Telegram Web Link
Forwarded from ቅንድል ኢትዮጵያ (Ermiyas Dejene)
#ቀንዲል ዲጂታል መፅሔት 👇👇👇

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው እውቀትን እና ልምድን ባካበቱ አምደኞች የተፃፈ አዝናኝ እና አስተማሪ ዲጂታል መፅሔት፡፡
Forwarded from ቅንድል ኢትዮጵያ (Ermiyas Dejene)
ቀንዲል Digital Magazine 01.pdf
7.5 MB
#ቀንዲል ዲጂታል መፅሔት

ቅፅ 1- ቁጥር1

💰ፓኬጅ ከገዙ 0.90 ሳንቲም ብቻ💰

@kendilM
@kendilM
ይህ ህዝብ፦

አድዋ ላይ ነጭ ተራ ፍጡር መሆኑን ያስመሰከረ፡፡ “ጥቁር ሠው” የሠው ዘር መገኛ ብቻ ሳይሆን ከሌላው ዕኩል መሆኑን ያረጋገጠ ኩሩ ሕዝብ ነበር፡፡

ይሕ ሕዝብ፡-
ክፉ ቀንን ያለፈ፤ ከ66 የተረፈ፤ 77 ትንም 97ትንም ያያ… ተአምረኛ ሕዝብ ነው፡፡

ይሕ ሕዝብ፡-
ለኮሪያ የዘመተ፤ ማንዴላን ያሠለጠነ፤ ለአፍሪካ የነፃነትና የባንዲራ እርሾ ያበደረ… ገራሚ ሕዝብ ነበር፡፡

ይሕ ሕዝብ፡-
እየሱስ ክርስቶስ ሲጠመቅ ቆሞ የመሠከረ፤ ሞስሊሞች ሲሳደዱ ያስጠጋ፤ በመጽሐፍ ቅዱስ እስከ ቱንት የተጠቀሰ፤ በቅዱስ ቁራን የተወደሰ፤ በእየሩሳሌም ርስት ያለው፤ለነብዩ መሐመድ አዛን ያለ፤ የጠገበ መንፈሳዊ ታሪክ ያለው ሕዝብ ነው፡፡

©ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን
@wegoch
@wegoch
@gebriel_19
‹‹ሉሲ የሰላምና የፍቅር ጉዞ›› - ቋሚ የጭካኔና ግፍ አዋጅ፣ በድን አጽም የሰላምና የፍቅር
አማላጅ!
(ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ)
"ግልብ አእምሮ ደርዝ ያለው፣ እየተቀናጀ የሚጎለብት ተግባር ሊከውን አይችልም፤ ይህ
ደግሞ የአብዛኞቹ የለውጡ መሪዎች መለያ እየሆነ ነው፡፡
.
የለውጡ መሪዎች በህይወት ቆመው የዜጎችን ቤት እያፈረሱ፣ ህጻናትንና አዛውንቶችን ሜዳ
በትነው ሰላምና ፍቅር እየነሱ፣ የበሰበሰ አጥንት ከሙዚየም አውጥተው ለሰላምና አፍቅር
አማላጅነት ይልካሉ፡፡ በዚህ ዘመን ከዚህ በላይ ድንቁርና የወለደው ግልብነትና የህዝብ
ንቀት የወለደው ምጸት አይገኝም፡፡
.
ከወራት በፊት የአዲስ አበባን የመንገድ ዳር ለንግድ ፈቅዶ፣ የእግረኛ መንገድ ሳይቀር
በላስቲክ ዳስ ያዥጎረጎረ፣ የለውጥ መሪ ዛሬ የከተማ ውበት ጠፋ ብሎ የህዝብ ጎጆ
ይደረምሳል፡፡ በፍርድ ቤት የእስር ማዘዣ የተቆረጠለትን ተጠርጣሪ ወደ ህግ አቅርቦ ህግን
ያላስከበረ የለውጥ መሪ፣ ከህግ በላይ ማንም እንደሌለ ለማሳየት የዜጎችን መኖሪያ
በቡልዶዘር ይንዳል፡፡
..
አዲስ አበባ ላይ ዜጎችን ፍቅርና ሰላም ነስተው ደም እያስለቀሱ፣ አጽም ለሰላምና ፍቅር
ምልጃ አፋርና ሱማሌ ይልካሉ፡፡ ለነገሩ ካለማወቅ የተደረገ ቢሆንም፣ ቋሚ የጭካኔና ግፍ
አዋጅ፣ በድን አጽም የሰላምና የፍቅር አማላጅ መሆናቸው ዘመኑን በሚገባ ይገልጸዋል፡፡
.
አንድ ነገር ግን መታወቅ አለበት፤ ለውጡ ያለ ጥያቄ የምንቀበለው ሀይማኖት አይደለም፤
መሪዎቹም እየበደሉ እንኳ ተንበርክከን የምንማጸናቸው መላእክት አይደሉም፡፡ ይህን
የሚገነዘብ የለውጥ መሪ ፣ ለውጡን ለማምጣት ከፈሰሰው የሰማእታት ደም ጋር በለውጡ
ሳቢያ የሚፈስ የተበደሉ ዜጎች እንባ እንዲቀላቀል መፍቅድ የለበትም፡፡ ያለዚያ ወደ ደምና
እንባ ቅብብሎሽ ታሪካችን እንመለሳለን፡፡"
--------------------------------
--------------------
# ከድንቅነሽ_ስልት_በላይ !
የሉሲ "አማላጅነትና አስታራቂነት" ንድፈ-ሃሳብ ጉዳይ ከጣፎ ድርጊት ተቃርኖ በላይ ነው።
ሰውው ሁሉ በብሄር ከረጢት ተቋጥሮ፣ አካል አምሳል በነብስ ያለን ሰው ተጸይፎ "አይንህን
አልይይይ" ብሎ በግፍ እየገፋ ሳለ እውን ይሄን እውክ ወቅት አጽም ያሽረዋልን? እውን
አሁን ያለውን ሰው ሉሲ ታስታርቀዋለችን? ይሄን መሰል ሰንፋጭና ምስቅልቅሉ የወጣ
ማህበራዊና ፖለቲካዊ ሽክረት ደረጃ በደረጃ እያዋዙ ለማርገብና ኅልዮት በሚፈቅደው
መስመር ለማስገባት እውን የለውጡ መሪዎች በዛ ደረጃ የሚሰፋ ስልት አላቸውን??
ለችግራችን "እናታችን" ሉሲን አንዷ የመዳኛ መንገድ አድርጎ ያሰበ የለውጥ ሀይል ሃገሪቱ
ያለችበትን ሁኔታ በቅጡ ያልተረዳ ወይም ችግራችንን መፍቻ አቅም ያጠረው
አይመስልምን? እንዲያ ሲሆን የጎመዠሁት ነገ በመቋመጥ ብቻ እንዳይቀር ያስፈራኛል።
የችግራችን ውስብስብነት እንዲህ በዘፈን የሚፈወስ አደለም። የችግራችን ጥልቀት
በማስመሰልና በመጋበዝ የሚፈታ አደለም።
እንዲያም ሆኖ ዛሬ ሀገሬ ያለችበት ሁኔታ ከትናንት በእጅጉ የሚሻልና ለዘመናዊ ሰው
መንገድ ምቹ መሆኑን አምናለሁ። በመሆኑም የእውነቱ ተጓዥና መሪ እንዳይደክም፣
የእውነቱን መንገድ እሾህ እንዳይደፍነው፣ ሴረኞችና ሃሳውያን ጎልብተው የልጆቼ አገር
ዳግም በውርደት ሁነት እንዳትዘወትር ከመውተርተር አልቦዝንም!!
ሰላም!!

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
በአንድ በኩል አምላክ በአምሳሉ የፈጠረኝ ፍጡር ነኝ የሚል አማኝ ነው። ተገልብጦ
ደግሞ የሰው ዘር መገኛ የሉሲና የአርዲ አገር ናት ይላል። ሁለቱ ይጋጫሉ አበሻ ግን
ሁለቱን ያምናል። ያስቃል። በፈጣሪ ለሚያምን የሉሲ እድሜ ሀሰት ነው። የሉሲን እድሜ
ለሚያምን ፈጣሪ የለም። አበሻ ግን ሁለቱን ያምናል። ያስቃል።😁 አንተ የቱን ታምናለህ
ካላችሁኝ ሁለቱንም አምናለሁ። ምክንያቱም አበሻ ነኝ😁

ሸጋ ሸጋዋ ሸጊቱ ቅዳሜ ትሁንላቹ❤️❤️❤️

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ዛሬ ፌስቡክ ላይ ያየዋት እና ያስገረመችኝ፣ያሳቀችኝም፣ወይ ጉድ ...ያስባለችኝ ናት..#ፎቶ ናት


ጎንበስ ያለው የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ቡኻሪ ሲሆን ወረቀት የያዘችው ደግሞ ሚስቱ ናት። እሱን መምረጥና አለመምረጧን እያረጋገጠ ይመስላል፤የፓለቲካ ነገር😂 ፣ የወንድ ነገር ፣ የሴት ነገር😂.....ቀጥሉበት


ወይ ቅዳሜ!!

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ታሪክ በዛሬው ዕለት


የካቲት18 ቀን የሎሬት ፀጋዬ ገብረመድኅን 13ኛ የሙት ዓመት መታሰቢያቸው
ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድኅን (1928-1998) ቦዳ ተብላ በምትታውቅ አምቦ ካተማ አካባቢ
በምትገኝ ተራራማ ቦታ ተወለዱ። በአምቦ ማአረገ ሕይወት ቀ.ኃ.ሥ. ትምህርት ቤት
ከዚያም ጀነራል ዊንጌትና በአዲስ አበባ የንግድ ትምህርት ቤት በአገር ውስጥ
ትምህርታችውን ከገፉ በኋላ በቺካጎ ብላክስቶን በህግ ትምህርት ተመርቀው በ1952
እንደ ወጡ በለንደን ከተማ የቴአትር ትምህርት በሮያል ኮርት ቴአትርና በፓሪስ ኮሜዲ
ፍራንሴዝ ተከታትለዋል።


ከ1954እስከ 1964 የብሔራዊ ቴአትር በአርቲስቲክ ዳይሬክተርነት አገለግለዋል። ከዚያም
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር ዲፓርትመንትን አቋቁመዋል።


ሆኖም በ1960ዎቹ ደርግ አብዛኛውን የቴአትር ሥራዎቻቸውን ሲያግድ እሳቸውንም
ለማሰር በቅቷል።


እንደ፡ አዉሮፓ፡ አቈጣጠር፡ በ 2002 ዓ.ም. የብላቴን ሎሬት ጸጋዬ፡ ገብረ መድህን፡
ግጥም፡ ("Proud to be African") አዲስ፡ በተመሰረተው፡ የአፍሪካ፡ ኣንድነት፡ ማሕበር፡
በሕዝብ፥ መዝሙርነት፡ ተመርጧል።


፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
የእረፍት ዋዜማ፦ ፀጋዬ ከማረፉ አራት አመታት ቀደም ብሎም በዶ/ር ኄራን ሠረቀብርሃን
አማካይነት በዋሽንግተን ዲሲ የፀጋዬ ግጥሞች በሲዲ ተቀርፀው ተመርቀዋል። 1 የስንብት
ዝግጅት ይሆን። ትንቢት አስቀድሞ ለነገር እንዲሉ።


ፀጋዬ ከማረፉ አስራ አምስት ቀን አስቀድሞ የ«አንድምታ» ባልደረባ አናግሮት ነበር። እስኪ
ሁለቱን የሎሬት ፀጋዬን ጥኡም ወጎች ላስቀድም።


በአፄ ምኒልክ ዘመን እንግሊዞች ቱርካና ሃይቅ አካባቢ ዝሆን ያድኑ ነበርና አንዴ አደናቸውን
ተከትለው ሲገስግሱ ከኢትዮጵያ ኬላ ደርሰው ኖሮ ድንበር አላሳልፍ ካሉ የኬላ ጠባቂዎች
ጋር የተኩስ ልውውጥ ይደረግና ከአዳኞቹ አንዱ በዚሁ ምክንያት ይሞታል። እንግሊዞችም
አቤቱታ ያሰሙና ነገሩ አባ መላ (ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ) ዘንድ ይደርሳል። እንግሊዞቹ
ያለአግባብ ሰው እንደተገደለባቸው አመልክተው የደም ካሳ እንዲሆናቸው ከኢትዮጵያ
ድንበር ውስጥ መሬት እንዲሰጣቸው ነበር የጠየቁት።


አባመላ ነገሩን ያጠኑና ችግር እንደሌለው ለእንግሊዞቹ ይገልጻሉ። ነገሩ ከመፈጸሙ በፊት
ግን “ይኸ ህግ እናንተ ሃገርም እንደሚሰራበት ማየት ስለምንሻ በሰነድ መልክ ረቂቁ ካለ
እስቲ እንየው። እውነት የእንግሊዝ ሰው የዌልስን ሰው ቢገድል እንግሊዝ ከመሬቷ ዌልስ
የምትሰጥ ከሆነ እኛም እንሰጣለን። እሱም የሚሆነው ለተገደለብን የኬላ ጠባቂ ካሳ
የሚሆን ከቱርካና ሃይቅ አካባቢ መሬት ከተረከብን ይሆናል ብለው መለሷቸው።

፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
ሌላው ደግሞ የሎሬት ፀጋዬ ከ«ሕይወት ቢራቢሮ» መታተም ጋራ ተያይዞ ለአንድምታ
ባልደረባ ያወጋው ነው። መጀመሪያ የግጥሟን ቅንጫቢ ነቢይ መኮንን ከተረካው እነሆ!


«...ምን አይተሻል ከቄጤማ፣ ምን አይተሻል ከለምለሙ
ቀን አብረሽ አብበሽ ውለሽ፣ ሲመሽ አብረሽ መስለምለሙ?..


አስተምሪኝ ቢራ ቢሮ፣ ሰው ለመባል አለኝታዬ
ቀድሞ የት ነው መነሻዬ ሲመሽ የት ነው መድረሻዬ...
ሲተረትማ ሲወጋ፣ ከየብልጭታው ውጋጋን
የሰው አራዊት የአእዋፍ፣ ውስብስብ ነገደ-ጉንዳን
ሲነሳ ሲሮጥ ሲደፋ፣ ሲያጋድል ሲያዛባ ሚዛን
በማይመጠን ታላቅ ኃይል፣ በተፈጥሮ ግዙፍ ሥልጣን
ሊፍተለተል ይወለዳል፣ ሳይነቃ ይወድማል ይባላል
ልደቱ ዕድሜና ሞቱ፣ አለማቋረጥ ይጓዛል፤
ይኸ ይሆን አልፋ - ኦሜጋ? ይኸ ይሆን አስቀድሞ ቃል?»


ፀጋዬ እንዲህ አለ። «እሷ ግጥም በጋዜጣ ታትማ በወጣች ማግስት መንግስቱ ለማ
ከቢሮዬ መጥቶ ቢራውን እስቲ አምጣው ወይስ ዝም ብለህ ነው ቢራ ቢሮ ያልከው» ብሎ
እንደቀለደብኝ ትዝ ይለኛል።ትንሽ ትከዝ ብሎም «መንግስቱ ምን የመሰለ ደማም ቋንቋ
የነበረው ሰው ነበር።አሁን እኮ ደማም ቋንቋ የሚናገር ሰው ሁሉ ጠፋ»።አፈሩ ይቅለለውና
ሎሬት ፀጋዬ የኛን ትውልድ <<ጫት አመንዣኪ>> ትውልድ ነበር የሚለው።እንዲህ እንደነሱ
ዘመን ባይጎሉም ውድድሩም ቢጠናባቸውም አሁንም እኮ አንቱ የተባሉ ወጣት ደራሲያን
ገጣሚያን አሉን። ጊዜው ሲደርስ እንዘክራቸዋለን።


፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አምቦ አካባቢ ልዩ ስሟ ቦዳ ከኦሮሞና ከአማራ ወገኖቹ የተወለደው ፀጋዬ ገና በልጅነቱ
ነበር ሶስቱ ቋንቋዎች አማርኛ፡ እንግሊዘኛና ኦሮሞኛ የተገሩለት። በትምሕርት እየጎለመሰ
ሲሄድም ደራሲነቱን ገጣሚነቱን እንዲያ ሲልም ፀሃፊ-ተውኔትነቱን በዋነኛነት በጎልማሳነት
ዘመኑ ደግሞ ማህበረሰባዊ ሃያሲነት እና የአፍሪካ የሰው ዘር እና የቅብጥ ቋንቋ እና ባህል
ጠቢብነትን አክሎበት እስከ እለተ ህልፈቱ ዘልቋል። በኩላሊት በሽታ መለከፉ እና
አለመዳኑን እንዲያም ሲል በጉብዝናው ወራት ያላሰበውን ስደት በሕክምና ሳቢያ የአብራኩ
ክፋይ ልጆቹ ወዳሉበት አሜሪካ አቅንቶ በዚያው አሸልቧል። የማሳረጊያ ግጥሙም ይህንን
ተስፋ ቢስነትን አመላካች ይሆን።


የማይነጋ ሕልም ሳልም
የማይድን በሽታ ሳክም
የማያድግ ችግኝ ሳርም
የሰው ሕይወት ስከረክም
እኔ ለኔ ኖሬ አላውቅም


፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
ብላቴን ሎሬት ጸጋዬ በርካታ ግጥሞችን፥ የቴአትር ሥራዎችን የተለያዩ መጣጥፎችንና
ዘፈኖችን አበርክታዋል። ጸጋዬ በ1998 ለጉበት በሽታ ሕክምና በመሻት ወደ ማንሃታን
በሄዱበት አርፈዋል። በአዲስ አበባ በቅድስት ሥላሴ ቤተክርቲያን ተቀብረዋል።


ነፍሳቸውን በአብርሃም እቅፍ ያኑርልን::
ነፍስ ይማር!


፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨

ምንጭ
ነቢይ መኮንን 2000 የእሳት ወይ አበባ ግምገማ። አንድምታ ቁጥር 9
መስከረም-ህዳር 2000 ገጽ 1።
ፀጋዬ ገብረመድሕን:: 1966:: እሳት ወይ አበባ::
ኢትዮጵያ ዛሬ


@wegoch
@wegoch
@balmbaras
አጠገቤ የተቀመጠች ልጅ ስሟ ለደህንነቷ ሲባል የተደበቀ...ለምንድነው ግን ዛሬ
ያገኘኸኝ? ትላንትን ስላላገኘሁሽ ነዋ።አንድ ነገር ልንገርህ መልሶችህ ሁሉ እንደሚያናድዱኝ
ታውቃለህ? አላውቅም ግን እንዴት ወደ ሚያናድድሽ ልጅ ትመጫለሽ ወይስ መናደዱን
ወደሽዋል? ከቀን ቀን ትስተካከላለህ በሚል ተስፋ እንጂ አንድም ቀን ተደስቼ
አላውቅም፣የማይገቡኝን ነገሮች ታወራለህ፣የተጠየከውን አትመልስም ብቻ ብዙ።
የማይገባሽን ካወራው ወይ አይገባሽም ወይ ማስረዳት አልችልም፣የተጠየከውን
አትመልስም ብዙ ግዜ የምትጠይቂው የወደፊቱን ነው የወደፊቱን ደሞ የመጠርጠር እንጂ
የማወቅ ስልጣን አልተሰጠኝም .......ምጠረጥረውን ስነግርሽ ደሞ አይስማማሽም...ቆይ
ፍቅር ለአንተ ምንድነው? አየሽ ችግርሽ ማንም ጠቢብ ያልመለሰውን ጥያቄ ስትጠይቂኝ
ብዙ ተማሪዎች መልሱ አልተሰጠም የሚለውን አክብበው ነው ራይት ያገኙት እኔም ምርጫ
ስጪኝ ግን ከመልሱ ውስጥ መልሱ አልተሰጠም የሚለውን አስገቢበት።
ደሞ ሳልነግርህ..... ባለፈው ደሜን ያፈላውን ነገር ምን ደሞ እላለው ፊቴን ከስክሼ ትዝ
ይልሀል ስልክህን ልደውልበት ብዬ የወሰድከት? አዎ ትዝ ይለኛል ፎቶዎቼን ቴክስቶቼን
እንዳየሽ ተረድቻለው እኮ ዝም ያልኩሽ ምንም ስለሌለው ነው።ምንም ስለሌለው? አዎ
ምንም ስለሌለው ስማ የምታወራው ከሴትጋ ብቻ እንደሆነ አይቻለው ይሄ ምንም ነው?
ያልተረዳሽው ነገር አንቺም ከነዛ ውስጥ ነበርሽ እኮ ስላወራሁሽ፣ ስለተግባባን መስሎኝ
ጠረጴዛ ላይ ቁጭ ብለን ማክያቶ ስታማስዪ የማይሽ፣ደግሞ ከወንድጋ ምን ላወራ
እችላለው ?ላግኛቹ ብዬ እድሉን ያልሰጡኝ ሴቶች እኮ አሉ በነሱስ ልከሰስ ነው? አሁን
እንኳን ወዳንቺ ስመጣ አንዲት ልጅን ስልክሽን ስላት የለኝም ብላኛለች..አልተሟገትኳትም
ሲኖርሽ ትሰጪኛለሽ ብያታለው አሁን በሴትኛ ስታስቢው እውን ልጅቷ ስልክ የላትም? ቆይ
ስለምንድነው የምታወራው?


ስለምንድነው ማወራው .....ገብቶሃል/ሻል.....ካልገባህ/ሽ ........ተወው/ይ

ሸጋ ቀን!💚!💛!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
.........አደዋ ዝም ብሎ ድል አይደለም💚
አድዋ የስነ-ልቦና ከፍታ ነው ;💛
አድዋ የእልህ ጥግ ነው ;❤️
አድዋ የነፃነት ዋጋ መለኪያ ነው ;💚
አድዋ የአገር ፍቅር ጫፍ ነው ; 💛
አድዋ የባርነት የሞት ጉድጓድ ነው ;💚
አድዋ ከመለያየታችን የለየን ድንበር ነው ;💛
አድዋ የእብሪተኞች ጥሩር ሀፍረት ነው ;❤️
አድዋ የሀበሻ የሞራል ከፍታ ነው ;💚
አድዋ የጥቁሮች አንገት ትራስ ሆኖ ቀና ያደረገ ነው ;💛
አድዋ የምኒልክ የመሪነት ጥበብ💚
የራስ መኮንን ራስነት ፣ የባልቻ ወኔ ፣ ያሉላ የድል ጮራ ❤️
ያያቶቼ የመንፈስ ከፍታ.ስጦታ ነው ።💛
አድዋ ከድል ባሻገር ሚሊዮን ርቀቶችን ከፍ ብሎ የተሰቀለው ለዚህ ነው።❤️
....... ያያቶቼ ደም መንፈሣዊ ፀበል ፣ አጥንታቸውም የፈውስ መናችን ነው ; ምልህ ለዚህ ነው።💚💛❤️

ይኸው ነው ለኔ.!!💚💛

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
💚💛❤️
የአድዋ ሳምንት ላይ እኮ ነው ያለነው እንዴት ዝም ይባላል።

አሁን ልጅ ቢኖረንና "አደዋ ግን ምንድን ነው?" ቢለን ምን ልንለው ነው?

ለናንተ አድዋ ምንድነው...? አድዋን ስታስቡ ምን ይሰማቹሃል...?


#እየጠበቅናቹ ነው.......ዛሬ እስቲ ስለዚህ እናውጋ....አድዋ ሁለት ቀንም አይደል የቀረው.....

👇👇👇
@balmbaras
@Gebriel_19
@getem
@getem
Miki:👇👇

Adwa lene ye andinstachin masaya
Ethiopiawinet mn malet endehone yasayenbet nw

Yotod Michael:👇👇

Adwa ene negn .........

🇧🇰вĸ:👇👇👇

Adiwan sasib zare be hodachin ena be ayimorochin wist yizen yeminzorow Kim ket yemeta nw biye asibalew.........kimu yanem kenebere min yahil Hagerachewin be minim endemayideraderubet asayitewinal.....enam zare chigrachin le mefitat sinasib Ethiopia mitibal hager mederaderyachin mareg endelelbin yaseyegnal....
Melikam beal le hulachum
Bk...ke *NAZU/Adama/*
💚💛❤️💚💛❤️

@balmbaras
@Gebriel_19
@wegoch
@wegoch
💚💛💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️
ስንት አየሁ አለም አየሁ:👇👇👇👇

አድዋን ለመግለፅ አድዋን መሆን ያለብኝ ይመስለኛል.....ተኑሮ የተሞከረ የአፍሪካ ብርቅዬ አይደገሜ ታሪክ ይመስለኛል። መተባበር......ልዩነትን መዘንጋት ሰው መሆን ግድም ያለን ስብእና ብቻ በማሰብ የተሰራ ትልቅ ታሪክ......የመንጋት እና የመጣስ እሳቤን ስንቅ አድርጎ የተኬደ ጉዞ......ሰው በምድር ሳለ ሊከውነው የሚገባን የህይወት ስንክሳር አኳኋን በተሞክሮ ያስተማረ ብዙ ነገር ነው አድዋ ማለት።
አድዋ ዕለት ነው
ሰው የማርቀቅ ዶሴ የተሰነደበት
አድዋ ወቅት ነው
ነፃነት አሽቶ የተቀመሰበት
አድዋ ቦታ ነው
የመዳን ደም ፈልቆ ህዝብ ያጠመቀበት
አድዋ ጥበብ ነው
ህያው ፍልስፍና ምጥቀትን ያኖረ
አስገዳጅ መግነጢስ ግርምት የፈጠረ
አድዋ ፊደል ነው
ወደው የሚያጠኑት ፈቅደው የሚያነቡት
ህያው መፅሐፍ ነው።
.....💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

mnase tamrat:👇👇👇

አድዋ
የአንድነታችን ውጤት
የህብረታችን ማሳያ
የኢትዮጵያዊነታችን መሠረት
የመደመር ቀመር መጀመሪያ
የነፃነታችን ማብሰሪያ
ድልን ክብርን ማንነትን አብሮነትን
በአንድ ላይ የተጎናፀፍንበት ቀን
"የደመቅንበት ቀን"

Meklit:👇👇👇

Adwa lene..... ETHIOPIAWIT yemilew ma'erege yetetsafebet be'er new....

Feker abe Weeknd💞💓🥊🥊🥊🥊💖💕💘💝💕:👇👇👇

ዝክረ አድዋ
እስኪ ከአድዋ ድል ምን የተማርኩት ነገር አለ? ስል እርሴን ስጠይቅ ከተለያየ የተውጣጣ የመጣን ህብረተሰብ በአንድ ጥላ ስር ሰክን ባለ መልኩ ህብረተሰቡን አሰባስበው አንድ ሆነው ጠላትን እንዴት ድል ማድረግ እንዳለባቸው ወስነው በአንድነት በአጭሩ ድልን ተቀናጅተዋል ።

አሁን እኔ እንደሚመስለኝ ስትሰባሰብ አንድ ስንሆን ምን ያህል እማይቻል ነገር እንደሚቻል እንዴት አስፈሪም እንደምንሆን እንደምንከበርም ጭምር በማንኛውም ዘርፍ ላይ ህብረት አንድነት ምንያህል ሀይል እንዳለው እማይቻል እሚመስለውን ገድል ሊፈፀም አንደሚቻል የተማርኩበት ነው ።ስለዚህ ቅድም አያቶቻችን የራሳቸውን ታሪክ ሰርተው አልፈዋል ።በአጭሩ በተባበርን አንድ መሆይንን በጋራ መስራትን በጋራ ማደግን እንማር እላለው ከተሳሳትኩም አርሙኝ😍

@balmbaras
@Gebriel_19
@wegoch
@wegoch
💚💛💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️
ስንት አየሁ አለም አየሁ:👇👇👇👇

አድዋን ለመግለፅ አድዋን መሆን ያለብኝ ይመስለኛል.....ተኑሮ የተሞከረ የአፍሪካ ብርቅዬ አይደገሜ ታሪክ ይመስለኛል። መተባበር......ልዩነትን መዘንጋት ሰው መሆን ግድም ያለን ስብእና ብቻ በማሰብ የተሰራ ትልቅ ታሪክ......የመንጋት እና የመጣስ እሳቤን ስንቅ አድርጎ የተኬደ ጉዞ......ሰው በምድር ሳለ ሊከውነው የሚገባን የህይወት ስንክሳር አኳኋን በተሞክሮ ያስተማረ ብዙ ነገር ነው አድዋ ማለት።
አድዋ ዕለት ነው
ሰው የማርቀቅ ዶሴ የተሰነደበት
አድዋ ወቅት ነው
ነፃነት አሽቶ የተቀመሰበት
አድዋ ቦታ ነው
የመዳን ደም ፈልቆ ህዝብ ያጠመቀበት
አድዋ ጥበብ ነው
ህያው ፍልስፍና ምጥቀትን ያኖረ
አስገዳጅ መግነጢስ ግርምት የፈጠረ
አድዋ ፊደል ነው
ወደው የሚያጠኑት ፈቅደው የሚያነቡት
ህያው መፅሐፍ ነው።
.....💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

mnase tamrat:👇👇👇

አድዋ
የአንድነታችን ውጤት
የህብረታችን ማሳያ
የኢትዮጵያዊነታችን መሠረት
የመደመር ቀመር መጀመሪያ
የነፃነታችን ማብሰሪያ
ድልን ክብርን ማንነትን አብሮነትን
በአንድ ላይ የተጎናፀፍንበት ቀን
"የደመቅንበት ቀን"

Meklit:👇👇👇

Adwa lene..... ETHIOPIAWIT yemilew ma'erege yetetsafebet be'er new....

Feker abe Weeknd💞💓🥊🥊🥊🥊💖💕💘💝💕:👇👇👇

ዝክረ አድዋ
እስኪ ከአድዋ ድል ምን የተማርኩት ነገር አለ? ስል እርሴን ስጠይቅ ከተለያየ የተውጣጣ የመጣን ህብረተሰብ በአንድ ጥላ ስር ሰክን ባለ መልኩ ህብረተሰቡን አሰባስበው አንድ ሆነው ጠላትን እንዴት ድል ማድረግ እንዳለባቸው ወስነው በአንድነት በአጭሩ ድልን ተቀናጅተዋል ።

አሁን እኔ እንደሚመስለኝ ስትሰባሰብ አንድ ስንሆን ምን ያህል እማይቻል ነገር እንደሚቻል እንዴት አስፈሪም እንደምንሆን እንደምንከበርም ጭምር በማንኛውም ዘርፍ ላይ ህብረት አንድነት ምንያህል ሀይል እንዳለው እማይቻል እሚመስለውን ገድል ሊፈፀም አንደሚቻል የተማርኩበት ነው ።ስለዚህ ቅድም አያቶቻችን የራሳቸውን ታሪክ ሰርተው አልፈዋል ።በአጭሩ በተባበርን አንድ መሆይንን በጋራ መስራትን በጋራ ማደግን እንማር እላለው ከተሳሳትኩም አርሙኝ😍

@balmbaras
@Gebriel_19
@getem
@getem

👋jerry dimple👇👇👇

አድዋ ማለት ማንነታችን ነው
አድዋ ማለት ቋንቋችን ነው
አድዋ ማለት መሰረታችን ነው
ብቻ አድዋን ሀረግና ፊደላት ተደራርበው የማይገልፁት የማይተኩት የኛነታችን መሰረት ነው።
የትላንት ጀግኖቻችን ለዚህ አበቁን
ኢትዩጽያ ለዘላለም ትኑር።

አድዋ

Neba Ye abatua lj:👇👇👇

adwa malet lene yetkur hzbochi enba yetabesebet ye andnetachin masaya nechi keler enji mnm grma edelelew yasayubet Ethiopia jegna korat ena adegegna hager mehonuan yasayubet beka adwa malet lene lgeltsew yemalchlew yewst smet malet nw

jo jo:👇👇👇

adwa malet ye netsanetachen belen becha yemenasebew aydelem mekenyatum ashenafiwoch nen ena ye deel kenachen new be adwa mekenyat 14 ye africa hageratoch bandirachewen kegna amesaslewal yegna becha aydelem ye africa kurat new ena adwan basebku kuter yehone seweneten neezer yadergegnal,ahun ahun geen egna ahun yet nen abatochachen yet neberu

$ ï$ kîñg:👇👇👇

ሰላምታየን ሳቀረብ ከራሴ ዝቅ ከጉልበቴ በርከክ ብዬ ነው. ምክንያቱም ኢትዮጵያዊ ስለሆንክ በተለይ ሰው ሁሉ ስለ ራሱ ስለ ብሔሩ ስለ ክልሉ በሚያወራበት ሰአት አንተ ስለ አድዋ. ሁሉን አንድ ስለሚያረገው ስለ አድዋ እናውራ. እንወቅ ስላልክ ነው አድዋ !!!! አድዋ!!!! አድዋ. በአጠቃላይ አድዋን ስናስብ መሪውን. እምዬን ሚኒሊክን መርሳት የለብንም. አሊጫው መረቁ ወጡም ሰለቸኝ ሚኒሊክ ተነስቶ ሽሮ ባበላኝ መልካም አዳር ወዳጄ

💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️


ሁላችሁንም እጅግ በጣም እናመሰግናለን🙏🙏ስለ አድዋ ስታስቡ የሚሰማቹን፣የምታስቡትን እና ስሜታቹን አጋርታችሁናልና ከልብ እናመሰግናለን 🙏🙏



*ሚኪ🙏
*ዮቶድ🙏
*b k ✔️bk tm🙏
* ስንት አየሁ አለም አየሁ🙏
*mnase tamrat
*meklit🙏
*feker abe weekend
*ገብርዬ🙏
*neba yeabatwa lij🙏
*jo jo🙏
*$i$ king🙏

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
አድዋ ኬኛ!!!

ሃገር ማለት ህዝብ ነው። ሃገር ማለታ ታሪክ ነው!! ታሪክም የሃገር ህዝብ ሁሉ ነው።
ክብር ለሰው ክብር፣ ለእውነ፣ ነጻነትና አንድነት ለተሰው ጀግኖች።
አድዋን "እኔ ብቻ ልሸልልበት" የሚል ያገር ልጅ ከገጠመህ "ምጽ" ብለህ እለፈው!!

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
Abebe Tolla Feyisa

እኔ የአድዋን ድል ሳከብር አባቶቼ ያከበሩትን አፄ ሚኒሊክም አብሬ አከብራለሁ!
ያለ አፄ ሚኒሊክ አድዋ ብቻውን ዛሬ ስናስታውሰው መለስ ዜናዊ የተወለዱበት ሃገር ብቻ ነበር የሚሆነው... አቶ መለስ ራሳቸው ከአቶ ዜናዊ ሳይሆን ከሚስተር አርቤርቶ ነበር የሚወለዱት😂
እውነት እውነት እልሃለሁ አፄውን ሳታከብር አደዋን ብቻውን ብትጠራው የአድዋ ተራሮች... የሃገሪቷም አድባር የአያቶችህ አፅምም ይታዘብሃል!

#Abebe_Tolla_Feyisa @ethpolitics
2024/09/28 11:16:33
Back to Top
HTML Embed Code: