Telegram Web Link
"ሰላሳ አስተናጋጅ ከመጀንጀን አንድ የወጥቤት ሴት መጥበስ ጥቅም አለዉ "ይልሃል በእንጀራ ስር ተደብቆ 3 የተሰነገ ቃሪያ ከች ያለለት ልጅ 😍😂

#ደርፌክ

@wegoch
@paappii
«ምን አስባ ነዉ. . . የሮፍናንን "እንደ ቀነኒሴ" የሚለዉን ዘፈን የጋበዘችኝ?» ይላል ምን ታስባለች! ቶሎ እየጨረስክ አስቸግረሃት ነዉ 😎🤩

#yoni

@wegoch
@paappii
ድሮ ነዉ አሉ አቦይ ስብሃት ያን የሚያህል ፊቱን ይዞ አንዱን ተጠርጣሪ «. . .ፊቴን እያየህ መልስልኝ» ይለዋል «አይቼ የማልጨርሰዉን ነገር አልጀምርም¡»
ህንድ ፊልም ፊት! ዘፈን ዘፈኑን እያሳለፈ አያየዉም¡ 😳😝

#yoni

@wegoch
@paappii
"አምባገነን " ማን ነው?

አንድ የሀገሪቱ ምሁር ስለሀገራቸው አንባገነን መሪዎች የሰጡት ምላሽ እውነታነቱ ለኛም በትክክል የሚሰራ ሆኖ በማግኘቴ ነው። ምሁሩ << በርካታ ፒሩቫውያን የትራፊክ ቀይ መብራት ሲበራ ምን እንደሚያደርጉ ታውቃላቹ? ግራ እና ቀኙን ተመልክተው መኪናቸውን ያስፈተልካሉ። ባንክ ውስጥ ረጅም ሰልፍ ሲመለከቱ ምን የሚያረጉ ይመስሏቹሃል? አዘናግተው ከመሀል ጥልቅ ይላሉ፤ሌላው እንደነሱ ሲገባ ሲገባ ከተመለከቱ ግን ይጮኻሉ። አረንጓዴ መብራት እስኪበራ የማንጠብቅ ከሆነ ፤ ሰልፋቸውን ይዘው ለሰዓታት የቆሙትን የማናከብር ከሆነ፤ታድያ ለምንድነው ፕሬዝዳንቱ ሥልጣን ተጠቅሞ ገንዘብ መዝረፉ የሚገርመን? ልዩነቱ እኮ የመጠን ጉዳይ ብቻ ነው፤የትምህርት ሥርዓቱ እንዲህ አይነቱን የሕዝብ ባህሪይ መቀየር ካልቻለ ፓለቲካዊ ብልሹነትን መዋጋት አይችልም። በተለይ ወጣቶች ይህንን ሊረዱ ይገባል። የአንድ ሰው መብት የሚያበቃበት ሥፍራ ላይ የሌሎች ይጨጀምራል>> ብለዋል። ሐሳቡ ሲጠቃለል የአምባገነንነት መነሻው ሕዝብ ነው። የፓለቲካ ሹሞች ባይሆን መድረሻው ናቸው።


ምንጭ:- ኃይለጊዮርጊት ማሞ ( ጲላጦስ )

"አምባገነን "ማን ነው ? ከሚለው ቅዳሜ ከወጣችው የፍትህ መፅሔት ላይ ለወግ የቴሌግራም ቻናል እንዲስማማ ተቀንጭቦ የቀረበ !!!!

ሸጋ ሸጊቱ ቀን ይሁንልን!!💚💛❤️

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ምን ለያየን?

ለአንዳንዶች ህይወት የተለየ ትርጉም አላት። ከጸሃይ መውጣት መግባት ባሻገር፤
ከክረምት በጋ መፈራረቅ ባሻገር፤ ህይወት የሆነ የተለየ ትርጉም አላት። እኒህ
ሰዎች ለአቅማቸው ግድብ አያበጁም፤ ታልቅ ለመሆን የሌሎች ሰዎችን ፈቃድ
አይጠይቁም፤ የተፈጠሩት ለሆነ አላማ እንደሆነ ያምናሉ። የተቀበረውን
ችሎታቸውን ለማውጣት ፤ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ይጥራሉ። መውደቅ ማለት
የአላማቸው ማክተም ሳይሆን፤ ይበልጥ የሚጠነክሩበት እና ገዝፈው
የሚመጡብት እድል ነው። አመንም አላመንም ታላቅነት በሁላችንም ውስጥ ያለ
ነገር ነው። ደስተኛ በሆኑት እና ባልሆኑት፤ ስኬታማ በሆኑት እና ባልሆኑት፤
በአሸናፊዎች እና በተሸናፊዎች መካከል ያለው ልዩነት የአስተሳሰብ ልዩነት ብቻ
እንደሆነ የተረጋገጠ እውነታ ነው። ታላላቅ ሰዎችን ልዩ ከሚያረጋቸው ባህሪያት
እና ከተገለጹላቸው ሚስጥሮች ውስጥ ጥቂቶቹ እነሆ…..

– የተመቻቸ ጊዜ አይጠብቁም- ቆይ ይሄን ሳገኝ ይህንን አደርጋለው፤ ይህ
ሲመቻች ያሰብኩትን እፈጽማለው ስንል መቼም የማንደርስበት የህይወት ቀጠሮ
እየያዝን ነው። ያሰቡትን ያሳኩ ሰዎች በሙሉ የተመቻቸ ጊዜ አግኝተው ሳይሆን፤
ጊዜውን ላለማጣት ሲሉ ብቻ ባልተመቻቸው ጊዜ እርምጃቸውን በመጀመራቸው
ነው። የተመቻቸ ጊዜ የምትጠብቅ ከሆነ መቼም አይመጣም። ሁሉም ሰዓቶች ፤
ሁሉም ጊዜያቶች ከኛ ውስጥ የሆን ነገር ማጉደላቸው አይቀርም፤ ስለዚህ
“የተመቻቸ ጊዜ” እየጠበቅክ ጊዜህን አታባክን….ከሁሉ በላይ ምቹዋ ሰዓት ይህች
ያሁና ደቂቃ ናት።

ደግመው ደጋግመው ይውድቃሉ- መጻፍ አትችልም ተብለህ ታውቃለህ፧ መሳል
አትችልም ፤ መዝፈን አትችልም፤ መናገር አትችልም፤ ጎበዝ መሆን አትችልም
ተብለህ የምታውቅ ከሆነ፤ የመውደቅን ስሜት ታውቀዋለህ ማለት ነው። እኔ
በግሌ ከአንዴ በላይ አትችይም ተብዬ አውቃለው። ያኔ ምኞቴ የሞተ ያከተመለት
መስሎኝ ነበር። በዚህ ምድር ላይ ህልም አጥፊዎች በማናችንም ህይወት
ውስጥ መኖራቸው አይቀርም። በወደቅክ ቁጥር የሚያነሳህ ሰው አትጥብቅ፤
እራስህን ቀና ማድረግ ካቃተህ ውድቀትህ ማንነትህ እንዲሆን ትፈርዳለህ። ብዙ
ስኬታማ ሰዎች ወዳቂዎች ናቸው፤ አንተ በወደቅክ ቁጥር ምን ያህል ትነሳለህ?

-“እንዴት” አይሉም- ብዙ ስኬታማ ሰዎች ሲጠየቁ፤ “እንዴት” የሚለው ጥያቄ
አላማህን እንድትጠረጥር እና በራስህ እንዳትተማመን ሊያደርግህ ይችላል
ይላሉ። ምክንያቱም እንዴት ካልን ብዙ መልስ የሌላቸ ጥያቄዎች ይነሳሉ። እንዴት
የሚለውን ጥያቄ ለማምልጥ፤ ትኩረታችንን በዛሬ ላይ ማድረግ ነው። አንዴ አንድ
ታዋቂ የውጭ ሃገር የፊልም ሰሪ አንድ ግሩም ታሪክ ሲናግር ሰምቼው ነበር። ይህ
ሰው ልጅ እያለ አባቱ እሱን እና ወንድሙን ወደ አንድ ወደፈረሰ ግንብ
ይወሳደውና፤ መለሰው እንዲገነቡት ይነግራቸዋል። ይሄኔ አባታቸውን “እንዴት ነው
ትልቅ ግንብ መስራት የምንችለው፧ አይሆንም ” አሉት። አባትየው መልሶ “እንዴት
አትበሉ….ማድረግ ያለባችሁ እያንዳንዱ ብሎኬት መቀመጥ እንዳለበት
ማስቀመጥ ብቻ ነው…..ትልቅ ግንብ መስራት ሳይሆን ፤ ብሎኬቱን በትክክል
በማስቀመጥ ላይ ብቻ አተኩሩ፤በመጨረሻ ትልቅ ግንብ ይኖራችሃል” አሉ።
አንተም እንዴት ታዋቂ እንደምትሆን፤ እንዴት ስኬታማ መሆን እንዳለብህ
አትጨነቅ፤ አሁን ማተኮር ያለብህ፤ ወደዛ የሚወስድህ መንገድ ላይ ነው። በቀን
ምን ያህል ጊዜ ለምትፈልገው ነገር ታሳልፋለህ፧……..መስራት ያለብህን ነገርስ
ምን ያህል በጥራት እና በልበ ሙሉነት ትሰራለህ

– ልዩ መሆንን አይፈሩም- እርግጥ ነው የተለየ አስተሳሰብ ካለህ ፤ ከብዙሃኑ
መለየትህ አይቀርም።በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት አታግኝም። ያ ግን ሃሳብህን እና
መንገድህን እንድትቀይር አያድርግህ። በተለይ ተዘፍቀህበት ከነበረው ህይወት
ለመውጣት የምትታገል ከሆነ፤ ብዙ ሰዎች መልሰው ሊጎትቱህ ይሞክራሉ። ለየት
በማለትህ፤ ከስዎች ላትጣጥም ትችላለህ፤ የሰው ስሜት ልትጎዳ ትችላለህ…
ላንተ የቱ ይገዝፍብሃል? ሰዎችን ማስደስት ወይስ? የምትፈልገውን መሆን?

-እራሳቸውን እጅግ ይወዳሉ- እራስን መውደድ ማለት ከልክ ያለፈውን እራስ
ወዳድነት ሳይሆን፤ እራስን መቀበል ማለት ነው። ሰውነትህን ተንከባከበው፤
ለጤናህ ትኩረት ስጥ፤ ምክንያቱም ስኬታማነት ወይም ደስተኛነት ንቁነትን
ይጠይቃል። ተፈጥሮ የሰጥችህን መልክ ውደደው። ትልቁ ውብት እራስን መሆን
ነው። አንዳንዴ መላካቸው አይን ውስጥ የማይገባ፤ግን ጠንካራ መንፈሳቸው
ፊታቸው ላይ ፈሶ ለመግለጽ የሚከብድ ውበት ያላቸው ስዎች አጋጥማችሁ
አያውቅም›፤ እኔ ብዙ ጊዜ አጋጥሞኛል።

----------------------------------------------

ሰውዬው!!!!!!!!

በእንቶ ፈንቶ ወሬ፣
በአርቲ ቡርቲ፣ ጩኸት፣
በድሪቶ ድልቂያ፣
ይወድቃል መስሏቸው፣ሲገፉ ሲገፉ፣
ጭራሽ!!!!
ጎራውን የሚንድ፣
ገፍትሮ የሚጥል፣
ጥሶ የሚገባ፣ የቆላ ጅግሳ፣
ሰባብሮ የሚጥል፣ አርማጃው ጃውሳ።
ልቡ ሙልት ያለ፣
ውስጡ የታተመ፣
በድልና ስኬት፣ ካፍ እስከ ገደፉ፣
ይህንን ጃውሳ፣
የብረት ግድግዳ፣
የብረት ምሰሶ፣አርገውት አረፉ!!!!!!!

((( ጃ ኖ ))💚💛❤️

ሸጋ ጁምኣ!!!💚💛❤️

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ይሄ አፍና ቂጡ የማይለይ የአዲስ አበባ ባቡር ራሱ አንዱ የሃገሪቱን ሁኔታ የሚያሳይ ነዉ .....ይለፍና እሻገራለዉ ብዬ ጠብቄዉ ወደኋላ አልሄደም? 😳😜

አሁን ይቺ ጃምቦ ዉስጥ ዘላ የገባችዉ ትንኝ ኮንፊደንሷን ስታየዉ ራሷ ያዘዘችዉ ድራፍት ነዉ ያስመሰለችዉ 😌😄

#ደርፌክስ

@wegoch
@paappii
“ከእንግዲህ እንቅልፍ የለችም፣
የዕረፍት አድባር አጣች መቅኖ
ማክቤዝ እንቅልፍን ገደላት፣
በእኩለ-ሌሊት አፍኖ”

ሼክስፒር
ትርጉም- ፀጋዬ ገ/መድህን


የናዚ ዘመን ታሪክ ከተከሰተ ረዥም ጊዜ ቢሆነውም፣ እስከዛሬ ግን ተተርኮ
አላለቀም፡፡ ይፈለፈላል፣ ይዘረዘራል፡፡ ይተረተራል፡፡ ድብቁ ይገለጣል፡፡
የተገለጠው ይብራራል፡፡
የእኛስ?
ገና መፃፍ አልተጀመረም ብንል ይቀላል፡፡
ማስረጃው የሰሞኑን ዓይነቱ መራራና ጭካኔ የተሞላ ዶኩመንታሪ ነው፡፡ ጥቂት
ቀልብን ሰብስቦ አድርጎ፣ መፃፍ መጀመር አለበት፡፡
ለዛሬ በናዚ ተረት እናዝግም፡፡
* * *
ከዕለታት አንድ ቀን አንድ የናዚ ጄኔራል፣አንድ መገደል ያለበት ሰው እንዲገደል
ለጋሻ ጃግሬዎቻቸው ትዕዛዝ እየሰጡ ነበር፡፡
ጄነራል፤
“ትሰሙኛላችሁ?”
አንደኛው ጋሻ ፤-
“አቤት ክቡር ጄኔራል? ምን እንታዘዝ?”
ጄኔራል፤
“አንተኛውስ?”
ሁለተኛው፤
“እያዳመጥኩ ነው”
ጄኔራል፤
“በደምብ ስሙ! አንድ ከከተማ ውጪ ተወስዶ መገደል ያለበት ፀረ-
መንግሥት ሰው አለ፡፡ መገደል ያለበት በጣም ራቅ ያለ ቦታ ተወስዶ ሲሆን፤
ምንም ዓይነት የጥይት ድምፅ የከተማችን ህዝብ መስማት የለበትም፡፡
ምክንያቱም ህዝባችን ከተረበሸ ሰላም ይደፈርሳል! ስለዚህ ማንም ሰው
የጥይት ድምፅ ቢሰማ ወዮላችሁ!!” አንደኛው - ጋሻ ጃግሬ (ሰላምታ
እየሰጠ)፤
“ታዛዥ ነን ጄኔራል!”
ሁለተኛው - ጋሻ ጃግሬ፤
“ፍፁም ታዛዥ ነን ጄኔራል!”
ቀጠሉ ጄኔራል፡፤
“ደግሞ ቢያመልጥ ወይም ቢድን፤ በገመዱ እንደምትገቡ እወቁ፡፡
እያንዳንድሽን አንጠለጥልሻለሁ!”
ሁለቱም ባንድ ድምፅ፤
“በፍፁም ጄኔራል ሆይ!”
ጄኔራል፤
“ነገ ጠዋት ይፈፀም!”
ሁለቱም፤
“ዝግጁ ነን ጄኔራል!”
ጄኔራል፤
“አሰናብቻችኋለሁ!”
ጋሻ ጃግሬዎቹ ወደ ክፍላቸው ሄዱ፡፡ በነጋታው እሥረኛውን አስጠርተው፣
እጆቹን አሥረው ወደ መገደያው ሥፍራ መንገድ ጀመሩ፡፡ መንገዱ ቢሄዱት
ቢሄዱት እንደ አዳል መጫኛ የረዘመ ሆነ፡፡ ሰው ጥይት አይሰማም የሚሉበት
ቦታ ለመድረስ የአንድ ቀን ጉዞ ሆኗል!
እሥረኛው ሰውነቱ ዛለ፡፡ ተዝለፈለፈ፡፡ እዚያው እንዲጨርሱት ፈለገ፡፡ ስለዚህ
ቆመና፤ “ጌቶቼ፤ ልትገድሉኝ እንደምትወስዱኝ ተገንዝቤአለሁ፡፡ እባካችሁ ብዙ
ሳልደክም፣ እዚሁ ብትጨርሱኝ ምናለበት?”
ጋሻ ጃግሬዎቹም፤
“ዝም ብለህ ሂድ! አንተስ እዛው ስትደርስ ትገላገላለህ፡፡ እኛ አለን አደለም
እንዴ ገና ይሄን ሁሉ መንገድ የምንመለሰው?!” ብለው እየገፈተሩ ይዘውት
ሄዱ!
* * *
ሰሞኑ የተሰሩ ግፎችን የምንቆርጥበት መሆኑ መቼም የአደባባይ ምስጢር
ነው፡፡ ጭካኔያችን ለከት አጥቷል፡፡ አረመኔያዊ ድርጊታችን፣ ይህ ወሰንህ፣
ይህ ዲካህ የሚባል አይደለም፡፡ ስለ ሰላም እያወራን፣ ምድራዊ ሲዖል
ስንፈጥር ከረምን፡፡ ስለ ነፃነት እያወራን፣ አሰቃቂ ባርነትን በወገኖቻችን ላይ
ጫንን፡፡ ስለ ልማት እየሰበክን ዘረፍን፣ መዘበርን። በህዝብ ላብ ፎቅ አቆምን፡፡
ችግር ከማባባስ በቀር የመፍትሄው አካል መሆን አቅቶናል፡፡ የሰብአዊ መብት
ጥሰት የቆየ ያመረቀዘ ቁስል ነው፡፡ ህብረተሰቡ የመከላከል አቅሙን
እንዳያጠነክር ተቋማት ራሳቸው አቅመ - ቢስና ለቋሳ ናቸው፡፡ አፍአዊ ሳይሆን
ልባዊ ሆነን ግፍን በተግባር መዋጋት አለብን፡፡
O Justice thou hast flown to Beasts!
ፍትህ ሆይ! ወደ አውሬዎች ተሰደድሽ!
የተባለውን የሼክስፒር ጥቅስ ቀልብሰን፤ፍትህ ለተገፉ እንድትቆም ለማድረግ
ሌት ተቀን መለፋት አለበት፡፡ የማታ ማታ በዳይ የእጁን ማግኘት ይኖርበታል፡፡
የኢትዮጵያ ጫንቃ ኢ-ዲሞክራሲያዊነትን፣ ሐሳዊ - ፍትሕን፣ ምዝበራንና ኢ-
ሰብአዊነትን ለመሸከም ከእንግዲህ ምንም ቦታ ሊኖረው አይችልም፡፡
ጭካኔና አረመኔያዊ ድርጊት በተፈረካከሰ ኢኮኖሚ ላይ ሲጫን፣ ዘግናኝ
ትርዒት ነው የሚሆነው፡፡ የሰው ልጅን ዘቅዝቆ ከመስቀል፣ ለወራት
አንጠልጥሎ ከማቆየት እስከ ከፎቅ መወርወር ድረስ ምን አሰየጠነን?
ኢትዮጵያን በመሰለች ሃይማኖታዊ አገር ላይ ይህን መሳይ ግፍ ሲፈፀም፣
እያየንስ ግፉን እንዳናስቆም ምን ልባችንን ደፈነው? ከእንግዲህ ዐይናችንን
ወደ ውስጥ ገርተን፤
“ኧረ ምረር ምረር፣ ምረር እንደቅል
አልመርም ብሎ ነው፣ ዱባ እሚቀቀል!”
የሚለውን ማሰላሰል ይኖርብናል፡፡ “የቆቅ ለማዳ የለውም፡፡” የሚለውን
ተረትም አለመዘንጋት ነው፡፡ ግፈኞችን ለፍርድ ማቅረብን ዛሬ ብቻ ሳይሆን
መቼም ወደ ኋላ የማንልበት ልማድ ማድረግ አለብን፡፡ የመከራችንን ስፋት
ያህል የፍርድ ሂደቱም ብዙ ሳንካ እንደሚኖርበት አምነን፣ እንቅፋቶቹን
ለመቀነስ ጨክነንና ቆርጠን መነሳት ግድ ነው፡፡
ህዝብ ግፍ እንደተፈፀመበት መረዳት ሲጀምርና ሲያውቅ፣ ግፈኛው ከእንቅልፍ
ጋር መለያየቱ አይቀሬ ነው፡፡ የሼክስፒሩ ማክቤዝ፤ ያለ የሌለ ግፉን ፈፅሞ፣
እጁን በደም ታጥቦ፣ የመጨረሻዋ ሰዓት ስትደርስ የሚከተለው ተባለ፡-
“ከእንግዲህ እንቅልፍ የለችም፣ የእረፍት አድባር አጣች መቅኖ
ማክቤዝ እንቅልፍን ገደላት፣ በእኩለ - ሌሊት አፍኖ”
ግፍ ሰርቶ ተኝቶ ማደር የለም፣ ነው የሚለን!! ጥናቱን ይስጠን!!


ምንጭ: አዲስ አድማስ ጋዜጣ

ሸጋ ቀን!!!💚💛❤️

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
🎅ለገና በዓል ሦዕል በማሳል ለወዳጅ ዘመዶ ስጦታ ማበርከት ለምትፈልጉ።
በ +251984740577
ወይም @gebriel_19 order ማድረግ ይቻላል።

@seiloch
@seiloch
እርሳስ የሆነ ነፍስ ይስጠን

ይህን ታሪክ ያገኘሁት ድንቅ ከሆነው የባህርማዶው ፀሃፊ፣ ከፓውሎ ኮሄሎ
አጫጭር የታሪክ ስብስቦች ላይ ነው….የጎበጠን ህይወት ለማቅናት ከስነፅሁፍ
የላቀ ሃይል ያለው ነገር ምን አለ? ለእኔ ምንም የለም። ይህችንም አጭር ፅሁፍ
ሳነብ፣ ነፍሴ ሲሞረድ ተሰማኝ። እናም ለናንተም እንዲህ ተርጉሜ ላቀርበው
ወደድኩኝ

ከእለታት አንድ ቀን አንድ ህፃን አያቱ ደብዳቤ ስትፅፍ ይመለከታል። እናም እናቱን
እንዲህ ሲል ይጠይቃታል
“አያቴ ይህ የምትፅፊው ደብዳቤ ስለኛ ነው? እኔ እና አንቺ ስላደረግነው ነገር?”
አያቱም መልሰው “አዎ ልጄ የምፅፈው ስለ አንተ ነው፣ ነገር ግን ከምፅፈው ፅሁፍ
ይበልጥ የምፅፍበት እርሳስ ትልቅ ትርጉም አለው፤ አንተም ስታድግ እና ትልቅ
ሰው ስትሆን እንደዚህ እርሳስ እንድትሆንልኝ እመኛለው “ አሉት የልጅ ልጃቸውን
ቁልቁል እየተመለከቱት።

ህፃኑም አያቱ በጨበጡት እርሳስ ላይ ምንም አዲስ ነገር ባለማየቱ ግራ ተጋብቶ
“አያቴ አሁን የያዝሽው እርሳስ ከሌላው እርሳስ በምን ይለያል” አላቸው፤ አያቱም
ቀጥለው
“አየህ ልጄ፤ ሁሉም ነገር እንዳመለካከትህ ይለያል፤ ይህ እርሳስ አምስት ድንቅ
ባህሪዎች አሉት
አንደኛው፤ ይህ እርሳስ ያለ እጅ መፃፍ አይችልም፤ አንተም ምንም ድንቅ ተዓምር
መስራት እና መከወን የምትችል ሰው ብትሆንም እጅ የሚሆንህ ፈጣሪ ከሌለ ወጋ
የለውም።
ሁለተኛው፤ እንደምታየኝ እፅፍ እፅፍና እርሳሱ ሲዶለዱም አረፍ እልና በመቅረጫ
እቀርፀዋለው፤ ይበልጥም ሹል ይሆናል። ሰውም ቢሆን በህይወቱ ብዙ ውጣ
ውረዶች ያጋጥሙታል፤ ፈተናውም ሲያልፍ ግን ይበልጥ ሹል ይሆናል ማለት ነው።
ሶስተኛው ደግሞ ልጄ….. ይህ እርሳስ በማንኛውም ሰዓት የምሰራውን ስህተት
በላጲስ አጥፍቼ እንዳስተካክል እድል ይሰጠኛል። ይህ ማለት በህይወታችን
የምንፈፅማቸውን ስህተቶች ማስተካካል ነውር አይደለም፤ ይልቁንም እራሳችንን
እያረምን እረጅም መንገድ እንድንጓዝ ይረዳናል:
አራተኛው ድንቅ ባህሪ ደግሞ፤ የዚህ እርሳስ ታላቅነት ያለው የውጪ አካሉ ላይ
ማለትም አንጨቱ ላይ ሳይሆን፤ ውስጡ የተቀበረው ቀጭን ነገር ላይ ነው።
ሰውም ቢሆን እንደዛው፤ ሁሌም ቢሆን ታላቅ ነገር የሚሰራው ውስጣችን ያለው
ነገር ነው። እናም ልጄ ለውስጥህ ሰላም እና ደስታ ትኩረት ስጥ። ውስጥህ
መልካም ነገር ከሌለ መልካም ነገር ማድረግ ይሳንሃል።
አምስተኛው እና የመጨረሻው ምን መሰለህ ልጄ….. ይህ እርሳስ በተፃፈበት
ቁጥር ምልክት ይተዋል። አንተም እንደዛው…..በህይወት ጎዳና ስትጓዝ
ምልክትህን መተውህ አይቀርምና በኑሮህ የምትወስናቸውን ነገሮች ሁሉ
አስተውል። ምልክት ጥለው ማለፋቸው ስለማይቀር።” አሉት

ድንቅ ታሪክ አይደለም?……የዚህ ገፅ አለማ ምንም ሳይሆን መልካም መልዕክትን
ማስተላለፍ ብቻ ነው። እንደ እኔ አስተሳሰብ፤ ቤተሰብን፤ ማህበረሰብን፤ አገርን
ብሎም አለምን ለመለወጥ ከማሰባችን በፊት፤ እራሳችንን መለወጥ መቻል
አለብን። እስቲ አስቡት፤ ቀና አሳቢ ትውልድ ማነፅ ከቻልን፤ ምን አይነት ተዓምር
መስራት እንደምንችል? ቅድሚያ ግን እራሳችንን ለመለወጥ እንትጋ……ይህንን
መልዕክት ለሌሎችም እንድታስተላልፉልኝ አደራ እላለው፤ ካልተደሰታችሁበት ግን
መተው መብታችህ ነው።
----------------------------------------------

የኔ ህልም!!!!!!!!


አይደለም ስተኛ፣
በአልጋዬ ስወድቅ፣ ሌሊት የሚመጣ፣
አይደለም ፍራሽ ስር፣
ጋደም ባልኩ ጊዜ፣
በሰመመን እንቅልፍ፣ ተጭኖ እሚወጣ።
የምን እንቅልፍ ነው???
ይልቅስ ነቃ በል፣
የምን በረከክ በረከክ፣
እያለ ጧት ማታ፣ የሚወዘውዘኝ፣
እሱ ነው የኔ ህልም፣
አተኛትም ዛሬ!!!!!!
በል ተነስ!!!!!! እያለ፣ የሚነዘንዘኝ።

((( ጃ ኖ ))💚💛❤️


ሰኞን በሳቅና በሳቅ ልናሸንፋት ተነስተናል!!!!!!!

ቀኑ ለሰው ተሰራ እንጅ ሰው ለቀኑ አልተሰራም!!!!!!! እናም
ቀኑ የእኛ ቀን ይሆን ዘንድ ግድ ይለዋል!!!!!!
ሰው በልቡ እንዳሰበ እንደዚያው ይሆናልና ሳቅ በሳቅ
በሆነው ሃሳባችን ቀኑን ወደ ሳቅ ጅረት ለመለወጥ
ቆርጠን ተነስተናል!!!!!!

ፍልቅልቅ ፣
ድምቅምቅ፣
ፍክትክት፣
ሽብርቅርቅ፣
ፍንድቅድቅ፣ ያለ ሳምንት አንድዬ ይሰጠን ዘንድ ማን

ከልካይ አለው???? ማንም!!!!!!!!!!

ሸጊቱ ቀን💚💛❤️

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
Forwarded from ግጥም ብቻ 📘 (☺️ልዑል☺️)
እንድቅትዩን የስነፅሁፍ ምሽት

ምርጥ ምርጥ የጥበብ ሰዎች ስራቸውን ያቀርባሉ
በዋቢ ሸበሌ ሆቴል
መግብያ 50 ብር
ሐሙስ ታህሳስ 18/2011 አ.ም
በ 11:30

@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
@ኑገበያ online shopping
You can shop any thing

@nugebeya_online
@nugebeya_online
@nugebeya_online

✦✧Laptops
✦✧Smartphone
✦✧Shoes
✦Smart televisions
✦Box Guitar

Just contact us on
@Sherlockseller
@KidusA16 call +251945421100
+251989820764
If you want to order contact us
ወደ አላማህ እየተጓዝክ ከሆነ
የተመልካቹን ጩኸት አትስማ


ብቅ ባልኩኝ ቁጥር የሚኮረኩሙኝ ሲበዙ……በእኔ ቅድሚያ ማመን ያለበት
ማነው? እያልኩኝ ማሰብ ጀመርኩኝ፤ እኔ ወይስ ሌሎች ሰዎች?

ከልጅነት እስከ እውቀቴ ድረስ አንድ ነገር ለመስራት ስነሳ “አዪ…..ይህማ
የማይሆን ነገር ነው”፤ “ አይሳካም”፤ “ሁሉም ሰው ሞክሮት አልተቻለም” የሚሉ
ኮርኳሚ ንግግሮችን እስኪሰለቸኝ ሰምነቻለው። ሰምቻለውም ብቻም ሳይሆን
ተቀብያቸው እግር እና እጆቼን እንደካቴና አስረዉኝ ኖረዋል። ሁሉም በክፋት
ሳይሆን ፤ ለእራሳቸው አይሳካም የሚል አስተሳሰብ ስላላቸው ነው። ይህንን ሃሳብ
በደንብ ፈትፍቶ የሚያስረዳ አንድ ሳነብ ያገኘሁትን ታሪክ ላጫውታቹህ…..


አንድ ቀን ኤሊዎች ሁሉ ይሰበሰቡና አንድ ትልቅ ተራራን ለመውጣት እንዲወዳደሩ
ተደረገ። ተራራው ትልቅ ነበርና ውድድሩን የሚመለከተው ሁሉ “አይ…
አይሆንላቸውም”፤ “ተራራው ጫፍም በፍፁም አይደርሱም” “ኤሊ እኮ ናቸው
እንዴት ሊሳካለቸው ይችላል”፤ “ኸረ አሁን ይወድቃሉ” “ሆ ሆ የማይሆን ነገር …
ለምን ይለፋሉ?” ይላል። ሁሉም የተሰማውን ይሰነዝራል።አንድም ተመልካች
አንዳቸውም ከተራራው ጫፍ ይደርሳሉ ብሎ ያመነ አልነበረም።
የተመልካቹን ጩኸት ተከትሎ ፤ቀስ ቀስ እየለ….ተወዳዳሪዎቹ አንድ በአንድ
መቀነስ ጀመሩ፤ አንድ በአንድ ተስፋ እየቆረጡ….ከውድድሩ ወጡ። ጥቂቶች
በተስፋ ውድድሩን ይቀጥሉ ጀመር። ተመለካቹ “የማይሳካ ነገር ነው…..ቆይ አሁን
ያቋርጡ የለ” ይላል። ውድድሩ በገፋ ቁጥር የተወዳዳሪዎቹም ቁጥር መቀነሱን
ቀጠለ……በመጨረሻ አንድ ኤሊ ብቻውን ቀረ። ያ ኤሊ ታራራውን መውጣቱን
ተያያዘው…..ውድድሩን ያቋረጡትን ኤሊዎችን ሳይመለከት ብቻውን ገሰገሰ።

ተመልካቹ አሁንም እንደማይሳካ ቢጮህ እሱ ግን መንገዱን ከራሱ ጋር ተያያዘው።
እንዳሰበውም ከተራራው ጫፍ ደረሰ። ይህ ሁሉንም ያስገረመ ነበር። ውድድሩን
ያቋረጡት ኤሊዎች እና ተመልካቾች ይህ ኤሊ ብቻውን ውድድሩን እንዴት
እንደጨረሰ ገረማቸው…..ሊጠይቁት ሲሄዱ ግን፤ ያ ውድድሩን ያሸነፈው ኤሊ
የማይሰማ ደንቆሮ ሆኖ ተገኘ። የአሸናፊነቱ ሚስጥርም የማንንም ጩኸት እና
ንግግር ባለመስማቱ ነበረ።

ታልቅ ምኞት ካለህ፤ ጆሮህ ሌላውን አይስማ፤ “አይቻልም” “የማይሆን ነገር ነው”
የሚል ተመልካች ሞልቷልና ዝም ብለህ መንገድህን ተጓዝ። የተምለካቹን ንግግር
የምንሰማ ከሆነ…..የነፍሳችንን ጥሪ መስማት ያቅተናል፤ አላማቸንን በእንጭጩ
ይቀጩታል፤ ልንኖርለት የሚገባንን ህልም ቅዠት ያደርጉታል። “አይቻልም”
“አይሆንም” ሲሉ…….ነገሩን በራሳቸው አቅም መዝነው መሆኑን መዘንጋት
የለብንም። ህልም ካለን፤ አላማ ካለን፤ የምንኖርለት ነገር ካለ፤ ጀሮዋችንን ደፍነን
መጓዙ ይጠቅመናል።

የተመላካች አፍ የስንቱን ተወዳዳሪ ተስፋ አጨለመ፤ የስንቱን የተስፋ ጭላንጭል
በትንፋሻቸው አጠፋ? የስንቱን ጉልበት አንብረረከ። ተራራውን በስኬት ወጥተው
የምናያቸው ሰዎች ሁሉም፤ ውድድሩን መጀመሪያ ሲጅመሩ ብቻቸውን አልነበሩም፤
እጅግ ብዙ ሰው አብሮ ተሳትፏል። ነገር ግን አሸናፊ የሆኑት የሰውን ጩኸት
ያልሰሙት ብቻ ናቸው። እኔም እናንተም ልንደርስበት የምንጓጓለት ትልቅ የህይወት
ተራራ ይኖራል…….እናም ከጫፉ ለመድረስ ከፈለግን ጆሮዎቻችን አሉታዊ ነገሮች
እንዳይሰሙ እንድፈናቸው።
----------------------------------------------

እንደፈረደበት!!!!!


በአይሆንም መፈክር፤
ባይችልም ቀረርቶ፤
ልቡናው ተጋርዶ፤
ቀልብያው ታፍኖ፤
ምናቡ ተሰርቆ፤
መክሊቱና ህልሙ፤ የተሸፈነበት፤
ማንም ይነዳዋል፤ """ተጎተት!!!!""" እያለ እንደፈረደበት።

((( ጃ ኖ ))💚💛❤️

ሸጋ ቀን!!!!💚💛❤️

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
<< ዳግመኛም ሰሎሞን ዋዘኛን የሚገሥፅ ለራሱ ስድብን ያቀብላል፡ ሕግ ተላላፊውን የሚዘልፍ ነውርን ይወስዳልዋዘኛን አትገሥፅ እንዳይጠላህ። ብልሃተኛን ብትገሥፅ ግን ይወድኻል፤>>
ምሳ፦፱፥፯-፰

አራት በአራት በሆነ ትንሽ መንደር ውስጥ ብዙ ብዙ በጣም ብዙ የሚያስተቃቅፍ ፍቅር! የሚያስገርም መተሳሰብ! የሚዘገንን ጥላቻ! የሚያስጮው ጭካኔ! የሚያስጨበጭብ ፈጠራ! የሚያስደምም ተፈጥሮ! የሚያስተዛዝብ ስህተት! የሚያስተሳስብ ድርጊት! የሚያስቀናና ዕድገት! የሚያወያይ ፅድቀት!  የሚያስተፋፍር ብልጠት! የሚያቀያይስ ምርጫ! የሚያጨባብጥ ዕውቀት! የሚያጓጉዝ ስምምነት! እልፍ አህላፍ መንደሬነት በዚች ትንሽ መንደር ስር እትብታቸው ተቀብሯል እትብት ቆፍሮ የማውጣት ያህል አጥንት ሰባሪ መቅኔ ቆፋሪ የወሬ አፈሙዛሞች መንደሩን ወረውታል እነዚህን ሊቀ-ወሬያንን አራዳው ቃሪያ ሰጪ ፣ ሶኬት ፣ ሰዲ ፣ የወሬ እናት ፣  አሽቃባጭ  ሲላቸው ባህሉ አሊያ ዘልማዱ ደግሞ ወንፊት ፣ ወረኛ ፣ አውጃማ ፣ ቱልቱላ፣ ምላስ ልኩ ሌላም ሌላም ይላቸዋል በየጊዜው ስያሜያቸው ቅርፁን ቀያይሮ ታርጋ ይለጥፍ እንጂ ሰዋዊ ማህደር የመሆን አቅም ያላትን መንደር ፣ ማቁሰል ፣ ማሳመም ፣ ማጎሳቆል ነው ትርፉ በዚች መንደር ውስጥ ከተሜነት ስልጣኔ ቢያጠላ በራሱ ከተሜነቱንም ስልጣኔውንም መሻር አቅም ያላቸው ኃያል ምላሶች የመንደሯን ምሶሶ ተጠምጥሞ ይገኛሉ። ሠውን ባልዋለበት የሚያስገኙ ያለስም ስም የሚሰጡ አንስተው የሚያፈርጡ አፍርጠው የሚያነሱ ጉልበታም ምላሶችም አሉ። እውቁ ፈላስፋ #ዲዮጋን ስለምላስ እንዲህ ይላል "በምድር ላይ በፀጉር ቁጥር ልክ ጠላት ቢኖርህም እመነኝ ከዚህ ሁሉ ጠላትህ ይልቅ ምላስህን ፍራ ምላስ በሰኮንዶች ጭራፊ ጠላቶችህን ወዳጅም ጠላትም የማድረግ ተፈጥሮዋዊ አቅም አለውና" ይላል እውነት ነው እንኳን ትንሽ መንደርን ይቅርና ዓለምን አንድም ብዙም ያረጉ ምላሶች ዘመናችንን ሲያሳምሩም ሲያወሳስቡም አይተናል ስለዚህ እመኑኝ ነዋሪዎቿ የሚናከሱባት እንኳን ጠብ ይቅርና ቅንድብ ማስቋጠር አቅም የሌላቸው ወሬዎች ለመቀያየም የሚያፈላልጉ ከሆነ የሆነች ማድያታም መንደር እንደተፈጠረች እመኑኝ ለጥቅሙ ያደረ ሰብሃዊነትና ፍቅር ከኪሱ የማይበልጥ የሚመስለው
በዳደረ ጡንቻው ሁሉ በእርሱን አምኖ መስመር ዘላይ ንቀት ያሰረው
መሃልት አልኮል ውስጥ አምሽቶ ከጓዴው ጋር ያፋቀርውን ርዕስ የመንደሩን መሪ ቃል የሚያደርግ
ዕድሜው ማምለጡን በታናሾቹ ተስፋ ላይ ቁጭቱን የሚያራግፍ የትልቅ ቀላል
ሕግን እንደነባራዊ ምቾቱ ተርጉሞ ሆዱን የሚያነግስ አጋሰስ
እራሱን ያፀደቀው በሚመስለው ነጠላ ውስጥ ከልሎ ጠቋሚ ጣቶቹን ለሚንከባከብ ውዳሴ ከንቱ
ኩርማን ፍልስፍናን እያገባ እየፈታ ቀዬው ላይ ያልገባውን ለሚነሰንስ የከሸፈ ፈላስፋ
ሴትነቷን በጭኖቿ ውስጥ  እያጋለች የጎረምሳ ጠረን በዋለበት ሁላ ባደረበት የምታድር
ይሄ ሁሉ የተጎሳቆለችና የተጠላች መንደር ለመፍጠር ከበቂ በላይ ነው።
መንደርን ፈገግ ለማድረግ ብዙ ስራ አይጠበቅም መንደርን ለማከም ብዙ መቆፈር አያስፈልግም ዋናው ጠቃሚና ለዋጭ ሃሳቦችን ማውራት ብቻ ነው። ወጣትነትን ማልፋት መቻል ጎልማሳነትን ማስመራት መቻል እርጅናን ማስመረቅ መቻል ከቻልን ከማድያት የነጣች ንፁህ መንደር ማውረስ ቀላል ነው። መንደር ማለት ሀገር ነውና መንደርህን ስታክም ሀገርህን ታክማለ አበቃ!!!
አዲዮስ
:- #ተክለ_ዮሀንስ(ከሰባተኛ)

@wegoch
@wegoch
ወርቃማ ህጎች!
Written by አብይ ተስፋዬ አሳልፍ (አተአ)

ወርቃማው ህግ 1 - የተቸገረን (ሁሉ!) እርዳ !?
ወርቃማው ህግ የገባት አንድ ባኪ የምንላት ዝንጀሮ ነበረችን፡፡ አንድ ቀን
የምትኖርበት አካባቢ በጎርፍ ተጥለቀለቀ አሉ፡፡ ሜዳዎቹም፣ ጫካዎቹም
ተጥለቀለቁ፡፡ ባኪም ከአንድ ዛፍ አናት ተንጠላጥላ ወጣችና ቁጭ አለች፡፡
በዚያች ቅጽበት ከውሃ ውስጥ አንዲት አሳ ትጮህ ነበር - ‹‹አድኑኝ! ጎርፍ
ወሰደኝ!›› እያለች፡፡
ዝንጀሮዋም ጩኸቱን እየሰማች ዝም ማለት አልቻለችም፡፡ በዛፉ ላይ ወደ
ታች ወርዳ አሳዋን ከውሃው ውስጥ መንጥቃ አወጣቻትና ከዛፉ አናት ላይ
አስቀመጠቻት፡፡ አሁን ሁሉም ሰላም ነው ስትልም አሰበችና ጋደም ብላ
እንቅልፏን ትለጥጥ ጀመር። ያደረገችው በጎ ነገር የሚያስደስት እንደሆነ
ሁሉም ያውቃል፡፡ ግና ምን ያደርጋል፣ አሳ ያለ ውሃ እንዴት ይኖራል፡፡ ከጎርፍ
የወጣችው አሳ በውሃ እጥረት ትቃትት ያዘች፡፡
በድጋሚ ‹‹አድኑኝ! እርዱኝ ወደ ውሃው መልሱኝ!›› የሚል ጩኸት ይሰማ
ጀመር፡፡ ማን ሰምቶ፡፡ ዝንጀሮዋም እጅግ ተናዳባት ነበር፡፡ ምንድነው እንዲህ
ያለ ነገር፣ አንዴ አውጡኝ አንዴ አውርዱኝ እያሉ መጮህ፤ አለችና ተመልሳ
ተጋደመች፡፡
*
ለእረፍት ገጠር ከአያቶቼ ቤት የሄድኩ ግዜ፣ አንድ እሁድ ማለዳ መደቤ ላይ
እንደተጋደምኩ፣ በጭላንጭል እያጨነቆርኩ በማለዳ የሚካሔደውን
እታዘባለሁ። እማመይ (ሴት አያቴ) በጧት ተነስታ የሰንበት ቡና ታጫጭስ
ነበር፡፡ ወዲያው ደግሞ ወደ በሩ ብቅ አለችና ወደ ውጪ ትጣራለች… ‹‹….
አበቡ … አበቡ … እስኪ እባክሽ ከከሰሉ ጨምሪልኝ፣ ደግሞ ወተቱን
ለጌታመሳይ እለቢለት ቶሎ፡፡››
የአበቡ ድምፅ በሩቁ ይሰማኛል፡፡ ምናልባትም ከጓሮው ክምር አካባቢ እንዲህ
ትላለች፤ ‹‹… እመይ ደግሞ ፊት ይሰጡታል! አሁን እሱ ትልቅ ሰው ነው፡፡
እዚህ ቢሆን ኖሮ እንዲያውም ልጅ ወልዶ ለትምህርት ቤት ያደርስ ነበር፡፡
ታዲያ ምን ይሁን ብለው ነው በጦም ወተት ይሰጠው የሚሉ! ሆሆይ! … ያቺ
ድመት እንኳ አሁን አትጠጣም፡፡ ከቴም ልጁ ከተማ ሲገባ ቀበጠኮ!…›› …
አበቡ ያሳደገችኝ ሰራተኛችን ናት። ምንም ብትል ከመሳቅ ውጪ አልናገርም፡፡
ኸረ እንዲያውም ጨከን ብላ አይሆንም ብትል ላልጠጣ እችላለሁ፡፡ በዚያ
ላይ አባበይ ይህንን ከሰሙ አለቀልኝ።
‹‹…አይ እንግዲህ በጧት አትጀምሪኝ፤ ልጄን በሚፈልገው መልኩ እንጂ
በዚህ ዕድሜው የሚበላውና የሚጠጣውን እኔ እየመረጥኩ አደለም
የምሰጠው። ከተማ ሲኖር የሚበላውን እኛ እየሰጠነው መሰለሽ! ይልቅ ቶሎ
ቡሬን እለቢ…››
እያጉተመተመች ስትናገር ይሰማኛል፡፡ ‹‹…እመይ እኔኮ ሚገርመኝ፣ የቡሬ
ወተት ጦም የሌለው ሆኖ ነወይ! ያለሱ አይጠጣም እንዴ፤ ይልቅ ይቀስቅሱልኝ
ጥጃዋን እንዳጣባ ያግዘኝ…››
‹‹ተይው ባክሽ አሁን ይተኛበት፡፡ ሊያርፍ መጥቶ አንችን ጣለበት፤ እስከዛሬ
ማን ያግዝሽ ነበር!…››
‹‹ይሁን ግዴለም፤ ግን እመይ ጌትዬንስ ለዚያች መጎጥ አንድረውም፤
ምነውቴ!…››
‹‹ኸረ በህግ አምላክ! … የፃድቁ ያለህ! ደሞ ይህን ወሬ ከየት አመጣሽ!…››
‹‹እንግዲህ አገሬው የሚያወራው ነው … የጋሽ አየለን ልጅ ሊያገባት ነው
ተብሏል! ደግሞኮ እርሷ እምቢ አለች ይላሉ፡፡ የኔን ጌታመሳይ አግኝታ ነው፡፡
ድንቄም እቴ፤ የሰው ልክ አለማወቅ፡፡ የኛ ልጅ ቅብርር ያለ ጌታ ነውኮ!….››
እማመይ ቀስ እያለች ትስቃለች፡፡ ‹‹..በይ ዝም በይ። ወሬና ሳቅ አይደበቅ!
ይላሉ፡፡ ሆሆይ…››
የምሰማው ነገር እየገረመኝ እኔ ራሴ ሳቄ መጣ። ማናት የጋሽ አየለ ልጅ፡፡
ደግሞ ማነው ሊድረኝ ያሰበው፡፡ አያቴ መቼም አያርፍምኮ! በራሱ ካመነበት
የሚያደርገው ነገር ብዙ ነው፤ የማንንም ፈቃድ አይጠይቅም፡፡ የጋሽ አየለ ልጅ
ትንሷ ‹አይናለም› መሆን አለባት መቼም፡፡ ያቺ ቆንጆ ልጅ፡፡ በውነት የገጠር
ልጅ ከመሆኗ ውጪ (በአለባበሷና በአነጋገሯ ከከተሜዎቹ ስለምትለይ!)
የአዲስ አበባ ልጆች ከእርሷ ጋር አይወዳደሩም! ታስከነዳቸዋለች፡፡ ደግሞ
ቀላል ቆንጆ ናት! ግን መቼም እኔ አልጠየኩ፡፡ ላግባ አላልኩ፡፡ ዳሩኝ አላልኩ፡፡
በዚያ ላይ አያቴ መክሊትን (እጮኛዬን) ታውቃታለች፡፡ እንደምትወዳትም
አውቃለሁ፡፡ አባባ ግን ከወራት በፊት ‹ለምንድነው እንዲህ ሳታገባ ብቻህን
የምታባትተው!› ብሎ እንደጠየቀኝ አስታወስኩ፡፡
እመይ … ቀስ ብላ ወደ ቤት ተመለሰችና ከሰሉ ላይ ጭሳ ጭሷን ጣል አድርጋ
ስራዋን ቀጠለች፡፡ የእድሜ ጣመን ያዛለው ሰውነቷ ለስንፍና ፊት አይሰጥም
እንጂ ደካክማለች፡፡ አሁንም ልክ እንደ ድሮው በለሊት ተነስታ ስራዋን እስከ
ውድቅት ትቀጥላለች፡፡ የመድሃኒያለም ያለህ! ምን ያለው ብርታት ነው ግን!
ጥቅልል ካልኩበት መደቤ ላይ የጧት እንቅልፍ እያንጎላጀኝ ቢሆንም፣ ፊቴ
ፈገግታ እንደሞላው የተጠቀለልኩበትን ብልኮ በቀስታ ገልጬ ብርሃን
በሚፈሩ አይኖች አስተውላለሁ፡፡ አባበይ ከቤተ ክርስቲያን መመለሻ ሰዓታቸው
ስለደረሰ (እንዲያውም ረፍዷል!) ቁርሱ ሁሉ ተዘገጃጅቷል፡፡ አሻግሬ በበሩ
ወደ ውጪ በትንሽ በትንሹ ብን ብን የሚለውን ዝናብ እከታተላለሁ፤ ቀስ ብዬ
ጋቢዬን በላዬ ላይ ጠቀለልኩና ተነስቼ እየተጎተትኩ ወጣሁ፡፡ ማለዳው እጅግ
ያምራል፣ ካፊያ ነገር ያለ ቢመስልም ቀኑ ግን ብሩህ ነበር፡፡
የአጥሩን በር ከፍቼ ወደ ሜዳው ወጣሁ፡፡ ማዶ ላይ ከፊት ለፊታችን
የተገተረው ተራራ በማለዳው በእሳት የተያያዘ ይመስል በእንፋሎት ጭስ
ተሞልቷል። በተራራው መቀነት ላይ እንደ ባልቴት ንቅሳት የሚታየው የእግረኛ
መንገድ ላይ ነጭ የለበሱና ከቤተ ክርስቲያን የሚመለሱ የሰፈራችን
አባወራዎችና እማወራዎች ይታዩበታል፣ አልፎ አልፎ በማለዳ የሚጓዙ
እግረኞች ይዞሩታል፣ እንስሳት የሚነዱ የሰፈሩ ሰራተኞችና እረኞች
በየማለዳው ይንከላወሱበታል። ደግሞ (አሁንም በዚህ ዘመን፣ አለም
ሰልጥኖ ስንት በሚራቀቅበት ወቅት!) እንስራ ያዘሉ ባልቴቶችና ልጃገረዶች
ሸክሙን በወገባቸውና በዳሌያቸው ላይ እያጫወቱ በየዕለቱ፣ ማልደውና
አረፋፍደው ሳይመላለሱበት አይውሉም፡፡
ተራራው ላይ ከተጠቀጠቀው ጢሻ ውስጥ የሚሰማኝ የእንስሳት ጩኸት፣
የከተማ ግርግር ሲሰለቸኝ በልቡናዬ የማስበው ውብ ዜማዬ ነው፡፡ ባሻገር
የሚያስካካውን የቆቆች ድምፅ መቼም ልረሳው የምችለው አይደለም፡፡
(ሳንባዬን በንጹህ አየር ሞልቼ አይኔን እንደጨፈንኩ ቆምኩ!) …. አውቃለሁ
ደግሞ ከዚያ … ከማዶ ከተራራው መሃል ቀበሮዎች አሉ፣ ከዚያ ከጠፍጣፎቹ
አለቶች አናት ዝንጀሮዎች፣ ደግሞ ከስር ከበሃ ድንጋዮቹ ውስጥ ጅቦች፣ በዚያ
ባሻገር በርቀት ላይ ጃርቶችና ቤተሰቦቻቸው የሚኖሩበት፣ በስሩ ካለው ጫካ
ውስጥ ሰስና አጋዘኖች፣ ደግሞ ከምንጩ አካባቢ … (በድጋሚ ሳንባዬን
በአየር ሞላሁና በረጅሙ ተነፈስኩ …. ይህ የማወራው ገጠር ላልኖረ ሰው
እንዴት ሊገባው ይችላል!) … ደግሞ ከትዝታዎቼ አንዷን ሳብ አድርጌ አያለሁ!
… አቤት! ... አያቴኮ በራሱ ሀሳብ ብቻ ነው የሚመራው! አንድ ጊዜ እንዲህ
አደረገኝ ፡፡
*

አንድ ጊዜ ገና በአስራዎቹ ዕድሜ እያለሁ … አያቴ ወደ ገበያ ይዞኝ ሄደ፡፡
በዚያን ወቅት እኩያዎቼ በራሳቸው ገበያ ደርሰው የሚመጡ ቢሆንም እኔ
መሄድ አይፈቀድልኝም ነበር፡፡ የ11 ክፍል ተማሪ እያለሁ አስተማሪዬ ከሴቶች
ጋር እያወራሁ እንደዳስቸገርኩት ነገረውና አባበይ ተናደደብኝ፡፡ ምዬ ተገዝቼ
ብናገርም አልሰማኝም፤ ከዚያም … ‹‹ለዚህ ለዚህማ ከመንደር አትውልም
ወይ!…›› … ብሎ ድብን አድርጎ ገረፈኝ፡፡ እየማልኩ ባስረዳውም አላመነኝም፡፡
ስለዚህ በሚቀጥለው የገበያ ቀን ለመጀመሪያ ግዜ አብሬው ገበያ ወሰደኝ፡፡
የሚገርም
አጋጣሚ ነበር … ሰውንም፣ እንሰሳውንም፣ አቧራውንም፣
ዝንቡንም፣ ትንኙንም … እንደ አዲስ በመገረም ሳስተውል ዋልኩ (ሁሉም
ቀድሞ የማውቃቸው ነገሮች አልመሰሉኝም ነበር!)… ስራችንን ጨርሰን
አመሻሽ ላይ ወደ ቤታችን መመለስ ስንጀምር ከከተማው አንድ ስርቻ ይዞኝ
ሄደ። ከዚያም ጭፈራና ሁካታ ወደ ሞላበት ቤት ገባን። ሰው ቤቱን ሞልቶ
ይጯጯሃል … (…እኔ በቀያችን ከገበያና ከንግስ በዓል ውጪ እንዲህ ሰው
የበዛበት ቦታ አይቼ አላውቅም ነበር፡፡) …. በቤቱ ውስጥ ጠርሙስና
ብርጭቆዎች ይዘው ወዲያ ወዲህ እያሉ ስራውን ከሚያቀላጥፉት ውጪ
ዝም ብለው የቆሙ ኮበሌዎች በጣም ብዙ ናቸው፡፡ ሙዚቃው ከቤቱ
የሚወጣ አይመስልም፣ እዚህም እዚያም የሰከሩ ሰዎች፣ ደግሞ ሴቶችን
የሚጎተትቱና ወደ ጓሮ የሚሰወሩ፣ ደግሞ የሚሰዳደቡና ለጠብ የሚጋበዙ፣
ደግሞ ከቴፑ በላይ ድምፃችን ይሰማ እያሉ የሚጮኹ፣ ደግሞ … ምን ዓይነት
አገር ነው! (ምን ዓይነት ነገርስ ነው!) … ፔፕሲዬን እያጣጣምኩ
ተቁለጨለጭኩ፡፡ (በወቅቱ ጥቁር ለስላሳ ነበር የምለው!)
አያቴ አንዷን ልጅ መሳይ ጠራትና አነጋገራት (…በኋላ ስሰማ የቀያችን ልጅ ናት
ሲሉ ሰማሁ፣ ወጣቱ ሁሉ ከገበያ መልስ መጀመሪያ እርሷ ዘንድ ይሄዳል
ይላሉ!) … በመቀጠል አየት አደረገኝና ወደ ጆሮዬ ጎንበስ ብሎ ‹‹አብረሃት
ሂድ!›› አለኝ፡፡ እየተጠራጠርኩ ተከተልኳት፤ በተደቋቆሱት ቤቶች ስር ወደ
ውስጥ ከአንዷ ጎጆ ዘልቅንና በሩን ከኋላዬ ዘጋች። ትንሽ
ከተቁለጨለጭችብኝ በኋላ በትዕዛዝ መልክ … ‹‹ልብስህን አውልቀዋ! … ››
አለችኝ (ግራ ገባኝ!)
‹‹…አባትህ አለማምጂው ብለውኝ ነውኮ! … ወይኔ! እኔ እንዲያው ስንቱን
ገበሬ ሳለማምድና ሳሰለጥን ልኑር! … በተለይ ከዚያ አገር የምትመጡ
ቆምጨዎች! …›› ከላይ የለበሰቻትን ሹራብ ጎትታ አወጣችና ስትጥላት
እንኮይ የመሰሉ ጡቶች ከፊቴ ተንጠለጠሉ፡፡ ደነገጥኩ … አይቼ አላውቅም
ነበር፡፡
‹‹…ደግሞ ከሴት ጋር መተኛት ምን ልምድ ያስፈልገዋል፤ እያንዳንዱ ያገርህ
ገበሬ በጨለማ እየዳበሰ አይደል እንዴ የሚያገኘው፡፡ ልክ ፍትፍት እንደ
መጉረስ ማለት ነውኮ፡፡ መብራት ቢጠፋም እጅህ አፍህን አያጣውም…››
ረጅም ሳቅ … ‹‹..በልቶሎ አውልቀዋ፤ ደግሞ አንተ ትንሽ የምትሻል
ትመስላለህ፤ ልብስህም ንፁህ ነው!፤ እንዲያው በሞቴ የከንፈር ወዳጅ
የለህምና ነው!…›› … ለደቂቃዎች ደነዘዝኩ፡፡ ለመጀመሪያ ግዜ ባየሁት ነገር
የደነገጥኩና የደም ስሮቼ ሁሉ የተገታተሩ ቢሆንም በመቀጠል ያደረግሁት
አስደንጋጭ ነገር ነበር፡፡ ገፍትሬ ከእንጨት አልጋው ላይ ፈነቸርኳትና በሩን
ታግዬ ከፍቼ ወጣሁ፣ ከዚያም … በሩጫ ድቁስቁሱን ሰፈር አቋርጩ የአገሬን
መንገድ እስካገኝ ሮጥኩ፡፡ ከገበያተኞች ጋር አብሬ ወደ ቤቴ ገሰገስኩ፤ አያቴ
የሰራኝ ስራ ግን … (ተቀየምኩት!)
ማታ ሲመጣ እየሳቀ ነበር … እኔ በጣም ተቀይሜዋለሁ፤ እየሳቀ እንዲህ አለኝ
… ‹‹….ጌታ! … አስተማሪህ ሴት ለምዷል ብሎ ሲከስህ ተጠራጥሬህ ነበር፡፡
በርግጥ ልጄን እኔ አውቅሃለሁ፡፡ ግና መቼስ አስተማሪ አስተማሪ ነው፡፡ እና
ከዚያ ቤት ያስገባሁህ ልፈትንህ ነበር፡፡ በሃሰት ስለከሰስኩህ ይቅርታ
አድርግልኝ…›› (… ድንቄም ፈተና፣ ለንቦጬን ጣልኩ… ደግሞ በኋላ ሲነግረኝ
… ከልጅቱ ጋር ተመካክረው ኖሯል! በጉርምስና ድፍረት አንቄ ብይዛት ኖሮ
ግን…!)
አንገቴን ቀልሼ ዝም አልኩት፡፡ እናም ለቀናት አኮረፍኩት፡፡ በርግጥ ፈተናውን
አለፍኩ ማለት ነዋ! ብወድቅስ! ምን ሊፈጠር ነበር …. አያቴን ከዚያ ወዲህ
አላምነውም፡፡
*
እናም በመጨረሻ አበቡ የዕድሞውን በር ከፍታ ብቅ አለችና እንዲህ አለች፤
‹‹…አንተ ጌታ! … በብርድ ምን ይገትርሃል፡፡ በል ቶሎ ግባ አባበይ ደርሰዋል፡፡
ደግሞ ሳይመጡ ወተትህን ጠጣ … አንዴ ክርህን በጥሰህ ጥለህ … ሆሆይ
መቅበጥ!…››
‹‹…አቤ እንዲያውም አንቺ ከምትቀየሚ ወተቱን ትቼዋለሁ አልጠጣም!…››
አልኩ ጋቢዬን እየሰበሰብኩ።
‹‹…ኸረግኝ…አላማረብህም ላንተ አደል በጧት የተለፋው!…በል ቶሎ ና ግባና
ጠጣ፡፡ አንድ ጊዜ ጀምረሃል ጨርስና ትጠመቃለህ!››
ልብሴን እያስተካከልኩና እየሳቅኩ ተጠጋኋት፤ ወዲያው ደግሞ ወደ አዲስ
አበባ መመለሻ ቀኔ መድረሱን አስብና ልቤን ስልብ የሚያደርግ ስስት
ይሰማኛል፤ አዝናለሁ፡፡ ነጠቅ ነጠቅ በሚያደርግ እርምጃ ከአጠገቧ ደረስኩና
በስራ እንደ ሞረድ የሻከሩ አሳዳጊ መዳፎቿን አንስቼ ሳምኳቸው፡፡
‹‹አይይይ …. እንደው ይህንን ልጅ ምናባቴ ላድርገው!›› እያለች መዳፏን
ነጠቀችኝና እንባዋን ከአይኖቿ መጠራረግ ስትጀምር፣ እድሞውን ዘልቄ
በፍጥነት ወደ ቤት ገባሁ፡፡ እውን አሁን ደግሞ አባባ ልዳርህ እያሉ
ሊያጨናንቁኝ ባልሆነ እያልኩ በልቤ እያሰላሰልኩ፣ በኩባያ ላይ የተቀዳውን
ትኩስ የታለበ ወተት ማጣጣም ጀመርኩ፡፡
*

ወርቃማው ህግ 2 - የምትረዳውን ለይ! (የምታደርገው … ሊደረግልህ
የምትፈልገውን ብቻ ነው!)
ኪባ የምትባል ሌላ ዝንጀሮም ነበረች፡፡ እንዲሁ ከሌላኛው ዛፍ ነበረች፡፡ እናም
የሌላውን አሳ እሪታ ስትሰማ አሰላሰለች፡፡ ‹‹ይህንን አሳ ከውሃው በማውጣት
ማዳን ይኖርብኛልን! እኔስ በአሳው ቦታ ብሆን ኖሮ፣ ከውሃው እንዲያወጡኝ
እፈልግ ነበርን!›› ስትል ጠየቀች፡፡
እናም ‹‹አይደረግም! ከውሃው እንዲያወጡኝ አልፈልግም!›› ስትል ወሰነች፡፡
እናም አሳው በውሃው ውስጥ ቁልቁል ሲምዘገዘግ ከዛፉ አናት ቁጭ ብላ
አየችው፡፡ ጭካኔ አይደለም፡፡ አሁን ለጥቂት ጊዜ ቢሰቃይም በህይወት
የመኖር ዕድሉ ግን ሰፊ ነው ስትል ወሰነች፡፡ ይህ የብልህ ውሳኔ ነው ስትልም
አሰበች፡፡

ምንጭ:- አዲስ አድማስ ጋዜጣ

ድምቅምቅ ያለች ቀን ትሁንልን!!💚💛❤️

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
እርስዎ እንዲሳተፉበት የቀረበ የዘመኑ አስደናቂ መጽሐፍ ፡ በፈለጉት ቋንቋ ፣ በፈለጉት ዓይነት የአፃፃፍ ዘዴ ፡ ስለ ኢትዮጵያ እና ስለ ኢትዮጵያዊነት እንዲጽፉ የመጽሐፉ አንድ ባዶ ገፅ በነፃ ተሰጥቶታል ።
በዚህ አድራሻ ብቻ ይላኩ [email protected]

@thebookofethiopia
ለጥበብ አፍቃርያን
--------------------------
ተናፋቂው የፋና ብዕር የጥበብ ምሽት በገና ዋዜማ ቅዳሜ27/2011 አ.ም ምሽት12:00ሰአት በዝዋይ ቱሪስት ሆቴል አዳራሽ
*ስነ-ግጥም
*መነባነብ
*ወግ
*ተውኔት እና ሌሎችም
ዳግም ልደት ለኢትዮጵያዊነት!
የመግቢያ ዋጋ 15 ብር ብቻ
አዘጋጅ ፋና ብዕር
@Tebeb_mereja
@tebeb_mereja
2024/09/28 23:22:05
Back to Top
HTML Embed Code: