Telegram Web Link
አንድ ወቅት ላይ ኣንዲት ጣልያናዊት ጋዜጠኛ ፊደል ካስትሮን እንዲህ ስትል
ጠየቀችው።
" ሶማልያ ኢትዮጵያን ወርራ በነበረበት ጊዜ ኩባ ለኢትዮጵያ ወታደራዊ እገዛ
በማድረግዋ ነው ኢትዮጵያ ያሸነፈችው ይባላል። ይሄ እንዴት ያዩታል?"
ካስትሮም እንዲህ ኣላት "ስለ ኢትዮጵያውያን ጀግንነት እኔን ባትጠይቂኝ ይሻላል። ስለ
ኢትዮጵያውያን ጀግንነት ከኔ የበለጠ ቅድመ ኣያቶችሽን በደንብ ይነግሩሻል።"

ሸጋ ቀን💚💛❤️

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
📌በተመጣጣኝ ዋጋ የሴትም ሆነ የወንድ የሚፈልጉትን እቃዎችን ለገበያየት 👇
📍አልባሳት፣ጫማዎች፣ኤሌክትሮኒክስ ፣ሰዐቶች፣ቦርሳዎች.... 👇@kiru04
📌 @onlinesaleandbuystore
➡️የሌለን የለም ብቻ ነው!
JOIN 👇 ብለው ቤተሰብ ይሁኑ ።
https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAEPkyx
"It is better to be a human being dissatisfied than a pig satisfied."
"የተደሠተ አሳማ ከመሆን ያልተደሠተ ሠው መሆን ይሻላል"!!
እኛ ግን ደስታችን በልባችን የተወሰነች ናት /The size of a person world is a size
of his heart !!!
እናም ከልባችን የራቀ ዝርፊያና የሞራል መላሸቅ አይገርመንም ምክንያቱም የኛ ደስታ
በልባቸን የሠፈረች እና ልዕልናን የተላበሰች ናት !!!!

ሰላም እደሩልኝ💚💛❤️

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
እንዲህ ከፍፍፍፍ ያለች ፍልቅልቅ ሰኞ ትሁንልን!💚💛❤️

@wegoch
@wegoch
ትመጣለች ብዬ እየጠበቅኳት ነው --አምባሰልን። ጠንካራው መንፈሴ --የፒያንስት ግርማ
ይፍራ ሸዋ ረቂቅ ሙዚቃ ቤቴ ውስጥ ስጋ ለብሷል። ፍርሃቴን እየረታሁ ጠንካራ ለመሆን
እጥራለሁ። በልጅነት (አማርኛ መምሕራኖቻችን) --እንደ ሀ ሁ ያስጠኑን የገጣሚ ደበበ
ሠይፉ ጠብቄሽ ነበረ (ግጥም) ታወሰኝ።
እንደ መስኮቶች ተዘግተው፧ ደጆች ተቆልፈው፧ በሮች ተከርችመው፧ የልጅነት ዓይኖች --
የሟሙ እንደበረዶ፧ ጭር ያለ ጎዳና . . .አያሌ ስብርባሪ ቃላት (ግጥሞች) ተደበላለቁብኝ።
`ሰዓቱ ሲደርስ ከመቅረቷ ይልቅ መምጣቷ ከበደኝ። የጠላሁት መቅረቷ ሳይሆን የናፈቅኩት
መምጣቷ --አስፈራኝ። ' አምባሰልን በሁለት ዓመት እበልጣታለሁ። ያደግነው --አንድ የኬር
ድንጋይ ንጣፍ ከለበሰ ሠፈር ነው። በወፌ ቆመች የወደቅኩበት ደረጃ ላይ --ጥርሷን
ነቅላለች። የወለቀ ጥርሴን የወረወርኩበት ጣሪያ ላይ --"ወፌ፣ ወፌ --ያንቺን ጥርስ ለእኔ፤
የእኔን ጥርስ ላንቺ..." ብላ --የተነቀለባትን እንቁ መሳይ ጥርሷን በያድግልኛል ተስፋ
ወርውራለች። በዕድሜ ታላቋ ብሆንም በድፍረቷ ትበልጠኛለች። የሚያምሩ ሁለት ሙሉ
ጨረቃ መሰል --ትልልቅ ዓይኖች አሉዋት። ለጆሮዋ ሳይሆን ለዓይኗ አንገቴን ደፍቼ አፏጭላት
ነበር። ፉጨት ያስተማረችኝ አምባሰል ራሷ ነች (ያዩዋት ሰዎች አረ ተይ እንደ ወንድ
አያድርግሽ ቢሏትም) ። እወዳታለሁ። ልጅነቴ ከእርሷ ባይጋመድ ኖሮ ከዓይናፋርነቴ የተነሳ
አንድም ቀን --ቀና ሳልል እሞት ነበር። ቀና በማለቴ ከዋክብትን የሚያስንቁ (ዩንቨርስ)
ዓይኖቿን አይቻለሁ።
የዓይናፋርነቴን ሸለፈት የገፈፈችው እርሷ ናት። እንዲህ ነበር የሆነው :
የመኝታ ቤቴ መስኮት --ወደ ሽንት ቤት ወደ 'ምትወስደው ቀጭኗ ጓሮ ይከፈታል (ተከፍቷል)።
አልጋዬ ላይ ትራሴን (ራሴን) አመቻችቼ፤ እግሬን ግርግዳው ላይ ሰቅያለሁ። የምሽቱ ነፋስ
በመስኮቴ ገብቶ እ'ልቤ ውስጥ ይጠልቃል። ምን እያሰብኩ እንደነበር አላስታውስም። ድንገት
ግርግዳዬ ላይ (የእግሬ እራፊ ጎን) እንደ ወፍ የሚንቀሳቀስ የእጅ ጥላ አየሁ --አምባሰል
ነበረች። ከቤት እንደ ወጣሁ እጄን አንከርፍፋ ከምሽት ጥላ ወስዳ --በጣቷ ከንፈሯን እየነካች
እዚህ ጋር ሳመኝ አለችኝ። ባልጠበቅኩት ጥያቄዋ፤ ያልጠበቅኩትን መደናበር --ተደናበርኩ።
ከፈራህ ዓይኔን ልጨፍንልህ ብላ በእጆቿ ዓይኖቿን ጋረደች። ልቤን በአፌ እንዳልተፋ
ተጠንቅቄ ከንፈሯ ላይ በቀስታ (ተጠግቼ) ሳምኳት። ከቀረፋ ተቀምሞ እንደፈላ ሻይ -- ትንፋሷ
ይሞቃል። ለምን ያህል ደቂቃ የቀረፋ ሻይ መዓዛ አዘል ትንፋሷን --በብርጭቋማ ከንፈሬ ስስብ
እንደቆየሁ አላውቅም። ዓይኖቼን መግለጥ ብፈልግም አልቻልኩም። ህሊናዬ በስሟ
ያጠናሁትን ዜማ ያለ ፍቃዴ ይጫወታል። እንዲህ እያለ :
ሁ ለ ት : ዓይኔን : አ ሞ ኝ : በአንዱ : ላ ይ ጣለበት
ብዙ : ነገር : አ ይ ቷ ል : ይጥፋ : ም ን : አለበት?
እ ሸ ው : እሸው : አለኝ : የ ዓ ይ ን : ሕመሜ : ጠ ና
አልድንም : ዘ ን ድ ሮ ስ : ጥሎብኛልና — መሐሙድ አሕመድ።
ዓይኖቼ አምቢን በመሳም ብዛት በደቂቃዎች ውስጥ የጠፉ መሰለኝ። የልጅነት ሀሌታ
ከናፍሮቻችን ተጋምደው ከተሰፉበት፣ ከተጣበቁበት --የቅጽበት መለልታ እንዴት እንደተላቀቁ
አላውቅም። ከንፈሬ ከከንፈሯ ሲነሳ እየሮጠች በራ ወደ ቤቷ ገባች። (ከአካሄዷ) የተሳመች
ሳይሆን ጠጠር የተወረወረባት ወፍ ትመስላለች። (እንደ ሳምኳት) ያጠናሁት ጂኦግራፊ ጠፋኝ
--ያሰርኩት የምድር ወገብም ተፈታ። (ወደ ቤት ስገባ) አባባ የራዲዮኑን አንጀት (አንቴና)
ጎልጉሎ --ሩቅ ያለ (በእሽሽሽሽታ የታጀበ) ትዝታ እንደሚሰማ ሰው በተቀመጠበት
ተመስ'ጧል።
ሌሊቱን --ከሳምኳት በኋላ (ከንፈሯ ላይ) ያገኘሁትን ጣዕም በጥልቅ ስመረምር አደርኩ። ራት
ላይ ማርማራ(ላ)ታ ሰርቄ በልቻለሁ። እኔስ ምን ምን ብያት ይሆን? ...የተሰማትን ስሜት
አለማወቄ የጭንቀት ቁርጥማት ጣለብኝ። እጄን ደረቴ ላይ ባደርግ የልብ ትርታዬ የለም።
ሌሊቱ ረዝሞብኝ ቀስ ብዬ መስኮቴን ከፈትኩ --ልቤን አላገኘሁም።
ጠዋት መስኮቴን ከፍቼ ጸጉሬን ሳበጣጥር ወደ ሽንት ቤት አለፈች --ደንግጬ አልጋዬ ስር
መሸግሁ። ንጹህ ሰማያዊ ዩኒፎርም (ሱሪ) ለብሳ ቁጥርጥር ተሠርታለች። ማታ በጨለማ
ያላስተዋልኩት የሚያምር --ፍሬሽ ቁጥርጥር። ግንባሯ ላይ ሰዓሊ በእርሳሱ የደፋቸው --ሻዶ
መሳይ ለጋ ጸጉሮቿ ተኝተዋል። እናቷ (ፍሬ የምንላት --ፍሬወይኒ።) ሴት ልታደርጋት ማለዳ
ተነስታ ትጠበብባት እንጂ --(አምቢስ) በሴት ገላ የወንድ ተራማጅ ናት። ስትመለስ ትላንት
የስኳር ደቃቃ እንክብሎች (ከቀረፋ ሻዩ በፊት) ቅማ እንደሆነ ለመጠየቅ አሰብኩ።
አልቻልኩም --ዓይኗን ፈርቼ ወደ ሳሎን ለቁርስ ተራመድኩ።
ወደ ትምህርት ቤት አብረን ስንሔድ፤ ማታ ስስማት ከንፈሬ ላይ ያገኘችውን ጣዕም ልጠይቃት
ድፍረት አሰባሰብኩ። ከግቢ ስንወጣ ድርጊቷ ትላንት ማታ ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ ዓይነት
ነበር። ያሰባሰብኩት ድፍረት ተበታተነና አረፈው። አንገቴን ደፍቼም ከርምጃዋ ጋር ራሴን
('ርምጃዬ) አስተካከልኩ። (እንደ ወንድ) ታፏጫለች። ደስ ሲላት። የሰማሁት የፉጨቷ ዜማ
የማን እንደሆነ አልመጣልህ አለኝ። (ከትላንትና ማታ ጀምሮ) አውቀዋለሁ እኮ --ታዲያ የማን
ነበር?? አካፋይ መንገድ ላይ ስንደርስ (ትምህርት ቤታችን ይለያያልና።) ቻው ተባብለን፤
እኔም የእኔን --እሷም የእርሷን መንገድ ያዝን።
ከረፍት መልስ ወደ ክፍል ስገባ። ጂኦግራፊ መምህራችን ዳስተር ሰጠኝ። በጠመኔ የተቀራረጸ
ሰሌዳውን እያጠፋሁ --ድንገት በሚረግፈው የቾክ ብናኝ ውስጥ በፉጨቷ ያዜመችውን ዜማ
(ኖታ) ያየሁ እየመሰለኝ ፈገግ አልኩኝ። ያን ዜማ በስርቆሽ ቀን ክፍሌ ተኝታ --አባብዬ
ብጠይቃትም ምሥጢር አደረገችው። ልቤ ውስጥ ባለ ድብቅ ስፍራ ውስጥ ግን 'ያ' ዜማ
በግልጽ አለ። ( ከአራቱ ቅኝቶች የወጣ፤ እኔ ውስጥ የተደበቀ፤ እርሷ ውስጥ የተገለጸ --
አንዳች ልዩ ዜማ ሊኖር አይችልም? )
ከዛ በኋላ ስንቴ ተሳሳምን? ፍቅርስ በእኔና በእርሷ ገላ ስንት ዜማ ሠራ? አምባሰል? ትዝታ?
አንቺሆዬ? ባቲ? ስንት ቅኝት ይዘን፤ ስንት ሰማይ ወጣን? ስንቴ የገላዋን በር ከፍታ --ወደ
አርያም የሚወስደውን መንገድ አስያዘችኝ?
ስንት ዓመት አለፈው? ሁለት አስርት ዓመታት?? ያ ከንፈሯ ዛሬም እንደ ጥንቅሽ ይጣፍጥ
ይሆን? ተፈላልገን ባንገናኝ? ድንበራችን እንደ ድር፤ በእሾህና ቀጋ እንደተሸፈነ ብንዘልቅ?
በዚህ ቅርበት (በዚህ ርቀት) እንዳልተገናኘን እንሞት ነበር ማለት ነው? ለዳግም ልጅነት
ተስፋ እንዲኖረን እንግዲህ በምን እንጠመቅ?
ስልኬ ጠራ። ከኮንደሚኒየሙ ወርጄ ካለችበት ተቀበልኳት። ከራይድ ስትወርድ --ሌላ ሰው
ሆና አገኘኋት። መልኳ፣ ጸጉሯ፣ ልብሷ --አረማመዷ ሴታዊ ነበር። መደናገጤን (--ግርምታም
አለበት።) ለመደበቅ እየሞከርኩ ተቃቅፈን ሰላም ተባባልን። ጠረኗ ይማርካል። አምቢ? --
ብዬ ጠራኋት፤ ፈገግታዋ ግሩም ነበር።
አምቢ --ቁልምጫህ ናፍቆኝ ነበር አለችኝ። ከድሮም ሳውቃት በሙሉ ስሟ የሚጠራትን ሰው
አትወድም። ሰዎች አምባሰልን (የሚለውን ስም) እንዴት ማቆላመጥ እንዳለባቸው
አያውቁም። ይሕን ስለምታውቅ በራሷ ስያሜ ላይ ቀድማ ትኳሽታለች።
አምባሰል --ከቅኝትነቱ ይልቅ፤ አፈር ለለበሰ ለአንድ የድሮ ቅርስ የተሰጠ ስያሜ ነው
የሚመስለኝ --ብላ። (እፍ፣ እፍ ብዬ ቅርስነቷን ላይ ስሻ አልነበረም ወይ???? )
እኔም እንዲህ ብዬ የምጠራው ሰው ናፍቆኝ እንደነበር --ነገርኳት። ድሮም --ስሟ በየመንገዱ
እንደሚገኝ የአንበሳ ባስ ፌርማታ
አይደለም። ስትወለድ (እኛ ቤት) (የረሳሁት) የአንባሰል
ሙዚቃ ተከፍቶ ነበር። ከእርሷ ውጪ በአምባሰል የሚጠራ ሌላ ሰው አላውቅም
(አላጋጠመኝም)። ስሟን ሳልሰማ መዋሌ ማደሬ --ሁለንተናዋን አስናፍቆኛል። በሌላ ሰው
የተወረሰ ቤታቸውን እያየሁ (አዲሶቹ ጎረቤቶቻችን) መልመድ ከብዶኝ አለቅስ እንደነበር
አስታውሳለሁ። በልቤ 'ያ እኮ የእነ አምቢ ቤት ነበር' እላለሁ። ከአካልዋ ቀድሞ የስመ ስጋዋ
ናፍቆት --እንደማሪቱ ለገሠ ሙዚቃ ያገማሽረኝ ነበር።
--ተቀይረሃል? አለችኝ።
--ልክ ነሽ ጊዜ ሰውን ይቀይራል ! አልኳት።
(ከዛ ብዙ ለውጥን ያለማመን የዝምታ መመለካከቶች --ደጋግመን ተያየን።)
ቤት ገብተን ራሴ የሠራሁትን (ያበሰልኩትን) ራት ጋበዝኳት። የድሮ ትዝታዎቻችን (የጊዜስ
ይሁን። የትዝታ ድሮ አለው ወይ??) አንስተን ተጨዋወትን። ገበታው ከፍ እንዳለ ወደ ሲዲ
ማጫወቻው (የወይን ዋንጫዋን እንደያዘች) ሔዳ ሲዲ (መርጣ) ቀየረች።
ድምጼን ከፍ አድርጌ ሳቅኩኝ። የማሪቱን አልበም ነበር የከፈተችው።
--ይሕን የመሰለ ሳቅ ይዘህ፤ ድሮ ድሮ እንዴት ድምጽህን ከፍ አድርገህ አልሳቅህም?
--አባባ..
--አይ አይ በ'ሱ አታሳብብ። ምን ነበር የሚባለው?
--ዓይን ዓፋር..--ስለነ
--ያ ! እሱን ስለነበርክ ነው። (ሳቅ!)
ሶፋው ላይ ተቀምጣ ታየኛለች። ቀና ብዬ በድፍረት አየኋት። ዓይኖቿ...--የናፈቁኝ። ከንፈሯ
ስኳር...-ያስላሰኝ። ዓይኖቿ ብዙ ይናገራሉ። ከንፈሮቿም ብዙ ብዙ።
ገልጠን ያወራነው የለም። እንደተዳፈነ ነው። የምናወራው፣ የምናጠራው ድፍርስ --ሐቅ
ይጠብቀናል። ለዛ፣ ለዛ አንድ ሌሊት አለን። (ይሄ) ዛሬ --አንድ ክፍልና አንድ ሌሊት
ሰጥቶናል። (ይሄ) ጊዜ-- በአንድ ክፍልና በአንድ ሌሊት አገናኝቶናል። ( ግን፣ ግን? ለሺህ
ናፍቆት፣ ለሺህ ትዝታ --አንድ ክፍልና አንድ ሌሊት ብቻ ይበቃል ወይ?) ይገርማል። እርሷን ሳይ
የረሳሁት ሕመም፤ አንድ በአንድ ትዝ አለኝ። የአምቢም ሕመም ከዓይኗ ይታየኛል። አሁን
(ድክመቴ ፊት ለፊት ነኝ።) መንፈሴ ጠንካራ ሆኖ በፍጹም ሊቆይ አይችልም።
ሙዚቃው --በዝምታ መተያየታችንን ትልቅ ክፍተት አድርጎ የራሱን ቦይ ቀደደ። እንዲህ
እያለም በዜማ እንክብል ከጆሮ ፈሰሠ :
ቅ ኝ ቱ ን : ስሰማ : አ ም ባ ሰ ል : አመመኝ
ፈውስ : ነ ው : መድሐኒት : ዜ ማ ው : ደግሞ አ ከ መ ኝ — ማሪቱ ለገሠ።

((( እሱባለው አበራ )))💚💛❤️

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ትናንት Seyoum Teshome እና አስራት አብረሃም በLTV ቀርበው ባደረጉት ክርክር
ላይ <<ኃ/ማርያም ከስልጣን ሲወርድ በብዛት ቅሬታዎች የመጡት ከትግራይ ነው፤
ከወላይታ ግን <ለምን የኛ ሰው ከስልጣን ወረደ?> የሚል ምንም ቅሬታ አልነበረም>>
አሉ።
.
እዚህ መንደር አንድ ዘወትር የሚያነፍረኝ ባለጌ ጓደኛ አለኝ፤ ይህን ንግግር ሲሰማ
<ኮንዶም ሲፈነዳ ደንግጦ የሚጮኸው ያጠለቀው እንጂ ያመረተው አይደለም!> ብሎ
አሳቀኝ
.
ይሄው ባለጌ ከዚህ ቀደም ህወሃትን <ኮንዶሙ ከፈነዳ በኋላ እስኪረካ መቆየት የሚፈልግ
ሞኝ> ብሎ ገልጿት ነበር ። ባለጌወች አይጥፉ ይኑሩልን፤ ለአጭርና ገላጭ
ምሳሌያቸው እናመሰግናለን

ሸጊቱ ምሽት!💚!💛!❤️!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
“ሰባቱ እኔነቶቼ”……ካህሊል
ጂብራን


“the mad man” ከተሰኘው መጽሰሃፉ ላይ “the seven selves” የተሰኘው
ጽሁፍ እንዲህ ተተርጉሞ ቀርቧል


እንደ ሞት ያለ ጸጥታ ባለው ጨለማ ውስጥ በግማሽ ልቤ ተኝቻለው። ጨለማ
ከጸጥታ ጋር ሲደመር እጅጉን የሚያስፈራራ ይመስላል። እንቅልፍ ቢወስደኝም
እንቅልፌ የከበደ አልነበረምና፤ ከጎኔ ተቀምጠው ሰባቱ ማንነቶቼ ሲንሾካሾኩ
ይሰማኛል።

አንደኛው ማንነቴ እንዲህ ሲል ሰማሁት “ እዚህ እብድ ሰው ጋር እንደ መዥገር
ተጣብቄ ለዘመናት አብሬው ኖርኩኝ፤ ህመሙን እንዲድን ሳይሆን እንዲያገረሽበት
ሳደርግ፤ ስቃዩን በቀን ሃዘኑን በማታ እያደስኩበት አብሬው ከረምኩኝ፤ እነሆ
ቢበቃኝ ይሻላል፤ ከዚህ በኋላ አብሬው ልኖር አይቻለኝም” ይህንን ተናግሮ
ሲጨርስ ፤

ሁለተኛው ማንነቴ ቱግ ብሎ እንዲህ ተናገረ
“ ምነው ወዳጄ? ከኔ ህይወት ያንተ በእጅጉ ይሻላል፤ ወንድሜ እኔ ከዚህ እብድ
ሰው ጋር ሲስቅ አብሬ ስስቅ፣ በደስታው ሁሉ አብሬው ስደሰት ፣ ከደስተኛ
ህይወቱ ሌላ ምኑንም ሳልካፈል ይኸው እድሜውን በሙሉ አብሬው ኖሬአለው፣
ስለዚህ የኔ ህይወት ነውና አሰልቺ እኔ ባምጽ ይሻላል” አለ።

ሶስተኛው ማንነት
ሁላቸውም እንዲሰሙት በሚመስል ድምጽ ጮክ ብሎ መናገር ጀመረ
“ተው ተው እኔ ምን ልበል? እኔ የምኞቱ ደራሲ የፍላጎቱ ምንጭ ምን ልበል?
ወሰን የሌለው ምኞት ሳስመኘው የማይፈታ ህልም ሳሳልመው የከረምኩት እኔ
ከንቱ ማንነቱ ነኝ ከዚህ እብድ ሰው ውስጥ ማመጽ እና መውጣት ያለብኝ”

ይህንን ተናግሮ ሲጨርስ ከሁሉም በላይ በሚያስፈራ ድምጽ አራተኛው ማንነቴ
ንግግሩን ጀመረ፤ የድምጹ ከፍታ የኔን መተኛት እንደረሱት ይናገራል
“አትሳሳቱ ወንድሞቼ ከሁላቹህም በለይ በዚህ እብድ ሰው ላይ ማመጽ ያለብኝ
እኔ ነኝ፤ እኔ ከጨላማ ዋሻ የተገኘው ክፉ ማንነቱ ነኝ፤ ልቡን በክፋት እና በጥላቻ
የምሞላው ከዚህ በኋላ ግን ይህንን እብድ ሰው ማገልገል እንደሌለብኝ
ይሰማኛል” አለ ከድምጹ በብሶት እንደሚናገር ያስታውቃል


“በጭራሽ” አለ አምስተኛው ማንነቴ “ እኔ ማሰብ የምችለው ማንነቱ ነኝ ከዚህ
እብድ ሰው መራቅ ያለብኝ፤ እረፍት የማሳጣው፤ ብክን ያለ ኑሮ የማስኖረው
የሌለውን የማሳስበው ባልተፈጠረው እንዲደመም የማደርገው እኔ ነኝ፤ ታድያ
ማነው ይህን እብድ ሰው ማገልገል ማቆም ያለበት? እኔ ወይስ እናንተ?”

ይህን
ጊዜ ስድስተኛው ማንነቴ በንዴት መናገር ጀመረ
“እኔ የስራ ማንነቱ ብቸኛ ነኝ፤ ጉልበቴን ሳልስት ቀኑን ቀን እንዲመስልለት በስራ
በታታሪነት ሳገልግለው ከርሜአለው አይኖቹ እረቀው እንዲመለከቱ፤ ምስል
አልባው ማንነት ምስል እንዲይዝለት ስለፋ የከረምኩት እኔ ብቸኛው ነኝ ከዚህ
እብድ ሰው እርቄ መሄድ ያለብኝ” አለ
ሁሉም የልባቸውን ተናገሩ፤ ለዘመናት ችለውት የነበረውን አንዳቸው ላንዳቸው
ተነፈሱ፤ ማንም ዳኛ በሌለበት ብሶታቸውን አራገፉ፤ የመጨረሻው እና እስካሁን
በዝምታ ሌሎቹን ሲሰማ የነበረው ሰባተኛው ማንነቴ ሊናገረው የሚፈልገው ነገር
እንዳለው ለማሳወቅ ጉሮሮውን ጠረረገ
“ይገርማል እኔ እያለው እናንተ እዚህ ሰው ላይ ማመጻቹህ፤ እናንተስ የየራሳቹህ
የስራ ድርሻ አላቹህ፤ ልታደርጉት የሚጋባቹህን ሁሉ ታውቃላቹህ፤ ቢያንስ
የየራሳቹህ እጣ ፋንታ አላቹህ፤ እኔ ምንም የሆንኩት ማንነቱ ነኝ ማመጽ ያለብኝ፤
ወዴት እንደምሄድ አላውቅም ፤ ምን እንደምፈልግ አላውቅም፤ የስራ ድርሻዬን
አላማዬን ፍጹም አላውቅም፤ እናም ወንድሞቼ እናንተስ ስራ አላቹህ በህይወቱ
የራሳቹህን አሻራ ልታኖሩ ነው፤ ስለዚህ ይህን እብድ ሰው ትቶ መሄድ የምትሉትን
ሃሳብ ወዲያ ጣሉት በህይወቱ ድርሻ አላቹህና” አለ ሃዘን እየገባው
ሰባተኛው ማንነቴ የሁሉንም ልብ ነካ፤ ስድስቱም በሃዘን በግማሽ ልቤ የተኛሁትን
እኔን ተመለከቱኝ፤ ሰዓቱ ገፍቶ ሌሊቱ ተጋምሶ ነበረና ሁላቸውም ደከማቸው፤ እንደ
ድሮ ሳይሆን በአዲስ መንፈስ ቀስ በቀስ እንቅልፍ ፈነጋላቸው፤ ከሰባተኛው ማንነቴ
በቀር ፤ እሱ ሁሉንም በትካዜ ይመለከት ነበር


ሰው አንድ አካል ሆኖ ይፈጠር እንጂ ውስጡ ብዙ ማንነቶች እንዳሉት እኔም እንደ
ካህሊል ጅብራን አምናለው። ደግ ማንነት አለን፤ እራስ ወዳድ ማንነት አለን፤ ታታሪ
ማንነት አለን፤ ሰነፍ ማንነት አለን፤ ታማኝ ፤ከሃዲ፤ አሩቅ አሳቢ፤ ቅርብ አላሚ፤
በተስፋ የሚኖር፤ ተስፋ የቆረጠ ከዚህም በላይ ብዙ መልክ ያላቸው ብ6
ማንነቶች አሉን፤ ዋናው ቁም ነገር ግን የትኛው ማንነታችን ነው መሪ ነው?
የሚለው ነው።

((( በሚስጥረ አደራው ))

ሸጋ ቀን!!!💚💛❤️

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ሀሙስ ከደረስን እሁድ ብዙ
አይርቅም!!!💚💛❤️

(በሚስጥረ አደራው)
ህይወት ከሰባት ቀናቶች የበለጠ እድሜ የላትም፤ የትኛው ቀን ላይ ነን? ይህንን
ያለው ታዋቂው ገጣሚ ሮበት ብላይ ነው። ገጣሚው ይህንን የተናገረው አሜሪካ
በወቅቱ የነበረችበትን ጦርነቶች አስመልክቶ ተቃውሞውን በገለጸበት ግጥሙ
ውስጥ ነበር። ይህ ሰው ስነጥብበን ለሰላም ለማዋል ብዙ ተግቷል፤ እንደውም
“American Writers Against the Vietnam War” የሚል ማህበርም
መስርቶ ነበር፤ ይህ ማህበር በወቅቱ የነበረውን ጦርነት የሚቃወም ማህበር
ነበር። ብዕር ከምንም አይነት ጦር የበለጠ ጉልበት እንዳለው ስላመነ፤ በብዕሩ
ብዙ ስለሰላም ብዙ ብሏል።

በጽሁፎቻቸው ለሰላም የሚታገሉ ጀግኖች በሁሉም ቦታ አሉ፤ የዛኑ ያህል ግን
የጥፋት መልክተኞችም ብዙ ናቸው። ብዕር እንደሌሎች መሳሪያዎች ሁሉ
በጥንቃቄ ሊያዝ የሚገባው መሳሪያ ነው። ሰው ሽጉጥ ስላለው ብቻ፤ ሽጉጡን
በየቦታው አያወጣም፤ ለቁምነገሩም፤ ለጨዋታውም እየመዘዘ ልዋጋበት
አይልም። ብዕርም የዛኑ ያህል ጥንቃቄና ማስተዋልን የሚጠይቅ መሳሪያ ነው።
ሁሉም ነገሮች በቃላት ስለሚጀመሩ፤ ቃላትን የሚተኩሰው ዋነኛ መሳሪያ ደግሞ
ብዕር ስለሆነ። ለዚህ ነው ይህንን ሰው ላነሳው የወደድኩት፤ ስለሰላም በብዕሩ
ስለተዋጋ።

አዋቂ ነን ካልነው ጨቅላዎች ተሻሉ

በከፋቸው ቁጥር ያለ አንዳች ይሉኝታ ይነፋረቃሉ

አዋቂ ሰው ሁኖ ሰው መጮህ ካልቻለ

ካልተወለደ ጽንስ እንደምን ተሻለ?

I say to myself: “Go on, cry. What’s the sense
of being an adult and having no voice? Cry out!” –Robert Bly

ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት ነው። የሚያሳዝነው ሁላችንም የምንጣለው
ዘለዓለም እንደሚኖር ሰው ነው። እኔ በህይወቴ ከሞቶ ዓመት በላይ የኖረ ሰው
አጋጥሞኝ አያውቅም፤ እሱንም በቴሌቭዥን ድንቃድንቅ ወሬዎች ላይ። አብዛኛው
ሰው የእድሜው ጣሪያ ከሰማኒያና ከዘጠና አያልፍም፤ ይህንን አጭር ህይወት
ነው “ሰባት ቀናቶች” ያለው ገጣሚው። እንደው ሰባ አመትን ብንወስድ እንኳን፤
አርባ የሞላው ሰው ሃሙስ ላይ ደርሷል ማለት ነው። ይህ ጨለምተኝነት
አይደለም እውነታ እንጂ። አንዳንዴ ብዙ ጊዜ እንዳለው ሰው እንዘናጋለን፤
በጥላቻና ሰላምን በማራቅ ሳናውቀው እሁድ ይመጣል። ሰው የወጣትነት
እድሜው ላይ ከደረሰ፤ እሮብን እንዳለፈ ይቆጠራል፤ ህይወት አትተነበይምና።
ያም ሆነ ይህ፤ እሁድ ሳይመጣ ሰላምና ፍቅርን በየቤታችን ያግባልን። የደካሞች
አስተሳሰብ ቢመስልም እንኳን፤ ብዙ የምንጣላባቸው ነገሮች ከንቱዎች ናቸው፤
ይዘናቸው የማንሄድ፤ በሰማያዊው ቤት እንኳን ዋጋ የማያሰጡን። ጽድቅና ኩነኔ
ቢኖርም ባይኖርም ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም የተባለው እኮ፤ ጥላቻና
ክፋት በምንም ስሌትና ቦታ ዋጋ እንደሌለው ስለታወቀ ነው።

“Some masters say our life lasts only seven days.
Where are we in the week? Is it Thursday yet?
Hurry, cry now! Soon Sunday night will come.”-Rober Bly

ህይወት ከሰባት ቀናቶች አትበልጥም፤ እሁድ ከደረሰ የደቂቃ እድሜ እንኳን
ምርቃት አትሰጥም። ሀሙስ ላይ ካላችሁ ይላል ጸሃፊው፤ እሁድ ብዙ አይርቅም።
በቅዳሜ እና እሁድ እድሜ ደግሞ ከሰላምና ከፍቅር የበለጠ እፎይታን የሚሰጥ
ምንም ነገር የለም።

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ሌሎች ስላንተ ያላቸው
አስተያየት ማንነትህ
እንዳይመስልህ ተጠንቀቅ!!!


በአሁኑ ሰዓት ስለራሳችን ያለን አስተሳሰብ ከየት እንደመነጨ ጠይቀን
እናውቃለን? ስለራሳችሁ ተናገሩ ብንባልስ ምን መልስ ይኖረናል? አቅማችንንስ
ስንመዝን በማን መመዘኛ ነው? እንችላለን ብለን የምናስባቸው ነገሮችም ሆኑ
አንችላቸውም ብለን የምናስባቸው ነገሮች በመጀመሪያ እንዴት ወደ
አይምሮዋችን ዘለቁ?

ይህንን ያልኩበት ምክንያት ብዙዎቻችን ያለንን አቅምም ሆነ ተሰጥዎ አውጥተን
ያልተጠቀምንበት ዋነኛው ምክንያት ሌሎች በአንድ ወቅት እንደማይቻል ሹክ
ስላሉን ነው ወይም ብቁ እንዳልሆንን ስላሳመኑን። በተለይ የሚወዱን እና
የምንወዳቸው ሰዎች፤ እምነት የጣልንባቸው ወዳጆች ሳያውቁ በህሊናችን
ውስጥ እውነተኛውን ማንነታችንን የሚያደበዝዝ አሻራ ሊያኖሩብን ይችላሉ።

ስንቶች ናቸው በልጅነት ጓደኞቻቸው ተስቆባቸው ነፍስ አውቀው እንኳን
ማንነታቸውን ለመቀበል የሚከብዳቸው? አንድ የትምህርት አይነትን ስለወደቁ
ብቻ በመምህራቸው “ደደብ” ተብለው እድሜ ልካቸውን ደደብ እንደሆኑ አምነው
ሳይበሩ የከሰሙ ስንት ሰዎች አሉ? በተለይ በልጅነታችን እንደዘበት የሚወረሩብን
ቃላቶች ምን ያህል የወደፊቱ ህይወታችንን እንደሚቀርጹት የማያስተውሉ
ብዙዎች ናቸው።

ሁሌም ይህንን አስተሳሰብ በደንብ የሚገልጽልኝ ታሪክ አለ። በአንድ ወቅት አንድ
ጎብኚ ትልቅ የእንስሳ ማዕክለን ሲጎበኝ እጅግ የሚገርም ነገር ያስተውላል። አንድ
ትልቅ ዝሆን በቀጭን ገመድ ታስሮ ይጎበኛል (ለማምለጥ ሳይሞክር)። ገመዱ
እንኳን ያንን የሚያክል ዝሆን ይቅርና ዶሮንም በቅጡ የሚያስር ጠንካራ ገመድ
አይደለም። ይሄኔ በማዕከሉ የሚሰራውን አንድ ሰው ተጠግቶ እንዲህ ሲል
ጠየቀው “ቆይ ይህንን የሚያክል ዝሆን እንዴት በዚህች በምታህል ገመድ ብቻ
ታስሮ ይቆያል? ገመዱን በማንኛውም ሰዓት በጥሶ ማምለጥ ሲችል” አለው።
ሰራተኛውም እንዲህ ሲል መለሰለት “ይህ ዝሆን አሁን የታሰረበት ገመድ ትንሽ
እያለ የታሰረበት ገመድ ነው፤ ትንሽ እያለ ገመዱን በጥሶ ማምለጥ አይቻለውም
ነበር። ያንን አይምሮው አንዴ ስላመነ ምንም ያህል ቢገዝፍም ለማምለጥ
አይሞክርም” ብሎ አስረዳው።

ምንም ያህሎቻችን ነን በልጅነት ገመዳችን እስካሁን የታሰርነው? ሌሎች ሳያውቁ
ባጠለቁብን ገመድ መሄድ ከሚገባን የተገታን ጥቂቶች አይደለንም። እንደዘበት
የተሰነዘረብን አስተያየት እውነተኛ ማንነታችን መስሎን የማንደሰበትን ኑሮ
እንኖራለን። “አትችልም” ስለተባልን አንችልም ብለን አምነናል። “አስቀያሚ”
ስለተባልን ውበታችንን ማየት ተስኖናል። “ደደብ” ስለተባልን ለም አይምሮዋችንን
ሳንጠቀምበት ቀርተናል። ልዩ በመሆናችን ጥቂቶች ስለተሳለቁብን ብቻ ከሰው
የማንገጥም እየመሰለን እራሳችንን አግልለናል።

አስታውሳለው ከአመታት በፊት አንድ ጓደኛዬ መቼም የትዳር ጓደኛ የሚኖረኝ
እንደማይመስላት ስትነግረኝ እርግጠኝነቷ ፊቷ ላይ ይነበብ ነበር። ለብዙ
ጊዜያትም እውነት መስሎኝ ኖሬያለው። አይምሮዬ ነገሮችን ማስተዋል ሲጀምር
ግን ሌሎች ስለኔ ያላቸው አስተያየት የኔ ማንነት እንዳልሆነ ተረድቻለው።ሰዎች
ስለኛ አስተያየት ሲሰጡን ከምን ተነስተው እንደሆነ አናውቅም። እኔ በክፋት
አልወስደውም አልያም በምቀኝነት፤ ነገር ግን ካለማወቅ ነው ብዩ አምናለው።
እንደቀልድ ብዙ ሰዎች በህይወታችን ውስጥ ገመድ አጥልቀውብናል። ያኔ
አይምሮዋችን ስላልበሰለ ማምለጥ አቅቶን ይሆን ይሆናል። እናም አሁንም ድረስ
እራሳችንን ነጻ ማውጣት የማይቻል እየመሰለን እንደ ዝሆኑ በቀጭን ገመድ
ታስረናል።

አንተን ወይም አንቺን ያሰረሽ ምንድን ነው? ሌሎች የሰጡህ ወይም የሰጡሽ
አስተያየ እውነት ነው ብለሽ/ብለህ እየኖርክ ነው? ማንነታችን እኛ እንመርጠዋለን
እንጂ ሌሎች ሊመርጡልን አይችሉም። ሳያውቁ በመንገዳችን የቆሙትን ሰዎች
ይቅር ብለን፤ የምንፈልገውን ኑሮ እንዳንኖር ያሰረንን ያንን ቀጭን ገመድ
እንበጥስ። በዚህ ምድር ላይ ከፈጣሪ በታችን ካንተ በቀር ያንተን ህይወት
በሃላፊነት ሊወስድ የሚችል ማንም ሰው የለምና።

በመጨረሻ ለሰዎች የምንነግራቸውን ነገር እናስተዋል፤ እንደዘበት የሚያስራቸው
ገመድ ሊሆን ይችላልና!!!💚💛❤️
-------------------------------------------------


የታሰረ!!!!!


ገና በአሻጋሪ፣
ገመድ ባየ ቁጥር፣
ጠፍር ባየ ቁጥር፣
""" አሰሩኝ!!!!!"""" እያለ፣
""" ጠፈሩኝ!!!!!!!"""" እያለ፣ እስር እያሰላ፣
ስንቱ ዳማ ፈረስ፣
አንድ ቀን ሳይሰግር፣
ይኸው ተገትሯል፣ ገለባ እየበላ።

(((( ጃ ኖ )))💚💛❤️

ሸጋ ጁምኣ!!!!!!!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
Mufti Hajji Omer Idriss
----------------------------
" አንድነት ማለት አብሮ በመቀማመጥ አይመጣም ። አንድነት እንደዚህ በመሰባሰብም
አይገኝም ። አንድነት በጉርብትናም አይመጣም ጎረቤት ሆኖ እንደተጣላ የሚኖር አለና ።
አንድነት አብሮ በአንድ ቤት በመኖርም የሚመጣ ነገር አይደለም ፡ ባልና ሚስት ሆነው
አይጥና ድመት ሆነው የሚኖሩ ሰወች አሉ ። አንድነት ልባዊ ነው ። አንድነት ልባዊ. ..ልባዊ
ተግባር ነው ስለዚህ ከልባችን አንድ ለመሆን እንትጋ "

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ኡመር ኢድሪስ

የተገማሸረ ቅዳሜ ይሁንልን💚💛❤️

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ትናንት ዛሬ አደለም
( በእውቀቱ ስዩም)
ይገርማል!! ያገራችን ገበሬ የሚያርስበት በሬና ማረሻ ጥንታዊ ሰው ከአራት ሺህ አመት
በፊት ይገለገልበት የነበረውን ነው:: ይሁን እንጂ ቢቀናው ክላሺንኮቭ ይታጠቃል:: ደሞ
ገበሬውን ዘመናዊ ጠመንጃ እንጂ ዘመናዊ ማረሻ ለማስታጠቅ የሚያልም አክቲቪስት
አይተን አናውቅም::
ዘመናይ የብሄር አክትቪስት ጦርነት በናፈቀ ቁጥር ያባቶቹን ጀብድ ይዘክራል:: ባባቶቹና በሱ
መካከል በሰፊው የሚያዛጋ የጊዜ ገደል እንደተዘረጋ አይገባውም:: የድሮ ሰዎች ከማረስ
ይልቅ መዋጋት ቢወዱ አይገርምም:: ያኔ ጦርነት ወጭው ትንሽ : ትርፉ ብዙ ነበር:: ጥቂት
የተደራጀ ጭፍራ ጥቂት ፈረስና ጦር ይዞ በሺ የሚቆጠር የቀንድ ከብት መማርክ ይቻል
ነበር:: ዛሬ አንድ መንደር አርሶ የሚያበላ ትራክተር ባስራ አራት ሺህ ዶላር መግዛት
ትችላለህ:: አንድ መንደር አፈር የሚያስበላ ታንክ ለመሸመት ከፈልግህ ግን ዘጠኝ ሚሊዮን
ዶላር መክፈል ይጠበቅብሃል:: እና በዚህ ዘመን ተዋግቼ አተርፋለሁ ብሎ ጉራውን የሚነፋ
አዲስ የተመረተ ዴዴብ መሆን አለበት!!!
ድሮ በሰላምም ሆነ በጦርነት ባጭሩ መቀጨት ያባት የናትህ እዳ ነበር:: በጦርነትም ሆነ
በሰላም ጊዜ ከሞት ጋር ያለህ ርቀት ተቀራራቢ ነው:: ይህን የሚያውቁት ቀዳማዊ
ሀይለስላሴ በማይጨው ዋዜማ የክተት አዋጃቸው "ቤትህ ቁጭ ብለህ በሳልና በጉንፋን
ከመሞት ጠላትን መክተህ ብትሞት ክብር ነው" ብለው ዜጋውን ጀንጅነውታል:: ልክ ነው!
በህዳር በሸታ ከመሞት በጦርነት መሞት ስም እና ምርኮ ሊያስገኝ ይችላል::
ዛሬ ሰላም ወጭ ቆጣቢ ነው:: ሰላም ያለው ብዙ ሀብት ብዙ እድል ብዙ ተስፋና ብዙ
እድሜ ይኖረዋል:: ታድያ ለሰላም ሲባል ወደረኞቻችንን ብንለማመጣቸው ብናቆላምጣቸው
ብንወያያቸው እንዴት ነውር ይሆናል? ዛሬ መደራደር መወያየት የሚያሳፍርበት : ውረድ
እንውረድ የሚያስኮራበት ዘመን አይደለም::
ዛሬም እንደ ጥንቱ በርስት ወይም በማንንት ሰበብ የሚደረግ ጦርነት የሚጎዳው ዜጎች
እንጂ ጌቶች አይደለም:: ከእምባቦ ከሰገሌ እና ከባድመ ክሽፈት እንዳየነው አገሬው
በጦርነት ያልፋል: አገር መሪው ግን ይተርፋል:: በምባቦ ጦርነት ንጉስ ምኒልክና ንጉስ
ተክለሃይማኖት ገጥመው በብዙሺህ የሚቆጠር ባላገር ያአሞራ ቀለብ ሆነ:: ሁለቱ ሃያላን
ግን ታርቀው ተፋቅረው ረጅም እድሜ ኖሩ:: ሰገሌ ላይ የንጉስ ሚካየል ባላገርና የተፈሪ
መኮንን ባላገር ተፈሳፈሰ:: ደሙን ለሁለቱ መሳፍንት የክብር ሲል አፈሰሰ:: ንጉስ ሚካኤልም
ሆነ ተፈሪን ግን ከጦርነቱ ማጠናቀቂያ ባንድ ድንኩዋን ውስጥ ተቀምጠው " አባቴ
እንኩዋን አተረፈዎ! ልጄ እንኩዋን አተረፈህ" እየተባባሉ ተቃቀፉ:: በባድመ ጦርነት ያ ሁሉ
ወጣት አላማም ሆነ ኢላማም በሌለው ጦርነት ሜዳ ላይ ቀረ:: የጦርነቱ ጠንሳሾች
ለሙታን ተገቢውን መታሰቢያ ሳያደርጉ ላደረጉት ይቅርታ ሳይጠይቁ በህይወት
ይርመሰመሳሉ :: ነገም ከዚህ የተለየ አይሆንም!!
እና እምቢ በል!!! አሻፍረኝ በል!! በቀረርቶ አትወሰድ! በመፈክር አትሸወድ!! ለሚያዋጉ እንጂ
ለማይዋጉ ጦርአውርዶች : እንኩዋን ህይወትህን ትኩረትህን ለመሰጠት አትሞክር!!

@wegoch
@wegoch
የሕይወት ትርጉም/Logotherapy

ቢነበቡ ብዬ ከምጠቁቸው መጻሕፍት መካከል  በቪክቶር ፍራንክል የተጻፈውና ከ10 ሚሊየን ኮፒ በላይ የተሸጠው  “Man’s Search for Meaning”አንዱ ነው።ጸሀፊው አይሁዳዊ በመሆኑ ብቻ በናዚዎች ብዙ ስቃይ ደርሶበታል።የቅርብ ዘመዶቹንና ወዳጆቹ ተገለውበታል።እርሱም ስቃይ በሚካሄድበት የማጎሪያ ካምፕ ውስጥ ለመናገርና ለማሰብ የሚከብዱ ስቃዮች አጋጥመውታል።ፍራንክል የየስነ አዕምሮ ሐኪም/Psychatrist/ስለነበር ሁሉንም በማስተዋል ይመለከት ነበር።በማጎሪያ ካምፕ ውስጥ ሁለት አይነ ሰዎች ነበሩ ይለናል።የመጀመሪያዎቹ የመኖር ትርጉም ያላቸው ሲሆኑ ሁለተኞቹ ደግሞ ለምን በሕይወት እንዳሉ የማይገባቸው ነበሩ።ፍራንክ እራሱ የመኖር 
ትርጉም ካላችው ሰዎች ውስጥ ነበር።በስቃይ ካምፕ ውስጥ ታማሚችን ይረዳ ነበር።በአዕምሮ ውስጥ ደግሞ ከዛ አስቀያሚ ሁኔታ አንድ ቀን ወጥቶ  ሚስቱን አግኝቶ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ሲያስተምርና ለማህበረሰብ  የሆነ ነገር ሲያበረክት ይታየው ነበር ።ከዚሀ በመነሳት አዲስ የስነ ልቦና ሕክምና / psychotherapy/ አሰትዋውቆናል።የሕክምናው መሰረታዊ ሃሳብ ይሄ ነው።

👉 የስነ ልቦና በሽታ
/Psychopathology/ የሚጀምረው መሆን በሚገባክና በሆንከው ፤ ልታደርግ በሚገባክና እያደረክ ባለከው መካካል ትልቅ ክፍተት ሲፈጠር ነው።

👉የችገሩ መፍትሄ የምትኖርበትን ምክንያት መፈለግና የሕይወት ትረጉም ማግኘት ነው።

👉 ስቃይክ ውስጥ
ትርጉም ስታገኝ ስቃይ መሆኑ ይቀራል።

👉በህይወትክ ውስጥ የሚሆነውን መምረጥ ባትችልም እንዴት መመለስ እንደምትችል ግን የመምርጥ ነጻነቱ አለክ።

👉ሰዎች የሆነ ነገር ከሌሎች  ከመጠበቅ ይልቅ ከእነሱ ምን እንደሚጠበቅ ላይ   ትኩረት ማድረገ አለባቸው።

👉ደስታና ስኬት በልፋት ተፈልገው የሚገኙ ሳይሆኑ ትርጉም ያለው ሕይወት የመኖር 
ውጤት ናቸው።

👉በሕይወትክ ውስጥ ለምን እኖራው የሚለውን ከመለስክ እንዴት እኖራለው የሚለው ቀላል ይሆንልካል።
          
  "እነዴት ልኑር ከሚለው ሃሳባችን ላይ ቀንሰን ለምን እንደምንኖር እናስብ"!

ኤርሚያስ ኪሮስ


@wegoch
@wegoch
@gebriel_19
 
2024/09/29 03:26:12
Back to Top
HTML Embed Code: