Telegram Web Link
Forwarded from Mykey (Mikiyas Liyew Mykey)
Ethiopia Professional Footballer Association
#Covid19virusAwarenessmessage
#Challenge
March 2020
@Mykeyonthestreet
🎧ቀኑ ሲመሻሽ ብለሽ አትፍሪ ፋኖስ የለም፣
ፀሃይ ነሽ እና ለዚህች አለም!🎧🎼

ይህ ግጥም ከድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን የዘፈን ግጥም ላይ ተቀንጮቦ የቀረበ ነው፡፡ "አይዞ ልቤ" ይላል የሙዚቃው ርዕስ፡፡
.
እናም በዚህ ሁለት ስንኝ ውስጥ የምናገኘው አንድ ትልቅ አሳብ አለ- #ፀሃይነት ወይንም ትልቅ ብርሃናዊ ሃይል በልባችን እንዳለ በደምብ ይነግረናል፡፡
.
ሕይወት በተለያዩ መንገዶች እና በተለያዩ እርምጃዎች አጅባ በማናውቀው የጨለማ አለም ውስጥ ልታስገባን ትችላለች፡፡ ሁሌም ከጨለማ ማግስት ብርሃን እንዳለ ግን እንመን፤ የነበርንበት ጨለማ ጨለማነቱን ቀጥሎ እኛነታችንን የማጨለም አቅም የለውም፤ ምክንያቱም እኛ ጋር ያለው የፀሃይነት ባህሪይ አይደለም ያለንበትን የኛነታችንን ጨለማ ቀርቶ አለምን ማብራት የሚችል ብርሃን ስለሆነ፡፡

ጨለማ ውስጥ ስንሆን ፋኖስ ይዘን አለመገኘታችን ሊያስጨንቀን አይገባም፡፡ የፋኖስን ብርሃን በእጅጉ የሚያስንቅ የፀሃይ ወገግታ በልባችን አለና፡፡
.
ስንጨነቅ ፣ ተስፋ መቁረጥ ሲያደባብን ፣ እምነታችን ሲጠፋ ፣ ፍቅራችን በጥል ሲበረዝ በርግጥም ጨለማው ውስጥ ነን እና የውጪውን ፋኖስ ከመለመን ወደ ልባችን እንመልከት፡፡

አዎ ዛሬ በሃሳብም በአካልም ደክመናል፡፡ ነገር ግን ነገ የተሻለ ቀን ይመጣል፡፡ በርትተን ወደ ፈጣሪያችን እንፀልይ፡፡

#እጃችን_ደጋግመን_በሳሙና_እንታጠብ
#ከሰዎች_ጋር_ያለንን_ርቀት_እንጠብቅ
#የቫይረሱን_ምልክቶች_ስናይ_በቶሎ_ወደ_ጤና_ተቋማት_እንሂድ
#አስገዳጅ_ነገር_ካልሆነ_ከቤት_አንውጣ
#በመንፈስ_ጠንካሮች_እንሁን
@wegoch
@wegoch
@wegoch
በቀደም ለት ማታ ቡና ከምጠጣበት ቦታ ወደ ቤቴ እየተጣደፍኩ እየሄድኩ እያለው አንድ እድሜው 10 እስከ 12 የሚገመት ጎዳና ቤቱ የሆነ ልጅ እግሬ ላይ ጥምጥም ብሎ ሳንቲም ይለምነኝ ጀመር ፡፡ ይሄ አይነቱ ልመና በምኖርባት ከተማ በጣም የተለመደ በመሆኑ በመሰልቸትም ጥድፊያ ላይ ስለነበርኩም (እንደ ምንክንያት)ለልመናው ቦታ አልሰጠሁትም ነበር ብቻ የሆነው ሆኖ ሳንቲም ሳልሰጠው ከእግሬ ላይ አስነስቼው ወደ መንገዴ ...ጥቂትም ሳልራመድ አባት አባት አለኝ ዞርኩ ኮሮና ቫይረስ ስለገባ ምግብ ቤቶች የተራረፈ ምግብ (ቡሌ) ስለማይሰጡን እኮ ነው አለኝ ፡፡ ያማል ፡፡ያለኝን ሰጠውት ወደ ቤቴ እየሄድኩ መንግስት ምን እያሰበ ነው ብዬ እንጠይቅ ውስጤ አስገደደኝ እነዚህ ልጆች ጎዳና ላይ ውለው ጎዳና ላይ እንደሚያድሩ የሚጠፋው ያለ አይመስለኝም እንደ በሽታው አካሄድ ከሆነ ደግሞ ቢያንስ ልጆቹ እንደ ዜጋ ለጊዜውም ቢሆን ተመርምረው አንድ ቦታ የሚቀመጡበት መንገድ አይታሰብም ወይ እነዚህ ልጆች ከባለሀብቱ እስከ ወጣቱ የማይነኩት ሰው አለ ወይ የማይሄዱበት የማይንቀሳቀሱበት ስፍራ አለ ወይ በሽታውን ለማሰራጨት ከፍተኛ እድል እንዳላቸው ሳይታሰብ ቀርቶ ነው ወይ ? እነሱስ ቢሆን ልብሳቸው ቢያድፍ ሰውነታቸው ቢቆሽሽ ሰው አደሉ ወይ ዜጋ አደሉ ወይ ?ጥያቄ ይሆንብኛል ፡፡ነገሮች እንዴት እየሄዱ እንዳሉ ያሳስበኛል ሀገሬን እወዳለው ደሜ አጥንቴ ገለመሌ ቅብርጥሴ ሲል የነበረ ሁሉ ማንነቱን ክዶ ቃሉን በልቶ ለገንዘብ ሲያደገድግ ሳይ ያሰጋኛል ገንዘቡን ሀይማኖት አድርጎ ሲያጎበድድ ሲያይ ያመኛል ፡፡ይገርማል እንዴት ሰው ነኝ በዛ ላይ ሀገሬን ወዳለው ከሚል ሰው እንደዚ አይነት ተግባር ይፈፅማል ይሉኝታ እሴቴ ነው መገለጫዬ ከአባቴ ቃል ውልፊት ..ለኔ ያለው የትም አይሄድም.. የኔ እድል ከኔ ውጪ የት ገብታ ..ሲል የነበረው ሁሉ ለገንዘብ ሲያጎበድድ ማየት ይቀፋል ፡፡በምን ሂሳብ በምን ህግ አንድ እቃ 80 እና 90 በመቶ ይጨምራል በምን አይነት ልኬት እራሱን ቢለካ ፊት ለፊት አስቀምጦ የለም ጨርሻለው ለማለት የበቃው ?ያስደነግጣል ፡፡ሲደመር መንግስት እያደረገው ያለውን ጥንቃቄ ባልጠላም ቡዙ የታሰበበት አይመስለኝም ፡፡እንዴት ?ቫይረሱን ለመከላከል ታስበው እጃችንን እንታጠብበት ዘንድ የተቀመጡት ሮቶዎች የተቀመጡበት አከባቢ ያለው ጭንቅንቅ ለታክሲዎቹ የወጡት አዎጆች ከመሀል ከተማ እንደተንቀሳቀሱ አለመስራታቸው ሁሉ ያሳስባል ፡፡ከህግ ውጪ የምግብ ሸቀጦች ላይ ሁሉ የተጨመሩት የዋጋ ጭማሪዎች ያሳስባሉ ፡፡ያሰጋል ፡፡ስለዚህ አስብ ታክሲ ስትሳፈር የምትይዘውን ብረት የገንዘብ ልውውጦችህ ካፌ ቁጭ ስትል ብና የምታማስልበት ማንኪያ የበርህ እጀታ የስልክህ የላይኛው ክፍል የተቀመጥክበት ወንበር ብቻ ተወው ነገሮችህ በሙሉ ለኮሮና ቫይረስ መስፈሪያ የሆኑ ናቸው ፡፡ያገባቸዋል የሚባሉና የሆነ ለውጥ ሊፈጥሩ የሚችሉ ሰዎች በአብዛኛው ጆሮ ዳባ ልበስ ስላሉ እራስህን /ሽን/ጠብቅ ጠብቂ "አትጨባበጡ" ባለባጃጆች እና ባለ ታክሲዎች ከገንዘብ ውጪ አስቡ "ተራርቃቹ ተቀመጡ"ባለ ሀብቶች ብትችሉ ምናችሁም አደለም እና ሰርቪሶቻችሁን ለህዝቡ በማሰማራት ተባበሩ ከወሬ ያለፈ ነገር ለመስራት ተንጠራሩ መንግስት መደረግ ያለበትን ሁሉ ለማድረግ ይሞክር አስገዳጅ መመሪያዎችን ያውጣ ግን ባንተ በኩል የሚጠበቅብህን አድርግ ቢያንስ እራስህን ከጠረጠርክ ተመርመር ከሰው ጋር ላለመገናኘት ሞክር በተረፈ ሳኒታይዘር (ውድ ነው ላታገኝም ትችላለህ )ጓንት ተጠቀም እጅህን ታጠብ (ውሀ ከየት አምጥቼ እንዳትለኝ)ለማንኛውም ሞክር ከዛ ፀሎት እና ዱአ አድርግ ወደ ፈጣሪህ ጩህ

እግዜር ይጠብቀን
አላህ ይጋርደን

አሜን !!
ንጉስ ደረሰ
@wegoch
@wegoch
@wegoch
የጤና ባለሙያዎች ራሳቸውን ከኮሮና ቫይረስ እንዲጠብቁ የሚለበስ ልብስ (PPE) ያዘጋጀው ወጣት ኢትዮጵያዊ ኢንጂነር!

... ሁሉም በየሙያው ይረባረብ! ይህ የገጠመን ጠላት ሁላችንንም የሚፈትን ነው። አገራችንን ለማዳን ኃላፊነቱ የጤና ባለሙያዎች ብቻ ከመሰለን ተሳስተናል። ሁሉም በየእውቀቱ፣ በየሞያው የበኩሉን አስተዋጽኦ ማድረግ አለበት። ዛሬ የማስተዋውቃችሁ ኢንጂነር ሳሮንም ለሁሉም አርአያ መሆን የሚችልና ሊደገፍ የሚገባው ወጣት ነው። ይህ የምታዩት ልብስ በራሱ ተነሳሽነት ጥናት አድርጎ፣ በራሱ ወጪ ያዘጋጀው ነው። ለቫይረሱ ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ ጤናው ላይ የሚሰሩ ያገሩን ልጆች ለማገዝ ካለው መልካም ሐሳብ ነው ይህን ያደረገው። በፎቶው ላይ ለብሶት የምታዩትን አንዱን ልብስ ከውጭ ለማስገባት ከ2000 እስከ 3000 የኢትዮጵያ ብር ያስፈልጋል። ኢንጂነር ሳሮን ግን ዋጋውን በ1/4ኛ ቀንሶት በ500 የኢትዮጵያ ብር ገደማ አንድ የፕላስቲክ ልብስ ማዘጋጀት እንደቻለ ነው የነገረኝ። ከተማሩ አይቀር እንዲህ ላገር መትረፍ ያኮራል።
*እንግዲህ መንግስትም ሆነ ባለሐብቶቻችን ይህንን ጎበዝ ወጣት ለማበረታታት ብቻ ሳይሆን የብዙ ሺህ ሐኪሞች፣ ነርሶችና የጤና መኮነኖችን ጤና ለመጠበቅ ስትሉ እንድታግዙት እጠይቃችኋለሁ።
እሱን ቀጥታ የምታገኙት በስልክ ቁጥሩ 0917807480 ሲሆን ጥያቄ ካላችሁም በውስጥ መስመር ልትጽፉልኝ ትችላላችሁ።
ይህን ያነበባችሁ በሙሉ ሼር እያደረጋችሁ፣ እየደወላችሁ አቅም ላላቸው ሰዎች እንድታዳርሱልኝ፤ ወጣቱንም እንድታበረታቱት ይሁን!
#የኔትውልድ
............ (ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አዕምሮ)

@wegoch
@wegoch
 

  ### ከድሮም ጭምር ነው ###


አባት እና ልጅ እናቲቷ ከሞተች በኃላ መንገድ ላይ ውለው ማደር ከጀመሩ ሠምበትበት ብለዋል ፡፡ ድሮም የአቅሙ ጉዳይ ያን ያክል አጥጋቢ አልነበረም እና እናቲቱ ከዚህ አለም ስትለይ ደግሞ የቤቱን ጣጣ መቋቋም አቅቷቸው ቢያንስ የቤት ኪራይ እናሸንፍ ብለው ከድልድይ ሰር ኬንዳ ወጥረው ሂወታቸውን መምራት ቀጠሉ ፡፡ ለተወሠነ አመታት ከዚች ድልድይ ሥር ቤታቸው ክፉውንም ደጉንም ሲያፈራርቁባት ኖሩ፡፡ በአንድ ወጥመደኛ ቀን ትኩሥ ወሬ በከተማይቱ ተሠማ ፡፡ ሁሉም ወሬውን ያጧጡፈዋል ፡፡ ማብረጃ የሌለው ወሬ ሆነ ፡፡ ውሰድ መልስ ፣ ግጥም ሁሉም አፍ ለአፍ እንች እንካ ፤ እኔ በደንብ አብራረዋለሁ ሠለ ወቅታዊው ጉዳይ ይል ጀመሯል የከተማይቱ ወጣት የለ ፤ ሽማግሌ የለ ፤ አሮጊት የለ ፤ ህፃን የለ ፡፡ ከድልድዮ ስር የሚኖሩት አባት እና ልጅ ግን ሁሉም በሚያቦካው ወሬ ደንታ አልሠጡትም ፡፡ የራሳቸውን ፀጥ ረጭ ያለ ሂወት ይገፍሉ እንጅ ፡፡ አንድ ቀን በጥዋት ግን ደንገት ያልጠበቁት ክስተት ከተፍ አለ ቤታቸው ፡፡ ሁሉም የከተማይቱ ህዝብ ለአስራ አምስት ቀን ቤታቸው እረፍት እንዲያደርጉ፡፡ እንዳይወጡ የምትለውን መልክት ይዛ ቤታቸውን አንኳኳች ፡፡ በነገሩ የተደናገጠው ልጅም አባቱን " አባየ ምን አጠፋን ?" ብሎ ጠየቀው አባቱን ፡፡ 

" ወይ ልጀ ለአስራ አምስት ቀን መንገድ ላይ መሆን አይቻልም ይላሉ ፡፡ በትንፋሽ የሚተላለፍ በሽታ ስለመጣ ሁላችሁም በየቤታችሁ ግቡ ተብሎ ስለተነገረ እኛም መስመር እንድንይዝ ፤ ከዚህ ቦታ እንድንወገድ ነው መልክት ያስተላለፈ " አለ አባት እጥፍ ባለ አንጀቱ ፡፡ 

"እና የት ብለን እንሠደድ አባ ? " አለ ልቡ እየተሸበረ ፡፡

" አይ ልጀ ሀገር ሲከፋ ወደ ህዝብ ትሸጎጣለህ ፤ ህዝብም ሲከፋ ወደ ምድረ በዳ ወደ ሌላ ቦታ ትሰደዳለህ ፡፡ ሁለቱም ከከፉ ግን ወዴት ይደረሳል ፡፡ 


በድሮ ጊዜ ምን ተደረገ መሠለህ ፤ ሠውየው ገበያ ውሎ ሲመጣ ፤  አንድ ማዳበሪያ ሙሉ እህል ሸምቶ አህያውን ጭኖትም ነበር ፡፡ ገበያው እሩቅ ከመሆኑም የተነሳ ቤቱ ሳይደርሥ ይመሽበታል ፡፡ መንገድ ላይ አንድ አስቀያሚ ገጠመኝ አጋጠመው ፡፡ ከመጨለሙ የተነሳ መንገዱን ሲሄድ የወንዝ መቀመቅ ላይ አህያው እስከ ተሸከመው ጭነት ገብቶ ተሠነቀረ ፡፡ ሰውየዉ አህያውን ሊያወጣ ቢለፋ ፣ ቢነሳ ፣ ቢወድቅ ፣ ቢታገልም አልሆንልህ አለው ፡፡ በዚህ ጊዜ ምን አልባት የሚረዳኝ ባገኝ ብሎ እሪ ብሎ ጮኸ የሚደርስለት ግን ጠፋ ፡፡ የአካባቢው ሠው ከፍቶ ነበር እና ከገደል ማሜቱ ውጭ ምንም ድምፅ የሚመልስለት አልተገኘም ፡፡ በሁኔታው ግራ የተጋባው ሠውየ አህያው እንደ ተከተተ ከአረግረጉ ፈንጠር ብሎ በጊዜው ፣ በአካባቢው ሠው መክፋት ትክን እያለ ከደረቁ መሬት ላይ ሄዶ ቁጭ አለ ፡፡ ከትንሽ ቆይታ በኃላ ሁለት ጅብዎች እየተሳሳቁ መጡ ፡፡ ሠውየው ግራ ተጋባ ፤ ፈራ ፤ በጣም ተንቀጠቀጠ ፡፡ ግን አማራጭ የለውም እና ምራቁን ውጦ ፤ ጥርሱን ነክሶ ተቀመጠ ፡፡ ሁለቱ ጅብዎችም የተከተተውን አህያ ከእነ ጭነቱ መንጥቀው አወጡት ፡፡ ከአወጡት በኃላ ሠውየው ሲታያቸው ጅብዎች ለቀውለት ሄዱ ፡፡ ሠውየውም ፈጣሪውን እያመሠገነ አህያውን ይዞ ወደ ቤቱ ሄደ ፡፡ እና ልጀ በዚያ ጊዜ ከሠው ልጅ እንሥሣቶች አራውቶች የሚሻሉበት  ነበር ስትመለከተው ፡፡ ከዚህ ሲያባርሩን ከሰው መንደር እንዳንጠጋ በራቸውን ቀርቅረዋል ፣ ሠፈራቸውን አጥረዋል ፡፡ ችግር በአንድ የሚቀር መስሏቸው መካረሚያቸውን ምግብ ሸምተው ሶፋቸው ላይ ፈልሰስ ብለዋል ፡፡ ሂዱ ብለው ከጨከኑብን እንልቀቅ እና የሚራራ እንስሳ አሊያም አራዊት ከገጠመን ከእነርሱ ጋር እንጠጋለን ፡፡ እንጅ የሰው ነገር እማ አይተነው አይደለ ይኸን ያክል ጊዜ በኬንዳ ስንከራተት ፡፡ " ብሎ ጓዙን ይሸክፍ ጀመረ አባትም ፡፡

"እሽ አባ" ብሎ እያለቀሰ ቅራቅንቦውን ይሠበስብ ጀመር ልጅም ፡፡ 


ፈጣሪ ከሠው አውሬ ይጠብቀን!!!!




ከዘገዬ ታዴ

መጋቢት 22 / 2012

####################
@wegoch
@wegoch
[April 1]

ነገ የፈረንጆቹ የውሸት ቀን ( ኤፕሪል ፉልስ ዴይ)
መሆኑን ተከትሎ አንዳንድ ሀላፊነት የጎደላቸው
ሰዎች ሊፈጥሩት ከሚችሉት የሀሰት ወሬ እራሳችሁን ጠብቁ።

#በደህናቆዩ #በጥንቃቄይቆዩ
@getem @wegoch @seiloch
ይሄን መልክት ያስታወሰችን #ribka ናት እናመሰግናለን!
@wegoch
"....ብዙ ኢትዮጵያውያን ጉጉታቸው ነዳጅ ተቆፍሮ አልወጣም ነው። እኔ ደግሞ ነዳጅ ተቆፍሮ ከመውጣቱ በፊት ንዴታችንን ይውጣ እላለሁ። ብስጩ ህዝብ፣ እልኸኛ ህዝብ፣ ፈሪሀ እግዚአብሔር የሌለው ህዝብ፣ የማይግባባ ህዝብ... ነዳጅ ቢያወጣ የመኪና ፋብሪካ ሳይሆን የሚያቋቁመው፥ ሰይጣን #የክብሪት_ፋብሪካ ያቋቁምለታል፤ ክብሪት ያቃብለዋል።
.
አጼ ኃ/ሥላሴን ስንገለብጥ እኮ ሌባ ብለን አባርረናቸው ነበር፤ ቀጥሎ ለመጣ መንግስትም ስናጨበጭብ ነበር፤ ህዝቡ ደርግ ሲመጣ እኮ ሶሻሊዝም እግዚአብሔር የለም ለማለት እኮ ቄሱ ነው አስቀድሞ ካድሬ የሆነው። ይሄ መንግስት ሲመጣም በብሔር በቋንቋ ይደራጅ ሲባል ህዝቡ አጨብጭቦ ነው የተቀበለው፤ ነገም ሌላ ቢመጣ ለማጨብጨብ የኢትዮጵያ ህዝብ ለምን እንደሚያጨበጭብ
የሚጠይቀው አጨብጭቦ እጁ ከተላጠ በኋላ ነው። በጣም ችግር አለ። ምክንያቱም #አያነብም። ህዝባችን የጥቂት ፓለቲከኞች #የሀሳብ_መስጫ ሳጥን ነው የኢትዮጵያ ህዝብ። ጥቂት ፓለቲከኞች ሀሳባቸውን ያራግቡበታል።"
......
☞ መጋቢ ሀዲስ እሸቱ ዓለማዮህ በአንድ ወቅት ከተናገሩት
@wegoch
@wegoch
@wegoch
ለሳምንት ያህል ከታጎርኩበት ቤቴ በአስገዳጅ ሁኔታ ወጣሁ (ያው የቢዴና ነገር 😉)
ባለቤቴ ወደ ቢሮ እንደሚሄድ ባል ሳይሆን በደርግ ጊዜ ለግዳጅ እንደተጠራ ሰው ቆጥራኝ እንባዋ በአይኖቿ ግጥም ብሎ ሸኘችኝ።
እኔም ዝናሬን አደግድጌ.. .(ማነው...ይቅርታ! )... የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ዶክተር ይመስል ይፕእጅ ዋንቴን ገርግጄ ...ፊቴን በጨርቅ ተሸፍኜ ወጣሁ ።
"HONEY! አይዞን ጨከን በል !" ...የውዲቷ ባለቤቴ ድምፅ ከጀርባዬ ተከተለኝ ።
።።።።
መንገዱ ከወትሮው ተለይቶ ረጭ ብሏል.. .ሜኪሲኮ ሞልቷል አቦ ሌላ ታክሲ ፈልግ! ብለው በጩኸት የሚያስበረግጉኝ የታክሲ ረዳቶች እንደ እንቁላል ተንከባክበው ጋቢና ከተቱኝ። ... (የተጓዡ ቁጥር ከማነሱ የተነሳ ከ ሰላሳ ደቂቃዎች በላይ ታክሲ ውስጥ ቁጭ አልን)...ታክሲዋ በቆመችበት ስትራፖ ሊይዛት ደቂቃዎች ሲቀሯት😊 እንቅስቃሴ ጀመረች።
ሰው ገብቶ...ሞልቶ...ተትረፍርፎ ...ፈሶ ...የሞላ የማይመስላቸው ረዳቶች በጣት የሚቆጠር ሰው ብቻ ጭነው...ሌላ ተጓዥ ሲያናግራቸው ለስለስ ባለ ድምፅ "ሞላ ...በቂ ነው። አምላክ ይህችንም ይባርክልን 😜" ይላሉ ።
ዘና ብለን ተጓዝን። መንገዱ ብዙ ሰው አይታይበትም...ሰዎች ርቀታቸውን ጠብቀው ይንቀሳቀሳሉ.. .በፊት የነበረው ቸልተኝነት አሁን ላይ ቀንሷል.. ፊትህ ላይ ጨርክ ስትልደርግ "ታካብዳለህ እንዴ?" ይልህ የነበረ ከተሜ ሁላ"አካብዳለሁ !..." የሚል መፈክር በልቡ ተሸክሞ ይውተረተራል ።
አዲስ አበባዬ እንደ ለቅሶ ቤት ተፋዛለች...ዘራ ...በረሮ ...ድንች በኪሎ ...ጫማዋን በሰላሳ ምናምን የሚሉ ሰቅጣጭ ድምፆች አይሰሙም።
ይሄን እያስተዋልሁ በአንዱ ክፋይ ልቤ እፎይታ ቢሰማኝም ...ሸገርዬ ውጭ ስትዞር ተይዛ አባቷ በቀበቶ እንደገረፋት ህፃን ልጅ ኩርምት ብላ ሳያት ደግሞ አንጀቴ በሀዘኔታ ተላወሰብኝ ።
"ወንድም ካላስቸገርሁህ ሂሳብ ልቀበልህ? "
ዞር አልኩኝ...ረዳቱ ነው ...
የኔ ትሁት! ምፅ

@wegoch
@wegoch
@wegoch

#Michael Aschenaki
እንዴት ናችሁ? ስንቶቻችን ነን ስለ COVID-19 ስናስብ ስለ ጤና ባለሞያዎቻችን ያሰብነው?
በምን መልኩ እንደምንረዳቸው አስበናል? ያሰብኩትን እንካቹ...ከአንድ መረጃ እንደተረዳሁት የአፍ መሸፈኛ (Mask) በይበልጥ N-19 በመባል የሚታወቀው ለእኛ በቤት ውስጥ ለምንቀመጥ ሳይሆን Hospital area በይበልጥም ከበሽተኞች ጋር ንክኪ ያላቸውና በተለይም የአየር ግፊት (pressurized air) የሚጠቀሙ የህክምና መሣሪያዎች ያሉበት ክፍሎች ውስጥ ለሚሰሩ እንደሆነ ሰማሁ።ታዲያ የሁሉም ሀኪም ጥያቄ የሆነው የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል (mask) እና glove እጥረት በምን እና ምን ታጥቀን የመጣውን ጉድ እንዋጋ እንደሆነ ከብዙኃኑ አንደበት እንደሰማችሁ ጥርጥ ር የለኝም። ታድያ እንዴት እንደግፋቸው? ጥሩ ጥያቄ ነው።
አብዛኞቻችን COVID-19 ወደ ሀገር ቤት የመግባቱ ዜና ከተሰማ ጀምሮ እንዴት፣ መቼ እና የት መጠቀም እንዳለብን ሳናውቅ ቤታችን አከማችተነዋል ፣አሁን ግን ቢያንሰ ሆስፒታል ገብተን በሽታውን ባንዋጋም ሊዋጉልን የገቡትን ሀኪሞቻችንን ትርፍ የለን ካለን ላይ በመስጠት በቂ የመከላከያ መሣሪያ አስታጥቀን እንሸኛቸው ።።።በነገራችን ላይ አንድ ሃሳብ አለኝ !! ነገሮች እየከፉ ሲሄዱ የማይዘጉ የንግድ ቦታዎች ይኖራሉ ለምሳሌ እንደ supermarket,pharmacy and banks.
የእናንተን አስተያየት እና መነሳሳት አይተን እነዚህ ከላይ የጠቀስኩዋቸው ቦታዎች ማንኛውም ካለው ላይ የማካፈል እድሉ ያለው ኢትዮጲያዊ መከላከያዎቹን የሚያስቀምጥልንን ጊዜአዊ ማከማቻ ቦታ እንዲተባበሩን እኔና መሰል ሀሳብ ያለን በመነጋገር የምንጠይቅ ሙሆኑን ለመግለጽ እወዳለሁ ።
በቅን አዕምሮ ቅን ለሆነ ሐሳብ እየተባበርን አንድም የጤና ባለሞያ በመሳሪያ ጉድለት ላለማጣት እንትጋ።
ገንቢ ሀሳብ ልታጋሩን ምትፈልጉ በ0953932279 ይደውሉ።
Share በማድረግ ሀሳቡን እንጋራው። share on pages

@wegoch
@wegoch
......
ካለንበት ሁኔታ ጋር የተያያዙ አንዳንድ የእንግሊዝኛ ቃላትን ወደ አማርኛ ለመመለስ የሚደረጉ ጥረቶችን አያለሁ ፤ ባህላችን ለበሽታ እንግዳ ባለመሆኑ ላዳዲስ በሽታዎችና ልምዶች ካልሆነ በቀር አዲስ ቃል መፍጠር አያስፈልግም ፤ የነበረውን ባግባብ መጠቀም ይበጃል፤ ለምሳሌ እኒህን እንሆ! plague = ቸነፈር ( የቃሉ ምንጭ ነፈረ ነው፤ በሽታው ያደረበት ሰው ገላው ላይ የመንፈር ምልክት ስለሚያሳይ ፤ ከዚያ የወጣ ስም ነው፤ ) Epidemic= ወረርሽኝ፤ ኩዋራንቲን የሚለውን ዘመኑ ፈትቶ የለቀቀብንን ቃል አንዳንዶች ወሸባ( sic) ብለው ተርጉመው ሲጠቀሙበት አያለሁ ፤" ውሸባ መግባት " ባንድ ክፍል ውስጥ ተቀምጦ መታጠብና መታጠን ነው፤ ከምቾትና ከፈውስ ያለፈ አላማ የለውም ! በዛሬ አጠራር steam bath ከምንለው ጋር ይቀራረባል፤ በተለይ ቁርጥማትና ሽፍንፍን በሽታ የነበረባቸው ጌቶችና እመቤቶች ውሸባ የመግባት ልማድ ነበራቸው ፤ ምናልባት ከምስራቃውያን የተቀዳ ባህል ሳይሆን አይቀርም ፤ አንድ የተጠመቀ የቱርክ ጥበበኛ፤ የሸዋ ባላባት ለነበሩት ሳህለስላሴ ውሸባ እሚጠመቁበት ባኞ እንደገነባላቸው ተነግሮናል፤ ኩዋራንቲን የሚለውን ቃል አማርኛ ፍቺ “ቀሳ “ ነው፤ ኩዋራንቲን ላይ ያለ ሰው ደግሞ” ቀሳ ወጣ” ይባላል፤ ጥቂት ወዳጆቼ ቃሉን በትክክል ሲጠቀሙበት አይቼ ተደስቻለሁ ! ጉዳዩን ለማጥራት አለቃ ደስታ ተክለወልድ ከዛሬ አምሳ አመት በፊት ባሰናዱት መዝገበቃላቸው ላይ ያሰፈሩትን ልጥቀስ “ ቀሳ፤ ብቻ ለብቻነት ፤ፈረንጆች ካራንቴን ከሚሉት ጋር ይስማማል” ( መዝገበ ቃላት፤ ገፅ 1119) ይላል ወንድማችሁ፤ ኢጆሌ ማንኩሳ ከቀሳ!

[በእውቀቱ ስዩም]
@wegoch
@wegoch
ከዓመታት በፊት ብዙዎች ወረርሽኝ ይነሳል ብዙ የዓለም ህዝብ ያልቃል ተዘጋጁ እያሉ አባቶች ሲናገሩ ይሄ ተረት ነው የደብተራ ወሬ ጥንቆላ ወዘተ እያሉ ያለምጡና ያጣጥሉ ነበር:: ዛሬ የተባለው ደረሰ:: አሁንም ይህን ፈታኝ ጊዜ ለማለፍ አባቶች የሚመክሩትን ምክር እየናቀ የ"CDC" መድኃኒት ይናፍቃል:: ልንገርህ : ከተፈጥሮ ውጭ የሆነ መድኃኒት የለም:: የኛ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ደግሞ ተፈጥሮን ጠንቅቀው የተረዱ ናቸው:: የአበውን ቃል እንስማ! #ምክራቸውን_እንተግብር_እንጠንቀቅ :: መፍትሔ እየፈለጉ ያሉ የመድኃኒት ሊቃውንቶቻችንን በፀሎት እናግዛቸው::

@wegoch
@wegoch
2024/09/25 20:28:15
Back to Top
HTML Embed Code: