውነቴ ስብርብር ያለ ያክል እየተሰማኝ ታጥቤ ጨረስኩ

፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨

"አንተ ቢኒ ግን አልተኛህም እንዴ አይንህ እኮ በርበሬ ነው የሚመስለው" ወደ ግቢ እየሄድን ጠየኩት

"ሩት ፊቴን አንብበሽ መረዳት ከቻልሽ እባክሽ አሁን ምንም ማውራት አልፈልግም.... እና ካወራሁም በጣም አስከፋሻለሁ ስለዚህ እኔም ተረጋግቼ አንቺም እረፍት አድርገሽ የተለመደው ቦታ ዘጠኝ ሰዓት እንገናኝ... ቻው" መልሴን ሳይጠብቅ ትቶኝ ሄደ። ግራ እንደተጋባሁ ዶርም ገብቼ ጥቅልል ብዬ ተኛሁ ግን እንቅልፍ ከየት አባቱ ወደ ግራ ወደቀኝ እየተገላበጥኩ አሰብኩ.... አሰብኩ.... አሰብኩ... ግን ትላንትና ማታ ምን እንደተፈጠረ ማስታወስ አቃተኝ

፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ፧፧፧፧፧፧፧፧ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ፧፧፧፧፧፧፧ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ፧፧፧፧፧፧፧

ከቀጠሯችን አስር ደቂቃ ቀድሜ ተገኘሁ... ብዙም አላስጠበቀኝም። እንደመጣ

"በናትህ ቢኒ እኔ ምንም ማስታወስ አልቻልኩም የቀጠሯችን ሰዓት እስከሚደርስ ድረስ ሳልተኛ ብዙ አሰብኩ ግን ምንም ትዝ አይለኝም"

"የእውነት ምንም አታስታውሺም"


" እነሱን አይቼ ተናድጄ ካንተ ጋር እየጠጣሁ ነበር ከዛ እነሱ ወደተቀመጡበት እንደሄድኩ ትዝ ይለኛል ከዛ ውጪ አዎ ምንም አላስታውስም"

"እሺ ጥሩ እንደዛ ከሆነ እኔ ላስታውስሻ....
በጣም ሰክረሽ ነበር ጠርሙሱን ቀምቼሽ ወደ ዶርም እንሂድ ስልሽ  አልሰማሺኝም ተቀብለሽኝ እየተንገዳገድሽ ዮናታንና የትናዬት ወደተቀመጡበት ቦታ ሄድሽ። ሁኔታሽ ስላላማረኝ ተከተልኩሽ... ከዮናታን ውጪ ማንም አልነበረም እናም አንዴ እየሳቅሽ ሲልሽ እያለቀሽ እንዴት እንደምትወጂው ለእናትሽና ለአላማሽ ብለሽ ከሱ እንደራቅሽ ነግረሽው የየትናዬትን ተንኮል እየነገርሺው እያለ ከየት መጣች ሳትባል ፀጉርሺን ጨምድዳ ይዛ በጥፊ መሬት አነጠፈችሽ..."

"ምን ጭራሽ ተደባድቤም ነበር" አሁን የተመታሁ ይመስል ጉንጬን በእጄ ዳበስኩት

"አዎ.... ያም ብቻ ሳይሆን በወደቅሽበት ትንሽ መታሻለች... ብዙም ሳይቆይ ሰዎች አገላገሏችሁ እና እኔ አንቺን ይዤሽ ከዛ ወጣን እና አልጋ ፈልጌ ያዝኩ አንቺን አስተኝቼሽ ትንሽ ቆዬት እንዳልኩ የክፍሉ በር ተንኳኳ ሄጄ ስከፍት ዮናታን በር ላይ ቆሟል..."

"ምን...... ማለት ለምን ነበር የመጣው" ወይኔ ነገሩን ሀሉ በአንድ ቀን ስካር አበላሸሁት ማለት ነው። ቢኒ ለመናገር ሲታሽ አየሁት

"ምንድነው እሱ ቢኒ ንገረኝ እንጂ..."

"ይሄ እኔን ይጎዳኝ ይሆናል አንቺን ስለሚጠቅምሽ ግን ልንገርሽ"ለአፍታ ዝምምም አለ

"ምን ቢኒ" ልቤ ስቅል አለ

"ዮናታን እንደምናስበው አይነት ሰው አይደለም"

"ማለት" አልኩት ግራ ተጋብቼ

"ማለትማ ከየትናዬት ጋር ያላቸው ግንኙነት እኛ እንደምናስበው አይደለም...."

ይቀጥላል......

ቻናላችንንይቀላቀሉ
         ┏━ 🦋 ━━━━ 🦋 ━┓
       @yefeker_tiksoche
       @yefeker_tiksoche
       @yefeker_tiksoche
         ┗━ 🦋 ━━━━ 🦋
‌‌‌‌‌
ከወደዳችሁት ❤️
😘 ያበደው ፍቅሬ 😘


ክፍል 1⃣1⃣

"ዮናታን እንደምናስበው አይነት ሰው አይደለም"

"ማለት" አልኩት ግራ ተጋብቼ

"ማለትማ ከየትናዬት ጋር ያላቸው ግንኙነት እኛ እንደምናስበው አይደለም...."

"እኔ ምንም እየገባኝ አይደለም ቢኒ ምንድነው እያወራህ ያለኸው"

"ተረጋጊ እነግርሻለሁ.... ዮናታን የያዝነው ክፍል ድረስ መጥቶ እንድናወራ ጠየቀኝ.... እሺ ብየው ተያይዘን ወደ ሆቴሉ ባር አመራን እናም ቁጭ ብለን ያልጠበኩትን ነገር ነገረኝ"

"ቀጥል ምን አለህ"

፧፧፧፧፧፧፧፧ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ፧፧፧፧፧፧፧፧

#ምሽት_8_ሰዓት_ላይ

የሆነውን ሁሉ እኔ ነኝ የምተርክላችሁ.... ቢኒያም

ከዮናታን ጋር ወደ ባሩ ከወረድን በኋላ መጠጥ አዘዘ እና
"የውልህ ቢኒያም ተረጋግተህ እንድትሰማኝና ከቻልክ እንድታግዘኝ እፈልጋለሁ..."

"ለማንኛውም የምትለኝን ልስማህ" እስከዚህ ድረስ እንኳን አብሬው የመጣሁት ድጋሚ ካስተማረን F እንዳያስታቅፈኝ በሚል ፍራቻ ነው

"ሁሉም ሰው የሚያውቀው እኔ ሴት አተራማሽ እንደሆንኩ ነው። በእርግጥ እውነታም አለው ጥቂት ከማይባሉ ሴቶች ጋር ግንኙነት ነበረኝ ግን ነበር ነው ከ2 አመት በፊት በመጀመሪያ እይታ አንዲት ልጅ ልቤ ውስጥ ገባች። እናም ልክ ለሌሎቹ እንደሚሰማኝ ተራ ስሜት ነው ብዬ የነበረው ህይወቴን ለመቀጠል ሞከርኩ ግን እንደድሮው መሆን አቃተኝ። ለተወሰነ ጊዜ ስወዛገብ ከረምኩና ፍቅሬን እንዴት መግለፅ እንዳለብኝና እሷን የኔ እንዴት እንደማደርግ ማሰብ ጀመርኩ።

ልጅቷ ኮስታራ እና የማያስቀርብ ፊት ነው ያላት ያለኝ አማራጭ አብራ ከምትማራቸው ሴቶች ስለሷ ሊነግረኝ የሚችል ሰው ፈልጌ መቅረብ ነበር እናም የትናዬትን ቀረብኳት...."

"ሰውዬ ስለምን እያወራህ ነው" እዚህ ጋ መምህር መሆኑን ረሳሁ

"ቢኒያም ለኔ ሁሉም ነገር የተገለፀልኝ ዛሬ ነው.... እና ከቻልክ ተረጋግተህ ስማኝ"

"ከየትናዬት ጋር ከተቀራረብን በኋላ በተደጋጋሚ ቢሮዬ እየጠራኋት ስለ ሩት እንድትነግረኝ አደርጋት ነበር።"

"ምን እያልክ ነው እና ሩትን አንተም ታፈቅራታለህ" ማመን ከበደኝ

"አዎ ያውም በመጀመሪያ እይታ ነው ያንበረከከችኝ ለማንም ሴት እንደዚህ ሆኜ አላውቅም። የኔ ብትሆን ብዬ በምናቤ ስስላት የነበረችን ልጅ ነው በአካል ያገኘኋት"

"እሺ ከዛስ ምን ተፈጠረ"

" የትናዬት እንኳን ጠርቻት ሳልጠራትም እየመጣች ብዙ ነገር እንዳውቅ አደረገችኝ። የምትነግረኝ ነገሮች ግን ሩትን እንድቀርብ ሳይሆን እንድፈራ እና እንድሸሽ የሚያደርግ ነበር።"

"ምን ብላህ ነው"

"በመጀመሪያ ከሷ ጋር ኢለመንተሪ ጀምሮ አብረው እንደተማሩ እና እንደምትታየው ሳይሆን ውስጥ ውስጡን ወንድ አተራማሽ እንደሆነች ነገረችኝ። አላምንም ስላት በማስረጃ አረጋገጠችልኝ።"

"መቼ ነበር ያረጋገጠችልህ ማለቴ የት"

"ከአመት በፊት ካንተ ጓደኛ ጋር ቤርጎ ሲገቡ በአይኔ በብረቱ አየሁ እናም የምትለኝ እውነት እንደሆነ አረጋገጥኩ"

"የውልህ ዮናታን ያየኸው እውነት ነው ግን እንደምታስበው አይደለም። ጓደኛችን በሀይሉን ፍቅረኛው ከድታው ሌላ ሰው ጋር ሆነች እናም እሷን ማስቀናት እንደሚፈልግ ነገረን.... እኔም ለሩት ነገርኳትና እምቢ ብትልም በግድ አሳመንኳት ከዛ ፍቅረኛው የምታይበትን ሁኔታ አመቻችተን አብረው ወደ ክፍል ሲገቡ እንድታያቸው አደረግን።  ግን አንተ እዛ እንደነበርክ ማንም አላወቀም እንዴትስ ልትገኝ ቻልክ"

"የትናዬት ናት አላምንም ስላት 'ከቢኒያም ጋር ፍቅር ፍቅር እየተጫወተች የገዛ ጓደኛው ጋር ትማግጥበታለች' አለችኝ ማረጋገጥ ከፈለክ ብላ ወደዛ ቦታ ወሰደችኝ እና በአይኔ እንዳይ አደረገችን በሰዓቱ ራሴን መቆጣተር አቅቶኝ ነበር እናም እሱን ልደበድብ እሷን ልሰድብ ስራመድ የትናዬት አስቆመችኝ.... ከዛ በኋላ የምትለኝን ሁሉ አምናት ነበር እስከ ትላንትና ድረስ..... አሁን ግን ሁሉንም ከራሷ ከሩት ነው ማረጋገጥ የምፈልገው"
ነገሩ ካሰብኩት ውጪ ሆነብኝ የትናዬት ተንኮለኛ ብትሆንም ይህን ያክል ርቃ ትሄዳለች ብዬ ግን አላሰብኩም ነበር።

"እሺ ሌላስ ምን ነገረችህ"

"አንተ ፍቅረኛዋ እንደሆንክ እና አዲስ አበባ ከሌላ የወለደቻት ልጅ እንዳለቻት"

"ምንድነው የምታወራው እኔ ከሩት ጋር አብሬ ስለምታይ ፍቅረኛዋ ነው ብትል እሺ ግን ልጅ ከየት ፈጥራ ነው የነገረችህ...." ኪሱን በርብሮ የሆነ ፎቶ አወጣና እጄ ላይ አስቀመጠልኝ። ሩት ልጅ አቅፋ.....

"ግን እኮ እህቷም ልትሆን ትችላለች" ካልኩ በኋላ ለእናቴም ለአባቴም አንድ ነኝ ብላ የነገረችኝ ትዝ አለኝ።

"አይደለችም ልጇ ነች ይሄን አረጋግጫለሁ ግን አንተ የምታውቅ ነበር የመሰለኝ"

"ኧረ በፍፁም ግራ እያጋባህኝ ነው" ፎቶውን ተቀብሎኝ ወደ ኪሱ ከተተና

"ቢሆንም ይሄ ጉዳዬ አይደለም.... ለሷ ያለኝን ፍቅር ያለፈ ታሪኳ ሊቀይረው አይችልም የሚያሳስበኝ የአሁኑ ነው..." ግንባሩን አሸት አሸት እያደረገ ትንሽ ከቆየ በኋላ

"ቢኒያም አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ እናም ሳትዋሽ መልስልኝ" አለኝ

"እሺ ጠይቀኝ"

"ከሩት ጋር ፍቅረኛሞች ናችሁ?"

"አይደለንም"  ፈገግ ሲል አየሁት

"እሺ ታፈቅራታለህ" ከንግግሩ እኩል ደነገጥኩ

"አይ አላፈቅራትም" መሬት ተንበርክኮ መሳም ነው የቀረው ደግሞ ደጋግሞ ፈጣሪን አመሰገነ... ሁኔታውን ሳይ የነገረኝ ሁሉ እውነት እንደሆነ ገባኝ።

"እኔም አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ"

"ጠይቀኝ" አለኝ በፈገግታ ተሞልቶ

"የትናዬት ፍቅረኛህ ካልሆነች ወይም የሆነ ግንኙነት ከሌላችሁ እንደዛ ተጠባብቃችሁ አንገትህን ስትስምህ...." ሳያስጨርሰኝ

"እሱ ለኔም የሚገርም አጋጣሚ ነበር። ሩት እኛ  ወደተቀመጥንበት ስትመጣ እኩል አየናት እናም የትናዬት ሳላስበው ጥምጥም ብላብኝ ሳመችኝ። ደንግጬ ስለነበር ላስቆማት አልቻልኩም ምን እያረግሽ ነው ብያት ዞር ስትልልኝ ሩት ቆማ እያየችን ነው ወዲያው አንተ መተህ ወሰድካት"

"እንጂ ምንም አይነት ግንኙነት የላችሁም"

"ቢኖረን ለምን እዋሽሀለሁ"

፨፨፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨፨

ወደ ያዝነው ክፍል ከተመለስኩ በኋላ ረጅም ሰዓት ወስጄ ለማሰብ ሞከርኩ ከሁሉም አንድ ነገር ደጋግሞ አቃጨለብኝ.... "ሩትን ታፈቅራታለህ"

አዎ አፈቅራታለሁ አልኩ ጮክ ብዬ ልክ እንዳንተ መጀመሪያ ያየኋት ቀን ነው ልቤን የሰረቀችው ግን ምን ያደርጋል እሷ የምታፈቅረው አንተን.... ወዲያው በንግግሬ ደንግጬ ዝምም አልኩ ደግነቱ ከራሴ ውጪ የተናገርኩትን ማንም ሊሰማ አይችልም። ፍጥጥ እንዳልኩ ነጋ ግን ከራሴ ጋር ልስማማ አልቻልኩም እውነት ሩት የሌላ ሰው ስትሆን ማዬት እችል ይሆን???


ይቀጥላል......

         ┏━ 🦋 ━━━━ 🦋 ━┓
       @yefeker_tiksoche
       @yefeker_tiksoche
       @yefeker_tiksoche
         ┗━ 🦋 ━━━━ 🦋
ቻናላችንንይቀላቀሉ
ከወደዳችሁት ❤️
2024/09/21 03:18:57
Back to Top
HTML Embed Code: