Telegram Web Link
ፖሊማጅ!
(አሌክስ አብርሃም)

ከአመታት በፊት ሽመልስ ሀብቴ አካባቢ እኖር ነበር! አንድ ቀን ቤተሰቦቸን ለመጠየቅ ወደክፍለሐገር ልሄድ ተነሳሁ! በሌሊት የልብስ 'ባጌን' በጀርባየ አዝየ ወደአውቶብስ ተራ የሚሄድ ታክሲ ለመያዝ ጠደፍ ጠደፍ ስል የገነት ሆቴል የግንብ አጥር ስር የተቀመጡ ሁለት ፖሊሶች አጋጠሙኝ፤ አንዱ ክላሽንኮቩን ታፋው ላይ አጋድሟል ፣ሌላኛው ዝነኛውን ጥቁር ዱላ ይዟል! ብርድና የጧት ጨለማ ስለነበር ተጀቡነው መልካቸው እንኳን በወጉ አይታይም! ቦታዋ ጨለም ካለ ተደጋጋሚ ስርቆት የሚፈፀምባት በመሆኗ ፖሊስ በማየቴ ውስጤ ዘና አለ! "ሄይ ወደየት ነው?" አለኝ አንዱ ፖሊስ ...ርምጃየን ገታ አድርጌ "ወደአውቶብስ ተራ" አልኩ!

"ና ጠጋ በል እስቲ ...መታወቂያ ይዘሀል?" ጠጋ ብየ መታወቂያ ለማውጣት ስንደፋደፍ "ያ ምንድነው?" አለኝ በጅንስ ሱሪየ ላይ ቅርፁ ጎልቶ ወደሚታየው ስልኬ በጥቁር ዱላው እየጠቆመ
"ስልክ" አልኩ
"እስቲ አምጣው " ብሎ እጁን ዘረጋ ...ሰጠሁት፤ ሳምሰንግ ጋላክሲ ኖት 6 (በወቅቱ የመጨረሻው የሳምሰንግ ዘመናዊ ስልክ የነበረ ነው)! እያገላበጡ ለሁለት ሲያዩት ቆዩና ...."እና የት እየሄድክ ነው? "
"ወደክፍለ ሀገር "
"የት"
"ደሴ"
"ይሄን ስልክ ይዘህ ደሴ?" ሁለቱም ተሳሳቁ! አሳሳቃቸው አላማረኝም!
"ስትመለስ ጣቢያ መጥተህ ውሰድ " አለኝ ባለዱላው መጀመሪያ ቀልድ ነበር የመሠለኝ... ጥቁር ዱላውን አመቻችቶ "ምን ይገትርሀል ሂዳ ፤ ወይሰ እንሸኝህ?" ሲለኝና ከኋላችን የአንዲት ፒካፕ መኪና መብራት ሲያርፍብን አንድ ሆነ! እዛው ሰፈር የሚያውቀኝ 'ታዋቂ ሰው' ነው ...(እግዜር ልኮት ይሁን እድሌ ጎትቶት እንጃ) መስተዋቱን ዝቅ አድርጎ አንድ ነገር ብቻ አለ "ደህናደራችሁ? ቤተሰብ ነው! " ሞቅ ያለ ሰላምታ ተለዋውጠው .... ስልኬን በ"ስታይል" መለሱልኝና አጭር ምክር መከሩኝ ..."ለወደፊቱ ውድ እቃ ይዘህ ሌሊት ብቻህን አትሂድ ...ማጅራት መችዎች ሊጎዱህ ይችላሉ" አለና ከኋላየ ወደቆመችው መኪና እያዩ ስልኬን ላተረፋት ሰው ምን ቢሉት ጥሩ ነው ? " ምከረው! " 😀 አመስግኘ መንገዴን ቀጠልኩ! ከብዙ ግርምትና እስካሁን ልመልሰው ካልቻልኩት የዕምነት መፈራረስ ጋር!

ፖሊማጅ "ፖሊስ" እና "ማጅራት መች" ከሚሉት ቃላት አዳቅየ የፈጠርኩት አዲስ ቃል ነው! ማጅራት መች ፖሊስ እንደማለት! "ምላጭ ከለገመ በምን ይበጣል...ውሃ ካነቀ በምን ይዋጣል" እንዲሉ! ማጅራት ከሚመታ ፖሊስ ይጠብቀን🙏

@wegoch
@wegoch
@paappii
ከአንዲት የባላገር ጎጆ በዚህ ሰዓት የሚወጣ ድምፅ-

[ ለመተኛት እያኮበኮቡ ነው ፣ ከመደቡ ፈቅ ብላ እግሯን በቆሮቆንዳ እየታጠበች ነው። ዴስ ብሏታል። የአቡዬ ዕለት ነበር...]

' ምነው ከረምሽሳ አመጭም እንዴ? ' አላት በጀርባው ተንጋሎ;

' ጨርሻለሁማ! ልለቃለቅ ብዬ ነው ' አለችው። በኩራዙ ብርሃን ብቅ የምትል ፈገግታ እያሳየችው;

' ትመጪ እንደው ነይ ' ፊቱን ከስክሶ;

ሄደችለት;

የአቡዬ ምሽት ነው። የረጠበ እግሯ በቅጡ አልደረቀም ነበር። ገና ከመደቡ እንደወጣች። ተፈናጠጠባት። የረሀብ አንጀት ያዘለ ህጣን ይመስል ነበር። መንሰፍሰፉ!

ከደቂቃዎች ትንቅንቅ በኋላ-

' አንቺዬ '

' ወዬ '

' ዛሬ ጣፈጥሽኝና እ '

' አመዳም ሌላ ቀንስ ? '

' እሱስ ሁሌ! የዛሬው ባሰ ማለቴ ይ '

' ምን ተገኝቶ ? ' አለችው። ለምን እንደተለየበት አሳምራ ታውቃለች።

' ስሜን ደጋግመሽ ጠራሽ እኮ '

' ኤዲያ ቀጣፊ '

' አቡዬን! ጋሹ ጋሻዬ ጋሻ ምን ያላልሽኝ አለና '

' ሆሆይ ጋሻዬ ጋሹ ' አለችው በስሱ እየሳቀች;

' አንችው መልሶ እንደ መነሳት አለብኝ '

' ኧረ ኤዲያ! ስጠራህ? '

' አቡዬን ስልሽ! የሞተው ተነሳ! '

[ መተሻሸት ጀመሩ እየደጋገመች ጠራችው ' ጋሹ' እያለች ]

@wegoch
@wegoch
@paappii

By Noah z adwa
ተማሪ ሆነን ነውስ:: ጏደኛችንን ሳራን የወደደው የሰፈራችን ልጅ እኩያችን ቢሆን ነው ከትምህርት ቤት ወደቤት ለምሳ ስንሄድ እየተከተለ ያወራናል:: እንድንጀነጅንለት መሆኑ ነው::

ልክ ለቤታችን ትንሽ ደቂቃ ሲቀረን ያለ ዳቦ ቤት ጋር ስንደርስ ዳቦ ልጋብዛችሁ? አለን :: እኔና ጏደኛዬ ተያየን!! እሺ አልኩ ፈጠን ብዬ....::

ለምትሸጠው ልጅ ሳንቲሞች ከኪሱ አውጥቶ ዘረገፈላት እና 2 ዳቦ አቀበለችን:: እቤት ማን እንደገዛልን እንዳንጠየቅ እዛው ዳቦ ቤቱ ጋር ሆነን ደረቅ ዳቦውን ቅርጥፍ አርገን በላን::

ከብዙ ዓመታት በኃላ መች ለታ ዝንጥ ብዬ ከስራ ስመለስ መንገድ ላይ ተገናኘን:: ባላየ አለፍኩት :: ትንሽ እንዳለፍኩ...::

"ዳቦ እያበላሁ አሳድጌ....." ሲል ሰማሁት😂

@wegoch
@wegoch
@paappii

By Ma Hi
ወጣቱ በጣም ኳስ ይወዳል። አንድ ቀን ምግብ ሲያመጣልኝ ጆሮው ላይ ማድመጫ ተክሎ ሬድዮ እያዳመጠ ነበር።

''ምን እየሰማህ ነው'' አልኩት

''ኳስ ጨዋታ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ'' አለኝ።

''አ የዛሬን አያድርገውና እኔም የአርሰናል ደጋፊ ነበርኩ'' አልኩት።

ለካ እሱም አርሰናልን ልቡ እስከሚጠፋ የሚደግፍ ሰው ነው። ከዛ ቀን በኃላ ሁሉም ነገር ቀርቶ ወዳጆች ሆንን። ብቻውን የሆነ እለትና አርሰናል የሚጫወት ከሆነ በሬን ይከፍታል። በር ላይ ይቆምና አንዱን የጆሮ ማዳመጫ አውጥቶ እኔ እንዳዳምጥ ይሰጠኛል።

ሁለታችንም '' ብስራት '' የሚባል የኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ በአማርኛ የሚያስተላልፈውን ግጥሚያ እናዳምጣለን። የጋዜጠኞቹ አቀራረብ በጣም የሚያስደንቅ ነው። የሁለታችንንም ልብ ጉሮሯችን ስር ገብቶ እንዲቀረቀር የሚያደርግ ዘገባ ነው የሚያስተላልፉት። እኔ ና ጠባቂዬም አርሰናል ሲያሸንፍ ተደስተን ሲሸነፍ ተኳርፈን እንለያያለን። አንዳንድ ጊዜ ካልተመቸው ሌሊትም ቢሆን በር ከፍቶ '' አርሰናል በዚህ ውጤት አሸንፏል '' ይለኛል።

ይህን ሲያደርግ አለቃው እንዳይጠረጥረው ድምጹን ከፍ አድርጎ '' አንኳኳህ መሰለኝ '' ይለኛል። እኔም አንዳንድ ቀን ለመተግባበር '' አዎ ሆዴን ጎርብጦኛል ሽንት ቤት መሄድ እፈልጋለሁ'' እላለሁ። ለማስመሰልም ሽንት ቤት እሄዳለሁ። አንዳንድ ቀን ''ውጤት እነግርሃለሁ '' ብሎ ቃል ገብቶ ይጠፋል። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ለምን እንደሚጠፋ ገባኝ። የሚጠፋው አርሰናል ሲሸነፍ ብቻ ነው።

የዚህ ጠባቂ ድርጊት የሚያሳየው የሰው ልጅ የማንነቱ መገለጫዎች ብዙ መሆናቸውን ነው። ለኔ በሰዎች መሃከል ዘርን አቋርጦ የሚሄዱ ተመሳሳይነቶች በዘር ላይ ከተመሰረቱ ተመሳሳይነቶች የሚበዙ መሆናቸውን ስለማውቅ በጠባቂዬ ድርጊት አልተገረምኩም።

- የታፋኙ ማስታወሻ ( አንዳርጋቸው ጽጌ ) ከገጽ 111 - 112 የተወሰደ ——————————————————————

@wegoch
@wegoch
@paappii
"የማይረሱ ግን የማይወሱ ... ተራ ያልሆኑ ተረኞች"
.
1988
ፍቼ ከተማ አንድ እሁድ ረፋድ…ገብርኤል ቤተክርስቲያን መግቢያ የአንገት ልብሴን ተከናንቤ፤ ከእማዬ ኋላ ኋላ እየተከተልኩ፤ የሰንበቴ ቤት ዳቦዬን እየገመጥኩ ፤ ከቅዳሴ መልስ ወደ ቤት ስንሄድ … አንድ ከወገቡ በላይ የተራቆተ ፣ በቁምጣ የቆመ ያልተጎሳቆለ ደመግቡ ጎልማሳ ሰው፤ ድርስ ነፍሰጡር ሚስቱን አጠገቡ አድርጎ ሸሚዙን ፊትለፊቱ አንጥፎ አንገቱን ደፍቶ የሚለምን ፣ እጆቹን አመሳቅሎ የት ነበር ያደረጋቸው? በእግር ኳስ ጨዋታ የቅጣት ምት ሲመታ የተደረደሩት ተከላካዮች የሚያደርጉበት ቦታ። ሲለምን ምን ነበር ያለው? "ከጅማ መጥተን ያረፍንበት ቤርጎ ተዘርፈን ወደ አገራችን ለመመለሻ አጣን እርዱን " እሷ ምንም አትናገርም። አንገቷን ደፍታለች። ብቻ አጠገባቸው ከተኮለኮሉት ነዳያን የበለጠ ብሮች እና ሳንቲሞች ፊታቸው ተበታትኖ ነበር፡፡ ምናቸው እንደገረመኝ አላውቅም መንገዴን ትቼ ለአፍታ ቆሜ አየኋቸው፡፡እማዬ አጠገቧ እንደሌለሁ ያስተዋለችው ከራቀች በኋላ ነበር፡፡ ተመልሳ መጥታ "አንቺ ወሬኛ" እያለች እጄን ጎትታ ልትሄድ ስትል ዞራ ያየሁትን አየች፡፡ ከሙዳየ ምፅዋት የተረፋትን ስሙኒ ከመሀረቧ ፈትታ ለገሰቻቸውና ይዛኝ ሄደች፡፡ እስከዛሬ አልረሳኋቸውም፡፡ እነዛ ባልና ሚስቶች አሁን የት ይሆኑ? ብሩ ሞልቶላቸው በሰላም አገራቸው ገብተው ይሆን? ወይስ የለመኑትም ድጋሚ ተዘርፎባቸው? ከዛ በኋላ ወዴት ሄዱ? የት ደረሱ? በሰላም ወልዳ ይሆን? ወንድ ይሆን ሴት የወለዱት? ልጃቸው ስንት አመት ይሆነው/ይሆናት ይሆን?
.
ሰባተኛ ክፍል ሳለሁ ሰልፍ አበላሸሽ ብሎ በጥፊ የመታኝ ርዕሰ መምህርስ? በእሱ ጥፊ ደንግጬ ሂሳብ ትምህርት የክፍል ስራ 3/10 እንዳገኘሁ ይገምት ይሆን? ጡረታ ወጣ? ከአገር ወጣ? ሞተ ወይስ አለ?
.
1997
በ3 ቁጥር አውቶቡስ ወደ ሜክሲኮ ስሄድ ከኋላዬ በእናትዋ እቅፍ ላይ ሆና ፀጉሬን እየጎተተች በብስጭቴ ስትዝናና የነበረች ሳቂታ ህፃንስ? ልደታጋ ወርደው ወዴት ሄዱ ቤተክርሰቲያን ተሳለሙ? ፍርድቤት ገብተው ችሎት ታደሙ? ልጅቷ አሁን ስንት አመት ይሆናት ይሆን? ትምህርት ቤት ገባች? ስንተኛ ክፍል ደርሳ ይሆን? ወንድም ወይ እህትስ ይኖራት ይሆን?
.
ሃይስኩል ተማሪ እያለሁ ደሞ ጋንዲ ሆስፒታል ሄጄ (እናቴ እዛ ትሰራ ነበርና እሷጋ ... በዛውም 7ኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን ምግብ ቤት ምሳ አትክልት ልጋበዝ ፤ የገብስ ሻይ ልጠጣ)ሆስፒታሉ በር ላይ ሚስቱ በምጥ ተይዛ ሆስፒታል የገባች ባል ፊቱን ወደ አጥሩ አዙሮ በድሮ ኖኪያ ስልክ ምን ነበር ያወራው? "120 ብር ብቻ ጎደለኝ ከነገ ወዲያ እመልስልሃለሁ ፤ እባክህ አበድረኝ፤ መድሃኒት መግዣ ጎድሎኝ ነው" እያለ የሚማፀነው ሰውዬ የት ደርሶ ይሆን? ብሩን አግኝቶ ይሆን? ፊቱን ያላየሁት፣ ፊቴንም ያላየኝ ድምፁን ብቻ የሰማሁት ፣እንባዬን ያመጣብኝ (ያኔ እኔም ተማሪ ከየት አባቴ ላምጣለት)
.
2005
ፒያሳ አቡነ ጴጥሮስ ሐውልትጋ በክረምት፣ በማታ ፣ ጎርፍ በሞላው መንገድ ስደናበር ፤ እጁን ዘርግቶ እጄን ይዞ ያሻገረኝ ረዥም ሰውዬ ስሙ ማን ይሆን? ልጆች አሉት? ታሞ ሳልጠይቀው ቀረሁ? ለቅሶ አልደረስኩትም? ሁሌም ለችግረኞች እጁን የሚዘረጋ ይሆን? ጌታ ይባርከው!
.
2006 በበጋ ወቅት… ወደ ፀሐይ መጥለቂያ ገደማ ፤ ቦሌ ወሎ ሰፈር
አይቤክስ ሆቴል አካባቢ ከስራ ወጥቼ ወደቤቴ ሳዘግም፤ የሚያውቋት አንድ ዘመዳቸውን መስያቸው "ሰናይት" ብለው አገላብጠው የሳሙኝ ጥቁር ጥለት ነጠላ ያዘቀዘቁ እናት፤ አሁን የት ይሆኑ? እኔስ ምናለ" ተመሳስዬብዎት ነው ሰናይት አይደለሁም" ብላቸው? ሰላምታቸው ደስ ብሎኝ፤ እንዳላሳፍራቸው፤ እንዳላስደነግጣቸው፤ ከዛ ሰናይትን የሆነ ቀን ሲያገኟት "ምነው ያኔ አግኝቼሽ" ብለው ሲከራከሩ ምን ትመልስላቸው ይሆን? ማን ሞቶ ይሆን ነጠላ ያዘቀዘቁት? ከኔ በኋላ ተሳስተው የሳሙትስ ሌላ ሰው ይኖር ይሆን? ሰናይት ግን ደህና ናት?
.
የዛሬ አመት አካባቢ የመገናኛ ታክሲ ሰልፍ ላይ ሆኜ "የካሳንቺስ ነው?" ብሎ ሲጠይቀኝ "አይ የመገናኛ ነው" ያልኩት ሰውዬስ? በኋላ ለካ እኔም ተሳስቼ ሰልፉ የካሳንቺስ ሆኖ ሲገኝ ... ስቼ ያሳሳትኩት ሰውዬ የት ደርሶ ይሆን? ታክሲ አገኘ? ካሳንቺስ ለምን ነበር የሚሄደው? አውቄ ያሳሳትኩት መስሎት ተቀይሞኝ ይሆን? ይቅርታ እሺ!
.
ትናንት
.
.
.
በጣም ብዙ መሰል ሁነቶች ...የጭንቅላቴ ውስጠኛው ግድግዳ ላይ ተለጥፈዋል ፤"በሚያስደነግጥ ሁኔታ ነው የምታስታውሺው" ያልከኝ ወዳጄ ይህንን
ስታነብ ምን ትል ይሆን?

By teym tsigereda

@wegoch
@paappii
ከቤሩት እስከ እየሩሳሌም

(በሰዎች ልብ ውስጥ ያለውን ዘልቆ ያነበበ ደራሲ)

የዚህ መፅሐፍ ደራሲ (ቶማስ ፍሬድማን) በመካከለኛው ምሥራቅ በተከናወኑ አሉ የተባሉ ታሪካዊ ክስተቶች ሁሉ ውስጥ ከ10 ዓመት በላይ የኖረ አሜሪካን ጂዊሽ ጋዜጠኛ ነው።

ከጥቂት ዓመታት በፊት ይሄንን "From Beirut to Jerusalem" የተሰኘ እጅግ ድንቅ መፅሐፉን ካገኘሁ በኋላ የዚህ ደራሲ ሥራዎች አሳዳጅ ሆኜ ቀረሁ። ሁሉም መፅሐፎቹ አሉኝ። ፍሬድማንን አንዴ ካነበብከው፣ በትረካዎቹ ተለክፈህ የመቅረት ዕድልህ ከአስር አስር ነው።

"The Lexus and the Olive Tree" የተሰኘውና ፑሊትዘርን ጨምሮ ለበርካታ ዓለማቀፍ ሽልማቶች ያበቃው መፅሐፍ። "The World is Flat" የተሰኘው መፅሐፉ። እና ከእርሱ ቀጥሎ ያሳተመው "Hot, Flat and Crowded" የተሰኘ መፅሐፉ። ሁሉም እጅግ ድንቅ ናቸው።

"ዊት" አለው። ከሁሉ የህይወትና የዕውቀት ተሞክሮ የተቀዳ ምጡቅ ዕውቀት። እና ያንን እያዋዛ፣ እያጫወተ የመናገር ልዩ ተሰጥዖ። ከልጅነቴ ያዳበርኩት ነው ይላል ስለራሱ ሲናገር።

ፍሬድማንን ስታነብ የልብወለድ ድርሰት የምታነብ እንጂ በዕለት ጦርነቶች በሚታመስ ክፍለ ዓለም የተኖረን ዕውነተኛ የህይወት ገጠመኝ የሚፅፍልህ አይመስልም። ፍሬድማንን ሳነብ በዓሉ ግርማ ነው የሚመጣብኝ። ኦሮማይን ይዞ። የቀይ ኮከብ ጥሪን ይዞ። ሀዲስን ይዞ። ይሄ ፍሬድማን ጉድ ነው።
በነገራችን ላይ ያጋጣሚ ጉዳይ ሆኖ ሌላ ከዚህኛው ፍሬድማን በፊት የማውቀው ሌላ ፍሬድማንም አለ። የህግና ኢኮነሚክስ ፕሮፌሰር ነው። ዴቪድ ፍሬድማን ነው እሱ።

ዴቪድ ፍሬድማንም እጅግ "ዊቲ"፣ እጅግ አዋቂ፣ እጅግ ቀልደኛ፣ ህግን የመሠለ ደረቅ ጉዳይ አስገራሚ ለዛና ውበት አላብሶ የሚተርክ፣ ፕሮፌሽናል ተሆኖም ለካ እንዲህ ዘና ብሎ መፃፍ ይቻላል! ብዬ እጅግ እንድደነቅ ያደረገኝን ዓይን-ገላጭ መፅሐፍ የፃፈ ሰው ነው። እና በአጋጣሚ ሆኖ ስመ ሞክሼው ቶማስ ፍሬድማን ደሞ ከእርሱም የባሰ ጉደኛ ደራሲ ሆኖ አገኘሁት።

በግሌ ምርጫ፣ ይሄን ከቤሩት እስከ እየሩሳሌም የሚል መፅሐፉን የሚያህል በውብ አተራረክ፣ በጥልቅ ዕውቀትና በቀጥታ የዓይን እማኝነቶች የተደገፈ ድንቅ ድርሳን በመካከለኛው ምሥራቅ ጉዳዮች ላይ ዳግመኛ መፃፍ ይችላል ወይ? ብዬ እስክደመም ድረስ የመሰጠኝ መፅሐፉ ነው።

ይህ ከቤሩት እስከ እየሩሳሌም የተሰኘው የቶማስ ፍሬድማን መፅሐፍ በእርግጥ በቅርብ ዓመታት ደግሞ "update" አድርጎ ቢያወጣውም፣ ከታተመ ቢያንስ ሶስት አሰርት ዓመታትን ያስቆጠረ መፅሐፍ ነው። ስለሆነም የቅርብ ጊዜ መረጃዎችንና ክስተቶችን አልያዘም። ነገር ግን የእስራኤልና ፍልስጥኤምን (አጠቃላይ የአረቦችና እስራኤልን) ጉዳይ ለማወቅ የሚሻ ሁሉ የግድ ማንበብ ያለበት ድንቅ ድርሳን ነው።

የመፅሐፉ ጥቅጥቅ ያለ ወደ 600 ገፅ የሚጠጋ የገፅ ብዛት ትዕግሥትን የሚፈታተን መስሎ ቢታይም፣ እንደ ኦሮማይ የመሠለ አጓጊ ድርሰትም ይመስላል። ሳይታወቅህ ላፍ ይላል። ከሚያውቅ ጋር ነው መጫወት - እንዲል ያገራችን ሰው። ፍሬድማን ሳያሰለችህ የልብ የልቡን፣ matter የሚያደርገውን፣ ለነገም ለሁልጊዜም ነገሮችን በትክክል ልታይበት በምትችልበት መልኩ፣ መንገርን ያውቅበታል። ተክኖበታል።

ጦርነትና ግጭት፣ ፍንዳታና ሥጋት፣ ጥቃትና ጉዳት... የዕለት ተዕለት ቀለብ በሆኑበት እንደ መካከለኛው ምሥራቅ ባለ የዓለም ክፍል ላይ ስትገኝ፣ ምን ያህል ተማስ ሆብስ የተባለው ፈላስፋ "ሌቪያታን" በሚለው መፅሐፉ የገለፀው "state of nature" የሚባለው የሰው ልጅ የእርስበርስ ጥርጣሬ የነገሰበት፣ አንዱ ከሌላው ጥቃት ተሰነዘረብኝ እያለ በሥጋት የሚያድርበት፣ ህይወት አስመራሪ፣ አረመኔያዊ፣ ሽሚያ፣ አስቀያሚና አጭር የሆነችበትን የሰው ልጅ ህይወት ሲያብራራ - ሆብስ የሚናገረው ቲዎሪ ሳይሆን በትክክል የሆነንና ወደፊትም የሚሆንን ነገር ተመልክቶ ተንብዮ የፃፈ ነው የሚመስልህ - እያለ ይገረማል ባጋጠመው አስመራሪ የህይወት ምስስሎሽ።

አንድ ዕለት በአንድ ምግብ ቤት ምግብ አዝዞ እስኪመጣለት እየጠበቀ በረንዳው ላይ ቁጭ ባለበት አካባቢው ድንገት በተኩስ መናወጥ ይጀምራል። ጩኸቶች ከዘዚህም ከዚያም ይሰማሉ። የፍንዳታ ጭሶች ከሩቅ ይታያሉ። ነዋሪዎቹ ግን ምንም አዲስ ነገር እንዳልተፈጠረ እንደ "normal" ነገር የሚታየውን ግርግር ለምደውታል። አይደናበሩም። አይሯሯጡም።

በመንገዱ እየሄደች ያለች እናት ህፃን ልጇን ይበልጥ ወደራሷ ጥብቅ አድርጋ መንገዷን ትቀጥላለች። ፍሬድማን በዚህ ሲገረም የምግብ ቤቱ አስተናጋጅ መሀመድ መጣ ወደበረንዳው ፈገግታ ባልተለየው ትሁት ፊት ተሞልቶ። ምርጫውን ሊጠይቀው፦ "ቁርሱ ደርሷል ሚስተር... አሁኑኑ ይምጣልህ? ወይስ ተኩሱ ሲበርድ ቢመጣልህ ይሻልሀል?"።

ማመን አቃተኝ ይላል። ግርግሩ ሳይበግራቸው ቁርሳቸውን በትኩስ ሻይ የሚያወራርዱ ደንበኞች ሁሉ አሉ ይላል። ይገረማል። አይይ.. ትንሽ ይቆየኝ። አመሠግናለሁ። ይህን ከማለቴ አንድ ሮኬት መጥቶ አካባቢው ላይ እንደ ነጎድጓዳማ መብረቅ ወርዶ ተከሰከሰ። ሁሉም ወደ ውስጥ ሩጫና ነፍስ አድን ግርግር ሆነ። ከግማሽ ሰዓት በኋላ ሁሉም ፀጥ።

ከዚያ አስተናጋጁ ወደ ፍሬድማን መጣ። ከነፈገግታው። "አሁን ይቅረብልህ አይደል?"። መሀመድ የሚኖረው የዕለቱን ነው። የሰዓቷን ነው። የደቂቃዋን ነው። ስለሌላ ነገር የሚያስብበት ቅንጦቱ የለውም። አስቦም የሚቀይረው ነገር የለም። የነዳጅ ዋጋ 0.50 ሣንቲም ጨመረብን ብለው ለተቃውሞ ሰልፍ የሚወጡት፣ ከስድስት ወራት አስቀድመው የገና በዓል ጌጣጌጥ የሚገዙት፣ ያገሬ ሰዎች ሳልወድ አሳቁኝ። አሳቀቁኝ። ይላል ፍሬድማን።

ስለ ፍልስጥኤም ነፃአውጪ ድርጅትና ስለ እስራኤል መከላከያ ሠራዊት እያነፃፀረ ሲናገር ፍሬድማን፦

"ያሲር አራፋትና ኤሪየል ሻሮን ያው የሚዋደዱ
ሰዎች አይደሉም፣ የገና ስጦታ አይሰጣጡም፣
የሚለዋወጡት ነገር ቢኖር ተኩስ ነው፣ ያሲር
አራፋት ከሻሮን የሚቀበለው የአየር ጥቃትና
የጓዶቹን አስከሬን ነው፣ ሻሮንም ከአራፋት
የሚቀበለው አጥፍቶ ጠፊ ቦምበኞችንና
ተወንጫፊ ሮኬቶችን ነው፣

"በመሐላቸው ምንም ዓይነት ሮማንቲክ
ነገር የሌለን ሰዎች ነው አሜሪካና አውሮፓ
በቴሌቪዥን ካሜራ ፊት እያጨባበጠ
የሚደሰተው፣ ፋንታሲ ነው፣ እውነታው የዳንቴ
አሌገሪን ትራጀዲክ ኮሜዲ የመሠለ ዘግናኝና
አጓጊ ነው፣ አስፈሪና የተለመደ ነው፣ ሞትና
ህይወት፣ ስቃይና ፈገግታ ነው፣ ይሄንን
ተቃርኖአዊ ህይወት በድርሰት ካልሆነ በቀር
በእውን ከዚህ ሥፍራ በቀር የትም አታገኘውም!"

አንድ በሰሜን እስራኤል (በጎላን በዌስትባንክ በሊባኖስ ወዘተ) ዕድሜውን ሙሉ ከፍልስጥኤሞች ጋር ሲዋጋ ያሳለፈ የእስራኤል ሜጀር ጀነራልን አባባል ይጠቅሰዋል ፍሬድማን አንድ ምዕራፉ ላይ፦

"ይኸው አርባ ዓመት አለፈን፣ በግሌ ከጠየቅከኝ ፍልስጥዔሞቹን አልወዳቸውም፣ እነሱም አይወዱኝም፣ ግን በአንድ አልጋ ላይ አርባ ዓመት ሙሉ አብረን አለን፣ በመሐላችን ፍቅር የለም፣ ሴክስ የለም፣ አብሮ የሚያቆየን ሀባ የጋራ ነገር የለም፣ እና በኔ ቦታ ብትሆን ምንድነው የምትፈልገው? ግልፅ ነው፣ ፍቺ (ዲቮርስ) እፈልጋለሁ!"

እነዚህ ለዓመታት ሲታኮሱና ሲጠላሉ እርስበርስ ሲጠራጠሩ የኖሩ ሁለት ህዝቦች፣ ምናልባት የሚያስፈልጋቸው ጥሩ ፍቺ ይሆን ይሆናል። ግን ያንን ጥሩ ፍቺም ማምጣት ነው ያልተቻለው። ተፋተውም አምባጓሮው የሚቀጥልበት ዕድል ከፍ ያለ ነው።

በዚያ ላይ ደሞ - ይላል ፍሬድማን - የፍቺውንም ሆነ የጋብቻውን ስምምነት የማይፈልጉ ብዙ ዓይነት ሰዎች በሁለቱም በኩል አሉ። የእስራኤል ለዘብተኛ መሪዎች ከያሲር አራፋት (ፒኤልኦ) ጋር እርቀሠላም ሊፈራረሙ ጫፍ ሲደርሱ፣ ሞሳድ ይሄድና በዮርዳኖስ ያገኘውን የሀማስ ከፍተኛ አመራር ይገድላል። ሀማስ ደሞ እስራኤል ላይ ሮኬት አዝንቦ ሰላማዊ እስራኤሎችን ይገድላል። ነገሩ ይቀጣጠልና የሰውም የሠላም ስሜት ተቀይሮ ሁሉም ወደግጭት ይገባል። የሠላም ፊርማው በዚያው ይቀራል።

ደሞ ሌላ አደራዳሪ፣ ሌላ አስማሚ ይመጣና፣ እስራኤልና ፍልስጥኤም የመጨረሻውን ሠላም የሚያመጣ ስምምነት ሊፈራረሙ ነው ይባላል። ይሄን ሲሰማ ሀማስ ይመጣና ያለ የሌለ መቅሰፍቱን በእስራኤሎች ላይ ያወርደዋል። አይዲኤፍ ደሞ ጋዛን ይወርና በፍልስጥኤሞች ላይ መቅሰፍቱን ያወርዳል። ስምምነቱ ተዳፍኖ ይቀራል።

ደሞ ሌላ። ደሞ ሌላ። በጣም የሚገርመው ሁለቱ ደሞ ፀጥ ብለው የሚስማሙ ሲመስል ሌሎች አደፍራሾች ደሞ ብቅ ይላሉ። አንዴ ሁለቱ የሠላም ሰነድ ሊፈራረሙ ነበር። ዓለም ሁሉ እያጨበጨበ ነው። በመሐል የያክ አክራሪ እስራኤላዊ ባሩክ ጎልድስታይን እስካፍንጫው ታጥቆ በሄብሮን መስጊድ በሠላም በሚሰግዱ ፍልስጥዔሞች ላይ የጥይት እሩምታውን ያዘንብባቸዋል። ሁሉም ፍልስጥዔም እሳት ጎርሶ ከየቤቱ ጋዝ የተሞላ ጠርሙስ እያነደደ በእስራኤሎች ላይ ያፈነዳል። የሠላሙ ተስፋ ተዳፍኖ ይቀራል።
በዚህ ሥፍራ ሁሌም ሠላም የለም። እርቅም አይፈለግም። አደፍራሽም ፈፅሞ አይጠፋም። እስራኤሎችም፣ ፍልስጥኤሞችም፣ ጆርዳኖችም ሠላምን ይናፍቃሉ። ሌሎችም እነ ኢራንና ሶርያ፣ ሊባኖስና ግብፅ የሠላምን ዓየር በረዥሙ ስበው ማጣጣምን ይመኛሉ። በመሬት ላይ የሆነውና የሚታየው ግን ከዚህ ተቃራኒው ነው።

ፍቺ የሌለበት የጋራ የፀብና የጦርነት ህይወት ብቸኛውና መፍትሄም ያልተገኘለት የአኗኗር መንገድ ሆኗል። እነዚህ ህዝቦች እርስበርስ እየተፋተጉ ከግማሽ ክፍለዘመን በላይ አሳልፈዋል። በማይበርድ ጦርነት ውስጥ ተጥደው ፍዳውን እያወራረዱ ናቸው።

በጣም በቅርበት ተጠግቼ ሁሉንም አይቼያለሁ። በሁሉም ሰው ፊት ላይ መሰላቸትን አነባለሁ። ግን መፍትሄው እንዴት እንደሚመጣ ያወቀ የለም። ማንም አያውቅም። በዚህ ስለምንም ነገር እርግጠኛ በማትሆንበትና የዕለት-የዕለቱን ብቻ እያሰብክ በምታድርበት የምድሪቱ ሥፍራ ላይ ነገና ከነገወዲያ ስለሚሆነው ነገር በእርግጠኝነት መናገር የሚችል የለም።

በአንድ ወቅት ስፅፍ በእኔ ዕድሜ በእስራኤልና ፍልስጥኤም መሐል እርቀሠላምና ስምምነት ነግሦ ከማይ፣ ከምላሴ ፀጉር በቅሎ ባይ ብዬ መመኘትን እመርጣለሁ፣ ባጭር አነጋገር የማይሆን ምድራዊ ቅዠት ነው - ብዬ ነበር።

ፕሬዚደንት ክሊንተን አራፋትንና ራቢንን ባፈራረማቸው ዕለት እኔን በእንግድነት ጋብዞኝ ነበር። እና ፀጉርህ በቀለ ወይ? ይኸው ምንትሆን እንግዲህ ተፈራረሙ - አለኝ። ተሳሳቅን። እና ፈጣሪ እንዲያፀናላቸው እመኛለሁ አልኩት። ያፀናላቸው ግን አልመሠለኝም።

አሁን ላይ እንደ ቀድሞው ፈፅሜ ጭፍን መሆን አልፈልግም። በሰው ልጅ ያልተገደበ አቅም አምናለሁ። ኦፕቲሚዝም አለኝ። ሁለቱ ህዝቦች ዛሬም በእኔ ጊዜ ባይሆን፣ ወደፊት በፍቅር ተቀራርበው፣ ለፍቅርና ለአብሮነት እጅ ሰጥተው፣ ተፋተውም ይሁን ተጋብተው፣ በሠላምና በጉርብትና መኖሩን የሚመርጡበት ቀን እንደሚመጣ እርግጠኛ ሆኜ እናገራለሁ።

መቼ ነው ያ ቀን? - አታስዋሸኝ። የዚህ ጥያቄ መልስ ዛሬ ላይ ማናችንም ጋር እንደሌለ አሳምረን እናውቃለን። ዛሬ ላይ ሆኜ አንድ ነገር በእርግጠኝነት የምነግርህ ነገር ግን አለ። ሁለቱም ሕዝቦች በቅቷቸዋል። ታክቷቸዋል። እና ሁለቱም ወደወደፊቱ የሚያደርሳቸውን የሠላም ትኬት ቆርጠዋል። መቼ ነው ደፍረው የሚሳፈሩበት?

እሱን ለማየት በትዕግሥት መጠበቅ ያለብን ይመስለኛል። በእኔ ዘመን ያን ጉዞ ለማየት ባልታደል፣ ይህን የፃፍኩትን ቃል በጉልምስና ዘመናቸው ቁጭ ብለው የሚያነቡ ልጆቼ በዘመናቸው ለማየት እንዲታደሉ ከልቤ እመኛለሁ።

ቶማስ ፍሬድማን። በመረጃዎች፣ በክስተቶች፣ በዕውቀቶች የተሞላ ርቱዕ ደራሲ ነው። ይህ መፅሐፉ በብዙዎች ሲደነቅ የሚኖር የሰው ልጆች ትራጀዲና ተስፋ አንድላይ ተሰፍተው በማራኪ ብዕር የቀረቡበት ሀቀኛ መፅሐፍ ነው። ያገኘው ቢያነበው ዘና ብሎ እጅግ ብዙ ያተርፍበታል።

ሠላም ለዓለም ይሁን!🙏🙏

@wegoch
@wegoch
@paappii

By Assaf Hailu
........ ይዘባር(ረ)ቃሉ ........

         ‹ከጊዜያት ባንዱ›……. የሚለው አገላለፅን ተጠቅመን የኋሊት እንዳንቃኘው የተምታታ ስፍር ይሆንብናል (‹ጊዜ›)፡፡ ጭል ጭል ከምትል እና ደብዛዛ እሳት ከምትተፋ አምፖላችን በታች፣ ከተጋጋጠ ጠረጴዛችን ፊት ለፊት እግሩ በሚንጥ ወንበራችን ተቀምጠን አምሽተን ይሆናል (በእኛ የጊዜ ሚዛን)፡፡ ፀሃይም እደኛ አይነት ቤት ያመሸች መስሎን ይሁን ሌላ….. እኛም ተከትለን እንወጣለን፡፡ አንድ ምሽት ብለን የሰፈርነው ቆይታችን ለካ በዐለም የጊዜ ሚዛን አስ ደቂቃ ብቻ ነው፡፡ ወደ ድንኳናችን (የምድር አይደለም! ከበረሃ ምናባችን እያፈራረቅን የምንተክለው ነው) ሀሳብ ስንጥል፣ ሀሳብ ስናነሳ አሁንም ‹10 ደቂቃ› የሚል ስም የሰጠነውን የጊዜ ውል ያህል እንቆያለን፡፡ እንደ ቤ/ክ መጋረጃ የገብርኤል ሰይፍ (ጦር?) ያልቀደደው መጋረጃችንን ወደ አንድ እናንሸራትትና ለ1 ደቂቃ ብቻ (ባልነው) በብርሃን ጮራ ስንጫወት እንቆያለን፡፡ ከበራችን አካላችንን ስናሻግር እና ከዐለም ስንቀላቀልስ?....... 10ሩ ደቂቃ ለካ 3 ቀን ነበር! ለየቅል የሆነ ሚዛን………. ከዴሞክራሲ ወዲህ ከብዙኃኑ በተቃራኒ መቆም ትርፉ፣ ትርፍ ማጣት ሆኗል፡፡ አሁንም ግን ፈለግነውም፣ አልፈለግነውም…..... ገባንም፣ አልገባንም…… ከጊዜ ሆነ ከዐለም መታረቅ አልተቻለንም፡፡   ከነዚህ ቀናቶች (በዚህ እንስማማና) ስዋልል፣ በገዛ ምናቤ…… ቀንበር ከጫንቃው ያረፈ ደመና ሰማይ እያረሰ ወደ ምዕራብ ያዘግማል፡፡ ጉልበቱ ሲበዛበት ሌቱን ማሳለፊያ ጎሕ ይቀዳል፡፡ ሲሻው በዚህ ደግሞ ምድር ዳምኖ ሽቅብ ያዘንባል፡፡ ነገሩ እስኪምታታኝ፣ አቅሌን እስኪመታኝ የተፈጥሮ ህግ ሲዛነፍ፣ ልማድ ተሸራርፎ ከማይነሳበት ሲያርፍ አስተውላለሁ፡፡ (ትቢያ ይጫነው ይሆን ይሄም? ማለት ከአጥንቶች ጋር ለምፅዓት ሊሰበሰብ? እንጃ!) ብቻ ጊዜም እንደ ፈትል ውሉ ተዘባርቆ አልፈታ ይለኛል፡፡ በራሱ የመተርኩት አጭር ስለው ተለጥጦ ጥጉ እና ቅጡን ያጣል (ይዝረከረካል!)፡፡ ስንዝር የመሰለኝ በብዙ ተመንዝሮ ዘላለም ያህላል፡፡ አጭር ያልኩትማ……. በዐለም ስፍር ርዝመቱ ከሁሉ ይጋጫል፡፡ በእርግጥ ይሄ ሁሉ ዝብርቅርቅ ውበቱ አጀብ ነው፡፡ ግና ውበት፣ ልክነት አይሆንም፡፡ ውበት አፈንጋጭ እና ልዩ እንጂ ተለምዷዊ አይደለምና…….



By Lewi @Lee_wrld777


@wegoch
@wegoch
@wegoch;
“ማንም ስለ እናንተ ግድ የለውም” | ጥቂት የግል ምልከታ
.

ሼክስፒር «ዓለም የቴአትር መድረክ ናት፣ ተዋናዮቹም እኛው ነን» ያለው “እኛን” ሳያይ መኾኑ ይገርማል። በስመአብ —አደገኛ ቴአትረኞች ነን። የተካንን አስመሳዮች፣ “ቪሊያን” ካራክተሮች ነን። በተለይ እንደ ልብ መተጣጠፍ፣ መለጠጥ፣ መለወጥ፣ መቀየጥ የሚቻልበት የማኀበራዊ ሚዲያ ሜዳ ይኽን አመሳሶነታችንን ጎልቶ ያወጣዋል። ማናችንም ከዚህ ፍርድ አንተርፍም።

ትንሽ ጨከን ብለን መነጋገር ካለብን በተለይ ሰዎች ራሳቸውን ሲያጠፉ ወይም በሌላ ምክንያት ሲሞቱ የምናሳየው ባሕርይ በአጥንታችን ውስጥ ያለውን ዘግናኝነት ያጋልጣል። ያመመን እናስመስላለን እንጂ ያን ያሕልም አያመንም። ሰውን በአፍጢሙ ለመድፋት በምላሱና በግብሩ የተሰለፈ ኹሉ ልክ «እገሌ ሞተ …» ሲባል የተጠና ሙሾ አውራጅ ኾኖ ብቅ ይላል። ትንሽ ወቀሳ ካደረግኹት ይቅርታ!

የኾነ ሰው ሲሞት እየጠበቁ “ጓደኛዬ አልደረስኩልኽም/ሽም …” የሚሉ፣ የተላላኩትን መልዕክት የሚለጥፉ፣ በድንገተኛ ኀዘን የደቀቁ የሚመስሉ ትዕንግርቶች እዚኽም እዚያም ብቅ ብቅ ይላሉ። ይኽ የሚያሳየው ቀሽም ጓደኛ መኾናቸውን መኾኑ ግን አይገለጥላቸውም። “እናውራ…”፣ “በሕይወት እያለን እንዋደድ …”፣ “ሲከፋችኹ አለኹላችኹ አውሩኝ… ” ምናምን ምናምን የሚል የተሰላ ሽሙጥ መሳይ እዝነታቸውን ለአደባባይ ያበቃሉ።

እነዚኽ ሰዎች ኀዘናቸው ለይምሰል መኾኑን ለማወቅ ጎበዝ ታዛቢ መኾን አያስፈልግም። ድርጊታቸውን ብቻ ማየት በቂ ነው። እነዚኹ ሰዎች በነጋታው ኹሉን ነገር ረስተው በሁካታና ቱማታ፣ በሳቅና ቀልድ፣ በብሽሽቅና በስድድብ ውስጥ ተጠምደው ይታያሉ። ከመቼው ከእንባ ወደ ፌዝ እንደተከረበቱ እንጃ!

የግል ሐሳቤ ትርጉም ካለው ይኽንን እላለኹ!

ለሰው አደገኛ ተስፋ አትስጡ! ላትኖሩ “አለኹልኽ” አትበሉ። ላታዳምጡ “ንገረኝ” አትበሉ! መሸከም የማትችሉትን “እንሸከማለን” አትበሉ! የማንንም ሕመም የማስታመም ግዴታም የለባችኹም። ከማስመሰል “ጆሮ ዳባ” ማለት ሰውን ያተርፋል።

ለሰው “ያልፋል!” ብቻ ሳይኾን “ላያልፍ ይችላል፣ ባያልፍም ግን መኖር ትችላለኽ” በሉ። ለደከማቸው እውነቱን ንገሯቸው! አንዳንዴ የሠሚም ጆሮ ይዝላል … አንዳንዴ ማንም ላይሰማኽ ይችላል። በጣም የቅርብ ጓደኛኽ ቀርቶ እናትህ እንኳ ስላንተ ግድ ላይሰጣት ይችላል። ሕይወት ይኽንንም ችሎ መኖር ነው። በቃ እንዲኽም ከባድ ነው።

ኹሉም ነገር በንግግር አይፈታም። አንዳንዱ ችግር አንተ ጋር ብቻ የሚቀር ነው። እናትኽ፣ አባትኽ፣ ወንድምኽ፣ ጓደኛኽ፣ ፍቅረኛኽ የማይራመዱልህ መንገድ ሊኖር ይችላል። ኹሉም በራሱ ዓለም ውስጥ የተጠመደ ነው። ለራሳችኹ ራሳችኹ ብቻ አዳኝ ኾናችኹ የምትቀሩበት ጊዜ አለ። ለብዙዎች ስታትስቲክስና የከርሞ ዜና ብቻ ናችኹ።

የአንድ ሰው ራስ ማጥፋት “የአንድ ሰው ጉዳይ” ሳይሆን ከሥር ያለውን መዋቅራዊ ችግር የሚያሳይ ትንሽዬ ምልክት (tip of the iceberg) ነው። የሰዎች ራስ ማጥፋት ጥላ (shadow) ነው። ጥላውን የጣለው ቅርጽ (shape) ላይ አተኩሩ። ሴተኛ አዳሪነት፣ አስገድዶ መድፈር፣ ተስፋ ማጣት ኹሉ ጥላ ናቸው …ወደ አንድ ትልቅ ምስል ይጠቁማሉ። ኹሌ ነገሩን ዜናና ሰሞነኛ ወሬ ማድረግ ምንም አይፈይድም። በዚህ መንገድ ሊሞቱ ያሉ ተሰልፈዋል። ገና ለብዙዎች ተመሳሳይ እንባ ልናለቅስ ጊዜ እየጠበቅን ነው። ምክንያቱም ብዙ ፈሪዎች ለመሞት የመጨሻዋን ድፍረት በጽዋቸው ውስጥ እያጠራቀሙ ነው።

Dostoevsky በ “The Karamazov Brothers.” መጽሐፉ ላይ አንዲት መሥመር አለች…
“Adelaida Ivanovna muisov's action was similarly no Doubt, an echo of other people's Ideas”

ለቀደመው አረፈድን ካላችኹ ለሚቀጥሉት ድረሱላቸው። ከንግግር በላይ ግን ተግባሩ ላይ አተኩሩ። ሰው በስውር የነገራችኹን በሰው ፊት አትግለጡ። የመጣው ማዕበል ከ“ቴራፒ” ወይም ንግግር ይበልጣል። ብቻውን መኾንን ያልተማረ፣ ለብቻው ዋጥ አድርጎ መቻልን ያልሠለጠነ ሰው እንደ ምዕራባውያን በትንሽ ዱላ የሚሰበር፣ በትንሽ ወሬ የሚፈራርስ ሴንሰቲቭ ልፍስፍስ …ትውልድ ይፈጥራል። ይኽን መዋቅራዊ ችግር እስካልፈታን “አውሩኝ…” እያሉ የሰውን ሕመም ጥም ማርኪያ ማድረግ በቦሃ ላይ ቆረቆር ዓይነት ነገር ነው።

P.s:- ሳቃችሁን ከሰው ጋር አድርጉ ለቅሷችሁ ግን ከጸሎት ቦታችሁ አይለፍ!

———-
Sorry for the incoherence — T.P

@wegoch
@wegoch
@paappii

By Henock Bekele
አባቴ ድሃ ታግሎ ኗሪ ነበር ። ነፍስ እስካውቅ የሆነ ኮት ነበረው ፤ ዘወትር ነበር የሚያደርገው ፤ እሱን ኮት ሳይለብስ ከመንገድ ባገኘው የማልፈው ሁላ ነው የሚመስለኝ ።

ረጋ አባባሉ የሞላለት ያስመስለዋል ።
በትንሽ በትልቁ አይናደድም ፤ በትንሽ በትልቁ አይመክረኝም ። ከሰው ጋ ሲጣላ አጋጥሞኝ አያውቅም ።

ሰላማዊ ሰው ነው ፤ ሁሉንም ሰው በሙሉ ስም ነው የሚጠራው እኔንም ጭምር ። እናቴን ግን ያቆላምጣታል ። እሷ ጋ ሲደርስ የሚሆነው መሆን ለየት ይላል ፤ ይቀልዳል ፣ ያሾፍባታል ግንባሯን ይስማታል ።

አጠገባችን ላሉ እጅግ ከእኛ የበለጠ ደሃ ለነበሩት እማማ አዛሉ እና ከእኛ ቤት ፊት ለፊት ሰፊ ትልቅ ግቢ ላላቸው ለዲታው ጋሽ ይልማ የሚሰጠው ሰላምታም ተመሳሳይ ነው።

አባቴ ችግር ሲያወራ አይቼው አላውቅም ፤ ዝም ብሎ የቻለውን ያደርጋል ፤ ምን አልባት ለእኔ ማውራት አያበድረኝ ፣ አይሞላልኝ ብሎ ይሆናል እንዳልል ስራ ላለው ለታላቅ ወንድሜም እንኳን አያወራም ።

ስራ በያዝኩ በሶስተኛ ወሬ በአንዴ አራት ሙሉ ልብስ ገዛሁለት ። ደስ አለው በጣም ።
እጄን ይዞ
አትጣ
ሞገስ ልበስ
የአንተ የሆነ ሁሉ ይባረክልህ ብሎ መረቀኝ

በአራተኛው ቀን ........ከገዛህልኝ ሁለቱን ሙሉ ልብስ ለወዳጄ እና ለበሪሁን መስጠት ፈልጌ ነበር አለኝ (ወዳጄ እና በሪሁን ወንድሞቹ ናቸው)

ቅር ይልህ ይሆን ብሎ አይን አይኔን አየኝ

አጠያየቁ አስተያየቱ የሆነ የሚያሳዝን ነው ፤ አንጀቴን በላው

ከእነሱ ጋ በጋራ መዘነጥ ፈልጎ ከእነሱ ተለይቶ ላለመድመቅ ነው መሰለኝ

ሌላ ቃል ስላጣው አይ ጋሼ ብዬ እጁን ሳምኩት!!!

By Adhanom Mitiku

@wegoch
@wegoch
@paappii
#መርሳት እና ማበድ
…….መርሳት እውነትም ፀጋ ነው፡፡ ማን ነበር ይህን ያለው? ያለበድነውም ስለምንረሳ ነው ሁላ ብሏል፡፡ እና እኔ አብጃለሁማለት ነው? ይሄን የመሰለ ፀጋ ለፍጥረት የት ነበርኩኝ? በየትኛውም የህይወቴ ክፍል ነገሮችን ከተፈጠረ በኋላ በቀላሉ ረስቼ ማለፍ አይቻለኝም፡፡ ከመለያየት ወዲህ ማንም ቢሆን ትዝታ እያመሰው የሚቆይበት የጊዜ ልክ አለ፡፡ ለኔ ሲሆን ግን ይሄ ተለጥጦ ከዘለዓለም እኩል ረዝሟል፡፡ እንደ ገዛ ስሜ፣ ኑሮዬ፣ ልጅነቴ ያሉ የግል መረጃዎቼ ሳይሰረዙና ጨርሶ ላይሻሩከሚቀመጡበት የአዕምሮዬ ቋት እሷና ያሳለፍነው ሁሉ ተፅፏል፡፡ ስለፈለኩ አልረሳውም፣ ስላልፈለኩ ደሞ አለማስታወስ አልችልም፡፡
ለስንተኛ ግዜ እንደሆነ እንጃ ብቻ ሁሌ እንደማደርገው ለመጨረሻ ግዜ ተገናኝተን ከተለያየንበት ካፌ እየወጣሁ ነው፡፡ ከሳምንት፣ ሳምንት ‹እንለያይ› ብላ አፍ አውጥታ ከጠየቀችኝ ስፍራ ማመን ቢሳነኝ ከእውነት ልሟገት እሄዳለሁ፡፡ ቅዱስ ሚሉት ሀሙስ እረክሶብኝ ጠላሁት፡፡ ምነው እሮብ ብሎ አርብ ቢሆን? ለነገሩ ሊሄድ ለወሰነ ቀን ቢሻር ምን ገዶት? በርግጥ ከጥያቄዋ ወዲህ ተነስቼ የሄድኩት እኔ ነኝ፡፡ በድን አካሌን እየጎተትኩ ለዚያውም፡፡ ቀልቤና ደመ ነፍሴ፣ ሙሉ እኔነቴማ እዚያው ወንበር ላይ ስንት ሳምንታቸው! መሄድ እና መንገድ ስል ይሄ የምንረግጠውን ምድር ሳይሆን የረቀቀውን የልብ ላይ ፍኖት ማለቴ ነውው፡ ወደኔ የሚያመጣትን ስታ መሸሽ ከጀመረች ከርማለች፡፡ አለማየት ደጉ ስንቱን ጋርዶ ገላግሎኝ እንጂ ከዛች እርኩስ ሀሙስ በፊት ስንቴ እከስም ነበር፡፡ ደውዬላት ሺህ ግዜ ስልኳ ከጠራ በኋላ ተይዟል ብሎኛል፡፡ ሺህ ግዜ ሺህ ምክንያት ፈጥሬላት ሺህ ግዜ አልፌዋለሁ፡፡ ካልደወልኩ ቀኑ የማያልቅላት ተገልብጣ ጥሪዬን ሆን ብላ መዝጋት ስትጀምር አንድም አልጠረጠርኩም፡፡ ቀጥሪያት መምጣት ካቆመች ወራት ሄደዋል፡፡ ስትፈልግ ብቻ ከግማሽ ሰዓት ላነሱ ደቂቃዎች ታገኛለች፡፡ እኔ ሞኙ ያቺም ግማሽ ሰዓት ዐለሜ ናት! እሷ ናታ! ምን ብዬ አማርራለሁ?
ከሁሉም የሚገርመኝ የአክስቷ ልጆች፣ ጎረቤቶቿ እና የጎረቤቶቿ ልጆች መብዛታቸው፡፡ ደሞ ሴት ዘመድና ጎረቤት የላትም እንዴ? ወንድ ላይ ተንጠልጥላ ባየኋት ቁጥር አንዳች ስጋዊና ቤተሰባዊ መስር አጠገቧ ካለ ሰው ጋር ተዘረጋለች፡፡ እኔ እንኳን ምክንያ ደርድራ እንዲሁም ከዐይኔ በላይ አምናታለሁ፡፡ አፍቃሪነት ይሄ መሰለኝ፡፡ 6ኛ ምናምን የሚሉት ስሜታችን እውነቱን ከአጋጣሚ እየገለጠልን ተፈቃሪን ላለማጣት እውነተን የመግፋት ነገር……. የሆነ የሆነውን ሽሮ የሌለን መልካምነት ከገዛ ልብ እያደሉ የመልካምነት ኒሻን ለማያፈቅር የመስጠት አይነት፡፡ ልክ እኔ እንዳደረኩት! ይሁዳነቷን ገና ስማ ስላልሸጠችኝ የአለማመኔ ነገር…… ምናልባትኮ እሷ ሳትነግረኝ መንገድ እንደጀመረች ሁሉ እኔም እንዳደርገው እየተበቀች ይሆናል፡፡ እኔ እና እሷ ግን የተለያየን ነን፡፡ እኔ አፍቃሪ፣ እሷ ይሁዲ!
ብቻ ከሁሉም እየገረመኝ ያለው ነገር ንዴቴ ችሎ ለሷ ያለኝን ፍቅር ማክሰም ያለመቻሉ ነገር ነው፡፡ ለዚህም ይመስላል ያወቅኩትን እውነት ተቀብዬ መዋጥ የተሳነኝ፡፡ ከእውነት መታገል ደሞ የማበድ ጠርዝን ይዞ መራመድ ነው፡፡ በዚያ ላይ መርሳት የሚሳነው አቅሉን ከመሳት ብዙ አይርቅም፡፡ በርግጥ አላበድኩም! ባለፍንበት ሳልፍ የነገርኳትን ቀልዶች እንዳለች ሁሉ ደግሜያቸው በሀይል ስቄያለሁ፡፡ ሰፈር የምንቀመጥበት ቦታ ሆኜ ብትኖር የምነግራትን እንዳለች ሁሉ ደአውርቻለሁ፡፡ ከምናዘወትረው ካፌ እየሄድኩኝ ሁለት ኬክ አዝዣለሁ፡፡ ከተለያየንበት ወንበር ሀሙስን እየጠበቅኩኝ በሌለችበት ለምኛታለሁ፡፡ ግን አላበድኩም! ምክንያቱም አውቃታለሁ፡፡ ድሮ ገና ያፈቀርኩት የሆነ እሷነቷ ነበር፡፡ የእውነተኛ ነፍሷ አማናዊ የማንነቷ ተቀፅላ የሆነ እሷነት! ዛሬ ባይመልሳት የምናደርገውን መላልሼ ሳደርግ የሆነ ቀን አለስልሶ ወደኔ ያመጣት ይሆናል፡፡ የሆነ ቀን…… ዛሬ ወይንም ነገ ያልሆነ የሆነ ቀን!

By Lewi @lee_wrld777

@wegoch
@wegoch
@paappii
[…ማኀበራዊ ዝ-ሙ-ት አዳሪነት…]

—መግቢያ—

የአንዳችን ትራጀዲ ለአንዳችን ኮሜዲ ነው። አንተ ትስቅ ዘንድ እኔ ማልቀስ አለብኝ። የዘለለት ስቃይኽና መከራኽ ለአንዳንዶች ስሙ «ፖለቲካ» ነው —ይዝናኑበታል፣ ይተነትኑታል፣ ይነግዱታል፣ ይበሉበታል። መጣላትም ለትርፍ ነው፣ መታረቅም ለትርፍ ነው። እንባም ጥበብ ነው፣ ኀዘንም ሒሳብ ነው።

መንገዱ ይለያይ ይኾናል እንጂ ማኀበራዊ ዝ-ሙ-ት አዳሪነት ውስጥ ነን። አንዳንዱ ገላውን ይሸጣል፣ አንዳንዱ ዕውቀቱን ይሸጣል፣ አንዳንዱ ክፋቱን ይሸጣል። አንዳንዱ በክርስቶስ ስም ይነግዳል፣ አንዳንዱ በሰይጣን ስም ያተርፋል። አንዳንዱ መናፍቃን እያለ ይበለጽጋል፣ አንዳንዱ አሕዛብ እያለ ይከበራል። እምነትና ተስፋ በገበያው ዋጋ ይመነዘራሉ … ፍቅር ግን አልፎበታልና ወደዚያ ይጣላል።

— አንድ ታሪክ እዚኽጋ…—

እናት ልጇ የት ይግባ የት ሳይታወቅ ድንገት በወጣበት ጠፍቶ ይቀራል። ወሬ ስታፈላልግ መንግሥት አሥሮታል ትባላለች። የቀበሌው ሊቀመንበር ጋር አቤት ትላለች። ቀበቶውን እያላላ «ያው መቼም አሠራሩን ታውቂዋለሽ» አላት። ደነገጠች። «መፍትሔው የወረዳው ሊቀመንበር ጋ ነው፣ እርሱ ጋር መቅረብ ከፈለግሽ ለአልጋ ተስማሚኝ» አላት —አማራጭ አልነበራትም። ከነድንጋጤዋ ተስማማች።

የወረዳው ሊቀመንበር ጋ ቀረበች። እርሱም እንደ በፊቱ «የአውራጃው ገዢ ጋ እንዳደርስሽ አብረን እንተኛ» አላት። ድንጋጤዋ አኹንም አለ። ቢኾንም ጥቂት ለምዳዋለች።

የአውራጃው ገዢ ጋ ቀረበች። ተኛችው። እርሱ ወደ ሀገረ-ገዢው ላካት —እዚያም ተኛች። ልጇን ፍለጋ በየቦታው መውደቅን ሥራ አለችው —በቃ ለመደችው። ተዋረዱን እያለች እያለች ንጉሡ ጋር ደረሰች። ንጉሡ ፊት ቀርባ እጅ እንደነሣች ምንም ሳይላት ልብሷን ማውለቅ ጀመረች —እንደቀደሙት መስሏት ። በሀገሩ እንዲህ ያለ ግፍ እንዳለ ያልጠረጠረው ደግ ንጉሥ ተደናግጦ

«ምን ኾነሻል? ልብስሽን ለምን ታወልቂያለሽ?» ሲላት እዚያው ስቅስቅ ብላ ማልቀስ ጀመረች።

«ምነው?»

«ንጉሥ ሆይ ምነው አልወደዱኝም? ልጄን አስፈታ ዘንድ ምኔን ልስጥዎት? እባክዎት»

— መውጪያ —

አስገድዶ መድፈር ግዴታ እጅ መያዝ፣ አንገት ማነቅ፣ በኃይል ጭን መክፈት ብቻ አይደለም። እንዲኽ በአቅም ማጣት የተስማማናቸው፣ ሳንወድ በግድ «እሺ» ብለን ከአልጋ የወደቅንላቸው፣ ከአልጋ የጣልንባቸው፣ የቅድስና ስም የሰጠናቸው ኃጢአቶች አሉን። መቃወም፣ ማፍረስ ፣ demythologize ማድረግ ያለብን እርም አለ —ማኀበራዊ ዝ-ሙ-ት አዳሪነት

By henock Bekele

@wegoch
@wegoch
@paappii
ካሊድ መሻል በነጮቹ በ1997 ነበር የተመረዘው። የካናዳን ፓስፖርት በያዙ ሁለት የሞሳድ ቅጥረኞች። ላኪው ኔትንያሁ ነበር። ቦታው ደግሞ ጆርዳን ኦማን ውስጥ።

ካሊድ መሻል በወቅቱ የሃማስ ፖለቲካ አመራር ነበር።ኑሮውን በስደት ጆርዳን አድርጓል። ከመኪናው ወርዶ ወደ ቢሮው በመሄድ እያለ ነበር በሞሳድ ሰዎች ግራ ጆሮው አካባቢ በኤልክትሪክ ንዝረት የተመረዘው። በረጅም ግዜ ውስጥ እያዳከመ የመተንፈሻ አካልን በመዝጋት የሚግድል መርዝ ነበር።
በወቅቱ ካሊድ መሻልን ሲመርዙት አብሮት የነበረው ጠባቂው ከመኪናው ወርዶ በመከታተል ሁለቱን የሞሳድ ሰዎች ተያያዛቸው። ረጅም ሰዓት ተደባደቡ። መንገደኛ ከበባቸው። በመጨረሻም አንድ ሲቪል PLA አባል አጋጣሚ ደርሶ ፖሊስ ጣቢያ በመውሰድ የሞሳድ ሰዎች ታሰሩ።
:
በምርመራ ሂደትም ነገሩ የጆርዳን መሪ የነበሩት ንጉስ ሁሴንጋ ደረሰ። እሳቸው ቀጠናው ላይ በሳል ፖለቲከኛ ነበሩ። ኔትናያውጋ ደውለው ጉዳዩን አጣሩ።
የሃማሱን ማሻል ላስነካችሁት መርዝ ማርከሻ መድሃኒት ባስቸኳይ የማትልኩ ከሆነ ከእስራኤልጋ የጀመርነው ግንኙነት ወደ ዜሮ ይመለሳል አሉ። በወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ለነበሩት ክሊንተንም ደውለው ነገሩ። ክሊንተን የኔትናሁ ጨዋታ አልተመቸውም። ጎረበጠው።ይልቅ የጆርዳኑን የንጉስ ሁሴን ሃሳብ ደገፈ። ንጉስ ሁሴን ዲፕሎማሲያቸው ሰምሮ እስራኤል ማርከሻውን ተገዳ እንድትልክ ሆነ።
:
ካሊድ ማሻል እየተዳከመ መጥቶ በእለተ ሀሙስ ራሱን ስቶ ነበር።መድሃኒቱ ከተሰጠው በኃላ ቅዳሜ ነቃ። ከኮማ ሲነቃ እንደሌላው ግዜ ሃሙስ ተኝቶ አርብ የነቃ ነበር የመሰለው። ጁምዓ ሰግቼ ልምጣ በሚል ተነስቶም ቅዳሜ እንደሆነ ነግረው ነበር የመለሱት።

By abinet addis

@wegoch
@wegoch
@paappii
[እኔ አለሁ እንዳለሁ
እንዴት ነሽ እመ?]

ከጦርነት ቀጠና ወጥቼ አዲስ አበባ እንደገባሁ የመጀመሪያው ስራየ ስራቦታ ጎራ ማለትና ቤት መፈለግ ነበር። እውነት ለመናገር ከሆነ አዲስ በብዙ ግልምጫዎችና በሰቃዥ የኑሮ ውድነት የታጀበች እጅግ ባይተዋር ከተማ ሆና ነው የጠበቀችኝ።

አዲስ አበባ ቁመት ሙሉ እንባ ስጋ ሙሉ ኧረወይለሊቴ ሆናለች ወገን።

“ጃክሮስ ቆንጆ ቤት አግኝቼልሀለሁ” ደላላው ነበር

ሄድኩ

ቤቷ ሁለት በሶስት ናት። ጭራሽ መሀከሉ ላይ እንደሰፊው ህዝብ መድረሻ ያጣ የሚመስል ኮለን ተገትሯል።

“ኧኸ እንዴት ነው ወደድሻት? 3500 ናት”

ምን ነካህ ደላላ!? ይሄኮ እንኳን አልጋ ሊያዘረጋ ጠረንጴዛና ወንበር ሊይዝ ፍራሽ እንኳን ካላጠፍኩት አያስነጥፈኝም።

😳

የውሻውን ቤት ነው እንዴ ልታከራዮኝ ያሰባችሁት🤔

“ውሻውማ የተሻለ አግኝቶ ስለወጣ ነው እምናከራይህ” አከራዩዋ

እንባየ ደርሶ ግጥም አለ🥴

ደግሞ ሌላ ቤት መስቀል ፍላወር

“ድርድር የለውም። 6 ክፈል” ሸምገል ያሉ ናቸው አከራዮ

ቆንጀት ያለ ቤት ነው እሺ እከፍላለሁ

“ታመሻለህ?”

አዎ አንዳንዴ ሚቲንግ ሲኖረኝ እስከ 4 ምናምን ላመሽ እችላለሁ

“አይሆንም አይሆንም እስከ 2 ልፍቀድልህ”

እንዴ ልጅዎ አደረጉኝ እንዴ!

“ምን አልክ? ይሄንም እኔ ሆኜ ነው”

እንዴ ትራንስፖርቱ ራሱ ያስመሻል እኮ። ቁልፍ ካለ ይስጡኝ ላስቀርጸው።

“ቁልፍ? ለምንድን ነው ቁልፍ እምሰጥህ? አምሽተህ እየገባህ ልታዘርፈኝ!”

😳

“ተወው ለሌላ አከራየዋለሁ። በዚያ በኩል ውጣ”

እንባየ ደርሶ ግጥም አለ🥴

ከሰአቱን ድክም ሲለኝ ልረፍ ምሳም ልብላ ብየ የሆነ ሆቴል ገባሁ

ቅቅል ተፈርሾ አምጪልኝ።

By the way ቅቅል ኢዝ ማይ ተወዳጅ ምግብ

በድንች፣ በካሮት እና በሆኑ ቅጠላቅጠሎች የታጀቡ 3 ግድንግድየ ቅልጥሞች መረቅ ደፍቀው መጡ

ተጠራጠራጠርኩ

ሂሳብ ስንት ነው እናት?

“550”

😳

እንስቷ እንባዋ ደርሶ ግጥም አለ🥴

ከጎጃም በእግርና በባጃጅ ያስወጣኸኝ አንድየ አንተ ታውቃለህ ብየ በላሁት

ሂሳብ ከፍየ ስወጣ ከጀርባየ የሆነ ድምፅ ሰምቼ ዞር ስል አስተጋጇ እጇን እያውለበለበች

“ዌል ካም ቱ አዲስ የዝቅተኛው ማህበረሰብ አባል” ስትለኝ ደረስኩ

እስኪ ሆዴ ቻለው ቻለው ቻለው እያልኩ ወደስራ ቦታየ ወክ አደርግ ጀመር

አለም ሲኒማን እልፍ ስትሉ ባስ መጠበቂያው አለአይደል፣ አንድ በግምት 60 ዎቹ አካባቢ የሆነ ሰውየ እግሩን አጥፎ ወንበሩ ላይ ተቀምጦ አይኑን ጨፍኖ
“ኦም…ኦ….ም…. ኦ….ም” ይላል

ሆዴ ቦጭ ቦጭ አለ
ዝርዝር የአምስት ብር ሳንቲሞች መፀወትኩት

ሰውየው ግን አንድ አይኑን ገልጦ
“ወንድም ዮጋ እየሰራሁ እንጂ እየለመንኩ አይደለም። አዲስ አበባ መቆየት ከቻልክ ይጠቅምሀል ገንዘብህን ያዝ” አለኝ

አደነጋገጤ😳

ህዝቤ እንዳለ ለቆ ነው🤔

ቢሮ ልደርስ አካባቢ የሆነ ሙዚቃ ሰመቼ ዞር ስል የሬሳ ሳጥን የሚሸጥበት ሱቅ ላይ ሁለት ወጣቶች እየቃሙ በትንሽየ ስፒከር

“ጉርምርሜ ና ጉርምርሜ ያሆ መሌ ያሆ መሌ ና ጉርምርምርሜ” የሚል ሙዚቃ ያዳምጣሉ

ጆሮየ ፕራንክ ነው በለኝ😳

እውነት ለመናገር የሬሳ ሳጥን መሸጫ ውስጥ ሙዚቃ ስሰማ ይህ የመጀመሪያየ ነው

“የኔ ልጅ ተውው አሽሙር ነው። መንገድህን ቀጥል” አሉኝ በአጠገቤ ሲያልፉ የነበሩ እናት

ወይ አዲስ አበባ እንዲህ ሁሉን ነገር ድብልቅልቅ አደርጋ ትጠብቀኝ። ታክሲዎች ትንሽ መንገድ አምቦራችተውህ 10 ብር አምጣ ይሉሀል። ከመሸብህ ይሄ ብር ሁለት እጥፍ ሁሉ ሊሆን ይችላል። ራይድ ልያዝ ካልክ happy textile road bruh በሶስት ቀን ሆድህ ፈርደሀል ማለት ነው!

ደግሞ ሰው ምንድን ነው እንዲህ የተፈራራው🤔ለንደን ያለህ ይመስል ማንም ሰላም ሊልህ አይፈልግም። ሰላምታ ብታቀርብም አበጀህ የሚልህ የለም።

ወንድም ሰአት ስንት ነ..?

“እግዜር ይስጥልኝ እኔ ራሱ የታክሲ ብቻ ነው የቀረኝ። እህል ከቀመስኩ ዛሬ ሁለት ወሬን ደፈንኩ”

😳

“ተወኝ በቃ እኔ የትኛውንም ፖለቲካ ፓርቲ አልደግፍም። የሁሉም ባንክ አካውንት አለኝ”

ዋ ኧረ ምንጉድ ነው ብየ ወደ ጎዳናየ ተመለስኩ

ወገን እንግዲህ አዲስ ጥይት አልተተኮሰባትም እንጂ ጦርነት ላይ ናት የሚባለው ነገር እውነት ነው መሰል…

ቢጨንቀኝ
እመ ጋ ደወልኩና
“እመ ለካንስ ይሆን መስሎኝ እንዲያው ሳላውቀው ከሞት ሸሽቼ ወደ ሞት ነው የመጣሁት” አልኳት

እመ ግን ሳግ በሚተናነቀው ድምፅ
ምን አለችኝ?

“ልጅ ታምሩ ምን የሚያጓጓ ህይወት ኖሮህ ነው ሞት የሚያስፈራህ!”

እንባየ ደርሶ ግጥም አለ🥴

@wegoch
@wegoch
@paappii

By Tamiru Temesgen
የምንወደው "The Lion king" የተሰኘው ፊልም ላይ ያለች አባት እና ልጅ ወግ ናት...

ትንሹ ሲምባ እድሜ አንበሳነቱ ውስጥ አውሬነትን ሳይከትበት ጊዜ ጉልበቱ ውስጥ ጭካኔ ሳይቀረቅርበት ከግዙፍ አባቱ ሙፋሳ ጋር እየተራመደ ሲሄድ በተኮላተፈ የደቦል አፍ አባቱን አንድ ጥያቄ ይጠይቀዋል...

"አባዬ ሚዳቋ እና አጋዘን የመሳሰሉትን እንስሳት ለምን እንበላቸዋለን" 🦁

ሲምባ እነዚህን እንስሳት የሚያውቃቸው ለአባቱ ንግስና ሲሰግዱ በመንገድ ሲያዩት ትንሽነቱን ሳይንቁ ለርሱ ሲያሸረግዱ ነውና ስጋቸው ተዘነጣጥሎ ለመበላት ደማቸው ተንቆርቁሮ ለመጠጣት የሚያበቃ በደል ቅን ልቡ ውስጥ አልታየውም

አባቱ ሙፋሳ ሲመልስ ምን አለው

"ልጄ አየህ እኛ መሞታችን አይቀርምና በማንኛውም ሁኔታ እንሞታለን ስንሞት ደግሞ ገላችን ይበሰብሳል ያ የበሰበሰ ገላችን ከቆይታ በኋላ ሳር ሆኖ ይበቅላል ሳር ሆኖ የበቀለን የኛን ገላ ደግሞ እነዚህ እንስሳት ይበሉታል... ስለዚህ እነሱም ስለሚበሉን ነው የምንበላቸው"

ይሄ ተረት ነው ልብ ወለድ ነገር... ግን የአለም እውነታ ከዚህ የሚሸሽ ሆኖ አይሰማኝም... የሰው ልጅ ሰው መሆኑ ውስጥ ለሚያሳድገው አውሬነት የሚሰጠው ምክንያት የዋህ ልቡን ለማጨከን የሚያቀርበው ማስተባበያ ከዚህ አያልፍም።

@wegoch
@wegoch
@paappii

By Biniyam behaylu
Forwarded from ሥዕል ብቻ © (Leul M.)
THE WINDS OF FERENSAI
Art exhibition by Hailemikael Wegayehu.

Opening 10th November 2023.
📍Tikimt, 2nd floor, ambassador mall, 4kilo

@seiloch
ከሰሚት ወደ ሀያት የሚወስደው መንገድ ላይ አንድ ባለ መኪና እና የምግብ ማድረስ/ ብዩ ደሊቨሪ የሚሰራ ባለ ሞተር ሳይክል ቆመው እያወሩ ነው

መንገዱ ተጨናንቆ ቆሜ ስለነበር ድምጻቸው ከፍ ብሎ ይሰማኛል:: እየተጣሉ ስለመሰለኝ ወደ መንገዱ ዳር ወጥቼ ሳጣራ ይህ ነው የሆነው


ባለሞተሩ በከፍተኛ ፍጥነት እጁን ለቅቆ ጭራሹኑም ስልክ እያወራ ሲነዳ ያየው ባለመኪና ከኃላው ተከታትሎ አስቁሞት ነው

ከዚያም ይህንን ታሪክ ይነግረዋል "እኔ እንዳንተ እሳት የላስኩኝ ባለ ሞተር ነበርኩኝ: በፍጥነትም ሆነ በብልጠት ማንም የማይስተካከለኝ:: ታዲያ በአንዱ ክፉ ቀን በከፍተኛ ፍጥነት ስበር ከመኪና ጋር ተጋጭቼ ከጥቅም ውጪ ሆንኩኝ:: ለህክምና ወጪ ያለኝን ሁሉ ሸጥኩኝ: አሁን እግሬ ውስጥ ብረት አለ:: እንደፈለግኩኝ አልንቀሳቀስም"

ባለሞተሩ ፉቱ ላይ ድንጋጤ ይነበባል: አመስግኖት እና "ለልጆቼ ስል ከዚህ በኃላ ተጠንቅቄ ነው የምነዳው" ብሎ ቃል ገብቶለት ሄደ

ሰውዬውን "ይህንን ሁሉ ህመም እንዴት ቻልከው?" አልኩት

"አደጋው እኔ ላይ አልደረሰም:: ነገር ግን ፍጥነቱን አይቼ ለህይወቱ ስላሰጋኝ ነው እንደዚያ ብዬ የመከርኩት: አንዳንዴ ሰዎች ከሌሎች መከራ ይማራሉ " አለኝ


አንዳንድ ሰው ብልህ ነው: ፈውስ ነው ❤️🙌🏼

@wegoch
@wegoch
@paappii

By Andi lemenged
ድሮ አምስተኛ ክፍል ሳለን እርስ በርሳቸው የሚፎካከሩ ሁለት ዲያቆናት ነበሩ። ከአብነት ትምህርት የጀመረ ፉክክራቸው ወደ ዘመናዊ ትምህርቱም አምጥተውት ነበር። በተለይ የሽምደዳ ትምህርቶችን የሚችላቸው አልነበረም። ልጅ እያሱ የት ተወልዶ.. .የት እንደሞተ ከነቦታው ከነ ዓመተ ምህረቱ ዱቅ ያደርጉታል። (በነገራችን ላይ አንድ ቀን ልጅ እያሱ ሀይቅ ዳር ተቀምጠው ሲፍታቱ መኮንኖች ከሩቅ ሾፏቸው ። ያን ጊዜ ልጅ እያሱ በርጫ እያደቀቁ ብን ብለው በምርቃና ፏ ብለው ነበር። ከዛ በኋላ ቤተ መንግስት አካባቢ ልጅ እያሱ የእስላም ቅጠል ያላምጣሉ ተብሎ እንደተወራባቸው ታሪክ ይናገራል 😂 ልጅ እያሱ አንቱ ለመባል የማያበቃ ልጅነት ነበራቸው። ሀገራችን በዘመኗ ካጋጠሟት የህፃን ባህሪ ካላቸው ንጉሶች ቀዳሚውን ቦታ ይወስዳሉ። በተለይ ጢዝ ያላት እንስት ካዩ ቅቤ እንደላሰ እባብ ይቅበዘበዛሉ ይባላል ። ብዙው የንግስና ዘመናቸው ላይ ሲወሸክቱ ራስ ተፈሪ በርቀት ይጠባበቋቸው ነበር። ራስ ተፈሪ ቤተስኪያን ተመሳም አንስቶ በቤተ መንግስት ዘንድ እጅግ የተወደደ ምግባር ነበራቸው። በንግስና ዘመናቸውም ትንሽ እንኳ ሳት ብሏቸው ከማጀት ሴቶች አንዷን ቢመቻቹ ለፀፀት ቅርብ ናቸው። ከአልጋ ወርደው ደበሎ አንጥፈው ጌታ ሆይ አፉ በለኝ ይላሉ በፍጥነት። ልጅ እያሱ ግን አንዷን ቆንጆ እየቀመሱ የሌላዋ እንስት ገላ ያሻፍዳቸው ነበር )

ወደ ዲያቆናቱ ልመለስ.. .

እንዳለ ተብየው አንዲት ሸጋ ወዶ ጠየቀ። መጀመሪያ ይሄ የማርተሬዛ ሽልንግ የሚደብቅ ተረከዝህን አለስልስ ብላ ኩም አደረገችው ቆንጆዋ!

እንዳለ ከዚህ የሞራል ስብራት በኋላ ሰይጣን በጆሮው አንድ በቀል ሹክ አለው።

ጱጵ የሚል ድምፅ ከጎናችን ሰማን ። ደግሞ ለክፋቱ እኔ ከቆንጆዋ ልጅ ጎን ነው የተቀመጥኩት። ቆንጆ ይፈሳል ተብሎ ስለማይገመት ተሜው ሁላ አይኑን አጉረጠረጠብኝ። አፍንጫዬን በሹራቤ ስሸፍን ደግሞ ከሱ ብሶ ፈስ እንደሸተተው ሰው አፍንጫውን በጨርቅ ይሸፍናል እንዴ? ተባልኩ...ከ አምስት ደቂቃ ለጥቆ ቆንጆዋ ልጅ ሌላ ጋዝ ለቀቀች። ከመቅፅበት ደንግጣ ክፍሉን ለቃ ሮጠች። ዞር ስል ደብተራው እንዳለ ሆዱን እስኪቆርጠው ድረስ ይስቃል።

የፈስ ድግምት ለቆባት መሆኑ ያኔ ገባኝ 🙂

በዚህ እውቀቱ የቀናው ደብተራው ሸዋ ሌላ ጉድ ይዞ ከተፍ አለ ።

የበቀል በትሩ አንዲት ምስኪን መምህራችን ላይ አረፈ ። ቲቸር አስካል መክራን ዘክራን አልሰማ ስላልናት ብዙ ጊዜ በአርጩሜ መከራችንን ታበላናለች። ተማሪው ግርፊያዋን ስለሚጠላ እሷንም አብሮ አይወዳትም ነበር። በተለይ ሸዋ ... የክፍል መልመጃ 3/10 ስላመጣ ክፉኛ ጥርስ ነክሶባት ነበር ። የታሪክ ትምህርትን እንደ ውሀ የሚጠጣው ጎበዝ ተማሪ የሂሳብ ትምህርት ግን አናቱን እንደ ሀበሻ አረቄ ይነካዋል።

በተለይ ማካፈል የሚባል ስሌት በቀን ሶስት ጊዜ አስረድተውት በቀን አስራ ሶስት ጊዜ ይስታል 😑

አሁን በምን ተዓምር ነው 19 /12.... 21 የሚመጣው ። መምህራችን በአዕምሮህ ነው ወይስ በእግርህ አውራ ጣት አስበህ ነው ይሄንን ውጤት ያመጣኸው ብላ ስትጣይቀው.. ." በ 16 ኪዳነምህረት ነች ። በ12 ሚካኤል ነው። እመቤቴንስ እንዴት ረሳታለሁ?" አለ አሉ 😑
በዚህ ጥርስ የነከሰው ሸዋ ዛዲያ አንድ ከሰዓት ላይ አደናግር ድግምቱን አነብንቦ ክፍል ውስጥ እንትፍ እንትፍ አለ።

ቲቸር አስካልዬ እጇ ቄጠማ ሆነባት። እግሯ እንደ ህልም ሩጫ አልታዘዝ አላት። ጠመኔው ተሰሌዳው እንዴት ታዋህደው?

አይነ አፋር ነች አይነ አፋርነቷ ጎልቶ አንገቷን ደፋች ።

ደግሞ ለዛን ቀን ያለወትሮዋ እንኳን ሂሳብ ዓ ነገር መፃፍ አትችሉም ብላ አማርኛም እያስተማረችን ነበር።

አማርኛ ብላ ለመፃፍ አገርኛ ብላ ስትፅፍ ሳቅንባት ። የግንባሯ ላቦት ተንዠቀዠቀ ። መልሳ መልመጃ ን ለመፃፍ መግለጫ ብላው አረፈች። ከተማሪው ሁሉ የሸዋ ሳቅ ጎልቶ ተሰማ ።

መጨረሻ ላይ የሰራችው ስህተት ሲታከል ደግሞ ክፍሉ በሙሉ እንደ አደዋ ማስጀመርያ መድፍ አጓራ!

አንብቡ አለችን ዓ ነገር ጥፋ.. .

ምድረ ውሪ ተሰሌዳው የጣፈችውን ጥሁፍ እኩል አነበበው።

"አበበ በሶ በዳ !"😆

ድንጋጤ ጨው አደረጋት ። የፃፈችውን ዞራ አነበችው ።

ቂ....ቂ...ቂ ...ቂ...ቋቂ

ሸዋንም ሳቁንም እኩል ጠላኋቸው 🙂

ሚካኤል .አ

@wegoch
@wegoch
@paappii
ይሔ ዘፈን ስለምንድን ነው? ስለ አባቱ? ስለ ሙዚቃ? ስለ ህይወት? ስለ አምላክ? ስለውበት? መተው ስለማይችሉት ፍቅር? ስለ ፀፀት? ስለ ኑዛዜ? ስለ ዕጣ ፋንታ? ስለ ምርጫ? ከራስ ጋ እርቅ ስለማውረድ?

ስለሁሉም ነው በ'ርግጥ።

ግን እንዴት ነው በአንድ ርዕስ ውስጥ ሁሉንም ስሜት ማንሳት የቻለው? ይሔ'ኮ ነፍ ሙዚቃ ነው። ይሔ'ኮ የመጥፎ ስራ ባህሪ ነው። እንዴት አስማምቶ እና አዋድዶ ሊሰራቸው ቻለ? እንዴት ነው ያልተበላሸበት?

ሲገባኝ (የገባኝ ሲመስለኝ) መልሱ የጥያቄውን ያህል ውስብስብ አይደለም።

ይሔ ዘፈን... ስለአባቱ፣ ስለሙዚቃ... አልያም ደግሞ ስለ አምላክ የተዘፈነ አይደለም። ይሔ... ቴዲ የሚባለው ሰውዬ እነዚህ ነገሮች ጋር ስላለው ግኑኝነት የተሰራ ስራ ነው።

ስለ'ሱ ማወቅ የምትፈልጓቸው ነገሮች ሁሉ እዚህ ውስጥ አሉ።

የሚፈራውን፣ የሚያፈቅረውን፣ የሚፀፅተውን፣ ራሱን ለማግኘት የሔደበትን ርቀት፤ ታግሎ የጣለውን ፈተና፤ ዛሬ ላይ የሚኖርለትን ፍልስፍና ጭምር ታገኟቸዋላችሁ። እጥር ምጥን ባለ መንገድ። ሳይጎረብጣችሁ። ሳያስጨንቃችሁ። የራሳችሁ ታሪክ እየመሰላችሁ።

ብዙ ሰዎች ትረካ ከተራኪው ጋ ሲያያዝ....ጉዳዩን ማሳነስ ወይም ማጥበብ መስሎ ይሰማቸዋል። ግን አይደለም። ይሔ ማጥበብ ሳይሆን ማጉላት ነው።

ለምሳሌ...ኤላ በመሰሉ ድምፅ "ወይ ምጣ ወይ ልምጣ" ሲል እንዴት ነው የሚጨንቅህ?
...ልጅ ሚካኤል ታቱውን እያሳዬ.."አትገባም አሉኝ" ሲልህ... "ኧረ በናታችሁ አስገቡት!" ብለህ ልትለማመጥለት አያምርህም? እንድታስብስ አያደርግህም? የወንዶች ጉዳይ ላይ እንዳለው ሰርግ ቤት "የእህቴ ልጅ ነው" ብለህ ይዘኸው መግባት አትመኝም?🙂
...ጂጂ "ናፈቀኝ" ብላ የጎረቤቶቿን ስም እየጠራች ስታለቃቅስብህ...ከሀገርህ ሳትወጣ ሀገርህ አይናፍቅህም?

ብቻ...ወዳጆቻችን እንደሚሉት..."The most personal is the most creative" ...
..."ሙዚቃ ህይወቴ" ደግሞ የቴዲ ፐርሰናል ስራው ነው። ምርጥ ስራው ነው። የቴዲ ምርጥ ስራው ነው ብቻ ሳይሆን ከምንጊዜም ምርጥ ስራዎች ውስጥ አንዱ ነው።

አውቃለሁ'ኮ ስለቴዲ ብዙ ተብሏል። አሰልቺ ርዕስ ነው ሁላ። ግን ስለፖለቲከኝነቱ እንጂ ስለጥበበኝነቱ የሚገባውን ያህል አልተባለም። እኔ እንዲያውም ምንም አልተባለም ባይ ነኝ። በፖለቲካው በጣም ከመወደሱ የተነሳ አንዳንድ ምዕመናን ቴዲ ቴዲ የሆነው በፖለቲካ ተሳትፎው እንጂ.....ያን ያህል ጥበበኛ ስለሆነ እንዳልሆነ ለማስረዳት ሲጣጣሩ ታገኟቸዋላችሁ።

I am truly speechless እንደዚህ ለምታስቡ ሰዎች🙂

አንዱ እንዲህ ሲል ደርሼ አውቃለሁ እኔም። ያው በዝምታ ላልፈው ነው የሞከርኩት። ግን አስታወቀብኝ መሰል ልጁ ትንሽ ቆይቶ "ምነው ፊትህ ተቀያዬረ?...አይነኬውን ነክቼ አሳዘንኩህ እንዴ?" አለ የሹፈት ሳቅ እየሳቀ...
"ኧረ በጭራሽ ወንድሜ!..ለሟች ማዘን የለም ባለው መፅናናት ነው!" ብዬ በህይወት ወደቀሩት ወዳጆቼ ዞርኩ😑

@wegoch
@wegoch
@paappii

By mickel azmeraw
2024/09/21 16:56:32
Back to Top
HTML Embed Code: