Telegram Web Link
​​​​♥️✿ፍቅር በ አማርኛ✿♥️

          አጓጊ እና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ


             ♥️ክፍል 4♥️

...🖊እርሷ ግን ምንም መናገር እልፈለገችም ግን ምንም ቢሆን ጓደኛሽ ነኝ ብላት ብሰራት ምንም ልትመልስልኝ አልቻለችም የማትነግረኝ ከሆነ ደግሜ እንደማላናግራት ነግሬ ላስፈራራት ሞከርኩ ግን ተሳክቶልኛል እሺ እነግርሻለው ግን እባክሽ የምነግርሽን ለማንም እንዳትናገሪ እባክሽ አብሶ ለአማን እና ለአቤል አለችኝ በጣም ደነገጥኩ ከእነርሱ ምን ልትደብቅ ትችላለች ብዬ ደነገጥኩ ከዛ እኔ ፍቅር ይዞኛል ብላ ስቅስቅ ብላ አቀሰች ልቤ ቀጥ ብላ ቀረች በጣም ደነገጥኩ ለአማንም ለአቤልም አትናገሪ ያለችኝ ከእነርሱ አንዳቸው ናቸው ብዬ ደነገጥልኩ አንድም ቀን ለአቤል ልዩ ስሜት እንዳለኝ ነግሬአት አላውቅም የመሸነፍ ያክል ተሰማኝ ተቀደምኩ ብዬ አሰብኩ ግን ከጓደኛዬ አይበልጥም ብዬ መልሼ አሰብኩ ከዛም እርሷን ላማረጋጋት እየሞከርኩ ከማን ፍቅር እንደያዛት ስጠይቃት ይባስ ብላ በጣም ማልቀስ ጀመረች ከዛም ትንሽ እንደቆየን ልክ ልትንግረኝ አ... እንዳለች ስልኬ ጠራ ከዛ አቤል ነበር የደወለው ልቤ ክፍል አለ ላንሳው አላንሳው እያልኩ እያለ ሜሮን አንሽው እንጂ ስልኩን ስትለኝ እ እ እ እሺ እልኩ እና አነሳውት አቤት እቤል አልኩት ቃልዬ የት ነሽ አለኝ ዶርም ነኝ ፈልገኸኝ ነበር አልኩት አዎ በፍጥነት ነይ እፈልግሻለው ምን የሚያስቸኩል ጉዳይ ተገኘና ነው እንዲህ የምታጣድፈኝ ስለው እርሱ ስትመጪ ይነገርሻል አሁን እታች እየጠበኩሽ ነው አታስቁሚኝ ፈጥነሽ ውረጂ አለኝ ከዛም እሺ አሁን መጣው በቃ ብዬ ስልኩን ዘጋውት ሜሮን በቃ ሂጂ ስትምጪ እናወራለን አለችኝ ትንሽ አረጋግቻት ሄድኩ በጣም ጨንቆኛል አሁን አቤልን ነው ምወደው ብትለኝ ምን ይዉጠኛል ደግሞስ እርሱ ለምንድን ነው እንዲህ እያጣደፈ የጠራኝ እርሱም እንደሚወዳት ሊነግረኝ ይሁን እያልኩ እያሰላሰልኩ ሳላስበው አቤልን አልፌው ሄድኩ አቤል አውቆ አይቶኝ ዝም አለና ከኃላዬ ይከተለኛል እኔ ግን ከገባውበት ውስብስብ ሀሳብ መውጣት አልቻልኩም ከዛ ትንሽ ከቆየ በኃላ ጃስ ሲለኝ በጣም ደንግጬ በስመአብ ብዬ አቀፍኩት ከዛ የልብ ምቱ ይሰማኝ ነበር ልቡ በጣም ይመታል ከዛ ቀና ብዬ ስመለከተው ቁልቁል ወደኔ በስስት እያየኝ ለምን ግን አወኩሽ ባላቅሽ ይሻለኝ ነበር አለኝ በጣም ደንግጬ ለምን ምን አጠፍው ስለው አይ ምንም ብሎ ለቀቀኝ ከእቅፉ ባልወጣ ደስ ይለኝ ነበር ግን ግድ መውጣት ነበረብኝ ከዛም ለትንሽ ሰአታት በመሀከላችኝ ዝምታ ሰፈነ ዝምታውን ለመስበር ያክል ለምን ነበር እንዲህ በአስቸኳይ የፈለከኝ አልኩት እርሱም ጥቂት እንደማሰብ አለና ይኸውልሽ ቃል ልነግርሽ የምፈልገው ነገር አለ አለኝ እኮ እሱን አቃለው ግን ምንድነው ልትነግረኝ ምትፈልገው ነገር አልኩት በጣም የተጨናነቀ ቃላቶቹን እያወጣ ቃል በመጀመሪያ ስለ እኔ ምታስቢውን ነገር ንገሪኝ አለኝ እኔም በጣም ደነገጥኩ እ እ እ ምን ማለት ፈልገህ ነው ምትነግረኝን ነገር በግልፅ ንገረኝ አልኩት ከዛ ከመች ጅምሮ እንደሆነ ባላውቅም አንቺን ማሰብ ከጀመርኩ ግን ቆይቻለው ቃልዬ በጣም ነው ማፈቅርሽ አለኝ አንደበቴ ቁልፍልፍ አለ መናገር አቃተኝ....

       ✎  ክፍል አምስት   እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ። 

✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄
             
 ╔═══❖•🌺•❖═══╗
         ❤️#ፍቅር_ያሸንፋል❤️

‌‌‌‌‌‌‌‌
 
                   #እውነተኛ ስሜት

ቻናላችንንይቀላቀሉ

@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
ከወደዳችሁት ❤️
​​​​♥️✿የተራራቀ ልብ✿♥️

          አጓጊ እና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ



             ♥️ክፍል 5♥️

...🖊ቃልዬ በጣም ነው ማፈቅርሽ አንደበቴ ቁልፍልፍ አለ መናገር አቃተኝ በወቅቱ ምን እንደሚሰማኝ አላውቅም በጣም ደስ እንዳለኝ አቃለው ግን ቅር ቅር የሚለኝ ነገር አለ ምንድን ነው እንዴ እረስቼው ሜሮን አ.... ስትል ነበር ስልኬ ጮሆ ማንን እንደነበር ሳልጠይቃት ነበር የመጣውት አሁን ለአቤል እንደምወደው ከነገርኩት እርሷም እርሱን ከወደደችው ትጎዳለች ታዳ ምን ልበለው በጣም ጨነቀኝ ዝምታዬ ያስጨነቀው አቤል ቃልዬ ምነው ዝም አልሽ አንድ ነገር በይ ማፍቀሬ ስህተት ሆኖ ከታየሽ ስደቢኝ ምችኝ ብቻ አላውቅም ቅጪኝ ግን እባክሽ ዝም አትበይኝ ዝምታሽ ያስፈራል አለኝ እኔም እንደማንገራገር አልኩና ትንሽ ጊዜ ስጠኝ ማሰብ እፈልጋለው አልኩት እርሱም ችግር የለውም የፈለግሽውን ያክል ጊዜ ወስደሽ አስቢበት አለኝ እሺ ብዬው ቻው ተባብለን ተለያየን ከአቤል አፍ ይሄ ይወጣል ብዬአንድም ቀን አስቤው አላውቅም ግን በጣም ደስ ብሎኛል አሁን ችግሩ ሜሪ ማንን ነው ምትወደው ነው ከራሴ ጋር እንዲህ እየታገልኩ ዶርም ደረስኩ ስደርስ ግን ሜሪ ብዙ ከማልቀስዋ የተነሳ እራስዋን አሟት ተኝታለች አስተኛኘቷ ልክ እንደህፃን ነው ታሳሳለች በቃ ነገ አወራታለው ብዬ ወደ መኝታዬ ሄድኩ ለመተኛት ብሞክርም ምንም እንቅልፍ አልመጣም አለኝ ላነብ ብልም እንኳ በቃ ቅዥብ ብያለው አይነጋ ነገር ለሊቱ አመታት ሆኖብኝ ነጋ ጠዋት ገና እንደተነሳን በደንብ እንኳን ሳትነቃ ከማን ፍቅር እንደያዛት ጠየኳት ትንሽ እንደመሽኮርመም ብላ አ አ አ ስትል ኧረ በፈጣሪ ይሁንብሽ ንገሪኝ ስላት በቃ እሺ አማንን ነው የወደድኩት አለችኝ ምን አማን አልኳት አዎ አማን አለችኝ እርግጥኛ ነሽ አልኳት ያምሻል ምን ማለት ነው ስትለኝ እውንትም ያመኛል ምን አይነት ጥያቄ ነው የጠየኳት

ግን አቤል ትላንት እንደሚያፈቅረኝ  ከነገረኝ በላይ ዛሬ ደስተኛ ሆንኩ ከዛ የስ ምናምን እያልኩ ሳብድ ምን ሆነሽእንዴት ነው ዛሬ ግን በሰላም ነው አለችኝ በጣም ደነገጥኩ የማደርገው ነገር ለራሴም ገርሞኛል ወደ ማታ አካባቢ እኔና ሜሪ ቁጭ ብለን እያወራን  እንደወደደችው እና ብዙ ነገር ነገረችኝ ከዛም ቃል ግን እስኳሁን በፍቅር ያሰብሽው ሰው የለም ስትለኝ አሁን አልነግርሽም ሰርፕራይዝ ነው አልኳት እንድነግራት ብዙ ብትለምነኝም አልነገርኳትም የምንመረቅበት ጊዜ ደርስዋል ለፈተና በጣም እየተዘጋጀን ነው በብዛት ላይብረሪ ነው ምናሳልፈው ለአቤልም ልክ ፈተና እንደጨረስን ሁሉንም ነገር ልነግረው አስቤያለው ይህንኑ ሀሳቤን ስለነገርኩት እርሱም እየተጫነኝ አይደለም ዛሬ ግን በጣም የሚያስጠላ የሚያናድድ ነገር ተፈጠረ አማን ደውሎ ሊያገኘኝ እንደሚፈልግና በጣም አስቸኳይ እንደሆነ ነገረኝ ከዛም እኔ ጋር እንደምትመጪ ለማንም እንዳትናገሪ ብሎኛል ከዛም አስቸኳይ ነው ስላለኝ ፍንጥር ብዬ ስወጣ ሜሪ ወዴት ነው ስትለኝ ማሚ ጋር ልደውል ነው እዚህ ኔቶርክ የለም አልኳት ያልኳት ነገር ባይዋጥላትም እሺ አለችኝ ከዛም አማን ከርቁ ሆኖ እየተንጎራደደ አየውት በቻልኩት ፍጥነት ደርሼ ምን ተፈጠረ ችግር አለ አቤል ምን ሆነ አልኩት አይ ማንም ምንም አልሆነም እኔ  ለራሴ ጉዳይ ፈልጌሽ ነው አለኝ ምነው ምን ሆንክ አልኩት ይኸውልሽ ቃል ችግር ውስጥ ነኝ አለኝ የምን ችግር አልኩት ፍቅር ያዘኝ አለኝ እኔም ሜሪን ወደዳት ማለት ነው በቃ ጎደኝነታችን ወደ ፍቅር ሊለውጥ ነው ደስ ይላል እያልኩ እና ጥሩ እኮ ነው ግን ከማን እልኩት አማን ዛሬ አስተያየቱ ተቀይሮብኛል ወደ እኔ ቀስ እያለ መጠጋት ጀመረ ቀስ እያለ በጣም ተጠጋኝ ከዛም ካንቺ ሲለኝ ልቤ ቀጥ አለ መናገር አቃተኝ ደርቄ ቀረው አማን ግን ቀስ ብሎ ልክ ሊስመኝ ሲል ዋው ዋው ስታምሩ የሚል ከጭብጨባ ጋር...

    ✎  ክፍል ስድስት  እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ። 



✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄
             
 ╔═══❖•🌺•❖═══╗
         ❤️#ፍቅር_ያሸንፋል❤️

‌‌‌‌‌‌‌‌
 
                   #እውነተኛ ስሜት

ቻናላችንንይቀላቀሉ

@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
ከወደዳችሁት ❤️

‌‌‌‌‌‌‌‌
​​​♥️✿የተራራቀ ልብ✿♥️

           አጓጊ እና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ


             ♥️ክፍል 6♥️

...🖊በጣም ተጠጋኝ ከዛም ካንቺ ሲለኝ ልቤ ቀጥ አለ መናገር አቃተኝ ደርቄ ቀረው አማን ግን ቀስ ብሎ ልክ ሊስመኝ ሲል ዋው ዋው ስታምሩ የሚል ከጭብጨባ ጋር ድምፅ ሰማው ስዞር ሜሪ እና አቤል ናቸው በጣም ደነገጥኩ ግን ስረዳ አቤል እኔ ጋር ሲደውል ሜሪ አንስታ እየተጣደፍኩ እንደወጣው እና የሆነ ነገር እንዳለ ስትነግረው ነው ተከታትለው የመጡት ግን አቤል በጣም እንደተናደደ ያስታውቃል በቃ ለዚህ ነበር ምላሽ መስጠት ያቃተሽ ብትነግሪኝ እኮ ችግር አልነበረውም ለምን ለምን ታሰቃይኛለሽ ቆይ ምን ጋር ጥፍቴ አንቺን ማፍቀሬ ግን እንደዚህ አይነት ሴት አልመሰልሽኝም ነበር ብሎኝ ምላሼን ሳይጠብቅ ሄደ ላስቆመው ሞክሬ ነበር ግን አልቻልኩም ይሄ ሁሉ ሲፈጠር ሜሪ ከማልቀስ ውጪ ያወራችው ነገር አልነበረም አሁን ግን ተራዋ የደረሰ ይመስል ቃል አንቺ እኔን እንዲህ ታረጊኛለሽ የውስጤን ስለነገርኩሽ ትረጂኛለሽ ብዬ አንቺ እኮ ጓደኛዬ ሳትሆኚ ልክ እንደህቴ ነበር ማይሽ አሁን ግን እምነቴን ሙሉ በሙሉ አጥፍተሽዋል ክፉ ክፉ ነሽ እያለች እያለቀሰች ወደ ዶርም ሄደች የሚሆነው ሁሉ በህልም ነበር የመሰለኝ ደርቄ ቀረው የቆምኩበት መሬት ላይ ወደኩ ልክ እኔ ስወድቅ አማን ተንበረከከ ምን ሆንሽ ምንድን ነው የተፈጠረው እነ ሜሪ ምን ሆነው ነው እለኝ ምንም ማለት አልቻልኩም አሁን ብቻዬን መሆን እፈልጋለሁ ነገ ስረጋጋ ሁሉንም እነግርሀለሁ አልኩት ሊያስጨንቀኝ ስላልፈለገ እሺ ወደ ዶርም ልሸኝሽ አለኝ አይ እራሴ እሄዳለው ደና ነኝ እልኩት እባክሽ እንዲ ሆነሽ ብቻሽን ትቼሽ መሄድ አልችልም ሲለኝ እባክህ እማን ተወኝ እራሴ መሄድ እችላለሁ ብዬ ጮኩበት እስከዛሬ ስስቅ እንጂ እንዲህ ስሆን አይቶኝ ስለማያቅ በጣም ደነገጠ እሺ በቃ እሺ ተረጋጊ እሄዳለው ብሎኝ ቀስ እያለ መሄድ ጀመረ የሜሪን አይን እንዴት እንደማየው ምን ብዬ እንደማስረዳት ግራ ገብቶኛል ግን ዶርም ስገባ ጥቅልል ብላ ታለቅሳለች ላናግራት አልቻልኩም በቃ ስትረጋጋ አናግራታለው ብዬ አልጋዬ ላይ ጋደም አልኩ በቃ ከአቤል ጋር እስከመጨረሻው ተጣላን ብዬ አለቀስኩ በጣም በሸኩ ከሁሉም በላይ ከአቤል በፊት የማቃትን ጓደኛዬን ጎዳዋት በእርሷ ዘንድ ታማኝነቴን አጣው ሁሉም ቀርቶብኝ ብያንስ ባናግራት ደስ ይለኛል ግን እርሷ አይኔን ማየት አትፈልግም እንደምንም እየተሟዘዘ ነጋ ገና ሲነጋ አማ ደውሎ ላግኝሽ አለኝ እኔም ትላንት ስላስከፍውት በዛው ይቅርታ እለዋለው ብዬ እሺ አልኩት ከአማን ጋር ተገናኝተን ስለተፈጠረው ነገር በሙሉ ነገርኩት አቤል እንደማፈቅረው ሜሪ ደግሞ እርሱን እንደምትወደድ ብቻ ሁሉንም ነገርኩት ሆድ ብሶኝ ስለነበር ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ ከዛም እንድረጋጋ ብሎ አማን እቅፍ ውስጥ አስገባኝ ክፍቶኝ ስለነበር ምንም አላልኩም ማታ አቤል እንደዛ ስለተናገረኝ ይቅርታ ሊጠይቀኝ እና ምን እንደተፈጠረ ላስረዳው ፈልጎ ሲመጣ እኔን እና አማንን ተቃቅፈን አየን ከዛ...

    ✎  ክፍል ሰባት   እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ። 



✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄
             
 ╔═══❖•🌺•❖═══╗
         ❤️#ፍቅር_ያሸንፋል❤️

‌‌‌‌‌‌‌‌
 
                   #እውነተኛ ስሜት

ቻናላችንንይቀላቀሉ

@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
ከወደዳችሁት ❤️

‌‌‌‌‌‌‌‌
​​​​♥️✿የተራራቀ ልብ✿♥️

                  አጓጊ እና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ


             ♥️ክፍል 7♥️

...🖊ማታ አቤል እንደዛ ስለተናገረኝ ይቅርታ ሊጠይቀኝ እና ምን እንደተፈጠረ ላስረዳው ፈልጎ ሲመጣ እኔን እና አማንን ተቃቅፈን አየን ከዛ ቃል አለኝ እያለቀስኩ እንደነበር አይቷል እና አማንን ጥሎን ሄደ አቤል አማን የተቀመጠበት ቦታ ላይ ቁጭ አለና ልትነግሪኝ ምትፈልጊው ነገር አለ ብሎ ጠየቀኝ እኔም ከምላሼ ይልቅ እንባዬ ነበር የቀደመኝ ከዛም ሊያረጋጋኝ ሞከረ ግን ባሰብኝ እኔ አልጠቅምም እያልኩ ማልቀስ ጀመርኩ እንዴ ለምንድነው እንዲህ ምትይው አለኝ አቤሌ የተፈጠረውን እንዳልተፈጠረ አድርጎ ጠየቀኝ የገዛ ጓደኛዬ በኔ ምክንያት ተጎዳች አንተንም አሰቃየውህ እያልኩ አለቀስኩ ከዛ አቤሌ አንድ ነገር ልንገርህ አልኩት ምንድነው ቃሌ ንገርኝ አለኝ እቤሌ ገና እንዳየውህ የመጀመሪያ ቀን ነበር የወደድኩህ ግን ልነግርህ አልቻልኩም ስለው ስልኬ ጮኽ ማም ነበረች አቤት እማዬ አልኳት ምነው ልጄ ይሄን ሰሞን አልደወልሽም በሰላም ነው አለችኝ ደና ነኝ እናቴ ሰለም ናቹ አልኳት እማ ድምፄ ሲለወጥ ታቃለች ልጄ አሞሻል እንዴ ድምፅሽ ትክክል አይደለም አለችኝ አይ እናቴ ምንም አልሆንኩም ትንሽ ጉንፍን ነገር ይዞኝ ነው አልኳት እሺ በቃ ችግር ካለ ልጄ ደውይ እባክሽ አለችኝ እሽ እማ አታስቢ አልኳት ከዛ እርሷን አናግሬያት ዞር ስል አቤል በቦታው የለም ደነገጥኩ ስደውል ስልክ አያነሳም ከዛም ወደ ዶርም ስሄድ ሜሪ የለችም በቃ ዶርም ቁጭ ብዬ ማልቀስ ጀመርኩ ከ1 ሰአት በኃላ ሜሪ መጥታ ቃል በጣም ይቅርታ ሳልሰማሽ እንደዛ መሆን አልነበረብኝም አለችኝ ግራ የማጋባት ፊት እያሳየዋት አልገባኝም ሜሪ ይቅርታ አረግሽልኝ አልኳት ሲጀመር ምን አጥፍተሽ አማን ሁሉንም ነገር ነግሮኛል አቤልንም እንደምትወጂው እርሱም እንደዛው አይደል አለችኝ እኔ ግን ምንም ሳልላት ተጠመጠምኩባት ከዛ ኧረ ቀስ ገደልሽኝ አለችኝ እና ተሳስቀን ትላንት እና ዛሬ ምንም እንዳላነበብን ፈተና ከ3 ቀን በኃላ እንደሆነ እረስቼዋለው ግን ጊዜው በጣም ይፈጥናል ትኩረታችንን ሙሉ በሙሉ ጥናታችን ላይ አረግን አቤልን ከዛ ቀን ጀምሮ አይቼው አላቅም በጣም ቢያሳስበኝም ግን አሁን ጥናቴ ላይ ትኩረቴን ማረግ እንዳለብኝ አውቃለሁ እንዲህ እያለ ምርቃታችን ደረሰ አራታችንም ተመራቂ ለመሆን በቃን ማም በጣም ደግሳ ነው የጠበቀችኝ

አሁን ከተመረቅን 2 ሳምንት ሞላን አሁን እኔ ድሬ እናቴ ጋር ነኝ ሜሪም አቤልም አማንም ሀዋሳ ናቸው ከአማን እና ከሜሪ ጋር በስልክ እናወራለን አቤልን ግን አግንቼው አላቅም ግን ዛሬ የማላቀው ቁጥር ተደውሎ ማንነቱን ስጠይቅ አቤል ነበር በጣም ደስ አለኝ ምገባበት አጣው ከዛም ድሬ እንደመጣና ማንንም እንደማያቅ ወጥቼ እንድቀበለው ነገረኝ ትንግርት ነው የሆነብኝ አቤል ድሬ ነው ያለው እሺ መጣው በቃ መጣው አልኩት እና ሊያሳምረኝ የሚችል ልብስ መምረጥ ጀመርኩ...

       ✎  ክፍል ስምንት  እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ። 


┄┉┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄
             
 ╔═══❖•🌺•❖═══╗
         ❤️#ፍቅር_ያሸንፋል❤️

‌‌‌‌‌‌‌‌
 
                   #እውነተኛ ስሜት

ቻናላችንንይቀላቀሉ
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
ከወደዳችሁት ❤️
​​​♥️✿የተራራቀ ልብ✿♥️

                         አጓጊ እና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር


             ♥️ክፍል 8♥️

...🖊ሊያሳምረኝ የሚችል ልብስ መምረጥ ጀመርኩ ግን የትኛውንም ልወደው አልቻልኩም ከዛ ከታናሽ እህቴ ለመበደር ፈለኩ እና ዛሬ ቅዳሜ ስለሆነ ክላስ አልነበራትም ማርቲ 12 ክፍል ተማሪ ናት እናም ማርታ እያልኩ መጮህ ጀመርኩ ከዛም የክፍሌን በር ከፍታ ምንድነው ምትተረተሪው ቀስ ብለሽ አትጣሪም አለችኝ ድንጋጤው ነው መሰለኝ በጣም ጮኬያለው አይ ልብስ እንድታበድሪኝ ነበር አልኳት ምን አይነት ልብስ ፈለግሽ ደሞ የት ልትሄጂ ነው አለችኝ አይ የትም አንድ ጓደኛዬን ላገኘው ነው አልኳት እየሳቀች ኧረ ማነው ባክሽ እንዲህ ማዘንጥሽ አለችኝ ኧረ ዝም ብሎ ኖርማል ጓደኛዬ ነው ልብሴ ዛሬ ቆሽሸዋል ለዛ ነው አንቺን ምጠይቅሽ አልኳት ኮስተር ብዬ ትንሽ ማስመሰል እችላለው እና ወድያው አመነችኝ ግን ማስመሰል በጣም ነው ምጠላው ዛሬ ግን ምንም ባልተወራ ወሬ ነገር ብለኩስ መቀጣጠሉ ስለማይቀር ዝም ማለትን መረጥኩ ከዛም በጣም ምወድላትን ቀይ ትሸርት ከሱሪ ጋር ይዛልኝ መጣች ከዛም ፀጉሬን ወደሀላ ለቅቄ ለአመሉ የውሃ ቻፒስት ከንፈሬን ተቀባው ያው ቀይ መቀባት ብዙም ደስ አይለኝም እና ሸንቀጥ ብዬ ወጣው ከዛም ወደ መናሀሪያ ሄድኩ የሚገርመው አቤልን ከብዙ ሰው መሀል ነበር ነጥዬ ያወኩት ከዛም ደወልኩለት አንስ ያለች ጥቁር ቦርሷ ይዟል ወድያው አነሳው የቱ ጋር ነሽ አልኝ አይቼሀለው ፊትህን አዙር አልኩት ልክ ሲዞር አየኝ ከዛም እጄን አውለበለብኩለት ወድያው ስላወቀኝ ወደ መምጣት ጀመረ እኔም ወደሱ እየሄድኩ ነበር ግን ልቤ እጅግ ይመታ ነበር ከዛም ድርሶ ሰላምታ ከተለዋወጥን በኃላ ሻንታውን ልቀበለው እጄን ስሰረጋ አይሆንም ብሎ ለትንሽ ጊዜ ከተከራከርን በኃላ ሳይፈልግ ተቀበልኩት ከዛም እየተራመድን እንዴት እንደመጣ ጠየኩት እኔን ለማየት እንደመጣና ማንንም እዚህ እንደማያውቅ ነገረኝ ከዛም እኔን ለማየት በመምጣቱ እጅግ በጣም ደስ አለኝ እና ልክ ወደ ኪሱ እጁን ከተተ ከዛ በጣም የደነገጠ ይመስላል ወደሌላኛው ኪሱ እጁን ሰደደ አሁን ይበልጥ ደነገጠና እስቲ ቦርሳውን ስጪኝ ብሎ ቦርሳውን ተቀበለኝ ከዛ ወይኔ እናቴ ቀለጥኩ አለኝ ምነው ስለው ቃልዬ ተዘረፍኩልሽ አለኝ ምን ብዬ ጮውኩ ምን ምትፈልገው እቃ ነበር አልኩት አይ እቃስ ምንም አልተነካም ግን የነበረኝን ገንዘብ በሙሉ ተወስዶብኛል አለኝ እና ስልክህ እንዴት ተረፈ አልኩት ኧረ በእጃ ይዤው ስለነበር ይሆናል አለኝ በቃ አትጨናነቅ ለማሚ ደውዬ እኛ ጋር እንድታርፍ እጠይቃታለው ከዛም ትንሽ ከሱ ገንጠል ብዬ ለማም ደወልኩ እናም ሁሉንም ስነግራት በጣም ደስ እያላት ይዤው እንድመጣ ነገረችኝ ከዛም ና አንድ ማረፊያ ተገኝቷል አልኩት የት ሲለኝ አይ እዚው ቅርብ ነው ዝም ብለህ ና ብዬ ባጃጅ መጠበቅ ጀመርን ከዛም ከመናሀሪያ እቤት ድረስ አንድ ባጃጅ አደረሰን ከምስጋና ጋር ከንዘቡን ሰጥቼ ላኩት ከዛም ለማርቲ ነግሬያት ስለነበር ወጥታ ደጅ እየጠበቀችን ነበር እና ሰላምታ ከተለዋወጡ በኃላ ወደ ቤት ገባን ከዛም ማም መጥተናል ስላት ከክችን ወጥታ አቤል እርሱ ነው ተዋወቂው አልኳት ባትይኝም እተዋወቀዋለው ይሄን የመሰለ ቆንጆ ከት አመጣሽ አለችኝ ኧረ እማ አልኳት እንደማፈር ብዬ ከዛ ተቀመጥ ከመንገድ ነው የመጣኸው ደክሞሀል አልችው ወደ ሶፍው እየጠቆመች እሺ ማዘር ብሎ ቁጭ አለና በአይኑ ጠራኝ እ አልኩት አጠገቡ ሄጄ አውቆ ፈገግ እያለ እዚህ እንደምንመጣ ለምን አልነገርሽኝም ብሎ አልኝ እና ወደ እህቴ እያየ ፈገግ አለ ከዛ እ አለኝ ቆጣ እያለ ኧረ አትጨናነቅ ልክ እንደ እቤትህ እየው አልኩት እና ማም ስትጠራኝ ማርቲ አጫውቺው ብያት ሄድኩ ከዛ እጁን አስታጥቢው የሚቀምሰው ነገር አዘጋጅቻለው አልችኝ እሽ ብዬ እጁን ላስታጥበው ስሄድ ማርቲናእቤል በጣም የረጅም ጊዜ ጓደኛማቾች ነው የሚመስሉት ማርቲ ታወራለች አቤል ይስቃል ከዛ በቃ ምንድነው ልጁን ልገይው ነው እንዴ አልኳት ከዛ ጓደኛሽ ደስ ይላል ወድጄዋለው አለችኝ ማርቲ ሲበዛ ፈጣጣ ናት እርስዋ ለምታወራው እኔን ሼም ይይዘኛል እሺ አሁን ይብላ እና እረፍት ያርግ አልኳት እና እኔ መች እጁን ያስኩት አለችኝ ከዛ በአይኔ ተይ የሚል ምልክት ሰጠዋት ማርቲ ቀልቃላና ቀበጥ ብቻ አይደለችም ምትፈልገውን ነገር በእጇ ካላስገባች በጣም ድርቅ ያለች ልጅ ናት በጣም ምትገርም ልጅ ናት እና መጣው ብላ ወጣች ከዛ ሳሎን እኔና አቤል ቀራን አንቺ ካልበላሽ ብቻዬን አልበላም አለኝ ከዛ እሺ ብዬ አብሬው ቁጭ አልኩ የቀረበውን እየበላን ልክ የሆነ ሰአት ላይ ሊያጎርስኝ ሲል...

      ✎  ክፍል ዘጠኝ  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።  #25 like ሲደርስ "ክፍል 9 ይለቀቃል 😢😢😢



┄┉┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄
             
 ╔═══❖•🌺•❖═══╗
         ❤️#ፍቅር_ያሸንፋል❤️

‌‌‌‌‌‌‌‌
 
                   #እውነተኛ ስሜት

ቻናላችንንይቀላቀሉ
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche

ከወደዳችሁት ❤️
​​​♥️✿የተራራቀ ልብ✿♥️

       
አጓጊ እና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር


             ♥️ክፍል 9♥️

...🖊ልክ የሆነ ሰአት ላይ ሊያጓርሰኝ ሲል ማርቲ ገብታ ኧረ ጨረሽበት አለችኝ ከዛ እንደማፈር ብዬ አንገቴን አቀረቀርኩ አቤል ለኔ ያነሳውን ጉርሻ እራሱ ጎረሰው የሆነ ሼም ሳይዘው አይቀርም በልተን እንደጨረስን ማም ቡና አፍልታ እስከማታ እየተጫወትን አመሸን ከዛም የት ይደር የሚለው አከራካሪ ሆነ ማርታ እኔ ክፍል ስትል ማም ቃል ክፍል አቤል ሶፋ ላይ በማለት ብዙ ተከራከርን በመጨረሻ ደረቋ ማርታ እርሷ ክፍል እንዲተኛ አሳመነች እኔ የትም ቢተኛ ችግር የለብኝም ዋናው እርሱን ይመቸው እንጂ ከዛ ማርቲ ከማም ጋር አንድ ላይ ማም ክፍል ተኙ እኔ ክፍሌ ተኛው እና ዝም ብዬ facebook ላይ ገባው አማን online ላይ ነበር hi እለኝ እኔም ሰላም ካልኩት በኃላ ወሬ ጀመርን እና ድሬ ለስራ እንደሚመጣ እና በዛው እንደምንገናኝ ነግሮኝ ተሰነባብተን ስልኬን ዘግቼ በጀርባዬ ጋደም አልኩ እና የአማን መምጣት ብዙም ደስ ባይለኝም ትንሽ ቀን ስላልተገናኘን ናፍቆኝም ነበር እና እንዲህ እንዲህ እያልኩ እንቅልፍ ይዞኝ ሄደ ከዛ ጠዋት ማም መጥታ ቃል ኧረ ተነሽ አመሸሽው እኮ አለችኝ እየሳቀች እማ ትንሽ ብቻ 5 ደቂቃ አልኳት ደግሞ እህትሽ ጓደኛሽን ይዛ ኮብልላለች ስትለኝ ተስፈጥሬ ተነስቼ የት አልኳት እኔንጃ መጣን ብላ ነው ይዛው የወጣችው አለችኝ የት ይሄዳሉ እዚው ቅርብ ነው ሚሆኑት አለችኝ እሺ ብዬ አልጋዬን አንጥፌ ማም ቁርስ እስክትሰራ እኔ ቤቱን ፏ አርጌ ጠበኳቸው እነ ማርቲ ግን አልመጡም መጠበቁ ሲሰለቸን እኛ በቃ እንብላ አልኳት እሷም ትንሽ እጠብቃቸው ስትለኝ ቆይ እሺ በቃ ልደውውልላቸው ብዬ ለአቤል ስደውል ስልኩን እቤት ትቶት ነው የሄደው ከማርቲ ክፍል ሲጠራ ይሰማል ማርቲ ጋር ስደውል ደግሞ አታነሳም በጣም ተናድጄ እማ አሁን ካልበላሽ ከዚህ በኃላ አልበላም ስላት እያቅማማች እሺ አለች ከዛ ወደ 6:15 አካባቢ አቤል እና ማርቲ መጡ ስልኳን ስላላነሳችልኝ ተናድጄ ለምንድነው ስልክሽን ማታነሽው አልኳት እንደመቆጣት ብዬ እሷ ግን ቀለል አርጋው ደውለሽ ነበር እንዴ አላየውትም አለችኝ ይበልጥ ማላገጥዋ እያናደደኝ እንግዳውን  ይዘሽው ሄደሽ ነው አልኳት ማ አቤሌን ነው እንግዳ በቃ እሱ እኮ ቤተኛ ሆኖዋል አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው እንዲህ ምታናግሪኝ አለችኝ እኔም ለራሴ ግራ ገብቶኛል ከዛ ለማስቀየስ ያክል ትላንት ደክሞት መጥቶ በስርሀቱ እንኳን ሳይተኛ የትበለሊት ይዘሽው ትዞሪያለሽ አልኳት እሷም ኧረ ተረጋጊ ሲነሳ ነው የወጣነው ደግሞ ቦታ ላሳየው ነበር አለችኝ ይሄ ሁሉ ሲፈጠር ግን አቤል ዝም ብሎ ነበር የሚያየን በመጨረሻም በቃ አትጨቃጨቁ ይሄ ሁሉ በእኔ ምክንያት ነው አለ እኔም በራሴ አፈርኩ በእርሱ ፊት እንዲህ መሆን አልነበረብኝም ከዛ ማም መጥታ መጣችው ልጆቼ ግቡ ወደቤት ብላ አስገባችን ከዛም ማም እና ማርቲ ምሳ ለማዘጋጀት ክችን ገቡ  ትንሽ ቆይቶ ስልኬ ንዝር አረገኝ እየተደወለ ነበር አማን ነበር የደወለው አንሳውት ሄሎ አማን አልኩት አማን ስል አቤል የደነገጠ ይመስል ነበር ሰላምታ ከተለዋወጥን በኃላ አቤል እኔ የለውም የሚል ምልክት በእጁ አሳየኝ ለምን እንዲህ እንዳለ ባይገባኝም እሺ አልኩት ትንሽ ካወራን በኃላ ከአቤል ጋር አውርታችው ታቃላቹ አግንቼው አላውቅም አለኝ ከዛ አቤል ያለኝን እረስቼ እቤልማ እኮ....

      ✎  ክፍል አስር  ከ50 Vote♥️ በኋላ ይለቀቃል....  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።




┄┉┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄
             
 ╔═══❖•🌺•❖═══╗
         ❤️#ፍቅር_ያሸንፋል❤️

‌‌‌‌‌‌‌‌
 
                   #እውነተኛ ስሜት

ቻናላችንንይቀላቀሉ
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
ከወደዳችሁት ❤️
_​​​♥️✿የተራራቀ ልብ✿♥️

       

                         አጓጊ እና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር

             ♥️ክፍል 10♥️

...🖊አቤል ያለኝን እረስቼ አቤልምማ እኮ ብዬ ገና ሳልጨርሰው አቤል ከመቀስፈት መጥቶ አፌን ያዘኝ አፌን የያዘኝ በጣም ተጠግቶኝ ነበር አይኖቼ ከአይኖቹ ጋር አረፉ አቤል በጣም እየተመለከተኝ ነበር የሆነ የሚስለኝ ነበር ሚመስለው ላየው ሰው ግን አሁን ይበልጥ እየተጠጋኝ እንደሆነ ይታወቀኛል ሰውነቴ እየነዛዘረኝ ነው ከዛ አፍንጫዬን በስሱ ሲስመኝ አይኖቼ ሲከደኑ ይታወቀኛል የምሆነውን በሙሉ  ከእኔ ቁጥጥር ውጭ ነው ከዛም ቀስ ብሎ ከአጠገቤ ተነስቶ ቦታው ተቀመጠ እና አይኖቼን ቀስ አርጌ ገለጥኳቸው እና ከኔ ፊት ለፊት ተቀምጦ ፈገግ ይላል ከዛ ስልኩን ዘጋውት አማን በድጋሚ ደወለ እና ትንሽ እንደማመንታት ብዬ አነሳውት እና አንቺ ምን ዋጠሽ ገሮሮዬን እኮ እፈልገዋለው አለኝ ከዛ በጣም ይቅርታ አማንዬ ኔቶርክ ትንሽ እያስችገረ ስለሆነ ነው ስለው አቤል ከት ብሎ ሳቀ ድምፁ እንዳይሰማ ብዬ ወደ ውጭ ወጣው ቢሆንም አማን በትንሽውም ቢሆን ድምፁን ሰምቶ ነበር ከዛ ማነው እንዲ ድዱ እስኪታይ የሚስቀው ብሎ ሲጠይቀኝ አይ የጎረቤት ልጅ ነው አልኩት ብዙም ግድ አልሰጠውም ነበር እና ፈልገኸኝ ነበር ስለው ምን ባክሽ ስራዬ ሊያቆየኝ ስለሚችል እቤት እንድፈልጊልኝ ነበር አለኝ እሺ ከተገኘ ችግር የለውም ብዬ ተሰነባብተን ዘጋውት እቤት ስገባ ምሳ ቀርቦ ነበር እጄን ለቅለቅ ብዬ ተቀላቅያቸው በልተን ከጨረስን በኃላ ማም ቡና አፍልታ እየተጫወትን ሳለ ትዙ ደወለች ወዬ ትዙዬ አልኳት የት ነሽ አለችኝ እቤት ስላት ባክሽ ውጪ ከመቅዲ ጋር እየጠበቅንሽ ነው በርጋ አልችኝ መጣው ብያት ስልኩን ዘጋውት ትዙና መቅዲ የሰፈር ጎደኞቼ ናቸው ማም ደግሞ የት ልትሄጂ ነው አለችኝ አይ እነ ትዙ በር ላይ ናቸው አይቻቸው መጣው አለኳት እሺ ቶሎ ተመለሽ እንግዳ አለ አለችኝ እሺ ብዬ ወጣው ትዙ አንቺ ግን አለሽ አልኳት ተጠፍፍተን ስለነበር መች ፈለግሽኝ እና አለችኝ አልሰማሽም እንዴ ስላት የሆነ ትልቅ ነገር ምነግራት መስልዋት ሰፍ ብላ ምን ስትለኝ በየቦታው አፍልጉኝ ፎቶሽን መለጠፌ ስላት ሂ ወረኛ ብላ በስሱ መታችኝ እና መቅዲ ስላት ምን አለችኝ ትንሽ የደበራት ትመስል ነበር ምነው አልኳት ምንም ምነው አለችኝ የውሸት ፈገግታ እያሳየችኝ ከዛ ትዙ እቤት ተፈለጋ መጣው ብላን ባለንበት ጥላን ሄደች ከዛ መቅዲ የሆነ ነገር አለ ንገሪኝ ብዬ ጎተጎትኳት ከዛ ታሪኩ እረጅም ነው ግን እያሳጠርኩ ልነግርሽ እሞክራለው አለችኝ
ችግር የለም ንገሪኝ አልኳት ወክ እያረግን እንድትነግረኝ ነግሬያት በዝግታ እየተራመድን ወሬዋን ጀመረች ከዛ በፊት ግን መቅዲ የ 4ተኛ አመት የዶክትሬት ተማሪ ነች እና ታሪኩን እንዲህ ብላ ጀመረች...

     ✎  ክፍል አስራ አንድ  ከ50 Vote♥️ በኋላ ይለቀቃል....  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ


┉┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄
             
 ╔═══❖•🌺•❖═══╗
         ❤️
#ፍቅር\ያሸንፋል❤️

‌‌‌‌‌‌‌‌
 
                   #እውነተኛ ስሜት

ቻናላችንንይቀላቀሉ
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
ከወደዳችሁት ❤️
​​​♥️✿የተራራቀ ልብ✿♥️

      
                         አጓጊ እና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር 


             ♥️ክፍል 11♥️

...🖊ታሪኩን እንዲህ ብላ ጀመረች እንድ የክፍሌ ጎበዝ ተማሪ ነበር እና ብታይ ሲበዛ ጢባራም ነው እና መጀመሪያ አካባቢ በጣም ያስጠላኝ ነበር እና አንድ የክፍሌ ጎደኛዬ ሰአዳ የምትባል ልጅ ነበረች እና ለምን ሙድ አንዚበትም ሄደሽ አውሪው አለችኝ ከዛ እኔም ለማፌዝ እሺ አልኳት እና እስክርቢቶም መፅሀፍም በማለት ተግባባውት ከዛ እንድ ቀን አጠገቤ መጥቶ እንዲቀመጥ በአይኔ ነገርኩት እሱ ግን ኮስተር ብሎ አቤት ፈለግሽኝ አልኝ ተቀመጥ አልኩት ከዛ ተቀመጠና አቤት አለኝ ከዛ ፈገግ እንዲል ብዙ ነገር አወራውት እርሱ ግን በስሱ ነበር ፈገግ የሚለው ይበልጥ ያበሽቀኝ ጀመር ከዛ telegram እንደሚጠቀም ጠየኩት አዎ አለኝ እና ለመጀመሪያ ጊዜ ከወንድ ስልክ ስቀበል እና ስልክህን ስጠኝ በዛ እናወራለን አልኩት ከዛ 09 ሲለኝ አላመንኩም ቶሎ ብዬ እስክርቢቶ አንስቼ በእጄ ለመፃፍ እሺ አልኩት 75 እ አልኩት 50 እ አሁንም ስልኩን ለመቀበል ጎጉቼ ስሙኒ አለኝ ከዛ ከት ብዬ ሳቅኩና አትቀልድ ስጠኝ አልኩት ምን ያረግልሻል አለኝ እናወራለና ስለው ትክክለኛ ስልኩን ሰጠኝ ከዛ ተቀበልኩት ከዛ ማታ ብፈልገው ላገኘው አልቻልኩም ለአንድ ሳምንት ያክል ላገኘው አልቻልኩም አንድ ቀን የሆነ ድንጋይ ላይ ቁጭ ብዬ መጣና አብሮኝ ተቀመጠ እና ለምን online ላይ እንደማይገባ ጠየኩት ከዛ ከዚህ በኃላ ስትገቢ miscall አርጊልኝ ግን መልሼ miscall ካረግኩልሽ አልገባም ማለት ነው አለኝ እሺ ብዬ ማታ ማታ miscall ማድረጌን ቀጠልኩ እናም እኔ እረስቼው ከተውኩት ወይም ከደበረኝ እርሱ ሱስ የሆነበት ይመስል አንድም ቀን አያልፈውም ስትል ስልኬ ጠራ ወይ ማም አልኩ ማም ነበረች አንቺ እንግዳ እቤት አስቀምጠሽ የት ጠፍሽ አለችኝ ውይ እረሳውት እኮ በቃ መጣው ብያት መቅዲን ነገ እናወራለን ብያት ተሰናብቻት እቤት ገባው ስገባ ግን አቤል ሻንጣውን እያስተካከ ነበር እና ወዴት ለመሄድ ነው ስለው ነይ ማወራሽ ጉዳይ አለ አለኝ ብሎ ይዞኝ ወጣ እና እእእ ቃልዬ በመጀመሪያ ይቅርታ ልጠይቅሽ እፈልጋለው አለኝ ግራ በመጋባት ለምኑ አልኩት እእ ድሬ ማንንም አላቅም ስልሽ እና ገንዘቤ ተሰረቀ ያልኩሽ በሙሉ ው.. ሸ ..ቴ ..ን ነ..በ..ር አለኝ በተቆራረጠ ድምፅ ምን አልኩት ለምን ዋሸኸኝ አልገባኝም እየቀልድክ ነው ስለው...

      ✎  ክፍል አስራ ሁለት  ከ50 Vote♥️ በኋላ ይለቀቃል....  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።


┉┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄
             
 ╔═══❖•🌺•❖═══╗
         ❤️#ፍቅር_ያሸንፋል❤️

‌‌‌‌‌‌‌‌
 
                   #እውነተኛ ስሜት

ቻናላችንንይቀላቀሉ
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
ከወደዳችሁት ❤️
​​​♥️✿የተራራቀ ልብ✿♥️

       
                         አጓጊ እና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር


             ♥️ክፍል 12♥️

...🖊በጣም ይቅርታ አርግሊኝ ግን በእኔ እና ባንቺ መሀል ያለውን ችግር ለመቅረፍ በማሰብ ነው እና ደግሞ ትክክል ነው ያረኩት አለኝ ምን መዋሸትህ ትክክል ነው ምንድነው ምትለው ቃልዬ ሁሉንም ነገር እንድታስረጂኝ እኮ እያመቻቸው ነው እሺ አሁን እሱን ተወውና ወዴት ለመሄድ ነው ሻንጣህን የምትሰበስበው አልኩት እሱም እዚህ አክስቴ አለች እና ማም እዚህ መሆኔን ስትነግራት ካልመጣ ብላ ቀወጠችው እና ካልሄድኩ ችግር ትፈጥራለች እና ደግሞ ለአማን እዚህ ነው እንዳትይው አለኝ እና ለምን እንደዛ እንዳለ መጠየቅ ፈልጌ እረስቼው ነበር በዚህ እጋጣሚ ለምን እንዳልነግረው እንደፈለገ ጠየኩት እሱም ሳልነግረው ስለመጣው ይደብረዋል ለዛ ነው አልኝ ወሬ ማብዛት ስላልፈልኩ ነገ ስንት ሰአት ነው የምትሄደዉ አልኩት ወደ 5 ሰአት አልኝ እና ጥሩ በቃ እሸኝሀለው በል እንግባ ብርዱ ከባድ ነው አልኩት እየገባን እያለ አቤል ስልኩ ጮኸ አባቢ አለ ምን ፈልጎ ደወለ አለኝ አንሳና ሚሉህን ስማ አልኩት አቤት አባቴ ከዛም ትንሽ ካወሩ በኃላ ፊቱ እንደመለዋወጥ አለ እና እሺ ብሎ ስልኩን ዘጋው ምንድነው ምን ተፈጠረ ስለው ከ 1 ወር በኃላ ለስራ ድርጅታችን ወደ አሜሪካ እንደምላክ ነው የነገረኝ አለኝ አልገባኝም አልኩት ልክ ገና እንደተመረቅን አባዬ ድርጅቱን እንዳስተዳድር ሀላፊነት ሰጥቶኝ ነበር እና አሁን ወደ ውጭ እንደሚሄድ ነው የነገረኝ አልኝ እስከ መች ትቆያለህ ስለው አላውቅም ግን ብዙ ጊዜ እንደማልቆይ ነው የነገረኝ አልኝ ዱካክ ለቀቀብኝ እና በቃ እሺ እንግባ ተባብለን ውስጥ ገባ እንቅልፍ ምንም አልመጣልሽ አለኝ እንዲሁ መገላበጥ ሆነ ስራዬ በመጨረሻም Facebook ስገባ ሜሪ ኦንላይን ላይ ነበረች ወድያው ነበር ሀይ ያለችኝ ትንሽ ሰላምታ ከተለዋወጥን በሀላ ከአቤል ጋር እንዴት ናችሁ አልችኝ ከሷ ምንም መደበቅ ስላቃተኝ ሁሉንም ነገርኳት ምንም ልታምነኝ አልቻለችም አብሶ እኛ እቤት ነው ስላት ግን ላሳምናት ቻልኩ እና ነገርሽው እንዴ አለችኝ ምኑን ስላት እንደምትወጅው ነዋ ባለፈው ከነገርኩት በኃላ አላወራንም በዚህ እርስ አልኳት እንዴ ለምን ብላ ብዙ የጥያቄ ምልክት ላከችልኝ እኔም እኔንጃ ጊዜ ምንም አልተመቻቸልንም እንደሚሄድም ነገርኳት እሷም እንደምወደው ይሄን አጋጣሚ ተጠቅሜ እንድነግረው ነገረችኝ እሺ ብዬ አምስግኛት ተሰነባብት ከ ኦንላይን  ላይ ወጣች የተላኩ ሚሴጆች ወደ 150 ገብተዋል ግን አንዱንም ከፍቼ አይቼ አላውቅም በቃ ማቀው ሰው ኦንላይን ላይ ስለሌላ ሁሉም ስለማላቃቸው ደብሮኝ አጥፍቼ ጋደም ብዬ ማሰብ ጀመርኩ ነገ ምን ልበለው እያልኩኝ በቃ እንደማወራው ብቻ እርግጠኛ ነበርኩ እንዲህ እንዲህ እያልክ እንቅልፍ አሸልቦኝ ሄደ...

     ✎  ክፍል አስራ ሦስት  ከ50 Vote♥️ በኋላ ይለቀቃል....  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።


┉┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄
             
 ╔═══❖•🌺•❖═══╗
         ❤️
#ፍቅር_ያሸንፋል❤️

‌‌‌‌‌‌‌‌
 
                  
#እውነተኛ ስሜት

ቻናላችንንይቀላቀሉ
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
ከወደዳችሁት ❤️
                                        
​​​♥️✿የተራራቀ ልብ✿♥️

       
       
                         አጓጊ እና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር


             ♥️ክፍል 13♥️

...🖊በጠዋት ተነስቼ ቤታችንን ካስተካከልኩ በኃላ ቁርስ ለመስራት ወደ ክችን ስገባ ማም ጉድ ጉድ እያለች ነበር ልክ ስታየኝ ዛሬ እንዴት በጠዋት ተነሳሽ አለችኝ አይ አቤል ዛሬ የሚሄደው አልኳት እንዴ ወዴት አለችኝ አክ...አልኩ እና አፌን ያዝ አረግኩት ወደ ሀገሩ መሰለኝ አይ አንቺ ትላንት አነግሪኝም ነበር አለችኝ እኔም ማታ ነው የነገረኝ ደሞ ወደ ውጭ ሊሄድ ነው በቅርቡ አልኳት እሷም በድንጋጤ ለመኖር አለችኝ አይ ለስራ አባቱ ልከውት ነው አልኳት አይ ልጁ እኮ በጣም ጥሩ ልጅ ይመስላል በዛ ላይ እረጋ ያለ ነው ግን ልጄ ምንም ነገር ሳትዋሺ ንገሪኝ ምንም ነገር የለም ከእርሱ ጋር ስትለኝ የሌለ ሼም አስያዘችኝ ኧረ ማም ተይ እያሳፈርሽኝ ነው አልኳት ማም ገና ከመጀመሪያው ቀን አንስታ ነበር አይንዋ አቤል ላይ ያረፈው ከዛ ምን ከእኔ ከእናትሽ ምደብቂው ነገር አለ አለችኝ ኧረ ካንቺ ሌላ ምን ህይወት አለኝና ካንቺ እደብቃለው አልኳት እኮ ንገሪኛ አለችኝ ምን ልንገርሽ አልኳት ሁሉንም ነገር አለችኝ ከዛ ግን እኮ እማ ስላት ሳታስጨርሰኝ እንዳትዋሺኝ ልጄ ስትዋሺኝ አቅብሻለው አለችኝ ከዛም ምንም ልደብቃት ስላልፈለኩ ሁሉንም ነገርኳት እንዴት እንደተዋወቅን እንዴት እንደተጣላንና ለምን እንደመጣ ጭምር ሳልደብቅ ነገርኳት እና አሁንም እዚህ አክስት እንዳለው እና እዛ እንደሚሄድ ነገርኳት እርስዋ ግን አንድ ጥያቄ ብቻ ነበር የጠየቀችኝ ደስተኛ ነሽ የሚል አላውቅም አልኳት ከእርሱ ጋር ስትሆኚ ሰላም ይሰማሻል አለችኝ በጣም እንጂ ድምፁን መስማት በራሱ ደስታ ይሰጣል አልኳት እርሷም አይ የሚያስደስትሽ እና የምታምኝበት ከሆነ እኔም ወጌን ልይ አልችኝ ከዛ ሁለታችንም ስንስቅ አቤል ሰምቶ መጣ ከዛ ደና አደራቹ አለ እንደም አደርክ ልጄ ሂድ ፊትህን ታጠብ ቁርስ ደርስዋል አለችው እና ሄዶ ታጥቦ መጣ ቁርስ ለመብላት ተሰብስበን ቁጭ አልን እና እማዬ ወሬ ለማስጀመር ያክል እና ልጄ ስራ እንዴት ነው አለችው ስራ ጥሩ ነው እና ዛሬ ነው ምትሄደው አሉ ስትለው አንገቱን አቀርቅሮ እእእእእ አለ መልስ ምት የሚመስል ነገር እና ለምን በጊዜ አትነግረንም የሆነ ነገር እናዘጋጅ ነበር አለችው  ኧረ ችግር የለውም ማዘር አትጨነቂ አላትና በላልተን እንደጨረስን ወደ ውጭ ወጥቶ ለእክስቱ መኪና እንድትልክለት ነገራት ከዛም ሻንጣውን ለማምጣት ማርቲ ክፍል ሲገባ ተከትዬው ገባውና በሩን ዘጋውት አቤል አልኩት አቤት አለኝ ፊቱን ወደ እኔ እያዞረ ባለፈው አንድ ነገር ነግሬህ ነበር አልኩት ምን አለኝ ምንም እንደማያቅ ሰው እንደው ባለፈው የተጣላን ሰሞን አልኩት ይቅርታ ግን አላስታወስኩም ሲለኝ የሌለ አበሳጨኝ ተወው በቃ አልኩትና ልወጣ ስል እጄን ቀበል አደረገና ወደ እኔ እየተጠጋ ለምንድነው ወድያው ምትናደጅው አለኝ አይን አይኖቼን እያየ መናገር አቃተኝ እእእ...

    ✎  ክፍል አስራ አራት  ከ50 Vote♥️ በኋላ ይለቀቃል....  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ። 

┉┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄
             
 ╔═══❖•🌺•❖═══╗
         ❤️#ፍቅር_ያሸንፋል❤️

‌‌‌‌‌‌‌‌
 
                   #እውነተኛ ስሜት

ቻናላችንንይቀላቀሉ
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
ከወደዳችሁት ❤️
                                   
​​​♥️✿የተራራቀ ልብ✿♥️

        አጓጊ እና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ 


             ♥️ክፍል 14♥️

...🖊እእ እና ታድያ ገብቶህ እንዳልገባህ ስትሆን ነዋ አልኩት እና ከአንደበትሽ መስማት ስለምፈልግ ነዋ አለኝ እንደውም አልነግርህም ስለው ኧረ ወደሽ ነው በግድሽ አልኝ ባልነግርህ ምን ታመጣለህ አልኩት እጮኻለው አልኝ ወንድ ስለው ሊጮህ ሲል እፉን ያዝኩት አበድክ ስለው አዎ አሁን ሳይሆን ገና አንቺን ያየው ቀን አለኝ ወረኛ አሁን አትፈላሰፉ አልኩት እየተፈላሰፍኩ አይደለም እውነት ነው አንቺስ አለኝ አይኖቹን አይኖቼ ላይ ተክሎ ምን ይመስልኸል አልኩት እኔ እራሴን ከምወደው በላይ አብልጠሽ እንደምትወጅኝ እእ ትክክል ነኝ ሲለኝ አዎ ብዬ ገፍትሬው እየሮጥኩ ልወጣ ስል እጄን ይዞ ወደ ደረቱ ልጥፍ አረገኝ እኔም እቅፉ ውስጥ ስገባ ሌላ አለም ውስጥ የገባው መሰለኝ የሆነ  የስልክ ጥሪ እኔንም እርሱንም ካለንበት መአበል ፈልቅቆ አወጣን አክስቱ ነበረች መኪናው እንደደረሰና እንዲወጣ ነገረችው እሺ አለና ሻንጣውን ይዞ እንደመውጣት አለና ተመልሶ መጥቶ ግንባሬን ስሞኝ ወጣ ከዛም ተከትዬው ወጣው ማም ልትሄድ ነው ስትለው አዎ ማም በቃ ቻው እየመጣው እጠይቃችኃለው አልና ተሰናብቶን ወጣ በአይኔ መኪና ውስጥ ገብቶ እስኪሄድ ከሸኘውት በኃላ እቤት ገባው እና ቁጭ እንዳልኩ ለካ ትላንት መቅዲ ያስከፉትን ነገር ሳትጨርስልኝ ነበር ስደውል ስልክ አታነሳም ድግሜ ስደውል ተይዝዋል ይለኛል በቃ ሚስኮል አይታ ትደውላለች አልኩና ስልኬን ቁጭ አረኩት ብዙም ሳትቆይ ደወለች ምንድነው ስልክ ማታነሽው አልኳት ኧረ ስደውል ተይዝዋል ብሎኝ እኮ ነው አለችኝ የት ነሽ ስላት እቤት ነኝ ፈለግሽኝ ስትለኝ አዎ መምጣት ትችያለሽ አልኳት የት እቤት አለችኝ አይ ሰፈር ወጣ በይ እኔም ንፍስ መቀበል አምሮኛል አልኳት እሺ በቃ ውጭ መጣው አልችኝ እና ተሰነባብተን ስልኩን ዘጋነው ከዛ ከ 15 ደቂቃ በኃላ ውጭ አለችኝ ደውላ እሺ ብያት ወጣን ከዛም በማርያም ቤተክርስቲያን በኩል ወክ እያረግን ማውራት ጀመርን ከዛም ከአንዱ መቀመጫ ድንጋይ ላይ ሄደን ቁጭ አለን እና መቅዲዬ የባለፈውን ቀጥይልኝ እንጂ አልኳት እሷም ለማውራት ትንሽ ካንገራገረች በኃላ ለመናገር ጉሮረዋን ጠረግ ጠረግ አርጋ በቃ ከናቲ ጋር በቴሌግራም ማውራታችን ቀጠልን ግን እኔ ምንም አይነት ነገር ለእርሱ አልነበረኝም ያው ጉረኛ ስለሆነ ትንሽ ላስተንፍሰው ብዬ እንጂ አንድ ቀን ግን ምሳ ሰአት ላይ ኪሩቤል የሚባል ልጅ ሊያወራኝ እንደሚፈልገኝ ነገረኝ እኔም እሺ ብዬው የምንገናኝበትን ቦታ ነግሮኝ እርሱን ለማግኘት ሄድኩ ኪሩቤል በጣም ደስ የሚል ተጫዋች የደስ ደስ ያለው ልጅ ነው ደግሞ ሲስቅ ድምፒሉ እንዴት እንደሚያምር እና እርሱ ጋርም እንደደረስኩ ሰላምታ ከተለዋወጥን በኃላ በጣም ትልቅ ነገር እንደሚነግረኝ ነገረኝ ምን እንደሚነግረኝ ብዙ ነገር እያወጣው እያወረድኩ ምን ሊነግረኝ እንደፈለገ ጠየኩት እርሱም እንዲህ በማለት ጀመረ ብዙ የፍቅር ጥያቄዎች ደርሰውሽ ይሆናል ብዙ ሰዎችንም ተተዋውቀሽ ይሆናል ግን አሁን የምነግርሽ ሰው በጣም ከልቡ የሚወድሽ እራሱን እስከመጣል የደረሰልሽ ሰው ነው ከአንቺ በፊት ብዙ ሴት ቢያቅም ነገር ግን የትኛዋንም ልክ እንዳንቺ ወድዶ አያውቅም አለኝ ምንም ማለት አቅቶኝ ዝም ብዬ እሰማው ነበር አሁን ላይይ አንቺ ለእርሱ ምንም ስሜት ባይኖርሽም እስከ መጨረሻው እንደሚጠብቅሽ እርግጥኛ ነኝ አለኝ እኔም በመደንቅ ይሄን ያክል ልጁ ማን ቢሆን ነው እንዲህ ስለሱ እርግጥኛ ሆኖ የሚያወራው አልኩና ማነው እርሱ አልኩት ከዛም መናገር ያቃተው ይመስል ዝም አለ እኔም አላስችል ብሎኝ ንገረኛ ማነው አልኩት አሁንም ምላሹን እየጠበኩ እእእ እባክሽ ስሙን ስነግግሽ እንዳደነግጭ ግን አንድ ነገር እወቂ መልስሽ ምንም ቢሆን እርሱ ከምታስቢው በላይ እንደሚወድሽ እሺ አለኝ እኔ ትዕግስቴ እያለቀ ማነው እርሱ አልኩት እእእ እሺ እነግርሻለው ግን ባትወጂው እንኳን አትጥይው አለኝ ሳላውቀው በመጀመሪያ ልጁ ማነው አልኩት እርሱም በጣም በመጨነቅ ስሜት ሆኖ እእእ እኔ እራሴ ነኝ አልኝ ድርቅ ብዬ ቀረው ምን አልኩት አዎ እኔ ነኝ መቅዲ አንቺ ሳታቂ ለብዙ ጊዜ ወድጄሻለው አንቺን ለመርሳት ከብዙ ሴት ጋር ሆኛለው ግን አልቻልኩም አንዴ ልቤ ላይ ተፅፈሽ የማይጠፍ እስክርፒቶ ሆነሽብኛል መቅዲ መልስሽ ምንም ቢሆን አንቺን መውደዴን አላቆምም አለኝ እልሻለው ስትለኝ የሆነ ፊልም የምትነግረኝ ነበር የመሰልኝ ቀጥይ በሚል አስተያየት እያየዋት ቅንድቤን ከታች ወደላይ ከፍ በማድረግ ቀጥይ አልኳት እርሷም ይሄን ነገር ኪሩቤል ከነገረኝ ቀን ጀምሮ ስለሱ ማሰብ ጀመርኩ ከዛ ግን ስልኬን ማን እንደሰጠው ባላውቅም ቴሌግራም ላይ ሀይ ብሎ ላከ እኔ መልስ ከመመለሴ በፊት ፕሮፍይል አይ ስለነበር የእርሱ መሆኑን አውቅኩ እና ከትንሽ ቀን በኃላ እኔም ሀይ ብዬ መለስኩለት ከዛ ለረጅም ጊዜ ማውራት ጀመርን ቀስ በቀስ በጣም እወደው ጀመር እና በመሀል ስለ እኔ እና ናቲ መወራት ጀመረ እኔ እና ናቲ አንድ ላይ እንደሆንን ማውራት ጀመሩ አንድ ቀን ግን ክፍል ውስጥ ያለመደባቸውን ትዕዛዝ እንጫወት ብለው ናቲ እኔን እንዲስመኝ ታዘዘ ከዛ ልሳምሽ አለኝ ላሳፍረው ስላልፈለኩ እሺታዬን አንገቴን በመነቅነቅ ገለፅኩለት ከዛ ልክ ገና ሲስመኝ የክላስ ተማሪዎች በጩኸት ክፍሉን ቅውጥ ግማሾቹ ፎቶ አነሱንና ቴሌግራም ላይ የአመቱ ምርጥ ፍቅረኛማቾች ብለው ግሩብ ላይ በተኑት ይመስለኛል ናቲ ጎበዝ እና ቆንጆ ጉረኛ ስለሆነ ይመስለኛል እንዲህ ያካበዱት ከዛ ግን...

   ✎  ክፍል አስራ አምስት  ከ50 Vote♥️ በኋላ ይለቀቃል....  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ። 


┉┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄
             
 ╔═══❖•🌺•❖═══╗
         ❤️#ፍቅር_ያሸንፋል❤️

‌‌‌‌‌‌‌‌
 
                   #እውነተኛ ስሜት

ቻናላችንንይቀላቀሉ
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
ከወደዳችሁት ❤️
ታላቅ ቅናሽ

Unlimited data ፈላጊዎች

1ወር 650

3ወር 1800

የ1አመት 5500

inbox @R2ebi
0933620136
           0932473792
ይደውሉልን በታማኝነት እንሰራለን
የፍቅር ጥቅሶች 💖 pinned «ታላቅ ቅናሽ Unlimited data ፈላጊዎች 1ወር 650 3ወር 1800 የ1አመት 5500 inbox @R2ebi 0933620136            0932473792 ይደውሉልን በታማኝነት እንሰራለን»
​​​♥️✿የተራራቀ ልብ✿♥️

        አጓጊ እና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ 


             ♥️ክፍል 15 እና 16
ከዛ ግን የክፍሉ ተማሪ ሁሉ ሲጮህ
ኪሩቤል የሆነውን ነገር አይቶ ነበርና
እየሮጠ ወጣ እኔ ምን ሆኖ ይሆን ብዬ
ተከትዬው ወጣው ምን ሆነህ ነው አልኩት እሱ ግን ምንም መልስ ሳይሰጠኝ እሩጫውን ቀጠለ እኔ ወዴት
ይሄዳል ብዬ ስከተለው በአከባቢው
ወደ አለው ጫካ ገባ ከዛን ምን ያደርጋል
ብዬ ተከተልኩት ተደብቄ ሳየው የሆነች
የዘመመች ዛፍ ላይ ገመድ እያሰረ ነው
ደነገጥኩ ከተደበኩበት እሮጬ ወጥቼ
እግሩ ላይ ጥምጥም አልኩበት እሱ ግን
ባትወጂኝ እንኩን ለምን ትጎጂኛለሽ አለኝ
ልክ ሊታነቅ ሲል እኔም በጣም አፈቅርሀለሁ አልኩት እሱም ዞር ብሎ አይቶኝ በፍቅር አቀፈኝ
ከዛን እንደዛ በተቃቀፍንበት ቅፅቀት
የማይታመን ነገር ተፈጠረ ኪሩቤል
ከኪሱ ትንሽ ብቃት አወጣ ,,,,,

  

┉┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄
             
 ╔═══❖•🌺•❖═══╗
         ❤️#ፍቅር_ያሸንፋል❤️

‌‌‌‌‌‌‌‌
 
                   #እውነተኛ ስሜት
​​​♥️✿የተራራቀ ልብ✿♥️

        አጓጊ እና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ 


             ♥️ክፍል 17♥️

...🖊ከኪሱ ውስጥ አንድ ብልቃት ምትመስል ምታምር ነገር አወጣ እና ሲከፍታትያየውትን ነገር ማመን አልቻልኩም በጣም ደነገጥኩ የምታምር ትንሽዬ ቀለበት ናት እና ከአይኔ የእምባ ዘለላ የሚወርድ ይመስለኛል አቤል ምንድነው ይሄ ሁሉ አልኩት የእኔ ማር ዘመኔን በሙሉ ላንቺ ተገዝቼ እንድኖር ትፈቅጅልኛለሽ አለኝ ድርቅ ብዬ ቀረው ከዛ አቤልምቃል ቃል እያለ ይጣራል የአቤል ድምፅ ወደ ቀጭን መጣ እንደውም በቀረበ ቁጥር የእናቴን ድምፅ መሰለኝ እናቴ መጥታ አንቺ ኧረ ተነሽ አለችኝ ብርግግ ብዬ ተነሳውና የታለ የታለ አልኳት ምኑ አለችኝ በህልሜ እንደሆነ ገባኝና አይ ምንም አልኳት እሺ ቶሎ ተነሽ አለችኝ እና ወጣች በህልሜ እንደሆነ ሳስብ እጁጉን ተቃጠልኩ ከዛም ሰውነቴን እየጎተትኩ ከመኝታዬ ላይ ተነሳው ምናለ ህልም ባይሆን አሁን ትንሽ ቆይታ ብትመጣ ማሚ ምን አለበት ቢያንስ ቀለበቱን እስኪያረግልኝ ብትቆይ እያልኩ በጣም ተናደድኩ ከዛም ሚሴጅ ገባልኝ እንደምን አደርሽ የኔ ፍቅር የኔ ሁሉ ነገር የሚል ከአቤል ነበር ንጋቴን በምርጥ ቃላት ከፈተልኝ የኔ ማር የዋህ እኮ ነው ጥያቄውን በጥያቄ ደና አደርክ ፍቅሬ አልኩት እግዚአብሔር ይመስገን ተነሳሽ አለኝ አዎ ገና ከመነሳቴ መልክዕክት ላክ አልኩት አየሽ ልቤ ነግሮኝ ነው አለኝ ወረኛ ደሞ ሳልነግር እረስቼው አማን መጥቷል አልኩት ከዛ አልመለሰልኝም ትንሽ ቆይቶ ደወለ እና ማሬ ደህና አደርሽ አለኝ በድጋሚ እግዚአብሔር ይመስገን ፍቅር እንዴት ነህልኝ አልኩት አለው የዋህ ምን ይሆናል ሲል ሚስቱን ይቀማል አልኩት ምን አለና ግን አማን እውነት ድሬ ነው ያለው አለኝ አዎ እንደውም ዛሬ እንገናኛለን አልኩት ምነው ችግር አለ እንዴ አለኝ የምን ችግር እኔ እና እርሱ ለችግር ብቻ ነው ምንፈላለገው አልኩት እና ለምን ፈለገሽ አለኝ እንዴ አቤል ምን ሆነህ ነው ከተገናኘን ስንት ጊዜ አልኩት እሺ በቃ በእርሱ ምክንያት በድጋሚ እንድንኮራረፍ አልፈልግም አለ እኔም እሺ በቃ ደህና ዋል አልኩት ትንሽ በአነጋገሩ ተከፍቼ ስለነበር ኮስተር እንደማለት ብዬ ነበር ያናገርኩት አኮረፍሽ እንዴ አልኝ ለምን ብዬ አኮርፋለው አልኩት እና ድምፅሽ ትክክል አይደለም አለኝ አይ ምንም አልሆንኩም አልኩት እሺ እወድሀለው ብለሽ ስልኩን ዝጊው አለኝ እወድሃለሁ አልኩት ድምፄ ሳይቀየር ኧረ ባክሽ አልቀበልም እንደውም ተይው አለኝ ምኑን አልኩት መወደዱን ሌላ ቆንጆ ሴት እፈልጋለው አለኝ እስቲ ሞክረው አንተንም እሷንም ሹካ አግዬ ነው ቂጣቹን ምወጋላቹ ስለው በሳቅ ፍርስ አለ ከዛም ትንሽ ከተቀላለድን በኃላ እወድሻለሁ ሲለኝ እኔም አልኩት አይ ቃሉን በይልኝ አለኝ እወድሃለሁ አልኩት እና ስልኩን ዘጋውት እየነጠርኩ ወደ ሳሎን ሄድኩ እና ሶፍ ላይ ተዘረርኩ ማሚ ከክችን ትጣራለች አቤት ስላት ቁርስ እንዳዘጋጅ ነግራኝ ሳሎኑን ለማስተካከል ሄደች ቁርስ ሰርቼ በልተን ምናምን የቤቱን ስራ እንደጨረስኩ ትንሽ እራሴን ፈታ ለማድረግ ፊልም ከፈትኩ እና የማየው ፊልም በጣም አስለቃሽ ነበር ቁጭ ብዬ ስነፋረቅ ስልኬ ጮኸ...
       ✎  ክፍል አስራ ስምንት ከ 50 Vote♥️ በኋላ ይለቀቃል....  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ። 


┉┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄
             
 ╔═══❖•🌺•❖═══╗
         ❤️#ፍቅር_ያሸንፋል❤️

‌‌‌‌‌‌‌‌
 
                   #እውነተኛ ስሜት

ቻናላችንንይቀላቀሉ
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
ከወደዳችሁት ❤️
​​​♥️✿የተራራቀ ልብ✿♥️

        አጓጊ እና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ 


             ♥️ክፍል 18♥️


...🖊ስልኬ ጮኸ ሳየው አማን ነው ውይ ለካ አገኝሻለው ብሎኛል ከዛ ወዬ አማን ሰላም ነው አልኩት አለው እንዴት ነሽ አለኝ አለው አልኩት ትንሽ ካወራን በኃላ ቃልዬ በጣም ይቅርታ ዛሬ በጣም ብዙ ስራ ተደራረበብኝ እና ሲለኝ ችግር የለውም አትጨነቅ እኔም ዛሬ ማረፍ ፈልጌ ነበር አልኩት እርግጥኛ ነሽ አልተቀየምሽኝም አለኝ ኧረ ምን በወጣህ ችግር የለም አልኩት በቃ ነገ ግን እክስሻለው ምሳ በእኔ ወጪ የምትፈልጊው ቦታ ወስጄ ዘና ማረግህሽ አለኝ እሺ በቃ አትጨናነቅ አሁንም የስራህን ጊዜ አልሻማብህ በል ደና ዋል አልኩት እና ስልኩን ዘጋውት ትዙ እቤት መጣች እና አንቺ አለሽ አለችኝ አለው ውዷ ፕሲ ነው አልኳት አለው ምነው የቤት ልጅ ነኝ አልሽብኝ አለችኝ አልገባኝም አልኳት በጣም ጠፍተሻል ሰፈር ውስጥ አትታይም እኮ አለችኝ ባክሽ እንዲው እቤት ልቀመጥ ብዬ እንጂ ሌላ ምክንያት የለኝም አልኳት በይ ካልሽ ምን አረጋለው አለችኝ እና እስቲ ዞር ዞር እንበል አለችን ትዙዬ መውጣት አልፈልግም እቤት ይሻለኛል አልኳት ምነው ችግር አለ አልችኝ የምን ችግር ነው ምትይው አልኳት አይ እቤት ስላበዛሽብኝ ነው ለማንኛው ዛሬ ማታ የጓደኛዬ ልደት ነው ለምን አብረን አንሄድም አለችኝ እኔጃ እስቲ ላስብበት አልኳት ምን የፍቅር ጥያቄ አስመሰልሽው እኮ አልችኝ አይ ትንሽ ስለደበረኝ እኮ ነው ለማንኛውም እደውልልሻለው ስንት ሰአት ነው ምንሄደው ያው እኛ ቤቱንም ማስተካከል ስላለብን በጊዜ እንሄዳለን በቃ እሺ አልኳት እና ትንሽ ተቀምጣ በቃ ደውይ ወይም እደውላለው ብላኝ ሄደች ወድ 10 ሰአት አካባቢ ሱቅ ወጣውና አንዳንድ ልብሶች መግዛት አሰብኩ ከዛ አንዳንድ  ልብሶች ገዛዝቼ ወደ እቤት እየተመለስኩ እያለ አቤልዬ ደወለ...

    ✎  ክፍል አስራ ዘጠኝ ከ 50 Vote♥️ በኋላ ይለቀቃል....  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድራግ አይርሱ


‌‌‌‌‌
┉┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄
             
 ╔═══❖•🌺•❖═══╗
         ❤️#ፍቅር_ያሸንፋል❤️

‌‌‌‌‌‌‌‌
 
                   #እውነተኛ ስሜት

ቻናላችንንይቀላቀሉ
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
ከወደዳችሁት ❤️
​​​♥️✿የተራራቀ ልብ✿♥️

        አጓጊ እና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ


             ♥️ክፍል 19♥️


...🖊አቤል ደወለ አንስቼ ወዬ አቤሌ አልኩት ሰላም ነው ውዴ አለኝ አለውልህ እንዴት ነህልኝ አለው ዛሬ ምን ትሰሪያለሽ አለኝ አሁን ከፑቲክ እየወጣው ነው ግን በኃላ ልደት አለብኝ አልኩት ውይ ሲያናድድ አለ ምነው ስለው አይ የአክስቴ ልጅ የሆነ ነገር አዘጋጅታ ነበር እና ብትመጪዬ ብዬ አስቤ ነበር የደወልኩት ሲለኝ ወይ አንዳፍታ ታይቻቸው እመጣለው አልኩት እንደዛ ከሆነ ጥሩ ሀሳብ በቃ ስትወጪ ደውይልኝ አለኝ እሺ ማሬ በቃ ቻው አልኩት እሺ ቻው ብሎኝ ዘጋው ከዛም እቤት ገብቼ የገዛውትን ልብስ መሞከር ጀመርኩ ከዛም አንድ ጠቆር ያለ የሚያምር ቀሚስ መረጥኩ ፀጉሬን መስራት አስቤ ነበር ግን ሰአት እንደማይበቃኝ ስላወኩ ፍሪዝ አረኩት እና ዘጉሬን ወደ ትከሻዬ ለቀቅኩት ከዛም ጥቁሩን ቀሚስ አረኩት ሼፕ አለሽ ይሉኛል ግን ዛሬ ኩልል ብሎ ታየኝ ቀሚሱ እላዬ ላይ ስለተጣበቀ ነው መሰለኝ ከዛም በጣም ከፍታ የሌለው ሂል ጫማዬን አድርጌ ቡኒ ቻፕስቲክ እና ኩሌን ተቀባው ዛሬ የሌለ ፋ እንዳልኩ ለራሴ ታውቆኛል እኔ ብዙም መቀባባት አይመቸኝም ግን አቤልን ስለማገኘውም ነው ከዛ ትዙ የክፍሌን በር ብርግድ አርጋ ስገባ በስማም አለች ምነው አልኳት ይቅርታ ክፍል ተሳስቼ ነው ቃል የትናት ስትለኝ በሳቅ ፍርስ አልኩና ቃል መጣው ብላ ወጣች አልኳት አንቺ ምንድነው ባለ ልደቱ አንቺ መሰለሽ እኮ አለችኝ እና ልቀይረው ስላት ኧረ እስቲ ወንድ ቀይሪው እና አለችኝ ትዙ እንዲህ ስቀባባ ስለማታየኝ ነው እንዲህ ያለችው ዛሬ እሷም አምሮባታል ፒንክ አጭር ቀሚስ ነው ያረገችው ግን በጣም ሄዶባታል ከዛ በቃ ከጨረሽ እንውጣ ስትለኝ እኔ ብዙም አልቆይም የማገኘው ሰው አለ አልኳት እኔም ጠርጥሬያለው ድሮም እኮ ለማታውቂው ሰው እንዲህ እንደማዘንጭ ግን የት ነው ምትሄጂው አለችኝ ሚስጥር ነው አልኳት ከዛ ከእኔ ምደብቂው ነገር አለ አለችን አንቺ ደሞ እስቲ ምን ገዛሽላት ብዬ ስለ ስጦታው እየጠየኩ አረሳሳዋት ከዛም መንገድ ላይ ለፍላፊው እንዲው ሲያሰለቸን የጓደኛዋ ቤት ደረስን ዋው ልብ የሚያስደነግጥ ውበት ግርማ ሞገሱ ብቻ ጊብያቸው ስፍቱ ፈረስ ያስጋልባል በዛ ላይ ፅዳቱ አበቦቹ ብቻ በዚህ አይነት የዱር እንስሳት እንደሌለ መጠራጠር ነው በዚህ አይነት ቤታቸውን ስስለው ዋው ጓደኛዋ በር ጋ ቆማ ስጦታ እየተቀበለች የሚመጣውን ወደ ውስጥ ታስገባለች ከዛ ትዙ መጣሽልኝ አለቻት ቤቲዬ ማሬ ተባብለው ተቃቀፉ ከዛ ዞር ብላ አይታኝ የማን ቆንጅዬ ናት አለችኝ ፈገግ ብዬ ሰላም ቃል እባላለው አልኳት ቤቲ አለችኝ መልካም ልደት አልኳት አመሰግናለው ኑ ወደ ውስጥ እንግባ ብላን ሜላት ነይ የሌሎቹን ስጦታዎች አንቺ ተቀበይ ብላ እኛን ወደ ውስጥ ይዛን ገባች እና ሰው ታስተዋውቀን ጀመር ፕሮግራሙ ገና አልተጀመረም ግን አሁንም ደምቋል እና በመሀል ወንድሜ አሁን ይመጣል አስተዋውቃችኋለው አለችን እና መጣው ብላን ሄደች ከዛም ከዛ ቀበል አርጋ ትዙ ወኔ ወንድሟ እንዴት አባቱ እንደሚያምር አለችኝ ታውቂዋለሽ ስላት ኧረ በፎቶ ነው ያየውት አለችኝ ኧረ ቅንብር ሊሆን ይችላል ይሄኔ በአካል ገመጨጭ ፊት ነው ስላት ትንሽ ሳቀችና አይናን ከአንድ አቅጣጫ አፍጥጣ ተ ሳ ስ ተ ሻ ል ቃል አለችኝ ቃላቶቿን ዝግም እያረገች ምኑን ስላት ወንድሟ እየመጣ ነው አለችኝ እና ይምጣ ምን ታካብዳለች አልኳት ዞሬም ሳላየው ከዛ ወደእኛ መጣ ግን ሌላ ሴት በእጁ ይዟል ከአጠገቡ ሜላት አለች አለችኝ በቃ ተስፍሽን ቁረጭ ጓደኛ አለችው አልኳት ኧረ ከማንም እጅ ላይ ነጥቄ የራሴ አረገዋለው አለችኝ ከዛ አንቺ እብድ ስላት ቤቲ መጥታ ትዙ ወንድሜን ተተዋወቂው ብላ ስታስተዋውቃት ትዙ ስትለው እርሱ ደግሞ አ ሲል እኔ ቀና ስል እዛው ደርቄ ቀረው አይን ለአይን ተፍጠጥን ከዛ ከተቀመጥኩበት ቀስ ብዬ ብድግ አልኩ እና መልሼ ደግሜ አየውት ማመን ስላቃተኝ ነው መሰለኝ ከዛ ቤቲ እንዴ ምን ሆናችው ትተዋወቃላችሁ እንዴ ስትለን ትዙም ቃል ታቂዋለሽ ስትለኝ እኔ በድንጋጤ ሆኜ አ...

     ✎  ክፍል ሀያ ከ50 Vote♥️ በኋላ ይለቀቃል....  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ። 


┉┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄
             
 ╔═══❖•🌺•❖═══╗
         ❤️#ፍቅር_ያሸንፋል❤️

‌‌‌‌‌‌‌‌
 
                   #እውነተኛ ስሜት

ቻናላችንንይቀላቀሉ
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
ከወደዳችሁት ❤️
​​​​♥️✿የተራራቀ ልብ✿♥️

        አጓጊ እና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ 


             ♥️ክፍል 20♥️


...🖊ትዙም ቃል ታውቂዋለሽ ስትለኝ እኔ በድንጋጤ ሆኜ አማን አልኩ ከዛ እሱም ቃል አለኝ እንዴ እዚህ ምን ትሰራለህ ስለው የአክስቴን ልጅ ልደት ላከብር ነው የተገኘውት እንቺስ አልኝ የትዙ ጓደኛ ናት ለዛ ነው አልኩት በግርምት እያየውት ከዛ ሚገርም አጋጣሚ ነው አለኝ በጣም ስራህን ጨረስክ አልኩት ምን እጨርሳለው ይቺ እያለች ብሎ ቤቲን ዞር ብሎ አያት ዝም በል ብላ በስሱ ትከሻውን መታችው ከዛ እ ምን ልትይ ነው ካልመጣህ ብላ ጭቅጭቅ ነው ያረገችኝ አለ ከዛም ከአጠገቡ የቆመችውን ልጅ ሰላም ትባላለች ተዋወቂያት ጓደኛዬ ናት አለኝ ትዙ እእእእ አለች ከዛ ሁላችንም ዞር ብለን ስናያት እንደማፈር ብላ አንገቷን አቀረቀረች ከዛ ጥሩ ብለን እቤቱ በሰው ጢም ብሎ መንጫጫት ጀመረ የሰውም ብዛት እንደዛ እኔ ከአሁን አሁን ሰው መምጣት ያቆማል እላለው እንደውም ይጨምራል ከዛም አማን ነይ ውጭ እንውጣ አለኝ ከዛም ቦርሳዬን ለትዙ ሰጥቻት መጣው ብያት ወጣን ዛሬ ግን ለየት ብለሻል አለኝ ከአንድ ወንበር ላይ እንድቀመጥ ምልክት እየሰጠኝ እንዴት አልኩት ምን እንደሚል ለመስማት እየጓጓው አይ በጣም ነው ያማረብሽ ምን የተግኘ ነገር አለ አለኝ ኧረ ምን ይኖራል ብለህ ነው ለማንኛውም አመሰግናለው አንተም አምሮብሀል አልኩት ኧረ አለኝ አዎ እንደውም ትዙ የቤቲ ወንድም እንዴት እንደሚያምር ስትለኝ ነው አንተን አልጠበኩህም ነበር አልኩት ኧረ ተይ እንዲህ ብለሽኝ ደሞ በሀላ ጭንቅላትሽ ላይ እንዳልወጣ አለኝ ወንድ ነሀ ደሞ ወንድሜ ስትል ሰማዋት አልኩት አዎ ልክ እንደ ወንድሞ ነው ምታየኝ የአክስት ልጅ ሲባል በጣም የራቀ ስለሚመስላት ነው አለኝ ደስ ይላል እና ለምን እዚህ አትቆይም ለምን ሆቴል ያዝክ አልኩት ባክሽ ሰው ማስቸገር አልወድም ደሞ comfort አይሰማኝም ነበር አለኝ አይ ደስ ይላል አልኩት ስማ ደሞ ቅድም ያየዋት ልጅ ጓደኛዬ ናት ነው ያልከው ስለው አዎ አለኝ ምን አይነት አልኩት እንዴ አንቺ ልጅ እንደ ውበትሽ ምላስም ጨምረሻል አለኝ ወይኔ ብዙ ለፈለፍኩ አልኩት ኧረ እንደውም አውሪ አለኝ ከዛ ፀጉሬን በሀፍረት እክክ እክክ እያረኩ አንገቴን አቀረቀርኩ ከዛም ስራ ቦታ ነው የማውቃት በጣም ተጫዋች እና ፈታ ያለች ልጅ ናት ቤቲ ስትጨቀጭቀኝ ሰምታ አብረን ካልሄድን አለች እኔም እምቢ ማለቱ ሼም ስለሆነብኝ እሺ ብዬ ይዣት መጣው አለኝ እእእእ አልኩት ስለ ጠየቅሽኝ ልጅ እየነገርኩሽ ነው አለኝ እሺ ብዬ የባጥ የቆጡን ስናወራ ሰአቱ እልም ብሎ ሄደ ከዛ ትዙ መጥታ አንሄድም እንዴ አለችኝ ስንት ሰአት ነው እንዴ አልኳት 3:00 ሆነ እኮ አለችኝ ምን ብዬ ከመቀመጫዬ ብድግ አልኩና ስልኬ የት ነው አለኩ እኔ ጋር ቅድም መጣው ብለሽ ሰጥተሽኝ አልነበር አለችኝ እሺ ስጭኝ አልኳት ከቦርሳዬ ውስጥ አውጥታ ስትሰጠኝ 15 ሚስኮል አለ በጣም ደነገጥኩ...

      ✎  ክፍል ሀያ አንድ ከ50 Vote♥️ በኋላ ይለቀቃል....  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ። 


┉┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄
             
 ╔═══❖•🌺•❖═══╗
         ❤️#ፍቅር_ያሸንፋል❤️

‌‌‌‌‌‌‌‌
 
                   #እውነተኛ ስሜት

ቻናላችንንይቀላቀሉ
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
ከወደዳችሁት ❤️
♥️✿የተራራቀ ልብ✿♥️

        ✍️አጓጊ እና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ 


             ♥️ክፍል 21♥️


...🖊ስትሰጠኝ 15 ሚስኮል አለ በጣም ደነገጥኩ ከዛም መልሼ ስደውል ስልኩ አልሰራም ይላል ደግሜ ደጋግሜ ብደውልም አይሰራም ተናዶብኝ ነው ብዬ አሰብኩ እና ወደ ቤት ገባው በጣም ተናደድኩ ማታ ምንም እንቅልፍ ሊወስደኝ አልቻለም እንዲው በቃ ስገላበጥ የሆነ አካሌ የተቆረጠ እስኪመስለኝ ድረስ ከዛም በጣም በጨለማ ከቤት ወጣውና መራመድ ጀመርኩ ወዴት እንደምሄድ ባላውቅም ዝም ብዬ እራመዳለው የሆነ ጫካ ሚመስል ነገር ውስጥ ገባው ምንም ድምፅ አይሰማም አንድ ስራመድ የረገጥኩት የደረቀ ቅጠል ጩሀት ሲያሰማ ሁሉም ዛፎች መነቃነቅ እና ሰምቼው የማላውቀውን የሚያስፈራ የሴት ድምፅ ሰማው የሆነ ስላቅ አይነት ሳቅ ትስቃለች ከዛ ግን አንድ ነጭ የለበሰ ሰው ወደ እኔ መቅረብ ይጀምራል እኔም ሳልፈራ ወደ እርሱ እየተጠጋው መራመድ ጀመርኩ እንዴ አቤሌ በዚህ ሰትአት ምን ትሰራለህ አቤል ነበር ነጭ ለብሶ ወደ እኔ ሚጠጋው ከዛ ይቅርታ የኔ ማር ሲለኝ ለምኑ ብዬ ወደ እርሱ ተጠጋው ከዛም በጣም ጥቁር ትልቅዬ አሞራ መጥቶ አቤልን ወሰደው በድንጋጤ ከእንቅልፌ ባንኜ ተነሳው ሰውነቴ ላብ በላብ ሆናል በእየሱስ ስም ብዬ አቤሌ ምን ሆነብኝ ብዬ ተጨነኩ የስልኬ ጥሪ ካለውበት ሰመመን አወጣኝ የማይታወቅ ቁጥር ነበር አንስቼ ሃሎ አልኩ .......

እንዴት ሆስፒታል እንደደረስኩ አላቅም የለበስኩት የለሊት ልብስ በባዶ እግሬ ፀጉሬ ተንጨቧራል ወደ ድንገተኛ ክፍል እየሮጥኩ ሄድኩ የአቤል አክስት ኮሊደር ላይ ትንጎራደዳለች በጣም ከማልቀስዋ የተነሳ አይንዋ ቀይ ሆኗል አንዴ ተያይተናል እቤት አቤሌን ልትወስደው የመጣች ጊዜ አቤልስ ምን ተፈጠረ አቤሌ ምን ሆነ አልኳት ልጄ ተረጋጊ ቀዶ ጥገና እየተደረገለት ነው ምንም ማሰብ አልቻልኩም የቆምኩበት መሬት ላይ ወደቅኩ እባክሽ ተረጋጊ ልጄ ጠንከር ማለት አለብሽ አለችኝ ሜሮን የፁሁፍ መልክት ላከችልኝ ሳየው አማን አብረው እንዲሆኑ እንደጠየቃት ነበር ፅሁፍ የላከችልኝ የአቤል ቤተሰብ ሲል ስልኬን ጥዬ ተነሳው...

   ✎  ክፍል ሀያ ሁለት የመጨረሻው ክፍል ከ50 Vote♥️ በኋላ ይለቀቃል....  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ እና ሼር ማድረግ አይርሱ። 


‌‌‌‌‌
┉┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄
             
╔═══❖•🌺•❖═══╗
         ❤️#ፍቅር_ያሸንፋል❤️

‌‌‌‌‌‌‌‌
 
                   ♥️#እውነተኛ ስሜት♥️

ቻናላችንንይቀላቀሉ
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
ከወደዳችሁት ❤️
​​​​​♥️✿የተራራቀ ልብ✿♥️

        አጓጊ እና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ 

               ♥️ክፍል 22♥️
         🌿የመጨረሻው_ክፍል🌿

...🖊የአቤል ቤተሰብ ሲል ስልኬን ጥዬ ተነሳውና አቤት አልነው እእእእ አቤል የደረሰበት አደጋ በጣም ከባድ ነው እና አሁን ደም አንሶናል ይህ ማለት ካልፈጠንን አቤልን ልናጣው እንችላለን ኧረ ዶክተር ምን ትጠብቃለህ ይኸው እኔ አለዋ ከእኔ ውሰድ አልኩት የደም አይነትሽ o ነው አይ አይደለም አልኩት እንግዲያው o የሆነ ሰው ፈልጉ ምንም ጊዜ የለንም አቤልን ልናጣው እንችላለን አለን ደርቄ ቀረው ለኔ ባረገው ለምን አቤል ጥለኸኝ መሄድ አትችልም ያለበለዚያ እኔም እከተልሀለው አቤልልልልል እያልኩ እየጮሁክ ማልቀስ ጀመረኩ አማን አማን አልኩና በእንብርክክ ስልኬን መዳበስ ጀመርኩ ስልኬን ከጣልኩበት አንስቼ ደወልኩለት ወዬ ቃል አለኝ አቤል አቤል አልኩት አቤል ምን አለኝ ተደናግጦ የመኪና አደጋ ደረሰበት እና o የደም አይነት ካልተገኘ መሞቱ ነው አልኩት..........


ከ3 ወር በኃላ💘


ህይወት በቃ ለካ እንዲህ ናት እኛ በምናስበው ሳይሆን እሷ ባለችው ነው እኔ አቤሌን በጣም እወደው ነበር ሁሌም ከአጠገቤ ሲርቅ ነገሮች ይርቁብኝ ነበር ፍቅረኛዬ ነው ብዬ ለሰው ላስተዋውቀው እፈልግ ነበር እኔ አሁን ላይ ላለውበት ነገር የአቤል እጅ አለበት የእርሱን ፍቅር በማሰብ ዛሬ ዳግም እንድቆም እና እንደሰው አንገቴን ቀና አርጌ እንድሄድ አድርጎኛል ቆይ አንዴ ስልኬ እየጠራ ነው መቅዲ ናት ወዬ ማሬ ቃል አታምኝም በዚህ ሰአት እንዲህ አይነት ወሬ ላወራሽ አይገባም ግን በቃ ከአይምሮዬ በላይ ስለሆነ ነው ምንድነው ንገሪኝ አልኳት ኩሩቤል እኮ ፕሮሚስ አረገልኝ አለችኝ እንኳን ደስ አለሽ የኔ ውድ እና አሁን የት ነሽ እየመጣው ነው ኩሩቤልንም ይዤው ነው ምመጣው ጥሩ አርገሻል በዛው እንተዋወቃለን ፕሮግራም ሳይጀመር ቶሎ ነይ እሺ የኔ ውድ ብላ ስልኩን ዘጋችው ማም የክፍሌን በር ከፍታ ከብዙ ጓደኞቼ ጋር ገባች የኔ ልዕልት እንዴት እንዳማረብሽ ከአይን ያውጣሽ ስትለኝ እነ ትዙም ዛሬ እማ እንኳን አቤል አምላክ ይማረክብሻል ስትል ሁሉም ሳቁ ዛሬ የእኔ እና የአቤል ሰርግ መሆኑ ህልም እንጂ እውን አልመስል ብሎኛል አማን ላረገልን ውለታ ፈጣሪ ይክፈለው ያኔ በወቅቱ ባይደርስ ዛሬ በዚህ ሰአት አቤል አይኖርም ነበር ፍቅረኛዬ ብዬ ያልጠራውትን ግን ከልቡ ሚያፈቅረኝ ከልቤ ማፈቅረውን ልጅ ባሌ ልለው ነው አቤሌ ከልቤ አፈቅርሀለው ብልህ ቃላቱ ያንስብኛል እኔ አንተን የማፍቀሬ ልክ በቃላት ድርደራ አረፍተነገር ሚሰራ አይደለም ማንም ሰው አይንህ ውስጥ ልገባ ይችላል ልብህ ውስጥ ግን ለመግባት ልዩ ሰው መሆን ይኖርበታል ልክ እንደ አቤል ህይወት ውብ ትሆንልናለች እውነተኛ ስንሆን እና ባጠገባችን ላሉ ሰዎች የደስታ ምክንያት ስንሆን ውይ ሙሽራው መጣ በቃ ቻው ታሪኬን ጨርሻለው እናንተም እንደ እኔ ምርጡን አቤል ይስጣቹ

               ♥️ተፈፀመ♥️

     💈ምስጋና
👉
#ታሪኩን_በመከታተል_አስተ_የታችሁን_ላደረሳችሁኝ_በሙሉ!
     
#በቀጣይ_ታሪክ_እስከምንገናኝ_በሌሎች_ፕሮግራሞች_አብራችሁን_ቆዩ_እናመሰግናለን🙏
┄┉┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄
ሀሳብ አስታየት ካላቹ
#comment ይናግሩን
‌‌‌‌‌‌‌‌🌹🍃𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌𝐒𝐇𝐄𝐑🍃🌹
‌‌‌‌‌‌
2024/09/21 01:17:06
Back to Top
HTML Embed Code: