Telegram Web Link
ለውብ ቀን!
💚

"… የሕይወትን ችግር በሎጂክ ድራድር ትተበትበዋለህ። ቦቅቧቃነትህን በአይናውጣነት
አንቀልባ አዝለህ፣ የባጥ የቆጡን በመቀባጠርህ ትኩራራለህ። እፍረተ ቢስ ነገር ታወራና፣
ወዲያው በፍርሃትና በሰበብ ትከልሰዋለህ። የምፈራው የለም እያልክ፣ ዞር ብለህ
ትለማመጣለህ። በሰቆቃ ጥርሴን አፋጫለሁ ብለኸን፣ ኋላ ደግሞ እየቀለድክ ሳቁልኝ
ትለናለህ። ቀልዶችህ ጣዕመ–ቢስ መሆ ናቸውን ስታውቅ፣ በስነ–ፅሑፋዊ ዋጋቸው
ትመፃደቃለህ። መከራ ደርሶብህ ብታውቅም እንኳን ለስቃይህ ቅንጣት እንኳ ዋጋ
አትሰጠውም። ከምትቀባጥረው አንዳንዱ እንኳ እውነት ቢሆንም ይሉኝታ ቢስነትህ መጠን
የለውም። ከግብዝነትህ የተነሳ ሀቅህን አደባባይ አውጥተህ ታረክሰዋለህ። በእርግጥ
ማለት የምትሻው ነገር አለ፣ እቅጩን እንዳትናገር ግን ፍርሃት ጠፍሮ ይዞሃል፣ለመናገር
የሚያበቃ ድፍረት አጥሮሃል። የፈሪ ባለጌ ነህ። በአእምሮህ ንቃት እየተኩራራህ ሳለ
ትወላውላለህ። ምክንያቱም አእምሮህ ብሩክ ቢሆንም እንኳን፣ ልብህ በልክስክስነት
ፅልመት ተወርሷል። ንፁህ ልቦና በሌለበት ደግሞ ምሉዕ ንቃተ– ህሊና ሊኖር አይችልም።
ወራዳነትህ! አትርሱኝ ባይነትህ !
የመቀላመድህ ገደብ አጤነት! …"


– "የስርቻው መጣጥፍ" ፣ ገፅ 38፣ ከተሰኘው መፅሐፍ የተቀነጨበ ( ደራሲ፣ ፊዮዶር
ዶስቶየቭስኪይ – ትርጉም፣ ፋሲል ይትባረክ)

"ናካይታ"💚

@wegoch
@wegoch
ቀን ዝንብና ንብ እያወሩ በወሪያቸው መሀል ዝንብ ንብን እንዲህ ስትል
ጠየቀቻት
" ንብ ሆይ ለምንድነው የሰው ልጆች እኔን የሚጠሉኝ? ለምንስ ነው
የሚጸየፉኝ ?
ቤታቸው ስገባ ያባርሩኛል ይገድሉኛል።
የሚጠጡት ነገር ላይ ከተገኘሁ ይደፉታል የሚበሉት ነገር ላይ ካረፍኩ
ያረፍኩበትን ቦታ ያለውን እህል ቆርሰው ይጥሉታል::
አንቺን ግን እንደ እኔ አይገፉሽም እንደውም ቤታቸው ስትገቢ ይንከባከቡሻል
ደግሞም መልካም ነገርን ተስፋ በማድረግ ደስታቸው እጥፍ ነው
ለምንድነው?" ስትል ዝንብ ንብን ጥያቄዋን አቀረበች
በዚህ ጊዜ ንብ እንዲህ አለቻት
"ውሎሽ የት ነው?"
አዋዋላላችን እኛነታችንን ይገልጻል !!

@wegoch
@wegoch
@paappii

#eled aymen
°°° Hiking ወደ ድንባሮ °°°

ቦታ፡- ደብረሲና ድንባሮ(144 ኪ.ሜ)
ቀን፡- ታህሳስ/5/2012(እሑድ)

* እሑድ ታህሳስ እምስት ከመዲናችን ከአዲስ አበባ ተነስተን 140 ኪ.ሜ በመኪና ከተጓዝን በኋላ ከ4-10 ኪ.ሜ በእግር ጉዞ፣ ድንባሮ(የሚሊኒክ መስኮት)፡፡

* በአቀማመጥ 9°45'00.7"N 39°38'47.7"E የሆነው ይህ ቦታ በተራሮች የተከበበ እንዲሁም የተለያዩ ምንጮች የፈለቁበት ሲሆን እጅግ ውብ ተፈጥሮና ለአይን ማራኪ የሆነ ቦታ ነው፡፡

"ጥቅል ፓኬጅ"

★ ደርሶ መልስ የትራንስፖርት አገልግሎት ጨምሮ።
★ ስናክ
★ የታሸገ ውኃ
★ አምስት ፕሮፌሽናል ፎቶ የሚያነሱ ፎቶ ግራፈሮች
★ የምሳ ግብዣ ከአዝናኝ ጫዎታዎች ጋር

@sunsethiking
@sunsethiking
#እምድሽዋ ቅዳሜዋ!

#ስዕል ለምትወዱ ቅዳሚትን ሸራተን ሆቴል ጎራ ብትሉ እጅግ ተደስታቹ ትመለሳላቹ!

"አርት ኦፍ ኢትዮጵያ" የስዕል አውደርዕይ በ ሸራተን ሆቴል ከ ህዳር 26 - 29

#መግቢያ በነፃ!!

"Art Of Ethiopia" art exhibition on December 6 - 9 @ Sheraton hotel
Entrance free!!

@getem
@balmbaras
"አንዳንድ ነገሮችን ማብራራት ይከብዳል"
:
:
ገበሬው በአቅራቢያው ያለ ጃምቦ ቤት በቀን አረቄ በጃንቦ ይጨልጣል። አንድ ሌላ የሚያውቀው ሰው ይመጣና ይጠይቀዋል
" በዚ የስራ እና የምርት ሰዓት ግን እዚ መጠጥ ቤት ምን ታደርጋለህ?" ገበሬው ጭንቅላቱን እያወዛወዘ "አንዳንድ ነገሮችን ማብራራት ይከብዳል።" ይላል። ሰውዬው ወንበር ስቦ እየተቀመጠ ገበሬውን ይጠይቀዋል
"ወዳጄ ምን ሆነህ ነው ንገረኝ፣ሲያወሩት ይቀላል"
"እሺ ካልክ...!" ብሎ ገበሬው ይጀምራል
"እሄውልህ ዛሬ ጠዋት ተነስቼ ግብርና በብድር የሰጠንን ነጯን ላም እያለብኩ ነበር። አንድ እቃ እንደሞላው ግራ እግሯን አንስታ የታለበውን በሙሉ ደፋችው"
"እሺ ግን ይሄ እኮ ታድያ ብዙ አያስከፋም ለዚህ ሁኔታም አይዳርግም "ይላል ሰውየው
"አንዳንድ ነገሮችን ማብራራት ይከብዳል።" ብሎ ገበሬው አሁንም ይተክዛል ...ጭማሪ አረቄም ያዛል።
"እሺ ከዛስ ምን ሆነ" ሰውየው አለሳልሶ ለማረጋጋት ይጠይቃል ገበሬው እየጠጣ ንግግሩን ይቀጥላል
" ከዛ ያው ግራ እግሯን ከ አንዱ ቋሚ ጋር አሰርኩት"
"ከዛስ....?"
"ከዛማ ድጋሚ ተቀምጬ ማለብ ጀመርኩ....በሌላ እቃ ሞልቼ እንደጨረስኩ ቀኝ እግሯን አንስታ ድጋሚ የሞላውትን እቃ ደፋችው"
ሰውዬው ከት ብሎ ስቆ "እንዴ ድጋሚ?" ይለዋል ገበሬው አሁንም
"አንዳንድ ነገሮችን ማብራራት ይከብዳል " ይለዋል።
"ከዛስ ምን አረክ?" ሰውዬው በጉጉት ይጠይቃል።
"ያው ከዛ በጣም ተማርሬ ቀኝ እግሯንም ከሌላ ቋሚ ጋር አስሬ ማለብ ጀመርኩ...የሚያሳዝነው ይቺ የተረገመች ላም ይሄኛውን በጥንቃቄ እንደጨረስኩ በጭራዋ ደፋችው"
"ያሳዝናል በእውነቱ "አለ ሰውዬው ጭንቅላቱን እየነቀነቀ።
"አንዳንድ ነገሮችን ማብራራት ይከብዳል።" ብሎ ጭንቅላቱን በሃዘኔታ ይነቃንቃል አሁንም ገበሬው
"ከዛስ?" ሰውዬው የገበሬው ችግር መጨረሻው አጓጉቶታል "ከዛማ ሌላ ገመድ ፈልጌ ስላጣው ቀበቶዬን ፈትቼ ጭራዋን አስሬ እንደጨረስኩ ሱርዬ ወለቀ፣በዝች ቅጽበት ሚስቴም ወደውስጥ እየገባች ነበር"
"አንዳንድ ነገሮችን ማብራራት ይከብዳል።"

@WEGOCH
@WEGOCH
ምሰለ ምሳሌ
( ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር )
.
.
.
....
........
ፈገግ እንደማለት እያለች በወፍ መሳይ ድምጿ ጆሮው ሥር አንኳኳችና ልቡ ውስጥ ረጋች፡፡ በገዛ ብረሃኗ ወገግ ብላ ታየች እና ዐይኑንና ልቡን ሞላችው፡፡
አንድ ቀን መጥቶ ጠይቋት ተሰናብቷት ወጣና አንድ ሁለት ምዕራፍ ከሄደ በኋላ ናፍቆት አላስችል ብሎት ተመለሰ፡፡
.
.
”ተመለሰክ እንዴ?” ስትለው ድንግር አለውና፤
”ከዘራዬን ረስቼ” አለ፡፡
”እ . . . . እ” ሳቀች፡፡ ከዘራውን በእጁ እያየች፡፡
”ከዘራ ካልሆነ ምንድነው የረሳሁት?” አላት፡፡
ዝም አለች፡፡
”ትንሽ ከሄድኩ በኋላ ዐይኔን ሲበዛ ራብሽው የትዝታሽ ጥም ስቦ መለሰኝ”
”ግባ ቡና ላፍላልህ” አለችው፡፡
፨ ፨ ፨
አንድ ቀን ደግሞ ወደ ጎንደር ሊሄድ አውቶብስ ተሳፍሮ ደብረ ማርቆስ ደርሶ ተመለሰ፡፡
”ጎንደር መሄዱን ተውከው?” አለችው፡፡
”ርቀቱ በዛ፡፡ ካንቺ መራቅ አልሆንልህ አለኝ” አላት፡፡
”አትራቅ” አለችው፡፡ በወፍ ድምጿ፡፡
፨ ፨ ፨
በሌላ ጊዜ ሊጠይቃት መጣ፣ ቡና አፈላችለት፡፡ ቡና ካከተመ ረጅም ጊዜ ቆየ፡፡ ተነስቶ መሄድ አቅቶት፤
”ቤቴ መሄድ ከጎንደር እኩል ራቀብኝ” አላት፡፡
”ላንድ ቀን እንኳ ካንቺ መለየት ይበዛብኛል” አላት፡፡
”አትለዬኝ ” አለችው፡፡ በጽድቅ ድምጿ፡፡
”አኔስ አብረን ብንኖር እንዴት በወደድኩኝ” አላት፡፡
”እኔም” አላችው በፍስሐ ድምጿ፣ በብርሃን ፈገግታ ፡፡
እና ቤቱን ሞላችው፡፡
፨ ፨ ፨
ኖረውም ጠዋት ሥራ ሲሄድ ቁርሱን አብልታ ሸኘችው፡፡ አንድ ሁለት ምዕራፍ ከሄደ በኋላ ናፍቆት አላስችል ብሎት ተመለሰ፡፡
”ተመለስክ እንዴ?” ስትለው፤
”ባርኔጣዬን ረስቼ” አላት፡፡
”እ . . . ም” ሳቀች፡፡ በራሱ ላይ ባርኔጣውን እያየች፡፡
”ባርኔጣዬን ካልሆነ እንግዲህ ምንድነው የረሳሁት?” አላት፡፡
ዝም አለች፡፡
”ትንሽ ከሄድኩ በኋላ ናፈቅሽኝ፡፡ አንድ አፍታ አይቼሽ ልሂድ ብዬ መጣሁ”
”እንኳን መጣህ” አለችው፡፡
”እኔም ናፍቀኸኝ ነበር ናማ ሳመኝ” ።
ሳማት ለመምጣቱ ። ሳማት ለመሄዱ ፡፡
፨ ፨ ፨
ከተጋቡ እነሆ ሰባት ዓመት አለፋቸው፡፡ ግን ዛሬም ቢሆን ጧት ጧት ቁርስ አብልታ ስትሸኘው አንድ ሁለት ምዕራፍ ይሄድና ናፍቆቷ ስቦ ይመልሰዋል።
ይስማታል መልሶ ለመገናነቱ፡፡ ይስማታል መልሶ ለመለያየቱ፡፡
፨ ፨ ፨
እነሆ ከተጋቡ ሰባት ዓመት አለፈ፡፡ ታዲያ መዋደድ መተቃቀፍ ሳይጎድላቸው ወይስ አበዙት ይሆን? አልወለዱም፡፡
አንድ ቀን እንደተለመደው ደህና ዋይ ብሏት ወጥቶ እንደተለመደው ሁለት ምዕራፍ ሄዶ የተለመደውን ስንቅ ከብርሃን ዐይኗ፣ ከወፍ ድምጿ፣ ከጽድቅ እቅፏ፣ ከፈጣሪ ከንፈሯ ትለግሰው ዘንድ ሲመለስ፤ ከተለመደ ሁኔታዋ ያልተለመደ ስንቅ ሰጠችው ፡፡
”የኔንና ያንተን ያህል ውብ ፍቅር እንዴት እስካሁን አልወለድንም?”
ነገራት፡፡
”በህልሜ ይሁን በውስጤ እንጃ፣ ትውለድልህ ወይ? ተባልኩ፡፡ እንቢየው እኔን ብቻ ትውደደኝ አልኩ”
”አሁን ትውለድልኝ ከሌላ ብዬ አልኩና ውለጅልኝ”
”እ. . .ም”
”ይገርምሃል! ሊያስወልደኝ ካልሆነለት ከሌላ ሰው ልውለድለት ይሆን እያልኩ ሳስብ ነበር” ።
እና ከሌላ ወለደችለት ።

@WEGOCH
@WEGOCH
Forwarded from 👋ገብርዬ
#ለሰንበታችን!
💚
ጉዞ ወደ ሀሳብ

እንግዲ ስዕል ከማንበብ የሰው መዳፍ ማንበብ ሳይሻል አይቀርም ትላላቹ ..

#ይሄንን ስእል አንብቡትማ የተረዳችሁችን፣የገባችሁን...እንዲህ አይነት መልእክት ለማስተላለፍ ፈልጎ ነው ብላቹ የምታስቡትን ንገሩን እኛም ለናንተ መልሰን የምናቀርብላቹ ይሆናል !

መልካም ሰንበት !💚

@wegoch
@balmbaras
ወግ ብቻ
#ለሰንበታችን! 💚 ጉዞ ወደ ሀሳብ እንግዲ ስዕል ከማንበብ የሰው መዳፍ ማንበብ ሳይሻል አይቀርም ትላላቹ .. #ይሄንን ስእል አንብቡትማ የተረዳችሁችን፣የገባችሁን...እንዲህ አይነት መልእክት ለማስተላለፍ ፈልጎ ነው ብላቹ የምታስቡትን ንገሩን እኛም ለናንተ መልሰን የምናቀርብላቹ ይሆናል ! መልካም ሰንበት !💚 @wegoch @balmbaras
I Me my self:👇👇👇

Wey gud, yemigomeziz dimts?
Endene ateyay yetesalw wede lay sizelu bimeslim gn wede gon sizelu new weym yehone hayl be washaw ber sisbachew ,mekuamiyachewn alekekutm meskelu gn amiltuachewal tigil nw bahl vs zemenawinet,alem vs menfes(gira aynachew na ejachew kekegnochu ga siteyayu) beberu ga yalw birhan wede kifu neger eyehedu endalhone tesfa yimeslegnal,neger gin yale meakelachew new yemihedut yemidersubet aymeslegnim ...sile kebaterku yikrta......

Meli @ h:👇👇

ይህ ምስል ይመስለኛል technology ሀይማኖታችንን፣ወግ ልማዳችንን እየሣበዉ ወይንም እየወሰደው ነው።እናም የሀይማኖት አባቱ በሀይማኖትና በቴክኖሎጂ መሀል ትግል ዉስጥ ያሉ ይመስለኛል።
አመሠግናለሁ

Wegen Yesak:👇👇

agatemo yakal befet yanete yenebere ahun kejeh ameleto dagem leneyaze setefecheeecher yederesek simeselh gn esu demo sirekeh becha men lebeleh hisab laye kasetawesek ayenke yetege yemelewn mesemere takewalh esun belew

Eyuel Sebsbe:👇👇👇

Legemt, menem wede technology ena zemenawi negeroch benhedem mecheresha gen haimanotachen (eslmna yihun kirstna malet new) mecheresha yemiawatan esu new. Sengodam kedmo miadnen haimanotachn new

maharba:👇👇

ስዕሉን ሳየው መዘናጋትን፣ማርፈድን፣ባለቀ ሰአት መፍጨርጨርን ያሳያል በተለይ ያላትን ትልቅ ሀብትና ህዝብ መጠቀም ያልቻለችው ኦርቶዶክስን! ያስፈራል እግዚአብሔር ያስበን

it's me😁:👇👇👇

Ye sielun tibeb madneq enji manbebu ykebdal sealiw rasu yngeren ene gin tibebun adeneku😱👏

እኔስ የ ማርያም ነኝ:👇👇

sielu and abat be fetena weym mekera wst honew enkuan le emnetachew yalachewn kbr ena fikir esun lalematat miyadergut tgll ymeslegnal

#እናመሰግናለን ለምትልኩል ሌሎቻቹም እንጠብቃለን !🙏

@wegoch
@balmbaras
Enuti:👇👇

Bergit bzu alakim gin betinishum bihon yetayegn 1 abat betebab, asferina amarach belelebet menged siguazu yenegeroch mekbed min yahil haymanotachewin yizew endayketilu endaderegachew ena esachew degmo bemetagel lay endalu teredahu. Batekalay Orthodox min aynet huneta lay endalech yemiyasay new. Sealiw gobez new

kidist:👇👇

ስላም፡ እኔ ከስዐሉ የተረዳሁት ነገር በሃይማኖት ና በ Technologies መካከል እየተፈጠረ ያለውን ተቃርኖ ነው፡፡ በእርግጥ technology ህይወት ቀላል ለማድረግ የሚጠቅም ነገር ነው ሆኖም ግን አንዳንዴ ለፍተን ማግኘት ያለብንን ነገሮች በአቋራጭ ማግኘትን አለአግባብ አጭር መንገድ ፈላጊ ያደርገናል የማስተዋል የማገናዘብ ችልታን ያዳክማል ይህ ስዕል ያሳየኝ ይህን ነው አንድ መንፈሳዊ አባት በፍቅር በተስፋ በማገናዘብ እና በማስተዋል ማግኘት የሚችሉትን ግን ጊዜ እና ትግስት ሚፈልገውን ነገር መጠበቅ አቅቷቸው በአቋራጭ ለመግኘት ሲሞክሩ ነው፡፡ አሁን ላይ ይህ ችግር በሁላችንም ላይ ያለ ነው ትግስት የሌለን ማስተዋል ማገናዘብ የረሳን እራሳችን አሳልፈን ሰው ለፈጠረው ቴክኖሎጂ የሰጠን የፈጣን መንገድ የረሳን ሆነናል፡፡ ቸሩ እግዚያብሄር ማስተዋልን ይሰጠን፡፡ ነገ የሚፈጠረውን አናውቅም እና ትግስተኞች እንሁን አመሰግናለሁ

Meg@tg:👇👇

ለኔ መስቀሉ ዕውነት ፍቅር እምነት ወይም በአጭሩ ሰውነት ይመስለኛል እና እሱ ላይ ለመድረስ የሀይማኖት ሰውም መሆን ቴክኖሎጂ መጠቀምም ቢሆን በቂ እንዳሎነ ከዚህ በላይ እንደሚያስፈልግ ወይም ሀይማኖት እና ቴክኖሎጂ ሰውነትን ቢያሳዮን እንጂ ሰውነት ጋር እንደማያደርሱን ያ ልዩ ልፋት በጉልበት ላይሆን ይችላል ግን ብቻ ጥረት እንደሚጠይቅ እንደዛ ነው እኔ የታየኝ::

አብ:👇👇

እንደኔ አተያይ መስቀሉን በፈጣሪና ለሱ ባለን እምነት ተርጉሜዋለሁ ሰውየዉ ላይ የማየው አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ሲሆን በዙሪያው መፅሐፍና ከበሮ እንዲሁም የተለያዩ ንዋየ ቅድሳት ወድቀዋል ከመቋሚያው በቀር …ይህ የገለፀልኝ ቄሱ ለዕይታ ብቻ ነው ቄስ የሆኑት ጥበብን ጥለዋል ብርሀኑም ጥበብ በዛ እንዳለና ረግጠውት እንደሚንጠራሩ ነው የገባኝ የሚዘሉት ደግሞ ወደ መስቀሉ ነው (ወደ ፈጣሪ) ለዛውም በሳይንስ ታግዘው ይሄ ማለት ጠቅለል ሳደርገው እንደ ባቢሎናውያን ያለ እምነት ፈጣሪን እናየዋለን እንደርስበታለን ብሎ መንጠራራት ነው
እኔ እንደገባኝ

fikr Yo:👇👇

እኔ እንደተረዳሁት
አሁን ላይ ያለነው ትዉልዶች በጣም ግራ እንደተጋባን የኛ ያልሆነን ነገር ለማወቅ በሞከርን ቁጥር የኛ የሆነው ከኛ እየራቀ ይሄ ደግሞ ከማሕበራዊ ሂወታችን አልፎ በሀይማኖታዊ ኑሮአችን ችግር እየፈጠረብን እንዳለ እገምታለሁኝ ይህ ደሞ Technologyን የት ላይ መጠቀም እንዳለብን ያለማወቅ ችግርን ለማስረዳት የተጠቀመበት ይመስለኛል

Elias Eyasu:👇👇

ሥለ ሥዕሉ
.
.
.
ሶስቱ የህይወት መንገዶች
፩..science
፪.ሀይማኖትና
፫. ፍልስፍና
እና የወደፊታችን ሶስቱን ነገሮች አጣምሮ ለመጓዝ ሚደረግ ትግል ነው ሚያሣየሁ .... ሀይማኖት ውስጥ ሳይቴክን ለማካተት ሲሞክሩ .... ሣይቴክን ሢጨብጡ ሃይማኖት ሢሾልካቸው ... ሀይማኖትን ለመያዝ ሌላ ውጥንቅጥ ውስጥ ሢገቡ ሚያሣይ ይመሥለኛል ...... ፍልስፍና ደሞ ሥእሉን በሳለው ሰው ተተግብሯል

Who Knows:👇👇

Misilu lay yetayegn neger endene eyita malet nw. egna abat 1 ayn ena 1 ej yelachewim ena esun lemamualat የሳይንስ wutet yehonewin neger tetekemu kezam yekibrun meskel meyaz akituachew or beza betekoretew ej meyaz ayichilum neberina be ሳይንስ mareg endemichilu amenuna ya sayisaka siker or mareg yetesanachewin hulu ሳይንስ mareg endemayichil nw yemiasayew

MARTIAN:👇👇👇

ከኢዮብ

የቤተክርስቲያን ቄስ ናቸው፡፡ ነገር ግን ግማሹ አካላቸው የሮቦት ነው እናም የሚያሳየን የወደፊቱ የአለማችን ሁኔታ ቤተክርስቲያንን ምን ያህል ውሰጥ ድረስ ገብቶ Affect ሊያረጋት እንደሚችል ሲሆን፡፡ ቄሱ ወደ ገደል እየወደቁ ነው ነገር ግን መስቀሉ ላይ የሆነ አይነት ምስጢር ያለ ይመስላልና ከከበሮው እና ከብራናው ይልቅ ወደሱ አድልተዋል ምናልባትም ለመያዝ ስለሚቀል ይሆን?
ምናልባትም ቄሱ ቤተክርስቲያንን ከጥፋት ሊያድኗት እየተዋጉም ይመስላል፡፡ አመሰግናለሁ
#Just_a_thought


#እውነት እጅግ በጣም እናመሰግናለን በጣም ብዙ ሰው ስእሉን እንደወደደው እና የተሰማውን ፣ ያነበበውን በገባው መጠን ገልፆልናል !! ግን የሁሉንም ሀሳብ ማቅረብ ባለመቻላችን ታላቅ ይቅርታ እንጠይቃለን 🙏 🙏

ለተሳትፏቹ ከልብ አመሰግናለሁ ወርቆቼ !
"ናካይታ"💚

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ለውብ ቀን!
💚

የጥዋት እሳቤ ለውብ ቀን


አመስግኑ
በህይወትህ ውስጥ የሚከሰት መጥፎ ነገር ቢኖር!
ምንም ያህል አስጨናቂ ቢሆን ነገሮች በተስፋ መቁረጥ ሰፈር ውስጥ አትግባ ፡፡
ምንም እንኳን ሁሉም በሮች ዝግ ቢመስሉም ፈጣሪ አዲስ መንገድ ይከፍታል ፡፡
አመስጋኝ ሁኑ! ሁሉም ነገር ሲሻሻል አመስጋኝ መሆን ቀላል ነው። ነገር ግን አንድ ሰው
ለተሰጠው ነገር ብቻ ሳይሆን ለተከለከለውም ሁሉ አመስጋኝ ሁኑ ፡፡
ተመስገን

ዛሬ በውሎዋቹ የምታመሰግኑበት ቀን ይሁን !💚

@wegoch
@wegoch
አልፍሬድ ኖቤል
((ስለ ኖቤል ሲነሳ ሊረሳ የማይገባው ሰው ))

ከመቶ ዓመታት በፊት አንድ ሰው በማለዳው የጠዋት ጋዜጣ ገዝቶ ሲያነብ ባየው ነገር ደነገጠ።አንድ ሰው ማረፉን የሚገልጽ የኋዘን መግለጫ የሞቱ ሰዎች በሚወጡበት አምድ ላይ ሰፍሮ አገኘ።እጅግ የገረመውና ያስደነገጠው ነገር ደግሞ ሞተ ተብሎ የተዘገበው እርሱ እራሱ መሆኑ ነው።
መጀመሪያ ተጠራጠረ።"እኔ እዚህ ነኝ ወይስ እዛ?"ሲል እራሱን ጠየቀ ።በመጨረሻም እንዴት እንዲህ ሊሆን ቻለ?ብሎ አሰበ።ዘግይቶ ሲረጋጋ ግን ጋዜጣው በስህተት ስሙን ከሌላ ሰው ጋር አምታቶ እንደዘገበው ነገረው።ዝቅ ብሎ ስለ እርሱ ሞት የተጻፈውን ነገር ለማወቅ ፈለገ።ለመሆኑ እርሱ ቢሞት ኖሮ ጋዜጦቹ ምን ብለው ነበር የሚዘግቡት? እሱ ለዚች ዓለም ዕሴት ነው ወይስ ዕዳ ?ጥቅም ነው ወይስ ጉዳት?የሚለውን ለማወቅ መልካም አጋጣሚ ተፈጠረለት።ይህንን አጋጣሚ ሲሞት አያገኘውምና።
ይህ ሰው የኖቤል የሰላም ሽልማት መስራችና የዲናሚት ፈጣሪ አልፈርድ ኖቤል ነበረ፣ በ1888 እኤአ የእርሱ ወንድም ሉድቪግ ዐረፈ።የፈረንሳዩ ጋዜጣም አልፌርድ ኖቤል የሞተ ስለመሰለው ጋዜጣው ኖቤልን እያወገዘ ነበር የጻፈው።አነበበው።
የጋዜጣው ርእስ "le marchand de la mort est mort" "የዲናሚቱ ንጉስ ሞተ"ይላል። ቀጥሎም "ብዙ ሰዎችን ከበፊቱ በተሻለ ፍጥነት ለመግደል የሚያስችል መንገድ በመፈልሰፍ ሀብታም ለመሆን የቻለው ዶክተር አልፌርድ ኖቤል ትናንት ሞተ።"ይላል። ከዚያም "አርሱ የሞት ነጋዴ ነበር" ይለዋል።ጥቅምት 21 ቀን 1883 ዓም እኤአ በስውዲን ስቶክሆልም የተወለደው አልፌርድ ኖቤል መሀንዲስ ነበረ።በመንገድ ግንባታ ወቅት ያጋጥም የነበርውን ታላላቅ ቋጥኞችን የማፍረስ ስራ ለማቀላጠፍ እኤአ በ1866 ዓም ዲናሚት የተባለውን ማፍረሻ ቴክኖሎጂ ፈለሰፈ።ከዚያም የራሱን ኩባንያ አቋቁሞ ቴክኖሎጂውን በማሻሻል ከፍተኛ ገቢ አገኘ።በዚህ ሁኔታ እያለ ነበር ያንን በፈረንሳየኛ የተጻፈ ጋዜጣ ገዝቶ ያነበበው።አልፍሬድ ኖቤል ወዲያውኑ አንድ ነገር አሰበ።
"ለመሆኑ ስሞት ሰዎች እንደዚህ ነው ማለት ነው የሚያስታውሱኝ ?"አለ። ኖቬምበር 27 ቀን 1895 እኤአ በራሱ ፍቃድ በፈረመው ፊርማ ከድርጅቱ አስገላጊ ወጭዎች ከተቀነሱ በኋላ ለእርሱ የሚደርሰው ገንዘብ ለሰላም ሕይወታቸውን ላበረከቱ ሰዎች እንዲሰጥ ወሰነ።የኖቤል የሰላም ሽልማት ድርጅትንም መሰረተ።የሰጠውም ገንዘብ በአሁኑ ግዜ ወደ 300 ሚልየን ሊጠጋ የሚችል ነበር።እንዳሰበው አልቀረም ።አልፍሬድ ኖቤል የጋዜጦቹን ርእስ ቀይሯል ።ዛሬ እርሱን ለሰላም ባበረከተው አስተዋጾ ዓለም በየ ዓመቱ ያስበዋል።ኖቤል የሚለው ስምም ከሰላም ጋር የተያያዘ ስም ሆኗል።


ከዳኔል ክብረት
(እኛ የመጨረሻዎቹ እና ሌሎችም ) ከተሰኘው የወግ መድብል ገጽ 40 (የሰው ሐውልቱ) ከሚለው ክፍል ለዛሬ እንዲመጥን ተደርጎ የተቀነጨበ።


30/03/12 ወልዲያ

@wegoch
@Ezihbetsanaddis
2024/09/26 21:35:38
Back to Top
HTML Embed Code: