Telegram Web Link
ከሚስቴ ጋር በማይረባ ነገር ተጋጨን

👇🏾

ከነኩርፊያችን ሳንነጋገር ሁለታችንም ወደ ስራ አቀናን: እንደ አጋጣሚ ሆኖ ግን ሁለታችንም የምንሳፈረው በአንድ ታክሲ ነው

እኔ ካዛንችዝ ስወርድ እሷ ደግሞ ወደ ፒያሳ ትቀጥላለች

ቀድሚያት ከቤት ወጣሁኝ: በሮቹን ዘጋግታ ተከተለችኝ:: የታክሲው ሰልፍ ላይ ምንም አላወራንም:: ተራችን ደርሶ ስንሳፈር እኔ የታክሲው መጨረሻ ወንበር ላይ ተቀመጥኩኝ: እሷ ደግሞ ከእኔ ፊት ለፊት ካለው ወንበር ላይ ተቀመጠች

ታክሲው መንቀሳቀስ ሲጀምር ከሚስቴ ጎን የተቀመጠው ጎረምሳ ሚስቴን ማውራት ጀመረ

አጠገቧ ከተቀመጠበት ሰአት አንስቶ ሚስቴን በተደጋጋሚ ሲመለከታት አይቼዋለሁኝ: አንዴ ፀጉሯን ሌላ ጊዜ ደግሞ ፊቷን እያየ ምራቁን ሲውጥ ተመልክቼዋለሁኝ

ሚስቴን ወዴት እንደምትሄድ በመጠየቅ ነበር የጀመረው: ስራ እየሄደች እንደሆነ ስትነግረው ይሰማኛል

"ስሜ ሚኪ ይባላል: ለከተማው አዲስ ነኝ:: ለብዙ አመታቶች ውጭ ሀገር ትምህርት ላይ ነበርኩኝ: እዚህ ሰፈር ቤት ተከራይቼ ገብቼ ነው"

"በጣም ደስ ይላል: እኔ እንኳ እዚህ ሰፈር ከገባሁኝ ሁለት አመታቶች ሆኑኝ" ሚስቴ ፈገግ ስትል በጎን ይታየኛል

ሰውዬው አላቆመም

👇🏾

“ለምን ታዲያ ሰሞኑን አንገናኝም: ቤታችን አንድ ሰፈር በመሆኑ ተደዋውለን መገናኘት እንችላለን:: በዚያ ላይ በጣም ነው የምታምሪው

“አመሰግናለሁ በጣም"

የታክሲው ረዳት ሚስቴን ሂሳብ ሲጠይቃት ጎረምሳው ከፈለ

"ቁጥርሽን ልቀበልሽ?" ብሎ ስልኩን ለመመዝገብ ሲያዘጋጅ ጣልቃ መግባት እንዳለብኝ ተረዳሁኝ

ሚስቴን ጀርባዋን መታ አድርጌ ወደ እኔ ስትዞር "ለግፋባቸው ወተቱን በጡጦ አድርገሽለታል?" ብዬ ጠየቅኳት

ሚስቴ ግራ ተጋባች : ግፋባቸው ደግሞ ማነው ሳትል አልቀረችም

"አልጋነሽን ደግሞ ከትምህርት ቤት ማምጣት እንዳትረሺ" ጨመርኩኝ

ሚስቴ እንደ እብድ እያየቺኝ ሳቀች

"አዎን ፍቅሬ ወተቱን አዘጋጅቼ ነው የመጣሁት: አልጋነሽንም ከትምህርት ቤት አመጣታለሁኝ" አለችኝ

"ባልሽ ነው?" ጎረምሳው ጠየቀ

ሚስቴ ራሷን በአዎንታ ነቀነቀች

የእኔ መውረጃ ላይ ስንደርስ ይዣት ወረድኩኝ: እየሳቀች ተከተለችኝ

"ቆይ አንተ! ማነው ግፋባቸው ማናት አልጋነሽ?"

"የወደፊት ልጆቻችን ናቸዋ" እየሳቅኩኝ መለስኩላት

በሌላ ታክሲ አሳፍሪያት ወደ ስራ ቦታዬ አቀናሁኝ

👇🏾

በኩርፊያ መካከል ሰይጣን እንዳይገባ መጠንቀቅ ነው

ቢቻልስ ተኮራርፎ አለመቆየት መልካም ነው ❤️🙌🏼

(አንብቤ ወደ እኛ ሀገር ለዛ የመለስኩት ነው)

@wegoch
@wegoch
@paappii

By zemelak
ተካፍሎ የመብላት ፀጋ

-

አንድ የሕክምና ዶክተር አሜሪካ ውስጥ የሮዜቲ መንደር/ከተማ ነዋሪዎች የጤና ሁኔታ ይገርመውና ጥናት ይጀምራል። የዚያ ማህበረሰብ ከ65 ዓመት ዕድሜ በላይ የሆኑ አዋቂዎች ከእድሜ አቻዎቻቸው ሌሎች አሜሪካውያን በተለየ ሁኔታ የልብ ሕመም ወይም ችግር የለባቸውም። የሚሞቱት በዕድሜ አርጅተው ብቻ ነው። ፍፁም ጤነኞች ናቸው። ይሄ ያልተለመደ ነበረና ማጥናት ጀመረ።

መጀመሪያ ከጣልያን ሮዜቲ ከተማ የመጡ እንደመሆናቸው መጠን ሌሎች ጣልያናውያን የሚመገቡትን የወይራ ዘይት ለምግብነት ስለሚጠቀሙ ነው የሚል መላምት ይዞ ነበር የተነሳው። ነገር ግን ሲያያቸው ሌላው ሕዝብ የሚጠቀመውን ተራ ዘይት ነበር የሚጠቀሙት። ሌሎች የአመጋገብና የጤና ልማዳቸውን ቢያጠናም የተለየ ነገር አላገኘም።

ከሙያው አንፃር ብቻ ያደረገው ጥናት የትም አላደረሰውምና አንድ ሌላ አንትሮፖሎጂስት ወዳጁን ጋብዞ ጥናቱን ጀመሩ። በሂደት አንድ ነገር አገኙ። የሮዜቲ ማህበረሰብ አባላት ረጅምና ጤነኛ ሕይወት የሚመሩት ሌላውን የሚያስጨንቅ ሕይወት ስለሌላቸው ነው። ፉክክር የሌለበት ማህበረሰብ ነው። ከሀገራቸው የሚመጡ አዳዲስ ስደተኞችም ሆኑ ነባሮቹ የከተማው ነዋሪዎች ለአንድ ተመሳሳይ ሕግ ይገዛሉ። ከሌላው የማህበረሰብ አባል በተለየ ሁኔታ ሀብትና ንብረት አጋብሰው ነጥረው አይወጡም። ሁሉም እኩል ኑሮ እንዲኖሩ የሚያደርግ ሥርዓት ነበራቸው። ይሄ የፉክክር ያለመኖር ነው አብዛኛውን ከ65 ዓመት በላይ የሆነ ግለሰብ የሚያጠቃው የልብ ሕመም እነሱን የማያጠቃው ሲሉ ይደመድማሉ። ይሄንን የሚነግረን ማልኮም ግላድዌል ነው - ካነበብኩ ረዥም ጊዜ በሆነኝ መፅሐፉ።

-

እኛ ጋር ~ ሀዋሳ

ሁል ጊዜ ሀዋሳ ስሄድ የማደርጋት አንድ routine አለ - አሞራ ገደል ሄዶ ጥሬ አሳ በብዙ ዓይነት ዳጣ እየተለበለቡ መብላት። እዚያ ስሄድ ታዲያ ሁሌ የሚገርመኝ አንድ የምግብ/የሥራ ሰንሰለት አለ። ገና በሩ ላይ ስትደርስ የሚቀበሉህ አሳ ገፋፊ አለ። ሥራው አሳውን ገፍፎና በላልቶ ማቅረብ ነው። ከቻለ ከሚያውቀው አሳ አጥማጅ/ሻጭ ያገናኝሀል፣ ካልፈለግክ ግን ራስህ የመረጥከው ቦታ ትሄድና ትመርጣለህ። ቢላውን ይዞ ይከተልሀል። በመሀል ግን ልጅ እግር ሴት ልጆች የውሀ ጆግና ጄሪካን ይዘው ውሀ ልሽጥልህ ይሉሀል። አሳው በንፁህ ውሀ መታጠብ ስላለበት ከጠያቂዎችህ አንዱን እሺ ትላለህ።

አሳ ሻጩን፣ በላቹንና ውሀ ቀጂዋን በእግርህ እየሄድክ ዞር ስትል ተጣምረው ታገኛለህ። ከዛ ቁጭ ብለህ የምትበላበት ቦታ ፍለጋ ዞር ስትል አሳውን የምትበላበት ቂጣ የሚሸጡ ሴቶች ታገኛለህ። መርጠህ ተናግረህ ታልፋለህ። ከዛ አምስት ስድስት ዓይነት ዳጣ የሚሸጡ ሴቶች ጋር ትሄድና ዳጣ ታዛለህ። ቀጥለህ ውሀ፣ ጠላ ወይም የአሳ ሾርባ የሚሸጡ ቤቶች ያዘጋጁት ወንበርና ጠረጴዛ ላይ ቁጭ ትልና አሳህ አልቆ እስኪመጣ ትጠብቃለህ።

ከአንድ ምግብ ላይ ስንት ሰራተኛ፣ ስንት ለዕለት ጉርስ ተሯሯጭ ቆጠርክ? ሁሉም ተካፍሎ ነው የሚበላው። አንዱ የሌላውን ሥራ ጠቅልሎ ሊያቀርብልህ ይችላልኮ። ግን አያደርጉትም። ለዓመታት ታዝቤያለሁ። ይሄንን ሳስብ ደስስስስስ ይለኛል። ይሄንን ምግብ ጥንቅቅ ብሎ አልቆ አንድ ያማረ ሆቴል ላይ በተመሳሳይ ዋጋ ባገኘው ያን ያህል አልደሰትም።

ሁላችንም በዙሪያችን ያሉ ነገሮችን፣ ሥራዎችን፣ ገቢዎችን፣ ሸክሞችን ወዘተ እንደነሱ ብናደርግ እንዴት አሪፍ ነበር! ሰላማዊ ሕይወት!

@wegoch
@wegoch
@paappii

By gemechu merara fana
በፍም እሳት ማቃመስ
(እንደ ማስተዋወቂያ እነሆ...)
(ያዕቆብ ብርሃኑ)
*

የሰውን ልጅ ከተራ አውሬነት ጎራ ነጥሎ ወደ መለኮታዊነት ያሸጋገረው እሳትን መፈልሰፉ ነበር፡፡ እሳትን ከማላመዱ በፊት የሰው ልጅ ከ20 በማይበልጡ ትንንሽ ቡድናት የሚንቀሳቀስ፣ የአዳኝ አራዊት ሰለባነትን ሽሽት የእውርድንብር የሚቃትት ድንጉጥ ፍጥረት ሆኖ አሳለፈ፡፡ እሳትን ማላመዱ ግን በአንድ ጊዜ ድርድርብ መሳሪያዎችን እንደመታጠቅ ሆነለት፡፡ አብስሎ መብላት ተቻለው፤ ጤናው ተሻሻለ፡፡ ምግቡም በረከተ፡፡ በአንድ ጊዜ ‹food chain›ኑ አናት ላይ ለመቀመጥ በቃ፡፡ እሳቱ ራሱን ከቅዝቃዜና ከአራዊት ጥቃት ለመከላከል እንደ ሁነኛ መሳሪያ አገለገለው፡፡

በእርግጥም የሰው ልጅ እሳቱን እስኪፈለስፍ ድረስ ለመጥፋት የተቃረበ፣ በስራ ፈትነት የሚንጀባረር ለአደጋ የተጋለጠ እንሰሳ ነበር፡፡ (Man was a meandering and jabbering around beast until he discover fire...) እሳትን ካላመደ በኋላ የሰው ልጅ ለስልጣኔው -ም-ት-ክ-የ-ለ-ሽ- መሠረቶች የሆኑትን የእሳት ግኝቶች -
ምድጃን (hearth) -
መሰዊያን (Altar) እና
ማቅለጫን (forge) ፈለሰፈ፡፡

ምድጃው ሁለተናዊ ደኅንነት እና መረጋጋትን አቀዳጀው፡፡ ምድጃው እንደ ‹ሴል› (cell) ሆኖ የሰው ልጅ በዙሪያው እንዲሰባሰብ ምክንያት ሆነ፡፡ ቤተሰብ እንዲመሰረት አገዘው፡፡ ከቤተሰብ አስር ሃያ እያለ ወደ ትንንሽ ማኅበረብነት አደገ፡፡ መረጋጋት ቻለ፡፡ ቀስበቀስ መንደሮችን መገንባት ጀመረ፡፡ በምድጃው ዙሪያ ብዙ ዓይነት ተረቶችን አደራ፡፡ የሰው ልጅ ተረቶች፣ ታሪኮች፣ ሚቶች በሙሉ የመነጩት ከምድጃው ነበር፡፡ ተረቶቹ አፈታሪኮቹ ምናቡን ለመሳል ጠቀሙት፡፡

መሰዊያው መንፈሳዊ በጎነትን አጎናጸፈው፡፡ የዓለም ኃይማኖቶች በሙሉ የመነጩት ከመሰዊያው ነበር፡፡
ማቅለጫው ቅኝቱ የፈጠራ ሆነ፡፡ ከጦር አንካሴና ማጭድ ጀምሮ እስከ ሮኬት ሳይንስ ዛሬም ድረስ እየተራቀቀ ለቀጠለው ቴክኖሎጂያዊ መራቀቁ መነሻው እሱ ማቅለጫው ነበር፡፡

ነገርግን በግሪክና መሰል ጥንታዊ ተረታዊ ትርክቶች እንደሚባለው የሰው ልጅ እሳትን ከአማልክት አልሰረቀም፡፡ የሰው ልጅ በመጀመሪያ እሳትን የከዋክብቱ ገጽ ላይ ተጽፎ አየው፡፡ ጫረውም... እሳትን ከክዋክብት ገጽ ለመጫር ደግሞ ከገል እና ኩበት ይልቅ ምናብ ያስፈልጋል፡፡

ምናብ ምንጊዜም አሸናፊ ያደርጋል፡፡ ጥቂትስ ስንኳ የተሳሉ ምናቦችን ከመካከሉ መፍጠር የሆነለት ሕዝብ ምንጊዜም የትርክት የበላይነትን ይቀዳጃል፡፡ ስለምናብ ሳወራ ስለድርሰት ብቻ እየተናገርሁ የሚመስለው ካለ መቸስ ምን እላለሁ፡፡ ነገርግን ቴሌስኮፕ፣ ማይክሮስኮፕ፣ የማተሚያ ማሽን፣ ኢንተርኔት፣ ፌስቡክን ጨምሮ በጠቅላላው የኤሮፓ ሥልጣኔ ግኝቶች የምናብ ውጤቶች መሆናቸው እሙን ነው፡፡

የእሳትንም ያህል ፍጹም ቅን፣ ገር እና በስነተፈጥሮው ቀጥተኛ ነገር መኖሩን አላውቅም፡፡ እሳት ከብሉያት፣ ነብያት፣ ወንጌላዊያን፣ ከአፈታሪኮች እና ባለቅንያት ዘመን ጀምሮ ብዙ የተባለለት መለኮት አከል ረቂቅ ክንውን ነበር፡፡ እሳት ሲፈጅ፣ ሲበላ እንጂ ሲያርፍ ማደሪያው የት፣ ሲግለበለብ መከሰቻው ከወዴት እንደሆንስ ስንኳ የሚያውቅም የለም፡፡ እሳት ስሪቱ የነበልባል፣ የፍላጻ ብቻ አይደለም፡፡ የቃል፣ የቀለም፣ የመንፈስ ልዩ ልዩ ዓይነት አለው፡፡ እሳት ንጹህ ነው፤ ቅን ነው፤ ገር ነው፡፡ ግን ደግሞ አውዳሚ፣ ጨራሽ፣ ፈጅ፣ ቀሳፊ፣ ቁጡም ነው፡፡ የዚህ ረቂቅ የነበልባል ቅኝት ጥሪ እና ምሪት ሰብዓዊነትን ማበልጸግ መሆኑ ጥንት ከአፈታሪክ፣ ከነፕሮሚተስ ዘመን ጀምሮ ይታወቃል፡፡

አሳት ሥሪቱ የእንከንየለሽነት፣ የምኅረትየለሽነት መሆኑም እሙን ነው፡፡ እሳት በመንፈሳዊውም (spirited) ይሁን በገቢራዊ (empirical) ባህሪው የሚያሻግር (fire of transmuting) እና የሚያሳርር (fire of destruction) መንታ ጉልበት ያለው ረቂቅ ሁነት ነው፡፡ እሳት የነካውን ሁሉ የሚያነጻ (purifying) ወይም የሚያገረጣ (terrifying) አቅም አለው፡፡ ቁም ነገሩ ለየትኛው አሰልጥነሽዋል/ አሰልጥነኸዋል የሚለው ብቻ ነው፡፡
ቀደም ብዬ እንዳልኩት የሰው ልጅ በመጀመሪያ እሳትን የከዋክብቱ ገጽ ላይ ተጽፎ አየው፡፡ ያም በቅዱስ መጽሐፍ እንደተጻፈ - ምልክት ሆነለት - ... ነብዩ ኢሳያስ ለነብይነት የተመረጠበትን አኳኋን በሚናገርበት በትንቢተ ኢሳያስ ምዕ 6፡8 ላይ እንደምን በፍም እሳት መቃመስን ተቃምሶ መንጻትን እንደተቀዳጀ ሲገልጽ...
‹‹ከሱራፌል አንዱ ወደ እኔ ተላከ፡፡ በእጁም ከመሰዊያው በጉጠት የወሰደው ፍም ነበረ፡፡ አፌን ዳበሰበትና ‹እነሆ ይህ ከንፈሮችህን ነክቷል፡፡ በደልህም ከአንተ ተወገደ፡፡ ኃጥያትምህም ከአንተ ተሰረየልህ› አለኝ፡፡›› ይላል፡፡
የሰው ልጅም የእሳት አቀባበል እንዲህ ይመስለኛል፡፡ ልክ የባላገር እናት የአራስ ቤት ጨቅላ ልጇን ወደ ሕይወት ለመጥራት በቅቤ እንደምታቃምስ እንዲያ የሰው ልጅ የነቢይ በሆነ በእሳት መቃመስን ተቃመሰ፡፡ ከእሳት ጋር መገናኘቱ ሁለንተናውን የሚያሻግር ክስተት ሆነለት፡፡ መቼ? የት? የሰው ልጅ ከእሳት ጋር ተዋወቀ ሳይንስ ባዝኖ ባዝኖ መልስ ቁርጥ ያለ መልስ ያጣላቸው ጥያቄዎች ናቸው፡፡ በደፈናው እስከ 2 ሚሊዮን ዓመታት ይገመታል ብሎ ማለፍ ይሻል ይመስለኛል፡፡ ነገርግንስ የሰው ልጅ እሳቱን ማላመዱ፣ በትንታግ መፈተኑ፣ ነበልባሉን መግራቱ ራሱ የሰው ልጅ ብዙ ዓይነት ሞራላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ሥነልቦናዊና አካላዊ ሽግግር እንዲያከናውን ረዳው፡፡
እሳትን ከፈለሰፉት የመጀመሪያዎቹ አውሬ መሰል የሰው ልጆች እስከ እሳትን ወደ ኤሌክትሪክ የቀሩት ድረስ ከ50 - 60 ሺህ ትውልዶች እንደተፈራረቁ ይገመታል፡፡ የእኛ ግን እርግማን ይመስላል፡፡ ሌላው ዓለም እሳቱን ከአመድነት ወደ ስማርት ምድጃነት ከፍታ ሲያሻግር እኛ ዛሬም ጉልቻዋን የሙጥኝ ብለናታል፡፡ ከጥንታዊነት (primitive sentiment) ያልተሻሻለ ቢሆንስ ስንኳ... ለዘመናት ጉልቻውን ታክከን ተረቱን ማንዘገጋችን አልቀረም፡፡ መሰዊያዎችንም (የአምልኮ ቦታዎች) በዓይነት እና በጥራት እየገነባን ስናደገድግ ምዕታት አልፈዋል፡፡ ለሰብዓዊ ልማት ከፍተኛ ጠቀሜታ የነበረውን ዋነኛውን የእሳት ግኝት ማቅለጫውን (forge) ግን ሆነ ብለን ረሳን፡፡ ማቅለጫውን ሙሉ ለሙሉ ብንረሳ ከብዙ መቶ ሺህ ዓመታት በፊት የመጀመሪያው የሰው ልጅ በተጠቀመበት ጦር ጀት የታጠቀውን ጣሊያንን ለመግጠም ተገደድን፡፡

የኢትዮጵያን የሥልጣኔ ታሪክ በተለይ ከአክሱም ውድቀት በኋላ የነበረውን ሂደት በጥልቀት የሚመረምር ሰው የጎደለን ነገር ማቅለጫው እንደነበር ግልጽ ይሆንለታል፡፡ ማቅለጫው ጥበብ፣ ዕውቀት፣ ፈጠራ፣ ቴክኖሎጂ፣ ሌላም ሌላም ብዙ ነገር ነው፡፡ በዚህ መጽሐፌ ከተካተቱ አስራ አንድ መጣጥፎች ውስጥ ስድሳ ገጾችን በሚሸፍነው የመጀመሪያው ክፍል የኢትዮጵያ ሥልጣኔ የጎደለው የመሰለኝን የማቅለጫውን ነገር በጥድፊያም ቢሆን ለመዳሰስ ሞክሬያለሁ፡፡ ሌሎች በዚህ መጽሐፍ ስር የተካተቱ ሌሎች አስሩም መጣጥፎቼ በልህቀት ለሚያነባቸው የእሳት ንክኪ እንዳላቸው አምናለሁ፡፡

ከዛሬ ጀምሮ በየመደብሩ ትገ ኛለች!!!
በዓለም ላይ በጣም ብልህ ሰው

አንድ ዶክተር፣ ጠበቃ፣ ትንሽ ልጅ እና አንድ ቄስ በትንሽ የግል አውሮፕላን በረራ ላይ ነበሩ። በድንገት አውሮፕላኑ የሞተር ችግር አጋጠመው። አብራሪው ከፍተኛ ጥረት ቢያደርግም አውሮፕላኑ መውረድ ጀመረ። በመጨረሻም ፓይለቱ ፓራሹት ይዞ ተሳፋሪዎቹን ቢዘሉ እንደሚሻል ተናግሮ ጮኸ ወጣ ።

እንደ አለመታደል ሆኖ የቀሩት ሶስት ፓራሹቶች ብቻ ነበሩ።

ዶክተሩ አንዱን ያዘና "ሀኪም ነኝ ህይወትን አድናለሁ ስለዚህ መኖር አለብኝ" ብሎ ዘሎ ወጣ።

ከዚያም ጠበቃው "እኔ ጠበቃ ነኝ እና ጠበቆች በአለም ላይ በጣም ብልህ ሰዎች ናቸው መኖር ይገባኛል." ብሎ ፓራሹት ያዘና ዘሎ ወጣ።

ቄሱም ወደ ትንሹ ልጅ ተመለከተ እና "ልጄ ረጅም እና ሙሉ ህይወት ኖሬአለሁ አንተ ወጣት ነህ እና ሙሉ ህይወትህ ከፊትህ ይቅደም። የመጨረሻውን ፓራሹት ይዘህ በሰላም ኑር" አሉት ።

ትንሹ ልጅ ፓራሹቱን ለካህኑ ሰጣቸውና "አይጨነቁ አባቴ በአለም ላይ በጣም ብልህ እና አስተዋይ ሰው ያስፈልጋልና እርሶ ኖረው ትውልድ ያንፁ " ብሎ እርሱ ብቻ ሊቀር ሲወስን ቄሱም " አይ ልጄ ታላቅን የሚያከብር እና ምሳሌ የሚሆን ሰው ያስፈልጋልና በአንዱ ፓራሹት ለሁለት መዝለል እንችላለንና ና ልዘልህ ብለው ተያይዘው ወረዱ ።

ስራህ ሁል ጊዜ አይገልፅህም ጥሩ ሰው መሆን ግን ይገልፅሀል።

@wegoch
@wegoch
@paappii

By Tariku
#ማጣት እና ጊዜ

         ……..ጊዜ የሆነ የውሃ አካል አይነት ቅርፅ አለው፡፡ አንሳፎ ወይንም አጣድፎ መውሰድ የመሰለ፡፡ በሄደ ቁጥር እያገላበጠ ያበስለናል፡፡  እድሜያችንም ይቆጥራል፡፡ ትንሽ እንኳን ፍጥነታችን ከፍጥነቱ ካልተመጣጠነ ደሞ ደርሰን ላንደርስበት ቀናት እያደነቃቀፉን እንካለባለን፡፡ እንግዲህ ድንገት አዝግመን ጊዜ ካመለጠን እንዲህ ነው፡፡ አካልና ጥላ እንሆናለን፡፡ ይሄዳል፣ እንከተላለን፡፡ ላንቀድመው ወይ ላንተካከለው መሮጥና መከተል እያዛለን እናረጃለን፡፡ በመደበኛ ሁኔታ ጊዜ እንደ ጎርፍ እሽሩሩ በሚመስል አሳስቆ መውሰድ አዝሎን የሚሄድ ከሆነ ግን ነገሩ ጊዜን እንደ ጥላ ከሚከተሉት ይለያል፡፡

           ጊዜ ብቻውን ጊዜ ብቻ ሳይሆን የሁነቶች ጥርቅም ጭምር ነው፡፡ ከነዚያ ሁነቶች አንዱ አይሰብሩት ሊሰብረን ይችላል፡፡ ጊዜ ደግሞ ሁሌም የህመም እና የልብ ስብራት ወጌሻ ሆኖ ቶሎ ቁስልን መሻር አይቻለውም፡፡ ጊዜ እራሱ ጊዜ ይፈልጋል፡፡ ይሄኔ እኛም ማጣታችንን መቀበል ሲሳነን፣ ከምናፈቅረው መለየታችንን ለማመን ሲያቅተን በጊዜ ታዝለን አንሄድም፡፡ ወይንም ጊዜን እንደ ጥላ አንከተልም፡፡ በውስጡ ሰጥመን እንጠፋለንን፡ ወይንም ጊዜ ሲሄድ ተገትረን እንቀራለን፡፡ ስለ ነገ ግድ አይኖረንም፡፡ አሁን የሚባል የጊዜ ልክን ክደን ‹ዛሬ› ባልነው ትላንት ላይ እንቆማለን፡፡ ያፈቀርነውን ካጣንበት ቅፅበት ወዲህ ዐለም ምኅዋሯን ስታ መሽከርከር አልገታችም፡፡ ፀሃይና ጨረቃ፣ ወቅቶች መፈራረቅ አላቆሙም፡፡ ወንዞች ሽቅብ ፈሰው፣ ሰማይ አልታረሰም፡፡ ቀናትም ቢሆኑ እንደ ሃውልት ተገትረው አልቀሩም፡፡ ይሆን የነበረው ሳይሻ ቀጥሏል፡፡ ጊዜም መሳሳቡን አልገታም (አይገታም)፡፡ እኛ ግን ላንዘም፣ ላንነቃነቅ አንዳች ‹አፍዝ፣ አደንግዝ› የተደረገብን ያህል ተገትረን እንቀራለን፡፡ ቀናት እየተጎተቱ ወራትን፣ ወራትም አመትን ያህላሉ፡፡ ዘመን ሲሄድ አኗኗር በየጊዜው ይቀየራል፡፡ ይሄኔ ትላንት ላይ የቆምን እኛ ከዘመን እና ከአኗኗር መቃቃር እንጀምራለን፡፡ ድርጊቶቻችን ሁሉ ጊዜን እንደሚከተሉ ወይንም ከሱ እኩል እንደሚሄዱ ብዙኃን ስላልሆነ ማህበራዊነታችን ሳናውቀውና ሳናስተውለው እንሸረሽረዋለን፡፡ ከሰው ፈልገን እየሸሸን የተገፋን ይመስለናል፡፡ ቅርባችን ላሉ ሁሉ ትላንት የነበረው ትዝታ፣ ለኛ ግን ‹ዛሬ› ሆኖ ሰፊ ቦታ ይይዝብናል፡፡
‹ማጣት› እና ‹ጊዜ› በሆነ አይነት ቀጭን ክር ተጠላልፈው የተያያዙ ናቸው፡፡ ጊዜ ማጣትን አጠንክሮ የደደረ የሀዘንነት ቅርፅ ይሰጠዋል፡፡ ካልሆነም ደሞ ይሽረዋል፡፡ የጉዳቱ ልክም ጨምር የሚሰፈረው በጊዜ ነው፡፡ መቼስ በአብዛኛው ለአጭር  ወቅት ከምናውቀው ይልቅ ለረጅም ጊዜ አብሮን የቆየን ስናጣ ሀዘን ይበረታል፡፡ ቅርበትም ቢሆን እየተበበ የሚመጣው ጊዜ በገፋ ልክ ነው፡፡

         ብቻ ማጣት የሚሉት እዳ ከጊዜ ያጓድላል፡፡ ከመኖር ያቃቅራል፡፡ ሞትንም ያረክሳል፡፡ መኖርም፣ አለመኖርም ጣዕም ያጡብናል፡፡ ጣዕም በራሱ ምንነቱ ይጠፋብናል፡፡ እንደ ፈሰሰ ውሃ በማይታፈስ አካሄድ የተለየን ሰው የሚሄድ ጊዜ ትዝታውን እያደበዘዘ እንዳያስረጀው እና በለጋነቱ እንዲቆይልን ስንል ካጣንበት ቀን እንቆማለን፡፡ በገዛ ራሳችን ፈንታ ትዝታችንን ‹እሹሩሩ› እንላለን፡፡ ግን አባባይ የሚያስፈልገን አልቃሾች እኛ ነን፡፡


By #Lewi @Lee_wrld777


@wegoch
@wegoch
@paappii
ጀለስ . . .

ጀለስ ወደ ሸገር ሊሄድ ፕሌን ውስጥ መቀመጫውን አግኝቶ ቦታውን እንደያዘ አንዲት ቀሽት ቺክ አይቶ ልቡ መምታት ጀመረ። ወደሱ አቅጣጫ እየመጣች መሆኑን ሲያውቅ አይኑን በለጠጠ። አጠገቡ መጥታ ስትቀመጥማ መተንፈስ አቃተው።

እንደተቀመጠች በወሬ አጣደፋት።

«የአዲሳባ ልጅ ነሽ?»

«አይደለሁም»

«እና ለሥራ ነው ለመዝናናት?»

ፈገግ ብላ «አንድ በሥነ-ፆታ እና ወሲባዊ ግንኙነት ባለሙያዎች የሚደረግ ኮንፈረንስ ላይ ልሳተፍ ነው የምሄደው።»

ምራቁን ጉርጭጭ ሲያደርግ እየሰማችው ነበር። ቀሽት መሆኗ ሳያንስ ወሲብ ነክ ነገር ላይ ልትሳተፍ እየሄደች . . . . በለው! ሁኔታው እንደያስነቃበት ተጠንቅቆ ጠየቃት፣

«እና አንቺ ምን በምን አግባብ ተሳታፊ ሆንሽ ኮንፈረንሱ ላይ?»

«ጥናት አቀርባለሁ። ከሕይወት ልምዴ ተነስቼ በሕብረተሰቡ ውስጥ ሥነ-ፆታን እና ወሲብን በተመለከተ ያለውን የተሳሳተ ግንዛቤ ለማስተካከል ነው የምሄደው።»

ጀለስ ምራቁን እየዋጠ «እንዴ? በሀገራችን ደግሞ ምን ዓይነት የተሳሳቱ ግንዛቤዎች አሉ?»

«ለምሳሌ በሀገራችን ትልቅ ቸንቸሎ አላቸው የሚባሉት ኦሮሞዎች ሲሆኑ እውነታው ግን ትልቅ ቸንቸሎ ያላቸው ወላይታ ወንዶች ናቸው። ሌላው ደግሞ ሴት አያያዝ ያውቃሉ፣ አፍቃሪ ናቸው የሚባሉት ተጋሩ ወንዶች ሲሆኑ እውነታው ግን አፍቃሪዎቹ ኦሮሞ ወንዶች ናቸው።» ይሄንን ካለች በኋላ ሴትየዋ ትንሽ ደንገጥ ብላ . . .

«ይቅርታ ምንም ለማላውቀው ሰው ስለራሴ ብዙ ነገርኩና uncomfortable አደረግኩህ መሰለኝ» አለችና አቆመች። ይሄኔ ጀለስ . . .

«ኧረ ጣጣ የለውም፣ ገመቹ እባላለሁ። ጓደኞቼ ግን “ጦና” ብለው ነው የሚጠሩኝ»

🚶‍♂️🚶‍♂️🚶‍♂️

@wegoch
@wegoch
@paappii

By Gemechu merera fana
የኢትዮጵያ ቡድን የዛሬ ምሽት ነገር ይህን አስታወሰን

ከአመታት በፊት ነው ። Charlton Athletic እና Chelsea በለንደኑ ስታምፎርድ ብሪጅ ስታዲየም ጨዋታ ነበራቸው ።
....
እና ጨዋታው ከተጀመረ ከደቂቃዎች በኋላ ፡ ዝናቡ እየበረታ ፡ ጭጋግና ጉም ስታዲየሙን ሸፈነው ። ተጫዋቾች አደለም ኳሷን አይተው ፡ መምታት ፡ እርስ በርስ መተያየት ሁሉ እያቃታቸው መጣ ።
......
በዚህ ጊዜ ዳኛው ውጡ አሉ " ይሄ ጭጋግ እስኪገፍ ጨዋታው መቆም አለበት "

ልክ ከዳኛው ይህ ቃል እንደተሰማ ፡ በሜዳው ላይ የነበሩት የቼልሲና የቻርልተን አትሌቲክ ተጫዋቾች በፍጥነት ሜዳውን ለቀው ወደ መልበሻ ክፍል ገቡ ።
.....
ጭጋግና ጉሙ እየባሰ መጣ ። የስታዲየሙ ሜዳ የመጨለም ያህል ሆነ ። በሜዳው ላይ አንድም ተጫዋች የለም ። ከአንድ ሰው በስተቀር ።

ይህ ሰው የቻርልተን አትሌቲኩ በረኛ Sam Bartram ነው ። ሳም ፡ በድቅድቁ ጭጋግና ጉም መሀከል ካሁን ካሁን ኳስ ወደሱ ግብ ከተመታ በማለት ፡ የጎሉን በር ይዞ እየተጠባበቀ ነው ።
......
ሆኖም እስካሁን ምንም ኳስ አልተሞከረበትምና ፡ ጭጋጉ ባያሳየውም ቡድኑ የቼልሲን የግብ ክልል እያጠቃ እንደሆነ እያሰበ ፡ ምንም በማይታየው ጭጋግና ጉም ውስጥ ብቻውን ቆሟል ።
............
በዚህ ሁኔታ እያለ ፡ አስራምስተኛው ደቂቃ ላይ ግን በስታዲየም ውስጥ ከሱ ብዙም ባልራቀ ቦታ ላይ የነበረ ፖሊስ ፡ የበረኛው ቦታ ላይ የቆመ የሚመስል ብዥታ ተመለከተ ።
ፖሊሱ ለማረጋገጥ ወደ ግቡ ተጠጋ ። ግብ ጠባቂው Sam Bartram ጎሉን እየተጠባበቀ አገኘው ።
.....
ወደ መልበሻ ክፍል ይዞት ከተመለሰ በኋላ ሲጠየቅ ፡ ፖሊሱ መጥቶ እስከሚያገኘው ድረስ ተጫዋቾች መውጣታቸውን አያውቅም ነበር ። የክለቡ ተጫዋቾችም በረኛው አብሯቸው እንደሌለ ልብ አላሉም ።

@wegoch
@wegoch
@paappii

By wasihun
አህያ ላይ ከከረምን አይቀር . . .

ገሜ/ጦና ከተማ ውስጥ ዎክ እያደረገ አንድ ጠጅ ቤት በር ላይ "አህያውን ላሳቀው ሰው 5000 ብር እና ነፃ ጠጅ እንሸልማለን" የሚል ማስታወቂያ ያያል። ይገባና ባለቤቱን አናግሮ ወደታሰረው አህያ ሄደና በጆሮው የሆነ ነገር ሹክ አለው። አህያው ፍርፍር ብሎ መሳቅ ጀመረ። ጦናም ጠጁን ጠግቦ ብሩን ተቀብሎ ወደ ቤቱ ሄደ።

በሳምንቱ እዚያው ጠጅ ቤት በር ላይ "አህያውን መሳቅ ላስቆመው ሰው 5000 ብር እና ነፃ ጠጅ እንሸልማለን" ተብሎ ተለጥፏል። ጦናም ባለቤቱን አናገረና ወደ አህያው ሄደ። ከደቂቃ በኋላ አህያው መሳቁን አቆመ። ጦናም ጠጁን ጠግቦ ብሩን ተቀብሎ ወደ ቤቱ ሊሄድ ሲል ባለቤቱ ተገርሞ ጠየቀው።

"እንዴት እንደዚህ ማድረግ ቻልክ?"

ጦና "ባለፈው በጆሮው የኔ ቸንቸሎ ከሱ ጀላ እንደሚበልጥ ነግሬው ነው የሳቀው" ሲል መለሰ።

"እሺ አሁንስ ሳቁን እንዴት አስቆምከው?"

"አውጥቼ አሳየሁት!" 😂

@wegoch
@wegoch
@paappii

By Gemechu merera fana
ጃፓን ውስጥ አንድ ሬስቶራንት አለ ።
እና የምግቡን ዝርዝር ወደኛ ቀይረን እንቀጥል
.....
በመጀመሪያ ቀን በዚህ ሬስቶራንት የተጠቀመ ሰው ሲናገር ፡ ወደ ምግብ ቤቱ ገብቶ አረፍ እንዳለ ፡ አንድ በእድሜ የገፉ አስተናጋጅ ተቀበሉት ።
ምን ልታዘዝ
" ምሳ ምን አላችሁ ? "
ትልቋ አስተናጋጅ ለሰውየው የሚፈልገውን ምግብ እንዲያዝ ሜኒውን ሰጡት
አተኩሮ ካየ በኋላ ፡ ...
"እሽ አንድ ጥብስና ፡ የሚጠጣ ደግሞ አምቦውሀ ያምጡልኝ "
....
አስተናጋጇ ትእዛዙን ተቀብለው ሄዱና ፡ ትንሽ ቆይተው ተመለሱ ። ምግቡን ያዘዘው ሰው ፡ ባዶ እጃቸውን የመጡትን አስተናጋጅ እያየ ፡....
" ምነው አልደረሰም ? " ብሎ ጠየቀ .

ኸረ ደርሷል ይኸው ይዤ መጥቻለሁ አሉና የሂሳብ መጠየቂያ ቢሉን አቀበሉት ።
" ምንድነው ይሄ ፡ ከምግቡ በፊት ነው እንዴ ሂሳብ ? "

አስተናጋጇ ፈገግ እያሉ .... ኸረ በፍፁም ፡ አሁን የበላኸው ቅቅልና የለስላሳ መጠጡ ሂሳብ ነው

" እንዴ እኔ ያዘዝኩት ጥብስና አምቦውሀ ነው ፡ እሱም አልመጣልኝምኮ "

የዚህ ጊዜ ትልቋ አስተናጋጅ ስህተት እንደሰሩ ገባቸውና ፡ ይቅርታ ለካ ያንተ አይደለም ብለው ቢሉን ከሱ አጠገብ ላሉ ተስተናጋጆች ሰጧቸውና
ያንተን አሁን ይዤ እመጣለሁ ብለውት እየተቻኮሉ ወደ ኪችን ተመለሱ ።
.....
እና ብዙም ሳይቆዩ በእጃቸው ምግብ የያዘ ሰሀን ይዘው መጡና ጠረጴዛው ላይ አስቀምጠው ፡ ቆይ የሚጠጣውን ይዤልህ ልምጣ ብለው ሄዱ ።
......
ሰውየው የመጣለትን ምግብ አየው ። በቅቤ ያበደ የቋንጣ ፍርፍር ነበር ፡ አሁን ተናደደ እሱ ያዘዘው ጥብስና አምቦውሀ ነው ። በዚህ መሀል እያለ አስተናጋጇ የቀዘቀዘ ቢራ ይዘው ተመለሱና እየከፈቱ መልካም ምግብ ብለውት ሊመለሱ ሲሉ ፡ ጠራቸው ።

" እየውሎት እኔኮ ያዘዝኩት " .....ብሎ እየተናገረ እያለ ፡ አለመግባባት መኖሩን ያስተዋለው የሬስቶራንቱ ሃላፊ መጣና ቀረብ ብሎ የሆነ ነገር ነገረው ።

ሰውየው ልክ ይህን እንደሰማ መከፋቱን ትቶ እየሳቀ ምግቡን ተመገበ ።
........

በቃ እዚህ ቤት እንዲህ ነው ። የዚህ ቤት ደንበኞች በብዛት ስለቤቱ የሚያውቁና ፡ ዝናውን ሰምተው የሚመጡ ሰወች ናቸው ።
እና ምሳህን ቁርጥ ልትበላ ገብተህ ፡ ዱለት ሊቀርብልህ ይችላል ። የመጣልህን መመገብ ነው ። ብዙ ሰወች ፡ ክትፎ አዘው ፡ ተጋቢኖ መጥቶላቸው ያውቃል ።
እየሳቅህ በልተህ ትወጣለህ ።
......
ይህ ምግብ ቤት የተሳሳቱ ትእዛዞች ምግብ ቤት ( Restaurant of Mistaken Orders ) በመባል ይታወቃል ። የዚህ ምግብ ቤት አስተናጋጆች ፡ Dementia በሚባል ፡ መርሳትን በሚያስከትል በሽታ የተያዙ ሰወች ናቸው ።
የምግብ ቤቱ ባለቤት በዚህ ህመም የተጠቁ ሰወች የሚደርስባቸውን መገለልና ጭንቀት ለማስወገድ ሲል የከፈተው ነበር ።
.....
አላማውም ሰወች እነዚህን ወገኖች ከማግለል ይልቅ ፍቅር እየሰጧቸው የሳቅና የደስታ ምንጭ እንደሆኑ እንዲሰማቸው ለማድረግ ነው ።
.......
እና በዚህ ቤት ስትመገብ እድለኛ ከሆንክ ከስንት አንዴ በትክክል ያዘዝከው ሊመጣልህ ይችላል ። ብዙ ጊዜ ግን ፡ ኬክ አዘህ ፡ ቁርጥ ከቢላ ጋር ወይም እንደሰውየው ጥብስ አዘህ ሳትመገብ የሂሳብ ቢል ይመጣልሀል ።
....
አሁን ላይ ይህ ሬስቶራንት በጃፓን ብዙ ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን ፡ ከሀገሬው ነዋሪ ሌላ ፡ ስለምግብ ቤቱ በሰሙ ቱሪስቶችም ይጎበኛል ።

@wegoch
@wegoch
@paappii

By wasihun tesfaye
' ለመሸወድ ከተዘጋጀህ ሁሉም እንዳቅሙ ሊያታልልህ ይጣጣራል ። '
                                     ( ካሊድ አቅሉ)


ቤት ውስጥ አንዱን ጥግ ይዤ መፅሀፍ አነባለው ፣ ታላቅ እህቴ የሁለት አመት ልጅዋን እላይዋ ላይ አስቀምጣ ትመግባታለች ። ልጅትዋ እሺታን አታሳይም ምግብ ወደ አፍዋ ሲጠጋ ጥርሶችዋን ትገጥማለች ። የእናትዋን የበዛ ቁጥ ስታይ በየመሀሉ ፈገግ እያለች አፍዋን ትከፍታለች አየሀት ካሉ ልትሸውደኝ ስትሞክር አለችኝ  እኔም ስመለከታት ደገመችው አብረን ተሳሳቅን ወድያው አንድ ሀሳብ አይሞሮዬ ላይ ብልጭ አለብኝ እንዲህ የሚል ....

ለመሸወድ ከተዘጋጀህ ሁሉም እንዳቅሙ ሊያታልልህ ይጣጣራል ፤ የራሱን ምቾት ለመጠበቅ ያንተን ፍላጎት በሳቅ ቃሬዛው ከፍኖ አርቆ ይቀብረዋል ። "አልሸወድም" ማለት በራሰ መሸወድ ቢሆንም የቅንነት መንገዳችንን ሊሸራርፉ የሚፍጨረጨሩ የመንገዳችን ተጓዦች መስመጫቸውን እያመቻቹ እንደሆነ ማስገንዘብ ያሻናል ።

by @kalidakelu

@wegoch
@wegoch
@paappii
የሆነ ጊዜ አንድ ፍሬንዴ የሆነ ልጅ ትጠብስና ቤቱ ይወስዳታል:: ቁልፍ ይሰጣታል:: እንደቤትሽ እይው ብሎ::

ከዛ ዶሮ አሮስቶ እንደሚወድ ነግሯት ስለነበር ብትሰራልኝ ብሎ ከሱፐር ማርኬት ያለቀላት ዶሮ አምጥቶ ፍሪጅ ውስጥ አስቀመጠ::

ልጅት ቤቱ በሄደች ቁጥር ዶሮዋን ታያታለች: ፍሪጁን ልታፀዳ ታወጣትና : መልሳ ታስገባታለች::

ከሆነ ጊዜ በኃላ ልብ ስትል ዶሮዋ የለችም:: "ቤብ ዶሮዋስ?" አለችው::

እሱ:- "ውይ ሳልነግርሽ ተነሳች እኮ::"😂

ከዛ ብዙም አልቆዩ ተለያዩ::

@wegoch
@wegoch
@paappii

By Mahi
text ገባልኝ :

"ግሩሜ ቸገረኝ ብር ላክልኝ "

"ስንት ብር ልላክልሽ?"

"አምስት ሺህ ብር
አካውንት ቁጥር 100056.... "

ቴክስቱን ሚስቴ አየቺው።
'ምን ማለት ነው ?! ፣ እ? ፣ ያልጨረሳችሁት ነገር አለ?!፣ በየግዜው ትገናኛላችሁ ማለት ነው ? ...." ብዙ ብላ በመጨረሻ "እንዳትሞክረው!" አለችኝ።

ዝም አልኳት : የመስማማት አይነት ዝምታ ።

እንደ ነጋ ባንክ ሄጄ አርባ ሺ ብር አስገባሁላት !

ሜሪ ላሁኑ ባሏ 'Achievement' ጥንካሬ ሰሊና ድርሻ ምን ያህል እንደነበር ብነግራት በሌላ ቀን ፣ በሌላ መንገድ ጭቅጭቅ ሆኖ ይመጣል ብዬ ነው ልቤ ውስጥ የቀበርኩት ! ።

ሰሊና እንዴት አይነት ደግ ፣ መለመን የማትችል ፣ ለገንዘብ ግድ የሌላት ፍጡር እንደሆነች፣ ይሄን ቴክስት ለመፃፍ ስንት ቀን እንደፈጀባት ፣ የላከችውን አሃዝ ለመፃፍ ስንቴ አሰላስላ እንደፃፈች እኔ ነኝ የማውቀው ።

እኔ አሁን የሆንኩትን እንድሆን የሆነችው መሆን ፣ የምወድቅ ሲመስላት ስንቴ እንደተጨቃጨቀች፣ እኔን ለማበርታት የሄደችው ርቀት፣ ሳገኝ በደስታ ፊቷ ላይ የሚነበበውን እልልታ ፤ማንም አያውቀውም ከኔ በቀር !።

ቸገረኝ ብላ ስትፅፍ እያለቀሰች እንደሆነ አውቃለሁ ፣ ስንት ብር ስላት እየተሳቀቀች እንደሆነ የፃፈችው ... ከስሜ በላይ እርግጠኛ ነኝ ።

የልብ እውነት ይኖራል እንጂ አይብራራም !!

By Adhanom Mitiku

@wegoch
@wegoch
@paappii
[ በመጀመሪያው መንገድ የሚተውሽ ሰው ደስታሽን ይሰርቅሻል ]

የፍቅር ግንኙነት ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው በተመሳሳይ ግለት እና ስሜት አይዘልቅም። የትኛውም ፍቅር የራሱ ኡደት አለው።

የፍቅርን ተአምር ለማየት ጊዜ ያስፈልግሻል። ፍቅር ጥንካሬን ብቻ ሳይሆን ብልሀትን ይፈልጋል። የተሳካ የፍቅር ጉዞ ተለዋዋጭ ነገሮችን ተቀብሎ እራስን እያስተካከሉ መሄድን ይፈልጋል።

ፍቅርን ስንጀምር እጃችን ውስጥ የገባውን ውድ ሀብት እናስተውለውም። ለራሳችን የምንሰጠው ግምት ነገሩን ቀለል አድርገን አይተን ለጨዋታ አይነት በሚመስል መንገድ እንድንጀምር ያደርገናል። እንደቀልድ የፅሁፍ መልዕክቶችን ከመለዋወጥ ወደ ስልክ ማውራት፤ ለደቂቃዎች ከማውራት አብሮ ሲያወሩ ሌሊቱን ወደ ማንጋት ይሸጋገራል። በቃ ሁሉም ነገር ደስታ እና ፈንጠዝያ ብቻ ይሆናል። በአጋጣሚ ትንንሽ አለመግባባቶች ከተፈጠሩ ግብረ መልሶቻችን ከልክ በላይ ይሆናሉ።

ተስፋ እና ፍርሀትን ጎን ለጎን ይዘሽ ለመሄድ ትሞክሪያለሽ። ሁሌም አሁን ያለው ወንድ ከበፊቶቹ የተሻለ እንደሆነ ታስቢያለሽ። ከጥሩ ጥሩው ነገር በዛ ያለውን፤ ከመጥፎ ከመጥፎው ደግሞ አነስ ያለ (አንዳንድ ጊዜ ጭራሽ ድክመት የሌለው) ነገሮችን የያዘ ወንድ እንዳገኘሽ ይሰማሻል። ችግሩ አብሮሽ ያለው ወንድ "የገባው" ካልሆነ ሊጫንሽ ይሞክራል። አንቺ ደግሞ ነፃነትሽ አሳልፈሽ መስጠት አትፈልጊም። ይህ ነገር ሲደጋገም አንቺ ፈላጊ እሱ ተፈላጊ አይነት ስሜትም ሊሰማሽ ይችላል።

ይሄንን ፍቅር ለማስቀጠል ፍርሀትሽን ተቋቁመሽ ሊመጡ የሚችሉትን ያልተገመቱ ነገሮች እየፈታሽ፤ ራስሽን ገዝተሽ ለመኖር ትገደጃለሽ። ይሄ ግንኙነት ወደ ፍቅር ካደገ ለሰዎች ድብቅ የነበሩ ማንነቶችሽን ለዛ ወንድ ቀስ በቀስ መግለጥ እና ማሳየት ይመጣል። እነዚህን ነገሮች አብሮሽ ያለው ወንድ ለማሸነፊያነት ሊጠቀምባቸው ሲሞክር ይሄንን ተከትሎ ጭንቀት፣ ውጥረት እና አለመረጋጋት ሊሰማሽ ይችላል። በስሜትሽ ለራስሽ "ትልቅ" ነኝ ብለሽ ስታስቢ የኖርሽውን ሴት በአንዴ እንደ ህፃን የሆንሽ መስሎ ይታይሻል።

እዚህ ጋር ነው አዲሱ ፍቅር ጉልበትሽን እየጨረሰው፣ ትኩረትሽን እየሰረቀሽ፣ አንድ ሰውን ከማሰብ በስተቀር ሌላ ነገር ለማድረግ አቅም እንዳሳጣሽ፣ ጨቅጫቃ እና ነዝናዛ የሆንሽ የሚመስልሽ፣ በግንኙነቱ ቀጣይነት ላይ ፍራቻ የሚሰማሽ ከሆነ፣ ከእነ አካቴው ረስተሽው የነበረው የቀደመ የፍቅር ህይወትሽን አፈፃፀም እየደጋገምሽ ማሰብ ከጀመርሽ ህልምሽ እንጂ ፍቅርሽ ሩቅ ተጓዥ አይደለም።

ለዚህ ሁኔታ አብቅቶሽ ጥሎሽ የሚሄድ ወንድ ፍቅርን እንድትሸሺ ባያደርግ እንኳን ደስታሽን ይነጥቅሻል !

by Abby

@wegoch
@wegoch
@paappii
ከተለቀቀ ቡኃላ በሁላችንም ዘንድ እጅግ የተወደደው አልበም ሊያልቅ አንድ ዘፈን ቀርቶታል። ሙዚቀኛው "የመጨረሻዋን ዘፈን ነፍሷን አላገኘሁትም" በሚል ጭንቀት ከተወጠረ ወራት ተቆጥረዋል። ድምፃዊው ጥበቃው ደክሞት ዘፈኖቹን ከስቱዲዮ አስዘርፎ ስለሚያወጣበት መንገድ እያሰበ ነው።

"የቀረው ግጥሙ ብቻ ነው አይደል? እሱን ደግሞ በአምስት ደቂቃ መጨረስ እንደምትችል በተደጋጋሚ አይተናል። ችግሩ ምንድን ነው?" አለ እየተማረረ።

(ድካም ተሰማው ሙዚቀኛው) "እውነቱን ልንገርህ? ... እኔ አንተ እንደምታስበው አይነት እውነተኛ አርቲስት አይደለሁም።" አለ በተሸነፈ ድምፅ።
"እንዴ? እና ታዲያ ምን ልትባል ነው?"

"....እኔ አርቲስት ሳልሆን ሙዚቃ በመስራት የሚያገግም በሽተኛ ነኝ።"
"አልገባኝም!"
"ማለቴማ...የሆነ ህመም ሲያንሳፍፈኝ እንጂ እንደ'ናንተ በፈለግኩት ሰዓት ተነስቼ መብረር የምችልበት ክንፍ አልታደልኩም። እኔን አርቲስት ማለት እፉዬ ገላን 'በራሪ ፍጡር ነች' እንደማለት ነው።"

"እስኪ ተው በናትህ!...አንተ አርቲስት ካልተባልክማ እኛ ስቱዲዮ ድርሽ ማለት የለብንም።"
"አያይ...እናንተማ ባሻችሁ ሰዓት ድምፃችሁን ማዘዝ ትችላላችሁ። አዬህ? ክንፉ ተሰጥቷችኋል። ትክክለኛ ስታሮች እናንተ ናችሁ።"
"ትሰማኛለህ?!...እኛ ኮከብ ከተባልን አንተ ፀሀይ ነህ። ምክኒያቱም የምናፀባርቀው ያንተን ብርሀን ነው። ይሔንን መቼም እንዳትረሳ።" (ሁኔታው ስላስፈራው በራስ መተማመኑን ሊመልስለት ታገለ።)

"ፀሀይ?!.." ፂም አልባ ፊቱን እየደባበሰ "...ታውቃለሀ እሷንም እኮ ከርቀት ስለምናያት ነው እንጂ የምታበራ የሚመስለን ጠጋ ብለን ስናያት እየነደደች ነው። The sun is actually burning. ...እንደምትለው 'ፀሀይ' ከሆንኩ እንኳን... ወይ ነድጄ አልቄያለሁ። ወይ ደግሞ የሚለኩሰኝ አጋጣሚ አጥቻለሁ።"

"እንዲህ እንደዋዛ የምትነግረኝን ወሬዎች ቤት እንዲመቱ ብታደርጋቸው እኮ ጨርሰናል ወንድሜ።"
"ግጥሙ በውስጡ አምቆ የሚይዘውን ታሪክ ሳናገኝ? በድኑን ብቻ ልናውጣው? ያለ ነፍሱ? ተው እንጂ!!..ስንቴ ነው የምነግርህ እንደዚህ እንደማይሆን?!"
"ምናለበት አንዳንዴ እንኳን ቀለል ብትል አንተዬስ?! ሁሉንም ነገር ካላመናፈስክ ደስ አይልህም እንዴ?!..." ሊስቅ ብሎ ፊቱ መቀያዬሩን ሲያይ ደንግጦ ዝም አለ።

(ሙዚቀኛው እንዳኮረፈ ስቱዲዮውን ጥሎለት ወጣ።)

ዘፋኞቹ ሁላ ወሬ አስጀምረውት ጠለቅ እያለ ሲሔድባቸው ጨዋታውን ወደ ሹፈት የሚቀይሩበት ነገር ሊለመደው ያልቻለ የጋራ አመላቸው ነው። "..'በልተህ ላትበላ አታስፈትፍተኝ፤ ጠተህ ላትጠጣ ጋን አታስከፍተኝ' የሚለው እኮ ወዶ አይደለም አያ ሙሌ።" እያለ ብቻውን እያነበነበ ወጣ።

ሰዎች እንዳይለዩት አፉን በስካርፍ...አናቱን ደግሞ በኮፍያ ከልሏል።
በአይኖቹ አካሔዱን የሚኮርጀውን ጉብል፤ ፈገግታዋን የሚዋሳትን ሴት ያማትራል።
"በህይወት ካሉ ሰዎች ላይ ብቻ ነው ታሪኬን የምወስደው እንጂ ፈጥሬ አልፅፍም!" የሚል ፍልስፍና አለው። ለዚህም ነው ደራሲ ሲሉት "ደራሲ አትበሉኝ...የአምላክ ጋዜጠኛ ነኝ!" እያለ የሚሟገተው። (ሀይማኖተኛ ነኝ ቢልም ፍልስፍናው ሳይበዛ አይቀርም።)

ጎዳናው ላይ እየኳተነ መሸበት። ቢጨንቀው ከአመታት ቡኃላ ግሮሰሪ ገብቶ ተቀመጠ። ሲገባ በተስፋ መቁረጥ እንጂ "ፍለጋዬ የሚቋጭበት ቀን ይሆናል!" በሚል ጥርጣሬ አልነበረም።

ከተቀመጠበት ጠረጴዛ ላይ ብዙም ሳይቆይ ሁለት ጠብደል ጎረምሶች ሳያስፈቅዱት ተቀመጡ። ውሀውን ጨበጥ እያደረገ በሰቀቀን አያቸው። አንደኛው ሁኔታውን አይቶ..."ከደበረህ መነሳት ትችላለህ!..ይሔ የኛ ቦታ ነው።" አለው።
"ኧረ...ኧረ ችግር የለውም። እንዲያውም ልሔድ ስል ነው የመጣችሁት።" አለና ሒሳቡን ለመክፈል አስተናጋጁን በእጁ ጠራው። ወዲያው ሶስተኛ ሰው ወደነሱ ጠረጴዛ መጥቶ እየተቀላቀላቸው..."አንድ ጮማ ወሬ ብነግራችሁ ድራፍት ትጋብዙኛላችሁ?" አለ።
"እንደ ወሬው ጮማነት ይወሰናል!" አሉት።
"በሱ ምንም ጥርጥር አይግባችሁ።"
"እሺ ቀጥል!"

ሙዚቀኛው ለአስተናጋጁ ሂሳብ መክፈሉን ትቶ ለራሱም ቢራ እያዘዘ ጆሮውን ቀሰረ።

"እሺ..." አለና ወንበር ስቦ ድራፍት ካዘዘ ቡኃላ ግማሽ አድርሶ እስኪያስቀምጠው ድረስ "ቆዩ" እያለ ትግስታቸውን ተፈታተነው። ሙሉ ትኩረታቸውን ማግኘቱን ሲያውቅ...."ትላንትና ማታ ሌላ ሰፈር ሂጄ እየተዝናናሁ ነበር።" ብሎ ወሬውን ጀመረ።..."ከዛ ማንን ባገኝ ጥሩ ነው?"
"ማንን አገኘህ?"
"የቢኒን ሚስት ማሒን!"
"እንዴ? ምን እየሰራች?" (ሌላኛው)
ዘና ብሎ ወደኋላ እየተደገፈ..."ቂጧን አስጥታ እ የ ሸ ረ ሞ ጠ ች ነዋ!"

ባለማመን አዩት።

ስልኩን አውጥቶ ፎቶ እያሳያቸው ሌላ ድራፍት አዘዘ። ሙዚቀኛው ሰረቅ አድርጎ ሊያይ ቢሞክርም አልመቸው አለ። ጠብደሎቹ ፎቶውን በግርምት እያዩ .. "ጭራሽ ተኝተሀታል?...የፈጣሪ ያለህ!"
(ፎቶው ከጠረጴዛ ጠረጴዛ መዟዟር ጀመረ። ግሮሰሪዋ ባንድ እግሯ ቆመች።)

ድንገት አንድ ሰው እየገነፈለ ወደ ውስጥ ከገባ ቡኃላ ወሬኛውን ልጅ ተንደርድሮ በቦክስ ነረተውና ወለሉ ላይ ዘረረው። ሁሉም ፀጥ ብሎ ሲያይ ሙዚቀኛው ሩጦ ገብቶ መገላገል ጀመረ። ሌሎቹም ከድንጋጤያቸው ነቅተው መሀላቸው ገቡ። የወደቀውን ልጅ አፋፍሰው ወደ ጓዳ ወሰዱት። የሚገለገለው ልጅ መንጭቆ ወደ ገላጋዩ ሲዞር...ያዬውን ሰው ማመን አቅቶት...."እንዴ ኤላ? እዚህ ምን ትሰራለህ?" አለ ግራ ተጋብቶ።
ሲያገላግል ስካርፍ እና ኮፍያው መውደቁ ታውቆት ፀጉሩን እያከከ ዝም አለ ሙዚቀኛው።
"የምትተዋወቁ ከሆነ አንተ እሱን ይዘህልን ውጣ ወንድሜ!" አለው አንደኛው ወደ'ሱ እየመጣ። ተያይዘው ወጡ።

ወጣቱ ከግሮሰሪው ከወጡ ቡኃላም በግርምት ማዬቱን አላቆመም። ጠቁሮበታል። ተጎሳቁሎበታል። ግን ሊጠይቀውም አልፈለገም። እንዳይሰማው ብሎ ... "ያው ብዙዎቻችን ከካሜራ ጀርባ ያሉ አርቲስቶችን በመልክ ስለማናውቅ ነው እንጂ ስምህን ብነግራቸው ሁሉም ያውቁህ ነበር!" አለ።
"ይገባኛል።" አለ ሙዚቀኛው እንዴት ወሬውን እንደሚያስጀምረው እያውጠነጠነ።

ትንሽ ዝም ዝም ተባብለው ቆዩ።

ልጁ አሁንም እጁን እያፍተለተለ "ባይዘዌ ሚስቴ ሴተኛ አዳሪ አይደለችም።" አለ።
"ኧረ? አይ ጥሩ...ጥሩ ነው።" አለ በሀፍረት አቀርቅሮ።
"የምሬን ነው!..መንታ እህቷ ነች ያን ስራ የምትሰራው። ውሀ እና ፀበል ናቸው። መልካቸው እንጂ ውስጣቸው አይገናኝም። ወይም ጨረቃ እና ፀሀይ በላቸው። ቅርፃቸው እንጂ ብርሀናቸው አይመሳሰልም።" እጁን በእልህ ጨበጥ ዘርጋ እያደረገ..!
"እና ውሸት ከሆነ ምን ስሜታዊ አደረገህ? ማስረዳት አይቀልም ነበር?"
"ልክ ነህ እሱማ ግን....ባልዋለችበት ስሟ ሲነሳ...ባልሰራችው ወንጀል እየተቀጣች ሳይ በጣም ከፋኝ። ትዕግሥት አጣሁ እውነት!! መጀመሪያ ላቅምሰው አልኩ።" ሳቀ!

ሙዚቀኛው ከረጅም ጊዜ ቡኃላ እፉዬ ገላ ነፍሱ ከያዛት አጥር ተላቅቃ በህይወት ንፋስ ወደላይ ስትንሳፈፍ ተሰማው። እሱም ፈግግ አለ። የዛኑ ምሽት ስቱዲዮ ገብቶ የመጨረሻዋን ዘፈን በግጥም ሞልቷት አደረ። ድምፃዊው ሲያዬው "እንኳን ጠበቅኩህ!" እያለ በደስታ አቀነቀነው። እንዲህ እያለ...

"ግልፅ እውነትሽ መች ጠፋኝ?
ባላዩት እንጂ ባሙሽ የከፋኝ!

"ሌትም ወ'ታለች አሉ
አንቺን በማታ...ጨረቃ እያዩ!..

"ስትመጭ አይን ያያል...መውጣትሽን
ጧት ሲነጋ..ሲመሽ መግባትሽን
የሞቀው ወርቃማ ብርሀንሽን
ጨፍኖስ ማን ያጣል ተፈጥሮሽን? (×2)..
"አውቃለሁ አንቺ አይደለሽም! ... አንቺ ቀን ነሽ በቃ
'እሷው ነች አታርፍም' ቢሉም...ቢያሙሽም በጨረቃ
እያዬው ሳይመሽ በጊዜ ... ቀን ተግተሽ ስትሰሪ
ማታ ግን ተራሽ አይደለም...ምን በወጣሽ ልትበሪ?!..

"ጀንበርዬ ጀንበርዬ ጀንበርዬ ጀንበርዬ
ጀንበርዬ ጀንበርዬ ጀንበርዬ ጀንበርዬ..."



(፨ የግርጌ ማስታወሻ:- ይሕ "እንዲህ ቢሆንስ?" በሚል ስራ ፈትነት የተፃፈ ልብወለድ ብቻ ነው)

@wegoch
@wegoch
@paappii

By mickel Azmeraw
[ የዘገያችሁ ከመሰላችሁ .... ገና ናችሁ]

አንዳንድ ሰው በ24 አመቱ ተመርቆ ስራ ለማግኘት 6 አመት ሊፈጅበት ይችላል

አንዳንዱ በ24 አመቱ የድርጅት ስራ አስኪያጅ ሆኖ በ30 አመቱ ሊሞት ይችላል

ሌላው ስራ አስኪያጅ ለመሆን የ26 አመት ልምድ አስፈልጎት 80 አመቱ ኖሮ ይሆናል

አንዳንዱ በ49 አመቱ ገና ላጤ ሆኖ ህይወቱን ለመቀየር ሲታገል የትምህርት ቤት ጓደኛው የልጅ ልጅ አይቶ አያት ለመሆን በቅቶ ይሆናል

ኦባማ በ55 አመቱ ጡረታ ሲወጣ ትራምፕ በ70 ባይደን በ77 አመታቸው ነው ፕሬዝዳንት የሆኑት

በዚህች ምድር ላይ ሁሉም የራሱ ጊዜ አለው

ሰዎች የቀደሙህ ወይም አንተ የዘገየህ ሊመስልህ ይችላል። አንተ ወደፊት ገስግሰህ ሌላው ወደኋላ የቀረ መስሎ ሊታይህም ይችላል።

እውነታው ግን ሁሉም ሰው በራሱ ጊዜ፣ በራሱ ፍጥነት እየሮጠ ነው።

አንተም በራስህ እነሱም በራሳቸው ጊዜ ከተፃፈላቸው ቦታ አይቀሩም።

ልጅ ለመውለድ፤ ገንዘብ ለመያዝ፤ ትዳር ለመመስረት፤ አገራችሁ ለመግባት፤ ተምሮ ለመመረቅ፤ ለመዝናናት ...... የዘገየህ ለመሰለህ ....

አልዘገየህም፤ ከማንም አትቀድምም፤ በራስህ ጊዜ ላይ ነህ !!

By Abby abby

@wegoch
@wegoch
@paappii
ፉንግግ ያለ ፉንጋ ነበር። የጥርሶቹ ትልቀት፣ የአፍንጫው አቀማመጥ፣ የፀጉሩ ግንባሩ ድረስ አመጣጥ፣ አጉጩን ሳይቀር አለማስተዋል አይቻልም ... ተፈጥሮ እንዴት እንደጨከነችበት ሳየው ይገርመኛል ተቀራረብን... ከፉንጋነቱ ጎን ለጎን ጥሩ ያስባል አዛኝ ልብ አለው።

እይታው ጥሩ ነው ፣ ጭንቅላቱ ላይ ቀድሞ የተንሻፈፈ ነገር አይታየውም ፣ ፉንጋነቱ አይታወቀውም ፣ መልኩ ላይ እየቀለደ ፉንጋነቱን ኖርማል ለማድረግ አይሞክርም፣ የፊቱን አቀማመጥ እረስቶታል ....

ብዙ መደዋወል ያዝን .....ይሰማኛል፣ ይጠይቃል አሰማሙ እና አጠያየቁ እሱ ኑሮ ያለው አይመስልም ፤ ገጠመኝ የሚያገኘው አይመስለኝም።

በመስማት ብቻ ለካ መጉላት ይቻላል !!

ከአልአዛር ጋር ተዋደድን ። አልአዛር ፉንጋነቱ ተረሳኝ ...አይደለም ውበቱ ታየኝ ። አልአዛር ቆንጆ ነው። አንድ ቀን ከፍቶኝ ቤቱ ሄድኩ አልጋው ላይ ተኛን አስተቃቀፉ አለሁልሽ አለው ።

እንደ እህቱ እንደታናሹ አቀፈኝ ። ቀዝቀዝ ያለ ውሃ በማስታጠቢያ አምጥቶ ቀለል አድርጎ፣ ለግልግል እንዳላመች አድርጎ እግሬን አጠበኝ። እንደቀዝቃዛ ውሃ መንፈስ የሚያረጋጋ ነገር የለም እያለ በውሃ ዙርያ ትንታኔ አቀረበ ።

ንግስት የመሆን ስሜት ይሰማኛል ከሱ ጋ ስሆን Safe Zone
ነው ።

አልአዛር ቆንጆ እንደሆነ የማውቀው እኔ ብቻ ነኝ መሰለኝ ። እናቱ ሳይቀር መልኩ ላይ እንደሚቀልዱ በጨዋታ መሃል አንድ ሁለቴ ነግሮኛል ።

መቼ ነው ፎንጋነቱ የተነነብኝ ?
መቼ ነው ከበጣም ቆንጆ ልጅ በላይ የደመቀብኝ??
መቼ ነው የቆነጀብኝ ??

አላውቅም ግን አላዛር ቆንጆ ነው !!

አልአዛር ጋር ሳንገናኝ ወይ ሳንደዋወል አንውልም ። ገጠር ሄጄ ስመለስ ከድፍን ከተማው አልአዛር ብቻ ነው የሚናፍቀኝ ። ከአልአዛር ጋር ብሄድ ምን ምክንያት አለ ተመለሺ ተመለሺ የሚለኝ ??

አልአዛር ጋ አብሬው ተኝቼ ለሊት ላይ የተገለጠ ገላዬን ያለብሰኛል። ለጥቃቅኑ ስሜቴ ቦታ ይሰጣል ።

አብረን እቤቱ ስናድር
በጠዋት ተነስቶ የሆነ ነገር ገዝቶ ስነሳ የምንሰራው ወይ የምንበላው ያመጣል ...ለምዶኝ ችላ አላለኝም።

ምቾት ተሰማኝ ፤ ማንም አይቀማኝም ብዬ መሰለኝ ፣
ጨዋ ነው ብዬ መሰለኝ፣ የሚሰማኝ፣ የሚያግዘኝ ስላገኘሁ ነው መሰለኝ እለት እለት ፍቅሬ ጠነከረ ።

ድንገት የሆነ ቀን "እንለያይ" አለኝ ....ሳኩኝ። በርግጥ አንድ ሁለት ሳምንት ሙሉ ደብዝዞ ነበር ፣ እየራቀኝም ነበር። እኔ ከራሱ ጋር የተጣላ ነበር የመሰለኝ ።

ላለማስጨነቅ ነበር ምን ሆንክ ላለማለት የሞከርኩት

እሱ ፀቡ ከኔ ጋ ነበር መሰለኝ ...

ቀለል አድርጎ ነበር እንለያይ ያለኝ ።እኔ እና እሱ መሃል ጭቅጭቅ፣ መዋደድ ፣ መሳቅ እንጂ የመለያየት ፅንሰ ሃሳብ እንዳለ አላውቅም ነበር ።

"እንለያይ" አለኝ ..... "እየቀለድክ ነው አልአዛር ?"
"እውነቴን ነው ሶሲ "

የሆነ መፍራት ነገር ወረረኝ ። "ባይሆን አሪፍ ጓደኛ እንሆናለን እንደ ድሮ አለ ።"

የማደርገው ስላጣሁ ዝም አልኩ: እምባዬ ግን ፈሰሰ።
" ምን አደረኩ?
፣ ምን አደረገች ብለው ነግረውህ ነው? ፣
ምን ያልኩት ነገር ልብህ ውስጥ ሃዘን ፈጥሮ ነው? "

"ተይ አታወሳስቢው ሶሲ ተይ you are one of the strongest women I know ጓደኝነታችን አይቆምም እኔ ሪሌሽንሺፕ ይሰለቸኛል።"

እንዴ?! እንዴ ?! አላዛር አልመስል አለኝ

ጥሩ ልብ መኖሩ ፣ አዛኝነቱ ፣ አይነግቡ አለመሆኑ
መውደዴ .....የቱም እንዳይተወኝ ዋስትና አልሆነኝም ። ያስደነገጠኝ ፊቱ ላይ ያስነበበኝ የበቅቶኛል ሁኔታው ነው ።

ደነገጥኩ !!

ፈራው.

አዘንኩ መጠን አልባ ሃዘን ልቤ ውስጥ ተንከላወሰ።

መለመን ፈልጌ ነበር ፣ የሆነውን ማወቅ ፈልጌ ነበር ፣ተረጋግቼ ላናግረው ፈልጌ ነበር፣ ሲያቅተኝ ከተቀመጥንበት ጠረጴዛ ላይ አጎንብሼ አለቀስኩ ሰዎች ትኩረታቸው ወደ እኛ ሲሆን መሰለኝ ፦

"ኧረ አንቺ ልጅ This is totally attention-grabbering

አረጋጊው !

ሁኔታው ንግግሩ ከእንለያዩ የበለጠ ጎዳኝ ።ቀጥ ብዬ እያለቀስኩ ከፊቱ ከካፌው ከኑሮው ሄድኩኝ

አልተከተለኝም .....

በነጋታው ይመስለኛል ከእንቅልፌ ስነቃ ተስፋ ሙቁረጥ መላ አካላቴ ላይ ተጥለቅልቋል ። መነሳት አልቻልኩም ሁኔታው፣ አወራሩ፣ አኳኋኑ ፣ ልቤ ላይ መከዳት ተንጋለለብኝ ።
የአልፈልግሽም ውሳኔው ፣ ለሱ የነበረኝ ቦታ ፣ ክህደቱ በደም ዝውውሬ ተሰራጭተው ስነቃ አላላውስ ብሎኝ ነበር ።

ለሦስት ወር ከሃያ ቀን በራችን ጋ ካለው ሱቅ በቀር የትም አልሄድኩም።

ስልኬን ዘጋሁት ፣ ተብሰለሰልኩ፣ ተምሰለሰልኩ ፣
ሙዚቃ አልሰማሁም፣ ፊልም አላየሁም፣ ከወዳጆቼ ጋር አልተገናኘሁም ፣

ስለገንዘብ አላሰብኩም ፣ ሁሉን እርግፍ አድርጌ ተውኩት ። ከአልጋዬ አልተላቀኩም ፣ ከተከረቸምኩበት ስወጣ ከብዙ ግዜ በኃላ መስታወት አየሁ ሽበት ጣል ጣል ብሎብኝ ነበር ፣ ገርጥቼ ነበር፣ ብዙ ግዜ ጨለማ ክፍል ውስጥ የነበርኩ እመስል ነበር ።

የሆነ ቀን፤ ከሆነ ግዜ በኋላ ለፆታዊ ግንኙነት ያለኝ ቦታ ቀዝቅዟል። በወሬ መሃል ሳይታወቀኝ ከልቤ ግድ ነው እንዴ መጥበስ ? ግድ ነው እንዴ ፆታዊ ግንኙነት ፣ማግባት ግድ ነው ? የሰው ልጅን የተባለ ፍጡርን አምኖ ነገን በጋራ አብሮ ማለም መራመድ ይቻላል? ?

ምንስ ፉንጋ ቢሆን
ምንስ አዛኝ ቢሆን
ምንስ አሳቢ ቢሆን
ምንስ ቆንጆ ቢሆን

የሆነ ቀን ቢከዳንስ ዋስትናችን ምንድን ነው ?? እያልኩ ለነገ ዋስትና የሚሰጠኝ ፍለጋ ስሞግት ድምፄን ሰማሁት

ከጉዳቴ ያገገምኩ መስሎኝ ነበር ! ቁስሌ አልደረቀም ማለት ነው ? መዳን ስንት እድሜዬን ይበላ ይሆን ??

By Adhanom Mitiku

@wegoch
@wegoch
@paappii
እማማ እንዴት እንደሞተች...!
...
አባባ የስራ ሰው ነው። ሰፈር ውስጥ ስለሱ ሲያወሩ «ከስራው በቀር ምንም የማያውቅ ጨዋ» ይሉታል። እሱ ደግሞ አንድ ቀን እማማን አይን አይኗን እያየ «ትርንጎየ…እኔኮ ከስራዬ ቀጥሎ እወድሻለሁ» ብሎ ሲያስቃት ሰምቼዋለሁ። እሷ ትሳቅ እንጂ እኔ ግን የምሩን እንደሆነ አውቅ ነበር።
ብዙ ጊዜ ቀን ቀን ሲሰራ ውሎ ማታ በጊዜ ነው የሚመጣው። የሆነ ወቅት ላይ ግን ይህ ልምዱ ተቀየረ። የተቀየረው ባንዴ አይደለም ፤ ሚስቱ ትርንጎዬ እና እኔ ልጁ ሳናውቅበት ቀስ በቀስ ነው።

በመጀመርያ ሰሞን… ትንሽ አምሽቶ ነበር የሚመጣው። ያኔ እማማ እና እኔ እራታችንን ሳንበላ ቴሌቬዥን እያየን እንጠብቀዋለን። እሱ ካልመጣ አንበላም። እኔ በርግጥ ስለሚርበኝ እሱን የምጠብቅበት ትዕግስት አልነበረኝም። ግን እማማ እሱ ካልመጣ አትበላም። አንድ ጊዜ ለምን እንደሆነ ጠይቄያት «የነፍስ ጉዳይ ቢመጣ እንኳ ትቼው አልበላም» ነበር ያለችኝ። እኔ ደግሞ እሷ ካልበላች አልበላም። እጆቿን እንደገዛ መዳፌ ለምጃቸዋለሁ። ለስሙ እሰየማለሁ እንጂ በጉርሻዋ ነው የምጠግበው።

ይህንን አኗኗር ከለመድነው በኋላ ከበፊቱ የበለጠ አምሽቶ መምጣት ጀመረ። የእራት ሰአት አልፎ እንኳ ቶሎ አይደርስም። አሁን እማማ የምትፈተንበት ሰአት ደረሰ። የእኔ ረሀብ እና በትዕግስት የሚያስጠብቃት የአባባ ፍቅር። ግን ለመምረጥ አላመነታችም። ለራሷ አንድ ለእኔ ሁለት እያጎረሰች እራት በላን። የዚያ ሰአት «የነፍስ ጉዳይ ቢመጣ እንኳ ትቼው አልበላም» ያለችውን አስቤ… እናቴ ለካ ቃሏ ከልብ አልነበረም ብዬ… ተገረምኩ። የነፍስ ጉዳይ ቀርቶ የእኔ መራብ ሲመጣ እንኳ ሳታቅማማ አባባን ትከዳዋለች።

ከዚያ አባባ የበለጠ ማምሸት ጀመረ። ማታ ማታ በፍጹም አላየውም። ጠዋት ወይም ቀን ብቻ ነው የማገኘው። ማታ የት እንደሚሆን አላውቅም።

«አባትህ ስራ በዝቶበታል እሺ?» ትለኛለች ። እሷ እንደዛ ስትለኝ እየዋሸች ይሆናል ብዬ አላምናትም።ምክንያቱም ሌሎችን ልትሸውድ ትችላለች እንጂ እኔ ግን አንዳንዴ እንደምትዋሽ አውቃለሁ። አባባን ጠይቄው አዎ ሲለኝ ግን በደንብ አምነዋለሁ። በቃ እሱ የስራ ሰው ነው እላለሁ።

ታድያ የሆነ ሰአት ለመጀመርያ ጊዜ ሲጨቃጨቁ ሰማኋቸው። … በወቅቱ በጣም ልጅ ብሆንም የተነጋገሩትን ግን አሁንም ድረስ አስታውሳለሁ።
«…ሰምቻለሁ! ያዩ ሰዎች ነግረውኛል!…እኔን ከዳሺኝ ትርንጎዬ…እኔን?» ... በጣም እየጮኸና በእልህ እየተንቀጠቀጠ
«…ልጄን ይንሳኝ እልሀለሁ!…ውሸት ነው! የነገሩህ ሁሉ… ውሸት ነው!»
ትንሽ ከተጨቃጨቁ በኋላ ወዲያው ተስማሙ። አባባ ይቅርታ ጠይቋት… እየተሳሳቁ አየኋቸው።

ምስኪን አባት በእኔ ከማለች ያምናታል ማለት ነው። እኔ ግን በጣም ተጠራጠርኩ…ለምን? ምክንያቱም ማታ ማታ የሌላ ሰው ድምፅ መስማት ጀምሬ ነበር። አባባ በጣም አምሽቶ ምናልባትም ሌሊት ነው የሚመጣው። እሱ በሚመጣበት ሰአት ስለምተኛ ሲገባ አላየውም። ግን ምሽት ላይ … የሌላ ሰው ድምፅ እሰማለሁ። የመኝታ ክፍሌ ውስጥ ሁኜ <<ገጭ ጓጓጓ! ገጭ ጓጓጓ!>> የሚል የእግር ኮቴ እሰማለሁ። የአባባ ኮቴ እንደዛ አይደለም። አባባ ሲገባ ደረጃ የሚወጣበት ስልት የለመድኩት ዜማ አለው። <<ገጭ ገጭ ጓ>> የሚል። ይሄ ግን ሌላ ኮቴ ነው። ከኮቴው በኋላ የተኮላተፈ አንደበት ሰላምታ (ት…ል..ን..ጎ..የ.. የሚል)…ከዚያ ደግሞ የመሳሳም ድምፅ ይሰማኛል። ያ የሚመጣው ሰው አንዳንድ ጊዜ ያስለቅሳታል። አላውቅም ለምን እንደሚያስለቅሳት። ከዚያ በኋላ ግን እየሳቀች ስትስመው ድምፁ ይሰማኛል። እና ደግሞ…ሲጥ ሲጥ የሚል የአልጋ ድምጽ!

እስከሆነ ጊዜ ድረስ ሰውየውን በመልክ አላውቀውም ነበር። ሰውየው ከመምጣቱ በፊት እማማ የመኝታ ክፍሌ ውስጥ ስለምትቆልፍብኝ አይቼው አላውቅም። ነገር ግን ኮልታፋ እና የመራመድ ችግር ያለበት ሰው እንደነበር እርግጠኛ ነበርኩ። የሆነ ቀን ይህንን ሰው መንገድ ላይ ፊት ለፊት አገኘሁት። ዘሪሁን ነው ስሙ…ሲናገር ኮልታፋ እና...እግሩ ደግሞ ችግር ያለበት ነው። አንዳንዴ እኛ ቤት ሲመጣ እማማ እንጀራ ትሰጠው ነበር። ፊት ለፊት ስንገጣጠም አገላብጦ ከሳመኝ በኋላ << ያቺ ደግ እናትህ ት..ል…ን..ጎ..የ.. ደና ናት?>> ብሎ ሲጠይቀኝ ከእቅፉ ወጥቼ ሮጥኩ። አባባ እንደዛ አይኮላተፍም። የአባባ ድምፅ እንደሰውየው አይሻክርም። አባባ አያነክስም። አባባ በየመንደሩ እየዞረ እንጀራ አይለምንም። ታድያ ለምንድን ነው የተሻለ ሰው እያላት ከዚህ ሰው ጋር የምትገናኘው? ሁሌም እገረም ነበር። ለአባባ ለመንገር ብዙ ጊዜ ሞክሬ ፈራሁ።

አንድ ቀን ምሽት እራት ካበላችኝ በኋላ ክፍሌ ውስጥ ልትቆልፍብኝ ስትል «እንቢ»አልኳት።
<<ምን ሆንክ?>>

«የሚመጣውን ሰው ማየት እፈልጋለሁ!!» ደነገጠች። ሲሰርቅ እንደተያዘ ሌባ… በረት ውስጥ ገብቶ ባለቤቱ እንደመጣበት ወሮበላ ፣ ማንም አያውቅብኝም ያለው ሚስጥር እንደወጣበት ወራዳ ሰው!…ተንቀጠቀጠች። እኔም ድርቅ ብዬ ቆምኩ። ቁና ቁና እየተነፈሰች ካፈጠጠችብኝ በኋላ ማጅራቴን አንጠልጥላ ወደ ክፍሌ አስገባችኝ። ከዚያ ቆለፈችው።

ከሶስት ቀን በኋላ ት/ቤት ልሄድ ስል አባባን በር ላይ ቁሞ ጢሙን እየከረከመ አገኘሁት። አይኖቹ ደም ለብሰዋል ፤ የስራ ልብሱን እንደለበሰ ነው። አቅፎ ከሳመኝ በኋላ « ምን ሁነህ ነው? » አለኝ። ትኩር ብዬ ተመለከትኩት። ጉዳዩን ከዚያ በላይ ሚስጥር አድርጎ መሸከም ከብዶኛል። መናገር ነበረብኝ።

« አባባ…ማታ ማታ የሚመጣ ሰው አለ »አልኩት… ድንጋጤ ለቅጽበት ድርቅ አደረገው!
«እርግጠኛ ነህ አይተኸዋል?» እየተንቀጠቀጠ
«ፊቱን አላየሁትም…ሰውየው ሊመጣ ሲል…እማማ ትቆልፍብኛለች»አባቴ እጆቹ ተንቀጠቀጡ። በንዴት ጦፈ
«…እሺ የሰማኸውን በሙሉ ንገረኝ..»

ነገርኩት…ስለ እግሩ ኮቴ…ስለ..ኮልታፋነቱ….እንደሚያስለቅሳት…እንደምትስመው….ስለ አልጋው…
ከዚያ በኋላ አባባ ብድግ ብሎ ያደርጋል ያላልኩትን ነገር አደረገ። ጓዳ ገብቶ…መሳቢያውን ከፈተ….ከዚያ ሽጉጡን አወጣ…ከዚያ….
ሁለት ጥይቶችን ተኮሰ…ሞተች!!!!! ዷ! ጠሽ! የሰፈሩ ሰው ግልብጥ ብሎ ወጣ…ጉድ! ጉድ!.ኡኡኡ! ብዙ ድምጾች!!..ቀስ በቀስ የማየው ሁሉ ብዥዥዥ እያለብኝ .መሬት ላይ ወደኩ።

ፖሊስ አባባን ፍለጋ ብዙ ደከመ። እሱ ግን ዱካውን አጥፍቶ ተሰወረ። ከዘመዶቹ ፣ ከጓደኞቹ ቤት…ብዙ ቦታ ተፈለገ! የውሃ ሽታ ሁኖ ቀረ። እኔም ከዚያች ቀን ጀምሮ ከአጎቴ ጋር መኖር ጀመርኩ። መጀመርያ ላይ አጎቴ ከራሱ ቤት ነበር የሚያኖረኝ። ትንሽ ቆይቶ ግን ከወላጆቼ ቤት እንድንኖር ይወተውተኝ ጀመር። በተደጋጋሚ አንቢታየን በለቅሶና በጩኸት ገለጥኩለት። እሱ ግን ከእኔ የስነልቦና ጉዳት ይልቅ የቤቱ ማማር ማርኮት አስገድዶ አመጣኝ።
ህይወት የጊዜ ባቡር አይደለች? ጥቂት አመታት እንደቀልድ አለፉ...
በየ ቀኑ እንቅልፍ እንደራቀኝ…ሌሊት ሌሊት እንደቃዠሁ ነበር። ብዙ ጊዜ የማስበው ደግሞ…ያ….ዘሪሁን የተባለን ሰው መበቀል ነበር። ህይወታችንን ያመሰቃቀለው እሱ ነው !

አንድ ግዜ በተኛሁበት ላብ ሰውነቴን አጥምቆኝ ከቅዠቴ ባተትኩ።
አልጋዬ ላይ እንደሆንኩ የሆነ ድምጽ ሰማሁ። መጀመርያ አይምሮዬ የፈጠረው መስሎኝ ነበር። በኋላ ግን ድምጹ…ጎልቶ መሰማት ጀመረ። አዎ ያን ድምጽ አውቀዋለሁ…የሰውየው ኮቴ ነው
«ገጭ ጓጓጓ! ገጭ ጓጓጓ!»…..ኮቴው ጆሮዬ ላይ አስተጋባ። አጎቴ እንዳንቀላፋ ነው። ደግሞ ምን ቀርቶት መጣ ? እማማ እንደሆነች ሙታለች! ….በተደበላለቀ ስሜት ውስጥ ሁኜ በሩን ከፈትኩ…
በሩን ከፍቼ ያየሁትን ማመን አልቻልኩም። አባባ ነው። እጁ ላይ ትልቅ የቢራ ጠርሙስ አለ…እግሮቹ ይወላገዳሉ…መቆም አልቻለም። እሱ ሲወላገድ ወለሉ«ገጭ ጓጓጓ! ገጭ ጓጓጓ!» የሚል ድምጽ ያሰማል
«ት…ል…ጎ…ዬ» …ስካር ባኮላተፈው ድምጽ

(A masterpiece by ናትናኤል ጌጡ💙)

@wegoch
@wegoch
@paappii

By mickel asmeraw
2024/09/21 14:50:45
Back to Top
HTML Embed Code: