Telegram Web Link
#ወግ_ብቻ
.
እ ግ ር በ እ ግ ር
አሌክስ አብርሃም

ክፍል - ፩ -

አንድ ቀን ሰይጣን በመንደሩ ወደሚፈሩትና ወደሚከበሩት አስር አለቃ ደባልቄ ግዛው ቤት ሄደና ተቀዳሚም ተከታይም ሳያደርግ፣ "ደባልቄ!!" ብሎ በስማቸው ጠራቸው።

አስር አለቃ ፊታቸውን በቁጣና በግርምት አኮማትረው ድምፁን ወደሰሙበት ዞር ቢሉ በአካባቢው ሰው የሚባል የለም። እዚህ ሰፈር አንድም ሰው የአስር አለቅነት ማዕረጋቸውን ሳያስቀድም፣ የአባታቸውን ስም ሳያስከትል እንዲህ ንፋስ እንዳነሳው ፌስታል ስማቸውን ለብቻው አንጠልጥሎ የሚያነሳ ሰው የለም። እንኳን ሰው የዚህ ሰፈር ሰይጣን ቢሆን ራሱ እንደዚህ አስር አለቃን አቃሎ እና አበሻቅጦ ይጠራቸዋል ተብሎ አይታሰብም። እንዴት ሆኖ! ምን ሲደረግ...!

እንግዲህ አስር አለቃ የተጣሉ ባልና ሚስት አስታርቀው ገና መመለሳቸው ነበር። ልክ በራቸው ላይ ሲደርሱ ነው ሰይጣን የጠራቸው። ምን ይጠራቸዋል፣ ያዋረዳቸው እንጂ! ቢሆንም 'ጆሮዬ ነው' ብለው ወደ ቤታቸው ግቢ ሊገቡ ርምጃ ሲጀምሩ፣

"አንተ ደባልቄ! የሚደባልቅ ይደባልቅህ! ሲጠሩህ አትሰማም!? ደንቆሮ!!" ብሏቸው እርፍ። በዚህ ቢበቃማ ጥሩ ነበር፣
"ምን ያሯሩጥኻል? ያች መንሽ እግር ሚስትህ እንደሆነች የትም አትሄድብህ፤ ተወዝፋ ነው የምትጠብቅህ" ሲል ዘለፋቸው።
አስር አለቃ መጀመሪያ በተናጋሪው ድፍረት ግርርርርርርርርርርም አላቸው፤ ቀጥሎ የንግግሩ ትርጉም አዕምሯቸው ውስጥ ሲተረጎም ደማቸው ፈላ። ላለፉት አርባ ዓመታት እንዲህ ተንቀውም፣ እንዲህ ደማቸው ፈልቶም አያውቅም። ከዘራቸውን ጠበቅ አድርገው ጨበጡና ድምፁን ወደሰሙበት ፎክረው ዞሩ።

"ያንበሳው ግልገል!" በአካባቢው የሰው ዘር የለም!!
"እንኳን ፊቴ ያላገኘሁት፤ ደመ-ከልብ አድርጌው ዘብጥያ መውረዴ ነበር።" አሉና ከዘራቸውን ወደ ግራ እጃቸው አጋብተው ከዘራ በያዙበት እጃቸው አማተቡ።

"ሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂ ... " የሰይጣን የሚያበሳጭ እና የሚሰቀጥጥ ሳቅ ጆሯቸው ስር ተቅጨለጨለ...

"ድሮም ከእግዜራችሁ በፊት ዱላችሁ ነው ትዝ የሚላችሁ... ነውጠኛ ሁሉ፤... የምትዠልጠው ስታጣ ታማትባለህ? አይ ሸፋፋው አስር አለቃ ... ሂሂሂሂሂ ሁሁሁሁ ቂቂቂቂቂቂ..." አለ ሰይጣን ቀድሟቸው ግቢያቸው ውስጥ ገብቶ ከጀርባቸው ከቆመ በኋላ። አስር አለቃ ግራ ተጋቡ። ንዴታቸውን ዋጥ አድርገው እየተጣደፉ በቁጣ ወደቤታቸው በር ገሰገሱ።
. . . . .
( ይቀጥላል
@wegoch
@wegoch
#ወግ_ብቻ
.
እ ግ ር በ እ ግ ር
.
ክፍል - ፪ -
.
አሌክስ አብርሃም
. . .
አስር አለቃ አቋማቸው እንደ ሰምበሌጥ ቀጥ ያለ ስፖርተኛ አቋም ነው፤ ሰው ሁሉ "አቤት ቁመና!!" ይላቸዋል። ሰይጣን ግን ወደ ቤታቸው ሲጣደፉ በሚያበሽቅ ንግግር፣
"ሸፋፋ ... ሸፈፍ ሸፈፍ ትላለህ! ሲራመዱ አይተህ... ደግሞ ወታደር ነኝ ይላል እንዴ? ይሄን ደጋን የመሰለ እግር ይዞ...፣ ሂሂሂሂሂሂሂ... እንኳን አገር ልትጠብቅ፣ በዚህ ሸፋፋ እግርህ ሚስትህንም አትጠብቅ፤... ተመልከት የእግርህን ክፍተት፤ በልጅነትህ ፀሐይ አላሞቀችህም ያች ጨብራራ እናትህ!! ኪኪኪኪኪኪ..."
አስር አለቃ ከሳቸው አልፎ እናታቸውን ማዋረዱ ቢያንገበግባቸውም የተናጋሪው ማንነት ስለገባቸው እንደገና አማተቡና፣

"የማርያምን ብቅል ፈጭቻለሁ! ቱ! ቱ! አንተ ፖለቲከኛ ሰይጣን!" ብለው አንዴ ወደ መሬት፣ አንዴ ወደ ሰማይ ትፍ! ትፍ! ቀጠል አድርገውም፣ "አንተ ክፉ አውቄኻለሁ፤ እንዲህ አቅልሎ የሚጠራኝ እንዳንተ ያለው ቀላል እንጂ ሌላ እንደማይሆን መች አጣሁት?" ካሉ በኋላ፣ ቆይ ላግኝህ በሚመስል ዛቻ ከዘራቸውን ነቀነቁና ነጠቅ ነጠቅ ብለው በመራመድ ወደ ቤታቸው ገቡ።

ሰይጣንም አጀንዳውን ከፍቶ፣ "አስር አለቃ ደባልቄ" በሚለው ፊት ለፊት በቀይ እስክርቢቶ 'ራይት' አደረገ። መንገዱንም ቀጠለ! እየሳቀ እና እያፏጨ...!
"ይሄ ሸፋፋ ለዛሬ ይበቃዋል ሲበሳጭ ይደር። ነገ ደሞ በተመቸኝ ሰዓት ብቅ ብዬ ነጅሸው እሄዳለሁ።" አለና እየሳቀ መንገዱን ቀጠለ። ከአስር አለቃ ቤት ግራና ቀኝ ባሉት ጫት ቤቶች ታኮልኩለው ጫት የሚቅሙትን ወጣቶች በኩራት እየተመለከተ፣
"ርስቴ እየተስፋፋ ነው!" ብሎ እየኮራ ቁልቁል ወደ ወንዙ!

፨ ፨ ፨

በእርግጥም ሰይጣን እንዳሰበው አስር አለቃ ሌሊቱን እንቅልፍ በዓይናቸው ሳይዞር ነበር ያደረው። እንደዛ ያበሻቀጣቸው ሰይጣን ነው ለማለት ጥርጣሬ ገባቸው፣
"እኔ የትኛው ቅድስና ኖሮኝ ሊፈትነኝ ይመጣል?" አሉ ለራሳቸው። እንደውም አንዱ ጎረቤታቸው ተደብቆ እንደሰደባቸው ጠረጠሩ። "ማን ሊሆን ይችላል?" ሌሊቱን ሙሉ ተብሰለሰሉ።

"ይች ጎረቤቴ የትነበርሽ ትሆን እንዴ? የለም ድምፁ የወንድ ነው። ግንበኛው አሰፋ መሆን አለበት፤ እሱ ለካ ለሥራ ክፍለ ሀገር ከሄደ ሁለት ወሩ፣ ...እና ማናባቱ ነው...።" ወደ ንጋቱ ላይ አንድ ሐሳብ ብልጭ አለላቸው። አረጋ!! ድንበር እየገፋ የበጠበጣቸው ጎረቤታቸው! አረጋ! ኧረ እሱስ ሚስታቸውንም በምኞት ዓይኑ የሚቃኝ ጥጋበኛ ነው፤ ድምፁም መጣላቸው፤ ራሱ ነው!

"አገኘሁት" ብለው ዘለው ከአልጋቸው ተነሱ።
. . . . .
(ይቀጥላል)
@wegoch
@wegoch
@wegoch
👆👆👆👆
አጭር፣አስተማሪና አዝናኝ ወግ ናት።

ምንጭ
ደራሲ አሌክስ አብርሀም
ከ "ዙቤይዳ " መፅሐፍ
ገፅ 201 የተወሰደ
ርዕስ ፡-"እግር በእግር"
ተራኪ፡-ስንታየሁ አዲሱ ሳንታ

(@san2w)
10/5/2011 Woldia Yniversity

@wegoch
@wegoch
አውራጅ
(ቡሩክ ካሳሁን)
ጥንት…ከጥቂት አመታት በፊት አያቶቻችን ከገበያ እቃ ጠልጠል አድርገው ሲመጡ ተሯሩጦ ተቀብሎ መመረቅ ወግ ነበር፡፡ እንደው ከበድ ያለ እቃ ገዝተው አልያም ቤት ቀይረው ከሆነ ተባብሮ አግዞ “እቺን ያዙ” (ያው ለወጉ ነው) ሲባል ኸረ ግዴለም ተብሎ፤ ውስጥ እየፈለገም ቢሆን በአፍ ተፎጋግሮ፤ “በቃ እንደዚያ ከሆነ ቤት ያፈራውን ቅመሱ” ብለው እቤት አስገብተው ጋብዘው መሸኘት ልማድ ነበር፡፡ ‹‹ነበር ለካ እንደዚ ቅርብ ነው›› አሉ፤ አሉ የአባይ ግድብን በ5 ዓመት እንጨርሰዋለን ብላቹ ነበር ተብለው ከ7 አመት በኋላ የተጠየቁት የሜቴክ ሹማምንት፡፡ ወደቀደመው ነገራችን ስንመለስ ያ ወግ ልማዳችን ሞቷል ብቻ ሳይሆን ግብዓተ መሬቱ ራሱ የት እንደተፈፀመ እንኳን ያየ ሰማሁ የሚል ሰው በከተማው(አ.አ) የለም፡፡ የኔ ጌታ ዘንድሮ ሶፋ ገዝቼ እቤቴ አስገባለው፤ እንደው ቁምሳጥን ነገር ብገዛ ብለህ ካሰብክ “ብሰርቅ” ብሎ እንዳሰበ ሰው በሌሊት ወጥተህ፣ በሌሊት ገዝተህ፣ በሌሊት ማስገባት ይኖርብሀል፡፡ እንቢ ብለህ ቀይ መስመሯን አልፈህ በቀን ገዝተህ የመጣህ እንደሆነ ግን 3ሺ ብር ለገዛኸው ቁምሳጥ 4ሺ ብር ማውረጃ ተጠይቀህ፤ ልብስ አስቀምጥበታለው ያልከው ሳጥን ደም ግፊትህ ገንፍሎ መቀበሪያህ ነው የሚሆንልህ፡፡ ችግሩ ደግሞ እጅግ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደደረሰ የምታውቀው፤ ሰፈር ውስጥ በስራ እጦት ተስፋ የቆረጡ ወጠምሾች መጥተው ለሚተምኑልህ ዋጋ ድርድሩን በዲፐሎማሲያዊ መንገድ ለማድረግ ‹‹ወገን እስኪ መጀመሪያ 30 ፑሽ አፕ እንወረድና ነገሩን በተረጋጋ ህሊና እንመርምረው›› ስትላቸው ‹በል ተነስ እዛው ወገብህን ረግጬህ ተሳቢ እንስሳ እንዳላረግህ› ብሎ አንዱ ያፈጥብሀል፡፡ የነገሩን አዝማሚያ አይተህ ‹‹ሀቅ ነው! የእናንተ ጉልበት 4ሺ ያወጣል ግን የኔ ቁምሳጥን 3ሺ ብቻ ስለሚያወጣ እኔው እራሴ ቁምሳጥኔን አስገባለው›› ብለህ አስታራቂ ሀሳብ ብታቀርብ ያቀረብከው አስታራቂ ሀሳብ እነሱ ጆሮ ጋር ሲደርስ አተናናቂ ይሆንና 32 እጆች በድንገት አንገትህ ላይ ሲያርፉ የአንዱ እጅ የአንዱን ጣት ይሰብርና ዋጋውን አስተካክለው 14ሺ ብር እንዳይጠይቁህ ፈርተህ ‹‹በቃ ዋጋ አስተካክሉልኝ ሚስቴ እርጉዝ ናት›› ስትላቸው ‹በእውነት?› ብለው ሲጠይቁህ፤ ሊምሩኝ ነው ብለህ ሰፍ ብለህ ‹‹በእወነት..ገብርኤልን…ሚካኤል…›› እያልክ መሀላ ስትደረድር ‹እና የታለች› ይልሀል አንዱ፤ ቀልጠፍ ብለህ አንተም ‹ያው መኪና ውስጥ ናት› ስትላቸው ‹በቃ እሷንም እኛ ነን ምናወርዳት፤ እሷን በአስተያየት 2ሺ እናወርድልሀለን› ብለውህ ደም ግፊትና ደም ማነስ በእኩል ሰዓት ታስተናግዳለህ፡፡ በጣም በጣም ሚያሳዝነው ደግሞ ፀጥታ እና ሰላም እንዲያስጠብቁ ሀላፊነት ያለባቸው የመንግስ አካላት ለዚህ አይነት ጋጠወጥነት መፍትሄ መስጠት አለመቻላቸው ነው፡፡ ‹‹እንዴዴዴ… መንግስት ባለበት ሀገር በጠራራ ፀሀይ ማጅራታችንን እንመታ እንዴ…›› እያልክ እየጦፍክ ፖሊስ ጣቢያ ሄደህ ለአንዱ ፖሊስ ስትነግረው፤ ‹ቆይ ስንት ብለውህ ነው?› ሲል ይጠይቅሀል ‹‹አይገርምህም 4ሺ አላሉኝም መሰለህ›› ስትለው ‹የኔ ጌታ እታች ሰፈር 6ሺ ነው ሚያወርዱት እነሱም መጥተው ተደምረው 10ሺ ብር ሳይጠይቁህ ቶሎ አስወርድ ሂድና› ብሎ የምክር አገልግሎት ይሰጥሀል፡፡ ‹‹እንደዚማ አይደረግም ለበላይ ክፍል አመለክታለው›› ብለህ ከቢሮው ተንደርድረህ ልትወጣ ስትል ‹ወዳጄ እንኳን አንተ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር ከቤተመንግስት ወጥተው ቤት ሲቀይሩ ለማን አቤት እንደሚሉ ቸግሯቸው በ8ሺ ደሞዛቸው 10ሺ ከፍለው ነው እቃቸውን በሰፈሩ ልጆች ያስወረዱት፤ እና አንተ ማነኝ ነው ምትው?› ብሎ የማንነት ጥያቄ ይጠይቅሀል፡፡ ነገሩ ወደ ብሄር ግጭት እያደገ መሄዱን ስትረዳ እቃህን በ4ሺ ብር አስወርደህ የሻይ ትልና 5ሺ ብር ሰጥህ ‹ታዲያ የሻይ ማሽን ግዙበት› ብለህ እንደ አቅሚቲ ኮምከህ ወጠምሾቹን በተቻለ ፍጥነት ከበርህ ላይ ድራሻቸውን ታጠፋዋለህ፡፡
“እኔ እንደውም ማጋነን ስለማልወድ ነው እንጂ…” ብለው እንደሚያጋንኑ ሰዎች የሀሳቤን መጠቅለያ በዚህ ሀረግ ባልጀምርም ይህ አይነቱ ተግባር ግን በተለይ አሁን አሁን እጅግ በጣም እየተበራከተ ስለመጣ መንግስት 4ኪሎ ቤተ መንግስት ገብተው “እኛ ነን የምናወርደው” እስኪሉት ድረስ መጠበቅ ያለበት አይመስለኝ፡፡ መንግስት ሆይ! 4ኪሎ ቤተ-መንግስት ከገቡ ደግሞ በጣም ብዙ የሚወርድ ነገር ስላለ በጊዜ ከሰፈር ብታስታግሳቸው መልካም ነው!!!

ነሀሴ 2011 ዓ.ም


😉      @wegoch
👕👉 @wegoch
👖      @burukassahunc
Forwarded from ግጥም ብቻ 📘 (ልዑል)
ሰርጂካል ማስክ

500 እና ከዛ በላይ ለሚገዛ የአንዱ ዋጋ 11 ብር

250ዉን(5ፓክ) ለሚገዛ የአንዱ ዋጋ 13 ብር

150ውን (እስከ 3ፓክ) የአንዱ ዋጋ 15 ብር

ለመግዛት በ +251901927999 ይደውሉ

🛑ብዛት እስከሚፈልጉት ማዘዝ ይቻላል
አድምጡ ለቅዳሚታችኹ
መፅሐፍም ላስተዋውቃችኹ


@Wegoch
@Wegoch
@Wegoch
#የሰኔ መቅሰፍቶች

  ክፍል - ፮

የትናቷ ጨረቃ ከሰማዩ ብጠፋም ከቤተሰቡ አእምሮ ላይ ልጠፋ አልቻለችም ለሀገሩ ነግቷል ለቤተሰቡ ግን ክፉኛ ጨልሟል ከዛሬዋ ጠዋት ጀምሮ ቤተሰቡ አንድ ነገር ይጠባበቃል
ዘንድሮ ከቤተሰቡ አልፎ ለሀገሩም ጭንቅ ነው ሰኔ ሰኞ ሲባል ሁሌም ክፉ እንደሚሆን የሀገሬው ሰው ያውቃል
ይህን የሰኔ ወር ቤተሰቡ ብቻውን አይተክዝም ሀገሬው አብሮ ስለሚጨነቅ ሰኔ ለዚህ ቤተሰብ የምጥ ወር ነው በዘንድሮው ደሞ ችግሩን ሚካፈለው ብዙ ቤተሰብ አግኝቷል
ህፃናቱ በወላጆቻቸው መተከዝ እነሱም ተክዘዋል ዝምታው ይባላል
ወሩን ይወቁ እንጂ ሚመጣባቸውን ነገር አያውቁትም እንቅልፍ የለ ተፋጦ ማደር ሚመገቡትን ምግብ አያምኑትም በእርግማኑ ምክንያት በትንታ ሊሞቱ እንደሚችሉ ያስባሉ
የትናንቷ ጨረቃ ደም ለብሳ በመታየቷ የቤተሰቡን ትንሽ ደስታ ደም አልብሳዋለች
ህፃናቱ ሞክረው ሞክረው አሁን እርስ በራሳቸው ደስታ የሌለበት ጨዋታ ይዘዋል
በሚያዝን አንጀታቸው ለቤተሰቡ እራርተዋል ለምን እንዲህ እንደሆኑ ባይገባቸው
አባዬ እማዬ እናቴ የኔ አባት አቤት በሌለው አቤት ውስጥ ያዘነ ፊቶቻቸውን ይሰዱላቸዋል
ምን ሆንሽ እናቴ ምን ሆነሀል አባቴ ምንም በሚለው መልስ ውስጥ ሞትን መጋፈጥ ፈርተው
ፊንሀስ ምን አለ ጨረቃን ባላያት አይቼስ ባልነግራቸው ኖሮ እያለ ይብሰለሰላል በትንሹም ቢሆን ለቤተሰቡ መልሶት የነበረው ደስታ በሱ በሪሱ ምክንያት ሲንደው ሲያይ በጣም አዘነ
ምንም ቢል ሲያሞግሳት በነበረችው ጨረቃ ምክንያት የቤተሰቡ ደስታ በመጥፋቱ ከእንግዲህ በተስፋ የተሞሉ ቃላትን ለቤተሰቡ ቢያወራ ሰሚ እንደማያገኝ አውቆታል
ተከፍቷል ትኩረቱን ከህፃናቱ ቢያረገም አብሯቸው እያለ በሀሰብ መንጎዱን ተያይዞታል እያለ እንደ ሌለ ሲሆን ህፃናቱም ተከፍተዋል
ፊያሜታም በፊንሀስ እቅፍ ውስጥ መዋል ጀምራለች ፍርሀቷ አይሎ ባጣው ወይስ ቢያጣኝ እያለች ትብሰለሰላለች
ተስፋ ሚያስቆርጡ አስተያየቶችን እያየችው ሆዱን ታባባዋለች
ፊንሀስ መቅሰፍቱን ባያጠፋ እንኳ ይሄን ስሜት እንዴት ሊያጠፋ እንደሚችል ያሰላስላል ሞትን መፍራት በሕይወትህ ደስታ እንዳታገኝ እንቅፋት ይሆንብሃል ዕብራውያን 2:15 ብሎ ያነበበውን እያስታወሰ ነገሩ በሙሉ ዞሮበታል ህይወት ህይወት የሆነው በሞት እንደሆነ ስለሚያስብ እሱ ሞትን አይፈራም ይልቁንስ አጠገቡ ያሉትን በሞት ሲነጠቅ ነው ህይወት ለእሱ ትርጉም አልባ ምትሆነው
ቤተሰቡ አሁንም በሀሳብ እያለቀ ነው

ይቀጥላል...
 ብላቴናው በእርግማን ገፆች ላይ

@wegoch
@wegoch
@wegoch
አመፅ!!
(በእውቀቱ ስዩም)
በለው! በለው! ዛሬ ታሪክ ተሰራ! ከተማውን ባንድ እግሩ አቆምነው!!
“ሽጉጥ መትረይሱን አንግቶታል
ያ ጥቁር ግስላ ደም ሽቶታል”
የሚለውን የአለማየሁ እሼቴን ዘፈን በአለማየሁ ፋንታ ድምፅ እያንጎራጎርሁ ከቤቴ ወጣሁ ፤ ፓርኩ ላይ ስደርስ አንዲት ደርባባ ኤሽያዊት ሰልፈኛ ተዋወቅሁ፤
ከኢትዮጵያ እንደሆንኩ ስነግራት አይኗ በደስታና ባድናቆት ብዛት ተጨፈነ ፤ባጠቃላይ ፊቷ ግንባር ሆነ ፤
“ እኔ ከደቡብ ኮርያ ነኝ “
“ አያቴ ስለ አገርሽ ብዙ ይነግረኝ ነበር ፤ በነገርሽ ላይ አያቴ እናንተ አገር ዘምተው ከነበሩት ዘማቾች አንዱ ነው ” ብየ ቀደድኩ፤
“የምርህን ነው?”
“ አያቴ ይሙት”
‘ ኦ ማይ ጋድ ! “ ልትጠመጠምብኝ እጆቿን ዘርግታ ስትንደረደር ገለል አልኩ፤ ከፊት ለፊቷ ከቆመው ዘንባባ ላይ ተጠመጠመች፤
“ ዛሬ በተቃውሞ ላይ ለመሳተፍ መወሰንህ ያያትህን ጀግንነት መውረስህን ያሳያል” አለችኝ::
“ነው ብለሽ ነው?” አልኩና እየተሽኮረመምሁ ወደ ለበሰቺው ቁምጣ ተመለከትኩ::
እሷ በቁምጣ እኔ በቁጣ ተሞልተን መራመድ ጀመርን!! የኦሃዮን ወንዝ የሚያሻግረውን ብጫ ድልድይ አልፈን ዳውንታውን የሚያስገባ አውራ ጎዳና ላይ ስንደርስ የተቆጣው ሰልፈኛ ቁጥር እየጨመረ ሄደ ፤ ጥቁር፤ ነጭ፤ ላቲኖ ኤሽያ የቀረ የለም፤ ዳውንታውን ስንደርስ የቤት መዝጊያ የሚያካክል የመስታወት ጋሻ የያዙ ፖሊሶች ተሰልፈው ጠበቁን ፤ ካጠገባቸው ፤ አድማ በታኝ መኪና ፤ ብረት ለበስ መኪና ፤ ታንክ እና ያየር መቃወሚያ ሳይቀር ያየሁ መስሎኛል፤ ሰልፉ በሰላም እየተካሄደ እያለ አንድ የተረገመ ጎረምሳ ጋዝ የተሞላ የሄኒከን የቢራ ጠርሙስ ወደ ፕሊሶች ወረወረ! (ሄኒከን ቢራ የሚቀጥለውን ፅሁፌን ስፖንሰር እንደሚያደርግ ተስፋ አደርጋለሁ )፤
ወድያው ከፊት ያለው ፖሊስ ሰልፈኛውን የፕላስቲክ ጥይት ተኩሶ ጠነበሰው ’፤ አየሩ በስጋትና በቁጣ ተሞላ፤፤ ji young ( የኮሪያይቱ ስም ነው) መፈክሯን አንከርፍፋ አይን አይኔን ታየኛለች፤
“ ጥግሽን ይዘሽ ጠብቂኝ “ አልኩና ጃኬቴን አውልቄ አቀበልኳት
“በጨበጣ ልትገጥማቸው ባልሆነ” አለችኝ ባድናቆት ጮሃ ::
“ በጨበጣ ካልሆነማ በርቀት በፕላስቲክ ጥይት ለቅመው ይጨርሱናል” ስል መለስኩላት፤
“ ስማኝ ሃኒ “ አለችኝ “ በጣም ከተጠጋኻቸው pepper spray ይረጩሀል አለቺኝ”
“ አታስቢ ! በርበሬ ስታጠን ስላደግሁ ችግር የለም፤ “
ወደ ፖሊሶች መራመድ ጀመርኩ፤ ተቃዋሚው ሰልፈኛ ፀጥ አለ! ፖሊሶች አይናቸውን ማመን አልቻሉም፤ ቶሎ ብለው አንድ ቁና ጭስ ለቀቁብኝ፤ በልጅነቴ፤ የጎረቤታችን ጠላ ሻጭ ሴትዮ የጠላ ቂጣ ሲጋግሩ ያለ ፍላጎታችን ጭስ ሲያካፍሉን ስለኖሩ አይኔ ለምዶታል ፤ እንዲያውም ቤት ውስጥ መለስተኛ ጭስ ከሌለ አይኔ በቅጡ አያይልኝም፤
ፖሊሶች ሁለተኛ ዙር ጭስ ለቀቁብኝ ፤ ይሄኛው ጭስ አፕል ፍሌቨር እንዳለው ልብ አልኩ!
ከፊት ለፊት ከቆመው ፖሊስ ልደርስ ሁለት ጫማ ሲቀረኝ ስልኬን አውጥቼ ፎቶ አነሳሁት፤
ከጥቂት ደቂቃ በሁዋላ ወደ ነበርኩበት ተመልሼ ስቆም::
“ ለመሆኑ አያትህ ኮርያ የዘመቱት በምን ዘርፍ ነበር ?” አለቺን ጂ ያንግ !
“ በጋዜጠኝነት”

@wegoch
@wegoch
ጓዶች በምሽጋችሁ ሆናችሁ ስለሰዓት ሽግሽጉ አድምጡ!

ወደ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ደወልን እንዲህም አልናቸው

<< አብዮተኞች መታገስ አልቻሉም ቶሎ አፍጥኑትና ፕሮግራማችን ይተላለፍ ፡ አለበለዚያ ሽምቅ ተዋጊ ገጣምያን የሰላ ብዕራቸውን ያነሳሉ በቃላት ወጋ ወጋ ማረጋቸውም አይቀርም >>

እነሱም << መቼስ አብዮቱ ካዘዘ የማይሆንለት የለም ብለው ዛሬ ምሽት 2:30 አይናችሁን ETV መዝናኛ ላይ አርጉ>> ብለውናል

እናመሰግናለን!!!

ከሁሉ የናፈቀኝ እኔና ጋዜጠኛዋ የተወዛወዝናትን ነገር

ሚካኤል አስጨናቂ ሳኒታይዘር አረጋለሁ ብሎ ሲነሳ ሆዱ አከባቢ ያለችዋ ቁልፍ ተስፈንጥራ ስለመወደቋ

#ማየት ! 2:30 እንገናኝ ETV መዝናኛ

አብዮተኞች ብትችሉ ይቺን ፎቶ እየወሰዳችሁ ራሳችሁ ጋር አስተዋውቁ፡፡

@wegoch
@wegoch
@wegoch
#ወንዶቹን ምን ነካቸው?
<<ሚካኤል አስጨናቂ>>
የሆቴሉ በረንዳ ላይ ያለን የአዳም ዘሮች ሁሉ ፊታችን በጀርባችን አቅጣጫ እስኪደርስ ድረስ ተሽከረከርን :)
ድምቅ ያለው ጨዋታ ከየት መጣ ባልተባለ ምትሀታዊ ውበት ረጭ አለ !
ለካ የሴት ልጅ ውበት ጥይት ነው አልኩኝ።
አማፂ ተሰብስቦ እየወከበ ሳለ ድብልቅ ብሎ እንደጮኸ ጥይት ከየት መጣ ያልተባለ ፀጥታን አጥለቅልቃን ሄደች።
እሷ መታጠፊያው ዘንድ እስክትደርስ ድረስ ከልጅ አባቶች ጀምሮ እስከኛ አፍላ ወጣቶቹ ድረስ ትንፍሽ ያለ የለም።
የቤታቸው ሸለቆ ጋር ደርሳ እጥፍ ስትል ።
"ፓ !" አለ አቡሻ እየተቅበዘበዘ.. .
እውነትም ፓ !
ፓ ዳሌ ...ፓ ጠጉር ...ፓ የእግር ጣት ...ፓ ፈገግታ ።
ወንዶች ላይ መዓት ወረደብን....መብረቅ ተላከብን...ወጀብ አንገላታን ...ማዕበል ናጠን....የሁላችንም ምናብ በዝሙት ጦር ተወጋ ።
ይህች ሴት ማናት ?
ዳዊት ማብራራቱን ያዘው....ይህችን ልጅ እንዴት እስከዛሬ አታውቋትም? የእትዬ ዓለም ልጅ እኮ ነች...ቂጥ የዘራቸው ነው...ቤቱ እንዳለ በቂጥ ደኖች የተሞላ ነው አለን ...
መስፍኔ ቀጠለ ..."ይህችን ሴት ማን ወንድ ደፍሮ ይናገራታል? ባለ መኪና ነሽ...ባለ ህንፃ ነሽ...ባለ ድርጅት ነሽ ሁሉ ይፈሯታል....ውበቷን ይፈሩታል....ሁሉም ይመኟታል አንዳቸውም አይጠይቋትም" አለ..
እውነት ነው !
ልጅቷን እኔም የመጀመርያ ጊዜ ሳያት
"ይህች ልጅ ታውቃታለህ?" የሚል ቃል ከአንደበቴ እንዴት እንዳመለጠኝ አላውቅም...
ያኔ በግዜው አጠገቤ ተቀምጦ የነበረው ስምረት.. .
"ተው ! ተው ! ይሄ እቃ ገራሚ ባሉካ አለው። ባሉካው አሜሪካ ነው ያለው...ቀላል ገንዘብ አይበጭቅም አልኩህ...በቀን ብቻ ሶስት ጊዜ ነው ልብሷን የምትቀይረው" ብሎ ሙቁ ስሜቴ ላይ በረዶውን ወረወረ ።
ዝም አልኩኝ...ከዛ ቀን በኋላ ዛሬ ያቺን ሴት ደግሜ እስካያት ዘንግቻት ሰንብቻለሁ ....
ይህን ጊዜ ታድያ የሁሉንም አዳም ሀሳብና ግምት በፅሞና ሲከታተል የነበረው ፍቅሩ ይግረማቸው ብሎ እስካሁን አምቆት የነበረው ጉድን አፈነዳው።
"ልጅቷ የባቢ ቺክ ናት።" አለን!
......ገረመን ....
ባቢ ያ ቺስታው ?
ባቢ ያ ገራጅ ቤት በቡትቶ ቱታ የሚወላገደው?
ያ ጥራዝ ነጠቁ ቀለም የማይዘልቀው ባቢ
ያ ጥርሰ ብልዝ ጫታም...ሲጃራም...አረቄያም እውነት ይህችን ሴት ጠብሷታል?
.
"አዎ !ድብን አድርጎ ... ድንግልናዋ ሁሉ ለሱ ነው ሰፈፉ የደረሰው ..."
እርፍ!
"ያ አሜሪካ አለ የተባለ ባሏስ?
ያ ገንዘብ በየወሩ እየላከ የሚይፕብነሸንሻት ሸበላ ልጅስ?" ...ጠየኩት
"ማነው ይሄን ያለው?...ሰው እኮ ወሬ እየፈጠረ ነው የሚያወራው...ምንም ባል የላትም :) ...እንደውም ባቢ እሷን ለፍቅር የጠየቃት የመጀመርያ ወንድ እንደሆነ ነው የነገረችው ።"
"እርግጠኛ ነህ ?"
"ድብን አድርጌ !...ባቢ ደባሌ እኮ ነው...ፍቅራቸው ከተጀመረ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ያለውን ሂደት ከኔ በላይ የሚያውቀው ማን አለ ?"
ከጥግ በኩል ያ ነፍሰ ሰላላ ው አቡሻ እየተቅበጠበጠ አንድ ቃል አወጣ ።
"ፓ !...እውነትም ደፋርና ጭስ መውጫ አያጣም !
ባቢ ይመቸው :) "

@wegoch
@wegoch
@wegoch
K ቅንድል ቅፅ 2 ቁጥር-2_edited8.pdf
6.8 MB
ቅንድል ዲጂታል መፅሔት
#ቅፅ-2 #ቁጥር-2


#ልዩ እትም
#ሚያሸልሙ_ጥያቄዎች_የተካተቱበት



💵ፓኬጅ ከገዙ 60 ሳንቲም ብቻ💵

ቅን ፣ ምክንያታዊ እና ሀገር ወዳድ ትውልድ ለኢትዮጵያችን !!!
@KendelM
@KendelM
💧💧ቂም የሸፈነው እውነት💧💧
ክፍል ሁለት

የደስታዬ ጫፍ ይሆናል ብዬ የማስበው ቀን ሲመጣ እርካታን ሳይሆን ባዶነትን ተሸክሞ ነው የመጣው፡፡ የምፈልገው ሁሉ ኖረኝ፡፡የማስበው ሁሉ ሰመረልኝ፡፡ ግን ትርጉም አልባ፣ ደስታ የለሽ ሙት ሆነብኝ፡፡

                                                 ******
እንደማንም ያልነበረው ልጅነቴ፡-
ሰዎች ስለልጅነታቸው ሲያወሩ ‘እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ…..’ ሲሉ እገረማለሁ:: ‘ማንኛውም ኢትዮጵያዊ’ እኔን ያቀፈ ማዕቀፍ ይሆንን?

በቀን አንዴ ትርፍራፊ ለመቅመስ መስገብገብ፣ ጎዳና ላይ በገነባቻት የላስቲክ ቤት አጠገብ ተቀምጣ የምትለምን ወፈፍ የሚያደርጋት እናት፣መለመኛ የሆኑ መንታ ታናናሽ እህትና ወንድም፣ አስር ሳንቲም ለመመፅወት የሚመፃደቅ ሂያጅ፣ በባዶ እግርና በእኮዮች ምፀት ታጅቤ የምዳክርበት ትምህርት ቤት…….. ከማንኛውም ኢትዮጵያዊ የተለየ ልጅነት ነው፡፡

ማንኛውም ኢትዮጵያዊ እናቱ ልመናን ተናዛለት አባት አልባ ህፃናት መንገድ ዳር አስታቅፋው አልሞተችም፡፡

ማንኛውም ኢትዮጵያዊ እናቱ የሚበር መኪና ውስጥ ገብታ ስትሞት የሚሰማውን ከእብደት ያልተለየ ስሜት አያውቀውም፡፡

የኔ ልጅነት ‘እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ’ የሚባለው ማዕቀፍ ውስጥ የማይገባው ልጅነት የሚባለው ዘመኔ በአስር ዓመቴ አክትሞ የሁለት አመት ጨቅላ መንታ ታናናሾቼን እየለመንኩ ማሳደግ ግዴታዬ ስለነበር ነው። ዓለም ስትከረፋብኝ፣ በርሃብ ከሚጮሁ ታናናሾቼ ጋር ኡኡኡ ብዬ ሳለቅስ “እንደእናቷ ጠሸሸች” እተባልኩ አራት ዓመታትን ጎዳና መግፋቴ ነበር፡፡

አንድ ምሽት ታናናሾቼን አስተኝቼ ነትቦ እርቃኔን ያጋለጠውን ልብሴን እየሳብኩ ከላስቲክ ጎጆአችን ፊት ለፊት ቆሚያለሁ፡፡ መኪና ሲጢጥ ብሎ ሲቆም ሰማሁ፡፡ የሰከረ ወንድ ድምፅ ተከትሎ ተሰማኝ፡፡

“እሙዬ ነይ እስኪ……”

“እሙዬ ነይ እስኪ……”

“ምን ፈለግክ?”

“አንቺን”

“ሸርሙጣ አይደለሁም፡፡”

“ታዲያ እዚህ ምን ይገትርሻል?”

“ቤቴ ነዋ…..” ብዬ የላስቲክ ቤቴን በእጄ ጠቆምኩት።

“ስንት ዓመትሽ ነው?”

“አስራ አራት” ከመኪናው ወርዶ እየተንገዳገደ ተጠጋኝ፡፡

“300 ብር እሰጥሻለሁ፡፡”

“ሸርሙጣ አይደለሁም አልኩህ እኮ……”

“ሸርሙጣ ነሽ ማን አለሽ? ጎዳና እያደርሽ ምንም አልቀመስኩም ለማለት ነው?” እዚያ ጎዳና ላይ ስኖር ከዛ በላይ ፀያፍ ቃላቶች ሰምቼ አውቃለሁ፡፡ የዛን እለት ግን ሰውየው የተናገረው ንግግር ሰቀጠጠኝ፡፡ አጠገቤ ያገኘሁትን ድንጋይ አንስቼ ከፍ አደረግኩ

“በዚህ አናትህን ሳልከፍልህ ሂድ ከዚህ ጥፋ”

“ምንም የማታውቂ ከሆነ 1000 ብር እሰጥሻለሁ”

ደጋግሜ የብሩን መጠን ለራሴ አነበነብኩት፡፡ በህልሜ እንኳን አስቤው የማላውቅ ዓይነት ነበር፡፡ ምን ያህል ፍርሃት ቢያርደኝም ከብሩ መጠን ጋር ሲወዳደር ቀለለኝ፡፡ በዛው ቅፅበት ምን እንደማደርግ እቅድ አወጣሁ፡፡ ጭንቅላቴ እጄን አላዘዘውም፡፡ የመኪናውን በር ከፍቼ ገባሁ፡፡ ሲኦልን የዛን ምሽት አየኋት፡፡ በአለም ላይ ካሉ አስቀያሚ እና ጨካኝ ፍጥረታት መሃከል ዋነኞቹ ወንዶች መሆናቸውም የዛን እለት ገባኝ፡፡ ገና የ14 ዓመት ልጅ ነበርኩ፣ በችግር ሰውነቴ ደቆ የእድሜዬን ያህል ያላደግኩ፣ ምንም የማላውቅ………… ሰው እንዴት በህፃን ህመም ይደሰታል? እየተሰቃየሁ በፈሰሰኝ ደም እንዴት ድል እንዳደረገ ይፈነጫል? እሱ ወዙን ሲያዘንብ እኔ እንባዬ ሲዘንብ እንዴት ሰብዓዊነት አይሰማውም? እንዴት በ1000 ብሩ ስቃዬን ይገዛል? እንዴትስ ያ ደስተኛ ያደርገዋል? ይኼ ፍጡር ወንድ ነው።……  በስቃይና በተስፋ ተሰቅዤ ሊነጋ አካባቢ ወደ ላስቲክ ቤቴ ተመለስኩ፡፡ እነ አቢን ቀሰቀስኳቸው፡፡ …………… ርሃብ የለም፡፡ ልመናም የለም፡፡ ገበያ ይዣቸው ወጣሁ፡፡ ለብሰውት የማያውቁትን ልብስ ገዛሁላቸው፡፡ ካፌ ወስጄ ኬክ አበላኋቸው፡፡ ጠግበን ዋልን፡፡

በዚያው ሰሞን በተረፈኝ ገንዘብ መንገድ ላይ ሲቆሙ የማያቸው ሴቶች የሚለብሷቸውን የመሳሰሉ አልባሳት ገዛሁ፡፡ ያደርጉታል ብዬ ያሰብኩትን አደረግኩ፡፡ ይመስላሉ ብዬ ያሰብኩትን መሰልኩ። ዘወትር ማታ ሲዖል ደርሶ መልስ የኑሮዬ አንድ ክፍል ሆነ። ገንዘብ እየተቀበልኩ ስቃዬን መጨጥ (ለወንዶቹ እርካታቸውን) የየቀን ስራዬ ሆነ። አሁን ገንዘብ ማግኘት ቻልኩ፡፡ እንዳቅማችን ቤት ተከራየን፡፡ እህትና ወንድሜ ትምህርት ቤት ገቡ፡፡

ወንዶችን አልወድም ገንዘባቸውን እንጂ። ከወንድነታቸው የሚተርፈኝ ስቃይና ላባቸው ነው፡፡ ገንዘባቸው ግን የማልፈውን ሲኦል ያስረሳኛል፡፡ መንገድ መቆሙን ትቼ ትልልቅ ሆቴል ውስጥ መስራት ጀመርኩ፡፡ እንደዋዛ ትልቅ ሴት ሆንኩ፡፡ ሃያ አንድ ዓመት ሞላኝ፡፡ በዚህ ወቅት ነው ካሳሁንን ያገኘሁት፡፡ የሆቴሉ ደንበኛ ነው፡፡

“ቆንጆ እኮ ነሽ እዚህ ቦታ መገኘት አልነበረብሽም::” አለኝ።

“አየህ ተፈጥሮ ቁንጅናን እንጂ የተደላደለ ህይወትን አብራ አልሰጠችኝም::” መለስኩለት።

“የዛሬ ገቢሽን ልስጥሽና እቤትሽ አርፈሽ ተኚ?”

… አሁንም አልጨረስንም…

@wegoch
@wegoch
@paappii

#meri feleke
💧💧ቂም የሸፈነው እውነት💧💧
የመጨረሻ ክፍል

“የዛሬ ገቢሽን ልስጥሽና እቤትሽ አርፈሽ ተኚ?”

“ይበዛብሃል::”

“እጥፍ ላድርግልሽ!!”

በራሱ መኪና እቤቴ አደረሰኝ፡፡የጠየቅኩትን ገንዘብ ሳያቅማማ ሰጠኝ፡፡ በተደጋጋሚ እንዲህ አደረገ፡፡ ለዘመናት የሆቴሉ ደንበኛ ሲሆን ከሆቴሉ ሴቶች ጋር ስሙ ተነስቶ እንደማያውቅ ሰማሁ። ከአመታት በፊት ብቸኛ ወንድሙ ከእርሱ ጋር ተጣልቶ በባህር አቋርጦ ወደውጪ ሀገር ሊሄድ ሲሞክር የመሞቱን መርዶ ከሰማ ጀምሮ በየምሽቱ ይመጣል፣ እራቱን ይበላል፣ ይጠጣል፣ ለሴቶቹ ይጋብዛቸዋል፣… … ወደቤቱ ይሄዳል። ከቀናት በኋላ አብሬው እንዳድር በትህትና ጠየቀኝ፡፡ እቤቱ ነበር ይዞኝ የሄደው፡፡ ከሱ ጋር ካደርኩ በኋላ ወደ ሆቴል ተመልሼ መሄድ አላስፈለገኝም፡፡ በየእለቱ ማታ እቤቱ እጠብቀዋለሁ፡፡ ሲነጋ ወደቤቴ እመለሳለሁ፡፡

እንዳገባው የጠየቀኝ ቀን እብደት የቀላቀለው ስሜት ነበር የተሰማኝ፡፡ ምክንያቱ ባል ማግኘቴ አይደለም፡፡ ባል ወንድ ነው ወንድ ደግሞ የገንዘብ ምንጭ ነው። ከዛ ያለፈ አይደለም ለኔ፡፡ ካሳሁን ብዙዎች የሚያውቁት ሀብታም ነጋዴ ነው፡፡ …… በቃ!! ብር አገኛለሁ፡፡ የትኛውም ወንድ እንደሸቀጥ የሚገዛት ሴት መሆኔ ይቀራል፣ እነ አቢዬ ያለስጋት ትምህርታቸውን ይማራሉ፣ በለውጥ ገላዬን እሰጠዋለሁ፡፡ ልቤ ያውቀዋል እንደምፈታው፡፡ ተጋባን፡፡ እህትና ወንድሜን ይዤ እኔ ገንዘብን እሱ ትዳሩን ስንጠብቅ ኖርን፡፡
                                      
  *

ሳምንታት አለፉ፡፡ ሲመቸው ለቤቱ ፕሮሰስ እንደሚመጣ ቢነግረኝም  ካሳሁን አልመጣም ፡፡ አልደወለም፡፡  በቤቱ ምክንያት ቢመጣና ባየው ተመኘሁ፡፡ቤቱ አስክሬን የወጣበት ቤት መስሎ ረጭ አለ፡፡

የቤቱ ድምቀት፡- ትልቅነቱ፣ የቀለማቱ ስብጥር፣ በውስጡ ያጨቀው ውድ እቃ አልነበረም፡፡ ሞገሱን ተገፏል፡፡ ካሳሁን የለበትም፡፡

የምግቡ ጣዕም የሰራተኛዋ ጥበብ አልነበረም፡፡ ከካሳሁን ጋር የምግብ ጠረጴዛው ላይ መታደሙ እንጂ።

የእንቅልፉ መጣፈጥ የአልጋው ምቾት አልነበረም በካሳሁን እቅፍ ውስጥ ማደሩ እንጂ።

ይሄ ሁሉ የገባኝ አምስት ዓመታት ዘግይቶ ሆነ፡፡ የህይወት ዘመን ልምዴንና እውቀቴን ያስከነዳው እውነት ካሳሁን ‘ሴት ልጅ ለገንዘብህ ስትል ትወድሃለች’ ብለው እንደሚያስቡ ወንዶች አልነበረም፡፡ ገንዘቡን እንደወደድኩት እንጂ ለእሱ ግድ እንደሌለኝ ያውቃል፡፡ ራሱን እንድወደው ነበር አምስት ዓመት ሙሉ ሲጥር የነበረው፡፡ የፈለግኩትን ሁሉ እንኳን አጊንቼ እሱ ከሌለበት ባዶ መሆኑን ነበር ያሳየኝ፡፡ እድሜውን ካፈራው ንብረት እንደበለጥኩበት አሳይቶኝ እድሜዬን ሙሉ የጓጓሁለት ሀብታምነት ከንቱ መሆኑን ነገረኝ፡፡ አብሬው ስኖር ያላየሁት እውነት ያ ነበር፡፡

“ ማንም የኔን ያህል አውቆሽ አያውቅም፡፡” ይለኝ ነበር ሁሌም ሳበሳጨው፡፡ አሁን ነው ምን ያህል እንደሚያውቀኝ የገባኝ፡፡ ባዶነቴ በፍቅር እንጂ በገንዘብ እንደማይሞላ ያውቅ ነበር፡፡ እሱ ብቻ ይሄን ያውቅ ነበር።

ስልኬን አንስቼ ደወልኩለት፡፡

“ሰብሊ ይቅርታ ደንበኞች እያናገርኩ ነው፡፡ ቆይቼ እደውላለሁ፡፡” ብሎኝ ስልኩን ዘጋው፡፡ ‘ቆይቼ’ ያለው ሰዓት ዘላለም መሰለኝ፡፡ ሲሊፐር እንዳጠለቅኩ ተነስቼ ከቤት ወጣሁ፡፡ እንዲህ ላብድ የሚመስለኝ ሰዓት እብደቴን የማስታግሰው እህትና ወንድሜ ጋር ስሆን ነበር፡፡ አሁን እነሱ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ናቸው፡፡ እንድረብሻቸው አልፈልገኩም፡፡ ደግሞም ካሳሁንን የአባታቸው ያህል ነው የሚወዱት። በቀስታ እየተራመድኩ ማሰብ ጀመርኩ፡፡ አሁን ያለኝን ሁሉ አጥቼ ካሳሁንን ብቻ ማግኘት ተመኘሁ፡፡ እግሬን ጭንቅላቴ አላዘዘውም፡፡ ወደካሳሁን ቢሮ ሮጥኩ። ርቀቱ፣ አለባበሴ፣ የፀጉሬ መንጨፍረር…….. ምኑም ግድ አልሰጠኝም፡፡ ትንፍሼ ቁርጥ ቁርጥ እያለ በሩን ከፍቼ ገባሁ፡፡ ሁኔታዬ ያስደነገጣት ፀሃፊው መውጣቱን ነገረችኝ፡፡ በደከመ ነፍሴ ወደቤቴ ማዝገም ጀመርኩ፡፡ የመጣሁት መንገድ ርቀቱ የታወቀኝ ስመለስ ነው። ብዙ መንገድ ሮጫለሁ፡፡ መንገዱ ዳር ድንጋይ ላይ ተቀመጥኩ፡፡ ለብዙ ቀናት የረባ ምግብ ያለመብላቴን፣ እረፍት ያለው እንቅልፍ ያለመተኛቴን አሁን ነው ያስታወስኩት፡፡ ላዳ ይዤ ወደቤቴ ሄድኩኝ፡፡ በሩ ላይ የካሳሁንን መኪና ቆሞ ሳየው ‘እሪሪሪሪረ……’ ማለት አማረኝ፡፡ በሩጋ ስደርስ እሱ እየወጣ ነበር፡፡ ከላይ እስከታች እያስተዋለኝ

“ስደውልልሽ አታነሺም?”



“ስልኬን ጥዬው ነው የወጣሁት፡፡ ቢሮህ እኮ ሄጄ…..”

“አሁን መጥታ ነበር ሲሉኝ ነው ወደቤት የመጣሁት። ሰላም አይደለሽም?” ይዞኝ የመጣው ታክሲ ጥሩንባውን አስጮኸው፡፡

“አልከፈልሽውም እንዴ?” ብሎ እጁን ኪሱ ውስጥ እየከተተ ወደታክሲው አመራ፡፡ በዛው የማይመለስ መሰለኝ፡፡ ድጋሚ ለሳምንታት የማላየው መሰለኝ፡፡ ምን እንዳደረግኩ የገባኝ ካደረግኩት በኋላ ነው፡፡ አፌን ጭንቅላቴ አላዘዘውም፡፡

“እሪሪሪሪሪሪ…….” ብዬ አቀለጥኩት፡፡ በታክሲውና በኔ መሃከል ባለ እኩል እርቀት መሃል ደንግጦ ዞረ፡፡

“ምን ሆንሽ?” አጠገቤ ዘሎ ደረሰ፡፡ ምን እንደምለው ግን ግራ ገባኝ፡፡ የእንባዬ ጠብታ መሬቱ ላይ ተከታተለ፡፡ ባለታክሲው በጩኸቴ ተደናግጦ መውረዱን ሳይ ደነገጥኩ፡፡

“ምንም አልፈልግም፡፡ ሁሉም ይቅርብኝና አትሂድብኝ!!” እንባዬን እየታገልኩ ያወጣሁት ቃል ይሄ ነው፡፡

“አልሄድኩም እኮ ታክሲውን ልሸኘው ነው::”

“አልፈልግም እኮ ነው የምልህ፡፡ ቤቱንም ብሩንም ምኑንም አልፈልግም፡፡ ሁሉንም አልፈልግም። አልፈልግም በቃ!!” በእንባዬ ታጅቤ አምባረቅኩኝ፡፡

ያልኩት እንዳልገረመው ፤ እንዲህ እንደሚሆን እንደሚያውቅ ሁሉ ፈገግ እንደማለት ብሎ ወደታክሲው ሹፌር ፊቱን አዞረ፡፡ መሬት ላይ እየተንከባለልኩ መጮህ አማረኝ፡፡ ብሩን ሰጥቶት ሲመለስ በእንባ በተጋረደ ዓይኔ አየዋለሁ፡፡

“ላቆሰልኩህ ቁስል በሌላ በፈለግከው ነገር ቅጣኝ እባክህ ትተኸኝ አት….” ያልኩትን የሰማ አይመስልም፡፡ አጠገቤ ከመድረሱ ከንፈሮቼን ጎረሳቸው።

አምስት ዓመት ሙሉ እንዲህ ነበር የሳመኝ?

ጨርሰናል!!

@wegoch
@wegoch
@paappii

#meri feleke
ለቀናችኹ ይህን አድምጡማ
@Wegoch
@Wegoch
@Wegoch
ደግሞ ለምሽታችኹ ይኽን ያዙ
@Wegoch
@Wegoch
@Wegoch
ለሌላኛዉ ቀናችኹ ይኾን ዘንድ
@Wegoch
@Wegoch
@Wegoch
ለቅዳሚታ'ችኹ ከጀመርነዉ ላይ ይኽን ያዙ
@Wegoch
@Wegoch
@Wegoch
"በብዙ ምክንያት፣ ሰው ቢያሳምመኝም፤
ከሰው የተሻለም፣ መድኃኒት የለኝም።"
-----/መላኩ አላምረው/-----
"የመወለድ ብልጫው ምንድነው?"
--->-->->
ከዓመታት በፊት የሥነ ፍጥረት ኮርስ ሳስተምር "አምላክ ሰውን በመፍጠሩ ተፀፀተ" የሚለውን ጠቅሼ "ይህ የተጻፈልን እውን አምላክ የመፀፀት ባሕርይ ኖሮት ነውን? አይደለም። ይህ ጥቅስ የሰውን ልጅ ክፉነትና በተፈጠረበት ዓላማ አለመኖሩን፣ አፈንጋጭነቱን፣ ከጽድቅ ሸሽቶ ኃጢኣት ቆፋሪነቱን... በአጠቃላይ የሰው ልጅ የክፋት ጥግ አምላክ የሚፀፀት ባሕርይ ቢኖረው ኖሮ በትክክል ለፀፀት የሚያበቃ መሆኑን ለማጠየቅ ነው" እያልሁ እያስረዳሁ እያለ ከሰንበት ተማሪዎች አንዱ እጁን አወጣና እንዲህ አለ። "በእኔ እምነትና መረዳት በመፈጠሩ መፀፀት መቆጨት ያለበት ራሱ የሰው እንጅ አምላክ አይደለም ሰውን በመፍጠሩ መፀፀት የነበረበት። ምክንያቱም የሰው ልጅ ወደዚህች ምድር በመምጣቱ የሚያገኘው አኗኗሪ ያው በክፋት የተሞላውን የሰውን ልጅ ነው። ምድርን የስቃይ ዓለም አድርጎ በሴራና ተንኮል ተሞልቶ ለመኖር የተፈጠረው የሰው ልጅ ነው ለእንዲህ ያለ ኑሮ በመምጣቱ መፀፀት ያለበት። እኔ በበኩሌ በመወለዴ እፀፀታለሁ።"
እንዲህ ተናግሮ እንደተቀመጠ በፈገግታ እያየሁት መለስሁለት። "ወንድሜ አመክንዮህ አያስኬድም። ሲጀመር አንድ ሰው የመፀፀት ዕድል የሚኖረው ራሱ ባደረገው ድርጊት ነው። ራሱ ምንም ድርሻ ባላዋጣበትና በሌላ አካል በተከወነ ነገር በውጤቱ ምንስ መሆን ለምን ይፀፀታል? ባይሆን ሊያማርር ይችላል። ሰው በአምላክ ተፈጠረ እንጅ ራሱን ስላልፈጠረ ብቸኛ መብቱ 'ለምን ተፈጠርሁ?' እያለ የማማረር እንጅ 'መፈጠር አልነበረብኝም፣ ተሳስቻለሁ' ብሎ የመፀፀት ዕድል የለውም። መፀፀት የአድራጊ/ተግባሪ/ከዋኝ ድርሻ ነው። የአምላክ የመፍጠር ክዋኔ ውጤት የሆነው ሰው ሊፀፀት የሚችልበት አመክንዮ/Logic የለም። ልፈጠር ብሎ እንኳን ፍላጎቱን የመግለፅ ዕድል አልነበረውምና።" አልኩት።
ተማሪው መለሰ። "እንጃ ብቻ... እኔ በመፈጠሬ እፀፀታለሁ። የተወለድሁባትን ቀንም ረግማለሁ። የክፋትን ዓለም የኃጢአትን ምድር አይ ዘንድ ለምን ተወለድሁ? እ...."
አቋረጥሁት።
"እየውልህ ወዳጄ! አንተ በክፉዎች መሃል በጎ ሰው የመሆን ዕድል እያለህ፣ በኃጢአተኞች መካከል ጻድቅ ሆነህ መኖር እየተቻለህ ስለምን ክፋትና ኃጢአት ስለበዙ ብቻ መወለድህን ትርገማለህ? አምላክህን ስለፈጠረህ የምታማርረው እርሱ ክፋትን ፈጥሯልን? ኃጢአት ከክፉ ሰው አእምሮ ታስቦ ከርጉም ልብ ይወለዳል እንጅ በአምላክ ተገድደን የተሰጠን ነው እንዴ? አምላክ ለሰው ልጅ የማሰብና ምንም ነገር የመተግበር ፀጋን ሰጠ። በዚህ የአእምሮ የመፍጠር ፀጋ መልካም ነገርን ብቻ ማሰብና መተግበር እየቻለ ስለምን በክፉ ምግባር ይፀፀታል? ኃጢአትን ወዶና ፈቅዶ እንጅ ተገዶ የሚያደርግ አለ? ንፁህ ሆነህ የመኖር ምርጫና አቅም እያለህ በቆሻሻ መኖር ማማረር ምን ይሉታል? መፀፀት ካለብህ መልካም ነገር ማድረግ እየቻልህ ለበጎ ተግባር ዋጋ ሳይጠየቅብህ የክፋትን መንገድ በነፃ ፈቃድህ መርጠህ ለምድር መርገምን ከጨመርህ ነው።"
መልስ አልሰጠኝም።
--->->
ከዚህ ጊዜ በኋላ የተወለድሁበት ቀን (ግንቦት 27) በመጣ ቁጥር ከልጁ ጋር የነበረን ውይይት ትዝ ይለኛል። በተለይ ዘንድሮ በደንብ ነው ትዝ ያለኝ። ምን አልባት የሰውን ልጅ የክፋት ጥግ ከመቼውም ጊዜ በላይ ያለፉት ሁለት ዓመታት የመረዳት ዕድል ስለሰጡኝ በተግባርም ስላሳዩኝ ይሆናል። ሰው ወዶ አያማርርም። አንዳንዴ መኖር በራሱ ያስጠላና ፈጣሪን ያለ አግባብ የማማረር ከንቱነት ውስጥ ሁሉ ይከታል። ግን ትርጉምም ትርፍም መፍትሔም የሌለው ማማረር።
ብቻ ግን አንድን ጥያቄ በአግባቡ ጠይቀን መልስ ለራሳችን ማግኘት ይኖርብናል።
"የመወለድ ብልጫው ምንድነው? መወለድ ካለመወለድ በምን ይሻላል? ባንወለድ ምን ይቀርብን ነበር? በመወለድ ምን ተጠቀምን? ለመጣንባት ዓለም ምን በጎ ድርሻ አለን? እስካሁን ምን መልካም አስተውልፅኦ አበረከትን? ነገስ? ለምን እንኖራለን? ለምድር በክፋት ተፀንሶ በሴራ የሚወለድን መርገም ለመጨመር? ወይስ ለችግሯ መፍትሔ ለማውጣት? በምድር ላይ መልካም ነገርን ተግብሮ በጎ አሻራን አስቀምጦ ከማለፍ በስተቀር የመወለድ ብልጫው ምንድነው? እኛ ባንወለድ ይህች ምድር የሚቀርባት መልካም ነገር አለ? ወይስ የሚቀርላት መከራ? በእውኑ መወለዳችን ካለመወለዳችን ብልጫው ምንድነው? ክፋት ወይስ መልካምነት? ኃጢአት ወይስ ጽድቅ? በመወለዳችን አለመወለዳችንን በምንድነው የምንበልጠው? ችግር በመጨመር ወይስ መፍትሔ በማዋጣት?"
--->->
ለማንኛውም በእኔ በኩል እንኳንም ተወለድሁ ባይ ነኝ።
የሰውን ልጅ የክፋት ጥግም ቢሆን አይቼ እመሰክር ዘንድ መወለድ ነበረብኝ። ፈጣሪውን በመፍጠሩ ያሳዘነውን የሰውን ልጅ ብሽቅነት፣ ውለታ ቢስነት፣ አማራሪነት፣ ምስጋና ቢስነት አይቼ እረዳ ዘንድ እንኳንም ሰው ሆኜ ተፈጠርሁ። በመወለዴ ልፀፀት እንዴ? በፍፁም። ባይሆን ከክፋት መሃል ጥቂት በጎነትን፣ ከጥላቻ መሃል ጭላንጭል ፍቅርን እየፈለግሁ ልኑር እንጅ።
እርግጥ ነው ምድርን በክፉ ሰዎች ክፋት ልክ ብቻ ከተመለከክናት ደንበኛ ሲኦል ናት። ፈጣሪንም ለምን በሲኦል ፈጠረኝ ማለታችን አይቀርም። ነገር ግን መልካምነቷን እንመርምር። ምን በመንፈስ ተራቀን ረቂቅ ምሥጢራዊ በረከቷን ባንመረምር ቢያንስ በሥጋ እይታ ምድራችን ያላት በረከት ቢቆጠር መወለዳችን ልክ ነበር። ንፁህ ውሃን ከሆዷ አፍልቃ የምታጠጣን፣
ኦክስጅንን ከእፅዋቷ እያመነጨች ሕይወት የምትሰጥን ገነት ማየት አልነበረብንም?
በአበቦቿ አሸብርቃ፣ በማዕድኖቿ አብረቅርቃ የምታስውብን ይህችን ውብ ምድር ሲኦል ብቻ ናት ብለን የገነትነት ገጿን መሰረዝ ልክ ነው? በፍፁም። ሕይወታችንን የምሬትና የሀዘን ብቻ ሆኖ እንዲያልፍ ካልፈረድንበት በቀር በደስታ ውስጥ ሆነን ፈጣሪን የምናመሰግንበት ብዙ ጸጋና በረከትም ምድር ይዛለች።
ደግሞስ ከተፈጠሩ ወዲያ ለምን ተፈጠርሁ ብሎ ማማረር ምን የሚሉት ከንቱነት ነው? ባይሆን የተፈጠሩበትን ዓላማና ሊያበረክቱት የሚገባን በጎ ድርሻ ለይቶ ለእርሱ መድከም እንጅ። መቼም አምላክ ቅዱስ ነው ለርኩስ አላማ አይፈጥረንም። መልካም ነውና ለክፉ ድርሻ አላመጣንም። የመክፋት ነፃነታችንን ያከብርልናል ማለት ክፋታችንን ይፈልገዋል ማለትም አይደለም።
መልካምን እያሰቡ በጎ ነገርን የመተግበር ሙሉ መብት እያለን በተቃራኒው ጎን መድከምን ከመረጥን ምን ያድርግ? ነፃነት ባይኖረንም መከራ ነው። ሰው ነፃ ፈቃዱን ቢያጣ ከግዑዝ ዓለም ወይም ከደመ ነፍስ እንስሳት በምን ይለያል? ክፋትንም በጎነትንም የመሥራት ነፃነት ባይኖረኝ ማለት ግዐዝነትን/እንስሳትን መምረጥ ነው።
--->-->->
ወዳጄ የሰውን ልጅ የክፋት ገፁን ብቻ እያሰብህ የምትብሰከሰክ ከሆነ ጤነኛ አትሆንም። የሰው ክፋቱ ምኑ ይተረካል? የክፋት አሠራር፣ የሴራ አኗኗር ሕይወት ሆኖን የለ?! ራሳችን የምኖረውን ሕይወት ለማን እንተርከው?
አብዛኛው ሰው እኮ (በዚህ ባለንበት ዘመን በተለይም በፖለቲካው ዓለም) ሰብዓዊ ባሕርይውን በፈቃዱ ጥሎ ሌላ ነገር የሆነ እስኪመስል ድረስ ክፉ ሆኗል። ሁሉንም ነገር በክፋት ያያል። ሁሉንም ነገር ሴራ ያደርገዋል። "ሁሉም ነገር የሴራ ውጤት እንጅ ምንም ነገር አጋጣሚ አይደለም" በሚል የሴራ ንድፈ ሐሳብ ልቡ የተነደፈ ትውልድ አንተ መልአክም ብትሆን ሰይጣን ያደርግሃል።
በቃ ይኸው ነው።
👆ከላይኛው የቀጠለ
.

መስቀል ይዘህ ልትባርከው ብትሄድ "የዋህ ካህን መስሎ መስቀል እያሳዬ ሊገድለኝ የመጣ እባብ ነው። መስቀሉን የሚይዘው እኔን ወግቶ ለመግደል እንጅ ሊባርከኝ አይደለም" እያለ ካህኑን ሰይጣን ያደርግሃል። ወደኸው ብትቀርበው "በጣም ስለሚጠላኝ በፍቅር ቃላት እየሸነገለ ቀርቦ አስብቶ ሊያርደኝ ነው።" ይላል። አብዛኛው የአዳም ዘር (በዚህ ባለንበት ዘመን በተለይም በፖለቲካው ዓለም) ክፋት ብቻ ካልሆነ በቀር መልካምነትን ላያይ ዓይነ ልቦናው የታወረ፣ እዝነ ልቦናው የደነቆረ ነው። ሲጀመር ክፉ ሰው አንተን በራሱ ልክ ነው የሚያስብህ። እርሱ ልቡ ጥላቻን አእምሬው ሴራን የተሞላ ስለሆነ በቃ ያንተ ምንም ነገር ለእርሱ የተሰወረ ክፋት ነው። መስቀልህ ጦሩ፣ ፍቅርህ ፀሩ ነው። ያንገትህን ማተብ እንኳን "እኔን አንቆ ለመግደል ነው አስሮት ሚዞር" ሊልህ ይችላል። አደግ ያለ ጥፍር ካለህም የእርሱ መውጊያ ነው። ሻርብ ብትለብስ ማነቂያ ነው።
ከእናት አባትህ፣ ከወንድሞችህ፣ ከአብሮ አደግ ጓደኞችህ ሁሉ ጋር ሰብሰብ ብለህ ስትጫወት "እርሱን ለማጥፋት ከሆኑ ጠላቶቹ ጋር እየመከርህ ነው።"
እና ይህን ሁሉ ስታይ ሰው የሌለበት ዓለም ይናፍቅሃል። መወለድህም መርገም ሆኖ ሊታይህ ይችላል። ግን አስተውል።
ከዚህች ምድር በዚህ ሰዓት መድኃኒት ሆነው የሚፈውስህ ሰውም አለ። ሞትህን የሚሞትልህ፣ መከራህን የሚሸከምልህ ሰው በዙሪያህ አለ። ለዚህ ሰው ስትል ብቻ መኖር የለብህም? ምን በክፉዎች ተከበህ ብትኖር በዚህ ሁሉ መሃል በደግነት ጥግ ለሚኖሩ ለመልካም ሰዎች ስትል መኖር ላኖራቸውም ማመስገን የለብህም? ክፉን ብቻ እየቆጠርህ የበጎ ሰዎችን ድርሻ በዜሮ ማባዛትህ ከክፉዎች አያስመድብህም?
ይልቅ እንዲህ በል።
"በብዙ ምክንያት፣ ሰው ቢያሳምመኝም፤
ከሰው የተሻለም፣ መድኃኒት የለኝም።"

@wegoch
@wegoch
2024/09/24 22:28:59
Back to Top
HTML Embed Code: