Telegram Web Link
«እትዬ አምላክ እንደአዲስ በንፁህ ልብ የመኖር እድል ሲሰጥዎ እርሱ አዋቂ አይደል? እንደው ያለፈውን ከመበርበር እንደአዲስ......... »

«ንገረኝ ምንድነው? ንገረኝ አልኩህኮ!» ብዬ ጮህኩ

«ባለቤትዎ እንደነበሩ ሲወራ ሰምቻለሁ።» ብሎ ዝም አለ
«ይሄን ሁሉ የታሸኸው ይሄን ልትነግረኝ አይደለም! ከዛስ? ምን ሆነ?»

«ሞተው ነው (እንደበረዶ የቀዘቀዙ ቃላት ) እንደሚባለው ከሆነ እርሶ በሞታቸው እጅዎ አለበት ተብሎ ታስረው ነበር።»

«ለንብረት ብለው የገደሏቸው ነው የሚባለውማ ከወሬው» አለች ተናኜ ለማውራት ሰበብ ትፈልግ ይመስል። ጎንጤ ሲያፈጥባት «እህእ ንገሩኝ ብለው አይደል?» ብላ አፈጠጠች። ያቺን ሜላት እኔ ራሴ ጠላኋት። እኔ ራሴ ባገኛት አልገላትም ነበር?

«እትዬ እውነታውን የሚያውቀውኮ አንድ ፈጣሪ ብቻ ነው።» አለኝ ሊያፅናናኝ ይሁን ከልቡ አልገባኝም። ፖሊሶቹ እየደጋገሙ ሊገድለኝ የሚችል የምጠረጥረው ጠላት እንዳለኝ የማስታውስ ከሆነ ብለው ሲያደርቁኝ ይሄን ክፍል ለእኔ መንገር አልታያቸውም? የአደጋው መንስኤ ከዚህኛው ጋር የተያያዘ ነገር ይኖረው እንደው ማሰብ ተስኗቸው ነው? ወይስ አያውቁም? ወይስ እውነትም ወሬ ነው? ምኑ ነው ልክ ? ምኑ ነው ቅዠት?

እንደእብድ መዥረጥ ብዬ ተነስቼ ፖሊሶቹ የማስታውሰው ፍንጭ ካገኘሁ እንድመጣ የነገሩኝ ቢሮ ጎንጤን አስከትዬ ሄድኩ። ገና ኮሪደሩን አልፌ እየሄድኩ እኔ የማላውቀው እሱ ግን በትክክል እንደሚያውቀኝ የሚያስታውቅ ፖሊስ

«እሺ አጅሪት?» አለኝ። አጅሪት አባባሉ ስልችት ያለበት፣ ትዝብት ያለበት ፣ ፍርድ ያለበት አይነት ነው።

                         ................  ይቀጥላል .............

@wegoch
@wegoch
@paappii
#የመኖር አጋማሽ ..የመሞት ሲሶ ... መሃል መንገድ ላይ ..... (ክፍል አምስት)
(ሜሪ ፈለቀ)

ማነኝ?
ለመርማሪ ፖሊሱ 'ነፍሰ ገዳይ' ነኝ:: እገሌ ዶክተር ነው: ኢንጅነር ነው... ምናምን እንደሚባለው... 'እ ... ሜላት? እሷኮ ነፍሰ ገዳይ ናት!' የሚል ማዕረግ ያለኝ ነኝ:: .. ድርጊት ወይም ድርጊቶች ናቸው ማንነቶቻችን?? እንደዛስ እንኳን ቢሆን እኔ የትኛዋን ነኝ?? እንደተናኜ አባባል 'አር ከማር የምትለየዋን' የአሁኗን ሜላት ወይስ ነፍሰገዳይዋን ሜላት?

"እትዬ በሰዓቱ የሆነውን ያደረጉበትን ምክኝያት: የነበሩበትን ሁናቴ እና ሌሎች አጃቢ ግብሮች ማወቅ ባልቻሉበት ሁኔታ ድርጊቱ ብቻውን የተሟላ መረጃ አይደምኮ!!" ዝም ስለው አሁንም ይቀጥላል!

ከፖሊስ ጣቢያው ከተመለስኩ ጀምሮ ለሰዓታት የማውቃቸውን ቃላት እዛ መርማሪ ፖሊስ ጠረዼዛ ላይ አስቀምጬው እንደመጣሁ ሁላ ዲዳ ሆንኩ:: ሳሎን ሶፋው ላይ እንደተጋደምኩ  ተናኜ የሚለበስ አምጥታ ደረበችልኝ:: ጎንጤ ለእኔ ይሁን ለራሱ እንጃ ብቻ ነፍሰ ገዳይነቴን ማለዘቢያ ሰበብ ያስረዳኛል::

የሚለው ነገር እኮ እውነት ነው ለምሳሌ 'ሜላት ባሏን ገደለች' ከሚለው በምንም አጃቢ ምክንያት ካልታሸ ዓረፍተ ነገር:: 'ሜላት ባሏ ሊገድላት ሲል ሽጉጡን ቀምታ ገደለችው' ቢባል ራሱ ነፍሰ ገዳይነት ግን ራሷን ለመከላከል የገደለች ትንሽ የሚታዘንላት ነፍሰ ገዳይ ያደርገኛል:: ወይም 'ሜላት እህቷን ሊገድል ሽጉጥ ደግኖ የነበረውን ባሏን እህቷን ለማትረፍ ባደረገችው ትግል የባሏ ህይወት ሊያልፍ ችሏል' ያው ነፍሰ ገዳይነት ትንሽም ጀግንነት ሁሉ ይኖረዋል:: .... የእኔው አጃቢ ሁኔታኮ 'ሜላት ባሏን ገደለች' የሚለው ልዝብ ገላጩ ነው:: ... 'አጅሪት' ያለኝ መርማሪ ፖሊስ የማስታወስ ችሎታዬን ማጣቴን ከግምት አስገብቶ በማባበል ቃል መርጦ እንደነገረኝ.... እስከዛሬ በስራው እንደእኔ ዓይነት ኬዝ ገጥሞት አያውቅም!! እንደእርሱ ገለፃ ..

የሆነ ቀን ቢሮው ተቀምጦ የተለመደ ስርቆት: ድብድብ... ወንጀሎችን ሲመረምር በሩን ከፍቼ ገባሁ:: ሁለት የሰው ቆለጥ ጠረዼዛው ላይ ዱብ ሲል ነው የገባው ሰው ባልደረባው አለመሆኑን ያወቀው... በደም የተለወሰ እጄን ልብሴ ላይ እየጠራገግሁ

" ፍሬውን ማስረጃ እንዲሆንህ ነው ያመጣሁልህ! ዋናውን ከፈለግከው አጉርሼዋለሁ:: " አልኩት:: ሬሳው ያልኳቸው ቦታ እንዳልኩትም ዋናውን ጎርሶ አገኙት:: የወንድነት ንብረቱ ከፊሉ መርማሪው ጠረዼዛ ላይ ... ከፊሉ አፉ ውስጥ ከመዝረክረኩ ውጪ በጥይት ነው የተገደለው.... ምክንያቴን እንዳስረዳ ስጠየቅ 'እንዴት እንደምገድለው ለረዥም ጊዜ ሳስብ ቆይቼ ተሳካልኝ::... ለዝህችው አቅሙ ይሄ የማይረባ.. ስንት እንዳስለፋኝ::" ብቻ ነው ያልኩት... በድርጊቴ ከልኩ በላይ መርካቴ ሲደመር ሟች ለመሬት ለሰማይ የከበደ በህዝብ ዘንድ የተወደደ ባለስልጣን መሆኑ ፍርዱን የእድሜ ልክ እስራት አስፈረደብኝ::

እኔ ይሄ ነፍሰ ገዳይነት በምን ምክንያት ቢቀመም: በምን ነባራዊ ሁኔታ ቢሰነግ ነው የሚለዝበው??

ገዳይነት ብቻ አይደለም እንደሁኔታው ሊገዝፍ እና ሊቀል የሚችለው?? የሟች ነፍስም ሊገዝፍ እና ሊቀል ይችላል... እንትን አውራጃ በነበረ የእርስ በእርስ ግጭት 200 ሰው ሞተ ከሚል ዜና እና እገሌ የሚባለው እውቁ ፖለቲከኛ ተገደለ! ከሚል ዜና ሲነፃፀር ከ200 ነፍስ የአንዱ ታዋቂ ነፍስ ይገዝፋል:: ... ያው ሞት ሚዛን ይሰፈርለታል:: ....

"እኔ ምን አውቃለሁ የሳብሽውን ገመድ!! " ብሎኝ ነበር መርማሪው የእድሜ ልክ ከተፈረደብኝ እንዴት ልወጣ እንደቻልኩ ስጠይቀው::

ሰውዬው ስለነገረኝ ይሆን አስታውሼ አላውቅም:: አይኔን ለመጨፈን ስሞክር የሚታየኝ ጠረዼዛ ላይ የሚንከባለል ቆለጥ ነው::....  የምግብ ጣዕም ሁሉ ደም ደም አለኝ:: .... ከዚህ በኃላ ስላለፈው ለማወቅ መቆፈሬን ማቆም ይኑርብኝ መቀጠል ግራ ገባኝ::... ፍርሃት ብቻ ነው የሚንጠኝ:: ጎንጤ አርጅቶ ሽፋኑ የተልፈሰፈሰ መፅሃፍ ቅዱስ አምጥቶ ከተኛሁበት ራስጌ እያስቀመጠ

"ባታነቢው እንኳን ከራስጌሽ ይኑር :: ከበረታሽ ግን አንብቢው ያበረታሻል:: " ብሎኝ ብሎኝ ሲወጣ መፅሃፍ ቅዱሱን አንስቼ አገላበጥኩት:: በእርግጠኝነት የማልገልፀው የእሩቅነት ... የባይተዋርነት ስሜት ተሰማኝ:: ከመንፈሳዊነት የራቀ ህይወት እንደነበረኝ ለመረዳት ምንም ቀመር የሚያስፈልገው ሆኖ አይደለም:: እንደው ግን ቢያንስ በልጅነቴ... አንዱ የህይወቴ ቀን ላይ እንኳን ከእግዚአብሄር ደጅ ተገኝቼ አውቅ ይሆን??

"ተናኜ? ተናኜ? (በሩ ላይ ተለጥፋ እስክጠራት እየጠበቀች ይሁን ዘላ ገባች) ቤተክርስቲያን የሚለበስ ልብስ አውጪልኝ እስኪ... ይዘሽኝ ትሄጃለሽ" አልኳት... ሄዳ የሆነ የራሷን ሰፊ ጉርድ ይዛ ተመለሰች

"ይሄ ከበቃዎት ይሞክሩት እንጂ እትይ እርሶ ቀሚስ የሚመስል ነገርኮ የሎትም" አለች... ጎንጤ ብድግ ብሎ ሲከተን

"አንተ እዚሁ ሁን ችግር የለውም!" ብዬው ነበር:: አልሰማኝም!

"የማይሆነውን! በመንገድ ምን ሊገጥሞት እንደሚች ምን አውቃለሁ? አንዱ የጠገበ ቢጋጭዎትስ? ደሞ ቤተክስኪኑ ትንሽ ያስኬዳል እንደዚያ እርቀት ለመሄድ የሚያስችል አልጠነከሩም! ታክሲ ይጠራልዎ!" ብሎ ለሶስት በታክሲ ሄድን... ቤተክርስትያን ጊቢ ውስጥ አንዱን ዛፍ ደገፍ ብዬ ተቀመጥኩ... ተናኜ ትታኝ ልትፀልይ መሰለኝ ሄደች:: ጎንጤ ትንሽ ራቅ ብሎ እጁን ደረቱ ላይ መስቀልኛ አጣምሮ ያነበንባል:: .... የመጣሁት ላዋራው ነበር:: ልፀልይ: ልለምን.... ዝም ብቻ ነበር ግን ያልኩት... ምን ብዬ ነው የምለምነው?? ብዙ ደቂቃ ፀጥ ብዬ ተቀመጥኩ...

"ልጅ ሜላት" የሚል ድምፅ ሰምቼ ዞርኩ!! ነጭ ነጠላ ራሳቸው ላይ የጠመጠሙ : በእድሜ ተለቅ ያሉ ሰው ናቸው::

"አንቺ ነሽ? " ብለው የተገረመ እና የመደሰት ቅልቅል ፈገግ እያሉ በትኩረት እያዩኝ.... " ያሰብሽው ሞላልሽ?" አሉ እየተጠጉኝ በጋቢያቸው ስር ደብቀው የያዙትን መስቀል አውጥተው እየተጠጉኝ..... ዝም ብዬ አያቸዋለሁ:: ከመፅሃፍ ቅዱሱ ይልቅ እኚህን ሰው ልቤ ያውቃቸዋል:: ብርድ ያንዘፈዘፈው ልቤ ባልገባኝ ምክንያት ሞቀው...

"ምነው ልጄ ደህናም አይደለሽ? ምነው አፍሽ ሰነፈብኝ?" አሉኝ ቀርበው ግራ በመጋባት እያዩኝ .... ጎንጤ ቀረብ ብሎ የሚሆነውን ይከታተላል:: .... ሳላስበው እንባዬ ይፈነቅለኝ ጀመር.... ለመጀመሪያ ጊዜ ከአደጋው ከነቃሁ ከወር ከአንድ ቀን በኃላ ... በስሜ ጠርቶ በፍቅር ያየኝ ሰው ገጠመኝ.... ድምፅ አውጥቼ እነፋረቅ ጀመር::

"እኔን ልጄ!! ምን ገጠመሽ? " ሲሉኝ ከተቀመጥኩበት ዘልዬ ተጠመጠምኩባቸው... ግራ እንደገባቸው ያስታውቃሉ:: አቀፉኝ..... እቅፋቸው ውስጥ ነፍሰ ገዳይ መሆኔን ረሳሁት.... ያየኝ ሁሉ ዓይን ውስጥ ያየሁትን ፍርድ እና ጥላቻ ረሳሁት... ግራ መጋባቴን ረሳሁት.... ባዶነቴን ረሳሁት .... ለደቂቃዎች ብዙ ነገሬን ረሳሁት... ሲያባብሉኝ ቆይተው .... እኔ ተቀምጬበት የነበረ ዛፍ አጠገብ ያለ ጉቶ ላይ አረፍ አሉ እንድቀመጥ እግራቸው ስር አስዩኝ:: .... ከሁኔታቸው ከዚህ በፊት አድርጌው የማውቀው ነገር እንደሆነ ገባኝ:: እግራቸው ስር ተዘርፍጬ ጉልበታቸውን ደገፍ ብዬ የተፈጠረውን ነገር ሆስፒታል ከነቃሁ ሰዓት ጀምሬ ነገርኳቸው:: ዝም ብለው ሲሰሙኝ ቆይተው ብርዳሙ ልቤን የሚያሞቅ ፈገግታ ፈገግ ብለው::
"ልጄ እኔ በዘመናት እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ፀሎት በአንድም በሌላም መንገድ ሲመልስ አይቻለሁ:: ያንቺ ግን ይለያል! (መገረማቸው ይሰማል) የዛሬ ሁለት ወር ገደማ የገብርኤል እለት ማግስት እዝህችው ቦታ እንደዝህችው ተቀምጠሽ 'ያለፈውን ሁሉ በላዺስ ማጥፋት ቢቻል እና እንደአዲስ ሀ ብዬ መኖር ብችል?' ያልሽኝ! 'በቃሉ: በንሰሃ: በጌታችን ደም እንደአዲስ ስርየትን አጊንተሽ መኖር ትችያለሽኮ!' ብልሽ .... 'አይ አባ መች እንዲህ ቀሎ!' ነበር ያልሽኝ:: ልጄ የተመኘሽውን አዲስ ህይወትኮ ነው እግዚአብሔር የሰጠሽ!! " አሉኝ ትከሻዬን ዳበስ ዳበስ እያደረጉ.... እዚህችው መኖር አይቻልም?? ቤት አልፈልግም... ፀሃይም ዝናብም... ክረምትም በጋም ለምን እዝህችው እግራቸው ስር ሆኜ አያልፍም?

የጠየቅኩትን አዲስ ህይወት እንድፅፍ ጭንቅላቴን ነጭ ወረቀት አድርጎ እንደሰጠኝ ቢነግሩኝም ስለራሴ የነገርኳቸው ነገር ካለ እንዲነግሩኝ ጠየቅኳቸው::

"መጀመሪያ ያገኘሁሽ ቀን ... እርግጠኛ ቀኑን አላስታውሰውም... ሰባት ስምንት ወር ቢሆን ነው... እዝህችው ጋር ቆመሽ በአምላክሽ ተቀይመሽ ጮክ ብለሽ እየተጣላሽው ነበር:: እያለፍኩ ገርመም ሳደርግሽ 'ምን ያፈጣሉ? በእግዚአብሄር የተናደደ ሰው አይተው አያውቁም? ' ብለሽኝ ነው ያስቆምሽኝ.... የዛን እለት ለብዙ ዓመታት ፈልገሽ አስፈልገሽ ያገኘሻት እናትሽ ስታገኛት በማይድን በሽታ ልትሞት ወራት እንደቀራት የሰማሽ ቀን ነበር:: ... ዝርዝሩን አልጠየቅኩሽም... ሲጠይቁሽም አትወጂም.... ከዛን ቀን በኃላ ቢያንስ በሳምንት ካልያም በሁለት ሳምንት አርብ አርብ ትመጫለሽ... ያሳለፍሽው ህይወት በዝርዝር ባትነግሪኝም ከባድ እንደሆነ ግልፅ ነው:: .... መጥተሽ እዚህጋ ትቀመጫለሽ... አንዳንዴ ታዋሪኛለሽ ሌላ ጊዜ በዝምታ ቆይተሽ ትሄጃለሽ.... "

"እናቴ ምን ሆነች ከዛ? የት እንደሆነች ነግሬዎታለሁ?"

"አልነገርሽኝም ልጄ! እናትሽ እኔ እስካገኘሁሽ ድረስ በህይወት ነበሩ:: ወንድም እንዳለሽ ነግረሽኛል:: ስለእናትሽ ለወንድምሽ መንገር ተጨንቀሽ ነበር:: አዝናለሁ ልጄ ከዚህ በላይ የማውቀው የለም!" አሉኝ አሁንም ትከሻዬን ዳበስ ዳበስ እያደረጉኝ.....  እናት? የት ናት? ወንድም?? ታዲያ ለምንድነው ብቻዬን የምኖረው? ለምንድነው ጎንጤም ተናኜም ፖሊሶቹም የማያውቋቸው?? እነርሱስ ቢሆን እንዴት ሊፈልጉኝ አልመጡም? ....

            ...........ይቀጥላል.......

@wegoch
@wegoch
@paappii
#የመኖር አካፋይ ፣ የመሞት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል ስድስት)
(ሜሪ ፈለቀ)
«ልጄ ዘመንሽን ሁሉ ክፉ ያደረጉብሽን ሰዎች ለመበቀል ስትዪ ነው የኖርሽው። እንደገባኝ ከሆነ ከበቀል እና ለወንድምሽ ከመኖር ውጪ ሌላ ልምድም ህልምም ስላልነበረሽ የጎዳሽን ሰው ካጠፋሽ በኋላ አንቺ የምትኖሪለት ነገር አጥተሽ ነበር። ልጄ የበደሉሽን ይቅር በይ፣ ራስሽን ይቅር በይ! ለፍቅር በፍቅር ለመኖር ራስሽን አስለምጂ! እግዚአብሄር አዲስን እድል ሰጥቶሻል።» አሉኝ ከጉልበታቸው ላይ ሳልነሳ ብዙ ደቂቃዎች ወይም ሰዓት ካለፈኝ በኋላ
«አባ ለምንድነው ብዙ የሚያውቁት ነገር ያለ ግን ያልነገሩኝ የሚመስለኝ?»
«የማይበጅሽን ብነግርሽ ምን ሊጠቅምሽ ልጄ? ስላሴ ከጭንቅላትሽ ብን አድርጎ ያጠፋው ባይጠቅምሽ አይደል? ወይም ለጊዜው ባያስፈልግሽ? »
«አባ ያለትናንት ዛሬን መኖር ይቻላል? ትናንት የሌለበትስ ዛሬ አለ? እያንዳንዱ ከሰዎች ጋር የሚያያይዘኝ ገመድ ከትናንት ጋር የተጋመደ አይደለም? ቤተሰቦቼም እኮ ትናንቴ ውስጥ የነበሩ ናቸው። እሺ ካልነገሩኝ እናቴን ወይ ወንድሜን እንዴት አገኛቸዋለሁ?»
«የሚጠቅምሽን መረጃ አልደብቅሽም ልጄ። ስለእናትሽ ብዙም አላወራሽኝ ስለወንድምሽ ግን አውርተሽ አትጠግቢም። ስሙ በየእለቱ የምደግመው ስለለሆነ አልዘነጋሁትም። ኪዳን! አዎ ኪዳን ነው።» ጀርባዬ ላይ በትልቁ የተነቀስኩት የወንድሜን ስም ነው ማለት ነው። «ጥይምናው እና ፈገግታው ያንቺው ነው።» ሲሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ከጉልበታቸው ቀና አልኩ
«እንዴ አባ ያውቁታል? አብሮኝ መጥቶ ያውቅ ነበር?» አልኩኝ በጉጉት
«እንደዛ አይደለም ልጄ! በስልክሽ ነው ምስሉን ያሳየሽኝ። » ጠይም ሳቂታ .......... የአልጋዬ ኮመዲኖ ላይ ያለው ፎቶ ነው የሚሆነው
ስልኬ! ......... እንዴት እንደምከፍተው ማወቅ አቅቶኝ መሳቢያ ውስጥ ያስቀመጥኩት መስታወቱ የተሰነጣጠቀ ስልኬ! ቀና ብዬ ጎንጤን አየሁት። ከተቀመጥኩበት እየተነሳሁ
«አባ ልሂድ በቃ! ብመጣ አገኝዎታለሁ? »
«አለሁኝ ከቤቱ የት እሄዳለሁ? (ወደ ሰማይ መልከት አደረጉ) በአይንሽ ካጣሽኝ መልከፃድቅን ጥሩልኝ በይ!» የለበስኩትን እያጤኑ «ለምስጋና እንደመጣሽ አምኜ አምላኬን አመሰግናለሁ» አሉኝ። መጨረሻ ላይ የተናገሩት እንዳልገባኝ ገብቷቸው ፈገግ እያሉ። «ሁሌም ስትመጪ  ሌጣሽን ያለክንብንብ ደግሞም የክፉ ነገሮች ምስል ያለበት ልብስ ለብሰሽ ነበር። አንድ እለት ከጀርባው ትልቅ የእባብ ምስል ያለበት ጃኬት አድርገሽ 'ምነው ልጄ  ከጀርባሽ ፈልገሽው ነው?' ብልሽ። ' ከእግዚአብሄር የታረቅኩ ቀን ለምስጋና ስመጣ ቀሚስ ለብሼ ነጠላ ደርቤ እመጣለሁ።' ብለሽኝ ነበር።» አሉኝ።
እቤት የምደርስበት ሰዓት እርቆብኝ ከደረስኩ በኋላ ከስልኬ ጋር ተፋጥጫለሁ። ጭንቅላቴ ውስጥ ምስላቸው የሌሉ ነገሮችን እንኳን ስይዛቸው በደመነፍስ ምን ማድረግ እንዳለብኝ አውቅ ነበር። ለምንድነው ስልኬን ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ የገባኝ?
«ባትሪ ያለው አልመሰለኝም! እንዱለው ይሆን?» አለኝ ጎንጤ አለማወቄ ቢገባውም እንዳያሳፍረኝ በመጠንቀቅ ዓይነት። አቀበልኩት። ተቀብሎኝ ግድግዳው ላይ ተሰክቶ ገመዱ የተዝረከረከ ገመድ ብድግ ሲያደርግ የሚቀጥለው ሂደት ጫፉን ስልኩ ላይ መሰካት እንደሆነ አውቃለሁ። የሆነ አለ አይደል ሰው መንገድ ጠፍቶበት ልክ ቤቱን ሲያየው ይኸው እንደሚለው ዓይነት ነገር?
አባ 'እግዚአብሄር ጭንቅላትሽን እንደህፃን ልጅ ነጭ ወረቀት አድርጎ ሰጥቶሻል፣ የሚቀጥለውን ዘመንሽን አስተካክለሽ ፃፊበት' ይበሉኝ እንጂ እንደህፃን ነጭ ወረቀት የሆነ ጭንቅላት እንዳልቀረኝ አውቃለሁ። እንደህፃን እንዴት እንደምበላ ከ 'ሀ' አልጀመርኩም ወይም አፌ አልጠፋብኝም፣ መራመድ ለመቻል ከመዳህ አልጀመርኩም ፣ 'ኡፉ ነው' ባልባልም እሳት እንደሚፋጅ ሳየው አውቄያለሁ፣ ሽንቴን ልብሴ ላይ ይሁን ሽንት ቤት የምሸናው ሳላውቅ እላዬ ላይ አልለቀቅኩም፣ ሱሪ ለመልበስ በአንገቴ አላስገባሁም ወይም ጫማ ለማጥለቅ ግራ አልተጋባሁም፣ አልጋ ሳይ ይሄ መተኛሽ ነው ሳልባል ገልጬ ውስጥ ገብቼ ተኝቻለሁ ፣ የጥርስ ብሩሽ ሳይ ምንም ሳልጠይቅ እጂ አንስቶ ጥርሴን ቦርሿል  .........
2. ስልኬ
ስልኬ ለመጀመር የሚያስችለውን ባትሪ ሲያገኝ ራሱ ከፈተ። እስክሪኑ ሲበራ ዘልዬ አጠገቡ ደረስኩ እና አነሳሁት። ያ አልጋዬ አጠገብ ያለው ፎቶ ላይ ያለው ልጅ ዓይኖች ያሉት ፎቶ ይታያል። ራሱ ነው! ኪዳን ነው። ትልቅ ሰው ሆኖ! ይሄን ምስል ሳየው እስከአሁን ምስሎቹን በወረቀት ሳየው ከተሰማኝ የተለየ ስሜት ተሰማኝ። የሆነ የሚያፍን ፈንጠዝያ! ልቤ ሰውነቴ ውስጥ ይነጥር ጀመር። ስልኬን በችኮላ ብነካካውም በኮድ ተዘግቷል። ተስፋ ቆርጬ መሬቱ ላይ እንደተቀመጥኩ
«እትዬ ስልኮትን በፊትዎት ነው ሲከፍቱ ያየሁት!» አለችኝ። እንዳልገባኝ አውቃ ስልኩ እጄ ላይ እንዳለ ወደ ፊቴ ስታቀርበው እውነትም የኮድ ምልክቱ ተነሳ። የሚቀጥለውን ፍለጋዬን ለማድረግ  በረጅሙ ተነፈስኩ። ወዲያው ስልኩ በመደዳ የማያቆም ተደጋጋሚ ድምፅ ያሰማ ጀመር። ለምን እንደሆነ ድምፁ ረበሸኝ። የሆነ ቀጥሎ መጥፎ ክስተት ይከሰት ይመስል ጭንቅላቴን ወጠረኝ። መሬቱ ላይ አስቀመጥኩት። የሆነ ግጭት ጭንቅላቴ ውስጥ የተከሰተ መሰለኝ። የሆነ የተኩስ ድምፅ ነገር።
«ምነው እትይ? አመሞት እንዴ? » ወድያው አስከትላ «ጎንጥ! አንተ ጎንጥ» ጆሮዬ ላይ አምባርቃ ተጣራች። በረንዳው ላይ የነበረ መሰለኝ
«ምንድነው?» ዘሎ አጠገቤ ደረሰ።
«እኔእንጃ የስልኩ ድምፅ ረበሸኝ።» አልኩት ስልኩን ካስቀመጥኩበት አንስቼ እያቀበልኩት።
«ደውሎ ያጣዎትን ስልክ መልእክት እየላከልዎት ነውኮ! ሌላም መልዕክቶች አሉት።»
«የሚጠቅም ነገር ካለው አንብብልኝ» አልኩት ልቤ ለምን እንደፈራ ሳላውቀው እየተርበተብኝ። ዝም ብሎ ስልኩን ሲነካካ ቆይቶ
«ሾካካ የሚባል ሰው 'ዛሬ ፖሊሶች ለድንገተኛ ፍተሻ ስለሚመጡ ቤቱ ይፅዳ' የሚል መልዕክት ልኮልዎት ነበር። ኦው ብዙ መልዕክት ነው የላከው። 'ምነው ዘጋሽኝ? በሰላም ነው ስልክሽ የማይሰራው?'......... 'ኸረ ምንድነው ጉዱ አንቺ ሳይኖሪኮ ቤቱ ስርዓት አጣ! '...... »
«ተስተምረሃል እና?» አለች ተናኜ በጣም በተገረመ አባባል አገጭዋን በእጅዋ ደግፉ ጎንጤን እያየችው። እሷ ማንበብ እንደማይችል እንዴት አሰበች እኔ እንዴት እንደሚያነብ እርግጠኛ ሆንኩ? አላውቅም! እሱ ተናኜን ቁጣና ግልምጫ ደባልቆ ለግሷት ወደንባቡ ሲመለስ የሚያነብበት ስልት እና ፍጥነት ስለእርሱ ብዙ የማላውቀው ነገር እንዳለ እንድጠረጥር አደረገኝ።
« ........ 'ሜሉ መላ ሳይገባልኝኮ ሁለት ሳምንት ተቆጠረ.' ........... እእ 'መታመምሽን በወሬ ሰማሁ መጥቼ እንዳልጠይቅሽ ቤትሽን የሚነግረኝ አጣሁ። ብደውል ስልክሽ አሁንም ዝግ ነው።'»
«ራሱ ሾካካው ነው?» ያልኩት አስቤው አልነበረም። ሁለቱም እኩል ሲስቁ አባባሌ ራሴንም አሳቀኝ! ጎንጤ ሳቁን ሲገታ

«አዎ ራሱ ነው!........ ' አንቺ በቅርቡ የማትመለሺ ከሆነ ለዳዊት መላዬን እንዲቆርስልኝ ንገሪልኝ ዛሬ ሄጄ ስጠይቀው የማውቅልህ ነገር የለም ብሎ አባርሮኛል።' ......... እ ሌላ ያልተመዘገበ ቁጥር........ ' እመቤት ነኝ ሜሉ ያለፈውን ሳምንት ስትቀሪ ባይመችሽ ነው ብዬ አለፍኩ ይሄንን ሳምንት ስትቀሪ ግን አሳሰብሽኝ። በሰላም ነው?' ........ሌላ ደግሞ ዳዊት የሚባል ሰው.........
»ካለ በኋላ ድምፁን ዝግ አድርጎ «እትይ ይሄን ራስዎ ቢያነቡት ሳይሻል አይቀርም ብሎ ስልኩን ዘረጋልኝ። እትዬ ነበር የሚለኝ እሱም እንደ ተናኜ እትይ ብሎ መጥራት መጀመሩ ቁልምጫ መሆኑ ነው?
«አንብበው ችግር የለውም ኸረ!» አልኩት እስከዛሬ ከሚያውቀው የባሰ ምን ሊመጣ ይችላል ብዬ እያሰብኩ። መቼም የገዛ ባሌን ፍሬዎች የቲማቲም ወይ የብርቱካን ፍሬ ከዛፉ እንደመቀንጠስ ቀለል አድርጌ ከሰውነቱ ቆርጬ ፖሊስ ጣቢያ ድረስ ከመውሰድ የባሰ ጉዳይ ሊኖር አይችልም!
«አይ እትይ ግድ የልዎትም ራስዎ ያንብቡት!» አለ እያመነታ ስልኩን የዘረጋበት እጁን ሳይመልስ
«ግድ የለህም አንብበው» ስለው እያመነታ
«ካሉ እሺ!» ብሎ እስከዛሬ ያላየሁበት አይነት የማፈር ይሁን የመቅለስለስ ያልገባኝን ፊት እያሳየኝ ማንበብ ጀመረ። « የእኔ ፍቅር ስደውልልሽ አታነሺም  ስትመጪ የምንጠጣውን እንዳትረሺ! በጣም ቆየሽኮ ፍቅር በሰላም ነው ስልክ የማታነሺው? ....... »
«እሺ እሱን ተወው እና ሌላ አንብብ ኪዳን የሚል መልእክት የለም?» አልኩት እኔም እንደማፈር እያደረገኝ። ፍቅረኛ ነበረኝ? ቢያንስ የእኔ ፍቅር የሚለኝ ሰው ነበረ።
«እኮ!» ብሎ ጣቱን ወደላይ እና ወደ ታች ኪዳንን ፍለጋ ይፈትለው ጀመር። «አይ እትይ ኪዳን የሚል የለም! ምናልባት በሌላ ስም ይሆናል የመዘገቡት! ስም መዝገቡም ውስጥ ኪዳን የሚል የለም!»
«እሺ እስቲ ሊሎቹን አንብብልኝ እና በሌላ ስምም ከሆነ ከመልእክቱ እንደርስበት ይሆናል።» አልኩኝ።
«ሌላ ያልተመዘገበ ቁጥር አሁንም 'እመቤት ነኝ ሜሉ ያስቀየምኩሽ ነገር አለ እንዴ? በባለፈው ንግግሬ ተቀይመሽኝ ይሆን? ግራ ገባኝኮ!  ምንም ውስጥ ሆነሽ ቢያንስ መልእክት ትልኪብኝ ነበር። እንዲህ ጨክነሽብኝ አታውቂም! ብደውልም ስልክሽ አይሰራም። እባክሽ ቢያንስ ደህና መሆንሽን እንኳን አሳውቂኝ!»
«እናቴ ትሆን እንዴ?»
«መደወል እንችል ነበር ግን በሁለት የተለያየ ቁጥር ነው መልእክቱ የተላከው። በየትኛው እንደውል?» አለ ጎንጤ
«ምናልባት የራሷ ስልክ የላትም ይሆናል። አባ ታማለች ብለውኝ የለ? ባለፈው ሳምንት ሳትጠይቂኝ አይደል የሚለው የመጀመሪያው መልእክት?»
«ይሆን ይሆናል። ግን እትይ ለማንኛውም ለጊዜው ማን ምን እንደሆነ እስኪለይ ላገኙት ሁሉ ሰው ምንም እንደማያስታውሱ አይናገሩ! አጋጣሚውን ተጠቅሞ ሊጎዳዎት የሚያስብ ሰው ሊኖር ይችላል።» አለ ሀሳብ እንደገባው ሰው።
«አንደኛው ስልክ ላይ እንደውል!» አልኩኝ። ስልኩ አድምቆ ሶስታችንም በምንሰማው መጠን ሲጠራ ቆይቶ ከወድያኛው ጫፍ ተነሳ እና የወንድ ድምፅ «ሀሎ» አለ። ቀጥሎ የምለው ግራ ገብቶኝ ሳለ ጎንጤ ስልኩን ወደራሱ አስጠግቶ
«ይቅርታ ያድርጉልኝ እና በዚህ ስልክ እመቤትን ማግኘት እችል ይሆን? ሰው መልዕክት ሰዶኝ ነው!» አለ። የሰውየው ድምፅ ያመነታ መሰለ።
«ማነህ አንተ? እመቤትን ለምንድነው የፈለግካት? ማነው የላከህስ?»
«እኔን አያውቁኝም! እንደው እመቤትን ማግኘትን ብችል ወይ የማገኝበትን ሌላ ስልክ ቢጠቁሙኝ።»
«ተሳስተሃል። እመቤት የምትባል ሴት በዚህ ስልክ የለችም!» ስልኩ ተዘጋ። መልሶ እየደወለ። «ሲወሸክት ነው! » አለኝ ለእኔ
«እመቤት የምትባል ሴት አላውቅም አልኩህ አይደል?» አለ ሰውየው እየተቆጣ
«እየዋሹ ነው እሎታለሁኝኣ! በዚሁ ስልክ ከእመቤት መልዕክት ተልኮ ነበር። እመቤትን ካላወቋቸው እመቤት ነኝ የሚል መልእክት እንዴት እዚህ ደረሰ?» አለ ጎንጤ ቆፍጠን ብሎ ሰውየው ስልኩን ሲነካካ ድምፁ ይሰማል።
«ማነው ላከኝ ያልከው?» አለ በጥርጣሬ እንደማጣራት
«ሜላት»
«ታዲያ ራሷ ሜላት ለምን አልደወለችም አንተጋ ስልኳ ምን ይሰራል?»
«ለጊዜው እትዬ ሜላት ታመዋል። እንደየትም ብለህ መልእክት አድርስልኝ ብለውኝ ነው!» ሲለው ሰውየው የጠበበው ድምጽ አሰማ።
«እ መልእክቱን ብትነግረኝ እኔ እመቤትን ሳገኛት አደርስልሃለሁ። እመቤት የት እንዳለች ሜላት ነግራሃለች?» አለ አሁንም እንደጨነቀው።
«በፍፁም! በዚህ ስልክ ደውል ብቻ ነው ያሉኝ!»
«ዌል ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ናት!» አባባሉ 'እስቲ መልእክትህን እዛ ሄደህ ታደርስ እንደሆነ እናያለን!' አይነት ነው።
«እባክዎትን ካላስቸገርኩ ደውዬ እንደነበር መልእክት ያድርሱልኝ!» ብሎ ዘጋ ስልኩን። እናቴ ልትሆን አትችልም! እናቴ እስር ቤት ምን ታደርጋለች? ታማ የለ? ጎንጤ ስልኩን ሲበረብር ስልኩ እጁ ላይ ጮኸ
«እትይ ዳዊት እየደወለ ነው!» አለኝ ስልኩ ላይ አንዳች ነገር ያየ ይመስል እያፈጠጠ።
«አንሳዋ!» አልኩት መልሼ እያፈጠጥኩ
«ኸረግ! ተዚያ ምን ልለው?» ብሎ ስልኩን ክፍት አድርጎ ጆሮዬ ላይ ለጥፎልኝ ለተናኜ እንድትወጣ በዓይኑ ምልክት ሰጥቷት እሱም ወጣ!
«ኦህ ማይ ጋድ ፋይናሊ! በሀሳብ ከማለቄ በፊት! ስልክሽ መከፈቱን ቴሌ ማሳወቂያ ሲልክልኝ አይኔን ነበር ማመን ያቃተኝ! ሜሉዬ የኔ ፍቅር! ምን ባደርግሽ ነው እንዲህ የጨከንሽብኝ?» ሀሎ እንኳን ሳልለው ያለማቋረጥ ይለፈልፋል።
«ትንሽ አሞኝ ነበር» አልኩኝ ጎንጤ ያለኝን አስታውሼ
«ኦህ ማይ ጋድ! ታዲያ አትደውዪልኝም ነበር? እሺ አሁን የት ነው ያለሽው? የት ልምጣ? ኦህ አምላኬ? እሺ አሁን እንዴት ነሽ?»
የሚጠይቀኝ እንድመልስለት አይመስልም! የሆነ ልክ ያልሆነ ስሜት እንዲሰማኝ አደረገኝ። እቤት እንዲመጣ ስነግረው የቤቴን አቅጣጫ አልጠየቀኝም!
«ጎንጥ ? ዳዊት የሚባል ሰው እዚህ ቤት መጥቶ ያውቃል? ሆስፒታል እያለሁ መጥቶ ጠይቆህ ከሆነ?» አልኩት ወደበረንዳ ብቅ ብዬ። እኔስ ጎንጤን ተናኜ እንደምትጠራው ጎንጥ ማለቴ ማቆላመጤ ይሆን?
«በፍፁም እትይ!»
በር በሩን እያየሁ ቆይቼ መጣ! አራት ጊዜ ባጥፈው ያለምንም መጣበብ ሰፋፊዎቹ ጅንስ ሱሪዎቼ ጎን ኪስ መሰስ ብሎ ጥልቅ የሚል፣ ቀጭን ለመባል ራሱ መወፈር ያለበት ፣ አጭር ቀይ ስጋም ቀልብ የራቀው የሆነ ጥላ ቢስ ነገር ነው። አሁን ከዚህ ጋር ምን ይደረጋል? መቼም ወንድ ነው ብዬ ከስር ሆኜ አልደረግለትም! ከላይ ብሆንበት ከእጥረቱ ከቅጥነቱ ፈሱ ነው የሚያመልጠው።
                            ....................ይቀጥላል.........

@wegoch
@wegoch
@paappii
ሥዕል ለማሳል በ+251984740577
ወይም @gebriel_19 ላይ  ፎቶ  በመላክ በ ተመጣጣኝ ዋጋ  ማዘዝ ይችላሉ!


@seiloch
@seiloch
#የመኖር አካፋይ ፣ የመ-ሞት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል ሰባት)
(ሜሪ ፈለቀ)


በር በሩን እያየሁ ቆይቼ መጣ! አራት ጊዜ ባጥፈው ያለምንም መጣበብ ሰፋፊዎቹ ጅንስ ሱሪዎቼ ጎን ኪስ መሰስ ብሎ ጥልቅ የሚል፣ ቀጭን ለመባል ራሱ መወፈር ስጋ መጨመር  ያለበት ፣ አጭር ቀይ……….. ስጋም ቀልብም የራቀው የሆነ ጥላ ቢስ ነገር ነው። አሁን ከዚህ ጋር ምን ይደረጋል? መቼም ወንድ ነው ብዬ ከስር ሆኜ አልተደረግኩለትም አይደል?! ከላይ ብሆንበት ከእጥረቱ ከቅጥነቱ ፈሱ ነው የሚያመልጠው ነውኮ የሚመስለው። ኸረ እንደው በፈጣሪ ምኑ ደስ ብሎኝ ይሆን አብሬው የነበርኩት? ምናልባት ሌላ በፍቅር የሚፈልገኝ ወንድ ጠፋቶ ምርጫ አጥቼ ይሆናል።

ዓይኖቹ የሌባ ዓይኖች ናቸው…….. ቅብዝብዝ የሚሉ ከይሲ ዓይኖች……. ሲያወራ ሁሉም የሰውነቱ አካል ይሳተፋል። በእግሮቹ ጥፍር እንደመቆም፣ ጫማውን መሬቱ ላይ እንደመሳብ፣ ጉልበት እና ጉልበቱን እንደማጋጨት፣ ከወገቡም ሰበርበር እንደማለት፣ የእጁቹን ጣቶች እንደማፍተልተል ነገር ፣ መዳፍ እና መዳፉን እንደማሻሸት፣ ትከሻውን እንደመስበቅ፣ አንገቱን ከወሬው ስልት ጋር እንደመወዝወዝ ፣ ከንፈሩን እንደመንከስ፣ አፍንጫውን እንደመንፋት፣ ዓይኖቹ ከወዲያ ወዲህ እንደመቅበዝበዝ፣ በቄንጥ ያበጠረው ሉጫ ፀጉሩ እንደመንቀጥቀጥ…………. ብቻ ከወሬው ጋር የማይሾር አካል የለውም።

ምንም ከማላስታውሰው ከእኔ በላይ እሱ ግራ ገባው! እንደመነካካካት እንደማቀፍ እንደመሳም ሁሉንም ቅጥ በሌለው ሁኔታ ለኮፍ ለኮፍ አድርጎ ከወነ። አንድ ነገር በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል። ይፈራኛል! እንዲህ አገጩ እስኪዝረበረብ እየፈራኝ ምን ሆኖ ነው «የእኔ ፍቅር » የሚለኝ? አስገድጄው ወይ በቦክስ አላግቼው ይሆን እንዴ ፍቅረኛዬ ያደረግኩት? ጎንጥ ባያስጠነቅቀኝ ምንም እንደማላስታውስ ነግሬው ምን ሲሆን አብሮኝ እንደሆነ ባወቅኩ! ………

«በቀናችን ስትቀሪ እና ስልክ ሳታነሺ ስትቀሪ መጀመሪያ ያው break ፈልገሽ መስሎኝ ነበር። በኋላ ስታመሪ ግራ ገባኝ! በዛ ላይ ስልክሽ ዝግ ሲሆን በቃ ከአንዱ ተጣልታ አንዱ ሸቤ ናት ብዬ አስቤ ሳጣራ መታመምሽን ሰማሁ! ማለቴ መመታትሽን! ያው መጥቼ እንዳልጠይቅሽ ያው አንቺ ነሽ!» ያሄን ሁሉ የሚያወራው እዛው ደጅ እንደቆመ ነው። ጎንጥ እንዳልወደደው ያስታውቃል። በአይኑ ቂጥ በጥርጣሬ እና ባለመደሰት ሲያየው ቆይቶ እኔ ወደ ቤት እንዲገባ ስጋብዘው እሱ ደጅ ቀረ። ‘ያው አንቺ ነሽ!’ ማለት ምን ማለት ነው? መጠየቅ አትወጂም ነው? አትፈልጊም ነው? ምን ማለት ነው? ምንም ነገር ብናገር ከትውስታ ነፃ መሆኔን ላቃጥር ስለምችል እኔ ብዙ ዝም ማለት መረጥኩ። ያለማቋረጥ ከለፈለፈው ብዙ ነገር ገጣጥሜ የተረዳሁት እኔ እና እሱ የምንጋራው ምን እንደሆነ በግልፅ ያላወቅኩት ንግድ ቤት አለን። ስለመጠጥ፣ ሙዚቃ እና ሴቶች የሆነ የሆነ ነገር አውርቷል። ……ብቻ  በወሬው መሃል ጣል ጣል ካደረገው የሚያያዝ ነገር በመነሳት  ለመገመት ብሞክርም ከስልኬ ካገኘሁት መልእክት ጋር ተደምሮ ብዙ አልገባኝም። ፖሊሶች ለድንገተኛ ፍተሻ የሚመጡት ምን ዓይነት ንግድ ቢሆን ነው?

«….. ብቻ ብዙ ነገር በአንድ ወር ተመሳቅሏል። ያ ሾካካ ደግሞ ገንዘብ አልተሰጠኝም ብሎ ሊያስፈራራኝ አልዳዳው መሰለሽ? ቃልኪዳን በጣም ስለጠገበች አባርሪያታለሁ። በወሬ አላድክምሽ ስትመለሺ ሁሉንም ትደርሺበት የለ! ይልቅ አንቺ እንዴት ነሽ? የመታሽ ሰው ማንነት ታወቀ? …… »

«ዛሬውኑ መመለስ እፈልጋለሁ። ለምን አሁኑኑ አብሬህ ሄጄ ፊቴን አሳይቼ አልመለስም?» አልኩኝ ሄጄ የምገባው ምን ውስጥ እንደሆነ ባላውቅም ማወቅ እያጓጓኝ

«አሁን ይሻላል? የምልሽ አሁን ምን እንሰራለን ወይ አንደኛሽን በኋላ ሁሉም ሲገቡ ብትመጪ አይሻልም?» ፊቱ ላይ ግራ የመጋባት እና ጥርጣሬ ነገር ነገሰ። የሆነ ነገር እንደተሳሳትኩ ገባኝ

«ይሁን ሁሉም ባይኖሩም ቤቱ ያለበትን ሁኔታ ቃኘት አድርጌ እመለሳለሁ።» አልኩኝ እሱ ሲያወራ «ቤቱ» እያለ ሲያወራ ከሰማሁት ኮርጄ

«ካልሽ እሺ! ወስጄ እመልስሻለሁ!» አለኝ የሆነ ያልተዋጠለት ነገር እንዳለ እያስታወቀበት።

መኝታ ቤት ገብቼ ተናኜን ጠራኋት እና በፊት እንደምለብሰው አለባበስ ልብስ መርጣ እንድትሰጠኝ አደረግኩ። ምንድነው ብዬ ነው ይሆን እንደዚህ እለብስ የነበረው? መለወጤን ለማንም በቃልም በተግባርም ማሳየት ስላልነበረብኝ ያወጣችልኝን ልብሶች ለባብሼ ከዳዊት ጋር ለመሄድ ተነሳሁ።

«እትይ አንዴ ለብቻዎ ላናግሮት?» አለኝ ጎንጥ ወደ ውጪ ብቅ ስንል። ወደጓሮ ዘወር ብለን ድምፁን ዝግ አድርጎ በሹክሹክታ
«ይቅርታ ያድርጉልኝ እትይ ከዚህ ሰውዬ ጋር ብቻዎትን መሄድዎን አልወደድኩትም። የት እንደሚሄዱስ ያውቃሉ? ልከተልዎት!» አለ ፍርጥም ብሎ

«ግድ የለህም ጎንጥ ምንም አልሆንም! እስከመቼ እንደህፃን ልጅ ትጠብቀኛለህ? የከፋ ነገር እንኳን ቢመጣ ምንም የበፊቷን ሜላት መሆን ባልችል ይሄን አንድ ጭብጥ ሰውዬ መገንበር ያቅተኛል? » ስለው ፈገግ ነገር ብሎ

«ብቻውን ከሆነስ ቆርጥመው ይበሉታል። የት እንደሚወስድዎ ነው ያሳሰበኝ።»
«ግድ የለህም አጠራጣሪ እና ሰው የሌለበት ቦታ ከሆነ እጠነቀቃለሁ።»
«ግድ የሎትም ልከተልዎት?»
«ግድ የለህም ይሄን ብቻዬን ልወጣው! ይልቅ አንቱ የምትለኝን ነገር ተው!»


እንደጠበቅኩትም መኪናውን እየነዳ ያለማቋረጥ እየለፈለፈ ፣ እንዳልጠበቅኩትም አልፎ አልፎ አንድ እጁን እየሰደደ ወይ ትከሻዬን አልያም ጭኔን እንደመዳበስ እያደረገኝ (በጣም ደስ የማይል ስሜት አለው። በተለይ ጭኔ ላይ እጁን ሲያሳርፍ! መጀመሪያ ሲነካኝ ከመቀመጫዬ እንደመዝለልም አድርጎኝ ነበር። ) መንገዱን ተያያዝነው። የምንሄድበትን መንገድ በጭንቅላቴ ለመመዝገብ ፣ የማያቸውን ፅሁፎች ጭንቅላቴ ውስጥ ለማስቀረት እሞክራለሁ። አንዳንዶቹን በትልልቅ የተፃፉ ጽሁፎች የማውቃቸው የማውቃቸው ይመስለኛል። ይመስለኛል እንጂ ከምስሉ ተያይዞ የማስታውሰው ነገር የለም። ይሄ በጣም የሚያስጨንቅ ስሜት አለው። ትውስታ ይሆን ጭንቅላቴ የሚፈጥረው ስሜት ይሆን አለመለየት ፣ የቱ የነበረ የቱ አዲስ መሆኑን አለመለየት ከመርሳቱ በላይ ጭንቅላት ይወጥራል። ለምሳሌ መንገዱን አላውቀውም ነገር ግን መታጠፊያ ጋር ስንደርስ በዛ መታጠፊያ እንደሚታጠፍ ገምቼ ይሁን አውቄ አላውቅም። ግን ልክ መኪናውን እየነዳሁ ያለሁት እኔ ብሆን ልክ እዛ መታጠፊያ ጋር ስደርስ ማንም ሳይነግረኝ መሪውን የማዞር ይመስለኛል። ከትውስታዬ ማህደር ከሆነ መንገዱን ሳላውቀው እንዴት መታጠፊያዎቹን ብቻ አስታውሳለሁ? የሆነ ቀን ለክትትል ሀኪም ቤት ስሄድ ለሀኪሙ የሚሰማኝን መቀዣበር ስነግረው

«በህይወትሽ ውስጥ በተደጋጋሚ ታደርጊያቸው የነበሩትን ነገሮች በደመነፍስ ሰውነትሽ ሲያደርጋቸው ልታገኚ ትችያለሽ። ሳታውቂው ታዘወትሪበት የነበረ ቦታ መገኘት፣ ቋንቋ ድንገት ሰዎች ሲያወሩ መረዳት ወይ መንገር ፣ በፊት ትወጃቸው ከነበሩ ነገሮች ጋር መቆራኘት፣ ትጠያቸው የነበሩ ነገሮችን መጥላት ……..
የመሳሰሉ ነገሮች የሚከሰቱ ናቸው። ከነገሮች ጋር ተያይዞ ጭንቅላትሽ የሚከስተው ምስል ካለ ግን ያ የትውስታሽ አካል ነው። ምናልባት እቦታው ላይ ብትገኚ ክስተቱን የማስታወስ እድልሽ ሰፊ ሊሆን ይችላል።» ብሎኝ ነበር። በእርግጥ የአዕምሮ ክፍላችንን የሚያሳይ ምስል አስቀምጦ ብዙ የተወሳሰበ ነገር ሊያስረዳኝ ሞክሯል። አልገቡኝም እንጂ! ቤተ ክርስቲያን ሄጄ እቀመጥበት ከነበረበት ቦታ እና ከወንድሜ መልክ የቱ ነበር ለስሜቴ መቅረብ የነበረበት? የጎንጥን ፊት ሳላስታውስ እንዴት ሽጉጥን ማስታወስ አወቅሁበት? ዋናውን መንገድ ወይም መዳረሻዬን ሳላውቅ እንዴት ኩርባዎቹን አወቅሁ?

አንድ የሆነ ትልቅ ህንፃ ጋር ደርሰን መኪናውን ካቆመ በኋላ ሰባተኛው ወለል ላይ እየመራ አደረሰኝ እና የሆነ በር ከፍተን ገባን።  የማያቸውን ነገሮች የማውቃቸው ወይም አዲስ እንዳልሆነብኝ ለማስመሰል የማደርገው ሂደት ምን ያህል ይሳካልኝ አላውቅም! ሁለት ሴቶች ወለሉን እያፀዱ ነው። እዚህም እዚያም ወለሉ መሃል ዘርዘር ብለው የተቀመጡት ጠረጴዛዎች ላይ ወንበሮች ተደፋፍተውባቸዋል። ጥግጥጉን በቀይ ገመድ የታጠሩ ጥቋቁር ሶፋዎች አሉ፣ አንደኛውን ግድግዳ ሙሉ በተለያዩ ጠርሙሶችና ሌሎች ነገሮች የተሞላ መደርደሪያ ሸፍኖታል። ከመደርደሪያው እና ከፊቱ ካለው ከፍ ያለ እግራቸው ረዣዥም ወንበሮች ከተደፋበት መደገፊያ ነገር መሃል ሁለት ወንዶች እየተቀባበሉ ብርጭቆ እያደረቁ ይደረድራሉ። መግባቴን ሲያዩ ሁለቱ ወንዶች ስራቸውን ትተው ቆሙ። አንደኛው ወገቡጋ የሚደርሰውን መደገፊያ ነገር ዘሎ አጠገቤ ደረሰ።

«ውይ ሜሉዬ እንኳን እግዚአብሄር ለዚህ አበቃሽ! » ጭንቅ አድርጎ እያቀፈኝ በጆሮዬ እንደማንሾካሾክ ነገር «ቤቱ በአፍ ጢሙ ተደፍቶ ስራ አጥ ከመሆኔ በፊት ለጥቂት ነው የደረሽልኝ» ብሎ ለቀቀኝ። ፈገግ ብቻ አልኩ። የበፊቷ ሜላት እንዲህ ያለ አስጨናቂ መታቀፍ ሲደርስባት በጥፊ ትለፈው በፈገግታ መገመት ባልችልም……. እየተቀባበሉ እንኳን ደህና መጣሽ ይበሉኝ እንጂ መጀመሪያ ካቀፈኝ ሰው ውጪ የጨበጠኝም ያቀፈኝም የለም። ልክ እንደሚያውቅ ሰው የሽንት ቤት ምልክት ከሚታይበት ተቃራኒ ያለውን  ቀጣዩን በር አልፌ ወደ ውስጥ ገባሁ። ሰፊ ኮሪደር እና የተለያዩ ክፍሎች አሉ። እያንዳንዱ ክፍል ውስጥ ሶፋ እና መሃሉ ላይ የብረት ዘንግ ያለበት ከፍ ያለ በቆዳ የተለበጠ ክብ አልጋ መሳይ ነገር አለ። የመጨረሻውን ክፍል ከፍቼ ስገባ አንዲት ቢነኳት ቆዳዋ ተሰርጉዶ የሚቀር የምትመስል ቆንጅዬ ወጣት በፓንት እና በጡት ማስያዣ እዛው አልጋ መሳዩ ቦታ ላይ ተኝታለች። በሩን ከፍቼ ስገባ ብንን ብላ ነቃች እና እንደመደንገጥ ብላ

«ማታ በጣም ዝዬ ስለነበር እዛ ድረስ ከምሄድ ብዬ እዚሁ ተኝቼ ነውኮ! እ? አሁኑኑ ተጣጥቤ ፏ እላለሁ። ይቅርታ በጣም» እያለች ተለማመጠችኝ። ለምን ይቅርታ እንደጠየቀችኝም፤ ስራዋ ምን እንደሆነም፤ ለምን እርቃኗን እንዳለችም ……. ምኑም በእርግጠኝነት ስላልገባኝ በአጠገቤ አልፋ ልትወጣ ስትል ትከሻዋን በአይዞሽ ዓይነት መታ መታ አደረግኳት። ልምምጧ ያሳዝናል። እንዴት ባሳቅቃት ነው ይህችን የመሰለች ልጅ ስታየኝ እንዲህ የምትርመጠመጠው?

እንደገባኝ ከሆነ እቤቱ ውስጥ የሚከወነውን ለማየት ሲመሽ መምጣት አለብኝ። ስር ስሬ ሲከተለኝ የነበረው ዳዊት ወደ ቤት እየመለሰኝ አስብ የነበረው ……. ስንት ዓይነት ሰው ነኝ? ወይም ነበርኩ የሚለውን ነበር። አንደኛው መጥቶ የሚጠመጠምብኝ፣ ሌላኛዋ ስታየኝ ሽንቷ ሊያመልጣት የሚዳዳ ፣ ለዳዊት የሚፈራን ግን የእኔ ፍቅር የሚለኝ …….. አባ እንደልጃቸው ፀጉሬን የሚደባብሱኝ ፣ ጎረቤቶቼ የሚጠሉኝ ፣ ጎንጥ እና ተናኜም ቢሆኑ እንደክፉ ሴት የሚያዩኝ …….. ትክክለኛዋ ሜላት የትኛዋ ነበርኩ? ወይስ ሁሉንም ነኝ? ለማናቸው ነው ትክክለኛ ማንነቴን የገለፅኩት? ለማናቸውስ ነው ያስመሰልኩት? ዝም ብዬ ሳስበው ለምሳሌ ልጅ ቢኖረኝ ፍቅረኛዬ ወይ ባሌ በሚያውቀኝ መልኩ ሊያውቀኝ አይችልም። ምናልባት ባስታውሰው ወላጆቼም ጓደኞቼ በሚያውቁኝ መንገድ አያውቁኝም። የምወደው ጓደኛ ኖሮኝ ቢያውቅ ለእሷ የምሆነውን መሆን ቅድም ብርጭቆ ሲያፀዳ ለነበረው ልጅ አልሆንም። ምናልባት እያስመሰልኩ አይደል ይሆናል። እኔ እንደልጅ፣ እኔ እንደሚስት፣ እኔ እንደጓደኛ፣ እኔው እንደእናት፣ እኔው እንደአለቃ …… እንደብዙ ነገር እንደብዙ የምኖር የእነዚህ ሁሉ ስብጥሮች እሆን ይሆናል።

በር ላይ አድርሶኝ ስንሰነባበት ከንፈሬን ሊስመኝ ሲጠጋኝ ሳላስበው ገፋሁት። ካደረግኩት በኋላ እሱ ፊት ላይ የነበረው ምላሽ እንድፀፀት አደረገኝ።

«ይቅርታ ጥሩ ስሜት ላይ ስላልሆንኩ ነው!»
«እረዳሻለሁ የኔ ፍቅር!» ብሎ ወደመኪናው ገባ!

እቤት ከገባሁ በኋላ ቅድም አስቀምጬው የነበረውን ስልክ መበርበር ጀመርኩ። ብቻ የሆነ ፍንጭ! የሆነ መረጃ! ያልነካሁት ያልፈተሽኩት ምልክት የለም። ከፎቶዎቹ ውጪ ለኪዳን የተጠጋጋ ስምም ሆነ መልእክት የለም። ሌሎች የማላውቃቸው ሰዎች ብቻቸውንም አንዳንዱ ከእኔ ጋር ፎቶ አይቻለሁ። የሆነ ነገር ካስታወስኩ ብዬ ፎቶዎቹን እየደጋገምኩ ባይም ጠብ የሚል ነገር የለም። እናቴ ልትሆን ትችላለች ብዬ የጠረጠርኳት አንዲት ሴት ጋር ተደጋጋሚ ፎቶ አለን። አልጋ ላይ ተኝታ አጠገቧ ተጋድሜ፣ አልጋ ላይ ተኝታ ጉሉኮስ ተሰክቶላት አልጋዋ አጠገብ ተንበርክኬ፣ የሆነ በረንዳ ላይ የሚመስል ቦታ ምግብ እየበላን ፣ ደግሞ ብቻዋን ፈገግ ብላ ……… አንዳቸውም የት ላገኛት እንደምችል መላ አልሰጡኝም።

«እትይ ይሄ መኪና ለምን ጋራዥ አይገባም? በታክሲ ከሚመላለሱም ሰው ከሚያስቸግሩም ይሻልዎታል!» አለኝ ጎንጥ አመሻሽ ላይ ብቅ ብሎ አንድ ጎኗ የተጋጨ እና የጥይት ብስ ያለባት መኪናዬ ወደቆመችበት አቅጣጫ በአገጩ እየጠቆመ።

«ማን ሊነዳው?»
«እሷ ትሰራና መንዳቱስ አይጠፋዎትም! ካልሆነም …… ብሎ አቅማማ
«መኪና መንዳት ትችላለህ እንዴ?» አልኩት ደገፍ ብዬ ከተቀመጥኩበት እየሰገግኩ
« እንዲያ ነገር! ለአንዱ ዲታ ሹፌር ሆኜ 7 ዓመት ሾፍሬያለሁ።» አለ በማጣጣል አይነት።
«ታዲያ ለምን አልነገርከኝም እስከዛሬ? ደግሞ አንቱ አትበለኝ አላልኩህም?»
«አይ እትይ አፌ አይለምድልኝም አንች ማለቱን! ልምድ እንዲህ መች ቶሎ ይለቃል?»
«ሞክረው! መኪናዋን ነገ ውሰዳት ጋራዥ እኔ በታክሲ ደርሼ እመጣለሁ።» ካልኩት በኋላ ነው ስለቤቱ ያየሁትንም ያሰብኩትንም እንዳልነገርኩት ያስታወስኩት።

«እንዲህ ከመሸ ወዲያ መሄድ ደግ ነው ታዲያ? ወይ ልከተሎት!» ብሎ ይተገትገኝ ጀመር። «እትይ ዘንግተውት እንጂ ብዙ ጠላት ያሎት ሰው ኖት!» አሁንም ትንሽ ይቆይና «ባይሆን ከደጅ እጠብቆታለሁ! መንገዱን ላካሂዶት!»
«አንቱ አትበለኝ አልኩህኮ!»
«ይሁን እሺ እኔ ምኑም አላማረኝ እትይ!»
«እህእ!»
«ኸረግ እትይ እንዳትለኝማ አይበሉኝ!»

ባያሳምነውም ታክሲ ጠርቶ ሸኘኝ። የህንፃውን ስም ስነግረው ባለታክሲው አወቀው። እየሄድን የሆነ ጭር ያለ መንገድ ላይ የሆነ መኪና መጥቶ መንገድ ዘጋብን። ባለታክሲው እየተሳደበ መኪናውን አቆመ። ከቆመው መኪና ውስጥ ሁለት የገዛዘፍ ወንዶች ወርደው ደረታቸውን አሳብጠው እየተራመዱ ወደእኛ ቀረቡ!!

@wegoch
@wegoch
@paappii
[ Behavioral Economics ተፈርሾ]

(#አሃዱ)

የአበሻ ፊልም ላይ ሁሌ ድሃው ሲበደል፣ ሲገፋ፣ ሲከፋ ይከርምና - መጨረሻ ላይ ፈጣሪ ጣልቃ ገብቶ ይታደገዋል። ይረዳዋል። ሃብታምየውን ክፉ ገፀ-ባህሪ ደግሞ አግዜሩ ይቀጣለታል።

ቆንጅዬዋም ልጅ ታፈቅረዋለች።

ድሃውም ልቡ በሐሴት ይሞላል። እንደ ፈንዲሻ ይፍነከነካል።  እሺ ትለውና አልጋ ላይ ፈገግ ብለው ይተቃቀፋሉ። (ያው ሲፋቅ በመላጣው ሲከካት ያድራል)

ከዛም ፊልሙ ሲያልቅ

ለአለም፣
ለአለም፣
እንዳይለያየን ዘለዓለም።

የሚል ማጀቢያ ዘፈን ይለቀቃል። ተመልካቹም በከፍተኛ አድናቆት ያጨበጭባል።

(#ክልኤቱ)

ፊልሙን ጨርሰው ከወጡ በኋላ ወንድየው ሲኒማ የጋበዛትን ቸከስ ወይን ይጋብዛታል። ስለፊልሙ፣ ስለፍቅር ሃያልነት፣ ስለ ቸሩ እግዚአብሔር ፈራጅነት ይቀደድላታል። ይስቃሉ ይጫወታሉ። ከዛም አልጋ እንያዝ ይላታል። እሷም በአንዴ ከሰጠሁትማ ይንቀኛል፣ ትንሽ ልሸው ብላ፣ 'አልችልም። ዛሬ ፔሬድ ላይ ነኝ' ትለዋለች።

ይናደዳል።

'ለምን ቀድመሽ አልነገርሽኝም?!' ብሎ ይቆጣል። ያወጣው ወጪ፣ ገተታው፣ ጉጉቱ፣ ኪሳራው ቱግ ያደርገዋል። ኑሮ ውድነቱ፣የጋበዛት ሸክላ ጥብስ፣ አለቃው፣ አከራዩ፣ ATM ምናምን ትዝ ይለዋል።

ይጣላታል።

ሙልጭጭጭ አድርጎ ይሰድባታል። ደንግጣና በርግጋ ጥላው ትሄዳለች። መልሶ በቴክስት ሊሰድባት ሜሴንጀሩን ሲከፍተው ብሎክ አድርጋዋለች።

(#ሰልስቱ)

ወንዶች ጓደኞቹ ጋራ ተደዋውሎ ይሄዳል። ስለኳስ ስለ ፖለቲክ እያወራ ውሎውንና ብስጭቱን ይረሳዋል።  ማታ አልጋው ላይ ሆኖ አስቴር በዳኔን እና መስከረም አበራን ፌስቡክ ላይ ይዘራጠጣል።  አዲስ ቸከስ በሜሴንጀር መጀናጀን ይጀምራል። ስልኳን ይቀበላል። ተቀጣጥረው፣ በሳምንቱ ተገናኝተው ሲኒማ ይዟት ይገባል።

¤

እዚህኛው ፊልምም ላይ ድሃው ሲበደል፣ ሲገፋ፣ ሲከፋ ይከርምና - መጨረሻ ላይ ፈጣሪ ጣልቃ ገብቶ ይታደገዋል። ይረዳዋል። ሃብታምየውን ገፀ-ባህሪ ይቀጣለታል። ለአለም፣ ለአለም፣ እንዳይለያየን ዘለዓለም የሚል ማጀቢያ ዘፈን ይለቀቃል። ተመልካቹም በከፍተኛ አድናቆት ያጨበጭባል።

. . . . ያወጣው ወጪ፣ ገተታው፣ ጉጉቱ፣ ኪሳራው ቱግ ያደርገዋል። ኑሮ ውድነቱ፣የጋበዛት ሸክላ ጥብስ፣ አለቃው፣ አከራዩ፣ ATM ምናምን ትዝ ይለዋል። ይናደዳል - ይጣላታል።

¤

[ህይወትም ይቀጥላል]

@wegoch
@wegoch
@paappii

By Eyob mihreteab yohannes
አስበላሽው
።።።።።።።።
ቆሜ ልቀር ነው ብዬ በተቀመጡት (ቅምጥ በሆኑት)መቅናት ስጀምር መላዕክ ይላከው ሰይጣን በውል የማላውቀው ሰው ሽማግሌ ላከብኝ።

  መኩራት!አይታሰብም!ለምን ጥቁረቱ ኮሎኔል መንግስቱን አያስንቅም?ለምን አይኑ የመርፌ ቀዳዳ አታክልም?
ለምን አፍንጫው ግሪደር እንደባረከው የኮረኮንች መንገድ አይደፈጠጥም?
ለምን ከንፈሩን የቄራ በላቾች አይሻሙበትም?
ለምን ጥርሱ የሕወሃትን አውደ ውጊያ አይመስልም?
ኧረ ለምን እንትን ራሱ የሌለው አይሆንም? "የሰው ልጅ በስጋ ምግብ ብቻ አይኖርም፤ በእግዚአብሔር ቃል ጭምር እንጂ" ብለው የለ አባቄሱ?

  እናማ ቆሞ የመቅረት ፍርሀቻ ከ 'ዙስ' (ከእንስሳት ጋር ከሚገናኙ ሰዎች)መሀል አንዷ ሳያረገኝ እግዜር ማንን እያክለፈለፈ እንዳመጣልኝ ለማየት ቋመጥኩ።ሽማግሌዎቹ በተባለው ቀን መጡ።የምኝታ ክፍሌ መግቢያ ላይ ያለውን መጋረጃ በትንሹ ገልጬ የሚነጋገሩትን ለመስማት ጆሮዬን አሾልኩ።አያቴ እናቴን ለአባቴ ስትድር የለበሰችውን ግማሽ ምዕተ አመት ሊያስቆጥር ጥቂት የቀረውን ጉንፍ ቀሚሷን ከተቆለፈበት አውጥታ ከነኩታው ግጥም አርጋ ለብሳዋለች።ይህ ቀሚስና አያቴ የሚገርም ጥምረት አላቸው።ሰው በተሰበሰበበት

"ይሄንን ቀሚስ የሰራልኝ ሸማኔ ነፍሱን ይማርና ዕውነተ ሸማኔ ነበር...ልብስ ብቻም አልነበር አከላት ሲሸምንም ወደር የለው ነበር..."ስትል ስቅቅ ብዬ

"ኧረ አያቴ እባክሽን እየመረጥሽ አውሪ"እላለሁ።

"ምራጭ ይንሳሽ!ለነገሩ ነስቶሻል...ቆሞ ቀር በቅሎ!አሁንማ ምን ሸማኔ አለ?ወንዱን ሁላ አመንምኑ ጨረሰው...ምድረ ላስቲካም!የቀረውም በግዜ ገብቶ ተምሽቱ ወገብ ይልቅ የብርሌ አንገት ማነቅ ይቀናዋል የጀጋው ጅወርጅስ ይነቀውና!"

ደግሞ ሌላ ጊዜ

"አቤት ይኸን ቀሚስ ሳሰራ የነበረው አጀብ!አቤት!እኔ ይደነቁ እንደሁ ነገር  እሚደንቀኝም አልነበርኩ...አረቄ አውጭታይቱም፣ቅጠል ለቃሚይቱም፣የመሳፍንቱም ቅምጥ፣የወዛደሩም ምሽት ዐይኗን ጥላብኝ...በስተመጨራረሻ እሱ መልዐኩ ህብስቷን ያንጥፈውና...ያች ህብስቴ የሚሏት ጋለሞታ በመተቷ ተብትባኝ አደናቅፎኝ ብወድቅ እንዲህ አጉል ቦታ ተቀዶ ቀረ..."ትላለች ከእንትኗ ዝቅ ብላ ያለችዋን ትንሽዬ ቀዳዳ እያሳየች።ምን ዓይነት አወዳደቅ ልብስን እዚያ ቦታ ላይ እንደሚቀድ ለሰሚው ግራ ቢሆንም ከይደነቁ አፍ ከወጣ ምንም ነገር ሳትወድ በግድህ ታምናለህ!ካልሆነ የእርግማን በኮንቴነረሯን ታራግፍብሀለች።

  ከተላኩብኝ ሶስት  ሽማግሌዎች አንዱ ቀትረ ቀላሉ አባ ሙሉነህ ናቸው። ''ስምን ሳጥናኤል ያወጣዋል! ''ያስብለኛል ተፈጥሯቸው!አንድ የሞላ ነገር ሳይኖራቸው ምን የታየው ደንባራ ነቢይ 'ሙሉነህ' እንዳላቸው ሳስበው ይደንቀኛል። ደሞዛቸው ጎደሎ፣ባለቤታቸው ጎደሎ፣ ልጆቻቸዉ ጎደሎ፣ጓዳቸው ጎደሎ ፣ ዘመዶቻቸው እንዳል ጎደሎ!!ትልቁ ልጃቸው በዓመታት ልምምድ ዘርፈ ብዙ ማጅራቶችን መቶ  በገዛላቸው 'ቲቪ'  ከእሁድ እስከ እሁድ ተቀምጠው ያለ ደህና ቀለብ የፓለቲካ ክርክር ሲያዩ መንምነው ሰንደል ካከሉ ቆይተዋል። እሳቸውን የላከብኝም ጎደሎ እንዳይሆንብኝ ሰጋሁ።

ሁለተኛው ሽማግሌ አባ ምህረቴ ናቸው።የመንደሩ እድሜ ጠገብ ሰይጣን(ማለቴ አዛውንት) በመሆናቸው ሁሉም ያውቃቸዋል ።ከአያቴ ጋር ከተኮራረፉ ቢቆዩም ማህበራዊ ገፃችን ይኸው ዛሬ አገናኛቸው።

የዛሬ ሁለት ዓመት ገደማ ይመስለኛል የሰፈራችን የኪዳነምህረት ደብር የሰበካ ጉባኤ አባላት ሲመረጡ አንዳንድ አሽለጥላጮች ለአባ ምህረቴ ድምፅ ይሰጡና ያስመርጧቸዋል።ከመራጮቹ አንዱ

"አባ ምህረቴ'ኮ ማለት የታፈሩ ጨዋ አዛውንት ናቸው!ሰው በልቶ የጠገበ የማይመስላቸው፣ትሁት፣ሰው ቀና ብለው የማያዩ..."ሲል አያቴ ከተሰብሳቢው መሀል ተነስታ

"ማነህ...ማነህ አስመራጭ!ያልከው በሞላ አንድ ሀሰት የለውም...ልክ ነው!'ሰው በልቶ የጠገጠ አይመስላቸውም' ላልከው እኔ አለሁ ምስክር!አንዴ ለምሳ የሚበሉት የኔን የዕለት ቀለብ ስለሆነ ሰው በልቶ የጠገበ ባይመስላቸው አይደንቅም!አዎ አይደንቅም!...ደሞ ' ሰው ቀና ብለው አያዩም ' ላልከው ሌላ ተዓምር የለውም ጎባጣ ስለሆኑ ነው ''ካለቻቸው ወዲህ የእግዜር ሰላምታ እንኳን መለዋወጥ ትተው ነበር።

ሶስተኛው ሽማግሌ ቆጥቋጣው አባ ዘለዓለም ናቸው።መብራት አጥፋ አላጠፋም በሚል ግብግብ ከተከራያቸው ተጋጭተው ባተረፏት መጠነኛ የግንባራቸው ጠባሳ ነው መንደርተኛው አፍ ውስጥ የገቡት።እንደሰማሁት ከሆነ ሚስቱ የወለደች ተከራያቸውን

"አንተ ማነህ...መብራቱን በግዜ አታብራው እንጅ ገና ቀን አይደል?"ሲሉት

"ኧረ  ጋሼ መብራቱ ሲጠፋኮ ጨቅላው እያለቀሰ አስቸግሮን ነው"ብሏቸዋል ።

"ኧና  ምሸቱ ጠንከር እስቲል ጨረቃ ላይ አውጥታችሁ አታጫውቱትም?"ብለው ያንን ያልጠነከረ ጨቅላ የበረንዳ ብርድ አስመትተው ሳንባውን ከጥቅም ውጭ አረጉት አሉ።ህፃኑ ትኩሳትና ሳል ሲያዳፋው የጨነቃቸው እናትና አባት ከምሽቱ 05:00 ገደማ መብራት ሲያበሩ፣አባ ዘለዓለም ለሽንት ሲወጡ ይገጣጠማሉ!ሶስተኛው የዐለም ጦርነት ሆነ!...ሚሳኤል ተተኮሰ!

  "አተ! ምንድነው በዚህ ለ
ምሸት መብራቱን የለኮስከው?"

  "ኧረ ጋሼ ልጁ ታሞብን ነው"

  "ምንድነው ያመመው?"

   " እንጃ ትኩሳት አለው"

"ዋእ!እና በትኩሳቱ ላይ አምፖሉን ለኩሳችሁ ልታነዱ ነው?"ብለዋል አሉ ዕውነት ይሁን ግነት ባላውቅም!በመሀል ግብግብ ተነስቶ የበሰጨው ተከራይ በጠርሙስ ግንባራቸውን ከተረከካቸው ወዲህ ነው አደብ የገዙት።

ሽማግሌዎቹ ከአያቴ ፊት ለፊት ተደርድረው እርስበርሳቸው ይተያያሉ።

ወዲያው አባ ሙሉነህ ከቀሪዎቹ ሽማግሌዎች አንድ እርምጃ ወደፊት ወደ አያቴ ጠጋ አሉና

  "እንግዲህ እማ ይደነቁ ያው እንደሚያውቁት ዛሬ የመጣነው መልካም ፈቃድዎ ተሆነ ልጅዎትን ለልጃችን ልንል ነው"ሲሉ አያቴ

"ለመሆኑ ምንምን ጥሪት አለው?"ብላ የሀብት ክፍፍሉን ከአሁኑ ልታሰላ ነው ብዬ ስጠብቅ የግንባሯን ቆዳ ሰብሰብ አድርጋ

  "ለመሆኑ ሰውየው ማነው?"አለች ።

"እሱንማ  በቀደም ዕለት ተነጋገርንም አይደል እማ ይዴ?"(አባ ሙሉነህ)

"የለም!የተነጋገርነውማ የሰውየውን ስም እና የምጫችሁን ቀን ብቻ ነው!አዎ!እሱንም እኔን ሳታማክሩ በግላችሁ ነው የወሰናችሁት።አሁን እሱን ተውትና ስለ ሰውየው  ንገሩኝ ማነው ያላችሁት ስሙን ?ሺመክት ነው?"

"አዎ ሽመክት!እንደው እንዴት ያለ የቤት አስተዳደር የተካነ ቆጣቢ መሰለዎት!"አሉ አባ ዘለዓለም ጣልቃ ገብተው።

"ስራውስ?"

"ስራው ተሰው አልፎ እግዚሀር የወደደው የተመረጠ የበተስኪያን አገልጋይ ነው።እዚሁ እኛው ደብር ችዳነምረት የመጣ አዲስ ዲያቆን ነው"(አባ ምህረቴ)

"ዲያቆን?"

"አዋን ዲያቆን ምነው?"(አባ ምህረቴ)

"ኧረ ምንም...ዲያቆን ሸጋ ነው ወንድሞቸ...ግን እንዲያው..."

"ግን ምን እማ ይዴ?"(አባ ሙሉነህ)

"ምንም ...እንዲያው ዲያቆን ተሆነ ጋብቻው በበተስኪያን ይሁን ማለቱ አይቀርም ብየ ነው እንጅ"

"አሀ!እሱማ ምን ጥያቄ አለው?እግዚሀሩ በወደደው በፈቀደው በቅዱሱ ተክሊል ቢጋቡ ምንድነው ችግሩ?"(አባ ሙሉነህ)

"ትክል ያርጋትና አንዳች ተካይ ቆይ እስቲ ወዳጆቸ አረፍ ብላችሁ ጠብቁኝ መጣሁ "አለችና አያቴ ወደኔ መጣች።

[[[እዚህ ጋር "ትክል ያርጋትና አንዳች ተካይ"የሚለውን እርግማን አያትየው ድምፃቸውን ዝቅ አርገው ነው የሚሉት]]]

ደመነፍሴን ወደሁዋላ ተራምጄ አልጋዬ ላይ ከመቀመጤ መጋረጃዬን ገልጣ በተማፅኖ እያየችኝ
"አንች ጀጤነሽ" አለችኝ።
"አቤት"
"እንደው በጣድቁ ...አደራሽን በጣድቁ እንዳታሳፍሪኝ!"
"ምንድነው አያቴ?"
"ንጡህ ነሽ አይደል?"
"ማለት?"
"የሚል አላት ብያለሁኮ እችን ተንከሲስ!ንጡህ ነሽ ድንግል ነሽ ወይ ነውኮ 'ምልሽ" አቀርቅሬ ዝም አልኩኝ።ለሰከንዶች ምላሼን ስትጠብቅ ቆይታ ተስፋ ስትቆርጥ

"በይ'ንጂ ንገሪኝ ...አየ!አየ!አየ ለፍቶ መና አስበላሽው? ጀጤነሽ አስበላሽው?ያን የመሰለ ዳቦ አስበላሽው?ሀይ!ሀይ!ሀይ!ሀይ!ሀይ!"አለችና ወደሽማግሌዎቹ ሄደች።እኔም ባቀረቀርኩበት ቆየሁ።ከዚያ በላይ የተነጋገሩበትን የምሰማበት ድፍረት አልነበረኝም።

✍️ማዕዶት ያየሕ

@wegoch
@wegoch
@paappii
ባለትዳሮች ደግሞ እስኪ አዳዲስ ጅንጀና ፍጠሩ...

እንዴ ሁሌ አንድ አይነት ያለፈበት ነገር ቸከሶቹም ይደብራቸውል እኮ!

“ይሄ በትዳሬ ደስተኛ አይደለሁም”፣ “አልጋ ከለየን ቆየን”፣ “ሶፋ ላይ ነው ማድረው”፣ “ለልጆቹ ብለን ነው አብረን ያለነው”፣ “በትክክል ካወራን እራሱ ረጅም ግዜ ሆኖናል”፣ “”ምግብ እንኳን አንድ ላይ ከበላን ቆይተናል”... ምናምን ዝብዘባ ኸረ ላሽ እንዲ ብላችሁ እኮ ብትፋቱ አሪፍ ነበር በስንተኛው ወር መንታ ልጅ ትወልዳላችሁ እኮ ደሞ!

እስኪ አዲስ የተጣላችሁበትን ምክንያት ፍጠሩ እስኪ ላይክ...

ወንዶቹ..

ቅልጥም በልታ መጣ ከዛ በዘነዘና ሰብራ ትበላለች

ስስማት እንጥሏ ይዋጋል

ጉልበቷ እያደር መጥቆር አመጣ

ቅቤ ተቀብታ በስስ ፌስታል አስራ ማደር ጀመረች

የብብቷን ፀጉር ማሳደግ ጀመረች

ፓንቷን በሶስት ቀን ነው የምትቀይረው

ሁሌ ሽንት ቤት ገብታ ፍላሽ ሳታደርግ ትረሳዋለች

ሴቶች ደግሞ...

ስኪኒ ሱሪ መልበስ ጀመረ

መጠጥ መጠጣት አቆመ

አፍንጫውን ይጎሮጉራል

ሲቀመጥ የቂጡ ፍንክት ይታያል

ሁለት ካልሲ ብቻ ነው ያለው

አፉ ጥግ ጥግ ላይ ነጭ ነገር ማውጣት ጀመረ

የሆነ ነገር በወደቀ ቁጥር "እሜ ድረሽ!" እያለ ከወንድ ልጅ የማይጠበቅ ቀጭን ድምፅ ያወጥል...

ምናምን የሚሉ የማያስሟሟችሁን ምክንያቶች ደርድሩ እንጂ!

@wegoch
@wegoch
@paappii

By Habtish doi yilma
#የመኖር አጋማሽ ..የመ: ሞ : ት ሲሶ ... መንገድ መሃል ..... (ክፍል ስምንት)
(ሜሪ ፈለቀ)

'ማናችሁ? ምን ፈለጋችሁ?' ከማለቴ በፊት ከታክሲው ኃላ መቀመጫ ጎትተው አስወጥተው ያበጥሩኝ ጀመር:: .... 'ምን አድርጌያችሁ ነው?' ማለት አፌ ይፈልጋል... በየትኛው ትንፋሽ?... እንኳን የማወራበት... የምተነፍስበት ፋታ ሳይሰጡ ተቀባበሉኝ.... ባለታክሲው ሁለት ቡጢውን ሲያጣጥም መፍጨርጨሩንም ተወው:: ... ሶስተኛ ሲሰልሱት እንዲተውኝ መለመኑንም ተወው! መሬቱ ላይ ወድቄ 'እንካ በእርግጫ' ተባባሉብኝ.... የምቱ ቁጥር ሲጨምር የህመሙ መጠን ቀነሰ... ሰውነቴ የደነዘዘ መሰለኝ.... አንደኛው በጫማው ደሬቴን ሲለኝ... ቁስሌ የተቀደደ አይነት ስሜት ተሰማኝ... ሳያስፈቅደኝ ልቤ ክድት ... ጭልጥ ይልብኝ እና ምቱ ያነቃኛል.... በስልምልምታ ከሩቅ እየቀረበ የመጣ የመኪና ድምፅ እና መብራት የተፈራረቁብኝ ይመስለኛል::..... የሚደልቁኝ ጫማዎች በፍጥነት ጥለውኝ ሲሄዱ ነገር.... ... ልቤ ቅልጥ ብሎ ጥፍት አለብኝ....

የሆነ በርቀት ነገር "እትይ! እትይ!" ... የሚል ጥሪ ይሰማኛል:: ... አይኖቼን ልገልጥ ስሞክር የአይኖቼ ቆቦች ህመማቸው ያሰቃየኛል:: ... ያልታመመ የሰውነት አካል የለኝም:: ... ሀኪም ቤት ተኝቻለሁ::.... ጎንጥ የአልጋዬን ጠርዝ ይዞራል:: ያልተጠቀለለ የሰውነት አካል የለኝም::.... አይኔን መግለጤን ሲያይ

"እትይ ነቁ? ክብር ምስጋና ይግባህ አምላከ ስላሴ!" ብሎ ወደ ሰማይ አየ.... ፊቴ ላይ ሳይቀር በፋሻ ተጠቅልያለሁ!.... እንባዬ ሲወርድ ወደ ጆሮዬ እየሄደ የሚያልፍበት ቆዳ ሁሉ አልኮል እንደተደፋበት ቁስል ያቃጥለኛል::... አንገቴ ቀስሮ በሚይዝ መደገፊያ ተደግፎ ስለታሰረ አይኔን እንጂ አንገቴን ማዞር አልችልም:: አፌን ላንቀሳቅስ ብሞክር የተሰነጠቀ ከንፈሬ ስቃይ ውስጥ ይጥደኛል::...

"እትይ! ግድ የለም እነዚህን ሽንታሞች አገኛቸዋለሁ!!" ይለኛል ጎንጥ እሳት በሚተፋ የንዴት እና የእልህ ትንፋሽ .... በቁጭት አንዱን እጁን በቡጢ ጨብጦ ሌላኛውን ይመታል::

በጥይት ተመትቼ ስነቃ እንዲህ በህመም አልተሰቃየሁም ነበር::.... ተኛኜ እና ጎንጥ እየተፈራረቁ እያስታመሙኝ ሆስፒታል ከረምኩ::.... ከሳምንታት በኃላ የተሰበረ አፍንጫዬ አገገመ.... የተሰነጠቀ ከንፈሬ ቁስል ሻረ... የተሰባበሩት የጎድን አጥንቶቼ ተደጋገፋ... የበለዙ ስጋዎቼ ፈዘዙ..... አንገቴ ያለ ድጋፍ ዞረ.... የዞረ ክንዴ ቦታው ሰገበ... ወደ አንጀቴ የፈሰሰ ደሜ ተቀዳ..... የተቀደደ ቁስሌ ተሰፋ......

"ተሻለሽ?" ሲሉኝ .... "ደህና ነኝ!" እላለሁ! ... የጠየቁኝ የስጋ ቁስሌን እንደሆነ ስለማውቅ...

እኔ ግን አልተሻለኝም!! ደህና አይደለሁም!! ጭራሽ ለደህና የቀረበ ነገር አይደለሁም!! ... ጎንጥ አጠገቤ ሆኖ እጄን ካልያዘኝ እንቅልፍ የማይወስደኝ ፈሪ ሆኛለሁ:: ኮሽ ባለ ቁጥር ከአልጋዬ የማልዘለው እሱ እየጠበቀኝ እንደሆነ ሳውቅ ብቻ ነው:: .... ካለበለዚያ ኮቴ ያስደነግጠኛል:: .... የትንኝ ጥዝታታታ እንኳን ጩሂ ጩሂ ይለኛል:: መጠየቅም መመለስም ተውኩ:: መሞትም መኖርም ፈራሁ!! ... ተናኜ አብራኝ ስትውል.... የቆጥ የባጡን ስትለፈክፍ አልመልስ ስላት!!

"ኸረ እትይ በማርያም እንዲህ አይሁኑ!" ትለኛለች:: ጭንቅ ጥብብ ሲላት ደግሞ
"እትይ? ካልሆነ እብስ ብለው ለምን የሆነ ሀገር አይሄዱም?" ትለኛለች::
"እትይ? እስኪ ትንሽ ነገር ደግሞ ይቅመሱ በማርያም?"

..... አግጯን ደገፍ ታደርግና "ምፅ!" ብላ እንባዋን ትለቀዋለች:: ...

"ምን ልሁን ነው የምትይ?" ይላታል ጎንጥ ማልቀሷን ሲያውቅ:: ....

የዛን ቀን ሹፌሩ የመኪና ታርጋቸውን መዝግቦ ስለነበር ለፖሊስ መረጃ ብንሰጥም ፖሊሶቹ የእኔ ጉዳይ ግድ የሚሰጣቸው አልመሰሉም:: ጎንጥ ብስጭት ብሎ

"በነጋ በጠባ 'ያላሰለሰ ጥረት እያደረግን ነው! ' ይሉኛል:: ጠብ የሚል ነገር የለም! እንዴት ያለ ህግ ነው?" አለኝ የሆነ ቀን.... አልመለስኩለትም!! .... ቀን ቀን ተናኜ ትውልልኛለች:: ማታ ማታ እሱ ያድራል:: ... ዳዊት አንድ ሁለቴ ሊጠይቀኝ መጥቶ ነበር:: እንዳይመጣ ስለነገርኩት ቀረ!! ....

"እትይ ? ዛሬ ጎንጥ ስለማይመጣ ምሽቱንም እኔ ነኝ የማስተዳድሮት.... እቤት ደረስ ብዬ እራት አበሳስዬ ላምጣ?" አለች በጨነቀው ልምምጥ....

"ለምንድነው ጎንጥ የማይመጣው? " አልኩኝ የወላለቀ ሰውነቴን እየጎተትኩ ተቀምጬ

"አላውቅም እትይ!! የምፈጣጥመው ነገር አለኝ ! ነው ያለው!"

"እሺ ትተሽኝ አትሂጂ.... ከካፍቴሪያ የሆነ ነገር ግዢ" ብያት (የሆስፒታሉ ጊቢ ውስጥ ያለ ካፍቴሪያ ነው) እሷ ልታመጣ ስትሄድ ከፋኝ!! እንደህፃን ልጅ አለቀስኩ:: .... ሆስፒታል ማደር ደክሞት ይሆን??? እኔን መጠበቅ ከነአካቴው ደክሞት ይሆን?? ጠልቶኝ ይሆን?? .... ላይመለስ ትቶኝ ቢሄድ ምንድነው የምሆነው?? ከእርሱና ከተናኜ ውጪ ማንንም እንደማላውቅ እያወቀ ትቶኝ ይሄድ ይሆን?? ይቅር ይበለኝ እና ብር አምጣ ብዬ ከካዝናው ውስጥ ያወጣሁት ብር የት እንዳለ ነግሬዋለሁኮ .... ብሩን ይዞ እኔን ትቶኝ ሄዶ ቢሆንስ? እኔ በወር የምከፍለውን ደመወዝ ከ20 ዓመት በላይ የሚከፍለው ብር ነው..... በስመአብ !! ኸረ እንደሱ አያደርግም!!!

ለሊቱ እንቅልፍ በአይኔ ሳይዞር ነጋ!! ተናኜ ሳለቅስ ካየችኝ ከእኔ ብሳ ታርፈዋለች:: አልጋዬ ስር ፍራሿን ዘርግታ እንቅልፍ እስኪወስዳት ጠብቄ ..... ብዙ አልቅሼ እንባዬ ሁላ ያለቀ መሰለኝ!! ፍርሃት ሆዴን አላወሰው!!! የበር ድምፅ በሰማሁ ቁጥር ልቤ ይርዳል:: ሰውነቴ ይንቀጠቀጣል::....  ነግቶ ብርሃን ሲሆን እንቅልፍ ጣለኝ:: .... ብርሃን ከክፋት የሚጠብቀኝ ይመስል ሲፈካ ልቤ ይረጋጋል:: ከእንቅልፌ ስነቃ አይኔን ሳልገልጥ በፊት እጄን የያዘኝን እጅ ጨበጥኩ.... አይኖቼን ስገልጣቸው ጎንጥ ለሊት ሲያድር እንደሚያደርገው ወንበር ላይ ተቀምጦ እጄን ይዞኝ ... አንገቱን አልጋው ላይ ደፍቶ ተኝቷል::  .... ደስታ ይሁን መከፋት የማላውቀው ስሜት ናጠኝ::: ህቅታዬ እንዳይረብሸው እየታገልኩ ተንሰቀሰቅኩ:: ... ከደቂቃዎች በኃላ ግን ልያዘውም ብል ፈንቅሎኝ የወጣ ህቅታዬ ቀሰቀሰው.... እንደነቃ ሳየው ይብስ ድምፅ አውጥቼ ማልቀስ ጀመርኩ:: ....

"መድሃንያለም! እትይ? ምን ሆነው ነው?? ኸረ በመድሃንያለም ነፍስያዬን አያስጨንቋት?? " የሚያደርገው ግር ብሎት እጄን ባልጨበጠ እጁ እንባዬን ሊጠርግ ይታገላል::

"የሄ.... ድክ ... መስሎኝ..." ብዬ መጨረስ አቃተኝ:: ህቅ ማለት ቀጠልኩ:: ክፉ ነገር እንደነገርኩት ሁሉ ... ዝግንን ብሎት እጄን እንደጨበጠ ከተቀመጠበት እየተነሳ

"መሄድ ሲሉ?? መሄድ ! መሄድ!? ... ይቅር ይበሎት! ምኑን አሰቡት? እንዲህ ያለ ሁኔታ ላይ እንዴት ትቼዎት እሄዳለሁ?? እንዴት ያለ ሰው ነው ብለው ነው የሚያስቡኝ?" አለ ቁጣም በቀላቀለው አነጋገር!!

"ይቅርታ አድርግልኝ!! እኔ አላውቅም!! ምን እንደማስብ... ግራ የገባኝ ሰው ነኝ! ካንተ እና ከተናኜ ውጪ ማን ምን እንደሆነ እንኳን አላውቅም!! አንተ ብትሄድ..." ብዬ መጨረስ ቸገረኝ:: ተመልሶ እየተቀመጠ በሚለማመጥ ድምፅ

"የትም አልሄድም! እርሶ አልፈልግህም ብለው እስካላበረሩኝ ድረስ እኔ የትም አልሄድም!!" አለኝ:: ...
በአንድ አፍታ በእጄ የያዘኝን እጁን አጥብቄ ስይዘው እና ዓይኖቼ የበለዘ አይኑን ሲያዩ እኩል ሆነ... አጥብቄ ያያዝኩት እጄ ህመም እንደሰጠው ፊቱ ላይ ስቃዩ ታየ:: እያየሁት እንደሆነ ሲያስተውል ህመሙን ለመዋጥ ታገለ:: እጁን ስቤ አየሁት:: እንደማበጥም እንደመቁሰልም ብሏል::

"አምላክ ሆይ!! ምን ሆነህ ነው?" ብዬ ጮህኩ:: እሱ ከአፉ ቃል ሳይወጣ የሆነው ነገር ከእኔ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ገባኝ::

"ምንም አልሆንኩ! እንዲያው ዝም ብሎ ነገር ነው!" ይለኛል ደጋግሜም ብጠይቀው:: ቅስስስ ብዬ ተነስቼ እየተቀመጥኩ አገጬን በእጆቼ ወደራሴ እያዞርኩ ፊቱን አየሁት....

"እሺ የተፈጠረውን አትንገረኝ!! ተጎድተሃል?? ሌላ ቦታ ተመትተሃል?"

"ምንም አይደልኮ ትንሽ ነገር ነው!" ይበለኝ እንጂ ትልቅ ነገር እንደሆነ ሆዴ ነግሮኛል:: የዛን ቀን ከሰዓታት በኃላ ያላሰብኩት እንግዳ ጎበኘኝ..... ማንነቱ የገባኝ ከደቂቃዎች በኃላ ነው:: ... የዛን ምሽት ከደበደቡኝ ውስጥ አንዱ ነው:: ..... ጎንጥ አጠገቤ ቆሞ እንኳን ፍርሃት ልቤን ከደረቴ ጎትቶ ሊያስወጣት ታገለኝ:: ... ሳይታወቀኝ አይኔን ከድኜ እግሬን ሰብስቤ ጉልበቴን አቅፌ ጥቅልል አልኩ:: ....


        .......... ይቀጥላል........

@wegoch
@wegoch
@paappii
ፓብሎ ኢስኮባር- ቱጃሩ የናርኮቲክ ወንጀለኛ
----
ጸሐፊ: አፈንዲ ሙተቂ
----
ፓብሎ ኢስኮባር ማለት በአንድ ዘመን በCIA በጥብቅ ሲፈለግ የነበረ ቱጃር ነው። በዜግነቱ ኮሎምቢያዊ ነበር። ይህ ሰው በዓለም ታሪክ የሚታወቀው ትልቁ የአደንዛዥ እጽ አምራችና አከፋፋይ ድርጅት የሆነው Medellin Cartel መስራችና ባለቤት በመሆኑ ነው። በዚህ ድርጅት አማካኝነት በየወሩ እስከ ሰማኒያ ቶን የሚደርስ የኮኬን እጽ ወደ አሜሪካ ያስገባ ነበር። ይህ መጠን በሂደት እየጨመረ ሄዶ በ1980ዎቹ መጨረሻ ላይ ድርጅቱ በየቀኑ 15 ቶን ኮኬን ወደ አሜሪካ መላክ ጀምሯል።

ታዲያ ይህ ትልቅ መጠን ያለው እጽ ወደ አሜሪካ ይገባ የነበረው እጅግ በተደራጀ የኮንትሮባንድ መስመር እና የትራንስፖርት ቻናል ነው። ኢስኮባር ከዚህ ንግድ እጅግ ብዙ ሀብት መሰብሰብ ችሏል። ድርጅቱም በዓለም ዙሪያ ከሚመረተውና ከሚሸጠው ኮኬይን የሰማኒያ በመቶ ድርሻ ነበረው።

ኢስኮባር የተሰማራበት የኮኬን ኤክስፖርት በዓለም ታሪክ እጅግ ሀብታሙ ወንጀለኛ እንዲሆን አስችሎታል። ኢስኮባር በ1993 በተገደለበት ወቅት የተጣራ ሀብቱ ከሰላሳ ቢሊዮን ዶላር በላይ ደርሶ ነበር።
----
ኢስኮባር ንግዱን ሲያካሄድ መንገዱ አልጋ በአልጋ አልነበረም። ከእርሱ ጋር ከሚወዳደሩ የኮኬን ነጋዴዎች፣ ከፖሊሶች፣ ከወንጀል መርማሪዎችና ከድንበር ጠባቂዎች ጋር ብዙ ህይወት የጠፋበት ውጊያ ውስጥ ገብቷል። በዚህም የተነሳ በሀገሩ በኮሎምቢያ እና በአሜሪካ መንግሥት በጥብቅ ይፈለግ ነበር። የአሜሪካው CIA ሊገድለው ብዙ ሙከራ አድርጓል።

ኢስኮባር በ1991 ከኮሎምቢያ መንግሥት ጋር የገባበትን ውዝግብ ለመፍታት ሲል ድርድር ጀመረ። በድርድሩም "ለአሜሪካ መንግሥት አሳልፋችሁ ካልሰጣችሁኝና ራሴ በሰራሁት እስር ቤት እንድታሰር ከፈቀዳችሁልኝ እጄን እሰጣለሁ" በማለት አስታወቀ። የኮሎምቢያ መንግሥትም በዚህ ተስማምቶ ለፍርድ አቀረበው። ፍርድ ቤቱም የአምስት አመት እስራት ፈረደበት። ኢስኮባርም La Chatedral ብሎ በሰየመው የግል እስር ቤቱ የወህኒ ጊዜውን ጀመረ።

ከአንድ ዓመት በኋላ የኮሎምቢያ መንግሥት ወደ መደበኛ እስር ቤት ሊወስደው ሲሞክር ግን ኢስኮባር ሊያስሩት የመጡትን ፖሊሶች ገድሎ አመለጠ። የኮሎምቢያ መንግሥት እና የአሜሪካው CIA በቅንጅት ያሳድዱት ጀመር። ከአስራ ስድስት ወራት ፍለጋ በኋላም ለብዙ ዓመታት በነገሰባት የሜዴሊን ከተማ በተደበቀበት አንድ አነስተኛ ፎቅ ቤት ውስጥ ተገደለ።
----
ፓብሎ ኢስኮባር የ'"ናርኮ-ቴሬሪስት" ወንጀለኛ ተብሎ በብዙ የዓለም ሀገራት መፈረጁ እውነት ነው። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ግን ሰውዬው በሁለት ነገሮች ዘወትር ይታወሳል።

የመጀመሪያው ፓብሎ ኢስኮባር በቤቱ ውስጥ የኖረበት ምቾት በብዙ ሀገራት ቤተ መንግሥታት እንኳ የሌለ መሆኑ ነው። ኢስኮባር በሰፊው ግቢ ውስጥ ከገነባቸው ታላላቅ ቪላዎች በተጨማሪ በርካታ እንስሳት ያሉት የግሉ Zoo ነበረው። በተለይም በግቢው ውስጥ ብዙ ጉማሬዎች ያሉት መለስተኛ ሐይቅ ይገኝ ነበር።

በሌላ በኩል ፓብሎ ኢስኮባር በከተማዋ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ድሆችን ሕይወት ለመቀየር የSocial Service ፕሮጀክት መዘርጋቱ ተመዝግቧል። በዚህ ፕሮጀክት አማካኝነትም ለብዙ ድሆች የመኖሪያ ቤቶችን አሰርቷል። ልጆቻቸው የሚማሩበትንም ትምህርት ቤት ከፍቶላቸዋል። በዚህም የተነሳ በ1982 የከተማዋ ህዝብ የፓርላማ አባል እንዲሆን መርጦት ነበር። ከከተማዋ ድሆች መካከል አንዳንዶቹ እስከ ዛሬ ድረስ "ፓብሎ ቅዱስ ሰው ነበር" ይሉታል።

ከዚህ በተጨማሪም ፓብሎ ኢስኮባር Atheltico Nacional የተሰኘውን የሜድሊን ከተማ ታዋቂ የእግር ኳስ ቡድን በገንዘቡ ይደግፍ ነበር። ይህ ቡድን በ1989 የላቲን አሜሪካ ክለቦች ዋንጫ (Copa Libertadors) አሸናፊ ለመሆን የበቃ ነው።
-----
አፈንዲ ሙተቂ
ጥቅምት 13/2013 ተጻፈ።

@wegoch
@wegoch
@paappii
#የመኖር አካፋይ ፣ የመ ፤ ሞ ፣ ት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል ዘጠኝ)
(ሜሪ ፈለቀ)

ፍርሃት ልቤን ከደረቴ ጎትቶ ሊያስወጣት ታገለኝ። ሳይታወቀኝ ዓይኔን ከድኜ እግሬን ሰብስቤ ጉልበቴን አቅፌ ጥቅልል አልኩ። ጎንጥ በፊት ለፊቴ መጥቶ ጉልበቴን ያቀፍኩበትን እጄን አምባር ማሰሪያው ጋር ያዝ ሲያደርገኝ ዘለልኩ። ሰውነቴ በሙሉ እየተንቀጠቀጠ ነበር። በሌላኛው እጁ ጀርባዬን እንደልጅ አሸት አሸት አደረገኝ እና ወደጆሮዬ ጠጋ ብሎ

«እትይ ይቅርታ ሊጠይቆት ነው የመጣው! እኔ እዚህ ቆሜ ማን አባቱ ምን ያደርገኛል ብለው ነው የሚፈሩት?» ያለኝ መርበትበቴ አናቴ ላይ ወጥቶ የሰማሁት የቅዠት ድምፅ ይሁን ወይም ያለው ነገር ከነጭራሹ የገባኝ ይሁን እንጃ ብቻ የተናገረበት ድምፅ እና ጀርባዬን ከላይ ወደታች እያሸ የሚያባብለኝ እጁ አላውቅም በአፌ ልትወጣ ጉሮሮዬጋ እየደረሰች የምትመለስ ልቤን በቀስታ ወደቦታዋ መለሳት። በቀስታ ዓይኔን ገልጬ ሰውነቴን ዘና ለማድረግ እየሞከርኩ እየሆነ ያለውን ማጤን ጀመርኩ። እንግዳው ሰው በእኔ አልጋ እና በበሩ መሃል ያለ ቦታ ላይ ቆሞ አንዴ እኔን አንዴ ጎንጥን ያያል። ይሄኔ ነው ከደበደቡኝ ሰዎች መሃል አንዱ መሆኑ የገባኝ እንጂ የዛን እለት ምሽት ፊታቸውን በስርዓት የማይበት እድል ስላልነበረኝ ላውቀው አልችልም ነበር። አይቼው የነበረ ቢሆንም እንኳን በዛሬው ሁናቴው ላስታውሰው አልችልም ነበር። ፍርሃቴ ትንሽ ገለል ሲልልኝ ፊቱ ‘ንፋሱ ተንፍሶ ህፃናት እየተቀባበሉ የተጫወቱበት ኳስ’ መስሎ መጨረማመቱን አየሁ። ግንባሩ ላይ ሁለት ትንንሽዬ ፕላስተር ተለጥፎበታል። ጎንጥን አየሁት። በዓይኑ ሰውየውን ወደ እኔ እንዲጠጋ አሳየው። በዓይኑ ገፈተረው ብል ይቀለኛል። ወደ እኔ እየተራመደ ሲጠጋ እያነከሰ መሆንኑን አስተዋልኩ።

«ይቅርታ!» አለኝ አጠገቤ ደርሶ መሬት መሬቱን እያየ። ጎንጥ የሆነ መልእክት በማስተላለፍ አይነት ጉሮሮውን ጠረገ።

«ይቅርታ አድርጊልኝ! አንቺ ላይ እጃችንን ማንሳት አልነበረብንም! በእኔም በጓደኛዬም ስም ይቅርታ እንድታደርጊልን ልለምንሽ ነው የመጣሁት!» ብሎ እሱም የሆነ መልእክት እንደማስተላለፍ ጎንጥን አየው። ጎንጥ ጭንቅላቱን በአወንታ ነገር ነቀነቀ።

«እሺ» ከማለት ውጪ ግራ የገባው ጭንቅላቴ መልስ አላቀበለኝም። እንደአመጣጡ ፊቱን አዙሮ እግሩን እየጎተተ ሲወጣ ጭንቅላቴ ያልተዘጋጀበትን ጥያቄ አፌ ጠየቀ

«ለምን? ለምንድንነበር ግን እንደዛ ያደረጋችሁት?» አልኩኝ። መለስ ብሎ እኔን ሳይሆን ጎንጥን አየው። እኔም ወደእሱ ዞርኩ።

«የተጠየቅከውን መልስ!» አለው እንደትእዛዝ

«እህቴን …… ፍሪታን ስለቀማሽኝ። ተናድጄ ነበር። በፀባይ ላናግርሽ ስራሽ ቦታ ድረስ ብመጣም አላገጥሽብኝ። እኔ አቅሜ ጉልበቴ ብቻ ነው። አንቺ የገንዘብ አቅም አለሽ ፣ በአንድ ፉጨት ያልሽውን የሚፈጽሙልሽ ቁልፍ ሰዎች አሉሽ፣ ፖሊሶቹ በእጅሽ ናቸው፣  በዛ ላይ ጉልበትም መሳሪያም አለሽ! ........ በእህቴ ገላ አንቺ ገንዘብሽን ስታካብቺ አንጀቴ እየተቃጠለ ዝም ከማለት ውጪ ምንም ማድረግ አልቻልኩም ነበር። ባለፈው ሳምንት አደጋ ደርሶብሽ ምንም እንደማታስታውሺ ስሰማ ደስ አለኝ። (ቀና ብሎ ጎንጥን አይቶ ቀጠለ) እየተከታተልኩሽ ነበር። » ብሎኝ ትከሻውን ሰበቀ። ምንም እንደማላስታውስ ካወቀ የነገረኝ ነገር እንደማይገባኝ እንዴት ጠፋው? ቀና ብዬ የአልጋውን ራስጌ ተደግፌ ተቀመጥኩ። ከምን ጀምሬ ምን እንደምጠይቀው ግራ ገባኝ። ከነአካቴው መጠየቁ ራሱ ልክ ይሆን አላውቅም! የተናገረው ነገር ውስጥ ምንም ለልክ የቀረበ ድርጊት መች አለ? አሰላስዬ ሳልወስን አፌ ቀደመኝ።

« እህትህን? ምን አድርጌ ነው የነጠቅኩህ? በእህቴ ገላ ያልከኝ እህትህ ምንድነው የምትሰራው? እንዴት ነው እኔ በእህትህ ….. (እሱ ያለውን መድገም ዘገነነኝ) እየተከታተልከኝ ከነበር ምንም እንደማላስታውስ የሰማኸው እውነት መሆኑን ማረጋገጥ አይከብድህም መቼም? » አልኩኝ ፍርሃቴ ድምጥማጡ ጠፍቶ። እሱ አሁንም በማስፈቀድ አይነት ጎንጥን አየው። በቁመት ከጎንጥ ጋር ተቀራራቢ ናቸው። ጎንጥም ግዙፍ ዓይነት ወንድ ቢሆንም ደብዳቢዬ ግን የበለጠ ጡንቻው የተወጣጠረ እና ደረቱ የተነፋፋ ነገር ነው። እጅ በእጅ ቢያያዙ ማንም ሰው የሚያሲዘው በደብዳቢዬ ጡንቻ ነው። ታዲያ ጎንጥ ምን ቢያደርገው ወይስ ምንስ ቢለው ነው ይሄን የሚያክል ሰውዬ እንዲህ የሚንበጨበጨው? የተነፈሰ ባሎኒ ኳስ ካስመሰለው በኋላ እንኳን እዚህ ድረስ መጥቶ ይቅርታ እንዲጠይቀኝ ያስደረገው ያልገባኝ ነገር ምን ተከውኖ ነው?

«እናንተ ቤት ስትሪፐር ናት! (እንደማፈርም እንደማዘንም የቀላቀለው ስሜት ድምጹን ወሮታል። ያለኝ ነገር እንዳልገባኝ ሲያውቅ አሁንም ጎንጥን ዞሮ አየው። ጎንጥ በአይኑ <ቀጥል> እንደማለት ነዳው።) አንድ እህቴ ናት ያውም ታናሼ! ልጠብቃት ይገባ ነበር። ማታ ማታ ሆቴል ውስጥ ሪሴፕሽንነት ስራ አገኘሁ ስትለኝ እንኳን <አይሆንም አንቺ አርፈሽ ተማሪ። እኔ አኖርሻለሁ> ብያት ነበር። እንቢ ብላ ስራውን መጀመሯን ነገረችኝ። የምትሰራበትን ቦታ ልትነግረኝ አለመፈለጓ ስለከነከነኝ የሆነ ቀን ተከተልኳት እና እናንተ ክለብ ደረስኩ። (ለሰከንዶች ዝም አለ። የሆነ የሚቀጥለውን ለመናገር ጉልበት እንደሚሰበስብ ያለ ዝምታ) በአይኔ እንኳን ጫን ብዬ ላያት የምሳሳላት እህቴ ስራዋ እቤታችሁ ለሚመጡ ነውረኛ ባለስልጣናት እና ባለሃብቶች እርቃኗን እየደነሰች ማስደሰት መሆኑን አየሁ።» ብሎ ሆነ ብሎ ይመስለኛል ፊቴ ላይ አተኮረ። መደበቅ ያልቻልኩት ድንጋጤ እና መደናገር ፊቴ ላይ ተተረማመሰ። እሰራ የነበረው ስራ ፅድቅ ያለበት አለመሆኑን ምንም በማያስታውስ ወና ጭንቅላቴ እንኳን መገመት ከባድ አልነበረም። ሴትን ልጅ ራቁት እያስጨፈሩ ገንዘብ ማግኘት ግን ሌላ ደረጃ ብልግና መሰለኝ። ከዳዊት ጋር ቀን የሄድኩኝ እለት ያየሁት …… ቤቱ ውስጥ የነበሩት የተለያዩ ክፍሎች…….. ክፍሎቹ ውስጥ የነበሩት ሶፋው መሃል የተንጣለሉት አልጋ የመሰሉ መሃከላቸው ላይ የቆመ ብረት ያለባቸው ሰፊ ክብ መድረኮች ……. መድረክ ነገሩ ላይ አለመልበስ ለብሳ እንቅልፍ ወስዷት የነበረችው በጡት ማስያዣ እና በፓንት የነበረችው ቆንጅዬ ልጅ ……. አንድ በአንድ ከነገረኝ ጋር ላዛምድ ሞከርኩ። ልጅቷ ስታየኝ እየተደነባበረች  «አሁኑኑ ተጣጥቤ ፏ እላለሁ! ይቅርታ»  ብላኝ የነበረው ይሄን ልትሰራ ነበር? እሷው ልጅ ትሆን እንዴ እህቱ?

ጭንቅላቴ ውስጥ የሚተረማመሱትን ጥያቄዎች ሁሉ መጠየቅ ቢያምረኝም የሰውየው ሁኔታ ለመጠየቅ የሚጋብዝ አይደለም። ተገድዶ ቆመ እንጂ በጣም እንደሚጠላኝ ያስታውቃል።

«አሁን ላይ ሆኜ ……ምን አድርጌ እንደነበር ወይም ለምን እንዳደረግኩ የማውቀው ነገር የለም። ምንም ይሁን ብቻ እህትህንም አንተንም ስለበደልኳችሁ ነገር በጣም ይቅርታ! ባለፈው ህይወቴ በጣም ክፉ፣ እግዜአብሄርን የማልፈራ ጨካኝ ፣ ሀጢያትንም ወንጀልንም የምደፍር ሴት እንደነበርኩ ቀስ በቀስ እያወቅኩ ነው። የእኔ ዛሬ ሌላ ሴት መሆን ወይም ምንም አለማስታወስ የደረሰብህን በደል እንደማይሽረው አውቃለሁ። በቃ ግን በጣም ይቅርታ አድርግልኝ ከማለት ውጪ ማድረግ የምችለው የለም።» አልኩት ከልቤ። ምንም እንዳልተዋጠለት ያስታውቃል። <አሁንስ መሄድ እችላለሁ?> በሚል አስተያየት ጎንጥን አየው። የጎንጥን ፈቃድ በምልክት ሲያገኝ ወጥቶ ሄደ።
በትክክልም ክፉ ሴት ነበርኩ ማለት ነው። የሚያዩኝ ሰዎች ዓይን ውስጥ ለሞላው ጥላቻ እና ፍርሃት ምክንያት ከክፉነቴ ውጪ ሌላ ሰበብ የለም። ባለፉት ቀናት ሁሉ የምሰማውን ድርጊቴን ምክንያት እያጋባሁ <እንዲህ ስለሆነ ሊሆን ይችላል ይሄን ያደረግኩት> እያልኩ ድርጊቴን በሰበብ እየደገፍኩ ራሴን ይቅር ለማለት ፣ ያለፍኩትን ጥፋት ለመካስ፣ በንሰሃ ተመልሼ የበደልኳቸውን በመልካም ስራ ልዋጅ ……… አውጠንጥኜ ነበር። የትኛውን ሀጢያቴን ከምን ጀምሬ ነው ይቅር የምለው? ማን ያውቃል ከዚህ የባሰም ፀያፍ ነገር ሰርቼ ይሆናል።

«ጎንጥ?» አልኩት ሰውየው ከወጣም በኋላ እዛው በቆመበት የነበረውን ጎንጥን

«አቤት እትይ?»

«ህገ-ወጥ አይደለም በሴቶች መነገድ? ያለው በሙሉ እውነቱን ይመስልሃል? መቼም ህግ መንግስት ባለበት ሃገር እንዲህ አይነት ነገር ስሰራ አንድ እንኳን ለህግ የሚያቀርበኝ ሰው ጠፍቶ ነው? ወይስ ህገ-ወጥ አይደለም?»

«አላውቅም እትይ! ስለነገርየውም ሰምቼ አላውቅ!»

«ነውረኛ ሴት ነበርኩ አይደል? አንተም አውቀህ እየደበቅከኝ እንጂ ብዙ የሰማኸው እና የምታውቀው ነውር አለኝ አይደል? ንገረኝ እስኪ ምን ዓይነት ሴት እንደነበርኩ እያወቅክ አሁንም ድረስ ለምን ትጠብቀኛለህ? ለአንተም ለተናኜም ቢሆን ክፉ ሴት እንደነበርኩ ግልፅ ነው። እንዴት ነው በደሌን ረስታችሁ ከጎኔ የቆማችሁት? እስኪ ንገረኝ አንተንስ ምን ቀምቼህ ይሆን? »

«እትይ ደክሞዎታል ትንሽ ይረፉ ግድ የለም!»

«አንቱ አትበለኝ ማለት አይሰማህም?» በማን እንደተናደድኩ አላውቅም ግን እየተቆጣሁ ነው።

«ይሁን! ይሰማኛል! አንቺ እሎታለሁ። ግን እንደው እትይ በማያስታውሱት ነገር መብሰክሰኩ ምንም ፋይዳ የለውኮ! …….»

«አንቱ አትበለኝ! አንቱ የሚባለው የሚከበር ሰው ነው። አንቱ የሚባለው ክብርን ለመግለፅ ነው። ለየትኛው ክብሬ ነው አንቱ የምትለኝ?» አሁንም እየተቆጣሁ እና እየጮህኩ ነው። እየተቆጣሁ ያለሁበት ምክንያትም እየተቆጣሁ ያለሁትም ሰው የቁጣዬ መንስኤ አለመሆናቸውን ባውቅም ልቆጣጠረው ግን አልቻልኩም። አልጋው ጫፍ ላይ በአንድ ጎኑ ተቀምጦ በግንባሩ እያየኝ እኔ ከምናገርበት ድምፅ በተቃራኒ በእርጋታ እና በለሆሳስ

«እትይ ማንም የነበሩ ቢሆን አለቃዬ ነበሩ! ኖትም! አለቃን አንቱ ማለት ያደግኩ የጎለመስኩበት ስርዓት ነው። ተው ካሉኝ ካስከፋዎት እተዋለሁ። ግን ከበሬታዬን  የተውኩ እንዳይመስልብኝ!»

«አዎ ተው!» አልኩኝ ስናገር በነበረበት ቁጣ

«እሺ እተዋለሁ!» አባባሉ የተረጋጋ ነገር ....... የተከፋ ሳይሆን ለእኔ ያዘነ ዓይነት ነው። ለምን እሱ ላይ እየተናደድኩ እንዳለሁ አላውቅም። የሚያውቀውን ሁሉ አልነገረኝም ብዬ ስላመንኩ? ጭርሱኑ አብልጦ ሊጠላኝ ሲገባ አብልጦ ስለተንከባከበኝ? ወይስ የክፋቴን ልኬት በሱ ጥላቻ ልክ መመዘን ፈልጌ? ከሁሉ ከሁሉ ሚዛኔ እሱ እንዲሆን ለምን ፈለግኩስ?  ለደቂቃ ዝም ማለቴን ተከትሎ እንደቅድሙ ጀርባዬን በቀስታ ወደላይ እና ወደታች ማሸት ጀመረ። ውስጤ እየጎፈላ የነበረ ንዴቴ እየበረደ በምትኩ ሀዘን እና ተስፋ መቁረጥ ተተካ። የፈለግኩት ማልቀስ ነበር።

« እንዴት አገኘሃቸው? ፖሊስ እንኳን ፈልጎ ያላገኛቸውን አንተ እንዴት አገኘሃቸው?» አልኩት ድንገት

«ፖሊስ አልፈለጋቸውም። ያልተፈለገ ወንጀለኛ እንዴት ይገኛል? መድሃንያለም ብቻ በሚያውቀው ምክንያት ፖሊሶቹ ይሄን ጉዳይ መንካት አልፈለጉም። እንደው እትይ ልቤ ሲነግረኝ የተኮሰቦትንም ሰው መፈለጉን እርም ብለው ትተውታል።»

«እነሱ እንዴት አላገኟቸውም አይደለም ያልኩህ አንተ እንዴት አገኘሃቸው ነው ያልኩት። ደግሞ አሁንም አንቱ ማለትህን ተው!» አልኩት በደከመው ለዛ

«መንገዱ ምን ያደርጋል እትይ? ዋናው መዳረሻውም አይደል? እንዴት እንዳገኘሁት ዝርዝሩ ምን ይፈይዳል? ዋናው መገኘቱም አይደል?»

«ለእኔ ዝርዝሩ ይረባኛል! ማወቅ እፈልጋለሁ። አውቀህ ነው የምትጠመው?» አልኩት መልሼ እየተቆጣሁ።

«ካሉ መልካም ….. ይቅር ይበሉኝ  ካልሽ ይሁን! የሰው ፊት አየሁ!» ብሎኝ ይቀጥላል ብዬ ስጠብቅ ልክ የጠየቅኩትን የመለሰ ይመስል ዝም አለ።

«ምን ማለት ነው?»
«እንዴት አገኘኻቸው? አይደልም ጥያቄ …. ዎ …ሽ ? <የሰው ፊት አይቼ!> ነው መልሱ! ከሰው ፊት ቆምኩ!» አለ መልሶ። ከሰው ፊት መቆም ወይም የሰው ፊት ማየት ሀሳቡ የደበደቡኝን ሰዎች ከማግኘት ጋር የሚያያዝበት ገመድ በግልፅ ባይገባኝም እሱ ሲለው ደስ የሚል ነገር እንዳልነበረ ለማወቅ አልተቸገርኩም። ቃላቶቹን እየረገጣቸው ባለመደሰት ነው ያወራው።

«የማንን ፊት ነው ያየኸው? ማን ፊት ነው የቆምከው?» እያልኩት በጭንቅላቴ ውስጥ ድንበር ላበጅለት የማልችለው ሀሳብ ይጓዛል። ጎንጥ ራሱ ማን ነው? ፊቱን አይቶት ወይም ፊቱ ቆሞ ከመኪና ታርጋቸው ውጪ ስለማንነታቸው ምንም ፍንጭ ያልነበራቸውን ደብዳቢዎቼን ያስገኘለት ማነው? ለሰከንድ ክፉ ሀሳብ ሽው አለ። ጎንጥ ራሱ ነኝ ያለኝን ሰው ባይሆንስ?


                                         ………………….  ይቀጥላል   …………………………

@wegoch
@wegoch
@paappii
#የመኖር አካፋይ ፣ የመ ፤ ሞ ፣ ት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል አስር)
(ሜሪ ፈለቀ)


«ንገረኛ? የማንን ፊት ነው ያየኸው?»

«የሚያውቋቸው  እ የምታውቂያቸው ሰዎች አይደሉም!! ከራሴ ያለፈ ህይወት ጋር እንጂ ካንቺ ጋር የሚያያዙ ሰዎች አይደሉም!»

«ንገረኛ ልወቃቸው? አሁንኮ ከእኔ ህይወት ጋርም የሚያገናኛቸው ድርጊት ኖረ አይደል?»

«እትይ አያስጨንቁኝ ስለራሴ ማውራት አልፈልግም!» ካለ በኋላ አንቱ ማለቱ ሲታወሰው «አይ እንግዲህ! እትይ ሱሪ ባንገት አያድርጉብኝ ቀስ ብዬ ልልመደው!» አለ እጁን አየር ላይ እየወረወረ። የሆነች ጥርጣሬ ልቤ ውስጥ ተሰነቀረች። ቅሬታ ያቀፈች ትንሽዬ ጥርጣሬ …… መከፋት ያዘለች ትንሽዬ ጥርጣሬ …… በእንባ የዳመነ ዓይኔን ያስከተለ ትንሽዬ ጥርጣሬ ……. የገባው መሰለኝ አልጋው ጠርዝ ላይ እየተቀመጠ ድምፁን ዝግ አድርጎ

«እትይ ጠረጠሩኝ እንዴ?» ሲለኝ በትክክል የጠረጠርኩት ምን እንደሆነ ጠፋኝ! ቅሬታዬ ማን መሆኑን አለማወቄ እንጂ ልቤን በየትኛውም ጠርዝ ብበረብረው ይጎዳኛል የሚል የጤፍ ፍሬ የምታክል ጥርጣሬ አጣሁ። እንዴት ነው ማን መሆኑን የማያውቁትን ሰው በዚህ ልክ ማመን የሚቻለው?

«አላውቅም! አትቀየመኝ ጎንጥ አላውቅም! …….. በየትኛውም አቅጣጫ ብዞር ካንተ ሌላ ፊቴን ላዞር የምችልበት ሰው የለኝም ፤ ብቸኛው የማልፈራበት ሰዓት አንተ አጠገቤ ስትሆን ብቻ ነው ፤ ያለቅዠት የምተኛው እንኳን አንተ እጆቼን ስትይዘኝ ነው። በዚህ ርቀት የተደገፍኩት ሰው ማን እንደሆነ አለማወቅ ……. » ሳልጨርስ ሀሳቤን ቀማኝ

«እትይ ያለፍኩትን መንገድ አለማወቅዎ የሚያውቁትን እኔን እንዴት ያጠፋብዎታል? (<እኔን > ሲል ደረቱን በቡጢ ነገር ደለቅ ደለቅ አደረገ።) ትናንት ምንም ዓይነት ሰው የነበርኩ ቢሆን እንዴት ዛሬ ላይ የሆንኩትን እኔን ይውጠዋል?» አለኝ ማባበል ባለው ድምፅ

ይሄ <ትናንት> የሚሉት ጦስ ይኸው ዛሬዬን መዞሩን አልተወም!! የሰው ልጅማ ትናንቱን ነው ብያችሁ አልነበር? ነው ግን?

ጎንጥ ዛሬ የማውቀው ፣ ልቤ ያለገደብ የተደገፈው ደግ ፣አማኝ ፣ ለሳምንታት ለሊቶቹን ጎኑን ሳያሳርፍ የሆስፒታል አልጋ ላይ አንገቱን ደፍቶ እጆቼን ይዞ የተኛው ፣ ጎንጥ ነው ወይስ የማላስታውሰው እና የማላውቀው ያለፈ ትናንቱ ውስጥ ያለው እሱነቱ? አያድርገው እና በማላውቀው ትናንቱ ክፉ ሰው የነበረ ቢሆን ዛሬ የሰጠኝን የደግነት ጥግ አጣፋበታለሁ? እሱ ለትናንቱ ክፋቴ ሳይሆን ለዛሬ መሸነፌ ህይወቱን አደጋ ላይ ጥሎ የደበደቡኝን ሰዎች ደብድቦልኝ የለ?

ትናንትማ የዛሬ ማንነታችን መንገድ እንጂ የእኛነታችን መገለጫ አይሆንም። ትናንት ማንነት ቢሆን የትናንት ትውስታ የሌለኝ እኔ ማንነት ላይኖረኝ አይደል? ትናንት ለዛሬ ማንነታችን መንገድ ነው!! እርግጥ መንገዱ ለዛሬ መዳረሻ የሚያዋጣው ምሰሶ እና ማገር ዛሬ ለቆምንበት እኛነት መሰረት ነው።

«ቃሌን እሰጥሻለሁ!! አቅሜ በፈቀደ ሁሉ እጠብቅሻለሁ!! በምችለው ሁሉ ማንም እንዳይጎዳሽ መድረስ ያለብኝ ጥግ ድረስ እደርሳለሁ። እትይ? እንዲያምኑ …. እንድታምኚኝ እፈልጋለሁ? እ? በአምላክ ስም እምልልሻለሁ አንቺን የሚጎዳ ነገር አላደርግም! እ?» እያንዳንዱን ዓረፍተ ነገር <አንቺ> ብሎ ለመጨረስ እየታገለ <እትይ> ማለቱ ፈገግ አስባለኝ።

«እንደማትጎዳኝ ልቤ ያምንሃልኮ …… አላውቅም! ምናልባት እኔ አንድም ነገሬ ሳይቀር ለትናንትም ለዛሬም እንዳመንኩህ ሁሉ ትናንትህን ልትነግረኝ እንድታምነኝ ፈልጌ ይሆናል። አላውቅም!»

«አሁን አይደለም! እትይ እባክዎ አያስጨንቁኝ! ጊዜው ሲሆን አወጋዎታለሁ!»

«እሺ!» ብቻ አልኩኝ። እንደቅድሙ ጀርባዬን እያሻሸ በዓይኖቹ ሌላ ቦታ ተጓዘ። ልቡም ዓይኑን እንደተከተለው ያስታውቃል።

«እትይ ካልከኝ ቀጥለህ አንቺ ልትለኝ አትችልም! በስሜ ጥራኝ ! ስሜን አትወደውም እንዴ ለምን ከበደህ?» ስለው እንደመባነን ነገር ብሎ

«ኸረ ይቅር ይበሎት!» ካለ በኋላ ራሱ ሳቀ …….. ብዙ ጊዜ አይስቅም! ከንፈሩን ለወጉ ሸሸት ያደርጋል እንጂ! ሲስቅ የሚያማምሩት ችምችም ያሉ ጥርሶቹ ብቻ አይደለም የሚስቁት ዓይኑም ፣ ግንባሩም ፣ ጉንጩም ይስቃሉ። እያየሁት እንደሆነ ሲያውቅ ጥርሱን ከድኖ በከንፈሩ ብቻ ፈገገ።

«ሜ - ላ - ት » አለ የሆነ አጠገቡ ያለሁትን እኔን ሳይሆን እሩቅ ያለ ሰው አስታውሶ የሚጠራ በሚመስል ድምፅ

«አየህ ? አያንቅህም ወይ ትን አይልህም! ደግሞ አፍህ ላይ ያምራል!» ብዬው ሸርተት ብዬ ተኛሁ። እንደተለመደው ወንበሩን ወደ አልጋው ጠጋ አድርጎ ተቀምጦ ሲያበቃ እጄን ያዘኝ። መልእክቱ ዓይንሽን ከድነሽ ማረፍ ትችያለሽ ነው። እንደማመስገን ነገር የያዘኝን እጁን ጨበጥ ሳደርገው ጥርሱን ነክሶ ፊቱን ቀጨም አደረገ።

«ውይይ ይቅርታ ረስቼው ነው» ብዬ እጄን አስለቀቅኩ። ከንፈሩን አሽሽቶ መልሶ እጄን ያዘኝ። እንደደከመው ያስታውቃል። ምናልባት እንቅልፉን ከተኛ ብዙ ሰዓታት አልፈውት ይሆናል። ምናልባት እህል የአፉን ደጃፍ ካለፈ ቆይቷል። ምናልባት ያበጡት እጆቹ እና የበለዘ አይኑ እየቆጠቆጠው ይሆናል። ለመጀመሪያ ጊዜ ከፀጉሩ ጀምሮ ፍትፍት አድርጌ በዓይኔ አስተውለው ጀመር። እያደገ ያለ ያልተበጠረ ጥቁር ፀጉሩ ፊት ላይ በጎን በኩል ሆነ ብሎ ያቀለመው የሚመስል ሽበት አለው። ግንባሩ ላይ ያሉት የሚኮሳተርባቸው መስመሮች ሞገስ ነገር ሆነውታል ልበል? ዓይኖቹ ብቻቸውን መሳቅም መኮሳተርም ያውቁበታል። ዓይኖቼን በዓይኖቹ ሲቀልብብኝ አፍንጫ ፣ ከንፈር ፣ አገጩን ዘልዬ ትከሻው ላይ ደረስኩ። ትከሻው ስፋቱ ተጣበው ቢቀመጡ ….. ሁለት በአንደኛው ጎን ሁለት በሌላኛው ጎን አድርጎ  አራት ህፃናት ያሰፍራል። ደረቱ ቀብረር አድርጎ አስር ኪሎ ፍትግ ገብስ ያሰጣል። ክንዱ ……… ክንዱ እየደማ ነው! የለበሰውን ግራጫማ እጅጌ ያለው ቲሸርት እያረጠበው ነው።

«እየደማህ እኮ ነው! » ብዬ ጮህኩ። ዓይኔን ተከትሎ እየደማ ያለ ክንዱን አየት አደረገ እና ህመሙን ሊደብቀኝ እንደፈለገ በሚያቃጥርበት ሁኔታ

« እ ትንሽዬ ቁስል ናት!» ብሎ በእጁ ደገፍ አድርጎት ተነሳ። ከዓይኖቼ ርቆ ደሙን ሊጠራርግ እንደሆነ ገብቶኛል።

«አሳየኝ?  ትንሽዬ አይሆንም አሳየኝ !» ብዬ ስጮክበት የለበሰውን ቲሸርት በቀስታ በአንድ እጁ በኩል ወደላይ አውልቆት ተቀመጠ። ቁስሉ በነጭ ፋሻ ታሽጓል። እኔጋ ከመምጣቱ በፊት ሀኪም ቤት ሆዶ የነበረ ሰውዬ ነው ይሄን ሁሉ ሰዓት ህመሙን ውጦ አጠገቤ የተቀመጠው? ወይስ ስቃዩን አላስተዋልኩለትም?  የታሸገበትን አልፎ ነው ደሙ ልብሱን የነካው።

«በምንድነው የተመታኸው?» አልኩት

«ስለት ነው! » ካለ በኋላ ፊቴን አስተውሎት «መድሃንያለም በሚያውቀው ብዙ አይደለም! ከላይ ነው ጨረፍ ያደረገኝ! ደሙ ዝም ብሎ ሲያዳምቅ ነው!» አለኝ።

«እሺ የታሸገበትን ይቀይሩልህ እና እቤት ሄደህ እረፍ! ተናኜን ላካት!» አልኩት አልሰማኝም! ወጥቶ ቁስሉን አሳክሞ ተመልሶ መጣ ወደቤት ግን አልሄደም!



                                                 *****
ቁስሌ አገግሞ ከሆስፒታል ከወጣሁ በኋላ ፤ ጎንጥ አንቱ እና አንቺ ማምታታት ካቆመ በኋላ ፤ እቤት እንደገባሁ ሰፋፊ ጅንሶች እና ብረታ ብረት የበዛባቸው ልብሶቼን ካቃጠልኩ በኋላ ፣ ብዙ ነገሮችን እንደአዲስ ከተማርኩ በኋላ ፤ እናት እና ወንድሜን ለማግኘት ብዙ ያልተሳካ ፍለጋ ካደረግኩ በኋላ ፣ አባን ደግሜ አጊንቼ ጉልበታቸውን ተደግፌ ከተመከርኩ በኋላ ፣ ብዙ ቀናት ዳዊት ደውሎ ከተልመጠመብኝ በኋላ …….. ስልኬ ጠራ!

«ሜላት ነሽ? አስካለ ደውዪላት ብላኝ ነው።»

«አስካለ? አስካለ?»

«እናትሽ !» አባባሏ መገረም ነበረው። ከተቀመጥኩበት ዘልዬ ተነሳሁ።

«የት ልምጣ?» አልኩኝ ሳላስበው።

«ህም! እቤት ገብታለች። ዛሬ ነገ ሳትዪ መጥተሽ እያት! ጥሩ ሁኔታ ላይ አይደለችም!» ያለችኝ ቤቱን እንደማውቀው እርግጠኛ ሆና ነው።

«እባክሽ የቤቱን አድራሻ ንገሪኝ?» አልኳት ገና ሳትጠይቀኝ እንዴት የእናቴን ቤት እንደረሳሁት ማብራራት እያደከመኝ። አልጠየቀችኝም። እጅግ ግርምት ባለበት አነጋገር ሰፈሩን ነገረችኝ።

«ስትደርሺ ደውዪልኝ እና እመራሻለሁ!» ብላ ስልኩን ዘጋችው። ለተወሰነ ደቂቃ በቆምኩበት ደርቄ ቆየሁ። እየቆየሁ እንደመባነን ነገር አደረገኝ እና ልብሴን መቀያየር ጀመርኩ። ከታች ቀይሬ ከላይ ሳልቀይር ወደሳሎን ተመልሼ ጎንጥን መጣራት ጀመርኩ።

«በትክክል እናትሽ ባይሆኑስ?» ብሎ ያላሰብኩትን ጥርጣሬ አቀበለኝ የተደወለልኝን ስልክ ስነግረው

«ማረጋገጥ የምንችልበት ብቸኛ መንገድ ስንሄድ ብቻ አይደል?» አልኩት። ተመልሼ የቀረኝን ልብስ ቀያይሬ ስመለስ እሱ መኪናውን ከጊቢ እያወጣ ነበር።

በስልክ እየተመራን ደረስን። ልቤ እየዘለለች በአፌ ልትወጣብኝ ታገለችኝ። በስልክ ያናገረችኝ ሴት በሩ ላይ ጠብቃን እየመራችን ወደጊቢው ስንዘልቅ ጎንጥ እጄን ያዝ አድርጎ ከፊቴ ቀደመ። በአንድ እጁ አንድ እጄን እንደያዘ ሌላኛውን እጁን ወደ ወገቡ አካባቢ ሲሰድ ዓይኔ እጁን ተከትሎ የጨበጠው ነገር ላይ አረፈ። በደረበው ጃኬት ስር ሽጉጥ ይዟል። መጮህ ቃጣኝ ነገር እና የሆነ ድምፅ አወጣሁ።የያዘውን እጄን ሳላውቅ መነጨቅኩት።  ሴትየዋ ስትዞር ደንግጬ ቆምኩ። ከዚህ በኋላ ልቤን እንዲህ የሚያስደልቃት የጎንጤ ሽጉጥ ይሁን እናቴን ማግኘት አልገባኝም። እግሬን ብርክ ያዘው። ጎንጥ መልሶ እጄን ቀለበብኝ እና ወደጆሮዬ ጠጋ ብሎ

«ምን እንደሚገጥመን አናውቅም! መሳሪያ ቢገጥመኝ በባዶ እጄ ልጠብቅሽ አልችልም!! » አለኝ ድምፁ ቁጣ ነገር አለው። የሆነ <ዋጥ አድርጊያት> የሚል ዓይነት ቁጣ …… ምርጫ ነበረኝ? ማሰቢያ ጊዜ አልሰጠኝም። ድንጋጤዬን ዋጥ አድርጌ ተከተልኩት። ሴትየዋ እየመራች የሆነ ድክም ያለ ባለሁለት ክፍል ቤት አስገባችን!!

                  ………. ይቀጥላል ………..

@wegoch
@wegoch
@paappii
#የመኖር አካፋይ ፣ የመ ፤ ሞ ፣ ት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል አስራ አንድ)
(ሜሪ ፈለቀ)

ጭንቅላቷ ከአልጋ ልብሱ ወጥቶ ባይታይ ኖሮ የደቀቀ ሰውነቷ ከአልጋው ተጣብቆ አልጋው ላይ ሰው የተኛ አይመስልም ነበር። ፊቷ አጥንቱ ቢገጥም መልኳን የት እንደማውቀው ለማስታወስ አልተቸገርኩም። ስልኬ ውስጥ ካገኘኋቸው ፎቶዎች ውስጥ አይቻታለሁ። እናቴ ትሆናለች ብዬ ጠርጥሬም ነበር። አጠገቧ ከተቀመጥኩ ደቂቃዎች ቢያልፉም ከጥቂት የ<ደህና ነሽ?> ቃላት ልውውጥ ውጪ ከምን ጀምሬ ምን እንደምነግራት ወይም ምን እንደምጠይቃት ግራ ገብቶኝ ተጎለትኩ። እሷም እንደእኔ ግራ ገብቷት ይሆን ወይም ስትናገር እያማጠች በመከራ በመሆኑ ደክሟት አላውቅም ዝም ብላለች። በዝምታዋ መሃል እንባዋ ወደጆሮዋ ፈሰሰ። የእኔም እንባ የሚወርድበት ሰበብ እየጠበቀ ያለ ይመስል ተንደረደረ።

«ልጄ ማሪኝ!?» አለችኝ እንባዋን ዋጥ እያደረገች። ላቅፋት እፈልጋለሁ። ወይም እንድታቅፈኝ እፈልጋለሁ። ልጅ እናቱ ጉያ ሽሽግ ብሎ ፍቅር እንደሚምገው እቅፏ ውስጥ ገብቼ ይሄ ብርዳሙ ልቤን ላሞቀው እፈልጋለሁ። ባልገባኝ ምክንያት ልቤ ባዳነት ነው የሚሰማው ……….  እሩቅነት ….. ማን ብዬ ነበር ይሆን የምጠራት? እማዬ? እማ? እናቴ? እትዬ? አስካለ? አቅፋኝ ታውቅ ይሆን እንደዛ? የተፈጠረውን በአጭሩ ነገርኳት።

«ምህረት የምትጠይቂኝ ለምን እንደሆነ አላውቅም!! አንቺንም አላውቅም! ያሳለፍነው ምን እንደሆነም አላውቅም! ራሴንም አላውቅም! ምንም ይሁን ይቅር ብዬሻለሁ። የበደልሽኝ ነገር ካለ እሱን አትንገሪኝ ይቅር። አብረን ያሳለፍነውን ጥሩ ጊዜ እና ፍቅር ብቻ ንገሪኝ። ማወቅ ያለብኝን ራሴን ብቻ ንገሪኝ።» አልኳት አባ ያሉኝን አስታውሼ። <ለበቀል ነው የኖርሽው ልጄ በተሰጠሽ አዲስ ህይወት ለፍቅር ኑሪ! > ብለውኝ ነበር። የቱን እንደምትነግረኝ ጨንቋት ይሆን ዝም አለች ለብዙ ደቂቃ ከዛ መልሳ ማልቀስ ጀመረች።

« አሁን ብሞትም አይቆጨኝ! » አለች ደግሞ ደስ የተሰኘች ነገር መስላ። ግራ አጋባችኝ። ምኑ ነው ደስ ያላት? የእኔ ምንም አለማስታወስ? ወይስ ይቅር ብዬሻለሁ ማለቴ? ግራ እንደገባኝ ስታይ
«የእኔ አበባ ብታስታውሺውም ከሚያንፅሽ የሚያፈርስሽ ታሪክ ይበዛናል። ያለፈውን ለማስታወስ የምታጠፊውን ግዜ አዲስ ህይወት ለመገንባት ብትጠቀሚበት ነው የሚጠቅምሽ የሚመስለኝ። ካለፈው መንገድሽ የሚጠቅምሽን ብቻ አንስተሽ ተጓዥ» ስትለኝ ሳላውቀው ተናደድኩ

«ለምንድነው ማናችሁም የማይገባችሁ? የሚጠቅመኝንም የማይጠቅመኝንም የማስታውሰው ምንም የለምኮ ነው የምልሽ! የገዛ እናቴን አላስታወስኩሽም እኮ ነው የምልሽ! ወንድሜ የት እንዳለ አላውቅም! የት እንደማገኘውም አላውቅም! የማውቀው የነገሩኝን ነው የነገሩን ደግሞ የሰይጣን ቁራጭ እንደነበርኩ ነው። ቢያንስ ያን የሆንኩበትን ምክንያት ማወቅ የለብኝም? ራሴን እንኳን ከማን እንደምጠብቅ ጠላቶቼን እና ወዳጆቼን ለይቼ የማላውቅ ሰው ነኝ። ሌላው ይቅር ለእናቴ ምን አይነት ልጇ እንደነበርኩ ማወቅ እፈልጋለሁ። » ስጮህባት እጇን ሰዳ እንባዬን ጠረገችው።

«ለእናትሽ መተኪያ የሌለሽ ጀግና ልጇ ነበርሽ» አለችኝ ተረጋግታ! እኔ እየጮህኩ እሷ ፈገግ የምትልበት ምክንያት አልገባኝም። ልክ አባ ያለፈውን መርሳቴን ሲያውቁ እንደሆኑት ነው እየሆነች ያለችው። « ልጅም ሆነሽ እንደአባትሽ ጀብደኛ ነበርሽ» አለችኝ ያለፈውን ዘመን ልጓም ስባ በምናቧ ወደዛሬ እያመጣች ፈገግ ብላ

«እኔ ነኝ ሜላት ያልኩሽ! አባትሽ የመጀመሪያ ልጁ  እሱን የሚተካ ወንድ እንዲሆን ይመኝ ስለነበር <አምሳል> ነው የሚልሽ የነበረው። (አባቴ በህይወት አለ? ብዬ ልጠይቃት ፈለግኩ እና ወሬውን ብታቋርጥብኝስ ብዬ ፈርቼ ዝም አልኩ።) መቼም እንዴት ይሳሳልሽ እንደነበር ምንም ቃል አይገልፀውም! የትም ቦታ ሲሄድ ትከሻው ላይ ሰቅሎሽ ነበር የሚሄደው። ከአራት አመት በኋላ ወንድምሽን ብንወልድም አባትሽ ከወንድምሽ ይልቅ ትኩረቱ አንቺ ነበርሽ። እያደግሽ እንደእኩዮችሽ እንጀራ ማስፋት ከመማር ይልቅ የአባትሽን መሳሪያ መወልወል እና ፈትቶ መግጠም ነበር የሚያስደስትሽ። አድገሽ ምን መሆን ነው የምትፈልጊ ስትባዪ <ሽፍታ> ነበር የምትዪው (ፈገግ አለች እና የሽፍታ ትርጉም እንዳልገባኝ ጠርጥራ መሰለኝ ቀጠለች።) አባትሽ ወታደር ነበር። ከውትድርና ከተመለሰ በኋላ ቀዬአችን በማይረባ የይገባኛል ሽኩቻ ስትታመስ አባትሽ ራሱን የቀዬው ጠባቂ አድርጎ ሾመ። ዋጋ እንደሚያስከፍለው ብነግረውም አልሰማኝ። የእርሱ ቢጤ ደጋፊዎቹን አስከትሎ ጫካ ገብቶ ሸፈተ።»

«አባቴ ያጨስ ነበር?» አልኳት

«ከጊዜ በኋላ ያመጣው ዓመል እንጂ አጫሽስ አልነበረም።» ካለችኝ በኋላ በጥርጣሬ ዓይን አተኩራ አየችኝ።
«የወታደር ልብስ ቀለም ያለው የሲጋራ መለኮሻ እቤቴ ካዝና ውስጥ አጊንቼ ነበር። የሆነ ብልጭ የሚል ምስል ጭንቅላቴ ውስጥ ሽው ይላል። የሆነ ደም የነካው እጅ ያንን የሲጋራ መለኮሻ ይዞ …… ፊቱ ወይም የቀረው ሰውነቱ አይመጣልኝም። ፍርጥም ያለ ሰፊ በደም የራሰ ጠይም እጁ ብቻ ነው የሚታየኝ።» እያልኳት ጭንቅላቷን በአወንታ እየነቀነቀች ፊቷ ላይ የነበረው ደስታ በአንዴ ድፍርስርስ ብሎ ሃዘን ይንጣት ጀመር። ማስረዳት የማልችለው ስሜት አባቴ እንደሞተ ነገረኝ። ያ ቀን እጁ …..የሚታየኝ ቀን ….. አባቴን ያየሁበት የመጨረሻ ቀን መሆኑን ገመትኩ። 

«ሞቷል አይደል? ምን ሆኖ ነው የሞተው? ሰው ነው የገደለው? ሲሞት አጠገቡ ነበርኩ አይደል? የሚታየኝ ምስል የሞተ ቀን ነው አይደል?» ቃላት ከአፏ ማውጣት አቅቷት በጭንቅላቷ ንቅናቄ ብቻ አዎ አለችኝ ከእንባዋ ግብግብ እየገጠመች። ዝም አልኩ። ዶክተሩ የሲጋራ መለኮሻ ላይተሩን ፣ ሽጉጡን ፣ ንቅሳቴን ሳይ ሽው የሚልብኝን አንድ የሰው እግር እና ጨለማ ክፍል ፣ ፎቶውን ሳይ የተሰማኝን የሳር እርጥበት ስነግረው

«ምንም እንኳን ያለፈ ትውስታሽን ብታጪ ጭንቅላታችን ያሳለፍነውን ከባድ ጊዜያት ወይም ትሮውማ የፈጠሩብንን አጋጣሚዎች በተለየ መዝግቦ የመያዝ አጋጣሚው ሰፊ ነው። ከገጠመኙጋ የሚያያዙ ነገሮች ስታዪ ጭንቅላትሽም ሰውነትሽም ሪአክት ያደርጋል። ምናልባት በተለየ ያስታወስሻቸው ነገሮች እንደእነዚህ ያሉ ክስተቶች ይሆናሉ።» ብሎኝ ነበር። ያ ቀን ፣ ያ የሲጋራ መለኮሻ ላይተር ፣ የሚታየኝ የአባቴ እጅ …….. የመራራዋ ሜላት ጥንስስ ሊሆን እንደሚችል አሰብኩ። ስለዛ ቀን እንድትነግረኝ ፈለግኩ ግን ደግሞም ፈራሁ። ክፉ ትውስታዎቼ ሁሉ ግልብጥ ብለው የሚመጡብኝ መሰለኝ። ትናንቴን መፈለጌ ውስጥ እስከዛሬ ያላሰብኩበት ነገር ሰውነቴን አደነዘዘኝ።

ትናንቴን ሳገኘው ተመልሼ የትናንትናዋን ሜላት ብሆንስ? ከትውስታዬጋ ማንነቴም ተመልሶ ቢመጣስ? ያቺን ሴት ተመልሼ መሆን እንደማልፈልግ እርግጠኛ ነኝ። ግንሳ ያቺን ሴት ያደረጉኝን መንገዶቼን ሳውቅ ቂሜ ፣ መከፋቴ፣ ንዴቴ ፣ መራርነቴ ፣ ሁሉም ስሜቶች ከትውስታው ጋር መጥተው ይወሩኝ እና ያቺን ሜላት እንቢ ብዬ ላመልጣት ባልችልስ?

«ማነው የገደለው?» አልኳት ሳላስበው ውስጤ የሆነ የተለየ ስሜት እያፈነው። ምናልባት ያቺ አባ የነገሩኝ በቀለኛዋ ሜላት ተሸፍና እንጂ አልጠፋች ይሆናል።

« የእኔ አበባ አባትሽን የገደሉትን ሰዎች አድገሽ አንድ በአንድ ተበቅለሻቸዋል። አታስታውሺው ይሄ ይቅርብሽ!! » አለችኝ በልመና።
«አባቴ ሲሞት ስንት ዓመቴ ነበር?» አልኳት ውስጤን የአባቴን መልክ የማስታወስ ከፍተኛ ፍላጎት እያተራመሰው። ወዲያው ቀጥዬ «አባቴ ምን ይመስል ነበር?»
2024/09/22 08:37:23
Back to Top
HTML Embed Code: