Telegram Web Link
ገብርኤል ሀያል 🙏❤️ 19
ሰኔ 21 ጎለጎታ ማርያም እንኳን አደረሳችሁ

በስሟ_ያመናችሁ_በምልጀዋ_የቆማችሁ
#ድንግል_ማርያም_የልባችሁን_መሻት_ሁሉ
ትፈጽምላችሁ አሜን አሜን አሜን

እመቤታችን ማርያም በተገባልሽ ቃልኪዳን ሃገራችንና ህዝቦቿን ተዋህዶ ሃይማኖታችንን ቅድስት ቤተክርስቲያንን ጠብቂልን አሜን

#OrthodoxTewahdo #ኦርቶዶክስ
#profile #timline #post #story

On Telegram👇
         • www.tg-me.com/winagfx2
         • www.tg-me.com/winaGraphics
Share 🙏
https://www.tg-me.com/winaGraphics
ክበር ባለኝ ነገር

#OrthodoxTewahdo #ኦርቶዶክስ
#profile #timline #post #story

On Telegram👇
         • www.tg-me.com/winagfx2
         • www.tg-me.com/winaGraphics
Share 🙏
https://www.tg-me.com/winaGraphics
የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

#OrthodoxTewahdo #ኦርቶዶክስ
#profile #timline #post #story

On Telegram👇
         • www.tg-me.com/winagfx2
         • www.tg-me.com/winaGraphics
Share 🙏
https://www.tg-me.com/winaGraphics
የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

#OrthodoxTewahdo #ኦርቶዶክስ
#profile #timline #post #story

On Telegram👇
         • www.tg-me.com/winagfx2
         • www.tg-me.com/winaGraphics
Share 🙏
https://www.tg-me.com/winaGraphics
ሰኔ 30 በዚህች ዕለት ነብይ፤ ካህን፤ መጥምቅ፤ መምህር፤ ፃድቅ፤ ሰማዕት፤ ሐዋርያ የሆነ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ተወለደ።
‘‘ የበራክዩ ልጅ ዘካርያስ ሆይ ልጅ ሰጠኝ ብለሕ የፀለይከው ፀሎት ተስምቶልህልና አትፍራ ሚስትህ ኤልሳቤጥ ወንድ ልጅ ትወልዳለች ሰሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ፡፡ ' ዮሐንስ ' የእብራይስጥ ቋንቋ ሲሆን ትርጓሜውም ፍስሐ ወ ሐሴት ርህራሄ ወሳህል (ፍፁም ደስታ ደግነት ይቅርታ) ማለት ነው:: በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል : በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናል የወይን ጠጅ የሚያስክር መጠጥ አይጠጣም የእግዚአብሔርን ጎዳና ይጠርጋል ።” አለው ወደ ዘካርያስ ለብስራት የተላከ መልአክ:: ዘካርያስም በእድሜ አርጅቶ ነበርና ይህ ነገር እንዴት ይሆናል አለ ። መላኩም በቁጣ ‹‹ እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው መላኩ ቅዱሰ ገብርኤል ነኝ ! ይህን አበስርህ ዘንድ ከእግዚአብሔር ተልኬ ነበር ፤ ነገር ግን የምነግርህን አልሰማኸኝምና ብትሰማኝም አላመንክምና ይህ ነገር እስኪሆን ድረስ ድዳ ትሆናለህ ›› ብሎት ወደ ሰማይ አረገ።

ኤልሳቤጥም ፀነሰች እግዚአብሄርንም እንዲህ ብላ አመሰገነች “ ስድቤን ከሰዎች ያርቅልኝ ዘንድ እግዚአብሔር በረድኤት ጎበኘኝ ” እያለች ብዙዎችም ባለመውለዷ ተገዳድረዋት ነበር እግዚአብሔር የጠላት ጌታዋ የረሳት አድርገዋት ነበር፡፡ ቢወልዷት እንጂ አትወልድም ጡቷ የደረቀ እሷ ጡቷ ጠባች እንጂ አታጠባም ደረቅ ናት መርገም የተመላች ነች ይሏት ነበር፡፡ ኤልሳቤጥ ግን ልጅ በማጣት እንደኔ የሚያዝኑ ሴቶች ሁሉ ያመስግኑታል ትል ነበር፡፡ በወርሃ ሰኔ (ሰኔ 30) ቅድስት ኤልሳቤጥ ቅዱስ ገብርኤል የተናገረለትን ክብሩ ከፍ ያለ መንገድ ጠራጊ ሐዋርያ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስን ወለደች፡፡ በተወለድ በ8ኛውም ቀን ሊገረዙት ሲሉ አባቱ ዘካርያስ ለልጁ ስም ለማውጣት ቀለም እየነከረ ብራና ላይ ‹ዮ ሐ ን ስ› ብሎ ፅፎ ሲጨርስ የካህኑ ዘካርያስ አንደበት ተከፈተ፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ከዮሐንስ መወለድ 6 ወር ቡኃላ በቤቴልሄም ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደ። የጌታን መወለድ የሰማው ሄሮድስ ከ2 አመት በታች ያሉትን 14 እልፍ ከአራት ሺ የቤቴልሔም ሕፃናትን አሳረደ፡፡

በእድሜያቸው አመሻሽ ላይ የተሰጣቸውን ልጅ ሞት እንደሚያባርረው ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ ሲሰማ አለቀሰ ህፃኑንም አቅፎ እየሳመ በሽምግልናዬ ወራት እፅናናብህ ዘንድ የወለድኩህ ልጄ ካንተ ልለይ ነው ሽማግሌ አባትህ ደከምኩ የአይኖቼም ብርሐን ፈዘዙ በፊት በኋላዬ አባቴ የሚለኝ ምንም ልጅ የለኝም ልጄ አንተ ብቻ ነህ የሸምግልናዬ ተስፋ የእድሜዬ መስላል እያለ ዘካርያስ አለቀሰ ። ኤልሳቤጥንም ዩሐንስን ይዘሽ ወደ ዚፋት የሚባል በርሃ ሽሺ ከንጉሱ ወታደሮች ከእርጉም አውሬ ይሰውርሽ ብሎ ባርኮ አሰናበታት፡፡ኤልሳቤጥም አራዊቱን ሳትፈራ ወደ ምድረ በዳ ተሰደደች ። የሄሮድስ ወታደሮችም ሕፃኑን ባጡት ጊዜ በሕፃኑ ፋንታ አረጋዊው ሊቀካህን ዘካርያስን መስከረም 8 ቀን አንገቱን ቆርጠው በቤተመቅደስ ውስጥ ደሙን አፈስሱና ገደሉት ። ደሙም ወደ እግዚአብሔር ጮኸ ከካህኑ ዘካርያስ መገደል ቡኃላ ለአገልግሎት ወደ መቅደስ የሚገቡ ሁሉ ‹‹ ዘካርያስ በግፍ ተገደለ ደሙን የሚበቀል እስኪመጣ ይጮኸል›› የሚል ድምፅ ይሰሙ ነበር ።

"ስለዚህ፥ እነሆ፥ ነቢያትንና ጥበበኞችን ጻፎችንም ወደ እናንተ እልካለሁ፤ ከእነርሱም ትገድላላችሁ ትሰቅሉማላችሁ፥ ከእነርሱም በምኵራባችሁ ትገርፋላችሁ ከከተማም ወደ ከተማ ታሳድዳላችሁ፤ ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደስና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው የጻድቅ ደም ሁሉ ይደርስባችሁ ዘንድ። እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ሁሉ በዚህ ትውልድ ላይ ይደርሳል። ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ነቢያትን የምትገድል ወደ እርስዋ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም። እነሆ፥ ቤታችሁ የተፈታ ሆኖ ይቀርላችኋል። እላችኋለሁና፥ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እስክትሉ ድረስ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩኝም።" (የማቴዎስ ወንጌል 23:34-39)

(መስከረም 7) ቀን ቅድስት ኤልሳቤጥ በበረሃ አረፈች፡፡ በብሩ ደመና ተጭነው ድንግል ማርያም ከልጇ ጋር እና ከሶሎሜ ጋር ቅድስት ኤልሳቤጥ ካረፈችበት ደረሱ አልቅሰውም ቀበሯት፡፡ ዩሐንስም ለእስራኤል እስኪገለጥ ድረስ በብርሃ በንፀህና ይኖር ነበር፡፡

ጊዜውም ሲደርስ ብርታት የተሞላበትን የተግሳፅ ቃል የሚናገር ሰው ይኸውም እንደነገስታቱ ጌጠኛ ልብስ እንደዘመኑም ሐብታም በዋጋ የከበረ እንደተራው ሕዝብ የክትልብሰ አለበሰም የግመል ፀጉር ለብሷል ወገቡን በጠፍር ታጥቋል የተለመደውን የከተማ ምግብ አይቀምስም አንቦጣና የበርሃ ማር ይበላል፡፡

በዬርዳኖስ ወንዝ እየጮኸ ተናገረ የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ ሰው ድምፅ ነብይ፤ካህን፤መጥምቅ፤መምህር ፤ፃድቅ ሰማዕት፤ ሐዋርያ፤ እየተባለ በ7 ስም የሚጠራ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ። ማንንም ሳይፋራ እውነት ይናገራል ‹‹አብርሃም አባት አለን በአብርሃም ቅድስና መንግስተ ሰማይ ትሰጠናለች›› ብለው የሚኩራሩትን ፈሪሳውያንና ሰድቃውያንን ፈፅሞ አልፈራቸውም አብርሃም አባት አለን እንደምትሉ አይምስላቹ እያለ ገሰፃቸው ፡፡ ለተቸገረው እርዱ፤ 2 ልብስ ያለው ለሌለው ያካፍል፤ ለተራበ ምግብን በቤቱ ያለ ይስጥ፤ መልካም ፍሬን አፍሩ ፤በሐሰት አትክስሱ፤ ማንንም አታስለቅሱ፤ ከታዘዘላቻሁ አብልጣችሁ አትውሰዱ፤ እውነት አድርጉ ፤መልካም ሰው ሁኑ እያለ ህዝቡን ያቀና ጎዳናውን እየጠረገ ያዘጋጅ ነበር፡፡

ግርማው ሐይሉ ያስፈራቸው እየሩሳሌማውያን ይሄ በነብዩ እንደሚመጣ የተነገረው የአባቶቻችን የተስፋ ፍፃሜ እየሱስ ክርስቶስ ነው አሉ፡፡ እርሱ ግን እኔ ክርስቶስ አይደለሁም የጫማውን ጠፍር መፍታት የማይገባኝ ከእኔ የሚበረታ ይመጣል እኔ በውሃ አጠምቃኋለው እርሱ ግን በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል እያለ ስለ ክርስቶስ መሰከረ ይህንንም እየመሰከረ ሳለ ኢየሱስ ክርስቶስ በገዳመ ቆሮንጦስ ፆምን ከመጀመሩ አስቀድሞ ወደ ዬርዳኖስ መጣ ። ዪሐንስም እየሱስ ክርሰቶስን ሲያይ ‹‹ እነሆ ሐጢያትን የሚያስተሰርይ የእግአብሔር በግ›› እያለ ጮኸ ይኸውም ከእኔ ቡኃላ ይመጣል ከእኔም በፊት ነበረ ከእኔ ይልቅ የከበረ እርሱ እየሱስ ነው እያለ መሰከረ፡፡

ራጉኤል በትጋቱ እዬብ በፅድቁ አባቶች በስራቸው የሚያቃጥለውን እሳተመለኮት ጌታን ማጥመቅ አልተቻላቸውም ። ዩሐንስ ግን አጠመቀው ዩሐንስም እውነት እየተናገረ ነገስታትን እየገሰፀ በክርስቶስ ፊት መልእክተኛው ሆኖ ይሄዳል፡ በወቅቱ የ4ኛው ክፍለ ገዥ የነበረው ሄሮድስ የወንድሙን የፊሊፖስን ሚስት በማግባቱና ስለሚሰራው ክፉ ስራ በህዝብ ፊት ይገሰፀው ነበር ‹‹የወንድምህን የፊሊፖስ ሚስት ልታገባ አይገባህም›› እያለ በአደባባይ ገልጦ ይናገር ነበር፡፡ ይሄ የዩሐንስ ተግሳፅ ለሄሮድስ ሽንፈት ላገባት ለሄሮድያዳ ሐፍረት ነበር፡፡ ሄሮድስም ተገሳፅ ቢበዛበት ዮሐንስን አሲዞ አሳሰረው። እለቱ የሄሮድስ ልደት በታላቅ አዋጅ እየተከበረ ነው የሄሮድያዳ ልጅ ወለተ ሄሮድያዳም በንጉሱ ልደት ልትዘፍን ከንጉሱ ፈቃድ አገኘች በዘፈኗም የሁሉንም ልብ ማረከች ንጉሱ ሄሮድስም በልደቱ ቀን የወደደችውን ሊያደርግላት እስከ መንግስቱ እኩሌታ በሽልማት መልክ ሊሰጣት ቃል ገባላት፡፡
2024/10/01 11:11:09
Back to Top
HTML Embed Code: