Telegram Web Link
ከመነሻ እስከ መድሻ ድል አድራጊ አባቶቻችንን እንዘክራለን ፤ የአንድነት ቀንን አንድ ሆነን እንድናሳልፍ የዓደዋ አለባበስ መርጠናል።


ቲሸርቱም ታሪካዊ፤
ጉዞአችንም ትዝታዊ፤
ዋጋውም መጠናዊ(280 ብር)
@ribki
+251926743929
አድዋ
GIGI (Ejigayehu Shibabaw)
ልዩ አዛዜም ከመላዕክት የዜማ ስድር የተቀዳ የሚመስል የዜማ ውበት እና የግጥም ፍሰት!!
እጅጋየሁ ሽባባው( ጂጂ)
#አድዋ
@wegoch
@wegoch
@wegoch
#c_ራክ
የኔ ቀን😄
ጀንበር በስተምሥራቅ ክንፏ እንደተመታ አሞራ ወደ ተራሮች ግርጌ በፍጥነት ስትወድቅ እንዲህ ስል አሰብኩኝ..
'የሰው የኑረት የጊዜ ወሰን በሶስት ይከፈላል ትላንት ፣ ዛሬ ፣
እና ነገ ታዲያ ይህቺ አለም የምታውቀኝ በዛሬው ማንነቴ አይደለም? ጊዜስ የሚያውቀኝ አሁን ያለውን ማንነቴን አንደል?
ቲዲያ ነገ የሚል ተስፋን እስካነገብኩኝ ድረስ አለምንም ሆነ ጊዜን በማያውቁኝ ማንነቴ ለምን አልቀድማቸውም?
አሁን ላይ እኔን ከእኔ በላይ ሊያውቀኝ የሚችለው እኔነቴ ነው።
እኔነቴ ደግሞ በትላንት ጭቃ ተቦክቶ ዛሬ ላይ ቆሟል
እምነቱን እና ተስፋ ፍቅሩን ሸክፎ ከማያውቀው ነገ ጋር ተጋብቶ ፍሬውን ሊያይ በፅናት ወደፊት እየተመመ ነው።
"ለማታውቀው ሰው ገንዘብህን እንደማትሰጥ ሁሉ ለማታውቀው ነገ ለምን ዛሬህን ትሰጣለህ ??" የምትለዋን የዳንኤል ምልከታ ጠቅ ብታረገኝም ሀሳቡን በሙሉ ድምፅ በልቦናውዬ አፅድቄ ዛሬን እየኖርኩኝ ለነገ እለፋለሁ' አልኩኝ
'#ወርቄን_ከትቢያ_አሳንሶ_ከአልመጠመጠኝ_ሰበካ_ጋር_ስዋጋ_ከምኖር_የአንድ_ጀንበር_ሞቴን_እመርጣለሁኝ 'ስል አጉተመተምኩኝ ......
ቀና ስል ምድር በጥቁር ሸማ ተደርታ የምትቆዝም ባልቴት መሰለችኝ።
ለአይን ያዝ ካደረገው ጨለማ ጋር እየተጋፋሁ ወደ ጌልጌላዬ አዘገምኩ።
ጓነዬ በምሽት ቡና አፍዪዎች የቡና ሽታ ታውዳለች። እረኞች ከብቾቻቸውን ወደ ማደሪያቸው ለማስገባት ከወዲያ ወዲህ ይዋከባሉ።
ከስማቸው ፊት 'አያ' የምትለዋን ማዕረግ እያስቀደምኩኝ ሰላምታዬን እየቸርኩ ከታዛዬ ደረስኩ።
ከቆጥ ላይ ከሰፈሩት ዶሮዎች ጋር ተስፋዬን ሰቅዬ ንጋቴን ልጠባበቅ ፣ ተስፋዬን ልናፍቅ ፣ ጥኡም የወፎችን ዝማሬ ለመስማት እየጓጓው ወደ አልጋዬ አመራሁ....
ከትንሹ ሞት ጋር ግብግብ ለመግጠም!!
---------------°°°°°°°°°°-----------------------
ሻሎም ለኢትዮጵያ
ሲራክ ነኝ @siraaq
የኔ ቀን
@wegoch
@wegoch
@wegoch
አድዋ የታሪክ ባለውለታ

አድዋ በታሪክ ክስተት ውስጥ በኢትዮጵያ እና በጣልያን መሀከል የተደረገ ጦርነት ብቻ አይደለም። በእውነት እና በሀሰት፣በነፃነት እና በባርነት፣ በሰባዊነት እና በኢሰባዊነትም መሀል የተደረገ ውጊያም እንጂ። አድዋ የሰው ልጆችን ታሪክ የቀየረ እኩልነት ይነገሰበት የስነልቦና ከፍታ ነው።

ጠየኩ: ያለ አድዋ ታሪክ እንዴት ይቀጥል ነበር?
ምናልባትም አለም የነጭ የበላይነትን አምኖ እንደተቀበለ፣ሰው የመሆን እውነት ተቀብሮ፣ጥቁር የነጭ እቃ እንደሆነ በቀጠለ ነበር፣ የሰው ሁሉ ፀጋ የሆነው ነፃነት የአንዳንዶች ፈቃድ መሆኑን በቀጠለ ነበር፣ ምናልባትም ቋንቋችንና ባሕላችንን ተስርቀን ዛሬ በምንጠራራበት ስም ባልተዋወቅን ነበር.........
ክብር አልተማሩም ለተባሉት በባዶ እግር ዘምተው ለረቱት፣ሰውነትን ላደመቁት፣ ወድቀው ታሪክን ላቀኑት ለአድዋ ሰማዕታት።
እናመሰንግናለን።🙏🙏

Nuye

@wegoch
@wegoch
አርብ እንዴት ተተኛልህ?
.
ተኝቶ ይሆን? ስልኬን ያላነሳው!
ከለሊቱ 5:18 ሆኗል፡፡
አርብ ቶሎ እንቅልፍ አይወስደንም ነበር...
እንባ ወደ ጆሮአችን እየወረደ የዚችን አለም ከንቱ አዙሪት ያወራንባቸው እነኛ የቅዳሜ ጥላዎች፡፡ ኤፍሬም "መሸ ደና እደሩ" እያለ በአራራዩ ሊያራራን(ሊያስተኛን) ሲዳክር......
.
የእርጅናን ብልግና የማለፍን እርግማን በቅርበት እያሸተትን
አንተ ባትኖር ግን መኖር እንዴት ይለመድልኛል? ስንባባል፡፡
"ያጣሁህ ቀን ብቻዬን እያወራሁ እምሔድ ሁሉ ይመስለኛል" ይል ነበር....
አሁን ብቻውን ማውራት ጀምሯል አሉ! ሞቅ ካለው እንደ ፍቅረኛ ስምህን ጠቅሶ ብቻውን ይተባተባል አሉኝ!
የሔደበት ቦታ እንደማይመቸው አውቅ ነበር፡፡
ነገ ሊሔድ ዛሬ አዲስ የገዛሗት ወረቷ እና እዳዋ ያላለቀ ሸሚዜ ላይ አፈጠጠ፡፡ የታባቱንስና ሳሙና ለሚበላው ጓዴን አይክፋው ብዬ ትከሻው ላይ ጣልኳት፡፡
ፊቱን ሳይዞር....
"እወድሀለሁ"
ብሎ ሔደ፡፡
አቃለሁ ይወደኛል!
እኔንም በጨርቅ የረታኝ አንድ ታናሽ ወንድም ነበረኝ እለው ነበር፡፡ (ሰው ፍቅሩንም ሆነ ጥላቻውን ጨርቅ ላይ ይቋጥራል? ኢየሱስን መስቀላቸው ሳያንስ ጨርቁን ቀደው የተካፈሉት ም/ታቸው ይናገሩ...ጨርቁን ነክታ የተፈወሰችውም)
እኔንም በጨርቅ የረታኝ ታናሽ ወንድም ነበረኝ፡፡
አዎ
ወደ ዩኒቨርስቲ ልሔድ ዋዜማ!
☞ ለሊት
የበግ ተራን ቤርሙዳ ቀድሜው ልረዳ በተሰናዳሁባት የመጨረሻዋ ምሽት፡፡ ከወንድሜ ጋር እንቅልፍ አጥተን አደርን፡፡ ስንቱን አወራን ያን ለት!
.
☞ ጠዋት
አምሽቶ የማያውቅ ልጁን ተማር ብሎ ሊልክ ከሴት ልቡ ጠብ የገጠመ ጋሻ-ዬ የሚሉት አባት ልጁ የተሳፈረበትን አውቶብስ ከመናኻሪያ እስኪወጣ ራቅ ብሎ ይጠብቃል፡፡ ታናሽ ወንድምዬው አባቱ ጎን ቁጢጥ ብሎ እንደ በረደው ሰው አናቱን ደረቱ መሀል ደፍቶ እንባውን ያርመጠምጣል፡፡
አየህ.... ከአውቶብሱ ሳልወርድ ብዙ ነገር ተገለጠልኝ፡፡
[መለየት የሚባል ሌባ በተለቀቀባት አለም የምንኖረው ፍዝ ሒዎት ስንት ውድ ቀኖች እና ለሊቶች ሰረቀን! መልመድ ክፉ በሽታ ሁሉን ቋሚ አስመስሎት የቆመ ሁሉ መልኬን አልመሰለም ብለን ለመናድ ስንደክም! ባንነካው ፀንቶ ይቆም ይመስል! ማን ወደ ማን እንደሚገሰግስ ተምታቶብን የሚመጣውን ስንከተል የሚሔደውን ስንቀበል እንደኖርን ተገለጠልኝ! በአውቶብሱ መስታወት ሁሉ ነገር ወደሗላ እንደሚሮጥ እርጅናም እንዲህ ይመስለኛል በኩርፊያ እና በመግደርደር ያለፉ ቀናትን መካስ የማይቻልበት የአካል ስንፍና]
.
እናም በዛ ዮኒቨርስቲ ከብዙ ድካምና እንግልት በሗላ ዶርም አገኘሁ፡፡ በሩ ያልተገነጠለ ሎከር ተሻምቼ ልይዝ ልብሴን ከሻንጣዬ እያፈስኩ በደመነፍስ ስወረውር ጣቶቼ እንግዳ ነገር ነኩ፡፡
ጅንስ፡፡
ይቺ ጅንስ ማለት ወንድሜ ያለችውና የሚወዳት ብቸኛ ጅንሱ ነበረች፡፡
ኸረ ለመሆኑ እንዲህ እንዴት አርብ ተተኛልህ? ለሴቶቹ የምትነግረውን ነግረኽ ካልረታኸው በቀር!
አርብ እንዴት ተተኛልህ?

ተፃፈ:- በሀይሉ ሙሉጌታ

@wegoch
@wegoch
ከሌሊቱ 10:30 ላይ "የኔ ፍቅር ከመስሪያ ቤት ትዕዛዝ ስለመጣልኝ(ብኝ) በጠዋት ወደ ክፍለ ሀገር ልሄድ ነው" የሚል በኔ እሳቤ ነገ ጠዋት ውብ አይኖቿ ሲገለጡ የሚነበብ መልዕክት ላኩላት።"የተረገመ መስሪያ ቤት!!የት? ስንት ሰዓት? ለስንት ቀን? ከማ ጋ?" የሚል የጥያቄ አገልግል አስታቀፈችኝ፣ሰዓቴን አየሁት 10:31 ይህቼ ሴት አትተኛም እንዴ እያልኩ በመገረም ውስጥ "የነዚህን ጥያቄዎች መልስ" ብዬ ከመፃፌ ስልኬ እጄ ላይ ተንቀጠቀጠች፣እጅግ የምወደው ስም በስልኬ መስታወት ላይ ብቅ አለ "አለሜ" አነሳሁት፣ ሙሉ አካላትን በሚቀሰቅስ ለሆሳስ "የኔ ፍቅር፣ ብላ ከላይ በፅሁፍ የላከቻቸውን ጥያቄዎች አዥጎደጎደች፣ ሳቄ አመለጠኝ፣ለምን እንደሳቅኩ ገብቷታል፣ "ምኗ እብድ ነኝ በናትህ! ተደናብሬ ሰላምታውንም ረሳሁትኮ፣እንደምን ነህልኝ የኔ ንጉስ" አለችኝ "ደህና ነኝ አለሜ አሁን ይሄን የምናወራበት ግዜ አይደለም፣አሁን ተኚ ጠዋት ከመውጣቴ በፊት ደውዬልሽ ሁሉንም እናወራለን" አልኳት "ልብሶችህ ንፁ ናቸው? ገንዘብስ እጅህ ላይ አለ?" "አለሜ" አልኳት አንድ አይነት ጥሪ እንኳን ሆኖ የፍቅር፣የቁጣ፣የደስታ፣የሀዘን፣የናፍቆት፣የመከፋት ሲሆን ለይታ ታውቀዋለች። ከዚህች "አለሜ" ከምትል ቃላት ውስጥ" አንቺ አርፈሽ ተኚ ጠዋት እናወራለን" የሚል ወርቅ አወጣች፣"ደህና እደርልኝ እንደነቃህ ደውል" ብላኝ ስልኩ ተዘጋ።አዓምሮዬ እሷን እያሰበ፣መላ ሰውነቴ እሷን እየናፈቀ፣አልጋዬ ጎን ከቆመው ሳጥን መሳብያ ውስጥ ግራ እጄ አንድ ነገር አቀበለኝ፣ትናንት ቤቴ ውስጥ ረስታ የሄደችው ሻርፕ!!ሁሌ በቦርሳዋ ትርፍ ሻርፕ ስለምትይዝ ቤቴ የመጣች ቀን አድርጋ የመጣችውን ማስቀረት ልማዴ ነው። መጀመሪያ አከባቢ ትቃወመኝ ነበር ታድያ አንድ ቀን ልትቀበለኝ ስትታገለኝ አንገቷ ስር ገብቼ "አለሜ ተጠናቀሽማ አትሄጂም ባይሆን ጠረንሽን እዚህ ተይልኝ" አልኳት ፈቀደች ፣ወደ አፍንጫዬ አስጠጋሁት ኡፍ ብዬ በረጅሙ ተነፈስኩ፣የሷን ጠረን ከአንገቷ ስር የማግኩ ያህል ተሳምኝ!!
በሬ ተንኳኳ በድንጋጤ ከእንቅልፌ ባንኜ(ለካ እሷን እያሰብኩ እንቅልፍ ወስዶኝ ነበር) ሰዓቴን ተመለከትኩ 12:01 ይላል፣ ድንጋጤዬ በእጥፍ ጨመረ ሊነጋ አከባቢ ቤቴ ሲንኳካም ሆነ ስልኬ ሲጠራ ይረብሸኛል፣የሆነ በጣም የምወደው ሰው ሞቶ ሊያረዱኝ የመጡ ይመስለኛል!! ድጋሚ ተንኳኳ "አምላኬ ሆይ ቸር ወሬ አድርገው" እያልኩ ተነስቼ ከፈትኩት፣ ልክ ከፍቼ ውጭ ላይ ያለውን ሰው ስመለከት መላ አካላቴ በድንጋጤ ራዱ፣የልብ ምቴ ጨመረ፣እጆቼ ተንቀጠቀጡ አለሜ ነች! (ቤቷ ከቤቴ በፈጣን እርምጃ 40 ደቂቃ እኮ ነው)"በሰላም ነው አለሜ?" በኔ አፍ ሌላ ሰው የጠየቀበት ነው የመሰለኝ፣ዘላ እቅፍ አደረገችኝ እና "በርዶኛል እንገባ" ብላ የሆነ በትልቅ ቦርሳ ያንጠለጠለችውን ነገር ተሸክማ ገባች፣ተከትያት ገባሁ "አንተ ጉዞ አለብኝ እያልክ ትተኛለህ እንዴ" አለችኝ ያን ሁሉ ነገሬ የሆነውን ፈገግታ እያሳየችኝ፣ቦርሳዋን ከፈተችው የታሰረ ብር(አምስት ሺህ ይመስለኛል)፣የታጠበ ሱፍ(መቼ ይታጠብ ብዬ ከሰጠሁበት እንዳወጣችው!)፣የተቋጠረ ምግብ(የምወደውን ፍርፍር) ተገረምኩኝ "እኔ የምልሽ አለሜ አለቃ እኔ ጋ መልዕክት ከመላኩ በፊት ላንቺ ደውሎልሽ ነበር እንዴ?" ደነገጠች "ማለት?" አለችኝ "ማለቴማ ቀድሞ ካልነገረሽ እንዴት በአንድ ሰዓት ውስጥ ያውም በጠራራ ሌሊት ይሄን ሁሉ ማድረግ ይቻላል?" ሂድ ወረኛ! በል አሁን ተነስ እና ተጣጠብ"
1:30 በሬ ላይ ሹፌሩ የመኪናውን ጥሩንባ አጮኸው፣ ያጩኻ! እኔ አንደሆንኩ በአለሜ ውብ ጣቶች ቁርሴን በልቼ፣ጥቁር ሱፍ ለብሼ፣ገንዘብ በኪሴ ከትቼ ተጠናቅቄያለሁ!!
"ደሞ የት ሂዱ አለ" አልኩት ሾፌሩን
"መቀለ" አለኝ ሰላም ግባ የኔ ንጉስ ብላ ከንፈሬን ሳመችኝ፣ሾፌሩ ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ ዞረ።
መኪናው አቅጣጫውን ወደ ሰሜን አዙሮ መጋለብ ጀመረ።
ሰው እንዴት እንዲህ ሁሉ ነገር ተሟልቶ ይፈጠራል? እንዴት ምንም አይጎለውም? እንዴት ምንም ያልጎደለውን እንደኔ ካለው ምንም ከሌለው ያቆራኛል? ይህች ሴት የእናቴ ፀሎቶች ድምር ውጤት ነች እንዴ? "እሺ አለቃ አዲስ አበባ መውጫ ላይ ደርሰናል የምገዛልህ ነገር አለ?" ሀሳቤን አቋረጠብኝ " አይ ምንም አልፈልግም፣ እንካ የምትገዛው ነገር ካለ ግዛ ብዬ 100 ብር ሰጠሁት።
ስልኬን አነሳሁና "አለሜ አንቺ ለኔ የመኖሬ ምክኒያት ነሽ አፈቅርሻለሁ!" ብየ ላኩላት!!!!

ተሞነጫጨረ: አልኑር

@wegoch
@wegoch
"የከንቲባው ከተማ"

ተዋወቃት፣የፌዴራላዊ መንግስት መናገሻን፣

እህል ተነቅሎ ኮንዶሚኒየም የሚተከልባት፣በ2009 ዳታ መሰረት ከ896 የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 690ናው የግል የሆናባት፣ከ1180 መዋእለ ህፃናት 216ቱ ብቻ የመንግስት የሆነባት፣ወላጆች ለትምህርት ቤት ወጪ ከእለት ጉርስ ቀንሰው የሚቆጥቡባት፣ቴክስት ቡክ በነጋዴ የሚቸበችቡባት ፣ አከራይ ከብርሃኑ ጁላ በላይ የሚፈራት ፣ ጫት ቤት ከፋርማሲ የሚበዛባት፣ከጫት ቀረጥ የማትሰበስብ፣ወጣቱ ሞፈሩን ጥሎ ያለፍተሻ "ለስራ" ብሎ የሚሰደድባት፣ሴትን የሚያህል ክቡር ፍጥረት ባሬላ ተሸክሞ የሚያድርባት፣ደላላ የሚያሽከረክራት፣የታክሲና የዳቦ ቤት ሰልፍ የሚያደናግርባት፣ቡና እና ጤፍ እንደኢምፖርት ሸቀጥ ሰማይ የነኩባት፣ባለስጋ ቤት ኮንትራክተር ሆኖ ኢንጅነሩ ቀጥሮ የሚያሰራባት፣የመንግስት መስሪያ ቤቶች በሚዘገንን ብር የግለሰብ ህንፃ የሚከራዩባት፣ውልና ማስረጃ የግለሰብ ህንፃ ላይ ተከራይቶ ሲሰራ እያየህ ምኑን ውል ምኑን ማስረጃ አለኝ ልትል.?ገቢዎች የሰበሰበውን ገንዘብ ለቢሮ አከራዮች የሚከፍልባት፣ኤምባሲዎች የባለስልጣን ቪላ የሚከራዮባት፣መከላከያ ሚኒስትር አጠገብ ብላክ ማርኬት የደራባት፣ከዩኒቨርስቲና ከሆስፒታል በፊት ትምባሆ ፋብሪካ የገነባች፣የከተማ እርሻን የምትጠየፍ "የአፍሪካ ኩራት" ከምትለው አየር መንገድ መንገዷ ስር ሰው በመኪና አደጋ እንደቅጠል የሚረግፍባት፣ድህነት በሚንጎማለልባት መሃል ጨርቆስ ላይ ኳታርና ዱባይን የሚያጋጭ ግንባር መሬት ያላት (ከስሩ ውሃ ነው እሺ!) እንቁላል ፋብሪካ የሚባል ሰፈር ውስጥ እንቁላል ፈልገህ የማታገኝባት፣ለቦብ ማርሌ ሀውልት ሰርታ ለጣይቱ ቦታ ያጣች፣የካ፣ለቡ፣ኮልፌ፣ጉለሌ፣አባዶ፣አቃቂ፣ቃሊቲ፣ቀበና፣ቁርጥሜ፣ኮዬ ፈጬ፣ጀሞ ላፍቶ ወዘተ የሚሉ ስሞች ተጠራርታ እያደረች የታከለ ኡማን ኦሮሞነት ማጦዝ የሚያምራት፣ቀላል ባቡር በሁለት ብረቶች ላይ በሚሄድበት ዘመን ይሄንን ሁሉ መሬትና ቁስ በባቡር ስም ያባከነች፣ለንብም ለአይንም የማይሆን(በዚያ ላይ በበጋ የሚደርቅ ) አበባ በዶላር ከውጭ አስገብታ የምተክል፣አረም በለው! ለም መሬቷን ለአደባባይና ለቆሻሻ ሰጥታ ነጭ ሽንኩርትን በወርቅ ግራም የምትሸጥ፣በሸዋ ሚልክ ሼዶች ተከብባ ወተት እንደ ጣዝማ ማር የተወደደባት፣ቴአትር ቤቶቿን በፓለቲካ ቀፍድዳ በቴአትር ፈንታ የሰራተኞቹ ህይወት ወደ ቴአትር የተቀየረባት፣የአርብቶ አደሮች ጉዳይ መስሪያ ቤት አዲሱ አበባ ላይ የሚቀመጥባት አዝናኝ ከተማ ናት፣

ሲጠቃለል፣አዲስ አበባ ማለት፣ሰገጤ፣ከእውቀት ጽዱ፣ከሉሰስ፣ግሪዲ፣ሉዘር፣ወዘተ ከተማ ናት ስልህ እንግሊዝኛ ቀልሎኝ አይደለም። አለ አይደል?የአፍሪካን መቀመጫ በአማርኛ ከመስደብ ቢያንስ በኢጋድኛ ላጥረግርጋት ብዬ ነው። አሁንም ስጠቀልለው፣እንደ ሪዮ ዲጄይኔሮ ሳኦፓውሎን ሰርቶላት የሚያሳርፋት አጥታ ነው እንጂ አዲስ አበባ ከተማ አይደለችም፣ማክተሚያ እንጂ!

ቢሆንም ቢሆንም ይላሉ አለቃ ታከለ ኡማ ገብሩ

የአዲስ አበባ ቁልፍ እያሽከረከሩ

ቢሆንም

ዋጋዬ ለገሰ ወሬ ቢያራቅቅም፣

"ቆሻሻ ነሽ" ብለው ሲንቋት አናውቅም።

#ዋጋዬ ለገሰ

(ትናንት ከወጣችው ፍትህ መፅሔት ተቀሽባ የቀረበች )

@wegoch
@wegoch
@nagayta
ብቸኝነት ሲሰማህ ማሰብ ከቻልክ የአሳብህ ጓደኛ ነህ። ማሰብ ካልቻልክ ብቻህን ነህ። መነጠል የስጋ ሳይሆን የአሳብ ስሜት ነው። ብቸኝነትህን አሳብህ ሲጋራ የአሳብ ጓደኛ አለህ። ብቸኝነትም ጓደኝነትም ስጋ አይደለም። የአብሮነትና የመነጠል ስሜት ነው።
ከሰው ጋር ስትሆን ለብቻህ እንደሆንክ ከተሰማህ በግርግር መሀል ብቸኛ ነህ። በስጋህ ብቻህን ሆነህ ከአሳብህ ጋር አብረህ ከሆንክ አንተማ ጓደኛ አለህ። ከቻልክ የወዳጅ አስፈላጊነትን ቀንስ። ሰው ብታጣም ያጣኸው ስጋ ነው። አብሮህ የሆነ አላቂ ነው። ዛሬ የሚቀርብህ ነገ የሚርቅ ነው። ወሳኙ ጉዳይ ህሊናህን አለማጣትህ ነው። የሌላ ስጋ ሲለይ አሳብህ ካንተ ጋር ነው።

መለየት የስጋ ነው። ብቻህን እንዳልሆንክ ከተሰማህ የአንተ ጓደኛ ስሜትህ ነው።
©ይስማዕከ ወርቁ
@wegoch
@wegoch
@wegoch
አንድ ወጣት መንገደኛ አንድ ቀን አንድ በጣም ያረጁ ሽማግሌ የዛፍ ችግኝ ሲተክሉ ያገኛቸው እና "የምን ችግኝ ነው የሚተክሉት አባቴ?" ብሎ ይጠይቃቸዋል ።እርሳቸውም "ጣፋጭ ፍሬ የሚያፈራ ዛፍ ነው። "ይሉታል፡፡
.

"ከስንት ዓመት በኋላ?"በማለት ሲጠይቃቸው፣ "ተሰባ ዓመት በኋላ"ሲሉት ወጣቱ በጣም ይገረምና፣ "ከፍሬው ላይቀምሱ ምን ያደርግልዎታል? እንዲያው በከንቱ ነው የሚለፉት።" ይላቸዋል፡፡ሽማግሌው በወጣቱ ነገር ተገርመው "አይ ልጄ እንዳልከው እኔ አልደርስበትም ፡፡ግን ወደዚህ ዓለም ስመጣ ዓለም ባዶ አልነበረችም፡፡እኔም ከሄድኩ በኋላ ባዶ አትሆንም ፡፡እኔ ስበላ የኖርኩት ፍሬ አባቶቼ ከተከሉት ዛፍ ነው። እኔም በተራዬ ለልጆቼ በመትከል ላይ ነኝ። "አሉት ይባላል፡፡

በዓሉ ግርማ፤ ሀዲስ ፣ገጽ 143
@wegoch
@wegoch
@wegoch
*ባለ መሰንቆውና ባለ ወለሎው *


“ ሮድ ደሴት” በተባለ አገር ውስጥ እንደ እንደምኖር የነገርኩት ጓደኛየ“ እና ባሣ አጥማጅነት ነው የምትተዳደረው?”ብሎኛል፡፡ ሮድ ደሴት አበሻ እጥረት ክፉኛ ከሚያጠቃቸው ክልሎች አንዱ ነው ፡፡ አሁን ምድሩም ሰማዩም ሰውም ነጭ ነው፡፡
ያገር ሰው በጣም ይናፍቀኛል፡፡ የሆነ ያበሻ ዓይነ ውሃ ያለው አልፎ ሒያጅ መንገድ ላይ ካየሁ ከሚበር አውቶብስ ላይ እንደ ጅምስ ቦንድ ተወርውሬ ወርጀ ስልኩን በቃሌ እቀበለዋለሁ፡፡ ከሁለት ሱዳናውያን ጋር የተዋወቅሁት በዚህ አጋጣሚ ነው፡፡
ያበሻ ናፍቆቴንአናቴ ላይ ሲወጣ ወደአበሻ- ጠገብ ክልሎች እቀላውጣለሁ ፡፡ ባቡሬን ጭኘ መጭ ወደ ውሻንግቶን ዲሲ! ዲሲ የውሃና የመብራት እጥረት የሌለበት አዲስአበባ ማለት ነው፡፡
ባለፈው ሳምንት ሚኒሶታ ወረድሁ፡፡ ከተማይቱ በበረዶ ተዝረክርካ የሰነፍ ቡሃቃ መስላለች፡፡ የተፈጥሮን ጨካኝነት፤ የቶማስ አልቫ ኤዲሰንን ያለም ቤዛነት ለማረጋገጥ የሚፈልግ ሚኒሶታ ይሂድ፡፡ ወይ አዲስ አበባ! አዱ ገነት፡፡ እብድ የያዘሽ ውበት፡፡ ሰው እንዴት ጥሎሽ ይመጣል? ሰው እንዴት ከገነት ያመልጣል?
ከመኪና ማቆምያው ተሥቼ አዳራሹ ድረስ እስክገባ ድረስ የተቀበልኩት መከራ ራሱን የቻለ ሰማእትነት ሆኖ ለትውልድ ይዘከርልኝ ፡፡ ብዙ ብርድ አጋጥሞኛል እንዲህ አራት ጃኬትና ሁለት ሱሪ ገልቦ፤ አስገድዶ የሚሠር ብርድ ደርሶብኝ አያውቅም፡፡ እድል ፈንታየ ብሎ ብሎ ደም እንደ ብይ በሚጠጥርበት፤ ያፍንጫ ጸጉር እንደጃርት ወስፌ በሚቆምበት አገር ይጣለኝ?
ደሞ እቺም ኑሮ ሆና “በርገርህን እየገመጥክ ትደነፋለህ አይደል?” የሚል ብሽቅ መልክት ይልኩልኛል። ባለመልክቱ! እስቲ ያዲሳባን የጧት ጸሐይ፤ በበርገር ለውጠኝ!!
ሳይደግስ አይጣላም በህይወቴ ባካል ላገኛቸው ከምፈልጋቸው ሰዎችአንዱ የሆነውን ጋዜጠኛ ሰሎሞን ደሬሳን አገኘሁት፡፡ ሰሎሞን ፈላስፋ ነው፡፡የመጀመርያው የሥእል ሓያሲም ነው፡፡ በኦሮምኛ ፤አማርኛ እንግሊዝኛና ፈረንሳይኛ የሚራቀቅ ሊቅ ነው፡፡ ወዳጅ ባታደርገው እንኳ ለፍልምያ የምትመርጠው ሰው ነው፡፡ እንድታስብ የሚገፋፋህ ፤አርፈህ እንድትቀመጥ የማያደርግህ ሰው ማግኘት መታደል አይደል? መጣጥፎቹ ተሰብስበው በመጽሐፍ አለመውጣታቸው ያስቆጫል፡፡ ”ልጅነት ” የምትል በዘልማዳዊው የአማርኛ ስነግጥም ላይ የሸፈተች የግጥም መደብል ሲያሳትም እንደ መናፍቅ ተቆጥሯል፡፡ የትውፊት አስጠባቂው አቤ ጉበኛ በሰሎሞንን ግጥምና በዳኛቸው ወርቁ ልቦለድ ላይ ለማላገጥ “ጎብላንድ አጭበርባሪው ጦጣ”የሚል መጽሐፍ እስከማሳተም ሂዷል፡፡ የአቤ ጎብላንድ ዛሬ በታሪክ ቅርጫት ውስጥ ተጥላለች፡፡ የሰሎሞንና የዳኛቸው መጽሐፎች ግን ገቢያ ላይ በጣም ይፈለጋሉ፡፡ ለምሳሌ ስለባህል ግብዝነት በተነሣ ቁጥር ይችን የሰውየውን ግጥም ማን ይረሣታል?
በኢትዮጵያ ባልጎ መታየቱ
ሳይሆን ቂንጥር ማስቆረጡ
ህጻኗን ልጅ እንደ ቆዳ መስፋቱ
መባለጉ
ኣፉን ሞልቶ” ቂንጥር “ ብሎ መጥራቱ
የሆነ ጊዜ ላይ፤ ስብሐት ገብረእግዚኣብሄር ስለወዳጁ ስለሰሎሞን ”ከሸክስፒርና ከዳንቴ ቀጥሎ ትልቁ ባለቅኔ ሰሎሞን ነው” ብሎ ጻፈ፡፡ ላዲስ ነገር ጋዜጣ የሚሆን ቃለመጠይቅ ሳደርግለት“ሰሎሞንን በዓለም ሦስተኛ ገጣሚ አድርገህ ጽፈሐል፤ አግባብ ነው?”አልኩት፡፡
“እንደዛ ብያለሁ?”
“ኣዎ”
ስብሐት ትንሽ አሰበና መለሰ፤ “ እንዲህ ያልኩት በጣም በናፈቀኝ ሠአት መሆን አለበት“
ከሥነጽሁፉ ምሽት በበኋላ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማኅበር ”ሬድ ሲ” ሬስቶራንት ራት ጋበዙን፡፡ እንደምንም እየተንፏቀቅሁ ከሰሎሞን አጠገብ ያለውን ቦታ ያዝኩ፡፡ ይችን ብርቅ አጋጣሚ ተጠቅሜ ከልጅነት እስከ ሽበት ያሳለፈውን ገድሉን አናዝዘዋለሁ ብየ አሰብኩ፡፡አልቀናኝም፡፡ ከሰለሞን ጋር ጨዋታ እንደ ጀመርሁ ከኋላየ ባለጌ ወንበር ላይ የተቀመጠ ተስተናጋጅ፤ ባንገት ጥምጥሜ ጎትቶ ካዞረኝ በኋላ” ቢራውን ትተህ ለምን ጠንከር ያለ ነገር አትወስድም?”በሚል ጥያቄ ጠመደኝ፡፡ ቢራውን ትቸ ጠንከር ያለ ነገር የማልወስድበትን ሰባት ምክንያት ስዘረዝር ራቱ ተገባድዶ ከፍ አለ፡፡
ከእራት በኋላ አዝማሪው ወደ መድረክ ወጣና ማሲንቆውን ማስተከዝ ጀመረ ፡፡ በቤቱ ያለው ሰው በማሲንቆ ዜማ ታጅቦ ወደ ግል ወሬው ተጠመደ፡፡ “ኣንድ ኮርኔስ እዚህ ጋ ያዘዘ ማን ነው?” የሚለው ያስተናጋጇ ድምጽ ካዝማሪው እንጉርጉሮ በላይ ጠብድሎ ይሰማኛል፡፡ ሰሎሞን ከወንበሩ ተነሥቶ በዝግታ እየተራመደ ወደ መድረኩ ከወጣ በኋላ አዝማሪውን ሸልሞ አጠገቡ ቁጭ አለ፡፡ ዓይኑን ለበስ አድርጎ እልምም !! በማሲንቆው ተሳፍሮ የት ደርሶ ይሆን? ወለጋ-አዲስአበባ - ደጃች ውቤ ሠፈር- ፤ የከተማ መኮንን ክራር - ምኒልክና ጊዮርጊስ በፈረቃ ከሚጋልቡት የአራዳ ፈረስ፡፡
ልጅነት በተባለቸው መድብሉ ስለአንድ የውቤ በረሃ ጀግና በጻፈው መወድስ ውስጥ እኒህ መስመሮች ተካትተዋል፡፡
”ደኑ ርቆት፤
መንገዱ ጠፍቶት
ጓዱ ረስቶት
በጨለማ ቤቱን ስቶት“
ዛሬ እኒህ መስመሮች በግዞትና በስደት ሰጥመው የቀሩ ድንቅ ኢትዮጵያውያንን ሁኔታ የሚገልጹ አድርጌ ብተረጉማቸው ማን ይፈርድብኛል?
( ወዳጄ ገጣሚ ዮናስ አንገሶም ኪዳኔ የሰሎሞንን መጽሐፎች ስለሰደድክልኝ ምስጋናየ ይድረስህ፡፡)

በእውቀቱ ስዩም

@wegoch
@wegoch
አንድ ሰው ሌላውን ሰው ለምን ይወዳል? አንድ ብላቴና አንዲትን ኮረዳ የሚወዳት ለምንድን ነው? ስለሌሎች ሰዎች አላውቅም:: እኔ ግን ወሰንን የወደድኳት በብርሀን ተከባ ስላየሁአት ነው::
ለመስቀል ለመስቀል የከተማችን ህዝብ በጠቅላላ ተሰብስቦ ዳመራ የሚያቀጣጥልበት ጉብታ ከከተማው ወጣ ብሎ አለው::እስላሙ የሙስጠፋ አባት እንኳን ከነቤተሰባቸው ለወሬ ብለው ይመጣሉ:: ሲመሽ አንድና ሁለት ሰአት ገደማ ህዝቡ ዳቦቱን ይዞ ከየቤቱ ሲወጣ የንፋስ መውጪያ ከተማ ከሰማይ የወረደች ትመስል ነበር::
. . . . .
ወሰን የለሽን ያየሁዋት ይሄን ጊዜ ነበር:: ሰዎች ወደ የቤታቸው ለመሄድ መበተን ሲጀምሩ ወደ እሳቱ ተጠግታ ተቀመጠች:: ብን ያለች ነጭ ኩታ ለብሳለች::
. . . . .
የወሰን ፊት ፀጥ ያለ ነበር:: ሰላም ያለበት ይመስላል:: አልፎ አልፎ ምክንያቱን ባላውቅም በትንሹ ፈገግ ትላለች::አፌን ከፍቼ አያታለሁ:: ከበስተኋላዋ የቆመው ከነጠላና ከጋቢ የተሰራው የሰው ግድግዳ ሲፈርስ ተአምር ተፈጠረ:: ያ የኖራ አገር ባህል ልብስ ግድግዳ ሰማይ ላይ የምትፎልል ድፍን ጨረቃ ከልሎ ኖሯል:: ታዲያ ጠቆር ያለው የወሰን ጭንቅላት ድፍኗ ጨረቃ መሀል ላይ የተቀመጠ መሰለ:: ጨረቃዋ ቢጫ ናት:: የጨረቃዋ ማድያት የለም:: ታዲያ ወሰን በስዕል ላይ የማያትን ትንሽ ማሪያም መሰለችኝ::

**

#ግራጫ ቃጭሎች
#አዳም_ረታ

@wegoch
@wegoch
ደራሲ:- አሌክስ አብርሀም
ከ "ዙቤይዳ " መፅሐፍ ገፅ 201 የተወሰደ
ርዕስ ፡-"እግር በእግር"
ተራኪ፡-ስንታየሁ አዲሱ ሳንታ


@wegoch
@wegoch
@wegoch
ይኼን ጽሁፍ ፖስት ካደረግኩት በሒወት አለሁ ማለት ነው፡፡]
.
የተሳፈርኩበት መኪና ለምሳ አውርዶኝ አንድ ድምጽ የበዛው ኩሽና የመሰለ ቤት ገብቼ ምሳ ስጠብቅ መኪናው አምልጦኝ ሔደ፡፡
እመኪናው ውስጥ የተዋወቅኩት አንድ ልጅ በመስኮት እያፏጨና ጣቶቹን በፍጠን መልክ እያራገበ አስቸኮለኝ፡፡ መኪናው ተፈተለከ..ልደርስበት አቃተኝ፡፡
ከሆነ ነገር የሚሸሽ ይመስላል፡፡
ፈራሁ! ብቻዬን ነኝ!
ያለሁበት ቦታ ሀገሬ አልመስልህ አለኝ፡፡ በአስፓልቱ ግራና ቀኝ ቅኔ ያለው ረጅሞ ሳቅ አሁንም አሁንም ይሰማል.... [ቅኔ የመሰለኝ ዞሬ ማየት ስለፈራሁ ይሆን?]
አዎ ይህን መንገድ አውቀዋለሁ.... መንገዱ የፍርሀት ነው፡፡ በእግሬም አልፌበት አውቃለሁ...ያተጋኝ የነበረው ፍርሀት ነበር፡፡ በዚህ መንገድ የመኪኖች ፍጥነት ድንጋይ እንደ ተነሳበት ውሻ ያለ ማፈትለክ ነው፡፡ ፍርሀት ፍርሀት ፍርሀት....
መሮጥ ጀመርኩ...
አንዳች ነገር እንዳባረረው ሰው፡፡ ቁልቁለት እንዳተጋው አዳኝ...ሮጣለሁ፡፡
በሩቅ እሳት ያነደዱ ሰዎች አየሁ፡፡ ከአስፓልቱ ጠርዝ ከፍ ካለ ዲብ የዱር እንስሳ ይሁን ሌላ ፍጡር መለየት ያቃተኝ ደሙ የሚፈስ ትኩስ ሬሳ እግራቸው ስር አጋድመዋል፡፡...ከመጋጣቸው ሲያርፉ ደሞ ቅድም የሰማሁት አይነት ሳቅ ያፈነዳሉ፡፡
ሩጫዬን ገታሁ....በጎናቸው ባልፍ..."ንሳማ እሱን ቢለዋ አቀብለው! "ባሻዬ" ካሻህ ቁረጥና ስትፈልግ በጥሬ ስትፈልግ በጥብስ አንጀትህን አርስ! መንገድህ እሩቅ ነው..እረፍና ብላ"
የሚሉኝ አልመሰለኝም፡፡ አየሗቸው አበላላቸው ስርአት አገዳደላቸውም ገርነት የለውም፡፡ አረመኔ ናቸው!
ወገኔ አይመስሉም....
በጢሻ ላሳብር ጫካው ውስጥ የሰነዝርኳት የመጀመርያዋ እርምጃ ከደረቀ (ነጭ)የባህር ዛፍ ቅጠል ላይ አረፈች፡፡ ከመቅጽበት ከሚግጡት አጥንት አርፈው ....ቁጣ የተሞሉ የሚደውን እሳት የመሰሉ አይኖቻቸውን በኔ አቅጣጫ ወረወሩ!
☞ የማላውቀው ሲኦል እንደዛ አያስፈራም፡፡
☞ የማላውቀው ሴጣን እንደነሱ የሚያየኝ አይመስለኝም፡፡
ግን
የማውቃቸው ጥቁርና ነጭ የተዋቡ ሽፋሽፍት የሚባል ከላባ የለሰለሰ የጸጉር ሰልፍ የሚከድናቸው አይኖች ነበሩ ያዩኝ፡፡
የጠለቁ በትውልድ ቅብብሎሽ ተንደው የጨረሱ ቁጣዎች ነበር ያተኮሩብኝ፡፡ ሩጫዬን ቀጠልኩ፡፡
ከመቸው ስሬ እንደ ደረሱ እንጃላቸው ከትከሻዬ አናት ሲያለከልኩ ይሰማኛል፡፡
አንድ ጫማ እርቀት ደም ሲመጥ የነበረ አፋቸው እየተከፈተ ይዘጋል....
መዞር ፈራሁ መሮጥ ብቻ፡፡ እነሱም አይዙኝም መከተል ብቻ...
ፊታቸውን ባይ ድንጋጤ ይገለኛል፡፡ መደንገጥ ደሞ አልወድም፡፡ መሮጡ ይሻለኛል..."
ስነቃ ህልመ ለሊት መቶኛል....
ህልም መሆኑ ነው
.
በሒወት አለው

📝 በሀይሉ መለሉጌታ

@wegoch
የኮሮና ቫይረስ ተጠርጣሪውና አመላለጡ
(ልዑል ሀይሌ)

@wegoch
@wegoch
በኮሮና ቫይረስ ተጠርጠጥሮ ያመለጠው ግለሠብና አመላለጡ!..
Based on true story
........................
ባለፈው ያ ገጀራ እኔን ነው...ምንም አታመጣም ብሎ ዝቶብኝ የሄደው? ...አሁን እሱን ሠላም ሳልለው ብሄድ እውነት ፈጣሪስ ይቅር ይለኛል?!..ያ አመዳም ሰውዬስ ቤቴን ሊያፈርስ ዕድሜ ልኩን እንደሞከረ አይደል የኖረው?..መች እንቅልፍ ወስዶት ያውቅና? ...እንደሱ ተንኮልና ሸር ቢሆንማ እኔ ሰንደል ለኩሼ በየጎዳናው እየዞርኩ አልነበር?...እሱንማ አቅፌ ሠላም ሳልለው ብሄድ ጉዞዬ እንዴት ይቀናል? ...ያቺ ከሃዲስ..እምነቴን ፍቅሬን ቀብራው እየተሳለቀችብኝ አይደል የሄደችው?!...በመንገዴ ዳግመኛ እንዳላይህ ብላ በሠዎች ፊት አዋርዳኝ አይደል የሄደችው?....ሠርፕራይዝ አዘጋጅቻለሁ ብላኝ ስሄድ B-29 ሳሙና ጠቅልላ ሰጥታኝ "እኔን ከመፈለግህ በፊት መጀመሪያ እድፍህን አፅዳ!" ብላ አይደል የላከችልኝ?!...ታዲያ ለዚህ ሁሉ ውለታዋ የእጅ ሠላምታዬ ይነሳት? ....አዳሜ ጠብቂኝ!...በእጄ ምን ያህል መሳሪያ እንደታጠቅኩ አላየሽም....ይልቅ አሁን እንዴት ልውረድ?!...."ዶክተር አንዴ ሽንቴን ልሽና መኪናውን አስቁሙልኝ?! .." ..."ደርሰናል ለኮሮና ተጠርጣሪዎች የተዘጋጀ ቦታ አለ እዛ ትጠቀማለህ
" ..."እንዴ!...ኧረ ልፈነዳ ነው አልቻልኩም!...አለበለዚያ እዚሁ ነው ምለቀው!..." ጤነኛ ነህ?... " "ጤነኛ ብሆንማ መች ታፍሱኝ ነበር?...ቤተሠቦቼንም ሳልሰናበት እንዲሁ መንገድ ላይ ልቅር?"...ዶክተሮቹ ውስጤ ሚመላለሠውን ቁጭት መቼም ሊገባቸው አይችልም!...ይሄንን አጋጣሚ ሳልጠቀምማ አልሞታትም!... (በሩን ገንጥሎ ማምለጥ!..)... [እውነት ግን የሠውየው ማምለጥ ግራ ያጋባል!..የራስንም ሕይወት የሌሎች ሠዎችንም ሕይወት አደጋ ላይ ለመጣል መሞከር ምን ይሉት ይሆን?...ፈጣሪ ምሕረቱን ይላክልን ] መልካም ዕለተ ሠንበት
ልዑል ኃይሌ
መጋቢት 6, 2012 ዓ.ም.

@wegoch
@wegoch
ኢትዮጵያዊያንና ወረርሽኝ

ከ101 ዓመት በፊት ዓለምን ከወደ ስፔን በመነሳት አሸብሮ፣ከአውሮፓ ህዝብ ሲሶውን(1/3ኛውን) ረምርሞ፣ ከአስር ወራት በሗላ በቅድስቷ አገር ኢትዮጵያ የደረሰው የህዳር በሽታ ዘጠኝ ሺህ አዲስ አበቤን እና 40 ሺህ ኢትዮጵያዊያንን ቀባሪ አሳጥቶ ፈጃቸው።

በተለይ ህዳር 12 ቀን 1911 ዓ.ም በመዲናይቱ አዲስ አበባ ለአስከሬን መቅበሪያነት የተቆፈረ ጉድጓድ የተሰረቀበት፣ጅብ የሰው ሬሳ ለመብላት አቃቂር ያወጣበት እንደነበር መርስኤ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ "የ20ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ፤ካየሁትና ከሰማሁት" በሚል ርዕስ በፃፉት ውድ የታሪክ ማስታወሻቸው ተከትቧል።

የዚያን ጊዜ በሽታው ወደ ኢትዮጵያ ምድር በንፋስ አማካኝነት የመጣ ሲሆን ጥበበኛው የአገሬ ሰውም በብዙ ዘመን ልምዱ ባካበተው እውቀቱ በመታገል ለ አዕላፍ(ሚሊዮን) የዓለም ህዝብ ህይወት መቀጠፍ ምክንያት የሆነውን ጉንፋን መሠል ወረርሽኝ ተዋግቶ አሸንፎታል።

አዲስ አድማስ ጋዜጣ በ2006ዓ.ም ህዳር ወር ይዞት በወጣው ፅሁፍ እንደሚያትተው በወቅቱ የመንዝ ተወላጅ የነበሩት ወይዘሮ ዘነበች የተባሉ የባህል መድሃኒት አዋቂ ለአዲስ አበቤ ያስተማሩት የአበሻ አረቄን መጠጣት እና ቀይ ሽንኩርት በየ ቤቱ እንዲሁም በእየ አንገቱ ማንጠልጠል በፈረንሳይ ቆንሲል በኩል ሳይቀር ተኮርጆ ወደ አውሮፓ በመላክ "የሠለጠነውን" ዓለም ለመፈወስ በቅቷል።

የሴትዮይቱ ከልምድ የተገኘ መድሃኒት በተለይም አረቄው ከነበረበት በጠርሙስ 10 ሳንቲም ዋጋ ወደ ሰባት ብር አድጎ ሜዲትራኒያንን ተሻግሮ አውሮፓዊያኑን አልቦ(ዜሮ) ከመቅረት ታድጓቸዋል።

ኢትዮጵያዊያን ከዚህም በተጨማሪ የደረቀን የበሬ ቆዳ በታማሚው አካባቢ በማንኳኳትና ጠብ መንጃ ወደ ጆሮው አስጠግቶ በመተኮስ በሽታውን አስደንግጦ ለማባረር ተሳክቶላቸዋል፤ይሄንን ስልት እስካሁን ድረስ ጥቅም ላይ የሚያውል ማህበረሰብ እንዳለ እኔም አውቃለሁ---ጎጃም ሰው ሊሞት ጥቂት ሲቀረው በጠብመንጃ ተኩስ ለማንቃት የመጨረሻ ሙከራ ይደረጋል።

እንግዲህ እኛ እንዲህ ያሉ ከላይኛው ጠቢብ የተላከ ጥበብ ያለን ልዑላን ህዝቦች ነንና ዛሬ መቶ ሰው ይዞ ሁለት(ለዚያውም በዕድሜ የገፉትን) ለሚገድል በሽታ ብለን ከሰውነት ጣሪያ ወርደን ርስ በእርስ እንዳንፈራራ ይሁን።

መጠንቀቅና መሳቀቅን ማመጣጠን ከቻልን ኮሮናን እናሸንፈዋለን።

8335 እንዳይረሳ

።፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ይቆየን!

@wegoch
@wegoch
ጥቁር ድንጋይ

የገንዘብን ጠባይ የእነርሱን ያህል የሚያውቀው የለም
የሚባሉት ስዊዘርላንዳውያን እንዲህ ይተርካሉ፡፡
አንዲት ውብ ልጅ የነበረቺው አንድ ነጋዴ ነበር፡፡ ከአንድ አራጣ
አበዳሪ ከረጢት ሙሉ ብር ተበድሮ ማትረፍ አቅቶት ከሠረ፡፡
የመክፈያውም ጊዜ ደረሰ፡፡ የብድር ውሉ ነጋዴው በጊዜው
ብድሩን ካልከፈለ ወደ እድሜ ልክ ወኅኒ እንደሚወረወር
ይገልጣል፡፡ ይህ ቀን መድረሱ ለነጋዴውና ለልጁ አስደንጋጭ
ሆነባቸው፡፡
የአራጣ አበዳሪው የ80 ዓመት ሽማግሌ፣ ጠባየ ክፉና መልከ
ድፉ ነው፡፡ በዚያ አካባቢም እርሱን የሚወደው አንድም ሰው
አልነበረም፡፡ ነገር ግን ነጋዴዎች ገንዘብ ሲፈልጉ ከእርሱ
ውጭ የሚያበድራቸው አልነበረም፡፡ ይህ አራጣ አበዳሪ
ነጋዴው ከወኅኒ የሚተርፍበትን አንድ ሸውክ አቀረበ፡፡
‹የነጋዴው ልጅ እኔን ለማግባት ፈቃደኛ ከሆነች ነጋዴው ከወኅኒ
ይተርፋል፤ ያለበለዚያ ግን እድሜ ልኩን ይማቅቃል› አለ፡፡
ነጋዴውም ልጁም ደነገጡ፡፡ ሁለቱም ለምርጫ አስቸጋሪዎች
ናቸው፡፡ በአንዱ አንደኛው በሌላውም ሌላኛው ይሠዋሉ፡፡
የአንዱ መሠዋት ደግሞ ሁሉንም ይሠዋል፡፡ ምን ይደረግ?
በሁለት ሞት መካከል የሚደረግ ምርጫ፡፡ መጨነቃቸውን
ያየው አራጣ አበዳሪ ሁለተኛ አማራጭ አቀረበ፡፡ ‹እዚህ
ማሠሮ ውስጥ ሁለት የባሕር ድንጋዮች እከታለሁ፡፡ ነጭና
ጥቁር፡፡ ልጅህም እዚያ ባሕሩ ውስጥ ሆና ዓይኗን ተጨፍና
እጇን ወደ ማሠሮው ውስጥ ትከታለች፡፡ ነጩን ካወጣች እኔን
አታገባም፣ አንተም አትታሠርም፤ ጥቁሩን ካወጣች ደግሞ
እኔን ታገባለች አንተ ግን አትታሠርም› አላቸው፡፡ አራጣ
አበዳሪው ውርርዱ ባሕሩ ውስጥ እንዲሆን የፈለገው ልጂቱ
ባሕሩን ፈርታ ያቀረበላትን ጥያቄ እንድትቀበል አስቦ ነው፡፡
አባት ተጨነቀ፡፡ ልጁ ግን ስለ ችግሩ ብቻ ማሰብ ጥቅም
እንደሌለው ገባት፡፡ ችግሩን ተረድታ መፍትሔውን ማሰብን
መረጠች፡፡
‹የጊዜህን ሃያ ከመቶ ችግሩን ለመረዳት አውለው፤ ቀሪውን
ሰማንያ ከመቶ ደግሞ መፍትሔውን ለመፈለግ› ይባል የለ፡፡
ከወደቁ በኋላ ለመነሣት መሞከር እንጂ መንፈራገጥ ትርፉ
መላላጥ ነው፡፡ ጥርስን ነክሶ ቁስልን ማከም እንጂ ስለ ቁስል
ማልቀስ ቁስልን አያድነውም፡፡ ልጅቱ ተስማማች፡፡ አባቷ ግን
በኀዘን ልቡ ተሰበረ፡፡ አራጣ አበዳሪውም ‹በሂደቱ ላይ ምንም
ዓይነት ጥያቄ ማቅረብ አይቻልም፤ ይህንንም በዳኞች ፊት
እናደርገዋለን› አላት፡፡ ነገሩን አሰበችና ተስማማች፡፡ አራጣ
አበዳሪው የልጂቱን መስማማት ሲመለከት ደስ አለው፡፡ አያሌ
ሕዝብ ነገሩን ሊያይ ተሰበሰበ፡፡ አራጣ አበዳሪውም ከሕዝቡ
ተነጥሎ ብሎ ወደ ባሕሩ ዳር ሄደና ድንጋዮችን መፈለግ
ጀመረ፡፡ ልጂቱ እንዳያውቅባት አድርጋ በንቃት
ትከታተለዋለች፡፡ ሆን ብሎ ሁለት ጥቁር ድንጋዮችን ወደ
ማሠሮው ውስጥ ሲጨምር አየቺው፡፡ አሁን የበለጠ ነገሩ
ተወሳሰበ፡፡ ስለ ሂደቱ ደግሞ ቅሬታ ማቅረብም ሆነ ጥያቄ
መጠየቅ አይቻልም፡፡ ወዲያው መፍትሔውን ወደማሰብ
ተሸጋገረች፡› ‹በችግር ላይ መቆዘም ወደ ድቅድቅ ጨለማ
ይነዳል፤ በመፍትሔ ላይ ማምሰልሰል ግን ወደ ብርሃን አዳራሽ
ይወስዳል› ይባላልና፡፡
አራጣ አበዳሪው አባትና ልጅን ወደ ባሕሩ ዳር ጠራቸው፡፡
የልጂቱ ዓይን ተሸፈነ፡፡ እጇንም ወደ ማሠሮው ውስጥ
ከተተችው፡፡ ሕዝቡ ልቡ ቀጥ ብሎ የሚፈጠረውን መከታተል
ጀመረ፡፡ ልጂቱ ወደ ማሠሮው ውስጥ የከተተቺውን እጅ
አወጣችውና ያመለጣት አስመስላ የባሕሩን ድንጋይ ባሕሩ
ውስጥ ጣለቺው፡፡ አራጣ አበዳሪው ደነገጠ፡፡ ልጂቱም
‹አትደንግጥ፡፡ በማሠሮው ውስጥ አንድ ነጭና አንድ ጥቁር
ድንጋይ ነው አይደል የከተትከው?› አለቺው፡፡ እርሱም
ማጭበርበሩ እንዳይታወቅበት ‹አዎን፤ በተባባልነው መሠረት
አንድ ነጭና አንድ ጥቁር ድንጋይ ነው የከተትኩት› አላት፡፡ ‹ያ
ከሆነ ነገሩ ቀላል ነው፡፡ ማሠሮው ውስጥ የቀረው ድንጋይ
ይታይ፤ የቀረው ነጭ ከሆነ ያወጣሁት ጥቁሩን ነበረ፤ የቀረው
ጥቁር ከሆነ ደግሞ ያወጣሁት ነጩን ነበረ ማለት ነው›
አለቺው፡፡ አራጣ አበዳሪው መበላቱ ገባው፡፡ ዳኞቹም ‹ልጂቱ
ትክክል ናት› አሉና ወደ ማሠሮ እጃቸው ከትተው ጥቁሩን
ድንጋይ አወጡት፡፡ የወደቀውም ነጩ መሆኑን ተናገሩ፡፡ አራጣ
አበዳሪውም ሁለቱንም ከሠረ፡፡
ማንኛውም ችግር መፍትሔ አለው፡፡ ብቻውን የተፈጠረ ችግር
የለም ይባላል፡፡ እንዲያውም አንድ ችግር በሥሩ ከዐሥር
በላይ መፍትሔዎችን ደብቋል የሚባል ነገርም አለ፡፡ በችግሩ
ላይ አትዘን፣ አትናደድ፣ አትቆዝም፤ አታላዝን፤ ስሜትህን
ተቆጣጠረው፤ መሆን አልነበረበትም እያልክ አትብገን፤
ለመፍትሔው ተነሥ፤ አካባቢህን ቃኘው፤ ቀዳዳዎቹን
ተመልከት፤ ስንጥቆቹን አስተውል፤ ችግሩን በሚገባ ተረዳው፤
ከዚያም መፍትሔውን ለመውለድ አምጥ፡፡ ፈታኝህን ሙሉ፤
ፈተናህንም ፍጹም አድርገህ አትቁጠራቸው፤ ፈታኙም ክፍተት፤
ፈተናውም ንቃቃት አለው፡፡ የተዘጉ የሚመስሉ በሮች ሁሉ
የተከፈተ ቦታ አላቸው፤ የተደፈኑ የሚመስሉ ግንቦች ሁሉ
የተሸነቆረ ቀዳዳ አላቸው፤ የሞሉ የሚመስሉ ወንዞች ሁሉ
የሚጎድሉበት ቦታ አለ፤ አንተ ብቻ መፍትሔ ከማሰብ
አታቋርጥም፡፡ ጥቁር ድንጋይ ብቻ ሲቀርብልህ፤ አንተ
በጥበብህ ነጭ አድርገው፡፡
=======////////=======
© ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ብርሃኔ
@wegoch
@wegoch
@wegoch
⁉️

ይሄ የአንድ ጣልያናዊ ሰው ታሪክ ነው፡፡ እጅግ በጣም ረዘም ኣርጎ ዛሬ በሙሉ
የለይቶ ማቆያ ሁናቴ ውስጥ ያለችው ሀገሩ ከየት ተነስታ የት ደረሰች የሚለውን
ይናገራል፡፡ እንደወረደ ነው የተረጎምኩት፡፡ በየመሃሉ ስብር ስብር ማለቱን ችለህ
አንብብና ፍረድ፡፡

ዛሬም እንደትናንቱ ከጓደኞችህ ጋር ፈታ እያልክ ከሆነ፣ በሰው የተጨናነቁ ክለቦች ውስጥ ስትጨፍር እያነጋህ ከሆነ፡፡ ራስህን በመስታወት ተመልከትና ስርዓትህን መያዝ ጀምር፤ በሽታ በካልቾ እየጠለዘ ቤትህ ሳያስቀምጥህ፡፡ አለም ምን እየመጣባት እንደሆነ ገና ፍንጩም የላትም!!!" መቼም በዜና ሰምተሃል፣ ሙሉ ሀገሪቷ- ጣልያን-ራሷን በለይቶ ማቆያ ውስጥ
ከትታ፣ ከአለም ተገልላ ተቀምጣለች፡፡ በኮሮና ምክንያት፡፡ ሁኔታው በጣም መጥፎና አሳዛኝ ነው፡፡ ይበልጥ ልብ የሚሰብረው ግን፣ ቀሪው ኣለም " አይ እኔን አይነካኝም " በሚል ሀሳብ እጁን አጣጥፎ መቀመጡ ነው፡፡
ይሄንን የቀሪውን አለም ሀሳብ የማውቀው፣ እኛም ከሁለት ሳምንታት በፊት እናስበው ስለነበር ነው፡፡
ነገሮች ከየት ተነስተው የት እንደደረሱ፣ አሁን ምን ላይ እንዳለን፣ በየት በኩል
እንዳለፍን ደረጃ በደረጃ እንየው፡፡
ደረጃ አንድ... ኮሮና የሚባል ቫይረስ የሆነ ቦታ መኖሩን ሰምተሃል፡፡ አለ ብቻ፡፡ ከዛ የመጀመሪያዎቹ ተጠቂዎች በሀገርህ ብቅ ብቅ ማለት ይጀምራሉ፡፡ አንተ ግን ለትንሽዬ ጉንፋን ምንም ሀሳብ አይገባህም፡፡ "ገና ወጣት ነኝ፡፡ እድሜዬ ከ75 አልገፋ፡፡ ምን እሆናለሁ? ምንም!!!" " እኔን ምንም አያገኘኝ፡፡ ሰዉ ያለቅጥ
እያካበደ ነው፡፡ አሁን እኔ የፊት ማስክ እና የሽንት ቤት ሶፍት ልገዛ የሚገባኝ ሰው
ነኝ??? ኧረ በጭራሽ!!" " ከፈለገ ሰዉ ይነፋ እንጂ፣ እኔ ኑሮዬን እቀጥላለሁ፡፡"

ደረጃ ሁለት...

አንድና ሁለት እየተባለ የሰማኸው የበሽተኞች ቁጥር፣ እየጨመረ እየጨመረ ይሄዳል፡፡ መንግስትህ " አደገኛ ክልሎች" ብሎ የመጀመሪያዎቹ በሽተኞች ያሉባቸውን ጥቂት፣ ትናንሽ ከተሞች ይዘጋል- ለይቶ ማቆያ፡፡ ያገልላል፡፡ እነዚህ ከሌሎች ከተሞች የበለጠ የህመምተኛ ቁጥር ያለባቸው ናቸው፡፡
እንዲሄ ስትል ትሰማለህ፡፡ " ውይ ሰዎቹ በቃ ተገለሉ? ሲያሳዝን፡፡" ትንሽ ትንሽም
ቢሆን ያስጨንቅሃል፡፡ "ግን መንግስት ጉዳዩን ስለያዘው መደናገጥ
አያስፈልግም" የተወሰኑ ሰዎችን ህልፈት ትሰማለህ፡፡ ግን በእድሜ የገፉና በሞት አፋፍ ላይ የደረሱ ሰዎች ናቸው ብለህ ትፅናናለህ፡፡ እንደውም፣ ሚዲያው ለትርፍ እና ለእይታ ሲል ያሳያቸው ናቸው ፣ እነዚህ ወራዶች ብለህ ትወቅሳለህ፡፡
ህይወት መልኳን ሳትቀይር ትቀጥላለች፡፡ "ከጓደኞቼ ጋር እየተገናኘሁ ፈታ
ማለትማ አልተውም፡፡ እኔ!?? ኧረ በደንብ፡፡ ያለንበት አካባቢ ሰላም ነው፣ እኔን ኮሮና ከሚይዘኝ፣ ፍቅር ቢይዘኝ ይቀላል" እያልኽ ትቆያለህ.

ደረጃ ሶስት

የበሽተኞች ቁጥር መመንጠቅ ይጀምራል፡፡ በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ በሁለት እጥፍ አድጎ ያድራል፡፡ የሟቾች ቁጥርም እንደዛው፡፡ የአደጋ ክልሎች ይታወጃሉ፡፡ በሀገራችን በሽታው በጣም የገነነባቸው ኣራት ክልሎች- የሀገሪቱ 25% የሚሆነው- ከሌሎች እንዲለዩና እንዲገለሉ ተወሰነ ( የካቲት-29)፡፡ በነዚህ ክልሎች ውስጥ ትምህርት ቤቶችና ዩኒቨርሲቲዎች ቢዘጉም፣ መጠጥ ቤትች፣ ሆቴሎችና የስራ ቦታዎች ክፍት ነበሩ፡፡ አንድ ውስጥ አዋቂ ነኝ የሚል ሀላፊነት የጎደለው ጋዜጣ፣ የመንግስትን ውሳኔ መንግስት ከመዘጋጀቱና ለህዝብ ከማሳወቁ በፊት ለህዝብ ይፋ አወጣው፡፡
በዚህም በተፈጠረው መደናገጥ፤ አደገኛ ተብለው ከተለዩት አራት ክልሎች
ውስጥ 10ሺ ሰዎች አምልጠው ወደ ቀሪው የጣልያን ክፍል ተበታተኑ- በአንድ
ለሊት ብቻ፡፡ የቀረው 75% የሀገሪቱ ህዝብ፣ ከዘወትር ተግባሩ አንዳች እንኳን ሳይስተጓጎል ኑሮውን ይመራል- ኮሽም አይልበት፡፡ በሀገሬ፣ አብዛኛው ህዝብ ገና የጉዳዩን ከባድነት አልተረዳም፡፡ በየመገናኛ ብዙሃኑ- እጃችሁን ታጠቡ፣ ህዝብ የሚበዛባቸው ቦታዎች መሄድ ቀንሱ፣ በብዛት እየሆናችሁ አትሰብሰቡ እየተባለ በየአምስት ደቂቃው ይነገራል፡፡ ጆሮ የሚሰጥ የለም፣ ከልቡ የሚያስቀምጥ
አልተገኘም፡፡

ደረጃ አራት

በሽታው እንደ ክፉ ወሬ እየተዛመተ ነው፤ የበሽተኛው ቁጥር ደግሞ ሀገሪቱን
እንደ ድንገተኛ ደራሽ እያጥለቀለቃት፡፡ በየክልሉ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችና
ዩኒቨርሲቲዎች ቢያንስ ለ1 ወር ያህል እየተዘጉ ነው፡፡ መንግስት በሀገር ደረጃ
የድንገተኛ የጤና አደጋ ቀውስ ውስጥ መግባታችንን አውጇል፡፡ ሆስፒታሎች
በሙሉ አቅማቸው ህዝብ ያስተናግዳሉ፡፡ ሌሎች አገልግሎቶች ሁሉ ተዘግተው፣
የኮሮናን ታማሚዎች ብቻ እያስተናገዱ ነው፡፡ በቂ ሀኪምና ነርስ በሀገሪቱ የለም፡፡
በጡረታ የተገለሉና ትምህርታቸውን ለሁለት አመታትና ከዛ በላይ የተከታተሉትን ሁሉ እየቀጠሩ እየሰሩ ነው፡፡ በዚህ ወቅት፣ የማታ የቀን ተረኛ ነኝ ብሎ ነገር የለም፡፡ ሀኪም ከሆንክ መቆም የቻልክበትን ያህል ቆመህ ስራህን ትሰራለህ፡፡ ካለረፍት የሚያገለግሉት ሀኪሞች፣ በሽታው ይተርፋቸዋል፡፡ ወደ ቤተሰቦቻቸውም ይወስዱታል፡፡ በመተንፈሻ ህመም የሚሰቃዩ ፣ ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ ውስጥ ያሉ ሌሎች በሽተኞች ቢኖሩም፣ ለሁሉም የሚበቃ መታከሚያ ቦታ የለም፡፡ እዚህ ጋ ስትደርስ፣ በቃ ይህ ሁኔታ ልክ እንደ ጦር ሜዳ ነው፡፡ ሀኪሞቹ የሚያክሙት የመዳን እድሉ የየትኛው ከፍ ያለ ነው በሚለው ላይ ብቻ ተመስርተው ነው፡፡ ይህ ማለት፣
አዛውንቶች፣ በእድሜና በጤና ሁኔታቸው የገፉ ሰዎች ይረሳሉ፣ ይተዋሉ፡፡
ቅድሚያ ለኮሮና ህመምተኞች፡፡
ለሁሉም የሚበቃ ሀኪምም የህክምና መገልገያም የለም፡፡ በቃ፡፡ ይሄ ሁሉ ጨዋታና ተረት አይደለም፡፡ በሀገሬ ሲከሰት ቆሜ የታዘብኩት እንጂ፡፡
ሰዎች በኮሮናም ይሁን በሌላ በሽታ ተይዘው፣ የመታከሚያ ቦታ በማጣት ብቻ
እየሞቱ ነው፡፡ አንድ ሀኪም ጓደኛዬ እጅግ በተሰበረ ልብ ሆኖ " ዛሬ ብቻ ሶስት
ሰዎች ሞቱብኝ " ብሎ ደውሎልኛል፡፡ ነርሶቹ ዘወትር እንባ እንዳፈሰሱ ነው፡፡
ምክንያቱም፣ ለህመምተኞች የተወሰነ ኦክስጅን ከመስጠት ውጪ ምንም እርዳታ የሚሰጡበት አቅም የላቸውምና፡፡
ትናንት አንድ የጓደኛዬን ዘመድ በሞት አጣን- በቃ የሚያክመው አላገኘም፡፡
ቀውስ ላይ ነን፡፡ ቀውስ፡፡ የገነባነው ስርዓት ወደ መፈራረስ ተቃርቧል፡፡
በምትሄድበት ሁሉ፣ የሚሰማውም የሚታየውም የኮሮና ቫይረስ ወሬ ነው፡፡ በቃ!!

ደረጃ አምስት

እነዛ 10ሺ ሰዎች ትዝ አሉህ፣ ከተለዩት ክልሎች ያመለጡት? በነሱ ምክንያት
ሙሉ በሙሉ ሀገሪቱ ራሷን በለይቶ ማቆያ ውስጥ ትከትት ዘንድ- ከቀሪው አለም ትቆራረጥ ዘንድ ግድ ሆኖባታል፡፡ ( የካቲት 30) የመለየቱ አላማ፣ የቫይረሱን ስርጭት መቀነስና መቆጣጠር ነው። ኣሁን... ዛሬ ሰዎች ወደ ስራ ይሄዳሉ፡፡ ገበያ ወጥተው ሸመታ ያከናውናሉ፡፡
መድሀኒት ይገዛሉ፡፡ የንግድ ቦታዎች ሁሉ ክፍት ናቸው፡፡ ያ ባይሆን የሀገሪቱ
ኢኮኖሚ ሽባ ይሆን ነበር፡፡( አሁንም ኢኮኖሚው እየተጎዳ መሆኑን የሚያሳዩ
ምልክቶች ቢኖሩም)፡፡ እንዲህም ቢሆን ግን አሳማኝ ምክንያት ሳይኖርህ ከቦታ
ቦታ መንቀሳቀስ አትችልም፡፡
የት ደረስን? በቂ የሆነ ፍርሀት ላይ ደርሰናል፡፡ ብዙ ሰዎችን የፊት "ጭምብል" እና የእጅ ጓንት አጥልቀው ታያቸዋለህ፡፡ ግን ደግሞ፣ "አይበገሬ" ነን የሚሉ የጅል ጀግኖች አሁንም እየተሰበሰቡ ወደ ሬስቶራንቶች ይሄዳሉ፡፡
ቀጥሎሳ? ከሁለት ቀናት በኋላ ሁሉም አይነት የንግድ እንቅስቃሴዎች እንዲቋረጡ ታዘዘ፡፡ መጠጥ ቤት የለ፣ ምግብ ቤት፣ ሱቅ... ምንም፡፡ ከመድሃኒት ቤቶችና ከሱፐርማርኬቶች በቀር ሁሉም ተዘጉ፡፡ አንተ እንኳን መንቀሳ
2024/09/25 13:26:28
Back to Top
HTML Embed Code: