Telegram Web Link
ሎጎ ቴራፒ- ከትርጉም የለሽ እና
ከተስፋ መቁረጥ ኑሮ የሚያላቅቅ
የስነ-ልቦና ጥበብ (ክፍል አንድ)


Logo therapy – Part one
” When I was in the concentration camp, I was confronted with
Two people who attempted to commit suicide and i asked them
why they want to take their lives, I asked both of them
independently. Both of them told me “see doctor I don’t have
anything to expect from my life anymore” you know why I asked
them? “listen, isn’t it considerably possible that instead life
expects something from you?”


ፕሮፌሰር ቪክተር ፍራንኪል የኦውስትሪያ ኑሮሎጂስት እና የስነልቦና አማካሪ
ነበሩ። በ1940ዎቹ የናዚ ጦርነት ወቅት በናዚ ቁጥጥር ስር ውለው በአስፈሪዎቹ
የናዚ ኮንሰንትሬሽን ካምፖች ውስጥ ለሶስት አመታት የግፍ ጊዜያቶችን
አሳልፈዋል። የሚወዷትን ሚስታቸው፤ እናት እና አባታቸውን ያጡት በነዚህ እስር
ቤቶች ውስጥ ነበር። በነዚህ የሰቀቀን ጊዜያቶች፤ ረሃብን፤ በሽታን፤ ስቃይና ግፍን
ከበቂ በላይ ተመልክተዋል። እንደሳቸው የናዚ እጣፋንታ ከደረሰባቸው ሚሊየን
እስረኞች በተለየ መልኩ ግን ቪክተር ዛሬም ድረስ ስማቸው ይነሳል። በነዛ የስቃይ
ጊዜያቶች ውስጥ ሆኖ የመኖርን ትርጉም ለመመርመር የጣሩ፤ የጣሩ ብቻም
ሳይሆን የስነ-ልቦና ጥበብ ላይ ተጽዕኖ ማድረግ የቻሉ ሰው ነበሩ።
ቪክተር ከ 1945 እ.ኤ.አ በኋላ ማለትም ከእስር ነጻ ሲወጡ፤ ወደ ኦስትሪያ
በመመለስ በእስር ጊዜያቶች ያዩትን እና ያስተዋሉትን ከስነ ልቦና ምርምር ጋር
በማዋሃድ አዲስ ምዕራፍ ለመፍጠር ችለዋል፤ ቪክተር ምርምር ካደረጉባቸውና
ለአለም ካበረከቷቸው ስራዎች ዋነኛው Logo therapy ይባላል። በዚህ በክፍል
አንድ ጽሁፍ ውስጥ በጥቂቱ ይህንን የስነልቦና ዘርፍ እንዳስሳለን


ሎጎቴራፒ ምንድን ነው???

ከቪክተር ፍራንክሊን ተቋም (Victor Frankl Institute of logo therapy)
ያገኘሁት ጽሁፍ እንዲህ ይላል
” Victor Frankl’s Logo therapy is based on the premise that the
human person is motivated by a “will to meaning” an inner pull
to find a meaning in life.”

የሎጎቴራፒ መሰረተ ሃሳብ የሰው ልጅ ለህይወቱ የሚሰጠው ትርጉም ካለው
ለኑሮው መነቃቃትን ይፈጥርለታል የሚል ነው፤ ይህ ማለት የምንኖርለት ነገር
ሲኖረን የሚገጥሙንን ከባድ ፈተናዎች እንኳን መጋፈጥ የሚያስችል ጉልበት
ይኖረናል። ፕ/ር ቪክተር በእስር በቆዩባቸው ጊዜያቶች እንዳስተዋሉትና በኋላ
ከእስር ወጥተው እንዳስረዱት ከሆነ፤ በእስር ቤት ውስጥ ካሉት እስረኞች
ውስጥ፤ በህይወታቸው የሚኖሩለት ነገር ያላቸው ወይንም ከእስር ሲወጡ
የሚያድረጉትን ነገር የሚያውቁ (ለማድረግ የሚጓጉ) እስረኞች የመትረፍ
እድላቸው ሰፊ ነበር ብለዋል። በምሳሌም ሲያስረዱ፤ ከእሳቸው ጋር ከታሰሩት
ሰዎች መካከል አንደኛው ሲበዛ የመጻፍ ፍቅር ነበረው፤ በዛ በመከራ ጊዜ ውስጥ
ሆኖ እንኳን የሚያስበው ከእስር ሲወጣ ስለሚያሳትመው መጽሃፍ ነበር። ሌላኛው
እስረኛ በበኩሉ ለልጁ የነበረው ፍቅር ካለበት የመከራ ጊዜ አሻግሮ እንዲመለከት
አድርጎት ነበር። ፕ/ሩ የራሳቸውንም ታሪክ እንደምሳሌ ሲወስዱ፤ በወቅቱ
ለነበረችው እና በናዚ ግፍ ህይወቷን ላጣችው ሚስታቸው የነበራቸው ፍቅር
ከዛም በላይ ለመኖር የሚያበቃ ምክንያት ስለነበራቸው፤ ያንን መከራ በጽናፍ
ለማለፍ የሚያስችል ጉልበትን አግኝተው ነበር።
ምንም እንኳን ፕ/ር ቪክተር የሎጎቴራፒን ሃሳብ ያመነጩት ወደ እስር ቤት
ከመግባታቸው አስቀድመው ቢሆንም በእስር ቤት በቆዩባቸው ጊዜያቶች ግን
ጽንሰ ሃሳቡን አጠንክረውታል። የፕ/ር ቪክተር ተቋም የሎጎቴራፒን ምንነት እና
ትርጉም በሚከተሉት ሶስት ነጥቦች ያብራራል
The following list of tenets represents basic principles
of Logo therapy
1- Life has meaning under all circumstances, even the
most miserable ones.
2- our main motivation for living is our will to find
meaning in life
3- We have freedom to find meaning in what we do,
and what we experience, or at least in the stand we
take when faced with a situation of unchangeable
suffering.


ሶስቱን ነጥቦች እንዲህ እንመልከታቸው
1ኛ– ህይወት በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ብንሆንም ትርጉም አላት፤ ለጊዜው
ከባድ በሚመስሉን ጊዜያቶችም ጭምር- ፕ/ሩ በተለያዩ ጥናቶች እንዳስረዱት
ሰዎች ለመኖር ምክንያት ሲኖራቸው ህይወታቸው በማንኛውም ማዕበል ውስጥ
ቢሆን እንኳን ትርጉም ይኖረዋል። ከላይ እንደጠቀስኩት በናዚ የእስር ቤቶች
ውስጥ ሆነው እንኳን ስለነገ ተስፋ የሚያደርጉ ሰዎችን ስናይ ምን ያህል ለመኖር
ያላቸው ምክንያት ጽናት እንዳሰጣቸው ነው። ስለዚህ የሎጎ ቴራፒ ዋና መሰረት፤
ለህይወታችን ትርጉም በመስጠት እራሳችን ከተስፋ መቁረጥ አልያም ከትርጉም
የለሽ ኑሮ ማላቀቅ ነው። ለወደፊቱ የሚኖረንን ኑሮ በህሊናችን መሳል ስንችል እና
ሲያጓጓን አሁን ያለንበትን ፈተና ለማለፍ ጽናት ይኖረናል።
2ኛ– ዋና የህይወታችን መነቃቂያ ለህይወታችን ትርጉም መፈለግ ነው- ብዙ
ሰዎች ለጭንቀት ወይንም ለትርጉም አልባ ኑሮ የሚዳረጉት በህይወታቸው
የሚያነቃቃቸው ነገር ስለሌላቸው ነው። በየቀኑ የምናደርገው ነገር ለእኛ ትርጉም
ካልሰጠን ህይወት ድግግሞሽ ከመሆን የዘለለ ትርጉም አይኖራትም። ለዚህ ነው
ፕ/ር ቪክተር ሰዎች በሎጎ ቴራፒ ወይንም ለህይወታቸው ትርጉም በመፈለግ
ያንቀላፋውን ኑሮዋቸውን ማንቃት እንደሚችሉ የሚያስረዱት። ከላይ በምሳሌ
የጠቀሷቸው ሰዎች እራሳቸውን ጨምሮ እንዲሚያመላክቱት፤ ለሆነ ነገር ፍቅር
ሲኖረን ትልቅ መነቃቃት በህይወታችን ይፈጠራል። “ፍቅር” ከፍተኛ መነቃቃትን
እንድሚያመጣም ፕ/ሩ በመጽሃፋቸው አስረድተዋል። ለምሳሌ አንዱ እስረኛ
ለልጁ የነበረው ፍቅር፤ ሌላው እስረኛ ለመጽሐፍ የነበረው ፍቅር፤ ፕ/ሩ እራሳቸው
ለሚስታቸው የነበራቸው ፍቅር፤ ያፈቀሩት ነገር ይለያይ እንጂ፤ ለሶስቱም
በአስቸጋሪው የሰቆቃ ጊዜ እንኳን የመኖርን ጉልበት ሰጥቷቸዋል። ሰዎች
ለሚወዱት ነገር መስዋት ለመክፈል ፈቃደኛ የሚሆኑትም በዚሁ ምክንያት ነው።
3ኛ– የመጨረሻው ነጥብ ሰዎች በህይወታቸው በሚያደርጉት ነገር፤ ወይም
በሚኖራቸው ልምድ ለህይወታቸው ትርጉም የሚሰጣቸውን ነገር የመፈለግ ነጻነት
አላቸው። ይሄ እንኳን ባይቻል ችግር እና መከራ ሲገጥማቸው ሁኔታው የማይቀየር
ከሆነ ለችግሩ የሚኖራቸውን አመለካከት የመወሰን ነጻነት አላቸው የሚል ነው።
ፕ/ር ቪክተር ይህንን ነጥብ በምሳሌ ሲያስረዱ
“እርግጥ ነው ሰዎች በሁሉም ነገሮች ላይ ነጻነት ሊኖራቸው አይችልም፤ ከእኛ
ቁጥጥር ውጪ የሆኑ ነገሮች መፈጠራቸው ስለማይቀር ። ነገር ግን ለነገሮች
የሚኖረን አመለካካት ለህይወታችን የሚኖረንን ትርጉም ይወስነዋል። ለምሳሌ
አንድ የ17 አመት ልጅ የጻፈልኝ ደብዳቤ ይህንን በደንብ ያስረዳል፤ ይህ ልጅ
የደረሰበት የመኪና አደጋ ከአንገቱ በታች
መንቀሳቀስ እንዳይችል አደርጎታል፤
በደብዳቤው ግን እንዲህ ነበር ያለው “ምንም እንኳን አደጋው አንገቴን
ቢሰብረውም፤ “እኔነቴን” ግን አልሰባበረውም” ሲል የደረሰበትን ክፉ እጣ በራሱ
አመለካከት እንዴት እንደቀየረው ተናግሯል ።” እንግዲህ ሁኔታዎችን የምናይበት
መንገድ ለህይወት የሚኖረንን ትርጉም ምን ያህል እንደሚቀርጸው ያስረዳል።
ልንለውጣቸው የማንችላቸውን ነገሮችን የምናቀላቸው አመለካከታችንን
በመቀየር ብቻ ነው እንደማለት ነው።



(በክፍል ሁለት በዚሁ የስነ-ልቦና ጥበብ እራሳችንን እንዴት ማከም
እንደምንችልና እንዴት ትርጉም ያለው ኑሮን መምራት እንደምንችል
እንመለከታለን)

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ሎጎ ቴራፒ- ከትርጉም የለሽ እና
ከተስፋ መቁረጥ ኑሮ የሚያላቅቅ
የስነ-ልቦና ጥበብ (ክፍል ሁለት)
...
በመጀምሪያው ክፍል (ሎጎቴራፒ ክፍል አንድ ) ስለ ሎጎ ቴራፒ በጥቂቱ
ተረድተናል። ለማስታወስ ያህል ሎጎ ቴራፒ ሰዎችን ከጭንቀት ወይም ከተስፋ
መቁረጥ ስሜት ለማላቀቅ ከሚረዱ የስነልቦና መንገዶች አንደኛው ነው። ሰዎች
ተስፋ የሚቆርጡት አልያም ትርጉም የለሽ ኑሮ እንደሞኖሩ የሚሰማቸው
የሚኖሩለት ነገር ስለሌላቸውና ለህይወታቸው ትርጉም የሚሰጥ ነገር
ባለማግኘታቸው ነው በሚል መሰረተ ሃሳብ ላይ የተንተራሰ የስነልቦና ጥናት ነው።
በሎጎ ቴራፒ አማካኘነት ሰዎች በህይወታችን ትርጉም የሚሰጣቸው ነገር
ሲያገኙ፤ ወይም የሚኖሩለት ነገር ሲኖራቸው ትልቅ መነቃቃትን በህይወታቸው
ይፈጥርላቸዋል።

እንደ ፕ/ር ፍራንክል ጥናት በህይወታችን ትርጉም ልናገኝ የምንችልባቸው ሶስት
መንገዶች አሉ። እነዚህ ሶስት መንገዶች የሚከተሉት ናቸው

According to Frankl “we can discover this meaning in life in
three different ways
1- By creating a work or doing a deed
2-By experiencing something or encountering someone
3-By the attitude we take toward unavoidable suffering

ነጣጥለን እንያቸው ካልን

1ኛ– ሰው በሚሰራው ስራ ለህይወቱ ትርጉም ሊሰጥ ይችላል- እዚህ ላይ ብዙ
ሰዎችን በምሳሌ መውሰድ እንችላለን፤ የፈጠራ ስራ የሚሰሩ ሰዎች፤ በበጎ ስራ
ላይ የተሰማሩ ሰዎች፤ በጥበብ ውስጥ ያሉ ሰዎች፤ ከብዙሃኑ ተነጥለው
የልባቸው ጥሪ በማድመጥ የሚኖሩ ናቸው። የሚሰሩት የሚወዱትንና ትርጉም
የሚሰጣቸውን ነገር ነው። እዚህ ላይ የሁላችንም ዝንባሌ እና ፍላጎት ይለያያል።
ለእኛ ትርጉም የሚሰጠንና ልባችንን የሚያስደስተው ነገር ለሌላው ሰው ምንም
ትርጉም ላይሰጠው ይችላል። የሚወዱትን የሚሰሩ ሰዎች ግን የሌላው ሰው
ማረጋገጫ ሳያስጨንቃቸው ለሚኖሩለት ነገር ጊዜያቸውን፤ ገንዘባቸውንና
መንፈሳቸውን አሳልፈው ይሰጣሉ። ስለዚህም እያንዳንዷ ቀን ለነሱ ትርጉም አላት፤
የጥቅም የለሽነት እና ትርጉም ማጣት አይሰማቸውም።

2ኛ– ሁለተኛው የህይወት አጋጣሚዎች ወይንም በህይወታችን የምናገኛቸው
ሰዎች ለህይወት ያለንን አመለካከት ይቀይሩታል- ለምሳሌ ልጅ እና ሌሎች
አብዝተን የምንወዳቸው ሰዎች የምንኖርለት ነገር እንዳለን ያሳስቡናል። ፕ/ሩ
በዚህ ነጥብ ላይ እንደ ምሳሌ የሚጠቅሱት፤ በነዛ አስፈሪ የናዚ ኮንሰንትሬሽን
ካምፖች ውስጥ ሆነው እንኳን አንዳንድ እስረኞች ልጆቻቸውን፤ ባሎቻቸውን፤
እናትና አባቶቻቸውን እያሰቡ ያንን የመከራ ህይወት በጽናት ያሳልፉት ነበር።
መከራው ሲያበቃ ለመገናኘት የሚፈልጓቸው ሰዎች እንዳሉ ስለሚያስቡ ሞትን
ይሸሹ ነበር። ለእነሱ ህይወት ትርጉም አላትና። ሌላው ደግሞ አንዳንድ የህይወት
አጋጣሚዎች እንደ ዘበት የምንኖረውን ኑሮ እንድንቃኝና እንድንነቃ ያደርጉናል።

3ኛ-ከእኛ ቁጥጥር ውጪ በሆኑ ነገሮች ላይ ያለንን እይታ ማስተካከል-ይህ
የመጨረሻው ነጥብ በህይወታችን መመሪያ ልናደርገው የሚገባን ትልቅ ነጥብ
ነው። ልናስወግዳቸው የማንቻልቸውን ነገሮች እንዴት ነው መጋፈጥ የምንችለው?
ከእኛ ቁጥጥር ውጪ የሆኑ አጋጣሚዎች የሚያሸክሙንን መከራ እንዴት ማቅለል
እንችላለን? መልሱ አመለካከታችንን መቀየር የሚል ነው። ዶ/ር ኖርማን ቪንሰንት
እንዲህ ሲል ተናግሯል “የሚያሳስበን ችግሩ ሳይሆን ችግሩን የምናይበት መንገድ
ነው”። ብዙዎቻችን ችግሩን እንጂ ችግሩን እንዴት እያየነው እንደሆነ ልብ
አንልም። የሚያሳስበን የደረሰብን አጋጣሚ ብቻ ሳይሆን አይምሮዋችን
በምናልባት እየፈጠረ የሚስልልን መላምቶች ናቸው።

“A major cause of depression is self-absorption. By drawing on a
person’s strengths, the tools and techniques of logotherapy help
bring about a profound shift in awareness, from a ‘victim’
mentality to an optimistic attitude. Clients and students of
logotherapy are in the habit of questioning themselves about
what they really want and which kinds of choices will be most
conducive to growth”

ለጭንቀት የሚዳርጉ ብዙ ምክንያቶች አሉ፤ ዋናው ምክንያት ግን በነገሮች ተስፋ
መቁረጥ እና ነገን አለመናፈቅ ነው። ነገን የማንናፍቀው ደግሞ የምንኖርለት ነገር
ስለሌለን፤ ለህይወታችንም ትርጉም የሚሰጥ ነገር ስናጣ ነው። ከእንደዚህ አይነት
ጭንቀት ለመወጣት ሎጎቴራፒ በጣም ትልቅ እገዛ ያደርግልናል። ይህንን ጥበብ
በስራ ላይ ለማዋል እራሳችንን ልንጠይቀው የሚገቡን ጥያቄዎች አሉ ለምሳሌ፦
ብንሰራቸው የሚያስደስቱን ነገሮች ምንድን ናቸው? ለፍላጎታችን ቅድሚያ
መስጠት ብንችል ምን ይሆናል ቅድሚያ የምንሰጠው? ህይወታችን አጭር
መሆኗን ስናስብ ሳንፈጽመው ብንሞት የሚቆጨን ምንድን ነው? ለመኖር
ምክንያት ይሆነናል የምንለውስ ነገር አለን? ለነዚህ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት
ከቻልን ህይወታችን ተመልሶ አሰልቺና ድግግሞሽ አይሆንብንም። ይህ
የሎጎቴራፒ ሃሳብ ሁላችንንም በተለያየ መጠን የሚረዳን ይመስለኛል፤ ከዚህ
በተጨማሪ የራሳችን ምርምር በማድረግ ይህንን ጽንሰ ሃሳብ መሰረት በማድረግ
ህይወታችንን መለወጥ እንችላለን።

💚💛❤️

@wegoch
@wegoch
@wegoch
አዲስ አበባ የማናት??? የወሎየዎች ናት!!!!!!!
እኛ ወሎየዎች ተገፍተን ተገፍተን የዛሬውን ወሎ ሰፈር ብቻ ይዘን እንድንቀር ተደርገን ነው
እንጅ አዲስ አበባ የወሎየዎች ናት!!! የጥንት ስሟ "ሸጋ" ነበር የሚባለው ። የአዲስ አበባ
ልጆች ናቸው እኛ ወሎየዎችን እርርር ይበሉ ብለው "ሸጋ" ከሚለው ስያሜ ላይ "ር" ፊደልን
ጨምረው"" ሸገር "" ብለው በጉልበት የቀየሩብን ። እንዲያውም
ከደሴ ወለጋ ስትመላለሽ ፤
ሸጋ ላይ ጠብቂኝ እንዳጫውትሽ።
የሁላችን ወንድም ፤ያ አብዲሳ አጋ ፤
ንገሩት በአውቶብስ ፤ እንዲመጣ ሸጋ ።
ወሎየ ዘንድሮ ፤ አየሁት ተከፍቶ ፤
አያሳዝንም ወይ ፤ ሸጋን ተቀምቶ ።
የሚሉ ስነ ቃሎች ለረጅም ሺህ አመተ አመታት በምስራቅ አፍሪካ ሲነገሩ መኖራቸው
የሚያመለክተው አዲስ አበባ የድሮ ስሟ ሸጋ እንደሚባልና ወሎየዎች ያላግባብ የተነጠቁ
መሆናቸውን ነው ።
በቅርቡ "ሸጋ" ከተማችንን እናስመልሳለን ።
((አዲስ አበባን ለወሎየዎች አስመላሽ ኮሚቴ= አለወአኮ))

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ሦዕል ለማሳል
በ +251984740577
ወይም @gebriel_19 order ማድረግ ይቻላል።

ሦዕል ለ ስጦታ ጥሩ አማራጭ!
@seiloch
@seiloch
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ አንድ ሰው በቀን ውስጥ እስከ 60 ሲህ ሐሳቦችን ያስባል።ከዛ ውስጥ 95%
የሚሆነው ተደጋጋሚ ሲሆን 85% የሚሆነው ደግሞ አሉታዊ ነው።ያለን ስሜት /mood/በምናስበው ሐሳብ
ይወሰናል።ስለ ራሳችሁ መጥፎ ነገር አትናገሩ።ይልቁኑ ለትልቀሸ አላማ እንደተፈጠራቹ ከፊታችሁ እጅግ በጣም ብዙ መልካም ነገር እንደሚጠብቃቹ፣ራስችሁን አስታውሱት።

ንዴት ከአቅማቹ በላይ የሆነን ነገር ለመቆጣጠር ከመፈለግ የሚመነጭ ነው።መተው ያለባችሁን ለመተው
ሞክሩ።በትላንትና ላይ ትኩረት እያደረጋችሁ የዛሬን ደስታ አትጡ።ዛሬ አዲስ ቀን ነውና የቀኑን ባለቤት
እያመሰገናችሁ ለራሳችሁና ለሌሎች መልካም ነገር ለማድረግ ሞክሩ።

በሌላችሁ ነገር ላይ በማተኮር ራስችሁን አትጉዱ።ከፈጣሪ የተቀበላችሁትን በረከት እየቆጠራቹ በልባችሁ
የረዳችሁን ፈጣሪ አመስግኑ።
ደስ የሚል ቀን ይሁንላቹ።

/// ኤርሚያስ ኪሮስ///

@getem
@getem
@gebriel_19
‹‹በነጋታው››
የአጭር አጭር ልብወለድ
-------------------------------
ያልጠገበችውን እንቅልፍ በግድ አቋርጣ አልገለጥም ብለው ያስቸገሩ ትላልቅ አይኖቿን እንደምንም ከፈተቻቸው፡፡ከስካር እና ከሌሊቱ እንግልት ያላገገመው ገላዋ አንዳችም ልብስ አልለበሰም፡፡ ለሰከንዶች ቤቷ እና አልጋዋ ውስጥ ብቻዋን ያለች መስሏት ፈገግ ብላ፣ ጭንቅላቷን ከሚመቸው ትራሷ ሳታነሳ፣ ወደ ተቃራኒው አቅጣጫ ተገለበጠች፡፡ አጠገቧ፣ አልጋዋ ውስጥ የተኛ ሰው አለ፡፡ በአንሶላ ከተሸፈኑት እግሮቹ በቀር ሙሉ በሙሉ እርቃኑ የተጋለጠ ፣ ከጎኗ በጎኑ የተኛ ወንድ አለ፡፡ እንደ ጫካ አውሬ ያንኮራፋል፡፡ በብዙ መዶሻዎች እንደሚመታ ሁሉ ክፉኛ የሚያማትን ራሷን በቀኝ እጇ ደግፋ ፣ ቀ….ስ ብላ ከአልጋው ወጥታ ከመቆሟ፣ ራቁቱን የተኛው የጫካ አውሬ ማንኮራፋቱን አቆመ፡፡ ዞር ብላ አየችው፡፡ አቅጣጫ ቀይሮ፣ አንሶላውን ደረቱ ድረስ ለብሶ፣ በጀርባው ተኝቶ ያያታል፡፡ በደመነፍስ በቀኝ እጇ ሃፍረተ ስጋዋን፣ በግራ እጇ ደግሞ ቀኝ ጡቷን ሸፈነች፡፡ ሸፍና ሞታለች፡፡ ፊቱ ላይ ፈገግታ አየች፡፡ ከመቅፅበት ተመልሳ አልጋዋ ውስጥ ገባችና ብርድልብሱን እስከ አንገቷ ለብሳ በዝምታ፣ በጀርባዋ ተኛች፡፡ ብዙ ሳይቆይ፣ ሰውየው አንሶላውን እንደለበሰ በየቦታው ከወዳደቁት ልብሶችና ጫማዎች መሃከል የራሱን እየመረጠ ማድረግ ጀመረ፡፡ መጀመሪያ የውስጥ ሱሪውን፣ ከዚያ የተጨማደደ ሸሚዙን፣ ከዚያ ቀዳዳ የበዛበት ጅንስ ሱሪውን….በግማሽ አይኗ ታየዋለች፡፡ ለብሶ ሲጨርስ ያላወቀችውን ነገር ፍለጋ ትንሽ ቤቷን ያተራምስ ያዘ፡፡ የተኛበትን የአልጋውን ክፍል ይገላልጣል፡፡ ጡት መያዣ እና ፓንቷ ተወርውሮ ያረፈበትን ሶፋዋን ያመሳቅላል፡፡ አስር ጊዜ በቢራ ጠርሙሶች የተሞላውን ትንሽ ጠረጴዛ ያተራምሳል፡፡ደግሞ እንደገና ይሄንኑ ይደግማል፡፡ አሁንም ዝም ብላ በግማሽ አይኗ ታየዋለች፡፡ በመጨረሻ ተናገረ፡፡ ድምጹ ለጆሮ ይሰቀጥጣል፡፡ ቆርቆሮ ሲፋቅ የሚያወጣው ድምፅን ይመስላል፡፡
‹‹ታምቡሬን…እባክህ ታምቡሬን እንዳትፍቀው›› አለች በሆዷ፡፡ ‹‹ስልኬ ጠፍቶብኝ ነው….አይተሸዋል?››› ነው ያለው፡፡ ‹‹ አላየሁትም…ምናልባት መኪናህ ውስጥ ጥለኸው ይሆን?››ደግሞ እንዳይናገር እየተመኘች ቶሎ ብላ መለሰች፡፡ ‹‹ኖ…ትዝ አይለኛል እዚህ ነበር….የት ሄደ ይባላል አሁን…..?›› ተመልሶ ክፍሉን መቃኘት ጀመረ፡፡ ዝም አለችው፡፡ ‹‹እ….›› አለና በቁሙ አያት፡፡ ዝም ብላ አየችው፡፡ ‹‹ትደውይልኛለሽ? እዚህ ነው ሚሆነው…እስቲ ስልኬ ላይ ደውይልኝ? ›› አላት፡፡ ከዚህ ድምፅና የሚጎረብጥ ሁኔታ ለመገላገል ብድግ ብላ ስልኳን ከቦርሳዋ አምጥታ ልትደውልለት ብትመኝም እርቃኗን መሆኗ ትዝ አላትና፣ ወደ ሶፋው እያመለከተች፣ ደግሞ እያዛጋች ‹‹ኦኬ….ከዚያ ቦርሳ ውስጥ ስልኬን አቀብለኝ›› አለችው፡፡ አቀበላት፡፡ ስልኳን ከፈተችና ቀና ብላ አየችው፡፡ ዝም ብሎ ያያታል፡፡ ‹‹እ…ቁጥርህን ንገረኛ? ›› አለችው፡፡

By hiwot emishaw


@paappii
@wegoch
‹‹. . .‹ጅሐድ› የሚል ቃል ስንሰማ በአዕምሯችን ቀድሞ የሚመጣዉ ፤ በደም-የተነከረ
ሰይፍ-የጨበጠ ሙስሊም - ‹‹ትሰልማለህ›› ወይስ ‹‹አትሰልምም›› እያለ ሲያስገድድ ፤
እጅግ አስከፊ ምስል ያለዉ ጦረኛ-ዐረብ እና የመሳሰሉ አሉታዊ ገፅታን የሚያሳይ ነገር
አድርገን የምንወስድ ብዙዎቻችን ነን ፡፡ ግና ፤ ዑስታዝ ሐሰን ታጁ ‹‹ሰይፍን ፍለጋ››
በሚለዉ መጽሐፉ ስለ-ጅሐድ የሚያወራን ሌላ ገፅታ/ትርጉም ያለዉ ነዉ ፡፡ ዑስታዙ
በመጽሐፉ ዉስጥ ፤ መንፈሳዊ-ጅሐድ . . ፣ የሰበካ-ጅሐድ . . . ፣ ወታደራዊ-ጅሐድ . . . ፣
የሲቪል-ጅሐድ የሚል አራት አይነት የጅሐድ አይነቶችን ይገልፃል ፡፡ ከመረጃ ድርቀት
የተነሳ ስለነገሮች ያለን አመለካከት የተዛባ ሊሆን ግድ ብሏል ፡፡››
-
‹‹የኢህአዴግ ቁልቁለት(2007)›› ገፅ-168/169 ፤ ሙሉዓለም ገ/መድህን
-------------------------------------------
ትልቁ ጀሀድ ነብሲያን ማሸነፍ ነው !!(ሰ, ዐ ,ወ)

ከራስህ ጋር የምታደርገው ትግል ነው!!!


ሸጋ ምሽት💚💛❤️!!!


@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ያያ Original Human Hair
አዳዲስ ባስመጣናቸው Quality የሆኑ
የItaly and
Brazil products and with full Guarantee እንሸጣለን.እንዲሁም እቃችን ሙሉ ለ ሙሉ የማይነቃቀልና ቀለም የሚቀበል መሆኑን በደስታ እናበስራለን.
https://www.tg-me.com/yayahumanhair
ሎጎ ቴራፒ- ከትርጉም የለሽ እና
ከተስፋ መቁረጥ ኑሮ የሚያላቅቅ
የስነ-ልቦና ጥበብ (ክፍል ሁለት)
...
በመጀምሪያው ክፍል (ሎጎቴራፒ ክፍል አንድ ) ስለ ሎጎ ቴራፒ በጥቂቱ
ተረድተናል። ለማስታወስ ያህል ሎጎ ቴራፒ ሰዎችን ከጭንቀት ወይም ከተስፋ
መቁረጥ ስሜት ለማላቀቅ ከሚረዱ የስነልቦና መንገዶች አንደኛው ነው። ሰዎች
ተስፋ የሚቆርጡት አልያም ትርጉም የለሽ ኑሮ እንደሞኖሩ የሚሰማቸው
የሚኖሩለት ነገር ስለሌላቸውና ለህይወታቸው ትርጉም የሚሰጥ ነገር
ባለማግኘታቸው ነው በሚል መሰረተ ሃሳብ ላይ የተንተራሰ የስነልቦና ጥናት ነው።
በሎጎ ቴራፒ አማካኘነት ሰዎች በህይወታችን ትርጉም የሚሰጣቸው ነገር
ሲያገኙ፤ ወይም የሚኖሩለት ነገር ሲኖራቸው ትልቅ መነቃቃትን በህይወታቸው
ይፈጥርላቸዋል።

እንደ ፕ/ር ፍራንክል ጥናት በህይወታችን ትርጉም ልናገኝ የምንችልባቸው ሶስት
መንገዶች አሉ። እነዚህ ሶስት መንገዶች የሚከተሉት ናቸው

According to Frankl “we can discover this meaning in life in
three different ways
1- By creating a work or doing a deed
2-By experiencing something or encountering someone
3-By the attitude we take toward unavoidable suffering

ነጣጥለን እንያቸው ካልን

1ኛ– ሰው በሚሰራው ስራ ለህይወቱ ትርጉም ሊሰጥ ይችላል- እዚህ ላይ ብዙ
ሰዎችን በምሳሌ መውሰድ እንችላለን፤ የፈጠራ ስራ የሚሰሩ ሰዎች፤ በበጎ ስራ
ላይ የተሰማሩ ሰዎች፤ በጥበብ ውስጥ ያሉ ሰዎች፤ ከብዙሃኑ ተነጥለው
የልባቸው ጥሪ በማድመጥ የሚኖሩ ናቸው። የሚሰሩት የሚወዱትንና ትርጉም
የሚሰጣቸውን ነገር ነው። እዚህ ላይ የሁላችንም ዝንባሌ እና ፍላጎት ይለያያል።
ለእኛ ትርጉም የሚሰጠንና ልባችንን የሚያስደስተው ነገር ለሌላው ሰው ምንም
ትርጉም ላይሰጠው ይችላል። የሚወዱትን የሚሰሩ ሰዎች ግን የሌላው ሰው
ማረጋገጫ ሳያስጨንቃቸው ለሚኖሩለት ነገር ጊዜያቸውን፤ ገንዘባቸውንና
መንፈሳቸውን አሳልፈው ይሰጣሉ። ስለዚህም እያንዳንዷ ቀን ለነሱ ትርጉም አላት፤
የጥቅም የለሽነት እና ትርጉም ማጣት አይሰማቸውም።

2ኛ– ሁለተኛው የህይወት አጋጣሚዎች ወይንም በህይወታችን የምናገኛቸው
ሰዎች ለህይወት ያለንን አመለካከት ይቀይሩታል- ለምሳሌ ልጅ እና ሌሎች
አብዝተን የምንወዳቸው ሰዎች የምንኖርለት ነገር እንዳለን ያሳስቡናል። ፕ/ሩ
በዚህ ነጥብ ላይ እንደ ምሳሌ የሚጠቅሱት፤ በነዛ አስፈሪ የናዚ ኮንሰንትሬሽን
ካምፖች ውስጥ ሆነው እንኳን አንዳንድ እስረኞች ልጆቻቸውን፤ ባሎቻቸውን፤
እናትና አባቶቻቸውን እያሰቡ ያንን የመከራ ህይወት በጽናት ያሳልፉት ነበር።
መከራው ሲያበቃ ለመገናኘት የሚፈልጓቸው ሰዎች እንዳሉ ስለሚያስቡ ሞትን
ይሸሹ ነበር። ለእነሱ ህይወት ትርጉም አላትና። ሌላው ደግሞ አንዳንድ የህይወት
አጋጣሚዎች እንደ ዘበት የምንኖረውን ኑሮ እንድንቃኝና እንድንነቃ ያደርጉናል።

3ኛ-ከእኛ ቁጥጥር ውጪ በሆኑ ነገሮች ላይ ያለንን እይታ ማስተካከል-ይህ
የመጨረሻው ነጥብ በህይወታችን መመሪያ ልናደርገው የሚገባን ትልቅ ነጥብ
ነው። ልናስወግዳቸው የማንቻልቸውን ነገሮች እንዴት ነው መጋፈጥ የምንችለው?
ከእኛ ቁጥጥር ውጪ የሆኑ አጋጣሚዎች የሚያሸክሙንን መከራ እንዴት ማቅለል
እንችላለን? መልሱ አመለካከታችንን መቀየር የሚል ነው። ዶ/ር ኖርማን ቪንሰንት
እንዲህ ሲል ተናግሯል “የሚያሳስበን ችግሩ ሳይሆን ችግሩን የምናይበት መንገድ
ነው”። ብዙዎቻችን ችግሩን እንጂ ችግሩን እንዴት እያየነው እንደሆነ ልብ
አንልም። የሚያሳስበን የደረሰብን አጋጣሚ ብቻ ሳይሆን አይምሮዋችን
በምናልባት እየፈጠረ የሚስልልን መላምቶች ናቸው።

“A major cause of depression is self-absorption. By drawing on a
person’s strengths, the tools and techniques of logotherapy help
bring about a profound shift in awareness, from a ‘victim’
mentality to an optimistic attitude. Clients and students of
logotherapy are in the habit of questioning themselves about
what they really want and which kinds of choices will be most
conducive to growth”

ለጭንቀት የሚዳርጉ ብዙ ምክንያቶች አሉ፤ ዋናው ምክንያት ግን በነገሮች ተስፋ
መቁረጥ እና ነገን አለመናፈቅ ነው። ነገን የማንናፍቀው ደግሞ የምንኖርለት ነገር
ስለሌለን፤ ለህይወታችንም ትርጉም የሚሰጥ ነገር ስናጣ ነው። ከእንደዚህ አይነት
ጭንቀት ለመወጣት ሎጎቴራፒ በጣም ትልቅ እገዛ ያደርግልናል። ይህንን ጥበብ
በስራ ላይ ለማዋል እራሳችንን ልንጠይቀው የሚገቡን ጥያቄዎች አሉ ለምሳሌ፦
ብንሰራቸው የሚያስደስቱን ነገሮች ምንድን ናቸው? ለፍላጎታችን ቅድሚያ
መስጠት ብንችል ምን ይሆናል ቅድሚያ የምንሰጠው? ህይወታችን አጭር
መሆኗን ስናስብ ሳንፈጽመው ብንሞት የሚቆጨን ምንድን ነው? ለመኖር
ምክንያት ይሆነናል የምንለውስ ነገር አለን? ለነዚህ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት
ከቻልን ህይወታችን ተመልሶ አሰልቺና ድግግሞሽ አይሆንብንም። ይህ
የሎጎቴራፒ ሃሳብ ሁላችንንም በተለያየ መጠን የሚረዳን ይመስለኛል፤ ከዚህ
በተጨማሪ የራሳችን ምርምር በማድረግ ይህንን ጽንሰ ሃሳብ መሰረት በማድረግ
ህይወታችንን መለወጥ እንችላለን።



@wegoch
@wegoch
@wegoch
#ወገንሽን_እርሺ_የአባትሽን_ቤት_እርሺ_እግዚሃብሄር_ወዶሻልና!!!

ይህ ለማርያም በ፩፭ ዓመቷ የተሰጠ ቃል ነው ትህዛዝም ጭምር!!!
እኛም ወገናችን ማነው? ዘመዳችን ማነው? ዘራችን ማነው?ፈጣሪ እግዚሃብሄር አይደል!!!
እስኪ በማመልከቻ #ትግሬ የሆነ አለ #አማራስ የሆነ #ኦሮሞ የሆነስ #ጋምቤላ #ሌላም_ሌላም የሆነስ አለ? የሁላችንም የዘር ሃረግ የሁላችንም አባት የሁላችንም ወገን የሁላችንም የአባት ቤት ፈጣሪ እና ፈጣሪ ብቻ ነው። #ኢትዮጵያ_ደግሞ_የፈጣሪ_ሳሎን_ቤት!!!

#ኢትዮጵያ_ለዘላለም_ትኑር!!!
#ተክለ_ዮሀንስ

@wegoch
@wegoch
የ20ኛው ክፍለ ዘመን አስርቱ
ትዕዛዛት!!!

እኒህ ትዕዛዛት፤ ሙሴ የጻፋቸው አስርቱ ትዕዛዛት አይደሉም፤ የመጽሃፍ ቅዱሱን
ትዕዛዛት የሚጋፉም አይደሉም። ከየትኛውም ሃይማኖት የማይወግኑ ህግጋት
ናቸው። እኒህ ትዕዛዘት ከደስታ ለራቀው ለዚህ ትውልድ የተጻፉ ናቸው።አሁን
ከምኖረው ኑሮ በመነሳት ደስታችንን ለማግኘት የሚረዱን ትዕዛዛት ናቸው
።ሳንሰብር ሳናጣምም ከተገበርናቸው፤ ደስተኛ ለመሆን መንገዳችችንን ቀላል
ያደርጉልናል….

ትዕዛዝ አንድ – እራስህን ከሌላ ሰው ጋር አታፎካክር-ሁላችንም እንደ አሻራችን
ሁሉ ባህሪያችን እና ፍላጎታችንም በጣም ይለያያል። ደስታን ከሚያጠፉ
ምክንያቶች አንደኛው እራስን ከሰው ጋር ማፎካከር ነው። አሳ ደስታዋን እንደ ወፍ
በሰማይ ልፈልግ ብትል፤ ወፍ ደግሞ እንደ አሳ በውሃ ውስጥ ለፈልግ ብትል፤
ሁለቱም ሳይደሰቱ ይቀራሉ። ስለዚህ ደስታህን በራስህ መለኪያ ለካው። አንተ
በሌሎች ስትቀና ሌሎችም ባንተ ይቀናሉ። አይገርምም?

ትዕዛዝ ሁለት– አትኩሮትህን በሌለህ ነገር ላይ ሳይሆን ባለህ ነገር ላይ
አድርገው-የጎደለህ ምንድን ነው? ያለህስ ምንድን ነው ?ብታመዛዝነው የቱ
ይበልጣል? ብዙዏቻችን ሃሳብ እና አትኩሮትቻን በሌለን ነገር ላይ ስለሆነ፤ ያለንን
ነገር ሳንጠቀምበት እንቀራለን። ደስተኛ ለመሆን ሁሉም ነገር ሊኖርህ አይገባም።
በደንብ ካስተዋልከው አሁን ያለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን በቂ ነው። ምክንያቱም
አንተ ያለህን የሚመኙ ምስኪኖች ብዙ ናቸውና።

ትዕዛዝ ሶስት- እራስህን ሁን- በዚህ ምድር ላይ ሌላውን ለመምሰል
እንደመሞከር ከበድ ነገር ምን አለ? ሌላውን ለመምሰል ስትሞክር፤ የምትጣላው
ከሰው ጋር ሳይሆን ከገዛ እራስህ ጋር ነው። እናም እራስህን አታስቀይመው፤
እውነተኛ ወዳጆችህ አንተን ባነተነትህ ይቀበሉሃል…..ከምንም በላይ እራስህን
በመሆን ከራስህ ጋር ሰላም ሁን

ትዕዛዝ አራት- ሁሉን ለማስደሰት አትሞክር- አንድ ነገር ስታደርግ ሰዎች ደስ
እንዲላቸው ብለህ ሳይሆን ትክክለኛ እና አንተ ያመንክበት ነገር ስለሆነ ይሁን።
በዚህ ምድር ላይ ምንም አይነት ጻዲቅ ሰው ብትሆን እንኳን ሁሉንም ሰዎች
ማስደሰት አትችልም። ስለዚህ የምታደርጋቸው ነገሮች ከህሊናህ ጋር
እስከተስማሙ ድረስ በቂ ነው። ለሰው ሳይሆን ለህሊናህ ኑር።

ትዕዛዝ አምስት- የውሸት ደስታን አትፈልግ- በውሸት ደስታና በእውነተኛ ደስታ
መካከል ትልቅ ልዩነት አለ።የውሸት ደስታ፤ ጊዜያዊ በሆኑና ከውጪ በምናገኛቸው
ነገሮች የሚመጣ ነው። ሃዘናችንን ለጊዜው የሚጋርድ ጊዜያዊ ማስታገሻ ።
እውነተኛ ደስታ ግን ሃሳባችን፤ አላማችን፤ ምግባራችን ሲጣመር የሚፈጠር
ስሜት ነው። ሃዝን እና መከራችንን ሳንደብቅ የምንጽናናበት ደስታ።

ትዕዛዝ ስድስት- ማንን እንደምታገኝ አታውቅምና ለሁሉም ሰው ቅን ሁን-
ከመንገደኛው አንስቶ እስከ ቅርብ ወዳቻችን ድረስ፤ ሰዎች በኛ ላይ ትልቅ
አስተዋጽዎ አላቸው። በህይወትህ የምታሰፍራቸው ነጥቦች ሁሉ በኋላ ላይ
ተያይዘው መስመር መስራታቸው አይቀርም። የተናቀው ድንጋይ የማዕዘን እራስ
ይሆናል ተብሏልና ሰዎችን አትናቅ። በየትኛውም አጋጣሚ ለምታገኛቸው ሰዎች
ትክክለኛውን ነገር አድርግ።

ትዕዛዝ ሰባት- መለወጥ የማትቻለውን ነገሮችን ተቀበላቸው- ብዙ ሰውች
ጭንቀት ውስጥ የሚገቡት መለወጥ የማይችሏቸውን ነገሮች ለመለወጥ
ስለሚጥሩ ነው። ምንም እንኳን በህይወታችን ውስጥ አብዛኛው ነገሮች ላይ
ስልጣን ቢኖረንም፤ መለወጥ የማችላቸው ነገሮች አሉ።ከአቅምህ በላይ በሆኑ
ነገሮች እራስህን አታስጨንቅ። ከአቅምህ በላይ የሆነውን ነገር ለአለሙ ፈጣሪ
ስጠው።

ትዕዛዝ ስምንት- የራስህ እውነተኛ ወዳጅ ሁን- ምንም እንኳን ሰዎች በአንተ
ቢያምኑብህም እና ቢመኩብህም ፤ አንተ በገዛ እራስህ ካላመንክ ህይወትህ
ምንም ዋጋ የለውም። ከሰዎች ፍቅር በላይ የራስህ ፍቅር ወሳኝ ነው።
የሚገርመው ሰዎች እራሱ ሊወዱህ የሚችሉት አንተ በመጀመሪያ እራስህን
መውደድ ስትችል ነው።እራስህን በደንብ ተንከባከበው። ሲያጠፋ ይቅር በለው፤
ሲደክም አበርታው፤ ሲሳካለት አሞካሸው። ላንተ ካንተ የቀረበ ማን አለህና?

ትዕዛዝ ዘጠኝ- መልካም አስብ መልካም ተናገር- በመጀመሪያ ሰው ያስተሳሰቡ
ውጤት መሆኑን እመን፤ አሁን የምንኖረው ህይወት ያመለካከታችን እና
ያስተሳሰባቸን ውጤት ነው። ይህን ካወቅ፧ አስተሳሰብህን በጥንቃቄ አጢነው።
ደስተኛ ለመሆን የተመረጠ አስተሳሰብ ሊኖርህ ይገባል።

ትዕዛዝ አስር- ለምን እንደምትኖር እወቅ- ህይወት ማለት የተሰጠህን ሃላፊነት
ለመጨረስ የተሰጠችህ ጊዜ ናት።ሃላፊነትህ ምንድን ነው? በህይወትህ ማድረግ
የምፈልገው ነገር ምንድን ነው? መልሱ ካወቅክ ለህይወት ያለህ አመለካከት
የለወጣል።

ይኸው ነው!!!💚💛❤️ ሸጋ ቀን!!

@wegoch
@wegoch
@wegoch
በለውጥ እንደገና መወለድ … __ ንስር አሞራ እስከ
ሰባ ዓመት በሕይዎት የመኖር ጸጋ ተሠጦታል፡፡ ነገር ግን
ይህን 70 ዓመት የዕድሜ ፀጋን አጣጥሞ ለመኖር አርባኛ
ዓመቱ ላይ በሕይዎቱ ወሳኝ የሚባል ውሳኔን ማሳለፍ
ይጠበቅበታል፡፡ ይኸውም ንስሩ አርባኛ ዓመት ዕድሜው
ላይ እነዛ እረዥምና እንደልብ የሚተጣጠፉት ጥፍሮቹ
እንደ እነጨት ይገራሉ፡፡ ስል የነበረው ማቁርቱም ወደ
አንገቱ ይታጠፍና ምግቡን አንድኖ እንዳይዝ ያግደዋል፡፡
የገረጀፉት ላባዎቹም ከደረቱ ላይ ተጣብቀው የመብረር
ስራውን አስቸጋሪ ያደርጉበታል፡፡ በዚህ ወቅት ንስሩ ሁለት
ወሳኝ አማራጮች ይጠብቁታል፡፡ አንድም ሞትን አሜን
ብሎ መቀበል ወይም ደግሞ አንድ መቶ ሃምሳ ቀናት
ሚፈጅን ፈታኝ የለውጥ ሂደት ማካሄድን፡፡ በለውጡ ሂደት
ለማለፍ ከወሰነ ቀጣዮችን ተግባራት መፈጸም
ይጀምራል፡፡ በመጀመሪያ ንስሩ ከፍ ብሎ ከወጣ ተራራ
አለት ላይ ይቀመጥና የታጠፈውን ማንቁርቱንና ጥፍሮቹን
ከአለቱ ጋር ደጋግሞ በመምታት ወልቀው እንዲወድቅ
ያደርጋል፡፡ የገረረውና የታጠፈውን ማንቁርት እንዲሁም
ጥፍሮቹን አውልቆ ከጣለ በኋላ ከስር የወጣው ሙሽራ
ማንቁርትና ጥፍር እስኪጠነክር ድረስ ለቀናቶች
ይታገሰዋል፡፡ ማቁርቱና ጥፍሮቹ ከጠነከሩ በኋላ ቀጣይ
የሚጠብቀው ተግባር የደረቁትና ከደረቱ ጋር ተጣብቀው
ከመብረር ያገዱተን ላባዎች እየነጨ በማራገፍ በአዲስ
እንዲተኩ ማድረግ ነው፡፡ ይህን እልህ አስጨራሽና አንድ
መቶ ሃምሳ ቀናት ወይም አመስት ወራት የፈጀውን
የለውጥ ጉዞ ካካሄደ በኋላ ዳግም ውልደቱን የሚያበስር
ቀጣይ ሰላሳዎቹን ዓመታትም በትኩስ ኃይል መኖር
የሚያስችል ለውጥ አደረገ ማለት ነው፡፡ በዚህ ሁኔታም
የዳግም ውልደቱን በረራ ወደ ሰማይ ተነጥቆ ይጀምራል፡፡
ብዙውን ጊዜ አዳዲስ ክስተቶችን ተገንዝቦና ተላምዶ
በለውጡ ተጠቃሚ ለመሆን እልህ አስጨራሹን ለውጥ
ሂደትን መታገስ ይጠይቃል፡፡ የቆዩና ያፈጁ አስተሳሰቦችን
ከእሳቤ ውስጥ ማስወገድ፡፡ ከቆዩና ኋላ ቀር ልማዶች
እራስን ነፃ ማድረግ አሁን የተፈጠረልንን ጥሩ እድል
ለመተቀም ያስችላል፡፡

---------------------------------------------
የከፍታ ቅኔ!!!


ነገረኛ ሁሉ
ክንፉን ሰብሮ ሊያወርድ
የድንጋይ ውርጅብኝ እየወረወረ
እሱም አልተመታ ጠላት ጓጉቶ ቀረ
ሰውየው እንደሆን
እየዋል እያደር
እንደ ንስር ሽቅብ ከፍ ብሎ በረረ፡፡

(( ጃ ኖ ))💚💛❤️

ሸጋ ጁምኣ!!!💚💛❤️

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
Professor መስፍን ወሎየ ነው ። ያውም ደግሞ ቀብራራው የጁየ ። ከታላቁ ራስ አሊ ቀየ
መርጦና ውድመን ዘንድ የዘር ሃረጉ የሚመዘዝ ። የየጁ ስርዎ መንግስት ባለሟሎች
በእምነት ነጻነትና በሃሳብ ነጻነት የማይደራደሩ ነበሩ ። ይህ የሃገር አድባር ሽማግሌ
ወሎየነቱ በራሱ ጸረ ጎሳና ጸረ መንደርተኛ ስብእና ያጎናጸፈው ይመስለኛል ። ይህች ሃገር
በጎሰኝነትና በመንደርተኝነት በሽታ እንዳትመታ እድሜ ዘመኑን የለፋ ሊቅ ነው ። ስሙን
አስተካክሎ የማይጽፍ የመሸታ ቤት አስደላቂ የማታ ተማሪ ሁሉ የካድሬ ብእሩን እየወደረ
ይህንን ዋርካ ለመድፈር ቢሞክርም በአፍጢሙ እየተደፋ አምቡላ ማፍሰሻ ስር ወድቋል ።
የኔታ መስፍን ግን ዛሬም በጦቢያነት ሞገስና ክብሩ እንዳማረበት ተኮፍሷል ። ዛሬም
ለዘረኞች እንቆቆ ሆኖ እያጥወለወላቸው ነው ። የማንም እምባጮ ብድግ ብሎ ትልቁን
አድባር ለመዳፈር ሲጥመለመል እየተደረገመ ተመልሷል ።
ወይራና ክትክታ ባለባቱ ጠፍቶ ፤
እምባጮ ነገሰ ያለቦታው ገብቶ ።
ያለው ማን ነበር??? Professsor ያበሻ ምድር ወይራና ክትክታ ነው!!!!! እምባጮና ጎጋ
ሁላ ጥግህን ያዝ!!!!!
ለየኔታ መስፍን እድሜና ጤና ተመኘሁ!!!!


የተገማሸረ ቅዳሜ ይሁንልን!!💚💛❤️

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ግርምሽ ሲታወሱ
( በእውቀቱ ስዩም)
ግርማ ወልደጊዮርጊስ ፕሬዚዳንት ሁኑው የተመረጡ እለት ብዙ ሰዎች ተገርመዋል ::
ከእስክንድር ነጋ ጋዜጦች አንዱ ዜናውን የዘገበችው " ወያኔ አበደች " በሚል ርእስ
እንደነበር ትዝ ይለኛል:: አንድ አሙስ የቀረው ሽማግሌ እንዴት ለዚህ ሚና ይታጫል በሚል
እብሪት የተቹ አልጠፉም :: ብዙዎቻችን "ሽማግሌ ከወጣት ቀድሞ ይሞታል " የሚል
ጅልነት ሰለባ ነን::
አፈሩን የስፖንጅ ፍራሽ ያድርግለትና አቶ አሰፋ ጫቦ ስለፕሬዚዳንት ግርማ ሹመት ሲተች"
ወያኔ ያልጋ ቁራኛ ኦሮሞ ባሻንጉሊትነት አስቀምጦ" ብሎ ፃፈ:: የታሪክ ምፀት ሆኖ አሰፋ
ያልጋ ቁራኛ ብሎ ከፈረጃቸው ሽማግሌ ቀድሞ ሞተ::
መቼም: ቀልድን የሚያህል የድሜ ማራዘሚያ ክኒን የለም:: መቶ አለቃ ግርምሽ ደግሞ
በድካማቸው ላይ በመቀለድ ማንም አይደርስባቸውም :: ባንድ ወቅት ፓርላማ ላይ ቆመው
ንግግር ባለማድረጋቸው ይቅርታ ሲጠይቁ " መቆም ያልቻልኩት በቴክኒክ ብልሽት ምክንያት
ነው" ብለው የባርላማውን ተቀማጭ በሳቅ ፈጅተውታል ::
ሰውነታቸው የተሸከመው የስጋ ጉዋዝ ከርጅናቸው ጋር ተባብሮ የቀልድ ሰለባ አድርጉዋቸው
ነበር:: በተለይ - ችግኝ ተከላ ዘመቻ ላይ ሲሳተፉ ሁለት ችግኝ ተክለው ስድስት ችግኝ
ድጠው ይመለሳሉ" የሚለውን ተረብ ሳልፈልግ ያስቀኛል::
ወዳጄ ዘላለም ኩራባቸው በግርምሽ ዙርያ ለሚፈለፈሉ ቀልዶች ዋናው ምንጭ ነው::
ለሱ እንዳውጋኝ -አንድ ጊዜ ፕሬዚዳንት ግርማ የቦብ ማርሊ ልደት ሲከበር የክብር እንግዳ
ሆነው ተገኙ ይ የበአሉ ማክበርያ አዳራሽ በጋንጃ ታጥኖ ጠበቃቸው::
ንግግር ለማድረግ ሲነሱ ጋንጃው ናላቸውን እንዳጦዘው አልተረዱም::
" እኔ ፕሬዚዳንት መለስ ዜናዊ" ብለው ጀመሩ::
ታዳሚው ሲያጉረመርም::
" ይቅርታ .. እኔ .....ግርማ ብሩ"
ታዳሚው መሳቅ ጀመረ::
በመጨረሻ ስማቸውን ካዳራሹ መሀል ይፈልጉት ይመስል ዞር ዞር ብለው ሲያዩ ታዳሚው
ሁላ የቀዳማዊ ሀይለስላሴ ምስል የታተመበት ቲሸርት ለብሱዋል::
ይኸኔ-
" እኔ .....ግርማዊነትዎ"
---
ብዙዎቻችን ፕሬዚዳንት ግርማን የምናውቃቸው በርጅናቸው ዘመን ነው:: በዚህ ምክንያት
አስተያየታችን በጉብዝናቸው ዘመን የፈፀሙትን ሙያ ያገናዘበ አይደለም::
ፕሮፌሰር ጌታቸው ሃይሌ በግለታሪካቸው እንደመሰከሩት ደርግ አቁሞት በነበረው የህዝብ
ሸንጎ ውስጥ ያለፍርሀት ሀቅ የሚናገሩ ሁለት ኢትዮጵያውያን ያውቃሉ:: አንዱ ሀዲስ
አለማየሁ ሲሆኑ ሁለተኛው ግርማ ወልደጊዮርጊስ ናቸው:: ግርምሽ ከዚያ ልበሙሉነትና
ሀቀኝነት ተነስተው በመለስ ዜናዊ አገልግሎት ስር እንዴት ወደቁ ? የሚለውን ጥይቄ ታሪክ
ይመልሰው::
-በመጨረሻም ዘላለማዊ የሰላም ረፍት!!

መልካም የረፍት ቀን!!!💚💛❤️

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
2024/09/29 01:23:11
Back to Top
HTML Embed Code: