Telegram Web Link
Forwarded from Sunset Hiking (yise)
Explore the incredible world we live in with SUNSET HIKING TEAM!

Do you love hiking + traveling + adventures and new experiences?......You are at the right place. This is the adventurers family!!!
Welcome

"Join our telegram channel" @sunsethiking
"Join the discussion group" @sunsethike
"Our photographs are shared on" @sunsetphotography
Forwarded from ቅንድል ኢትዮጵያ (#ነፂ-ከዕለታት)
ሁለገቧ አርቲስት ሳያት ደምሴ በአዲሱ አመት በአዲስ ስራ ብቅ እንደምትል ነግራናለች...........ምን ይዛ ትመጣ ይሆን?

"በሴቶች ላይ እየሆነ ያለውን አግባብ ያልሆነ ተፅዕኖ ለማቆም ሴቶችን ብቻ ማስተማር ተገቢ አይደለም ችግራቸውን ለራሳቸው መልሼ መናገር አልፈልግምና........" ታድያ ሳያት የተሻለ መንገድ ነው የምትለው ምን ይሆን?



#እነዚህን እና መሰል ጥያቄዎችን ይዘን በአውደብሩሃን ገፃችን ከሳያት ጋር ያደረግነውን ቆይታ በቅንድል ዲጅታል መፅሔት ወደ እናንተ ልናደርስ አንድ ቀን ብቻ ቀረው፡፡



ቅን ፣ ምክኒያታዊ ፣ሀገር ወዳድ ትውልድ ለኢትዮጵያ

Kendel on Telegram
http://www.tg-me.com/KendelM
Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine
Forwarded from ቅንድል ኢትዮጵያ (Ermiyas Dejene)
ቅንድል መፅሔት ቅፅ-2 ቁጥር-5_edited87.pdf
5.8 MB
#ቅንድል_ዲጂታል_መፅሔት

ቅፅ2- ቁጥር-5

ልዩ የበዓል ዕትም

በርካታ አስገራሚ ፣ አስተማሪ እና አዝናኝ ፅሁፎች የተካተቱበ

ያንብቡት እና ብዙ ያትርፉበት📝

ቅንነት ድል ያደርጋል!

Kendel on Telegram
http://www.tg-me.com/KendelM
Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine
Me trying to flirt
*sends a picture that is completely black*
እኔ ፡ A pic of me at the moment. እጄ ምን እያደረገ እንደሆነ ገምት
እሱ ፡ ምንም አይታየኝም፣ ጥቁር ብቻ ነው
እኔ ፡ እኮ ገምት ነው ያልኩት፣ use your imagination
እሱ፡
እኔ፡ ሶኬቱን እየፈለገ
እሱ፡
እኔ፡ መብራቱን ለማብራት
እሱ፡
እኔ፡ እንዴ! can I be more obvious?
እሱ፡ ምንም የምትይው አልገባኝም! መብራት ጠፋባችሁ?
አዪዪዪዪ 😂

@wegoch
@wegoch
@wegoch

#hewan huletshi
#ወግ_ብቻ
.
............“አንድ ሰው ሕጻን ሆኖ ሲወለድ እጁን (መዳፉን) ጨብጦ ነው፤ አንድ ሰው ሸምግሎ ሲሞት ደግሞ እጁን (መዳፉን) ዘርግቶ ነው” ይላል ካልታወቀ ምንጭ የተቀዳ አባባል፡፡

ለአንድ ሕጻን አንድን ነገር በእጁ አስይዛችሁት ካወቃችሁ ልጁ የያዘውን ነገር በቀላሉ እንደማይለቅ ትደርሱበታላችሁ፡፡ አንድ ሕጻን ልጅ እጁን ጨብጦ መወለዱ ሁሉን ለመያዝ፣ ሁሉን በእጁ ለማስገባትና ሁሉን ነገር በቁጥጥሩ ስር ለማድረግ የመሞከሩ ምልክት ነው፡፡

አንድ ሰው ሸምግሎ ሲሞት እጁን ዘርግቶ መሞቱ ደግሞ ሁሉን አይቶት፣ ሞክሮት፣ ጨብጦና “የእኔ ነው” ብሎ በመጨረሻ ምንም ነገር የእርሱ እንዳልሆነና አንድ ቀን ሁሉም ነገር ከእርሱ ቁጥጥር ውጪ እንደሚሆን የመገንዘቡ ምልክት ነው፡፡

እውነታው ይህ ነው፡- ተወልደን በልጅነት ባሳለፍንበት ወቅትና ሸምግለን ከዚህ አለም ወደመሰናበት በምንደርስበት ወቅት መካከል ባሉን እንደ ጥላ በሚያልፉት አመታቶቻችን መያዝና መቆጣጠር በምንችለውና በማንችለው መካከል መለየት አስፈላጊ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ነገ ሁሉንም ነገር ትተነው እንደምናልፍ በመገንዘብ ሁሉን ነገር የእኛ ለማድረግ ጦር ስንማዘዝ ዘመናችንን እንዳናባክነው እናስተውል፡፡

እጅህ በገባው ነገር ደስተኛ ሁን፣ ለመልካም ነገር ተጠቀምበት፡፡ እጅህ ለማስገባት ያልቻልከውን ነገር ለማስገባት ሞክር፣ ነገር ግን ሁሉን ካልያዝኩ በማለት ስትሟገት በጦርነትና በፍርድ ቤት ዘመንህን አታስበላ፡፡ የአለምን ምድር ሁሉ ጨብጠን የእኛ እናደርጋለን ብለው የነበሩ ምእራባውያን ቅኝ ገዢዎች የጨበጡትን ሁሉ ቀስ በቀስ እየለቀቁ እንደሄዱ አትዘንጋ፡፡ እንዲያውም የእነሱንም ቀስ በቀስ የሚያስለቅቃቸው ሁኔታ እየተጋረጠባቸው ነው፡፡

ለጊዜው ነው እንጂ ምንም ነገር በቋሚነት የአንተ አይደለም፡፡ የእኔ ነው ብለህ የምታስበው ሁሉ ለጊዜው በአደራ የተሰጠህ ነው፡፡ ዛሬ አንተ የምትኖርበትን ቤትና መሬት ትናንት የእኔ ነው ብሎ የሚኖርበት ሰው ነበር፡፡ ዛሬ ግን የአንተ ነው፡፡ ነገ ደግሞ ይህንን ስፍራ ሌላው ተረኛው ጨባጭ ይረከበዋል፡፡ ቁም ነገሩ በዘመንህ የጨበጥከውን ነገር የመልቀቂያህ ጊዜ እስከሚመጣ ድረስ ለመልካም ዓላማ የመጠቀምህ ጉዳይ መሆኑን ላስታውስህ፡፡

ዶ/ር እዮብ ማሞ
@wegoch
@wegoch
@wegoch
.......,,......,,.......,,......,,.......,,...
“… ብገልህ ደስ ይለኛል !... እንንንንቅ አድርጌ እንደዚህ … “ አንገቴን አንቃ … አይኖቿ ደፍርሰዋል … አፏ መጠጥ መጠጥ ይሸታል … አልታገልኳትም ! … ስለማውቃት እንኳን እጄን ላነሳባት ያነቀችውን አንገቴን ላስለቅቃት አልሞከርኩም …
“በ…ል ታገለኛ ! አስለቅቀኝና ምታኝ!..” … የያዘችው የዋይን ጠርሙስ ስባሪ ያሳቅቃል … ራሷን እንዳትጎዳ ነው ፍርሃቴ …
ገና ከመግባቴ ነው በጩኸት የተቀበለችለኝ …ስራ አምሽቼ ነው የገባሁት… አስቀድሜ ገዝቼ ያመጣሁትን ዋይን መንጭቃ ተቀብላኝ ወደጭንቅላቴ አስተካክላ ወረወረችው … ነጩን ግድግዳ ስስ ቀይ ቀለም አለበሰው … ስብርባሪው መሬት ተበተነ … ፀጉሯ ተበታትኗል … ያደረገችው የሌሊት ፒጃማ ለአስፈሪነቷ ተጨማሪ ሆኗታል … ተንደርድራ ሄዳ የጠርሙሱ ግማሽ አልተሰበረ ኖሮ አነሳችው … ወደኔ መንገድ ጀመረች …
“እገድልሃለው!... “ ወደኋላ ሸሸሁ …
“ብጥስጥስ ነው የማደርግህ …!” ስባሪውን አስቀድማ… ሶፋውን ከነሲሊፐር ጫማዋ ረግጣ ከበላዬ ቆመች … የሶፋው ጠርዝ የሌሊት ፒጃማዋን ይዞ በከፊል ተራቆተች
“ጭንቅላትህን ከአንገትህ ለያይቼ ደምህን….” መሸሻዬን ጥግ ጨረስኩ … ትልቁ ሶፋ ላይ ተንጋለልኩ … የጠርሙስ ስባሪ የያዘው እጇ ወደኔ ተሰነዘረ …ተረጋግቼ ክንዷን ያዝኩና ብዙም ባላሰበችው ሁኔታ በቅልጥፍና ስባሪውን አስጣልኳት … ጥንካሬዋ እኔ የጥቁር ቀበቶ ባለቤቱን እንኳ በቀላሉ የምቋቋመው አይደለም !
በምድር የቀረችኝ ልቤ ላይ ቦታ ያላት ብቸኛ ሴት ናት … ማንም በሌላት እንቁ ሴት ነፍስ ላይ ብቸኛው ንጉስ ነኝ ! … እናት አባት እህት ወንድም ዘመድ አላውቅም … ጭልም ካልኩበት ፀሃይ ሆና የመጣችልኝ እቺው ውዷ ሚስቴ ናት ! … እሷ ፀሃይ ከሆነችኝ ድፍን አስር አመት …
በተገናኘኝ በሁለተኛ አመታችን ሌላ ዘመድ እንዳለኝ ሌላ ስሜን አስከትላ የምትጠራ ነፍስ ሆዷ ውስጥ እንዳለች ስታበስረኝ አልቅሼ በማላውቀው ሁኔታ አለቀስኩ !.... ለህይወት ጉጉ ሆንኩ … ስልችት ያለኝ ህይወት ከእንደገና ታድሶ ብርሃን ሆኖ ያጓጓኝ ጀመር …
ልጄን እቅፌ ላይ ሳያት እግዜር በፍጥረቱ ምን ያህል ተደንቆ እንደነበረ በስሱ ገባኝ!... እግዜርን ሆንኩት … ልጄን ቁልቁል እናቷ ደረት ላይ እያየኋት ብዙ አሰብኩ …ብዙዙዙዙዙዙዙዙዙዙዙ!
በዳዴ ስትሄድ… “አባዬ!” ስትለኝ … በትናንሽ ከንፈሮቿ ስትስመኝ … የአንገቷ ጠረን … እኔና እናቷ መሃል ስትሆን … ትናንሽ እግሮቿን በስስት ስስማቸው … ከፍ ብላልኝ እሽኮኮ አድርጌ ትምህርት ቤት ስወስዳት … ሳደምጣት … እጄ ላይ እንቅልፍ ሲወስዳት ( አይኖቿ ተከድነው ስታምር ደግሞ ) … ደስታዋን ሀዘኗን (ውይ ሀዘንስ አይይብኝ .. የውዴንም የልጄንም ሀዘን እኔ ልዘን !) በእቅፏ ስትነግረኝ … ስታጋራኝ …. በጣም ብዙ አሰብኩ !

ብዙዙዙዙ ብመኝም አልሆነም !... ምክንያቱ ግልፅ ባልሆነ ሁኔታ ውዴ እቅፍ ውስጥ እያለች በአራስነቷ ጥላን ሄደች ! … ለክርስትናዋ እንኳ አልደረሰችም … አግኝቼ አጣሁ !... ልጄ ትንሹዋ እኔ ሞተች ! … በልጃችን እልፈት ክፉኛ ባዝንም አልተቀየምኳትም …
ከዛን በኋላ ለኔ ስትል የተፅናናች ትምሰል እንጂ ሀዘኑ ከሰውነት አወጣት … የሷ ፀሃይ እየጠለቀች … አይኔ እያየ ጀምበሬ ታዘቀዝቅ በአስፈሪው ደመና ትዋጥ ጀመር… ለልጃችን ሞት ራሷን ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ አድርጋ ለራሷ ይቅርታ የማታደርግ ሆነችብኝ !...
እንዲህ እንደዛሬው የልጃችንን ልደት እየጠበቀች በፀፀት ራሷን ትቀጣለች … ሌላ ማንነት ውስጥ ሰምጣ ቀረችብኝ … ያልሞከርኩት ሃኪም ያልሞከርኩት ፀበል ያላየሁት ነገር አልነበረም !... ቢያንስ በወር አንዴ እዚህ ማንነት ውስጥ ሆና አገኛታለሁ … መቼ እንደምትቀየር ስለማላውቅ ሁሌም ከኔ አልፋ ራሷን እንዳትጎዳ ነው ፍርሃቴ ! … በዚህ ሌላኝው ማንነቷ ፍርሃት እሷም ሰው አትቀርብም … ሌላ ልጅ ለመውለድ አልደፈረችም !

የልጃችን የሙት መንፈስ እንደሚያሰቃያት ደህና ስትሆን እያነባች ደጋግማ ነግራኛለች … እያነባች ማታ ስላደረገችው ነገር ይቅርታ ትጠይቀኛለች … እያነባች ድጋሚ እንደማታደርገው ትነግረኛለች … እያነባች ቁስሌን ትጠርጋለች …
ከነእንባዋ እስማታለሁ …. ሌላ ቀን ቢደገምም … ሌላ ጊዜ እነደዛው አስፈሪ ብትሆንም ዛሬም ከነእንባዋ እስማታለሁ … ዛሬም ከነአውሬ ማንነቷ ባልቀነሰ ፍቅር አፈቅራታለሁ …
ትላንት ካደረገቸው ትዝ የሚለኝ ያ ነፍስ ነጣቂ አሳሳሟ ነው …
ትላንት ትዝ የሚለኝ ያ በሳቅ እንባ የሚያመጣ ጨዋታዋ ነው …ከዛ አሟሚ የፍቅር ቃሎቿ … ስሜ አፏ ላይ ፍስስ የሚለው… ስስቷ…. ጥፍጥናዋ ብቻ ነው … !
ትዝ የሚለኝን የመምረጠጥ መብት ለራሴ ሰጥቻለሁ !... የምወደውን ብቻ ነው የማስታውሰው !... ትውስታዬ ላይ ብርሃኗ እቺው ውዷ ሚስቴ ናት!
እና……!
ነገም ያን ዋይን ይዤ እሄድና እንደሌላው ጊዜ የሰራችውን ምግብ እየተሳሳቅን ከበላን በኋላ እንደአዲስ ቀለበት ተንበርክኬ አጠልቅላታለሁ … (እንደሁሌው ህመሟ ሲነሳ አውልቃ ብትጥለው እንኳ እስካልቀየማት ድረስ )
ነገም ገና እንደገባሁ ከንፈሯን ስሜ በሌሊት ልብሷ ታቅፌያትq መኝታ ቤታችን ወስጄ …
ነገም ብትቧጭረኝ … ብትመታኝ … ልትገለኝ ብትጥር…
ነገም… በቡጭሪያዋ የቆሰለ ገላዬን እየነካካች …በእንባዋ ብታጥበኝ … እንደሁሌው “… ስትሄድ ገድለኸኝ ሂድ! “ ብትለኝ …
ነገም…
ነገም..
ነገም…
ነ…ገም …. አሁን ከማፈቅራት በላይ አ.ፈ.ቅ.ራ.ታ.ለ.ሁ !...

የጠቆረ ልብ

@Wegoch
@Wegoch
ለቤተሰቤ ግድ የለሽ ነኝ … በድህነት ለማደጌ … ቁርሴን በልቼ ምሳ ላለመድገሜ ጥፋተኛ አድርጌአቸዋለሁ !... አዲስ ለላመልበሴ በሰቀቀን ከጓደኞቼ አንሼ ..ከነኣካቴውም ጓደኛ እንዳይኖረኝ በጭምት ለማደጌ ከነሱ ውጪ ማንም ተወቃሽ የለም !...
አዎ ከነዚህ እናትና አባት ተብዬዎቼ ውጪ ማንንም አልወቅስም !... ሆዴን ረሃብ እየሞረሞረኘኝ እናቴ ብታቅፈኝ ምኔ ነው … ሱሪዬ ተቀዶ ወሸላዬ ታይቶ ጓደኞቼ አይተው ስቀው ሲያሳቅቁኝ ሳለቅስ የአባቴ “ወንድ አይደለህ አታልቅስ !” የሚለው የቁጣ ቃል እንዴት ማፅናኛዬ ይሆናል !...
ሲርበኝ መታቀፍ አይደለም የምፈልገው … ምግብ ነው !...
ሲጠማኝ ቁልምጫ አይደለም የምፈልገው ….ውሃ ነው !
ሲያመኝ “እኔን !” መባል አይደደም የምፈልገው ….ህክምና እንጂ !...እና … ቀይ ስጋ ቢያምረኝ ውሻ የማይበላው ነጭ ቅንጥብጣቢ ገዝቶ “ይሄን ብላ ያለኝ ይሄ ነው !” ቢል ከደግነት ይቆጠርለታል አይደል !... እኔስ … ፈልጌ ነው እንዴ የመጣሁት !...
እንዲሁ በጥላቻ አንገቴን ደፍቼ ጭምድድ እንዳልኩ አደኩ!... አባት ተብዬውንም እናት ተብዬዋንም ጥልት እንዳደረኳቸው አደኩ … ሰውየውን “ደመቀ!” ሴትየዋንም በስሟ “ዘሪቱ!” እያልኩ በስማቸው ነው የምጠራቸው ….እህትና ወንድሞቼን ጠርቻቸውም አላውቅ!...
አሁን ታዋቂ ተዋናይ ሆኛለሁ ! … አድናቂዎቼ በመላው አለም የሚገኙ ለፊልም የደረሱ ሁሉ ናቸው … ዝናዬ ቆንጆ እንስቶች ገላቸው ላይ ስሜን እስኪነቀሱ ድረስ ነው … ደብቅነቴ … ከስራዬ ውጪ አንድ ጊዜም እንኳ የትኛውም ሚዲያ ላይ አለመታየቴ የበለጠ ተወዳጅና ተፈላጊ እንድሆን አድርጎኛል … አሁን አልራብም … አሁን አልታረዝም …
ከስንት የውዷ ሚስቴ ውትወታ በኋላ ቤተሰቦቼን ልጠይቅ ሀገሬ ገባሁ …
“እልልልልልልልልልልል …. እሰይ……እልልልልልልልልልልልልል….” አለች እናቴ ገና ስታየኝ … ኑሯቸው አልተቀየረም … እናቴ ፀጉሯ ነጭ ከመሆኑ በላይ ቆዳዋ ተሸብሽቦ የእርጅናና የድህነት ሜካፑ ማዲያት ቤቱን ቀልሶባታል … ቤት ተቀምጠን ልጆቼን እኔንና ሚስቴን አይታ አልጠግብ አለች … ሚስቴ ራሷን መቆጣጠር አቅቷት ከአይኗ እንባ ይወርዳል …
ስንረጋጋ …
“ደመቀስ …!?“ አልኳት … የሆነ ነገር የሰኩባት ይመስል ጭምድድ አለች …
“ማረፉን አልሰማህም !” አለችኝ ድምፁዋ ስልምልም ብላ …. “ደምዬማ አረፈ … ጨክኖ ጥሎኝ ሄደ ልጄ … ይሄ ክፉ አባትህማ ሄደ … ጨካኝ አይደል … ጀብደኛ ነውኮ ያንተ አባት ያለስንቅ ሄደ …. እህህህህህ… ደምዬ ሞተ … “ ቡና የምታፈላበት ወንበር ላይ እንደተቀመጠች ከአይኗ እንባ ይፈሳል … ጥቁር በጥቁር እንደለበሰች አሁን ገና አስተዋልኩ …. በድን ሆንኩ !.. ምን ሆኜ ነበር?! … ሚስቴ እንኳን ምክንያት አግኝታ … ድሮ በእንባዋ በስብሳለች
“ደምዬማ ሞተ ልጄ … የልጄን ፍሊም አድርጉ ከወንድሞችህ ጋ ጭቅጭቅ ነው … እዚች አልጋ ላይ ሁኖ … ታዲያ እዛች አንተ ፍሊምህ ላይ ለአባትህ “አባዬ…!” ብለህ ስትጣራ ተሸቀዳድሞ “ወዬ !” ይላል … የፍሊምህ አባት እንዳይቀድመው ነውኮ … “ወዬ ልጄ !...እኔንኮ ነው አባዬ የሚለው …” ይላል ደስስስ ብሎት …” አለሜ ልጃችን አባዬ ሲል አያምርም …!?” ይለኛል … ሁሌም ነውኮ … አይቶህ አይጠግብም … በቲቢው ባዬህ ቁጥር “ወዬ ልጄ…” እንዳለ አይኑ ላይ እንደተንከራተትክበት ሞተው … አይ ደምዬ የኔ ከርታታ….!”
ከዚህ በፊት እንደዚህ አልቅሼ አውቅ ነበር!? …
ከዚህ ቀደም እንደዚህ ራሴን ጠልቼው ነበር !?….
ፍርክስክስ አደረገችኝ …
ማታ አልጋችንን እያነጣጠፈች …
“ባርዬ …” በልጅነቴ እንደምትጠራኝ
“ኧ…!” እንደልጅነቴ መለስኩላት …. ሽቁጥቁጥ እያለች …

“መቼ ነው እናት ያለችበት ፍሊምህን የምትሰራው ?… “እማዬ !” የምትልበት ያለው …? “ … ልቤን እፍፍፍፍን አደረገኝ …ሌሊቱን በብርድልብሱ አፌን አፍኜ ሳለቅስ አደርኩ …
በጠዋት ተነሳሁና ….
“እማዬ …. “
“ኧ!” ክው ብላ ደንግጣለች
“መቼ ነው አባዬ መቃብር የምንሄደው …!”
“እልልልልልልልልልልልልልልልልልልለልልልልልልልልለልልልልለ!” ........................,,,,........................ ✍🏽የጠቆረ ልብ @Wegoch @Wegoch @Wegoch
ስሟ ጆይሲ ቪንስንት ይባላል 38 አመቷ ነበር ነዋሪነቷ የነበረው እንግሊዝ ወስጥ
ለንደን ነው:: ትኖር የነበረው አፖርትመንት ተከራይታ ሲሆን የቤቷ የኪራይ ውል በማለቁና ያለባትን የኪራይ ውዝፍ ልትከፍል ባለመቻሏ አከራይዎቿ ለፖሊስ አሳውቀው ፖሊስ ቤቷ ሲገባ ያገኘው ሶፋ ላይ ቁጭ ብላ ሲሆን እሷ የሞተችው ግን በ2003 ነበር:: ከሞተች ከሶስት አመት በጏላ በቤቷ ፈሪጅ ውስጥም የአገልግሉት ዘመናቸው በ2003 ያለቀ ምግብና መጠጦች አግኝቷል ሌላው ፖሊስ ያስደነቀው ነገር ቴሌብዥኑ በርቶ ፕሮግራም እያስተላለፍ ነበር:: ሀገሬን የምወዳት ለዚህ ነው:: ከፋም ለማም ተጣላክም አልተጣላክም ወዴት ነህ የሚል ነገረኛም እንኳን ቢሆን ደሞ ዛሬ ምን ነው ድምፁ ጠፋ የሚል ጎረቤት ሁሌም ቢሆን ይኖርሀል:: መኖርህ ነው የኖሮ መለኪያ የሰለጠነው አለም ግላዊነት ከመጣባቱ የተነሳ ሁሉም በየራሱ ይኳትናል እንጂ አጠገቡ ስላለው ጎረቤቱ አይጨነቅም:: አብረህው ስለኖርክ ብቻ መጠጋጋትን
እና ማህበራዊ ቅርርብን አይፈቅድም....
እናም የሀገሬ እናቶች ተሰብስበው ስናያቸው ቡና ከመጠጣት በዘለለ የአብሮነት ድራቸውን እየፈተሉ እንደሆነ መገንዘብ ተገቢ ነው::

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Danny magna
ከወንጌላዊነት ወደ "ዶክተርነት" ያደረኩት ሽግግር!
(አሌክስ አብርሃም)
ሒሳብ አስተማሪያችን ‹‹ስታድጉ ምን መሆን ትፈልጋላችሁ ›› ብሎ አንድ ክፍል
ማቲ ሲጠይቅ ከእኔ በስተቀር ሁሉም ‹‹ዶክተር›› እና ‹‹ፓይለት›› አሉ ! እኔ ግን
‹‹ወንጌላዊ›› አልኩ !አስተማሪያችንን ጨምሮ ሁሉም ተገረሙ ! እየቀለድኩ
አይደለም …ይሄ አራተኛ ክፍል አብረውኝ የተማሩ ልጆች ሁሉ የሚመሰክሩት ሃቅ
ነው ! በወቅቱ ወንጌላዊነት ይዘፈንበትም ይለቀስበትም አላውቅም ግን አንድ
ጴንጤ ጓደኛ ነበረኝ ...አባቱ ወንጌላዊ የነበሩ ! በመካነ ኢየሱስ ውስጥ የሚገኝ
የሆነ ‹ልማትና ተራድኦ› ድርጅት ይመስለኛል ሃላፊ ነበሩ ! ይሄ ሰውየ …
1ኛ. ነጭ ቲዮታ ላንድ ክሩዘር የሚነዱ
2ኛ. ሽክ ያሉ ሰውየ !
3ኛ. በትርፍ ጊዚያቸው በሚያምር ቪላቸው በረንዳ ላይ ጊታር እየተጫዎቱ
በሚያምር ድምፅ የሚዘምሩ …ሚስታቸው (የጓደኛየ እናት ፊት ለፊታቸው ቁጭ
ብለው አብረዋቸው ይዘምራሉ) መጀመሪያ አካባቢ ሳያቸው ከብዙሃኑ ኢትዮጵያዊ
ባለትዳር ስለተለዩብኝ …የሆነ የህንድ ፊልም ነገር ነበር የመሰለኝ ! ይሄ ሰውየ
ተፅዕኖ አሳድረውብኝ ይሆናል! ፓስተር ፣ ነብይ ወላ ዘማሪ መሆን አልፈልግም
ነበር …..ወንጌላዊ! ወንጌላዊ ሁሉ መኪና የሚነዳ፣ የሚዘንጥና ሚስቱ ጋር ቁጭ
ብሎ በጊታር የሚዘምር ይመስለኝ ነበር !
በኋላ እዚህ ጓደኛየ ጋር ቸርች ሔድኩ …የዛን ቀን ከደቡብ የመጡ እና ለ33
ዓመት ወንጌል ሲሰብኩ የኖሩ ወንጌላዊ ‹‹የእግዚአብሔር ጥበቃ ›› በሚል ርዕስ
እያስተማሩ ነበር ! እዚህ ግባ የማይባል ልብስ የለበሱ ጎስቋላ ፊት ያላቸው
ሽማግሌ ነበሩ! ሰውየው በየገጠሩ የተከሉት ቸርች ብዛት ዛሬ ላይ አንዳንድ
አገልጋዮች ከዶ/ር ዓብይ ኋላ እየተከተሉ ከተከሉት ችግኝ በቁጥር ይበልጣል !
ደስ በሚል የደቡብ አክሰንት ነው የሚናገሩት እንዲህ አሉ ‹‹…ጓደኛየና እኔ
በልጅነታችን እኔም እሱም ሌቦች ፣መልከመልካም እህቶችን የምናስቸግር ፣
ዱርየዎች ነበርን …
የዛሬ 35 ዓመት አካባቢ እኔ ጌታን ስቀበል እሱ ያው በሌብነት በአመፅ ቀጠለ …
የጌታ ጥበቃና ምህረት በዛልኝ …በደርግ ጊዜ ወንጌል ሰበክ ተብየ ስታሰር ይሄ
ጓደኛየም መጋዘን ሰብሮ በቆሎ ሲሰርቅ ተይዞ ታሰረ …እንደገና እስር ቤት
ተገናኘን …ለዚህ ወዳጀ ቀን ከሌት በእንባ ነበር የምፀልየው ! ይገርማችኋል እሱ
በነፃ ሲለቀቅ እኔ ክፉኛ ለወራት ተገረፍኩ …እስካሁን ይሄ ግራ አይኔ በግርፋቱ
ተጎድቶ እስካሁን በደንብ አያይም ….ቀኝ እግሬም ያዝ ያደርገኛል …ግራፋቱን
ያባሰው ለገራፊየ ‹‹ኢየሱስ ይወድሃል… ››በማለቴ ነበር ! ጌታ ይባረክ! (ፈገግ
ብለው) …
ወገኖቸ ጥበቃው በዝቶልኝ ከዛ ግርፋት ተረፍኩ ! ቆይቶ የእጮኛየ ቤተሰቦች
አንተ ገንዘብ የለህም …አሁን ደግሞ ሰርተህ እንኳን ልጃችንን እንዳታኖር ጤናም
የለህም ብለው ለሌላ ሰው ዳሯት! እስካሁን መልካም እህቴ ናት …ባለቤቷም
መልካም ሰው ነው ! ጌታ ይባረክ …እኔ ከዛ በኋላ 15 ዓመታት ቆይቸ ነው
ያገባሁት ! ይሄ ጓደኛየ አንዲት ከውጭ አገር የመጣች ሴት አግብቶ አራት ልጆች
ወለደ …እኔ በጌታ ብዙ ሽዎችን ወለድኩ የስጋ ልጅ የለኝም ጌታ ይባረክ (ፈገግ
አሉ) ይሄ ጓደኛየ ዛሬ አዲስ አበባ ትልቅ ቤት ሰርቶ ትልቅ ድርጅት ከፍቶ አንዳንዴ
ራቅ ወዳለ ቦታ ለወንጌል ስሄድ ሁሉ መኪና ከነሹፌሩ ያውሰኛል … ! ዛሬም
አጥብቄ የማለቅሰው ለእኔ የበዛው የጌታ ጥበቃና ምህረት ለሱም እንዲበዛለት
ነው !
እኔም የእግዚአብሔርን ቤት መስሪያ በየመንደሩና በየአብያተ ክርስቲያናቱ
እየዞርኩ እለምናለሁ …ለወንጌል ገጠር ስዞር የሞላ ወንዝ ወስዶኝ ሌላ መንደር
ጥሎኛል ….እዛ ያሉ አርሶ አደሮች ሙቷል ብለው ሲያወጡኝ የሞትኩ እኔ
የህይዎት ወንጌል ሰበኳቸው ! ከበቅሎ ወድቄ ክንዴ ተሰብሮ ወጌሻ ጋር ወሰዱኝ
ያን ወጌሻ ስለጌታ ነገርኩት ዛሬ እዛ አካባቢ የተተከለች ቸርች ፓስተር ሁኗል !
ሚስቴ ሰው ቤት የቤት ስራ ትሰራ ነበር …ዛሬ ወደጌታ ሂዳለች (ሙታለች) …ጌታ
ስሙ ይባረክ! ይሄን የምነግራችሁ ወዳጀን ለማማት አልያም ለጌታ እንዲህ
አደረኩ ለማለት አይደለም …ማንም ለጌታ ምንም አያደርግም ! እግዚአብሔር
እኔን የጠበቀኝ በዚህ ሁሉ መከራ ተማርሬ ከቤቱ እንዳርቅ ፀጋን በመስጠት ነው !
የእግዚአብሔር ጥበቃ ከመከራ እና ከስቃይ ማዳን ብቻ አይደለም… በመከራ
ውስጥ ፀንተን እንድንኖር ፀጋውን በማብዛትም ጭምር እንጅ ! ተደሰትንም
ከፋንም ይሄ ዓለም እንደሆነ ያልፋል !
ከቸርች ስንወጣ ጓደኛየን ‹‹የአባትህ ኢየሱስና የዚህ ሰውየ ኢየሱስ አንድ አይነት
ነው ወይ? ››ብየ ጠየኩ …የእውነት ወንጌላዊነት መኪና መንዳት ብቻ ሳይሆን
እንደአህያ እየተወገረ ወደእስር የመነዳት እጣም እንዳለበት ገባኝ …ወንጌላዊነት
ወደቸርች ሰዎችን መውሰድ ብቻ ሳይሆን ራስንም በጎርፍ እስከማስወሰድ
የሚደርስ ዋጋ እንዳለበት ገባኝ …ወንጌላዊነት በተመቸው ስጋ ውስጥ የምትኖር
ጎስቋላ ነፍስ ላላቸው ሰዎች እንደማትሆን ገባኝ ! ከምንም በላይ እንደነዛ አይነት
ሰዎች እስከሞት በከፈሉት ዋጋ ላይ አሁን የምናያቸው መሬት አይንካን የሚሉ
የዩቲዩብ እና የስክሪን ላይ አለሌዎች መፈጠራቸው ያሳዝናል !
የሆነ ሁኖ ከዛች ቀን በኋላ አስተማሪዎቻችን ምን መሆን ትፈልጋላችሁ ሲሉ
‹‹ዶክተር›› የሚል ድምፅ የኔ ሆነ! መኪናውና ጊታሩ አብራ የምትዘምር ሚስትና
ሽክ ያለ አለባበስ ...ዝና ከሆነ ፍላጎቴ በጌታ ስም ምን አስታከከኝ …ዶክተርም
፣ግንበኛም ሹፌርም ዛፍ ቆራጭም ዘፋኝም አርቲስትም ሁኘ ማግኘት
የምችላቸው ነገሮች ናቸው ! ከአስመሳይና ማይክ ይዞ መድረክ ላይ
መንጠላጠል ከሚወድ ‹‹ ወንጌል ሰባኪ›› ጥሩ የቤት ሰራተኛ በፀባይዋ ወንጌል
ትሰብካለች ! ያችኛዋን መንገድ ለተጠሩት ተውኳት !

@wegoch
@wegoch
@paappii
ኢሬቻ - «ሆ...ያ...መሬዎ...መሬዎ»
___________________
ዘመድ አዝማዱ ተጠራርቶ የባህል ልብስ በመልበስ እርጥብ ሣርና አደይ አበባ በመያዝ «ፈጣሪን እናምናለን፤ በምድር ላይ በፈጠራቸው ነገሮች በሙሉ እንደነቃለን፤ እናደንቃለን...... ሆ...ያ... መሬዎ .... መሬዎ» የሚሉበት ወቅት ....ኢሬቻ ። ክረምቱ በሠላም ተገባዶ፣ ፀደይ አብቦ፣ ተራራውና ሜዳው አሸብርቆ፣ እንስሳቱ እርጥብ ሳር ግጠው ሲፈነጥዙ፣ በአሮጌው ዘመን የተዘራው በአዲሱ ዓመት ሲያፈራ የሚስተዋልበት ጊዜ .... ኢሬቻ።
ወዳጅ ዘመድ በሰላም በመገናኘታቸው ፈጣሪን እያመሰገኑ ወደ ወንዝ ወርደው ሙላቱ የቀነሰውን ወንዝ በእርጥብ ሳርና በአደይ አበባ እየነከሩ በክረምት ዶፍና ጎርፍ ዝናብ የደፈረሰው ወንዝ ውሃው መጥራቱን፣ የፀደይ መገለጫ መሆኑን ያሳያሉ። ቀጣዩ ወቅትም የሠላም፣ የጤና እና ሁሉ ነገር በፌሽታ የተሞላ ይሆን ዘንድ ፈጣሪን እየተማፀኑ ኢሬቻን ያከብራሉ።
የኢሬቻ በዓል ኢሬቻ ቱሉ እና ኢሬቻ መልካ በሚል ሁለት ዓይነት አከባበር አለው። ኢሬቻ ቱሉ የሚከናወነው የክረምቱ ዝናብ በሚጠበቅበትና ሰማዩ እየጠቆረ፣ ዝናብ እያረገዘ መሬት ከበጋው ፀሃይ እፎይ በምትልበትና ልምላሜ ለመላበስ በጉጉት በምትጠብቅበት ወቅት ነው። ኢሬቻ የክረምቱ ዝናብ በሚጠበቅበት ወቅት ካልጣለ በድርቅ ሳቢያ የተለያዩ ችግሮች እንዳይከሰቱ በየካቲት ወር አጋማሽ ከፍ ባለ ተራራ ላይ በመውጣት ፈጣሪ ክረምቱን ሰናይ እንዲያደርገውና ዝናብ እንዲያዘንብ የሚለመንበት ነው።
ኢሬቻ መልካ ደግሞ ክረምቱ ተጠናቆ ፀደይ ሲገባ መስከረም ወር አጋማሽ አካባቢ የሚከበር ሲሆን፣ በክረምት የውሃ ሙላት ተራርቆ የነበረው ዘመድ አዝማድ ተገናኝቶ ምስጋና እና ደስታ የሚገለፅበት ወቅት ነው። በዚህ ወቅትም አደይ አበቦች ፍክት ብለው ተማሪዎችም ወደ ትምህርት ቤት የሚተሙበት ብሎም የክረምቱ ጭጋግ ተገፎ የደስ ደስ ያለው ነፋሻማ አየር ሰዎች በአፍንጫቸው የሚመገቡበት ወቅት ነው። እሸትም ተቀጥፎ የሚቀመስበት የቀጣይ ኢሬቻ መልካ እና ኢሬቻ ቱሉ በናፍቆት የሚጠበቅበት ወቅት ነው። ኢሬቻም ሲከበር በርካታ ትሩፋቶችን ይዞ ብቅ ይላል። ኢሬቻ ጥቅሙም ዘርፈ ብዙ ነው። በተለይ ደግሞ ከጥንት ጀምሮ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ በስፋት ሲከበር የኖረው የኢሬቻ በዓለ ዛሬም ይከበራል። በዓሉም የያዛቸው ትርፋቶች እነሆ!
እርቅ የሚሰበክበት ማንኛውም የኢሬቻን በዓል ለማክበር ሲንቀሳቀስ መጀመሪያ ማድረግ ያለበት ነገር ቢኖር የበዓሉን ህግጋቶች ጠንቅቆ ማወቅ ነው። ከእነዚህም ውስጥ እርቅ ከሁሉም የቀደመ ሥፍራ ይሰጠዋል። በኢሬቻ በዓል «ሳል ይዞ ስርቆት ቂም ይዞ ፀሎት» የሚባለው ባህላዊ ትውፊት ወይንም ኢትዮጵ ያዊው አባባል በትክክል ይተገበራል። የኢሬቻ በዓል ከመጀመሩም በፊት እርቅ ይካሄዳል።
በሆራ አርሰዲ በተካሄደው የኢሬቻ በዓልም አባገዳው ድምፃቸውን ሞርደው እንዲህ አሉ። « አጠገባችሁ ካለው ሰው ጋር እጅ ለእጅ ተያያዙ፤ ሠላምታም ተለዋወጡ። አንዳችሁ ሌላችሁን አስቀይማችሁ ሊሆን ይችላል። ይቅር ተባባሉ። ይህ ቦታ እርቅ፣ ሰላምና አንድነት የሚሰበክበት ነው።»
የበዓሉ ታዳሚዎች በሙሉ እጅ ለእጅም ተያይዘው ይቅር ተባባሉ። እነሆ! ኢሬቻ በዚህ መልኩ እርቅን ይሰብካል። የበዓሉ አንዱ እና ትልቁም ዓላማ ልማት ለማምጣት ሰላም ይቀድማል የሚለው ነው። የኢሬቻ በዓል በአባገዳዎች እየተመራ በእርጥብ ሳርና አደይ አበባ ውሃው ውስጥ እየተነከረ ወደ ሰዎች ውሃው ፍንጥር... ፍንጥር.... ሳይደረግ የሰዎች ልብ በቅድሚያ በይቅርታ ሙላት መሸነፍ አለበት። ከፊትም ከኋላም ስጋት የለም። ይቅርታ ተሰብኳልና። በዚህ ስፍራ ስርቆት ማሰብም ፍፁም ከበዓሉ ጋር የማይሄድና የተወገዘ ነው። በዚህ አካባቢ ስለ በዓሉ ደስታ እንጂ ሰዎችን ማሳዘን እንደ ኢሬቻ ሕግ ፈፅሞ የተከለከለ ነው። በኢሬቻ እለት «የወደቀን አንሳ የሞተን ቅበር» የሚለው አባባል የወደቀውን እንስተህ ለባለቤቱ መልስ በሚለው የተተካ ይመስላል።
በርካቶችም የወደቀ ንብረት እያነሱ ይመልሳሉ። በቃ! እለቱ የማዘን ሳይሆን የደስታ፤ የኩርፊያ ሳይሆን የእርቅ፤ የመራራቅ ሳይሆን ሰው በአካል ብቻም ሳይሆን በመንፈስ ልብ ለልብ የሚናበብበት ልዩ ቀን ስለመሆኑ ከኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።
የባሕላዊ እሴቶች ማስተዋወቂያና የቱሪስት መሳቢያ
የሚዘወተሩ አልባሳት ብዙም በኢሬቻ ቀን አይመከሩም። ኢሬቻ ከገዳ ሥርዓት ጋር የጠበቀ ግንኙነት ያለው ከመሆኑም በተጨማሪ አለባበሱም በገዳ ሥርዓት የተቃኘ ነው። ወጣቶች፣ አረጋውያንና ሌሎችም በዓሉን የሚታደሙ አካላት አለባበሳቸው ባህላዊ ነው።
ከበዓሉ ታዳሚዎች መካከል አቶ ፍሰሃ ገብረ ሚካኤል ኢሬቻ፤ ባህላዊ እሴቶችን ለማስተዋወቅ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ይናገራል። በተለይ አባገዳዎች የሚጫሙት ባህላዊ ጫማ፣ የሚለብሱት ቡልኮና ቦላሌ እንዲሁም በገዳ ሥርዓት ከእግራቸው እስከ እራሳቸው ድረስ ባህላዊ እሴት ያረፈባቸው ሌሎች ጌጣጌጦች ቀልብ የሚስቡ ናቸው። ከዚህ ባሻገር ግን የቀድሞው ባህል እንደተጠበቀ ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ፣ ኦሮሞ የራሱን ባህል እንዲያከብርና እንዲያዳብር ብሎም እነዚህ ባህላዊ እሴቶች አብይ የኩራት ምንጭ አድርጎ እንዲጠብቃቸው ለማስተዋወቅ ነው ኢሬቻ የሚከበረው።
ከዚህም በተጨማሪ በዓሉ የቱሪስት መዳረሻ እየሆነም ነው። ከጀርመን የመጣውና በኢትዮጵያ ባሕላዊ እሴቶች ቀልቡ የተሳበው ሚስተር ቲም ፓስካል ኢሬቻ ውበት ያለው በዓል እንደሆነ ይገልጻል። በርካታ ሰዎች እንዲህ በአንድ ላይ ተሰብስበው የሚያከብሩትና በአንድነት እየጨፈሩ የሚደሰቱባቸው በዓላት በኢትዮጵያ በርካታ ናቸው። የኢትዮጵውያን ባህልዊ እሴቶች የሚያደንቀው ጀርመናዊው ሚስተር ቲም የመስቀል ደመራ በዓልን እንደታደመና እንደተደመመም ያስታውሳል። «ይኸው የመስቀል ደመራ በዓል የፈጠረብኝን አግራሞት አጣጥሜ ሳልጨርስ ነው የኢሬቻን በዓል የታደምኩት። ኢትዮጵያውያን ያልተነካና ያልተበረዘ ባህል አላቸው። በቅኝ ግዛትም አልተያዙም። ለዚህም ሳይሆን አይቀርም ቱባ ባህላቸው እንዲህ ከነድንግልናው የቆየው» ይላል። ኢሬቻ ኢትዮጵያውያን በአግባቡ ከተንከባከቡት የዓለም ቅርስ ሆኖ የቢሊዮኖችን ቀልብ የሚይዝ ህዝባዊ ትዕይንት እንደሆነ ያበስራል። ከዚህም ባሻገር በርካታ ቱሪስቶችን በመሳብ አገሪቱን የበለጠ ለማስተዋወቅ ትልቅ ሚና እንዳለው ሚስተር ቲም ፓስካል ይጠቁማል።

💚💛❤️
baga Ayyaanna kabajamaa ummata Oromootti issin gahee.
🔴⚫️⚪️
#በረከት_ግርማ

@wegoch
@wegoch
~ራሴው ማበዴ ነው~
(ሜሪ ፈለቀ)

"ተሳፋሪዎቻችን ይህ የበረራ ቁጥር 206 ነው… … ” ጭንቅላቷ እየሸወዳት እንደሆነ የማውቀው እንዲህ ማለት ስትጀምር ነው። በግልቡ እብደቷ እየጀመራት ነው ማለት ነው። እናቴ ናት!!

ይሄን ሀረግ ማለት ከጀመረች ትርጉሙ የዛሬ 20 ዓመት ወደ ኋላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሆስተስ የነበረችበት ዘመን ላይ ናት… … ማርጀቷን አታውቅም፣ እኔንም አታውቀኝም ፣ ባሏ እሷን ትቶ ጓደኛዋን እንዳገባ አታውቅም ፣ ንብረቷን እንደተቀማች አታውቅም ፣ ጡቶቿ እንደተቆረጡ አታስታውስም ………… አንዳንዴ ራሷንም አታውቅም ~ ሰው ካላያት ራሷን ትጎዳለች። እብደቷ ሲነሳባት መከራዬ ናት። ምሬቴ ናት። ስቃዬ ናት። …… ጥለሻት ጥፊ ጥፊ ይለኛል። ጭንቅላቴን በቅውሰቷ ትዋጀዋለች። ብገላገላት የምታስመኘኝ መንቻካ አሮጊት ትሆናለች። መድሃኒቷን አትውጥልኝም፣ እንድነካት አትፈቅድልኝም ፣ አምናኝ እንቅልፏን አትተኛም…… ከየት የምታመጣው እንደሆነ የማይገባኝ ጉልበት አላት…… ታጠፋበታለች። እንደእኔ የምትጠላውና የምትፈራው አይኖራትም።

"የማላውቅሽ መስሎሽ? ቅናታም መርዘኛ! …… መድሃኒቱን በምግብ ለውሰሽ ልታበይኝ? አንድዬን ልትወስጂብኝ? እኔ አይናለም በህይወት ሳለሁ ቤቴ ሊፈርስ?” ትለኛለች ያገኘችውን እቃ እየወረወረችብኝ። አንድዬ የምትለው አባቴን ነው። የድሮ ባሏን።

"ማነሽ ደግሞ አንቺ? ወደ ቤቴ ውሰዱኝ… …… ኡኡኡኡኡ… … መድሃኒት ሊያበሉኝ ነው።……”

ዶክተሯ መጥቶ መርፌዋን እስኪወጋት በሷ እብደት እኔ አብዳለሁ። ስትረጋጋልኝ እብዷ እናቴን ከጠባቂ ጋር እቤት አስቀምጬ እወጣለሁ። …… ያበደች እናት እንደሌላት፣ አንዲት የኑሮ ሰበዝ እንዳልጎደለባት ፣ እንደደላት ሴት ሁኜ…… አዘውትሬ እንደምለብሰው ሙሉ ልብሴን አጊጬ ወደ ስራዬ እሄዳለሁ።

“ ኪዳነ ምህረት ምን በደልኩሽ? ምነው ጌታዬ ስቃዬን ቆለልክብኝ? ምናለ ብትገላግለኝ?” ስትል ደግሞ ትርጉሙ ወደ አሁን ተመልሳለች ማለት ነው። ያሳለፈችውን ስቃይ እያስታወሰች መታመም ጀምራለች ማለት ነው። እብደቷ ሲተዋት ታስለቅሰኛለች። ሆዴ ኩርምትምት ይልላታል። እንዳሰቃየችኝ ታውቀዋለች። ላበደችባቸው ቀናት እንግልቴ ስትከፍለኝ ጡት የለሽ ደረቷ ላይ ለጥፋኝ ታባብለኛለች። ምን መስማት እንደምትፈልግ አውቃለሁ።

"እማ በህይወት እስካለሽ አልተውሽም። ምንም ብታደርጊ እችልሻለሁ።” እላታለሁ። አትመልስልኝም። ብቻ ጨምቃ አቅፋኝ ትንሰቀሰቃለች። የአዕምሮ ህሙማን ሆስፒታል መግባት ሞቷ ነው። ትለምነኛለች። ሁለቴ ገብታ ታውቃለች። ይብስባታል እንጂ አይሻላትም። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሰውነቷም እየደከመ ህመሟም እያዛላት ነው። ትናንትና የሚሚን የሰርግ መጥሪያ ወረቀት ካየች ጀምሮ የበረራ ቁጥሯን መቁጠር ጀምራለች።

ሚሚ አባቴ ከሌላ ሚስቱ የወለዳት እህቴ ናት። ሰርጉን እኔም እናቴም እንደማንሄድ ያውቃሉ። ለምን እንደማይተውን አላውቅም። ባገኙት ሰበብና አጋጣሚ እኔና እናቴ ሰላም እንዳይሰማን ይታትራሉ። እማዬን ለማረጋጋት እማይኮነውን ሁሉ እየሆንኩ እንፈራገጣለሁ። በሚሚ ሰርግ ጉዳይ ግን ከእማዬ ይልቅ እንዳላብድ መጠበቅ ያለብኝ እኔ ነበርኩ። ምክንያቱም ሚሚ የምታገባው የልጅነት ፍቅረኛዬን ነው። የሰርግ ወረቀቱን ለእኔ አምጥተው የሰጡበት ምክንያትም እንደእናቴ እንዳብድላቸው ነው። ኡፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍ……

እኔ በሙያዬ ጠበቃ ነኝ። ……… በአንድ ቅሌታም ከፍተኛ ባለስልጣን ኬዝ ሰበብ ስሜ በሀገሪቷ የናኘ ጠበቃ…… አስታወሳችሁትኣ? አያቱ ከሚያክሉ አሮጊቶች ጋር የሚወሰልተው ሰውዬ…… አዎን ለደፈራቸው የ70 ዓመት ምስኪን አሮጊት የቆምኩት እና ያስፈረድኩበት እኔ ነበርኩ። ያ መርገምት ካርቱሚስት በአንደኛው ሳምንታዊ ጋዜጣ ላይ ጥርስ የሌላት ድዳም እና ምላሷ ከፒያሳ እስከመገናኛ የሚደርስ አሮጊት አድርጎ የሳለኝ… … አዎን እኔ ነኝ። ……… አሁን ማን እንደሆንኩ አወቃችሁኣ?

“ቢሮሽ ሰው እየጠበቀሽ ነው።” አለችኝ ወይኗ ገና ከመግባቴ።

"ደህና አደርሽ ወይኗ።” ብዬ እየተጣደፍኩ ስገባ

"አባትሽ ነው። አባቷ ነኝ ነው ያለው። አባት እንዳለሽ አልጠረጠርኩም ነበር። ……” አለኝ ፍትህ።

"አባትሽ?” ተንደርድሬ ቢሮዬ ገባሁ። ደንግጦ ተነሳ። በዓይኔ ካየሁት እንኳን ሰባት ዓመት ሆኖኛል። ምናባቱ ሊሰራ ነው አሁን የሚፈልገኝ? ጭራሽ ቢሮዬ ድረስ?

★ ★ አልጨረስንም ★ ★

@wegoch
@wegoch
@paappii
ዜማና ሰውነት
ግዕዝ (ተቀዳሚ)
ሰዎች "እንዴት ነው ሰብራህ የሄደችው ?" ብለው ሲጠይቁኝ " ልቤ
እስከሚያነክስ" ብዬ ከመለስኩላቸው ረጂም ጊዜ ቢያልፍም ድንገት ቀና ስል
የጠራ የመስከረም ሰማይ አይቼ ናፈቀችኝ ። ለእንቁጣጣሽ በፈካ ቢጫ አደይ ያቆጠቆጠ አረንጓዴ መስክ ላይ ይሄን ብራ ሰማያዊ ሰማይ ደርበን የተራከብን ነን ። በሚያሳሳ የመስከረም ቀን መኻል አፍላነት ያቀጣጠለው፤ ነፋስ ስሞ ያበረደው ገላችን ላይ ጣል ያደረግነው ፤ የተጋፈፍነው ሰማይን ነው ። ሽቅብ ያየሁበትን አይኔን ቶሎ ሰበርኩ እንጂ ባተኩር ከጭኗ የተላቀቀ የጠይምነቷን ባዘቶ ጉም ሰርቶ አየው ነበር ። ሁሉ እንደዛሬ ስላይደለ ልብ ብዬ ባየው ህመሙ ነፍሴ ላይ ያረብባል እንጂ ። በልጅነት ቀናቷ ድንግል ልቧን እና ነፍሷን የገረሰስኩ ተቀዳሚ ግዕዟ ነኝ። ማለት የመጀመሪያውን መሳም የትኛውም መሳም እንደማይሽረው ፤ የመጀመሪያው ዜማ ድንቅነት በሌሎች እንደማይሸፈነው ፤ በልቧ ቅኝት ላይ ተደላድዬ የተፃፍኩ ማንም የማይሰረዘኝ ዜማዋ ነኝ ። ለመጣ ለሄደው ሳትሰለች የምትነግረኝ ገድሏ ከአንደበቷ የምወጣ ብቸኛ ተረኳ መሆን ትምክተኛ አድርጎኝ ፤ ልታቅፈኝ የዘረጋቻቸው እጆቿ አየር ላይ
እንደተንከረፈፉ ትቻት ስነጉድ ፤ በማንም ያልተሳሙ ለጋ ከንፈሮቿ ሊስሙኝ ሲተጉ
ስገፋ ተስፋ ቆረጠችና ያልቃል ብዬ ያልገመትኩትን ለኔ ያላትን ፍቅር ለሌላ
አጋርታ አገኘኹዋት ። በኔ ግዕዟ ላይ እዝል ደርባ የምታዜም ሆነች ። ፀፀት ልቤን ሲበላኝ እስከዛሬ ትምክህት የሸበበው አንደበቴን ከፍቼ እንደምወዳት
ነገርኳት ። ሁለተኛ ፍቅሯ ከኔ እንደማይበልጥባት አውቃ ይሁን የዘመናት ህልሟ ስለሆንኩ ብቻ ግን መውደዴን ስነግራት ደስ አላት አቅፋኝ አለቀሰች ። "ሁሌም አለሁልህ "አለችኝ ።
ፍቅሬ በእኔ በግዕዟ በሁለተኛዋ እዝሏ ዜማ የምትንገላታ አሳዛኝ አራራይ ሆነች ። በዚህ ዜማ የታመምን ሶስት ሰዎች ነበርን ። ከእርሱ ጋር አሸብሽባ እንደምትመጣ እያወኩ በቅዳሴዋ ልዘምም ደፋ ቀና ስል ከጠይም ገላዋ ላይ የሚነሳ የእዝሏ ጠረን ፣ ከሴትነቷ የሚተን የእርሱ ጢስ ዜማዬን እና አቋቋሜን ቢያዛባውም ። በ"የኔ ነበረች ፤ ሁሌም የኔ ነች። " እምቢተኝነት በቅኝት መኻል ሽብርክ የሚል ልቤን ታቅፌ ወረቧ ላይ ከርሚያለሁ ። አሁን ይሄን እኔ እና እርሷ የተጋፈፍነውን የመስከረም ብራ ሰማይ ቀና ብዬ ባይ በተመሳሳይ ቀን እኔ ጋር ከመምጣቷ በፊት ከእዝሏ ጋር የነበራትን ወረብ በበራሪ ኮከብ እንደ ስዕል አስቀምጦ ያሳየኛል ። ግን አይኔን አቅንቼ ሰማዩን ሳይ ትዝ ባለችኝ ቅፅበት አንገቴን መልሼ እጄን ደረቴ ላይ አጣምሬ የልቤ ድሪቶ ውስጥ ቀበርኳት ። ቢሆንም እኔ ምንም የልቤ ስርቻ ውስጥ እንደመነኛ ልጥላት ብሞክር
በእርሷ ልብ ውስጥ ግን ያለኝን ቦታ አውቃለሁ ፤ ብዙ ሁለተኞች ያልሻሩኝ የሁሉ ነገር አሃዱዋ ተቀዳሚ ግዕዟ ነኝ ።
እዝል (ተደራቢ) ትዝ የምትለኝ በእኩለ ሌሊት ነቅቼ ሲጋራዬን ለኩሼ ያጨስኩ ቀን ነው ። ከሁሉ ከሁሉ የምትወደው ከንፈሬን ነው ። ከንፈሬ ላይ ባለችው ጥቁር ነቁጥ ሁሉ ሳትቀር ትቀና ነበር "ማርያም ለምን ሌላ ቦታ አልሳመችህም?" ብላ ታኮርፈኛለች
። ሌሊት እንዳልቀሰቅሳት ተጠንቅቄ ተነስቼ ወንበር ስቤ ተቀምጬ ሲጋራዬን
ስለኩስ ከእንቅልፏ ትነቃለች ። በቅጡ ያልተከፈቱ አይኖቿን ገርበብ አድርጋ "
ጭሱን ከአፍህ ልውሰድ?" ትለኛለች ። ቀጥላ ከመኝታዋ ተነስታ ጭኔ መሃል
ትንበረከክ እና አጭሼ የምተነፍሰውን ጭስ ከአፌ አንደ ወፍ ትቀበላለች ። የዛኔ
ከንፈሮቻችን ተጋጥመው ቅጡ በማይገባን ወረብ ቆመን መወዛወዝ
እንጀምራለን። ሁሉም እንደሚያውቀው ከኔ ቀድሞ በገጠማት ዜማ ያልተደሰተች ዘማሪ ነች እኔ አፍላነቷ ጎትቶ ከቀሚሷ ስር ከገላዋ ላይ ያዋለኝ እዝሏ ተደራቢ ዜማዋ ነኝ ። አለ አይደል በግዕዝ የጋለ እሳቷን አቀዝቅዤ አረጋጋታለሁ ። ቀልበ ቢስ ቀልቃላ እና ሃይለኛ ቅላፄዋን ዳብሼ ገርቼ እመልስላታለሁ ። የመጀመሪያዋ ነውና ለግዕዟ ያላትን ስሜት በአንዴ አውጥተሽ ጣይ ባልላትም ። በኔ እርጋታ
አገግማለች ። ፍቅር ከጀመርን ከጥቂት ጊዜ በኹዋላ በወረባችን መኻል የቀደመ ትትርናዋን ችላ ብላ ሁሉ ነገሯ ሲቀየርብኝ ግራ ገባኝ ። ቆይቼ አስቸጋሪ ግዕዟን አስጣልኳት ያልኳት እርሷ የቀደመ ቅላፄዋን ሳትተው በእኔ ላይ ደርባ ማዜም መጀመሯን አወኩኝ ። ይህን ሳውቅ እውነቱን በልቤ ደብቄ ሸፋች ልቧን ላረጋጋ ርቃኗን አስተኝቼ ከላይ እስከ ታች በከንፈሬ እየዳበስኩ በእንባዬ አርጥቤ አጠብኳት ። እንዲህ ሳደርግ በሃይለኛ እና እምቢተኛ የሚማረክ እርሷነቷ ለኔ መለማመጥ
ትኩረት መስጠት ተሳነው ። እናም ያኔ የጀመርነው ለስላሳ ቅኝት ዜማችን
ተቆራረጠ ። አሁን ዛሬ ላይ ስለ እርሷ ሳስብ ሃዘን በልቤ ያልፋል ። በህይወቷ ከተጣባት ጠንካራ ግዕዝ ላሳርፋት የጣርኩ ለስላሳ እዝሏ ብሆንም እዚያና እዚህ የሚረግጥ አሳዛኝ አራራይ ነፍሷ ግን ያን እንድታደርግ አልፈቀደም ። ከብዙ ጊዜ በኹዋላም ቢሆን እኔ ላይ ካደረገችው ክህደት ይልቅ ለቅብዝብዝ እርሷነቷ እና በዚህ ምክንያት ለሚበላሹ ዜማዎቿ የማዝን ተደራቢ ዜማዋ እዝሏ ነኝ ። አራራይ ( አሳዛኝ) ሰዎች በሰራኹዋቸው ነገሮች በሙሉ ይበሳጫሉ ። ይበሳጩና ያዝናሉ ።
የበደልኳቸው እንኳን ትንሽ ተበሳጭተውብኝ ቀጥሎ የሚያደርጉት ነገር ቢኖር ለእኔ ማዘን ነው ። እኔነቴ ሰው ጨክኖ ጆሮ እንደ ማይነፍገው አሳዛኝ ዜማ ነው ፤ እንደ አራራይ ።
ስለ ዜማ ሳስብ ስለ ሁለቱ የቀድሞ ፍቅረኞቼ አስባለሁ ። የመጀመሪያው ግዕዜ ነው ...... ልጅነቴን በጥበቃ የጨረሸ ፤ የኮራብኝ ፤ የተጀነነብኝ ፣ ደጅ ያስጠናኝ ፣ ያስለመነኝ ፣ እልህ ያጋባኝ ፣ የፈተነኝ ። ሁለተኛው ደግሞ እዝሌ ነው ......የደረብኩት ፣ ያረጋጋኝ ፣ያበረደኝ ፣የወደደኝ ። ስለምነው የከረምኩት ግን የገፋኝ ። በኋላም ከሚያሳርፈኝ ጋር እፎይ ማለቴን ሲያይ ስመኘው የኖርኩት ፍቅር ካልሰጠሁሽ ብሎ ፊቴ ቆመ ። አመታት እርሱን የኔ በማድረግ ምኞት አልፈው በመጨረሻ ፊቴ ሲቆም አይሆንም ማለት አቅቶኝ ፤ እዝሌንም በቃኸኝ ግዕዜን አግኝቻለሁ ብዬ እንዳልለው የምጠለልበት የምሰክንበት ጥጋቴ ነውና እንዳላጣው ፈርቼ በሁለት ቢላ የምበላ ሆንኩኝ ። ሁለቱንም በተለያዩ ምክንያቶች ሳላስባቸው ውዬ አላውቅም ። ባስታወስኳቸው ቁጥር ግን ሃዘን ይከበኛል ። ሁለቱም በመቅበዝበዝ እና በመንገብገብ ያበላሸኹዋቸው የህይወቴ ዋና ዋና ዜማዎች ናቸው ። በእርግጥ ከነርሱ በኋላም ያማረብኝ ቅላፄ የተዋጣልኝ አቋቋም የለም ግን እንደ ሁለቱ ያበላሸሁት የለም ። አሁን ላይ ከግዕዜና ከእዝሌ የተረፈኝን አራራይ ዜማ ለራሴ ወስጄ ሌት ተቀን እህህ እላለሁ ። ሁሉን የእኔ ይሁን የሚል ልጅነቴን ለተከተለ ደመነፍሴ ፣ በሁለት ዜማ አንድ ቅኝት ለናፈቀ ለጋነቴ ፣ ለባተልኩት ፣ ለባከንኩት ፣ ከሁሉ ከሁሉ በአንድ እለት ግዕዝም እዝልንም ለተቀበለ ሴትነቴ በአራራይ ዜማ እህህ እላለሁ ።
በመጨረሻ የገባኝ ግን ሁሉ በአሳዛኝ ዜማ እንደሚቋጭ ነው ፤ ህይወት የሚባል ውብ ነገርም ቢሆን ........

@wegoch
@wegoch
@paappii
★ ★ ራሴው ማበዴ ነው……#2 ★ ★
(ሜሪ ፈለቀ)

"አቤት?” አልኩት ለሰላምታ የዘረጋውን እጁን ችላ ብዬ ወንበሬ ላይ እየተቀመጥኩ። ፀጉሩ አልፎ አልፎ ከመሸበቱ ውጪ ብዙም አልተለወጠም።

"ደህና ነሽ ሚሚሾ?"

"ምን ፈልገህ ነው የመጣኸው? ደህና መሆኔ አሳስቦህ አይሆንም መቼም!! የልጅህ ሰርግ ጥሪ ወረቀት እንደደረሰኝ ለማረጋገጥ ከሆነ ደርሶኛል። እማም ደርሷታል። ጨርቄን ጥዬ እንደሆን እንድታይ ሚስትህ ከሆነ የላከችህ። ሂድና ንገራት! ረስተናችኋል። እባካችሁ ከህይወታችን ውጡ። እና ከቢሮዬም ውጣ……” መናደድ አልፈልግም። ግን አስቤያቸው አለመናደድ ያቅተኛል። ሁሌም እንዲህ ናቸው። ስተዋቸው አይተውኝም። ዝቅጥ ብለው ያዘቅጡኛል። ስለእውነቱ የሁሉም ክፉ ነገር ሀሳብ ባለቤት ሚስቱ ናት። እሱ መልሱ ዝምታ ነው። ጋግርት። ግን ከእርሷ ቅጥ የለሽ ክፋት በላይ የሱ ዝምታ ይሰብረኝ ነበር።

"ለግሌ ጉዳይ ነው የመጣሁት።” አለኛ አፉን ሞልቶ።

"ሰውየው ከእኔ ጋር የሚያገናኝ የግል ጉዳይ የለህም። እባክህ መጥፎ ነገር አታናግረኝ። ውጣልኝ……”

"የውብዳርን ልፈታት ነው። በመሀከላችን ብዙ ጣጣዎች ስላሉ ጠበቃ ያስፈልገኛል። …” ወደ በሩ እየተራመደ “… ትረጂኛለሽ ብዬ ተስፋ ነበረኝ። ጭራሽ ልትሰሚኝ እንኳን ፈቃድሽ ካልሆነ ምን አደርጋለሁ? ባልደረቦችሽን ላማክራቸዋ?” በሩን ከፍቶት ወጣ። ምን? እኮ የቤተሰቤን ጉድ ባልደረቦቼ ሊሰሙ? በተለይ ደግሞ ፍትህ? ኡኡኡ ልል ትንሽ ነበር የቀረኝ። በሩጫ ተከተልኩት። አጠገቡ ስደርስ እልህም ንዴትም አነቀኝ። ጮኬ ማውራት ግን አልችልም። እኔን የሚያነድበት አንዲት የነገር ሽራፊ ለሚፈልገው ፍትህ ራሴን አላጋልጥም።

“ምንድነው ግን ከኔ የምትፈልገው? ምን አድርጌ ነው እየተከታተላችሁ ልታጠፋኝ የምትተጉት? በምትወዳት ልጅህ ይሁንብህ ተወኝ?” አልኩት ጥርሴን ነክሼ ከእንባዬ እየታገልኩ። ሁሌም እንደዚህ ነው። ቤተሰቤን አስመልክቶ መጨረሻዬ እንባ ነው። ተሸናፊ ነኝ። አሸናፊዎች ናቸው። በፈለጉበት ቀን መጥተው ከዓይኔ እንባዬን ለመቅዳት የመብታቸው ያህል ቀላል ነው። የፈለጉትን ይቀሙኛል። …… እኔ ይህቺ ነኝ! የአደባባይ አንበሳ! የቤቴ አይጥ ነኝ።

"አንድ ጊዜ ብቻ ቁጭ ብለሽ እንድትሰሚኝ እፈልጋለሁ። እውነቱን ላስረዳሽ እፈልጋለሁ። የምፈልገው እሱን ነው።”

"እባክህ ሂድልኝ። እባክህ ተወኝ። አንድ ያልነጠቃችሁኝ ነገር ስራዬ ነው። አንድ የእናንተ የክፋት እጅ ያልደረሰበት ቦታ የስራ ቦታዬ ነው። እባክህ ልለምንህ እሱን ተውልኝ።………” ከየት መጣ ሳልለው ፍትህ አጠገባችን ደርሶ

"እንዴ አባባ ሻይ ቡና ምን ይምጣሎት?…” እየለፈለፈ እያለ አየኝና ደነገጠ። “…… እንዴ ቦስ ችግር አለ እንዴ?ምነው የተፈጠረ ነገር አለ?” አብረን ስራ የጀመርን ሰሞን ሊያናድደኝ ሲፈልግ ‘ቦስ’ እያለ መጥራት ጀመረ። ዛሬም ድረስ እንደዛ ነው የሚጠራኝ። ዝም ካልኩት መጠየቁን እስከማታ አያቆምም።

"ፍትህ ዘወር በልልኝ!” ብዬ ጮህኩበት።

ለምኜም ተቆጥቼም አባቴን ሸኘሁት። ሌላ ቀን እንደሚመለስ ነግሮኝ ሲወጣ ያዘነልኝ ይመስል ነበር። የውላችሁ…… እዚህ ተረክ ውስጥ ማንም ጥሩ ማንም መጥፎ የለም። ሁሉም ጥሩ አይደሉም። ሁሉምም መጥፎ አይደሉም። እናቴን ጨምሮ!! ስለቤተሰቦቼ ሁሉንም ባላውቅም አንዳቸውም ንፁህ አይደሉም። የተዘራሩትን ነው የሚተጫጨዱት። ለነገሩስ የሰው መቶ ፐርሰንት ጥሩ ወይ መጥፎ የታለው? ጥሩ የምንለው ሰው ክፋቱን በጥሩነቱ የሸፈነ። ክፉ የምንለውስ ጥሩነቱን በክፋት የሸፈነ አይደለምን? እንጂማ ሁሉም የክፋትና የመልካምነት ስብጥር አይደል? ጎልቶ ባሳየው ይጠራበታል።

እኔስ? ባልበላሁት ጉሮሮዬን እየቧጠጠ ያስመልሰኛል። ያልዘራሁት እሾህና አሜኬላ እየበቀለ እድሜዬን ሙሉ ሲያንቀኝ አለ። ራሴ ከዘራሁት መልካም ዘር ቀድሞ እነሱ የዘሩት እንክርዳድ ደርሶ እበላዋለሁ። እንደአረቄ አዙሮ ይደፋኛል።

"ቦስ ቡና ላምጣልሽ?” ቢሮዬ መጥቶ ነው።

"እባክህ ፍትህ… … እየደጋገምክ የቢሮዬን በር መክፈት አቁም።”
"Am just worried… … የሆንሽውን እያየሁ ዝም ብዬ ልቀመጥ?”

"አዎን እንደሱ አድርግ። ዝም በለኝ።”

"እሺ እቤት ሄደሽ እረፊ። እዚ ሆነሽ ምንም ነገር በትክክል አትሰሪም።” አለኝ። እማ ትዝ አለችኝ። ኮቴን አንስቼ አልፌው ሄድኩ። እቤት ስደርስ የቀረበላት ምግብ ላይ ትተክዛለች። የማይሰማ ነገር ታጉተመትማለች። ሰራተኛዋ ቆማ እየጠበቀቻት ነበር።

"እማ እባክሽ ዛሬ አይሆንም። ዛሬ ደህና ሁኚልኝ። ዛሬ አልችልም። አልችልም!!”

ቀና ብላ አየችኝ። “አንቺ ደግሞ ማነሽ? የውብዳር ናት የላከችሽ? ” አምላኬ ሆይ አይሆንም! አይሆንም!!

"አይደለም እማ አንዱዓለም ነው የላከኝ።" ከቃላቶቹ ጋር እንባዬ ይወርዳል። እሷ የእሱ ስም ከተነሳ እያለቀስኩ ይሁን እየሳቅኩ ግድ የላትም። ሲጀምራት ሰሞን የእርሱ ስም ያረጋጋታል። እሱ ይሄን ማወቁን እንጃ! እብደቷም መድሃኒቷም እሱ ነው።

"እና ምን አለሽ?”

"የኔ ጨረቃ ናፈቅሽኝ እኮ! ባክሽ ይሄ ስራ ይቅርብሽና ሁሌ ማታ ማታ ልይሽ?………”ባሏ እሷ ስራ ስትሄድ የፃፈላት ደብዳቤዎች ናቸው። እሷም በቃሏ ሁሉንም ታውቃቸዋለች። እኔም እንደዛው። ለዓመታት በቃሌ አነብንቤላታለሁ። አብራኝ ቃሎቹን እያጣጣመች እንቅልፍ ይወስዳታል። ……… ዛሬም ለአንድ ሰዓት ያህል የባሏን መልእክት ነግሪያት እሷ ሶፋው ላይ ፈገግ እንዳለች እንቅልፍ ጣላት።

★ ★ አሁንም አልጨረስንም ★ ★

@wegoch
@wegoch
@paappii
Forwarded from Sunset Hiking
#Hiking #outdoor #photography

Hiking to the majestic Mt. #Eerer with #Sunset Family.

📅Hiking Date :- October 11, 2020 (ጥቅምት 1, 2013)

💵 Hiking Cost #400 ETB only

🛫Departure: Shebelle (Mexico)🍁

Departure Time - 12:00 LT 🍂🌴🍁

🎉🎊Package includes🎋🎊

🚍 Transportation
🌲 Bottled water
🌺 Guide
🍂 photography 📷
💐 snack
🌷 Family Chilling & Talent performance ( if any)🙊🙊

NB.
🏖 Package does not include lunch.
🚫 Sanitizer & facemask mandatory!

Brought to you by
💥#Sunset_Hiking_Team

for more join the
🔸channel @sunsethiking🍁

🔻📷 @sunsetphotography🍁

🎫 tickets available at
@Paappii
@thomaskagnew
@Chere_daregot
~ ራሴው ማበዴ ነው… …#3 ~
(ሜሪ ፈለቀ)

ከሀያ ዓመት በላይ የሆናቸው በወጣትነቷ ውዷ ከፃፈላት ደብዳቤዎች ዛሬም ድረስ አብረዋት ያሉ እያንዳንዱን በቃሏ የምታውቃቸው 23 የፍቅር ደብዳቤዎች አሏት። ሁሉንም ከነተፃፉበት ቀን ሳይቀር እኔም በቃሌ አውቃቸዋለሁ። እንደዚህ ከፍ ያለ ፍቅር መቋጫው እንዴት አስከፊ መለያየት እንደሆነ ሳስብ ይገርመኛል። እሷ ዛሬን ማሰብም መኖርም አትፈልግም። በትናንት ትዝታዋ ውስጥ ተወሽቃ ቀኖቿን መጨረስ ነው የምትፈልገው። እናቴ ያልገባት ነገር የሷን ትዝታ ስተዘትዝ የእኔም ቀኖች ከመድረሻቸው እየተቀነሱ እንደሆነ ነው።

"ቦስ ሰላም ነሽ?” ለሶስተኛ ጊዜ ስልክ ደውሎ ነው።

"ደህና ነኝ አልኩህ እኮ ፍትህ! ነገ እንገናኛለን። በቃ ደህና እደር!”

"እሺ ምግብ በልተሻል? አድራሻሽን ከነገርሽኝ ያለሽበት ላምጣልሽ?”

“ፍትህ ምግብ በልቻለሁ። ራሴን መንከባከብ አያቅተኝም። ባክህ እረፍ!”

ፍትህ ማለት በብዙ የሚያበሽቀኝ በበሽ የሚያበግነኝ ባህሪ ያለው ነው። ቢሯችንን የከፈትነው ከሁለት ምርጥ ጠበቆች ጋር በጋራ ነበር። አንደኛው ከወራት በፊት በግሉ ምክንያት ስራ ሲያቆም ፍትህን የቅርብ ጓደኛውና ጎበዝ ጠበቃ መሆኑን አሳምኖን ነው አብረን መስራት የጀመርነው።ፍትህ ቅንጡና ለብዙ ነገር ግድ የለሽ ነው። ለምን በየዕለቱ ቢሮ እንደሚገባም ሆነ ለምን ጠበቃ መሆን እንደፈለገ አይገባኝም። ምክንያቱም ለስራው ፍቅርም ትጋትም የለውም። ገንዘብ የሚያሳስበው ሰው እንዳልሆነ ለመገመት ደግሞ የሚጠቀማቸውን ቁሶችና አላስፈላጊ ወጪዎቹን ማየት በቂ ነው።

ከነገረስራው ሁላ ሴትን ልጅ ከአልጋ ወርዳ ማሰብ የሚከብደው ብሽቅ መሆኑ ያናድደኛል። ስማቸውን እንኳን በውል ከማያስታውሳቸው እልፍ ሴቶች ጋር ነው።

"ባል ሳታገቢ ነው የምታረጂው ታስታውቂያለሽ።” ይለኝ ነበር ስራ የጀመረ ሰሞን እራት ልጋብዝሽ ብሎኝ እንቢ ስላልኩት ሲያበሽቀኝ።

"አንቺ የሴት ልስላሴ የለሽም። ነገር ላይ እርርርር ትያለሽ። ጠብሰሽ ማወቅሽንም እንጃ።” ይለኛል በሌላ ቀን። ልስማው አልስማው ግድ የለውም ይለፈልፋል። ልቀየመው ልናደድበት ግድ የለውም አፉ እንዳመጣለት ነው የሚመርገው።

"አለቃ አለቃ መጫወት ትወጃለሽ። ሁሉም ቦታ ዋና አክተር መሆን አይደብርሽም?” ይለኛል በምንም ጉዳይ አስተያየት ልሰጠው ከሞከርኩ።

"በራስሽ ትመፃደቂያለሽ። ራስሽን ለዓለም ህዝብ እንደተላከ መሲህ ነው የምትቆጥሪው። ሁሌ ልክ እንደሆንሽ፣ ካንቺ በላይ አዋቂ እንደሌለ ነው የምታስቢው።……” ብሎኛል ጠጥቶ አድሮ የፍርድ ቤት ቀጠሮ ያመለጠው ቀን ልክ እንዳላደረገ ስነግረው። ለምን እንደሆነ አይገባኝም ብቻ የምሰራው ሁሉ አይዋጥለትም። እንደማንኛዋም ሴት መሆኔን ሳይጠቁመኝ አያልፍም። እኔን የሚናገርበት ስህተት ያገኘብኝ ከመሰለው አለቀልኝ። በነገር ሲተረኩሰኝ ይሰነብታል።

አባቴ ቢሮ መጥቶ ዓይኖቼ በእንባ ተሞልተው ሳወራው ካየኝ ቀን ጀምሮ የማውቀው ፍትህ አልሆነም። ምናልባት ግትርና ደንዳና የምትመስለው ሴትዮ ተሸንፋና ተመሳቅላ ስላያት የቆለላት ሴት ተንዳበት ግራ ገብቶታል ወይም ደካማ ጎኔን አውቆ ሊሳለቅ እየተከታተለኝ ነው አልያም አሳዝኜዋለሁ። ሁሉም እንዲሆኑ የማልፈልጋቸው ናቸው።

"ቦስ ቅድም አባትሽ መጥተው ነበር።” አለኝ ከፊቴ ላይ ስሜቴን እየዘገነ

"እና?” አልኩት ምንም ያልተሰማው ለመምሰል ዘና እያልኩ።

"እኔን ፈልገው ነው የመጡት። አንቺ ፍርድ ቤት መሆንሽን አስቀድመው አረጋግጠው ነው የመጡት።” አነጋገሩ ‘ምን ማድረግ እችል ነበር?’ የሚል አንድምታ አለው። ፀጥ አልኩ። ለሰከንዶች ጭንቅላቴ ረጭ አለ። ማሰብ አቆምኩ።

"ከእናትሽ ጋር መፋታት እንደሚፈልጉ እና አንቺ እንቢ ስላልሻቸው ሊያማክሩኝ ነበር። ጠበቃቸው እንድሆን ይፈልጋሉ።” የውብዳርን እናትሽ ማለቱ ብዙ እንዳላወሩ ገባኝ። …… ጭንቅላቴ ወና ስለሆነ የምጠይቀውም የማወራውም አልነበረኝም።

"የእህትሽን የሰርግ ካርድ ሰጥተውኝ ነው የሄዱት። እንዳልቀርና ብዙ የሚያጫውቱኝ ነገር… …” ቀጠለ…… “የሆነ ነገር በይኛ ቦስ?” ምን ልበለው? አትሂድ? እንደውም አባቴን አታናግረው? ለአባቴ ጠበቃው ከሆንክ ስለእኔ ብዙ ታውቃለህና ይቅርብህ? እናስ? ደከማ ጎኔ እንዳይታወቅ? ፍትህ እንዳያሸንፈኝ? በስራዬ የሚያውቁኝ ሁሉ የሚያውቋትን ጠንካራ እና በራሷ የምትተማመን ሴት ዙፋን ለማስጠበቅ?

ስራዬንም ቢሮዬንም እወደዋለሁ። ምክንያቱ ደግሞ ከቢሮዬ ውጪ ያለውን ፣ ያለፈውንና የሚመጣውን የማላስበው እዚህ ነው። እዚህ ሌላ ሴት ነኝ። አንድ ደራሲ መፅሃፍ ሲፅፍ የሚቀርፃቸውን ገፀ ባህሪያት ኑሮ ሲያበጅ ራሱን በፈጠራቸው ገፀ– ባህርያትና ዓለም ውስጥ የሚደብቅ ይመስለኛል። ለኔ ስራዬ እንደዛ ነው። በማገለግላቸው ደንበኞቼ ውድቀትና መነሳት ውስጥ ራሴን ደብቃለሁ። አንዳንዱ በመጠጥ አንዳንዱ በሌላ ሱስ ያደለው ደግሞ በሚወደው ሰው እና በፍቅር ውስጥ ራሱን እንደሚደብቀው።

ፍትህ የአባቴ ጠበቃ ሆነ ማለት ስለቤተሰቦቼ እኔ የማላውቀውንም ጉዳይ ጭምር አወቀ ማለት ነው። ያ ማለት ደግሞ ቢሮዬ ውስጥ የነበረኝ በራስ መተማመን እና ነፃነት ጠፋ ማለት ነው። ከዛ ቢሮ መግባት እጠላለሁ። ያኔ ራሴን የምሸሽግበት ቦታ አይኖረኝም። አደባባይ ተሰጣሁ ማለት ነው። ያኔ ለመንኮታኮት ተምዘገዘግኩ ማለት ነው።

"እና ትሄዳለህ? ማለቴ ሰርጉን?” አልኩት በመጨረሻ። ሰርጉ የድሮ ፍቅረኛዬና የእህቴ እንዳልሆነ ሁሉ እንደማንኛውም ‘ሰርጉን’ ብዬ

"ለምን እቀራለሁ?”

“ጠበቃው ልትሆን ወስነሃል ማለት ነው?”

“እንዳልቀበል የሚያደርገኝ ምክንያት አለሽ?”

"አይ ምክንያት የለኝም። ግን ባትቀበለው ደስ ይለኛል።”

"እኮ ለምን?” ለምንም ነገር ግድ የሌለው ሰው ይሄ ኬዝ እንዲህ ሀሳቡን የሰረቀው ከእኔ ጋር ስለተያያዘ ብቻ ነው። ለ‘ለምኑ’ መልስ የለኝም።


★ አሁንም በድጋሚ አልጨረስንም ★

@wegoch
@wegoch
@paappii
~ ራሴው ማበዴ ነው… …#4 ~
(ሜሪ ፈለቀ)

"ልትነግሪኝ የምትፈልጊው ነገር አለሽ?”

"ማለት? ስለምን?”

"እኔ እንጃ ቦስ አባትሽ እዚህ ቢሮ እግራቸው ከረገጠ ቀን ጀምሮ ላለፉት ሁለት ሳምንታት ፍፁም ልክ አይደለሽም። ያዘንሽ ያዘንሽ ፣ የተከፋሽ ፣ የሆነ ነገር ያደከመሽ አይነት ነው የምትመስዪው።” ሲለኝ ለቅፅበት ያደከመኝን ሁሉ ልነግረው ዳድቶኝ ነበር።

ራሴን አውቄ ሀላፊነትን መሸከም ከቻልኩበት ጊዜ ጀምሮ ለሚያውቀኝ ሰው ወይም በምንም አጋጣሚ ቢሆን ድጋሚ ላገኘው ለምችለው ሰው ስለራሴ ተናግሬ አላውቅም። ነገር ውስጤ ተቆልሎ የሆነ ዓይነት እምቅ ሀይል ሆኖ እንደ ኒውክለር ሊፈነዳ የመሰለኝ ወቅት ላይ አንድ ሶስቴ ከዛን ቀን በኋላ ፊታቸውን አይቻቸው ለማላውቃቸው ሰዎች የተሰማኝን ዝርግፍግፍፍፍ አድርጌ ከመፈንዳት ተርፊያለሁ። አንዷ ‘ነገ አረብ ሀገር ልሄድ ነው።’ ያለችኝ ፀጉር ቤት ያገኘኋት ሴት ናት። ፀጉራችንን ተስርተን ስንወጣ ለማኪያቶ ካፌ ተቀምጠን ያወራኋት። ሁለተኛው ናዝሬት ለስራ ሄጄ ያረፍኩበት ሆቴል ብቻዬን ራት ስበላ አይቶኝ ‘እንብላ’ ባለኝ ሰበብ ያወቅኩት ጎልማሳ ነው። (ሊበላኝ(ሊያባላኝ) ባሰበ ምሽቱን የተበላው።) ሶስተኛው ከቂሊንጦ ስመለስ ሊፍት የሰጠኝ ሽማግሌ ነው። አንዳቸውንም ከዛ በፊትም ሆነ ከዛ በኋላ አይቻቸው አላውቅም። ስሜን አያውቁም ፣ ማን መሆኔን ፣ የት መሆኔን አያውቁም……… ሳወራላቸው ነገ ሲያዩኝ ምን ይሰማቸዋል? አልልም…… ሳለቅስ ወይ ስዝረከረክ ይዳኙኛል አያሰጋኝም…… በነሱ ፊት መሸነፌ ወይ ተስፋ መቁረጤ ድክመቴ አይሆንም። …… ለምንም ግድ የለኝም። ልግባቸው ላደናግራቸውም ጉዳዬ አይደለም። የተሰማኝን በሙሉ ዘርግፌ ተንፍሻለሁ።

ለሚያውቀኝ ሰው እንደዛ አላደርግም። ለሚያውቁኝ ሁሉ(ከቤተሰቦቼ ውጪ) ያቺ አልቅሳ የማታውቀው ፣ብርቱዋ ፣ ደካማ ጎኗን ማንም የማያውቅባት፣ መጠቃቷን ማንም የማያውቅላት… … የጉብዝና ምሳሌ የሆነችዋን ራሔል ነኝ።

"ፍትህ አንተ ደግሞ ላለፉት ሁለት ሳምንታት ስራህን እርግፍ አድርገህ ትተህ እኔን ስራ አድርገኸኛል። am fine!! በቀን አስሬ ቢሮዬን የምትከፍተውን ነገር አቁም። please?” አልኩት። ብዙ ቀን ብዬዋለሁ ሰበብ እየፈለገ በጥያቄ ይወጥረኛል እንጂ።

"እሺ። ከፈለግሽኝ ግን አለሁ።” ብሎኝ ቆይቷል። ከቢሮዬ ግን አልወጣም። ከወንበሩም አልተንቀሳቀሰም። ሁሌም የማስበው የኖህ ታሪክ ትዝ አለኝ። ከውሃ ጥፋቱ በኋላ ኖህም ገበሬ ሆነ። ወይንም ተከለ። ከወይን ጠጁም ጠጣና ሰከረ። …… በድንኳንም ውስጥ ራቁቱን ሆነ ታናሹ ልጁ ካምም የአባቱን እርቃን ባየ ጊዜ ተሳለቀ። በአባቱ ገመና ሙድ ያዘ። ሁለቱ ልጆቹ ያፌትና ሴም ግን እርቃኑን እንኳን እንዳያዩበት አክብረውት ፎጣ በትከሻቸው አድርገው የኋሊት እየተራመዱ የአባታቸውን እርቃን ሸፈኑ… …… ኖህም ካምን ረገመው… ………… ይመስለኛል። ሲመስለኝ ሲመስለኝ……… የካም ነገድ የአክሱምን ልጅ ወለደ…… የአክሱምም ልጅ ልጆች በወንድምና ወዳጃቸው ገመናና ድክመት ሲደነቋቆሉ… … ሲሸረዳደዱ…… አንዱ የአንዱን ድክመት ሲጋለቡ ኖረው ኖረው። የእንጀራ እናቴ አባት ላይ ደረሱ። እሳቸውም ቀንደኛ ሸርዳጅ የሆነች ትውልድ አፈሩ……… ምናምን ምናምን………

የኖርኩት ዘመን የተረዳሁት አብዛኛው ሰው ከትልቁ ስኬትህ ውስጥ እንኳን ምናምኒት የምታክል ውድቀትህን ወይ እንከንህን ይፈልጋል። ካገኘብህ አለቀልህ። ሰማይ ያከለ ስኬትህን የጎመንዘር በምታክል እንከንህ ያጣፋልሃል።

"ፍትህ?”

"አቤት ቦስ?”

"ነገ ሰርጉን ትሄዳለህ እንዴ?”

"አወና!! እንዴ ቆይ ቆይ…… ትሄዳለህ ነው ትመጣለህ? ያ ማለት የእህትሽ ሰርግ ላይ አንቺ አትኖሪም ማለት ነው? ኦ……ኬ …… I think ይሄ ኬዝ ካሰብኩት በላይ ሊመስጠኝ ነው። ምንድነው እሱ?”

"ምንም big deal አይደለም። መሄድ አለመሄድህን ለማወቅ ነው። አበቃ!! የሆነ ታላቅ ግኝት ያገኘህ አታስመስለው።”

"እሄዳለሁ።” ብሎኝ ዓይኖቹን ዓይኖቼ ውስጥ ዘፍዝፎ ስሜቴን ሊጨምቅ ይታገላል።

"መልካም።” አልኩት ድምፄ ከስሜቴ ጋር አብሮ ሲወርድ እየታወቀኝ።

"በቃ?” ብሎ አፈጠጠብኝ ከተቀመጠበት መንጭቆ እየተነሳ። "በቃ ሌላ የምትዪኝ ነገር የለም?”

"እንዴ? ምን እንድልህ ነው የምትፈልገው?”

"አላውቅም!! ብቻ ከቤተሰብሽ ጋር በተያያዘ አንድ እንዳላውቅ የፈለግሽው ነገር ያለ ይመስለኛል። አላውቅም!! ንገሪኝ ማወቅ ያለብኝ ነገር ካለ ከሌላ ሰው ከምሰማው በፊት ንገሪኝ!”

"Excuse me? ከሌላ ሰው ከመስማትህ በፊት?ራስህን ምን ቦታ ላይ ነው የሰቀልከው ባክህ?” ሆኖ እንደማያውቀው እየጯጯህን ነው።

"Sorry boss! ራስን መስቀል አይደለም። እንደጓደኛ……”

"እኔና አንተ ጓደኛሞች አይደለንም! ደግሞ ቦስ አትበለኝ። አለቃህ አይደለሁም። ስም አለኝ። እኔና አንተ የስራ ባልደረቦች ብቻ ነን። የሚያገናኘንም ስራ ብቻ ነው።” ንግግራችን የማያስፈልገውን ያህል ቁጣ እየተቆጣሁ እንዳለሁ ራሴን ስሰማው አውቃለሁ። ግን ቁጣዬ ምክንያቱ ፍትህ ብቻ አልነበረምና መመጠን አልችልም።

"እሺ ጓደኛሽ አድርጊኝ? I mean not just for sayin… … real ጓደኛሽ ልሁን?።” አለኝ ሹክሹክታ በመሰለ ድምፅ እና ከኔ በተቃረነ እርጋታ። ሁኔታዬ ራሴኑ አሳፈረኝ። እሱ ላይ የምጮህበት ምንም ምክንያት የለኝም። ፀጥ አልኩ። ጠረጴዛዬ ላይ በአንድ መቀመጨው እየተቀመጠ

" I know አንቺ በጣም ጠንካራ ሴት ነሽ። ያ ማለት ግን ሰው አያስፈልግሽም ማለት አይደለም። ያንቺን ጭንቀት ማወቄ ላንቺ ያለኝን ቦታ አይቀንሰውም። በምታልፊበት ነገር ሁሉ ውስጥ አልፈሽ እዚህ መገኘትሽ ምን ያህል ጠንካራ ሴት መሆንሽን ያገዝፍብኛል እንጂ።” አለኝ የፍትህ በማይመስል እርጋታና ብስለት።

"ለምን ብለህ ምክንያቱን አትጠይቀኝ። እባክህ ሰርጉን አትሂድ?” ማለት ብቻ ነበር የመጣልኝ ሀሳብ

"እሺ።” አለ እንደዘበት። ከዛም ያልሰጠሁትን እጄን ፈልቅቆ እየማለ “ ይኸው !ቦስ ይቅርታ ራሔል ሙች! አልሄድም። ከፈለግሽ በቤተሰብሽ ኬዝም አልገባም። ያ የሚያስደስትሽ ከሆነ ምክንያትሽንም ማወቅ አልፈልግም። ራስሽ ፈልገሽ እስካልነገርሽኝ ድጋሚ አልጠይቅሽም። ግን አንድ እንድታደርጊልኝ የምፈልገው ነገር አለ!” እያለኝ ስልኬ ጠራ። ከቤት ነው። አንስቼው ስለእማዬ በሰማሁት ነገር እግሮቼ ዛሉብኝ። የብርትኳን ቢላዋ አንስታ ታፋዋ ላይ ሰክታለች። ሰራተኛዋ እየተርበተበተች ነው የነገረችኝ። ስለእማዬ በሰማሁ ቅፅበት ፍትህን ረስቼዋለሁ።

"ምንድነው እሱ? ምንድነው? እናትሽ ምን ሆነው ነው?” አፌ ቃላት መትፋት አቃተው። ምንም አላስፈቀደኝምም። አልጠየቀኝምም። ስልኬን አንስቶ መልሶ ደወለ። ልሄድ ቆሚያለሁ። ግን መንቀሳቀስ ከበደኝ። ከሰራተኛዋ ጋር እያወራ እንደሆነ አውቃለሁ። ግን አልሰማውም። ኮቴንና ቦርሳዬን ሰብስቦ እጄን መንጭቆ ይዞኝ ሲወጣ እግሬን ለመራመድ ማዘዜን ባላውቅም ተከትዬው መኪናው ጋር ደርሻለሁ። በሩን ከፍቶ መኪናው ውስጥ ሲያስገባኝ፣ ስንሄድ፣ ከሰራተኛዋ ጋር ሲደዋወል፣ እቤት ይዞኝ ሲገባ… …… ጆሮዬ ጭውውውውው ይልብኛል። ጭንቅላቴ የሆነ ከባድ ነገር እንደተጫነብኝ ለአንገቴ ከብዶታል። …………

★ ★ ★ አሁንም በድግምጋሚ አልጨረስንም ★ ★ ★

@wegoch
@wegoch
@paappii
~ራሴው ማበዴ ነው… … #5~
(ሜሪ ፈለቀ)

"ራሔል ከዚህ በላይ እናትሽን እቤት ልታቆያቸው የምትችዪ አይመስለኝም። አደገኛ ነው የሚሆነው።”

"ዶክተር በፍፁም ሆስፒታል እንደማልተዋት ቃል ገብቼላታለሁ። አይሆንም!! ታውቅ የለ ምን ያህል እንደምትጠላ?”

“ራሔል እስቲ ተቀመጪ።” አለኝ ወንበሩን እያሳየኝ። በእማዬ ምክንያት ከማውቀው ልምድ በዶክተሮች አባባል ‘እስኪ አረፍ በይ፣ እስኪ ተቀመጪ፣ ለመረጋጋት ሞክሪ፣ የቅርብ ዘመድ ነሽ ወይ?…… ’ ዓይነት ንግግሮች ‘ ለሚከተለው አሳዛኝ ዜና ተዘጋጂ።’ የሚል አንድምታ ነው ያዘለው። ቅርፍፍፍፍፍ እያልኩ ተቀመጥኩ።

" አየሽ ራሔል በህይወት አንዳንዴ ትክክለኛው ውሳኔ ከባዱ ውሳኔ ይሆናል። አሁን እናትሽ ከፍተኛ የህክምና ክትትል ያስፈልጋቸዋል። እእ… … (እንዲህ እ…እ ሲጀምር የሚነግረኝ ነገር ጨንቆታል።) እ ራሔል ታውቂያለሽ እናትሽ ከአዕምሮ መታወኩ በላይ ካንሰሩ ጎድቷቸዋል። ብዙ ጊዜ የላቸውም።…… ” ምን እያለ እንደሆነ ገብቶኛል። ግን ደግሞ አልገባኝም። ብዙ ምክር አክሎበት እናቴ ከግማሽ ዓመት ያለፈ ጊዜ እንደሌላት ነገረኝ። በህይወት እያለች እንዳትሰቃይ ላደርግላት የምችለው ብቸኛ ነገር አባቴ እንዲያያት ማግባባት መሆኑንም አከለልኝ። …… አልጠየቅኩም። አልመለስኩም። ቢሮውን ለቅቄ ወጣሁ። ፍትህ ውጪ እየጠበቀኝ ነበር። ከትናንት ጀምሮ እዚሁ ነበረ።

"ፍትህ ምንም ነገር እንዳትጠይቀኝ።” ብዬው ነበር።

"ምንም ልጠይቅሽ አላሰብኩም።” ነበር መልሱ። እስከአሁንም ስለምንም አልጠየቀኝም። ወደ ስራው እንዲመለስ ደጋግሜ ወትውቼዋለሁ። አልሰማኝም እንጂ። ከዶክተሩ ቢሮ እንደወጣሁ ፍትህ ወደነበረበት ሄጄ ወንበር ላይ ዘፍ አልኩ። አጠገቤ ያለው ወንበር ላይ ተቀምጦ ሳይመቻች አቀፈኝ። ጥሩ ዜና እንዳልሰማሁ ገብቶታል።

"እማዬ መሞቻዋ ደርሷል ተዘጋጂ አለኝ።” ስለው ደንግጦ ለቀቀኝ። "ከስድስት ወር ያለፈ ጊዜ የላትም።”

"እሺ። እሺ በቃ! እሺ።” የሚለኝ ከኔ በባሰ ግራ ተጋብቶ የሚለው ጠፍቶት መሆኑ ገብቶኛል። "እሺ በቃ ማድረግ ያለብንን እናደርጋለን። አንድ መንገድ አናጣም።” ይለኛል።

"አሰቃየሁሽ አይደል?” አለችኝ እማዬ ገና ወደ ክፍሏ ስገባ። ሁሌም ቢሆን መጥፎ ነገር ካደረገች በኋላ ልክ ከቅዥቱ እንደባነነ ሰው ፍፁም ጤነኛ ጭንቅላት ይኖራታል።

"አንቺ ተሰቃየሽብኝ እማ።” እያልኳት ለአፍታ ሞት ለሷ ግልግል መሆኑ በጭንቅላቴ ሽው አለኝ። እንደዛ በማሰቤ ራሴን ተፀየፍኩት። ግን እንዳትሞት የምፈልገው ለሷ ነው ለራሴ? ዘመኗን ከመድሃኒት፣ ከቴራፒዎችና ከቅዥት ጋር በስቃይ እየኖረች ያለች እናቴ እንዳትሞት የምፈልገው ለሷ ስል ነው ለራሴ?

"እማ ፍትህ ይባላል። አንድ ላይ ነው የምንሰራው። ትናንት ሆስፒታል ያደረሰሽ……”

"አስታውሳለሁ። አውቄዋለሁ ልጄ…” አለችኝ ከግርጌዋ ቆሞ ወደነበረው ፍትህ እያየች። "መልካም ልጅ ነህ። በክፉ ሰዓት ባላውቅህ ደስ ይለኝ ነበር።” እያለችው። ወደ ክፍሉ አንድ ሰው ገባ። ድርብብ ያለ ጎልማሳ፤ ልብወለዶች ላይ ያለ ደግ አባት የሚመስል፤ ፀጉሩ እና ፂሙ ሽበት ጣል ጣል ያደረገበት፤ ቁመቱ ረዥም፤ ቀላ ያለ ፤በለስላሳ ፂም የተሸፈነ ጉንጭ ያለው፤ ደልደል ያለ…… ሰውዬ

"ካስዬ መጣህ?” አለ ፍትህ ከቆመበት ሳይንቀሳቀስ ቀጠለና “ራሔል እሷ ናት። እሳቸው እናቷ ናቸው።” አለው።

"እንዴት ነሽ ልጄ?” ብሎ ሳብ አድርጎ በግዙፍ ሰውነቱ ውስጥ ወሸቀኝ። ፀጉሬን ደጋግሞ እየሳመ ወደ ሰውነቱ አጣብቆ አቀፈኝ።ልል የነበረው ‘ፍትህ የማላውቀውን ሰው እንዴት ይጠራብኛል? ነበር። ደረቱ ላይ በእጆቹ ተከብቤ ላስብ የቻልኩት ግን ‘ይሄን ፍቅር የት ነው የማውቀው?’ የሚለውን ብቻ ነው። ጀርባዬን አይዞሽ እንደማለት፣ አለሁልሽ እንደማለት አሸት አሸት አድርጎ ወደ እማዬ ሄደ። ወንበሩን ሳብ አድርጎ አጠገቧ እየተቀመጠ

"ሽማግሌ ነኝ አንቺን አንቱ አልልሽም። እንዴት ነሽ? እጅሽን ደግሞ እንዲህ አታድርጊው (የጉሉኮሱ መርፌ የተደረገላትን እጇን አንስቶ አስተካክሎ እያስቀመጠላት።) ያብጥብሽና ያምሻል።…………” አኳኋኑ ትናንት አብሯት የነበረ፣ ሲያስታምማት የከረመ ፣ የምታውቀው፣ የቅርብ ወዳጇ ዓይነት እንጂ ዛሬ የሚያውቃት አይመስልም።

"አባቴ ነው።” አለ ፍትህ

ለወትሮው አዲስ ፊት የሚያስደነብራት እማዬ እንኳን እንደምታውቀው ሰው ሁሉ የሚጠይቃትን ጥያቄ ደስ እያላት ትመልስለታለች። እጇን፣ ፀጉሯን የለበሰችውን ጋቢ እያስተካከለ ነው የሚያወራው። "ምግብ መውሰድ ትችያለሽ? ምግብ ከወሰድሽ ስንት ሰዓት ሆነሽ? ምን ባመጣልሽ ደስ ብሎሽ ትቀምሻለሽ? ……… ”

(አንዳንድ ሰው ገጥሟችሁ አያውቅም? ሰውየውን ገና እንዳያችሁት ላትወዱት አትችሉም። አንዳንድ ሰው ደግሞ አለላችሁ ገና እንዳያችሁት አትወዱትም። ጥሩ እያደረገላችሁ እንኳን ይከብዳችኋል።ሰውየውን የከበበው ቫይብ ነው!! ወይ ይስባችኋል አልያም ይገፈትራችኋል።)

ፍትህን ሆስፒታል ከእማዬ ጋር እንዲቆይ እና እኔ አርፌ እንድመለስ የነገረን በማስፈቀድ ዓይነት አይደለም። ትዕዛዝም አይደለም። ብቻ ‘እንቢ’ የሚሉት ዓይነት አጠያየቅ አይደለም። የገረመኝ ግን የእማዬ ከፍትህ ጋር ለመቆየት በደስታ መስማማት ነው።

“ወዴት ነው የምንሄደው?” አልኩኝ በመኪናው እቤት ሊያደርሰኝ ተስማምተን መንገድ ከጀመርን በኋላ

"ወደቤት ነዋ!”

"መንገድ ስተዋል በዚህጋ ነው ቤቴ።”

"ውይይ ………አንቱ ብለሽ አግተለተልሽኝ እኮ።(ዝግንን እያለው) የምንሄደው እኛ ቤት ነው። አሁን እቤትሽ ባደርስሽም አታርፊም። ብትፈልጊም ትናንት የተፈጠረውን ረስተሽ ምንም እንዳልተፈጠረ ልትተኚ አትችዪም።”

"ኸረ እንደውም የማላውቀው አዲስ ቤት እንቅልፍ እሺ አይለኝም። እዛው እቤቴ ይሻለኛል።” ያልኩት ከምሬ ነው። በእርግጥ ቤቴም ብሄድ ሰውነቴን ባሳርፍ እንጂ እንቅልፍ እንደማይወስደኝ አውቃለሁ።

"እስቲ ግድ የለሽም። እንድረስና መተኛት ካቃተሽ ራሴው ቤትሽ አደርስሻለሁ።” ብሎኝ መንዳቱን ቀጠለ።

ክፉ እና ደግ እንዳለየች ህፃን ልጁ እጄን ይዞ እየመራኝ ሳሎን አስገባኝ። ጎኑ ስር ሲያቅፈኝ፣ አንዴ ግንባሬን ሌላ ጊዜ ፀጉሬን ሲስመኝ ፣ እጄን ሲይዘኝ… …… ለእሱ ብዙ ዘመን ሲያደርገው እንደኖረ ሁሉ የተለመደ አይነት ነው። እኔ ያልለመድኩት ነገር ስለመሆኑ ማወቁን እንጃ! ማወቅ መፈለጉንም እንጃ!! እቤቱ እንደገባሁ መብላት መፈለጌን አልጠየቀኝም።ለሰራተኛቸው ምግብ እንድታቀርብ እና ለእንቅልፍ እንደሚረዳኝ ነግሮኝ ወተትም አፍልታ እንድታመጣ አዘዛት። መታጠብ እፈልግ እንደሆነ አይደለም የጠየቀኝ። ውሃው ሙቅ ወይስ ቀዝቃዛ ቢሆን እንደምመርጥ እንጂ። በእያንዳንዱ እንቅስቃሴው ለዘመናት አብረን የኖርን አይነት እንዲሰማኝ ያደርገኛል። ከታጠብኩ በኋላ እንድለብስ የፍትህን ቢጃማ ሱሪና ቲሸርት መታጠቢያ ቤቱ መስቀያ ላይ ሲሰቅል ይደብረኝ እንደሆነ አልጠየቀኝም። ቢሰፋኝም የሱሪውን ወገብ በማሰሪያው አጥብቤ እንድለብሰው ነገረኝ እንጂ። ምግቡን በእጄ አላስነካኝም። እያጎረሰኝ መብላት ጀመርኩ። እየሆነ ያለው ሁሉ ግራ ገባኝ።

"ለምንድነው እንዲህ ጥሩ የሆንክልኝ? ወይስ ለሁሉም ሰው እንዲህ ነህ?” አልኩት

"ለማንም ሰው ቢሆን አዎን ጥሩ ለመሆን ነው የምሞክረው። ላንቺ ግን በተለየ ጥሩ ለመሆን እየሞከርኩ ነው።”

“ለምን? ለምን በተለየ?”
አልኩት የዘረጋልኝን ጉርሻ ከመጉረሴ በፊት.....

አሁንም አልጨረስንም ***

@wegoch
@wegoch
@paappii
ራሴው ማበዴ ነው ~6
(ሜሪ ፈለቀ)


"ምክንያቱም ልጄ ይወድሻል። አንቺ ትወጂዋለሽ ወይስ አትወጂውም ሌላ ነገር ነው። ይህን የማደርገውም push ላደርግሽ አይደለም።”

"ማን? ፍትህ? መውደድ ማለት? በፍቅር እያልከኝ አይደለምኣ?”

"ነው። እንደዛ እያልኩሽ ነው። ወተቱን ማጊበትና ይህቺን ጉረሺ።” ያጎረሰኝን አላምጬ ሳበቃ

"እስከማውቀው ድረስ ፍትህ እንደኔ አይነት ሴት ምርጫው አይደለችም። ደግሞ ይቅርታ አድርግልኝና በሴት ረገድ ልጅህ መረን ነው። በጣም ይቅርታ ግን!”

"አውቃለሁ። ስለልጄ የማላውቀው ነገር የለም። ፍትህ እናቱን ያጣው በ13 ዓመቱ ነው። እኔ ለስራ ሌላ ሀገር በሄድኩ ማታ እቤት ገብተው በዘረፉን ወንበዴዎች በሽጉጥ ነው የተገደለችው። (እስከአሁን ያላየሁበትን መከፋት ፊቱ ላይ አየሁ።) ስትመታና ስትወድቅ ስትሞትም ፍትህ እዛው ነበር። እያያት!! ለብዙ አመታት የእናቱ ሞት ሀዘን የተጫነው ምስኪን ልጅ ነበር። ተንከባክቤ አሳደግኩት ፤ ደስተኛ ያደርገዋል ብዬ ያሰብኩትን ሁሉ አደረግኩ ፤ የእናቱ መጉደል ፍፃሜውን እንዳያበላሽ ስለፈራሁ አቀበጥኩት። ነገር ግን ቆይቶ ሲገባኝ ልጄን ለድርጊቶቹ ሀላፊነት የማይወስድ ግድ የለሽ አደርጌ ነው ያሳደግኩት፤ መጎዳቱን ፍራቻ ሲያጠፋ እንኳን አምርሬ አልቆጣውም ነበር። ምንም ጎድሎበት አያውቅም።ያለው ሁሉ በጥረቱ ያገኘው አልነበረም እናም ዋጋ የሚያስከፍለው ምንም ነገር አይፈልግም። ጥሩ ትምህርት ቤት አስተምሬዋለሁ። አስጠኚ ቀጥሬ እንዲጎብዝ ጥሬያለሁ። ዩንቨርስቲ ገብቶ ተመርቆ ቢወጣም ስራ መስራት አይፈልግም። እኔን ላለማስከፋት ነው ስራ የሚሰራው። ከዛ ይልቅ ከሴትና ከመጠጥ ጋር ውሎ አዳሩ ቢሆን ደስተኛ ነው። ስለእውነት አሁንም ቢሆን ጨክኜ አምርሬ ልቆጣው ያሳሳኛል። ቁጭ አድርጌ እመክረዋለሁ። እናንተጋ መስራት ከጀመረ ቀን ጀምሮ ስለአንቺ ሳያወራልኝ አድሮ አያውቅም። ቆንጆ መሆንሽን፣ ደረቅ መሆንሽን፣ በስራሽ ጉብዝናሽን፣ ስቀሽ እንደማታውቂ…… ። ላለፋት ሁለት ሳምንት ግን ፍትህ ሌላ ሰው ነበር። በጊዜ ወደቤቱ ይገባና ሲጨቀጭቀኝ ያመሻል። ‘ምን ሆና ይሆን? አትወደኝም እኮ ቁምነገር የሌለው ዱርዬ ነው የምመስላት፣ ካስዬ ቆይ እሺ እንድታዋራኝ ከዚህ በላይ ምን ላድርግ?’ ሲለኝ ይመሻል። ትናንት ደውሎ የተፈጠረውን ነገረኝ። ልጄ በህይወቱ ስለምንም እንደዚህ ግድ ሰጥቶት አያውቅም።” የሚያወራልኝን እየሰማሁ የቀረበውን ምግብ በጉርሻ አገባድጄዋለሁ።

"በቃኝ በናትህ ብዙ በላሁ።”

"አንድ የመጨረሻ ይህቺን!”

የፍትህ መኝታ ቤት እንዳርፍ ተሰናዳልኝ። ድምፁ ዝግ ያለ ተመሳጮች ለተመስጦ የሚጠቀሙበትን የሚመስል የኮሪያ ክላሲካል ሙዚቃ ተከፍቶ ክፍሉ የሆነ የሚያባብል ድባብ አለው።
"በቃ ትንሽ አረፍ በይና እናትሽጋ እንሄዳለን። የምትፈልጊው ነገር አለ?”

“የለም። በጣም ነው የማመሰግነው።” አልኩት አልጋው ጫፍ ላይ እየተቀመጥኩ።

"እንደሱ ስትዪኝ ይከፋኛል። እቤቴ እኮ አስገባሁሽ ፤ በእጆቼ አጎረስኩሽ …… ከዚህ በላይ ቅርበት ምንድነው? እንደአባትሽ እይኝ።…… ” ይሄን ሲለኝ ከየት መጣ ያላልኩት የእንባዬ ጥርቅም በሳግ ታጅቦ ተንዠቀዠቀ።… … አጠገቤ መጥቶ በእጆቹ አጀብ ደረቱ ላይ አኖረኝ። አላባበለኝም። እንዳለቅስ ፈቀደልኝ።

"ንገሪኝ!” አለኝ ሲበርድልኝ ጠብቆ

"ምኑን?”

"ይሄ የዛሬ ወይ የትናንት ሀዘን የፈነቀለው ለቅሶ እንዳልሆነ አውቃለሁ። ንገሪኝ ሁሉንም!!”

እናቴ ከመሞቷ በፊት ልውልላት የምችለው አንድ ውለታ አባቴ እንዲያገኛት ማድረግ ነው። ቢያንስ የዘመናት ፍቅሯን እጁን ዳብሳ ደስተኛ ሆና ትሞታለች። እናቴን ማጣት ማሰብ አልፈልግም። የባሰው ደግሞ ስትለየኝ ማን መሆኔን እንኳን ሳታውቅ እብደቷ ተነስቶባት መሆኑን ማሰብ ያሳብደኛል። ያ እንዲሆን አልፈልግም። የቀራትን ጊዜ ጭንቅላቷ ልክ መሆን አለበት!! ውስጤ እንዲቀር የምፈልገው የእናቴ ምስል የምትፈራኝና የምትሸሸኝ ‘አንቺ ደግሞ ማነሽ?’ የምትለኝ እብዷ እናቴ ምስል አይደለም። ያቺ በለስላሳ እጆቿ ደባብሳኝ የማትረካዋ ፣ እሷ ያልኖረችውን የስነ ምግባር ኑሮ እንድኖር የምትመክረኝ፣ በሌላት ጡት ‘በጡቴ ይዤሻለሁ በቀል ከሀሳብሽ አይኑር።’ ብላ የምትለምነኝ፣ ልጄ ስስቴ የምትለኝ፣ አገላብጣ እየሳመች ‘አሳቃየሁሽ ልጄ’ እያለች የምትለማመጠኝ፣ ለእርሷ ስል መኖሬ የሚገባት(የሚያሳስባት) እናቴ… … እሷን እናቴን ነው በልቤ ይዣት መኖር የምፈልገው።

"እንደምንም ብዬ አባቴን ማናገር አለብኝ።” አልኩት ካሳሁንን ሳለቅስ ቆይቼ። ያልኩት ግርር እንደሚለው ያሰብኩት ባይገባውም የገባው ለመምሰል ሲሞክር ሳየው ነው።

"ግን ልታናግሪው አትፈልጊም?” አለኝ።

"ላገኘውም አልፈልግም። የእሱን እርዳታ መጠየቅ ደግሞ ያሳምመኛል። ለእማዬ ስል ግን አደርግላታለሁ። ለሷ ስል አደርግላታለሁ።” አልገባውም። በጥያቄ ሊያስጨንቀኝም አልፈለገም። ከእቅፉ ወጥቼ ጋደም እንዳልኩ ከየትኛው ሃሳቤ በኋላ እንቅልፍ እንደወሰደኝ አላውቅም።… ……

በሚቀጥሉት ቀናት የካሳሁንን እና የፍትህን እማዬ አጠገብ መሆን፣ ራሴን ካሳሁን እቅፍ ውስጥ ወይም የፍትህ አልጋ ላይ አልያም የፍትህ ቢጃማ ውስጥ ማግኘት፣ የፍትህን በቡናና በቁርስ ሰበብ የቢሮዬን በር መክፈት… የተለመድኳቸው ክስተቶች ሆኑ። የሚፈጥሩብኝን ስሜት ግን በደነዘዘ ልቤ መረዳት አልቻልኩም።

ከሳምንት በኋላ አራታችንም(እኔ እና የስራ አጋሮቼ ፀሃፊያችንን ወይኗን ጨምሮ) ቢሮ ተሰበሰብን እና ለተወሰነ ጊዜ ስራ ላቆም መሆኑን ስነግራቸው በድንጋጤ አፈጠጡብኝ።

"ለምን? ቆይ እስከመቼ? ምን ተፈጥሮ ነው?” ጌትነት ነው የሚጠይቀኝ።

"እስከመቼ እንደሆነ አላውቅም ጌትሽ! ከቤተሰብ ጋር በተያያዘ ምክንያት ነው። መቼ እንደሆነ ባላውቅም ቃል እገባልሃለሁ ወደ ስራዬ እመለሳለሁ። እስከዛ ድረስ እጄ ላይ ያሉትን እንድትሰራልኝ ፈልጋለሁ።”

"ስራ ማቆሙ አስፈላጊ ነው? ራሁ please ፍቀጂልኝ እኔ ልርዳሽ? በምትፈልጊው ሁሉ እኔና ካስዬ ከጎንሽ ነን።” አለኝ ፍትህ ሌሎቹ ሲወጡ ጠብቆ።

"ፍትህ ልትረዳኝ ትፈልጋለህ?” አልኩት (ቁልምጫው ልቤን ቢሰርቀውም ባልሰማ አለፍኩት)

"Whatever it is.”

"መልካም! ብዙ ትግል እና ትእግስት የሚጠይቅ ስራ እጄ ላይ አለ። ሙሉ ሰዓትና አቅም ይፈልጋል።አሁን በሙሉ አቅሜ ልሰራ አልችልም። አስቸጋሪ ቢሆንም ይሄን ኬዝ አንተ እንድትይዝልኝ እፈልጋለሁ።”

" ራሁ እኔ ያንቺን ያህል ጎበዝ አይደለሁም። ……”

“ሁና! ጎበዝ ሁን! ጉብዝና ተፈጥሮ አይደለም። ጎበዝ ለመሆን ትለፋለህ እንጂ ጉብዝና ድንገት ጉብ የሚልብህ መንፈስ አይደለም። እኔን መርዳት ትፈልጋለህ? ይኸው……(መረጃ የያዘ ፍላሽ ጠረጴዛው ላይ አስቀመጥኩለት)… አሁን እማዬጋ መሄዴ ነው። እየውና ስትወስን ደውልልኝ… ” ብዬው ወጣሁ።

"እሺ ላድርስሽ?”

"Am ok መንዳት እችላለሁ።”

እማዬጋ ስደርስ ካሳሁን ከእማዬ ክፍል አቅራቢያ ውጪ ተቀምጧል።

"አባትሽ ውስጥ ነው። ብቻቸውን ይሁኑ ብዬ ነው።” አለኝ ቀለል አድርጎ። ለመግባት ስፈጥን እጄን ይዞኝ። "ምንም አትሆንም እንደውም ደስተኛ ናት። ተያቸው።” አለኝ።

"ደስ የማይል ነገር ቢናገራትስ? የሆነ ነገር ብትሆን……” እጄን አስለቅቄው ገባሁ። መግባቴን ያየችው እሷ ብቻ ናት። እሱ (አባቴ) ከግርጌዋ ተንበርክኮ ሁለት እግሮቿን አቅፎ ያለቅሳል። እየሆነ ያለው ሁሉ ግርር አለኝ…… ከተቋሰሉት መቋሰል በላይ እንደምትወደው የሷን አውቃለሁ። የእሱ ግን… …

‘ገዳይሽ እኔ ነኝ ማሪኝ ፤ ያንቺን ስቃይ ለኔ
ያድርገው፤ ባንቺ ቦታ ልሰቃይልሽ……’ ይላታል። ያቀፋቸውን እግሮቿን ይስማል። ‘ማሪኝ እማ እኔው ነኝ በሽታሽ። ለምን አልነገርሽኝም? ለምን ሀጢያቴን አበዛሽው?’ እንባው እግሮቿን ያርሳቸዋል። እሷን አየኋት። እንባዋ ወደጆሮዎቿ ሲወርዱ ስትጠርጋቸው አየኋት።

* አሁንም አልጨረስንምኣ?******

@wegoch
@wegoch
@paappii
2024/09/24 09:21:07
Back to Top
HTML Embed Code: