Telegram Web Link
👆👆👆👆👆
ወዳጆች እስቲ አንብበን ተፅዕኖ ያሳደረብን ፣ ደጋግመን ያነበብነው ፣ ሁሉም ሰው ሊያነበው የሚገባው መፅሐፍ ነው የምትሉትን አካፍሉን.......

ሸጋ ጁምኣ!!!💚💛❤️

👇👇👇👇

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ወግ ብቻ
👆👆👆👆👆 ወዳጆች እስቲ አንብበን ተፅዕኖ ያሳደረብን ፣ ደጋግመን ያነበብነው ፣ ሁሉም ሰው ሊያነበው የሚገባው መፅሐፍ ነው የምትሉትን አካፍሉን....... ሸጋ ጁምኣ!!!💚💛❤️ 👇👇👇👇 @balmbaras @wegoch @wegoch
Tizita Desalegn:👇👇
ሰላም

ስሜ ትዝታ ይባላል
በህይወቴ ለውጥ ያመጡ መፃህፍት

(አወንታዊ
ሰመመን፣ አደራው እና የተቆለፈበት ቁልፍ

አሉታዊ
ያልሰከነ ዜማ
መሀልየ መሀልየ ዘካዛንችስ)

መርጣችሁ እንድታነቧቸው ጋበዝኳችሁ።

Helen👇👇
koreb ze tseat ........ be kidist tadesse

Hanan Seid:👇👇👇
Eshiiii
ye methehafu title Heywetehen tedesetebat nw
yethafut abdurehman al arifi
Yeteregomechew hidaya mohammed
endene betam arif metehaf nw heyweten endet kelel argona destegna hono lemenore endemichal yasnebebal

SSSS:👇👇
አመፀኛው ክልስ

Dr. Estif:👇👇
Ye burka zimeta

Kidane M.:👇👇
Selam sme kidane M. yibalal be hiwote lewt yametut metshaft Alemenor, yotor & lela sew nachew hulum degagemo biyanbachew des yilegnal.


በጥቂቱ ይሄን ይመስላል ....እናመሰግናለን 🙏🙏 ከዚህ ቦሀላ ለምትልኩልን....በአማርኛ እየፃፋቹ ቢሆን ደስ ይለናል 🙏

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
Ashenafi Ashea:👇👇
ሰላም፡፡
ስሜ አሸናፊ ገብሬ ይባላል፡፡
በህይወቴ ለውጥ ያመጡ መፅሀፎች ወይም የወደድኳቸው መፅሀፍት፡-
Dr. ምህረት ፡ ሌላ ሰው
Dr. ዳዊት ፡ አለመኖር
ቢልልኝ ሀብታሙ ፡ ሰው መሆን
Norman ፡ The power of positive thinking.
Hellen : The story of my life .
Tnx.

.............. .............:
ሰላም👇👇👇
ስሜ ቀመር ይባላል

በሂወቴ ውስጥ በጣም ብዙ መፅሀፎች ለውጥ አምጥተዋል እ.በጣም ከወደድኩት ውስጥ የምጋብዛችሁ
1,አለመኖር
2,የተቆለፈበት ቁልፍ
3,ሌላ ሰው
4,ብርቅርቅታ 5, ዮቶር(ኮብላዩ ካህን)


የደራሲ ቢንያም ሀብታሙ "የወንደላጤውና የሰራተኛዋ ሜሞ" በጣም ስለሚያዝናና ተጋበዙልኝ።

Hashim:👇👇
ለኔ አቤ ጉበኛ አልወለድ

በቅርቡ የብሩክ የሺጥላ ድንቅ መጵሀፍ (የኔ ስጦታ)


ስሜ መቅደስ ይባላል👇👇👇

በህይወቴ ለውጥ ያመጡት መፅሀፍት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
1፡ ይልተኖረ ልጅነት
2፡ የተቆለፈበት ቁልፍ
3፡ አለመኖር
ሁሉንም በፍቅር እንዲያነቡት ተጋብዘዋል፡፡🙏🙏🙏

Melika:👇👇👇
Eshi semi zakir.....kanbebkwachew methafoch le mjemriya gezi yaselkseg methaf ALeMeNoR yemilwn nw ...ewnt ewnt endetanbut gabzkuwachehu

Mohammed:👇👇
ሰላም ስሜ ሙሐመድ ሰዒድ ይባላል በሂወቴ ለውጥ ያመጣው መፅሐፍ የአቤ ጉበኛ "የህይወት ተርጓሚዎች" የተሰኘው ነው

Diyogan Diyogan:👇👇👇
ስሜ መግደላዊት ነው
በህይወቴ አሉታዊ ለውጥ የፈጠሩ መፅሀፍቶች የአለማየው ዋሴ (እምጓ መርበብት እና ዝጎራ) ፣ የ አዘርግ ኤጭ እና የቃልኪዳን አላቲኖስ
አሉታዊ ተፅእኖ
ብዙም ባይሆንም የአቤ አልወለድም

hayu:👇👇👇
selam selam.hayat ebalalhu.eee kanebekwachew methaf enalaye telke teseno yasadrew ,yetemchgne, lelochem endiyanbut megefafawe methafe 1 the secrets /ሚስጥሩ/ "የመረጥነውን ሁሉ ማግኘት እንችላለን።የትልቀቱ መጠን አያስጨንቀንም" kemthafu yetwesede.

ኪነ.አየለ ዳኒ:👇👇
ሰላም ወንድም ስሜ ኪነጥበብ ነው ።

በኔ ሕይወት ላይ ለውጥ ያመጡ ወይም ተፅዕኖን መፍጠር የቻሉ የምላቸው መጽሐፍት

በመልካም ጎኑ(ገጽ)
፨ የኔ ጀግና
፨ የተካሰ ፍቅር(ትርጉም)
፨ የአና ማስታወሻ(ትርጉም)
፨ ነብዩ(ትርጉም)
፨ ህያው ፍቅር (ትርጉም)
፨ ቆንጆዎቹ እና የቃየን መስዋእት
፨ አለመኖር

በአሉታዊው ገጽ
፨ የቡርቃ ዝምታ
፨ የኦሽዊትሽ ሚስጥር (ትርጉም)
፨ ሰባተኛው ሚስጥር (ትርጉም)


ሁላችሁንም እጅግ በጣም
እናመሰግናለን🙏🙏 ያነበብናቸውን መፅሐፍ ደግመን እንድናነበው ያላነበብናቸውን ደግሞ ገዝተን እንድናነባቸው...ጥቆማ ስለሰጣችሁን በድጋሚ ከልብ እናመሰግናቹሀለን🙏🙏


ሸጋ ምሽት !!💚💛❤️

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
fre:👇👇
ሰላም ፍሬ ነኝ ፡፡ በህይወቴ አዎንታዊ ለውጥ ካመጡ መፅሀፍት
1.ብርቅርቅታ
2.ሌላ ሰው
3.ሀኖስ.....

የሆነ ቦታ የሚኖር የሆነ ሰው:👇👇
ሰላም ወንድም ስሜ ብርሃነ ይባላል በኔ ሕይወት ላይ ለውጥ ያመጡ እና ቢነበቡ የምላቸው መጽሐፍት እነዚህ ናቸው
👇👇👇
1, ጠጠሮቹ (ዳንኤል ክብረት)
2, የኔ ጀግና (ዳንኤል ክብረት)
3, የጥበብ መንገድ 1 እና 2 (ካህሊል ጂብራን)
4, ፍቅር እስከ መቃብር (ዶክተር ሐዲስ ዓ. )
5, እመጓ ፣ ዝጎራ (ዶክተር አለማየሁ ዋሴ)
6, ዮቶር/ኮብላይ ካህን/ (አለማየሁ ደመቀ)
7, ከጥቁር ሰማይ ስር (እንዳለጌታ ከበደ)
8, ከአሜን ባሻገር (በዕውቀቱ ስዩም)
9, እፎይታ/የትርጉም ሥራ/
10, መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ ( ፕሮፌሰር መስፍን )
11, የይሁዳ ድልድይ እና ሌሎችም ወጎች ፣ የአዋጁ ግዜ ምልክት ፍለጋ እና ሌሎች (ኤፍሬም ስዩም )
12, ግራጫ ቃጭሎች ፣ መረቅ (አዳም ረታ)

ⓜⓓ Ûnïquê β๑γ😜😜 ★★★:👇

ስሜ ማህዲ ቡሴሪ ይባላል፡፡
በህይወቴ ለውጥ ያመጡ መፅሀፎች ወይም የወደድኳቸው መፅሀፍት፡-
1, ህይዎትህን ተዳሳትባት
2, ሌዉጥ
3, ስኬት በ30 ቀን


Marti😉:👇👇👇
"ሌላ ሰው "እና "የተቆለፈበት ቁልፍ " ..በ ዶ.ር ምህረት ደበበ + " አለመኖር" ...በ ዶ.ር ዳዊት የተፃፉትን መፅሀፍቶች ሁሉም ሰው ቢያነባቸው በርግጠኝነት ብዙ ነገሮች ይማርባቸዋል...

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ሒዊ የ እናቷ ልጅ (Pomi):👇👇
ሒዊ የእናቷ ልጅ ነኝ
ሰላም ላንተ ይሁን ወንድሜ!
መፃህፍት የምንግዜም ምርጥ ጓደኞቼ ናቸው።
በህይወቴ ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ ያሳደሩብኝ መፅፍት ብዙ ናቸው ጥቂቶቹን እነሆ:-
1. የአና ማስታዎሻ
2. ፍቅር እስከመቃብር
3. ቆንጆዎቹ
4. ከአድማስ ባሻገር
5. እቴሜቴ የሎሚ ሽታ
6. ሁሉም የ ሙሀዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት መፅሀፍት
7. ሁሉም የ አቡነ ሺኖዳ መፅሀፍት
8. ሁሉም የ ይስምዐከ ወርቁ መፅሀፍት
9. እሳት ወይ አበባ (ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን)
10. ሁሉም የ አለማየሁ ዋሴ መፅሀፍት
.
.
.
ተጋበዙልኝ ብዙ ዕውቀት ትሸምታላችሁ።

Kiru:👇👇👇
ስሜ፡- ብሩክ ይባላል

እኔ ካነበብኩት የወደድኩት
☞ ብርቅርቅታ
☞ ሰመመን
☞ እመጓ፡ ዝጎራ.... እናንተም ብታነቡት እንደምትወዱት አምናለሁ

ֆɨʍօռ ֆȶǟʀӄ:👇👇👇
የኔ የምን ጊዜም ምርጥ መፅሃፍት.....
1.እፎይታ.....(ትርጉም)
2.ሌላሰው.....ዶ/ር ምህረት ደበበ
3.ቆንጆዎቹ.....ሠርቅ ዳ.
4.የቃየል መስዋእት.....ሠርቅ ዳ.
5.ሀዲስ.....በዓሉ ግርማ
...

Yidnekachew Bekele:👇👇👇
Yidnekachew ebalalew ene lay tetsino amititwal bye yemaminaw metsehaf bzu nachew ye Dr miherat debebe yetekolefabet kulfina lela saw principle and power of vision Myles munroe,yaltenore lijenat enagni qedami nachew gn kelay ye burqa zimita yetebalew alidegifawum mikneyatum gudatu yibezal lane qoshasha metsehaf new

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ፌደራላዊቷ የግጭት ሀገር !!

((( ከሚለው ተቀንጭቦ የቀረበ ))

አንዳንዱ ጅል ነው ልበል?! ሕዝቡ ለነፃነቱ ታግሎ <<ነፃነት >> መቻል አቃተው ይላል። ለ27 ዓመት የላሰው የጥላቻ መርዝ ቀላል አድርጓታል። <<የጨቆነህ ይሄ ነው፤ያደኸየህ ይሄ ነው፤አደንቁሮ በመሃይምነት ያሰረህ ያ ብሔር ነው፤ከመሬትህ ያፈናቀለህ፣ከባህልህ ያፋታህ ፣ከሌማትህ፣ ያገለለህ ያ ብሔር ነው !....>>

እየተባለ ሃያ ሰባት ዓመት የኖረ ሕዝብ ፣ ጨቋኙን ከዙፋኑ አሽቀንጥሮ ጣለ እንጂ ፣ መች ስጋት የነበረውን መርዝ አረከሰው ! ልቦናን ከጥላቻ መርዝ ማጽዳት ፣ አምባገነን ንጉስን ከዙፋን እንደማንሳት ቀላል አይደለም። ሁለቱ ለየቅል ናቸው፤ ንጉስ ማውረድ ጉልበትን፣ልቦናን ማጽዳት ስክነትን ይጠይቃሉ።አምባገነኑ ከዙፋኑ የለምና ጉልበታችንን ከጡንቻችን መልሰን እንስከን፤ ያለ ስክነት ልቦናን እንኳን ማጽዳት ማዳመጥም ይገዳል።

#በድሉ ዋቅጅራ (ዶ/ር)💚💛❤️

ምንጭ:- ዛሬ ከወጣችው ፍትህ መፅሔት ቅፅ 01 ቁጥር 03 ህዳር 2011ዓ.ም

ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ !!💚💛❤️

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ወግ ብቻ
👆👆👆👆👆 ወዳጆች እስቲ አንብበን ተፅዕኖ ያሳደረብን ፣ ደጋግመን ያነበብነው ፣ ሁሉም ሰው ሊያነበው የሚገባው መፅሐፍ ነው የምትሉትን አካፍሉን....... ሸጋ ጁምኣ!!!💚💛❤️ 👇👇👇👇 @balmbaras @wegoch @wegoch
Waiting...📞👮😎 Ewedshalew:👇👇👇
Yidnekachew Lakew፦ Ebalalew lane be hiwete tetsino asadrewal yemlachew metsaf bzu nachew kenesu be tikitu። 1፦Papilon(ፓፒዮ)
2፦ ብርቅርቅታ እና የሪስኮቭኪ መፃፎች ናቸው

Dagi:👇👇
ስሜ ዳግም አስቻለሁ ይባላል በህይወቴ ለውጥ መፅሃፎች እና አዝናንተው እውቀትን እንድይዝ ያደረጉኝ መፅሀፎች
ሌላ ሰው,የተቆለፈበት ቁልፍ,ምንዱባን,ፓፒዮ,ክቡር ድንጋይ እና በጣም አስቆኝ ሁኔታዎችን እንድታዘብ ያደረጉኝ ሁለት መፅሀፎች እኔና ቹ(ፍስሀ ያዜ) ከከአሜን ባሻገር(በእውቀቱ ስዩም)

Zazza girl:👇👇
1,fenta
2,doctor Ashebr
3,alemenor

ሁላችሁንም እጅግ በጣም እናመሰግናለን ......ለላካችሁልን በሙሉ....እስካሁን የተላኩት በቂ ናቸው !!

@wegoch
@wegoch
ታሪከኛው ሰይድ ሚሊሻው ዛሬ ከስብሰባ በሃላ አብይን ጠጋ ብሎ ምን ቢለው ጥሩ ነው???
""" ጉድ በል አብይወይ!!! እኔ መቼም ዛሬ ተወሎ ስገሰግስ የመጣሁት አንተን ልመርቅህ ፣
ዱኣ ላደርግልህ ነው!!!! ግን እንደው አየለ ጫሚሶ የሚባል የውሎአበል መጋኛ ምን አባቱ
ሊያደርግ ነው የመጣው???
አብይወይ ስለ አየለ ጫሚሶ የገጠምኩት ግጥም አለኝ አፈር ስሆንልህ አድምጠኝ አለና
ቀጠለ፤
መራራ እንደ ኮሶ ፤
በጭባጭ እንደ በሶ ፤
ጥቁር መነጥር ለብሶ ፤
ይህ በረባሶ ፤
ዘፈኑ ካሊብሶ ፤
ወንድሙ አስፋው ጃርሶ ፤
ሊወስደው ነውና አበሉን ጨርሶ ፤
ክንፉ ይርገፍና ፤
ክንፈ ጋር ይደብለቅ አየለ ጫሚሶ ።

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
“ለሰጠውም አላሳነሰው ላልሰጠውም
አላቀመሰው!”
በድሮ ጊዜ አንድ አንቱ የተባሉ አገረ ገዢ፣ በየክፍለ ሀገሩ እየተዘዋወሩ፣
ህዝቡን እየሰበሰቡ፣ ያነጋግሩ ነበር ይባላል፡፡ አብረዋቸው አዋጅ ገላጮች
ነበሩ፡፡ አዋጅ ገላጮቹ በታወጁ አዋጆች ላይ ጥያቄ ቢነሳ የሚያብራሩ
የሚገልጡ ናቸው፡፡
ህዝብ ከተሰባሰበ በኋላ፣ ባለሟሉ ይነሳና፤
“የአገራችን ህዝብ ሆይ! አገረ ገዢው እዚህ ድረስ የመጡት የእናንተን
ማናቸውም ብሶት ሊያዳምጡ ነውና ጥያቄያችሁን አቅርቡ” ይላል፡፡
አንዱ ባላገር ይነሳል፡-
“ጌታዬ የግጦሽ መሬት አንሶናል” ይላል
አገረ ገዢው ወደ ፀሐፊው ዞረው፤
“ይመዝገብ፡፡ እናስብበታለን”
ሌላ ባላገር ይነሳል፤
“ማዳበሪያ ይሰጣችኋል ተብለን እስከ ዛሬ አልመጣልንም!”
አገረ ገዢው - “ይመዝገብ፡፡ እናስብበታለን”
ሌላ ባላገር ይነሳል - “የዘር እህል ይታደላል ተብለን ዛሬም አልተሰጠንም”
አገረ - ገዢው - “ይመዝገብ፡፡ እናስብበታለን”
ሌላ ባላገር በንዴት፤
“ጌታዬ! ባለፈውም እንዲሁ እናስብበታለን ሲሉ ነበር፡፡ መቼ ነው በተግባር
የሚፈፀምልን? ሁሌ እናስብበታለን ነው እንዴ?”
አገረ - ገዢው - “ይሄም ይመዝገብ፡፡ እናስብበታለን!”
ይሄ በጣም ያናደደው አንድ የጎበዝ - አለቃ፣ አገሬውን በመወከል ይናገራል፡፡
“ጌታዬ ሆይ! በእኛ ላይ የደረሰውን በደል የሚያህል የትም አገር አይገኝም!
ፍትህ ሲጠፋ አቤት የምንልበት ቦታ የለም! ጤና ሲጠፋ የምንታከምበት ቦታ
የለም! ትምርት ሲጠፋ የምንማርበት ቦታ የለም፡፡ መንገዱ ሲጠፋ አሳብረን
የምንሄድበት አቋራጭ እንኳን የለም፡፡ እህል ሲጠፋ አንጀታችንን
የምንጠግንበት፣ ውሃ ጥም ስንቃጠል ጥማችንን የምንቆርጥበት ምንም
መፍትሄ የለንም! አሁን እናንተ፤ እያስተዳደርን አገር እየመራን ነው ትላላችሁ?
እኛ ህዝቡን ማስነሳትኮ አላጣንበትም! እናንተም ደግ ደጉን አርጋችሁልን፣
እኛም ደግ ደጉን አስበንላችሁ ብንኖር አይሻልም?” አለ፡፡
አገሬው አጨበጨበ!
አገረ ገዥውም፤
“የአገሬ ህዝብ ሆይ!
ይሄ የጎበዝ አለቃ ጥሩ ይናገራል፤ ግን ዕድሜ የለውም!” አሉ
አገሬው አሁንም አጨበጨበ!
ያ ጎበዝ - አለቃም ከዚያን ቀን በኋላ አልታየም፡፡
***
ሁልጊዜ “እናስብበታለን” አያዋጣም፡፡ አፈፃፀም ያስፈልጋል፡፡ በዘመንኛው
ቋንቋ ቢሮክራሲያዊ ማነቆ (Bureaucratic red - tape) መበጠስ አለበት
እንደ ማለት ነው፡፡ ጥንት ንጉሡ የወሰኑትን አስፈፃሚዎቹ ባለሟሎች፤ “እሺ”
“እሺ” እያሉ በተግባር ግን አንዷንም ነገር አያውሉም ነበር ይባላል፡፡ ይሄ
ክፉኛ ያቆሰለው በደለኛ ንጉሡ ዘንድ ይቀርብና፤
“ጃንሆይ! ሁሉም ነገር ይቅርብኝና አንድ ሃያ አጋሠሥ ይሰጠኝ” ሲል አቤት
ይላል፡፡
ጃንሆይም “ለምንህ ነው?” ቢሉት፣
“የሸዋን መኳንንት ‹እሺታ› የምጭንበት”፣ አለ ይባላል፡፡ ውሳኔዎች፣
መመሪያዎች፣ አዋጆች፣ ወዘተ በሥራ ላይ ካልዋሉ፣ ካለንበት ንቅንቅ
አንልም፡፡ ጌቶች ቢያስነጥሱ መሀረብ የሚያቀብሉ ዓይነት ሰዎች መቼም፣
የትም ድረስ አያራምዱንም! ጉዳያችሁን ተናገሩ፡፡ ብሶታችሁን አውጡ፡፡
ጥያቄያችሁን አቅርቡ፤ ብሎ ‹እድሜህ አጭር ነው› ከሚል ይሰውረን፡፡
ለአጥቂውም ለተጠቂውም ከሚያጨበጭብ ተሰብሳቢም ይሰውረን፡፡
ያልተመለሰ ጥያቄ ያልተከፈለ ዕዳ ነው፡፡ ነገ ዋጋ ያስከፍለናል፡፡ ዛሬ
አድበስብሰን የምናልፈው ጥያቄ፤ የነግ የቂም ቋጠሮ ይሆንብናል፡፡ ያ ደግሞ
ዕድገትን ተብትቦ ያሰናክለዋል፡፡ የበላይ ወደ ታች የሚመራውን፣ የበታች እንደ
“ኮምፒዩተር ጌም” ሲጫወትበት የሚውል ከሆነ፤ እንኳን ትራንስፎርሜሽን
መደበኛውም ዕድገት አይገኝም፡፡ “ሩቅ አሳቢ ቅርብ አዳሪ” መሆን
የሚመጣው፣ ለትልቁ ስዕል አስተዋፅኦ የሚያደርጉት ትናንሽ ስዕሎች በቅጡ
ካልተሳሉና ሥጋና ደም ሳይለብሱ የቀሩ እንደሆነ ነው፡፡ የበታች አካላት
ማያያዣ ክር ናቸው፡፡ እነሱ ከተበጣጠሱ የበላይ አካላት የሉም፡፡ ይሄ
በቢሮክራሲያዊው ዓለም ብቻ ሳይሆን በፖለቲካ ፓርቲዎችም ዘንድ ያው ነው፡፡
ትናንሽ ስህተቶች ለግዙፍ ስህተት አሳልፈው ይሰጡናል፡፡ ያኔ ውድቀት ቅርብ
ይሆናል፡፡
ሱን ሱ የተባለ የቻይና ጦር መሪ “በጦርነት ድል ማድረግ የሚደጋገም ነገር
አይደለም፡፡ ሁሉ ቅርፁን ይለውጣል፣ ውሃ ሁሌም አንድ አይነት ቅርፅ የለውም
- እንደ መያዣው ዕቃ ይለዋወጣል፡፡ እንደ ባላንጣህ አካሄድ ቅርፅህን
እየለዋወጥክ ድል መቀዳጀት ረቂቅ - ሊቅ (genius) ይባላል” ይለናል፡፡ ስለ
ህይወት፣ ስለ ማናቸውም ትግል፣ ስለ ምርጫ፣ ስለ ለውጥ ስናስብ ሁሌም
እንደ ሁኔታው አካሄድን ቀይሮ በብስለት መጓዝን አንርሳ፡፡ ረቂቅ - ሊቅ
የመሆን ጥበብ ይሄ ነው፡፡ በሌሎች ድክመት ላይ ከመንተራስ በራስ
መተማመን ብልህነት ነው! አንዴ የሆነው ነገር ላይ ከማላዘን ይልቅ
ሁኔታዎችን በሌላ አቅጣጫ ለመለወጥ (Reversal) መሞከር አዲስ ቅያስ
ለማየት ይጠቅመናል፡፡ ሳይታለም የተፈታን ጉዳይ (de facto) ደግመን
ደጋግመን መወትወት ያው ውሃ ወቀጣ ነው፡፡ የተሰረቀው ተሰርቋል፡፡
የተሄደው ድረስ ተሄዷል፡፡ የባላንጣችን አቅም ታውቋል፡፡ ዘዴና መላው
በተደጋጋሚ ታይቷል፡፡ ስለዚህ የታወቀን መንገድ ትቶ፣ ያልተሄደበትን መንገድ
ወይም ብዙ ያልተሄደበትን መንገድ (The Road Less Travelled)
ማሰብና ማስላት ይሻላል፡፡ የሆነውማ ሆኗል - “ለሰጠውም አላሳነሰው፣
ላልሰጠውም አላቀመሰው!”

ምንጭ:- አዲስ አድማስ ጋዜጣ

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ብሔራዊ ጀግና💚💛❤️

የአንድ ሀገር የፓለቲካ ሁኔታ ሲበላሽ ሌባ እንደ ጀግና ይቆጠራል ። ሀገር አፍራሽ ጀግና ይባላል። በመሠረቱ ብሔራዊ ጀግና ማለት የራሱን ጥቅም ትቶ ፤ ያለፈውን የሀገር ታሪክ አስጠብቆ ፤ የዛሬውንና የነገውን መንገድ ብሩህ የሚያደርግ ነው። ጀግና ትሁት ነው ፤ ከራሱ አልፎ ለሌሎችም ከዚያም አልፎ ለመጪው ትውልድ የሚያስብ ነው ጀግና የሚባለው።

ኢትዮጵያ ጀግኖች ነበሯት። እንደ አብነ ጴጥሮስ ያሉ ለእምነታቸው፣ለወገናቸው ለሀገራቸው ሲሉ መከራን ለመቀበል የቆረጡ የመንፈስ መሪነት የተላበሱ ብሔራዊ ጀግኖች ነበሩ። ጀግንነታቸው በጊዜ ሂደት ዋጋ ያጣል የማይባል ነው። አንዲት ሀገር በመቶ ዓመታት ውስጥ አንድ ብሔራዊ ጀግና ካገኘች የታደለች ናት። ኢትዮጵያ አድዋ ላይ የጥቁር ህዝብ ነፃነትን የፈነጠቀ ድል ያስመዘገቡ ጀግኖች ሀገር ናት። ይህን ድል የመሩት ዐጤ ምኒሊክ ብሔራዊ ጀግናችን ተብለው ብቻ አይገልጹም፤ የጥቁር ህዝብ ኩራት ናቸው። ምኒልክ ለጀግና ከተቀመጠው ትርጉም አንፃር፤ ከፍ ያሉ ብሔራዊ ጀግና ናቸው።

ብሔራዊ ጀግኖች በህይወት ሳይኖሩም፤በስራቸው ህያው ሆነው አቅጣጫ አመላካች ናቸው። ዐጤ ምኒልክ ፣ እቴጌ ጣይቱ ፣ አሉላ አባ ነጋ፣ፊትውራሪ ገበየሁ ፣ ባልቻ አባነፍሶ እና ሌሎችም የአድዋ ድል ያስመዘገቡ ኢትዮጵያን በሰሯቸው ብሔራዊ ጀግና ሆነዋል።

ፓለቲካውን በጥላቻ የሚሰሩ ቡድኖች ዐጤ ምኒሊክን እና ተከታዮቻቸው የነበሩትን ጥላሸት ሲቀቡ እና ሊያቃልሉ ሲሞክሩ ይስተዋላሉ። ይህ የትውልዱን ሞራል እና የሀገር ፍቅር ስሜቱን ዝቅ ማድረግ ነው። ምኒሊክ በጦር ሊወጓቸው የተነሱትን ርህራሄ ያልነፈጉ ሰው ነበሩ። ይህንን በአርዓያነት ልንከተለው የሚገባ እንጂ ልናጣጥለው መድፈር አይገባንም። ጀግንነታቸው እሴታችን ነው። ዐጤ ቴድሮስም በራዕያቸው ብሔራዊ ጀግናችን ሆነዋል።

በአጠቃላይ፣ ኢትዮጵያ በታሪኳ ብሔራዊ ጀግኖች እንደነበሯት መካድ አይቻልም። ሆኖም አሁን ላይ እንደ ቀደሙት ከፍ ያለ ቦታ የምንሰጣቸው ብሔራዊ ጀግኖች የሉንም። በበኩሌ፣ በዚህ ወቅት አሉን የምንላቸው ጀግኖች ፣ ብሔራዊ ጀግኖቻችን የመሆን ደረጃ የደረሱ ናቸው ለማለት እቸገራለሁ።

በሌላ በኩል ፣ ብሔራዊ ጀግኖቻችን እንደ ነቀዝ ታሪካቸውን የመቦርቦር ስራ ይስተዋላል። ይህ አሳፋሪ ብቻ ሳይሆን ፣ ትንሽነትም ነው። ብሔራዊ ጀግኖቻችን የሚከተል፤አርዓያነታቸውን ለበጎ ሥራ መነሻነት የሚጠቀም ትውልድ ነው ሀገር የሚገነባው። ጀግናን ማንኳሰስ ጀግንነትን መሸሽ ነው። የአሁኑ ትውልድ ያለፉትን ጀግኖቻችን አለማክበርና ላነሰ ተግባር መሰለፍ፤ <<ወይራ ዶግ ይወልዳል >> እንደሚባለው ከአያት እና ቅድመ አያት ማነስ ይሆናል። ያለፈውን ያለፈውን ጉልህ አስተዋጽኦ በመካድ ወደፊት መራመድ አይቻልም። በለጸጉ የሚባሉ ሀገራት ህዝቦች ብሔራዊ ጀግኖቻቸውን ሲያከብሩ ነው የሚታዮት። የጀግኖቻችን ምልክት ስንከተል ነው ራዕይ የሚኖረን። ካለፋት ጀግኖች የተሻለ ታሪክ ለማስመዝገብ ሥራዎቻቸውን እውቅና ሰጥተን መመርመርና ለመማር ዝግጁ መሆንንን ይጠይቃል።

((( ዶ/ር ባይለኝ ጣሰው ))

ምንጭ:- ኢትዮጲስ ጋዜጣ ቁጥር 10 ኀዳር 16 ቀን 2011 ( ተቀንጭቦ የቀረበ )
---------------------------------------------------


የኛስ ትውልድ የሚያስማሙን ብሔራዊ ጀግኖች አሉት..? እነማን..?

ብሔራዊ ጀግናቹን አስተዋውቁን ህይወታቸው የሚማርከን አገልግሎታቸው ቀልባችንን የሚገዛው፤ትግላቸው ወይ ብልሀታቸው በፈለጋቹት መስፈርት ሊሆን ይችላል #የኔ ብሔራዊ ጀግና ብለን ልዩ ስፍራ የሰጠናቸውን ግለሰቦች አስተዋውቁን

#እንደማሳሰብያ
1 የጀግናችንን ማንንነት
2 ያበረከቱት አስተዋፆ
3 በጥበብ ያለፉትን መሰናክል
4ያሳለፉትንት ፅናት ወይም መከራ
5 ያላቸው ብቃት
6.ወ.ዘ.ተ......ቢዘረዘር ስለ ብሔራዊ ጀግኖቻቹ ያለን ምስል ሙሉ ይሆናል

#እየጠበቅናቹ ነው !!!!!

ሸጋ ሸጊቱ ምሽት 💚💛❤️

👇👇👇👇
@balmbaras
@Lula_al_greeko
@wegoch
@wegoch
(ዮሀንስ ደጉ)

ድሮሮሮሮ

ሐበሻ ሆነህ ዮኒቨርስቲ ከገባህ ያመልኩሃል፡፡ ያጨበጭቡልሃል፡፡ ያደንቁሃል፡፡ ጀለስካዎች ይቀኑብሃል፡፡ ጸዴ፥ የተማረች፥ የተቀሸረች ቸከስ ትጠብሳለህ፡፡ ላይፍ ይገባሃል፡፡ ራስህን ትችላለህ፡፡ ሰው አያነብልህም፡፡ በአውራ ጣትህ አትፈርምም፡፡ ፈረንጅ ማውራት ትችላለህ፡፡ ፖለቲካ ታውቃለህ፡፡ የመንግስት ስራ ትይዛለህ፡፡ ኮት ትገዛለህ፡፡ ምናምን ምናምን ብለው ያስባሉ፡፡
ቤተሰቦችህ ደረታቸውን ይነፋሉ፡፡ እህቶችህ የመጠበሻ ክላሳቸው ከፍ ይላል፡፡ ወመኔው ወንድምህ በስምህ ተበድሮ ያጨሳል፡፡ የሰፈሩ ቅያስ በስምህ ይጠራል "ያ ዮኒቨርስቲ የገባው ጨዋ ልጅ ቤት ጋ" ምናምን ነገር፥ የሰፈሩ ሼባዎች ያከብሩሃል፥ ወመኔ ጀለሶችህ በሹክሹክታ ያሙሃል፥ የተለየ ወጥ ይሰራልሃል፥ ትኩስ እንጀራ ይቀርብልሃል፡፡ ትከበራለህ፡፡
የዋለልኝን አርቲክል ታነባለህ፡፡ ጥላሁን ግዛው ይናፍቅሃል፡፡ መንግስትን ትጠላለህ፡፡ ቦርጫም ቢሮክራት ይደብርሃል፡፡ ፀጉርህን ታጎፍራለህ፡፡ ፂም ይኖርሃል፡፡ ፍልስፍና፥ ታሪክ፥ ፖለቲካ፥ ትንሽ ሳይንስ ትለበልባለህ፡፡ ትከራከራለህ፡፡ በካሴት ሙዚቃ ትሰማለህ፡፡ ሲጋራ ታጨሳለህ፡፡ ወሬህ ፀዴ ይሆናል፡፡ አይዲያሊስት ሆነህ ቁጭ ትላለህ፡፡ ምድር ላይ ገነት ትፈልጋለህ፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ባንተ ትግል ነፃ እንደሚወጣ ታምናለህ፡፡
ትመረቃለህ፡፡ በት በት ብለህ የመንግስት ስራ ትይዛለህ፡፡ ቤት ትከራያለህ፡፡ ኮት ትገዛለህ፡፡ መፃህፍት ይኖሩሃል፡፡ መንግስትን በጎሪጥ ታያለህ፡፡ እሱም ይገላምጥሃል፡፡ ሲመሽ ቢራ ትጠጣለህ፡፡ መንግስትን በሹክሹኩታ ታማለህ፡፡ መኖር ትጀምራለህ፡፡ ለናትህ ሻሽ ትገዛለህ፡፡ ለአባትህ የጠጅ መጠጫ ትሸጉጣለህ፡፡ ጨረቃን በገመድ ለማውረድ እንደሞከርክ ይገባሃል፡፡ ኒያላ ለኩሰህ ከት ብለህ ትስቃለህ፡፡ ታገባለህ፡፡ እናትህን አያት ታደርጋለህ፡፡ ሰፈሩ ለሚያሰራው መንገድ ሊቀመንበር ትሆናለህ፡፡

ዛሬሬሬሬሬሬ

በእድል ትገባለህ፥ ትኮርጃለህ፥ ወይ ትንሽ ታነብ እና ትገባለህ፡፡ አንዱ ክልል ይወረውሩሃል፡፡ ጉዳይህ አይደለም፡፡ ግቢ ትደርሳለህ፡፡ የሆነ ቋንቋ የሚያወሩ ቢጤዎችህ ይቀበሉሃል፡፡ ያወሩሃል፡፡ ጠላትህን ያሳዩሃል፡፡ ፌሮ የሚቀመጥበትን ቦታ ታያለህ፡፡ ፋራሽህ ስር ቆመጥ ትቀረቅራለህ፡፡ ይሄን ለምን እንደምታደርግ አታውቅም፡፡ አጠይቅም፡፡ አያገባህም፡፡
የሆነ ትምህርት ትጀምራለህ፡፡ ሲመችህ ታነባለህ፡፡ ብዙ ስለማይመችህ አታነብም፡፡ ሌክቸር ያመልጥሃል፡፡ ትናንት ከጀለሶች ጋር አዳር ስለጠጣህ ደክሞሃል፡፡ ትተኛለህ፡፡ ህንዱ ሰውዬ ስለሚደብርህ ከሰዓት ትቀጣዋለህ፡፡ ፈተና ይደርሳል ትፈተናለህ፡፡ እናትህ ስልክ ተውሳ ትደውላለች፡፡ ትንሽ መላ ትቀፍላታለህ፡፡ በሶስተኛው ቀን ይደርስሃል፡፡ ይቃማል፡፡ ይጠጣል፡፡ ቸከስ ትመቻቻለህ፡፡
ቋንቋህን የሚያወራ፥ ጥብቅ ያለ ጨርቅ ሱሪ የለበሰ፥ የተወጠረ፥ አጭር፥ ደማቅ ካናቴራ ያደረገ መንጋ ይከብሃል፡፡ ውሎህ እዛው ነው፡፡ በቋንቋ ተደራጅተህ ትኮርጃለህ፡፡ ታስኮርጃለህ፡፡ ሽመል ይዘህ ትፋለማለህ፡፡ አታነብም፡፡ አትመረምርም፡፡
የእናትህ ሐሳብ ልጄ በየትኛው ብሔር ሽመል ይሞታል የሚል ነው፡፡
ሲኒየር ስትሆን አዲስ ጅንስ ትገዛለህ፥ ጫማ ትቀይራለህ፥ ያንተን ቋንቋ የምታወራ ሴት ትፈልጋለህ፥ በቋንቋህ ሙዚቃ ትሰማለህ፥ የብሔር ፀብ ትሳተፋለህ፡፡ ሙዚቃ፥ ፍልስፍና፥ ሐሳብ፥ ክርክር፥ ሳይንስ አይገባህም፡፡ እየተፋለምክ ትመርቃለህ፡፡ ባንተ መመረቅ ማንም አይገረምም፡፡ መመረቅህን ስታውቅ የራስህን ባዶ ጭንቅላት ይዘህ ትስቃለህ፡፡
ኒቼ፥ አውግስቲን፥ ፕሌቶ፥ ቮልቴር፥ ከበደ ሚካኤል፥ ገ/ህይወት ባይከዳኝ፥ ምናምን ምናምን ላንተ ምንም ናቸው፡፡ የአንተን ቋ ንቋ አያወሩም፡፡ ካንተ ብሄር አይደሉም፡፡ ላንተ ትልቁ ሰው ጃዋር፥ ቬሮኒካ፥ ሚኪ አማራ....ምናምን ናቸው!

'ውነቴን ነው የምልህ አንተን ሳስብ ኤሊ እየጋለብኩ ወደሰማይ መብረር ያምረኛል!😂😂😂
@wegoch
@wegoch
@yeyhudaanbesa
ወግ ብቻ
ብሔራዊ ጀግና💚💛❤️ የአንድ ሀገር የፓለቲካ ሁኔታ ሲበላሽ ሌባ እንደ ጀግና ይቆጠራል ። ሀገር አፍራሽ ጀግና ይባላል። በመሠረቱ ብሔራዊ ጀግና ማለት የራሱን ጥቅም ትቶ ፤ ያለፈውን የሀገር ታሪክ አስጠብቆ ፤ የዛሬውንና የነገውን መንገድ ብሩህ የሚያደርግ ነው። ጀግና ትሁት ነው ፤ ከራሱ አልፎ ለሌሎችም ከዚያም አልፎ ለመጪው ትውልድ የሚያስብ ነው ጀግና የሚባለው። ኢትዮጵያ ጀግኖች ነበሯት። እንደ…
@nti:👇👇👇👇
በመጀመሪያ ጽሁፉ መሳጭ እንደሆነ ልገልፅ እወዳለው።

በመቀጠል የኔ ብሄራዊ ጀግና #ቴድሮስ ካሳሁን(ቴዲ አፍሮ) ነው።እሱን የማያቀው አለ ብሎ መለት ዘበት ይሆንብኛል።

ምን አልባት ብሄራዊ ጀግና አርጎ መቀበሉ ላይ እንጂ ማንነቱን በማወቅ
እንኳን እኛ የሀገሩ ልጆች ቀርተን ብዙ ጠጉረ ልውጦችም እንደማይደናገሩ
ጥርጥር የለኝም።

#ቴዲን ለመውደድና ብሄራዊ ጀግና አርጎ ለመቀበል ያረገውን አስተዋፆ፣
ያለፈውን ነገር ሆነ የሰራቸውን ስራ መዘርዘሩ ቀላል ስላልሆነ ከመዘርዘዘሩ
ይልቅ ብዙዎቻችን ልብ ያላልነውን አንድ ነገር ጠቅሼ ልለፍ።

ተወዳጅ እና ብዙዎች የሚያከብሩት አርቲስት መሆኑ ግልፅ ነው። ቅዱሱ መፅሀፍ"ነብይ በሀገሩ አይከበርም"ይላል።ነብይ ማለት ሰለሚሆነው ነገር
አስቀድሞ የሚተነብይ ሰው ማለት መሆኑ ካስማማን #ቴዲ ዛሬን በተስፋ
መነፅር ትላንት ላይ አሻግሮ እያየ ትንቢት በሚመስሉ ግጥሞች ግልፅ እና
ግልፅ በሆነ መንገድ አድርሶናል።

ትንቢት ትንቢትነቱ አፈፃፀሙ ላይ የሚያስማማን ከሆነ "ዳህላክ"ን የሰማ
ማንኛውም ሰው"ሀገሩ ለይ የተከበረ ብቸኛው ነብይ ነው"ብል ሚቃወመኝ
ይኖራልን? አይመስለኝም።

እውነተኛ ብሄራዊ ጀግና ያለፈውን ታሪክ አስጠብቆ የዛሬውን ታሪክ ደሞ
ለነገዎቹ የነገ ባለቤቶች ሚያስቀመጥ ነው ካልን፤ያለፈው የኢትይጵያችን
ታሪክ ከታሪክ ፀሀፊዎቿ ይልቅ በወቅቱ የፖለቲካ አየር ከመታጠን እና ታሪክን
ከመበረዝ አባዜ ተላቆ አቅሙ በፈቀደው መጠን ከሩቅ ሆነው ስለጮሁ ብቻ
ለውጥ ያለ ከሚመስላቸው በተቃራኒ ከሁኔታዎች አጠገብ ሆኖ እሚጋፈጥ
ጀግና ካለ በእርግጠኝነት #ቴዲ አፍሮ ነው ማለቱ ስህተተኛ የሚያስብል አ-ይመስለኝም።

ስለሱ ይህ በቂ ባይሆንም የብሄራዊ ጀግና አርጎ ለመቀበል ግን ከበቂ በላይ
ምክንያት መሆኑ የሚያስማማን ይመስለኛል።

Anteneh Tesfaye

እስካሁን የተሳተፈው ሁለት ሶስት ሰው ነው....የኛ ትውልድ ብሐራዊ ጀግና የለውም ማለት ነው??! .....የሚያስማማን ማለት ነው...? ወይስ ምንድነው..?

@balmbaras
@Lula_al_greeko
@wegoch
@weoch
ያልተኖረ ጸጋ ከመጥፋት አያድንም!!
--------
ይሄ አገር ጸጋው ብዙ ነው፥ የጸጋና በረከት መናጃ "እርግማኑም" አያል ነው። የተሰጠህ ጸጋ
የቱንም ያክል ቢበዛ እሱን መሸከሚያ ጫንቃና ዘመን ማሻገሪያ አስተውሎት ከሌለህ ወርቁ
ሁሉ ጨርቅ ነው!! በረከቱ ሁሉ እርግማን ነው።
--------
ያቺ ጽላት የበረከትና የእውነት መንገድ ክትብ ሆና ለሙሴ ስትሰጠው ለአማኙ ሁሉ ብርሃን
ትሆን ዘንድ ነው። የበረከትና እምነት ትርክቱን ያልኖረ ህዝብ በጸጋው አይኖርም፥ ከጸጋው
አይጠቀምም።
የአንድ ህዝብ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ምሪተ-ውቅር ከቆየ መልካም እምነቱና እውነቱ
ካልመነጨ ያ ህዝብ ወደ ፊት ከቶ አይሄድም፥ ቢሄድም ድክድክ ነው።
"ጽላቱ" ያላስታረቀውንና አንድ ያላደረገውን አንድ ህዝብ፣ አተልቆ መጉረሻ የማፈኛና
መዝረፊያ # ህገ_መንግስቱ እንዴት እጅ ያጣባዋል? ከስር ፈርሶ ከላይ ይገነባልን? ፍጹም።
-----
ለበረከትና እውነት ከሩቅ ምእመኗን የምትጣራ አክሱም ከብብቷ ስር የተወሸቁ የጥፋትና
ጭቆና መንገድ አሳማሪ "መናፍቃንን" ስለምን አይናቸውን አትከፍትም፥ ልባቸውን
አታገራም? ወደ በረከቷና እውነቷ ጽላት መገኛ ከሩቅ የሚተሙ ምእመንስ ስለምን በዛች
ከተማ ያሉ ወንድሞቻቸውን በበጎ አልተመለከቱም?? እመነት ልብን አይመራምን?
-------
ይሄ አገር አሰራሩ ብዙ ነው፥ በጎዎችም ብዙ ናቸው፥ ይሁን እንጂ ጥቂት አጥፊዎች
መልካም ዱካቸውን ሲንዱት ለምን አይሉም!! አብረው ሊጠፉ ዝምምም ይላሉ።
የዚህችን አገር ህዝብ በበጎ የሚያቆራኘውና የሚያቀራርበው ጸጋ ብዙ ነው፥ የጉልበቱ
ብክነት ግን በሚለያየው ነው። አሁንም እላለሁ ይሄ ህዝብ ሃይማኖተኛ እንጂ እምነቱንና
ሰውነቱን እየኖረ አደለም!! አክሱምን መሰል ጸጋ ያዙኝ ይላል፥ ኑሩኝ ይላል!!
በመዳኛው ቀየ አጥፊዎች ቢያይሉ ጸጋው እርግማን ነው። "አክሱም የክርስቲያኖች
የበረከትና የእውነት ትእዛዛት እንብርት ናት" ካልን አክሱም የሁሉም ነብስ መጠጊያ ጥላ
ናት። የራሷን ሰው በጎውን "መሃመድን" አትገፋም፥ "ትእዛዛቱን አልከተልም" ያለን አማጺ
አገር በታኝ የራሷን ልጅ "ጌታቸው አሰፋን"አታስጠጋም። እሷንም ያመኑ በእሷ ያለውን
በረከትና የእውነት መንገድ ይከተላሉ። በጎ እምነት በህዝብ በጎ ግብር ይገለጻል፣ ፖለቲካና
ማህበራዊ መስተጋብርም በህዝብ አቋቋም ቅርጹ ይወሰናል!!
---------
ሃገሬ ድንቅ ናት! ከነገ ተስፋ አልቆርጥም!!
የተሰጠህን ጸጋ ካልኖርከው ከመጥፋት አያድንህም!

((( ያሲን መሀመድ )))💚💛❤️

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
የወሎ ምልክት!!!!!
ወሎ ከሚሴ ላይ በአንድ የግል ድርጅት ውስጥ በጥበቃ ስራ ላይ ያገኘሃቸው ይህ ግርማ
የለበሱ ሽማግሌ ወሎየ እንዲህ ተናገሩኝ """ ወሎየነቴን የሚነካብኝ ከሾይጣን ለይቼ
አላየውም ፤ እንኳን በውጅግራ በጥርሴም አይተርፈኝ..." ባሉኝ ጊዜ የወሎየነት ቀልቤ
ይገማሸርብኝ ጀመር። የነገሩኝን አስገራሚ የወሎየነት ውህድ የትውልድ ግንዳቸውንና ስለ
ወሎየነት ህያው ማንነት ያወጉኝን ሁሉ record አድርጌያለሁ ። ሰሞኑን አጋራችሃለሁ ።
ወንዛችን ቦርከና ፤ እርሻችን ታች ቃሉ ፤
የወሎየን ፍቅር ፤
እንኳን ያደም ልጆች ፤ ወፎቹም ያውቃሉ ።
መገን ጃኖ ሙሄ ፤
መድሃኒቴ እኮ ናት እንደዳማ ከሴ ፤
ባይሆን ተቸገርኩኝ ፤
ቤቷ ጨፋ ሆኖ ፤ አልጋዋ ከሚሴ ።
አገሯ ወሎ ነው ፤ ደወይ ራህማቶ ፤
ልዘይር እያለ ፤
ሁሉም ቀልጦ ቀረ ፤ ከማጀቷ ገብቶ ።
በአንቻሮ በገዳም ፤
ከደሜ የገባች ፤ አንዲት ኮረዳ አለች ፤
ከረሚሌ ዳማ ሽቱ ብሬ እያለች ፤
ይሻለኝ እንደሆን ፤
ይቀለኝ እንደሆን ፤
በደዋ በጨፋ ፤አምጡ ፈልጋችሁ ፤
አልከጀለች እንደሁ ፤
አውጧት ከገላየ ሞኝ ባገይ ቀዳችሁ ፤
ካቲማየ ፈርሶ ፤
ጅስሜ ተደባልቆ እንዳልሞትባችሁ ።
ቲባል አልሰማህም እንዴ???? አሉኝና መላ ጅስማቸው እንደ ማለዳ ጠሃይ ይፈካ ጀመር....
እወደው አንተ ልጅ ቀርቶብሃልሳ..... ንግግሬን ትቀዳኝ ከጀልክ እንዴ.... ምን ገዶህ አየዋ....
እንኳን አንተ ስንቱ ጮሌ ቀድቶናል.... ና ቅዳኝ አቦ.... አህላቄ እንደ ቦርከና ነው.... ቢቀዱኝ
የማላልቅ..... ሽማግሌው አስደመሙኝ... መገን አንደበት.... መገን ዛትና ሙሃባ....እነየ
እነየ....

((( ጃ ኖ )))💚💛❤️

ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ ትሁንንልን!!💚💛

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
በተመጣጣኝ ዋጋ የሚፈልጉትን ነገሮች ለገበያየት 👇
@onlinesaleandbuystore
@onlinesaleandbuystore
@onlinesaleandbuystore
@onlinesaleandbuystore
@onlinesaleandbuystore
@onlinesaleandbuystore
@onlinesaleandbuystore
🛑የሌለን የለም ብቻ ነው!
JOIN ብለው ቤተሰብ ይሁኑ ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAEPkyxEP1snCoAkFGw
ሰፈራችን ዝነኛ ከሆነው ትልቁ ድንጋይ ላይ አራታችንም ተቀምጠናል አንዳንዴ ሳስበው ይሄን ድንጋይ የአራት ኪሎው መንግስታት ቢያዩት ለዙፋን ወስደው ወራጁም አውራጁም በተቀመጡበት ነበር ነበር ነው። አልሆነም
 ባይሆን ይሄ ድንጋይ ቦቸራ ሁለት ሠው ገሎ የታሠረው ምርሹ አጎቱን ወግቶ የጠፋው ብቻ ብዙ ብዙ ክቡር አደገኛ ቦዘናት መንበራቸው ነበር ነበር ነው።
አራታችንም ፊት ለፊታችን ወደ ቆመው አይደክሜው #ኑራሰን ምስጠት ውስጥ ነን
" መጀመሪያ ፒያሬ ብሎ አንገቷን አንገቱ ውስጥ ውሽቅ ሲያረገው እህህ ፋዘርየው #ከሶስት ፎቅ ጀርባ የወረወሩት ከዘራ ጀርባውን ሲመታው #ስድስት ፎቅ ዘሎ ወደቀና በስምንት አክሮባት ተነስቶ ቆመና *እኔ ደሜ በአንቺ ምራቅ ነው የተሰራው አንቺ ከሞትሽ እሞታለው* ብሎ አባትየውን ሊመታ ሲል ጋርዱ ከች ጋርዱን ሊለው ሲል ፖሊስ ከች"
አቤት ምስጠት ለካ ጋሽ ዘውዴ እኛ የቢጢሉ አባት መስፋት ትተው ሲያዳምጡ ቦኖ ውሃ የምታስቀዳው ሞላሽ ውሃ እያፈሰሰች ስታዳምጥ የጓደኞቼ ቆይ እንዲህ ላጭ በላጭ መሆንስ
"ከዛ ሊላቸው ሲል መታ አ_ፈ_ቅ_ር_ካ_ለ_ው በቀጣይ ህይወት አግባካለው አትለውም"
ከየት መጣች ሳንል ቆንጆዋ ጎራዳ ቅብጥብጥ
ቢጢሉ "ኑሬ ከንደገና ንገረኝ?"
 ኑሬ :- "እዚህ ይበጠብጡናል ሳሩ ሜዳ እንሂድ?"
ቢጤ:- እሺ!!
አራታችን:- አረ ለኛስ ሳጨርሰው?
ኑሬ:- በቃ ሞቱ ቻዎ!! (Timing)

ይዟት ይዟት በረረ!! ይዟት በረረ!!

ሞላሽ "ይድፋ ውሃዬን አስደፋኝ"(Engrossment)
ጋሽ ዘውዴ ቢጢሉን ባየነ ቁራኛ ሳሩ ሜዳ ድረስ ክትልትል (ዐይነ አውጣ ትውልድ ጉድ እኮ ነው ፎ )

ግንፍሌው አፍቃሪ አቡሽ:- "ጢሻው ይዟት ሄደ"
ጢሻው(እኔ):- "እና እኔ ምን ላርግህ?"
አቡሻ:- ርዕሱን ታውቀዋለህ?
ጢሻው:-የምኑን?
አቡሽ:- የፊልሙን?
ጢሻው:- አረ አቡሼ ሲሳይ ቪዲዮ ትላንት የታየው እኮ ነው።
አቡሽ:- አይተከዋል?
ጢሻው:- አዎ ግን ኑሬ እንዳወራው አላየውትም
አቡሽ:- ኑሬ እንዴት ነው ያየው?
ጢሻው:- እንደ ቢጢሉ
አቡሽ:- እናትህን እሺ ወይኔ እገላታለው
ሶስታችን:- ማንን?
አቡሽ:- ስዕል ቲቸር
ሶስታችን:-ምን ታርግ?
አቡሽ:- እሷ ነች በወረቀት እና በሙቅ ሰዐን ስሩ ብላ አስረፍዳብኝ ፊልም ያመለጠኝ እናቷንና ቆይ
 
ይሄ ግን ሳሩ ሜዳ አዲስ ዓመት ችቦ ሲበራ፣ ለኢድ ስግደት፣ ለመስቀል ዳመራ፣ ለጥምቀት ታቦት ማደሪያ፣ ለነ ኑሬ እና ቢጢሉ በሻሩክ ፊልም መዳሪያ ወይኔ ሳሩ ሜዳ ታድሎ ሳሮቹን ባረገኝ የቢጢሉን ጭን ስር ገብቼ ንክስ ነበር!!!
ቆይ የሰልማንንማ ፊልም ፊት ወንበር ላይ ነው የማየው ከዛ ቢጢሉን ሳሩ ሜዳ ይዣት እሄዳለው አቡሽስ? ገደል ይግባ ኑሬ ታድሎ
ማውራት የቻለ ይበላል ይኮራል ማውራት የቻለ ሀገር ይሸጣል ሀገር መሬቱን? ቲሽ ሕዝቡን ይቸበችበዋል እንደ ኑሬ ባወራ እኮ ቢጢሉ ሕዝቧን እበላላት ነበር።
የሕንድ ፊልም ግን ታድሎ እንደ ሕንድ ፊልም መኖር ብችል ሠማይን ስረግጥ በአንድ ቡጢ ሦስት መቶ ሠው ፌንት ሳስበላ ዝሆን በኩርኩም ሳደማ ስልጣን በግልምጫ ስቀማ ወዳ ነው ቢጢሉ ከኔ ጋር ሳሩ ሜዳ የምትሄደው ወዳ በሕንድ ፊልም የማይታፈሰው እውነት ከውሸት በላይ የሚሉት የቲቸር ዓለም ተረት ብቻ ነው።

በነገ #11:30 እንዴ ጋሽ ዘውዴ! እንዴ የቦኖዋ ሞላሽ! እንዴ አቡሽ! ፊት ወንበር ላይ ቲሽ ተቀደምኩ(Wreak)
ቢጢሉ ጨረታሽ ፈላ
ጉድሽ ፈላ
ወይ ስንፈተ ወሬ ኑሬ ታድሎ!!!
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
:- #ተክለ_ዮሀንስ

@wegoch
@wegoch
2024/09/29 05:25:52
Back to Top
HTML Embed Code: