Telegram Web Link
ከንፈርሽ ያምራል ማለት ልሳምሽ ማለት ይሆን?
ስማ የላኩልህን የጓደኝነት ጥያቄ ቶሎ ባትመልስ ኖሮ እሰርዘው ነበር ግን እንኳን
ተቀበልከኝ። እኔም እኮ ቆንጆ ሴቶችን የመግፋት ስነልቦና የለኝም ....ቢሆንም ተርፈሀል።
ያው የምትፅፋቸው ነገሮች ያዝናኑኛል አንዳንዶቹ አይገቡኝም...አንዳንዶቹማ እኔንም
አይገቡኝም ግን አብረን ለመረዳት እንሞክራለን ያው አብረን ስል ለማቅረብ እየሞከርኩ
እንደሆነ ይታወቅልኝ።አንድ ቀን እኮ በአካል ከአንድ ወዳጄጋ አንድ ቴብል ላይ ቁጭ ብላ
እጄን ጨብጣለች እኔ ቡና ስጠጣ እሷ ምን እንደጠጣች እኔንጃ ከንፈሯን እንጂ የያዘችውን
አላየሁም ነበር አሁን ስጠይቃት እሷም አታውቀውም እኔን እያየች ነበር ይሆን? የዛኔ
ዝምተኛ ትመስል ነበር እኮ ...ከማከብረው ሰው አጠገብ ነበር የተቀመጠችው ለዛ ነው
ዝምታዬ የታያት እኔኮ ዝም የምለው በእንቅልፍ ልቤ ነው እሱም ስላልተቀረፀ ነው።
ያቺ ጓደኛህስ የት
ሄደች? አብረን አይደለንም እንጂ አለች አልኳት በምን ተለያያቹ?ሴት መንከባከብ
አትችልም በሚል ተልካሻ ምክንያት አልኳት።ምን አለቺኝ መሰለሽ በፍቅር እንጂ በፍልስፍና
አይኖርም። ብትረዳው እኮ ፍልስፍና ውስጥ ብዙ ፍቅር አለ ቆይ ግን
ያልገባን፣ያልተረዳነው፣ያልደረስንበት ነገር ሁሉ ፍልስፍና ነው? በአንዳንድ ሴቶች ፍቅር
መስጠት ማለት አንድ ቺብስ አንስተሽ ካቻብ አስነክተሽ ማጉረስ ይሄ ነው እንክብካቤ? በሯ
ላይ ያደረስሻትን ልጅ በሰላም ገባሽ ወይ ማለት ነው እንክብካቤ? ቤታቸው ምሽግ ነው
እንዴ? ማነች ደሞ እቺ አሁን የምታወራላት ለምትሉ በሚቀጥለው ቻፕተር ታገኟታላቹ።

ሰላም እደሩልኝ!!💚💛❤️

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ቀይ ለባሾቹ……

ዛሬ ከቢሮዬ አርፍጄ ነበር የወጣሁት ። በጠዋት መግባት ነው እንጂ ሊሳካልኝ
ያልቻለው አምሽቶ መስራት ልምዴ ነው። ዛሬ ግን ብቻዬን አላመሸሁም ነበር
ያለልምዷ ፀሃፊዬም አምሽታለች። ለወትሮ መውጫ ሰአቷን ለደቂቃ እንኳን
አሳልፋ አታውቅም ከሰራተኛ ሁሉ ፈጥና የምትወጣው እሷ ናት ፣ የኋላ የኋላ
ስሰማ ባል ተብየው ሁሌ ሰአቷን ጠብቆ በር ላይ እንደሚጠብቃት ሰማሁ። ዛሬ
ግን አምሽታ ሳያት ተጣልተው መሰለኝ ። በዛ ላይ በጣም አምሮባታል…….ከላይ
ያረገቻት ቀይ ቢጢሌ ቀያይ ጡቶቿን አንሳፈዋቸዋል…..ወንድ ልጅ መቼም እውር
ካልሆነ በቀር ምንም አይነት ጠንካራ እና ግትር ቢሆን እንኳን አይኖቹን መግታት
አይችልም ። ዛሬ ግን ለምን እንደሆነ ባለውቅም ተለየችብኝ አዘውትራ ነጭ ልብስ
ስለምትለብስ ነው መሰለኝ ዛሬ ቀይልብስ አድርጋ ሳያት ልዩ ሆነችብኝ። ከስር
ያረገችውም ቀይ መሆኑን ያቅኩት ከወንበሯ ተነስታ ስትቆም ነበር . የወገቧ
ቅጥነት እና የዳሌዋ ስፋት ቀይ በቀይ ሆነው ልክ እንደ ኤድስ ሪቫን ተቆላልፈዋል.
ሰአቱ ይበልጥ እየመሸ ነው ። እኔ የራሴ ቢሮዬ ውስጥ ተቀምጫለው ….ቀጥሎ
ካለው ቢሮ ፀሃፊዬ ብቻዋን ተቀምጣለች ….ስራ አንዳልስቆያት እርግጠኛ ነኝ…
ከባሏ ብትጣላ ነው ያመሸችው ስል ገመትኩኝ…ደሞ ሴቶች ከባሎቻቸው ጋር
ሲጣሉ ለምን መዘነጥ እንደሚወዱ አላውቅም በእነሱ ቤት ማስቀናታቸው ነው
…..ፀሃፊዬም ዛሬ ባሏን ለማስቀናት ከመዘነጧ አልፎ ሌላ ቦታ እንዳመሸች አርጋ
ባሏን ለማቃጠል ቢሮዋ ተቀምጣለች….ሃሳቤን ሰረቀችው…..ቢሮዬን አልፌ
ቢሮዋ ስደርስ መስታወት ይዛ ፊቷን ስትመለከት አገኘኋት ሳታስበው ስለገባሁባት
ደነገጠች….ፈገግ ስል እሷም የእፍረት የሚመስል ፈገግታ አሳየችኝ….ይመስለኛል
ከመልኳ ጋር በእልህ እያወራች ነበር። አይ ሴት በመልካቸው ሲመኩ እኮ ….መልክ
ለፈረስም አልጠቀማትም አለች አያቴ.

“ዛሬ ስራ በዛ እንዴ?” አልኳት ጠረንቤዛዋ ላይ እየተቀመጥኩኝ
“አይ ስራ እንኳን አልበዛም ትንሽ ማምሸት ፈልጌ ነው” አለችኝ ቀይ የተቀቡት
ከንፈሮቿ የጥርሷን ንጣት አጉልተውታል …..ዛሬ ባጠቃላይ ቀይ ሆና ተውባለች
“በሰላም ነው ? ሌላ ቀን ከሁሉ ቀድመሽ የምትወጪው አንቺነሽ፣ እንደውም
እንዳወጣጥሽ አገባብሽ ቢያምር ኖሮ እስካሁን የሁላችንም አለቃ በሆንሽ ነበር”
ስላት ሳቀች ዛሬ ምንድን ነው? አሳሳቁዋ እንኳን ተለየብኝ ለነገሩ ከዚህ በፊት
ብዙም ንግግር አልነበረንም …..ስለዚህ አስተውዬ አይቻት ስለማላውቅ ይሆናል.
“ማን ነው ያለው?”
“ሁሉም የቢሮ ሰው ያማሻል……ዛሬ ግን እኔም ገርሞኛል…ሁሌ ብቻዬን
ስለማመሽ” አልኳት
“ሁሌ ለምን ታመሻለህ?”

“በጊዜ ቤት መግባት አልወድም በጊዜም መጠጥ ቤት መሄድም አልወድም…..
ግዴታ ከሁለት አንዱ ጋር ነው የምሄደው ፣ ሁለቱም ደግሞ በጊዜ የሚኬድባቸው
አይደሉም …….. የግድ ማምሸት አለብኝ”
ሳቀች እሷ ግን ዛሬ ያለወትሮዋ ለምን እንዳመሸች ጠየቅኳት መልሷን ለመስማት
ጓጉቻለው ያቃጠላት ባሏን ለመበቀል እንደሆነ ስትነግረኝ በቃ አይዞሽ ትንሽ ዘና
በይ ብዬ ይዣት ለመውጣት አሰብኩኝ…..እሾህን በሾህ አይደል።መለሷ ግን
ለምን እንደሆነ አላውቅም አስደነገጠኝ
“ዛሬ እኮ ቫለንታይንስ ዴይ ነው……ከጓደኛዬ ጋር ማታ ነው ቀጠሮዋችን….ስለዚህ
ቤት አምሽቼ ከምወጣ እዚሁ አምሽቼ ላግኘው ብዬ ነው” አለችኝ። ለካ የእኛ
ሙሽሪት ቀይ በቀይ የተበሰው ለቫለንታይን ቀን መሆኑ ነው……ፀሃፍዬን ውጪ
የማግኘት አላማው ኖሮኝ ባያውቅም ዛሬ ግን ሳላስበው …..የሆነ ነገር ተሰምቶኝ
ነበር…..ለነገሩ ግልብ ስሜት እንደሆነ ጥርጥር የለኝም….ምክንያቱም ከዚህ በኋላ
ለሴት የምሰጠው እንጥፍጣፊ ስሜት የለኝም.
ጠረንጴዛዋ ላይ እንደተቀመጥኩኝ ስልክ ተደወለላት
“ደረስክ ….በቃ መጣሁ…መጣሁ” ብላ ስልኩን ዘጋችው
“በቃ መሄዴ ነው …አንተ ብዙ ትቆያለህ?” አለችኝ
“አይ ……ትንሽ” አለኳት……ከሄደች በሁላ ቢሮዬ ገብቼ በመስኮት
ተመለከትኳት……ቀዩዋ ሙሽራ አስፋልቱን ተሻግራ መኪና ውስጥ ስትገባ
አየሁዋት……ተሳሳሙ

ዛሬ ቫለንታይን ቀን ነው ማለት ነው?…..አልኩኝ አይምሮዬ ፍቅር ነክ የሆኑ ነገሮችን
ሁሉ እየረሳ መጥታል….ከመስኮቱ ሳልንቀሳቀስ….ሁለት ጥንዶች የአስፓልቱን
ጠርዝ ይዘው ሲጓዙ ተመለከትኳቸው….ሴቲቱ ቀይ ለብሳለች……..አሃ ቫለንታይን!!!

ብዙም ሳልቆይ ቢሮዬን ለቅቄ ወጣሁኝ……ሀሳቤ ሲናወጥ ተሰማኝ…..የቀበርኩትን
ጉድ ሁሉ ቀይ ለባሾቹ ቆፈሩብኝ….ህመም ለቀቁብኝ…..ወደማዘወትረው መጠጥ
ቤት ስደርስ……ሁሉ ተለዋውጦ ጠበቀኝ
በየጠረቤዛው ቀያይ አበቦች ተቀምጠዋል…ጥንዶች ይበዛሉ….ቤቱ አንደሌላው
ጊዜ ሞቅ ሞቅ ያለ ሙዚቃ አልተከፈተበትም….ቀዝቃዛ
ዘፈኖች….ይከታተላሉ….ቢራዬን አዘዤ ዙሪያዬን ማስተዋል ጀመርኩኝ……ብዙ ቀይ
ለባሾች ቤቱን ሞልተዋል…..ጥንዶቹ ሁሉ እንደድራማ ሰሪ እንቅስቃሴያቸው
በጥንቃቄ ነበር…..እጆቻቸውን ሲያቆላልፉ…መልሰው ሲላቀቁ….ስደባበሱ…
ሲነጋገሩ …..እየተጠባበቁ ሲሳሳቁ….ሳቄ መጣ….እነባዬም ሳቄን ተከትሎ መጣ…
ቀይ ለባሾቹ ዛሬ ቁስሌን ቀሰቀሱብኝ….ቀይ ነገር ጠላሁኝ ….ቀይ ሽብር ሁሉ ትዝ
አለኝ…ለእኔ ሃዘኑ የዛን ያህል ነውና.

ሳልፈልግ በግድ ሰብለን አስታወስኳት……ገንዤ ከቀበርኩበት በግድ ቆፍሬ
አወጣሁዋት……..በፍርድ ቀን ማስታወስ ሲገባኝ በፍቅር ቀን
አስታወስኳት…….ሰው ሁለቴ ሶስቴ አፈቀርኩኝ ሲል ይገርመኛል…..ልብ እንዴት
ከአንድ ጊዜ ባለይ ለሰው ይሰጣል? እየተቆራረሰ? እየተሸራረፈ? እንዴት ሁለቴ
ይፈቀራል…..የሌላውን ባላውቅም እኔን ግን አቅቶኛል…..ከድታኝ ለሄደችው ልቤን
ሰጥቻለው….መልሼ ስላልተቀበልኳት…ከዚህ በሁዋላ የምሰጠው ምንም የለኝም.
መጠጥ ቤቱ እየቆየ በቀይ ለባሾች ሞላ……ዘፈኑ እየቀዘቀዘ በሄደ ቁጥር ከኔ በቀር
ሁሉም በትዝታ እና በፍቅር ይግላል….እኔ ግን በረዶ እየሆንኩ ስመጣ ተሰማኝ…
በላይ በላዩ የምጨልጠው ቢራ ግን እየቆየ ያቀልጠኝ ጀመር.
እንደ ፍቅር እራስን ከፍ የሚያደርጉበት ነገር የለም…..ሁሉም ሰው ሲያፈቅር
እንደሱ ማንም ያፈቀረ አይመስለውም…እንደሱ ስለፍቅር የተጎዳ…ስለፍቅር ብዙ
ብዙ ነገር የሆነ ማንም እንደሌለ በርግጠኝነት ይወራረዳል….እኔም እኔ ሰብለን
እንዳፈቀርኳት…እኔ ስለፍቅር ሁን የተባልኩትን እንደሆንኩት ማንም የለም ብዬ
እወዳደራለው…ከፊቴ ያሉትም ሁሉም ቢጠየቁ ይሄኔ እንደነሱ ያፈቀረ ያለ
አይመስላቸውም ። አይምሮዬ ሲደማ ተሰማኝ….እንደ ቀይ ለባሾቹ….ቫለንታይንን
በቀይ ለማክበር ተገደድኩኝ ቀይ ለብሼ ሳይሆን አልቅሼ…አይኖቼን አቅልቼ……
የበይ ተመልካች ሆኜ….ዙራዬን ከከበቡኝ ቀይለባሽ ውቦች ጋር….ብቻዬን
ተከዝኩኝ…..ሰብለም ይሄኔ ከባለተረኛው ጋር ቀይ ለብሳ ቫለንታይንን እያከበረች
ይሆናል……እሷ ምን አልባት የምትሰጠው ልብ ይኖራታል ፣ ምክንያቱም……ከኔ
ጋር እያለች ለኔ አልሰጠችኝም…..አላፈቀረችኝም……ስለዚህ የማፍቀር እድሉ
አላት…..እኔ ግን እሷን ብቻ አፍቅሬአለው በቃኝ!

ልክ ነው ሃዘንም እንደ ደም ቀይ ነው….ፍቅርም እንደ ፅጌሬዳ ቀይ ነው….ሁለቱም
በቀይ ይከበራሉ…..በቀይ ይመሰላሉ
ሞቅ ሳይለኝ አይቀርም…… አስተናጋጁ ቢራ ሊጨምርልኝ መጣ…..ጠርሙሱ
እየከፈተ ፈገግ ሲል….ቀይ ድዱ ፍንትው ብሎ ታየኝ…..ከዚህ በፊት ብዙ ጊዜ
አይቼው ባውቅም ቀይ ድዱን አስተውዬው አላውቅም. ከት ብዬ ሳቅኩኝ
“ወገኛ አንተም እንደ ቀይ ለባሾቹ…….ቫለንታየንን በቀይ ማክበርህ ነው?” ብዬ
ለብቻዬ ሳቅኩኝ…..አስተናጋጁ ይከፋብኝ አይከፋብኝ አላውቅም። ሌሊቱ እየነጋ
ነው…..ሰው ሁሉ ተደስቷል እኔ ግን
ሳልሰክር አልቀርም ……ቫለንታየንን እንደ ጉድ
አከበርነው አልኩኝ…..ዝሆኗ እና ጉንዳኗን አሰብኳቸው
ዝሆንን እና ጉንዳን ድልድይ ሲሻገሩ ድልድዩ ይነቃነቃል አሉ….ከዛ ጉንዳኗ
“ነቀነቅነው” አለች አሉ። እንደምንም……ግን አከበርናት….እስኪነጋ ጨፈርን
….አለቀሰን….ተከዘን…አይ ቫለንታይን….እንደ ለቅሶ በጥቁር መከበር የነበረበትን
በአል በቀይ አጨማለቁት!!!!ቀይ ለባሾቹ…

((( ሚስጥር )))💚💛❤️


@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ረባሿን ሴትዮ አገኘኋት!
«ዘውድአለም ታደሠ»
እንዴት አመሸህ ህዝቤ? ፒስ ነህ ወይ? እኔ ሳይቸግረኝ ኮንዶሚኒየም ግራውንዱን ተከራይቼ መከራዬን እየበላሁ ነው። ኮንዶሚኒየም መኖር መከራው ብዙ ነው። ረብሻና ጩኸቱ አይጣል! በተለይ ምን እንዳዩ እንጃ የብሎኩ አሮጊቶች ጌሾ ሚወቅጡት፣ ስንዴ ሚያበጥሩት፣ በረበሬ ሚደልዙት፣ ሰው ሚያሙት ሁሉ እኔ በር ላይ ተቀምጠው ነው!
ዛሬ በግዜ ገብቼ ገና አረፍ ከማለቴ የሆነ ነገር
«ግው ግው ግው» ሲል ደንግጬ ተነሳሁና ድምፁን አዳምጥ ጀመር ... «ግው ፣ ግው ፣ ግም ፣ ግው» ይላል። አረ ይሄ ነገር ምንሼ ነው? አልኩ ደንግጬ ።
ግው! ግው! ግው! ሲል መሬቱ ራሱ ይንቀጠቀጥ ጀመር ... ደጄ ላይ ዳይኖሰር ዱብ ዱብ የሚል ሁሉ መስሎኝ ነበር። (አቤት ግነት)
ቀስስ ብዬ መጋረጃዬን ገልጬ ሳይ ሁለት አሮጊቶች በትልቅ ሙቀጫ የሆነ ነገር ይወቅጣሉ! እቺን ይወዳል ቶኪቻው!
በደምፍላት በሩን በርግጄ ስወጣ የፊት ጥርሳቸው የወለቀ ኮሳሳ አሮጊት
«ጎሽ ጎረምሳው ና ወዲህ» ብለው የያዙትን ግድንግድ የእንጨት ዘነዘና አቀበሉኝ። መቼም የቄራን ልጅ ሼም ነው የገደለው ዘነዘናውን ተቀብዬ አንድ ሀገር ሚጥሚጣ ወቅጬ ዘነዘናውን ላስቀምጥ ስል ሌላኛዋ አሮጊት
«እቺን ሳትጨርስማ ንቅንቅ የለም!» አሉኝ ቆፍጠን ብለው ሌላ ማዳበሪያ እየጠቆሙኝ። አረ ያሮጊት ጉልቤ!
ወፈር ስል ተንቀሳቃሽ ወፍጮ አረጉኝ እንዴ ሰዎቹ? እያልኩ በሆዴ ሳልወድ በግዴ መውቀጥ ጀመርኩ። አሁን ቆይ አንድ ማዳበሪያ ሚጥሚጣ ምን ይሰራላቸዋል በናታችሁ? ወይስ እኔን አስፈግተው ለልኳንዳ ቤቶች እያዞሩ ሊያከፋፍሉት ነው? መቼም ዘንድሮ ሁሉም ነጋዴ ሆኗል። የመሸጥ ዘመን ነው! ሁሉም ሻጭ ሆኖ ገዥ የጠፋበት ዘመን! ... (ኢየሱስኮ በዚህ ዘመን ተወልዶ ቢሆን በጨርቅ እንደተጠቀለለ ተሽጦ ነበር)
ለነገሩ አለም ራሷ በተለይ አፍሪካ ትልቅ ጉሊት ሆናለች! ሁሉም እጁ ላይ የገባውን ነገር ይዞ ለመሸጥ ገበያ ይወጣል! አፍሪካውያን እጃቸው ከገባ በኋላ ጨክነው ለገበያ የማያቀርቡት ብቸኛ ነገር ...... ስልጣን ብቻ ነው!
እናማ .... እንደምንም ሙሉ ማዳበሪያ ሚጥሚጣ ወቅጬ ጨርሼ አሮጊቶቹ ይመርቁኛል ብዬ ስጠብቅ ወላቃዋ የድሮ አራዳ «እንግዲህ በተመሳሳይ ፕሮግራም እንገናኛለን» ብለው ፈገግ አሉ። ወይ ዘመን ደሞ «በተመሳሳይ ፕሮግራም እንገናኝ» የሚል ምርቃት አመጡብን? .. አረ እቺ ኮንዶሚኒየም ወዴት እየሄደች ነው? ብዬ ወደቤት ገብቼ አረፍ አልኩና እነዚያ የማይሞቱትን አክተሮች ለማየት ቃና ልከፍት ሬሞቴን ሳነሳ እቺ ለሊት ተነስታ ቡና እየወቀጠች ምትረብሸው አንደኛ ፍሎር ላይ ያለችው ረባሿ ሴትዮ ትዝ ስትለኝ ዛሬም እንደልማዷ እኩለለሊት ተነስታ ቡና በመውቀጥ ብሎኩን ከማናጋቷ በፊት ቤቷ ሄጄ ማስጠንቀቅ እንዳለብኝ ወሰንኩ።
አዎ በጣም መሮኛል! ጎበዝ! እስከመቼ ነው በገዛ ቤታችን (ይቅርታ በኪራይ ቤታችን ለማለት ነው) እየተረበሽን የምንኖረው?
ዘራፍ!! ወንድ ልጅ ቆረጠ! አላርፍ ካለች በያዘችው ዘነዘና ..... (አረ የሰይጣን ጆሮ ይደፈን) ..... ብቻ ዛሬ አስቁሚያት በሰላም መተኛት አለብኝ። ብዬ ተንደርድሬ ወደቤቷ በመሄድ በሯን በሃይል አንኳኳሁ!
ወዲያው በሩ ቀስስ ብሎ ተከፈተና .... አንዲት ውብ ልጅ ብቅ አለች!! የተመሰቃቀለው ጥቁርና ረዥዥም ፀጉሯ ከእንቅልፏ እንደነቃች ይናገራል። ሰማያዊና ትንንሽ አይኖቿ ግምባሯ ላይ የተተከሉ የሰማይ ቁራጮች ይመስላሉ! ቻፒስቲክ ያልነካቸው በምራቅ የረጠቡ ከንፈሮቿ ልብን ቀጥ ያደርጋሉ። አፍንጫዋ ከንፈሮቿን የሚጠብቅ ቀጥ ብሎ የቆመ ዘብ ይመስላል ..... ዝቅ ብዬ እግሮቿን አየኋቸው።
ቀለም ያልነካቸው የጣቶቿ ጥፍሮች ፣ የጣቶቿ ርዝማኔ ፣ (አሁን በዚህ እግር በካልቾ ቢመታ ቅር የሚለው ሰው ይኖራል?) .... በዚያ ላይ ጠረኗ .... በምን አቅሟ ነው ይሄ ሁሉ ውበት የተሸከመችው በናታችሁ?
ቆይ!! ምናባቴ ፈልጌ ነበር የመጣሁት? አዎ ያቺን ረባሽ ሴትዮ ፍለጋ! ግን ብስጭቴ የት እንደገባ እንጃለቱ የሰሞኑ የሃይለስላሴን ሃውልት መስዬ በዝምታ ስቃኛት ....
«ፈልገኸኝ ነው ወንድሜ?» አለችኝ።
ብዙ ሰው «ወንድሜ» ብሎኛል። እንደዛሬ ግን ቃሉ ማርኮኝ አያውቅም። ወይ ድምፅ!! አሁን ይሄ ድምፅ እዚህ ቆሽቋሻ ኮንዶሚኒየም ውስጥ ይኖራል ቢሉ ማን ያምናል? ድምጿ ጆሮ ጋር ሳይደርስ ቀጥታ የሚያርፈው ልብ ላይ ነው!! ይሄን ድምፅ ነበር ዳውንሎድ አርጎ እየሰሙ ለሽሽ ማለት!
እንደምንም ቀልቤን ሰበሰብኩና
«እዚህ ቤት ለሊት እየተነሳች ቡና ምትወቅጥ ሴት አለች?» አልኳት።
ደንገጥ ብላ
«እኔ ነኝ ቡና ምወቅጠው ረበሽኩህ እንዴ?» አለችኝ።
ያልጠበቅሁት ነገር ቢገጥመኝም ቆፍጠን ብዬ እንዲህ አልኩ ...
«ታዲያ ቡና ጠጡ አይባልም እንዴ?»😂😂😂
@wegoch
@wegoch
@kaleab_1888
“የታጠፉት ገፆች”
Written by ሌሊሣ ግርማ
fo


…. ለእሱ እውነት ያለው አየር ላይ ነው፡፡ አየሩን እንጂ በቴሌቪዥን
የሚቀርበውን አየር ትንበያ ፈፅሞ አያምንም፡፡… ሰዎች በአንደበታቸው
የሚናገሩት መቶ ፐርሰንት ውሸት እንደሆነ ያውቃል፡፡ በአንደበታቸው ሲጎርሩ
ፊታቸውን በጥሞና ያጠናል፡፡ አይን አይናቸውን። እንደ አይን ሀኪም፡፡…
ተረማምደው ደረስን ከሚሉበት የበለጠ አረማመዳቸውን ያነባል፡፡ እውነት
እንዳላቸው ይገባዋል፡፡ እውነታቸው ግን የሚናገሩት ላይ አይደለም ያለው፡፡
ወይንም ለሰው ብለው ከቤታቸው ተለማምደው ይዘው አደባባይ ላይ
በሚወጡት አኳሃናቸው ላይ አይደለም፡፡
እውነታቸው ያለው ራሳቸውን ለጥቂትም ቅፅበት በሚረሱበት ጊዜ ነው፡፡
አንዳንድ ጊዜ ድብን ያለ እንቅልፍ ጥሏቸውም መተወን የሚቀጥሉ አሉ፡፡
በጉራ የሚያንኮራፉ፡፡ እሱ ሰዎችን ማንበብ ይችላል። ያነበበውን ግን
አይነግራቸውም፡፡ ከነገራቸው፤ ይደነግጣሉ፡፡ ግራ ይጋባሉ፡፡ ይቆጣሉ፡፡
ስለዚህ አይነግራቸውም፡፡ እያነበባቸው ይመሰጣል፡፡ እንደ መፅሐፍ፡፡
መፅሐፍትንም የሚያነበው እንደ ሰዎች ነው፡፡ በመስመሩ መሀል፡፡ ፀሐፊው
መናገር ከፈለገው ጀርባ ያለው ንግግሩን፡፡ አንባቢን ለመስበክ ሲጥር፣ ጥረቱ
ከምን እንደመነጨ ይገባዋል፡፡… መፅሐፉን በጣም መሸጥ የፈለገ…መፈለጉን
አይገልፅም፡፡ እሱ ግን እንዳይገለፅ በጥንቃቄ የተደበቀውን ያነባል፡፡
ሰዎች የማያምንበትን የፃፈ ፀሐፊን፣ በሙሉ እምነት ተመስጠው ሲያነቡ
አንዳንዴ ያጋጥሙታል። ሌላ ጊዜ ደግሞ መፅሐፍ በመፃፉ በራሱ ለመገረም
ድርሰት ያበረከተን ሰው ስራ፣ በራሳቸው የማንበብ አቅም ለመደመም መፅሐፍ
ሲያገላብጡ ያገኛል፡፡ ሁለት ተዋናዮች ሲናበቡ፡፡ እሱ ሁለቱንም በቀረቡበት
ዋጋ አይቀበላቸውም፤ ይመነዝራቸዋል፡፡ በቃ ይሄ “ሆቢው” ነው፡፡ የሰውን
እውነተኛ ማንነት ማንበብ፡፡
አንዳንድ ጊዜ እንዲያውም ሰዎቹም አያስፈልጉትም። ሰዎቹ የተጠቀሙበትን
እቃ በማስተዋል እውነተኛ ገፃቸው ይነበብለታል፡፡ መኪናቸውን፣ ቤታቸውን…
አንዳንድ ጊዜ የቤት ሰራተኞቻቸውን አይቶ ቀጣሪዎቹን ያነባል፡፡… ደግሞ
“ንባቤ በጣም ትክክለኛ ነው” ብሎ ነው የሚያስበው፡፡ ግምቱን ተጨባጭ
መረጃ ነው የሚያደርገው፡፡ ግን ተጨባጭ መረጃ ማለት ጋዜጣ ወይም
የዘንድሮው የሬዲዮ ዜና ከሆነ…ምናልባት አንድ ፊቱን ግምቱ ሳይሻል
አይቀርም፡፡
* * *
እና ብዙ አስመሳዮች ይገጥሙታል፡፡ ወይን ጠጅ እዘው፣ ሻማ አስለኩሰው
በአደባባይ የግጥም መፅሐፍ የሚያነቡ አይነቶች፡፡… የሚያነቡት የግጥም
መፅሐፍ ምን እንደሆነ አሻግሮ ይመለከትና… እየተወኑ ያለው ዘውግ
ይገባዋል፡፡ ጎመን የግጥም መፅሐፍን እንደ ጮማ በወይን ለማወራረድ
ሲታገሉ እሱ ተሻግሮ ተቀምጦ ያስተውላቸዋል፡፡… ተውኔቱን የሚያካሂዱት
ተመልካችን ለመሳብ ቢሆንም እሱ ግን ተራ ተመልካች አይደለም።
የተተወነውን ሁሉ አያምንም፡፡ “ሮማንቲክ” ትዕይንት ለመፍጠር ሲጥሩ…
“ቧልታይ” ይሆናሉ፡፡ መሆናቸውን ግን አያውቁትም፡፡ ሻማው ቀልጦ
እስኪያልቅ ችክ ብለው ከማይረባው መፅሐፍ ጋር መታገላቸውን ይቀጥላሉ፡፡..
መምሰል እና መሆን አንድ እና ያው ሆነው አያገኝም፡፡ “ዓለም ትያትር ናት”
ተዋናዮቹ ግን በደንብ መተወን አይችሉም፡፡ ማስመሰላቸውን ወደ መሆን
ደረጃ ማስጠጋት ያቅታቸዋል፡፡ የራሳቸውን መኪና ሲነዱ ሰርቀው ነው
የሚመስሉት፡፡ ይንቀዠቀዣሉ፡፡… ፊታቸው እንኳን በውስጡ እድሜ ልካቸውን
የኖሩበት አይመስልም፡፡…መጀመሪያ፤ ፊታቸውን እንዳይቆጣ በሰላምታ
ማለስለስ ያስፈልጋል፡፡… ሰላምታ በቀን አስር ጊዜ ካልተሰጣቸው ፊት ሰርቀው
መልበሳቸው የተነቃባቸው ይመስላቸዋል፡፡ የተነቃ ሲመስላቸው ተንኮለኛ
ይሆናሉ፡፡
…እሱ ራሱን መመልከት ነው እንጂ የማይችልበት…እነሱን ጠርጥሮ ማየት
ተክኖበታል፡፡ ብዙዎቹ ከስልካቸው ጋር ነው የሚጫወቱት፡፡ ወይም ከስልካቸው
ጋር ነው ሲጨንቃቸው የሚያወሩት፡፡… ከስልክ ጋር የሚጫወቱት ጥልቀት
አይገኝባቸውም፡፡ እሱ መፅሐፍ የሚያነቡትን ማንበብ ያስደስተዋል፡፡
ተመስጧቸውን በማጥናት የሚተውኑት ተውኔትን ጥልቀት መለካት ይችላል፡፡
… በመሰረቱ ነገር አለሙ በሙሉ ተውኔት ቢሆንም አንዳንዶቹ ግን በቀላሉ
አያስነቁም….፡፡ አተዋወናቸው ከልብ የመነጨ ይመስላል፡፡ እስኪያስነቁ ድረስ
እሱ ያስተውላቸዋል፡፡
* * *
…እችኛዋ ሰሞኑን እዚህ ካፌ ያገኛት ናት፡፡…. ምንም ጥያቄ አልነበረውም፤ገና
ዓይኑን እንዳሳረፈባት የተለየች መሆኑዋን አወቀ፡፡ ልዩ መሆኗ ብቻ ሳይሆን ደስ
አለችው፡፡… የካፌው በረንዳ ላይ ሆና ነው ቡና የምታዘው፡፡ በወረቀት
የተለበዱ መፅሐፍት ጠረጴዛዋ ላይ ከክርኗ ሳይርቁ ይቀመጣሉ፡፡ መፅሐፍቱን
በሰው ፊት አታነባቸውም፡፡ ግን እሱ እንደምታነባቸው አውቋል፡፡… የሚያነብ
ሰው እና የሚነበብ መፅሐፍ ያውቃል፡፡… ብዙ ጊዜ መፅሐፍ የሚሸፍን ሰው፣
የንባብ አሻራውን መደበቅ የሚፈልግ ነው፡፡… እቺ እንዲህ ናት። መነፅር
አድርጋለች፡፡ የአይን ነው፡፡ የፋሽን አይደለም። ጭንቅላቷ ከዳሌዋ ጎላ ይላል፡፡
ጎላ ማለቱን በፍሪዝ ፀጉሯ ውስጥ ደብቃዋለች፡፡ ቀለበት አላደረገችም…ግን
ባል ያደከማት ወይንም ያዳከመች መሆኗ ሰውነቷ እንደ ድመት ዘና ብሎ
ወንበሩ ላይ የሚቀመጥበት መንገድ ይገልፀዋል፡፡… ወይ አንዱን አባራ ሌላ
ከማጥመዷ በፊት እረፍት እየወሰደች ነው፡፡… ተነስታ ከመሄዷ በፊት አንድ
ሲጋራ ታጨሳለች፡፡… የተመልካችን ትኩረት ለመሳብ ወይ የራሷን ብስጭት
ለመግለፅ አይደለም፡፡ በቃ ማጨስ ስለፈለገች ነው፡፡ አንገቷ ላይ እንደ ሻሽ
የመሰለ ባለ ብዙ ጠቃጠቆ ሻርፕ ታደርጋለች፡፡ “ለማንም ጉዳዬ አይደለም”
የሚል ተውኔትን ለማንፀባረቅ ፈፅሞ አትሞክርም፡፡ እሱ ግን ለማንም ጉዳዩዋ
እንዳልሆነ እርግጠኛ ሆኗል፡፡
በዛ ሰዓት ያንኑ ካፌ እሱም ማዘውተር ጀመረ፡፡ ስለወደዳት ሊሆን ይችላል፡፡
ወይንም ተውኔቷ አዲስ ስለሆነበት…ብቻ ነገም ደግማ እስክትመጣ ቀደም
ብሎ ደርሶ ይጠብቃታል፡፡… ምናልባት መኖሪያ ሰፈሯ እዛው አካባቢ ይሆናል
ብሎ እየጠረጠረ ይጠብቃታል፡፡ ሰዓት አታዛንፍም፡፡ ሶስት ሰዓት ላይ እዛ
በረንዳ ላይ ናት፡፡ መፅሐፍ ከክርኗ አጠገብ ይቀመጣል፡፡ ቡናውን ቀስ ብላ
ትጠጣለች፡፡
….ቀስ እያለ አጠገቧ ያለው ወንበር ላይ መቀመጥ ጀመረ፡፡ እጆቿን
ያስተውላል፡፡ እጅ ብዙ ነገር ይናገራል። በእንክብካቤ ነው ያደገችው፡፡ ምንም
አይነት ስራ ሰርታ አታውቅም፡፡ ኮምፒውተር ላይ በጣም ፈጣን የሚመስሉ
ረጃጅም ጣቶች ነው ያሏት፡፡… ሊያናግራት ሞክሮ ያውቃል፡፡ አጭር መልስ
ሰጥታው ያለ ሰዓቷ ለመሄድ ተነሳች፡፡ ከዛ በኋላ ጎኗ ላለመቀመጥ ማለ፡፡
ፈራት፡፡
በመስመር መሀል ሊያነባት አልቻለም፡፡ ተሰቃየ። የሆነ ማስተር ፒስ ነገር
ሆነችበት፡፡ ጠረኗ እንደ ልጅነት ትዝታ እየመጣ ማታ ይረብሸዋል፡፡… የካፌውን
አስተናጋጆች ስለ ማንነቷ ጠይቆ አጥጋቢ መልስ አላገኘም፡፡… አድራሻዋን
ማወቅ አልፈለገም፡፡ አድራሻ ምንም አያደርግለትም፡፡ የምታነበውን መፅሐፍ
ብትሰጠው በደንብ ያውቃት ነበር፡፡ እሷን ከማንበብ የምታነበውን መፅሐፍ
ማንበብ ይቀላል፡፡
…ከብዙ ክትትል በኋላ አንድ ቀን በጋዜጣ- ያልተለበደ መፅሐፍ ይዛ መጣች፡፡
የአማርኛ መጽሐፍ። ትንሽ ሳትቸኩል አትቀርም የዛን ቀን፡፡ የቡናዋን ከፍላ
ሲጋራዋን በጥድፊያ አጭሳ ተነሳች፡፡…ወጣች፤ አልተመለሰችም፡፡ ጠረጴዛው
ላይ የተወችውን መፅሐፍ፣ እሱ ተሸጉጦ ከሚያስተውልበት ተንደርድሮ
አነሳው፡፡… እንደ ሌባ በጉያው ሸጉጦት፣ ከዛ አካባቢ ተሰወረ፡፡
ሌላ ስፍራ ሄዶ ይገላልጠው ጀመር፡፡ መፅሐፉ የበዕውቀቱ ስዩም “ስብሰብ
ግጥሞች” ናቸው፡፡… መፅሐፉ ላይ ያለውን ግጥ
ም ሳይሆን የመፅሐፍ
ባለቤቲቷን አሻራ ለማንበብ ገፆቹን በጥንቃቄ ያገላብጥ ጀመር፡፡
በመግቢያው ገፅ ላይ “T” የሚል አንድ ፊደል ሰፍሯል፡፡…የእሷ ስም መሆን
አለበት ብሎ አሰበ፡፡…ወይ “ፅጌ”… “ፀደኒያ”… ፀሐይ እንኳን አትሆንም፡፡ በቃ
“ፀ” ብዬ ልያዛት አለ፡፡
እያንዳንዱን ገፅ በጥሞና መመርመር ጀመረ። አንዳንዶቹ ግጥሞች ያሉበት
ገፅ ጆሮው ታጥፏል፡፡ ለምሳሌ ገፅ አስራ ስምንት፣ “ሞኝ ፍቅር” የሚለው፡፡
“ለሱ
ሰው ብቻ አይደለችም
ጠፈር ናት ባካሏ
መሬት ናት በነፍሷ
ዕድሜ ልኩን ቢሮጥ
አያመልጥም ከሷ፡፡”
ይላል ግጥሙ፡፡ ፌመኒስት ናት ብሎ አሰበ፡፡ ወይንም ጥሏት የሄደው ወንድ
ተመልሶ መጥቶ መለመኑ አይቀርም ብላ አስባ ይሆናል…እያለ ገፆቹን ማጥናት
ቀጠለ፡፡ ሌላ የታጠፈ ገፅ አገኘ- “ይድረስ ለአድርባይ ጓዴ” ይላል የግጥሙ
አርዕስት፡፡
“እየለየ ጊዜ ቦታ እየመረጠ
እስስታማ መልክህ ገፅኽ ተለወጠ
አህያ እንዳልነበርክ በሰርዶዎች መሀል
አህዮች ሲበዙ ዛሬ ጅብ ሆነሀል”
ይኼም ያው ጥሏት የሄደው ሰውዬ የበደላትን የሚገልፅ ግጥም መሰለው፡፡
የሆነ አህያ ሰው ጋር ነው ፍቅር ይዟት የነበረው፡፡ ግን ፍቅሩ ወጥቶላታል፡፡ ለዛ
ነው “አድርባይ ጓዴ” ብላ የጠራችው፡፡…የታጠፉት ገፆች የተወሰኑ ናቸው፡፡..
እየመረጠ፣ በከፍተኛ ጥሞና ማንበቡን ቀጠለ፡፡ የግጥም መፅሐፉን ከዚህ
በፊት አንብቦታል፡፡ አሁን ግን እያነበበ ያለው እሷን ነው፡፡ “ፀ”ን፡፡ የእሷን
ደብዳቤ ነው በግጥሞቹ ውስጥ ተፅፈው ያገኛቸው፡፡
ቀጥሎ “የባይተዋር ገድል” የሚለው መልዕክቷን አነበበው፡፡ ገፁን በደንብ
አድርጋ ነው ያጠፈችው፡፡ ምን ያህል ባይተዋር ሆና እንደተሰቃየች ወለል ብሎ
ታየው። እንደዛ በረንዳ ላይ ተቀምጣ እያያት የሰበሰው ምስል ሁሉ በዚህ
ግጥም ውስጥ መልሶ መጣበት፡፡ የግጥሙ የመጨረሻው ስንኞች በጥቁር
ቀለም ተሰምሮባቸዋል፡፡
“…በሌሊት ወፍ ምትክ፣ ክንፍ ያወጣ ሌሊት፣ ጎጆህን ሲዞረው
መረሳት የሚሉት፣ የኑሮ ገባር ወንዝ፣ አልጋህን ሲገምሰው
“መንሳፈፉስ ይቅር፣ መስጠም ያቅተዋል ሰው” ሲያሰኝህ እድልህ
ያኔ ይጀመራል፣ የባይተዋር ገድልህ”
…የእሷን ድምፅ አንዴ ብቻ ነው የጠየቃትን አልባሌ ጥያቄ ስትመልስለት
ያዳመጠው፡፡ አንድ ጊዜ ብቻ፡፡ ያችኑ ትዝታውን ተጠቅሞ ግጥሙን
ሲያነብ፣በህሊናው የእሷ ድምፅ ነበር በለቅሶ ዜማ የሚንሾካሾክበት፡፡…
ህመሟ ቁልጭ ብሎ ታየው፡፡ እንባው እንደ ሳግ ጉሮሮው ላይ መጥቶ
ተጠራቀመበት፡፡… ሳያስበው አንድ ነገር ተገለፀለት፤ እቺን ልጅ ከገባችበት
ሀዘን ለማውጣት ከነገ ጀምሮ እንደሚጥር፡፡ “ይኼ ተውኔት አይደለም” አለ
ለራሱ፡፡ ይኼ እውነተኛ የሰው ነብስ ሀዘን ነው፡፡ እደርስላታለሁ…፡፡ ብሎ
በሀይል ማለ፡፡
የመጨረሻው የታጠፈ ገፅ ላይ ያለውን ግጥም፣ እንባ ብዥ ባደረገው አይኑ፣
ጉሮሮው ላይ ያለውን ሳግ ለመዋጥ እየታገለ አነበበው፡፡ “ምንቸት እና ጋን”
ይላል አርዕስቱ፡፡
“ይኑሩ እንጂ ባ’ገር
በቀዬ በሰፈር
ኩሬ ሙሉ ውኃ፣ ምድጃ ሙሉ ሻይ
ዳውላ ሙሉ አፈር
የምንቸቶች ስፍር መች በጋን ይለካል
ጋኖች እንኳን ቢያልቁ ሌላ አፈር ይቦካል፡፡”
በገፁ ላይ ጠብ ያለውን እንባ ሲጠርግ፣ የድል አድራጊነት መንፈስ እየዋጠው
ነበር፡፡ ያ አህያ ባሏ ጥሏት ቢሄድ…ሌላ አፈር ይቦካል፡፡ እኔ እሱን እተካዋለሁ፡፡
እንደኔ የሚረዳት የለም፡፡ እንደኔ እሷን ማንበብ የሚችል የለም፡፡…ድንገት
እርግጠኛ ሆነ- እቺ ሴት “ፐ”… “ፀ” የእሱ እጣ ፋንታ መሆንዋን አመነ፡፡
ቀኑ እንዴት እንዳለፈ አያውቀውም፡፡ ግጥሞቹን ከገጣሚው በላይ ተረዳቸው፡፡
የሚረዳቸው ደግሞ በእሷ አንፃር እያደረገ ሲተረጉማቸው ነው፡፡ ገፃቸው
የታጠፉትን ብቻ ሳይሆን ያልታጠፉትንም… ልክ እንደ እሷ ደብዳቤ እያሰባጠረ
አነበባቸው፡፡
በተከታዩ ቀን ካፌው ገና ሳይከፈት ቀድሞ ተገኘ። እሷ በሰዓቷ መጣች፡፡ ግን
ብቻዋን አልነበረችም። ለመጀመሪያ ጊዜ ከሆነ ጠና ያለ ሰውዬ ጋር ነው
የመጣችው፡፡ አጎቷ ለመሆን እድሜው ትንሽ ያጥራል፤ ግን እኩያዋ
ለመሆንም ይበዛል፡፡ ጥጥ እራስ ነገር ነው፡፡
እሱ… አዘጋጅቶ የመጣው ዲስኩር ጠፋበት። ሽማግሌው ሰውዬ ከየት
መጥቶ ህልሙ መሀል እንደገባበት አላወቀም፡፡… በስንት መከራ ኪሱ ውስጥ
የሸጎጣትን የግጥም መፅሐፍ በቀስታ አውጥቶ ወደ “T” አቅጣጫ ሰደደው፡፡
…የእጅ አዘረጋጉ ሊኮረኩራት እንደከጀለ አይነት ከተሸማቀቀች በኋላ…
መፅሐፉን ስታየው…ስትለየው ድንገት ፈገግ አለች፡፡
“ትላንት እዚህ ጥዬው ሄጄ ነው?” ብላ ጠየቀችው፤ ግልፅ በሆነ የዋህ
አንደበት፡፡
“አዎ” አላት እሱ፡፡
“…መፅሐፌን ብትጥይው ኖሮ አልለቅሽም ነበር” አለ አጎትየው፡፡ እና ጠጋ
ብሎ “አሁን ሳሚኝና መፅሐፌን ስጭኝ…” አላት፡፡
ሳመችው፡፡ አጎትየው ፍቅረኛዋ ሆነ፤ ሲሳም፡፡
“የግጥሙን መፅሐፍ እሱ ነው የሚወደው…እንኳን አልጠፋ…አይለቀኝም
ነበር፡፡” አለች፤ ወደ እሱ ዞር ብላ እንደ ማስረዳት፡፡ ከዛ ወደ አጎቷ ተመለሰች፡፡
እሱ ምንም ሳይናገር ከጎናቸው ተነስቶ ሌላ ቦታ ቀየረ። መሄዱን ልብ
አላሉም፡፡ … የሆነ ጥግ ተወሽቆ ሁለቱ ሲዳሩ፣ እሱ ብቻ ማየት የሚችለውን
ጥናት ማድረግ ቀጠለ፡፡ በመስመር መሀል ማንበቡን፡፡ መስመሮቹ ግን ብዥ
ብለው ያበጡ ሰንበሮች ይሆኑበታል፡፡…ቢሆኑም ማንበቡን አያቋርጥም፡፡

የኔዋ💚ሸጋዋ💛ቅዳሜ❤️!!!!

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ሰለም ሰላም እንደምን አላችሁ ውድ ኢትዮጵያውያን እህቶቸ እና ወንድሞቸ
፨ ፈለገ ጥበባት የሚል የቴለግራም ግሩፕ አለ አላማው የተደበቁ የኢትዮጵያን ማንነቶች፤ የአበው የአባቶቻችን የእውቀት ልቅህና ከውቂያኖስ የጠለቀ እወቀትና ሚስጥር፤ ተሰምተው እና ታይተው የማይታወቁ የተሰወሩ ገዳማትን፤ የኢትዮጵያን የትላት ድብቅ ና ሚስጥራዊ ማንነቷ የወደፋት እጣ ፈንታዋን የሚያትቱ ገዳማት ብቻ ላይ የሚገኙ የአበው የትነቢት መፅሀፍትን እነ ፥መፅሀፍ ሔኖክን እነ እራእየ ሳቤላ፥ መፅህፈ አክሲማሮስን፥ ፍካሬ እየሱስን የመሳሰሉ ፥ስለ ሀገራችን ምን ምን ሚስጥራትን ይተነብያሉ? አለም የሚመካባቸው ታላላቅ ስራወች ምንጫቸው ሰርቀው የወሰዶቸው የእኛው የብራ መፃህፍቶች አንደሆኑ በመረጃ አንመለከታለን ..ይህን እና የመሳሰሉትን በሰፊው እናያለን፡፡ ይህ ግሩፕ ማንኛውም ሀይማኖትን ፣ ዘርን ፣ ብሄርን አይከለክልም አላማውም ኢትዮጵያዊነትን ማስተዋውቅ ነው ፤ለሁም ክፍት ነው በሉ አሁን ወደ ዚህ ግሩፕ ለመቀላቀል ታች ያለውን ተጭነው ጆይን ያድርጉ::
👇👇👇👇👇👇
@Wegoch
@felegetibebat
@felegetibebat
ጓሳና ድንግል ያለአንድ ቀን
አይበቅል

ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ገበሬ አንዲት ክፉ ሚስት ነበረችው፡፡ በእርሻ
ሲደክም ውሎ ሲመጣ፤
“ና ወጥ ስራና ራቴን አብላኝ”
“ና እግሬን እጠበኝ” ትለዋለች፡፡
ሌላ ቀን ደግሞ፤
“ወገቤን አሞኛል ና እሸኝ” ትለዋለች፡፡
ደሞ ሌላ ጊዜ፤
“ና፤ እግሬን እጠበኝ”
“ና በቅባት እሸኝና አስተኛኝ!” ትለዋለች፡፡
እንዲህ ቁም ስቅሉን ስታሳየው ከርማ፣ የአምላክ ፈቃዱ ሆኖ ከዚህ ዓለም
በሞት ተለየች፡፡
ከሞተች በኋላ ብዙ ጊዜ በብቸኝነት መኖሩን ያስተዋሉ ሰፈርተኞች መክረው
ዘክረው፤ ሌላ ሚስት እንዲያገባ አደረጉት፡፡
አዲሲቱ ሚስት ደግሞ የመጨረሻ ደግ፣ አስተዋይ ሆነችለት፡፡
ጠዋት ከአልጋው ሳይነሳ ቆንጆ ቁርስ ሰርታ እዛው ባፍ-ባፉ አጉርሳው፤ ማታም
ከእርሻ ሲመለስ እግሩን አጥባ ወገቡን በቅባት አሽታ፣ ራቱን አጉርሳው
አቅፋው ትተኛለች፡፡
ይሄኔ ይህ ባል፤ እንዲህ ብሎ ፀለየ ይባላል፡-
“አምላኬ ሆይ፤ ስላደረክልኝ ሁሉ ምስጋና ይግባህ! አንድ ውለታ
እንድትውልልኝ እጠይቅሃለሁ፡፡ ይኸውም ከዚች የተሻለች የምትመጣ ከሆነ
እባክህ እቺንም ግደልልኝ!”
***
ዱሮ፤ ዱሮ ዱሮ፤
“ጉዟችን ረዥም
ትግላችን መራራ” ይባል ነበር፡፡
አንድ የደርግ ካድሬ አገሩን ሲያምስ ሲያተራምስ ከርሞ ተረኛ ታካሚ ሆኖ ራሱ
ታሰረ፡፡ ከዚያ ሲደጋግመው የኖረውን ያንን መፈክር መጠየቅና መቃወም
ጀመረ፡-
“ትግላችን መራራ፣ ጉዟችን ረዥም” ብሎ ነገር ምንድን ነው? መራራ ከሆነ
አጠር ይበል፣ ረዥም ከሆነ ጣፈጥ ይበል፡፡ ለምንድን ነው ለህዝባችን ደግ
የማንመኘው” አለ። ካልተቀጡ የማይማሩ አያሌ ካድሬዎች ስናፈራ ኖረናል፡፡
ዞሮ ዞሮ ቤት ያፈራቸው ናቸው!
ዛሬም ሊቀጥል እንደሚችል ጭንቅላትን ይዞ ማሰብ አይጠይቅም፡፡ ዋናው
ከሆነውና ከሚሆነው መማር ነው!
“ምንኛ ታድሏል የሰነፍ አዕምሮ
እንኳን መማር ቀርቶ ፊደል ሳያጠና
ሁሉንም ያወቀ ይመስለዋልና
አሁን የት ይገኛል ቢፈልጉ ዞሮ
መስማት ከማይፈልግ የባሰ ደንቆሮ”
ብለዋል ከበደ ሚካኤል፡፡ መስማት ካቃተን ለውጥ አናመጣም፤ ዕውነት
ለመናገር ለውጥን ከልብ ካላሰብነው አገር አንለውጥም፡፡ መቼም! መቼም!
መቼም!
የመከላከያን መዋቅርና አስተሳሰብ፣ መለወጥ፣ ስለደ ህንነት ያለንን ግንዛቤ
ማሻሻል፣ አገርን ከማዳን አኳያ መታደጊያችን ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ የንቃተ
ህሊናችን መበልፀግ እጅግ ወሳኝ ነው፡፡ እነዚህን የአገር ህልውናዎች
በጤናማ መንገድ አለመንከባከብ ቆይቶ ያስከፍለናል፡፡ ወታደራዊና
ደህንነታዊውን ኃይል በጤናማ ዐይን ካላየን፣ እንዲሁም የምንመኛትን
ኢትዮጵያ ለመገንባት ካልተዘጋጀን፣ እንደ ልማዳችን ይረፍድብናል፡፡ “ባለበት
ሃይ!” የምንባለው ለዚህ ነው!
አንዳንድ ዕድሎች አይደገሙም፡፡ አጋጣሚዎችን ቀልጠፍና መጠቅ ብለን
ካልተጠቀምንባቸው ያመልጡናል፡፡ አንዴ ከጠፉ የማይመለሱ ብዙ ናቸውና
ይሄንን ቀን አንጣው!
Girl, if you want to
Prove that you are a virgin
Don’t forget, that
you’ll never prove it again!
ድንግልናሽን ማረጋገጥ ከፈለግሽ ደግመሽ እንደማታረጋግጪው እወቂ፤
እንደማለት ነው፡፡ “ጓሳና ድንግል ያለአንድ ቀን አይበቅል” ማለት ይሄ ነው!!

(( ነብይ መኮንን ))💚💛

ምንጭ:-አዲስ አድማስ ጋዜጣ ( የካቲት 9/06/2011 )

ሸጋ የረፍት ቀን!!💚💛

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ግራዚያኒ እነዚህን ህዝቦች ሲጨፈጭፋቸው...አንተ ኦሮሞ ነህ፣አማራ ነህ ፣ትግሬ ነህ ጉራጌ ነህ ብሎ ወይም ዘርን ለይቶ አይደለም። አንተ የኢትዮጵያ ህዝብ ብሎ እንጂ። ( ዘረኞች ይሄንን እውነታ እንዴት መረዳት አቃታቸው .? )

አገር በቀልድ እንዳልተገነባች ማሳያ በቂ ነው እነዚህ ሰዎች የሞቱት በዘራቸው ሳይሆን ኢትዮጵያዊ በመሆናቸው !!!

ክብር ለሰማዕታት !!!💚💛

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ለሞተልህ ያልቆምክ አንተ ለማን ልትሞት? ኢትዮጵያዊነት ነጻነትና መስዋእትነት ነው።
አንገታችን የተቃናው፣ ልባችን የኮራው በሞቱልን ሰማእት ነው። ኢትዮጵያን አትግፋ፥ እሷን
ገፊ የስሪቷ አሻራ ጣይ የሚያኮሰምነው፣ ማቅናት ያልቻለ እብቅና ቅንቅን ነው!!

💚💛

@wegoch
@wegoch
የካቲት 12 ግን ታስቦ መዋሉ ብቻ በቂው ነው ትላላችሁ???

አስተያየታቹን ከነ ምክንያታቹ ብታደርሱን ደስ ደስ ይለናል....

ክብር ለሰማዕታት !!💚💛

@balmbaras
@Gebriel_19
Audio
የካቲት 12
በ ሀይማኖት ግርማ

ከ ጳውሎስ ኞኞ 'የኢትዮጵያ እና የኢጣልያ ጦርነት'.


@getem
@wegoch
Forwarded from ቅንድል ኢትዮጵያ (Ermiyas Dejene)
#ቀንዲል ዲጂታል መፅሔት 👇👇👇

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው እውቀትን እና ልምድን ባካበቱ አምደኞች የተፃፈ አዝናኝ እና አስተማሪ ዲጂታል መፅሔት፡፡
Forwarded from ቅንድል ኢትዮጵያ (Ermiyas Dejene)
ቀንዲል Digital Magazine 01.pdf
7.5 MB
#ቀንዲል ዲጂታል መፅሔት

ቅፅ 1- ቁጥር1

💰ፓኬጅ ከገዙ 0.90 ሳንቲም ብቻ💰

@kendilM
@kendilM
ይህ ህዝብ፦

አድዋ ላይ ነጭ ተራ ፍጡር መሆኑን ያስመሰከረ፡፡ “ጥቁር ሠው” የሠው ዘር መገኛ ብቻ ሳይሆን ከሌላው ዕኩል መሆኑን ያረጋገጠ ኩሩ ሕዝብ ነበር፡፡

ይሕ ሕዝብ፡-
ክፉ ቀንን ያለፈ፤ ከ66 የተረፈ፤ 77 ትንም 97ትንም ያያ… ተአምረኛ ሕዝብ ነው፡፡

ይሕ ሕዝብ፡-
ለኮሪያ የዘመተ፤ ማንዴላን ያሠለጠነ፤ ለአፍሪካ የነፃነትና የባንዲራ እርሾ ያበደረ… ገራሚ ሕዝብ ነበር፡፡

ይሕ ሕዝብ፡-
እየሱስ ክርስቶስ ሲጠመቅ ቆሞ የመሠከረ፤ ሞስሊሞች ሲሳደዱ ያስጠጋ፤ በመጽሐፍ ቅዱስ እስከ ቱንት የተጠቀሰ፤ በቅዱስ ቁራን የተወደሰ፤ በእየሩሳሌም ርስት ያለው፤ለነብዩ መሐመድ አዛን ያለ፤ የጠገበ መንፈሳዊ ታሪክ ያለው ሕዝብ ነው፡፡

©ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን
@wegoch
@wegoch
@gebriel_19
‹‹ሉሲ የሰላምና የፍቅር ጉዞ›› - ቋሚ የጭካኔና ግፍ አዋጅ፣ በድን አጽም የሰላምና የፍቅር
አማላጅ!
(ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ)
"ግልብ አእምሮ ደርዝ ያለው፣ እየተቀናጀ የሚጎለብት ተግባር ሊከውን አይችልም፤ ይህ
ደግሞ የአብዛኞቹ የለውጡ መሪዎች መለያ እየሆነ ነው፡፡
.
የለውጡ መሪዎች በህይወት ቆመው የዜጎችን ቤት እያፈረሱ፣ ህጻናትንና አዛውንቶችን ሜዳ
በትነው ሰላምና ፍቅር እየነሱ፣ የበሰበሰ አጥንት ከሙዚየም አውጥተው ለሰላምና አፍቅር
አማላጅነት ይልካሉ፡፡ በዚህ ዘመን ከዚህ በላይ ድንቁርና የወለደው ግልብነትና የህዝብ
ንቀት የወለደው ምጸት አይገኝም፡፡
.
ከወራት በፊት የአዲስ አበባን የመንገድ ዳር ለንግድ ፈቅዶ፣ የእግረኛ መንገድ ሳይቀር
በላስቲክ ዳስ ያዥጎረጎረ፣ የለውጥ መሪ ዛሬ የከተማ ውበት ጠፋ ብሎ የህዝብ ጎጆ
ይደረምሳል፡፡ በፍርድ ቤት የእስር ማዘዣ የተቆረጠለትን ተጠርጣሪ ወደ ህግ አቅርቦ ህግን
ያላስከበረ የለውጥ መሪ፣ ከህግ በላይ ማንም እንደሌለ ለማሳየት የዜጎችን መኖሪያ
በቡልዶዘር ይንዳል፡፡
..
አዲስ አበባ ላይ ዜጎችን ፍቅርና ሰላም ነስተው ደም እያስለቀሱ፣ አጽም ለሰላምና ፍቅር
ምልጃ አፋርና ሱማሌ ይልካሉ፡፡ ለነገሩ ካለማወቅ የተደረገ ቢሆንም፣ ቋሚ የጭካኔና ግፍ
አዋጅ፣ በድን አጽም የሰላምና የፍቅር አማላጅ መሆናቸው ዘመኑን በሚገባ ይገልጸዋል፡፡
.
አንድ ነገር ግን መታወቅ አለበት፤ ለውጡ ያለ ጥያቄ የምንቀበለው ሀይማኖት አይደለም፤
መሪዎቹም እየበደሉ እንኳ ተንበርክከን የምንማጸናቸው መላእክት አይደሉም፡፡ ይህን
የሚገነዘብ የለውጥ መሪ ፣ ለውጡን ለማምጣት ከፈሰሰው የሰማእታት ደም ጋር በለውጡ
ሳቢያ የሚፈስ የተበደሉ ዜጎች እንባ እንዲቀላቀል መፍቅድ የለበትም፡፡ ያለዚያ ወደ ደምና
እንባ ቅብብሎሽ ታሪካችን እንመለሳለን፡፡"
--------------------------------
--------------------
# ከድንቅነሽ_ስልት_በላይ !
የሉሲ "አማላጅነትና አስታራቂነት" ንድፈ-ሃሳብ ጉዳይ ከጣፎ ድርጊት ተቃርኖ በላይ ነው።
ሰውው ሁሉ በብሄር ከረጢት ተቋጥሮ፣ አካል አምሳል በነብስ ያለን ሰው ተጸይፎ "አይንህን
አልይይይ" ብሎ በግፍ እየገፋ ሳለ እውን ይሄን እውክ ወቅት አጽም ያሽረዋልን? እውን
አሁን ያለውን ሰው ሉሲ ታስታርቀዋለችን? ይሄን መሰል ሰንፋጭና ምስቅልቅሉ የወጣ
ማህበራዊና ፖለቲካዊ ሽክረት ደረጃ በደረጃ እያዋዙ ለማርገብና ኅልዮት በሚፈቅደው
መስመር ለማስገባት እውን የለውጡ መሪዎች በዛ ደረጃ የሚሰፋ ስልት አላቸውን??
ለችግራችን "እናታችን" ሉሲን አንዷ የመዳኛ መንገድ አድርጎ ያሰበ የለውጥ ሀይል ሃገሪቱ
ያለችበትን ሁኔታ በቅጡ ያልተረዳ ወይም ችግራችንን መፍቻ አቅም ያጠረው
አይመስልምን? እንዲያ ሲሆን የጎመዠሁት ነገ በመቋመጥ ብቻ እንዳይቀር ያስፈራኛል።
የችግራችን ውስብስብነት እንዲህ በዘፈን የሚፈወስ አደለም። የችግራችን ጥልቀት
በማስመሰልና በመጋበዝ የሚፈታ አደለም።
እንዲያም ሆኖ ዛሬ ሀገሬ ያለችበት ሁኔታ ከትናንት በእጅጉ የሚሻልና ለዘመናዊ ሰው
መንገድ ምቹ መሆኑን አምናለሁ። በመሆኑም የእውነቱ ተጓዥና መሪ እንዳይደክም፣
የእውነቱን መንገድ እሾህ እንዳይደፍነው፣ ሴረኞችና ሃሳውያን ጎልብተው የልጆቼ አገር
ዳግም በውርደት ሁነት እንዳትዘወትር ከመውተርተር አልቦዝንም!!
ሰላም!!

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
በአንድ በኩል አምላክ በአምሳሉ የፈጠረኝ ፍጡር ነኝ የሚል አማኝ ነው። ተገልብጦ
ደግሞ የሰው ዘር መገኛ የሉሲና የአርዲ አገር ናት ይላል። ሁለቱ ይጋጫሉ አበሻ ግን
ሁለቱን ያምናል። ያስቃል። በፈጣሪ ለሚያምን የሉሲ እድሜ ሀሰት ነው። የሉሲን እድሜ
ለሚያምን ፈጣሪ የለም። አበሻ ግን ሁለቱን ያምናል። ያስቃል።😁 አንተ የቱን ታምናለህ
ካላችሁኝ ሁለቱንም አምናለሁ። ምክንያቱም አበሻ ነኝ😁

ሸጋ ሸጋዋ ሸጊቱ ቅዳሜ ትሁንላቹ❤️❤️❤️

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
2024/09/28 17:20:30
Back to Top
HTML Embed Code: