Telegram Web Link
-ልብሷን አወላልቃ በጡት ማሲያዣ ብቻ ሆና አልጋዋ ላይ ስትወጣ አልጋው ላይ ያለበሰቺው ነጭ ላስቲክ ተንኮሻኮሽ-

"እዚህ ጋር ሽናብኝ"...ወደ አንገቷ እየጠቆመቺኝ...

"መሲ ደግሞ ኩላሊቴን እንደሚያመኝ እያወቅሽ እንደዚህ አይነት ቀልድ ትቀልጂያለሽ??...ቶል ሸንቼ ልምጣና እንደባለፈው..."

"አይ የትም አትሂድ!" 🥺 ብላ ታፋዬን በእጇ ይዛ ወደላይ እያየቺኝ መስለምለም ጀመረች...

:ስታሳዝን:

|አምስት ደቂቃ - ጭቅጭቅ|

|አስር ደቂቃ - ጭቅጭቅ|

|አስራምስት ደቂቃ - ጭቅጭቅ|

ሃያ...

ሃያ አምስት...

"እኔ እኮ ግራ ገባኝ... ሰው እንዴት ሽንት ላዬ ላይ ሽኑብኝ ይላል?"

ሠላሣ

"በእትዬ ሞት"

"እምቢ"....የእምቢዬ ጥንካሬ እየሟሸሸ ሲሄድ ይታወቀኛል...

ሠላሣ አምስት

"እሺ እቃ ባበላሽስ?...አልጋሽስ?"

"ላስቲኩ አለ ችግር የለም!"

"እሺ ሽንቴ ቢሸትሽስ??"

"አይሸተኝም!"

"እሺ ቢዬቃጥልሽስ?"

"አያቃጥለኝም!"

"እሺ..."

"አያ...!"

"እሺ..."

"አያ...!"

እሽሽሽሽሽሽሽሽሽ

ሸናሁባት...

ሁለታችንም ድምፅ አወጣን...እኔ የግልግል እሷ የእርካታ

•••

9, የዛን ቀን 🩸

ከመሲ ጋር እንደወጣሁ ሰፈር ሁሌ ወደምቀመጥባት ድንጋይ (ስፓት) ሄድኩ። የህፃን መአት ስፍር ብሎባት ነበር... ሌላ ጊዜ ቢሆን ጠጠር አንስቼ ወደየአቅጣጫው እነዳቸው ነበር...ዛሬ ግን ባዶነት እየተሰማኝ ስለሆነ ከነሱ ጋር ቁጭ ብሎ መጫወት አማረኝ።

"ና...ና እኔ ስመጣ የታባህ ነው ምትሮጠው...ስይዝህ እጨምቅሃለሁ..."

ሁሉም እኔን ሲያዩ ከሮጡበት ተሰበሰቡ።

"ና ቁጭበል...ሁልህም ና...አንቺም ነይ..."

አጠገቤ ኩልኩል አሉ...ሞቀኝ...

"እጅህን ምን ሆነህ ነው??" አንዱ ፈላ በምላጭ ሸረካክቼ ጠባሳ በጠባሳ ወዳረኩት እጄ እየጠቆመ...

"ባለፈው እነ አብዲ ቤት ዲሽ ስሰራ ቆርቆሮ ቆርጦኝ"

"አይዞህ እሺ"🥺 ያቀፍኳት ህፃን ነች እንደዛ የምትለኝ...

እንባዬ ክብልል አለ...ፊቴን ሞቀኝ...

እንባዬን እንዳያዩብኝ ብድግ አልኩ...

"እናንተ ያቺ ስንቴ አይደለችም እንዴ???"

"አዎ ስንቴ ናት" ከህፃኖቹ ትንሽ ተለቅ ያለው...

"እየጠራችህ ነው ቡቡ"...ራሱ ህፃኑ...

"እሺ ግን እሷ ጋር ከመሔዴ በፊት የሆነ ጨዋታ መጫወት የሚፈልግ ከእኔ ጋር..."

ትልቁ ልጅ 'እኔ እፈልጋለሁ' አለኝ...

"እሺ ና በጆሮህ ምን እንደምታደርግ ልንገርህ"

🗣️👂"የሚገርም ፊልም ልጋብዝህ ነው..."

°°°

9.1,ከምትጠልቀው ፀሐይ ስር... 🥀⚱️

ሁለታችን ቆመን ነበር...

"ኧ ስንቴ ፈለግሺኝ?"

"አዎ ቡቡ አንድ ነገር ላማክርህ ነበር..."

"እሺ ንገሪኝ"

"ፊትህ ጠቋቁሯል... ያቺ የተሸረፈቺው ጥርስህም ሐኪም ቤት አልሄድ ብለህ በልዛ ቀረች አ?..."

"ስንቴ... እነግርሃለሁ ያልሺኝን ንገሪኝና ልሂድ እንጂ...መንገድ ላይ አቁመሽ ከሳህ ወፈርክ ትዪኛለሽ እንዴ??"

"እሺ እሺ ቡቡ..."

"በይ"

"... ቡቡዬ ሃገሬ ልገባ ነው"

"እንዴ ለምን!?" ትንሽ ደንገጥ ብያለሁ

" ... በቃኝ ይሄ ከተማ፡ ይኸው ስምንት አመት ከሃገሬ ወጥቼ እዚህ ከመጣሁ አንድ የኔ የምለው ነገር የለኝም... መማሰን ብቻ!"

"እሱማ አዎ።" የምለው ጠፋብኝ...

"መሄድ ካሰብኩ ስድስት ወር ሆኖኛል... ያንተ ነገር አልሆንልሽ ብሎኝ ነው እስካሁን የቆየሁት፣... አሁን ግን ግቢያችሁ ካለቺው ቀዩዋ ወፍራም ሴትዮ ጋር የጀመራችሁትን እንዳለ መቅደስ (ሰራተኛችን) ነግራኛለች።

"ኧረ እኔ እና መሲ ምንም..."

"ይገባኛል እኮ ቡቡዬ..." ማልቀስ ጀመረች... ስታለቅስ አንጀት ታንሰፈስፋለች እንባዋ እንደሰው እንባ ተከታትሎ ሳይሆን 'ሚወርደው እንደ ቧንቧ ውሃ ዥቅ ብሎ ነው 'ሚፈሰው

... "አንተ የከተማ ልጅ ነህ... እኔ ደግሞ ለቂጤ ፓንት እንኳን የሌለኝ የገጠር ልጅ..."

"ኧረ እንደዛ አይደለ..."

"እየወቀስኩህ አይደለም...ለምን ለአይንህ አልሞላሁምም አልወጣኝም...እንዲያው ነገሩን ነው..."...

እንባዋ ጭራሽ እየጨመረ መጥቷል...

"...አረቄ መሸጥ እንዴት ያስጠላል መሰለህ... ስንት ባለጌ ያገናኝሃል መሰለህ... እኔ ግን ሁሉንም ቻልኩት... ሰካራም እየተፋብኝ እኔ ትዝ የሚለኝ ጄርካን አንጠልጥዬ ውሃ ልቀዳ ስምጥ እዛች ድንጋይህ ጋር ቁጭ ብለህ ፀጉርህን ስትጠመልል ሳይህ የሚሰማኝ ደስታ ነው... እዚህ አንተን ላይ ስመጣ ህፃናቱ 'ፕላክፖርድ' ፊት ይሉኛል...እንግሊዝ አፍ ባላውቅም ንቅሳቴ ላይ እየቀለዱ እንደሆነ አልጠፋኝም... ቢሆንም አንተን የኑሩ ሱቅ በር ላይ ከነ አምሐ ጋር ስለኳስ ስትከራከር ሳይህ ሀዘኔ ሁሉ ይተናል..."

አሁንም እያለቀሰች ነው... እኔ በድን ሆኛለሁ...

"...ጋሽ ከበደን አወቅካቸው... ከዛ ከጥበቃ ቤቱ እልፍ ብሎ ትልቅ ግቢ ያላችው ሰውዬ? እንደውም ሁለት አይሱዙ አላቸው..."

ጭንቅላቴን ነቅንቄ አዎ አልኳት...

"አዎ እሳቸው... ልጆቼን ሁሉ ውጪ ልኬ በስተርጅና ብቸኝነት እፍግ አደረገኝ... ላግባሽና እያስተማርኩሽ እሺ ካልሽ ልጆችም ወልደሺልኝ እንኑር ብለውኝ ነበር... እኔ ግን ያንተ ነገር አለብኝ ቡቡዬ... እንዴት ብዬ እሺ ልበል? ተመላልሰው ተመላልሰው ተስፋ ሲቆርጡ በዛው ቀሩ። "

እንባዋ ቢቆምም ንፍጧ እንደውሃ እየወረደ አስሬ እንፍፍፍ ያስብላታል...

"እና መቼለት ነው አባቴ ደወለልኝ... 'አሁን እንዲህ አይንሽ እንደራበኝ ብሞት አባቴ አባቴ ብልሽ ታለቅሺያለሽ ወይ?' አለኝ። በጀ አልል ስለው በሰው ታሟል አስብሎ አስደወለልኝ... ይሄ ሁሉ ሲሆን ይሄን ሰፈር ጥሎ መሔድ ያቃተኝ አንተን ስለምወድህ ነው"

አሁን በተራዬ እኔ ማልቀስ ጀመርኩ...

"... ቅድም መቅደስ ስላንተና ስለተከራያችሁ ስትነግረኝ ቆረጠልኝ እንጂ አልደነገጥኩም... ውስጤ ቀድሞ ተስፋ ቆርጦ ነበር... ድሮስ የከተማው ልጅ እኔን የገጠሯን ለቂጧ እንኳን ፓንት የሌላትን..."

-ቀጭን የፍልፈል ድምፅ የመሰለ ሳቅ ሁለታችንም ጆሮ ውስጥ ጥልቅ አለ-

ተያየን... ማንም የለም አጠገባችን...ደንግጠናል... ሰይጣን ነው እንዴ??

ግራ ተጋብተን እንደተፋጠጥን ግን... ድንገት የሆነ ነገር ከቀሚሷ ስር በእግሮቿ መሐል አልፎ እግሬ አውጪኝ ማለት ጀመረ። ትንሽ እንደሮጠ የሆነ የአፈር ክምር ጋር ቆመ... አይኖቼን ጠራርጌ አየሁት... የቅድሙ ህፃን ነው።

"...ቡቡዬ ይመችሽ ምርጥ ፊልም ነው የጋበዝሺኝ። በስማም ጥግብ እስክል ነው የከለምኩት...ቡቡ ... "

ልቤ ከደረቴ ተንሸራቶ ወርዶ ሆዴ ውስጥ ገብቶ ሲመታ ተሰማኝ። ጢንንንንንንንንንን አለብኝ... መተንፈስ ጠፋብኝ....

ቀና ብዬ አየኋት... ቅድም አይኗ ውስጥ የነበረው ፍቅር በመዘግነን ስሜት ተቀይሯል... ሐዘኑ ግን አሁንም አለ... ቆሞ የነበረው እንባዋ እንደ አዲስ ፏ ብሎ ወረደ... መሸት እያለ ስለነበር የንግድ ዳሩ አፕል ብርሃን በእንባዋ ሲንፀባረቅ ደም እያለቀሰች መስሎ ታየኝ። ልይዛት ፈለግኩ...ፈራሁ። ድንገት ግን ዞር ብላ ፈትለክ አለች...

"ስንቴ!" ብዬ ተከተልኳት...

ሮጠች ... ተከተልኳት...ሮጠች...ተከተልኳት... ደረስኩባት...ደረስኩባት... ደረስኩባት.... ገጭ!!!

ስንቴ ወደላይ ብድግ አለች.. ከዛ ደግሞ... ወደታች ተምዘግዝጋ ፍርጥ!! የፍንዳታው ድምፅ ከየት እንደመጣ አላውቅም... ስንቴ ግን አይደለችም... ስንቴ እኮ ፍንዳታ አይደለችም... ጨዋ ናት።
የጣት ማስገቢያው የተገነጠለ ጥቁር ሲሊፐር ፊት ለፊቴ አረፈ... አየሁት...ሳቄ መጣ.... ከትከት ብዬ መሳቅ ጀመርኩ.... ሃሃሃሃሃ....ሳቄን ሳላቋርጥ ብድግ አደረኩት... አገላብጬ አየሁት...የተገነጠለው ጫፍ ላይ መርፌ ቁልፍ አለ፣... ስንቴ ተንሸራታ መኪና ውጥ እንዳትገባ ቆልፎ ያልያዘ መርፌ ቁልፍ... ድምፄን ከፍ አድርጌ ሳቄን ቀጠልኩ... ከትከት....

"ኡኡኡኡ..." ጩኸት ከሳቄ አቋረጠኝ... ወደጩኸቱ አቅጣጫ ስዞር ከነጭ መኪና ውስጥ ወጥቶ እየጮኸ ወደእኔ የሚመጣ ሰውዬ ታየኝ። የእንጀራ አባቴ ነው። ይሄን ሰውዬ ሲጮህ ሰምቼው አላውቅም... ጩኸቱ ያስቃል.... ከትክት .... ሃሃሃሃ.... አስፋልቱ ላይ ተንጋልዬ መሳቅ ጀመርኩ.... አባቴ ይጮሃል... ሰው አንድ ሁለት እያለ እየተሰበሰበ ነው... በሳቄም በጩኸቱም በግርግሩም መሐል ከአባቴ መኪና ውስጥ ክራር ተምዘግዝጎ ይመጣል... ካሳ ተሰማ እየዘፈነ ይከተላል...

🎶...ውብዬ ውብዬ ...

አንቺ መንገደኛ...ቀረሁ ተነጥዬ...🎶

-----

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Girum
|•

በተፈጥሮህ ሴቶች አይን የማትገባ ድውይ ነህ። ድንገት ብትገባ እንኳን ጠዋት ጫማህን ስታስጠርግ ጮርናቄ የምታቀርብልህ የውብዳር ወይ ደግሞ ከግንባር ያለግራ እግር የተመለሰቺው ምክትል አስር አለቃ አይንዬ አይን ውስጥ ነው። አንተ ደግሞ እነሱን አትፈልግም... ልብህ ፑል አጫዋቿ ሊሊ ወይም ኮፒ ቤት የምትሰራው መአዛ ጋር ነው የሚያሮጥህ።

[ካንተም ብሶ ትመርጣለህ!]

ግና(😂) ከተወሰኑ የብቸኝነት ወራት በኋላ (በላጤ ካላንደር ከዘጠኝ የሎሽን ብልቃጥ በኋላ) ያለችህን ድፍረት አሰባስበህ የሃምሳ ብር ሻይ ጠጥተህ መቶ ሃምሳ ብር ቲፕ የምታደርጋትን አስተናጋጅ ትጠይቃታለህ። ውለታ የሚሰራ ሰው ፊት እያሳየች(የምርም ውለታ እየሰራችልህ ነው 😂) 'እሺ ግን እ'ራት ብቻ ነው' ትልሃለች... 'አዎ ራጉኤልን' ብለህ እጇን ትመታላትና የታምራት ደስታን ዘፈን እያፏጨህ ወደቤትህ ትሄዳለህ።

[🎶...የ•ማ•ይ•ረ•ሳ•ው ጌታ-የ•ማ•ይ•ረ•ሳ•ው ጌታዬ...🎶]

-ከቀጠሮህ ቀን ቀደም ብሎ: ቅድመ ዝግጅት

°ሃሳቧን እንደምታስቀይራት እርግጠኛ ሆነህ ከአንገት በታች ጸጉር የሚባል ነገር ሳታስቀር ድምጥማጡን አጥፍተሃል።

°'የፍቅር ኬሚስትሪ' መፅሐፍን ሶስት ጊዜ አንብበሃል...ኖትም አውጥተህ ይዘሃል

°ቴክኖ ስልክህን በጫት ደንበኛህ አይፎን ሰባት ቀይረሃታል...

°ተረከዝህ ጋር የተቀደደቺው አንድ ለእናቷ ካልሲህን ተመሳሳይ ክር ሁለት ፌርማታ ተጉዘህ ገዝተህ ሰፍተሃል...

°ከግራጁዌሽን በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥርስህን ቦርሸሃል( ለዛሬ ጥርስ መቦረሽ የአፍ ጠረን አያመጣም)

-የቀጠሮህ ቀን ጠዋት: ደስጋት(ደስታ + ስጋት)

°እንዳቅሚቲ ዘንጠሃል ፣ አክስ ዲኦደራንትህን ብብትህ እና ብሽሽትህ ውስጥ ነስንሰሃል ፣ ጸጉርህን በጄል ፈርዘሃል ፣ የክትህን ለብሰሃል ፣ ቆዳ ጫማህን ገድግደሃል ። ፏ!👌🏿

°ምንም እንዳልረሳህ ደብል ቼክ አድርገህ ትወጣለህ።

-የቀጠሮ ቦታ: ዴት ናይት

ተጠብቃ ተጠብቃ ከች ትላለች ፤ ጨብጣ እየሳመችህ "አስቆየውህ እንዴ" በአፍህ ጉንጯን እየሳምክ በአፍንጫህ ከአንገቷ ጠረኗን እየሳብክ "ኧረ እንደውም...ከመጣው አራት ሰአትም አልሞላኝ አሁን ነው የመጣሁት!" ትላታለህ

መጀመሪያ አካባቢ ፍርሃት ሽባ ቢያደርግህም ፣ እየቆየ ሲመጣ ሪላክስ ማድረግ ትጀምራለህ ፣ ኧረ እንደውም ቀልድ እየፈጣጠርክ ታስቃታለህ። አስተያየቷ ደስ ይልሃል ፣ 'አዪዪዪ ዛሬ ይቺ ልጅ ወደቤቷ የምትሄድም አይመስለኝ' ትላለህ(ኦፍኮርስ በውስጥህ)።

ራት በአሪፉ ያልቃል

ዲዘርትም እንደዛው

ቅምቀማም እንደዛው

"እና ምንድነው ሃሳብሽ??"

"ከጠበኩት በላይ በጣም ደስ ብለኸኛል...ግን በመጀመሪያ ዴት ምንም ላላደርግ የራሴ ህግ አለኝ"

"እና ሌላም ዴት ይኖረናል እያልሺኝ ነው??" ሰፍሳፋነትህ ለራስህም ያስደነግጥሃል። 🤦🏾‍♂️

"እንዴ ታዲያስ!? በጣም ደስ የሚል ምሽት ነው ያሳለፍኩት።"

"እሺ" ትላለህ ሁለመናህ ቦግ ብሎ።

"በል መሽቶብኝ ጎዳና እንዳላድር ቶሎ ሸኘኝ" ትልህና ብድግ ብላችሁ ወደቤቷ ወክ ትጀምራላችሁ...

ከሬስቶራንቱ ወጥታችሁ ቤቷ እስክትደርሱ ሰባት ጊዜ አስቀሃታል፣ ሁለት ጊዜ እጅህን ነክታሃለች ፣ የውዲ አለን ፊልም ላይ እንዳየኸው ኮትህን ልትደርብላት አስበህ ከውስጥ ቀዳዳ መሆኑ ትዝ ሲልህ ሃሳብህን ቀይረሃል ፣ ሒሏ ተሰብሮ ቦርሳዋ ውስጥ ያለውን ጫማ ስትቀይር የተሰበረውን ሂል ይዘህላታል...[ ከሞላ ጎደል ስኬታማ ምሽት!]

-የግቢዋ በር ላይ: ልሳማት አልሳማት ከራስ ጋር ግብግብ

"በል እሺ ደህና እደር" ✋🏿 እጇን ብቻ ዘርግታልህ ወደቤቷ ትራመዳለች...

"እንትን"

"ጠራኸኝ?"

"እእእእ ጫማሽን ረስተሻል" እጅህ ላይ ያለውን ታኮው የተሰበረ ጫማ ትዘረጋላታለህ...

"ውይ" ትልና ተመልሳ መጥታ ትቀበልሃለች... ከዛ ቀስ ብላ ወደ ጉንጭህ ትንጠራራ እና በስሱ 'እምጱዋ'...

🎶...ደስ ደስ እያለኝ ነው እንጃ ደስ እያለኝ ነው...🎶

-ማታ ቤትህ: የደስታ ባህር ውስጥ ዋና...

ደስታ እንቅልፍ ስላሳጣህ አጠገብህ ያለውን ሬዲዮ ትከፍታለህ...

"ጤና ይስጥልኝ አድማጫችን የፍቅር ክሊኒኮች ነን ማን እንበል"

"እገሊት ነኝ"

የደዋዩዋን ስም ስትሰማ ድንግጥ ትላለህ...እሷ ትሆን? ትልና ትስቃለህ 😂😂 አንተ ሰውዬ ልታፈቅር ነው እንዴ? ሁሉ ሰው እሷን እየመሰለህ እኮ ነው።

"እሺ እገሊት ከየት አካባቢ ነው??"

"ከእንትን"

"ምንድን ነበር ህመምሽ እገሊት"

"በመጀመሪያ ዮኒዬ በጣም ነው የምወድህ በጣም ነው የማደንቅህ"

"ቴንክዩ አድማጫችን...አሁን ወደህመምሽ ቀጥይ"

"እኔ ችግሬ ኤክሴን መርሳት አለመቻሌ ነው። የተለያየነው በኔ ጥፋት ስለሆነ ራሴን ይቅር ማለት አልቻልኩም በዛ ላይ ፍቅሩ አልወጣልኝም...እሱ ግን ከነመፈጠሬ ረስቶኛል...በኔ ጥፋት ስለተለያየን ራሴን ለመቅጣት ብዬ ከሊጌ በታች ከሆኑ ሰዎች ጋር ዴት እወጣለሁ። እነሱን ከኤክሴ ጋር በማነጻጸር ያጣሁትን ነገር እያሰብኩ ቤት ገብቼ ስቅስቅ ብዬ አለቅሳለሁ...ራሴን ቶርቸር ማድረጌ ትንሽም ቢሆን ፀፀቴን ያስታግስልኛል...የሚገርምህ ዮኒዬ ዛሬ ራሱ ከዴት ተመልሼ ነው የምደውልላችሁ... የዛሬው ደግሞ ይለያል ብታይ ፍፁም የኤክሴ ተቃራኒ ነው... መልኩ የማይስብ ቁመቱ ቁመት አስተኔ...ቀልዶ የሚያስለቅስ... በቃ ምኑም የማይስብ ሰውዬ ነው...የምሰራበት ካፌ በመጣ ቁጥር የሚጥልልኝ ቲፕ ተጠራቅሞ የቤት ኪራዬን ስለሚችልልኝ እምቢ ብለው ደንግጦ በዛው እንዳይቀር ብዬም ቅድም ባልኩህ ምክንያትም እሺ ብዬው ዛሬ ራት በላን... ሰአቱ አላልፍልሽ ብሎኝ ምግቤን ራሱ በስርዓት አልበላሁትም... ቶሎ ቤቴ እንድደርስ ስጣደፍ ኤክሴ ለልደቴ የሰጠኝን ውድ ጫማ ሰብሬው አረፍኩ...እሱ ጫማ ብቸኛ የኤክሴ ማስታወሻ ነው ብታይ ዮኒዬ...እና ስጣደፍ ረስቼው ልገባ ስል ጠርቶ እንኪ ሲለኝ በደስታ ብዛት ሳላስበው ሳምኩት... ብታይ ከሳምኩት በኋላ እንዴት ሽምቅቅ እንዳልኩ...እና ብቻ ዮኒዬ ይሄንን ነገር እንድተው ከተቻለም ኤክሴን መልሼ እጄ እንዳስገባ ምን ትመክሩኛላችሁ?..."

•ስቱዲዮ ውስጥ የአራት ሰው ጫጫታ ይሰማል•

"የሚገርም ነው እህታችን... የህክምና የመጀመሪያው ስቴፕ ህመምን አምኖ ወደሀኪም ቤት መሄድ ነው... ያንን ደግሞ አድርገሻል...ቀሪው የእኔ የዶ/ር ዮናስ እንዲሁም የባልደረባዬ የዶ/ር ግዛቸው ስራ ነው... እና እኛ የምንልሽ ምንድነው...ኤክስሽን አግኚው...አዋሪው...እሱ ጋር ስትሄጂ በተቻለሽ አቅም አጋላጭ ልብሶችን ልበሺ...ጠዋት ጠዋት ፀበል ጠጪ ከሰአት ደግሞ አንዱ ፓስተር ጋር እየሄድሽ ይፀለይልሽ... ዱአሽን ደግሞ እንዳትረሺ እሺ አድማጫችን... በተጨማሪ ደግሞ ዮጋ ግድ ነው...ራስሽን ተንከባከቢ ፎከስ ኦን ዩርሰልፍ... በሐማስ ሲሸልስ ምናምን እየሄድሽ ችግርሽን ለአንድ ለሁለት ሳምንት እርሺ... ጆርናል ነገር ብትፅፊም አሪፍ ነው... አሮማቴራፒም አንድ አማራጭ ነው...ኤክስሽ ካንቺ ጋር መሆን አሻፈረኝ ካለ የቀረበት እሱ እንደሆነ ማሳየት አለብሽ... መሐል ቦሌ ላይ ጂ ፕላስ ፋይቭሽን ግትር... ከተማ ውስጥ አሉ የተባሉትን መኪናዎች ንድት...
ስራዬ አስተናጋጅ ነው አልነበር ያልሺኝ በቃ እንደውም ይሄንን ማድረግ እኮ ላንቺ ቀላል ነው ዘንድሮ የአስተናጋጅ ደሞዝ ከአንድ የፕሪሚየርሊግ ኳስ ተጫዋች ደሞዝ እኩል ነው። ከዛ በተጨማሪ ትሪት ዩርሰልፍ ቱ ኧ ናይስ ዲነር...ለብቻ ራት አይበላም ያለው ማነው?? አቅም ካለሽ ሆንግኮንግ ከሌለሽ ዱባይም ቢሆን እየሄድሽ ራስሽን ራት ጋብዢ... እየሰማሽን ነው እህታችን??"

"አዎ አዎ ዮኒዬ...ማለቴ ዶክተር ዮኒ" ቅቅቅቅ

"አዎ ጎበዝ...ያልንሽን ሁሉ ካደረግሽ ህመምሽ ሙሉ በሙሉ ነው ሚፈወሰው ከዛ በተጨማሪ እንደ ክኒን ነገርም እናዝልሻለን...የባልደረባችንን የዶ/ር ብርሐኔ ንጉሤ መፅሐፍ 'የፍቅር ኬሚስትሪ'ን አዘንልሻል...እሱን በቀን ሶስት ጊዜ ከምግብ በኋላ...እሺ አድማጫችን!??"

"እሺ ዮኒዬ በጣም ነው ማመሰግነው...እንዳላችሁኝ አደርጋለሁ... እሺ....እሺ...መልካም አዳር ለእናንተም"

°ስልኩ ይዘጋና ...ሰአት ስለደረሰ ዝግጅቱ ይጠናቀቃል°

ያንተ መተንፈስ የተጠናቀቀው ግን ገና ቅድም ነበር...😂😂

@getem
@getem
@paappii

#Girum
ሁለት ፡ ነጥብ
#ስርዓተነጥቦች 1

ጉሊት ነጋዴዋ የተበሳሱ ቲማቲሞች መርጣ እንድሸጥልኝ ስለጠየኳት ግራ ገብቷት ተፋጥጠናል። እኔ ኑሮዬን የማይመስል ነገር መሸመት አቁሜ ፤ እሷ እንከን ያለባቸውን ቲማቲሞች ከጤነኞቹ ጋር ሸውዳ መቀላቀል እንጂ፣ ተጠይቃ መሸጥ ላይ ልምድ ስላልነበራት። ዛሬ... እርማቸውን ፈላጊ ቢያገኙ፣ ትል የገጠባቸውን ቲማቲሞቿን በስስት አየቻቸው። የሷን ሀሳብና ሂሳብ ቸል ብዬ... አጎንብሼ ከቲማቲም መደቦቹ ውስጥ የተበሳሱትን እየለየሁ በጨምታራ ፌስታሌ ማስገር ጀመርኩ። ጎላቿ ጃንጥላዋን ዘርግታ ግድ እንደሌላት ሆና ታየኛለች።

ድንገት ከበስተጀርባዬ... ሞቅ ያለ የማለክለክ ድምጽ ሰምቼ ዞርኩ። አንድ ኑሮ ያፍተለተለው ጎልማሳ... ክምር ቄጠማ አዝሎ እየመጣ ነው። ሁለመናው የድካሙ ምስክር ነው። ገና እንዳየችው፣ ባለጉሊቷ ጃንጥላዋን ከበስተአናቷ ወደ ስር ዝቅ አድርጋ መደቧን በገሚስ ከለለችው።

ጎልማሳው በገዛ ላቡ ረስርሶ አጠገባችን እንደደረሰ... በድካም እያቃሰተ
"ቄጠማ ነበረሽ እንዴ?" አላት፤ በጃንጥላዋ በገሚስ የከለለችውን መደብ በዓይኖቹ እያሰሰ።
"ሞልቶ! ሊያውም ለምለም!" አለችው ፈገግ ብላ።
"አዬ እድሌ! ወይ እድሌ! እንደአህያ ልፋ ያለኝ ፍጡር! ድንገት ባይኖራት ብዬኮ... በሌለ አቅሜ... ልሳለምበት ከሄድኩት ከልደታ ቤተስኪያን ደጃፍ ድረስ ተሸክሜ መምጣቴ ነው... !"
እንባ አቅርሮ ወደላይ ቀና አለ
"ምነው መድኃኒዓለም? ካልሞትኩ አታሳርፈኝም ማለት ነው? ምነው ምነው? ደጃፌ ላይ እያለ... እንደአጋሰስ ከአገር ቂጥ ተሸክሜ መዛል አለብኝ? "

ቅርዝዝ ብሎ ወደ ጉሊት ሻጯ ዞረና...
"ድንገት አነሰ ካሉኝ ... አንቺ ጋር ተመልሼ ብመጣ አያልቅብኝም አይደል?" አላት በልምምጥ።

"ኧረ አያልቅም ብዙ ነው ያመጣሁት!" ግንባሯን ቋጥራ።

መልስ ሳይሰጣት እየተንፏቀቀ አልፎን ሄደ። መሄዱን አይታ ጃንጥላዋን መደቡን ከጋረደችበት ወደላይ ከፍ አደረገችው። ወዲያው መደቧን በፍጥነት አሰስኩ። ቄጠማ አልነበራትም!

"እንዴት የሌለሽን አለኝ ብለሽ፣ ምስኪን ለፍቶ አዳሪ ተስፋ ላይ ትቀልጃለሽ? ቆይ ተመልሶ ቢመጣስ?" በንዴት ቀና ብዬ ጮህኩ።

"ተመልሶ ቢመጣማ... አለቀ... ተሸጠ! እለዋለኋ!" በግድ የለሽነት ትከሻዋን አራገፈችብኝ...
ፈራኋት... !

ትበልጠኛለች...
እንደኔ መሰሎቿን አትሰበስብም!

ቲማቲሞቹን መምረጥ አቁሜ፣ ራሷ መርጣ እንደእግዜር እስክትሰጠኝ መጠበቅ ጀመርኩ...
ትበልጠኛለቻ...!
እንኳን የተበሳሳባትን፣ የሌላትንም ጭምር... አዋድዳ መሸጥ ታውቅበታለች ...

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Rediet aseffa
" ለካስ ፍቅር ለሁለት ፍቅር እየተሰጣጡ ሌላውን አለም ጆሮ ዳባ ልበስ ሚሉበት የስስታሞች አዙሪት ነው ። ቅፅበት ብቻ ሚታይበት የስሜት ጨዋታ . . . . . "

~  ~   ~   ~   ~    ~    ~    ~  ~  ~ ~    

(ቁስሉን የነኩበት አፍቃሪ )

በካሊድ አቅሉ

ትኩስ አፍቃሪዎች ፍቅራቸውን ያጋሉ መስሉዋቸው ለጋ ቁስልን በእንጨት ይሰዳሉ ።  ምናለ በአይን ቢያወሩ በልብ ቢደማመጡ አስራ ሁለት ሰው የያዘ ሚኒባስ ታክሲ ውስጥ ሚስቱን የፈታ ፣ ባልዋን የፈታች ፣ ባል የሞተባት ፤ ሚስት የሞተበት የተከዳ የተከዳች ይኖርበታል ብሎ ማሰብ እንዴት ይቸግራል ?

" ከአሁን ወዲህ እንዳትደውልልኝ ካንተ ጋር ያሳለፍኩት ግዜ ግዜዬን እንደገደልኩ ይሰማኛል "   መልዕክቱን ማመን አቅቶኝ ደጋግሜ ሳነበው ነው ለመሙላት አንድ ሰው ሚፈልግ ታክሲ ላይ እየተግተለተሉ ለሁለት ገብ ። " እንዴ አንድ ሰው እኮ ነው ሚይዘው " አልኩኝ ብሶቴን መተንፈሻ ሰበብ ፈልጌ የተቀመጥንበት ቦታ ሁለት ሆነው ሲመጡ አንድዋ ስልክ ተደውሎላት ስትወርድ ተመቻችተው ተቀመጡ ።

"ደከመሻ? "
አፍቃሪ በሚመስል ቅላፄ ሄዋኑን ያበረታል። የሄለንን ቴክስት ደግሜ ደግሜ አነባለው ከነሱ ፍትጊያ ለመሸሽ .  .  .  .

አንገትዋን ክንዱ ላይ አሳረፈች

ቁስሌ መጠዝጠዝ ጀመረኝ  (ህመም)

ፀጉሩን ማሻሻት ተቀጠለ . .  .

ቁስሌን ያደሙት ሳያንስ በህብረት ጨው ነሰነሱበት    (የፍቅረኞች ወንጀል)

" ለካስ ፍቅር ለሁለት ፍቅር እየተሰጣጡ ሌላውን አለም ጆሮ ዳባ ልበስ ሚሉበት የስስታሞች አዙሪት ነው ። ቅፅበት ብቻ ሚታይበት የስሜት ጨዋታ . . ."

ቅርፅ  ያለው ሳቅ  "ወደህነው"
ሁሌ እንከባከብሻለው ብልዋት ነው መሰለኝ ።

" እዚህ ትወርዳለህ? ችግር የለም ቤብ እኔ ቤት ገባለው ። "

ተስማምተው እንደመነሳት አለና ተመልሶ መቶ ስምዋት ወረደ ።

በፍቅር ህግ ግን እርስ በእርስ ፍቅር እየተሰጣጡ ሶስተኛ ወገንን አንቆ መግደል ይቻላል ?

ገነት ውስጥ እየተንጎማለሉ ነፍሴን ገሀነም ውስጥ አሽከረከርዋት . . .  .

" ኪያ በግዜ ቤት ግባ እኔ እንደገባው እደውልልሀለው "  ፌርማታው ደርሶ የወረደው ፍቅረኛዋ በእሺታ አንገቱን ነቀነቀ ።

ለመሰዋት እያንደረደረችው እንደሆነ እሱ  መች ገብቶት

እኔም ፈገግ አልኩና ወደ ውስጥ ለራሴ ቃል አሻገርኩ " እኛም እንዲህ ተብለን ነበር "
~   ~   ~   ~    ~   ~    ~   ~    ~    ~

@wegoch
@wegoch
@paappii
" የንፁህ ፍቅር ስጦታው ከስጋ አልፎ ነፍስ ላይ መገኘቱ ነው ። ወደታች ተራመድን ወደላይ የመንገዱ ማብቂያ መገናኘት ነው ። "

(ካሊድ አቅሉ)

~    ~   ~    ~     ~    ~     ~    ~    ~

ከሙዚቃ ቤቱ ዘፈን ተሻግሮ ጆሮዬን ጎበኘው ። ሞት ያጎላል አምናለው የተለመዱትን ሲያነሳ ለነገ አይልም ሳቅን ጨዋታን ጥርግ አርጎ በነበር መዝገብ ይከትበዋል ። አሊ ፊቱ ጠቁርዋል ያጣት እናቱን በሰበብ አስባብ ያስታውሳታል ።

እናቱ ለእሱ የአባትም ሚና የነበራት በሰው ማትተካ ለሙሉነቱ ምክንያት ለመጉደሉም ክፍተት ናት ። እናትና ልጅ በመንገዱ  ችብስ እየተጎራረሱ ሲሄዱ አይቶ ነው ትኩስ ቁስሉ የጠዘጠዘው ቁስል ሲያሳክክ ዳር ዳሩ ይነካል እንጂ ዘው ካሉበት ትርፉ መድማትና እንደ አዲስ ማገርሸት ነው ።  ለዛም ይመስላል አሊ ቶሎ መለስ አለና ቀልብን ለመግዛት ሞከረ ። የእናቱን ናፍቆት ግን በብርቱ እንዲያስታውስ ሁለተኛው አብይ ምክንያት ከሙዚቃ ቤቱ አልፎ ጆሮው የደረሰው የክብር ዶክተር ጥላሁን ገሰሰ ዜማ ነው ።   
" ሞት እንኳን ጨክኖ ወስዶ
         ከሚያስቀረው
ምናለ ደጋጉን ዳግመኛ ቢፈጥረው "

ይላል ጥሌ ደግ ወዳጆቹን አስቦ በመብሰልሰል  የእናቴ ቅርብ ወዳጅ ይመስል በቀብርዋ ላይ ተገኝቶ ከእንባው ጋር ሚያንጎራጉር . . .

" ለተራበው አጉራሽ ላጣው ሰው ደጋፊ
  ሲሆን ያሳዝናል እንደ አፈር እርጋፊ "

ጥሌ ይንገበገባል አምላኩን በእርጋታ በሰከነ መንፈስ ስማኝ ለምን ይላል ቀስ ያለ አስመስሎ አምላኩ ላይ በቀስታ ይጮሀል እንደዚህ እያለ  . . .

" የሰራ ለሀገሩ ያልሰራም ሰነፉ
ያስኬዳል መንገዱ ለሞት ሲሰለፉ
ሞት ምርጫን ባወቀው እንዴት በወደደው
ስንዴን ከንክርዳዱ ለይቶ ቢያስቀረው "

አሊ ከስንኞቹ ጋር ከፍ ዝቅ እያለ እንባ አርሶታል ። አስተናጋጅዋ መታ የማክያቶ ቢል አምጥታ አጠገብ ስታኖር ብንን አለና አመሰግናለው ብሎ እጁን ወደ ኪሱ ለሂሳብ ሰዶ ሶፍትም አብሮ እውጥቶ እንባውን ጠረገ ።

" አምላክ የለየን የኔን ብርታት ለመታዘብና እናቴን ከመናፈቅ ነው  ። ማንንም አማልክት ቢወድ የእናቴን ጫፍ አያደርሳቸውም ። ለዛም አይደል ጀነት (ገነት ) ከእናት እግር ስር ናት ሚባለው ለዚች ሰናፍጭ ለምታክል አለም እናቴን ቀማህኝ ብዬ ከሱ ጋር ለምን ክርክር ልግባ ?    ሰማይ ቤት በባህር እየጠበቀኝ ለዚች ማንክያ ለማትሞላ አለምማ ዶሴ አላስከፍትም ።  " የንፁህ ፍቅር ስጦታው ከስጋ አልፎ ነፍስ ላይ መገኘት ነው ። ወደታች ተራመድን ወደላይ የመንገዱ ማብቂያ መገናኘት ነው ። "

~   ~     ~    ~     ~   ~     ~    ~    ~
@kalidakelu

@wegoch
@wegoch
@paappii
ውድ የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች,

አዲሱን መተግበሪያችንን El-Test(ኤል ቴስ) መለቀቁን ስናበስር በደስታ ነው።

ተማሪዎች የኢትዮጵያን ብሄራዊ ፈተና የበለጠ እንዲለማመዱ የሚረዳ መተግበሪያ ለማዘጋጀት ባለፉት ጥቂት ወራት ሳትታክት ስንሰራ ቆይተናል።

መተግበሪያችን ለፈተና የምታጠኑበትን መንገድ በመቀየር እና የሚገባዎትን ነጥብ እንድታገኙ ያግዛል። ባለፉት ዓመታት የወጡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ፈተናዎችን በጊዜ ቆጣሪ ይዉሰዱ እና የደረሱበትን ደረጃ ይገምግሙ። ለእያንዳንዱ ምዕራፍ በእርስዎ ውጤቶች ላይ ትንታኔያዊ መረጃ(analytical data) እና ምክረ ሀሳችን ያግኙ። ለአጠቃቀም ቀላል በሆነ መተግባሪያ ላይ ምንም አይነት ማስታወቂያ ወይም ብቅ ባይ ባነሮች ሳይረበሹ ፈተና በወሰዱ ቁጥር ለውጦትን እንገመግማለን።

የእኛን መተግበሪያ በቀጥታ ከ App Store እና Google Play ማውረድ ይችላሉ።
https://eltestapp.com/el-test.apk
ለበለጠ መረጃ: https://eltestapp.com/ ይጎብኙ።
ስልክ፡ 0923678876 / 0921484549
E-mail: [email protected]
--------------   ሸበላው -----------_

part-1

   ሴቶች ይወዱኛል። በጣም ። ከአንገት በላይ መውደድ አይደለም ። ከልባቸው ካለኔ መኖር እንደማይችሉ አይነት ። ብዙ ሰዎች እንደ ፀጋ ሊያዩት ይችላሉ ። ከእኔ ውጪ ማለት ነው ። በመልኬ ብቻ አይደለም የሚወዱኝ ታዲያ ።በእርግጥ ቆንጆ ነኝ ። ልቅም ያልኩ ሸበላ ። አውቃለው ትንሽ ስሙ ይደብራል ። ወንድ ብሎ ቆንጆ ሲባል እመኑኝ ግን የኔ ይለያል። ሁሉም ሴቶች ሳያፈጡብኝ አያልፉም ። እንደውም አብዛኞቹ ያነባሉ ። ለምሳሌ ከእንቅልፌ እንደተነሳው ፊቴን ሳልታጠብ ፣ ልብሴን ሳልቀይር፣ አይን አሬ ተዝረክረኮ ፣ በባዶ እግሬ የሆነ ሰርግ ቤት በስህተት ብገባ እንኳን ሴቶቹ አይናቸውን ከእኔ ላይ መንቀል ያቅታቸዋል። "ወይኔ ሲያምር" ፣ "አዪውማ አንትና " ፣ "ግርማ ሞገሱን አየሽው ... ውይይ ፎቶ አንሺው በናትሽ ስልኬን አልያዝኩም" ምናምን ይባባላሉ። ወጣቶች ብቻ አይደሉም እኮ በየትኛው እድሜ ያሉ ሴቶች እኔን ሲያዩ ያቅበዘብዛቸዋል ። ህፃናት ማሳደጊያም ሄድኩ አረጋውያን መርጃ ሴቶች ይጠመጠሙብኛል። ሌላው ቢቀር አራስ ልጠይቅ ሄጄ አራሷ ሴት ከሆነች "ጡት እሱ ካላጠባኝ" ብላ እሪ ትላለች ። ምኔን እንዳጠባት አስባ እንደሆነ እግዜር ይይላት። እንደፈረደብኝ ጡንጦ ደረቴ ላይ ሰክቼ ልጅቷ እስከምትተኛ ጠብቄ ነው የምወጣው። እሱንም በመከራ እናትየዋ
አራስ ገንፎውን በላይ በላይ አጉርሳኝ።

  ግን እንደተናገርኩት የሚወዱኝ ሴቶች ናቸው። ሴቶች ማለት ሴቶች ብቻ ። ወንዶች አይወዱኝም ። ይጠሉኛል በጣም ። እኔንጃ ለምን እንደሆነ ምንም ያጠፋሁት ነገር የለም ። በእርግጥ ከስድሳ በላይ ባለትዳሮች አፋትቻለው።  አስሩን ጠቅሼ ሀያውን አማግጬ ሲሆን ወደ ሰላሳ የሚጠጉትን ግን ምንም አላረኳቸውም። ካማገጥኳቸው ሴቶች ውስጥ አንደኛዋ አለቃዬ ነች። ያው አለቃዬም አይደለች የስራ እድገትና የደምዝ ጭማሪ ለማግኘት አብሪያት እንዳድር ጠየቀቺኝ ። አኔም አይኔን አላሸውም። በእርግጥ አብረን ያደርን ለት ልብሷን ስታወልቅ ሁለቴ ሙጭልፍ ሙጭልፍ አድርጌ አሽቻለው (አይኔን) ማለት ነው።
   ምንም ሳላደርጋቸው ባላቸውን ከፈቱት ውስጥ ትዝ የምትለኝ የጓደኛዬ ሚስት ነች። ቆንጅዬ ነች ። ያየቺኝ የዛን እለት መሆኑን ያወኩት እኔን ብቻ እየመረጠች ስታጎርሰኝ ነው። የዛን እለት ጓደኛዬ ያየኝ አስተያየት አይረሳኝም " እስካሁን ካንተ ደብቄ አቆይቻት መቼም በሰርጌ እለት ላይ ጉድ አታደርገኝም" የሚል መልዕክት ያለው አስተያየት ነበር። ተረድቼዋለው ግን አናዶኛል። ለምንድን ነው ወንዶች አስኮብላይ እንደሆንኩ የሚያስቡት። ሊያውም የጓደኛዬን ሚስት በሰርጉ እለት ላይ ምን ላደርግ እችላለው? ። ሊያውም አንደኛው ሚዜ ሆኜ ። ለማንኛውም የዛን እለት ከሙሽራዋ ጋር ነው ያደርኩት። አዎ ገንገበት ነኝ ፤ ትንሽ ጠጥቼ ነበር ግን ሚዜዋን ይዤ የገባው ነበር የመሰለኝ ። ጠዋት ስነሳ ነው የጓደኛዬ ጉድ መሆኗን ያወኩት። ሊያውም ካላገባኸኝ ብላ እየጮኸች። "እማ ትላንት እኮ ነው ያገባሽው እስቲ መጀመሪያ የበላሽው ይስማማሽ ቢያንስ እሱም ሰልስቱን ይብላ" ብላት አልሰማም ብላ እሪታዋን አቀለጠችው። እንዴት እንደወጣው ባላቅም ወደቤቴ ልደርስ አከባቢ ነው በሙታንቲ እንደሆንኩ ያስተዋልኩት።
.
.
@mikiyas_feyisa

@wegoch
@wegoch
@paappii
------------    ሸበላው -------------

(እራሱ የራሱን ትዳር ካልጠበቀ እንዴት ነው እኔ እራሴን ከሰከረው እራሴ ምጠብቀው?)

part-2 ❵

       እንደሰማሁት ከሆነ ከዛን እለት ጀምሮ ጓደኛዬ ምን የሚያክ ፍልጥ ይዞ እገለዋለው እያለ ሲዝት ነበር ። በማታ ወደቤት ልገባ ስል (እንኳንም አልገባውና) ግንድ የሚያክል ዱላው እያወዛወዘ ሲጠብቀኝ ከሩቅ አይቼ ከአንድም ሶስቴ ተደብቄው ነው ያመለጥኩት ። እኔ ቆይ ግን ምን አደረኩ  ... እህ ... ሳላያት መጥታ የተለጠፈቺኝ እሷው ። ባለ ትዳሯ እሷው ፤ አሱ የራሱን ትዳር ካልጠበቀ እንዴት ነው እኔ እራሴን ከሰከረው እራሴ የምጠብቀው።
  እሱ ብቻ አይደለም ወንዶች ሲሰበሰቡ የኔን ስም ሳያነሱ እና ሳይረግሙኝ አይለያዩም። የሆነ ጊዜማ የሀሰት ምስክር ሰብስበው ፍርድ ቤት አቆሙኝ። ምን ብለው ሊከሱኝ እንደሆነ ባይገባኝም ዳሩ። አቃቤ ህጓ እንደነገረቺኝ ከሆነ ግን "ሴቶችን ያለ አግባብ በማማለል ፣ በማስኮብለል እና የወንዶችን የማግባት መብት በመጋፋት" ብለው ነው የከሰሱኝ። እሷን በወንድ አቃቤ ህግ ሳያስቀይሯት በፊት። በዚ ክስ የመቅጫ ህግ እንዳለ ባላውቅም የወንዶቹን ህብረት ሳይ እና የዳኛውን ሚስት አማግጬ እንደሆን ስጋት ሲገባኝ ግን ደንግጬ ነበር። ዳኛዋ ሴት እንደሆነች እስከማውቅ ድረስ ፤ ወንዶቹም ይህን ሲሰሙ ነው ክሱን ያነሱልኝ።
    እስከዛሬ የሚገርመኝ ነገር ግን እስካሁን ለእናቴ እና ለአባቴ መፋታት እኔን እንደ ምክንያት ሲያዩኝ ነው። ቆይ እኔ ምን አደረኩ?። ገና ስወለድ ጀምሮ እናቴ ከኔ መለየት አልቻለችም። አዳር ላይም እንኳን ። አባቴ በዚህ ባህሪዋ በጣም እንደሚበግን አውቃለው ። መሀላቸው ስተኛ አይወድም እሷ ደግሞ "ብርድ ይመታብኛል " እያለች መሀላቸው ሸጉጣ ከአባቴ ደም ከመሰለ ፊቱ ጋር ታጋፍጠኛለች። ከአስተያየቱ በጣም እንደሚጠላኝ ብቻ ሳይሆን እኔን ከቤት ለማስወጣት የሚያስፈልገውን ሁሉ እንደሚያደርግ አውቃለው። ብዙዎቹን ለሊት እናቴ እንቅልፍ ሲወስዳት ጠብቆ እኔን አልጋ ስር ይከተኝና አቅፏት ይተኛል። እኔም ከመልመዴ የተነሳ አልጋው እንኳን እንደዛ አይመቸኝም። ግን የአባቴን ግፍ ያየሁት አልጋ ስር እንኳን አስተኝቶኝ ጫማውን እንዳነሳ ፍቃደኛ አይደለም። ልክ ሊነጋ ሲል (ሰዓቷን ያቃታል) የተንተራስኩበትን ካልሲ  መንጭቆ ይወስድና አድርጎ እኔን አልጋው ላይ ለጥፎኝ ወደስራ ይወጣል። ከአባቴ ጋር እንደዚህ ሆነን 18 አመት ሞለኝ።  የዛኑ እለት የራሴ አልጋ አዘጋጅቶልኝ "ሂድ ውጣ" ሲለኝ አባቴ እናቴ "አንገቴ በቢላ" በማለቷ እንደተፋቱ ሰምቻለው።
.
.
By mikiyas_feyisa

@wegoch
@wegoch
@paappii
-------------  ሸበላው ---------

Part-3 ❵
(የመጨረሻ ክፍል)

       ይኸው እስካሁን ድረስ ውጪ ባደርኩ ቁጥር እናቴ አየጮኸችብኝ 25 አመት ሞላኝ። ከሴቶች ጋር እንደ feminist ተሟጋች ስሞላፈጥ ህይወቴን መግፋት እየመረረኝ ሳለ እንዳጋጣሚ ሆኖ በስራ ምክንያት ከአንድ የሀብታም ልጅ ጋር ተገጣጠምኩ። እስቲ የእኔንም የእናቴንም ህይወት ልቀይር ፣ በዛውም ወግ ማዕረግ ላሳያት ብዬ ከልጅቷ ጋር ተጠቃለልኩ። ልጅቷ ልታብድልኝ ትንሽ ነው የቀራት። የርሷ ፍቅር ደግሞ እጅ እጅ ይላል ። ሀገር ሰላም ብዬ ተኝቼ ለሊት ላይ ተሳስቼ አይኔን ብገልጥ ቁጭ ብላ እያፈጠጠቺብኝ ነው ማገኛት። ስንት ጊዜ አስደነገጠቺኝ። ሁሌ ቁርስ ምሳ እራት አብሪያት ካልበላው ወይ ተሳስቼ ውጪ ከበላው ቤቱን መቅደላ ነው ምታደርገው። እንዴት እንደሆነ ባላውቅም ቢሮ ሆኜ ትን ሲለኝ እራሱ ውሀ ይዛ አጠገቤ ቆማ አገኛታለው። ከሁሉም ከሁሉም ደግሞ የከበደኝ ሁሌ ማታ ማታ ፍቅር መስራት አለብን የምትለው ነገር ነው። እንዴ .. ልገለኝ ነው ሀሳቧ? .. ፆም አትል ፣ ወርሀዊ ግዴታ አትል .. እንደ ሸማኔ እንዝርት ስውረገረግ እንዳድር ነው የምትፈልገው። የመጨረሻ ያንገሸገሸኝ ግን መፀዳጃ ቤት ብቻህን አትገባም ያለቺኝ ቀን ነበር። ለካ ፍቅርም ሲበዛ እንደዚህ ያንገሸግሻል። አልፀልይም እንጂ ብፀልይ ኖሮ "አቤቱ የዚህችን ልጅ ፍቅር በልኩ አርግልኝ" የሚል ቃል አክልበት ነበር።
   እንደመታደል ሆኖ ከዚህ ሁሉ ሴቶች በኋላ አንድ የምትጠላኝ ሴት አገኘው። እናቷ (ማለትም አማቼ) ። ባየቺኝ ቁጥር ደሟ ይፈላል። ከልጇ ጋር ስንጋባ ደስተኛ አልነበረችም እንድንፋታም የማትፈነቅለው ድንጋይ የለም። አጠላሏን በጣም ነበር ምወድላት (ተጠልቼ አላቅማ) ። ታዲያ በስተመጨረሻ የልጅቷም ፍቅር ሲበረታ የእኔም ትዕግስት ተሟጦ ሲያልቅ የእናቷም ነገረኛነት ሲታከልበት የፍቺያችን ቀን ደረሰና ተፋታን። የፍቺያችንን እለት ለማክበር ብዙ አንዕስቶች ተገኝተው ነበር። የሚገርመው ነገር ግን ከእነሱ ውስጥ በጣም ደስተኛ የነበረችው አማቼ ነበረች። አትታዘቡኝና የዛን እለት ከእርሷ ጋር ነበር ያደርኩት። የሚያበሽቀው ነገር ግን  ለሊት ላይ ተሳስቼ አይኔን ስገልጥ እንደ ሞኝ እያፈጠጠቺብኝ ነበር። አይ እድሌ!

አይቀጥልም

@wegoch
@wegoch
@mikiyas_feyisa
ይፈተኑ ይሸለሙ፡

ለ12ኛ ክፍል 10 ተፈታኞች እስከ ማክሰኞ ድረስ የሚቆይ የ 1.3GB የዳታ ፓኬጅ ሽልማት አዘጋጅተናል።

የኢትዮጵያን ብሄራዊ ፈተና እንዲለማመዱ የሚረዳችሁ መተግበሪያችን ምታጠኑበትን መንገድ ይቀይራል። ብሄራዊ ፈተናዎችን በጊዜ ቆጣሪ ይዉሰዱ እና የደረሱበትን ደረጃ ይገምግሙ። ለእያንዳንዱ ምዕራፍ በእርስዎ ውጤቶች ላይ ትንታኔያዊ መረጃ(analytical data) እና ምክረ ሀሳችን ያግኙ።

ሽልማቱን ለማግኘት ይህን ሊንክ በመጫን መተግበሪያውን  ያውርዱ👇👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.elevans.eltest

በመቀጠል መተግበሪያውን ተጠቅመው ሁለት የትምህርት አይነት ከ 90 በላይ ውጤት ካመጡ screenshot በማደረግ በቴሌግራም  @useryise ይላኩ ሽልማቶትን ይውሰዱ።

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን የቀላቀሉ
https://www.tg-me.com/eltest1


መልካም እድል 🚀
የመኖር አካፋይ የመሞት ሲሶ መንገድ መሃል........
(ሜሪ ፈለቀ)

ዓይኖቼን በቦዛዛው ስከፍት መጀመሪያ ያየሁት የጨለማ በር የመሰለ ሁለት ቀዳዳ ነበር። ቀዳዳው ውስጥ ጥቋቁር ሰበዝ የመሰሉ ነገሮች እጅብ ብለው ነገር………  እይታዬ እየጠራ ሲመጣ ነው የሰው አፍንጫ መሆኑን ያወቅኩት። የፊቴ ደፍ ላይ ይሄን የሚያህል አፍንጫ ምን ያደርጋል? ምን ሊሆን ነው እንዲህ የተጠጋኝ?

«ሜላት ትሰሚኛለሽ? የምለው ከተሰማሽ ዓይኖችሽን በጣቴ አቅጣጫ አንቀሳቅሺልኝ» ባለአፍንጫው ሰውዬ ፊቱን አሸሽቶ የሌባ ጣቱን ከአንዱ አቅጣጫ ወደሌላው ያወዛውዘዋል። ትንፋሹ የሚሰማኝ ቅርበት ላይ ሆኜ ምን ያስጮኸዋል? በአይኖቼ ጣቱን እየተከተልኩ ከቆየሁ በኋላ ዙሪያ ገባዬን ቃኘሁ። ሀኪም ቤት አልጋ ላይ ነኝ። ባለአፍንጫው ሰውዬ እና አጠገቡ የቆመችው በዓይኖቿ የምትስቅ ወጣት ሴት ከደረቡት ነጭ ጋውን በመነሳት ዶክተር ወይ ነርስ እንደሆኑ ገመትኩ። ዓይኔን ከጣቱ ጋር ስላዳከርኩት ደስ ያላቸው ይመስላሉ። ሴቷ ሰውነቴ ላይ እየተርመሰመሰች እንደሆነ ይታወቀኛል ግን የገዛ ሰውነቴ እንደባዕድ ነገር ነው የሚሰማኝ። ሽባ ሆኜ ነው? ለምንድነው ሰውነቴን የማልሰማው? አፌ ላይ የነበረውን የሆነ ፕላስቲክ ነገር ፈልቅቃ አንዳች የሚያህል ቱቦ ከአፌ ውስጥ እየመዘዘች ስትስብ የት ድረስ ዘልቆ እንደነበር ያልገባኝ ቱቦ ጉሮሮዬን እየፋቀው ሲወጣ ይታወቀኛል።

«ዌልካም ባክ ሜላት። ዶክተር ሀይሌ እባላለሁ። በቀስታ ለማውራት ሞክሪ እስኪ……. ዝምብሎ አንድ ቃል! የመጣልሽን» አለኝ በማባበል።

«ምን ሆኜ ነው ሀኪም ቤት የመጣሁት?» አልኩኝ ስሰማው የራሴ ባልሆነ ቀሰስተኛ ድምፅ።  ፈገግ አለ የሆነ ግልግል አይነት ስሜት በቋጠረ ፊት…………. ሴቷ ከግርጌዬ ዞራ የእግሬን መሃል በጣቷ እየነካካች።

«ጣቴ ከተሰማሽ እግርሽን አንቀሳቅሺልኝ እስቲ» አለችኝ። ጣቴን ይሁን ያንቀሳቀስኩት ሙሉ እግሬን ብቻ አንቀሳቀስኩላት። ተያይተው ያልገባኝን መልዕክት በግንባራቸው ተለዋወጡ። በደመነፍስ እጄ ይሰራ እንደሆነ ለማረጋገጥ ሳይጠይቁኝ እጄን አዘዝኩት። ይታዘዛል። ሰውየው የሆነች አንድ ቂጥ በአግባቡ የማታስቀምጥ መቀመጫ ነገር ስቦ በግራ ጎኔ አልጋው አጠገብ ተቀመጠ።

«ወይዘሪት ሜላት? አደጋ ደርሶብሽ ነው ወደዚህ የመጣሽው። ከደረትሽ ዝቅ ብሎ ሁለት ቦታ በመሳሪያ ተመትተሽ ነው። (እሱ እያወራ በእጄ ለመዳበስ ሞከርኩ።) ስለተፈጠረው ነገር የምታስታውሺው ነገር አለ?» በጭንቅላቴ ንቅናቄ እንደማላስታውስ ነገርኩት።

«እድለኛ ነሽ ጥይቱ ጉበትሽን ለጨረፍታ ነው የሳተው። በቀዶ ጥገና ወቅት ትንሽ ኮምፕልኬሽን ተፈጥሮ የነበረ ቢሆንም ቀዶ ጥገናው ስኬታማ ነበር። ነገር ግን ወደአዕምሮሽ ክፍል የሚሄደው ኦክስጅን ተቋረጦ ስለነበር የተወሰነው የእዕምሮሽን ክፍል ጎድቶታል። የዚህ ጉዳት ዋነኛው አካል ሜሞሪ ሎስ ነው።» ያለው ይግባኝ አይግባኝ እንጃ ብቻ በጭንቅላቴ የማስታውሰውን ነገር መበርበር ጀመርኩ። እሱ ማብራራቱን ቀጥሏል። ሀባ ምናምኒት ነገር ጭንቅላቴ ጓዳ የለም። አይ በደንብ ስላልነቃሁ ይሆናል፣ ድንጋጤ ላይ ስለሆንኩ ይሆናል፣ የሰጡኝ ማደንዘዣ አለቀቀኝ ይሆናል፣ ......... ምንም ምክንያት ይሁን ብቻ የሆነ ነገር ይሆናል እንጂ ዜሮ ዘጭ የሆነ ጭንቅላትማ አይኖረኝም።

«ጥያቄ አለሽ?» አለኝ ግማሹን ያልሰማሁትን ማብራሪያ ሲጨርስ።
«ማነው የተኮሰብኝ? ምን አድርጌያቸው ነው?» የሚለው ጥያቄ ከአፌ ወጣ!
«አልታወቀም። ማንም ይሁን ማን የተኮሰብሽ ሰው ፖሊሶች እቦታው ከመድረሳቸው በፊት አምልጧል። ዝግጁ ስትሆኚ ፖሊሶች ቃልሽን ሊቀበሉ ይመጣሉ። ምናልባት አገግመሽ ወደቤት ስትገቢ ፍንጭ የሚሰጥሽ ነገር ታገኚ ይሆናል።» ሲለኝ ቤቴን ለማሰብ ሞከርኩ።

«ቤት አለኝ? ቤቴ የት ነው? የሚያውቀኝ ሰው፣ ሊጠይቀኝ የመጣ ሰው የለም?»

«የቤት ሰራተኛዋ ነኝ ያለች ሴት ጠዋት መጥታ ነበር። ስልክ አስቀምጣ ነው የሄደችው። ደውለን እንደነቃሽ እናሳውቃታለን። አደጋው በደረሰብሽ ሰዓት መኪናሽ ውስጥ የእጅ ቦርሳሽ ተገኝቷል። ፖሊሶች በኤግዝቢትነት ይዘውት ነው። መታወቂያሽ ላይ ያለው አድራሻ አሁንም ድረስ የምትጠቀሚበት ከሆነ አራዳ ክፍለከተማ ነው የሚለው።» አለኝ ከተቀመጠበት እየተነሳ። የቤት ሰራተኛ ያለኝ ሴት ነኝ? እናት እና አባቴስ? አግብቼ ወልጄ ይሆን? ስንት ዓመቴ ነው? በወና ጭንቅላቴ ውስጥ መዓት ጥያቄዎች ሚሞሪ በሌለው ሰፊ ቦታ ተንቀዠቀዡበት።

«መቼ ነው አደጋው የደረሰብኝ?» አልኩኝ
«ከ27 ሰዓታት በፊት»
«ካላስቸገርኩኝ ትንሽዬ መስታወት ነገር ማግኘት እችል ይሆን? ፊቴ ምን እንደሚመስል ማስታወስ አልቻልኩም።» ስለው ግር በተሰኘ ሁናቴ ሲያየኝ እስከዛ ሰዓት እጇን ቆላልፋ ቆማ የነበረችው ሴቷ ሀኪም ፈጠን ብላ

«ቆይ ቦርሳዬ ውስጥ አለ» ብላ ወጣች። እንኳን የዘነጉትን ፊት አንድ ዓይን አጉልታ የማታሳይ ትንሽዬ መስታወት ይዛ ተመለሰች። መስታወቷን ቀረብ ራቅ እያደረግሁ ራሴን ላይ ሞከርኩ። ፊቴን አውቀዋለሁ። የሆነ 'የት እንደማውቀው ጠፋኝ እንጂ ይሄን ሰው አውቀዋለሁ' እንደሚሉት የሌላ ሰው ፊት አይነት እውቂያ ፊቴን አውቀዋለሁ። የሆነ ነገሩ የተቀየረም ይመስለኛል። ብቻ አላውቅም ቢዚ የሚያደርገው ሚሞሪ የሌለው ወና ጭንቅላቴ የፈጠረብኝ ቅዥብር ይሆናል። ያበጠ ከሚመስለው ዓይኔ ውጪ የተሸበሸበ ቆዳ ፊቴ ላይ የለም። አሮጊት አይደለሁም ማለት ነው።

«እድሜዬን መታወቂያዬ ላይ አግኝታችሁታል?»
«የትውልድ ዘመን 1980 ነው የሚለው።» ካለ በኋላ ያለንበትን ጊዜ ላላስታውስ እንደምችል አውቆ መሰለኝ «አሁን 2015 ላይ ነን!» አለ ቀጥሎ።

«እስከመቼ ነው ምንም የማላስታውሰው?» አልኩት ባወራሁ ቁጥር ሲደክመኝ እየታወቀኝ።

«አዝናለሁ! በእዚህ ጊዜ ብሎ ማለት አይቻልም። ወደኖርማል የበፊት እንቅስቃሴሽ ስትመለሺ ትውስታሽ በራሱ ጊዜ ሊነቃ ይችላል። ምናልባት እስከወዲያኛውም ላይመለስ ይችላል። ምናልባት ደግሞ የተወሰነ ትውስታሽ ተመልሶ የተቀረው ላይመለስ ይችላል። ቁስልሽ ድኖ ስትበረቺ የተለያዩ ቴራፒዎች እንድትሞክሪ እናደርጋለን። አዝናለሁ። » አለኝ አዝኖ ሳይሆን ማለት ስላለበት የስራ ግዴታው በሚመስል አነጋገር። ከዛ በኋላ ለረዥም ሰዓታት ዝም አልኩ። ብቻዬን ከተኛሁበት ክፍል በህመም ሲቃ በሚያዜሙ ታካሚዎች በተከበበ ክፍል ስድስተኛ ሆኜ ተደመርኩ። ሁሉም ታካሚዎች አስታማሚ አላቸው። የሚያጎርስ፣ የሚያገላብጥ፣ ምጽ ምፅ የሚል፣ ሲከፋም የሚያለቅስ፣ ሲበረታ አምላኩን የሚለማመንለት ብቻ ከጎናቸው ሰው አለ። ቀኑ የማላውቀውን የሰዓት ዙረት ቁጥር ዞሮ ምሽት እስኪሆን እኔን ብሎ የመጣ ሰው የለም። አደጋ እንደደረሰብኝ አልሰሙ ይሆን? ብቻዬን ይሆን የምኖረው? እሺ ይሁን ያቺ የቤት ሰራተኛ ነኝ ያለችውስ የት ገባች? ደውላ ለቤተሰቤ ወይ ለጓደኞቼ አትናገርም? ከአንዱ ሀሳብ ወደሌላው ስዘል፣ አናቴ ላይ የተንጠለጠለው ጉሉኮስ ሲያልቅ ሲቀየር ፣ በየመሃሉ መድሃኒት በክንዴ ሲሰጡኝ፣ ሳንቀላፋ ስነቃ ምሽቶ ነግቶ አረፋፈዱ ላይ የቤት ሰራተኛዋ ነኝ ያለችው ሴት በዶክተሩ እየተመራች መጣች። በትንሽዬ ዘንቢል የያዘችውን የምግብ ሰሃን እና ፔርሙዝ እያወጣጣች ከልብ ባልሆነ አጠያየቅ

«እንዴት ኖት እትዬ? ተሻሎት?» አለችኝ ባመጣችው ኩባያ ከፔርሙዙ እየቀዳች። ዓይኔን እንኳን አላየችንም። ዓይኖቼን ሽሽቷ የሀፍረት፤ የማክበር ወይም የፍራቻ አይደለም። የጥላቻ እንጂ! ሞቼም ቢሆን ግድ እንደማይሰጣት ታስታውቃለች። ወይኔ አምላኬ ክፉ ሴት ነበርኩ ማለት ነው?
«እቤት ሌላ ሰው የለም?» አልኳት ምን ብዬ መጠየቅ እንዳለብኝ ግራ እየገባኝ

«እ ሀኪሙ ገና መለመላውን ወደምድር እንደመጣ ህጣን ማር ከአር እንደማይለዪ ነገረኝ። አጠያየቅዎ ቤተሰብ እንዳሎት ከሆነ አይድከሙ። ብቻዎትን ነው የሚኖሩት። እኔና የበር ጠባቂው ጎንጥ ብቻ ነን!» አባባሏ ምንም የሰብዓዊነት ርህራሄ ያለው አይደለም። እንዴት ያለ ክፉ አሰሪ ብሆንባት ነው ?

«አብሮኝ የሚኖር ሰው እንኳን ባይኖር ሌላ ቦታ የሚኖር » ብዬ ሳልጨርስ

«እኔ እርሶ ቤት ከገባሁ ገና ሶስት ወሬ ነው። እርሶን ብሎ የመጣ ሰውም አላውቅም። እርሶም ፈልገውት የሄዱት ወዳጅ ይኑሮት የማውቀው የለኝም።»

«መቼም የምሰራበት ቦታ ባልደረቦች ይኖሩኛል። ምንድነው ስራዬ? የምሰራበትን ቦታ ታውቂዋለሽ?» እንደሁኔታዋ ብታውቅም የምትነግረኝ አትመስልም።

«እርፍ ወግ! እኔ አላውቅም እትዬ!! ከቀጠሩኝ ቀን ጀምሮ ሰው ብለው ያናገሩኝ ዛሬ ነው። እንዴት አውቄው? በወጉ እንደሰርቶ አዳሪው በጠዋት ተነስተው ስራ ሲገቡ አይቼዎት አላውቅም። እንደው ያሎት ቀን ውልብ ብለው ከቤት ይጠፋሉ። ለሊት በጭፍራው ሰዓት ወደቤት ይመለሳሉ። ብቻ ቤትዎ ከሳምንት እስከሳምንት ሙሉ ነው።» ቃላቶችዋ ውስጥ ያልተፋቻቸው ሌሎች ቃላት ይሰማሉ። በስመአብ!! ስራዬ ከወንጀል ጋር የተያያዘ ይሆን እንዴ? ብዙ ነገር ልጠይቃት ቅደም ተከተሉን እየሰካካሁ ፤ ምን ዓይነት ሴት ብሆን ነው እንዲህ ሆስፒታል አልጋ ላይ ተኮራምቼ እያየችኝ የማላሳዝናት እያልኩ አስባለሁ።

.............  ይቀጥላል...................

@wegoch
@wegoch
@paappii
የመኖር አካፋይ ፣ የመሞት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… ክፍል ሁለት
(ሜሪ ፈለቀ)

በአጭሩ የአዲስ አበባ ነዋሪ በሁለት ይከፈላል። ብዙሃኑ እኔን የማያውቀኝ እና የቀረው ጥቂቱ እኔን የሚጠላኝ።

«ይሄን ሁሉ ጥላቻ ትከሻዬ ላይ ቆልዬ እንዴት ኖርኩ? እንዴት አላጎበጠኝም? » በረንዳ ላይ ቁጭ ብዬ አትክልቱን የሚያጠጣውን ጎንጤን ጠየቅሁት።

« አይ እትዬ ዛሬ ሌላ ሰው ሆነው  በንፁህ ልብ ስለተቀበሉት ነው የሚያጎብጥ ሸክም የሆነብዎት። ቂም ባቄመና በጠለሸ  ልብ ሆነው ሲቀበሉት እንዲህ አልተሰማዎት ይሆናል።» አለኝ ከስራው ሳይስተጓጎል። እሱ 'ምንም የማውቀው የለም' ይበለኝ እንጂ በእያንዳንዱ የቃላት ምልሳችን ውስጥ ከነገረኝ በላይ ስለእኔ እንደሚያውቅ የሚያሳብቅ ንግግር ይሰነቅራል። ለጎንጥ ጥሩ ሰው የነበርኩ ሆኜ ወዶኝ አይደለም እንዲህ ቀና መልስ የሚመልስልኝ። እግሩ ስር ፈራርሼ በሽንፈቴ ነው ልቡን ያገኘሁት።

ሆስፒታል ተኝቼ ተናኜ (የቤት ሰራተኛዬ) እየተመላለሰች ስትጠይቀኝ በእያንዳንዱ ቀን ለምጠይቃት ጥያቄ በምትሰጠኝ መልስ ከአደጋው በፊት የነበረችውን ሜላት አበጃጅቼ ላውቃት ጣርኩ። ተናኜ የምታውቀው ጥቂት ነው። በሳምንት ውስጥ አብዛኛውን ቀን ጂም ሄጄ እሰራ ነበር ፣ አብዛኛውን ቀን አመሻሽ ወጥቼ ለሊት እሷ ስትተኛ ነው የምመለሰው፤ በእሷ አገላለፅ ከፈሴ የተጣላሁ ምንም የማያስደስተኝ መንቻካ ሴት ነበርኩ። ጎንጤ በዘበኝነት 1 ዓመት መስራቱን ስትነግረኝ ከሷ የተሻለ መረጃ ይኖረዋል በሚል ሆስፒታል መጥቶ እንዲያየኝ እንድትነግረው ጠየቅኳት።

«ይቅርታ ያድርጉልኝ እመቤቴ ስራዬ ደጃፎትን መጠበቅ ነው። ስራዬን ጥዬ መምጣት አይሆንልኝም። በተረፈው እግዜር ይማሮት!» ብሎ መልዕክት ሰዷል።» ብላ የእርሱን እንቢታ ስትነግረኝ በእርሱ እንቢታ ደስ ያላት ነው የምትመስለው። የሆነ 'የታባሽ' የሚል ዓይነት እምቅ! የዛን ቀን ማልቀስ አማረኝ። ወደሰማይ እያንጋጠጥኩ አምላክን ለመንኩት። ግንሳ ክፉ ሴት ከነበርኩ አምላክስ ያውቀኝ ይሆን?  ህይወት በረደችኝ .......የሆነ እራቁቴን አጋልጣ አደባባይ ያሰጣችኝ ዓይነት መንዘፍዘፍ ተንዘፈዘፍኩ።

አንዳንድ ገልቱኮ 'ያለፈውን ረስተህ አዲስ ህይወት ጀምር ......' ዓይነት ምክር ይመክር ይሆናል። ሰው ያለትናንቱ ምንድነው? ይኸው እጥብ አድርጌ ትናንትን ረስቼው መች ከአዲስ መጀመር ቻልኩ? ከምን እንደምጀምር ተደናብሮብኝ ተገትሬ የለ? ትናንት የዛሬ መንደርደሪያ ይሆናል እንጂ ትናንትን እርሳው እንዴት ይባላል? ትናንት ከሌለ ዛሬ መች ይመጣል? ሰውማ ትናንቱን ነው። ዛሬውን የሚንደረደረው ከትናንት ተነስቶ ነው። እረስቶ ሳይሆን ትናንቱ ጥፋት ከሆነ ተምሮበት፣ ጥሩ መሰረት ከሆነ ደግሞ አዳብሮት ይቀጥላል።

ከሆስፒታል የምወጣበት ቀን ሲደርስ ሆዴ በፍርሃት ሲላወስ ታወቀኝ። የቱ በትክክል እንዳስፈራኝ አላውቅም። እቤቴ ስሄድ ያቺ ተኛኜ የምትጠላትን ሜላት የማገኛት አይነት ስሜት ይሰማኛል። ከቤቴ ይልቅ ሆስፒታል ውስጥ የተሻለ ሰላም የማገኝ ዓይነት ስሜት ፣ ወደቤቴ ሳይሆን ወደግዞት የምሄድ ስሜት ልቤን ተጫነው። ሊገድለኝ የሞከረው ሰው ድጋሚ መጥቶ ቢጨርሰኝስ? ሆስፒታል ውስጥ አኑሩኝ ይባላል? አብሮኝ የተኛ ታካሚ ወዳጅ በተናኜ መሪነት በመኪናው እቤቴ እየሸኘን እጄ ይንቀጠቀጣል። መንገዱ ሩቅ ቢሆንና ቶሎ ባንደርስ?

«ልብስ ልደርብሎት እንዴ? እየተንቀጠቀጡ ነውኮ! » አለችኝ ተናኜ። መንቀጥቀጤን ለመደበቅ አንዱን እጄን በአንደኛው ጭምቅ አድርጌ ያዝኩት። የሆነ ጥቁርና ነጭ ቀለም የተቀባ የብረት በር ፊት ለፊት እንደቆምን የሰማይ ስባሪ የሚያህል፣ ፊቱ ላይ መጀነኑ የሚንጎማለል፣ አንገቱ ላይ ፎጣ ጣል ያደረገ  ጎልማሳ ሰው በሩን ከፈተልን።

«ጎንጤ እሱ ነው?» አልኳት ወደተናኜ ዘወር ብዬ ሳላስበው። በአዎንታ ራሷን ነቀነቀች። ጎንጤ ይሆናል ብዬ የሳልኩት ሰውዬ የሆነ ኮስማና ሸምገል ያለ ደካማ ነገር ነው። ያደረሰንን ሰው አመስግኜ በሩን እያለፍኩ።

«ደህና ዋልክ?» አልኩት ጎንጤን።

«እግዜሐር ይመስገን። እንኳን ለቤትዎ አበቃዎት!» ብሎኝ በሩን መዘጋጋት ያዘ።

ጊቢውን ዙርያ ገባውን አየሁት። ከቤቱ ፊትለፊት ባለ ሰፋ ያለ ቦታ አበቦች ፈክተውበታል። መለስተኛ ቪላ ቤት ነገር ነው። ከቤቱ በአንደኛው ጎን ባለ ክፍት ቦታ መኪና ቆሟል። እንደእንግዳ ዙሪያ ገባውን በአይኔ ስነቅስባቸው ግራ ተጋብተው ነው መሰለኝ። ሁለቱም ቆመው ያዩኛል። እንደተቆጡት ህፃን ብርግግ ብዬ ፈጥኜ ወደበሩ ሄድኩ። እቤት ገብቼ ምን እንደምፈልግ እርግጠኛ ባልሆንም ቤቱን መበርበር ያዝኩ። የፎቶ አልበም ፣ የትዳር ሰርተፊኬት ፣ ወይ የሆነ ደብዳቤ ብቻ አላውቅም አንድ የሆነ ነገር። ሳጎነብስ ቁስሌ እየተሰማኝ መበርበሬን ቀጠልኩ። ቤቱ ሳሎን ሶስት መኝታ ቤት እና ሰፊ ጓዳ እና መታጠቢያ ቤት ነው ያለው። መኝታ ቤቴ መሆኑን የነገረችኝ ክፍል ስገባ ሙሉውን የቁምሳጥኑን በሮች ከከደነው መስታወት ጋር ተፋጠጥኩ። ራሴን በደንብ አየሁት። ትክት ያለው ገፅታ! ክፉ ከመሆኔ ሌላ መከራ የበዛበት ህይወት ይሆን ያሳለፍኩት? የአልጋው ራስጌ ኮመዲኖ ላይ በፍሬም ያለ ፎቶ አይኔን ጠለፈኝ። አንደኛው የራሴ ምስል ነው። ወይም መሰለኝ። ከሆነ ወንድ ጋር ተቃቅፈን እየሳቅን። ከኛ ምስል ጀርባ ቁመቱ በረዛዘመ አረንጓዴ ሳር የተሸፈነ መስክ ይታያል። ቦታውን የማውቀው ዓይነት ስሜት ይሰማኛል ግን ትዝ የሚለኝ ነገር የለም። አሁን ካለሁበት ድንጋይ ቤት ይልቅ ምስሉ ላይ ያለው ሜዳ የቤት ዓይነት ስሜት ሰጠኝ። የሆነ በሳሮቹ መሃል ስሮጥ እርጥበት ያለው ሳር እግሬን እየሳመኝ ዓይነት። እዛ መስክ ላይ ደስተኛ ሴት የሆንኩ የምቦርቅ ዓይነት ሽውታ ትውስታ ይሁን ቅዠት ሰውነቴን ይወረዋል። እሺ የት ነው? እሱስ ማን ነው? አባቴ አይሆንም። በእድሜ እኩያዬ ቢሆን ነው። ተጨማሪ መረጃ ካገኘሁ ብዬ ቁምሳጥኑን አተራምሰው ጀመር። አንደኛውን መሳቢያ ስቤው በድንጋጤ እሪሪሪ ብዬ ጮህኩ። ጎንጥም ተናኜም  እየተሯሯጡ ሲደርሱ መሳቢያው እንደተከፈተ ራቅ ብዬ ቆሜ ደንዝዣለሁ።

«ሽጉጥ መኝታ ቤቴ ውስጥ ምን ይሰራል?» ስላቸው ግራ በመጋባት ተያዩ።

«የራስዎ ሽጉጥ ነዋ ሆ!» አለ ጎንጥ ለማይረባ ምክንያት ሮጦ በመምጣቱ እየተናደደ።

«እኮ ሽጉጥ ምን ያደርግልኛል?»

«እሱን እኔ በምን አውቃለሁ?» ብሎ አየሩን እየቀዘፈ በትክክል የማልሰማውን ነገር እያጉተመተመ ወጣ። ተናኜ ያሳዘንኳት መሰለች ወይም እኔ መሰለኝ ቆማ በግራ መጋባት ስታየኝ ቆይታ።

«እንግዲህ ጠላት ቢኖሮትም አይደል ሊገድሎት የሞከረው? ራሶትን ሊጠብቁበት ይሆናላ ያስቀመጡት።» አለች የተከፈተውን መሳቢያ መልሳ እየዘጋች።

«ገላዬን ታጥቤ የምለብሰው ንፁህ ልብስ አውጪልኝ በናትሽ።» አልኳት ለጊዜው እዛ ቁምሳጥን ውስጥ ያለ ተጨማሪ አስደንጋጭ ነገር ለመጋፈጥ በቂ አቅም አልነበረኝም።

ገላዬን እየታጠብኩ ጀርባዬን ለማሸት ስንጠራራ በመስታወቱ ውስጥ ጀርባዬን አይቼው

«በስመአብ !» ብዬ ጮህኩ። ሰካራም የሳለው ስዕል ይመስላል ጀርባዬ! ከማጅራቴ ጀምሮ የቂጤን ኳሶች ጭምር በንቅሳት የተዥጎረጎረ ነው። የንቅሳቱ ዓይነት አበዛዝ የሰው ጀርባ ሳይሆን ለህፃን ልጅ በምስል ማስተማሪያ ደብተር ነው የሚመስለው።  የልብ ምስል፣ አንበሳ፣ ፈረስ የሚጋልብ ሰው ወይ መልዓክ ያለየለት ነገር  በትልቁ የተፃፈ «ኪዳን» የሚል ፅሁፍ ፣ በደንብ የማይታዩኝ ብዙ ጥቃቅን ምስሎች  .......
በመስታወቱ ጀርባዬን ሙሉ በሙሉ ላየው ስታገል የሆነ ማስታወስ ይሁን ያልገባኝ የሳሩ መስክ ዓይነት ስሜት ሽው አለብኝ። የሆነ የተቆራረጠ ትርጉም የለሽ ምስል። ጨለምለም ያለ ክፍል ውስጥ የሚነድ ሊያልቅ የደረሰ ሻማ ፣ ስኒከር ጫማ የተጫማ አንድ የሰው እግር እና የመጠጥ ሽታ ከ30 ደቂቃ በላይ መስታወቱ ላይ ባፈጥም የተለየ ትዝ የሚለኝ ነገር የለም። ምን ዓይነት ህይወት የኖርኩ ሰው ብሆን ነው ቂጤን ንቀሱኝ ብዬ ገልቤ የሰጠሁት? ቤተሰብ አልነበረኝ ይሆን? በመሃል ደግሞ ሌላ ሀሳብ ይጠልፈኛል:: ቋንቋ የሚሞሪ አካል አይደለም ? ጭንቅላቴ ገደል ማሚቶ የሚያስተጋባበት ወና ሆኖ እንዴት አማርኛ ማውራት ቻልኩ? አነበብኩኮኣ? እንዴት ማንበብ አልጠፋኝም?

«ፖሊሶቹ መጥተዋል።» አለችኝ ተናኜ እዛው እንዳፈጠጥኩ። የምሰጠው ቃል ባይኖረኝም ቃሌን ሊቀበሉ መሆኑ ነው። ለባብሼ ወደሳሎን መጣሁ። ከእኔ ያገኙት መረጃ ባይኖርም ሲጠይቁኝ ቆይተው ቦርሳ እና ስልኬን ሰጥተውኝ ሄዱ። ስልኩን ከማገላበጥ ውጪ የማደርገው ግራ ገብቶኝ ቀና ስል ተናኜ እያየችኝ ነው። አፈርኩኝ መሰለኝ እሱን ቁጭ አድርጌ ቦርሳውን መበርበር ጀመርኩ። መታወቂያ ፣ መንጃ ፈቃድ እና የብር ኖቶች ያሉበት ትንሽዬ ቦርሳ ውስጡ አለ። ምንም ፍንጭ የለውም። የሆነች ተጨማድዳ የተቀመጠች ትንሽዬ ወረቀት አገኘሁ። አገላብጬ ሳነብ  የሽያጭ ሪሲት መሆኑን ተረዳሁ። ጂም ውሃ የገዛሁበት ነው።  ቁስል እንዳለኝ ሁሉ ዘንግቼ መዥረጥ ብዬ ወጣሁና

«እስፖርት የምሰራበት ጂም የት እንደሆነ ታውቃለህ?» አልኩት ጎንጤን
«እ!» አለ አዎ እንደማለት ነገር። እንዲያሳየኝ ጠይቄው ታክሲ ጠርቶ አብሮኝ ሄደ::

ገብቼ ምን እንደምል እንኳን አላውቅም! 'እስኪ ካወቃችሁኝ ራሴን አፋልጉኝ ማን ነበርኩ ?' ነው የምላቸው? በሩን አልፌ እንደገባሁ ቆምኩ። ከፊትለፊቴ እስፖርት እየሰራ ያለ ሰውነቱ የተነፋፋ ወጣት ነገር በሆነ ነገር ፈላጊ አይን አፍጥጦ እያየኝ ያዝኩት። የሚያውቀኝ ሰው ቢሆን ነው ብዬ የሆነ ነገር እስኪለኝ አትኩሬ ማየት ቀጠልኩ። የለበስኩትን ፒጃማ ቅንድቡን ሰቅሎ ከገረመመ በኋላ

«ምን ታፈጫለሽ?» አባባሉ። ቢያውቀኝም በወዳጅነት የሚያውቀኝ ሰው እንዳልሆነ ያሳብቃል። ምንም ሳላስብ ወዳለበት እየተጠጋሁ።

«ይቅርታ እና ታውቀኛለህ ማለት ነው?» ስለው እየጎፈላ ከማሽኑ ላይ ወርዶ ደረቱን እየነፋፋ
«ኸረ ተይ ሴት ነሽ ብዬ ነው የታገስኩሽ ግን?» ከማለቱ የሆነኛው ከሌላ አቅጣጫ እየሮጠ መጥቶ

«እኔ ብጥብጥ አልፈልግም ሜላት አርፌ ስራዬን ልስራበት!» አለ በልመና ዓይነት። መናገርም መራመድም የጠፋውን ሚሞሪዬን ተከተሉት መሰለኝ እንደተገተርኩ ቀረሁ።

       ..................... ይቀጥላል ..........................

@wegoch
@wegoch
@paappii
#አይኖች_ይሰማሉ_እጆች_ያወራሉ
የሥዕል አውደ ርዕይ
በ ሠዓሊ ኖህ አበበ

ረቡዕ , ጥቅምት 2 2015
ከምሽቱ 12:00 ሰዓት

እስከ ጥቅምት 21,2015 አ.ም ይቆያል።
@seiloch
የመኖር አካፋይ ፣ የመሞት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል ሶስት)
(ሜሪ ፈለቀ)

«ኸረ እኔ ብጥብጥ ፈልጌ አይደለም የመጣሁት ! እባካችሁ? አደጋ ደርሶብኝ ሚሞሪዬ በሙሉ ጠፍቷል። የማስታውሰው ነገር የለም! ካወቃችሁኝ ማን እንደነበርኩ እንድትነግሩኝ ልጠይቃችሁ ነው!» ያልኩት ምን ማለት ነው? አላውቅም! 'ማነኝ?' ብሎ መጠየቅ ምን የሚሉት የነፈዝ ጥያቄ ነው? 'ሜላት ነሽ!' ነዋ ሊሉኝ የሚችሉት አይደል? ስም ግን ማንነትን እንዴት ይገልፃል? እንዴት ነው ሰው 'ማንነህ?' ሲሉት 'እገሌ ነኝ 'የሚለው? ስሜንስ አስታውሼው ነው? ወይስ ዶክተሩ ስለነገረኝ ነው ያወቅኩት?

«ሙድ ትይዣለሽ እንዴ?  ባቡር በገጨሽ! እሱማ ፀሎቴ ነበር! ይህቺ ደግሞ የሰሞኑ ሙድሽ ናት? አደጋ ትላለች እንዴ በናታችሁ?» አለ የመጀመሪያው ሰውነቱ የተነፋፋው ወጣት ስነስርዓትም ርህራሄም በሌለው ሁኔታ። ያልኩትን እንዳላመነኝ ቢገባኝም ስሜቱ ግን ቅድም ከነበረው ፍርሃት ወይ ማክበር ያልገባኝ ማመንታት አሁን ወደ ንቀት ወይ ድፍረት ያልለየሁት ስሜት ተቀየረ:: ሊገላግል የመጣው ልጅ ግን እንደመረጋጋት ብሎ በጥርጣሬ አስተውሎ እያየኝ ነበር።

«በስመአብ! ምነው ይሄን ያህል? እንዲህ አይነት ነገር በራሴ ላይ አሟርታለሁ?» አልኩኝ በልመና! እንዴት እንደማሳምነናቸው ግራ እየገባኝ

«አንቺ የምርሽን ነው እንዴ?» አለ ሊገላግል የመጣው ልጅ! ባለ ንፍፊት ሰውነታሙም ከቅድሙ አሁን ግራ የተጋባ ቢመስልም ፍርጥም ብሎ

«ሰይፊኝ ካመንኩሽ!» አለ አንገቱ ላይ በጣቱ ከቀኝ ወደግራ የመቁረጥ ምልክት ሰርቶ

«ካላመንከኝ ላሳይህ » ብዬ የተመታሁበትን ቁስሌን ላሳያቸው ከላይ የለበስኩትን ልብስ ልገልጥ ስል ጎንጤ ከየት መጣ ሳልለው ዘሎ እጄን ቀጨም አደረገ እና ልገልጥ የጀመርኩትን ልብስ ወደታች እያለበሰ

«አንተ በአግባቡ ተጠየቅክ አይደል እንዴ? በወጉ አትመልስም? የምን ኩፍ ማለት ነው?» አለው ከእግሩ እስከጭንቅላቱ በንቀት እያየው።

«አንተ ደግሞ ማነኝ ነው የምትለው?» አለ ያኛውም እየተጠጋው።

«ሰውዬ ተከበር! ነገር አትፈልገኝ!»

«ምን እንዳታመጣ?»  ሁለቱም ተኮፋፍሰው ሊነካከሱ የተፋጠጡ አውሬዎች መሰሉ። ቅድም ሊገላግል የመጣው ልጅ በመሃከላቸው ገባ!

ጎንጤ እንድንሄድ በእጁ ወደበሩ እያሳየኝ በሚያስፈራ ፊት እንድቀድመው ሲጠብቀኝ ምንም ሳልል ወጣሁ። ተከትሎኝ ወጥቶ እያለፈ የነበረ ታክሲ አስቁሞ አሁንም እንድገባ በእጁ ምልክት ሰጠኝ። ምንም ቃል ሳይናገር ቁጣው ይጋረፋል። እንዲህ የሚያስፈራ ሰውዬ ሊያስተዳድረኝ ነው ላስተዳድረው የቀጠርኩት? እልህ የታጨቀበት አተነፋፈስ ቁና ቁና እየተነፈሰ ፈርቼው ምንም ሳልናገር እቤት ደረስን። ድንገት በመጣልኝ ሃሳብ

«መቼም ጎረቤቶቼ ያውቁኛል አይደል? » ብዬ ወደ ቀኝ ወዳሉ ጎረቤቶቼ በር ላመራ እግሬን ከመዘርጋቴ ወደቤት መሄዱን ሳይገታ እየተራመደ ዞርም ብሎ ሳያየኝ

«እእ (ጭንቅላቱን በተቃውሞ እየናጠ) እኔ እርሶን ብሆን አልሞክረውም!» ሲለኝ ቆምኩ።

«እህእ? ቆይ ሰላም የሆንኩት አንድ ሰው የለም?» አልኩኝ ለራሴ ይሁን ለእርሱ

«እሱን አላውቅም!»

«እሺ እነሱስ?» አልኩት በግራ በኩል ወዳለው በር እየጠቆምኩ።

«ህእ!(ፌዝ ባለበት ሽራፊ ፈገግታ) እሱኛውም ጥሩ ሃሳብ አልመሰለኝም!» እያለ በሩን ከፍቶ ክፍቱን ለእኔ ትቶት ወደጊቢ ገባ። ተከትዬው እየገባሁ።

«ይሄን ያህል ምን ዓይነት ሰው ብሆን ነው ከሰው ሁሉ ጋር የምናከስ የነበረው? መቼም ከዚህ ሁሉ ሰው ጋር ፀብ ከሆንኩ ችግሩ ሰውጋ ሳይሆን እኔጋ ነው የሚሆነው! ይሄን ያህል ክፉ ሰው ነበርኩ?» አልኩት

«እኔ አልወጣኝም!» ብሎ በሩ አጠገብ ያለ የእንጨት ወንበር ላይ ተቀምጦ እኔን ላለማየት በሚመስል አጥር አጥሩን ማየት ጀመረ።

«በአፍህ ባትልም ሁኔታህ ያስታውቃል። እሺ የሌላው ይቅር አንተ ምን አድርጌህ ነው እንዲህ የምትጠላኝ? ምን እንዳደረግኩ እንኳን በማላውቀው ጥፋቴ ስትቀጣኝ ግፍ አይሆንም?»

«ሆ! እኔ ክፉ ደግ አያናግሩኝ! እንዲህ ነው እንዲያ ነው አልወጣኝም! ከፈለጉ ሄደው ማንኳኳት ይችላሉ።»(ወደጎረቤት ጊቢ በእጁ እየጠቆመ)

«ከእነርሱ አንተ አትቀርብም? 1 ዓመት እዚህ ቤት ነበርክ! ንገረኝ ምን አይነት ሴት ነበርኩ? ምንድነው የምሰራው? ከማን ጋር ነው የምውለው? እንዴት አንድስ ወዳጅ የለኝም?»

«የማውቀው ነገር የለም። ምንም ነግረውኝ አያውቁም! ሆ! እኔ የምውለው እዚችሁ ደጅ እርሶ ከቤትዎ! ምን ያገናኘናል?» አለ አሁንም ወንበሩ ላይ እንደተኮፈሰ

«እኔ ባልነግርህም ወይ ያየኸው ወይ የሰማኸው ግን ይኖራል?»

«ወሬ ለቃቅሜ የማቀብል ባለጌ አይደለሁም። ያላየሁትን አላወራም!» አለኝ ድርቅ ብሎ

«እኮ ያየኸውን ንገረኝ! ቢያንስ ላንተ ምን ዓይነት ሰው እንደነበርኩ ንገረኝ?»

«ሆ!» ከማለት ውጪ አልመለሰልኝም! ተስፋ ቆረጥኩ። በተወሰነ መልኩ ድርቅናው አናደደኝም! ቅድም በዛ ንፍፊታም ሰውዬ ፊት ለእኔ እንደሚያስብ ዓይነት ሰው ሲሆን አልነበረ? ስራው ቤቴን መጠበቅ እንጂ እኔን መጠበቅ ነው? እየጠላኝ ግን ደግሞ ሊጠብቀኝ መሞከር አይጋጭም? ወደቤት ገብቼ የህመም ማስታገሻ ከዋጥኩ በኋላ ተኛሁ!!

«እራት አይበሉም?» ብላ ተናኜ ስትቀሰቅሰኝ ብዙ እንደተኛው ያወቅኩት። ማታ አራት ሰዓት ሆኗል። እራቴን ከበላሁ በኋላ ለመተኛት ብሞክርም አቃተኝ። ምሽቱን ፈራሁት። አይኔን መጨፈን ፈራሁ። ጨለማውን ፈራሁት። ፀጥታውን ፈራሁት። የተኛሁበትን መኝታ ቤት ፈራሁት:: የሆነ ሰው ተደብቆ እያየኝ ሁሉ መሰለኝ:: ከአልጋዬ እንኳን ተነስቼ መንቀሳቀስ ፈራሁ። 'አምላኬ ሆይ እባክህ ለሊቱን ቶሎ አንጋው' ብዬ የጅል ፀሎት ፀለይኩ:: መብራቱ እንደበራ እኔም ከአንዱ ጎን ወደሌላው እንደተገላበጥኩ ነጋ። ብርሃኑ ከክፉ ይጠብቀኝ ይመስል ብርሃን ወገግ ሲል ፍርሃቴ እየረገበ አይኔ ተከደነ። ስነቃ የመጣው ይምጣ ብዬ በሩን ከፍቼ የሚቀጥለውን ቤት በር አንኳኳሁ። የሆነ የዋህ የሚመስል ፊት ያለው አጠር ያለ ቀይ ሰው በሩን ከፈተ።

«ደህና አረፈድክ?» ከማለቴ የዋህ ፊቱ ደም መሰለ። በሩ ላይ ስላየኝ የደነገጠም የተናደደም መሰለኝ።

«ደሞ ምን ፈልገሽ ነው? እንዴ? አንቺ ትዳር የለሽም እና የሰው ትዳር ሰላም መሆን አይችልም?» ሲለኝ ህመም ተሰማኝ። ቁስሌንም ልቤንም ራሴንም አንድ ላይ ያመመኝ ነገር መሰለኝ። ዝም ብዬ ቆምኩ። አካሌ ቆመ እንጂ ውስጤ የሆነ ነገር ፈርሷል። የሆነ ራቁትነት ስሜት ተሰማኝ። በትክክል የማልገልፀው ስሜት ግን እርቃኔን በብዙ ሰዎች ፊት ቆሜ ሀፍረቴን ለመሸፈን ስቃዬን እየበላሁ ያለሁ  ዓይነት ስሜት ......... የተዋረድኩ ግን ውርደቴ ለሌሎች ጌጥ የሆነ የተሸነፍኩ ግን በመሸነፌ የሚደሰት እንጂ የሚያዝንልኝ የሌለ.......... እንክትክት ብዬ የወደቅኩ ግን ሊያነሳኝ እጁን የሚዘረጋ ሳይሁን የወደቅኩበት ሁሉም እያየኝ የሚያልፍ .......

«ድንቄም ሰላም ትዳር! (የጎንጤን ድምጽ ከትከሻዬ ላይ ሰማሁት) ከነገሩ የእግዜር ሰላምታ አይቀድምም?»

ሰውየው በሩን በሃይል አጋጭቶ ዘግቶት በጣም እየጮኸ «ኤደን? አንቺ ኤደን? » እየተጣራ ከበሩ ራቀ። ስድብ የቀላቀለው በጩኸት የታጀበ ንግግር ይሰማኛል።
«አልነገረኝም እንዳይሉ ተናግሬያለሁ!» ብሎ ጎንጤ ጥሎኝ እንደትናንቱ በሩን ክፍት ትቶት ወደውስጥ ገባ። የእንፉቅቅ እርምጃ እየተራመድኩ ወደጊቢ ገባሁ። ትኩስ እንባ ጉንጬን እያራሰ ያጥበኝ ጀመር። አምላክ ግን እንዴት ባሳዝነው ነው እንዲህ የሚቀጣኝ? ልብ ይበርደዋል? እንዲህ ያለ ነገር አለ ይሆን? ልቤን በረደኝ። ያለፈውን ራሴን ማወቅ የመፈለጌን ያህል በዛው መጠን ላውቀው የምችለውን ትናንቴን ፈራሁት። እግሩ ስር ፈራርሼ በሽንፈቴ ነው ልቡን ያገኘሁት ያልኩት ይሄን ቅፅበት ነው።

«እሺ በድዬህ የነበረውን ማረኝ? ይቅርታ አድርግልኝ? የማውቀውም፣ እርዳኝ የምለውም፣ የምሄድበትም ማንም የሌለኝ ሆኜ፣ ያጋጠመኝ ሁሉ ሲያላግጥብኝ አላሳዝንህም? እንዲህ ውሉ ጠፍቶኝ ስደናበር ምንስ ክፉ የነበርኩ ቢሆን ትንሽ ልብህ አይራራም? እባክህ እንድታግዘኝ እየለመንኩህ ነው።»  ብዬ በዛለ ጉልበቴ እግሩ ስር ተነጠፍኩ።

«ኸረ በመድሃንያለም!» ብሎ ደንግጦ ዘሎ አነሳኝ። « የምረዳዎት ነገር ካለ ምን ገዶኝ! ሆ! ሀጢያት ሊያስገቡኝ?» አለ ወደ ሰማይ መልከት አድርጎ እስከዛ ሰዓት ባላየሁበት እርግብ ያለ ድምፅ ..... እየተጎተትኩ በረንዳው ላይ ያለ ወንበር ላይ ሄጄ ተቀመጥኩ። እንባዬ አልቆም አለኝ።

«ኸረ በድሃንያለም ይሁንብዎት ሀጢያት አያስቆጥሩብኝ? » አለ በተጨነቀ ድምፅ ፊቴ እየተንጎራደደ። መቆሟን እስከዛ ሰዓት ድረስ ያላስዋልኳት ተናኜ ሳጓን ወደ ውስጧ ስትስብ በሩ ላይ ቆማ የሹራቧን አንገትጌ ስባ በጥርሷ ነክሳ አብራኝ እያለቀሰች እንደሆነ አየሁ። ስንተያይ እንባዋን እየጠራረገች ወደ ውስጥ ገባች። ጎረቤቴ አሁንም እየጮኸ ነው። ማልቀሴን ገታ አድርጌ ለመስማት ስጥር

«ደንፍቶ ደንፍቶ ይተዋል።» አለኝ ጎንጤ። 'ማን ላይ ነው የሚደነፋው?' ብዬ መጠየቅ አሰብኩ እና ስለደከመኝ ይሁን ባይመልስልኝስ ብዬ ይሁን አላውቅም ዝም አልኩ። ትንሽ ቆይቶ

«በገባ በወጣ ቁጥር ሚስቱን መርገጥ ነበር ስራው። በነጋ በጠባ እየደቆሳት ምን ጥሎባት እንደሁ ፍቅር አለባት መሰለኝ በየቀኑ ጎረቤት እየገባ ያስታርቃቸዋል መልሳ ስሩ ነች። ከሳምንት በኃላ መልሶ ያሻታል። ይጯጯሃሉ፣ ጎረቤት ይገለግላል። በሳምንቱ መልሰው እዛው ናቸው። እንደለመደው አንድ ማታ ሲያሻት በደም ብትነከር ልጃቸው እሪሪ ብላ ትጮሃለች፣ ጎረቤት የአጥሩን በር ይደበድባል፣ ለካንስ አጅሬው የቤቱን በር ዘግቶ ነው የሚደበድባት። እርሶ 'መሰላል አቀብለኝ!' ብለው በዚህ በኩል አድርገው (ከጎረቤት የሚያዋስነንን አጥር እያመለከተ) ዘለው ገቡ። የቤቱን በር በምን እንደሰበሩት ያየ የለም። ብቻ መስታወቱ ረግፎ ነበር።» ብሎ ዝም አለ። ሽራፊ ፈገግታው በአጋጣሚው የመኩራት ዓይነት መሆኑ ግራ አጋባኝ። ወሬውን ያጠናቀቀ ያህል ዝም ሲል

«ከዛስ?» አልኩኝ አንገቴን አስግጌ

«ህም! ከዚያማ እንዴት አድርገው ቢያሹት እንደሆነ እንጃ ለብዙ ቀናት 'እገሌ ነኝ!' ካላለ በቀር ፊቱ አይለይም ነበር! እንደመሰለኝ ከሆነ ከዱላው በላይ ሽጉጥ አውጥተው እንደሚገድሉት አስፈራርተውት ስለነበር መሰለኝ ወደፖሊስም አልሄደ ወደዚህም መልሶ ዝር አላለም። ያቺ ገልቱ ሚስትየው ናት በበነጋው መጥታ እንዴት ባሌ ላይ ሽጉጥ መዘዙ ብላ የደነፋችው! ከዛ ቀን በኋላ እንዳረጀ ውሻ ያላዝናል እንጂ እጁን አንስቶባት አያውቅም!» ብሎኝ አሁንም ሽራፊ ፈገግታውን ፈገግ ብሎ ዝም አለ።

                 .............. ይቀጥላል ...............

@wegoch
@wegoch
@paappii
#የመኖር አካፋይ ፣ የመሞት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል አራት)
(ሜሪ ፈለቀ)

«እትዬ ትናንት ሲያይዎት ሙታንቲው ላይ ቅዘኑን የሚለቅ ሽንታም ሁላ ዛሬ ዝቅ ብለው ይቅርታ ቢጠይቁት ለምህረት እቅፉን ከሚዘረጋልዎ ይልቅ በቀል የሚፈትል ይበዛል። የተዋረደ የመሰለውን ጊዜያት እርሶን በማዋረድ ሊያካክስ ይጥራል። ግድ የሎትም ይቅርታ መጠየቁ ይቆይዎት።» የሚለኝ 'ለምን ጎረቤቶቼን ይቅርታ አልጠይቃቸውም?' ብዬው ነው።

እቤቱ ገብቼ ከደበደብኩት ጎረቤቴ በተቃራኒ ካሉት ጎረቤቶቼ ጋር የፀብ መነሾዬ ምን እንደነበር ጎንጤም አያውቅም። ድንገት በር ላይ ከተገጣጠምን ግን በእርሱ ቃላት ፀያፍ ስድቦች እንለዋወጣለን።
'እስኪ ንገረኝ እንዴት ያለ ስድብ ነው የሰደብኳቸው?' ስለው። እያንገሸገሸው
'እትዬ ሲናገሩስ አፍዎ አለፍ ይላል! እኔ አልደግመውም' ነው ያለኝ። እሱን ምን አድርጌው እንደጠላኝ ስጠይቀው
' በይቅርታ አለፍነውም አይደል? ከይቅርታ በፊት እንጂ ከይቅርታ በኃላ የበደል ዝርዝር አይቀርብም።' ብሎኝ ነው ያለፈው።

«አንተ ይቅርታ አድርገህልኝ አይደል? ተናኜ ይቅርታ አድርጋልኝ አይደል? ወይስ አላደረግክልኝም? ልትበቀለኝ መች አሰብክ? ወይስ ታስባለህ?»

«ኸረ መድሃንያለም ይቅር ይበሎት! እኔ የመሰለኝን ነው የነገርክዎት። አይ አሻፈረኝ ካሉ ይሞክሩት። ኋላ የሚከተለው ምንም ቢሆን የመቋቋም አቅሙ አለኝ ካሉ ....... » ብሎ ትከሻውን በምንቸገረኝ ሰበከ። የሚያወራው ከልምድ ይመስላል፣ ከሚያውቀው ካለፈበት ልምድ፣

«ይቅርታ በመጠየቄ ከእነርሱ ይልቅ ራሴን ነፃ የማወጣው እኔ አይደለሁ? የሚሰማንን መጥፎ ስሜት ለይቅርታ ባጎነበስኩበት አራግፌ የምነሳው ራሴም አይደለሁ?»

«ከተነሱ ነዋ! ለይቅርታ ባጎነበሱበት የሚረግጥዎ ካጋጠሞትስ? በመድሃንያለም ዘንድ ይቅርታ መጠያየቅ ወደ ፍቅር መሸጋገሪያ ድልድይ ነው። ያ ግን የይቅርታ ትርጉም ለሚገባው ሰው ነው። የኛ ሰው ይቅርታ ጠያቂ የተዋረደ፣ ይቅርታ ተጠያቂ ክብር የተጎናፀፈ አድርጎ ነው ይቅርታን የሚፈታው። የኛ ሰው ለብቻው በጓዳ እግሩ ስር ወድቀው ይቅርታ ቢጠይቁት እንደማይረካ አያውቁም? ሰው በተሰበሰበበት ስህተትዎትን ማመንዎ አይደለም ይቅርታዎን ትልቅ የሚያደርግለት። በሰዎች ፊት ለእግሩ ስር መዋልዎ እንጂ ምክንያቱም በሰዎች ፊት የእሱን ልክነት እና ፅድቅ አወጁለታ። በሰዎች ፊት የእርሶን ከእርሱ እግር ስር ዝቅ ማለት አሳዩለታ። እንደዛም ሆኖ የሚረካ እንዳይመስልዎ! ከዛ ለሚቀጥለው ዘመን ሁሉ ፈቅ እንዲሉ አይፈልግም!»

አምርሮ ስለተናገረ ይሆን ስለይቅርታ ሌላ ሀሳብ መሰንዘር አልፈለግሁም። ግንስ ምን እንዳደረግኩ ሙሉውን ጥፋቴን የማላስታውሰውን በደል ይቅርታ አድርጉልኝ ማለት ልክ ነው? ከይቅርታው በፊት ሀጥያቱ ይቀድማል። እኔ ደግሞ እሱን አላስታውሰውም። ብቻ ምንም ይሆንና ብቻዬን አልሁን! ብቻ እግራቸው ስር መውደቄ ያደረግኳቸውን ነገር አስረስቶ ባይወዱኝ እንኳን ጥላቻቸውን እንዲተው ካደረገልኝ ምን አለበት? ልቤን ከሚበርደው የማወራው ሰው አጊንቼ ክብሬ ቢቀል አይሻለኝም? ክብር ያለሰው ምንድነው? ኸረ ከሰው ጋር የማይጋሩት ህይወት ምንስ በድሎት የተንቆጠቆጠ ቢሆን ትርጉም አለው?

ከዚህ በኋላ በሚቀጥሉት ቀናት ራሴን ፍለጋ ቤቴን መበርበሬም ሆነ ተናኜን እና ጎንጤን በጥያቄ ማስጨነቄ ትናንቴን ይበልጡን እንድፈራው እና እንድጠላው አደረገኝ። እያንዳንዱን ፍንጭ ሰካክቼ መረጃ ለማግኘት በቅደም ተከተል ሄድኩ። መክፈቻ ኮዱን የማላስታውሰው ዝግ ካዝና፣ 1.2 ሚሊየን ብር ተቀማጭ ያለበት የባንክ ደብተር፣ አብዛኛዎቹ ቀዳዳ የሚበዛባቸው ሰፋፊ ጅንስ ሱሪዎች ፣ ሰንሰለት እና ብልጭልጭ የሚበዛባቸው ጃኬቶች እና ኮቶች፣ የወንድ የሚመስሉ ጫማዎች፣ አልጋዬ ራስጌ ያለው ፎቶ ላይ ያለው ልጅ ሌሎች ፎቶዎች ፣ ሽጉጥ፣ ስልክ ፣ በንቅሳት የተዥጎረጎረ ጀርባ እና ቂጥ ያለው ሰውነቴ ፣ በአጭሩ የተቆረጠ ጥቁር ፀጉሬ ....
 
1. ኮዱን ያላስታወስኩት ካዝና

የተከረቸመ ነገር መቼም ሚስጥር ነው። ይሄ ዝግ ብረት የእንቆቅልሼ ሁሉ መፍቻ መሰሎኝ ነበር። ጎንጤን ካዝናውን የሚሰብርልኝ ባለሙያ እንዲያመጣልኝ አድርጌ ተሰበረ። ውስጡ ያገኘኋቸው ነገሮች የበለጠ የሚያወዛግቡኝ እንጂ ትክክለኛ መልስ የሚሆኑ አልነበሩም። ጥሬ ገንዘብ፣ የጋብቻ ቀለበቶች ፣ የቤት ካርታ እና ውል፣ የወታደር ልብስ ቀለም ያለው የሲጋራ መለኮሻ ላይተር ናቸው። በመጀመሪያ እጄ ፈጥኖ ያነሳው ላይተሩን ነው።

«አጨስ ነበር እንዴ?» አልኩት ጎንጤን
«እኔ ሲያጨሱ አይቼ አላውቅም! እትዬ አስታወሱ እንዴ?» አለኝ በጣም ተጠግቶ አይኖቹን አቦዝዞ እያየኝ።

«ምኑን?» ካልኩት በኋላ ካላስታወስኩ ሲጋራ መለኮሻ መሆኑን በምን አወቅኩ? ብዬ ግራ ተጋባሁ። አገላብጬ እያየሁት አስባለሁ። የቁሶቹ ምስል ጭንቅላቴ ውስጥ አይከሰትልኝም። ልክ በዓይኔ ሳያቸው ግን ምን እንደሆኑ አውቃለሁ። ለምሳሌ ሆስፒታል ከነቃሁ በኋላ እንጀራ ለመጀመሪያ ጌዜ ሲያቀርቡልኝ ሳልጠይቅ ጠቅልዬ እንደጎረስኩት። ሾርባ ከማንኪያው ጋር ሲያቀርቡልኝ በማንኪያው ተጨልፎ እንደሚበላ ማንም እንዳላስተማረኝ፣! ይሄ እብደት ነው ወይስ ትርጉም ይሰጣል? ስለሆነ ነገር ያለን እውቀት የትውስታ አንዱ አካል አይደለም? በአይኔ ቀለበቶቹ ላይ አፍጥጫለሁ እጄ ግን የሲጋራ መለኮሻውን ማስቀመጥ አቃተው። ግማሽ ትውስታ ብሎ ነገር አለ ይሁን? ላይተሩን የሆነ ሰው እጅ ላይ የማውቀው ይመስለኛል። በደም ተጨማልቆ በከፊል የተዘረጋ እጅ መዳፍ ላይ! አይኔን ከድኜ እከፍታለሁ............. እጅ ብቻ! ላይተሩን አስቀምጬ ቀለበቶቹን አነሳኋቸው። አነስ ያለውን ጣቴ ውስጥ አስገባሁት።

«አግብቼ ነበር?» ያልኩት መልስ ባልጠበቀ አጠያየቅ ነው። ሁለቱም ዝም ሲሉ ግን የሚያውቁት ነገር እንዳለ ተሰማኝ። «አግብቼ ነበር?» ብዬ አስረግጬ ጠየቅኩ። ተናኜ ተንተባተበች።

«እኔ እዚህ ቤት በነበርኩበት ጊዜ ብቻዎትን ነበሩ!» አለ ጎንጤ ፍርጥም ብሎ እና ተናኜን በቁጣ ዓይን እያጉረጠረጠባት።
«ከዛ በፊትስ?»
«እኔ የማውቀው የለኝም!» አለ አሁንም ፍርጥም ብሎ። የሚያውቀው እንዳለ ግን ያሳብቅበታል።

የራሴ ካልሆነ የሰው ቀለበት ካዝና ውስጥ ላስቀምጥ የምችልበት ምን ምክንያት ይኖራል? ከቤቱ ካርታ ጋር ያሉትን ወረቀቶች በሙሉ ለመረዳት ሞከርኩ። ብዙው ግራ አጋባኝ። ካርታውም ውሉም ሁለት የተለያየ ነው። ያ ማለት ከዚህ ቤት በተጨማሪ ሌላ ቤት በስሜ አለ። የንግድ ቤት የሚል። ውሉ ላይ ብዙ ያልገባኝ ጥልቅ ነገር አለ። በግርድፉ ከገባኝ ግን አቶ ሙሉ ሰው መሆን አንድአርጌ ከሚባል ሰው ነው ንብረቱ በእኔ ስም በውርስ የዞረው። ውሉ የተፈረመበት ቀን 08-11-2004 ፣ የሰውየው እድሜ 40 ይላል።

«አቶ ሙሉሰው መሆን የሚባል ስም ሰምታችሁ ታውቃላችሁ?» አልኳቸው

«በፍፁም!» አለች ተናኜ። የጎንጤ ዝምታ ግን ሰምቶ እንደሚያውቅ ነገረኝ።
«ምኔ ነበር?» አልኩት

«እትዬ እኔ በወሬ ብቻ የሰማሁትን ነገር እንዲህ ነው እንዲያ ነው ብዬ እንድነግርዎት አያስገድዱኝ። ምናልባትም ሀቁ ከዛ የራቀ ሊሆን ይችላል። እንኳን ዓመታት ያለፈው ወሬ ቀርቶ የትናንት ወሬ እንኳን ከአንዱ አፍ ወደሌላው ስታልፍ ተቀባብታ ወፍራ ነው። » አለ በልምምጥ። ምንም ይሁን ምን ወሬው ለመንገር እንደጎረቤቶቼ ፀብ ቀላል ያለመሆኑ ገባኝ።

«ምንም ይሁን የሰማኸውን ንገረኝ እና ማጣራቱን ራሴው ላጣራ! ምንድነው ወሬው»
2024/09/22 10:27:12
Back to Top
HTML Embed Code: