Telegram Web Link
እራቱን ለቅሶ ቤት ፈልጎ ሚበላው እኮ ነው ደውሎ «እራት በላሽ ማሬ» እያለ ሚያደርቅሽ 😁

@wegoch
@paappii

#yasino
አንዷ የቦሌ ልጅ ሰው ተሰልፎ አይታ አባቷን
"ዳዲ ይሄ ሰልፍ የምንድነው?"
"ለታክሲ ነዋ ልጄ" ይላታል
"ታክሲ ሊገዙ ነው?" 😳😝

@wegoch
@wegoch
@paappii

#natnael ayalew
ስልክ መንትፎ እየሮጠ ለማምለጥ መስጊድ ገብቶ ከሰጋጆች ጋር ተቀላቅሎ ሲሰግድ የሰረቀው ስልክ ሲጠራ ቀውጢ መዝሙር 😳😂

@wegoch
@paappii

#abdu abdel
ቺኳን አቩካዶ ፣ ድንች በዳጣ ፣ ባቄላ እሸት ምናምን ጋብዘሃት ከሸኘሃት ቡኋላ ቤት ስትደርስ የምትልክልህ text
«ምነው ሞዴል አርሷደር ነኝ አልክ?» 😁😂

@wegoch
@paappii

#yasino
ከሰውነት ማንም አያስጥልም !!

ማንም መጀመሪያ ሰው ሆኖ ነው የሚወለደው።

ከብሔሩ በፊት ፣ ከተወለደበት ማኀበረሰብ ሃይማኖት ከመቀበሉ በፊት ፣ ሰው ነው ፣ ማንም "ሰው ነኝ!" ብሎ ሐሳቡን ቢቀይር፣'ማጆሪቲ' ይሆናል።

ግን፣ ሰው መሆንም ነገሩን አያቀለውም። የሰውነት ተፈጥሮ በራሱ አስቸጋሪ ነው። ይሄ ዐቅሙ የተፈጥሮ አካል ነው። ምርጫ ማድረግ የሚችል የሰውን ተፈጥሮ በህግ ማስገዛት የሚከብደው ለዚያ ነው። ማሽን አንድ-ወጥ ሆኖ ተፈጥሮ ለፈጣሪው እንደሚኖር አይደለም የሰው ልጅነት። ይህ የምርጫ ተፈጥሮ በምክንያት ሆነ ያለ ምክኒያት እንዲያምፅ ሊያደርገው ይችላል።

አኹን፣ እዚያ የመኪና መብራቱ ጋ የሚለምኑት ልጆች ማስቲሽ እየተቀባበሉ ያሸትታሉ። ማስቲሽ የተሠራው ለጫማ ማጣበቂያነት ነው። ግን፣በቃ፣መርጠው ያሸትቱታል፤ ይሰክሩበታል። ማስቲሽ ፣ ላስቲክ ለማጣበቅ ካልሆነ፣ለሌላ አገልግሎት ማዋል አይቻልም ! የሚል ሕግ ቢወጣም ፣ ተደብቀው የተከለከለውን ያደርጋሉ፤ በማህበረሰቡ ይገለላሉ። ወይንም ፣ ማኀበረሰብ ስላገለለን፣በሚል ምክንያት ነው እና ፈቃድ እራሳቸውን እየጎዱ ነው። ሰው እራሱን በራ'ሱ ለመጉዳት እንኳን የምርጫ ዐቅም አለው። ብሔር ወይም ቤተሰብ ወይንም ሃይማኖት ስለሌላቸው አይደለም ወጣቶቹ በማስቲሽ ሳንባቸውን የሚያጣብቁት፤ ብሔር ወይንም ሃይማኖት ቢኖራቸውም ከሰውነት አያስጥላቸውም።

ሌላኛው ደግሞ ሲጋራ እያጨሰ ነው።

ከአጨሰ በኃላ ፣ ሳያናፍስ ታክሲ ውስጥ ጥልቅ በማለቱ፣ ተሳፋሪው የአፍጫውን የበላይኛው ከንፈሩ ይደፍን ጀመር። አንድዋ ጠና ያለች ሴት፣"ምነው፣ልጄ፣ሲጋራ መጠጣት ብትተው!?" ምናምን ብላ ምክክር ጀመረች። የሞራል ማማውን ከፍተኛ ስፍራ የተቆጣጠረችበት ቅልጥፍና አሮጊት አያስመስላትም።


እርስዋ ስትመክረው፣ ሰውየው እየተሸማቀቀ ይሰማል---እንዳይተነፍስ ተጠንቅቆ። እንዳይተነፍስ የተጨነቀው የእርሱ ሲጋራ ሽታ ወደ ሴትየዋ አፍንጫ እንዳይገባ ብቻ ሳይሆን ፣ እርስዋ የተቀባችው ቅቤ ሽታው ወደ እርሱ በተለዋጭነት እንዳይመጣበትም ሊሆን ይችላል።

ሰው ምርጫ ያለው ፍጡር ነው። አንዱ ማስቲሽ ያሸታል፤ሌላው ሲጃራ አጭሶ እንዳይሸት ይሸማቀቃል። ሌላው ደሞ ጫማው አለ-እርሱ ፈቃድ መሽተቱ አስጨንቆት ወንበር ሥር እግሩን ይደብቃል።

የአሮጊቷ ምርጫዋ ቅቤ መቀባት ነው፣የሰውየው ደግሞ ሲጃራ ማጨስ። ማኀበረሰቡ ግን፣በተቀባይነት ደረጃ አንዱን ምርጫ የሚደግፉ፣ሌላው ደግሞ የሚነቅፍ ያደርገዋል። የጠላውን ሁሉ ነቅፎ ወደ ሕግ ረቂቅ ለመለወጥ ሙከራ ቢያደርግ ግን ፣ ውጤታማ አይሆንም። የሰውን የምርጫ አቅም ከሰው ተፈጥሮ ውስጥ ለይቶ ማምከን አይችልም።

ለዚህም ነው ፤ አስጨንቆ የሚከለክል ሕግ በድብቅ ሕገ-ወጥ የሚያበረታታ የሚሆነው። ለዚህም ነው ፣ the best law is that which enforces least፣" የሚባለው። የማያስተነፍስ ህግ በድብቅ ሕገ-ወጥነትን የሚያስፋፋ ነው። ምክንያቱም፣ የሰው ልጅ ተፈጥሮው በምርጫ እንጂ በማስገደድ የሚሠራ ስላልሆነ ነው። አንዳንድ ጊዜ፣የሰው ልጅ የምርጫ ዐቅሙን የሚያመጣው ታሞ በአልጋ ሲወድቅ ብቻ የሚሆንበት ጊዜ አለ። የምርጫዋቹ ድምር፣መምረጥ ወደ ማይችልበት ሱሰኛነት ወይንም በግድ መቀበል ወደ አለበት የሐኪም ትእዛዝ ላይ ይጥለዋል። ምርጫዎቹ ወደ'አልመረጠው ፣ ባይመርጥም ፣ ወደ'ማይቀይረው ፣ ሞት ያደርሱታል።

ግን እንደዚያም ሆኖ፣ሰው ሰውነቱን በብሔሩ ምክንያት ወይንም በሃይማኖቱ ....በሕግ ወይንም በፈሪሃ እግዜአብሄር ምክንያት የሚለውጥ ከመሰለን የእምነት ስህተት ፈፅመናል።

ሰው በተፈጥሮ ፣ "አድርግ!" ተብሎ የታዘዘውን ለማድረግ ሲፈቅድ እንኳን፣የእራሱን አሻራ ጨምሮ የሚያከናውን ፍጡር ነው። ዘይቤ የሚፈጠረውም እንደዛዠዚያ ነው። ጥበብ እና ፈጠራ የዚህ የማፈንገጥ ወይንም የአለመስማማት ምርጫ ተፈጥሮው ዐይነቸኛ ማሳያ ናቸው።

"ሁሉንም ነገር በሕግ ለመቆጣጠር የሚፈልግ ፣ የተሻሻለ ማኀበረሰብ በመፍጠር ፋንታ ፣ ጥፋት እና ዝቅጠትን ማበረታታቱ የማይቀር ነው። ሙሉ በሙሉ ከገጸ -ምድር ለማጥፋት ለማይቻል ነገር ይሁንታ መስጠት የተሻለ ነው፣ምንም እንኳን ነገርየው በራሱ ጎጂ ቢሆንም እንኳን። ከድሎት፣ከቅናት፣ከስግብግብነት፣ከሰካራምነት፣ እና ከመሳሰሉት ባሕሪዎች ስንት ዓይነት ዲያብሎሳዊ ጥፋት ይመነጫል ?.....ግን፣እነዚህን ባህሪዎች በሕግ በረቀቀ አንቀጽ መከላከል አይቻልም። መከላከል እና ማጥፋት ስለማይቻልም በመፍቀድ መታገስ ግድ ነው፤"ይላል ቤኔዲክት ደ ስፔኖዛ ----freedom of thought and speech '

እንግዲህ፣አሮጊት ሲጋራ ያጨሰውን ሰውዬ እንደነተረከችው ፣ እኛም ከተለያዩ ምርጫዎቻችን አንጸር መነታረክ እንችላለን። ሴትየዋጨከ'ተቀባችው ቅቤ ሽታ የቱ ማኅበረሰቡን የበለጠ ይጠቅማል ? የሚል ነው ንትርኩ። ንትርኩ፣ እንደ የፓለቲካ ፓርቲዎች የሐሳብ ፍጭት፣በመጨረሻያ ላይ ሕግ እንዲጸድቅበት ለማድረግ የታቀደ ሁሉ ሊሆን ይችላል።

ተከናውኖም፣ ሲጋራ ማጨስ ሊታገድ ይችላል። የሲጋራ ፋብሪካ የማምረት ፍላጎቱ ሳይታገድ ፣ አጫሹ ግን ሲጋራ የመለኮስ ምርጫው ሊታገድ ይችላል።ከፈለገ ሲጋራውን በድራፍት እየነከረ ይብላው፣ሊባል ይችላል። ግን ይሄ ዓይነቱ ህግ ፣ ከሲጋራ የባሱ የሚጨሱ ነገሮችን በደድብቅ እንዲስፋፋ ያግዝ ይሆነናልን እንጂ የሰውን የተሳሳተ ምርጫ የማድረግ አቅም፣ ለአንዴ'ና ለመጨረሻ ጊዜ ፣ ገንዞ አይቀብረውም። እንዲያውም፣ አፈና ተፈጸመብኝ በሚል ፣ የሸመቀቀውን የሕግ ልጓም ለመበጠስ ወደ ሌላ አማራጭ ይዞራል። የሰውን ልጅ በሕግ ወጥመድ የተሻለ፣አዎንታዊ ውጤት ያስገኛል።

እንደ'ቤኔዲክት ስፔኖዛ እምነት:- በመንግሥት ሆነ በሃይማኖት ተቋማት ውስጥ ሌላ መንግሥትም ሆነ ሌላ የሃይማኖት ተቋም የመፍጠር እንቅስቃሴ የሚጠነሰሰው ፣ ከዚሁ የሕግ መጥበቅ እና የክልከላ መብዛት ጋር በተያያዘ ነው፣ይላል።

ለዚህ፣ነውጨ፣ ተቋማት የበለጠ ሥልጣን እንዲኖራቸው ከፈለጊ፣የበለጠ በሕግ የመፈጠር ፍላጎታቸውን መቀነስ አለባቸው ፣ የተባለው። በተለይ የአንድ ሰው ምርጫ በሌላው ላይ የሚያደርሰው አሉታዊ ተጽዕኖ ገና በሐሳብ ደረጃ ላይ ያለ እና የሚያከራክር በሆነበት ኹኔታ ውስጥ ፣ አንድ ጎኑን ለማስደሰት የሚወጣ ሕግ ብዙ እንቢልታ እና እልኽ የሚፈለፍል መሆኑ አይቀርም።

የምርጫ ነፃነቱ የታፈነ ማኅበረሰብ በሚፈለገው በሚፈለገው'ና በሚደረገው፣በማያስበውና በሚናገረው መካከል የተምታታበት ይሆናል። ምርጫውን በድብቅም ቢሆን ተግባራዊ ይሆናል። የተጫነውን ሕግ እንዲናገር ከ'ሚፈቅድለት አንጻር ይናገራል። እውነት መሆኑን የሚያውቀው ነገር ሲወነጅል ወይንም ማንንም የማይጎዳ ነገር ሲኮንን ይውላል። ይኮንን'ና ከተለያዩ አንጻር የኮነነውን መልሶ ሲያከናውን ይገኛል።

ጠረን የምርጫ ጉዳይ ቢሆንም፣ የሲጋራ ሽታ የማይወድደው በቅቤ ሽታ ይዋጋዋል። በአንድ በተፈጥሮ ላይ ያለ እንቆቅልሽ ነው። ሕግን እንደ ፈጣሪ በሁሉም ጊዜ የሚመለከት እና በሁሉም ስፍራ የሚያስከብር ቢኖር፣ አንድም ሰው ወህኒ ከመውረድ የሚተርፍ ባልኖረ ነበር።

(( ሌሊሳ ግርማ ))

ምንጭ:- ፍትህ መፅሔት ጥር 10 2011

የኔዋ ቅዳሜ!!💚💛

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
የአዲስ አበባ ልጅ ወግ
2

አዲስ አበባ ብሔር የላትም፣ ይሉኛል፣ ሰምቼ ጭጭ እላለሁኝ። ብሔር አላት---'ደፋር " ይባላል። አዲስ አበባ ደግሞ ታላቋ ጋለሞታ ናት። ለደፈራት ኹሉ ቀሚሷን ገልባ ትተባበራለች።'በሕግ አምላክ !' አትልም። ሕግም፣አምላክም ኖሯት አያውቅም። የአዲስ አበባ መተዳደሪያዋ ሕጎች ታክሲ ውስጥ በጥቅስ መልክ ተጽፈው ነው የሚገኙት። "እኔ ላይ የሚጮህ መብት ያለው ስልኬ ብቻ ነው" ይላል አንዱ የደፋር ሕግ። ይሄን ጥቅስ የለጠፈ ታክሲ አላግባብ ጠቅጥቆ ቢጭንኽ፣ለአጭር ጉዞ የረጅም ጉዞ ተመን ቢያስከፍልኽ .....ልትጮህበት አትችልም። ቀጭኑ የደፋር ትእዛዝ ሲተረጐም:- እኔ እንደፈለግሁ ማድረግ እችላለሁ፣ አንተ ግን መጨቃጨቅ እንኳን አልተፈቀደልኽም።

እና አዲስ አበባ የማን ናት ? ጮክ አድርጎ ስለ እራሱ ጥቅም በድምፅ ማጉያ የሚያስብ ደፋር ኹሉ ናት።

ማን ከቀድሞውም አዲሳበባ ውስጥ፣ማን ደግሞ መጤ ነው? የሚለው ጥያቄ ፈጽሞ አያከራክርም። እሱ አይደለም ነጥቡ። ነጥቡ ለማን ነው የተመቸችው ፣ ማንን ደግሞ ያገለገለችው? የሚለው ነው። አዲስ አበባ ላይ የተወለደ ግራ ገብቶት እንጂ ተመችቶት አያውቅም። ምክንያቱ ምንድነው? እኔ አላውቅም። ምናልባት፣በዝግመተ ለውጥ ግምታዊ መላምት እንደሚታሰበው "የተንቀሳቀሰ የበለጠ ይለወጣል፣ባለበት የተቀመጠ እዚያው ዝጎ ይቀራል፣" ይኾን? አላውቅም። ልክ የአውስትራሊያ አቦርጂኖች፣እዚያ በተቀመጡበት፣ነጮቹ በመርከብ መጥተው ሀገራቸውን እንደወረሷቸው፣የአውሮጳ ነጮች፣ዋሻ ውስጥ በነበሩ ጊዜ፣የአፍቃሪቃ ጥቁር ባህር ተሻግሮ ቅኝ ቢገዛቸው ኖሮ፣ምናልባት፣አፍቃሪ ውስጥ የሚታየው የአምባገነን መንግሥታት ታሪክ የምዕራባውያኑ ተሞክሮ ሊኾን በቻለ ነበረ።


በኾነ የዕጣ -ፈንታ አጋጣሚ አዲስ አበባ ውስጥ ተወልጄአለሁኝ። በኾነ የዕጣ -ፈንታ አጋጣሚ የተወለድኩት በመከነው የደርግ ዘመን ነው። ነፍስ ዐውቄ ሙሉ ሰው የኾንኩት ደግሞ ከደርግም በላይ በመከነው የኢሕአዴግ መንግሥት ነው። በአጠቃላይ የባከነው ትውልድ አባል ነኝ። ከ'ባከነው ትውልድ መካከል የብክነቱ ቁስል ለመፈወስ ሀገር ጥሎ የተሰደደው በንጽጽር የተሻለ ኾኗል ብዬ ዐስባለሁኝ። ዐስቤ ሳልጨርስ፣ሀገር ጥሎ ኼዶ፤የተሻለ ኾኖ የመጣው የገበሬ መሬት በብላሽ ከመግዛት እና ከሀገሩ ጋር የማይመጣጠን ምናባዊ ቤት ከመሥራቱ ውጭ ሌላ ምን ተአምር አመጣ? ብዬ እጠይቃለሁኝ። ቁስል ለመፈወስ ኼደው የተመለሱትን ለመኾን ቃዥቶ ፣ ኼዶ ሳይመለስ በ'የባሕሩ ሰጥሞ ቀረ ስንቱን ወይ ኼዶ ሳይኼድ፣ወይ ቀርቶ ሳይነቃ፣በሱስ እና በማይጨው ሕልም ውስጥ ነፍስ እና አካሉ ተነጣጥሎ መከነ!

ከተነሣሁበት ነጥብ አፈነገጥኩኝ መሰለኝ......ደግ አደረግሁኝ!ከሀገራዊ የኅሊና ውል ያፈነገጠ ስንት አለ? ስንት ስለ የኢትዮጵያ ጨዋነት እየሰበከ፣ስንት የብልግና ታሪክ ሠራ! ስንቱ በሕይወት ዘመኑ እና በቀዬው በረሓብ ዘመድ እና በጎረቤት ሲረግፍ ዐይቴ ፣እርሱ በሕይወት ተርፎ ግን በተሞክሮ አዎንታዊ ትምህርት ሳይማር ቀረ፣የተመጣጠነ ምግብ ሳየበላ ያደገ ሰው "የእንብላው"ባህል ተጠቂ መሆን አነበረበትም። በችግር ማደግ ፣እራሱንም እንዳይቸገር፣ሌላም ሲቸገር እንዲገባው፣ያደርጋል እንጂ፣ችጋራም የሚያደርግ ንቃተ-ህሊና መስጠት አልነበረበትም። የችጋራምነትን ባህል ተቀብላ ፣ ተንከባክባ እና እንደ ስለት ልጅ ከእራ'ሷ ልጆች አስበልጣ የምትይዘው ደግሞ ታላቂቷ ጋለሞታ ናት። አዲስ አበባ ፣ እንደረሳሽኝ ብረሳሽ አትፍረጂብኝ ፣ አስተምረሽ ያሳደግሺኝ እንደዚያ ማድረግን ነው።

የተለያዩ የፓለቲካ አመለካከቶች የሚያንጸባርቁ ታክሲዎችን እና በላያቸው የሚለጣጥፏቸው ትርኪ-ምርኪ እስቲከሮች እና ጥቅሶች ዐያለሁ። ኹሉም ከመጡበት አካባቢ ይዘው የመጡት መንፈስ ነው። ኹሉም ቀድሞ የነበረውን ነገር በእራሳቸው ቅርጽ ለመለወጥ የሚፈልጉት ናቸው። ለነገሩ የሚጠበቅ ነው ---occupational hazard ይሉታል ፈረንጆቹ። ጦር ሜዳ የዘመተ ወታደር በታይፈስ እና በታይፎይድ ወይንም በፍቅር ከመሞት ይልቅ፣ በጥይት ወይንም በፈንጂ የመሞቱ አማራጭ ሰፊ ነው። እንደኔ ጸሓፊ የኾነ ሰው በ 'የጸሓፊው ድብታ ' ( writer's block )የመጠቃቱ ዕድል ከሾፌር ወይንም ከልብስ ሰፊ በበለጠ ነው። እንደዚህም በብሔር ፓለቲካ የሚኖር ትውልድም፣ሥራው እና የሚገኘው ጥቅም ከብሔሩ ጋር የጠበቀ ቁርኝት እስካለው ድረስ ፣ የብሔር ባለሙያ መኾኑ አይቀርም። ከሴተኛ -ዐዳሪ ሥራ ጋር የሚገናኝ የሥነ-ልቡና ችግርም ተመሳሳይ ነው፤ብዙ ጊዜ በፍቅር የመውደቅ እና በአንዱም ያለመዝለቅ የሥነ-ልቡና ቀውስ ተጠቂ መኾኗ አይቀርም።

አዲስ አበባ የጋለሞታ ሥነ ልቡና ባይኖራት፣ ጠንኳራ ባህል አጽንታ ፣ማንም ደፋር እንዳይባልግ አደብ ታስይዝ ነበር። በዩኒቨርሲቲዎቿ፣በፍርድ ቤቶቿ ፣ በተለያዩ ተቋማት እና መሥሪያ ቤቶቿ አማካኝነት ያሳደገችው ጽኑ ባህል የላትም። ማንም ፣ ከየት መጥቶ ፣ ምንም ዓይነት ነገር እስከ ልቡ ፍላጎት ቢያረግ ፣ ተው የሚለው የለም።

የጋለሞታ ልጆቿ በደርግ ዘመን (ብሔር ባይኖራቸውም ) በሰፈር ነበር ጎራ ለይተው የሚደባደቡት። ተደባድበው ነፃ ያወጡትን ሰፈር ባይኖርም 'አራድነት' የሚባል የማይረባ ባህል አዳብረው ነበር። አራድነት ዋናው ሕጉ በብልጠት ላይ የተመሠረተ ነው ከ97ዓመተ ምህረት በኃላ ግን ፣ የአራድነት ሕግ በደፋርነት ሕግ ተሽሮ፣ዐዲስ ማንነት የጋለሞታዋን ሥነ -ልቡና ተቆጣጥሮአል።

ወደ'ዚያው የታክሲ ውስጥ ጥቅሳችን እንመለስ።ይሄኛው ደግሞ፣"በደህንነት ካሜራ ውስጥ መሆኖትን አውቀው የተጠየቁትን ለመክፈል ይዘጋጁ፣" ይላል። ደፋሩ የጋለሞታ ከተማ ሕግ-አውጪ የታክሲው አገልግሎት ተመንን ከደህንነት ካሜራ ጋር ያያያዘው ዝም ብሎ አይደለም። ደኀንነትም የሕዝብን ጉዳይ ሳይኾን፣ለእራሱ ጠባብ የብሔር ቡድን የፓለቲካ የበላይነት ሲሠራ እንደነበረው፣አስቀድመን የምናውቀውን፣አኹን ደግም፣ግልጽ ዕወቁለት እየተባለ እየተነገረለት ነው። ታክሲውም የሕዝብን ሳይኾን የእራሱን ፍላጎት አገልጋይ ነው።

የየሥነ ልቡና ዐይነተ ዘርፈ-ብዙ በመኾኑ፣መከታተልም ኾነ መረዳት ያዳግታል። ሥነ-ልቦናውን ወደ ቀላል የሐሳብ አምሳል (ሞዴል) ለመለወጥ ባደረኩት ሙከራ የተረዳሁትን እንደሚከተለው አስቀምጠዋለሁኝ።

በታላቂቷ ጋለሞታ ውስጥ በመሠረቱ ብሔር የለም፤ወይንም፣ቢኖርም፣ብሔር አይደለም ዋነኛው ነገር። በከተማይቱ ውስጥ በእርግጥና በተጨባጭ ያለው ኹለት መደብ ነው።

ከኹለቱ መደቦች አንደኛው በየትኛውም ብሔር ወይንም አስተሳሰብ ወይንም ሃይማኖት ቅርጽ ቢመጣ በመሠረቱ ፣ በየ በዩ መደብ ነው። ይሄ መደብ ከየትም አቅጣጫ ይምጣ፤ወይንም ሳይመጣ፤እዚያው በጋለሞታ ውስጥ ልብስ ውስጥ ይደግ፣ሚናው እና በምድር ላይ የሚኖርበት ምክንያት ለመብላት ነው። ለመብላት የሚያገለግሉትን የተለያዩ ቅርጾችን ይጠቀማል፣መሰላሎችን ያመቻቻል፣የተለያዩ ማርሾችን ይቀያይራል። ኹሌ ተጠቃሚ መሆን እና በጥቂት ልፋት ብዙ ትርፍ ማግኘት ነው ዋነኛ ግቡ። ኹለተኛው መደብ 'ተብዪው' ነው። የተበዪው ቁጥር ከበዪው በብዙ ዕጥፍ ይበልጣል። ተበዪው ህዝብ ነው። "ቢሞት ፣ቢሞት የማያልቅ!"ኹሌ፣እንደ 'ሳላይሰጥ' አጥንት፣አገላብጦ ላየው፣የኾነ የሚበላ ነገር ያገኝበታል። በዪው አበላሉን ያውቅበታል። ተበዪው ደግሞ እየተገላበጠ መበላቱን፣ሲበላ ጸጥ ብሎ ነው፣ሲጠየቅ ይከፍላል፣ተሰለፍ ሲባል ይሰለፋል፣የመብራት ካርድ ሲሞላ፣ባልታወቀ ምክንያት ቆጣሪው ብሩን በእስትሮ ሲጠጣበት፣ትንሽ ከማማረር በቀር፣አልበላም አይልም። በቃ፣ዝን
ተ አለም ለመበላት የተፈጠረ መደብ ነው። "the silent majority "ብለው ይጠሩታል ምሁሮች፤"እናንተ እስተካክላቹ ጥሩት፣እኛ እንበላዋለን፣"ይላል በዪው።

ለመብላት እንዲመች የተለያየ ስም ሲወጣለት ይቀልላል። ልክ የምግብ ሜኑ ላይ እንደሚጠራ የተለያየ የቄንጥ ስም። በተለያየ ቄንጠኛ ስም፣ያው፣ሥጋ ተሽሞንሙኖ ተጠርቶ እንደሚበላው። ለተበዪው፣የተለያየ ሲያወጡለት ለአበላል ይቀልላል።

አንዳንዴ "ደኻ" ብለው ይጠሩታል። ደኻ ብለው ሲጠሩት አንድ የአበላል እስታየል ይፈጥራል። በዪው፣ ድኻ ወዳጅ መስሎ፣በዳኻዊ ሥነ-ልቡና አንደቱ መጀመሪያ በልቶ፣ከዚያ ኪሱን ይደግመዋል። ዝምተኛው ብዙኃን ሲባልም እንደዚያው ነው፤ዘምተኛውን እንዳይናገር አፍኖ የመብያ ዘውግ ይፈጥራል። 'ሰፊው'ን ሕዝብ በሰፊው ለመብላት ለቆረጠ በላተኛ የሚጠቅም መርሐ -ግብር ይከፍታል።

ስለ'ዚህች ከተማ፤እንደ ነዋሪነቴ፣እንደ ተበዪ መደብነቴ ፣ የሚሰማኝ ብዙ ቢኾንም፣ለዛሬ ግን በመጠኑ የተነፈስኩት ይበቃል።


((( ሌሊሳ ግርማ )))💚💛

ምንጭ:- ፍትህ መፅሔት ጥር ቀን18 2011

መልካም የረፍት ቀን!!💚💛

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ምን ማለት እችላለሁ?
-------
መጥፋትማ እሳትም ቢሆን በልቶ ሲጨርስ ይጠፋል። ደግና ደግ ህዝብ ግን የተባይ እሳትን
ንዴት ቀድሞ ያጠፋል።
የአብሮነትና ህብራዊነት፣ የሰውነትና ፍትሃዊነት ሚዛን ልኩ የሚሰፈረው ቀን ሲከፋ
በሚወልደው ውጤት ነው።
ጉዱና መኣቱ የእኔ ሆኖ ሳለ ምን እላለሁ? ማፈር ብቻ። እኛ ኮ የጥርሳችን ንቅሳት ብልጫታ
በወዳቂዎች ገመና የሚገለፍጥ እንጂ ስለጭቅቅታችንና ቁልቁለታችን ለራስ አርምሞ
የሚሆን ራስን ማየትን አያውቅም።
ግንፉልና አንገት አልባ ትውልድ ጆሮው የፊትለፊት ከበሮን ጩኸት እንጂ የልቡን
የማስተዋል ምት በውል አይሰማም። ስለሆነም ሳቁም አያመሽ፣ ለቅሶውም አይቆም።

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
Forwarded from SPACE COMPUTER
በ"በመስተዋት ተጽእኖ " ፓለቲከኞቻችን ቢፈተሹስ?


ቻርሊ ቻፕሊን ዓለም የሚያውቀው በአስቂኝ (የኩምክና) አተዋወኑ ነው። በፊልሞቹ ውስጥ የሚያሳያቸው አካላዊ እንቅስቃሴዎች እና የሚፈፅማቸው በተንኮንል የተሞሉ ድርጊቶች ለሰው ልጅ የሳቅ ምንጭ ሆነው ዘመናትን ተሻግረዋል። በሀገራችን በየ-ሰፈራችን የማሳቅ ችሎታን የተካነ ሰው ሲገኝ፣ቻርሊ ቻፕሊን ተብሎ ይጠራ እንደነበርም አስታውሳለሁ። የቻርሊን ችሎታ በብዕራቸው ያደነቁም:-"ሰውን ለማሳቅ የተፈጠረ ሰው"በማለት ነበር። ነገር ግን፣የቻርሊ ማንነት በወጉ ሲፈተሽ፣ ሰውዬው ከዚህም የላቀ የፍልስፍና ጥበብን የተካነ እንደነበር የሚመሰክሩለት አሉ።ዓለም ግን የሚበልጥባት የማሳቅ ችሎታው ሆነ'ና ለፍልስፍናው ደንታ የሚሰጠው ዐጣ።ቢሆንም፣ለንግግር በተጋበዘባቸው መድረኮችና እና ለቃለመጠይቅ በተገኘባቸው ሚዲያዎች ላይ ቻርሊ ትልቅ ዐሳቢነቱን የሚመሰክርለት ነገር ሳይጥል አያልፍም ነበር። በዓለም ዙሪያ የምትታወቅለት ቀጣይ ንግግሩም ከእነዚሁ መድረኮች በአንዱ የተናገራት ነበረች:-"እውነተኛ እና ምርጡ ጓደኛዬ መስተዋት ነው፤ምክንያቱም፣እኔ ሳለቅስ እሱ በፍጹም አይስቅም።" (በእንግሊዝኛ ትጥመኛለች:-"my true best friend is a mirror ,because it never laughs when i cry.")

ምንም እንኳን ይህ የቻርሊ ንግግር ለሰፊው ሕዝብ ዘመናትን ተሻጋሪ እውነት የያዘ ቢመስልም፣በፓለቲከኞች ዘንድ ግን ተቀባይነቱ እምብዛም ነው። ሮበርት ግሪኔ "the 48 laws of power' በተሰኘው መጽሐፉ ውስጥ "መስታወት"ለፓለቲከኞች"እውነተኛና ምርጥ ጓደኛ" ሳይሆን፤ጠላቶቻቸውን ትጥቅ ማስፈቺያ እና አንበርክኮ ማስወገጂያ መሣሪያ ነው፣" ይለናል። ይህም መሣሪያ "የመስተዋት ተጽእኖ" (The mirror effect ) ተብሎ ይጠራል። ከጥንት ጀምሮ አንዱ ፓለቲከኛ ሌላውን ጥሎ ለማለፍ ሲጠቀም የኖረበት ዘዴ እንደነበርም ግሪኔ አክሎ ይነግረናል። እኔም ይህ ሀሳብ አሸነፈኝ። በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ፣"የመስተዋቱ ተጽእኖ" በሀገራችን ፓለቲከኞች ዘንድ ሲገለጥ የኖረ ዘዴ ሆነብኝ። ለማንኛውም "የመስተዋቱ ተጽእኖ"ምንነት እና አይነቶቹን ከታሪካዊ እውነታዎች ጋር አዛምደን እንቃኝ፤እግረመንገድ ደግሞ እናንተ የሀገራችንን ፓለቲከኞች በምናብ እየሞላቹሁ ተከተሉ።

በመጀመሪያ በዚህ እንስማማለን:-መስተዋት ለእኔ እና ለእናንተ እውነታውን (reality ) የሚያሳይ ቁስ ነው። ነገር ግን፣ስለዚህ ቁስ ያልተረዳነው ወይም የማያስማማን ነገር ደሞ አለ፤ይሄውም የሰው ልጅ አእምሮ መሸንገያ ጥሩ መሥሪያ መሆኑ ነው። ይህን ነው እንግዲህ "የመስተዋቱ ተጽእኖ"የሚሉት። ለጠቢብ ፓለቲከኛ የመስታወቱ ተጽእኖ ኃይል መሣሪያ ነው። መስተዋቱን በተቃዋሚዎቹ ሥነ-ልቡና ላይ ከፍ አድርጎ ይይዘዋል፤እነርሱን በመስተዋቱ ውስጥ የእራሳቸውን ቅዥት እና ምኞት ተመልክተው በዚያ ሲነሆልሉ እሱ ግን አሳፋሪ ድርጊታቸውን እንዲያስታውሱ የሚያደርገውን ምስል ያስከትላል፤በዚያም የእራሳቸውን ዋጋ እንዲተምኑ እያደረ ትምህርት ይሰጣቸዋል። የመስተዋቱን ተጽእኖ መቋቋም የሚችል ጥቂቱ ብቻ ነው። ብዙዎቹ በመስተዋቱ ውስጥ እራሳቸውን ተመልክተው ሲደሰቱ፤እግረመንገድ፣እየወደቁ እንደሆነ አይረዱም።


ለመሆኑ፣መስተዋት ፊት በትኩረት ስንቆም በእጅጉ እንደምንረበሽ የምናውቅ ስንቶቻች ነን?በእራሳችን የማንነት ነፀብራቅ ላይ እንደማፍጠጥ የሚያስጨንቅስ ምን አለ?ለዚህም ነው፣በመስተዋቱ ፊት ስንቆም የምናየው ማየት የምንፈልገውን ብቻ ነው።በፊታችን ላይ የወጣ አስቀያሚ ነገርን ማየት አንሻም። እንደዚያ ብናደርግ፤ከመስተዋቱ ፊት ዞረን ስንሄድም፣ተከትሎን በመሄድ ሲረብሸን ይውላል። በአንጻሩ፣የመስተዋቱ ተጽእኖን በሰዎች ላይ ፈጥረን እንዲረበሹ፣እንዲያዝኑ፣እንዲበሳጩ፣ብሎም እጃቸውም በሽንፈት እንዲሰጡ እንጠቀምበታለን። ወደ ፓለቲካው የሥልጣን ጨዋታ ሲመጣ ደግሞ አራት አይነት የመስተዋት ተጽእኖዎች እናገኛለን።


የመጀመሪያው #"የማለዘቢያው ተጽእኖ"(The Neutral -izing effect ) ነው።በጥንቱ በግሪክ አፈታሪክ ጎርጎን ሜዶሳ እጅግ አስፈሪ ገጽታ የተላበሰች ፍጡር እንደነበረች ይታመናል። ገላዋ በፀጉር የተሸፈነ ፣ተርገብጋቢ ምላስ፣የሾሉ ጥርሶች፣እና አስፈሪ ገጽታ የተላበሰን እባብ ትመስል ነበር።ሕዝቡም በታላቅ ፍርሐት ይርድላት ነበር።ወደ እርሷ ለአፍታ እንኳን የተመለከተ በድንጋጤ ደርቆ ይቀራል እንጂ አይተርፍም። የግሪክ ሕዝብ በዚህ ዓይነት ጭንቅ ተይዞ በነበረበት ዘመን ግን ከመካከላቸው አንድ ጀግና ተገኘ፤ ፔርሰስ ጀግናው ሕዝቡን ያስጨነቀችውን ሜዶሳን መግደል እችላለሁ አለ። ሕዝቡም ጸለየለት መረቀው'ናም ወጣ።

ፔርሰስ ሰይፋን ስሎ በአንድ እጁ ይዟል፤ በሌላው እጁ ደግሞ መስተዋቱን። ከሜዶሳ ፊት ሳደርስ ከመስተዋቱ ጀርባ እራሱን ጋረደ'ና መልኳን እንድታይበት ከፍ አድርጎ ያዘላት። ሜዶሳ ለመጀመሪያ ጊዜ በመስተዋቱ ውስጥ ፊቷን ተመለከተች። መርበትበት ያዛት፣ድንጋጤው አደረቃት። በዚህ ጊዜ ፔርሰስ ቀልጠፍ ብሎ ሰይፉን መዘዘ'ና ከአንገቷ ጋር አገናኘው። የሜዶሳ ጭንቅላት ከመሬት ተንከባለለ፣ሕዝቡም ከፍርሃት ባርነት ወጣ።

የማለዘቢያ ተጽእኖ ተቃዎሚህን በመስተዋቱ ውስጥ ማንነቱን እንዲያይ በማድረግ ተጽእኖ መፍጠሪያ'ና ማጥፊያው ጥበብ ሲሆን፣ተቃራኒው ደግሞ "ጥላ" ይባላል። ተቃዋሚህ እንዳያይህ ተጠንቀቅ ጥላውን መከተል ነው። ጥላውን ተከትለህ የገባበት እየገባህ ዕቅዱን ትፈትሻለህ፤ፍላጎት እና ልምዱንም እንዲሁም ትረዳለህ። ከዚያም እርሱን ለማንበርከክ ቀላል ነው።

ሁለተኛው ዐይነት ደግም#"የናርሲስ ተጽእኖ " (The Narcissus effect ) ይባላል። በግሪክ አፈታሪክ ናርሲስ ወጣት እና መልካም እጅግ የተዋበ ነበር። ይሁን'ና፣ክፋ ልማድ ደግሞ አለበት። በመንደሩ አቅራቢያ በምትገኝ ሐይቅ ዘወትር ማለዳ እየሄደ በውሃው ውስጥ ከሚመለከተው የእራሱ ምስል ሲጫወት ይውላል። እያደር ከዚህ ምስል ጋር በፍቅር ወደቀ።በአንድ አፍታ ከውሃው ውስጥ ወጥቶ እንዲያቅፈው፣እንዲዳብሰውም ይለምነው ጀመር።አንድ ቀን ናርሲስ ፍቅሩን መቋቋም ከማይችለበት ደረጃ ደረሰ፤በፍቅር የወደቀለትንም ምስል ሊያቅፈው ወደ ጥልቁ ውሃ ዘለለ። በዚያም ፍጻሜው ሆነ።
ፓለቲኛ አንድ ጠንቅቆ ማወቅ ያለበት፣ሰዎች ሁሉ እንደ ናርሲስ ተመሳሳይ ባህሪይ ያላቸው መሆኑን ነው። የሰው ልጅ ከእራሱ ጋር በፍቅር ወድቆ የሚሰቃይ ፍጡር ነው። ስለ'ተሸነፈበት ፍላጎቱ ሲል የማይሆነው ነገር የለም። ይህ ፍላጎቱ ገንዘብ፣ሴት፣ሥልጣን ሊሆን ይችላል። ጠቢብ ፓለቲከኛ ሆይ፣ተቃዎሚህ ፊት የምታቆመው መስተዋት የናርሲስ ተጽእኖ እንዳለበት የሚያረጋግጥለት ይሁን፤በዚህም፤እውነተኛ ፍላግት እና ሕልሙን በቀላሉ ትረዳለህ። ከዚያ በኃላማ፣ከተቃዋሚህ ጀርባ ቆመህ፤የተሸነፈለት ምስሉን እያሳየህ፣በትንሹ ወደ ሐይቁ መገፍተር በቂ ነው፤በቀላሉ ይሰጥማል።
ሦስተኛው #"ግብረገባዊ ተጽእኖ "(The moral effect ) ይባላል። አኹንም፣ጠቢብ ፓለቲከኛ ይህን ያስታውሳል:-"እውነት በደፈናው ትታያለች፤የምትደመጠው ግን አንዳንዴ ብቻ ነው።" በግብረገባዊ ተጽእኖ ተጠቅመህ ሰዎች ፊት የምታቀርበው መስተዋት ዓላማው ተቃዎሚዎችህ በአንተ ወይም በሕዝቡ ላይ ያደረጉትን እንዲያስታውሱ ማድረግ ነው። በዚህም፣ጥፋታቸው እንዲሰማቸው፣እንዲፀፀቱ ታደርጋለህ። ከባህሪያቸው ክፋት የተነሳ፣የፈጸሙትን ክፋ አድራጎት እንዲረዱት'ና እንዲያፍሩበት፣ብሎም እንዲማሩበት ይህን'ግብረገባዊ ተጽእኖ' የተባለ መስተዋት ከፊታቸው ታኖራለህ። ከዚያም፣ከድርጊታቸው መጠን፣አንተም መልሰህ ታደርግባቸዋለህ። ግብገባዊ ተጽእኖ ተቃዋሚዎችህን ለመቅጣት ብቻ ሳይሆን፤እነርሱም ሆኑ ሕዝቡ የአንተን ቅጣት ተገቢነት እንዲያምኑበት የሚያደርግ ኃይል አለው'ና ሞክረው።

የመጨረሺያው # "የመስታወት ተጽእኖ " ዐይነት "የማቀዥት ተጽእኖ " (The hallucinatory effect ) ይባላል። መስተዋት እጅግ አሳሳች መሆኑን አትዘንጋ። በመስተዋቱ ፊት በቆምክ ጊዜ የምታየው መልክህ እና ሰዎች የሚነግሩህ መልክህ የተለያዩ ናቸው። ጠቢብ ፓለቲከኛ በተቃሚዎቹ ፊት መስተዋቱን ሲያቆመው እራሳቸውን እና ዓለምን በውስጡ የሚመለከቱ ይመስላቸዋል፣ነገርግን፣የሚመለከቱትን መስተዋቱን እኮ ነው! መስተዋቱ ከፊታቸው በተነሳ ጊዜ፣በሚያዩት ግራ ይጋባሉ። መስተዋቱ የሚፈጥርባቸው "የማቃዥት ተጽእኖ " የሚባለውም ይሄው ነው። በመስተዋቱ ውስጥ ተቃዎሚህ እንዲመለከተው የምታደርገው ሁሉ የነገሩ፣የቦታው፣የግለሰቡ ማንነት ነጸብራቅ መሆኑን ዘንግቶ፣እውነተኛውን ነገር ይህ ነው ብሎ እንዲቀበለው ማሳመን ነው። በመስተዋቱ ውስጥ የሚመለከተው ቅዥት ፈጥረህበት ስታበቃ፣አንተ በእውነተኛ ማንነቱ ጠልፈህ ትጥለዋለህ።



ደራሲ ሐዲስ ዓለማም'ፍቅር እስከ መቃብር ' ውስጥ እመት ውድነሽ፥ ያናገሩት እውነት ይህኑን "የመስታወቱን ተጽእኖ " ያስታውሱናል። እመት ውድነሽ ከመስተዋቱ ውስጥ ብቅ ካለችው "ሴት"ጋር እንደልባቸው ተጫውተው ሲጨርሱ ደንግጠው ይነቃሉ፤ምናልባት፤ሰው አይቶኝ ይሆን?ብለው ነው። በመጨረሻም እንዲህ አሉ:-"ለካ ሰውን እብድ የሚያሰኘው እብድ የሚያደርገውን ማድረግ አይደለም፤ እብድ የሚያደርገውን ሲያደርጉ መታየቱ ነው።" ጠቢብ ፓለቲከኛ በተቃዋሚ ፊት መስተዋቱን የሚያኖረውም ለዚሁ ነው:-የደበቀውን እብደት በአደባባይ አጋልጦ ፍርድ መስጠት!!!!

#ኃይለጊዮርጊስ ማሞ (ጲላጦስ)💚💛

ምንጭ:- ፍትህ መፅሔት ቁጥር 13 (ጥር 24/05/2011)


ሸጋ ምሽት!!💚💛
@wegoch
@wegoch
@balmbaras
#Art_exhibition
Live music
Fashin show
Salsa dance

February 23
@ marriott excutive apartment

I care fund risinng event

@gebriel_19
@seiloch
@seiloch
ዴዝዴሞና
Written by መሐመድ ኢድሪስ

ከረፋፈደ በኋላ ነበር የትያትር ቤቱ የኋላ ረድፍ ላይ ቦታ ይዞ የተቀመጠው፡፡
የያዘው ክፉ የፍቅር ልክፍት ነው በዚህ ቲያትር ቤት ውስጥ እንዲገኝ
ያደረገው፡፡ ለሼክስፒር የተውኔት ድርሰቶች ፍቅርና ስሜት ኖሮት አያውቅም፡፡
እሱ ፍቅር የያዘው ከገፀባህሪዋ ስም ጋር ሞክሼ ስም ካላት የራሱ ዴዝዴሞና
ጋር ነው፡፡ ክፉ የቅናት ዛር መንፈሱን ከተቆጣጠረው ረጅም ጊዜ አስቆጥሯል፡፡
እርዳታ ፍለጋ ሃኪም ጋር ሄዶ “ፓራኖያ አለብህ” ተብሏል፡፡ ከወንድ ጋር ያያት
ሴት ሁሉ እስዋ ትመስለዋለች፡፡ ከንግግርዋ፣ ከአዋዋልዋ፣ ከአመሻሽዋ፣
ከአለባበስዋ፣ ከጓደኞችዋ፣ ከቤተሰቦችዋ፣ከትናንት ታሪክዋ ጋር የተገናኘ
የቅናት መንፈስ ተጠናውቶታል። ስልክ ስታወራ በቅናት ልቡ ይመታል፡፡ ትንሽ
ካመሸች ጓደኞቿ ጋር ሁሉ እየደወለ ወይም እየሄደ ሊሰልላት ይሞክራል፡፡
ባልና ሚስት ሳይሆኑ ሌባና ፖሊስ ናቸው፡፡ ሌላው ቀርቶ በእንቅልፍ ልብዋ
የሆነ ነገር ብታልጎመጉም፣ በሱ ነገር እየተጨነቀ፣ ፍችውን ለማወቅ ሲባዝን
ያድራል፡፡
ለእሷ ካለው እውር ጭፍን ፍቅር የተነሳ “ኦቴሎ”ን ሊያይ ቲያትር ቤቱ
የመጨረሻ ወንበር ላይ ቢሰየምም፣ መጋረጃው ተገልጦ ቲያትሩ የጀመረው
ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ነበር፡፡
ቃሲዮን ሲያይ፣ እጁን ቡጢ ጨበጠ፡፡ ይሄ ነው ሚስቴን ሲዳራ የሚያድረው
እያለ ጥርሱን በቁጣ ያፋጫል፡፡ ኢያጎ ለኦቴሎ በመሰሪ ቋንቋው የዴዝዴሞናን
አለመታመን በጆሮው ሲያንሾካሹክ፣ እሱም ከኦቴሎ ከራሱ በላይ ቁጣው
ገነፈለ፡፡
ወደዚህ ቲያትር ቤት ለመግባት ዋና ምክንያቱ፣ ፍቅረኛው ትላንት በስልክ
ከወንድ ጋር ስትቀጣጠር በመስማቱ ነው፡፡ ሁሉንም ንግግር በትክክል
ባይሰማም “ማዘጋጃ” እና “አስር ሰዓት” የሚሉት ቃላት ግን አላመለጡትም፡፡
ኦቴሎ በኢያጎ ስብከት በቁጣ ሲንጎራደድ፣ ድንገት አይኑ ውስጥ ገባች፡፡ ፊት
ካለው ረድፍ ወንበር ላይ አንድ ጎረምሳ እጁን ትከሻዋ ላይ ጣል አድርጎ
ተቀምጧል፡፡
እሷ ለመሆንዋ ምንም ጥርጥር የለውም፤ ምክንያቱም ከአመት በፊት
የገዘላትን ሻሽ አንገትዋ ላይ ጣል አድርጋዋለች፡፡ ረጅም ፀጉርዋንም ቢሆን
አሳምሮ ያውቀዋል፡፡ እንዴት የሚስቱ ፀጉር ይጠፋዋል፡፡ ቢሆንም የማይቀና
ጥሩ ባል ለመሆን በመሞከር፣ ስልኩን ከኪሱ አውጥቶ ቁጥርዋን መታ፡፡
ይጠራል፡፡ ግን አይነሳም፡፡ ሻሹን በደንብ አስተዋለ፡፡ ራሱ ነው፡፡ የሚያያት
ከጀርባዋ ቢሆንም፣ ከት ብላ ስትስቅ፣ ሰውየውም አብሯት ሲስቅ ተመለከተ።
አሁንም ደግሞ ደወለ፡፡ ሶስቴ ከጠራ በኋላ “የደወሉላቸው ደንበኛ ስልክ ጥሪ
እያስተላለፈ ነው” አለች፤ ኦፕሬተርዋ፡፡
እሱ ላይ ስልክ እየዘጋች ከማንም ውርጋጥ ጎረምሳ ጋር ስታስካካ ሊታገስ
አልቻለም፡፡ ሜሴጁን ማዥጎድጎድ ጀመረ፡፡
“አንቺ ውሻ፣ ሸርሙጣ፣ ድሮስ ማን ይፈልግሻል!” አንዱ ነው፡፡
ቲያትሩ ሊጠናቀቅ ተቃርቧል፡፡ ኦቴሎም የዴዝዴሞና አልፍኝ ለመግባት
እርምጃውን ጀምሯል፡፡
ሁለተኛውን ሜሴጅ ጻፈ፡፡
“በረጅም እንጨት አልነካሽም፡፡ ድሮስ እኔ አላቅሽም ወዘተረፈ …”
ለሃያ ደቂቃ ያህል ስምንት ሜሴጆችን አከታትሎ ቢጽፍም፣ የፍቅረኛው ሜሴጅ
የመጣው ግን ዘጠነኛውን ሊጽፍ ሲያስብ ነበር፡፡
እንዲህ ይላል፡-
“ረስተኸው ይሆናል፡፡ እኔ ግን አልረሳውም። ዛሬ የተገናኘንበት ቀን ነበር፡፡ ልክ
በዛሬው ዕለት፣ ከአራት አመታት በፊት፣ ምሽቱን ወጣ ብለን እንድናሳልፍ
አስቤ ነበር፡፡ ስጦታም አዘጋጅቼልሃለሁ፡፡ ከአራት ዓመት በፊት ለገዛህልኝ ሻሽ
እሺ ያልኩህ ጊዜ ትዝ ይልሃል፡፡ የኔ ፍቅር፤ የገዛሁልህን ሮሌከስ ሰዓት፣
ማዘጋጃ ቤት አጠገብ ካለው ስዊዝ ሰዓት ቤት ውሰድ፡፡ የኔ ፍቅር ደህና ሁን፡፡
በፍጥነት ተነስቶ እየተንደረደረ፣ ወደ ፊት ወንበሮች አመራ፡፡ ሻሹን እያየ ወደሷ
ቀረበ፤ አጠገብዋ ሲደርስ ፊትዋን በእጁ አዞረው። ዴዝዴሞና አልነበረችም፡፡
ሁለቱ ፍቅረኞች በድንጋጤ ፈጠው እያዩት ነበር፡፡
ኦቴሎ ዴዝዴሞናን ያነቀው በዚያ ቅፅበት ነበር፡፡

ሸጋ ጁምኣ!!💚💛

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ፎቶ በመላክ ሦዕል ለማሳል።
በ +251984740577
ወይም @gebriel_19 order ማድረግ ይቻላል።

@seiloch
@seiloch
የአማልፊዋ ወጣት
Written by መሐመድ ኢድሪስ

ከኡማ ጋር አስር ሰአት ላይ ቀጠሮ ነበረኝ። እዛው እስዋ የምትማርበት ኮሌጅ
አጠገብ ያለ ፌርማታ ጋ ነበር የተቀጣጠርነው፡፡ ዘወትር ወደምንሄድበት
መናፈሻ፣ በዘጠኝ ቁጥር አውቶብስ ለመሄድ ነው ያሰብነው፡፡ ወርቃማ
ፀጉርዋንና ውብ ሰማያዊ አይኖችዋን ለማየት ከመጓጓቴ የተነሳ ዘጠኝ ሰአት
ተኩል ነበር የደረስኩት። ቦታው ጭር ያለ ሲሆን ብዙ የመኪና ግርግር
አይታይበትም፡፡ በምስራቅ ሳንላጀሮ፣ በደቡብ ኮንካ ዲማሬኒ፣ በሰሜን
ምስራቅ ራቬሎ ማናሮ የሚያዋስናት አማልፊ ኮስት፤ በሎሚ እርሻዎቿም
ትታወቃለች፡፡ ከኡማ ጋር ከተዋወቅን ዘጠኝ አመታት ቢያልፉም፣ የፍቅር
ግንኙነት
የጀመርነው ግን ከአንድ አመት በፊት ነበር፡፡ ያን ቢጫ ቱታዋን ለብሳ ስፖርት
ስትሰራ ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ ያየኋት፡፡ አንድ ሸበቶ ፀጉር ያላቸው በደንብ
የለበሱና ከዘራ የያዙ አዛውንት መጥተው አጠገቤ ተቀመጡ፡፡ ዕድሚያቸው
በግምት ወደ ስድሳ አምስት ይጠጋል። ነጭ ሙሉ ሱፍ፣ ከቡናማ ሸሚዝ ጋር
አስማምተው ለብሰዋል፡፡ ወርቃማ ህብር ያለው ቢራቢሮ ከረቫት አስረው፣
ነጭ ባርኔጣ ደፍተዋል፡፡ ጫማቸው በደንብ የተወለወለ ሲሆን የሥነ ፅሑፍ
ተማሪ በመሆኔ ሰውየው ሰብአዊ ፍጡር ብቻ ሳይሆኑ ገፀ ባህሪ ጭምር
መስለው ታዩኝ፡፡
ምን ዓይነት ገፀ ባህሪ ይሆኑ፡፡ በጣም ሃብታምና የተካበደ ሳይሆን ቀለል ያለ
አኗኗር የሚመሩ፡፡ እንዲህ ዓይነት አለባበስ ለብሶ አውቶቡስ የሚጠብቅ
ሰው አይቼ ስለማላውቅ ነው፣ ስለሳቸው እንዲያ የገመትኩት፡፡
“ሶስት ቁጥር አውቶቡስ አልፋለች?” ሲሉ ጠየቁኝ፡፡
“ከመጣሁ ጀምሮ አላለፈችም” መለስኩኝ፡፡
“ከመጣህ ስንት ጊዜ ሆነህ?”
“ወደ ሃያ ደቂቃ ገደማ” በጥያቄው እየተገረምኩኝ፡፡
“ሶስት ቁጥርን ነው የምትጠብቀው?”
“አይ እኔ እንኳን ዘጠኝ ቁጥር ነው የምጠብቀው”
ሁለታችንም ዝም ብለን ተቀመጥን፡፡ ያጋጣሚ ነገር ሆነና፣ ወዲያው ዘጠኝ
ቁጥር አውቶቡስ መጣችና ፌርማታው አጠገብ ቆመች፡፡ ሰውየው ዞር ብለው
አዩኝና፤ “መጣችልህ” አሉኝ፡፡ አዛውንቱ ያልገባቸው ነገር አለ፡፡ እኔ ኡማን
ሳልይዝ አልሄድም፡፡
“አይ ትለፈኝ” አልኩኝ፤ በመጠኑ አፈር እያልኩኝ፡፡
በሩን ዘግቶ ሄደ፡፡
“እንግዳ ነገር ነው” አሉ፡፡
“አይ የምጠብቀው ሰው ስላለ ነው” አልኩኝ ፍርጥም ብዬ፡፡
“ሴት ናት?” ፈገግ አሉ፡፡
“እ…አዎ” እያመነታሁ፡፡
“እንግዲያማ እንዳንተ አይነት ጀግና ወጣት፣ እንዴት መንገድ ፌርማታ ላይ
ሊጠብቅ ይችላል?”
እኔ ስለ ሰውየው ስገምት፣ ሰውየው ግን ስለኔ ማወቃቸው ገረመኝ፡፡
“አያስደንቅም፡፡ ሁላችንም ያለፍንበት ነው፡፡ ወጣት ወንዶች---ማለት እንዳንተ
አይነት ተማሪ፣ የገንዘብ ችግር ሊኖርበት ስለሚችል፣ ፍቅረኛውን ፌርማታ
ጋ ቢቀጥር አያስገርምም”
እዚህ ላይ እንኳ ተሳስተዋል፡፡ ባይበዛም የተወሰኑ ሺ ሊሬዎች ይዤ ነበር፡፡
“ቀድመህ መገኘትህ ትክክል አድርገሃል፡፡ በምንም መንገድ ሴትዋን ማጣት
የለብህም፡፡ አንዴ ካጣሃት እንደገና ለማግኘት በጣም አስቸጋሪ ነው” አሉኝ፡፡
“እንዴት?”
“እኔ ላይ ስለደረሰብኝ ነው፡፡ እንደምታውቀው አማልፊ በሎሚ እርሻዎችዋ
ትታወቃለች፡፡ እና ወሲብ የጀመርኩት በአስራ ስድስት አመቴ ነበር፤ አስራ
ዘጠኝ አመት ከሞላት የጎረቤት ልጅ ጋር፡፡ መጀመሪያ እንደ ጓደኛ ነበር
የምንተያየው፡፡ አንድ ቀን ቤቷ ስሄድ ቤተሰቦችዋ ሁሉ እቤት አልነበሩም፡፡”
አሉና ጭልጥ ብለው በሃሳብ ተጓዙ፡፡
“ከዚያስ?” ጠየቅኩኝ፤ቀጣዩን ለመስማት እየጓጓሁ።
እንደመባነን አሉና፤ “ና አንድ ነገር ላሳይህ አለችና፣ ከመደርደርያው ላይ አንድ
ግማሽ የደረሰ የጂን ጠርሙስ አንስታ፣ ሁለት ብርጭቆ ላይ ቀዳች፡፡
ከዚያም ሁለት ትልልቅ አረንጓዴ የሎሚ ፍሬዎችን ቆርጣ ከጨመቀችበት
በኋላ ብርጭቆዋንና ብርጭቆዬን አጋጨች፡፡ ጠጣሁት፡፡ ትንሽ ቆይቶ
ሰውነቴን ሁሉ
ሲነዝረኝ ተሰማኝ፡፡ ከት ብላ ሳቀችና እንደገና ብርጭቆዎቻችን ሞላችና
አሁንም ሎሚ ቆርጣ ከጨመቀች በኋላ እንደገና አብረን ጨለጥነው፡፡ ከዚያ
በኋላ
ራሴን ያገኘሁት የሷ አልጋ ላይ ነበር፤ ሁለታችንም እርቃናችንን ሆነን፡፡ እንደዚያ
አይነት ወሲብ በመላው አለም ተደርጎ የሚያውቅ አይመስለኝም--”
ብለው ትካዜ ውስጥ ገቡ፡፡
“እባክዎትን አያቋርጡ” ለመንኳቸው፡፡
“እንደነገርኩህ ዋናው ነገር ሴትዋን ማጣት የለብህም፡፡ በፍቅር ከነፍን፡፡
ሁልጊዜ ከወሲብ በፊት ጂን በሎሚ መጠጣት አይቀሬ ሆነ፡፡ በሁለተኛው
አመት ኔፕልስ ኮሌጅ መግባት ነበረብኝ፡፡ በዚህ አጋጣሚ ለሶስት አመት
መለያየት የግድ ነበር፡፡ ከሶስት አመታት በኋላ እኔ የአስራ ዘጠኝ አመት፣ እሷ
የሃያ ሁለት ዓመት ጎረምሶች ሳለን፣ ኔፕልስ መጣችና ተገናኘን፡፡ የደረሰችው
በእኩለ ሌሊት ስለሆነ ሱቆችም ሱፐር ማርኬቶችም ዝግ ነበሩ፡፡ አንድ ክፍት
ግሮሰሪ ብቻ ነበር፡፡ ለረዥም ሰዓት ተቃቅፈን ከተሳሳምን በኋላ ልጋብዛት ወደ
ግሮሰሪው አመራን፡፡ የሚበላ ነገር ቀማምሰን፣ ጂን በሎሚ አዘዝን፡፡
“ጂን ቢኖርም ሎሚ ግን እንደሌለ አስተናጋጅዋ ነገረችን፡፡ ጂኑ ተቀዳና
ቀመስኩት፡፡ አጥወለወለኝ። እሷንም ሳያት ፊትዋ ኮሶ መስሏል፡፡ ሁለታችንም
ተግባባን፡፡ መጣሁ አልኩና ወጣሁ፡፡ ወዴት ነህ ብላ አልጠየቀችኝም፡፡
ምክንያቱም የት እንደምሄድ ታውቃለች፡፡ ክፍት ሱቅ ፍለጋ ማሰስ ጀመርኩ፤
ሁሉም ዝግ ነበር፡፡ ከሩቅ አንድ የበራ መብራት አየሁ። ልቤ እየመታ በፈጣን
እርምጃ መራመድ ጀመርኩ። ወደ መብራቱ እየቀረብኩ ነው፡፡ ስደርስ የሱቁ
በር ከውጭ በትላልቅ የሰረገላ ቁልፎች ተከርችሟል፡፡ ከዚያ ሱቅ ውጭ
ከተማው ሁሉ ኦና ሆኖ ጭር ብሎ ነበር። እንኳን ክፍት ቤት ሊኖር ቀርቶ የሰው
ዘር የለም። በፍርግርጉ የብረት መዝጊያ በመስተዋቱ ውስጥ የሱቁ
ሸቀጣሸቀጦች ሁሉ ይታዩኛል፡፡ የወተት ተዋፅኦ፣ ልኳንዳው፣ ለስላሳ መጠጡ፣
አልኮሉ፣ ፍራፍሬው---ከሁሉም በላይ ግን በግምት ሁለት ሳጥን የሚሆን
ትኩስ ትላልቅ አረንጓዴ ሎሚዎች---” አሉና ፈዘው ቀሩ፡፡
በመገረም አፌን ከፍቼ ቀርቻለሁ፤ “ከዚያስ?” አልኩኝ፤ በደከመ ድምፅ፡፡
“ሎሚዎቹን እያየሁ ፈዝዤ ቀረሁ፤ በሎሚዎቹ ውስጥ ግን እሷን ነበር
የማየው፡፡ አይኔ እንባ አቅርሮ እዛው እንደተገተርኩ ሁለት ፖሊሶች መጡ፡፡
“ምን ታረጋለህ?” ጠየቁኝ፡፡
“ሎሚ ልገዛ ነበር” መለስኩ፡፡
“ተዘግቷል! ቀጥል!”
እያዘንኩ ተመለስኩ፡፡ ግሮሰሪው ውስጥ ቁጭ ብላ ነበር፡፡ ምንም ሳንነጋገር
አንገታችንን ደፍተን ወደ ማደርያችን ሄድን፡፡ በነጋታው ጠዋት የማይታለፍ
የስራ ቀጠሮ ስለነበራት አማልፊ መመለስ ነበረባት፡፡ ምንም ፍቅርም
ወሲብም ሳንሰራ እንቅልፍ በአይናችን ሳይዞር ነጋ፡፡ ጠዋት ላይ ሸለብ
አደረገኝ፡፡ ስነቃ አልጋው ላይ የለችም፡፡ ኮሞዲኖው ላይ ግን አንድ ወረቀት
ነበር፡፡ ነገሮች ሲመቻቹ እመጣለሁ፡፡ ጠብቀኝ ይላል፡፡ የኮሌጁ ትምህርት ብዙ
ስላልተሳካልኝ ወደ ንግድ ገባሁ፡፡ አንድ ሱቅ ተከራየሁ፡፡ እቃ ስሞላ
የመጀመሪያው ዋናው ነገር ግን ሎሚ ነበር፡፡ ሱቁ እየተስፋፋ መጣ፡፡ ትርፉ
በጣም እየጨመረ
ስለመጣ፣ አሉ ከተባሉ የሎሚ ገበሬዎች እየወሰድኩ ሎሚ አከፋፋይ ሆንኩኝ፡፡
አማልፊ መጣሁና ብዙ ሄክታር መሬት የሎሚ እርሻ. አለማሁ። … እዚሁ
አማልፊ የሎሚ የታሸገ መጠጥ ፋብሪካ የከፍትኩት በዚያን ጊዜ ነበር…”
ሶስት ቁጥር አውቶብስ መጥታ ፌርማታው አጠገብ ቆመች፡፡
“ልጄ አደረቅኩህ ሰላም ዋል፡፡” አሉና ፈጠን ብለው ወደ አውቶቡሱ ውስጥ
ገቡ፡፡ የታሪኩን መጨረሻ ለማወቅ ተከትያቸው ወደ አውቶቡሱ ልገባ
ስል፤“ቻዎ …” አለችኝ ኡማ፤ ዞር ብዬ ሳያት ጉርድ ቀሚስ ለብሳ፣ ሎሚ
እየመጠጠች ነበ
ር፡፡
አንዴ እሷን፣ አንዴ ሽማግሌውን አፈራርቄ ተመለከትኩ፡፡ ፈገግ ብለው እያዩኝ
ጣታቸውን እሷ ላይ ቀሰሩ፡፡ “ዋናው ነገር ሴትዋን ማጣት የለብህም” እያሉ
እንደሆነ ገባኝ፡፡
እኔና ኡማ ፌርማታው ጋ ተቀምጠን ዘጠኝ ቁጥርን ስንጠብቅ፣ አዛውንቱ
የሎሚ ከበርቴ ለመሆን ያደረሳቸውን ጉዳይ እያሰብኩ ነበር፡፡ እንዲያ
ተዘጋጅተው
ግን ያቺ የሚጠብቋት ሴት መጥታላቸው ይሆን? አልኩ፡፡---

ሸጋዋ!! የኔዋ ቅዳሜ!!💚💛


@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ጃምቦ ከሞት ተነስቷል !
(አሌክስ አብረሃም)

አንድ ቀን በጧቱ አንድ የሰፈራችን ህጻን ልጅ በራችንን አንኳኳና <<አቡቹ ጃምቦ በፍጥነት
እፈልግሃለሁ ይልሃል ብሎ ተፈተለከ>> ቤተሰቡ ተጨነቀ ! እኔም ንስሃ ገብቸ ከቤቴ
ወጣሁ ! ጃምቦ መንደር ያንቀጠቀጠ ዱርየ ነው! ገና አጠገባችሁ ሲቆምና የገደል ስባሪ
የሚያህል ሰውነቱ ጥላ ሲያርፍባችሁ ሰማይ ምድሩ ይጨልምባቹሃል! ጃምቦ ጋር ተጣላሁ
ብሎ ፖሊስ መጥራት ጃምቦን መሳሪያ ማስታጠቅ ነው! እውነቴን ነው ፖሊሶቹን ጠረቃቅሞ
መሳሪያቸውን ከመቀማት የማይመለስ ጠረንገሎ ! እና ጃምቦ ጠራኝ ወገኖቸ !
እግሬ እርስ በርስ እየተጋጨብኝ እንደምንም ሁልጊዜ የሚቀመጥበት ድድ ማስጫ ስደርስ
እንዲህ ሆነ ! በዛ እድሜ ግጥም ስነጽሁፍ ምናምን እንደምሞካክር ሰምቶ ኑሮ መዓዛ
ለምትባል ታች ሰፈር ለምትኖር አባቷ መቶ አለቃ ለሆኑ ልጅ የፍቅር ደብዳቤ ጻፍ ብሎ
አዘዘኝ ሰኔና ሰኞ ሲገጥም ጥበብና ጃምቦ እኩል ይጠራሉ ! እስክርቢቶና ወረቀቴን አዘጋጅቸ
የሚለውን መጻፍ ጀመርኩ <<አንችን ካየሁሽ ጀምሮ ጸሃይ በመሬት ዙሪያ እንደምትዞር
ዞረብኝ >> በልና ጻፍ አለኝ <<ጃምቦ ጸሃይ አትዞርምኮ መሬት ናት በጸሃይ ዙሪያ
የምትሽከርከረው>> ብየ በትህትና የአምስተኛ ክፍል የጅኦግራፊ ተሞክሮየን አካፈልኩ !
ወዲያው ግን የሆነ ነገር ጓ ካለ በኋላ ጸሃይም መሬትም ደመናም እኔ ራሴም በጃምቦ ዙሪያ
መሽከርከር ጀመርን ከዛን ቀን ጀምሮ ጀኦግራፊ የሚባል ትምህርትና የፍቅር ደብዳቤ
አስጠላኝ !
እንደዛ የጃንቦን ኩርኩም ተቋቁሜ የጻፍኩትን የፍቅር ደብዳቤ ለመዓዛ እንድሰጥ ራሴን
ላከኝ! ወይ ጣጣ ይታያችሁ የመዓዛ አባት ጡረታ ከወጡ ጀምሮ ዋና ስራቸው በረንዳ ላይ
ተቀምጠው ሽፍታ ገድለው መንግስት የሸለማቸውን ማካሮቭ ሽጉጥ እየወለወሉ ስድስት
ቆንጆ ሴት ልጆቻቸውን መጠበቅ ነው! ከፊት እሳት ከኋላ እሳት ይሁን ዱርየ ከሚገለኝ
አገራቸውን አገልግለው ጡረታ የወጡ መቶ አለቃ ይግደሉኝ ሞቱም ስም አለው ብየ
የግቢያቸውን በር አንኳኳሁ ! በሩ ድንገት ተከፍቶ በጣም ቆንጆዋ የመዓዛ ታናሽ እህት ሳራ
<<አቡቹ በጧቱ ከየት ተገኝህ>> አለችኝ ! ቀጥላም መዓዛን መፈለጌን ስነግራት አባቷ ጋር
ዘመድ ጥየቃ መሄዳቸውን ነገረችኝ !
ጃምቦ ታዲያ መልሱን ስነግረው ትንሽ አሰበና ደብዳቤውን ከጀ ነጥቆ ከፋፍቶ ትንሽ
ካነበበው በኋላ <<መዓዛ>> የሚለውን ስም እየሰረዝክ ሳራ በሚል ተካው>> አለኝ !
ተካሁት ! ሂድና ለሳራ ጃምቦ ነው በለህ ስጣት አለኝ ! ሂጀ ሰጠኋት ! ሳራና ጃምቦ ጓደኛ ሆኑ
ጃምቦ ምን ይሳነዋል!
የሆነ ጊዜ ታዲያ <<ጃምቦ ጌታን ተቀበለ >> የሚባል ወሬ በሰፈሩ ተወራ ! በቃ ቢሰድቡት
አይመልስ ቢመቱት መልሶ አይማታ ተባለ ! እውነትም አንድ ቀን ሳምሶን የሚባል ልጅ የድሮ
ቂሙን ሊወጣ ጃምቦን እፊቴ በጥፊ ሲያጮለው ጃምቦ <<ጌታ ይባርክህ እኔ ከፉን በክፉ
አልመልስም ለዚህ አለም ነገር ሙቻለሁ >> ብሎ አለፈ ! ጃምቦ እውነትም ሞተ ተባለ !
ማመን አልቻልኩም! በቃ የሰፈሩ ልጅ ሁሉ ጃምቦን የጉልበቱ መፈተኛ አደረገው አንዱ
በርግጫ አንዱ በቦክስ ! እኔ ራሱ መሞከር አማረኝ ! አንድ ቀን ግን እንዲህ ሆነ ጃምቦ
ወደቸርች ሊሄድ ሲጣደፍ የሰፈር ጎረምሶች ፊቱ ቆሙና አላሳልፍ አሉት ! ጭራሽ የያዘውን
መጽሃፍ ቅዱስ ቀምተው መሬት ላይ ከመጣል አልፈው ያ ሳምሶን እንደለመደው ጃምቦን
ሊጠረቅመው ጥፊ ሰነዘረ፣ ግን ምን ዋጋ አለው የጃምቦ መዳፍ ድነት እንደዥንጥላ
ተዘርግቶ የሳምሶንን መዳፍ አፈፍ አድርጎ እጁ እስኪንቋቋ ጠመዘዘና ሁሉም እየሰማ
ባስገምጋሚ ድምጹ እንዲህ አለ << የጠበኝነት መንፈሴ እንጅ ጡንቻየ አልሞተም እሺ? >>
ወዲያው ጎረምሳው ሁሉ ግማሹ አጥር እየዘለለ ግማሹ መንገድ እያሳበረ ወደየመንደሩ
እግሬ አውጭኝ አለ . . .
<<ጃምቦ ከሞት ተነስቷል>>
<<ጃምቦ ከሞት ተነስቷል>> ከሚል ጩኽት ጋር !
እና ምን ለማለት ነው ? አገራችን ላይ የማሰር የመግደል የማፈንና የማሰቃየት መንፈስ
ለሰላም ለፍቅር ሲባል አሸለበ እንጂ አልሞተም ! በውሃ ቀጠነ እዚህና እዛ አጉል የተዳፈነ
ጉልበት እንፈታተን የምትሉ አቅመቢስ በጥባጮች ሁሉ የጦርነት መንፈስ እንጂ ራስንና
አገርን የመከላከል አቅም አልሞተምና እባካችሁ ስርዓት !!

መልካም የረፍት ቀን!!!💚💛

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ስሜ G እባላለሁ ስም መጥፎ ጎን ሊኖረው ይችላል በማለት ነው ግን በውስጥ መስመር ችግር የለውም የአፋልጉኝ ጥሪ ነው ።
ተወለድክ የተባልኩበት አገር መተማ ወይም ሸዲ ይባላል ስሙን እንጅ አገሩን በውን አላውቅም የኔ እናት ና አባቴ ለስራ የትውልድ አገራቸውን ለቀው ስራ ፍለጋ በተሰደዱበት ወቅት የእግዚአብሔር ፍቃድ ሆነና እኔን እድለቢሱን ልጃቸውን ወልዱ ግን ተስማምተው ተፋቅረው ትድረው ከወለዱኝ በሁላ ምክንያቱን ባልታወቀ ፀብ ተጣልተው ገና ቦርቄ ስልጨርስ እናቴ በሰው አስመጥታ ሰርቃ ወደ ጎንደር ይዛኝ ጠፋች 3 አመት ከሰው ቤት ተቀጥራ እዳሳደገችኝ ከዛም አሁን ወዳለሁበት አገር አመጣችኝ አባቴን ስላት ያኔ ልጅ እያለሁ ከአእምሮዬ በላይ የሆነ መልስ ትሰጠኝ ነበረች ከዛም አልፎ ብር ስትዚ። ስራ መስራት አለበህ ስትለኝ ያቅሜን እየሰራሁ ት.ት አቋረጥኩ ሀሳቤ ሁሉ ገንዘብ ለይ ሆነ ግን ሊሳካ አልቸለልኝም በዙ ለፋሁ የለ ወክቱ እዴት ይምጣ ገንዘብ እሷ አያደርገውም አያገኝም ዝም ይለኛል ይረሳዋል ትል ነበር ግን የናት ሞት ና የትን ድንጋይ እየቆየ ይቆረቁራል አይደል ሚባለው አሁን አባቴ በጣም ናፍቆኛል 19 አመት ያለ አባት ቆይቻለው እናቴ የተለያየ ምክንያት ታቀርባለች ግን የአባቴን ናፍቆት ግን አላስታገሰልኝም ይበልጥ ሳድግ ናፈቀኝ አሁን ክፉና ደጉን ለይቸ አወኩ አሁን ሶሻል ሚዲያም እደዚህ አይነትም በጎ ጎን አለው ብዬ ከስንት አመታት ደብቄ የያዝኩትን ሚስጢር በተዘበራረቀ ሀሳብ ሁኜ ትንሽ ለማለት ነው የመፃፉም ልምድ የለኝም ፍሬ ሀሳቡን ለማጋራት እንጅ ለማንኛውም እናቴ ፈንታ ጌታቸው ትባላለች እዚህ መጥታም አንድ ሰው አገባች አሁን 1ወንድም 1 እህት ወልዳለች 15 አመት ምናምን እየሆናቸው ነው ከተጋብ..................... የኔ ጉዳይ አንድም ቀን አስጨንቆት አያውቅም እጀራ አባቴ። አባቴ በለጠም የኔን እናት ከማግባቱ በፊት ከሌላ ወልዶ እደነበር ከውስጧ የልጠፋ እውነታ ነው ከዛ ውጭ አንድም ነገር የምታቀው ነገር የለም እናቴ እደ አባትም እናትም ሁና አሳድጋኛለች ቢሆንም እሷ ዘላለም አብራኝ እደማትሆን እና የፈጣሪ ነገር እሷን ይዞብኝ ከሄደ
ከዛ በሁላ ቤተሰብ ባገኝ ጣእም የለውም ለማንኛውም እናንተ በተቻላችሁ መጠን ቤተሰቤን እዳገኝ እርዱኝ

Call 0942329852

ለሌሎች በማስተላለፍ የወንድማችንን
ነፍስ እናስደስት።

@getem
@getem
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

#አድዋ

### የዓድዋ ድልና ዳግማዊ ምኒልክ ###

የዓድዋ ድል ያለ መሪዉ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ፈፅሞ ማሰብ አይቻልም ። በእሳቸው የአመራር ብቃት፣ስልትና አርቆ አስተዋይነት የመጣ ነዉና።
....
ከየት ተማሩት?
.
ፕ/ር ጌታቸዉ ኃይሌ "የአፄ ምኒልክ የአመራር ስልትና የአድዋ ድል" በሚለዉ ፅሁፋቸዉ እንዲህ ይላሉ :-

"የምኒልክ አርቆ አስተዋይነት ከምን እንደመጣ ገና ብዙ ጥናት ያስፈልገዋል። ትልቁ ምክንያት ግን በመቅደላ የአፄ ቴዎድሮስ እስረኛ በነበሩበት ጊዜ ከሀገር ሊቃውንትና ከውጭ ሀገር እስረኞች ጋር መጎልመስ ሳይሆን አይቀርም። የአፄ ቴዎድሮስ ጭካኔ ሽንፈትን እንዳስከተለ ስላዩ፥ ተቀናቃኞቻቸውንም በፍቅር አሸነፏቸው። የቅኝ ገዢዎችን ተንኮልና ዲፕሎማሲ አይተው በዘዴያቸው መቷቸው።" ይላሉ።
.....
* የአስተዳደር  ጥበብ

አፄ ምኒልክ የአስተዳደር ጥበባቸዉና ነገሮችን የሚመለከቱበት መንገድ እጅግ ብልህነት የተሞላበት ነበር። ሀገራችን ኢትዮጵያ ከእርሳቸዉ ቀድማ  እንደ አፄ ቴዎድሮስና እንደ አፄ ዮሐንስ ያሉ ታላላቅ ነገሥታት አግኝታ የነበረ ቢሆንም እንደ ምኒልክ ግን ጀግንነትን፥  ሃይማኖታዊነትን፥ ብልሃተኝነትን በአንድ ላይ አጣምሮ የያዘ አልነበረም። ታዲያ ይህ የአስተዳደር ብልሃታቸዉ ከሹመት አሰጣጥ ጀምሮ እንደነበር አለቃ አፅሜ እንዲህ ፅፈዋል:-

"አፄ ምኒልክ ዘውድ የደፉ ዕለት ከንጉሥ ሥልጣን ሰገድ ሱስንዮስ ጀምሮ የተሠራውን ሠላሳ አምስት ሹመት ለጦር አበጋዞቻቸው ሰጡ። አፄ ዮሐንስም እንደባህሉ አድርገዋል። ሹመቱን የሰጡት ግን ለትግራይ ተወላጆች ብቻ ነበር። አፄ ምኒልክ ግን ከሌላ አካባቢ ለመጡት ጭምር እንጂ ለሸዌዎች ብቻ አልነበረም።"

አስተዋይነትና ስልት

አፄ ምኒልክ በጣም አስተዋይና ስልት አዋቂም ናቸዉ። በዚህ ስልት አዋቂነታቸዉ ነዉ  ጣሊያንን ከራሱ በገዙት ጠመንጃና መድፍ ዓድዋ ላይ ጉድ የሰሩት። ይህንን ስልት አዋቂነታቸዉን ቀድሞ የአፄ ቴዎድሮስ እስረኛ ሆነው ሳለ ከመቅደላ ካመለጡበት  ጊዜ ጀምሮ ከአፄ ዮሐንስ ጋር ሊያደርጉት የነበረውን ውጊያ በወቅቱ ያላቸውን አቅም አይተው ከንጉሡ ጋር  በአማላጅ የታረቁበት መንገድ ላይ መመልከት እንችላለን ። በተጨማሪም  ሸዋ ሲገቡ ግዛቱ ይገባኛል በሚል ሹም ተይዛ ደረሱ። እሱን በጥቂት ሠራዊት ማሸነፍ ትልቅ ዕውቀት ያስፈልግ ነበርና ማድረጋቸውም እንዲሁ የምኒልክን አስተዋይነት አጉልቶ የሚያሳይ ነዉ ።


ሌላኛዉ የአፄ ምኒልክ ጊዜዉን የዋጀ ስልት አዋቂነት ማሳያ አፄ ዮሐንስ በንዴት በሱዳን ደርቡሾች ላይ ሲዘምቱ፥ አፄ ምኒልክ ከደርቡሾች ጋር በእንግሊዞች ላይ የጋራ ግምባር መፍጠራቸው ነዉ። በወቅቱ እንግሊዞች ሪር አድሚራል ሂወትን ልከው አፄ ዮሐንስን እንደቀለዱባቸው፥ ሬነል ሮድን ልከው አፄ ምኒልክን ሊቀልዱባቸው ቢሞክሩ አልተሳካላቸውም። በአንፃሩ አምባሳደር ሬነል ሮድ አፄ ምኒልክ እንደቀለዱበት ያወቀው ወደመጣበት ከተመለሰ በኋላ ነው። ግን እዚያው ባለበት ጊዜ የውል ውይይት ሳይጀምሩ ከማን ጋር እንደሚዋዋል በምልክት ሲያስጠነቅቁት፥ "ጣሊያን ምጽዋን እንድትይዝ ለምን ጋበዛችኋት?" አሉት። ሲሰማ ክው አለ። ምንም ከማያውቅ የዋህ ሰው ጋር የሚነጋገር መስሎት ነበር። የመጣው ኢትዮጵያ ከሱዳን ደርቡሾች ጋር እንዳትስማማ ቃል እንዲገቡለት ነበር። የማይከበር ቃል ያለው እንግሊዝ አገር ብቻ መስሎታል። "ግዴለህም፥ ደርቡሾች የሃይማኖታችን ጠላቶች ናቸው። እኛ እንደናንተ ክርስቲያኖች ነን" ሲሉትና በሰማው ሲደሰት፥ የደርቡሽ መልእክተኞች ከጓዳ ሆነው ይስቁ ነበር። እንግሊዝና ፈረንሳይ በኮሎኒ ሽሚያ ጊዜ በማህላቸው ግጭት እንዳይነሣ ሁለቱ ሀገሮች መስማማታቸውን ንጉሡ ስለሚያውቁ፥ የሱዳኖቹ መልእክተኞች ከመመለሳቸው በፊት የሰጧቸው ምክር፥ "በምሥራቅ (ከግብጽ) እንግሊዞች ሲመጡባችሁ፥ የፈረንሳይ ባንዲራ ሰቅላችሁ ጠብቋቸው። በምዕራብ (በፋሹዳ) ፈረንሳዮቹ ሲመጡባችሁ የእንግሊዝ ባንዲራ እያውለበለባችሁ ተቀበሏቸው" የሚል ነበር።

ታዲያ የተንኮታኮተችውን ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ ሌሎቹ ሲሳናቸው አፄ ምኒልክን የቀናቸውም በዚሁ  በዘዴኛነታቸው ነው።
.
ይቀጥላል....

#የጥቁር_ህዝብ_ኩራት
#ዓድዋ_123
#የኢትዮጵያውያን_ድል
#VictoryofAdwa
#Ethiopia

@wegoch
@wegoch
@kinchebchabi
2024/09/28 19:32:50
Back to Top
HTML Embed Code: