Telegram Web Link
እርሷም ከወርቅ ከብር ከንግስና ይልቅ የቅዱስ ዩሐንስን አንገት ቆርጦ እንዲሰጣት ጠየቀችው እርሱም ወታደሮቹን አስልኮ ለአለም መደሐኒት ለኢየሱስ ክርስቶስ ጎዳና የሚጠርግ ኑሮውን በበርሐ መታጠቂያው ጠፍር የሆነ የመጥምቀ መለኮትን አንገት መስከረም 2 ቀን አስቆረጠ፡፡ የዩሐንስንም አንገት በወንጭት አድርገው አመጡት። የቅዱስ ዩሐንስ አይኖች ተገልጠው ነበር ፊቱም እንደፀሐይ ያበራ መልካም ሽታ ከራሱ ላይ ይወጣ ነበር፡፡ የዩሐንስ ደቀመዛሙርት ግን ቀሪው ስጋውን በኤልሳ መቃብር ቀበሩት፡፡ የዩሐንስም አንገት 2 ክንፍ አወጣች

የዩሐንስም አንገት “ህገ እግዚአብሔር ተጥሷል” እያለች ትጮህ ነበር፡፡

ሄሮድያዳ እጆቹ ከትከሻዋ ተቆርጠው ወደቁ ምድር አፏን ከፍታ እስከ አንገቷ ድረስ ዋጠቻት ልጇም ህሊናዋን ሳተች እራሷን በእንጨትና በድንጋይ እየመታች “ሄሮድስ ሆይ የወንድምህን የፊሊፖስን ሚስት ልታገባ አይገባህም” እያለች ጮኸች ፈፅሞ አበደች፡፡ ሄሮድስም ህሊናው እየረበሸው አእምሮውን ሳተ፡፡ የገዛ አካሉን እየነጨና እየቦጨቀ ሽቶ ተልቶ አብጦ ሞተ፡፡

የቅዱስ ዩሐንስ አንገት ግን ለ15 አመት እየዞረች አስተማረች ‹‹ ህግ እግዚአብሄር ተጥሷል መንግስተ ሰማይ ቀርባለችና ንሰሐ ግቡ …..›› እያለች ጮኸች ሚያዚያ 15 የዩሐንስ አንገት አረፈች ደቀመዛሙርቱም አስቀድመው ከቀበሩት አካሉ ጋር አገናኝተው በነብዩ ኤልሳ መቃብር በታላቅ ክብር ቀበሩት፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ ሰኔ 30 ልደቱ ነው፤መስከረም 2 አንገቱ የተቆረጠበት ሚያዚያ 15 ያረፈበት፤የካቲት 30 ራሱ የተገለጸበት ነው። ከነዚህ ውስጥ መስከረም 2 እና ሰኔ 30ን ቤተክርስቲያን ሰማዕቱን በደማቁ ታዘክረዋለች።

ቅዱስ ዩሐንስ መጥምቅ በምድር ላይ 46 ዓመት ከ2 ወር ኖሯል ይኸውም ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ አሰቀድሞ 6ወር፤2 አመት ንጉስ ሄሮድስ እስኪያሳድደው፤5 ዓመት ከእናቱ ጋር በበርሃ፤23 አመት እናቱ ካረፈች ቡኃላ ለእስራሄል ሳይገለጥ በበርሃ፤ 8 ወር በውህኒ ፤አንገቱ ከተቆረጠ በኃላ 15 ዓመት፡፡

ነብይና ሐዋርያ የሆነ የቅዱስ ዩሐንስ ልመናው አማላጅነቱና ፀሎቱ እንደማይደርቅ የውሐ ምንጭ ቀንና ሌሊት እንደማይቆም እስትንፋስ ነው፡፡
ዛሬም ሸንኮራ ላይ ብዙ ተአምር ያደርጋል። ጌታ እግዚአብሔርም ደጅህን የረገጠ፣ ያልቻለ ደግሞ ዝክርህን ዘክሮ ዝክሩ ቢያልቅ እንኩአን ሰሃኑን የላሰውን እምርልሀለው፤ ዩሐንስ ሆይ ላልምረው ደጅህን አላስረግጠውም ብሎ ቃልኪዳን ገብቶለታል። የሸንኮራ ዩሐንስ ፀበል ድንቅ ስራማ እንደምን ይወራ? ሃኪም ቤተሰቦቿን ትንሽ ጊዜ ነው የቀራት እስክትሞት ድረስ ፍቅርና እንክብካቤ ስጧት፥ የተባለላት አንድ እህት ከሞትኩኝ አይቀር ዩሐንስ ፀበሉ ጋር ወስዳችሁ ጣሉኝ መጥምቀ መለኮት እንዲያድነኝ አምናለሁ ብላ ይኸው ዛሬም ድረስ ድና በቤቱ ትገኛለች። እንግዲህ አለም እንዲህ ናት ተስፋ የለህም ብላ የሞት ቀጠሮ ሪፈር ስትፅፍ፤ እግዚአብሔር ደግሞ የህይወት ሪፈር ይፅፍልናል።
ብዙ የተደረገለት ብዙ ያወራል
ያልተደረገለት ምን ያወራል ?

ነብዩ ዳዊት በመዝሙሩ ፃድቅ ሰው እንደ ዘንባባ ያፈራል እንደዝግባም ይበዛል እንዳለ ዛሬም የቅዱስ ዩሐንስ መጥምቅ ጸሎቱ በረከቱ በሁላችን ላይ ፀንቶ ይደርብን አማላጅነቱ ይደረግልን ዛሬም ዘወትርም ለዘለአለሙ አሜን፡፡

‹‹ ን ሰ ሐ ግቡ ን ሰ ሐ ግቡ... ›› በምድረ በዳ የሚጮህ ሰው ድምፅ፡፡

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ዛሬም ዘወትርም ለዘለአለሙ አሜን፡፡ .!.

#OrthodoxTewahdo #ኦርቶዶክስ
#profile #timline #post #story

On Telegram👇
         • www.tg-me.com/winagfx2
         • www.tg-me.com/winaGraphics
Share 🙏
https://www.tg-me.com/winaGraphics
ሰኔ 30 በዚህች ዕለት ነብይ፤ ካህን፤ መጥምቅ፤ መምህር፤ ፃድቅ፤ ሰማዕት፤ ሐዋርያ የሆነ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ተወለደ።

ነብዩ ዳዊት በመዝሙሩ ፃድቅ ሰው እንደ ዘንባባ ያፈራል እንደዝግባም ይበዛል እንዳለ ዛሬም የቅዱስ ዩሐንስ መጥምቅ ጸሎቱ በረከቱ በሁላችን ላይ ፀንቶ ይደርብን አማላጅነቱ ይደረግልን ዛሬም ዘወትርም ለዘለአለሙ አሜን፡፡

እንኳን አደረሳችሁ

#OrthodoxTewahdo #ኦርቶዶክስ
#profile #timline #post #story

On Telegram👇
         • www.tg-me.com/winagfx2
         • www.tg-me.com/winaGraphics
Share 🙏
https://www.tg-me.com/winaGraphics
የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

#OrthodoxTewahdo #ኦርቶዶክስ
#profile #timline #post #story

On Telegram👇
         • www.tg-me.com/winagfx2
         • www.tg-me.com/winaGraphics
Share 🙏
https://www.tg-me.com/winaGraphics
ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ!

#OrthodoxTewahdo #ኦርቶዶክስ
#profile #timline #post #story

On Telegram👇
         • www.tg-me.com/winagfx2
         • www.tg-me.com/winaGraphics
Share 🙏
https://www.tg-me.com/winaGraphics
ይለይብኛል ሚካኤል 12

#OrthodoxTewahdo #ኦርቶዶክስ
#profile #timline #post #story

On Telegram👇
         • www.tg-me.com/winagfx2
         • www.tg-me.com/winaGraphics
Share 🙏
https://www.tg-me.com/winaGraphics
ሰባቱ የእግዚአብሔር የተስፋ ቃሎች

ለምትወዷቸው አካፍሏቸው

#OrthodoxTewahdo #ኦርቶዶክስ
#profile #timline #post #story

On Telegram👇
         • www.tg-me.com/winagfx2
         • www.tg-me.com/winaGraphics
Share 🙏
https://www.tg-me.com/winaGraphics
2024/10/01 13:36:35
Back to Top
HTML Embed Code: