Telegram Web Link
#ቢያንስ_ከእሁድዎ_ላይ_15ደቂቃ_ብቻ_ይስጡን
#ዘወትር_እሁድ
#ይምጡ_እሁድን_በበጎ_ስራ_ያሳልፋ

ጉራማይሌ የበጎ አድራጎት ድርጅት ከ 8 ወራት በላይ የተለያዩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን ሲያግዝ እንደነበር እዚህ ላይ ፎቶዎችን በመለጠፍ ስናሳውቃችሁ ቆይተናል።

ሆኖም ህጋዊ ሰውነታችን ጥቅምት 13/2012 በመሰጠቱ አሁን ላይ የራሳችን ቋሚ ቦታ ኖሮን በጎ ስራዎቻችንን እየሰራን እንገኛለን!!

#ዘወትር_እሁድ
ቦታ ፡ መገናኛ ቦሌ ክፍለ ከተማ ህንፃ በር ላይ
ሰዓት ፡ ከ3:00-8:00

የስራ ግብዓቶቻችን ከስር ዘርዝረናል ከቻሉ ያምጡሉን ካልቻሉ በአካል በመገኘት በጉልበት ያግዙን ዘንድ በትህትና እንጠይቃለን!!

1 የገላም የፊትም ሳሙና
2 መታሻ ግላብ እና ግላብ
3 ያገለገሉም ይሁን ያላገለገሉ አልባሳት እና ጫማዎች
4 ማበጠሪያ
5 ጥፍር መቁረጫ
6 ሞዴስ
7 የወንዶች ጸጉር ማስተካከያ ማሽን
8 በርሚል እና ውሃ ማመላለሻ ባልዲዎች
9 ቅባት
10 ስፒከር ከእነማይኩ ለፕሮሞሽን ያስፈልገናል
11 ውሃ መቅጃ ጆክ

ለበለጠ መረጃ
+251955431015
+251912319263
+251988342836
+251931823235

ለሐሳብ አስተያዬትዎ
@Hab_G
"ጉራማይሌ የበጎ አድራጎት ድርጅት"
ለውብ ቀን!
💚

የጥዋት እሳቤ ለውብ ቀን

እንደምን አደርሽ ኢትተዮጵያዬ💚💛

በአመስጋኝነት ልብ እንነሳ ፣ የልቦናን ብርሀንን እንፍጠር!

ዛሬ አስደሳች ቀን ነው። ልዩ ቀን አዲስ እድል አዲስ ተስፉ ተሰጥቶናል። ተመስገን

"ናካይታ"💚

@wegoch
@wegoch
ለውብ ቀን!
💚


ሐጥያት መፈጸም ሰዋዊ ባህሪ ሲሆን
ለፈጸሙት ሐጥያት ራስን ተጠያቂ
ላለማድረግ ምክኒያት መደርደር ግን
ሰይጣናዊ ባህሪ ነው

Leo Tolstoy

@wegoch
@wegoch
ለውብ ቀን!
💚

የሚቀናብህን ሰው አትጥላው።
እንዲያውም ቅናቱን አክብርለት።
ምክኒያቱም በቅናቱ የሚያሳየው አንተ
ከሱ የተሻልክ እንደሆነ እውቅና
መስጠቱን ብቻ ነውና።

#ዴል ካርኒጌ

"ናካይታ"💚
@wegoch
@wegoch
ለውብ ቀን!
💚

ሞት ሊነጥለን ሲመጣ የአደጋ ምልክት ስለማይሰጥ እርስ በርስ እንዋደድ። ማንም ሰው
የመጨረሻ ንግግሩ አሊያም ግንኙነቱ ምን እና የት እንደሆነ አያውቅምና አንዳችን ካንዳችን
እንጠያየቅ። «ዋ'ኔ» የሚለው ቃል የሄደን ሰው መልሶ ስለማያውቅ እርስ በርስ እንቻቻል።
በህይወት ውስጥ መልካም ንግግር የሙታንን ግንባር ከመሳም በላይ ዋጋ እንዳለው
እንገንዘብ። በእጁ ቤሳቤስቲን ሳይዝ ነገ ይህችን ምድር ለቆ የሚሄድ መንገደኛ እንዲህ
ካላሰበ ህይወትን በወጉ ሳያጣጥም ሞት ይቀድመዋል።

ውብ ቀን!💚

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
የግሮ ሰሪ ልጅ!!

(ሚካኤል አስጨናቂ)

ሙሉ ስምህን እስከ አያትህ ድረስ ንገረኝ

"አለሙ ግሮሰሪ! :) " 

"ቂቂቂቂ...ኸረ ሰውዬ ድርጅትህን ሳይሆን ስምህን ንገረኝ እኮ ነው ያልሁህ"

ፊት ለፊቷ በተከመሩ የነተቡ የክላሴር ክምሮች ስር ያሰገገችው ሙቀጫ መሳይ ሴትዮ ያን የባቄላ ክክ የመሰለ ቀፋፊ ጥርሷን ገልጣ አስካካችብኝ።

ሰዎች በስሜ ሲስቁ ደስ አይለኝም!

"አዎን የአባቴ ስም ግሮሰሪ ነው ምን ይደንቃል?"

ቀፋፊዋን ሴት ተከትለው ሌሎችም የቀበሌው ሰራተኞች ገለፈጡብኝ።

ዞረብኝ!

ናላዬ ተቃወሰ!

ክፍሉን ለቅቄ ወጣሁ....

አንተ....ግሮሰሪ....ምን መሆንህ ነው ና እንጂ?  የሚለው ደባሪ ድምፅና.. .ብዙ ሰላም አልባ ሳቆች ከጀርባዬ ተከተሉኝ።

።።።።

መታወቂያህን አሳየኝ! ... ብሎ ዥንጉርጉር ቱታ ያደረገው ወታደር በቁጣ አናገረኝ!

"መታወቂያ የለኝም!"...እኔም በቁጣ መለስኩለት።

" ታድያ እንዳንተ አይነቱን ወሮ በላ አይደል እንዴ የምንፈልገው?-...አሁን ከመኪናው ውጣ ብሎ አንባረቀብኝ!

ተሳፋሪው ሁሉ እኔን አግዞ ተንጫጫ.. .ወደ ሱማሌ ክልል ለስራ ጉዳይ እየተጓዝን ነበር...

ልዩ ሀይሉ ሰውዬ ተሳፋሪውን ሁሉ በግልምጫ ማተራቸው።

ረጭ አሉ!

"ኦሪያ ጀርባህ ይጠናል !"

"ይሄ ጀርባ መጠናት ከለውጡ ጋር አብሮ አልቀረም እንዴ?"

ልዩ ሀይሉ ሰውዬ የጠየቅሁትን በመመለስ ፈንታ ጀርባዬን በያዘው የጠብ መንጃ ሰደፍ ደቃኝ።

ቀጥል!

ጉዞ ቀጠልሁ...በስሜ ምክንያት ዛሬም ድረስ መታወቂያ አልባ ሰው መሆኔን ለዚህ ሰው ብነግረው እንዴት ይረዳኛል?

አባቴ...እንደ ስራው ሁሉ ስሙ ግሮ ሰሪ ነው።

እቃ በኮንትሮባንድ እያመላለሰ ዘመናትን በበረሀ እየተንከራተተ የበረሀ ሰለባ ሆኖ የቀረ ምስኪን አባት!

እኔ ደግሞ የአባቴን ስራ አስቀጥዬ በስሙ ለመጠራት የምዳክር ምስኪን ልጁ!

ኮንትሮባንድ መጥፎ አልነበረም...በህጋዊም በህገ ወጥ መንገድ እቃ ማስገባት ምንም ነውር የለውም ብሎ ያስብ ነበር።

"እቃ በህጋዊ መንገድ ሲገባ ቀሪውን ትርፍ የመንግስት ባለ ስልጣናት ቅርጥፍ አድርገው ይበሉታል...እቃ በህገ ወጥ መንገድ ሀገር ቤት ሲገባ እንደ አባቴ ያሉ ምስኪናን ልጆቻቸውን ለማሳደግ እና ቤተሰባቸው ለማገልገል ትርፉን ቅርጥፍ አድርገው ይበሉታል" ይልሀል ።

አለቀ!

"ፍራኒክ ሀምጣ!"

" የምን ፈራንክ? ተጓዥ እኮ ነኝ ..."

"ኦሪያ...ገንዘብ ካላመጣህ.. .ከርቸሌ ህወረውርሀለሁ!"

"የለኝ...." ....አላስጨረሰኝም ድጋሚ ደህና አድርጎ ደቃኝ። ... የጠመንጃ ሰደፍ በዛ ጨካኝ ሰውዬ ድንጋይ ክርን ተደግፎ ሰውነቴ ላይ ሲያርፍ ...ሲኖ ትራክ ተንደርድሮ መጥቶ ስጋዬ ላይ ያረፈ እስኪመስለኝ ድረስ ስቅጥጥ አለኝ። ... አሰብኩ !.... ጨነቀኝ...ከዛ የቀረው ይቅር ብዬ አንድ ውሳኔ ላይ ደረስሁ ...

"እሺ ይሄን ወርቅ ልስጥህ?" ብዬ አንገቴ ላይ ያለውን ሀብል ፈታሁት።

ልዩ ሀይሉ ከመቅፅፈት በደስታ ተሞልቶ ተቀበለኝ ። ...የሰጠሁትን ሀብል አገለባብጦ ካየ በኋላ ይበልጥ ፈገግታው ደመቀ...እሳት እንደነካው ላስቲክ የተጨማደደ ፊቱ ...ያ የመከራ መዓት ለማውረድ የተቋጠረ ገፁ ተፈቶ በደስታ ላቦት ተጥለቀለቀ።

"የቱ ጋር ነው የመታሁህ ይቅርታ !" አለኝ በጠመንጃው ሰደፍ የመታኝ ቦታ ላይ መልሶ እያሻሸኝ።

ይልቅ ሸኘኝ.. .ብዬ ተለማማጥሁት.. ..እውነትም ሳይነጋብኝ መጓዙን ፈልጌዋለሁ ።...ይዞኝ በመጣበት መንገድ ተመልሶ ከኪሱ ሶስት የመቶ ብር ኖቶች አውጥቶ ሰጠኝና ሹፌር ለምኖ ሰደደኝ።

መኪና ውስጥ ገብቼ እየተጓዝሁ...የሰጠሁት የአንገት ሀብል በ 300 ብር የተገዛ አርቴፊሻል ቆርቆሮ መሆኑን አስቤ ፈገግ አልኩኝ።

አለሙ ግሮሰሪ...የአባቱ ልጅ ማለት ይሄ ነው!! :)

@wegoch
@wegoch
@paappii
join the creative and systematic plan to solve a problem or achieve certain objectives, to illustrate your mission, values, and expectations.

@solution_graphics
@solution_graphics
ለጁምኣችን!
💚

ቦ ! ጊዜ ለኩሉ !!

በአንድ ትንሽ ደሴት ላይ፡ ደስታ፣ ሓዘን፣ ሃብት፣ ጊዜ፣ ትዕቢት፣ እውቀትና ፍቅር አንድ ላይ
ይኖሩ ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን ደሴቷ በባህሩ ማዕበል ተጥለቅልቃ መስጠም ስትጀምር
ተፈጥሮ ብርቱ የማስጠንቀቂያ ድምጽ ታስተጋባ ጀመር። ከዚህ አደጋ ህይወታቸውን
ለማትረፍ ሁሉም ስሜቶች ጀልባቸውን እያነሱ ለመሸሽ መዘጋጅት ይጀምራሉ፡፡ ፍቅር ግን
ጀልባ ስላልነበራት ብቻዋን ደሴቱ ላይ ለመቅረት ተገደደች፡፡ ሆኖም ግን ከአደጋው ራሷን
ለመከላከል እስከ መጨረሻው ደቂቃ ድረስ የተቻላትን ሁሉ ጥረት አደረገች፡፡ ይሁን እንጂ
ደሴቷ በውሃ እየተሞላች መዋጥ ስትጀምር፡ ያላት ብቸኛ ኣማራጭ ከቦታው መራቅ ብቻ
መሆኑን ስለተረዳች፡ ጀልባ ያላቸው ይዘዋት እንዲወጡ እርዳታ መጠይቅ ትጀምራለች፡፡
.
ሃብት በርቀት ሲያልፍ ተመለከተችውና በሩጫ ሄዳ፡-
.
"ሃብት ፍቃድህ ከሆነ ከአንተ ጋር በጀልባህ አብሬህ ብሄድ ምን ይመስልሃል ?" ስትል
ጠየቀችው።
.
ሃብት፡-
.
" እዚህ ጀልባ ላይ በርካታ ወርቅና አልማዝ ስለጫንኩ ይቅርታ ለአንቺ የሚሆን ቦታ
የለኝም!" ይላታል፡፡
.
ፍቅር ምን ይሻለኛል እያለች ስትጨናነቅ ትዕቢት ምን የመስለች ዘመናዊ ጀልባ ይዞ ሲመጣ
አየችው፡፡
.
"ትዕቢት እባክህ በጀልባህ የሆነ ቦታ ወሽቀህም ቢሆን ከዚህ ደሴት አውጣኝ ?"
ትለዋለች፡፡
.
ትዕቢት፡-
.
"ሰውነትሽ ሁሉ በጭቃ ተጨማልቆ እንዴት ነው የምወስድሽ? ትንሽ አታፍሪም? አሁን ዞር
በይ ጀልባዬን እንዳታቆሽሺ !" ይላታል በንቀት፡፡
.
ፍቅር አሁንም ተስፋ ሳትቆርጥ ከደሴቷ የሚያወጣትን ጀልባ ስትፈልግ ሃዘን ቀስ እያለ
ሲያልፍ ታገኘዋለች …
"ሐዘን እባክህ ካንተ ጋር ውሰደኝ ?" ትለዋለች፡፡
ሐዘን፡-
"ፍቅር ይቅርታ አድርጊልኝ ! ጥሩ ስሜት ስለማይሰማኝ በዚ ሰዓት ብቻዬን ነው መሆን
የምፈልገው፡ ልረዳሽ ስላልቻልኩ አዝናለው" ብሏት ይሄዳል።
.
አሁንም ፍቅር በጭንቀትና ፍርሃት ተውጣ ሳለ፡ ደስታ ሲመጣ ተመልከተችውና እጆን
እያውለበለበች ጮክ ብላ እንዲህ ስትል ጠየቀችው።
.
"ደስታ እባክህ መሄጃ ቸግሮኝ ነው፡ በጀልባህ አሳፍረህ ከዚህ አደጋ ሰውረኝ ?" ስትለው...
ደስታ ሙዚቃ ጮክ አድርጎ ከፍቶ እየጨፈረ ሰለነበር፡ የፍቅርን የእርዳታ ጥያቄ ሊሰማት
ስላልቻለ መልስም ሳይሰጣት ዝም ብሎ ጥሏት እልም ይላል፡፡
እናም ፍቅር ሁሉም ፊቱን ሲያዞርባት በጣም ታዝናለች። ምን ማድረግ እንዳለባት ተጨንቃ
ሳለ ድንገት ከኋላዋ…
.
"ፍቅር አይዞሽ ! እኔ እወስድሻለው" የሚል ድምጽ ሰምታ ወደ ኋላ ስትዞር፡ የምትምር ጀልባ
ቆማለች፡፡ ፍቅር በደስታ እየፈነደቀች ከልቧ በማመስገን ጀልባው ላይ ተሳፈራለች።
በተደረገላትም መልካም ትብብር ልቧ እጅግ በጣም ተነክቷል፡፡ በሃሴት ተሞላታ ዋስትና
ያለው ቦታ በሰላም ስትደርስ፡ በጀልባው ጭኖ ያመጣትን ከልብ አመስግና ትወረዳለች፡፡
ከትንሽ ደቂቃ በኋላ በተደረግላት ደግነት ተመስጣ ሳለ በጀልባው ያመጣትን ስሙን
አለመጠየቋ ትዝ ሲላት...
" ውይ! በሞትኩት በመልካም ምግባሩ ህይወቴን የታደጋትን እንዴት ስሙን ሳልጠይቅ
እመጣለው !" በማለት እራሷን እየወቀሰች ባለውለታዋን ስሙን ለመጠየቅ ማፈላለግ
ትጀመራለች፡፡ እናም ድንገት እውቀትን ታገኘውና…
" ወዳጄ እውቀት ! ያ ቅድም በማዕበል ከሚናወጠው ደሴት በጀልባ ያመጣኝን ስሙን
ታውቀዋለህ ? እባክህ እውቀት የምታውቀው ከሆነ ንገረኝ፡ ማነው ስሙ ?" ስትል
ትጠይቀዋለች፡፡
እውቀትም በትህትና ረጋ ብሎ ፦
.
"ፍቅር... ቅድም ከደሴቷ ያመጣሽ ባለ ጀልባ ስሙ 'ጊዜ' ነው ፡ እሱ ነው ያመጣሽ"
ይላታል፡፡
.
ፍቅር፡-
.
"ለምንድነው ግን ሁሉም መተባበር እምቢ ብለውኝ ሳለ፡ 'ጊዜ' ራሱ ጠርቶ ያመጣኝ ?"
ስትል ሚስጥሩን ትጠይቀዋለች፡፡
.
እውቀትም ፈገግ ብሎ…
"ምን መሰለሽ ምክንያቱ፡ ፍቅር ለዚች ምድር ምን ያህል አስፈላጊ መሆንሽን፡ ጊዜ ብቻ ነው
ጠንቅቆ የሚያውቀው። ፍቅር አንቺ ካለሽ በጎነት፥ ርሕራሔና ሰላም እሴታቸው ከፍ ይላል፡፡
መተዛዘን፥ መግባባት፣ መረዳዳትና መቻቻል ዋጋቸው ይጨምራል። ያኔ ህይወት
የማትሰለች፡ ጣፋጭና አጓጊ ትሆናለች። ይህንን እውነታ ታዲያ፡ ጊዜ ብቻ ነው የሚያየው!"
ሲል እውቀት... በማስተዋል ልቦና፡ ያልተጋረደውን ሚስጥር ለፍቅር አስረዳት፡፡
.
እኛስ በየትኛው የሰሜት ጀልባ ውስጥ ነው ራሳችንን ያስቀመጥነው? ለሚያልፈው ማዕበል
የጊዜያዊ ስሜቶቻችን ባርያዎች ነን ወይ? በመሰረቱ አንዳችን ለአንዳችን ካልሆንን
የመኖራችን ትርጉሙ ምንድነው ፋይዳው? ካለ ሰዎች ትብብርና እርዳታ አንድ 'ስንዝር'
አንኳን መንቀሳቀስ ሰለማንችል፡ በሰብዓዊነት ጀልባ፡ የሰው ዘርን ከችግርና ፈተና ወጀብ
ለመታደግ፡ የጊዜን አርቆ አስተዋይነት፣ የእውቀትን ጥልቅ እይታ፣ የፍቅርን ሩህሩህ ልብ
ፈጣሪ አብዝቶ ይሰጥን !!


መነሻ ሃሳብ ፡- … Moral Stories
በረከት አብርሃም (ቲሞ)


ሸጋ ጁምኣ!💚

@wegoch
@wegoch
ለቅዳሚታችን!


ጸጉሬን እየተቆረጥኩ ነው - “ታምሩ የወንዶች ባርበሪ”። ፀጉር አስተካካዩ
ወሬ ይዟል፤ ሙግት ብለው ይሻላል፤ ቤቱን ካከራዩት ሠው ጋር። እኔ ግን
ትዕግስቴ እየተሟጠጠ ነው።
“አረ እባክህ ቶሎ በልልኝ፤ እዚህ ዋልኩ እኮ” አልኩ በብስጭት።
መልስ አልሠጠኝም፤ ሙግቱን ቀጥሏል።
“ስማ ታምሩ፤ ነግሬሃለሁ። 2000 ብር ከበደኝ ካልክ፣ እቃህን ጠቅልለህ
ውጣ!” አሉ አከራዩ።
ታምሩ፣ በቶንዶስ በቀኝ በኩል ፀጉሬን ለማስተካከል ዞሯል፤ የግራውን
ሳይጨርስ። ቀልቡ ስራው ላይ አይደለም፤ እያየም አይመስለኝም
የሚቆርጠኝ። ይባስ ብሎ ቶንዶሱን አስቀምጦ አከራዩ ላይ አፈጠጠ።
“ለዚህ ኩሽና 2000 አልከፍልም። እወጣልዎታለሁ። ይብላኝ ለርሶ እንጂ፣
ደንበኞቼ የሄድኩበት ይከተሉኛል”
“ጥሩ፤ ዛሬውኑ ውጣልኝ”
“ሠውዬ፣ እኔን መጀመሪያ አስተካክለህ ጨርስና ትወጣለህ” አልኩ -
ቢቸግረኝ።
ሞባይሌ ይጮሀል፤ ከቅድም ጀምሮ። አላነሳሁትም፤ ባለቤቴ ነች።
ዛሬ ጠዋት ተጣልተን ነው የተለያየነው። መጣላት ሳይሆን ትንሽ ግጭት
ብጤ። ዛሬ ቢሾፍቱ ለስራ ሄዳለች። አዳሯን ነው የሄደችው። መሄድዋ አደለም
ያናደደኝ። በጠዋት፣ ጎረቤታችን ወ/ሮ አማከለች ጋ ሄዳ፣ እሷ ስለማትኖር
ልጃችን ከትምህርት ቤት ስትለቀቅ እንድያመጥዋት አደራ ስትላቸው
አበገነችኝ። እኔ አባትዋ እያለሁ፤ ባዳ መለመን? እኔ አልችልም አላልኳትም።
በዚህ ተናድጄ ነው በጠዋት አምቧጓሮ የፈጠርኩት። “አይ ያንተ ነገር። አንዴ
አልተመቸኝም፤ አንዴ ረሳሁት ብለህ እንዳትቀርባት ብዬ ነው” ስትለኝ የበለጠ
ቱግ አልኩ። ረሳሁት ብለህ?... እንዴት ነው ልጄን የምረሳው! ደግሞስ፣ ስራ
የት አለና ነው፣ ልጄን ከት/ቤት ለማምጣት ጊዜ ያጣሁትና ያልተመቸኝ። ደላላ
ሁሉ በየካፌው ድዳችንን አስጥተን አደል እንዴ የምንውለው። ይሄን ደግሞ
ጠንቅቃ ታውቃለች። በተለይ፤ በሚጡ ጉዳይ ለአደራ አትበቃም ብላ እንደ
ዘበት መናገር ልማድዋ ነው። ይሄ በጣም ያናድደኛል። ባለፉት ስድስት ወራት
ደግሞ፣ በጣም ብሶባታል። ምንም እድል አትሰጠኝም።
መቆጣቴን አይታ መለስ አለች። “እሺ፤ እኔማ እንደ ሌሌሎቹ ልጆች፣ አባትዋ
ቢያመጣት ደስ ይለኛል” ስትል፣ ተቃጠልኩ። እኔ ከሌሎች አባቶች አንሳለሁ?
“ብቻ፣ አደራህን ዘጠኝ ሰዓት ከት/ቤት ስለምትለቀቅ፤ እሩብ ጉዳይ ድረስላት።
ብቻዋን እንዳትቀር አደራ!!!”
ያደራው ብዛት!
ልጄን ከት/ቤት አምጥቺያት አላውቅም። እንዴት አድርጌ? እድሉ መች
ተሰጥቶኝ። ሚጡ፣ ዛሬ ከት/ቤት የማመጣት እኔ እንደሆንኩ ስትሰማ፣ በደስታ
ፈነደቀች - “ባቢ ጓደኞቼ አባት የለሽም እያሉ ይተርቡኛል። ዛሬ አሳያቸዋለሁ፤
ታድዬ”። ወይኔ ልጄ! ሳልሞት በቁሜ።
ንዴቴን ለመወጣት፣ ወ/ሮ አማከለች ቤት ሄጄ፤ “ተውት ግድየለም። ልጄን እኔ
አመጣታለሁ” አልኳቸው ኮስተር ብየየ።
“እርግጠኛ ነህ? እኔ እኮ ምንም ስራ የለኝም። ተጎልቼ ነው የምውለው”
ብለው መለሱልኝ።
እርግጠኛ ነህ ብለው ይጠይቁኛል! ምን አይነት ጥያቄ ነው! ለነገሩ
አልፈርድባቸውም። ዞሮ ዞሮ የባለቤቴ ግርፍ ናቸው። ከባለቤቴ የሰሙትን ነው
መልሰው የሚነግሩኝ። “እኔ አመጣታለሁ አልኩዎት እኮ” ብዬ ጥያቸው ወደ
ጉዳዬ ሄድኩ።
ከጠዋት ጀምሮ ሌላ ሃሳብ አልነበረኝም። ልጄን ከት/ቤት የማምጣት ጉዳይ
ብቻ! አለም ብትገለበጥ ዛሬ አላረፈፍድባትም። ሚስቴንም ዛሬ አሳያታለሁ! እኔ
ነኝ ለእምነት የማልበቃው? “ተሳስቻለሁ፤ ይቅር በለኝ ነው የማስብላት”!
ካፌ ቁጭ ብዬ አስሬ ሰዓቴን አያለሁ። ሌላ ነገር ማሰብ አልቻልኩም። ጊዜው
ደግሞ ገና ነው። ካፌ ቁጭ ብዬ በጭንቀት ከምብከነከን፣ ልንቀሳቀስ... ወደ
ት/ቤቱ ጠጋ ልበል... ብዬ መንገድ ጀመርኩ። ሚኒ ባሱ ሀያሁለት ጣለኝ። ት/
ቤቱ ቅርብ ነው፤ የአስር ደቂቃ መንገድ ቢሆን ነው። ገና አንድ ሰዓት ተኩል
ይቀራል። አይ ጭንቀት! ዝም ብዬ ነው ምሳዬን ሳልበላ በርግጌ መንገድ
የጀመርኩት። ተረጋግቼ ጊዜውን መጠቀም እችላለሁ። ፀጉሬን ለመስተካከል
“ታምሩ የወንዶች ባርበሪ” ዘው አልኩ። ፀጉር ለመቆረጥ ቢበዛ 30 ደቂቃ
ቢፈጅብኝ ነው።
“እስኪ እግዜር ያሳያችሁ። ሀያሁለት አካባቢ፣ በ1000 ብር የሚከራይ ቤት
ይገኛል እስኪ እናንተ መስክሩ”፣ አከራዩ ወደ እኛ እያዩ ተናገሩ።
“ደግሞ ይሄን ጉድጓድ፤ ቤት ብለው ነው የሚያስፈራሩኝ፤ ስሙልኝ ብቻ!”፣
ታምሩ በተራው የደንበኞችን ፍርድ ይማፀናል።
“ጣሪያው እንደጉድ ያፈሳል። በክረምትማ ቤቱ ባህር ነው። ስራ መስራት
አይቻልም። በዚያ ላይ ሽንት ቤቱ፣ የሰፈር ቆሻሻ መጣያ ነው የሚመስለው።
መንገደኛው፤ ሠካራሙ ሁሉ ነው የሚገባበት። ለዚህ ነው 2000 ብር
የምከፍለው? ያሾፋሉ?”
“አማርኛ አይደለም እንዴ የምናገረው? ካልቻልክ ውጣ፤ ለሌላ
አከራየሁዋለሁ!”
በቃ፤ ከገባሁ ጀምሮ እንደዚሁ ያለ እረፍት ይጨቃጨቃሉ። በቶንዶስ ነካ ነካ
ያደርገኝና፣ ወዲያው ተመልሶ ንትርኩን ይቀጥላል። ከእኔ በኋላ የመጣው
ሠውዬ ተስተካክሎ ሄደ። እሱን ያስተካክለው ተቀጣሪ ነው፤ የእኔ አሰተካካይ
ዋናው ባለቤት ነው። አይ እድሌ!
ስልኬ እንደገና ጮኸ። ሚስቴ ናት።
“እኔ ወጥቼ ማን ሊገባልዎት፤ ባዶውን ታቅፈውት ነው የሚቀሩት፤ እኔ
እንደሆንኩ…”
ስልኬ ይጮሀል!
“ወይ አንሳው፤ ወይ አጥፋው። አላስወራ አልከን እኮ!” ታምሩ በቁጣ
ጮኸበኝ።
ለሱ ብዬ ሳይሆን፡ ሚስቴን ለማረጋጋት ስልኬን አነሳሁ።
“ለምንድን ነው ስልኬን የማታነሳው፤ ተጭንቄ ልሞት ነው” አለች ሚስቴ።
“ሳይለንት ላይ አርጌው ነው። ሁሉ ነገር ሰላም ነው” ብዬ ዋሸሁ።
“ደረስክላት! ዘጠኝ ሰዓት ሆኗል!”
ለአፍታ ቃላት ጠፉኝ። “እ… አዎ…ደርሼአለሁ። ከሩቅ እያየሁዋት ነው” ሌላ
ውሸት።
“ሚጡን አየሃት? እርግጠኛ ነህ?”
“ልጄ ትጥፋኝ እንዴ? ጀመርሺኝ ደግሞ! በይ ቻው ቻው” ስልኩን ዘጋሁባት -
“አቅርባት፣ ላናግራት” ብላ ጉዴ እንዳይፈላ።
ሰዓቱ ግን አስደንግጦኛል። 9 ሰዓት! እንዴት ሄዷል እባካችሁ።
ብድግ አልኩ! ፊቴን በመስታወት ስመለከት፤ ሌላ ድንጋጤ ተጨመረብኝ።
ፀጉሬ ግጥብጥብ ብሏል። ከግራና ከቀኝ መድምዶኛል። ከፊት ያለውን
አልነካውም። ከበስተኋላ ደግሞ፣ ጀምሮ ትቶታል። የባለገር ልጅ ባለ ቁንጮ
አድርጎኛል። ተራ የሚጠብቁ ደንበኞች በሳቅ ሲጉተመተሙ፣ ደምስሬ በንዴት
ተገታተረ።
“ስማ እንጂ! ትቀልዳለህ? ምንድነው እንደዚህ ገጥበህ የተውከኝ” አለኩ
በቁጣ።
አጅሬ ሊደነግጥ ነው! “ታገሳ! መቼ ጨረስኩ” መልሶ እኔን ተቆጣኝ።
“ከአንድ ሰዓት ተኩል እዚህ ጎልተኸኝ ነው፤ ታገስ የምትለኝ? ገንዘቤን ከፍዬ
እኮ ነው የምቆረጠው”
“እዚህ እኮ ቁምነገር ነው የያዝነው! መታገስ ካልቻልክ መሄድ ትችላለህ”
ብሎኝ ቁጭ።
ሰዓት አልፎብኛል፤ መሄድ አለብኝ። ግን እንዴት ነው እንደዚህ ሆኜ
የምሄደው።
ተቀጣሪውን ፀጉር አስተካካይ እንኳን ጨርስልኝ እንዳልለው፣ አዲስ ደንበኛ
ያዟል። አሳዘንኩት መሰል፤ “ሃያ ደቂቃ ይስጡኝ፣ ቀጥዬ እርስዎን
አሰተካክልዎታለሁ” አለኝ።
ሃያ ደቂቃ፣... አንድ ደቂቃም የለኝም። ልጄ ት/ቤት ደጃፍ ብቻዋን ቀርታ
ቁልጭ ቁልጭ ስትል ታየኝ። የሚስቴም ቁጣ ታየኝ፡ ደግሞም ልክ ነች።
ለማስረዳትም ይከብዳል። ለመውጣት ኮቴን ከተሰቀለበት አወረድኩ።
“ሂሳብ” አለ ይሄ የማያፍር ሰውዬ። ብልጭ አለብኝ። ቶንዶሱን ቀምቼ አናቱን
ብለው ደስ ባለኝ። ሳፈጥበት፤ “በቃ ግዴለም፤ ዛሬ ምሬሀለው”
አለ። የማነው ደረቅ!
አከራዩ ይስቃሉ፤ “አይ ታምሩ! ደንበኞቼ የሄድኩበት ይከተሉኛል ስትል
አልነበረም? እስኪ ይሄ ሰውዬ ሲከተልህ እናያለን” ሲሉ አንጀቴን አራሱኝ።
ከኪሴ የቢዝነስ ካርዴን አውጥቼ ለአካራዩ ሰጠሁዋቸው። “ጋ
ሼ! ካርዴን ያዙ።
ደላላ ነኝ፤ ቤትዎን ዘንጠው 3000 ብር እኔ አከራይልዎታለሁ” አልኳቸው።
“እግዚሀብሄር ይባርክህ ልጄ! ይሄ ሞላጫ 2000 ብር አልከፍለም፤ ሲል
3000 ብር የሚከፍል ተገኘልኝ፤ ታምሩ፤ ሰማህ - 3000 ብር!”
“በነፃ ባስተካከልኩህ ጠላት ትሆነኛለህ? ሁለተኛ እዚህ ቤት ድርሽ እንዳትል”
አለኝ ታምሩ።
መልስ ለመስጠት ጊዜ አልነበረኝም። ወጥቼ እየከነፍኩ ወደ ልጄ ት/ቤት
ዳገቱን በሩጫ ተያያዝኩት።
በራሴ በጣም ነው የተናደድኩት። ሚስቴ የፈራችው ደረሰ። ያንድ ቀን ፈተና
ማለፍ አቅቶኝ፤ እንደዚህ ልውደቅ? ት/ቤቱ ደጃፍ ስደርስ፤ ተማሪዎች
የሚሄዱባቸው ሚኒባስ ታክሲዎች፤ የቤት መኪናዎች ቆመዋል።
ግራ ተጋባሁ! ያረፈድኩ መስሎኝ ነበር። ሳይ ግን፤ ተማሪዎቹ ገና አልወጡም።
ቁና ቁና እየተነፈስኩ አንዱን ወላጅ ስጠይቅ፤ “ዘጠኝ ተኩል ነው የሚለቀቁት፤
ገና 15 ደቂቃ ይቀራቸዋል” አለኝ፤ ፀጉሬን በመገረም እየተመለከተ። እንዴ፤
ሚስቴ 9 ሰዓት ነው የሚለቀቁት አደል እንዴ ያለችኝ? ፈንጠር ብዬ ልጄን
መጠበቅ ጀመርኩ።
ጎረቤታችን ወ/ሮ አማከለች፤ ቱስ ቱስ እያሉ ከች አይሉ መሰላችሁ? “ወ/ሮ
አማከለች እዚህ ምን ይሰራሉ፤ እኔ አመጣታለሁ ብየዎት አልነበረም እንዴ?”
ብዬ አፈጠጥኳቸው። “ኧረ እኔ፣ ሾላ ገበያ እየሄድኩ ነው። ደግሞ ገበያም
አትሄጂም ብለህ ልትከለክለኝ ነው? ሆ! ሆ!” ብለው ተሞጣሙጠውብኝ
መንገዳቸውን ቀጠሉ። ልቤ ግን አላመናቸውም።
ዘጠኝ ተኩል ተደወለ። ልጆቹ አንዴ ግር ብለው ወጡ። እኔም እንደሌሎች
ወላጆች በጉጉት ሚጡን ፍለጋ ዓይኔ ወዲያና ወዲህ ይቃኝ ጀመር።
ከሩቅ አየሁዋት። ጓደኞቿ አጅበዋታል፤ ለምን እንደሆነ ገባኝ፤ አባቴን ላሳያችሁ
ነው ጨዋታው።
እጄን ሳወዛውዝ አይታኝ፤ “ባቢ! ባቢ! ያውና አባቴ” እያለች እየሮጠች
መጣች። ጓደኞቿ ይከተልዋታል። እኔ ጋር ስትደርስ፣ ፈገግቷዋ ተቀይሮ
ሽምቅቅ አለች። ጓደኞቿ፣ መሳቅ ጀመሩ። ልጄ ደግሞ ማልቀስ። “ባቢ ምን
ሆንክ! ጓደኞቼን አንተን ላስተዋውቃቸው ብዬ... እንደዚህ ታዋርደኛለህ?
ፀጉርህ ምንድን ነው?”
ምን መልስ አለኝ?
እኔማ ዛሬ ብዙ ነገር አስቤ ነበር። ከልጄ ጋር አሪፍ ጊዜ ላሳልፍ፤ ኬክ
ጋብዣት፣ ግዮን የልጆች መጫወቻ ቦታ ልወስዳት ነበር። ነገር ሁሉ ተበላሸ።
ሚኒ ባስ ውስጥ ግማሹ ሲስቅብኝ፤ ግማሹ ሲጠቋቆምብኝ እንደተሳቀቅኩ
ሰፈር ደረስን። ቤት ስንገባ ሚጡ አኩርፋ ቁጭ አለች። እኔም ይውጣላት ብዬ
ዝም አልኩ።
ቀስ እያለች እየሠረቀች ታየኝ ጀመር። በመጨረሻ፣ መሳቅ ጀመረች። እኔንም
አሳቀችኝ። አይ የልጅ ነገር! የገጠመኝን አወራኋት። ለሷ ከማረፍድባት ያገር
መሳቂያ መሆንን እመርጣለሁ። አቅፋ ሳመችኝ። “ከእንግዲህ ወዲያ ከት/ቤት
አንተ አምጣኝ” አለችኝ። ከእንግዲህማ አባትነቴን ማንም አይነጥቀኝም።
እንደማመጣት ቃል ገባሁላት።
ልጄ እንደተኛችልኝ ሚስቴ ጋር ደወልኩ፤ እንዴት እንዳናደደችኝ! ዘጠኝ ተኩል
የምትለቀቀውን ልጄን ዘጠኝ ሰዐት ብላ ትዋሸኛለች? ያረፍዳል ብላ እኮ ነው፤
ፀጉሬን በአግባቡ የምስተካከለውን፤ ወይኔ ያገር መሳቂያም ሆንኩ እኮ፤
ቆንጮ? በአሁን እድሜዬ? ሆ! ሆ!፤ ሚስቴ ስልኳን አታነሳውም፤ ይበልጥ
ተናደድኩ፤ ደግሞ ረስቼው ይባስ ብላ ወ/ሮ አማከልቸን መላክዋ!
እሳቸውንማ ቆይ ብቻ ልክ ልካቸውን የምነግራቸው፤ ብድግ ብዬ፤ ቤታቸው
ሄድኩ ፋታም አልሰጠሁዋቸውም፤ እንደገባሁ ተንጣጣሁባቸው፤
“የሰው ትዳር ሊያፈርሱ ነው? በማያገባዎት ገብተው የሚበጠብጡት” ምን
ያላልኩዋቸው ነገር አለ፤ ወረድኩባቸው፡፡
ዝም ብለው አዳመጡኝ።
“ቁጭ በል ልጄ! የምነግርህ ነገር አለ” ፊታቸውን ቁምጭጭ አደረጉ
“ባለቤትህ ብሸፍቱ የሄደችው ለስራ አደለም፤ ዝቋላ ጠበል ልትጠመቅ ነው”
“የምን ጠበል? ታማለች እንዴ?”
“አዎ ስድስት ወር ሆናት ከታመመች፤ ሀኪም ከእንግዲህ ሶስት ወር ብቻ ነው
የቀረሽ ብሏታል”
አለም ተገለባበጠችብኝ
“የልጅዋ ነገር ጨንቅዋታል፤ አደራው ላንተ ብቻ አደለም፤ ለእኔም ነው ልጄ”
በድንጋጤ ደነዘዝኩ፤
ቤቴ ገብቼ፤ ልጄን አቅፌ፤ ጣራ ጣራውን እያየሁ ተኛሁ።

#አደራው
Written by እስክንድር ኃይሉ

#ምንጭ:- አዲስ አድማስ ጋዜጣ


ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ!

@wegoch
@wegoch
ለውብ ቀን!
💚


“የሆነውን መቀበል የማይሻ ብቸኛ ፍጥረት የሰው ልጅ ነው! ”
* * *
“ከሁዋላዬ ሆነህ አትጓዝ ልመራህ አልችልም። ከፊቴም አትሁን አልከተልህም። ይልቁን
ከጎኔ ሆነህ ተጓዝና ጓደኛ ሁነኝ።”

- አልበርት ካሙ
(አልጄሪያዊ/ፈረንሳዊ ደራሲና ፈላስፋ)

@wegoch
@wegoch
2024/09/26 23:22:28
Back to Top
HTML Embed Code: