Telegram Web Link
ቀስ የምትችለው የይለፍ ወረቀት ይዘህ ስትገኝ ነው፡፡ ደረጃ ስድስት... የይለፍ ወረቀቱ፣ ከመንግስት የሚሰጥ ሲሆን፤ ስምህን፣ ከየት እንደመጣህ፣ ወደየት እንደምትሄድና ጉዳይህ ምን እንደሆነ ይገልጻል፡፡ ቅርብ ለቅርብ የተሰደሩ የፖሊስ ኬላዎች አሁንም አሁንም ይፈትሹሃል፡፡ ያለ ፍቃድ ከተያዝክ 206ዩሮ ( 8000ብር አካባቢ) ትቀጣለህ፡፡ ያለፍቃድ የተያዝክ ህመምተኛ ከሆንህ ደሞ፣ ነፍስ ማጥፋት ወንጀል ተከስሰህ ከ1-12 አመት የእስር ግዜ ይጠብቅሃል፡፡
ዛሬ ሀገሬ እዚህ ደረጃ ላይ ደርሳለች፡፡
.
ወሬኣችንን ስንደመድም
ሀገራት በቸልተኝነት በግዴለሽነት ዜጎቻቸውን ከመጠበቅ ሲፎርሹ ማየት ያማል፡፡ የሚችሉትን ሁሉ ያላረጉ እንደሚቀጡበት ግልጽ ነው፡፡
ይህንን እያነበብክ ከሆነ ተለመነኝ፣ ለጤናህ ስትል የተነገረህን የጥንቃቄ እርምጃ ሁሉ ውሰድ፡፡ ስለጉዳዩ አላወራህም፣ ረስተኸዋል ማለት እሱ ረስቶሃል፣ በራሱ ግዜ ብን ብሎ ይጠፋል ማለት አይደለም፡፡ ማመን ያለብኝ አንድ ነገር፣ የጣልያን መንግስት-መንግስቴ- ይህንን በሽታ ለመቆጣጠር እጅግ የሚያስመሰግነው ስራ መስራቱን ነው፡፡ የተወሰዱት እርምጃዎች፣ ከልክ ያለፉና፣ ያልተመጣጠኑ ቢሆኑም፣ እጅግ አስፈላጊ ነበሩ፡፡ ስርጭቱን ለመቀነስ ያለው ብቸኛ መንገድ ይኸው ብቻ ነው፡፡ ቻይናን ጠቅሟታል፡፡ ለእኛም ይጠቅመናል ብለን እናስባለን፡፡ መጀመሪያ ወደ ማግለያ በገቡት የእኛም ክልሎች ላይ ውጤት እየተገኘ እንደሆነ ሰምተናል፡፡ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በመቆሙ ምክንያት፣ መንግስት ድጎማ እያደረገ
ይገኛል፡፡ የቤት ተከራይ ዜጎቹን፣ ሱቃቸውን በኪራይ የያዙ ነጋዴዎችን ወጪ እየሸፈነ ይገኛል፡፡ ይሄንን በሌሎች ሀገራት ማስፈጸም ከባድ እና የማይታሰብ ሊመስል ይችላል፡፡ ሁኔታውን ከሀገሬ ድንበር አሳልፌ ሳየው ግን እጅግ እሰጋለሁ፡፡ ውስጥ እጅ የሚያልብ ድንጋጤ ይወርሰኛል፡፡ የማህበረሰባችንን አኗኗር ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ የሚቀይር መዓት መጣብን ይሆንን? እላለሁ፡፡ ይሄንን ብቻ ስማኝ
ባለህበት አካባቢ በበሽታው የተያዘ ሰው ከተገኘ፣ ቫይረሱ እየተስፋፋ ነው ማለት
ነው፡፡ አሁን የእኔ ሀገር ያለችበት ለመድረስ ሁለት ሳምንት ይበቃሃል፡፡ ዞሮ ዞሮ የእኛ እጣ እጣህ ነው፡፡
የምትችለውን ሁሉ ተጠንቀቅ፡፡
ከሁሉ በላይ ደግሞ እኔን አይነካኝም ብለህ አትበጥ፡፡ ከቻልህ ቤትህን ዘግተህ ተከርቸም፡፡

@wegoch
@wegoch
@paappii

#biniam teshome
ዳንኤል ክብረት
@Ethio_Tereka
ደሀ ወርቅ አይግዛ ከገዛም ይጥፋበት ምርጥ ወግ
@wegoch
@wegoch
@wegoch
Forwarded from ግጥም ብቻ 📘 (ዋላ)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Awareness creation video production for Corona Virus!
By amleset muchie

Share others...
@getem
@getem
ዘመዴ ... እጅ መታጠቡንማ ታጠብ ። በቀን አስር እና ሀያ ጊዜም መታጠብ ሸጋ ነው።
ግን ለኮሮና በሽታ አንደኛው መከላከያ እጅ መታጠብ ብቻ ከመሰለህ ተሸውደሀል :)
በሎጂክ ትምህርት "ግነት + ግነት + ግነት" ውጤቱ "እውነት" እንደሚሆን ታውቃለህን?
መንግስት ...ሳያነብ የሚጮኸው አክቲቪስት.. . ሳይገባው የሚለፈልፍ የሚዲያ ተቋም ሁሉ እጅ መታጠብን እንደ አንደኛ አማራጭ ይዞ ሲነሳ ያስገርማልም...ያሳቅቃልም።
ይልቅ ባሻዬ !!
የኮሮና ቫይረስ # Covid 19 ...ከምንም ነገር በላይ የመተንፈሻ አካላትን (Breathing system) የሚጎዳ ስለሆነ አፍና አፍንጫህን በተለየ መጠበቅ አለብህ ።
በሽታውን የመከላከል አንደኛው አማራጭህ ሊሆን የሚገባው ህዝብ በተሰበሰበበት እና በቂ የአየር እንቅስቃሴ በሌለበት ቦታዎች ላይ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ንፁህ ጨርቆችን መጠቀም ነው።
እጅህን ሺህ ጊዜ አንፅተህ አፍና አፍንጫህን መጠበቅ ካልቻልህ ከኮሮና ቫይረስ መዳን አትችልም።
እጅ መታጠብ የሚባለው እርምጃ ከመሸፈኛው ቀጥሎ የሚመጣና ፊትህንና በተለይ የመተንፈሻ አካላቶችህን በቆሻሻ መዳፍህ መነካካት እንደሌለብህ የሚያስገነዝብ ነው።
የኢትዮጵያ መንጋ ሚዲያዎች ባልተረጋገጠ መረጃ እንዳያወናብዱህ ከላይ የመከርሁህን እውነት ስማ ።
ቸር ዋልልኝ ባሹ :)

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ከጣልያን ካልተማርን ከማንም አንማርም!!

እነዚህ በሚዲያዎች እየተነበቡ ካሉ ገጠመኞች የተወሰዱና ለመማማር ይጠቅማሉ ተብለው የተመረጡ ቃሎች ናቸው(ተጨምቀው የቀረቡ)። ልብ ይነካል!!

1. "በርካታ ሰዎች በአንድ ጊዜ ሲሞቱ በአይኔ አይቼ አላውቅም ነበር... ልክ በሆነ ጦር ሜዳ መሃል የማልፍ እስኪመስለን ሁሉም ቦታ ሞት ነው... አንዱ እጅህ ላይ ሞቶ ወደሌላው ስትሄድ እዛም እጅህ ላይ ይሞታል …በሽተኞቹን ለማዳን ስትራዎጥ ነርሶቹ የስራ ባልደረቦችህ ከጎንህ በቫይረሱ ይያዛሉ" ብላለች አንዲት ነርስ።

2. "ሁሉም ነገር ዝግ ነው... የአለም ፍጻሜ ነው የሚመስለው... ጣልያን ዛሬ ላይ በእያንዳንዱ ሰዓታትና ቅጽበት ከጨለማ ውጪ ምንም የሌለባት የተወረረች ከተማ መስላ ነው የምትታየው፡፡ እኔ ራሴ ተመልሼ በዚህች መሬት ላይ እንደ ቀድሞው በህይወት እኖራለሁ የሚለው ተስፋዬ ጨልሟል... እዚህ አገር ህዝቡ ግራ ገብቶታል፣ በመከፋት አንገቱን አቀርቅሯል፤ ተስፋ በመቁረጥም ይህ ሁሉ መዓት እንዴት እንደታዘዘበትና ይህም በቅዠት እንጂ በውን የማይመስል የጭንቅ ወቅት መቼ እንደሚያበቃ ግራ ገብቶት በየቤቱ ተዘግቷል። ....ብታምኑም ባታምኑም ሀኪሞች ማንን እናትርፍ ሳይሆን ማን ቢሞት ብዙዎችን መታደግ ይቻላል የሚል አጣብቂኝ ሁኔታ ውስጥ ገብተዋል፡፡" ከአንዲት በቤት ውስጥ ተቀምጣ ካለች ሴት።

3. የኮሮና ቫይረስ ታማሚዋ ከሆስፒታል አልጋ ያስተላለፈችው መልዕክት "ቫይረሱን አቅልላቹ አትመልከቱ እዚ ሆስፒታል በከፍተኛ እንክብካቤ ነው ያለሁት። መጀመሪያ ከመጣሁበት ቀን በ10 እጥፍ ብሻልም ያለ ኦክስጅን መተንፈስ አልችልም።ሲጋራ የምታጨሱ ሰዎች ሲጋራውን ጣሉት ከምንም በላይ ሳምባቹ አሁን ያስፈልጋቹሀል።በመጨረሻም እባካችሁ ይሄን በሽታ ቀለል አድርጋቹ አትመልከቱት።"
እንደሁለተኛዋ ሴት ገለፃ ከኮሮና ጋር በተያያዘ የጣልያን ትልቁ ጥፋት ኮሮና ጣልያን ውስጥ ገባ ተብሎ ከተነገረም በኋላ እንደተለመደው ቀጠለ፣ ህዝቡ ወደ ስራ መሄዱን አልተወም፣ ወደ መዝናኛ ቦታዎች እንደ ተለመደው በጋራ ይሄዳል እንደእረፍት ጊዜ ከጓደኞቹ ከሌሎቹም ጋር እንደተለመደው በብዙ ቁጥር መንጎዱን አላቆመም ነበር። በነገራችን ላይ የጣልያናውያን ልክ እንደኢትዮጺያውያን ጠንካራ ቤተሰባዊ ግንኙነት ያንላቸውና ማህበራዊ ህይወታቸውና ያኗኗር ዘይቤያቸው የተጠጋጋ፣ የተቀራረበና እርስበርስ የተቆራኘ ነው። ለማስፈራት አይደለም ለማስጠንቀቅ ነው።

@wegoch
@wegoch
#zuki
ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የተላለፈ መልእክት፤

አገራችን ላይ የኮሮና ቫይረስ ከገባ ቀናት ተቆጥረዋል። ዳዴ እያለም ቢሆን ቁጥሩ እየጨመረ ይገኛል። ሊመጣ ለሚችለው ማዕበል ከሁላችንም ኃላፊነት ይጠበቃል። እርግጥ እኛ ሐኪሞችና የጤና ባለሙያዎች ወገናችንን የህይወት ዋጋ ከፍለንም ለማገልገል ዝግጁ ነን። በንደዚህ አይነት ጊዜ ከታማሚው የሚርቅ የጤና ባለሙያ የለም። ግን ጣሊያንና ስፔን መሰል ባለትላልቅ ኢኮኖሚና ጠንካራ የጤና ሴክተር አገሮች በሽታው የፈጠረውን ጫና ተመልክተናል። ለምሳሌ በዓለም 8ኛ የኢኮኖሚ ባለቤት የሆነችው ጣሊያን ኮሮና ከአቅሟ በላይ ሆኖ በአንድ ቀን ብቻ ከ700 ሰው በላይ ሰው ሲሞትባት አይተናል። እናም ከዚህ ተነስተን በአገራችን ካለው የጤና ሴክተር ደረጃና የሆስፒታሎቻችን አቅም አንጻር ትልቅ ፈተና ሊሆንብን እንደሚችል ከወዲሁ መገመት አለብን። እናም ከስር የዘረዘርኳቸውን ሐሳቦች በቀና ልብ እንድታዳርሱና የሚመለከታቸው አካላትም እንዲዘጋጁበት እንድናደርግ አሳስባለሁ።
1ኛ፤ ታማሚዎችም ለማከም በቂ ቦታ ስለማዘጋጀት፦ በመንግስታችን እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች እንዳሉ ባውቅም አይበለውና ቫይረሱ በስፋት መሰራጨት ቢጀምር በርካታ ታማሚዎችን ለይቶ ለማከም የሚያስችል፣ ለኮሮና ብቻ የሚያገለግል ሰፊ ቦታ ያስፈልገናል። ይህ ኃላፊነት በመንግስት ላይ ብቻ የሚጣል ሳይሆን የትላልቅ ሆቴል ባለቤቶችና ሌሎች ባለሃብቶች ወገኖቻቸውን የማስታመሚያ ስፍራ ለመስጠት ከወዲሁ ሊያስቡበት ይገባል። አብረን የመቆምና እንደምንለው የተቀደሰች ምድር ህዝቦች መሆናችንን የማሳየው ጊዜ አሁን ነው። ከመጸለያችን ጎን ለጎን በመረዳዳትና ከራስ ጥቅም በላይ ህዝብን በማስቀደም እንደ ስማችን መገኘት አለብን። በተጨማሪም እንደዚህ አይነት ማከሚያ ስፍራዎችን አዲስ አበባ ላይ ብቻ ማዘጋጀትም በቂ አይሆንም። በተለይ በዋና ዋና ከተሞች ለይቶ ማከሚያ ስፍራዎች ከበቂ አልጋና መሳሪያዎች ጋር ቀድሞ ማዘጋጀቱ በኋላ ከመጣደፍ ያድናል።
የቻይና ዉሃንና የሰሜን ጣሊያን ሆስፒታሎች በቦታ እጥረት ሰው በሰው ላይ ሲደራረብ ነበር። ይህም ተላላፊና ገዳይነቱን ጨምሮታል፣ ስለዚህ ቀድመን ቦታዎችን አዘጋጅተን እንጠብቅ። (ፈጣሪ ከጠበቀንና በሽታው እንደሌሎቹ ካላጠቃን ያዘጋጀናቸውን ቦታዎች ወደፊት ማፍረሱ ቀላል ነው፤ ሳንዘጋጅ ከተያዝን ግን ምንከፍለው ዋጋ ከባድ ነው!)
2ኛ፤ የህክምና መሳሪያዎች፦ በተለይም ጓንት፣ ጎግሎች፣ ማስክና የፕላስቲክ ልብሶችን መሰል የህክምና እቃዎች በተቻለው መጠን ተሰራጭተው በሚዘጋጁት ቦታዎች መቀመጥ አለባቸው። የአሊባባ ባላቤትና ሌሎችም የአገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶች እያረጉ ያሉትን ድጋፍ ማመስገን ያስፈልጋል። ግን እቃዎቹ ለክፉ ጊዜ በቂ መሆናቸውና መዳረሳቸውን በጊዜ ማረጋገጥ አለብን።
3ኛ፤ የህዝባችን ከበሽታው ራሱንና ሌላውን የመጠበቅ፣ ምልክቶቹ ካሉት ራሱን የማግለልና የሰውነቱ የመከላከል አቅም (Immunity) መገንባትን የሚመለከት ሲሆን በተለይም የሚዲያ ባለሙያዎች በዚህ 15 ቀን
ሰርግ፣ ስብሰባ፣ ለቅሶ፣ የመዝናኛ ኮንሰርትና ፓርቲዎች፣ የኃይማኖት ስርዓቶች፣ ትራንስፖርቶች... ወዘተ ላይ ሰዎች በብዛት መገኘት እንደማይችሉ አበክረው መናገር አለባቸው። ለትንሽ ጊዜ ሰዎች መራራቅና በተቻላቸው መጠን ንክኪን ማስቀረት እንዳለባቸው ማስተማር አለባቸው፤ ሁሉም በየአቅሙ ሳሙና፣ ሳኒታይዘር፣ መልቲቫይታሚንና ዚንክ እየገዛ አጠገቡ ለሚገኙ አቅም የሌላቸው (የኔ ቢጤና ጎዳና ተዳዳሪዎችን ጨምሮ) ማዳረስ አለበት።
እንዲህ በእውቀት፣ በእምነትና በመተሳሰብ ከቆምን እሱም ያግዘናል። ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ ነኝ - (ሼር በማድረግ የዜግነት ግዴታችሁን ተወጡ!

@wegoch
@wegoch
Forwarded from ግጥም ብቻ 📘 (Hulumbot)
መከራ ሲመጣ
ያንተ ስልጣኔ ደርሶ ካላዳነህ
ፈጣሪህን ጠርተህ
ከመማፀን በቀር ምን አማራጭ አለህ?
አቤቱ ፈጣሪ
ስምህን ሲጠሩ ማዳንህ ገብቷቸው
ደግ አባት ነህና
ከዚህ ክፉ ቁጣ እባክህ ማራቸው።

@getem
@getem
#taros_alemu
❗️
ውድ የጥበብ ቤተሰቦች የ#COVID-19 ለመከላከል የሚያስፈልጉ ቅድመ ጥንቃቄዎችን እያደረግን ሥዕል በመሳል፣ መጽሃፍ በማንበብ፣ የተለያዩ ጽሁፎችን በመጻፍ፣ የቤት ውስጥ ቀላል ስፖርት በመስራት እንዲሁም ሌላ የምትወዱትን የ ጥበብ ስራዎች በመስራት እራሳችን ገለል እድርገን #የኮሮናን ወረርሽኝ ከራሳችን እንከላከል! 😷

#COVID-19 ወረርሽኝ ለመከላከል ሁላችንም የራሳችንን ሚና ልንወጣ ይገባል።

#share

@getem
@seiloch
@wegoch
ይህን ፅሁፍ እንዳተነብበው!!...(መቼም የተከለከልነው ነው ሚያምረን አይደል?!...)

(ልዑል ኃይሌ)
¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤
ረወደቱን ውጣ ውረድ አይታ ላሳደገችህ ውድ እናትህ ወደቤት ስትሄድ ላደረገችው ውለታ ይዘህላት የምትሄደው 'የሞት ፅዋ' ነው ወይ?...መከታ ሆኖ አሁን ላለህበት ያደረሠህ ለምትወደው አባትህስ በእጅህ እና በትንፋሽህ ይዘህለት የምትገባው ውዱ ስጦታህ 'የሞት ጥቅል' ነው?!...እሺ ይህቺን ዓለም እያለቀስክ ከመጣህባት በእልልታ ለተቀበሉህ አሳዳጊዎችህ ወይም ዘመድ ወዳጆችህ? ያንተ ስጦታ በቸልተኝነትህ የምትሸከመው 'መግደያ መሣሪያ' ነው?....ለወንድሞችህስ?...ለእህቶችህስ?..እሺ ለልጆችህስ አያሳዝኑህም?!..እሺ አይኑሩህ ...ለወንድምህ ወይም ለእህትህ ልጆች..ወይም ለሚወዱህ ለምታጫውታቸው ህፃናትስ መጫወቻ አመጣሁላችሁ ብለህ በእጆችህ ወይም በትንፋሽህ አንከርፍፈህ የምትሰጣቸው 'ሞት'ን ነው ወይ?!...ደጅ እያደሩ በብርድና በርሃብ እየተገረፉ ለሚኖሩ 'ጎዳና ተዳዳሪዎችስ' ከምትሰጣቸው ሳንቲም ወይም ሌላ ነገር ጋር በገዛ ቸልተኝነትህ 'ሞት'ን ቀላቅለህ እንደምትሰጣቸው አስተውለሃል?!..ፍርድህ ይሄ ነው?!...ስለምን ለሚወዱህና ለምትወዳቸው ስትል አትኖርም?....ወጣት ነህ!..ይህ መዓት ደግሞ ብዙ ጊዜ ወጣቶችን አያስከነዳም?!...ኧረ ባክህ?!..አትለኝም!...እሺ ባንተ ምክንያት የሚጎዱትና የሚሰቃዩት ቤተሠቦችህስ?..የአካባቢህ ሠዎችስ?...ስለምን ተጠንቀቅ እየተባልክ ችላ ትላለህ?!...ቢያንስ ለራስህ ስትልም ባይሆን ካንተ ባሻገር ስላሉ ወዳጅ ቤተሠቦችህ ስትል ተጠንቀቅ!!...ቢያንስ ከፀፀት ትድናለህ!...ሳትጠነቀቅ ከምትሞት ተጠንቅቀህ ብትሞት ይሻላል!..ምክንያቱም ፀፀት ዳግመኛ ሞት ነውና!!..ብትተርፍም ከሙት የማይሻል ስጋ ተሸክመህ መንከርፈፍ ዋጋ አይኖረውም!..ማስክ አድርግ ከተባልክ አድርግ!(በዛውም ከአላስፈላጊ ጠረን ትድናለህ!)..ታጠብ ከተባልክ ታጠብ!(ከልጅነትህ ጀምሮ የዘመርከውን "ሳይንስ ሳይንስ መዳኒቴ!..."እያልክ መዘመር ትችላለህ!..ብቻ ታጠብ!)..ጓንት አድርግ ከተባልክ አድርግ!(ለእጅህም ጥሩ ነው!..በልጅነትህ የነበረውን ሐኪም የመሆን ምኞትህን ለአፍታ ታጣጥመዋለህ!..)..ርቀትህን ጠብቅ ከተባልክ ጠብቅ!(እግረ መንገድህን ከኪስ አውላቂ ሰለባነት ትድናለህ!)....ወደ ፈጣሪ ቅረብና ለምነው!..ሃገርህን ዓለምህን ከዚህ መዓት እንዲያሻግራት...ይህን በማድረግህ የምትጎዳውም የሚጎድልብህም አንዳች ነገር የለም!...እንደውም ካስተዋልከው በጫንቃህ የብዙ ሠዎችህ ነፍስ ታተርፋለህ!!... ከዛ ፈጣሪም ታዛዥነትህንና ትህትናህን ዓይቶ መዓቱን ያነሳልሃል!...ያኔ ሠው ትሆናለህ!...ከእንተ ባሻገር ላሉ ሠዎችህ ስትል ተጠንቀቅ!!..

(መጠንቀቅ መፍራት አይደለም!...እኔም ከዚህች ቀን ጀምሮ ለምወዳቸው ሠዎች ስል እጠነቀቃለሁ!!)

@wegoch
@wegoch
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ እራስዎን እና ወገኖን ከ Covid19 ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ይጠብቁ !
This video made by : @Gojofilms collaborated with @Utopiavisualarts
#ኢትዮጵያ የታጠቡ እጆችዋን ወደ ፈጣሪ ትዘረጋለች!!!💚💛❤️

ሶስት ወፎች ዛፍ ላይ አርፈዋል ፤ ከሶስቱ መካከል አንዱ ለመብረር ወሰነ ።ምን ያክል ወፎች ዛፉ ላይ እንደቀሩ ይገምታሉ ?

… መልስ ስጡኝ ! በእርግጠኝነት አብዛኞቻችን ሁለት ወፎች እንደቀሩ ነው የምናስበው። ግን እንዲያ አይደለም። ከሶስቱ ወፎች መካከል አንደኛው ለመብረር ወሰነ እንጂ በተጨባጭ አልበረረም ፤ ስለዚህ ዛፉ ላይ የቀሩት ወፎች ሶስቱም ናቸው ። በሌላ አገላለፅ አንዳች የተለወጠ ነገር የለም ማለት ነው ። … ውድ የፌስቡክ ወዳጆቼ ! አሁን እያንዳንዳችን ራሳችንን እንጠይቅ ።ለምን ያክል ጊዜ ይሆናል አንዳች ነገር ለመፈፀም ወስነህ ሳትተገብረው የቀረነው ? ያ ከግብ ለማድረስ ያሰብከው ጉዳይ ሳንሰራው በመቅረታችን ብቻ እንዳለ በመቅረቱ እና ባለመተግበራችን ምናልባትም የከፋ ሌላ ነገር ያመጣብንስ አጋጣሚ ምን ያክል ነው ? የአንድን ነገር ፍሬ ለመልቀም …. መመኘት ÷ ማቀድና የስኬቱን መዳረሻ መንገድ መቀየስ ብቻውን በቂ አይሆንም … ይልቁንም ወደ ትግበራው መስክ በተጨባጭ መዝለቁ ነው ስኬታማ ሊያደርግ የሚችለው !!!!
ወፏም በተግባር ሳትበር ለመብረር በታሳበ እቅድ ብቻ ሶስትነትን ወደ ሁለትነት ፈፅሞ መቀየር እንዳልተቻለ ሁሉ አንተም አድርግ በህክምና ባለሙያዎች አድርግ የተባልከው ወደ ተግባር የማትለውጥ ከሆነ በማሰብ ፣ ፌስቡክ ላይ በማውራት የምትለውጠው ነገር ፈፅሞ ሊኖር
አይችልም … ይባስ ብሎ የምታጣው ነገር ይኖር ይሆናል እንጂ !!! ይቅር በለኝ … እኔም የናንተው ቢጤ ስለሆንኩ ስድቡ የወል ነው አይዞን … በል አሁን ራሳችንን ካለንበት ተጨባጭ ለማውጣት በህክምና ባለሙያዎች የሚነግሩንን ምክር ወደ #ተግባር የምንለውጥበት ጊዜ አሁን ነው!! … ያኔ በዙሪያችን ያሉት አብረውን እንዲበሩተምሳሌት ሆንናቸው ማለት ነው ፣ ያኔ በዙሪያችን ያሉትን ቤተሰቦቻችንን ፣ ጓደኞችቻችንን ፣ ጎረቤቶቻችንን ፣ ሀገራችንን አዳንን ማለት ነው። እበራለሁ ብሎ ብቻ ማሰቡ፣አደርጋለሁ በሎ ማሰቡ በዙሪያህ ያሉትን ማዳከም ነው። የንድፈ-ሀሳብ ሀገር ነው የምትፈጥረው … በሉ እንብረር … ፋና ወጊ እንሁን … ብርር እያልን ሌሎችም ክንፍ ፣ ሌሎችም ማድረግ እንደሚችሉ እናሳያቸው …ኑ እንብረር … ኑ ተግባር የሚያመጣውን ለውጥ እናሳይ .... አርዓያ እንሁን ........

#"ግመልህን እሰርና በአላህ ተመካ" (ነብዩ መሀመድ ሰዐወ❤️)
#እምነት የምግባር ውጤት ነች!!

ጥንቃቄ ይጠብቅሃል÷ማስተዋል ይጋርድሃል።

ምሳሌ2÷11

@getem
@getem
@Nagayta
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በተገቢው ጥንቃቄ በማድረግ እራስዎን እና ወገኖን ከ Covid19 ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ይጠብቁ !
This video made by : @Gojofilms collaborated with @Utopiavisualarts

@wegoch
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በተገቢው ጥንቃቄ በማድረግ እራስዎን እና ወገኖን ከ Covid19 ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ይጠብቁ !
This video made by : @Gojofilms collaborated with @Utopiavisualarts

@wegoch
ተረት ተረት
በጣም ቀዝቃዛ በሆነ አንድ የክረምት ወቅት አንዲት ወፍ በጎጆዋ ተኝታ ነበር፡፡ ይሁንና ጎጆዋ ውስጥ ሆና ቅዝቃዜውን መቋቋም ስላልቻለች፤የዝናብም ጠፈጠፍ ከቅርንጫፎች ላይ ወደ ጎጆዋ እየሰረገ ስላስቸገራት ከጎጆዋ ወጥታ መብረር ጀመረች፡፡
ተቀምጬ ሞቴን ከምጠባበቅ እድሌን ልሞክር ብላ ከጎጆዋ ወጥታ ስትበር ቅዝቃዜውም እየባሰ ዝናቡም እያየለ ሄደ ከጥቂት ቆይታም በኋላ ቆፈን ክንፎቿን አላላውስ ብሏት መብረር ስላቃታት ከብቶች ሳር ከሚግጡበት መስክ ላይ ወደቀች፡፡
በመስኩም ላይ ከነበሩ ከብቶች አንዲቱ ላም ባጠገቧ ስታልፍ አዛባዋን ጣለችባት የአዛባውም ትኩስነት ለሰውነቷ ሙቀት ሠጣት፡፡ደሟ ሲሞቅ አካሏም ሲፍታታ ይታወቀት ጀመር፡፡
ከሞት ስጋት ተርፋ እንዲህም ህይወት ተስፋ ስለሰጠቻት ደስ ተሰኘች፡፡ ከደስታዋም ብዛት በአዛባው እንደተሸፈነች መዘመር ጀመረች፡፡ በአካባቢውም ርቦት ተኝቶ የነበረ የዱር ድመት የወፏን ዝማሬ ተከትሎ ወደ አዛባው ተጠጋ ፡፡ ከአዛባው መሃል አውጥቶ በላት።

@wegoch
@wegoch
‹‹አክስቴ ሰው ናት ?››
(አሌክስ አብርሃም)

ትላንት ለአክስቴ ደውየ ነበር ! እኔማ በቃ ሳምንት ደውየ ሰላሳ ደይቃ ሙሉ ስለኮሮና ቫይረስ በደንብ ነግሪያት ስለነበር ‹‹አፈፃፀሟን ለመገምገም ›› ነበር!

‹‹ሄሎ አክስቴ››
‹‹አብርሽየየየየየየ …የኔ ጌታ ! ምነው ጠፋህብኝ …በዚህ ክፉ ጊዜ ይጨነቃሉ አይባልም ?››
‹‹ኧረ አለሁ ….የዛሬ ሳምንት ደውየ ነበርኮ ››
‹‹ምነካህ ! በዚህ ዘመን ሳምንት ማለት አመትኮ ነው …እንኳን በሳምት በሰአት ስንት ነገር ይፈጠራል ?!… ››
‹‹እሱማ ….››

እና እንዲህ እያወራን ከኋላዋ የሚስቁ የሚያወሩ ሰዎች ድምፅ ሰማሁ ! የደወልኩት በቤት ስልክ ነው ውጭ ወጥታ ሊሆን አይችልም !
‹‹አክስቴ ››
‹‹ወይየ ››
‹‹የምን ጫጫታ ነው የምሰማው ?››
‹‹አስቱየና አልማዝ ናቸው ….መንግስት እግዜር ይስጠውና ስራውን ሁሉ ዘጋግቶ ረፍት ሰጥቷቸው ይሄውልህ በስንት ጊዚያቸው ልጆቻቸው ጋር ሊጠይቁኝ መጡ! ቡናችንን አፍልተን እያውካካን ነው …አንተ ብቻ ራክብኝ እንደው አንድ ሶስት ወር ረፍት በሰጧችሁና በመጣህልኝ ››

እንግዲህ ይታያችሁ አስቴርና አልማዝ የመንግስት ሰራተኞች ናቸው! መስሪያ ቤቶች መዘጋታቸውን እንደጥሩ አገጣሚ በማየት ዘመድ ጥየቃውን አጧጡፈውት ነው ! ያውም አንዷ ሶስት አንዷ ሁለት ልጆች ይዘው !

‹‹አስቴርን ካናገርኳት ስንት ጊዜየ እስቲ አገናኝኝ ››አልኳት !
‹‹እሷም ናፈቀን ስትል ነበር …ቆይ አግኛት ›› ብላ አገናኘችኝ
‹‹አብርሽ …የጠፋ ሰው አንተ …››
‹‹ አስቴር ›› አልኳት ሰላምታ የለ ምን የለ ….‹‹ አሁን በዚህ ሰዓት ሰው ቤት ይኬዳል …?መንግስት በየቤታችሁ ተቀመጡ እንጅ ቤት ለቤት እየሄዳችሁ ችግር ፍጠሩልኝ ነው ያላችሁ? ››

‹‹ሂሂሂሂ …ውይ አንተ !ቀልድ አያልቅብህ ...ይሄ ጨዋታህኮ ነው የናፈቀኝ !…አሁን አክስቴ ሰው ናት ? …ራቅ ራቅ ያለው ሰው ቤት ነው እንጅ …እሷ እንደሆነች ከቤት አትወጣ ››ትለኛለች ! በቃ እኔ ከምሬ ስለጉዳዩ አስከፊነት ላስረዳት ስሞክር እሷ ‹‹ወይ አንተ ቀልድ አያልቅብህ ሂሂሂሂ ›› ስትለኝ ድክም ብሎኝ ተሰናበትኳት …

አክስቴን አንደገና እያናገርኳት በመሃል እኔጋ ማውራቷን አቋርጣ…‹‹ውይ አንች ደግሞ ዝም ብለሽ ግቢ የምን ጫማ ማውለቅ ነው …›› ትላለች …ሌላ እንግዳ መጥቶ ነው ! ተሰናብቸ የማደርገው ግራ ጠፍቶኝ ዝም ብየ ቁጭ አልኩ ! ለመሆኑ እንዴት ነው ይሄን ነገር ለትልልቅ ሰዎች ማስረዳት የሚቻለው ...?????በእኛ ጠንካራ ማህበራዊ ኑሮ ምን ብናደርግ ነው የሚበጀን??
@wegoch
@wegoch
የጣሊያኑ ዶክተር የጻፈውን ልብ የሚነካ ደብዳቤ እነሆ ላስነብባችሁ:-
ይህንን መልዕክት ለሁሉም አዳርሱ!

በሀገራችን ጣሊያን እጅግ አሳዛኝ ነገር እየኾነ ነው።በእድሜያቸው የገፉ ሕሙማን ከመሞታቸው በፊት በጉንጮቻቸውላይ እንባቸው ሲወርድ ይታያል። ከቀረባቸው አደጋ ሊያመልጡ የሚችሉበት ምንም ዕድል የላቸውም። ሆኖም እንዲሁ ዝም ብለው መሞት አልፈለጉም። በካሜራ ፊት "ደህና ሁኑ" በማለት ነው የሚሰናበቱት።

ሁሉም ጭንቀታቸውን እንደተሸከሙ ነው በጥበብ እያንቀላፉ ያሉት።አብዛኛውን ጊዜ ባልና ሚስት በአንድ ቀን ይሞታሉ። ቅድመ አያቶችና አያቶች ፤ በመጨረሻዋ ሰአት የልጅ ልጆቻቸውን መሰናበት አልቻሉም።

ይሕ በሽታ ከጉንፋን እጅግ የከፋ ነው። እመኑኝ። ይሕ ከጉንፋን እጅግ በጣም የተለየ ነው።እባካችሁ ኮሮና ቫይረስን-"ጉንፋን" እያላችሁ አትጥሩ።

ትኩሳቱ የሚቻል አይደለም። ህሙማኑ ጨርሶ መተንፈስ አይችሉም።ብዙዎቹ ኦክሲጅን እንዲያገኙ ቢደረግም፤ በቀላሉ መተንፈስ የሚታሰብ አይደለም።

በሽታውን ለማከም በጣም ጥቂት የመድሀኒት አይነቶችን ለመጠቀም እየሞከርን ቢሆንም፤ እሱም በህሙማኑ አቅምና ጥንካሬ የሚወሰን ነው።በተለይ በእድሜ የገፉ ህሙማን በሽታውን መቋቋም አልቻሉም።

አሁን እኛ ዶክተሮቹ እያለቀስን ነው።ነርሶቻችንም እያነቡ ነው። የሀዘናችን ምክንያት የብዙ ሰዎችን ህይወት መታደግ አለመቻላችን ነው።

የሰው ልጆች የህይወት ዑደት አይናችን ፊት ለፊት ሲያከትም እያዬን ነው።አሁን ይህን እየነገርኳችሁ እንኳ እጅግ በርካታ ህሙማን ወደ ሆስፒታላችን እየጎረፉ ነው።በአስቸኳይ አስተኝቶ ማከም የሚያስችሉ በርካታ ክፍሎች ያስፈልጉናል።አሁን የሁሉም ህመም አንድ ዓይነት ነው። የሳምባ ምች እና በጣም ጠንካራ የሳምባ ምች !( ጄነራል ኒሞኒያ እና ቬሪ ስትሮንግ ኒሞኒያ!)

የትኛው ጉንፋን እንዲህ እንደሚያደርግ ንገሩኛ!?

ይህ ወረርሽን በጣም ተላላፊ ነው። ይህ ቫይረስ ጠቅላላ የተለየ ነው።

በተለይ ለአንዳንድ ሰዎች እጅግ በጣም አደገኛ ነው። በኛ ሀገር 65 እና ከዚያ በላይ ዕድሜ ያላቸው አብዛኞቹ ሰዎች የስኳር ህሙማን ናቸው።የደም ግፊት አለባቸው። ለእነዚህና ለአንዳንድ ወጣቶች ህመሙ ከባድ ነው።

አንዳንድ ወጣት ህሙማንን ብታዩ- ማናችሁም ወጣቶች ስለዚህ ህመም ልትዘናጉ አትችሉም።

በአሁኑ ሰአት በሆስፒታላችን የቀዶ ጥገና አገልግሎት የለም፤ የማዋለጃ ክፍሎች ተዘግተዋል፤ የአይንና የቆዳ ህክምናም ቆሟል። የቀዶ ጥገና ክፍሎች በሙሉ፤ ወደ ድንገተኛ ህክምና መስጫ ክፍል ተቀይረዋል።

አሁን ሁሉም ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር ውጊያ ላይ ነው። በእያንዳንዷ ሰዓት የህሙማን ቁጥር እያሻቀበ ነው።የህሙማኑ ወጤትም ያለማቋረጥ እየቀረበልን ነው።፡ሁሉም ፖዘቲቭ! ፖዘቲቭ!!ፖዘቲቭ!!!

አንድ ዓይነት ህሙማን።

የማይቻል ትኩሳት፣

የስቃይ ትንፋሽ

ሳል!

ድካም!

ሁሉም ሊባል በሚችል መልኩ በድንገተኛ ክፍል ህክምና እንዲያገኙ ጥረት እየተደረገ ነው። አንዳንዶቹ በኦክሲጅን እንኳ ታግዘው መተንፈስ አይችሉም።አሁን ኦክሲጅን ማሽን ከወርቅ በላይ ውድ ነው።

ይህ ሁሉ በምን ያህል ፍጥነት እየሆነ እንዳለ ማመን አልቻልኩም።

ቢሆንም ማናችንም ለመቆም አልፈለግንም። ሁሉም እስከ እኩለ ሌሊት እየሰራ ነው።ዶክተሮችም ልክ እንደ ነርሶች ሥራቸውን ቀጥለዋል።እኔም ለሁለት ሳምንታት ወደ ቤቴ አልሄድኩም።ምክንያቱም በእድሜ ለገፉ የቤተሰብ አባሎቼ እፈራለሁ።ልጆቼን እየደወልኩ በካሜራ ነው የማዋራቸው።አንዳንዴ የሚስቴን ምስል ሳይ አለቅሳለሁ።እኛኮ ምንም ጥፋት አልፈጸምንም።

ይህ ህመም አደገኛ እንዳልሆነ ያስወሩት ሁሉ ጥፋተኞች ናቸው። ምክንያቱም "ይህ ህመም ልክ እንደ ጉንፋን ነው" ብለው ነገሩን። እኛም ምንም የጥንቃቄ እርምጃ ሳንወስድ ቆዬን።አሁን በጣም ረፈደብን።

እባካችሁ ከቤት አትውጡ! የምንላችሁን ስሙን!ድንገተኛና አስቸጋሪ ህመም ካላጋጠማችሁ በስተቀር ከቤት አትውጡ! የፊት ጭምብል አድርጉ። የባለሙያዎችን ምክር ስሙ።

የኛ የጤና ሁኔታ ራሱ በጭምብል እጥረት ለአደጋ ተጋልጧል።አንዳንድ ሐኪሞች በቫይረሱ ተይዘዋል።የአብዛኞቹ የቤተሰቦቻቸው አባላት በሞት እና በህይወት መካከል ናቸው።ስለዚህ ራሳችሁን ለማዳን ከወዲሁ ጥረት አድርጉ።በእድሜ የገፉ ቤተሰቦቻችሁም ወደ ውጭ አይውጡ።

እኛ ግን በሙያችን ምክንያት በቤታችን መቆየት አንችልም።እስከ መጨረሻዋ ሰዓት ድረስ የታማሚዎቻችንን ሕይወት ለማዳን እንታገላለን።

እንዳ'ለመታደል ሆኖ ከብዙ ድካም በኋላ ወደ ቤታችን እንሂድ ብንልም በሽታውን ይዘን ነው በተሰበረ ልብ የምንሄደው።

አውቃለሁ። ነገ ጧት ሁሉም ነገር መልካም ሲሆን- ሁሉም ይረሳናል። ምክንያቱም ይህ የሕክምና ሙያ ባህርይ ነው። ለዚህ ነው ራሳችንን ሰጥተን የሰዎችን ህይወት ለማዳን የምንታገለው።

እናም እስካሁን በበሽታው ያልተያዛችሁ ብትሆኑም ፤ ህዝብ ከሚበዛበት ቦታ ራሳችሁን አርቁ።ወደ ፊልም ቤቶች፣ወደ ሙዚየሞችና ወደ መጫዎቻ ሜዳዎች አትሂዱ።ቢያንስ በእድሜ ለገፉ ቤተሰቦቻችሁ አስቡላቸው።አሁን የነሱ ህይወት በእናንተ እጅ ላይ ነው።እናንተ ከተጠነቀቃችሁ፤ እኛ ከምንታደጋቸው ነፍሳት በላይ ብዙዎችን ታድናላችሁ። አሁን እነሱን ልትታደጉ የምትችሉት እናንተ ብቻ ናችሁ።

ይህንን መልዕክት ለሁሉም አዳርሱ፦

(ዶክተር ዳኒየሌ ማቺኒ ከጋቫትሴኒ ሆስፒታል)

 @wegoch
@wegoch
@wegoch
የምናሳትማቸው መጻህፍት
ረጅም ልቦለዶች

*ቫይረስ ያልገደለው ፍቅር
*የኮሮና ሰሞን
*ኳረንቲን የገባው ሰላይ
*ኮሮንቶራ
*ሞት የጋለበው ከተማ

"ታሪካዊ ልቦለዶች"

*ቫይረስ ያስቀረው የዘር ሽኩቻ
*አክቲቪስቱን እንዴት ቫይረስ ያዛቸው?
*የቫይረሱ ምስጢር
*ከቤተ እምነት እስከ ቤተመንግሥት: ስሙነ ሕማማት

"ታሪክ"

*የኮሮና እልቂት: ካየሁት እና ከሰማሁት
*ከኮሌራ ተኮር መንደር እስከ ኮሮና ተኮር ከተሞች
*የቫይረሱ መገታት: እውነት በኢትዮጵያ ምድር?
*ኣባ ቫይረስ: በሽታ ገዳዩ መሪ
ሳይንስ
*እጅ እና ምስጢራቱ
*ቫይረስ ለምን ይገላል?
*የኮሮና በሽታ መንስኤና መፍትሔዎቹ: ከስነ ሕይወት አንፃር
*የመተንፈሻ አካላት አሠራር: መተንፈስ ለምን ይከብደናል?
*ጉሮሮ ምንድነው?: የጀማሪዎች መማሪያ

"ግጥም"

*ሞትም ቀን ወጣለት
*ከቫይረስ የተኮረጀ ዘመቻ
*ቫይረስ፣ ሞት፣ ሕይወት
*ሳሚኝና ልሙት
*ቫይረስ ያጠቃቸው ስንኞች
*ልየታ እና ፈቀቅታ
ፖላቲካ
*የተደናቀፈው ምርጫ
*የኢትዮጵያ አንድነት ተስፋ: ኮሮና እንደ መፍትሔ
*ከዘር ፖለቲካ ወደ ዘረመል በሽታ የተደረገ ቅልበሳ
*የቫይረስ ብሔር አነሳስ፣ እድገት እና ፖለቲካዊ ሚና
*እኛም እንታመም እነሱም ፕሮፓጋንዳ ያሙቁ: የሀገር ሉአላዊነትን ያስጠበቁ
የበሽታው ጀግኖች
*ቫይረሱን ያንቀጠቀጡ ፓርቲዎች


ኡፍፍፍፍ ለማንኛውም እየታጠባችሁ
እየተለያያችሁ ።

@wegoch
@wegoch
@paappii
2024/09/25 11:16:15
Back to Top
HTML Embed Code: