Telegram Web Link
አሁን ደሞ እኔ ራሴ በተራዬ ስለ አድዋ ...እንዲህ ልበልማ 💚💛❤️





# አድዋ_ማለት_አንተ_ነህ !
............................ .....
-----አንተ ብታሳንሰውም; ዋጋ ባትሰጠውም፣ አድዋ ጥፍጥፍ ሃውልት የማይሻ፣ ጭፈራና
አጀባ የማይከጅል በራሱ ዘመንን የሚያቋርጥ; ዘመንን የሚያናግርና የሚናገር ለራሱ በራሱ
የቆመ; የተተከለ; የከበደ የአበሻ ልጆች; አልፎም ተርፎ፣ አንተ የማታውቃቸው የጥቁር
ህዝቦች ሁሉ የጋራ ሃውልት ነው!!!!!!!
--------
የአድዋ ድል በረከትና ትሩፋት እንዲገባህ ከፈለግክ ከደቡብ አፍሪካ ወይም ጎረቤትህ
ከኬንያ አገር ሰው ጭንቅላትና ልብ ተውሰህ; ያዋጣኛል ካልክም ገዝተህ አንተ ላይ
ገጥመህ ለአንድ ሳምንት ሞክረው። እመነኝ; ነጩ ሁሉ አምላክህ; ጥቁር ሁሉ ከታች ሆኖ
ይታይሃል!! እምነት፣እኩልነት፣ሰውነት፣ ክብር፣ እዝነት፣ እርህራሄ፣ ወግ፣ ታሪክ፣ ገድል፣
ሽለላ፣ ዝና፣ ናፍቆት, ፣ ማንነት እና ሌላም ነገር ሁሉ አሁን በገጠምከው አዲስ ልብና
ጭንቅላት በዝቶና በርትቶ ስለማታገኝ በፍጥነት አውልቀህ ትጥለዋለህ። ለምን ብትል
ያንተ ጭንቅላትና ቅኝት የተጠመቀበት ወግና ልማድ ከአድዋ ገድልና በረከት ከሚመነጭ
የነፃነት ፀበል ስለሆነ ነው!! ልንገርህ ደሃ ነን; ግን ደግሞ አበሻ ደህይቶም; ከስቶም;
ጠቁሮም ለራሱ ዋጋና ነፃነት ዞን የሚከልል ጀግና ነው!!
አድዋ ማለት ከፍታ ነው፥ አድዋ ማለት እኩልነት!! አድዋ መብለጥ፣ ማሸነፍና እንቢተኝነት
ነው። አድዋ ማለት ለትውልድ መዳን፣ ለትውልድ አንገት መቃናት የተለገሰ ደም፣ የወደቀ
ነብስ፣ በባሩድ የተቀቀለ ስጋ ነው!! አድዋ ቀርታ ቢያንስ ለ40 አመታት ጣሊያን ጎጆዋን
በአያትህ አናት ላይ ሰርታበት ቢሆን ኖሮ አሁን አድዋን ለመንቀፍ የምትጠቀምበት ዘፈንህ;
እስክታህ፣ ቋንቋህ፣ አለባበስህ፣ ስነ-ቃልህና አቲያሞህ ላይኖር ሁሉ ይችል ነበር።
አይኖርምም ነበር። አየህ አድዋ ማለት ዛሬ አንተ ነህ።
-----
አድዋና አባት ምኒልክ ከደበሩህ አንተ ማስተንተን የጎደለህ እነ እንትና ሲነፉህ የምትጮህ
የኳስ ሜዳ ደጋፊ ቡቩዜላ ነህ!! በስማ በለው የመንደር ወሬ "የአያትክን" እውነትና የእውነት
ሞት ዋጋ አታሳጣ; "አባቴ ተገዶ ዘምቶ ነፃ አገር አወረሰኝ" እያልክ የአባትክን ልዕልና
ለልጅህ አጉድፈህ አትንገር። በርግጥ ልጅህ አይናምና አስተዋይ ከሆነ ወግህ እራሱን
በራሱ ወጊ ተጣራሽ ስለሆነ ከአንተ ድብልቅልቅና ምስቅልቅል ወግ ይልቅ ፊት ለፊቱ
በአካል ያለውን የቅድመ አያቱን በረከትና እውነት አድዋን- ነፃነቱን ያምናል። አድዋ ማለት
እራሱ ነውና!
------
ወዳጄ ከምኒልክ ወዲህ ስለ ኢትዮጵያ; ስለ እምነትና ሃለፊነት, ስለ ህዝብና ታሪካዊ
ተጠያቂነት ከጠላቱ ጋር ፊት ለፊት፣ አንገት ለአንገት ከጠላቱ ጋር ሳንጃ የተማዘዘ
አላየንም። ምኒልክ መቁረጫ ነበር!! ምኒልክ የቀዳማውያን አገር ወዳድ ታጋዮችን ልማድና
ወግ ያስከተለ፣ በጦር ሜዳ ለህዝብና አገር መሞት ያለውን ሳይኮሎጂካል ፋይዳ ለሞሶሎኒ
ሀ-- ሁ-- ብሎ ያስተማረ፣ እኔና አንተን ያስከበረ ዘመን ተሻጋሪ የአበሻ ሃውልት (legend)
ነው!! ምኒልክ እውነተኛ ነበር; ሸዋ ሸፍጥ ሸፍጥ ሲለው; በሞቱ መሃል ላይ ሆኖ እንኳን
ጭንቁ ማማ ጦቢያ እንጂ ስልጣንና ጎጥ ስላልነበር; በዙፋኔ ላይ እያሱ መሃመድ/ እያሱ
ሚካኤል ይሰየም; አገሩንም ይምራ ነበር ያለው!!!! ሸዋ ያሰበውን ማሰብ አቅቶት
አይምሰልህ; ኢትዮጵያ እንጅ ጎጥ ሰላላሳሰበው ነበር!!
አየህ እምየ እውነት ነበር; ትግሉም ላንተና ለእኔ ነበር!! ስለሆነም "ምኒሊክ ገፋኝ" አትበል;
"አድዋ ተራ ነው" አትበል; "አድዋ ግዳጅ ነው" አትበል; "አድዋ ማባበያ ነው" አትበል።
አድዋም ምኒሊክም ለአሁኗ ኢትዮጵያ ነብስና ስጋ ባለውለታ ናቸው።
ግን ግን ደግሞ አንተ ብታሳንሰውም; ዋጋ ባትሰጠውም፣ አድዋ ጥፍጥፍ ሃውልት የማይሻ፣
ጭፈራና አጀባ የማይከጅል በራሱ ዘመንን የሚያቋርጥ; ዘመንን የሚያናግርና የሚናገር
ለራሱ በራሱ የቆመ; የተተከለ; የከበደ የአበሻ ልጆች; አልፎም ተርፎ፣ አንተ የማታውቃቸው
የጥቁር ህዝቦች ሁሉ የጋራ ሃውልት ነው!!!!!!! የነጭ ሁሉ አስፈሪ ግርማ ሞገስ የነጻነት
ካባና ጥላ ነው። ወጪት ረጋጭና ራስክን አጉዳፊ ከሆንክ በእርግጥ አድዋን ትንቃለህ;
ምኒልክንና የምኒልክን ጋሻ መከታ ጦርኛ አርበኞች ሁሉ ዋጋ ታሳጣለህ!!
አድዋ ማለት አንተ ነህ። እራስክን ካላወቅክ አድዋን ከወዴት ታመጣውና??
------
ክብር አድዋ ላይ ታሪክ ለጻፉ ሁሉ!!


ሸጋ ጁምኣ!!💚💛


@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ከያኒ ሚካኤልን ሚሊዮን ለክብረ አድዋ በተዘጋጀው ቡክሌት ላይ ቀጣዩን መልእክት አስተላልፏል። ዛሬ ምሽት በ12 ሰዓት ከ1700 በላይ ታዳሚ እንደሚገኝ የሚጠበቅበትን የዋዜማ ቴአትር በጣይቱ ሆቴል ተገኘተው.....ይካፈሉ።

መግቢያው 200 ብቻ ነው!

ክብረ ድግስ 💚💛

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ከነ ገበየሁ ጎን!!!!!


ለምንድን አልተክዝ፣
ለምንድን አልቆዝም፣ እኔ አርበኛይቱ፣
የሚኒሊክ በልጅግ፤
የአድዋ ነበልባል ፣ የጧት ጠሃይቱ፣
የአሉላ ምንሽር፣
የጣይቱ ግንባር፤ የባልቻ ጉልበቱ።


ለምንድር አይከፋኝ፤
ለምን አልቀየም፤ ለምን አልቆጣ፤
"አድዋ ምኔ ነው???
ምኒሊክ ምኔ ነው????
ባፍንጫየ ይውጣ!!!!!!
ተውን አትጨቅጭቁን፤
ኳሱን እንይበት፤ ድራፍቱን እንጠጣ፤
የሚል የጉድ ጅራት፤
ጀምበር መሸኛው ላይ፤ ከኋላ ሲመጣ።


በላየ ላይ ሰፍሮ፤
በወሬ መቀነት፤
በምላስ ተከቦ፤
ታሪክ የሚሸፍጥ፤
ዘመን የሚያሳብቅ፤የዘመን ቡትቶ፤
ዙሪያየን ከቦኛል፤
ዝንጋኤ የበላው፤
እንዴት እንደቆመ፤
ማሰብ ያደከመው፤
ሃገርና ሰንደቅ፤ በደም ግብር ፀንቶ።


ምነው የጦቢያ አምላክ፤
በእድሜየ ጀምበር ላይ፤
ሃገርና ሰንደቅ፤
አፈርና ድካ፤
ቃልና መታመን፤
ሞትና ነፃነት፤
እንዴት እንደቆመ
በማይገባው ትውልድ፤
መሃል ተቀምጬ፤
መንፈሴ እየራደ፤
ወኔየ እየከዳኝ፤
በሰላቶ ምላስ፤
በባንዳዎች ሽሙጥ፤
በረከሰ ከንፈር፤
ምኒሊክ ተሰድቦ፤
ባንዳ እየገነነ፤
በጎጋ መፈክር፤
ቅስሜ ተፈርክሶ፤ አንገቴን ከመስበር፣
ሞት ይሻላል ብየ፤
ምነው አድዋ ላይ፣
ከነ ገበየሁ ጎን፣ ወድቄ በነበር።

((( ጃ ኖ ))💚💛❤️

የዛሬ አመት እንዲህ ብለን ነበር.....የዘንድሮ አድዋ ግን ይለያል......ብዙ ሰው ላይ አድዋን ለማክበር መነቃቃት ተፈጥሯል ብዬ አስባለው....በመንግስት ፣ በማህበራዊ ሚዲያ ፣ አዲስ አበባ ላይ ባሉ የተለያዩ ሰፈሮች እና በየመስሪያ ቤት እንዲሁም ከሀገር ውጪም የነገውን አድዋን ለማክበር ሁሉም ዝግጅቱን ጨርሶ ነገን በጉጉት ይጠብቃል.......ቢያንስ እስከ ሁለት መቶ ሀምሳ ሺህ ሰው ይጠበቃል.......የሚቀጥለው አመት ፈጣሪ ካደረሰን ከዚህኛው አመት በተሻለ እንደሚደምቅ ደሞ እርግጠኛ ነኝ.......በመጨረሻም ለረጅም ጊዜ እውቅና ተነፍጎት የተነበረው የአድዋ በዓል ዘንድሮ ለድሉ በዓል እንደሚገባው ባይሆን.....ባለፋት አመታት ከነበረው ....አንፃር ሲታይ ግን እጅግ በጣም አስደሳች ነው !!!!!!!


ነገ በጥዋቱ ሚኒልክ ሃውልት ስር እንገናኝ!!!💚💛❤️

ሰላም እደሩልኝ💚💛❤️

ያስከበሩኝን አያቶቼን ሳከብር እኖራለሁ!!!

@balmbaras
@getem
@getem
ሰራዊቱም ስለሃገሩ ስለመንግሥቱ ተናዶ ነበርና መድፉ ይመታኜል ነፍጡም ይጥለኛል እሞታለሁ ብሎ ልቡ አልፈራበትም። ተካክሎ ጀግኖ ነበር።
ጌታው ቢወድቅ ሎሌው አያነሣውም ወንድሙ ቢወድቅ ወንድሙ አያነሳውም ነበር። #የቆሰለውም_ሰው_አልጋው_ይጽና #(ይቁም) እንጂ_ኋላ_ስትመለስ_ታነሳኛለህ_በመሃይም_ ቃሌ_ገዝቼሃለሁ_ይለው_ነበር። ዕይርም (ጥይትም) ያለቀበት እንደሆነ የቆሰለውን ሰው ከወገቡ ዝናሩን እየፈታ እያባረረ ወደፊት ይተኩስ ነበር ።
ሰውም ከመንገድ ርዝመት ከተኩስ ብዛት የተነሳ ደክሞት የተቀመጠ እንደሆነ #የምኒልክ_ወሮታ_የጮማው_የጠጁ_ይህ ነውን እየተባባለ እንደገና እየተነሳ ይዋጋ ነበር።

ክብር ለእምዬ ምኒሊክ እና ለእቴጌ ጣይቱ
ክብር ለዛ ውድ ህይወቱን ለመሰዋት ያደረገው ለምስኪኑ የሃገሬ ገበሬ ።

እንኳን ለ123ኛው የአድዋ በአል አደረሰን!
መልካም የድል በዓል!

ከፍሬ እግዚ

@wegoch
@wegoch
@gebriel_19
እቴጌ ለምኒሊክ እንዲህ አሏቸው
"እኔ ሴት ነኝ፤ ጦርነት አልወድም፡፡ ግን እንደዚህ ዓይነት ውል ከምቀበል ሞትን (ጦርነትን)እመርጣለሁ”
ለእኛለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለመላው የጥቁር ህዝብ ኩራት የሆነው አድዋን ድል በጥቂቱ በወፍ በረር ቅኝት.....

"ምኒሊክ ተወልዶ ባያነሣ ጋሻ
ግብሩ እንቁላል ነበር ይሄን ጊዜ ሀበሻ"



ሃያዘጠኝሺህፈረሰኞችን ጨምሮ ከመቶ ሺህ እስከ መቶ ሃያ ሺህ የሚገመት አንድ ሺህ ኪሎ ሜትር በባዶ እግሩ የተጓዘ የኢትዮጵያ የገበሬ ሠራዊት በወታደራዊ አካዳሚ የሠለጠነውን የአውሮጳ ወራሪ ጦር የካቲት 23 ማለዳ አሥራ አንድ ሰዓት ግድም ገጥሞ ከረፋዱ አራት ሰዓት ላይ ሸልዶ ተራራ ወይም (ሶሎዳተራራ)፤ማርያምሸዊቶ፤አዲ ተቡን፤ ረቢ አርእየኒ (እግዚሃርአሳየኝ)…በመሠኘትየሚታወቁትእነዚህ ገመገሞችና ተራራማ ሥፍራዎች ዋነኞቹ የጦር ግንባሮች የጣልያንን ጦር ድል አደረገው ፡፡

የደረሰው ጉዳት
በኢትዮጵያ በኩል

የሞቱ፦፡ከ፬ እስከ ፭ ሺህ
የቆሰሉ፦
፰ ሺህ

በጥልያን በኩል
የሞቱ፦ ፯ ሺህ
የቆሰሉ፦ ፩ ሺህ ፭፻
የተያዙ፦፫ ሺህ
በጦርነቱ ወቅት ከተፈፀሙ እጅግ ከሚያስገርሙ ታሪኮች መካከል.......
“ጣሊያኖችእንዳስላሴወጥተው‘የእየሱስ ቤተ ክርስቲያንን ልቀቁ፤ ጦርነቱ ሲያልቅ በትልቅ ህንጻ እንሰራላችኋለን።’ አሏቸውና አንድ ሺህ ብር ሰጧቸው። ሁሉም ቤተክርስቲያኑን ሲልለቁ አንድ የሃምሳ አመት ቄስ ግን እምቢ አሉና ወዲያውኑ ተገደሉ። ከዚያም ቤተ ክርስቲያኑንና ቦታውን ጣልያኖች ተቆጣጠሩት። ሆኖም ክርስቲያን የሆኑ የጣሊያን ወታደሮች ‘ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብተን አንዋጋም’ በማለታቸው ክርስቲያን ያልሆኑ ወታደሮች እዚያ ገብተው ጦርነቱ ቀጠለ… በጣሊያኖቹ ወገን ከእንዳስላሴ የሚተኮሰው መድፍ ብዙ ኢትዮጵያውያንን ጨረሰ።
ይሄን ጊዜ ነበር እንግዲህ እንዲህ ተብሎ የተገጠመላቸው
"የአድዋ ሥላሴን ጠላት አረከሰው
ገበየሁ በሞቴ ግባና ቀድሰው"

““ ፊትአውራሪ ገበየሁ ደረታቸውን ሰጥተው የጠላትን ጦር መግቢያ መውጪያ በማሳጣት ሲተገትጉ፣ በጥይት ተመትተው ሞቱና እዚያው ምንድብዳብ ተቀበሩ፡፡

ፊታውራሪ ገበየሁ አባ ጎራው በጦርነቱ ላይ ሲሰዉ አጼ ምኒልክን ጨምሮ ብዙዎች አዘኑ። በዚህን ጊዜ ምኒልክንም ሆነ ህዝቡን ለማጽናናት፤ “ገበየሁ ቢሞትም ባልቻ አለልዎ” ለማለት ጭምር እንዲህ ተባለ።
"ገበየሁ ቢሞት፣ ተተካ ባልቻ፤
መድፍ አገላባጭ፣ ብቻ ለብቻ" ተብሎ ተፈከረ
በደጃዝማች ጦር ስር የነበሩትና ታላቅ ጀብድ የፈፀሙት ሌላኛው ጀግና ሊቀ መኳስ አባተ ቧያለው ናቸው፡፡
አንደኛዉ የጣልያን መድፍ አፈሙዝ ላይ አነጣጥረዉ ሲተኩሱ፣ መድፉ ለቅርስ እንኳ ሳይተርፍ እንክትክቱ ወጥቷል፡፡ በዚህም ምክንያት፣
‹‹አባተ አባ ይትረፍ-ነገረኛ ሰዉ
ይህን መድፍ ከዚያ መድፍ አቆራረጠዉ
አበሻ ጉድ አለ-ጣሊያን ወተወተ
ዓይነ-ጥሩ ተኳሽ!ቧያለዉአባተ፡፡›› ተብሎ ተገጠመላቸዉ፡
የኢትዮጵያ በሠላም ጊዜ ገበሬ በጦርነት ጊዜ ጀግና ተዋጊ እንጂ ዘመናዊ ወታደራዊ መሠረት ያለው Professional Army ባልነበራት በዚያ ዘመን ለአንድ መቶ ሃያ ሺህ ሠራዊት የሎጂስቲክ አገልግሎት እየሰጡ ለረጅም ጊዜ መቆየት አስቸጋሪ ነው፡፡ ስለዚህ የጀግንነት ግለት ሳይበርድ የሎጂስቲክ (ስንቅትጥቅመድሃኒት)አቅምሳይዳከምበፍጥነት ጦር መግጠም እጅግ አስፈላጊ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ሠራዊት ጦርነቱን ፈጥኖ ለመግጠም ጣሊያኖች ወደ አድዋ መምጣት አለባቸው፤ ወይም ደግሞ የእኛ ሠራዊት ጣሊያኖች ወደመሸጉበት የኤርትራ ከፍተኛ ቦታዎች መሄድ አለበት፡፡ ስለዚህ ጣሊያኖች ወደ አድዋ እንዲመጡ ማድረግ የግድ ሆነና የአድዋ ድል ቁልፍ የምላቸው የአርባ ዓመቱ ጐልማሣ ባሻዬ አውአሎም ሀረጐት ተጠሩና ለአንድ ታላቅ አገራዊ ኃላፊነት እንዲሠናዱ ተደረገ፡፡
ባሻ አውአሎም በኤርትራና በትግራይ የሚመላለሱ ነጋዴ ነበሩ፡፡ ቀደም ሲል ራስ አሉላ ኢጣሊያኖችን እየሰለሉ እንዲግሯቸው፣ የኢትዮጵያን ጦር ምስጢር ደግሞ አሳስተው እንዲጠቁሟቸው ከባሻ አውአሎም ጋር ተስማምተው ነበር፡፡ በሚቀጥሉት ቀናት አውአሎም ለኢጣሊያ ኮሎኒያሊስት ወራሪዎች ከሚሠልሉ የአገር ተወላጆች (ፌርማቶሪዎች)ጋርወደባራቴሪ ተላኩ፡፡ ከመሄዳቸው በፊት ስንቅ ማለቁና ተስቦ በሽታ በሠራዊቱ ውስጥ መግባቱ ፌርማቶሪዎች ባሉበት ተለፈፈ፡፡ አውአሎምና ፌርማቶሪዎቹ ወደ ኤርትራ ዘልቀው ለጄነራል ባራቴሪ ይሄንኑ ነገሩት፡፡
ባራቴሪ ጊዜው አሁን ነው አለና የካቲት 22 አመሻሽ ላይ በአውአሎም መሪነት ሠራዊቱን ይዞ ወደ አድዋ ተመመ፡፡ የካቲት 21 እንዳይነሣ ዝናብ ስለያዘው እንጂ ታላቁ ጦርነት የካቲት 22 ሊደረግ ይችል ነበር፡፡ ስለዚህ ጄነራል ባራቴሪ በዝናብ በመያዙ ምክንያት ዘመቻውን በማግሥቱ አደረገና የካቲት 22 ቀን 1888 ዓ.ምሌሊቱንሙሉሲጓዝ አድሮ ሊነጋ ሲል የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ምአድዋጦርግንባር ደረሠ፡፡ አውአሎም ከፊት ለፊታቸው የጀግናው የቱርክ ፓሻ የአፍሪቃ ጀኔራል አሉላ አባነጋ የገበሬ ሠራዊት ምሽግ እንደታያቸው መሮጥ ጀመሩ፡፡ ባራቴሪ፡- አውአሎም አውአሎም ብሎ ተጣራ፡፡ እስሀ ዝዋአልካዮ አያውለና ብለውት ዘለው አሉላ ምሽግ ውስጥ ገቡ፡፡ ዛሬ አንተን አያድርገኝ ማለታቸው ነው በአማርኛ፡- እስሀ ዝዋአልካዮ አያውለና፡፡
ከጥቂት ደቂቆች በኋላ ምድር ቁና የሆነችበት ድብልቅልቅ ያለው ጦርነት ተጀመረ፡፡ በዚህ ጊዜ እነ ራስ አሉላ በጀርባው ቆርጠው ገብተው መድፍ ሲተኩሱ ከአድዋ 10 ኪ.ሜወደኋላመሆኑን አርሞንዲ አያውቅም ነበር፡፡ ስለዚህ፣ ለተቀረው ጦር “ገብቻለሁ” ሲል በተመሳሳይ ሰዓት ከሦስቱም አቅጣጫ ተኩስ ተከፈተበት፡፡
የኢትዮጵያ ጀግና የገበሬ ሠራዊት ከጠዋቱ አራት ሠዓት ግድም ታላቁን የአድዋ ድል መቀዳጀቱን አረጋገጠ ፡፡ ብዙ ሺህ የኢጣሊያ ወታደሮች በጦር ሜዳ ተገደሉ፡፡ ብዙ ሺዎች ደግሞ ቁስለኛና ምርኮ ሆኑ፡፡ የተቀረውንና ድል ተመትቶ የተበታተነውን የኢጣሊያ ወታደር እያሣደደና እያባረረ አፍሪቃዊው ኃይል ፈጀው ፡፡
የዲፕሎማሲያዊ ድሉን የተቀዳጀችው ኢትዮጵያ፡- አውሮጳ ውስጥ ባስቀመጠቻቸው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ወላጅ አባት ራስ መኮንንና ግራዝማች ዮሴፍ በተሰኙ ዲፕሎማቶቿ አማካይነት ነው፡፡ ጣሊያኖች ኢትዮጵያውያን ያልሰለጠኑ በመሆናቸው በምርኮኞች ላይ ሠብአዊነት የጐደለው ድርጊት ይፈፅማሉ ብለው ያስወራሉ፡፡ ግራዝማች ዮሴፍ በተለያዩ ቋንቋዎች እየፃፈ ለአውሮጳ ጋዜጦች ይሄን ያስተባብላሉ፡፡ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ደግሞ ኢትዮጵያ ልክ ዲፕሎማቶቿ እንዳሉት ምርኮኞችን "ግብር አብልታ "አካላቸዉም ምቾታቸውም ሳይጓደል ወደ አገራቸው ሰደደች፡፡

በመቶ ሺህ የሚሠላ የኢትዮጵያ ገበሬ ሠራዊት ከአንድ ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የአውሮጳ ቅኝ ገዢ ወራሪዎችን ድባቅ ከመታና ረግጦ ካስወጣ በኋላ ከምሽቱ አራት ሰዓት ግድም (የካቲት23ቀን)እንዳማርያምላይተሰባስቦ በአንድ እግሩ ቆሞ ቀኙን (ድሉን)ለሰጠውአምላክምሥጋና አቅርቧል፡፡
"
አባት ሆይ፤ ንቀውን የመጡ የአገራችንን ድንበርና ልዕልና የደፈሩ የአውሮጳ ኮሎኒያሊስት ወራሪዎችን እንድናሸንፍ (ድልእንድናደርግ)ስለረዳኸንእናመሰግንሃለን..."
በጥቂቱየአድዋድልይህን ይመስላል፡፡
ክብር ክብር ክብር ክብር
ደም ከፍለው አጥንት ከስክሰው ሀገር እና ሀይማኖታቸውን ጠብቀው ቅድስቲቱን ሀገር ኢትዮጵያን ላወረሱን አባቶቻችን እና እናቶቻችን ይሁን፡፡

ዩርዳን

@wegoch
@wegoch
@gebriel_19
ሙሉ ንቃት



ሕልሞችሽ ላይ መንቃት ፥ በመካከላቸው መመላለስ ፥ በውስጣቸው መኖር እፈልጋለሁ፡፡
ድንቅ ሕልሞችሽ ላይ፡፡
እውንሽ ላይ ብቻ መኖሬ አይበቃኝም፡፡ያንሰኛል፡፡እውን ነጠላ ነው፡፡ሌጣ ኑረት፡፡ብዙ
አለመቻሎች ፥ በርካታ ጉድለቶች ፥ አያሌ እንከኖች አሉበት፡፡
በእውን እግር ተራማጅ እንጂ በራሪ አይደለም፡፡እግር ክንፍ አይደለም፡፡በእውን አይን
ከግድግዳ አልፎ ፥ ከመጋረጃ ጀርባ ፥ ከአድማስ ባሻገር ተሻግሮ አያይም፡፡የተከደነን ፥
የተዘጋን ፥ የታሸገን አልፎ በውስጥ ምን እንደሚገኝ አያይም፡፡ፊት ለፊቱ የተደቀነን ፥
የተገሰጠበትን ፥ ያልራቀውን ብቻ ነው የሚያየው፡፡
በእውን ጆሮ የራቀን አይሰማም፡፡ከትየለሌ የሚዜምን ጣፋጭ ማኅሌት አያደምጥም፡፡
ከሰባተኛው ሰማይ የሚመጣ የሚያድነው ቃል የእውን ጆሮ ጋር አይደርስም፡፡ያልተወራን
አይሰማም፡፡የእውን ጆሮ ከአጠገቡ የራቀን ድምፅ አይሰማ አይለማ፡፡
በእውን ልብ አይጨበጥም፡፡ከነአስደናቂ ፍቅሩና መሰጠቱ ፥ በእውን ልብ በመዳፍ
መካከል አይያዝም፡፡
በእውን አካል ከገለባ የቀለለ ፥ ከላባ የሳሳና የለሰለሰ አይሆንም፡፡አካል ጠጣርና ግዙፍ ነው
በእውን፡፡አካል ሲጠበድል ቋጥኝ ፥ ሲኮሰምን ጠጠር ነው በእውን፡፡ሲመቸው ትንቡክ ፥
ድሎት ሲርቀው ጋጥ ባይ ነው አካል በእውን፡፡
አየሽ.....
ለምን ሕልምሽ ላይ መንቃት እንደምፈልግ!?
ሕልም ብዙ የማይቻሉ ነገሮች የሚቻሉበት ነው፡፡በተለይ የእንዳንቺ አይነቷ ቆንጆ ሕልም
ሲሆን፡፡ራሱ ሕልሙ ይዋባል፡፡
< የቆንጆ ሕልም የተዋበ ነው፡፡ከቁንጅናዋ ወዘና ሩሑን ይጠነስሳል፡፡ከውበቷ ናሙና
ነፍስያውን ይቀምራል....> ይለኝ ነበረ ያ ቆንጆ አፍቃሪ ወዳጄ፡፡
የማፍቀር ቂልነቱ እንዲህ የሚያስብለውና የሚያሳስበው እየመሰለኝ እስቅበት ነበረ፡፡እሱ
አይስቅም፡፡ስለቆንጆው ሕልም ውብ መሆን ከልቡ ያወራል፡፡ቁም ነገር ብሎ ደጋግሞ
ስለውበታም ሕልም ደጋግሞ ይተርክልኝ ነበረ፡፡
እኔ እስቅበት ነበረ፡፡
ፍቅር እንዳጃጃለው አምን ነበረ፡፡
ጅል መሆኑን ደጋግሜ እነግረው ነበረ፡፡
አንድ ቀን እንዲህ አለኝ....
"እኩለ ቀንና እኩለ ለሊት ተጋቡ፡፡
እንደፋኖስና ብርጭቆ የድርሻ ፥ የድርሻ ጥምረት ፥ የኔ ይበልጥ ፥ ያንተ ያንስ አልነበረም
ውሕደቱ...
"ቀኑ እኩል...ለሊቱ እኩል...እኩል በእኩል ሲሆኑ ነው የተጋቡት፡፡
"እኩለ ቀን...እኩል ብርሃን ፥ እኩል ጨለማ አዛይ ነው፡፡
"እኩለ ለሊት....እኩል ጨለማ ፥ እኩል ቀን አቃፊ ነው፡፡
"እኩል በእኩል ነው ጋብቻው፡፡
"ሰምረት!!!
"አየህ....ይሔ ውብ ሕልም ነው፡፡ቆንጆ ያልሆነች አታየውም፡፡ይሔ ውብ ሕልም ፥ የቆንጆ
ሕልም ነው" አለኝ፡፡
በሕልሙ ሳኩኝ፡፡
በጅልነቱ አፌዝኩኝ፡፡
በነገረ ስራው ስላቄን ጠነሰስኩ፡፡
ዛሬ ግን ገባኝ፡፡ቆንጆ ሳፈቅር፡፡ነጠላ እውኗ ላይ ብቻ መገኘት እንደማይበቃኝ፡፡ውብ ሕልሟ
ላይ መንቃት እንዳለብኝ ገባኝ፡፡
ማነው ባለተራ!?
በኔ ማፍቀር የሚስቅ!?
ማነው ባለሳምንት!?
በኔ ጅልነት የሚንከተከት!?
የቆንጆ ሕልም ውብ ነው፡፡
እሱ ላይ መንቃትና መገኘትም ሙሉ ንቃት ነው፡፡ሙሉ ንቃት ሁሉን ቻይ መሆን ነው፡፡
ተአምርን እንደአክርማ መሰንጠቅ ነው፡፡መቻልን እንደጣሳ ውሃ በአንድ ትንፋሽ መጨለጥ
ነው፡፡
ይሄን ሁሉ ድንቅ ስጦታ ፍቅር ያመጣዋል፡፡በሙሉ ልቡ አፍቅሮ ፥ በፍቅሩ ምሕዋር የለቀቀ
ጅል የሆነ ሰው የሚሰጠው ስጦታ ነው ሙሉ ንቃ

((( ጆ ኒ ሀብቴ )))

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
#1
በአፄ ምኒልክ ጊዜ ምረቴ የሚባል አልቃሽ ነበር። አንድ አውዳመት ላይ ሰዎች ዳቦ
ይሰጡታል። ይሁንና ሌቦች ካስቀመጠበት ቦታ ወስደው በሉበት ። በዚህ ጊዜ ሁኔታውን
የሰሙ መጥተው “እከሌ ቤት ብታስቀምጠው ኖሮ አትሰረቅም ነበር።” እያሉ ይመክሩት
ጀመረ። በዚህን ጊዜ ምረቴ እንዲህ አለ፦
ከመከራ ኋላ ምክር መገኘቱ
ዳቦዬ ተበላ አበላለ ከንቱ!😢
#2
በአንድ ወቅት ደብረሊባኖስ ሁለት መነኮሳት ወደሴት ሄዳችኋል ተብለው ተከሰው ቀረቡ።
ይሁንና ከተከሳሾቹ አንዱ ሕጹብ (ስልብ) ነበሩና ወደተከሳሽ ጓደኛው እየተመለከቱ፦
“እርሳቸውስ እሺ፣ እኔ ምን አድርገሃል ተብዬ ነው የተከሰስኩት?” አሉ።
በዚህን ጊዜ ጉዳዩን ሲከታተሉ ከነበሩ አባቶች አንዱ እንዲህ ተናገሩ፦
“ይተዉ እባክዎ፤ እርስዎም አፍዎ አያርፍም” ( )😜😜

#3
ጥያቄ፦ ከዚህ በላይ ያሉት ሁለት ታሪኮችን አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ምንድነው?
መልስ፦ ዳቦ😊

ሸጋ ቀን!!💚💛

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
የካራ_ማራ_ጦርነት ( ኢትዮ - ሶማሌ ጦርነት )

የካቲት 26 / 1970 ዓ.ም
" የኢትዮ-ሶማሊ ጦርነት ተብሎ የሚታወቀው የኦጋዴን ጦርነት ከሶማሌ ዲሞክራቲክ ሪፖብሊክ ጋር በ1969 ዓ.ም ተጀምሮ የካቲት 26/1970 ዓ.ም የተጠናቀቀው ጦርነት ነው፡፡

መጀመሪያ.በሶቪዬት ህብረት ቀጥሎም በ ዩናይትድ ስቴትስ ድጋፍ ኢትዮጵያን የወረረው የሰይድ ባሬ (ዚያድባሬ) ጦር ‹‹የእናት ሀገር ጥሪ›› እያለ ከመላው የኢትዮጵያ ምድር በተሰባበሰበ
ጀግናው የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ድባቅ ተመታ፡፡

ዚያድ ባሬ የካቲት 26፣ 1970 ዓ.ም የኢትዮጵያን ምድር ዘልቆ በመውረሩ፣
የኢትዮጵያ ጦር በመልሶ ማጥቃት በአየርና በምድር # ካራማራ ተራራ ላይ ከባድ ውጊያ አካሄደ፡፡

የሶማሊያን የአየር ክልል ጭምር ዘልቆ በመግባት የኢትዮጵያ የጦር ጀቶች ማሰስና ማደባየት ቻሉ ።

ዓለምም ጭምር ሶማሊያን ማገዝ አይደለም ስለ ሶማሊያ ነጋሪ እስኪጠፋው ወደመች ።

የሶማሊያ ብሄራዊ ጦር ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ አደጋ ውስጥ ወደቀ ተራራዎቹ ሁሉ በምድር በካርቤል እና እና ቢየም ሮኬቶችና መካከለኛ
ርቀት ተተኳሽ ሚሳዮሎች ከሰማይ ደግሞ የአውሮፕላን ሮኬቶችና ቦንቦች ካራማራ ተራራ ላይ ዶፍ ወረደባት ፤ ከምድር እሳተገሞራ የፈነዳባት መሰለች ።

ከዚያም የኢትዮጵያ ጦር ጅግጅጋን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረ፡፡ ከ አራት ቀናት በኋላ ሁኔታው ያስፈራው ሰይድ ባሬ ፣ የሶማሊያ ሰራዊት የኢትዮጵያን
ምድር ሙሉ በሙሉ ለቆ እንዲወጣ ጥሪ አስተላለፈ፡፡

ኢትዮጵያውያንም በድል ተመለሱ፡፡ በጦርነቱ ኩባ ፣ ደቡብ የመን ፣ ምስራቅ ጀርመንን የመሳሰሉ አገሮች ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የጦር ድጋፍ አድርገዋል፤ ከ 16,000 በላይ የኩባ ወታደሮችም የታሪኩ ተካፋይ ናቸው፡፡ " ታላቋ ሶማሊያም" ፈራረሰች፡፡

የዚያድባሬ የመጨረሻ ቃልም ‹‹ Nothing is permanent on this
world’’ በሚል ተቋጨ፡፡ "

" ክብር የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ለማስከበር ደማቸውን ላፈሰሱ
የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰራዊት አባላት ። "

ምንጭ ፦
Office of the Prime Minister-Ethiopia /Abiy Ahmed's Speech

💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

ምንጭ:-....የታሪክ-ድርሳናት...የቴሌግራም ቻናል የተወሰደ


ከሶማሌ ወረራ ነፃ ለማውጣት 150 ሺህ የኢትዮጵያ ወጣቶች አልቀዋል።

ክብር ለጀግኖቹ ሰማዕታት!!!!💚💛

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ተቃርኖ



ወጥቷል፡፡
ወደዓለም፡፡ለዓለም፡፡
ሊኖር ነው፡፡
ከዓለመኞች ጋር፡፡
ዓለመኞች ቆንጆ መሳይ ናቸው፡፡ተጣዳፊዎች፡፡ለሁሉ የሚሮጡ፡፡የሞላላቸው መሳዮች ግን
በማብቂያው ፥ ምንም ያልያዙ መናጢዎች፡፡
ያፈቅራሉ፡፡
ቸኩለው ልብ ይሰጣሉ፡፡ተጣድፈው ሁሉን ተሰጣጥተው ይጨርሳሉ፡፡በንጥቀት ይሰለቻቻሉ፡፡
ደሞ ወደሌላ ይሮጣሉ፡፡መሬት ላይ ይሮጣሉ፡፡አልጋ ላይ ይሮጣሉ፡፡አየር ላይ ይሮጣሉ፡፡ፍቅር
ላይ ፥ ጥላቻ ላይ ይሮጣሉ፡፡ሳቅ እንባ ላይ ይሮጣሉ፡፡
ሁሉ ላይ ይሮጣሉ፡፡ረግተው ካየሀቸው ለሌላ እሩጫ እያደቡ እንጂ እርጋታን አውቀውት
አይደለም፡፡በዚህ ሁሉ ጥድፈታቸው ውሸታሞች ፥ ቀጣፊዎች ፥ አጭበርባሪዎች ሆነው
ይታዩታል፡፡
"አትሩጥ፡፡ለምንም ነገር አትፍጠን፡፡ያንተ ያንተ ነው፡፡ላንተ ያለው እንጀራ ሻግቶ ይወድቃል
እንጂ ማንም አይበላው" ይለው ነበረ እረኛ እያለ የሚያግደው በጉ፡፡
የታደለ ረኛ ነበረ፡፡የሚያወራ በግ የነበረው፡፡ይሄ ከሚሊዮን እረኛ አንዱ ብቻ የሚያገኘው
እጣ ነው፡፡ወርቅ እንቁላል እንደምትጥለው ዶሮ ነው ይሄ በግ፡፡አይገኝም፡፡ሲገኝም በዘመን
አንዴ ነው፡፡
አዋቂ ነው፡፡ልሳን አለው፡፡የጣፈጠ አንደበቱ እውቀቱን አሳምሮ ይናገራል፡፡
" ዛሬ ዛሬ ሁሉ ይሮጣል፡፡አንተ ግን ዝግ በል፡፡የሮጠውን ያህል ማንም አያገኝም፡፡
በማብቂያው ሁሉ በሮጠው መጠን እርካታ የለውም....." ይለዋል ተናጋሪ በጉ፡፡
" እኔና አንተ ያለነው እልም ያለ ገጠር ፥ ለምን ስለከተሜው ታወራኛለህ?የት
ታውቀዋለህ?"
ሳቅ ይልና " ዝም ብዬ የምታረድ በግ አልምሰልህ፡፡እሱ የአብርሐም በግ ነው፡፡እኔ
ብታረድም አዋቂ በግ ነኝ " ይለዋል፡፡
" እሺ ይሄ ወሬ ለኔ ምን ይረባኛል!?"
"ቀንህ ሲደርስ ከተሜ ነህ፡፡በጊዜህ ከተሜኛ ነህ፡፡ለዛ ጊዜ የሚሆንህን ነው ዛሬ
የምነግርህ፡፡"
ወጥቷል፡፡
ያየው ደነቀው፡፡ግራ ገባው፡፡
ይሄ ሕይወት እንቀልፍ አልባ ነው፡፡ንቃት ግን የለውም፡፡ረፍት አልባ ነው፡፡ስራው ግን
አጥጋቢ አይደለም፡፡ይኳኳላል፡፡ግን ውብ አይደለም፡፡ያነጣጥራል፡፡ኢላማ ግን ይስታል፡፡
ደስተኛ ነኝ ይላል፡፡ግን ብስክስክ ብሶቱን ታቅፎ ነዋሪ ነው፡፡ይብለጨለጫል፡፡ግን
አያበራም፡፡
መጥታ ያቀፈችው ማን ነበረች!?
አዎ!!
ሔርሜላ ነች፡፡
ብዙ ሳቅ ያላት ሔርሜላ፡፡ብዙ ድምፅ ፥ ምንም ዝምታ የሌላት ሔርሜላ፡፡እየሳቀች እዛው
የምታለቅስ፡፡እኩል በእኩል ሳቋም እንባዋም የበዙ፡፡
እንዴት ወደሱ መጣች!?
ከየት ወደሱ መጣች!?
ለምን እሱን አቀፈችው!?
ሁሉ ተሳከረበት፡፡ብብብብብብብብዥዥዥዥዥዥዥዥዥዥዥዥዥ ያለ ሆነበት፡፡አልጠራ
ያለ መደፍረስ፡፡አያጥቡት ግን የሁሌ ጭቃ፡፡ተወቅጦ የላመ ፥ የደቀቀ ውሃ፡፡
" የኔ ፍቅር !?" አለች ሔርሜላ፡፡
እ!?
" ወይዬ " አለ እሱም፡፡
እ!?
" ልሄድ ነው በቃ፡፡ "
ከአይኑ የእንባ ኳሶች አንከባለለ፡፡ጉንጩን አብዶ ሰርቶ ፥ አፍንጫውን በሎጬ አታልሎ ፥
ሪዙን አብዶ ሰርቶ የእንባ ኳሶቹን ቁልቁል ወደመሬት ጎሉ በሹት ጠለዘው፡፡
" እሺ በቃ ሂጂ " አለ እንደምንም ብሎ፡፡
መቼ መጥታ!?
መቼ ልትሄድ!?
አሁን አቀፈችው አልተባለም እንዴ!?
አሁን ሳቀች ሲባል አልነበረ እንዴ!?
ምን ጉድ ነው ይሄ!?
እያለቀሰ ፥ እያለቀሰች ተቋጨች፡፡አከተመች፡፡ተቋጩ፡፡አከተሙ፡፡
" አለህልኝ የኔ ፍቅር!?" እያለች ከንፈሯን ከንፈሩ ላይ አተመች፡፡
" የኔ ኮኪዬ " አለ ከንፈሯን እያጣጣመ፡፡
ኮኪ ማን ነች ደሞ!?
የኔ የኔ ከተባባሉ የእነሱ የራሳቸው ናቸው፡፡እሱ የእሷ ፥ እሷ የእሱ፡፡
ፍቅረኛሞች ናቸው፡፡
ሽቅርቅር ያለች፡፡የሽቅርቅሯ መርቀቅ ከአጠገቧ ያለን ሁሉ አፈር ድሜ አስበልቶ የሚያስረሳ፡፡
ሁሉ ነገሯ አይን ይጠራል፡፡አይን ማራኪ ጀግና መሽቀርቅር ፥ አይን ጎታች ማግኔት
መሽቀርቀር ፥ አይን ጋባዥ ለጋስ መሽቀርቀር ነው ያላት፡፡
ያያት ሁሉ ይስቃል፡፡እሷን እያየ አብሯት ያለን ይረሳል፡፡ሲያያት ይደሰታል፡፡ከተሜ ቅብ ደስታ፡፡
ጥድፊያ ውስዋስ ደስታ፡፡
" በጣም ነው የማዝነው የኔ ፍቅር፡፡"
" ይገባኛል፡፡"
" ግዴታ ስለሆነብኝ ነው፡፡መሄድ አለብኝ፡፡"
የእንባ ኳሱ.....የለቅሶ ግጥሚያው....የእንባ ሊጉ.....የዚህ ዘመኑ ውድድር ኮኪ ነበረች፡፡
የመለየት ዋንጫውን አብልታውና ሸልማው ሄደች፡፡
ያ በጉ ታውሰው፡፡ሊያወራው ፈለገ፡፡
እንዲህ አይነት ወሬ....
"የማዝነው...
ክፉዎች ባሸነፉበት ዓለም ላይ በመኖሬ አይደለም!!!
"ቅዱሳኖቹ ተለይተው ስላልታወቁ እንጂ!!!
የሚከፋኝ...
"ዋናው እርኩስ ታውቆ ፥ ታላቁ ቅዱስ በማይታወቅበት ዓለም ላይ ስላለሁ ነው
የሚያስጠላኝ...
"እኔ ለማን ፥ ማን ለኔ እንደቆምን አለማወቃችን ነው...." ሊለው ፈለገ፡፡
ግን አይለውም፡፡ሊለው አይችልም፡፡ሰንቆታላ፡፡ከገጠር ወደከተማ ሲገባ፡፡
" እረደኝ፡፡ግን ፈጥነህ አትግፈፈኝ፡፡ቃሌን ለማቋረጥ በጥድፊያ ካራ አትሳል...." እያለው
ከሚሊዮን አንድ እጣውን በፈጥነት ፈጣጥሞት ከተማ መግቢያ ስንቁ አድርጎታል፡፡
ምን አይነት ዓለም ላይ ነው የወጣው!?
ሰውዬው ከእንስሳው የሚያንስበት ፥ እረኛውን ከብቱ በሚያግድበት ፥ ጠባቂውን
ተጠባቂው ተግቶ ዘብ የሚቆምለት ዓለም ላይ ነው የወጣው፡፡

((( ጆ ኒ )))💚💛

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
"ዛሬ ዛሬ ሙሉ በሙሉ የተረዳሁት የሐበሾች ስር ነቀልነት መሠረቱ ስሜት መሆኑ ነው፡፡
ከዐሥረኛ ፎቅ እጅ ለእጅ ተያይዘው ሆሆሆ ብለው እርስ በርስ ተነዳድተው ይወድቃሉ፡፡
ለነሱ ዋናው ጉዳይ መውደቁ ሳይሆን ከፋም ለማም እጅ ለእጅ መያያዙ ነው፡፡ በሰው
የደረሰው ቢደርስባቸው ስህተት አይደለም።
ማሰብ የሚጀምሩት በመዋግደ ሕሊና ግፊት በመውደቅ ጎዳና ላይ ስምንተኛ ፎቅ ሲደርሱ
ነው፡፡ ወዴት እየሄድን ነው? ፓራሹት ይዘሀል ወይ? ይባባላሉ፡፡
ከአምስተኛ ፎቅ ጀምሮ ወሬያቸው ጭቅጭቅና ፀፀት ነው፡፡ እስከ ዜሮ ፎቅ ያለው ጉዞ
በጸሎት የታጠረ ምሬት ነው፡፡ በየደጀሰላሙ መንበርከክ ነው፤ ነጫጭ ለብሶ በኪራላይሶ
መንደድ ነው፤ ለ'ተለመነኝ' በሚያጤሱት ዕጣን መታፈን ነው፤ እዝጌር በምሬት
ይገጠምበታል፤ የሚረገም ይረገማል፤ ስለት ይገባል፤ ጥንቆላ ይጠነቆላል፤ የሚታማ ማሰስ
ነው። እጃቸውን የያዘውን ደባል ዘላያቸውን መርገም ነው፡፡ ወደ ኋላ እየተመለሱ
በአጀማመራቸው ማሳበብ ነው፡፡ መሬት ወድቀው በትዕንግርት ከመሰባበርና ከመሞት ቢድኑ
፤ የአወዳደቃቸውን ዚቅ ሊያርሙ እንደገና ከሌላ ሰው ጋር ተያይዘው ወደ ፎቁ ይወጣሉ፡፡
ስህተቱ መውደቁ ሳይሆን አወዳደቃቸው ይመስላቸዋል፡፡"

አዳም ረታ
# የስንብት_ቀለማት

ሸጋው ቀን!!💚💛

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ፈላስፈው እና ደራሲው ካህሊል ጅብራን:-"አንዱ ሰው በውስጡ ሁለት ሰዎችን ነው፤አንዱ በብርሃን ሲተኛ ሌላው በጨለማ ይነቃል" አለ። በዛሬዋ ኢትዮጵያ የብዙዎች ማንነት እንዲሁ መስሏል።😊😊

@wegoch
@wegoch
በጥንት ዘመን አንድ ንጉሥ ለህዝቡ የሚጠቅም ህግ ማውጣትን አሰበና ከ'የ ግዛቱ ጠቢባን የተባሉ አንድ ሺህ ሰዎች በቤተ መንግስቱ ሰበሰበ።እያንዳዳቸውንም ለሀገር ይጠቅማል የሚሉትን ህግ አርቅቀው እንዲያቀርቡለት አዘዘ። የጠቢባኑ ህግ ተረቅቆ በንጉሱ ፊት ሲቀርብ ግን፣እጅግ አዘነ፤አምርሮ አለቀሰ።በተረቀቀው ህግ አዝኖ መስሏቸውም ሊያፅናኑት ሲጠጉት:-"የለም፣እኔ ያሳዘነኝ ያረቀቃቹት አንድ ሺህ ህግ ሳይሆን፣በሀገሬ አንድ ሺህ ዓይነት ወንጀል መኖሩን እስከዛሬ አለማወቄ ነው:" አላቸው።

ንጉሱ በመቀጠል የጠቢባኑን አንድ ሺህ ህግ ከፊቱ አስነሳ በምትኩምእሱ ያዘጋጃቸው ሰባት ህጎች ለሕዝቡ በቂ ናቸው አለ። በዚህ ጊዜ ጠቢባኑ ተቆጡ:-"እኛን ያደከመን በከንቱ ነውን?!" አሉ። ወደ ግዛታቸው ተመልሰው የእነሱን ህግ ሕዝቡ እንዲከተል አሳመኑ። በዚያች ታላቅ ሀገር ዛሬ አንድ ሺህ ህጎችን የጣሱ ወንዶች እና ሴቶች የሞሉባቸው አንድ ሺህ አስር ቤቶች ይገኛሉ።

እርግጥ ነው ሀገሪቱ ዛሬም ታላቅ ነች፤ነገር ግን፣ህዝቡ የአንድ ሺህ ህግ አውጪዎች እና የአንድ ንጉስ ተከታይ ሆኖ ቀርቷል።

የእኛ እምነት "ሰው" አያውቅም። ዛሬ በኢትዮጵያ የአማኝ እንጂ የእምነት ተቋማት ችግር የለም። የእኛ አማኝ በጥላቻ፣በነቀፌታ፣እና በራስ ፍቅር የተጠመደ ነው። ለእኛ ሀገር አማኝ "ሰው" መሆንህን ብቻ አይበቃውም። እሱ የሚያምነውን ማመን፣እሱ የሚከተለውን መከተል፣የእሱን ቋንቋ መናገር ካልቻልክ፣"ሰው"ብቻ ብትሆን፣ምን ያደርግለታል?የቱንም ያህል ጥሩ እና በጎ አድራጊ ሰው ልትሆን ትችላለህ፤እንደ'ምትከተለው ሃይማኖት የሰማይ ዋጋህን በ'የ ጓዳቸው ይወስኑልሃል፣እንጂ፣በአንተ አይቀኑም። በአደባባይ ደግሞ "ተቻችሎ የመኖር ባህል"ይሉታል። ሰውን እንደ "ሰው"በእኩልነት የሚመለከት እምነት ቢኖረንማ፣ተቻችሎ መኖር ቀድሞውንም ባልተደሰኮረ ነበር።

በመጨረሻም እንዲህ እላለሁ:-"ማንም ሰው ጌታው እንዲሆን የማይፈቅድ እና እሱም የማንም ሰው ጌታ መሆን የማይሻ በእርግጥ እሱ ታላቅ ሰው ነው!"

👆👆👆👆👆በተለይ ይችን ነገር በደንብ ያዙልኝ....
💚❤️💛💚❤️💛💚💛❤️💚💛❤️

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ለውብ ቀን
💚💚💚💚
ከሱፊዝም የእምነትና የሕይወት ፍልስፍናና ስንጨልፍ ለጁመዐችን አል-ጋኽዛሊ ስለ ፍቅር
የተናገሩትን እናገኛለን፦
የፍቅር መኖሪያው ልባችን ነው። ፍቅር ልዩና የሚያስደስት ስቃይ የተሞላ የፈጣሪ ስጦታ
ነው። ፍቅርን በልቡ ተሸክሞ የሚዞር እሱ ሚስጥሩን ለማወቅም የሚቸግረው አይሆንም።
ፍቅርን ስትሸከም ነገር ሁሉ ለአንተ እዉነትና ወደእውነት ብቻ የሚወስድ ይሆናል።
በፍቅር ውስጥ ከእውነት በቀር ሌላ ነገር የለም። ለዚህም ነው አፍቃሪዎች በእውነት ባህር
እየተሸነፉ ሲሰምጡ የምናየው።


ሸጋ ጁመኣ!!💚💛

@wegoch
@wegoch
@balmbars
??????????
--------
ጦርነትን ለመጥላት በጦርነት ጠፍቶ ማወቅን አይሻም። ጦርነት ጦር የመስበቅን ያክል
ቀላል አደይደለም። ሰላም፣ እኩልነትና ፍትህን እንደ ህዝብ እርስ በእርስ በመጫረስ አንተ
ብቻ አታገኛቸውም።
-----
ዛሬ ትግሉን ያሸነፈ የሚመስለው ጦረኛ ሁሉ በእውነት በትልቅ የውድቀት መንገድ ላይ
ነው። አዎ፣ የነጻነት ብርሃኑ ልክ ነበር!! ላየንው፣ ለሰማንውና ለኖርንው አንጻራዊ ነጻነት
እውቅና እንሰጣለን። ግን ደግሞ ለአቅመ- ዲሞክራሲ ያልደረሰ ሰፊ ቀለም ጨላጭ
ተማርኩ ባይ ማይም በዚህች አገር አእላፍ መሆኑንም በውል ተገንዝበናል።
አዎ በህዝባዊ የፖለቲካ ትግል ወድቆ የመቅረት እንጂ ወድቆ የመነሳትና የማሸነፍ የስኬት
ታሪክ አልነበረንምና ዳግም ልንገነደስ አፋፍ ላይ ነን።
--------
ተስፋ አደርጋለሁ፥ ደም ያላጠባት፣ የከረፋ የመጠፋፋት ታሪክ የማይጣፍባት የልጆቼ አገር
ኢትዮጵያ ከህመሟ ትፈወስ ይሆናል። ለምን ቢባል፣ ምንም ስለማያውቀው መልካም
ህዝብ፣ ስለሚያሳሱ እንቡጥ ህጻናትና እናቶች ሰላምና ጸሎት ሲባል ባቻ። አዎ፣ የክፉዎች
መንገድና የሻጥረኞች ሴራ ይከስማል!!
----------
# የተደመርኩት ስላየሁት መልካም ብርሃንና የሰውነት መንገድ ነው፥ አልተሳሳትኩምም!!
ያሸነፉ የሚመስላቸው ደቂቃን-ኦነጎች፣ የጦርነት ነጋሪት ጎሳሚ እፍኝቶች፥ ቧልትንና
ፖለቲካን ቀላቅለው የሚያኝኩ የዋሆች ህልማቸው ቅዥት ነው!!

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
2024/09/28 13:23:39
Back to Top
HTML Embed Code: