Telegram Web Link
«የምትፈልገውን አታውቅም» ትለኛለች።
እውነቷን ነው። የምፈልገውን አላውቅም፣ አብዛኛውን ጊዜ። «የምትወደው ምግብ ምንድነው?» ስትለኝ ወዲያው ለመመለስ ተቸግሬኣለሁ። ምንድነው አብልጬ የምወደው? ሽሮ? ጎመን? አጠገቤ ከተቀመጠ እስኪያልቅ ወይም እስኪያነሱብኝ ድረስ መቆንጠሬን የማላቆመው ቆሎ? እኔንጃ። ሁሉንም እወዳቸዋለሁ። አንዱን ብዬ ለመወሰን ግን አልችልም። ያኔ ትናደዳለች። ምናልባት የምወደውን ምግብ ጋብዛ ልታስደስተኝ ነበር ዕቅዷ። ምናልባት . . . አላውቅም።
ምግብ ብቻ አይደለም። አብልጬ የምወደው ፊልም፣ ወይም መፅሀፍ፣ ወይም ቀለም፣ ወይም የሆነ ነገር ብቻ ነጥዬ ይሄ ማለት ይሳነኛል። ምርጫዎቼ እንደ «ሙዴ»፣ በተጠየቅኩበት ወቅት እንዳለሁበት ስሜት ጥሩነትና መጥፎነት ይለያያሉና ቋሚ ነገር መምረጥ አልችልም።
የዶ/ር ደረጀ ከበደን 8ኛ አልበም የመጀመሪያ መዝሙር «እግዚብሔር ግን ከላይ ሁሉን ተመልክቷል» ለቀናት ከጆሮዬ መንቀል እስኪሳነኝ ስሰማ በቆየሁ ማግሥት “Oh Brother Where Art Thou” በተሰኘው የጆርጅ ክሉኒ ፊልም ላይ የሰማሁትን የSoggy Bottom Boys ተወዳጅ ዘፈን ለሳምንት ጆሮዬ ላይ ልለግተው እችላለሁ።
እኔ እነሱን ያለማወቄ የተለየ ቁም ነገር አለው ብዬ አላምንም። ህይወት አይቀይሩ፣ ኑሮ አያሻሽሉ፣ ስሜት አይፈውሱ፣ ህመም አያስረሱ። ከእነሱ መካከል የምፈልገውን ለይቼ በማወቅና ባለማወቅ መሃል የማየው ልዩነት ወይም የማገኘው ጥቅም አይታየኝም። It doesn’t matter at all. ለሷ አይታያትም። ያበሳጫታል። ቁም ነገር የለህም ማለት እኮ ነው ብላ ትደመድምና ከሷ ጋር በማውራቴ፣ በመጫወቴ ብቻ የበራውን ስሜቴን ታጠይመዋለች።
ጥያቄዎቿ ባልረቡት ነገሮች ላይ ያበቃሉ። በእርግጠኛነት ለይቼ የማውቀውን፣ አጥብቄ የምፈልገውን አንድ ነገር ጠይቃኝ አታውቅም። መልሱን በእርግጠኛነት የማውቀውን እና ደግሜ ሳላስብ የምመልሰውን ነገር ግን አትጠይቀኝም። «አብልጠህ የምትወደው ሰው?» ብላኝ አታውቅም።
አንድ ቀን እመልሰው ብዬ አንዲት ቃል ስንት ዘመን አጠናሁ? የቃላት አወጣጤን ስንቴ አሳመርኩ? ስንቴ ብቻዬን ደጋገምኩት? ስንቴ? የምጠየቅበትን ቀን እየናፈቅኩ ስንቴ አነበነብኩ ስንቴ????????????
«አንቺን!»

#gamechu

@wegoch
@paappii
‹‹ ችግሩ እናንተ ናችሁ››
................................
አነቃቂ (ሞቲቬሽናል) ንግግር ወይ መፅሃፍ ምርጫዬ አይደለም፡፡ ሳይመን ሲኒክ ግን ደስ ይለኛል፡፡ ሳይመን ሲመቸኝ ሲመቸኝ ዩቱዩብ ላይ አስሼ የማየው በአነቃቂ ንግግሩ የተመሰገነ ሰው ነው፡፡
ዛሬ ያየሁትን ላጋራችሁ፡፡
ነገሩ የሆነው በእንግሊዝ በ18ኛው ክፍለዘመን ነው፡፡ ችግሩ አንድ ምእተ አመት ለሚጠጋ ጊዜ ቢቆይም አውሮፓን ሁሉ እያዳረሰ፣ እየተባባሰ የሄደ ነበር፡፡
ችግሩ ምን ነበር?
በጣም ብዙ ሴቶች ሃኪም ቤት ሄደው ይወልዳሉ፣ በወለዱ በ48 ሰአታት ውስጥ ይሞታሉ፡፡ ‹‹ብላክ ዴዝ ኦፍ ቻይልድ በርዝ›› ይሉት ነበር፡፡ የእናቶች ሞት መጠኑ በአንዳንድ ሃኪም ቤቶች 70 በመቶ ሁሉ ደርሶ ነበር፡፡ አስቡት…! በአንድ ቀን አስር ሴቶች እዚያ ሃኪም ቤት ቢወልዱ፣ ሰባቱ ልጅ አቅፈው በመሄድ ፍንታ ወደ መቃብር ይሸኛሉ ማለት ነው፡፡
እንግዲህ ዘመኑ እውቀት የተስፋፋበት፣ ሳይንስ እያበበ የመጣበት ቢሆንም ይህንን ችግር የሚፈታ ግኝት ግን ጠፋ፡፡ ወረቀት ቢገላበጥ፣ መፅሃፍ ቢገለጥ፣ ጥናት ቢደረግ፣ ምክንያት ቢፈለግ፣ ቢጠና …ቢጠና መላ ጠፋ፡፡ ተስፋ ያልቆረጡ ሃኪሞች ግን የዚህን አስከፊ ነገር ጭራና ቀንድ ለመያዝ ጠዋት ጠዋት በወሊድ የሞቱትን ሴቶች አስክሬን ይመረምራሉ፤ ከቀትር በኋላ ደግሞ ነፍሰጡር ያዋልዳሉ፡፡
ጠዋቱን ከሞቱ ሰዎች ጋር፣ ከሰአቱን ከተወለዱ ህጻናት ጋር ያጠፋሉ፤ የዘወትር የማዋለድ ስራቸውን ያከናውናሉ…አዲስ ሕይወትን ወደዚህች ዓለም ያመጣሉ፡፡ ነገር ግን፣ ድካማቸው ፍሬ ሳያፈራ እና ሁኔታው ሳይቀየር አስርት አመታት ካለፉ በኋላ ዶክተር ኦሊቨር የሚባል ሰው እንቆቅልሹን ፈታው፡፡
እንቆቅልሹ ምን ነበር?
እነዚህ ጠዋት የሙት እናቶችን አስክሬን የሚመረምሩ፣ ከሰአት ህጻናትን የሚያዋልዱ ሃኪሞች በመሃል እጃቸውን አይታጠቡም ነበር፡፡
ዶክተር ኦሊቨር ነገሩ ሲገለፅለት ሃኪሞቹ ጋረ ሄዶ ምን አለ? ‹‹ሰዎች…ችግሩ እናንተ ናችሁ›› …ሃኪሞቹስ ምን አደረጉ? ዶክተር ኦሊቨርን ‹‹ቀውስ›› ብለው ያቀረበውን ሃሳብም ለሰላሳ አመታት ከቁብ ሳይቆጥሩት ኖሩ፡፡
የዶክተሩ ሃሳብ ተሰምቶ እጅ መታጠብ እና የህክምና እቃዎችን በተለየ ሁኔታ ማፅዳት እሰኪጀመር ድረስ የእናቶች ሞት ቀጠለ፡፡ ሁኔታው ተቀይሮ እጃቸው መታጠብ፣ የህክምና እቃዎቻቸውን ማፅዳት ሲጀምሩ ግን እንደ እርግማን ይቆጠር የነበረው የወላዶች እልቂት ቀጥ አለ፡፡
ይሄ ታሪክ ምን አሳሰበኝ?... ስንቶቻችን ጠዋት አስክሬን መርማሪ ፣ማታ አዋላጅ ሆነን፣ የማይነካካ እያነካካን ስንት ነገር እያበላሸን ይሆን?
ስንቶቻችን መድሃኒት ነው ባልነው ነገር ስንቶቹን እየመረዝን ይሆን?
ስንቶቻችንስ ለዘመናት ያልተፈታ ቋጠሮ ሲገጥመን ቸኩለን ሌሎቸ ላይ ጣት ከመቀሰር ይልቅ ‹‹ችግሩ እኔ ብሆንስ?›› ብለን አስበን እናውቅ ይሆን?

#hiwot_emishaw

@wegoch
@paappii
ፕሮፌሰር #ፍቅሬ_ቶሎሳ እንዲህ ብለዋል...

"ጀርመን ሄጀ የወለድኩት ልጅ ጀርመነኛ ቢናገር፣ እንግሊዝ የወለድኩት ልጅ እንግሊዘኛ ተናጋሪ ቢሆን፣ ጣሊያን ሀገር የወለድኩት ጣሊያንኛ ተናጋሪ ቢሆን ልጆቼ የተለያየ ቋንቋ ስለተናገሩ ወንድማማችነታቸው ይፋቃል ወይ? እኔስ ኦሮሞኛ፣ አማርኛና ትግርኛ ተናጋሪ በመሆኔ ወይም ልጆቼ የሚናገሩትን ቋንቋ ስላልተናገርኩ አባትነቴ ይፋቃል ወይ? የሚያዛምደን ስጋና ደማችን እንጅ #ቋንቋችን አይደለም፤ ስለዚህ እኛ #ኢትዮጵያውያን የተለያየ ቋንቋ መናገራችን ሊከፋፍለንና ሊያጋጨን አይገባም"

@wegoch
ለገና ቅርጫ በሬ ለመግዛት የተመዘገባችሁ አባላት በሙሉ.. የጎጃም በሬ ይሁን የወለጋ ይሁን የሚለዉ ላይ ወሳኝ የሆነዉን ውሳኔ ለመወሰን አስቸኳይ ድንገተኛ ጉባኤ ነገ ጋሽ ጎሳዬ ጊቢ ይደረጋል እንድትገኙ 😳😇

@wegoch
@paappii

#ደርፌክ
.
.
.
.
በናትሽ ጥለሽኝ አትሂጂ "
በእናትሽ ? እንዳትጨርሰው በደሞዝ ሞት ....
ገና አሁን አግኝቶኝ ይሄን ያህል እንዳልለየው ለምን ፈለገ ? በቅፅበት ፎንቃ ጠልፎት ? ማን ያውቃል ። ... እጄን ይዞ ይለምነኛል " ልቤ ደንደን በል " ፀሎቴ ነበር .... ስልኬ ጠራ እሷ ነበረች ከርቀት እያየኋት አነሳሁት ።
" ምናባቱ ነው የሚልሽ ? መጥቼ ላዋርደው እንዴ ? "
መልስ አልሰጠዋትም እየሄደ የሚጠራ ሚኒባስ በምልክት አስቁሜ ዘልዬ ገባሁ ። ...
.
ግራ ገብቶት በዓይኑ ሸኘኝ ። እብድ ናት እንደሚለኝ ግልፅ ነው የእብድ ስራ ነውና የሰራሁት ። .... መቼስ መጥታ ኡሁሁ ስትል ከማየት ይሻላል ... ስልኬን ዘግቼ ከተረጋጋሁ በኋላ ነው ታክሲው እኔ ወደምፈልግበት መስመር እንደማይሄድ ያወቅሁት ።

በማግስቱ አልነጋላትም ቤቴ ስትደርስ ... መኝታ ቤቴ መጥታ ቀሰቀሰችኝና አልጋው ጫፍ ተቀመጠች ... ወይ ዕዳዬ አሁን ቁርሴን የሱን ስጋ እያበላች እንባዋን ልታጠጣኝ ነው " አሰብኩ
ዓይኖቿ እንቅልፍ አጥተው ማደራቸውን አባብጠው ይናገራሉ ....
" አየሽልኝ ይሄን ዶማ "
በስድብ ዝምታውን ሰበረችው
" የበለጠ ያፈቀርኩት መሰለኝ ስለሱ ማሰብ ማቆም አልቻልኩም " አለች በቁጭት
ፍቅሯ የጨመረ መስሏት ነው እንጂ እልህ ነው ። ...
እልህ አሽከርክሮ እሳት ወይም በረዶ ላይ ይፈጠፍጣል ።

" አሁን እዚህ ትንሽ ተኚና ከዛ ሻወር ወስደሽ ቁርስ ውጪ እንበላለን " በእኔ ቤት ማረሳሳቴ ነበር ።...
ኮመዲኖ ላይ ያለችው ስልኬ በቫይብሬት ደነሰች ... የሷ ይመስል ዘላ ተነሳችና አየችውና ...
" እሱ ነው " ብላ ጮኸች ።
ክፍሉ ውስጥ ወዲያ ወዲህ እየተንጎራደደች ጥሪውን እጇ ላይ አስጨረሰችው ።

መቋቋም አቃታት ስልኳን ከቦርሳዋ አውጥታ ደወለችለት ።
አያነሳም ። ደግሞ የኔ ስልክ ላይ ደወለ ። ባሰባት ።
እንደገና ደወለች ጠርቶ ፣ ጠርቶ ዘጋ ...
እኔ እሱን ስወደው እሱ ያቺን ፣ ያቺ ያንን ያ ደግሞ ሌላኛዋን ፦ የሚባለውን አባባል በተግባር ያየሁት መሰለኝ ።
አንዳንዴ ፍቅር አፍቃሪውን አያውቅም ሲያናድድ ።

ስልኬ ጠራ
ሳታስፈቅደኝ አንስታ ስድብ እየወረወረች ፈነካከተችው ... ዝም አልኳት ... ይሄንን ሁሉ ያደረገችው እሷ እንደሆነችና ድጋሚ ስልኬ ላይ እንዳይደውል ነግራው ጆሮው ላይ ጠረቀመችው ። ...
.
ስቅስቅ ብላ አለቀሰች ።
አላባበልኳትም ... ለምን ? ንዴቷ በእንባ ታጥቦ እንዲወጣላት ።
ስልኳ ጠራ
አንስታ ስታየው ፊቷ በራ ፈገግ ብላ እያየችኝ
" በስራው ተፀፅቷል አየሽ ይቅርታ ሊለኝ ነው ... ቆይ ላውድ ስፒከር ላድርገው "
አለችና አነሳችው ።
" ሉሊትን እኔ ነኝ የላኩብህ እያልሽኝ ነው ? "
ኮስተር ባለ ንግግር ጀመረ
" አዎ የምትለኝን ሁሉ ማረጋገጫ መስሎኝ አድርጌዋለሁ "
" እንግዲያውስ የላክሽልኝ ፈተና በጣም ከባድ ስለሆነ ወድቄያለሁ ። ... አዎ ሉሊትን ወድጃታለሁ "
" ምን ... አንተ ሸርሙጣ " አፀያፊ ስድብ አከታተለች
ጆሮዋ ላይ ዘጋው ።

ደጋግማ ደወለች አይመልስም
" ደውለሽ ስደቢው "
" አልደውልም አልሳደብም "
ከኔጋ የጦፈ ጭቅጭቅና ጥል በመሀል የኔ ስልክ ላይ የተደወለ ጥሪ ገላገለን ።
እሱ ነው ....
አምላኬ ድረስልኝ ።

@paappii
@wegoch

#lulit
ቦረና
።።።።።።።።።።።።።።።።
ክፋል አንድ

የባንክ ሥራ አስኪያጅ ሆኜ ወደ ደቡብ ኢትያጵያ የቦረና ኦሮሞዎች ዘንድ ሄድኩ። የአባ-ገዳ ሃገር የሆነችው ቦረና ለሸዌው ጥሌ ብዙም አልከበደችኝም። ህዝቡ ረሃ ነው። ቦረን ከወደዳችሁ ወደዳችሁ ነው። ያቀርባችኋል። ቦረና ጦርነት ከሌለ በሌላ አካባቢ እንዳሉ አርብቶ አደሮች ክላሽ ይዞ አይዞርም። "Nageenyii Badhaadhaa? Babaaroo Bulee? Babaaroo Fafayaa?" ብሎ ሰላምታ ያቀርብላችኋል። ስለ ሰላም ከቦረን በላይ ማን ይገባዋል? ምርቃቱ በሰላም ዙሪያ ያጠነጠነ ነው። ፀሎቱም ስለህዝቡ ስለከብቶቹ፣ ስለቦረን ምድር ልምላሜ ነው። ቦረን ደግ ነው። ውሃ ስትጠይቁት ወተት ይሰጣችኋል። የቦረን የከብቶችና ግመሎች ወተት ጨዋማውን ውሃ ያስረሳችኋል።
እሁድ የከብት የገበያ ማዕከል ወደሆነው"ሃሮ በኬ" ሚኒ ባሳስችሁን ይዛችሁ ትሄዳላችሁ። በአሜሪካኖች በተገነባው ዘመናዊ የከብት ገበያ ፍየል በሚዛን ተመዝኖ ሲሸጥ ታያላችሁ። ምርጥ ዘሮቹና ነጫጮቹ የቦረና ከብቶች፣ ረጃጅሞቹ የቦረን ምርጥ ዘር ግመሎች ባህር አቋርጠው ወደ ውጭ ሃገር ሊሄዱ ሲሸጡ ታያላችሁ። ገዢና ሻጭ እጅ ለእጅ ተሳስሞ ግብይቱን ያፀድቃል። ከዛም የፍንጥር ልትጠጡ ገበያው ዙሪያ ወደ ተገጠገጡት ዳሶች ትሄዳላችሁ። ካጠገባችሁ ስትግጥ የነበረች ፍየል ታርዳ፣ ምስጥ በሰራው "ኩይሳ" ውስጥ በተሰራ ምድጃ ተጠባብሳና ወደ "ወስላ" ነት ተቀይራ ትቀርብላችኋለች። ቆንጥርና እሾህ ስትበላ ባደገችው ፍየል ላይ ጥቂት ጨው ይነሰነስባታል። ሌላ ቅመም የለም። ጣታችሁን እየላሳችሁ ትበላላችሁ። ወስላ ስትበሉ ብትውሉ አትጠግቡም። የቦረን ፍየሎች ስጋ መድሃኒትም ነው። (ቦረን ስትሄዱ ሳትቀምሱ እንዳትመጡ።)
ያቤሎን ከተወለድኩባት ሃገር እኩል ለመውደድ ጊዜም አልፈጀብኝም። ህዝቡ ፍቅር ነው። ወርቅ ለብሳችሁ ብትሄዱ በክፉ አይን የሚያያችሁ የለም። በቦረን የሚኖረው የቦረን ኦሮሞ ብቻ ከመሰላችሁ ተሳስታችኋል። ቦረን ውስጥ ጉራጌ፣ ኮንሶ፣ አማራ፣ ሱማሌ፣ ቡርጂ፣ ስልጤ፣ ትግሬና ሌላም ብሄረሰብ በፍቅር ይኖራል። የቦረን ምድር እስከ ኬኒያ ድንበር የተንሰራፋ ነው። ቦረን በሰሜን ኬኒያ መርሳ ቤትና በደቡብ ኢትዮጵያ የሁለት ሃገር ዜጋ ሆኖ ይኖራል። የኬንያ ቦረናዎችም በገዳ ስርዐት ይተዳደራሉ። በኢትዮጵያውያን ቦረናዎች "ጉሚ-ጋዮ" የስልጣን ሽግግር ለመታደም ይመጣሉ። የኢትዮጵያ ቦረናዎችም ኬንያ ይሄዳሉ። ይጠያየቃሉ። ኬንያን "Keenyaa/ኬኛ" ይሏታል። ናይሮቢንም "ናሮቢ"/ዝነብልኝ ይሏታል። የቦረን ኦሮሞዎች ኬንያ ውስጥ እንደማንኛውም ዜጋ የመንቀሳቀስ መብት አላቸው። ኬንያ ሁለተኛ ሃገራቸው ናት።
ህዝቡ ሰላማዊ ነው።ቦረና ካልነካችሁን አይነካም። ለመሳሪያ የቀረበ ህዝብ አይደለም። መሳሪያ ተከሽሞም አይዞርም። ድንበሩን አጥርቶ ያውቃታል። በየስርዓቱ የደቡብ ኢትዮጵያን ድንበር ሲጠብቅ የኖረው የኢትዮጵያ መከላከያ ሳይሆን ቦረና ነው። ቦረን በሱሩጳ የሚኖሩ ሶማሌዎችን መብት በገዳ ጉሚ ስብሰባ አንስቶ ይወያያል። ያፀድቃል። ማንም ጫፋቸውን አይነካም። ከማንኛውም ቦረን እኩል መብት አላቸው። በቦረን ምድር " ጩቡ"/ግፍ እንዲፈፀም አይፈልግም።
ቦረን በማንኛውንም ከመካከለኛው ምስራቅም ሆነ ሩቅ ምስራቅ የመጡ ሃይማኖቶችን አይቀበልም። ቦረን ሃገር በቀል የሆነው የዋቄፈታ እምነት ተከታይ ነው። በአንድ "ዋቃ" ያምናል። አምላክ ለጥፋታችን በምድር ላይ ሳለን ይቀጣናል ብለው ስለሚፈሩ "ጩቡ" መስራት አይፈልጉም። በቦረን ምድር "ጩቡ ከተሰራ ቦረን ዝናብ ያጣል፣ ልምላሜ ይርቀዋል። ከብቶቻችን ያልቃሉ" ብለው ያምናሉ። የገዳ አባቶች ፍርድን ላለማዛባት ይጠነቀቃሉ።
.
.
ይቀጥላል

@wegoch
@paappii

#Tilahun Girma
-ቦረን-
ክፍል ሁለት
ቦረን ለሴቶችም ትልቅ ክብር አለው። ምንም እንኳ ሴቶች ጉሚ-ጋዮን የመሳሰሉ የገዳ ስርአት ስብሰባዎችን በቋሚነት ባይታደሙም በተወካያቸው አማካይነት ጥያቄአቸውን ማቅረብ ይችላሉ። "ጉዳት ደርሶብኛል እራሴ ጉዳቴን ለጀማው ላቅርብ" ያለች ሴት ካለች ጥያቄውን የማቅረብ መብት ይከበርላታል። ቦረን በሴት ቀልድ አያውቅም።
ለልጃገረዶች ከጋብቻ በፊት ግንኙነት መፈፀም በጥብቅ የተከለከለ ነው። ፈፅሞ መገኘት ትልቅ ሃጢአት ነው። ይቅርታ የማያሰጥ ጥሰት። ችግሩ ለሁለቱም ነው። ለወንዱም ለሴቷም። "በሮም ሳለህ እንደ ሮማዊ ሁን" እንደሚባለው የቦረንን ባህል እግሬ የተቀደሰ ምድራቸውን ከረገጠበት እለት አንስቼ ከሰው ጠይቄና አንብቤ ተምሬአለሁ።
የቦረን ልጃገረድ ከነካችሁ ምን ይገጥማችኋል? እንበልና ከቦረን ልጃገረድ ጋር ያልተቀደሰውን ነገር ፈፀማችሁ። ማንም አላያችሁም። የልባችሁን አድርሳሁ ቁጭ ብላችኋል። አያድርገውና በተመሳሳይ ሰዓት በቦረና ምድር ዝናብ ወቅቱን ጠብቆ አልዘነበም። ይሄኔ ህዝቡ "ዋቃ ዝናብ የከለከለን፣ ከብቶቻችን ውሃ ያጡት ከመሃከላችን ሃጥዕ ቢኖር ነው። ጩቡ የሰራ ሰው አለ" ብሎ ማጉረምረም ይጀምራል።
ድርጊቱን የፈፀመችው ልጃገረድ በጭራሽ ያሳደጋት ማህበረሰብ ላይ መጨከን አትችልም። በጭራሽ። በእርሷ ጥፋት ምክንያት ህዝቡ በዋቃ እንዲቀጣ አትፈቅድም። አስተዳደጓ ያንን እንድታደርግ አይፈቅድላትም። ስለሆነም ለአካባቢው ሽማግሌዎች ሃጢአቷን ትናዘዛለች። ጥፋቷን ብትናዘዝም ይቅርታ አይደረግላትም። ይሄንንም ጠንቅቃ ታውቃለች። የተናዘዘችው ቃል ያለምንም ምስክር ተቀባይነት ያገኛል። ልጃገረዶቹ በገዳ ባህል ተኮትኩተው፣ ፈሪሃ ዋቃ ያደረባቸው ንፁህ ነብሳት ናቸውና ውሸትን ከነመፈጠሯ አያውቋትም።
ከዚያ በኋላ ሴቷ የተናገረችው ቃል ብቻውን እንደምስክርነት ይቀርብባችኋል። ትከሰሳላችሁ። ለፍርድ ትቀርባላችሁ። ወንዱ ላይ "Mataa malee" የሚል የፍርድ ውሳኔ ይተላለፍበታል። "ከህይወቱ ውጪ ያለው ንብረት በሙሉ ተወርሶ ይባረር" ማለት ነው። ሴቷም "Caabanaa/ጫበና" የሚል ቅፅል ስም ይወጣላታል። ቤተሰቦቿም እያዘኑም ቢሆን ያባርሯታል። ከማህበረሰቡም ትገለላለች። ለሌላ ብሄረሰብ ትዳራለች። ቦረና የሆነ ሰው አያገባትም።
የቦረና ሽማግሌዎች ሲመርቁ "ዋቃ ሴቶቻችንን እውነት ያናግርልን!" በማለት ይመርቃሉ። ምክንያቱም በሴቷ ምስክርነት ላይ ብቻ ተመርኩዘው ፍርድን ይሰጣሉና። አንዳንዴ ሸገር ውስጥ ሴቶች ተደፍረው በማስረጃ እጦት ብቻ ወንዱ ነፃ ሲሆን "ምነው ይሄንን ክስ የቦረን ሽማግሌዎች በዳኙት" ስል እመኛለሁ።
ይቀጥላል...

@paappii
@wegoch

#tilahun girma
-ቦረን-
ክፍል ሶስት
የቦረን ልጃገረዶችን መንካት ከባድ ቅጣት ስለሚያስከትል ማንም ደፍሮ ቀበቶውን አይፈታም።በወግ በማዕረግ የተዳረች የቦረን ልጃገረድ የአባቷን ስም በባሏ ስም ትቀይራለች። የአባቷን ጎሳ ትታ የባሏ ጎሳ አባል ትሆናለች። ከወር በፊት "ሎኮ ጠደቻ" በሚል የቀበሌ መታወቂያ የባንክ ሂሳብ የከፈተች የቦረን ልጃገረድ አግብታ ስትመጣ በባሏ ስም "ሎኮ ገልገሎ" የሚል መታወቂያ ይዛላችሁ ትመጣለች። በአሜሪካም ይሄው ባህል አለ።
ይሄ ባህሏ ነው። ቦረን ናት። የእሷን ባህል ላገለለው የህግ ስርዓት ብላ የድሮውን መታወቂያ ተሸክማ አትመጣም። ቦረን የትኛውንም ህግ እራሱን ከሚያስተዳድርበት የገዳ ስርአት የበላይ አድርጎ አይመለከትም። ሁሌም እጠይቃለሁ። "ህጎችን ስናወጣ ለምን ከእራሳችን ባህል ጋር ልናጣጥም አንሞክርም? ለምን ገልባጭ እንሆናለን? ለምን የሚያስኮርጀውን ተማሪ ስም ጭምር እንደሚገለብጥ ሰነፍ ኮራጅ እንሆናለን?" ቢሆንም ለጥያቄዎቼ መልስ አግኝቼላቸው እላውቅም።
በምዕራባውያኑም ይሄው ባህል አለ። ሴቶች ሲያገቡ በባሎቻቸው የቤተሰብ ስም መጠራት ይጀምራሉ። ሲፋቱ ደግሞ ወደ ቀድሞ ስማቸው ይመለሳሉ። ጥያቄው እዚህ ላይ ነው። ምዕራባውያኑ የቦረናን ባህል ወረሱ ወይስ ቦረን የምዕራባውያንን ባህል ወረሰ? ይሄንን ጥያቄም መመለስ ባልችልም መደነቄ አልቀረም።
ከዚህ ሁሉ በላይ የገረመኝ ደግሞ ሴት ልጅ ትዳር ከያዘች በኋላ ፍፁም ነፃ መሆኗ ነው ። ከባሏ ውጪ በድብቅ ፍቅረኛ ይዛ ብትገኝ የሚከሳት የለም። ያገቡ ወንዶች ለድብቅ ፍቅረኞቻቸው ስጦታ የሚሰጣጡበት ስርዓት አለ። ይህ ስርአት የ"Jalaa jaaltoo" ስርአት ይባላል። የተማረው ቦረን ይሄንን ስርዓት ይቃወማል። ይሄንን ስርዓት በህግ የሻሩ አባገዳዎች ነበሩ። ሴቶቹ ውሃ ሲቀዱ፣ በየአደባባዩ በአሽሙር ሸነቆጧቸው። ተቃውሞአቸውን በዜማ ገለፁ። ህጉ ተሻረ።
በሰሜን ኢትዮጵያ ነገስታት "እረኛ ምን አለ?" ብለው እንደሚጠይቁት ሁሉ የደቡብ ኢትዮጵያዋ ቦረን አባገዳዎች "ሴቶች ምን አሉ?" ብለው ይጠይቃሉ። የሴቶቹ ጥያቄ የገዳ ሸንጎው ተወያይቶ ይፈታላቸዋል። ዲሞክራሲ በሽ ነው። "ይህ የወንዶች ዓለም ነው።" የሚለው ብሂል በቦረን አይሰራም። በእርግጥ እዚህ ላይ ገደብ አለ። ሴቷ በምንም ሁኔታ የእራሷን ጎሳ አባላት (ከባሏ ጎሳ) በድብቅ ፍቅረኛነት ለመያዝ አትችልም። ስለዚህ ሳይጠባበሱ በፊት ጎሳቸውን ያጣራሉ። ህጋቸውን በምንም መንገድ ለመጣስ አይሞክሩም።
ይቀጥላል....

@wegoch
@paappii

#tilahun girma
ቦረን-
ክፍል አራት
የቦረን ልጅ እንደተወለደ የላም ወተት እንዲቀምስ ይደረጋል። የላም ወተትን ጥቅም በጨቅላነቱ ይረዳል። ወንድ ሲወለድ አባት የከብት ቆዳ የጎጆው ደጃፍ ላይ ይሰቅላል። ሶስት ጊዜ "ወንድ ተወልዶልኛል!" በማለት ዜናውን ለጎረቤት ያበስራል። ነጭ መጎናፀፊያ ይደርባል። ረጅም ዱላም ይይዛል። ጎረቤቶች ወተት፣ ቅቤና ሽቶ በስጦታነት ይዘው ይመጣሉ።
የምርቃት ስነስርአትም ይደረጋል። መራቂው ምርቃቱን ሲያዥጎደጉዱ ታዳሚዎቹ መራቂው ያሉትን ተከትለው "Nagaa"/ሰላም/ ይላሉ።
Warri nagaa! ................................ቤተሰቡ ሰላም!
Warraa ollaan nagaa!...................ጎረቤቱ ሰላም!
Halkannii-guyyaan nagaa!.......ቀንና ሌሊቱ ሰላም!
Baraa-Bariin nagaa!...............አመቱና ንጋቱ ሰላም!
Elemtuu-Gaadiin nagaa!........ላም አላቢዋ ሰላም!
Tiksaa-uleen nagaa!.....................እረኛው ሰላም!
Maa'essii nagaa!..........................ድሃው ሰላም!
Sorressi nagaa!...........................ሃብታሙ ሰላም!
Yaa'aa fi yubbi nagaa! .......... ያአ እና ዩባ ሰላም!
Raabaa-Kuusi nagaa! ...............ራባ-ኩሲ ሰላም!
Ijoolee Kuuchuun nagaa!..........ወጣቶቹ ሰላም!
Gadaa sadeen nagaa!.........ሶስቱ ገዳዎች ሰላም!
Liiban latuun nagaa!..........ለምለሟ ሊበን ሰላም!
Lafti, sa'an namaan nagaa!..........................መሬቱ፣ ላሞቹና ሰው ሰላም! Dirren nagaa!........................
............ድሬ ሰላም!
Areero Boroon nagaa! ..................አሬሮ ሰላም!
Tuulaan Saglan nagaa!......ዘጠኙ ዔላዎች ሰላም!
Horaa! Bulaa! Deebanaa!...እድሜ ይስጣችሁ! ብዙ!
ከምርቃቱ በኋላ ወላጅ አባትየው እሸት ቡና፣ ወተት እና ምግብ ቀምሰው ለሽማግሌዎች ያስተላልፋሉ። ሽማግሌዎችም ቀምሰው ለጎረቤቶች ያስተላልፋሉ። ሁሉም ተራ በተራ ይቀምሳል። የሚታኘክ ትምባሆም ይሰጣቸዋል። በእሸት ቡናው(Buna-qalaa) ቅቤ ግንባራቸውን፣ ክንዳቸውን እና እግራቸውን ያብሳሉ። ከዚያ በኋላ ዘፈን ይዘፈናል።
Ilmi yasii dhalate! ...................እነሆ ልጅ ወለድህ
Haati ya lallatte! ....................በርትታለች ሚስትህ
Ilmi dhalate sii guddata!......የተወለደው ይደግልህ
Haadhaa fi abbaa bulfataa!....ያርገው የሚረዳህ
Eeyyee sii guddata! ...............የሚያድግ ያርግልህ
Maandhaa horataa! .................ታናሾች ያስከትል
Eeyyee sii guddata! ..................አዎን ያድግልሃል
Ya'a urgaa'a! ya'a urga'a!........እንደ ሽቶ ይሸታል!
ለሚቀጥሉት አራት ቀናት የአዲሱን እንግዳ ወደ ዓለም መምጣት በማስመልከት ሴቶች ይዘፍናሉ። ይጨፍራሉ። አራስ ጠያቂዎች ለጤንነታቸው ሲባል በጎጆው ግድግዳ ባለ ቀዳዳ ከርቀት አራሷን ይጠይቋታል። ለሚቀጥለው አንድ ሳምንት እናቲቱ ከጎጆዋ እንድትወጣ አይፈቅድላትም። ከወጣችም ጎህ ሳይቀድ ወይም ምሽት ላይ መሆን ይኖርበታል። ስትወጣም ለዚሁ የተዘጋጀ ባህላዊ ቢላና በትር በእጇ ትይዛለች።
እናትና አዲስ የተወለደው ልጅ በዚህ ሁኔታ ለአርባ አምስት ቀናት ከቤት ሳይወጡ ይቆያሉ። ለልጁም የመጀመሪያ ስጦታ ይሰጠዋል። የተወለደችው ሴት ከሆነች ዘፈንና ዳንስ አይኖርም። ስጦታም አይሰጣትም። ልጁ በእግሩ መራመድ እንደጀመረ ከሰፈር ውሪዎች ጋር እንዲጫወት ይለቀቃል። እንሽላሊት፣ ቢራቢሮና እንዲሁም አይጥ ለማደን ሲራወጥ ይውላል። የመጀመሪያውን ቢራቢሮ ሲያድን ከእናቱ ወንድም (ከአጎቱ) ሽልማት ይሰጠዋል።
ሴቶች ልጆች አደን አያድኑም። ትንንሽ ጎጆ ቤቶችን ይሰራሉ። አሻንጉሊት በጭቃ ወይም በእንጨት ያበጃሉ። እድሜአቸው አምስትና ስድስት አመት ሲሞላቸው በጎችንና ፍየሎችን በማገድና ህፃናትን በመንከባከብ ወላጆቻቸውን መርዳት ይጀምራሉ። ወንዶቹ ቀን ቀን ከተለያዩ አካባቢዎች ከተሰባሰቡ እረኞች ጋር አብረው ያሳልፋሉ። የትግል ጨዋታም ይጫወታሉ። ትልልቅ እየሆኑ ሲመጡ ደግሞ ከብቶችን ማገድ ይጀምራሉ። አነስተኛ በረቶችንም ይሰራሉ።
ይቀጥላል....

@wegoch
@paappii
-ቦረን-
ክፍል አምስት
ቦረንና ጦኾሳ ምንና ምን ናቸው?
ኔልሰን ማንዴላ የጦኾሳ ጎሳ ተወላጅ ነው። እድሜው አስራ ስድስት ሲሞላ በጦኾሳ ባህል መሠረት ወደ "ሙሉ ሰውነት" ለመሸጋገር ከእድሜ እኩዮቹ ጋር ከሚኖሩበት ሰፈር ራቅ ብለው ወደ ተሰሩ የግርዛት ጎጆዎች ተወሰዱ። የተወሰኑ ቀናቶችን ልጅነታቸውን እንዲሰናበቱ የተለያዩ ጨዋታዎችን ተጫወቱ።
በሌሊት ወደ ወንዝ ተወስደው ገላቸውን እንዲታጠቡ ተደረጉ። ከእዛም ብርድ ልብስ ብቻ ለብሰው ቆሙ። ተመልካቾች ባሉበት ብርድ ልብሱን መሬት አንጥፈው እግራቸውን ከፍተው ተቀመጡ። በግርዛት በሰለጠኑ ሽማግሌ በስለት ተራ በተራ ተገረዙ። ማልቀስ ውርደት ስለሆነ ግርዛቱ እንደተፈፀመ ስቃያቸውን ውጠው በውስጣቸው እያለቀሱ "ሙሉ ሰው!" እያሉ ጮኹ።
ቁስላቸው በቶሎ እንዲደርቅ ባህላዊ መድሃኒት ተቀቡ። እስኪድኑ ድረስ በጎጆዎቹ ውስጥ ቆዩ። ገላቸውን በኖራ ተለቀለቁ። ሸለፈተቸውን እርኩስ መንፈሶች ለክፉ ነገር እንዳይጠቀሙበት በሚል በሌሊት ወጥተው መሬት ምሰው ቀበሩ። ማንዴላ ሁኔታውን "ቅኔው ልጅነታችንን እየቀበርን እንደነበረ ገብቶኛል።" በማለት ገልፀውታል። (Long walk to freedom book)
ይኼው ሂደት በቦረና ይከናወናል። ወንዶና ሴቶች እድሜአቸው አስራ አምስት አመት ገደማ ሲሞላቸው በጠዋት ተቀስቅሰው ገላቸውን እንዲታጠቡ ይደርጋሉ። የከብት በረት ደጃፍ እንዲቆሙ ይደረጋሉ። አይኖቻቸው ይሸፈናል። ግርዛት ይፈፀምላቸዋል። ከዚያም ከመንደሩ ራቅ ብሎ ወደ ተሰሩ ዳሶች ይወሰዳሉ።
ቁስላቸው እንዲደርቅ ባህላዊ መድሃኒት ይደረግላቸዋል። እስኪድንምም ድረስ ወፎችን በቀስትና በደጋን እያደኑ በጎጆዎቹ ውስጥ ይቆያሉ።
በምሥራቅና በደቡብ አፍሪቃ የሚገኙ ሁለት ጎሳዎች ተቀራራቢ የግርዛት ስነስርዓትን ያከናውናሉ ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር። በእኩል እድሜ ያሉ ልጆች ከማህበረሰቡ ተነጥለው የግርዛት ስነስርአታቸውን ይፈፅማሉ።
በአፍሪካዊነታችን ከሚነጥለን ነገር ይልቅ አንድ የሚያደርገን ነገር ይበልጣል። የምንጋራቸው ባህሎችና ትውፊቶች ብዙ ናቸው።
ይቀጥላል..

@wegoch
@paappii
በመተው….

በቀደም ለታ አንዲት የማደንቃት ድምጻዊት ቃለመጠየቅ ሲደረግላት እየሰማሁኝ
ነበር። ይህች ምርጥ ኢትዮጵያዊ ድምጻዊት ባለትዳር ነበረችና ጋዜጠኛው
የሚከተለውን ጥያቄ ሰነዘረ።

“በዚህ ሙያሽ ላይ ባለቤትሽ እርዳታ ያደርጋል? ይደግፍሻል?”

“ባለቤቴ ይደግፈኛል……በመተው ይደግፈኛል፤ እራሴን እንድሆን በመተው፤ የስራ
ቀጠናዬ ውስጥ ባለመግባት በመተው ይደግፈኛል” ብላ መለሰች። መልሷ
ውስጤ በእጅጉ ስለገባ ይህንን አጭር ጽሁፍ እንድሞነጭር መነሻ ሆነኝ።
ምናልባት የድምጻዊቷን ማንነት መግለጽ ካለብኝ፤ ድምጻዊት ዘሪቱ ከበደ ናት።

እውነትም በተመው ብቻ ብዙ ሰው መርዳት እንችላለን። ሌላ ነገር ማገዝ
ቢያቅተን እንኳን በመተው ብቻ ያ ሰው ሙሉ አቅሙን እንዲጠቀም
እንፈቅድለታለን። ከዚህ ቀደም በአንደኛው የማነቃቂያ ጽሁፌ ላይ የተጠቀምኩትን
አጭር ታሪክ በድጋሜ ላንሳው። በአንድ የክረምት ወቅት፤ ሁለት ህጻናት እየተጓዙ
ነበር። እየተጓዙበት የነበረው መሬት በረዶ የሰራ ነበርና በጥንቃቄ መጓዝ
ነበረባቸው።ምክንያቱም መሬቱ ቢሰነጠቅ የሚቀበላቸው እጅግ የቀዘቀዘ ውሃ
ነበርና። አንድ ሰው ከሰመጠም የሰመጠውን ሰው ለማውጣት እጅግ ከባድ
ጉልበት ይጠይቃል። ታዲያ በጉዞዋቸው መካከል በረዶው ይሰነጠቅና አንደኛው
ልጅ ይሰምጣል። ሌላኛው ልጅ ጓደኛውን ለማዳን ያንን የተጋገረ በረዶ በሰፊው
መፈረካከስ ነበረበት፤ ለዛ ደግሞ ከፍተኛ ጉልበት ይጠይቃል። ሲበዛ የጨነቀው
ወጣት፤ ጓደኛውን ለማዳን ይሯሯጥ ጀመረ፤ በአካባቢው ማንም ሰው
አልነበረምና፤ እየሮጠ ሄዶ ከአንድ በረዶ ካደረቀው ዛፍ ላይ ትልቅ ቅርንጫፍ
ይዘነጥልና ያለ የሌለ ጉልበቱን ተጠቅሞ ጓደኛውን ከተቀረቀረበት በረዶ
እንደምንም ብሎ ያወጣዋል።

ቀጥሎ የሰፈሩ ሰዎች የሆነውን ሲሰሙ ግራ ተጋቡ። ደቃቃው ወጣት በምን
አቅሙ ያንን የሚያህል የዛፍ ቅርንጫፍ ገንጥሎ፤ ያንን የበረዶ ክምር ለብቻው ያለ
ማንም እርዳታ ደቅድቆ፤ ጓደኛውን እንዴት እንዳወጣው ግራ ገባቸው። ተዓምር
ሆኖባቸው በጥያቄ “እንዴት አድርገህ?” እያሉ ያጣዳፉት ጀመር። ይሄኔ
ከመካከላቸው አንድ አዛውንት እንዲህ ሲሉ ልጁን ወክለው መልስ ሰጡ።

“እኔ እነግራችኋለሁ፤ ይህ ወጣት ለጉልበተኛ ሰው እንኳን የሚከብደውን ስራ
ሊሰራ የቻለው፤ በአካባቢው ማንም “ተው አትችልም” የሚለው ሰው ስላልነበረ
ነው፤ ብቻውን ስለሆነ፤ ሌላ ሚስጥር የለውም” አላቸው። አጋዥ ባይኖር እንኳን
ተው የሚል አለመኖሩ እራሱን የቻለ ትልቅ እርዳታ ነው።

የዘሪቱን የቤተሰብ ሁኔታ አላውቅም። ለእኔ ግን ለጥያቄዋ የሰጠችው መልስ
አይን ገላጭ መስሎ ታይቶኛል። እውነተኛ ድግፍንና ፍቅርን ደስ በሚል
መልኩ ገልጻዋለች። አጠገባችን ያሉ ሰዎች “በመተው” ብቻ ብዙ እርዳታ
ማድረግ እንደሚችሉ፤ እኛም ለሌሎችን “በመተው”ብቻ ብዙ እርዳታ ማድረግ
እንደምንችል የሚያስታውስ ድንቅ ንግግር ነበር። የአና ፍራክን ያህል የዋህነት
ባይኖረኝም፤ በሰዎች መልካምነት አምናለሁ። የምንቀርባቸው ሰዎች አውቀው
ይጎዱናል ብዬ ማሰቡ ደስታን አይሰጠኝም። ከፍቅር የተነሳ እንቅፋት ሊሆኑ ግን
ይችላሉ። እኛም ከፍቅር እና ከቅርበት የተነሳ እንቅፋት ልንሆን እንችላለን።
ምክንያቱም ሰው እራሱን እንዲሆን መተው ከባድ ስለሆነ፤ ሰው በራሱ እቅድ
እንዲመራ መተዉ ቀላል ስላይደለ። እኛ ሰውን እንደምንፈልገው መለወጡ
ስለሚያስደስተንና ትክክል ስለሚመስለን።

ቤተሰብንና ጓደኝነትን የሚያስተሳስረውና ይበልጥ እንዲያብብ ማዳበሪያ
የሚሆነው “ነጻነት” ይመስለኛል። ሰው የሚወደውን እንዲሆን “መተው” ትልቅ
እገዛ ነው። ሌስ ብራውን የተባለው ጸሃፊ እንዲህ ይላል “ሌሎችን ለመለወጥ
አትሞክር፤ እራስን መለወጥ የሙሉ ሰዓት ስራ ነውና”። ሰዎችን እንደሆኑት
መቀበል ለእኛ ለሰዎች ከባድ ስራ ነው። ምክንያቱም ሌሎችን ለመወደድና
ለመቀበል እኛ እንደንፈልገው እንዲሆኑልን ስለምንፈልግ። ምንም እንኳን ሰዎች
እኛ እንደምንፈልጋቸው እንዲሆኑልን ብንፈልግም፤ ማንም ያለገዛ እራሱ ፈቃድ
አይለወጥም። በእኛ ጉትጎታ ያ ሰው ቢለወጥ እንኳን አስመሰለ ወይም ተገደደ
ነው እንጂ የሚባለው፤ እራሱን ሆነ ማለት አንችልም። በመተው ውስጥ ግን
የሰውን እውነተኛ ማንነትና ባህሪ ማወቅ ይቻለናል…….ከምንም በላይ ግን
ለሰዎች እውነተኛ ማንነታቸውን እንዲሆኑ መተው መቻላችን ለእነሱ ትልቅ እገዛ
ነው። ከማገዝ እኩል ትልቁ ድጋፍ መተው ነው ማለት ነው እንግዲህ!

ሸጊቱ ቅዳሜ!!💚💛❤️

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
“We live in a world full of mediocrities- lacking passion for things. People work for money, prefer texting instead of making face-to-face conversations, even sexting because making love is “too mainstream”. I walk around and see people hiding so much of pain within, their dull faces wearing the brightest smiles. It feels like the way people who are about to die smile for the last time. Nobody wants to commit to love, people want to cheat and fuck and get away with it. Their way of living has changed from relishing each moment to merely surviving each day as it comes. Everybody needs their own space and privacy and families do not stay together anymore. It is sad how ‘life’ is getting rare and how rotten we feel.”


But we can be different.
#19
#19

@words19
@words19
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለገና በአል በሰላም አደረሳችሁ።

Wishing my fellow Ethiopians a warm and happy Christmas!

@getem
@Wegoch
@seiloch
ክርስቲያን ወንድም እህቶቼ!
በገናው፣ "በእለተ-ሰላም ውልደቱ" ፊታችሁ ላይ የምናየው ሰላምና ደስታ ይቆይላችሁ፣
በቤታችሁና በቀያችን ይበርክት። ሳቅና ደስታ እድሜን የሚያረዝም፣ ጤናን የሚያለመልም
መድሃኒት ነውና፣ ዛሬ ስለገናው የምናየው የፍቅር ጭስ ሽታ በሁሉም ልብና በሚመጡት
ጊዜያት ይናኝ፥ ይበርክትልን!!💚💛❤️
ቅርርርርር ያሰኘናችሁና ያስከፋናችሁ ብትኖሩ ይቅር በሉን።
መልካም አውዳመት!!
ቀያችን ሰላም ይሁን።💚💛❤️

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
የዶሮ ብልት ለፖለቲከኞቻችን ቢከፋፈል ማን ምን ይደርሰዋል? 😁

ኦቦ ለማ― ፈረሰኛ
አብይ አህመድ ― ረጅም እግር
ደመቀ መኮንን ― ክንፍ
ገዱ አንዳርጋቸው ― ሌላኛውን ክንፍ
ደፂ— ታልማ
ጌታቸው አሰፋ ― ቆለጥ
(ያው እንደሚታወቀው አውራዶሮ ቆለጥ አለው)
ጌታቸው ረዳ ― ሳለአይሰጥ
ንጉሱ ጥላሁን ― ማላላጫ
ኦቦ አዲሱ ― ሌላ ማላላጫ
ዳውድ ኢብሳ ― ጉበት
ጃዋር መሐመድ ― ቆዳ

@paappii
@wegoch

#yoseph
ጥላቻ ቀድሞ የሚገለው ማንን
ነው? የምንጠላውን ወይስ
እኛን?
(በሚስጥረ አደራው)

እንደሚታወቀው የአሜሪካኖች ዋናው ችግራቸው በጥቁሮችና በነጮች መካከል
ያለው የዘር ልዩነት ነው። ይህም በተለይ የነጮችን የበላይነት በሚያራምዱ ጥቂት
በማይባሉ ሰዎች የሚቆሰቆስ እሳት ነው። የሚገርመው ግን ይህ የዘር ልዩነት
እሳት የሚነሳው፤ በእያንዳንዱ ግለሰብ ልብ ውስጥ በተቀጣጠለች ትንሽዬ ፍም
ነው። እኔም ሰሞኑን ጥያቄ የሆነብኝ ይህ “ፍም” እንዴት ልባችን ውስጥ ገባ?
የሚለው ነው። ነገሮች በአገር እና በማህበረሰብ ደረጃ ከመታየታቸው በፊት
በግለሰብ ደረጃ መቃኘት አለባቸው ብዬ አምናለው። ምክንያቱም አገር ማለት
“እኔ” እና “እኔ” ሲደመር ማለት ስለሆነ፤ የችግሮች ሁሉ እሳት መነሻው ግለሰብ
ነው ብለን መደምደም እንችላለን።

ጥላቻ ከፍቅር ይበልጥ ጉልበትን የሚጠይቅ ስሜት ነው። ፍቅርን በቁልቁለት፤
ጥላቻን በዳገት መመሰል ይቻላል። ፍቅር የሰው ልጅ ተፈጥሮ ስለሆነ፤ ምንም
ጉልበት የማይጠይቅ በቀላሉ የምንጓዘው መንገድ ነው። ጥላቻ ግን በጉልበት
የተሞላ፤ በፍርሃት የሚገፋ ከባድ ተራራ ነው። ምንም እንኳን ጥላቻ እጅግ የቆሸሸ
ነገር ቢሆንም፤ የሰውን ልጅ ልብ ግን ፈጽሞ ሊያመነችክ እንደማይችል የሚያሳይ
ታሪክ ላውጋችሁ። አመታትን ያስቆጠረ ጥላቻ፤ በፈጣሪ ሃይል ብቻም ሳይሆን
በተራ ሰው ትንሽ ፍቅር የሚረታ ነገር መሆኑን ይህ ታሪክ በእርግጠኝነት ያሳያል።

ጆኒ ሊ ኬሪ ይባላል፤ በወጣትነቱ ነበር የነጮችን የበላይነት ያራምድ የነበረውን
የጥላቻ ቡድን ኬኬኬን (KKK) የተቀላቀለው። በአንደበቱ እንደተናገረው ውስጡ
በጥላቻ የተሞላ እረፍት የለሽ ሰው ነበር። ሲበዛ ጥቁሮችን ይጠላል፤ ጥቁሮችን
ብቻም ሳይሆን ነጭ ያለሆነ ማንኛውንም ሰው ይጸየፋል። ጆኒ ኬኬኬን ከተቀላቀለ
በኋላ እንደሱ በጥላቻ ከተሞሉ ሰዎች ጋር በመሆን ሌሎችን በመመልመል፤ ከተራ
አባልነት ወደ መሪነት አደገ። በየሚዲያዎች እየቀረበም የቆመለትን የጥላቻ አላማ
ሲሰብክ እና ሲያራምድ ቆየ።

በ1979 እ.ኤ.አ ጆኒ ለአንድ የሬድዮ ጣቢያ ክርክር እንዲያደርግ ተጋበዘ። ክርክሩ
የተደረገው እሱ የነጮችን የጥላቻ ቡድን ደግፎ፤ ዌድ ዋትስ የተባለ ጥቁር
አሜሪካዊ ደግሞ የጥቁሮችን መብት ብቻም ሳይሆን የመላ ሰውን እኩልነት
ወክሎ ነበር። በነገራችን ላይ ዌድ ዋትስ የማሪቲን ሉተር ኪንግ የቅርብ ጓደኛ
ከመሆኑም በላይ ለጥቁሮች ነጻነት በተደረገው ትግል ከፍተኛ አስተዋጽዎ
አበርክቷል። በእለቱ የሆነውንና በጆኒ አንደበት የተነገረውን እነሆ

“የጠበቅኩት፤ የአፍሪካ ልብስ የለበሰ፤ ጸጉሩ የተንጨባረረ ጥቁርን ነበር፤ “ነጮች
ይውደሙ” የሚል ትቢተኛ ጥቁር። ነገር ግን ዌድ ዋትስ ሲገባ፤ ሱፍ ለብሶ በእጁ
ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ይዟል። እጁን ዘርግቶ ሲጨብጠኝ፤ የኬኬኬን ህግ
የጣስኩኝ መሰለኝ። በኬኬኬ ህግ መሰረት አንድ ነጭ ጥቁርን ከነካ ይበከላል።
የጨበጥኩበትን እጅ ስመለከት ዌድ ዋትስ ‘”አይዞህ ጥቁርነቴ አይለቅም” ሲል
አሾፈብኝ። ቀጥሎም “ምንም ብታደርግ እኔ አንተን እንድጠላህ አታደርገኝም”
አለኝ። ከዛን ቀን ጀምሮ ብዙ ጥቃቶችን አድርገንበታል። ለምሳሌ ከጥቂት አመታት
በኋላ ቤተክርስቲያኑን አቃጠልንበት። ቤተክርስቲያኑን ከማቃጠላችን በፊት ዋትስን
በብዙ ፈትነነው ነበር። ምላሽ ግን አላገኘንም። ቤቱን በቆሻሻ እንሞላዋለን፤ ነጩን
ልብሳችንን (የኬኬኬ አባላት የሚለብሱትን) ለብሰን ቤቱ ሄደን አስፈራርተነዋል፤
በስልክ በአካል ብዙ ብለነዋል እሱ ግን በቀልድ ከመመለስ በቀር ምንም
አይለንም ነበር። ከዛ ሁሉ በኋላ ቤተክርስቲያኑን አቃጠልነበት። ሌላው ቢቀር
ቤተክርስቲያኑን አቃጥለንበት በስልክ ደውዬ ድምጼን በመቀየር “ከዚህ በኋላ
ብትፈራና ብትጠነቀቅ ይሻልሃል” ፤ ስለው ያወቀኝ በቀላሉ ነበር “ሀይ ጆኒ፤ ጊዜ
ወስደህ ስለደወልክልኝ አመሰግናለው፤ እኔም ፈጣሪም እንወድሃለን” ነበር ያለኝ።
ግራ ገባኝ፤ ሰው እንዴት ይህን ያህል ዘመን ጥላቻን በፍቅር ይመልሳል?
በመጨረሻ አንድ አጋጣሚ ተከሰተ፤ በወቅቱ ጥቁሮች ነጮች ምግብ ቤት
እንዲመገቡ ቢፈቀድም፤ እንደኔ አይነት ነጮች ግን እናስፈራራቸው ነበር፤ ታዲያ
አንድ ቀን ዌድ ዋትስ የሆነ ምግብ ቤት ሲገባ አየንና እኔና ጓደኞቼ ተከትለነው
ገባን። ዋትስ ዶሮ አዝዞ ሊበላ ተቀምጦ ነበር፤ እኔም ወደሱ ሄድኩና “ስማ ይህ
ምግብ ቤት የነጮች ብቻ ነው ፤ ከዚህ ውጣ እምቢ ካልክ ግን አንድ ነገር ቃል
ልግባልህ ፤ የቀረበልህን ዶሮ ምን እንደምታደርገው አይሃለው፤ እኔም አንተን ልክ
እንደዛው ነው የማደርግህ፤ (ከበላኸው እበላሃለው ማለቱ ነው) ይሄኔ ዌድ ዋትስ
ዶሮውን አነሳና ሳመው (ከሳምኩት ትስመኛለህ ማለቱ ነው)፤ ምግብ ቤቱ ውስጥ
የነበሩት ሰዎች ነጮችን ጨምሮ በሳቅ ሞቱ፤ ከዛን ቀን ጀምሮ ይህ አንድ ግለሰብ
እኛን ሁሉ እንዳሸነፈን ተረዳው፤ እሱን ማሳደዱን ተውነው፤ አሸነፈን” ሲል ለተለያዩ
ሚድያዎች ቃሉን በተደጋጋሚ ሰጥቷል።

የጆኒ በጥላቻ የተሞላ ህይወት ከአመታት በኋላ ተለውጦ ነበር። የእሱን የለውጥ
ሂደት ማንሳቱ አሁን አይቻለንም፤እረጅም ስለሆነ። ነገር ግን ጆኒ ዌድ ዋትስን “
የኬኬኬን ቡድን ያሸነፈ ብቸኛው ጥቁር፤ ምክንያቱም አይምሮውን እና ልቡን
ስለተጠቀመ” ሲል ይገልጸዋል። የጆኒ ሊ ህይወት በራሱ አስገራሚ ነው። ከዛ
የጥላቻ ህይወት ወጥቶ በአለም አገራት እየዞረ ፍቅርን ሰብኳል። ብዙ በጥላቻ
መንችከው የነበሩ ልቦችን ከራሱ ህይወት በመነሳት አጥቧል። ጥላቻ የሚገድለው
ጠይውን እንጂ ተጠይውን አለመሆኑን መስክሯል። የሚገርመው ከብዙ ጊዜ በኋላ
ሲያሰቃየው እና ሲያንገላታው የነበረውን ዌድ ዋትስን አግኝቶ ይቅርታ በመጠየቅ፤
አመታትን የዘለቀ ጓደኝነት መመስረት ችሎ ነበር። ዌድ ዋትስ ሲሞትም በጆኒ
እቅፍ ውስጥ ነበር፤ የመጨረሻ ቃሉም “የማርቲን ሉተርኪንግ ህልም እንዳይሞት
አደራ” የሚል እንደነበር ጆኒ ተናግሯል። አደራውን ለመፈጸምም እሱም ህይወቱ
እስከምታልፍ ጊዜ ድረስ ፍቅርን ሲሰብክ ኖሯል።

ጥላቻ በሽታ ነው፤ ምንም ጥያቄ የሌለው በሽታ። ይህ የዘር ጥላቻ ግን
በማህበረሰብ ደረጃ የሚስፋፋው፤ ግለሰቦች የራሳችንን በሽታ መታከም ስላቃተን
ነው። ያለንበት ግዜ ያስፈራል፤ የኔ ዘር የበላይ፤የሚለው አስተሳሰብ፤ ከፍርሃት
የሚመጣ ካልታከመ የሚገድል አስከፊ በሽታ ነው። ግን ምንም ያህል ቆሻሻ ነገር
ቢሆንም ፤ የሰውን ልብ ሊያመነችክ አይችልም፤ የይቅርታ ጠብታ በቀላሉ
ስለሚያጥበው። አንዳንዴ እኮ ካስተዋልነው በአገር ስም፤ በሃይማኖት ስም፤ በዘር
ስም ጥላቻን ስንደግፍ የቆምነው ለሃይማኖታችን፤ ለዘራችን እንዲሁም
ለአገራችን ሳይሆን፤ ግላዊ ምክንያቶቻችን ለጠነሰሱት ከንቱ የጥላቻ አጀንዳ
ነው። በእርግጠኝነት እዚህ አለም ላይ ጥላቻ የፈታው ችግር የለም፤ ታዲያ
ለምን? ጥላቻ አሁንም ድረስ ስር ሰዶ ቤተ እምነታችንን፤ ዘራችንን እንዲሁም
አገራችንን የሚያመሰው፤ እያንዳንዳችን በሽታችንን መታከመ ስላቃተን ነው።
ቢሆንም ግን ተስፋ አለ፤ እንደ ዌድ ዋትስ አይነት ሰዎች አንድ ሆነው ሺዎችን
ባያሸንፉ ኖሮ ምን ይውጠን ነበር?

እንደው የአለሙ ሰላም
ም ይቅር፤ የአገሩም አንድነት ይቆይ፤ ሰው ለገዛ ሰላሙ
ካሰበ ጥላቻን ማስወገድ ግድ ይለዋል፤ አሲድ በአንድ እቃ ውስጥ ብዙ ሲቆይ
መዝምዞ የሚጨርሰው የተቀመጠበትን እቃ ነው፤ ጥላቻም እንደዚሁ፤
የተቀመጠበትን ልብ ገዝግዞ ይጨርሳል እንጂ፤ የምንጠላው ሰውማ ምን
ይሆናል? የሚጠላ ልብ ፈጽሞ ደስታን ሊያስተናግድ አይቻለውም፤ ምናልባት
ለገዛ እራሳችን ሰላም ስንል ፍቅርን ብንለምድ ይበጀናል እንጂ፤ አገርማ የሰው
ድምር ብቻ እኮ ናት። ጥላቻ ሰው መግደሉ አይቀርም፤ ቀድሞ የሚሞተው ግን
የጠላው እንጂ የተጠላው አይደለም።

ሸጋ ቀን💚💛❤️!!!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
አረ ሼም የሚባል ነገር አለ ባሻዬ!
«ዘውድአለም ታደሠ»
ስኳርህ ለምን ከፍ አለ? ሲባል “በልጅነቴ ብዙ ሸንኮራ ስለበላሁ ነው” ብሎ የሚመልስ፣ ማርክ ዙከርበርግን በአማርኛ ሙልጭ አርጎ የሚሳደብ፣ አርባ ሳንቲም መልስ ከለከልከኝ ብሎ የወያላ ጥርስ በቦክስ የሚያወልቅ፣ ገላውን ባለመታጠቡ እጁን ሲያሳክከው “ገንዘብ ላገኝ ነው” ብሎ የሚደሰት፣ ሚስቱን ወጡ ላይ ጨው አበዛሽ ብሎ እየቀጠቀጠ ስለሃይማኖት ሲከራከር የሚውል፣ ከአራተኛ D ክፍል ሮጦ ወጥቶ በዚያው ከትምህርት ጋር የተቆራረጠ፣ ደረጃውን የጠበቀ ደነዝ እኮ ነው የፌስቡክ አካውንት ከፍቶ ስለምስራቅ አፍሪካ ውስብስብ ፖለቲካ እየተነተነ ጆሯችንን የሚያደማን ጎበዝ!
ማነህ ተንታኙ እስቲ ትንታኔህን ትተህ ዊሊ የቋንቋ ትምህርት ቤት ተመዝግበህ ስምህን ከናባትህ በእንግሊዝኛ መፃፍ ተማር። tank you very march። ብለህ ፅፈህ አራት ነጥብ እየተጠቀምክ ተንቀሳቃሽ ላይብረሪ ነኝ ስትል አይደብርህም እንዴ? ፌስቡክ ላይኮ ጭጭ ብለው የሚያነቡ፣ ፈጣሪን ካልፈሩ ዶክተር አርገውህ መልሰው ሊያደድቡህ የሚችሉ ነፍ ምሁራን አሉ ባሻዬ!
@wegoch
@wegoch
@yeyhudaanbesa
2024/09/28 21:32:45
Back to Top
HTML Embed Code: