Telegram Web Link
[ፀሃይ፣ ዝናብ፣ ክረምት፣ ጷግሜ፣ ልብ፣ አዕምሮ እና አግዳሚ ወንበር ]

ሁሉ በትውልዱ በዘመኑ ከግብሩ የሚስማማ ስም ቢሰጠው የኔና አብሮአደጎቼ ስም "አንጋጣጭ" ይሆን ነበር። በመስከረም ብራ ሰማይ ላይ በምሽት የፈሰሱ ከዋክብት ተኮልኩለን የሞቅን ነን። ብሩህ አይኖቻችን ዘበን ተሻግረውም በብዙ ማየት ያመጣው ሞራ
ሊጋርዳቸው ያልደፈረው በነዚያ ቀናት አሻቅበን ያየናቸው የክዋክብቱ ብሩህ ጨረርሮች ለብሌኖቻችን ዘብ ቆመው ነው። ልኬቱን እና ስፋቱን የማናውቀውን ጠፈር የኮከብ ስብስቦች አቀማመጥ በምናውቀው ሰፈራችን ልክ ሰፍረን የጅራታም ድመት ቅርፅ ይዘው የተሰደሩ ክዋክብት መጠን "ከዘይነብ ሱቅ እስከ ጊዮርጊስ መሳለሚያ ይሆናል።" እንላለን። እኔና አብሮ አደጎቼ አንጋጠን ያየናቸው ከዋክብት ተባብረው ያበጇትን ባለ ጅራት ድመት በምናብ ምድር አውርደን ከዘይነባ ሱቅ እስከ ጊዮርጊስ መሳለሚያ ቦታ ስናስይዛት ግርምት እንደ ጣፋጭ አውጥ ፍሬ በትንሽ አፋችን ወስጥ ወደ ነፍሳችን እየሰረገ "ወይኔ ትልቅ ናት በጣምም" እያልን ....የርቀቱ ስሌት ባይገባንም ፊልም ላይ የምናያቸው የፈረንጅ ልጆች መሸት ሲል በየጣራቸው ወጥተው ሌንሱን ስበው ሰማይ ከሚያስሱበት ቴሌስኮፕ አይኖቻችን የተሻለ እይታ ነበራቸው። ከማንጋጠጣችን ብዛት ከክዋክብቱ ጋር ትውውቅ ያለንና ትልቋን ኮከብ ፀሃይን ሰርክ እለት አጅበን ለመሸኘት የተቀባን ነበርን። ከቅዱሳን ታሪክና ገድሎች ውስጥ ሁሌ የሚደንቀኝ ደመናን እንደ ራይድ ታክሲ ጠርተው እዛ ሃጫ በረዶ የጥጥ ባዘቶ መሳይ ነገር ላይ ተደላድለው ከአንዱ ሃገር ወደ አንዱ ሃገር
የሚጓጓዙት ነገር ነው። የልጅነት ቀናት ከስአቶቻችን እንደዘንድሮው ፀሃይ ያልጠነከረችባቸው ነበሩ። የደጋ ሃገር ከሰአት ነፋስ በአንቀልባ የሚያባብለን አይነት ነን፤ፉጨቱ መሃልም እሹሩሩ አይጠፋም። ዛፎች እርሱን ተከትለው ጎንበስ ቀና ይላሉ። ብሩህ ሰማይ ላይ ነጭ ዳመናት ቅርፃቸውን እየቀያየሩ ያልፋሉ። ተፈጥሮ ከሁሉ የሚልቅ የራሷ ኪን አላት። ብዙዎቻችን በልጅነታችን ካሜራ እንዲኖረን እንመኝ የነበረው የደመናትን ቅርፅ እና ሰማይን ፎቶ ለማንሳት ነው። ከረብሻችን ፋታ ካገኘንባቸው የትምህርት ቀናት መካከል "በወንዝ መሃል የበቀለ ዛፍ ለምን ያ ሁሉ ውሃ ከብቦት ይደርቃል?" ብለን ብንብሰለሰልም ልጅነት ደጉ ስለመዓድናት እናውቅ ዘንድ ስላልፈቀደልን መልስ የለንም ነበር። ስለ ትነት እና ደመና የተማርን ቀን ያሉንን ሁሉ የማንቀበል ነበር እና መምህሩ ያሉን ላይ የራሳችንን እምነት ጨምረን "የወንዝ ውሃ
እፀዋትን ለማለምለም አልተባረከም ተንኖ ደመና ሆኖ እግዜር ዙፋን ስር ደርሶ ሲመጣ ዝናብ ሆኖ ተርከፍክፎ ምድራቱን ያለመልማል" ብለን አመንን። ጥርጣሪያችንን ሲያበረታ የሰው ልጅ ያን የበረከት ወቅት ክረምት እያለ ሲጠራው ሰማን። ክረምት የሰማይና ምድር ፍቅር ሲጦፍ መሬት ከእቶን ከሙቀቷ አገግማ፤ ለአዲስ ተስፋ
ለአዲስ አመት ተሰናድታ ራሷን አጥባ ደማቅ አረንጓዴ ፀአደ ቢጫ ተጎናፅፋ ለመስከረም ልትዳር ጷግሜ ላይ ስትሽሞነሞን እማኝ ሆነናል።
እያልን እያወደስናት"ጷግሜ አንቺን መሆን መታደል ነው፤ ትንሽ ሆኖ ብርቅ መሆንን ማን
ታደለ ከአንቺ ሌላ? በሩፋኤል ጠበል ታጅቦ ፍጥረት የሚፈነጭበት ማን ወር አለ ከአንቻ
ሌላ ? ጷግሜ የወር ቅመም በአምስት ቀናት ብዙ ግብር እልፍ ተግባር ምትሸክፊ ፣ለወቅቶቹ መሻገሪያ አንቺ...የአሮጌ አመት መደምደሚያ አንቺ.... ለአዲስ ዘመን ዋዜማ አንቺ የአዲስ ተስፋ መባቻ አንቺ ...ይሄን ሁሉ በጨቅላ እድሜ ማን ታደለ ካንቺ ሌላ" እየዘከርን ጷግሚትን....ህይወት አልፎ ሂያጁ ሁሉ ለተወሰነ ቆይታ አረፍ የሚልባት የመንገድ ዳር ወንበር ናት። በዚያም በጎዳናው የሚያዘግሙ ሁነቶች፣ የሚያልፉ ወቅታትን፤ የእይታችን አድማስ እስከ ቻለ ድረስ ማየት የቻልነውን ተፈጥሮ ሁሉ የምናይበት .....ወደ ጥንቱ ዞር ብለን ልጅነትን ጉርምስናን በስስት የምንቃኝበት ። ልጅነታችን እንደ ታላቁ ተቀማጭ መዝገቡ ዱባለ ትዝብትና ማሰላሰል የሞላው ባይሆንም እሳቢያችን ወሰን አልባ፤ ህልሞቻችን ክንፋም ነበሩና ካለ ከልካይ በነፃ ምናብ እና ሃሳብ ያለፍነው ያ ዘመን አካል ቢሆን ባለ ነጭ አዕምሮው ልጅነት ካለ አእምሮ የሚመስለው የለም። ወጣትነት እንዳያልቅ እየሰሰቱት እንዳይጠፋ የሚለኩሱት፤ ሊያነዱትም ሊያጠፉትም የሚያሳስብ ሻማ ነውና ስለ ተሰጡን ስለሰጠናቸው ስለ ሰበሩን ስለሰበርናቸው ልቦች ብለን ይህ ዘመን አካል ቢሆን ልብ እንለው ነበር። እና እኔና አብሮአደግቼ በያለንበት ዛሬም ጀንበር ለመሸኘት አመሻሽ ደጃፋችን ላይ ስንሰየም በለሆሰስ እንዲህ የምንል ይመስለኛል "እንደ ፀሃይ፣ እንደ ዝናብ፣እንደ ክረምት፣ እንደ ጷግሜ፣ እንደ ወንበር፣ እንደ አዕምሮ፣ እንደ ልብ ያለ የህይወት ንጥረ ነገር ምን አለ?? መኖር ግን እንዴት ነው የሚያምረው ?!"

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Elsa mulugeta
የሞባይል ስልኬ አቃጨለች። አዲስ ቁጥር ነው። አንስቼ ማዋራት ጀመርኩ ...
"ሄሎ ሚኪያስ"
"አቤት "
"አይናለም ነኝ " ...
"አይናለም....አይናለም....ይቅርታ እናት አላወኩሽም...."
"ምነው ከዛሬ ሶስት ዓመት በፊት ጋሽ ክንዱ ሽንሽን ግዛላት ያሉህ ...ልጅ "
ስ....ስ....ስ! የሶስት ዓመት ትዝታዬ ሰተት ብሎ ከአዕምሮዬ ጓዳ ተሰነቀረ!!
ድሮ ልበል እንጂ.. .
ያው ድሮ አንድ ሽማግሌ አከራይ ነበሩኝ። የጠዋቷ ጀንበር ከረር ከማለቷ በፊት በረንዳቸው ላይ ካለች ብርኩማ ዘንድ ተቀምጠው መዝሙረ ዳዊት ያነባንባሉ ። አይናቸው ግን ፈፅሞ የፀሎት መፅሀፉ ላይ አርፈው አይቆዩም። ሀላፊ አግዳሚው ላይ እንከን ማውጣት አይሰለቻቸውም። እንኳን ተከራዮቻቸው ስናልፍ አይደለም የበረንዳው መደገፊያ ላይ ያረፈች ቢንቢን ብብትሽን ታጠቢ ለማለት ሁሉ ይዳዳሉ 😃
ታድያ እኔም ስለሚደብሩኝ ብዙ ጊዜ ከአንጀት ያልሆነ ሰላምታ ወርውሬላቸው ቶሎ ከስራቸው አልፋለሁ።
ሚ......ኪ........ያ......ስ.. .... ምናምን የሚል ድምፀታቸው የሚሰማኝ ከርቀት ነው።
አንድ ቀን ግን አይኔን የማያጠራጥር ቅፅበት ላይ ጉድ አየሁ !
አይ ...አይ ! ያው ወጣት ስለሆንኩ መስሎኝ ነው ብዬ አለፍኩት ያን ቀን።
የዛን ቀን ክስተት ግን ተደግሞ አይኔ ድርጊቱ ላይ ሲጋጭ ሰልስትም አልፈጀ ። የቤት ሰራተኛቸው ን መቀመጫ በከዘራቸው ሲጎሽሙት እጅ ከፉ ያዝኳቸው :)
ሼባው ትንሽ ደንገጥ ብለው.. .
አይናለም ምናለ ይሄን ቀሚስሽን በውሀ ነገር ብታለቀልቂው? አሏት። (በሳቸው ቤት ማስቀየሳቸው ነው። የውቤ በረሀ አራዶች ባንሆንም የውቤ ግሮሰሪ አራዳ መሆናችንን ማን በነገራቸው !)
ጋሼ ቀጠሉ...
"አባይ የኛ.. .ተከዜ የኛ...ይሄ ማነው...እ...እህ ! (ትንሽ እንደ ሳይንቲስት ሌባ ጣታቸውን ግንባራቸው ላይ አኑረው ተብሰለሰሉና ደግሞ ...) አዎ ! ...ዠማ ወንዝም የኛ አይደል ? ...ቀሚስሽን እጠቢ..."
ይሁና አለች ጥልያን.. .ለዛን ቀንም ባልገባው አለፍኳቸው።
ሶስተኛ ጊዜ ይሄ ክፉ እግሬ ክፉ አጋጣሚ ላይ ሲጥለኝ ደግሞ ቤት ኪራይ ለመክፈል በራቸው ድረስ መሄድ !
ጋሼ ለአይናለም ጎንጎ ጫማ ገዝተው እሳቸው ተንበርክከው ሮማንቲክ እየሰሩ ሲያጠልቁላት.. .አየሁ። ቀና ብለው ደግሞ ከንፈርሽን ታልጎረስኩት ብለው ተገለገሉ። አይናለም ገፈተረቻቸው... አሸዋ ላይ እንደቆመ ጎጆ ቤት በጀርባቸው ተገነደሱ ። ድሮንስ መጥሀፉም ቢሆን ሀጥያተኛ አሸዋ ላይ የቆመ ዳስ ነው ይል የለምን ? ግንድስ!
አቤት የሽማግሌ ቅሌታም!
በጀርባቸው ከተንጋለሉበት እጄን ዘርግቼ አነሳኋቸው... ይሄን ያደረኩት ለጋሼ ውለታ አይደለም...ገበናቸውን ስላየው ቢያንስ በይሉኝታ የአንድ ወር የቤት ኪራይ ይተውልኛል ብዬ አስቤ ነበር። ደግሞ መተውም አለባቸው እንጂ!
አያድርገውና ይሄን ክስተት አይቼ ለባለቤታቸው እትዬ ፋንቱ ባቃጥርስ ?...አዎ መብቴ ነበር !
ጋሼ ለአይናለም ጎንጎ ጫማ ገዝተው እግሯን እያሻሹ አጠለቁላት ማለት ብቻ ነበር የሚጠበቅብኝ....እትዬ በዛ እንደ ኢትዮጵያ መከራ በገዘፈ ጀበናቸው ጋሼን ያጠልቁላቸው ነበር።/አናታቸው ላይ ፍርክስ/ :)
ጋሼ "ተባረክ...ይህች አይናለም እኮ መሬቱን አለቅጥ በላርጎ እያጠበችው አዳልጦ ጣለኝ" አሉኝ። እኔ ንግግራቸውን እንዲህ ተረጎምኩት ...አይናለም የረጨችው የውቦት ፆር አይኔን ጠንቁሎት ኑሮ ከንፈሯን ክፉኛ ተጎመዠው ። እርሱን አጉርሺኝ ሰላት እሷ ግን እንደ ቅሪላ ለግታ ቅሌት አጎረሰችኝ ! እንዳሉ ቆጠርኩት።
አይናለም አንገቷን ሰብራ ስራችን ቆማለች።
ጋሼ ከምስጋናው ለጥቀው ብሩን ተቀበሉኝ። ምንም ሼም የሚባል ነገር የለም።
ጭራሽ የሰፈሩን ዘጠኝ ህፃናት ጭርት ሊያሲዝ የሚችል ምራቅ የቀኝ እጅ ጣታቸው ላይ ለድፈው ገንዘቡን አበጥረው ቆጠሩት ።
"ስማ! "
"እኔን ነው ጋሼ ?"
"እህሳ እዚህ ተጎንህ የቆመ መንፈስ አለ ?"
"አቤት ጋሼ "
"እየው ኑሮ እሳት ሆኗል ልጄ። እንደው ለሙከራ ሊጥ አዘጋጅተህ ገበያ ደረስ ብለህ ብትመጣ በኑሮ እሳት ተለብልቦ ሊጡ ዳቦ ይሆናል።"
"እውነት? "
"ገብሬልን ልጄ! ... እንደውም የዳቦው ገፅ እንደ ጋናዊ ከንፈር ም ሊጠቁር ይችላል"
"ይሁና! "
"አይ ምን ይሁና ነው ? ቤት ኪራይ ጨምር !"
ጭራሽ የጋሼን ገበና በሸሸግሁ ቤት ኪራይ ጨምር ?
"ጋሼ "
"አቤት ልጄ "
"እትዬ የሉም ?"
"ምነው ለምን ፈለካት ?"
"ጎንጎ ጫማ ለአይናለም እርሶ ስለገዙላት እሳቸው ደግሞ ሽንሽን ቀሚስ እንዲገዙላት ልንገራቸው ብዬ ነው"
ጋሼ ቆሌያቸው ሲገፈፍ ይታወቀኛል።
ቅዱስ ገብርኤል መብረቁን የሰደደ መሰላቸው።
ሳቁ....ሳቃቸው የውሸት ነው።
"ቂ......ቂ..... ቂ ....
አይ ልጄ ጎበዝ ተጫዋች እኮ ነህ። ደግሞ ቅን አሳቢ ነህ እሙት! ..."
"አይደል ?"
"ገብሬልን ስልህ! " ጋሼ ቀጠሉ ...
"ግን ያው ከአንድ ቤት ሁለት ወጭ ከሚወጣ ያሁኗን የቤት ኪራይ ልመልስህና ባይሆን ሽንሽኑን አንተ ግዛላት! "
ገንዘቤ ተመለሰ። ነቄ ለነቄ እንጠጣ አረቄ ።
"ውይ አስታወስኩሽ አይንዬ !"
"ምነው ሚኪያሴ ሽንሽኔን ሳትገዛ ሰፈር ቀየርክሳ ? የሰው አደራ ውጦ ዝም ግን አያስተዛዝብም 😃

@getem
@getem
@paappii
#ሚካኤል አስጨናቂ
አምስተኛ ክፍል ተማሪዎች ሳለን አንድ ተዓምር ክፍላችን ውስጥ ተፈጠረ። መነሻው ከየት እንደሆነ ያልታወቀ ሰላቢ አጠሬራ ለኤደን ደረሳት ። ኤደን እናቷ እንደሞተችባት ነገር ስቅስቅ ብላ አለቀሰች። ሰለስቱ ያልወጣ ትኩስ ለቅሶ ።
የለቅሶው ምንጭ የሆነ ሰይጣን ፈልፈላ I love you የሚል ፅሁፍ ፅፎ በእረፍት ሰዓት ደብተሯ ማህፀን ውስጥ በመሸጎጡ ነው😊
መቀመጫውን በቅጡ ካልጠረገ...ጡት ከጣለ ሰባት ዓመታት ካልቆጠረ ፈላ I love you የሚል ፅሁፍ ጡት እንኳ በቅጡ ላላጎጠጎጠች ሴት ሲላክ አይከብድም ወይ?
ከሁላችንም በእድሜ ከፍ የሚለው ነፍሰ ቀጭኑ አለቃችን ማሙሽ እንደ ሀይለስላሴ አንበሳ አጓራ!
በቃ የዛ ክፍል ወንዶች አለቀልን !
አንዲት ሰላቢ የኤደን ጓደኛ ደግሞ እጅግ አስደንጋጭ ሀሳብ አፈለቀች ።
ያቺ ልጅ ጁንታ ናት !
የሁሉም የዚህ ክፍል ወንዶች እጅ ፅሁፍ ይፈተሸ ተባለ። እኔን ጨምሮ የብዙ ወንዶች ልብ አታሞዋን ደለቀች። ልቤ ጎንደር መሸታ ቤት ገባች። ድም.. ..ድም.. .ድው.. .ድው.. .ድብልቅ!
የኋላ ወንበር የሚቀመጠው አቡላ ፅሁፉን ፅፎ እንዲያሳይ በጓድ ማሙሽ ተፈረደበት ።
I love you ብሎ ፃፈ። የእናቱ አጋዥ መልዓክ ቅዱስ ገብርኤል ከጉድ አወጣው ።
አለቃችን ለጥቆ ወደ እስጢፎ ቀጠለ።
እስጢፎ ገና ትምህርት በተጀመረ ሁለተኛው ክፍለ ጊዜ የጮርናቄ ሽታ የሚያስመንነው ወመኔ ነው። የብርሀኑ ይሁን የጨለማው ጌታ ከመዓት አወጣው።
ወደ ቦጌ ተቀጠለ።
ቦጌ እናቱ ጠላ ለመጥመቅ የሚያዘጋጁትን ቀለጦ ድምጥማጡን በማውጣት ፈላው ሁሉ ያደነቀው ጉደኛ ልጅ ነው። እንዴት እንዳለፈ እንጃ! ብቻ እሱም አይደለም ተባለ ።
ቀጣዩ እርምጃ ወደ ቸካዩ ተማሪ እዮቤ ቀጠለ ። እዮቤ እንዴት በዚህ ተልካሻ ነገር እጠረጠራለሁ ብሎ ትንሽ ከተነፋረቀ በኋላ I love you ብሎ ጣፈ ። ፅሁፉን ትኩር ብሎ ማሙሽ ካየ በኋላ ይቅርታ ጠየቀው። ከእዮቤ በፊት የፃፈ ጀማ ማንም ይቅርታ ግን አልተባለም።
ማሙሽ የኪዳነምህረት አገልጋይ የነበረው ዳንኤልን ባላየ ላሽ አለው ። የዛ ሁሉ ታቦት ጌታ በረቂቅ ጥበቡ ይሄን ጉድ አሻገረው ።
ማሙሽ ቀጥሎ ጴጥሮስ የሚባል ጴንጤ ልጅን አፃፈው ። የፓስተሮች ጌታ መንጥቆ አወጣው ።
የዛች የኡቃቢያም ልጅ ደጀኑም ጣፈ ። የእናቱ ቆሪጥ ከዚህ ጉድ ሰወረው ።
ከጎኔ የነበረው አህመድ ሽንቱ ጭርቅ አለ ። ካኪ ሱሪው በሰበሰ።
I Love you ብሎ ጣፈ ። አላህ ደጉ አላህ መሀሪው የት ሄዶ ?
ከዚህ መዓት ስውር :)
ቀጥሎ ማሙሽ ወደኔ ተምዘገዘገ ። በቃ እኔ ጋር እስኪደርስ ያለውን moment የሆረር ፊልም በሉት ። ሳጥናኤል ከነ ጀለሶቹ የቀረበኝ መሰለኝ ።
እግዚኦ በዛ ላይ አስተያየቱ !
ግልምጫው ብቻ ገሀነም ዶለኝ :)
እውነቱን ለመናገር እኔ በዛን ጊዜ ተረት እየፃፍኩ ለክፍል ልጆች አቀርብላቸው ነበር እንጅ የሴት ልጅ መሻት ተልቤ ዘልቆም አያውቅ!
ደግሞ ያስጠረጠረኝ ነገር የፍቅር ተረት ማብዛቴ ነበር።
እኔን ብሎ ደራሲ...እኔን ብሎ ሮማንቲክ ...እኔን ብሎ ተራኪ !
እነሱን ላዝናና በጣርኩኝ ...ተጠረጠርኩኝ (ይሄ ነገር ገጠመ መሰለኝ 😃)
በቃ ያለኝ አማራጭ ከትክክለኛ ፅሁፌ ውጬ ነገሩን አንጋዶ መፃፍ ብቻ ነው።
I.. ..LAVI YAOU ብዬ ጣፍኩኝ። እንጃ ብቻ ቃላቱን ማሳሳቴ ከጉድ ያወጣኝ መሰለኝ።
ማሙሽ መንኮራኩር እንደሚያመጥቅ ሳይንቲስት ጥሁፌን ለደቂቃዎች ትኩር ብሎ ከዛ በአጭር ወረቀት ከተፃፈ ደብዳቤ ጋር አነፃፀረ ።
አነፃፅሮ.. . ከክፍል ወጣ ።
ከዛ በኋላ የማስታውሰው ብቸኛ ነገር ቢኖር መምህር ሀንዴቦ የሀረር ቄሮን የሚያህል ዱላ ይዘው መምጣታቸውን ነው።
እንደ ጀት ፈጥነው ስሬ ተገተሩ ።
አንተ ? ነው ያሉኝ.. .
አንተ !
እንደ ወረብ ከበሮ ተደለቅሁኝ :)
አቤት ሼም !
አቤት ውርደት!
የክፍል ተማሪዎች ግልምጫ እሳት ሆኖ ለበለበኝ። ገና በእረፍት ሰዓት "ዬዩ....ዬዪ " ምናምን የሚሉ ነቆራዎች አሉብኝ።
ተዟዙሬ.. .እንደ ኳስ ከተለጋሁ በኋላ መምህራችን አንድ ሰቅጣጭ ቃል አወጡ።
ነገ ወላጅ ይዘህ ና !
በጀርባዬ ልወድቅ ምን ቀረኝ! ነፍሴ...ልቤ...አንጀቴና ጉበቴ እኩል ሸኑ ።
ስንት ጉድ ተፈጥሮ ካለቀ በኋላ ግን ያን ደብዳቤ የፃፈው ዳቆኑ ዳንኤል እንደሆነ ተደረሰበት። ነገሩ ስለተረሳ ብዙም አልተካበደበትም።
ከዛ በኋላ ኤደን የምትባለውን ልጅ ባየኋት ቁጥር ትደብረኛለች :)

@getem
@getem
@paappii

@Mikael aschenaki
ሥዕልን ለማሳል በ +251984740577
ወይም @gebriel_19 ላይ ፎቶ በመላክ በ ተመጣጣኝ ዋጋ ማዘዝ ይችላሉ!
#ሥዕል_ብቻ የቴሌግራም ገፅ


@seiloch
@seiloch
አንዳንዴ በሽምግልና የማያልቅ ነገር አለ። በፍርድ ቤትም ለመፍታት የሚቸገር። ተፈጥሮ
ከሽምግልናም ከፍርድ ቤት በላይ ወሳኝ የሚሆንበት።
:
ባልና ሚስት በሽምግልና መስማማት አቅቷቸው ፍርድ ቤት ሄዱ። ፍርድ ቤት ሃብታቸውን
እኩል እንዲካፈሉ ተወስኖ ተስማሙ። በጋብቻ ውስጥ ያፈሯቸውን ሶስት ልጆቻቸው ግን
እንዴት እንደሚካፈሉ መፍትሔ ጠፋ።
ባልና ሚስት ተመካከሩና ተጨማሪ አንድ ዓመት አብሮው በመኖር በሚቀጥለው ዓመት
አንድ ልጅ ጨምረው ከዛ በኃላ ለመለያየት ተስማሙ።
:
ቀጣይ ዓመት ደርሶ ፍርድ ቤት ሲመጡ ሚስት መንታ ወልዳ ቀረበቸ። አምስት ልጆች
ሆኑ።
በድጋሚ አንድ ዓመት አብረው ኖረው በቀጣይ ዓመት አንድ ልጅ ወልደው ለመመለስ
ተስማምተው ሄዱ።

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Abinet Addis
ዘመቻ አልሄድክም ለምትሉኝ ጓዶች ቤቴ ውስጥ የገጠመኝን ትግል ታውቁታላችሁ ወይ?

ወንድ ልጅ ማሳደግ ማለት በጁንታ መያዝ መሆኑንስ ታርፉታላችሁ?

ባባ እንደ ጌታቸው ረዳ ቦርጭ የገዘፈውን ኩባያ ወረወረው ! ... ደግሞ እኮ የአወራወሩ ሀይል ! ... ጁንታ ያስወነጨፈው ከባድ መሳሪያ የአከራዬ አናት ላይ መዓት ሆኖ ወረደ 🙂

ኡኡ ነው ያሉት 

አጋነንክ አትበሉኝና እሪ.....ሪ.... ብለው ግቢውን ደበለቁት ።

በዛ ላይ ያ መከረኛ CNN ህወሀት አዲስ አበባን ከቦታል ብሎ አሳምኖዋቸዋል። 

ሰላማዊ ዜጋ ላይ መድፍ አሉ ባለቤታቸው።

በዛ ላይ የኩባያው መሰበር ። ከዚህች ቀን ቀደም ምን ከሚያክል ብፌ ላይ ወድቆ እኮ ጭራሽ አዲስ ሆኖ ነው የተነሳው 🤔

በዛች ቅፅበት ግን ፍርክሽ አለ ...ቡም !

ያቺ እኔ ከተከራየሁበት ክፍል የተከራየችው የሺ ደግሞ ጩኸቱ ላይ ሌላ የራሷን ታለንት አከለችበት ። እማዬ ድረሱልኝ! 

አቤት ለአከራይ ማሽቃበጥ

ደግነቱ "ኸረ ለኔም አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ይድረስልኝ" ብለው ኩም አደረጓት ።

ደግሞ ያ የእንጀራ በወጥ ታጋይ ባሏም ቆመጥ ይዞ ወጣና እንደ ደህና የባህል ሙዚቃ ጨፋሪ ፎከረ !

ከበላይ ሆኜ በቁምጣው ስር የሚታይ ታፋውን ቃኘሁት ። ሰማኸኝ በለው ማረኝ!

ሲኦል ያሉ ፍጥረታት ላይ መከራ ለመጨመር በሚመስል አረጋገጥ ነው በዛ ሞፈር እግሩ ምድሪቷ ላይ የሚንጎማለለው። 
ምድር ወዮ ብላ ያለቀሰች ይመስለኛል ወትሮም ራመድ ራመድ ሲል ...

የግቢው መሰረት ተናጋ ! 

የአንድ ዓመት ከምናምን ወር ህፃን አልቆጣው ነገር ሆኖብኝ "እንዴ ባባ ?" የሚል ደንጋጣ ጥያቄዬን ሰነዘርኩኝ። አሁን ይሄ ጥያቄ የኒኬል መደቀኛ ያስወረውራል ወይ? 🙂

ኪችልችልችልችል.. .

ሰማኸኝ በለው (ውይ ያማነው ከበደ ) ፉከራውን ጥሎ በረረ ... 

አቤት ግዙፍ ሰው ባሏ በካልቾ እንደጠለዛት የሴት ሲሮጥ.. .

እማምዬ አለ ።

"ሰላማዊ ዜጋ ላይ ቦንብ ?" ብለው ለጠቁ ማዘር 🙂

እሺ ኒኬሉ ደግሞ ጣሪያው ላይ ጮሆ ቢያበቃ ምናለበት?

ሴራሚኩ ላይ ወርዶ ተቅጨለጨለ ።

ይህን ጊዜ ጋሼ ደምግፊታቸው ሶፋ ላይ ጥሏቸው ይሆናል መቼም !

ቂጭልልልልልልል ቀጭ....

ደቂቃዎች ሲያልፉ ከየትኛውም ክፍል ድምፅ ጠፋ ። ባባን ይዤው ወደሳሎን ወረወርኩና ወደ መሬት ተንደረደርኩ ።

አቶ ከበደ (ሰምን መቼም መልዓክ ያወጣዋል አይደል የሚባለው ?)...ለደቂቃዎች በመስኮት ሲያተኩር ቆይቶ የኔን መምጣት ሲመለከት ተስፈንጥሮ ወጣ ።

አወጣጡ ደግሞ እንደ ዱር አንበሳ እየተንጎማለለ እኮ ነው። ... የሆነ ነብር ገድሎ ቆዳውን ለምስክር ለብሶ የመጣ ጀብደኛ እኮ ነው የሚመስል ።

ሳቀ ...

"ሃሃሃ..... ማዘር የመጨረሻዋን ሳቅ የምንስቃት እኛ ነን አላልኩም ? አይዞን ተረጋጉ ኒኬል ነው 🙂

ከደቂቃዎች በኋላ ጋሼ ስክም ስክም እያሉ መጡ ።

"አሁንስ በዛ ! ከነገ ጀምሮ ቤቴን..."

ማንም አከራይ ተከራዩን እንዳያስወጣ የሚለውን አዋጅ ለማሳየት ስልኬን መዳበስ ጀመርኩኝ 😋

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Mikael aschenaki
አለ አይደል አንዳንዴ?... ማለት አበዛለው!.......ውስብስብ..... ብናገር ሰው ሊረዳው የማችለው ቢረዳውም ፈራጅ ይሆናል ብዬ ላሰብኩት ነገር...... የምመርጠውም የሚመጣልኝም ቃል ቢኖር አለ አይደል አንዳንዴ? የሚል ነው...... ብዙ ማስበውና የምደሰትበት ነገር አለኛ!..... ለሰሚ የሚያስገርም አይነት ለምን የሚል ጥያቄ የሚጭር አይነት.....እና እኔ ቀለል አድርግና.....ህመሙን ሀሴቱን ለራሴ በመተው
መናገር ሲከብደኝ አለ አይደል እላለው!
አዋ አለ አይደል አንዳንዴ ... ተንደርድረሽ እቀፊው እቀፊው ይለኛል .... ለምንስ ቶሎ ምንስ
ቢፈጠር ሌላ አለም ውስጥ ካስገባሽ ክንዱ ትነጠያለሽ ይላል አካሌ........ ቀን ማታ ናፍቆቴ
ነው ይኸው ደሞ ሁሉንም ሳልናገር ትቼው አለአይደል ልል ነው....ቀርቦም እርቆም የሚናፈቅ
ሰው ነው! .. አለ አይደል አንዳንዴ .........እንዝላልነትም ሲጨመርበት ናፍቆት ይበረታል መሰለኝ አይኖቻችን በተገጣጠሙ ጊዜ አንገቴን ሰበር .... ወይም ዘወር ማድረግ ስራዬ ነው....እወዳቸዋለው እፈራቸዋለሁም ........ከአፍህ ተቃራኒ እንዳይሆኑብኝ ይሆን? አሊያም
ተመሳሳይ ሆኖ ብርቱነታቸውን እኔ ላይ እንዳያረጋግጡ? ....... ወይም ደግሞ የእኔን ዐይኖች ጓደኛህ እንዳይሆኑ ሰግቼ....... ደካማነቴን እንዳያሳብቁብኝ ፈርቼ...... አቃጣሪ እንዳይሆኑብኝ እና እያንዳንዷን ሀሳቤን ሹክ እንዳይሉህ ለማምለጥ...... እሸሻቸዋለው...... በየትኛው ምክንያት እንደሆነ ባይገባኝም ላያቸው፣ በጥልቀት ልመረምራቸው ፈልጌ እተወዋለሁ ........

አትኩረህ እንዳታየኝ ደግሞ ስስ ነህ ፈራሀለሁ!...

@wegoch
@wegich
@paappii
#Muna Abduselam Mu
Forwarded from ዘፈን ብቻ (Ribka Sisay)
ዛሬ ቀጠሮ አለን!!!
ሰኑ . . . የጠዋቷ እማማ . . .ከሃዘን የተገነባች ሳቅ
Semur እንደፃፈችው!
- - - - - - - - - - - -
ሰኑ - ቢሮ ቡና እምትሰጠኝ ልጅ አፍንጫዋ ላይ ከጓደኛዬ እና ከTupac ቀጥሎ እሚያምር piercing ያየሁት እሷ ላይ ነው! ታምረኛለች ጎበዝ ናት፥ ንፁህ ናት ፥ያላትን ጽድት አድርጋ ትለብሳለች ብዙ አታወራም! የሆነ የተመታ ኮሌጅ ለዲፕሎማ ትማራለች፣ ቡና ታፈላለች፣ ታስተናግዳለች፣ ሁሉንም እንደ አመሉ ትንከባከባለች! ተስፋ ቢስ መሃል ደማቅ ተስፋ አላት፤ አይኗ ላይ የሚታይ! ዋጋዋን ታውቀዋለች፣ አትናገረውም፤ 'እዚህ አታዩኝም በጥቂት ግዜ ውስጥ' አትልም፣ ግን
ይገባናል እሷም ይገባታል ! ተሰብስበው የሚመጡ የገጠር አራዶች አሉ፣ እንደ እሷ እንደኔ እንደሁላችንም ድሃ ናቸው !ሁሌ ይመጣሉ - በትንሽ ብር የተሻለ ምግብ ፍለጋ ! 'ያስጠሉኛል' ትንሽ ቃል ነው! የገጠር ሰው ስነ ምግባር እና ጨዋነትም የከተማ ሰው easy spiritም የላቸውም። አዋህደው ያመጡት ነገር ቆምጫጫ ባለጌነትን ብቻ ነው! እናቴ እንዲህ ያሉትን ሰዎች የምትጠራበት ቃል በደንብ ገላጭ ነው "ጅምር ጆሊ" ስድነት ላይ ድርቅና ተጨምሮ ናቸው የገረጣ ቁርጭምጭሚታቸውን የማይሸፍን ገባጣ ቀጫጭን እግሮቻቸውን ደጅ ያሰጣ
አጭር ካልሲ ይለብሳሉ። ሊደርሱበት የሚፈልጉት" ክትምና" ከጉልበት መለስ ያለ ካልሲ
መልበስ መጀመሩን አልሰሙም። አስቀያሚ ጂንሶች ከኑሮዋቸው በላይ ከገረጣ ቲሸርት ጋር
ይለብሳሉ ብርድም ቢሆን እየተንቀጠቀጡ በቲሸርት ናቸው! ወይ ከዝነጣው ወይ ከምቾቱ
አልሆኑም! ሁሉም በየተራ ይጠሯታል . . .በሚረብሽ መልኩ! እንድትታዘዛቸው ብቻ አይደለም ! ማሳነስ
አለው "ማነሽ እንቺ ባላገር" ይላል፤ ምናልባት ቢጠያየቁ ዘመድ ናቸው! ማንነቱን በገዛ እጁ
ስድብ አድርጓል፤ ቢገባው የናቀው ራሱን ነው! እሷን ስላሳነሰ ከኛ መሃል ከተሜ ብሎ እሚሸልመው የለም ! መልዕክቱ "ማን ሆነሽ ነው የናቅሽኝ?" ነው። በዛች በምትንቋቋ ስልኩ
ስንቱን እንባ አንብቶ ዘግታው ይሆናል፤ "እኔ እኮ ለቁም ነገር ነው" ላለበት አፉ "አላማ አለኝ" ብላው ይሆናል (ሂሂሂ 'የድሮ ቃል' ነው ይሉናል ለማንም ከፍቶ መስጠትን የዛሬ ሊያስመስሉት!)
አሉ ደሞ የከተማ ባላገሮች! ጋንዲ ከመወለድ ጋር የሚመጣ የዝመና ፓኬጅ ያለ የሚመስላቸው ድልብ ሰገጦች! ድህነት ውስጥ ተዳልድሎ የሚኖር ዙርያን ያለመገንዘብ፣ የተሻለ አለም እንዳለ ያለማወቅ፣ እዝች አፍንጫ ድረስ ብቻ ማሰብን የመሰለ ድንቁርና ከተማ ገጠር ሳይል ድሃ ቤት ያለከልካይ እንደሚኖር ይረሱታል! ሁለተኛው ጀማ ናቸው፤ ባብዛኛው ሴቶች ናቸው!
ከተረከዛቸው በላይ የከረደደ እንጀራ የያዘ ምሳ ዕቃቸውን ከፍተው ያሻምዳሉ። በጣም ብዙዙ ልጆች አሏቸው እሚያማምር የፈረንጅ ስም ያላቸው፤ ማክቤል ፥አለን ፥ካለን ፥አሜን fancy ስም ሰጥተው ጥንት እነሱ እንዳደጉት ያኖሯቸዋል . . . "ውይይ አታቅብጪው ፥እንዴ ልጅማ መገረፍማ አለበት" ይባባላሉ። እዚህ ማዘር ቤት ከስራ ጋብ ሲሉ ይመጣሉ። ምግብ
አይበሉም፤ ቡና ፥ሻይ ይጠጣሉ። ባሎቻቸው በቂ ብር አይሰጧቸውም፣ ኑሮን መደጎም የነሱ
ድርሻ ነው ! ከልጆቻቸው፣ ከገዳማት ፥ ከአለቆቻቸው ሃሜት ፥ቢሮ ካለችው ዘናጯ ልጅ በተረፈ ሰዓታቸው ያበሻቅጧታል። "ይቺ ባላገር ጠገበች ሆሆሆ" ይላሉ። በዚህ ደቼ በበላ ኑሮ እንደሷ አይነቷ ጠግቦ እንደማያድር አያጡትም፤ እንለፋቸው ክምር ሽመል ናቸው !ቀና ብሎ የሄደን የማስጎንበስ የማህብረሰብ ልማዳቸውን ይወጣሉ !ብዙ ቁጭት ፥ቅናት ፥መበለጥ አለባቸው። ሊረሱት የፈለጉት አፍላነት አላት ፥በትጉህነት ራሷን ካለችበት እንደምታወጣ ታውቃለች በዛ ላይ ራሷን አትጥልም ! እነሱ ያን አልነበሩም፣ ወይ እንዲያ ሲሆን ብቻ እንደሆነ መውጫ ያለው አያውቁም! ከትናንት ቂም፣ ከዛሬ በቀል አለባቸው፤ የተረሱ ናቸው! "ማነሽ አንቺ!" (በማበሻቀጥ) . . .የማይከፈልበት ወጥ ጭማሪ ሲፈልጉ እስከ ምንጅላቷ ያቆላምጧታል! "ምንድነው ቡናው ፥ ሻዩ ሰው እንዴት ቡና ይጠፋዋል?" እንደ እናቶቻቸው አፋቸውን እያጣመሙ. . . ልባቸውም እንደአፋቸው ጠማማ ነው ! ቡናው ቆንጆ የሆነ ቀን እርስበርስ እየተልጎመጎሙ "ያን ነገር አድርገውበት ሙች!" . . . "እዚህ ቤት ቡና ስጠጣ ቃሩ ራሱ መች ያስቀምጠኝ" . . . "የ እንትና እህት አጎት ጠጥቶ ተመረዘ" . . . መሃላቸው ገብቼ እንኳን ጫት ወደል አይጥ ቢኖርበት ትጠጣላችሁ ብላቸው ደስ ይለኛል ! ይከታተሏታል . . . "ዛሬ ደሞ ምንድን ነው የለበሽው? እይይይይ! ባህላችንንማ አትጣሺ! አንቺ ጨዋ፥ ሃይማኖተኛ ልጅ ተይ!" . . . ይህን ባይ መካሪዋ የአለቃዋ ቅምጥ ናት። ለሷ ጭን ግርድና ያልተጠራ ባህል ለምስኪን ቡና ሻጭ ቆንጆ ቶፕ ግዜ ይጠራል !
ሰኑ እግር እግሯ ስር እሚሄድ ሰፊ የኔቲቭ አሜሪካዊ ፊት ያለው ድመት አለ። ምናልባት ሪኢንካርኔት ያደረገ keanu የሚባል ጎረምሳ ይሆናል! የሚወዷትን ይወዳል፣ የሚጠሏትን
ለማጥቃት ቀን ብቻ ነው የሚጠብቀው! አስልቶ ወንበር ስር ተደብቆ ይነክሳል። ያስደስተኛል። የሱ ፍትህ ጥርሱ ላይ ናት። ድመት አልወድም ይሄ ግን ያሳዝነኛል ደግሞም ያስደተኛል ! አስቀያሚ ቆሻሻ ሆኖም ኩሩ ነው፣ ከነ ግማቱ እንደ አዛዥ ነው ኩፍስ እሚለው። በጀበናው እና በዱካው መሃል ባለች ክፍተት ዝርፍጥ ይላል ጭራውን እሷ ላይ ጣል አድርጎ! ባተሌ ስትሆን ወይ ልብ የሚላት ከለለ ቀስ ብላ ትዳብሰዋለች ! ሰው ካለ አትነካውም፣ አፋቸው መዓት ነው! ከአፍንጫቸው
የማይፋታ ጣታቸውን እየቀሰሩ ስለ ንጽህና ሌክቸር ይሰጣሉ! Keanu ዝርፍጡ አንጀት ያባባል - በሷ ላይ ያለው እምነት ! እሷ ካለች ከፌስታል ጋር፣ ከወንበር ጋር፣ ከህፃናት ጋር፣ ከወንበር ጋር ይላፋል። ልክ መተጣጠብ ስትጀምር ቆቅ ይሆናል ! መሄጃዋ እንደደረሰ ያውቃላ! ግማሽ መንገድ ተከትሏት ሄዶ "ችፍ" ሲባል እየተልጎመጎመ ይመለሳል። ነግቶ እሷ እስክትመለስ እዛች ምግብ ቤት ዝር አይልም! በር
ላይ የእንስሳ ቀልቡን አንቅቶ ይጠብቃል። እሷ ከሌለች አደጋ እንዳለ ቀልቡ ይነግረው ይሆን
ነው ወይስ ያስጠሉታል ? ደጃፍ ያሉት ሊስርትሮዎች ስር እየተርመሰመሰ ይቆያል- ጓደኛው እስክትመጣ!
- - -
የጠዋቷ እማማ ሰፈሬ ኩርባው ላይ ይቀመጣሉ - "ኬኔዲ ባር" ከምለው የተመታ ጨብሲ ቤት ጎን። ኬኔዲ ባር አሳዛኝ አሳዛኝ ዘፈን የማያጣ ብዙ ግዜ የኬኔዲን ዘፈን የሚከፍት ግሮሰሪ ነው። ደማቅ
ሰማይ የመሰለ ሰማያዊ የተቀባ ብርሃን የማያስገቡ ትናንሽ መስኮቶች፣
ቀይ፣ ቢጫ፣ ሰማያዊ ድቡልቡል ዜሮ ሻማ መብራቶች . . . ብዙ ብዙ ያረጁ፣ ትዝታቸውም ያረጀ የጥንት ሰዎች - በዛ ዘመን ስለተበላ ጥብስ፣ ስለ ኪነት፣ ዘመቻ፣ መንጌ፣ መኢሶን፣ ኢህአፓ፣ አብዮት ጥበቃ ምናምን የሚሉ . . . አራት ልጅ ወልዳ የልጅ ልጇ መንታ ወልዳ አያት ስለሆነች የድሮ ገርላቸው አይናቸውን ጨፍነው
በተመስጦ የሚያወሩ፣ ከኑሮ ጋ በሩቅ የተላለፉ፣ የዚህ ዘመን ሆነው ጥንትን የሚያመልኩ፣ "ድሮ ቀረ " እያሉ የሚብሰለሰሉ ችጋራም ወጣቶች፣ በቢኪኒ ዘመን ስለ ሰፊው ፓንት መጥፋት የሚጨነቁ ፊታቸው ካለው ድንቁርና ስለ 666 የሚብሰለሰሉ ስራ አልባ ሃሜተኞች መሰብሰብያ ነው ! እማማ እዚህ ቁጭ ይላሉ ጠዋት ወጥተው፤ ለማኝ ናቸው (የኔቢጤ ምፅ ምፅ ቢጤነትም የኔነትም በሌለበት።) ከሰው ፊት ምፅዋት ለሚጠብቅ፣ ችግሩን፣ ገበናውን፣ ክብሩን ሸጦ ነዋይ ለሚጠብቅ ያልተገባ ፀዳል አላቸው። ብሩህ ነው ፊታቸው ! ከወልጋዳ ጥርሳቸው የሚመነጭ ውብ ሽንገላ የሌለው ሳቅ አላቸው።
ከሚቀመጡበት ኩርባ የጠዋት ፀሃይ ግማሽ ገላቸውን ታለብሳቸዋለች። ከሁሉ ጋ ይስቃሉ! ከሁሉ ጋ ያወራሉ! እግራቸው ስር እሚጋደም የጥጥ ባዘቶ የመሰለ ግዙፍ ውሻ አለ፤ ሁሌ እንደተኛ ነው ! እያወሩም ምን እያሉም የሆነ ነገር ከላዪ ላይ ያነሳሉ፤ ሁሌም! አልፎ ሂያጁን ሁላ "ደህና ዋይ እማይይይ" . . . " በሰላም ይመልስህ የኔ ልጅ" ይላሉ። ሲያዩኝ "እንቱፍ እንቱፍ" ወደ መሬት እየተፉ . . . ሽንገላ የለውም፣ ቅርበታቸው ብመፀውትም ብተወውም ያው ነው ! ያን እንቅልፋም ውሻ ከየት አምጥተውት ነው? ልብሳቸው ለምን አይቆሽሽም ? የሱስ ቆሻሻ
ለምን አያልቅም? የት እየዋለ ነው እንዲህ እሚተኛው? . . .
- - -
"የምወዳት ልጅ!" እላለሁ "ማናት? ምንሽ ናት ?" ሲሉኝ! ጓደኛ እንዳልል ቲኒጥ ነች፣ እህቴ እንዳልል እንደ እህት አይደለም እምወዳት። ባዕዴን እንደ እህት የወደድኩት አንዴ ነው ከሷ ሌላ ሰው የሚያስገባ ቦታ የለኝም ! 'ቲንጧ' ብላትም የሰማይ ስባሪ ናት። ብዙ አንቀራረብም ግን እወዳታለሁ። ቡዳ ቀልቤ ሳይጨነቅ ከሚያርፍባቸው መሃል ናት። ከብዙ መውደድ ጋር የተቀላቀለ ሃዘን ታሳዝነኛለች! ይባላል? በጣም ደስተኛ ስለሆነች ታሳዝነኛለች! ይሰምር ይሆን?
እሚያስተጋባ ሳቅ አላት . . . "ሃሃሃሃ..." ማለት ከጀመረች የደነቆረ እስኪድን፣ የታወረ እስኪበራለት ታስተጋባለች ! ችምችም ትንንጥ ጥርሶች አሏት። ስትስቅ ከፊቷ ብርሃን ይቀዳል። አለም በማትፈቅደው ልክ ደስተኛ ናት። የእርግብ ላባ የመሰለ ቅልል ያለ ነፍስ አላት። ደስታዋ ይጋባል! "አንቺ ፀሃይ!" ይሏታል ሌሎች፤ ሁሉም ይልካታል፣ ሁሉም ይወዳታል፣ ሁሉም ይጋብዛታል! እምትይዘው ምንም የለም ሁሉም የተሰጠ ነው ! እኔን ያስጨንቀኛል፤ የሆነ ትልቅ ሃዘን ቆፍራ የቀበረች ይመሰለኛል። "እኔ የእናቴ ዲቃላ" ትላለች፤ ይስቁላታል። የደቀለው ሰውዬ ታፍሮ ተከብሮ "የትዳር የማገር፣ የአብሮነት
ተምሳሌት" ተድርጎ እየኖረ መናቅን መልመዷ ያበሳጨኛል!! እንደሱ አትበይ እላታለሁ፤
"እውነታው እኮ ነው!" ትለኛለች። ሁለት ዘልዛሎች በወሰኑት ነገር አመለካከቷን እንዳንሸዋረሩት አልነግራትም! "በቂ ነሽ" ብላት ደስ ይለኛል! "አስመሳይ አንድ አይነት ልብሳቸው መሃል ስላልገባሽ፣ 'አባዬስ?' ስትይ 'ፊልድ ነው' እያሉ ስላሳደጉሽ፣ ተማሪ ቤት 'እህቶችሽስ?' ስትባይ 'የአባቴ ልጆች ሰለሆኑ እናታቸው ጋር ናቸው' ማለት አሳፍሮሽ 'የለኝም' ስላልሽ አታንሽም! የተሳሳቱት ጉራማይሌ ኑሮ ውስጥ አንድ አይነት ለባሾች ናቸው፣ ቤተሰብ ወጥ አይደለም ደም ብቻም አይደለም!" ልላት ብዙ ግዜ ያምረኛል!
አይን አይኗን ሳያት በለመደችው ሩህሩህነት ታቅፈኛለች። እቅፏ ይሞቃል! "I am a huger
ችግርሽን እስክትረሺ ነይ ልቀፍሽ" ትለኛለች፤ እስቃለሁ! መታቀፉ ከኔ በላይ ለሷ እንደሚያስፈልጋት እንደማውቅ አልነግራትም! በዝምታ እንተቃቀፋለን! የማይመለከተንን
አውርተን ስቀን እንለያያለን! እንደ አምላክ የምታየው ያልነገረችኝ ድብቁ ፍቅረኛዋ እሷን
ያሳጣትን እኔ ጋር ሊያዘርከርከው እንደሚመጣ አናወራም! ብቻ ካንገት በላይ "ውይይይ እሱ
እኮ ሴቶቹ ላይ ቀለደባቸው ሂሂሂሂ " እንባባላለን . . .በተካነችው ተውኔት ከቀልዶቹ አንዷ እንደሆነች ትሸሽጋለች። ብዙ ቀልድ አዋቂዎች እንዳላስተናግደን አይነት ይሰራናል። "ሸኚኝ" ብላኝ አድርሻት ፍቅር ልትለምን፣ መወደድ -
መፈለግ ልትለምን እየሄደች፣ አይኖቿ ስር ያደባ እንባ ሸሽጋ ቀልድ ታወራልኛለች። እሰማታለሁ፤ ተቃቅፈን መላቀስ ባለብን ሰዓት! "ዉይ ውይ ውይ ወንዶች!" እላታለሁ፤ ምን እንዳደረጉኝ ጠባሳዬን ሳላሳይ "አትመኛቸው" እላታለሁ ። ከጥርጣሬ መቅደም የነበረበት ራስን ማክበር እንደሆን አላስረዳትም! ቁስሏን አልነካባትም። ትክክል አይደለም፤ እንዲድንላት ግን እፈልጋለሁ!! "ለሱም ለማንም ስትይ አትነሺ፤ አሁን አድገሻል ለማንም prove የምታደርጊው ነገር የለም! አባት አያስፈልግሽም! የልጅነት ጠባሳሽ እንዲሰራሽ አትፍቀጅለት!" ልላት እፈልጋለሁ . . . ከብዙ ሃዘን የተገነባችውን ሳቂታዋን ልጅ!!!
- - -

@wegoch
@wegoch
@paappii
ትልቅ ሰው ሁሌም ትልቅ ነው!
(ሚካኤል አስጨናቂ)
ያደኩባት ከተማ ውስጥ እጅግ ትታወቅ የነበረች ጠጅ ቤት ነበረች።
አቤት ያቺ ጠጅ ቤት ስራ የጀመረች ጊዜ መቼም ዓለም ነበር !...ከሩቅ ሰፈር ድረስ የመጡ እንግዶች ጠባቧን ቤት ይሞሏታል።
ከቤቷ የተትረፈረፉ አርፋጆችም ግቢ ውስጥ የሚገኝ ጥላ ይመርጡና ቁጭ ብለው ይሸርባሉ :)
በረከታሙ ግቢ የውጭውን በር አለፍ ብለው ወደ ውስጥ ሲዘልቁ ጀምሮ መዓዛው ያውዳል። እኔ ልጅ ሆኜ ብዙ ጊዜ እዛ ቤት ስላክ ደስ ይለኝ ነበር። አባዬ ከጓደኞቹ ጋር ቁጭ ብሎ አንድ ሁለት ብርሌውን ሲልፍ ጊዜ ተካፋች የሞባይል ስልኩን ያነሳና ይደውላል።
ሄሎ.. . (እናቴ ስልኩን ታነሳዋለች)
እናቴ.. . (አባዬ እናቴን የሚጠራት እንደዚህ ብሎ ነው )
እሺ.. . ቤት አይመጣም?
(ጋሼ ምን እንደሚላት እንጃ ፈገግ ትላለች)
እሺ.. .
አዎ ...አለች ያቺኛዋ ጄሪካን...
እህ?
እሺ.. .እሺ.. .
እሺ በቃ ይመጣል ።...አንተም ደግሞ ፊት አገኘሁ ብለህ አታምሽ 😉
.
ሚኪ ... (እማዬ ትጣራለች)
በርሬ ስሯ እደርሳለሁ ። ... ወደ ጓዳ ገብታ አምስት ሊትር ጄሪካን ይዛ ትመጣና ክዳኑን ከበላይ ጥላ የምትዘጋበት ስስ ፌስታል እየፈለገች.. ..
'ሂድ አባትህ ... እከሊት ጠጅ ቤት ና ብሎሀል ። ' ትለኛለች።
መቋጠሪያ ላስቲኩንና ቢጫውን ጄሪካን ተቀብያት እከንፋለሁ።
የጠጅ ቤቷ በር ጋ ስደርስ የሰው አይን ስለሚያስፈራኝ አንገቴን ሰብሬ እገባለሁ።
ጫጫታው.. .ጨዋታው ግን አንዳች መስህብ አለው። አጎንብሼም ግን ቆሎ ከሚያዞረው ልጅ ቁና ላይ መስረቄን አልተውም።
"አባት መጣህ ? ...ግባ ወደ ጓዳ " ይላል አባዬ።
"ማነሽ ...የሺ ! ዘሪሁን መቷል ...ብርዝ ስጭውና ይዞ ይሂድ "
የጠጅ ቤቷ ባለቤት መልከ መልካሟ የሺ ትመጣለች። ሳያት ደስ ትለኛለች...እንደ እቴጌ መነን ጀነን ያለ ኩራት አለባት። በዛ ላይ እኔን ትወደኛለች...ስትንከባከበኝ ደስ ይለኛል።
"መቼም አባትህ ካንተ ውጭ ወሬ የለውም !"
ትለኛለች። ...
"ትምህርት ደግሞ ሁለተኛ ወጣክ አይደል?"
"አዎ እትዬ! "
" ታድያ ትምህርት ሁለተኛ ወጣህ ብሎ ለምን ይቆጣካል?"
"አንደኛ የወጣው ልጅም እንዳንተ እንጀራ ነው የሚበላው.. . አንተ ከሱ ለምን አነስክ ብሎ ነዋ "
"ቂ....ቂ....ቂ....ክፍል ውስጥ ስንት ተማሪ አለ ?"
"80 ነን እትዬ"
"እና ሎሎች ሰባ ስምንቱ የጠላ ቂጣ ነው የሚበሉት? ሁሌም ተማሪ ታለ ውድድር አለ ...ውድድር ካለ ደግሞ አሸናፊም ተሸናፊም አለ። ደግሞ ከአንድ እስከ ሶስት መውጣት ሁሌም ጉብዝና ነው። ምነው የአባትህ ጓደኛ የአያ ቸሬ ልጅም አለ አይደል እንዴ? እያንዳንዱን ክፍል እንደ ውዳሴ ማርያም ሳይደጋግም አያልፍም እኮ! ቂ...ቂ...ቂ "
እትዬ የሺ ትስቃለች። ስትስቅ የድዷ ውቅራት ደስ ይላል። በጥቁር ድዷ ላይ ደግሞ ነጭ ሳይሆን የሆነ ነጣ ያለ ማኪያቶ የሚመስሉ ስድር ጥርሶች አሏት ።
ከደቂቃዎች በኋላ በትንሿ ብርጭቆ ብርዝ ትሰጠኛለች። ገዝቻች አይደለም...ግዴታዋም አይደለም...ስለ ፍቅሯ ብቻ!
ብርዙን ፉት ስለው ገና ከገነት ፍሬዎች አንዱን ቀጥፌ የመጠጥኩት ይመስለኛል።
ጥፍጥ.. ..
....
ህይወት በዛ ቤት እንደዚህ ውብ ሆና ለመቀጠል ግን ጥቂት ዓመታት ብቻ ነበሩ ደግ ሆነው የቆዩት ።
ከሆነ ጊዜ በኋላ እትዬ የሺ ስኳር መጠቀም ጀመረች አሉ። ከዛ ብዙ ብዙ እኔ የማይገቡኝ የትልቅ ሰው መከራዎች ደርሰውባት ከአካባቢው ዞር አለች። የጠጅ ቤቷ ዝና ወረደ ...እኛም ያደግንባትን ከተማ ለቀን ለዩንቨርስቲ ትምህርት ተሰደድን ።
የሆነ ጊዜ ደግሞ እንደዚህ ሆነ...
5 ዓመታትን በተለያየ ከተማ ተበታትነን የነበርን ጓደኞች ተገናኝተን የድሮዋን ታዋቂ ጠጅ ቤት ለመጎብኘት ሄድን። አዲሷ ቤት ደመ ቀዝቃዛ ናት። ድሮ እታለም ጠጅ ቤት ስሄድ የነበረው ሁካታና ግርግር የለም። ቅር አለኝ። እትዬም ስራውን ለሰው ለቃ ስለነበር ብዙ ጊዜ ሳሎኑን አትጎበኘውም።
ከልጆች ጋር ተሰብስበን አንድ ሁለት ካልን በኋላ እትዬ መጣች።
ፍቅሯ እንደ ድሮው አልነበረም። ጭራሽ ረስታኛለች.. .ደግሞ ጉስቁል ብላለች ።
ስታወራ ድምፅዋ ቅልስልስ አለ ...
እኔ ከጓደኞቼ ጋር ስጫወት ቆየሁ። በመሀል የሺ ትክ ብላ አየችንና ከመሀል አንዱን ጓደኛችንን አንተ የጋሽ ክፍሌ ልጅ ነህ አይደል? አለችው።
"አዎ እትዬ" አላት...ሀዘንና ቁጣዋ እስከ አሁኗ ደቂቃ ድረስ ፊቴ ላይ አለ።
"እናንተ ባለጌዎች አሁን እናንተም አድጋችሁ ጠጅ ለመጠጣት በቃችሁ ?" እትዬ.. .ጮኸች!
እትዬ አልገባትም እንጅ አድገን ስራ ሁሉ ይዘናል እኮ ። እንደውም አንዱ ጓደኛችን ሚስት ሊያገባ ስላሰበ ለሚዜነት ሊጀነጅነን ነበር እዛች ቤት የገባነው። የሺ ግን ልጅ ሆነን ስለምታውቀን አንጀቷ እንቢ አለ ።
ለሶስተኛ ጊዜ መጥታ ጠጅ ልትቀዳልን ያለችው ዓለም ላይ እትዬ ጮኸችባት።
"ውጡ " ...
"እንዴ እትዬ ሂሳብ አልከፈሉም እኮ" አለች ዓለም።
"የራስሽ ጉዳይ ...እነዚህ እኮ ልጆች ናቸው። አባቶቻቸው ነበሩኮ እኔ ጋር የሚመጡት.. .የዛሬን አትይ ..." እትዬ እንባዎቿ ወረዱ !
እኔ ግን እንዴት እንደሆነ ባላውቅም እትዬ የሺ አሁንም ድረስ እንደ ንጉስ ሀይለ ስላሴ ሚስት በኩራት ታየችኝ።
በዚህ ገንዘቤን እንጅ ስለ ትውልዱ ምናገባኝ የሚል ስግብግብ ነጋዴ በበዛበት ዓለም...18 ዓመት ላልሞላው ልጅ ጫት እና መጠጥ በሚሸጥበት ዓለም... እኔ ያገባኛል የሚል ነጋዴ...ለዛውም ከስሮ ችግር ላይ ያለ ነጋዴ ሲታይ እንዴት አይገርምም?
ሁላችንም ተግተልትለን መውጣት ጀመርን። እትዬ ብትናፍቀኝም...እንደ ረሳችኝ አውቄ ባፍርም የአባዬ ልጅ ነኝ ብዬ ብነግራት እጅግ የምትናደድ ስለመሰለኝ ዝም አልኳት።
የናፍቆት የናፍቆቴን በር ጋር ደርሼ ዞር ብዬ አየኋት። ነፍሷ ዛሬም ውብ ናት !
ትልቅ ሰው መቼም ትልቅ ሰው ነው 🙂

@wegoch
@wegoch
@paappii
አዞዎቹ (The Crocodiles) እና የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ
--------
ክፍል አንድ
------
ጸሐፊ: አፈንዲ ሙተቂ
---------
በቅርቡ ታሪካቸውን የለጠፍኩላችሁ ዋለልኝ መኮንን እና ማርታ መብራህቱን የመሳሰሉ ፋኖችን የወለደው ታሪካዊው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ ነበር። ያ ንቅናቄ አጨራረሱ ላይ ተደነባብሮ የተነሳለትን ዓላማ ሙሉ በሙሉ ከታሪክ መድረክ ላይ ቢወርድም በአጀማመሩ ላይ የብዙዎችን አድናቆት አትርፏል። በዚያ ንቅናቄ የተሳተፈው ትውልድ በቆራጥነቱ፣ በአብዮታዊነቱ፣ በህዝባዊነቱ፣ በተራማጅነቱ፣ በአንባቢነቱ፣ በቀስቃሽነቱ ብዙ የተባለለት ነበር።

የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ ሲጀመር አንድ ወጥ መልክ ነበረው። በሂደት ግን የግራ መስመር ተከታዮች የሚበዙበት ክንፍ ከሌሎቹ የበለጠ በመንቀሳቀስ የንቅናቄው አቀጣጣይ ለመሆን በቅቷል። እነዚያን የግራ ርእዮት አቀንቃኞች በስውር ሲመራ የነበረው ደግሞ “አዞዎቹ” የሚባለው የስር-ነቀል ለውጥ (radical change) ደጋፊ የተማሪዎች ቡድን እንደነበር ሰነዶችና የንቅናቄው ተሳታፊዎች ይጠቁማሉ፡፡

የ“አዞዎቹ” ቡድን ምስረታ የተጠነሰሰው ገብሩ ገብረ ወልድ በሚባለው የያኔው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሤ ዩኒቨርሲቲ (የአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ) ተማሪ ነበር፡፡ ዘመኑም በ1955 ገደማ ነው፡፡ ገብሩ ገብረወልድ ቀደም ባለው ዘመኑ የዓለም-ማያ (ሀረማያ) እርሻ ኮሌጅ ተማሪ ነበር፡፡ ዘርዑ ክሕሸን የሚባለው ተማሪም ከርሱ ጋር ይማር ነበር፡፡ ሁለቱ ተማሪዎች በ1954 ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተዛወሩ፡፡ ከዓመት በኋላም በገብሩ ጠንሳሽነትና በዘርዑ ተባባሪነት ማርክሳዊ ርዕዮት የሚያጠኑበትን ቡድን መሰረቱ፡፡ ከነርሱ ጋር ተቀራራቢ ሀሳብ የነበራቸውን ሌሎች ተማሪዎችንም መሳብ ጀመሩ፡፡ በዚህ መሰረት የቡድኑ ቀዳሚ አባላት የሆኑት

1. ኃይሉ ገብረ ዮሐንስ (ገሞራው)
2. ስዩም ወልደዮሐንስ
3. አበራ ዋቅጅራ
4. ዮሐንስ ስብሐቱ ናቸው፡፡

በማስከተልም የነርሱን ዓላማ የሚደግፉ በርከት ያሉ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲገቡ የአዞዎቹ ቡድን መሰረቱን ማስፋት ጀመረ፡፡ በ1956 የተማሪ ማህበር አመራር አባላት የነበሩት ብርሃነ መስቀል ረዳ እና እሸቱ ጮሌ ከቡድኑ ጋር ተቀላቀሉ፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላም ሚካኤል አበበ፣ ታዬ ጉርሙ እና ሐብቴ ወልደ ጊዮርጊስ የአዞዎቹ ቡድን አባል ሆኑ፡፡
*
የአዞዎቹ ቡድን ጅምሩ ላይ የጥቂቶች ስብስብ ነበር፡፡ እያደር ግን ስር-ነቀል ለውጥ ደጋፊ የሆነ ተማሪ ሁሉ የሚሰባሰብት የጋራ ማህበር ሆኗል፡፡ ምንም እንኳ ቡድኑ ከ1960ዎቹ መግቢያ ጀምሮ “አዞዎቹ” በሚለው ስም መጠቀሙን ቢያስቀረውም በአዞዎቹ የተዘረጋው የስር-ነቀል ለውጥ ደጋፊ አብዮተኛ ተማሪዎች መስመር እስከ 1966ቱ አብዮት ድረስ ቆይቷል፡፡ በዚህ መሰረት ከ1950ቹ መጨረሻ ጀምሮ የአዞዎቹ መስመር ተከታይ በመሆን በንቅናቄው ውስጥ ከፍተኛ ሚና ከነበራቸው አብዮተኛ ተማሪዎች መካከል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡፡

1. ዋለልኝ መኮንን
2. ጥላሁን ግዛው
3. ጸጋዬ ገብረ-መድህን (ደብተራው)
4. ገዛኽኝ መኮንን
5. ተካልኝ ወልደ አማኑኤል
6. ጌታቸው ሀብቴ
7. ታምራት ከበደ
8. ሄኖክ ክፍሌ
9. ዳዊት ስዩም
10. ጸሎተ ህዝቅያስ
11. ሙሐመድ ማሕፉዝ
12. በድሩ ሱልጣን
13. ዳዊት ህሩይ
14. ተስፉ ኪዳኔ
15. ዮሐንስ በፍቃዱ
16. አማኑኤል ዮሐንስ
17. ሙሉጌታ ስልጣን
18. መስፍን ሐብቱ
19. አያሌው አክሎግ
20. ጌታቸው ሻረው
21. ፋንታሁን ጥሩነህ
22. ይርጋ ተሰማ
23. አባይ አብርሃ
24. መስፍን ካሱ
25. ዮሐንስ ብርሃኔ
26. ብርሀነ ኢያሱ
27. ወርቁ ገበየሁ
28. እሸቱ አራርሶ
29. ኢያሱ ዓለማየሁ
30. ብንያም አዳነ
31. ገዛኽኝ እንዳለ
32. ዮሴፍ አዳነ
33. አብዱል መጂድ ሁሴን
34. አብዲሳ አያና
35. ሀይለእየሱስ ወልደሰንበት
36. ማርታ መብራህቱ
37. ታደለች ኪዳነ ማሪያም
38. ተስፋዬ ቢረጋ
39. ገብሩ መርሻ
40. ታሪኩ ደብረ ጽዮን
41. ግርማቸው ለማ
42. ጌታቸው ማሩ
43. መለስ ተክሌ
44. ግደይ ገብረዋህድ
45. ረዘነ ታደሰ
46. አሰፋ እንደሻው
47. ሳሙኤል አለማየሁ
48. መላኩ ማርቆስ
49. ወርቁ ገበየሁ
50. ብርሃኑ እጅጉ
------
ከላይ በቀረበው ዝርዝር ውስጥ የተጠቀሱት በሙሉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ነበሩ፡፡ እነዚህ ተማሪዎች በህቡዕ የሚንቀሳቀሰውና በ1960ዎቹ መጀመሪያ መሠረቱን እያሰፋ የመጣው የአዞዎቹ ቡድን ቀጥተኛ አባላት ናቸው። የአዞዎቹ ቡድን አባል የሆነ ሰው ማንነቱን በግልጽ ሳያስታውቅ ሌሎች ተማሪዎችና ምሁራን የትግሉ ደጋፊ እንዲሆኑ ይቀሰቅሳቸዋል። ሰልፍና አድማ በሚኖርበት ወቅት ግንባር ቀደም ሆኖ ያስተባብራል። የንቅናቄው አባል የሆነ ተማሪ ከትምህርት ጉዳይ በስተቀር በሌሎች ጉዳዮች ላይ አድሃሪ አቋም ካላቸው ተማሪዎች ጋር ጉድኝት አይፈጥርም።

ከ1962 በፊት በነበረው ጊዜ የተማሪዎቹ ዋነኛ የትግል ስልት በተቃውሞ ሰልፍና በህትመት መድረኮች ንጉሣዊውን ስርዓቱን ማስጨነቅ ነበር፡፡ ከዚህም ጎን ህዝቡንና አብዮታዊ ምሁራንንም በተቃውሞው ጎራ ለማሰለፍ ጥረት ያደርጉ ነበር፡፡ ከ1962 በኋላ ግን የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ይህንን ስልት እርግፍ አድርገው በመተው ልዩ ልዩ የውይይት ክበቦችን እየመሰረቱ በሶሻሊስት ርዕዮተ-ዓለም እና በድርጅት ምስረታ ላይ ጥልቅ ውይይት ማድረግ ጀመሩ። አንዳንድ ተማሪዎች ደግሞ ከስርዓቱ ክትትል ለማምለጥ ከሀገር ተሰደዱ፡፡ በሀገር ውስጥ የቀሩት ተማሪዎች በውጪ ሀገር ካሉት የተማሪ ማህበር አባላትና ስደተኛ ተማሪዎች ጋር በመቀናጀት የስርዓት ለውጥ የሚመጣበትን መንገድ ለመሻት ተንቀሳቀሱ፡፡ በስተመጨረሻም በልዩ ልዩ የፖለቲካ ድርጅቶች (ኢህአፓ፣ መኢሶን፣ ኦነግ፣ ህወሓት፣ ጀብሃ፣ ሻዕቢያ፣ ወዝሊግ ወዘተ....) ስር በመሰለፍ ታገሉ፡፡ ይሁንና በጣም የሚበዙት ያሰቡትን ከግብ ሳያደርሱ ከዚህች ዓለም ተሰናበቱ፡፡
------
እዚህ ዘንድ ሁለት ነገሮችን መጨመር ተገቢ ይመስለኛል። የአዞዎቹ ቡድን ጀማሪ አባላትም ሆኑ ሌሎቹ የዚያ ዘመን የተማሪ ንቅናቄ ተሳታፊዎች በቆራጥነታቸው የተነገረላቸው ናቸው። ለምሳሌ አንድ ተማሪ ከመኳንንትና መሳፍንት ቤተሰብ የተወለደ ሆኖ የመደብ ጀርባው ሳያግደው ለገበሬው ሲል "መሬት ላራሹ" እያለ ይጮኽ ነበር። አባቱ ጄኔራል ሆኖ በቅንጦት መኖር እየቻለ ለትግል ሲል አባቱንም ከንጉሣዊው ስርዓት ጋር የህዝብ ጠላት አድርጎ ይፈርጅ ነበር። ከወንድሙ ጋር በዓላማ የማይጣጣም ከሆነም ከወንድሙ ይልቅ ትግሉን ያስቀድም ነበር። አንዳንድ ተማሪዎች ደግሞ በትግሉ ሳቢያ እየታሰሩ ሲፈቱ ከመቆየታቸው የተነሳ ትምህርታቸውን እርግፍ አድርገው በመተው የሙሉ ጊዜ አብዮተኛ ታጋይ ሆነዋል።

@wegoch
@wegoch
@paappii
አዞዎቹ (The Crocodiles) እና የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ
-----
ክፍል ሁለት
-----
ጸሐፊ: አፈንዲ ሙተቂ
----
በሌላ በኩል የአዞዎቹ ቡድን ጀማሪ አባላትም ሆኑ ብዙኃኑ የዚያ ዘመን ተማሪዎች በኃይለ ስላሴ እና በደርግ መንግሥት የጸጥታ ሃይሎች እጅ በሚወድቁበት ጊዜ ብዙ የጭካኔ ድርጊቶች ተፈጽመውባቸው እንኳ ሚስጢር አያወጡም ነበር። የደርግ የጸጥታ ሃይሎች በተማሪው እንቅስቃሴ የተወለደው "ኢህአፓ" የተሰኘው ድብቅ ፓርቲ አባላት ሚስጢር የማያወጡና ለዓላማቸው የሚሞቱ ቆራጦች ስለሆኑባቸው ነው ከፍተኛ ጭካኔ የተቀላቀለበትን የቀይ ሽብር ዘመቻ የጀመሩት (ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማሪያም የኢህአፓዎቹን ቆራጥነት በትዝታ መጽሐፋቸው በግልጽ አድንቀውላቸዋል)።

በሁለተኛ ደረጃ የአዞዎቹ ቡድንም ሆነ ሌሎች የተማሪዎች ንቅናቄ አባላት ለብዙ ዘመናት ህዝብን ቅር ሲያሰኙ እና ለአመጽ ሲያነሳሱ የነበሩ መሠረታዊ ችግሮችን በክህደት የማያድበሰብሱ በመሆናቸው ይታወቃሉ። የንቅናቄው ተሳታፊ ተማሪዎቹ ግፋ ቢል የሚያደርጉት ነገር ጥያቄዎቹን በሶሻሊስታዊ ዐይን እያዩ መተንተን እና ከሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ጋር አመዛዝኖ መልስ ለመፈለግ ነው።

ለምሳሌ፣ የኤርትራ ጥያቄ፣ የብሄረሰቦች ጥያቄ እና የሀይማኖት እኩልነት ጥያቄ ከ1950-1960 ባለው ዘመን በተማረው ማህበረሰብ ዘንድ በሹክሹክታ መነሳት ጀምረው ነበር። ይሁንና የዚያ ዘመን ኢንተሊጀንሲያ ትምህርቱ በአብዛኛው ምዕራብ ቀመስ በመሆኑ በጥያቄዎቹ አመላለስ ላይ ከሃይለ ስላሴ መንግስት የተሻለ አቋም አልነበረውም። ብዙዎቹ "እነዚህ ችግሮች በተጨባጭ በሀገራችን የሉም፣ ቢኖሩም እንኳ መሠረታዊ አይደሉም" እያሉ ይክዱ ነበር።

"አዞዎቹ" የተሰኘው የግንባር ቀደም አብዮተኛ ተማሪዎች ቡድን ሲመጣ ግን እነዚህ ጥያቄዎች የተማረው የህብረተሰብ ክፍል ዋነኛ የውይይት ርእስ ሆነዋል። በተለይ ደግሞ "የብሄረሰቦች ጥያቄ" ከሁሉም በላይ ገንኖ በመውጣት የአብዛኛው ተማሪ የውይይት አጀንዳ ሆኖ ነበር። በመጨረሻም አዞዎቹ እና ሌሎች ብዙ ተማሪዎች የተስማሙበት አቋም በዝነኛው ዋለልኝ መኮንን ብዕር በጽሑፍ ተቀነባብሮ በመጽሔት ወጥቷል (ልብ በሉ! ዋለልኝ ጽሑፉን በራሱ ስም ቢያቀርበውም ከሌሎች ጓደኞቹ ጋር በሰፊው ተወያይቶ እና እነርሱንም ወክሎ ነው ጽሑፉን የጻፈው። ጽሑፉ በአዞዎቹ ቡድን ስም ቢቀርብ ኖሮ ቡድኑ ይጋለጥ ነበር)።

እዚህ ላይ አንድ ነገር ያዙልኝ። በአሁኑ ዘመን በርካታ ሰዎች "የብሄር ብሄረሰቦች ጥያቄ የሚባል ነበር አልነበረም። ወያኔ ለአገዛዝ እንዲመቸው የፈጠረው አርቲፊሻል ጥያቄ ነው" ይላሉ። ይህ አባባል መሠረት የለውም። ብሄሮች ለመብትና ነፃነት መታገላቸው ከወያኔ በፊትም ነበረ። ከተማሪዎች ንቅናቄ መጀመር በፊትም ጥያቄ ነበር።

የብሄረሰቦች ጥያቄን በጽሑፍ በማቀናበርና በመጽሔት በማሳተም ብዙዎች ስለጉዳዩ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ያደረጉት ደግሞ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ነበሩ። በኢትዮጵያ ታሪክ በተደራጀ መልክ የፖለቲካና የለውጥ ትግል የጀመሩት ቀደምት ፓርቲዎችና ቡድኖች በሙሉ (ኢብነግ፣ ኢህአፓ፣ መኢሶን፣ ኦነግ፣ ግገሓት፣ ህወሓት፣ ሶወሊ፣ ወዘተ) "የብሄረሰቦች መብት መከበር አለበት" ይሉ ነበር። እነዚህ ድርጅቶች በዕድሜአቸው ከወያኔ ይቀድማሉ። ጥያቄውን ያነሱት በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን እውነታ ተንተርሰው ነው።

በጥያቄው አመላለስ ላይ መነጋገርና ሁሉንም የሚያስማማ መልስ መፈለግ ይቻላል። "ጥያቄውን ያመጣው ህወሓት ነው" ማለት ግን ታሪክንና ነባራዊ እውነታን መካድ ነው።
-------
በአዞዎቹ እና በሌሎች የተማሪው ንቅናቄ አባላት ላይ ብዙ ትችቶች ይቀርብባቸል። ከትችቶቹ መካከል አንዳንዶቹ ተገቢ ናቸው። ሌሎቹ ግን ከእውነት የራቁ ናቸው።

ለምሳሌ አዞዎቹም ሆኑ የግራ መስመር ተከታይ የሆኑ የዚያ ዘመን ተማሪዎች በሙሉ በአመለካከት መለያየትን እንደ መብት አይቀበሉትም። በአመለካከት የተለዩትን ሰው በጠላትነት በመፈረጅ በፕሮፓጋንዳ ሽብር ያጨናንቁታል። በመጽሔት ብዙ ይጽፉበታል። ከማህበራዊ ኑሮ ያገልሉታል። ይህ ባህሪያቸው ስር እየሰደደ ሄዶ በ1968-1970 የታየውን ከባድ ትራጀዲ ወልዷል። በአውሮጳ ጓደኛሞች የነበሩት ሃይሌ ፊዳ እና ተስፋዬ ደበሳይ ወደ ሀገር ቤት ከተመለሱ በኋላ ደመኛ ጠላቶች ሆነዋል (እርግጥ ሁለቱም የአዞዎቹ መስራች አባላት አልነበሩም። ሆኖም ጓደኞቻቸው የአዞዎቹ ቡድን አባላት ነበሩ)። የመኢሶን አባል የነበረችው ዶ/ር ንግሥት አዳነ ከአንድ ማህጸን ከእርሷ ጋር የተወለደውን ዮሴፍ አዳነ የተባለ ወንድሟን ከቢሮው አስይዛው እንዲገደል አድርጋለች። የመኢሶኑ ግርማ ከበደም ነፍስ ጡር የነበረችውን ወይዘሮ ዳሮ ነጋሽን ከአስራ ስድስት ሰዎች ጋር አስገድሎ ሬሳቸው በራስ መኮንን ድልድይ ላይ እንዲጣል አድርጓል። ኢህአፓዎች በበኩላቸው የመኢሶን መሥራች አባል የነበረውን ዶ/ር ፍቅሬ መርእድን በጠራራ ጸሐይ "ባንዳ" በማለት ገድለውታል። ሸዋሉል መንግሥቱ የተባለችው ታዋቂ ገጣሚና ጋዜጠኛም የቀበሌ ሊቀመንበር ሆና ስለተመረጠች ብቻ "ባንዳ" ተብላ በኢህአፓ ስኳድ ተገድላለች (ኢህአፓዎች "ሸዋሉል ገዳይ ጓድ እየመራች ብዙ ወጣቶችን ስለረሸነች ነው የተመታችው" እያሉ ቢጽፉም ይህንን የሚያረጋግጥ ማስረጃ አልተገኘም)። ከዚህ እልፍ ሲልም የኢህአፓ መሥራችና የመጀመሪያ ዋና ጸሐፊ የነበረው ብርሃነ መስቀል ረዳ ከጓዶቹ ጋር በሃሳብ ባለመጣጣሙ ምክንያት ከድርጅቱ ሲወጣ ራሱ የመሠረተው ድርጅት ሞት ፈርዶበታል። እርሱም "የእርማት ንቅናቄ" የተሰኘ የኢህአፓ አንጃ በመፍጠር በሌሎች ጓዶቹ ላይ ሞት ፈርዷል (ሆኖም እነርሱ ሳይገዳደሉ ደርግ ቀደማቸውና ሁሉንም ሰብስቦ ረሸናቸው)።

የዚያ ዘመን የተማሪ ንቅናቄ አባላት ሌላው ችግራቸው በሁሉም ረገድ የሚያሳዩት ችኮላ እና አለመስከን ነው። ብዙዎቹ ከሰላሳ ዓመት ያልበለጡ ወጣቶች በመሆናቸው ለመደመጥ እንጂ ለማዳመጥ ዝግጁ አልነበሩም። ከላይ እንደተገለጸውም በሃሳብ የማይጣጣሙትን ሰው "ባንዳ" ፣ "ትሮትስካይት" ፣ "አናርኪስት"፣ "ቀኝ መንገደኛ" እያሉ በጠላትነት ይፈርጁታል። ዛሬ የምናየው በችኮላ የመፈረጅና ቅጽል እየሰጡ የማጥላላት አድራጎት ከዚያ ዘመን የተወረሰ መጥፎ ልማድ ነው።

@wegoch
@wegoch
@paappii
አዞዎቹ (The Crocodiles) እና የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ
-----
ክፍል ሶስት
-----
ከላይ እንደጠቀስኩት በያኔው የተማሪ ንቅናቄ ግንባር ቀደም መሪዎችና ሌሎች የንቅናቄው ተሳታፊዎች ላይ ከሚቀርቡት ክሶች መካከል አንዳንዶቹ መሠረተ ቢስ ናቸው። አንዳንዶቹ ከመሠረተ ቢስነታቸው ባሻገር ጨዋነት የጎደላቸው ናቸው። ከነዚህ ክሶች አንዱ ተማሪዎቹን የሲ.አይ.ኤ እና የሌሎች የውጭ ሃይሎች ቅጥረኛ አድርጎ ማቅረብ ነው። በዚህ ክስ የሚታወቁ ሰዎች በዚህ ብቻ ሳያበቁ ተማሪዎቹ እርስ በራሳቸው በሴራ ተጠላልፈው ይገዳደሉ እንደነበሩ ሲጽፉ ታይተዋል። ለምሳሌ አንዱ ፕሮፌሰር "ተስፋዬ ደበሳይ እንዲገደል ሁኔታዎችን ያመቻቸው ጓደኛው የነበረው ክፍሉ ታደሰ ነው" በማለት ጽፈው ነበር። ይሁንና በጽሑፉ ውስጥ ስማቸው እንደ መረጃ ምንጭ የተጠቀሰው ዶክተር ነገደ ጎበዜ ፕሮፌሰሩ የጻፉት ታሪክ ሐሰት ነው ብለው በማስተባበል የተስፋዬ ደበሳይ አሟሟት ኢህአፓዎች ከጻፉት የተለየ እንዳልሆነ መስክረዋል።

በሌላ በኩል የያኔው ዘመን የተማሪ ንቅናቄ መሪዎች የኤርትራ የነፃነት ድርጅቶች ቅጥረኞች መሆናቸውን የሚጽፉ ሰዎች በዝተዋል። ዛሬም እንደዚህ እየተባለ ሲጻፍ እያነበብን ነው። እነዚህ ሰዎች ለክሳቸው እንደ ማስረጃ ከሚያቀርቡት ሰበቦች ዋነኛው የአዞዎቹ ቡድን አባላት ከሆኑት ተማሪዎች መካከል አንዳንዶቹ የትግራይ እና የኤርትራ ተወላጆች መሆናቸው ነው።

ይህ ግልጽ የወጣ ዘረኝነት እንጂ አሳማኝ ምክንያት ሊሆን አይችልም። ለምሳሌ የኢህአፓዎቹ ዘርዑ ክሕሸን፣ ተስፋዬ ደበሳይ፣ ብርሀነ እያሱ፣ ጸሎተ ህዝቅያስ፣ ዮሴፍ አዳነ ወዘተ የትግራይ ተወላጅ ቢሆኑም ከሌሎቹ የኢህአፓ አባላት በተለየ ሁኔታ ለኤርትራም ሆነ ለትግራይ የሰሩት ነገር የለም። የኢህአፓ አባላት በእነዚህ መሪዎቻቸው ላይ አሁን የምንሰማውን ክስ ያቀረቡበት ወቅት የለም። በአንጻሩ ግን ህወሓት በ1969 መጨረሻ በኢህአፓ ላይ ጦርነት ሲያውጅ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ብዙ የኢህአፓ አባላት ግንባር ቀደም ሆነው የህወሓትን ጦር ተፋልመዋል። ህወሓት ደርግን አሸንፎ ሲመጣም እነዚያ የትግራይና የኤርትራ ተወላጆች ህወሓትን መቃወማቸውን ቀጥለዋል። ሰዎችን በብሄር ብቻ እየፈረጁ ባልሰሩት ነገር መውቀስ ከዘመናችን ታላላቅ በሽታዎች አንዱ ነው። ሁሉም ለዚህ በሽታ መፍትሔ መፈለግ አለበት።
*
አነሳሴ የአዞዎቹን ቡድን በመጠኑ ማስተዋወቅ ቢሆንም ሌላውንም ቀላቅዬ በሰፊው አቅርቤላችኋለሁ። አሁን ወደ መነሻዬ ልመለስና ጽሑፌን ላብቃ።

"አዞዎቹ" በዚህ ዘመን በአብዛኛው በህይወት የሉም-ከላይ እንደጠቀስኩት፡፡ ብዙዎቹ የሞቱት በአብዮቱ አፍላ ወቅት ነበር፡፡ አንዳንዶቹ በወታደራዊው የደርግ መንግሥት ተይዘው ነው የተረሸኑት፡፡ ከፊሎቹ ደግሞ ከደርግ አሳሾች ሲሸሹ ነው የተገደሉት፡፡ ጥላሁን ግዛውና ዋለልኝ መኮንንን የመሳሰሉት ግን ቀደም ብለው በአጼ ኃይለ ሥላሤ መንግሥት ወታደሮች ተገድለዋል፡፡ አንዳንዶች በዚያው ዘመን ዱር ገብተው ሲዋጉ ህይወታቸው አልፏል፡፡ እንደ ዶ/ር እሸቱ ጮሌ፣ ዘሩ ክሕሸን እና አብዱል መጂድ ሑሴንን የመሳሰሉት በህመም ምክንያት ሞተዋል፡፡ በዚህ ዘመን በህይወት መኖራቸው የሚታወቀው የአዞዎቹ ቡድን መሥራች አባላት

1. ገብሩ ገብረወልድ (በአሜሪካ ሀገር የሚኖሩ)
2. አበራ ዋቅጅራ (አሜሪካ የሚኖሩ)
3. ኢያሱ ዓለማየሁ (ፈረንሳይ ሀገር የሚኖሩ)
4. አብዲሳ አያና (አውሮጳ የሚኖሩ) የመሳሰሉት ናቸው።
*
አፈንዲ ሙተቂ
መጀመሪያ ታህሳስ 2/2006
እንደገና ተሻሽሎ ታሕሳስ 3/2014 ተጻፈ።

(እንደ ማስታወሻ፡ እነ ኃይሌ ፊዳ፣ ተስፋዬ ደበሳይ፣ ሰናይ ልኬ፣ ነገደ ጎበዘ፣ ክፍሉ ታደሰ፣ ክፍሉ ተፈራ የመሳሰሉት አብዮተኞች የአዞዎቹ ቡድን አባላት አልነበሩም፡፡ እነዚህኛዎቹ ትምህርታቸውን በውጪ በሚከታተሉበት ወቅት ነው ወደ ንቅናቄው የገቡት)፡፡

@wegoch
@wegoch
@paappii
#የሐኪም_ቤቱ_መስኮት

ሁለት ሰዎች በአንድ ሆስፒታል ክፍል ውስጥ አልጋ ይዘው ተኝተዋል። ሁለቱም በጠና ታመው በአምላክ እጅ ተይዘዋል። አንደኛው ሳንባው የቋጠረውን ውሀ ለማድረቅ ሲባል ለሰአታት ያህል አልጋው ላይ ቁጭ እንዲል ይደረጋል። አልጋው የሚገኘው በክፍሉ ብቸኛ ከሆነው መስኮት አጠገብ ነው።

ሌላኛው ህመምተኛ ደግሞ በተቃራኒው ለሰአታት በጀርባው እንዲተኛ ይደረጋል። እነዚህ ህሙማን በቆይታቸው ብዙ ተጨዋውተዋል። ስለ ቤተሰቦቻቸው ፣ ስለ ኑሯቸው፣ በወታደር ቤት ስለሰጡት አገልግሎት፣ የእረፍት ጊዜያቸውን የት እንደሚያሳልፉ... ወዘተ አውርተዋል።

ከመስኮት አጠገብ ያለው ህመምተኛ ቁጭ በሚልበት ሰአት ወደ ውጭ እየተመለከተ ሁሉን ነገር በጀርባ ለተኛው ሰው ይገልጽለታል።

".....በሚያማምሩ ዛፎች የተከበበ ሀይቅ ይታየኛል፣... በሀይቁ ላይ ዳኪዬዎች ይዋኛሉ...... ህጻናት ደግሞ ከወረቀት የሰሩትን መርከቦች በሀይቁ ዳርቻ በማስቀመጥ ይጫወታሉ... ፍቅረኛሞች በአንድ እጆቻቸው አበባ በሌላው ደግሞ ተቃቅፈው ሀይቁን ይዞራሉ፣... ከሀይቁ ባሻገር ውብ የሆነ ከተማ ይታየኛል....." በማለት ዘወትር የሚያየውን ሁሉ ይተርክለታል።

በዚህ አይነት ሁኔታ ሳምንታት አለፉ።

አንድ ማለዳ ነርስዋ ገላቸውን ልታጥብ ውሀ ይዛ መጣች። ከመስኮት አጠገብ ያለው በሽተኛ ግን በህይወት አልነበረም። በጣም ደነገጠች። ጓደኛውም እንዲሁ አዘነ። ነርስዋ አስከሬኑን በቶሎ እንዲያነሱ ሰዎች ጠራች። ያ ብቻውን የቀረው በሽተኛ አልጋውን ከመስኮቱ አጠገብ ሊወስዱለት ይችሉ እንደሆነ ጠየቀ። ወሰዱለት። በመስኮት ለማየት በጣም ቸኩሏል። ቀና ብሎ ወደ ውጭ ተመለከተ። ከመስኮቱ ባሻገር ያለው ነጭ ቀለም የተቀባ ግድግዳ ብቻ ነው።

ደነገጠ!!!

"ምን ሆንክ?" አለቸው ነርስዋ። "ሰዉዬው ብዙ አስደሳች
ነገሮችን በዚህ መስኮት አሻግሮ ይመለከት ነበር" አላት። "ኧረ ሰዉዬው ማየት የማይችል አይነስውር ነበር አለችው።" ልብ የሚነካ ነገር.... ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ።

ለካስ እሱን ለማስደሰትና የመኖር ተስፋ ለመስጠት ነበር ያን ሁሉ ነገር ፈጥሮ የሚያወራው።
====================================
አንዳንድ ሠዎች እንዲህ ናቸው እነሡ እየሞቱ የሠውን የሕይወት ብርሃን ያለመልማሉ። የሠው ህይወት ማዳን ባንችል እንኳን ቢያንስ ለሠው ተስፋ 🌼 እንስጥ ይሄም የመልካምነት አንዱ ገፅ ነውና።

ከእግረኛ ወጎች ላይ የተወሰደ

@wegoch
@wegoch
@paappii
Audio
@wegoch
@wegoch
@wegoch

አቅራቢ፡ ናርዶስ
ፀሃፊ፡ ህይወት እምሻው
ገና አስፓልቱን ተሻግሬ ሳልጨርስ ድርድር ብለው የቆሙት መኪኖች ተለቀቁ.. ዘጭ ዘጭ እያልኩ ቂጤን እያናጋሁ ተሻገርኩ። እዛና እዚህ አራርቄያቸው የምተኛቸው እግሮቼ ብቸኝነት
ተመችቷቸው ዳሌያቸው እያደር ይሰፋል። ጎንበስ ብዬ ከሁለት ወር በፊት ይሰፋኝ የነበረ አሁን አጣብቆ የያዘኝን ሱሪ አየሁ ለንፋስ ቦታ የለውም። አፍ ቢኖረው ድረሱልኝ የሚል ያህል ከአካሌ ጋር ተዋድዷል። ምናልባት ሳወልቀው በሌሊት ተምበርክኮ ለጅንስ አምላክ ስቃዩን ያስረዳ ይሆናል። እንጃ... <<ምን እያየሽ ነው?>> አለኝ ካቀረቀርኩበት ጥቁር ከፋይ ጫማው ብቻ የሚታየኝ ሰው ... መንገድ ላይ የሚያዋራኝ አይደለም የሚያየኝን <<ምናገባህ>> ብለው ከእብድ ይቆጠርብኛል ብዬ እንጂ ደስታዬ ነው። ለጥያቄው ምላሽ የሚሆን በነገር አካሄድ ትከሻውን በሀይል ገፍቼው አለፍኩ። ውስጤ እጁን የሰቀሰቀ ወጠምሻ ፤ከልስልስ ገላዬ ስር ጉንጩን በፀብ የጫረ ነገረኛ ወንድ ያለ ይመስለኛል...ሁሌም። <<ኧረ ተይ እንተዋወቃለን >>አለኝ ያው ድምፅ ሮም የተሰራችበትን ግዜ ያህል ፈጅቼ ላየው ዞርኩ ... እሱ ነው። ረጅም፣ የቀይ ዳማ ፣ ትናንሽ አይኖች፣ የፊት ጎልማሳ የሌላቸው ልጅ እግር የጥርስ ቤተሰቦች፣ ኪንኪ ፀጉር፤ ጥቁር ኮት ያጠለቀ ሰፊ ትከሻ፣ ጥቁር ሰአት ያጠለቀ ደብዳቤ የፃፈልኝ እጅ፣ ለስላሳ ሽቶ የሚያተን ኩሩ ገላ ሁልጊዜም ከሚንደኝ ሳቁ ጋር ... እራሱ ነው።
-
አስታውሳለሁ ግቢ እያለሁ ከድርድር ሴት ጓደኞቼ መሀል በሚያማምሩ ትንንሽ አይኖቹ ይፈልገኝ ነበር። ሳያምረኝ ቀርቶ ሳይሆን እንደሁሉም ሴቶች እንዳልወደው እየፈራሁ <<መጣ መጣ>> ሲሉ ገና አይኔን በሌላ አቅጣጫ እጥል ነበር። እንደማላየው ሲያውቅ ይሆን ወይ የእውነት ደስ ብዬው አንድ እለት ግቢ በር ላይ ቆሜ ከቦርሳዬ መታወቂያ ፍለጋ ሳምስ<<የኔ ባሪያ>> ብሎኝ ገባ። ያን ለት በቤተስኪያን ደጆች ሳልፍ ሸብረክ የማይለው ጉልበቴ ሙሉ ቀን ከዳኝ። ብዙ የውበት አድናቂ አልነበርኩም ስኖር እንደሰማሁት ወንድ ልጅ ከጉማሬ መለስ ካለ የሚል ድግግሞሼን ያነገብኩ ነብርኩ። አንዱ ነገር ሲያምረኝ ሌላ የምጥልለት ብዙ መልክ አውቃለሁ። እንደእሱ ግን ምንም የማላወጣለት ሰው ማንንም አላውቅም። ቆንጆ ሲባል፤እንኳን ወንዱን ሴቷንም በእሱ ውበት ማንፀር ጀመርኩ። OCR ፊት ለፊት ፀሀይ ያጋለው ድንጋይ ላይ ከጓደኞቼ ጋር ስኮለኮል የሚሉትን መሳት፤ከአጀንዳቸው መራቅ ጀመርኩ። ስለእሱ አስባለሁ .... አንዳንዴም ስለሁለታችን፤ ስንተቃቀፍ፣ የምወደውን ቀለም ሲጠይቀኝ፣ አልጄሪያን ጥብስ ፍርፍር ሲያጎርሰኝ ሂሂ.. ከምናቤ ስባንን ግን በቀኝ ሲመጣ በቀኝ invisible gawn ለብሼ የምጠፋ ነበርኩ።
he was like a movie... a quantin tarentino movie .. that uma thurman and jhon travolta dancing scene ..He was that guy from adele's song "when we were young" and every actor in the movie that blows up a car and walks away in slow motion. . Every A- list celebrity from the
cover of vog megazine, He is that guy in every movie every women leaves her lawfull husband for, a hybrid of idris elba and michael ealy. He is a trap, a test, a temptation , you will never pass. And i fall for him over and over and over and over again.
-
It was at a party
ሳቅ፣ ስካር፣ ነፃነት ፣ ሀላፊነት የሌለው ደስታ፣ እና ጅምር ወጣትነት የሞላው ፓርቲ ...የሲጋራ ጢስ ያፈነው እዚህም እዛም የሚተዋወቁ ከዚህ ሲወጡ unprotected sex ሊደራረጉ የሚፈልጉ ፊቶች። በጆኒ አበሻዊ የሚወዘወዙ ጠያይም ፊቶች፣በጀንትልማን it is happening again ዳሌያቸውን የሚያዘልሉ ውብ ሴቶች ... አረንጓዴ ሜንት ጂን፣ የጓደኛዬ ሽኔል ሽቶ እና የእሱ stare የሞላበት ምሽት...<<አሁን ቢመጣ ምንድነው የምለው?፣ ምንድነው የምለው?፣ ምንድን ነው የምለው?፣ ምንድነው የምለው?፣ ምንድን ነው የምለው?፣ ምንድን ነው የምለው>>.. እያልኩ መልሱን ሳላገኝ መጥቶ በረጅም ቁመቱ የቤቱን ጭላንጭል ብርሃን ጋርዶ እጁን ለዳንስ ዘረጋልኝ...እየተርበተበትኩ በጓደኞቼ የድጋፍ ሳቅ ተነሳሁ... የትግስት በቀለ ና የኔ ገላ ጀመረ... እጆቹን ወገቤ ላይ አድርጎ ወደእሱ አስጠጋኝ፣ ከቁመቱ ቀንሶ ሸብረክ ስላለልኝ ለሚያምር ፊቱ
ቀረብ ብያለሁ። አይምሮዬ ውስጥ ከማውቃቸው ፊቶች ጋር አነፃፅሬ ይበልጥ የመሰለኝን አንስቼ በቀስታ <<ሲያምረኝን ትመስላለህ>> አልኩት
ወደጆሮዬ ተጠግቶ ሶስት ፊደሎችን በማይገባቸው ከባድ ትንፋሽ ጠቅልሎ ተነፈሰልኝ
<<ታድሎ!>>ሊያጨስ እጅ ለእጅ ተያይዘን ደጅ ወጣን... መንገዱ ያምር ነበር ... ጭር ያለ ...የመንገድ መብራቶቹ ብርቱካንማ ደብዛዛ ብርሃን እየተፉ ቆመው ኑ አንዳች ታሪክ ስሩብን በሚል ጭንቅላታቸውን ያዘነበሉ ይመስላሉ። ወገቤን ይዞ ወደ ራሱ አስጠጋኝ በሁለቱ እጆቹ ፊቴን አቅፎ በሚያምሩት ግን ሰስቼ ባልነገርኳችሁ ከንፈሮቹ ትንፋሽ እስኪያጥረኝ ጉርስ ሳም
አደረገኝ። ሰፊ ትከሻው ውስጥ ሰረግኩ ሰመጥኩ።
-
እንዴት አለቀ? እኔንጃ.. it was a slip,not a walk... it was one step back not break up , it was never good bye, It was i ll see you.
-
<<ራስሽ ላይ መመሰጥ ጀመርሽ?>> ያችን ፈገግታውን ከርጋታ እና ከበላይነት ስሜት ጋር ብልጭ እያደረጋት ...መኪናዎቹን እንደተሻገርኳቸው አይነት አሯሯጥ ሮጬ ላመልጠው ፈለግኩ...He is that ሽቦ that says ዴንጀር የሀብታም አጥር ላይ... he was a caution for a wet floor፣ he was that ጦር in a heart but not from cubid. He is a story that has to begin with <<once upon a time...>> run baby girl, run፨

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Bez brown
Forwarded from ❀ርብቂ Ribki Photography (Ribka Sisay)
ስለ ሰማይ ብዙ እንደማውቅ እንዳይሰሙ....ጥያቄያቸው ያዝለኛል...

ደመና የት ነው ሚቀመመው...

የዝናብ ጥንስስ መች መች ነው ሚወጣው...

ንፋስን የት ነው ሚያራግቡት...

እያሉ ሲነዛነዙ ሰምቻለው...እንዳያቁብኝ ቤተኝነቴን የሩቅ ወዳጅ የመሬት ዘመድ ብመስላቸው ይቀለኛል።
©Ribka Sisay
......
@ribkiphoto
አታምጣው ስለው .... አምጥቶ ቆለለው (ርዕስ ነው)

የስልኬ ጥሪ ነው ከእንቅልፌ የቀሰቀሰኝ። ከንጋቱ 12:10

"ከሆስፒታል ነው የምንደውለው!! ዶክተር ፈቃደ እባላለሁ።"

"በየሱስም! እናቴ ምን ሆነች?" ብድግ ብዬ ቁጭ አልኩ:: ማታ ስኳሬ ከፍ ብሏል ስትለኝ ነበር።

"ወይዘሮ ሄለን አበራ አደጋ ገጥሟቸው ...."

"ሄለን አበራ? በስመአብ! (ልቤ ጉሮሮዬጋ ደርሳ ነበር ምልስ ብላ አቃፊዋ ውስጥ ስትገባ ታወቀኝ) ምነው እያጣራችሁ ብትደውሉ? በዚህ ጠዋት ያልታመምኩትን ሴትዮ በድንጋጤ ልትገሉኝ ነው እንዴ? ተሳስታችኋል!! እኔ ሄለን አበራ የምትባል ሴት አላውቅም! "

"ወይዘሮ ፌቨን አዳነ አይደሉም?"

"ነኝ!" አሁን ግራ ገባኝ። ስልኬን ቢሳሳት ስሜን ግን አስተካክሎ ሊጠራ አይችልም።

"የአደጋ ጊዜ ተጠሪ ተብለው የተመዘገቡት እርሶ ኖት!" ከአልጋዬ በደመነፍስ ወረድኩ

"እህ እኔ እንዲህ የምትባል ሴት አላውቅማ? ቆይ የሆነውን አስረዳኝ ምን አይነት ሴት ናት? ምን አይነት አደጋ ነው የገጠማት?"

"የመኪና አደጋ ነው። ለጊዜው conscious አይደለችም:: ቦርሳዋ ውስጥ ባገኘነው መታወቂያ ላይ የእርሶን ስልክና ስም ነው ያገኘነው።"

"እሺ መጣሁ!" አልኩኝ ነገሩ ምንም ስሜት ሳይሰጠኝ ..... አደጋ ደርሶ ነው እየተባልኩ ከዛ በላይ ጥያቄ ማብዛት ክፋት ነገር መሰለኝ። የእኔን ስም የአደጋ ጊዜ ተጠሪ ብሎ ሊመዘግብ የሚችል ዘመድ አሰብኩ ........ ምናልባት በቤት ስሟ የማውቃት ዘመድ ..... ጭንቅላቴ እዚህም እዛም እየረገጠ የተባልኩት ሆስፒታል ደረስኩ እና የተባለውን ዶክተር አገኘሁት። የተባለችው ሴት የተኛችበት ክፍል ወሰደኝ። ሰውነቷ በአብዛኛው በፋሻ ስለተጠቀለለ የማውቃት ሴት እንኳን ብትሆን መለየት አልችልም ነበር።

"የማውቃት አይመስለኝም!" አልኩት ግራ ገባቶኝ። ከጋውን ኪሱ መታወቂያዋን አውጥቶ ሰጠኝ። ሲገለባበጥ ሌላ ምስል ያሳየኝ ይመስል እያገለባበጥኩ አየሁት። በፍፁም አላውቃትም! ስሜና ስልክ ቁጥሬ ግን የመታወቂያው ጀርባ ላይ ቁልጭ ብሎ ተፅፏል። እድሜ 30 .... ቆንጅዬ ወጣት ናት። ፎቶዋ ላይ ጥርሷን ሳትገልጥ ፈገግ ብላለች። በወፋፍረሙ ተገምዶ ደረቷ ላይ የተዘናፈለ ፀጉር አላት ..... በፍፁም አይቻት አላውቅም።

"ማነው ሆስፒታል ያመጣት?" አልኩኝ ትክክለኛ ጥያቄ ይሁን ሳልረዳ

"አደጋ ያደረሰባት ሰው ነው ይዟት የመጣው። መጠበቂያ ክፍል ተቀምጧል ልታገኚው ከፈለግሽ? " ብሎ መልሴን ሳይጠብቅ በሩን ከፍቶ ወጣ ተከተልኩት የተባለው ሰው ከዶክተሩ ጋር ወደክፍሉ ስገባ ሲያየኝ ዘሎ ከመቀመጫው ተነሳ ..... አጠገቡ ተቀምጦ የነበረ በግምት የ4 ዓመት የሚሆን ህፃንም ተከትሎት ብድግ አለ።

"ቤተሰቧ ነሽ? ምን ማድረግ እንደነበረብኝ አላወቅኩም ነበር! እጄን ለፖሊስ ልስጥ? እሰጣለሁ በቃ! (መላ አካሉ ይንቀጠቀጣል።) ከየት መጣች ሳልላት ነው ዘው ብላ የገባችብኝ በቦታው የነበረ ሰውም አልነበረም። አልነጋምኮ .... የሞተች መስሎኝ ነበር !" ድንጋጤው እንዳለ ነው የለበሰው ጥቁር ሱፍና ነጭ ሸሚዝ በደም እንደተነከረ ነው። እጆቹ ላይ የቀረውን የደረቀ ደም ሊጠርገው ግድ ያለው አይመስልም ወይም ከነጭራሹ ደም እጁ ላይ መኖሩንም አላስተዋለውም። ግራ ገባኝ። ምንም በማላውቀው ክስተት ውስጥ የተነከርኩት እኔ ምን ልበል? አይኖቼ ህፃኑ ላይ መንቀዋለላቸውን ሲያይ

"ልጇ ነው። አብረው ነበሩ። እማ ብሎ ሲጮህ ነው ያየሁት እኔ እንጃ ምን እንደተፈጠረ። እሱ የእግረኛ መንገድ ላይ ነበረ። ቤተክርስቲያን እየሄዱ መሰለኝ ነጠላ ለብሳ ነበር። .... ቤተክርስትያን ለመሄድ ራሱ በቅጡ አልነጋም ነበር:: "

ምን እንደማደርግ ሳላውቅ ህፃኑጋ ተጠግቼ በርከክ አልኩ። ደነበረ። ትንንሽ እጆቹን ልይዛቸው እጄን ስዘረጋ ሰበሰባቸው።

"ስምህ ማነው?" አልኩት እናቱን መኪና ሲገጫት በአይኑ ካየ ሁለት ሰዓት ላልሞላው ህፃን የእኔ ጥያቄ ምኑ ነው? እኔስ ምኑ ነኝ? ዓለምስ ራሱ ምኑ ናት?

"ባባ" አለኝ የደረቁ ከንፈሮቹን እያላቀቀ

"ባባዬ እኔን ታውቀኛለህ?" አልኩት የማይጠየቅ ጥያቄ እንደሆነ እያወቅኩ። በአሉታ ጭንቅላቱን ነቀነቀ።

"አባትህ የት እንደሆነ ታውቃለህ?" አሁንም በአሉታ ጭንቅላቱን ነቀነቀ። ግራ ገባኝ! ይህቺ ሴት ማናት? ለምንስ ነው የማላውቃት ሴት መታወቂያ ላይ የእኔ ስም የሰፈፈረው?

"ዶክተር እሷ ያለችበትን ሁኔታ ንገረኝ? ትድናለች አይደል? " እንድከተለው ምልክት ሰጥቶኝ ወደ ቢሮ ይዞኝ ሄደ። ያለችበት ሁኔታ አሳሳቢ እንደሆነ ለመገመት አልተቸገርኩም።

"ተጨማሪ ምርመራዎች አዝዣለሁ። ውጤቶቹ እስኪመጡ እርግጠኛ የሆነ ምላሽ ልሰጥሽ አልችልም። ጭንቅላቷ በሃይል ተጋጭቷል። እንዳልኩሽ ሁሉም ውጤት ሳይመጣ ብዙም ማለት አልችልም።"

"የምትድን ይመስልሃል ግን? የምትነቃ ይመስልሃል?"

"ይቅርታ ይሄን አሁን መናገር አልችልም።"

"እሺ እኔ ምን ላድርግ? አላውቃትምኮ? ህፃኑንስ ምን ላድርገው? ምን ጉድ ውስጥ ነው የገባሁት?"

"የማታውቂያት ከሆነ ሆስፒታሉ ለፖሊስ የማሳወቅ ግዴታ አለበት" አለኝ። አላውቃትም ያልኩትን ግን ያመነኝ አይመስልም።

"እሺ የገጫትስ ሰውዬ?"

"ቤተሰብ ቢገኝ ወይ በሽምግልና ያልቃል ወይ ይከሱታል። እንደምትዪው የማታውቂያት ከሆነ ጉዳዩን ለፖሊስ ማሳወቅ ግዴታችን ነው። ሰውየው የማምለጥ ሀሳብ የለውም። ሲገጫት ማንም አላየውም ጥሎ መሄድ ይችል ነበር። ይልቅስ ያላነሰ ብር ከፍሎ የግል ሆስፒታል ሊያሳክማት ፈቃደኛ ከሆነ በህግ ይዳኝ በሽምግልና ቤተሰብ ነው የሚወስነው።"

ሁሉንም ጥዬ መሄድ ፈለግኩ። ምን አገባኝ እና ነው እዚህ ጣጣ ውስጥ የምገባው ብዬ ..... ወደመጠበቂያው ክፍል ስመለስ ህፃኑ የምስራች የምነግረው ይመስል ከተቀመጠበት ዘሎ ተነስቶ በተስፋ አይን አይኖቼን ሲያየኝ እግሬ የሚቀጥለውን እርምጃ መራመድ አቃተው:: አጠገቤ ደርሶ ትንሽዬ ፊቱን ወደ ላይ አንጋጦ እያየኝ ሊያለቅስ ጉንጩ እየተንቀጠቀጠ

"እማዬስ?" አለኝ:: እንባው ከፊደሎቹጋ ከአይኑ እየወረደ..... ከሱ ብሼ እንደህፃን ማልቀስ አማረኝ:: አቅፌ ብድግ እያደረግኩት በዛች ቅፅበት አብሬው እማገዳለሁ እንጂ እሳት ውስጥ ጥዬው እንደማልሄድ አወቅኩ። ...

ይቀጥላል ........

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Meri feleke
አታምጣው ስለው አምጥቶ ቆለለው #2

"የገጨሃት ቦታ ውሰደኝ ምናልባት ሰፈሯ ሊሆን ይችላል። ምናልባት ስልኳን እዛ ጥላው ሊሆን ይችላል። የሚያውቃት ሰው ሊኖር ይችላል!"

በውስጤ ምናልባት ጎዳና ላይ ቢሆንስ የምትኖረው ብዬ አስቤያለሁ ጮክ ብዬ አላወራሁትም እንጂ ምናልባት ከነአካቴው ስልክም አልነበራት ይሆናል። መታወቂያዋ ላይ ያለውን ቀበሌና የቤት ቁጥር ተከትዬ ቀበሌ ሄጄ ቤቷን ፍለጋ አስቤዋለሁ። ቀላል እንደማይሆን ግልፅ ነው። ቀበሌ አልወድም!!

"በፍፁም እኔ አልነዳም። ህም ...በጭራሽ መሪ አልይዝም። ታክሲ .....ራይድ ይጠራ" ሲል አሳዘነኝ ማንም ትኩረት ሰጥቶ እሱን ያየው የለም እንጂ እሱም ከባድ ድንጋጤ ላይ ነው። አሁንም እጆቹ እየተንቀጠቀጡ ነው። ሲያወራ መሸሻ ያጣ አይነት ዓይኖቹ መሬቱን ይምሳሉ። ይሄን እያለኝ ድርብብ ያሉ የሴት ወይዘሮ የሚያነክስ እግራቸውን በጌጠኛ ከዘራ እያገዙ የሚራመዱ ሰውዬ አስከትለው ወደ ክፍሉ ገቡ።

"ኪያዬ ......ደስ አላለኝም ! በለሊት አትጓዝ እያልኩህ ...." እያሉ እያገላበጡ ሲስሙት እና ደህና መሆኑን ሲያረጋግጡ ልጃቸው ተገጭቶ እንጂ እሱ ገጭቶ አይመስልም። እሱም እናቱን ሲያይ የሆነው የልጅ መሆን ካቀፍኩት ህፃን አይለይም ነበር። በኋላ እሱም ገብቶት ነው መሰለኝ ከእናቱ እቅፍ ወጥቶ በማፈር ሲያየኝ ነው ገና ሰው እንኳን መኖሩን እናትየው ያዩት።

"እባክሽ ልጄ አንድ ልጄ ነው በሽምግልና እንጨርሰው? (ባጌጠ ልብሳቸው እግሬ ስር ሲንበረከኩ ክብራቸው አላሳሰባቸውም። እናት ናቸዋ! ደንግጬ ደነዘዝኩ። ካሰብኩት በላይ ውጥንቅጥ ውስጥ እንደተዘፈቅኩ ገባኝ። ከተንበረከኩበት ላነሳቸው እየሞከርኩ ከአፌ ግን ቃል አይወጣልኝም።) ካሱ የምንባለውን እንክሳለን። እናትየው እስኪሻላት ህፃኑንም ቢሆን ወስጄ እንከባከባለሁ። እባክሽ ልጄን አሳልፈሽ አትስጪብኝ?"

ለደቂቃ ህፃኑን ሰጥቻቸው ጭልጥ ብዬ መጥፋት ሁሉ አሰብኩ። ባባ ቀልቡ የነገረው ይመስል ጭምቅ አድርጎ አቀፈኝ። የተገጨችው እህቴ ብትሆን ምንድነበር የምወስነው? ብትሞት የእነሱ ካሳ የህይወት ካሳ ይሆናል? እሺ ጥፋቱ የሷስ ቢሆን? እንዳለው እሷ ብትሆንስ ዘው ብላ የገባችበት? ኸረ ምን አይነቷ ሴት ናት ግን እዚህ ጣጣ ውስጥ ዘፍቃኝ ማን እንደሆነች እንኳን የማላውቃት

"እባኮትን ይነሱ። እኔ ለራሴ ዞሮብኛል።"

የተፈጠረውን አስረዳኋቸው። አባትየው መታወቂያው ላይ ባለው አድራሻ ቤቱን ሊያፈላልጉ ሀላፊነት ወሰዱልኝ። ማን እንደሆነች እና ከእኔጋር የሚያዛምዳትን ነገር እስክደርስበት ባባ እኔጋ እንዲቆይ ወሰንኩ። እነርሱም የሚያስፈልገውን ሊያሟሉለት እና ሊጠይቁት ቃል ገቡልኝ። አንድ ላይ በእነርሱ መኪና እናትየው እየነዱ አደጋው የደረሰበት ቦታ ሄድን:: ምንም ነገር የለም። ከአልፎ አልፎ ሂያጅ መንገደኛ ውጪ በአካባቢው ማንም አይታይም። የመኖሪያ ሰፈርም አይደለም። ዓይኔ መሬቱ ላይ ካለ አንድ ብር ሳንቲም ላይ አረፈ። ደም ነክቶታል። ለምን እንዳነሳሁት አላውቅም ግን አነሳሁት። የሷ ይሆን? በእጇ ይዛው ነበር? ወድቆባት ልታነሳ ስትል ይሆን መኪናውን ያላየችው? ወይስ ሌላ ሰው የጣለው ሳንቲም ነው? ስልኬ ሲጠራ ባላወቅኩት ምክንያት ደንግጬ ዘለልኩ

"አይዞሽ አይዞሽ" አሉኝ እናትየው መደንበሬን ሲያዩ

"እማ በጠዋት የት ሄደሽ ነው? " ልጄ ናት። ቤቴን ረስቼዋለሁ። ሰዓቱን ረስቼዋለሁ። ዛሬ ቅዳሜ መሆኑንም እረስቼዋለሁ።

"መጣሁ እናቴ! ለባብሰሽ ጠብቂኝ" አልኳት ቅዳሜ ጠዋት ሁል ጊዜ እናትና አባቴ ጋር ነው ቁርስ የምንበላው።

እነርሱ ስልክ ተቀያይረን እቤት አድርሰውኝ ተመለሱ። የማልዋሸው በዛው ቢጠፉስ ብዬ አስቤያለሁ። ሰው ለማመን ቅርብ አይደለሁም። የመኪና ታርጋቸውን መዝግቤ መታወቂያቸውን ፎቶ ኮፒ አደረግኩ።

"እማ ትልቅ ሰው የሚበላውን ምግብ ይበላል ኸረ ጥርስኮ አለው" ትለኛለች ልጄ ለባባ ምግብ ምን ልስጠው ብዬ ስባዝን እየሳቀችብኝ። ልጄ 15 ዓመቷ ነው። በስንት ዓመቷ ምን እንደበላች ጠፍቶኛል። ለመጨረሻ ጊዜ ገላዋን መች እንዳጠብኳት ረስቼዋለሁ ..... ባባን አጣጥቤ እነእማዬጋ ተያይዘን ሄድን::

"እግዚአብሄር የሆነ ነገር ሊያስተምርሽ ነው ይሄን ህፃን ወደ ህይወትሽ ያመጣው" አለችኝ እናቴ የሆነውን ሁሉ ከነገርኳቸው በኋላ። ከቤተሰቡ አንድ ሰው እንኳን ድንገት ቢያውቃት ብዬ አስቤ ነበር:: ማንም አያውቃትም። (እናቴ ምን ማለቷ እንደሆነ አውቃለሁ። ማግባት አለብሽ ልጅ መድገም አለብሽ ነው ቅኔው። ወንድሜ በሚያስቀና ትዳር ሶስተኛ ልጁን ሰልሷል። የእኔ ያለባል መቅረት ያሳስባታል:: )

"እማ ደግሞ እግዚአብሄር እኔን ስለሚወደኝ እኔን ለማስተማር ይሄን ህፃን አይቀጣም! የሆነችን ሴት በመኪና አስገጭቶ ለኔ ትምህርት አይሰጥም። እነርሱምኮ ፍጡሮቹ ናቸው እኔን ለማስተማር ህይወታቸውን የሚያዘባርቅባቸው አሻንጉሊቶች አይደሉም!!" አልኳት። ወንድሜና አባቴ ተያይተው ጨዋታውን ቀየሩት። ከእማዬጋ እንዲህ አይነት ወሬ ከጀመርን ማባሪያ የሌለው ጭቅጭቅ እንደሆነ ያውቃሉ:: እዛው ቤተሰቦቼ ቤት ሆኜ ወደ ከሰዓት ስልኬ ጠራ ባባ ኩርምት ብሎ ከተኛ ሰዓታት አልፈውታል።

"አብርሃም ነኝ"

"አብረሃም? አብረሃም?"

"የግሩም አባት! ልጅቷን የገጫት ልጅ አባት... "
"እእ ....እሺ "

"የምትኖርበትን ቤት አግኝተነዋል። አከራዮችዋን አናግረን የእሷ ቤት መሆኑን አረጋግጠናል።"

"በዚህ ፍጥነት? እንዴት? ያውም በቅዳሜ?"

"ብዙም አስቸጋሪ አልነበረም:: የቤት ቁጥሩ የአከራዮችዋ ቤት ነው:: ደግሞስ የልጄ ጉዳይ አይደል? ይልቅ መምጣት ሳይኖርብሽ አይቀርም። ከባሏ ውጪ ማንም ዘመድም ሆነ የቅርብ ሰው እንደሌላት ነው የነገሩን።"

"ታዲያ ባሏ እያለ እኔን ምን ቤት ናት ብላ ነው የፃፈችኝ?"

"ባሏ ከታሰረ ሁለት ዓመት አልፎታል።"

"እሺ እኔ ምን ቤት ነኝ መታወቂያዋ ላይ የተገኘሁት? ወይ ፈጣሪ ! "

"እኔ ምን አውቄው ብለሽ? (እኔ አልፃፍኩሽ የሚል አንድምታ ባለው ለዛ) ምናልባት በባለቤትዋ? እስር ቤት ያለ የቅርብ ሰው ወይ ዘመድ የለሽም?"

"በፍፁም ኸረ እኔ ጭራሽ የታሰረ የሩቅም ሰው አላውቅም። "

"ምናልባት አከራዮችዋ ከሚነግሩሽ ነገር ፍንጭ ልታገኚ ስለምትችዪ ብትመጪ መልካም ይመስለኛል:: ብዙ አመት ኖራለች አብራቸው.... እ.... ባለቤቷ ... አሸናፊ ይባላል ነው ያሉኝ .......እንደው ካወቅሽው "

ከጀርባዬ የሆነ ነገር ማጅራቴን በሀይል የደለቀኝ ነገር መሰለኝ .........ጭው አለብኝ። አይሆንም። እሱማ አይሆንም! ሊሆን አይችልም።... ስም ተመሳስሎ ነው.... ማሰብ ተሳነኝ!!

"ምነው ሴትየዋ ሞተች እንዴ?" ትለኛለች የወንድሜ ሚስት ......

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Meri feleke
2024/09/23 03:24:58
Back to Top
HTML Embed Code: