Telegram Web Link
ሰአት ከ8_11
እኛ ጠግበን እያደርን ሌሎች መራብ የለባቸውም በሚል መሪ ቃል ቅዳሜ በአዲስ አበባ
ስታዲየም(ትሪቡን) የምግብ፣የሳኒታይዘር፣የሳሙና እና ሌሎች አቃዎችን የመሰብሰብ
ፕሮግራም ተይዟል ይሄንንም ማህበረሰቡ ከተጫዋቾች ማህበር ጋር በመተባበር ቅዳሜ
(ነገ)የሚጀምር ሲሆን የቅዳሜ ሰብሳቢዎች ተረኛ
1.ዳዊት እስጢፋኖስ
2.መስዑድ መሀመድ
3.እድሉ ደረጄ
4.ጀማል ጣሰው
5.ኤልያስ ማሞ
6.አማኑኤል ዮሀንስ
7.አቡበከር ነስሩ
8.አህመድ ረሺድ ይሆናሉ
ሰብሳቢዎቹ ራሳቸው በሚችሉት አቅም የድርሻቸውን ይዘው ይመጣሉ...ማንኛውም ሰው
መጥቶ ወገኑን ይርዳ መምጣት ያልቻለ በኢትዮጵያ ፉትቦለርስ አሶሴሽን አካውንት
የአቅሙን ገንዘብ ያስገባ ለሀሳብዎ፣ለጉልበትዎ ለገንዘብዎ ላበረከቱት ነገር ምስጋናችን
ላቅ ያለ ነው ንግድ ባንክ 1000299142788 እሁድ የጊዮርጊስ ቤተሰብ ሰብሳቢ
ይሆናል

@Nagayta
Audio
#ተመላላሽ _ሰይጣን
(በዘውድ አለም ታደሰ )
@wegoch
@wegoch
@wegoch
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ለህፃናት በተደጋጋሚ ስለኮሮና ቫይረስ መናገር አላስፈላጊ ጭንቀት ሊፈጥርባቸው ይችላል።

እስቲ በዚህ ሙዚቃና ዳንስ እንዴት እራሳቸውን መከላከል እንደሚችሉ እናጋራቸው

#safehands #unicefethiopia


@wegoch
@getem
@seiloch
@wegoch
የህንድ ፊልምን ሳይሆን የህንድ መንግስትን ተከተል

(በእውቀቱ ስዩም)

የሚሆነው አይታወቅምና ሀቅ ሀቁን ተናግሬ ልወገድ !


ድሮ ኤቺ አይቪ ባገራችን ገባ ገባ ብሎ ስታራቴጂያዊ ቦታዎችን በተቆጣጠረበት ጊዜ ህዝቡ ናላውን የክህደት ሞድ ላይ አድርጎት ነበር ፤ ዋናው መተላለፍያ መንገድ ግብረስጋ ግኑኝነት ሆኖ ሳለ ሚድያዎች ባልተቀቀል መርፌ የመጠቀም ጉዳት ስለሚያመጣው ጉዳት ሲዘበዝቡ ነበር እሚውሉት :: እኔ ራሴ ያስራሁለተኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ፤

“የወደቀ ምላጭ አታንሱ አትጠጉ
መርፌ ሳይቀቀል ይቅር አትወጉ”

የሚል ስንኝ ያለበት የቸከ ግጥም ፅፌ ተሸልሚያለሁ:: ( በኔ እንኩዋ አይፈረድብኝም፤ በጊዜው ስለምላጭና ስለመርፌ እንጂ ስለግብረስጋ እማውቀው ነገር አልነበረም )

የብዙ ሰው አእምሮ ፤ግብረስጋን የመሰለ የህይወት እና የደስታ ምንጭ የገዳይ ቫይረስ መተላለፍያ ይሆናል ብሎ ለመቀበል ዝግጁ አልነበረም :: በተፈጥሮ ደባሪ ሀቆችን ባላየ እንድናልፍ ሆነን ነው የተቀናበርነው !



መንግስት ዘንበል ሲል፤ ክፉ ዘመን ሲመጣ እብሪትንና አላዋቂነትን አስተባብረው የያዙ፤ የግዜር ወኪል ነን ባዮች መደረኩን እንደሚቆጣጠሩት የታወቀ ነው ፤ የህዝብ ግራ መጋባትና ጭንቅ እንደሻ ለማውራት ይመቻቸዋል ! የተሸበረ ህዝብና በጅምላ የሚሸሽ ሰራዊት መንገድ አይመርጥም! መውጫ ብሎ ያሰበው ላይ ሁሉ ይረባረባል!

እነሱን ትተን ስለ አሪፍ ሰባኪዎች ብናወራ ይሻለናል፤ በጣም የማከብራቸው መርጌታ ክፍሌ በቅርቡ በሰጡት ኦንላይን ስብከት የሚከተለውን ድንቅ ስብከት ሰብከው አስደምመውኛል፤

“ እግዚያብሄር በየዘመኑ በተለያየ መንገድ ይሰራል፤ በሙሴ ዘመን በእጣን በእሳት ይፈውስ ነበር፤ አሁን የሚፈውሰው በሳሙና እና በውሃ አድሮ ነው፤ ደሞ ተበተን ከተባልክ ተበተን! እግዜር የጉባኤ ብቻ ሳይሆን የብህትውናም አምላክ ነው፤ እንጦስን ታውቀዋለህ! ብቻውን በምድረበዳ የሚኖር ባህታዊ ነበር! እና ልጄ!
ከመሆን የህዝብ ጦስ !
ተነጠል እንደ እንጦስ ! "

የህንድ ፖሊስ ትምጣብኝ! በየቤትህ ገብተህ ተከተት ብላ አወጀች! እነ ኩማር ደሞ ቤት መቀመጥ ደበረን ብለው፤ አደባባይ ላይ በሞተር ሳይክል፤ ሽር ብትን ሲሉ ፖሊስ ከተፍ ብላ በወደላ ጨፈቃ እያበራየች ወደ ጎሬው አስገባቺው ! አንዱ ህንድማ በሞተር ሳይክል መጥቶ ዊልቼር ተመለሰ፤፤ “ በቸር እንጂ በዊልቸር ከመመለስ ይጠብቅህ” ይላሉ የህንድ እናቶች ልጆቻቸውን ሲመርቁ! እንዲያ ነው እንጂ! ቀውጢ ዘመን ቀውጢ ውሳኔ ይጠይቃላ!

ባለፈው ፑቲን የሞስኮብን ህዝብ አስቦክቶ ወደ ቤቱ ለማስገባት አንበሳ ፈቶ ለቀቀ የሚል አጉል ወሬ ሰምቼ ነበር ፤ እና አገር ቤት ደውየ ባለንጀራየ ምኡዝን “ አብይ አህመድ አንድ አስር አንበሶች ከነጭ ሳር ፓርክ አምጥቶ አዲሳባ ላይ ቢለቅ ምን ይፈጠ ር ይመስልሃል ?” አልኩት ፤

“ ህዝቡ አንበሶችን አልምዶ እንደ ሀረር ጅብ ተሰብስቦ ይዝናናባቸዋል! “
@wegoch
@wegoch
@wegoch
ነጭ እኮ አይደንግጥ?!
.
«ዘውድአለም ታደሠ»
.
አውስትራሊያ እስካሁን በኮሮና ጉንፋን 249 ሰዎች ተይዘው
የሞቱት 3 አዛውንቶች ብቻ ናቸው። ነገር ግን ህዝቡ በተጋነነው
የሚዲያ ወሬ panic ስላደረገ ልክ ፊልም ላይ እንደምናየው
ባለው ብር ሁሉ እህል እየገዛ ሱፐርማርኬቱን ባዶ አድርጎታል።
በግፊያው አካል ጉዳተኞችና አዛውንቶች እየተረጋገጡ ስለሆነ
ሱፐርማርኬቶቹ ተጨማሪ ሴኪዩሪቲዎች ለመቅጠር ተገድደዋል።
ምግብ ተርፎ በሚደፋባት ሃብታሟ አወስትራሊያ ባሁን ሰአት
ዘይት እንደሜርኩሪ እያደባደበ ነው። እግዚኦ አትሉልኝም ታዲያ?
በሽታው እጅ በመታጠብና ንክኪን በመቀነስ በቀላሉ የሚቆም
ቢሆንም የምእራባውያን ሚዲያ የቻይናን ኢኮኖሚ ለማንኮታኮት
ቻይና ላይ ኮሮና የተባለ መአት ወረደ ብለው አራገቡ። የቻይና
የንግድ እንቅስቃሴ በአንድ ቀን ወደቀ። ግዙፍ ካምፓኒዎቿ
ሰራተኛ በተኑ። ለአለም ገበያ ለማቅረብ ያመረተቻቸውን ምርቶች
መጣያ ስታጣ በመርከብ ወደቬትናም ወስዳ በርካሽ ጣለቻቸው!
አሁን የሆዷን በሆዷ ይዛ ነዋሪው ከቤቱ እንዳይወጣ በሩን
በመበየድ ጭምር አግሬሲቭሊ በሽታውን ተቆጣጠረችውና ኳሱን
መልሳ ወደአሜሪካና ወደአውሮፓውያኑ ጠለዘችው። እነአሜሪካ
ቻይናን ለማንኮታኮት ከሚገባው በላይ አጋንነው ያወሩለት ኮሮና
ወደራሳቸው back fire አደረገ! ይኸው ዛሬ በአመት 39 ሺ
ሰው በጉንፋን ብቻ የሚሞትባት አሜሪካ ህዝቧ ፓኒክ ስላረገባት
ብቻ ሳትወድ በግድ state of emergency ስታውጅ ቻይና
ፈገግ ብላ ታያታለች።
የአሜሪካና የቻይና trade war መጨረሻ ላይ የደረሰ
ይመስላል። ተንታኞቹ እንደሚሉት ከ 9/11 ጥቃት በኋላ ስቶክ
ማርኬቱ እንዳሁኑ ወድቆ አያውቅም። ኮንሲኩዌንሱ የኛን የሰፈር
ወንዝ ዳር ያለች ጀልባም ከአለት ጋር ማላተሙ አይቀርም።
ኦልሞስት ሁሉንም ነገሮች import እናደርጋለን። ከውጪ
የምናስገባው ከምርታችን ጋር በስልክም አይገናኝም። ( 3
billion ገደማ export እያረግን ለ import 11 billion
የምናወጣ ጉዶች ነን)
ቻይና በእርግጠኝነት በመጪው ጥቂት ቀናት ውስጥ ሪከቨር
አርጋ እንደመንግስቱ ሃይለማሪያም “ለምሳ ያሰቡንን ለቁርስ
አደረግናቸው” ብላ ወደሽቀላዋ መመለሷ አይቀርም።
አሁን ላደጉት ሐገራት በሽታው ሳይሆን ድንጋጤው ነው አስጊ
ደረጃ ላይ የደረሰው። ሰውን መቆጣጠር አቅቷቸዋል። ነጭ ለካ
እንዲህ ድንጉጥ ነው? እኛኮ ሴንትራል አፍሪካ ያ አስቀያሚ
ኢቦላ የተባለ በሽታ ሲከሰት እንዲህ አልቀወጥነውም። ነጮቹ
ግን ፍርሃታቸውን ማኔጅ ማድረግ አልቻሉም ነው የሚባለው። ለ
toilet paper ተናንቀው ሲደባደቡ ሁሉ አይተናል። ጣሊያን ሼባ
ስለሚበዛ ነው መሰለኝ በዛ ያለ ሰው ጭሮባታል። ሁለት
ጣሊያናውያን ኢትዮጵያ ለጉብኝት መጥተው መመለሻ ግዚያቸው
ሲደርስ “ተመልሰን አንሄድም” ማለታቸውን ስንሰማ «ቧ ግዜ
ለኩሉ» ብለናል!
እናማ ባሻዬ እንደነገርኩህ ነው ... ከአቅሙ በላይ የገዘፈው
ኮሮና እስካሁን 160 ሺ ሰዎችን ይዞ ስድስት ሺ ሰው ገድሏል።
ከ70 ሺ በላዩ ደግሞ ድነው ወደቤታቸው ሄዱ። ትናንት ቢቢሲ የ
104 አመት አዛውንት ከኮሮና አገገሙ ብሎ ፒፓውን ለማረጋጋት
ሞክሯል (“አንቺው ታመጪው አንቺው ታሮጪው” አለች ቢዮንሴ
)
እስካሁን አንድ ጥቁር ብቻ ነው የሞተው። (እሱም ሌላ ተጓዳኝ
በሽታ ነበረበት አሉ) ፈይሳ አዱኛ በኪነጥበቡ ጋርዶናል አባዬ።
ለማንኛውም ህዝቤ ሆይ ውሃ አይገድልም እጅህን ታጠብ።
እንደእቁብ ዳኛ ያገኘኸውን አትጨብጥ። ብትችል ባውቶቢስ
አትጠቀም (ዎክ እኮ ለጤናህም ጥሩ ነው) የኮሮና ሚመስል
ምልክት ካየህ ወደሰው ሳታስተላልፍ ሳትጨናነቅ ሃኪም ጋር
ደውል። ታክመህ ትድናለህ። በቀላሉ ለሚያገግም በሽታ
አምቡላንስ ሰብረህ የምታመልጠውኮ አለቅጥ አጋነው
ስላስደነበሩህ ነው። ንፅህናህን በመጠበቅና ቶሎ በመታከም
ሃላፊነትህን ተወጣ! ከዚህ ውጪ ግን አታካብድ! ከሰማይ
የወረደ መቅሰፍት አይደለም። ኮሮና በሽታም፣ ፖለቲካም፣
የኢኮኖሚ ጦርነትም፣ የሚዲያ ቢዝነስም ነው!
@wegoch
@wegoch
@wegoch
Forwarded from Mykey (Mikiyas Liyew Mykey)
Ethiopia Professional Footballer Association
#Covid19virusAwarenessmessage
#Challenge
March 2020
@Mykeyonthestreet
🎧ቀኑ ሲመሻሽ ብለሽ አትፍሪ ፋኖስ የለም፣
ፀሃይ ነሽ እና ለዚህች አለም!🎧🎼

ይህ ግጥም ከድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን የዘፈን ግጥም ላይ ተቀንጮቦ የቀረበ ነው፡፡ "አይዞ ልቤ" ይላል የሙዚቃው ርዕስ፡፡
.
እናም በዚህ ሁለት ስንኝ ውስጥ የምናገኘው አንድ ትልቅ አሳብ አለ- #ፀሃይነት ወይንም ትልቅ ብርሃናዊ ሃይል በልባችን እንዳለ በደምብ ይነግረናል፡፡
.
ሕይወት በተለያዩ መንገዶች እና በተለያዩ እርምጃዎች አጅባ በማናውቀው የጨለማ አለም ውስጥ ልታስገባን ትችላለች፡፡ ሁሌም ከጨለማ ማግስት ብርሃን እንዳለ ግን እንመን፤ የነበርንበት ጨለማ ጨለማነቱን ቀጥሎ እኛነታችንን የማጨለም አቅም የለውም፤ ምክንያቱም እኛ ጋር ያለው የፀሃይነት ባህሪይ አይደለም ያለንበትን የኛነታችንን ጨለማ ቀርቶ አለምን ማብራት የሚችል ብርሃን ስለሆነ፡፡

ጨለማ ውስጥ ስንሆን ፋኖስ ይዘን አለመገኘታችን ሊያስጨንቀን አይገባም፡፡ የፋኖስን ብርሃን በእጅጉ የሚያስንቅ የፀሃይ ወገግታ በልባችን አለና፡፡
.
ስንጨነቅ ፣ ተስፋ መቁረጥ ሲያደባብን ፣ እምነታችን ሲጠፋ ፣ ፍቅራችን በጥል ሲበረዝ በርግጥም ጨለማው ውስጥ ነን እና የውጪውን ፋኖስ ከመለመን ወደ ልባችን እንመልከት፡፡

አዎ ዛሬ በሃሳብም በአካልም ደክመናል፡፡ ነገር ግን ነገ የተሻለ ቀን ይመጣል፡፡ በርትተን ወደ ፈጣሪያችን እንፀልይ፡፡

#እጃችን_ደጋግመን_በሳሙና_እንታጠብ
#ከሰዎች_ጋር_ያለንን_ርቀት_እንጠብቅ
#የቫይረሱን_ምልክቶች_ስናይ_በቶሎ_ወደ_ጤና_ተቋማት_እንሂድ
#አስገዳጅ_ነገር_ካልሆነ_ከቤት_አንውጣ
#በመንፈስ_ጠንካሮች_እንሁን
@wegoch
@wegoch
@wegoch
በቀደም ለት ማታ ቡና ከምጠጣበት ቦታ ወደ ቤቴ እየተጣደፍኩ እየሄድኩ እያለው አንድ እድሜው 10 እስከ 12 የሚገመት ጎዳና ቤቱ የሆነ ልጅ እግሬ ላይ ጥምጥም ብሎ ሳንቲም ይለምነኝ ጀመር ፡፡ ይሄ አይነቱ ልመና በምኖርባት ከተማ በጣም የተለመደ በመሆኑ በመሰልቸትም ጥድፊያ ላይ ስለነበርኩም (እንደ ምንክንያት)ለልመናው ቦታ አልሰጠሁትም ነበር ብቻ የሆነው ሆኖ ሳንቲም ሳልሰጠው ከእግሬ ላይ አስነስቼው ወደ መንገዴ ...ጥቂትም ሳልራመድ አባት አባት አለኝ ዞርኩ ኮሮና ቫይረስ ስለገባ ምግብ ቤቶች የተራረፈ ምግብ (ቡሌ) ስለማይሰጡን እኮ ነው አለኝ ፡፡ ያማል ፡፡ያለኝን ሰጠውት ወደ ቤቴ እየሄድኩ መንግስት ምን እያሰበ ነው ብዬ እንጠይቅ ውስጤ አስገደደኝ እነዚህ ልጆች ጎዳና ላይ ውለው ጎዳና ላይ እንደሚያድሩ የሚጠፋው ያለ አይመስለኝም እንደ በሽታው አካሄድ ከሆነ ደግሞ ቢያንስ ልጆቹ እንደ ዜጋ ለጊዜውም ቢሆን ተመርምረው አንድ ቦታ የሚቀመጡበት መንገድ አይታሰብም ወይ እነዚህ ልጆች ከባለሀብቱ እስከ ወጣቱ የማይነኩት ሰው አለ ወይ የማይሄዱበት የማይንቀሳቀሱበት ስፍራ አለ ወይ በሽታውን ለማሰራጨት ከፍተኛ እድል እንዳላቸው ሳይታሰብ ቀርቶ ነው ወይ ? እነሱስ ቢሆን ልብሳቸው ቢያድፍ ሰውነታቸው ቢቆሽሽ ሰው አደሉ ወይ ዜጋ አደሉ ወይ ?ጥያቄ ይሆንብኛል ፡፡ነገሮች እንዴት እየሄዱ እንዳሉ ያሳስበኛል ሀገሬን እወዳለው ደሜ አጥንቴ ገለመሌ ቅብርጥሴ ሲል የነበረ ሁሉ ማንነቱን ክዶ ቃሉን በልቶ ለገንዘብ ሲያደገድግ ሳይ ያሰጋኛል ገንዘቡን ሀይማኖት አድርጎ ሲያጎበድድ ሲያይ ያመኛል ፡፡ይገርማል እንዴት ሰው ነኝ በዛ ላይ ሀገሬን ወዳለው ከሚል ሰው እንደዚ አይነት ተግባር ይፈፅማል ይሉኝታ እሴቴ ነው መገለጫዬ ከአባቴ ቃል ውልፊት ..ለኔ ያለው የትም አይሄድም.. የኔ እድል ከኔ ውጪ የት ገብታ ..ሲል የነበረው ሁሉ ለገንዘብ ሲያጎበድድ ማየት ይቀፋል ፡፡በምን ሂሳብ በምን ህግ አንድ እቃ 80 እና 90 በመቶ ይጨምራል በምን አይነት ልኬት እራሱን ቢለካ ፊት ለፊት አስቀምጦ የለም ጨርሻለው ለማለት የበቃው ?ያስደነግጣል ፡፡ሲደመር መንግስት እያደረገው ያለውን ጥንቃቄ ባልጠላም ቡዙ የታሰበበት አይመስለኝም ፡፡እንዴት ?ቫይረሱን ለመከላከል ታስበው እጃችንን እንታጠብበት ዘንድ የተቀመጡት ሮቶዎች የተቀመጡበት አከባቢ ያለው ጭንቅንቅ ለታክሲዎቹ የወጡት አዎጆች ከመሀል ከተማ እንደተንቀሳቀሱ አለመስራታቸው ሁሉ ያሳስባል ፡፡ከህግ ውጪ የምግብ ሸቀጦች ላይ ሁሉ የተጨመሩት የዋጋ ጭማሪዎች ያሳስባሉ ፡፡ያሰጋል ፡፡ስለዚህ አስብ ታክሲ ስትሳፈር የምትይዘውን ብረት የገንዘብ ልውውጦችህ ካፌ ቁጭ ስትል ብና የምታማስልበት ማንኪያ የበርህ እጀታ የስልክህ የላይኛው ክፍል የተቀመጥክበት ወንበር ብቻ ተወው ነገሮችህ በሙሉ ለኮሮና ቫይረስ መስፈሪያ የሆኑ ናቸው ፡፡ያገባቸዋል የሚባሉና የሆነ ለውጥ ሊፈጥሩ የሚችሉ ሰዎች በአብዛኛው ጆሮ ዳባ ልበስ ስላሉ እራስህን /ሽን/ጠብቅ ጠብቂ "አትጨባበጡ" ባለባጃጆች እና ባለ ታክሲዎች ከገንዘብ ውጪ አስቡ "ተራርቃቹ ተቀመጡ"ባለ ሀብቶች ብትችሉ ምናችሁም አደለም እና ሰርቪሶቻችሁን ለህዝቡ በማሰማራት ተባበሩ ከወሬ ያለፈ ነገር ለመስራት ተንጠራሩ መንግስት መደረግ ያለበትን ሁሉ ለማድረግ ይሞክር አስገዳጅ መመሪያዎችን ያውጣ ግን ባንተ በኩል የሚጠበቅብህን አድርግ ቢያንስ እራስህን ከጠረጠርክ ተመርመር ከሰው ጋር ላለመገናኘት ሞክር በተረፈ ሳኒታይዘር (ውድ ነው ላታገኝም ትችላለህ )ጓንት ተጠቀም እጅህን ታጠብ (ውሀ ከየት አምጥቼ እንዳትለኝ)ለማንኛውም ሞክር ከዛ ፀሎት እና ዱአ አድርግ ወደ ፈጣሪህ ጩህ

እግዜር ይጠብቀን
አላህ ይጋርደን

አሜን !!
ንጉስ ደረሰ
@wegoch
@wegoch
@wegoch
የጤና ባለሙያዎች ራሳቸውን ከኮሮና ቫይረስ እንዲጠብቁ የሚለበስ ልብስ (PPE) ያዘጋጀው ወጣት ኢትዮጵያዊ ኢንጂነር!

... ሁሉም በየሙያው ይረባረብ! ይህ የገጠመን ጠላት ሁላችንንም የሚፈትን ነው። አገራችንን ለማዳን ኃላፊነቱ የጤና ባለሙያዎች ብቻ ከመሰለን ተሳስተናል። ሁሉም በየእውቀቱ፣ በየሞያው የበኩሉን አስተዋጽኦ ማድረግ አለበት። ዛሬ የማስተዋውቃችሁ ኢንጂነር ሳሮንም ለሁሉም አርአያ መሆን የሚችልና ሊደገፍ የሚገባው ወጣት ነው። ይህ የምታዩት ልብስ በራሱ ተነሳሽነት ጥናት አድርጎ፣ በራሱ ወጪ ያዘጋጀው ነው። ለቫይረሱ ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ ጤናው ላይ የሚሰሩ ያገሩን ልጆች ለማገዝ ካለው መልካም ሐሳብ ነው ይህን ያደረገው። በፎቶው ላይ ለብሶት የምታዩትን አንዱን ልብስ ከውጭ ለማስገባት ከ2000 እስከ 3000 የኢትዮጵያ ብር ያስፈልጋል። ኢንጂነር ሳሮን ግን ዋጋውን በ1/4ኛ ቀንሶት በ500 የኢትዮጵያ ብር ገደማ አንድ የፕላስቲክ ልብስ ማዘጋጀት እንደቻለ ነው የነገረኝ። ከተማሩ አይቀር እንዲህ ላገር መትረፍ ያኮራል።
*እንግዲህ መንግስትም ሆነ ባለሐብቶቻችን ይህንን ጎበዝ ወጣት ለማበረታታት ብቻ ሳይሆን የብዙ ሺህ ሐኪሞች፣ ነርሶችና የጤና መኮነኖችን ጤና ለመጠበቅ ስትሉ እንድታግዙት እጠይቃችኋለሁ።
እሱን ቀጥታ የምታገኙት በስልክ ቁጥሩ 0917807480 ሲሆን ጥያቄ ካላችሁም በውስጥ መስመር ልትጽፉልኝ ትችላላችሁ።
ይህን ያነበባችሁ በሙሉ ሼር እያደረጋችሁ፣ እየደወላችሁ አቅም ላላቸው ሰዎች እንድታዳርሱልኝ፤ ወጣቱንም እንድታበረታቱት ይሁን!
#የኔትውልድ
............ (ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አዕምሮ)

@wegoch
@wegoch
 

  ### ከድሮም ጭምር ነው ###


አባት እና ልጅ እናቲቷ ከሞተች በኃላ መንገድ ላይ ውለው ማደር ከጀመሩ ሠምበትበት ብለዋል ፡፡ ድሮም የአቅሙ ጉዳይ ያን ያክል አጥጋቢ አልነበረም እና እናቲቱ ከዚህ አለም ስትለይ ደግሞ የቤቱን ጣጣ መቋቋም አቅቷቸው ቢያንስ የቤት ኪራይ እናሸንፍ ብለው ከድልድይ ሰር ኬንዳ ወጥረው ሂወታቸውን መምራት ቀጠሉ ፡፡ ለተወሠነ አመታት ከዚች ድልድይ ሥር ቤታቸው ክፉውንም ደጉንም ሲያፈራርቁባት ኖሩ፡፡ በአንድ ወጥመደኛ ቀን ትኩሥ ወሬ በከተማይቱ ተሠማ ፡፡ ሁሉም ወሬውን ያጧጡፈዋል ፡፡ ማብረጃ የሌለው ወሬ ሆነ ፡፡ ውሰድ መልስ ፣ ግጥም ሁሉም አፍ ለአፍ እንች እንካ ፤ እኔ በደንብ አብራረዋለሁ ሠለ ወቅታዊው ጉዳይ ይል ጀመሯል የከተማይቱ ወጣት የለ ፤ ሽማግሌ የለ ፤ አሮጊት የለ ፤ ህፃን የለ ፡፡ ከድልድዮ ስር የሚኖሩት አባት እና ልጅ ግን ሁሉም በሚያቦካው ወሬ ደንታ አልሠጡትም ፡፡ የራሳቸውን ፀጥ ረጭ ያለ ሂወት ይገፍሉ እንጅ ፡፡ አንድ ቀን በጥዋት ግን ደንገት ያልጠበቁት ክስተት ከተፍ አለ ቤታቸው ፡፡ ሁሉም የከተማይቱ ህዝብ ለአስራ አምስት ቀን ቤታቸው እረፍት እንዲያደርጉ፡፡ እንዳይወጡ የምትለውን መልክት ይዛ ቤታቸውን አንኳኳች ፡፡ በነገሩ የተደናገጠው ልጅም አባቱን " አባየ ምን አጠፋን ?" ብሎ ጠየቀው አባቱን ፡፡ 

" ወይ ልጀ ለአስራ አምስት ቀን መንገድ ላይ መሆን አይቻልም ይላሉ ፡፡ በትንፋሽ የሚተላለፍ በሽታ ስለመጣ ሁላችሁም በየቤታችሁ ግቡ ተብሎ ስለተነገረ እኛም መስመር እንድንይዝ ፤ ከዚህ ቦታ እንድንወገድ ነው መልክት ያስተላለፈ " አለ አባት እጥፍ ባለ አንጀቱ ፡፡ 

"እና የት ብለን እንሠደድ አባ ? " አለ ልቡ እየተሸበረ ፡፡

" አይ ልጀ ሀገር ሲከፋ ወደ ህዝብ ትሸጎጣለህ ፤ ህዝብም ሲከፋ ወደ ምድረ በዳ ወደ ሌላ ቦታ ትሰደዳለህ ፡፡ ሁለቱም ከከፉ ግን ወዴት ይደረሳል ፡፡ 


በድሮ ጊዜ ምን ተደረገ መሠለህ ፤ ሠውየው ገበያ ውሎ ሲመጣ ፤  አንድ ማዳበሪያ ሙሉ እህል ሸምቶ አህያውን ጭኖትም ነበር ፡፡ ገበያው እሩቅ ከመሆኑም የተነሳ ቤቱ ሳይደርሥ ይመሽበታል ፡፡ መንገድ ላይ አንድ አስቀያሚ ገጠመኝ አጋጠመው ፡፡ ከመጨለሙ የተነሳ መንገዱን ሲሄድ የወንዝ መቀመቅ ላይ አህያው እስከ ተሸከመው ጭነት ገብቶ ተሠነቀረ ፡፡ ሰውየዉ አህያውን ሊያወጣ ቢለፋ ፣ ቢነሳ ፣ ቢወድቅ ፣ ቢታገልም አልሆንልህ አለው ፡፡ በዚህ ጊዜ ምን አልባት የሚረዳኝ ባገኝ ብሎ እሪ ብሎ ጮኸ የሚደርስለት ግን ጠፋ ፡፡ የአካባቢው ሠው ከፍቶ ነበር እና ከገደል ማሜቱ ውጭ ምንም ድምፅ የሚመልስለት አልተገኘም ፡፡ በሁኔታው ግራ የተጋባው ሠውየ አህያው እንደ ተከተተ ከአረግረጉ ፈንጠር ብሎ በጊዜው ፣ በአካባቢው ሠው መክፋት ትክን እያለ ከደረቁ መሬት ላይ ሄዶ ቁጭ አለ ፡፡ ከትንሽ ቆይታ በኃላ ሁለት ጅብዎች እየተሳሳቁ መጡ ፡፡ ሠውየው ግራ ተጋባ ፤ ፈራ ፤ በጣም ተንቀጠቀጠ ፡፡ ግን አማራጭ የለውም እና ምራቁን ውጦ ፤ ጥርሱን ነክሶ ተቀመጠ ፡፡ ሁለቱ ጅብዎችም የተከተተውን አህያ ከእነ ጭነቱ መንጥቀው አወጡት ፡፡ ከአወጡት በኃላ ሠውየው ሲታያቸው ጅብዎች ለቀውለት ሄዱ ፡፡ ሠውየውም ፈጣሪውን እያመሠገነ አህያውን ይዞ ወደ ቤቱ ሄደ ፡፡ እና ልጀ በዚያ ጊዜ ከሠው ልጅ እንሥሣቶች አራውቶች የሚሻሉበት  ነበር ስትመለከተው ፡፡ ከዚህ ሲያባርሩን ከሰው መንደር እንዳንጠጋ በራቸውን ቀርቅረዋል ፣ ሠፈራቸውን አጥረዋል ፡፡ ችግር በአንድ የሚቀር መስሏቸው መካረሚያቸውን ምግብ ሸምተው ሶፋቸው ላይ ፈልሰስ ብለዋል ፡፡ ሂዱ ብለው ከጨከኑብን እንልቀቅ እና የሚራራ እንስሳ አሊያም አራዊት ከገጠመን ከእነርሱ ጋር እንጠጋለን ፡፡ እንጅ የሰው ነገር እማ አይተነው አይደለ ይኸን ያክል ጊዜ በኬንዳ ስንከራተት ፡፡ " ብሎ ጓዙን ይሸክፍ ጀመረ አባትም ፡፡

"እሽ አባ" ብሎ እያለቀሰ ቅራቅንቦውን ይሠበስብ ጀመር ልጅም ፡፡ 


ፈጣሪ ከሠው አውሬ ይጠብቀን!!!!




ከዘገዬ ታዴ

መጋቢት 22 / 2012

####################
@wegoch
@wegoch
[April 1]

ነገ የፈረንጆቹ የውሸት ቀን ( ኤፕሪል ፉልስ ዴይ)
መሆኑን ተከትሎ አንዳንድ ሀላፊነት የጎደላቸው
ሰዎች ሊፈጥሩት ከሚችሉት የሀሰት ወሬ እራሳችሁን ጠብቁ።

#በደህናቆዩ #በጥንቃቄይቆዩ
@getem @wegoch @seiloch
ይሄን መልክት ያስታወሰችን #ribka ናት እናመሰግናለን!
@wegoch
"....ብዙ ኢትዮጵያውያን ጉጉታቸው ነዳጅ ተቆፍሮ አልወጣም ነው። እኔ ደግሞ ነዳጅ ተቆፍሮ ከመውጣቱ በፊት ንዴታችንን ይውጣ እላለሁ። ብስጩ ህዝብ፣ እልኸኛ ህዝብ፣ ፈሪሀ እግዚአብሔር የሌለው ህዝብ፣ የማይግባባ ህዝብ... ነዳጅ ቢያወጣ የመኪና ፋብሪካ ሳይሆን የሚያቋቁመው፥ ሰይጣን #የክብሪት_ፋብሪካ ያቋቁምለታል፤ ክብሪት ያቃብለዋል።
.
አጼ ኃ/ሥላሴን ስንገለብጥ እኮ ሌባ ብለን አባርረናቸው ነበር፤ ቀጥሎ ለመጣ መንግስትም ስናጨበጭብ ነበር፤ ህዝቡ ደርግ ሲመጣ እኮ ሶሻሊዝም እግዚአብሔር የለም ለማለት እኮ ቄሱ ነው አስቀድሞ ካድሬ የሆነው። ይሄ መንግስት ሲመጣም በብሔር በቋንቋ ይደራጅ ሲባል ህዝቡ አጨብጭቦ ነው የተቀበለው፤ ነገም ሌላ ቢመጣ ለማጨብጨብ የኢትዮጵያ ህዝብ ለምን እንደሚያጨበጭብ
የሚጠይቀው አጨብጭቦ እጁ ከተላጠ በኋላ ነው። በጣም ችግር አለ። ምክንያቱም #አያነብም። ህዝባችን የጥቂት ፓለቲከኞች #የሀሳብ_መስጫ ሳጥን ነው የኢትዮጵያ ህዝብ። ጥቂት ፓለቲከኞች ሀሳባቸውን ያራግቡበታል።"
......
☞ መጋቢ ሀዲስ እሸቱ ዓለማዮህ በአንድ ወቅት ከተናገሩት
@wegoch
@wegoch
@wegoch
2024/09/25 09:18:38
Back to Top
HTML Embed Code: