Telegram Web Link
የመን፣ የጉድ ዘመን ምልክት!!
-----
ደሃ አትሁን እንጂ ሞትህን ማንም ከመጤፍ አይቆጥርም!! ደሃ ስትሆን ሞትህ እንዲህ
ይከፋል።
በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ የየመን ሕጻናት እንዲህ ሆነዋል! ልጅ ያለው ሰው ይሄን እያየ ቤቱ
በጥጋብና ቅምጣን ህመም መኖር ከቻለ ምጽኣት ቀርቧል ወይም ምጽኣት የለም!!
ልንረዳቸው አንችልምን?
የሰው ያለህ!!
የልጅ ያለህ!!

@wegoch
@wegoch
‹‹ግማሽ ስኒ ማኪያቶ ››
----።።።።።።።።
ሃሳብ- የዶርቲ ፓርከር ‹‹ ዘ ላስት ቲ››
።።።።።።።።።።።።።
እንዴት ብዬ እንደምነግረው ባሰብኩ ቁጥር ክፉኛ እያላበኝ ነው፡፡ ከቀጠሯችን ሰአት አንድ ሰአት ቀድሜ የደረስኩት ሃሳቤን ሰብስቤ፣ የምናገረውን አስቤ፣ መንፈሴን አረጋግቼ እንድጠብቀው ነበር፣ ግን አልሆነም፡፡ ከምን ጀመሬ ምን ላይ እንደምጨርስ፣ ምን ስለው ምን እንደሚለኝ እያሰብኩ ጭንቀቴ ናረ፡፡
ከ3 አመት በላይ አብረው በጓደኝነት የከረሙትን ወንድ ‹‹ ካንተ ፍቅር
ይዞኛል›› የሚባለው እንዴት ነው? ከምንድነው ነው የሚጀመረው?
በምን ቃላት ነው የሚወራው? ካፌ ውስጥ ይሻላል ወይስ መናፈሻ?
ቁጭ ብሎ ይሻላል እየሄዱ? አይን አይኑን እያዩ ወይስ ጣራ ጣራ እያሉ?.... መናገሩንስ ነገርኩት እንበል፡፡ ተነስቶ ጥሎኝ ቢሄድስ? ሰው ፊት ከት ብሎ ቢስቅብኝስ? የሚናገረው ጠፍቶበት ዝም ብሎ ቢያየኝስ? ከዚህ ሁሉ ብሶ ደግሞ ‹‹አረ…ይደብራል…. እኔ እኮ ልክ እንደ እህቴ ነው የማይሽ›› ብሎ ቢያሸማቅቀኝስ? እንዴት ብዬ እንደምነግረው ባሰብኩ ቁጥር እጄን፣ ግንባሬን፣ መቀመጫዬን እያላበኝ ነው፡፡ ግማሾቹ ጓደኞቼ ፣ ‹‹ለመንገር ስለዘገየሽ አሁን የሚያይሽ እንደወንድ ጓደኛው ወይ እንደእህቱ ስለሆነ አፍሽን አታበላሺ›› አሉኝ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ‹‹ ካለመናገር ማርቆስን የመሰለ ሸበላ ይቀራል፡፡ ንገሪውና ያበጠው ይፈንዳ›› ብለው መከሩኝ፡፡ ምን ዋጋ አለው..ከነገሩ በፊት እኔ በጭንቀት አብጄ መፈንዳቴ ሳይሆን አይቀርም፡፡ኡ….ፍፍፍ…… ሳልጠጣው የቀዘቀዘውን ሻይ ለመቅመስ ጆሮ የሌለውን ስኒ አነሳሁ፡፡ አለ ልክ ያላበው እጄ ልይዘው ስላልቻለ አዳልጦት ቀጥ ብሎ መሬት ላይ ከ……ሽ! ደነገጥኩ፡፡ ስኒ ስለሰበርኩ አልነበረም የደነገጥኩት፡፡ ገና ሳይመጣ፣ ገና ሳልነግረው፣ ገና አልፈልግሽም ሳይለኝ እቃ መፍጀት ከጀመርኩ ይህ ቀን እንዴት ነው የሚያልፈው? አስተናጋጇ እየሮጠች መጣችና ‹‹ውይ…አይዞሽ አይዞሽሽ..ፈሰሰብሽ
እንዴ!?›› አለችኝ፡፡ ጭንቅላቴን በአልፈሰሰብኝም ነቀነቅኩና የተሰባበረውን ብርጭቆ በፕላስቲክ አካፋ ታግዛ ስትጠርግ ፈዝዤ አየኋት፡፡
- አይዞሽ እዚህ ቤት ለእቃ አናስከፍልም…አለችኝ ትካዜዬ ያስከፍሉኛል ከሚል ጭንቀት የመጣ መስሏት ነው፡፡
- አይ…እከፍላለሁ…ችግር የለም አልኳት…
- አናስከፍልም…ሌላ ሻይ ላምጣልሽ? አለችኝ መጥረጓን ጨርሳ እያየችኝ፡፡ ‹‹ማርክ መጥቶ እወድሃለሁ ስለው እኔ አልወድሽም ብሎኝ ሕይወቴ ሲበላሽ ከማይ የአይጥ መርዝ ወይ በረኪና አምጪልኝና ድፍት ብዬ ልረፍ› ልላት እየፈለግኩ
- እሺ…አምጪልኝ…አመሰግናለሁ አልኳት ፊቴ ላይ የውሸት ፈገግታ ለመስራት እየታገልኩ…
- ያመመሽ ትመስያለሽ…ደህና አይደለሽም እንዴ? እንዴት አይነት መልካም ልጅ ናት? ‹‹አሞኛል እናቴ…ካመመኝ ቆየሁ መድሃኒቱ ግን በሽታዬ ነው›› ልላት እየፈለግኩ
- አይ ደህና ነኝ…ትንሽ…ትንሽ ደክሞኝ ነው…አልኳት
- ለማንኛውም ውሃ ላምጣልሽ አይሻልም?
- እሺ…ጥሩ ሃሳብ ነው…አምጪልኝ…
ሄደች፡፡ ሰአቴን አየሁ፡፡ አስራ አንድ ሰአት ከሃያ፡፡ ማርክ አለወትሮው አርፍዷል፡፡ ያውም ሙሉ ሃያ ደቂቃ፡፡ እግዜር ሃሳቤን እንድቀይር እድል እየሰጠኝ ነው? እግዜር ተናግሬ አፌን እንዳላበላሽ ማሰላሰያ ጊዜ እያዘጋጀልኝ ነው? ልጅቱ ሻዩን እና ውሃውን ስታመጣልኝ ማርክም ወደ ካፌው ሲገባ አየሁ፡፡ አርዝሜ ተነፈስኩ፡፡ ኡ….ፍ…..
- መርከብዬ….ሶሪ የኔ ቆንጆ…ብዙ አስጠበቅኩሽ አይደል? አለ ጉንጬን ስሞኝ ሲቀመጥ፡፡
- አይ…ገና አሁን መድረሴ ነው እኔም…አልኩ አይኖቹን እየሸሸሁ ለምን እንደዋሸሁ አልገባኝም፡፡
- ውይ አሪፍ….ጃሙ ናይትሜር ነበር ሜክሲኮ ጋር….ለነገሩ እኔም አርፍጄ ተነስቼ ነው…
- የት ነበርክ? አልኩት ደፈር ብዬ እያየሁት አዘውትሮ የሚለበስውን ግራጫ ጃኬት በጥቁር ቲ-ሸርት ከጂንስ ሱሪ ጋር ለብሷል፡፡ ጂንስ ሱሪ ነው ያልኩት? ድሮ ቀሚስ ሊለብስ ነበር? መረጋጋት አለብኝ፡፡ መረጋጋት አለብኝ፡፡
- ፒያሳ ነበርኩ…የመኪና ኢንሹራንስ ልከፍል…. እና ቆይ እዚህ ካፌ ነው የምነግረው?ለነገሩ ብዙ ግርግር የለውም፡፡ ከእኛ ሌላ ሶስት ሰዎች በርቀት ተቀምጠው ሞባይላቸውን ይጎረጉራሉ፡፡ ሌላው ቦታ እረጭ ብሏል፡፡ ሙዚቃ እንኳን አልተከፈተም፡፡
- እ…እሺ…አልኩና ውሃዬን ሳብኩ
- ምን ሆነሻል ዛሬ…ፊትሽ ጥሩ አይደለም…አለና ቀኝ እጁን ትኩሳት በመለካት አይነት ግንባሬ ላይ እያሳረፈ
አትንካኝ። የማትወደኝ…እሺ የማትለኝ ከሆነ በፈጠረህ እንደሱ አትንካኝ። ይሄ…ይሄ ንጹህ ንፁህ….እሱን እሱን ማርክ ማርክ የሚል ችግር ውስጥ የሚከተኝ ጠረኑ….
- መርከብ….
- ወዬ ማርክ….
- አሞሻል? ታተኩሻለሽ እኮ….እጁን ከፊቴ ላይ አንስቶ እጄን ያዘ፡፡
- ደህና ነኝ…ጉንፋን ሊይዘኝ ይሆናል
እሺ…ታዲያ ኢንሹራሱን ጨረስክ? አልኩት ወሬ ቅየራ እና ቆይ ይሄን የመኪና ኢንሹራንስ ወሬ ቀይሬ ነው እወድሃለሁ…ላገባህ…ልወልድልህ እፈልጋለሁ የምለው? መስፈንጠሪያ ወሬዬ ይሄ ነው?
- አዎ….ግን ዋናው ጉዳይ እሱ አይደለም….ብሎ ሲጀምር አስተናጋጇ መጥታ የሚፈልገውን ጠየቀችው፡፡
- ጥቁር ማኪያቶ….አለና ልጅቱ ስትሄድ….
- ከፋሲል ጋር ነበርኩ….እና መርከብዬ…የሰራችልን ልጅ….እንዴት እንደምታምር….. እሀ? ምንድነው የሚለኝ?
- ማ? ማናት የምታምረው አልኩ ውሃውን አንስቼ መጠጣት እየፈለግኩ እጄን እና አንጎሌን ማስተባበር አቅቶኝ ዝም ብዬ በደመነፍስ እያየሁት
- ሜላት የምትባል ልጅ….የገረመኝ ፋሲል ከእሱና ካንቺ ጋር እንደተማረች አይነግረኝም? ይህችን የመሰለች ፅጌረዳ የት ደብቀሽብኝ ነው በናትሽ? ሜላት ሜላት…..? የኮሌጅ የክፈል ጓደኞቼን በፍጥነት በአእምሮዬ አመላለስኩ፡፡ አልመጣችልኝም፡፡
- ሜላት? …አላውቃትም…ይልቅ ማርክዬ..ዛሬ ለቁም ነገር ነው የፈለግኩህ…አልኩ ማርሹን አሁን ካልቀየርኩ ነገሮች አቅጣጫቸውን እየሳቱ መሆኑ ስለገባኝ ቆፍጠን ብዬ..
- አረ በናትሽ…ሜላት ጌታነህ…በጣም ቀይ…መሰረት መብራቴን የምትመስል ግን ከእሷ የምትበልጥ….በጣም ቆንጆ….ፍዝዝ የምታደርግ….እሷ አውቃሻለች ወዲያው…እንዴት ትዝ አትልሽም? ወይ ጉድ…..ይሄ ነገር ምንም እንዳሰብኩት እየሄደ አይደለም፡፡
- የእኛ ባች ካልሆነች ረስቻት ይሆናል…እና ማርክ….ወደ ጉዳዬ ልግባ…ተረጋግተህ ስማኝ….
- ያንቺ ባች አይደለችም….አለ ቶሎ ብሎ ለምንድነው ማይሰማኝ? ይህቺ በድንገት ሕይወቴ ውስጥ ገብታ የምትበጠብጥ መሰረት መብራቴን መሳይ ሜላትስ ማናት?
- ምን ዲፓርተመንት ነበረች? አልኩት ስልችት እያለኝ
- ኤፍ ቢ ነበረች…ባስኬት ቦል ሁሉ ትጫወት ነበር…በጣም ረጅም ናት….ሚገርም ሰውነት…. ይሄን ሁሉ መረጃ ከምኔው ቃርሞ መጣ? ማናት? ጠንከር አድርጌ አሰብኩ..ሜላት ጌታነህ…ሜላት ጌታነህ….እንዴ! መጣችልኝ፡፡ የቁንጅና ውድድር አሸንፋ ሚስ ኤኤዩ የሆነችው ሜላት ባልሆነች….ናት መሰለኝ…ባልሆነች…ናት…
- ሚስ ኤኤዩ ነበረች መሰለኝ…እሷ ናት…አልኩኝ በማመንታት
- የስ! ፋሲል ስንመጣ እየነገረኝ ነበር ለነገሩ ባትሆን ነበር የሚገርመኝ….
- ግን እኮ እሷ የኔ ባች አይደለችም ማርክ…ማለቴ እድሜ በጣም ትበልጠናለች….እኔንም ፋሲልንም…ትልቅ ናት….በአንድ ቀን ከሞተላት ሜላት ላስጥለው ያቅሜን መንፈራገጤ ነው፡፡ አሳዝናለሁ፡፡ በጣም አሳዝናለሁ፡፡
- ያንቺ ታላቅ? ዋው…አትመስልም አንቺ…የስንት..ታናሽሽ ነው ምትመሰልው! ሆዴ ላይ በጩቤ የወጋኝ መሰለኝ፡ በጩቤ ጨቅ ያደረገኝ መሰለኝ፡፡
- እህ…አልኩ
- እኔ ታውቂኛለሽ ለሴት ወዲያው አላብድም …የዚህች ግን የተለየ ነው…አይ ሚ
ን…አይኗ….ሰውነቷ….ሁለ ነገሯ….ደግሞ በዛ ላይ ጨዋታ ስትችል…የሆነች የድሮ ጨዋ ልጃገረድ ነገር ናት….ጉርድ ቀሚስ ምናምን አድርጋ…በስማም የሆነ ነገር ሆንኩ ብታይ…ባንዴ የሆነ ነገር ሆንኩ…. ጩቤውን ሆዴ ውስጥ እያማሰለው መሰለኝ፡፡ አንጀቴ ተቆረጠ፡፡ ጣፊያዬ ተቆረጠ፡፡ ሃሞቴ ፈሰሰ፡፡ ልቤ መምታት አቆመ፡፡ አንጎሌ ማሰብ እምቢ አለ፡፡ የእኔ የስሜት መናወጥ ለእሱ ግን አልታየውም፡፡
- ፊልም ምናምን ለምን እንደማትሰራ አላውቅም..ምናልባት አብረን
እንሁን ምናምን እያሉ ስለሚያስቸግሯት ይሆናል…በመንገድ ራሱ እንዴት እንደምትሄድ አላውቅም….ሰው ያንን መልክ እና አቋም ይዞ እንዴት ይሄዳል…ያዲሳባ ወንድ ኢንች አያራምዳትም….ውሃዬን ጠጣሁ፡፡
- ብዙ ትዝ አትለኝም…እና ልልህ የነበረው ነገር…..አልኩ ለመጨረሻ ሙከራ
- ፋሲልን ስላየች መሰለኝ እንደዛ እየተደነባበርኩ ስጠይቃት ስልኳን
ስትሰጠኝ አላመንኩም….ውሸት ነው የመሰለኝ….ደሞ አለማፈሬ… ዛሬ ማታ ቀጠርኳት…እራት ልጋብዛት ነው፡፡ ሃሳቧን እንዳትቀይር….አሪፍ አላረኩም? በቃኝ፡፡ በቃ…በቃ…በቃኝ፡፡
ዝም አልኩ፡፡
- ምነው ዝም አልሽ? አለኝ
- አይ ምንም…እና እራት አብረን አንበላም? አልኩት ሳላስበው፡፡
- ውይ መርከብዬ እየነገርኩሽ አልችልም…አንቺ እኮ አንቺ ነሽ ጣጣ
አለው…ነገ እንበላለን…በዚያውም ሪፖርት ይቀርብልሻል…እ….ይልቅ አሁን ቶሎ ልሂድ…ፒያሳ ነው የቀጠርኳት…. አንቺ እኮ አንቺ ነሽ….ምን ማለት ነው? የትም አትሄጂም? እንደ ጉቶ ዛፍ ነሽ? እንደ ቋሚ የመንግስት ንብረት ነሽ? የትም አትሄጂም፡፡ የትም አታመልጪኝም፡፡ ብትሄጂም ግድ
የለኝም….?
- ስንት ስአት ነው ቀጠሮህ ? አልኩ ሰአቴን እያየሁ፡፡ ሃያ አምስት ጉዳይ ለአስራ ሁለት ፡፡ ከመጣ አስራ አምስት ደቂቃም አልሞላውም፡ማኪያቶውም ግማሽ ላይ ነው፡፡
- አንድ ሰአት ነው ግን ሪስክ መውሰድ አልፈልግም…በቃ…ልሂድ እሺ መርከብዬ….
- ሂድ…ለነገሩ እኔም አንተ ካልቻልክ ከሌላ ሰው ጋር እራት ልበላ ነበር…አልኩ ለምን ዋሸሁ? የተዋረደ የመሰለኝ ክብሬን ለማስመሰል? የተበጠሰ አንጀቴን በውሸት ክር ለማሰር?
- ተይ እንጂ…ከማ ጋር? አለ ተነስቶ እየቆመ - የሆነ እራት ካልጋበዝኩሽ እያለ የሚሟዘዝብኝ ነጋዴ አለ….ዛሬ ራሱ
ሰላሳ ጊዜ ደውሎልኛል ለምን ነጋዴ አደረግኩት? የኔ ሰው ካንተ ይበልጣል ለማለት? ለምን ሰላሳ ጊዜ ደወለ አልኩ? አንተ ባትፈልገኝም ሰፍ ብሎ የሚጠብቀኝ ሰው አለ ለማለት? - አረ መርከብዬ ነጋዴ ልትጠብስ ነው…አሪፍ ነው…ለሁላችንም ያልፍልናል….በቃ ልሂድ ቻው….. የመኪና ቁልፉን ፊቴ አሽከረከረና ጉንጬን እንደነገሩ ስሞኝ ሄደ፡፡ በቃ? ይሄው ነው? ለዚህ ነው እንደዛ ስናወጥ የከረምኩት? እኔ ሶስት አመት ሙሉ ወድጄው እሱ ግን …እሱ ግን ለግማሽ ስኒ ማኪያቶ እድሜ ቆይቶ… ብቻዬን ጥሎኝ አንዴ ወደ አያት ቆንጆ የሚከንፍ ወንድ ልብ ነው የተመኘሁት? ውሃ፡፡ ውሃ ያስፈልገኛል፡፡ የመጣልኝን ጨርሼዋለሁ፡፡ ልጅቱን በጣቴ ጠራኋት፡፡
- ሂሳብ? አለችኝ አዎ…ሂሳቤን ሰጥቶኝ ሄደ ልላት ፈልጌ እምባ እየተናነቀኝ - ውሃ…ሌላ ውሃ አምጪልኝ አልኳት፡፡ ውሃዬን ልታመጣ በቅድሙ ቅልጥፍናዋ ስትሄድ አይኔ ውስጥ የተከማቸው እምባዬ አለገደብ ወረደ፡፡

በ ሕይወት እምሻው

@paappii
@wegoch
ባል
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

አንዱ ባል ነው አሉ። ከሚስቱ ጋር በየቀኑ እየተጋጩ መስማማት ስላልቻሉ፥ እጅግ ተበሳጭቶ በሠርጋቸው ቀን ቃልኪዳን ላስገባቸው የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌ፥ ትዳሩን መፍታት እንደሚፈልግ በምሬት ይነግረዋል። ሽማግሌውም፡- (እየመከረው) ‹‹አየህ ልጄ... ስሜታዊ ሰው መሆን የለብህም፥ ...ነገሮችን ከቃሉ አንጻር ተመልከት...እግዚአብሔር መፋታትን ይጠላል... እርስበርሳችሁም መሸካከም አለባችሁ... ይኸ ሁሉ ቢቀር እንኳ፥ የዛኔ በሠርጋችሁ ቀን በእግዚአብሔርና በዚያ መዓት ታዳሚ ሕዝብ ፊት የገባኸችሁትን ቃልኪዳንም አስብ እንጂ...›› ሰውየው (የሽማግሌውን ንግግር አቋርጦ)፡- ‹‹የገባሁት ኪዳንማ እንዲያውም እኔን ይደግፈኛል...›› ሽማግሌው፡- ‹‹እንዴት ልጄ? አልገባኝም›› ሰውየው፡- ‹‹እኔኮ በሐዘኗ፣ በችግሯ፣ በሕመሟ ጊዜ ሳልለያት አብሪያት እሆናለሁ አልኩ እንጂ... በጥጋቧ ጊዜ አብሬያት እሆናለሁ ብዬ ቃል አልገባሁማ...››

በገመቹ መራራ

@wegoch
@paappii
ብርሃንና ጨለማ 
 ~
ጨለማ ተማሮና ተንገፍግፎ እፈጣሪ ዘንድ ቀረበ

""የእኔን መከራስ አያሳያችሁ" ብሎ አቤት ሊል ።
ምን እንደተበደለ ሲጠይቀው ወይዘሪት ፀሃይ አስቸገረችኝ ሲል ብሶቱን ተናገረ☹️🌚 ፈጣሪም ፀሀይ ትምጣና ትጠየቅ አለ 
ፀሃይ በፈገግታ🌝☀️ ደምቃ ብቅ ከማለትዋ ጨለማ የት እንደገባ ሳይታወቅ ከዛ አካባቢ ጠፋ ፈጣሪ ጨለማ በደለችኝ ብሎ ያቀረበውን ክስ ለፀሃይ ነገራት ፀሃይም እዝን ብላ 
ብዙ ወዳጆቼ የጨለማን ቅያሜ ነግረውኝ ይቅርታ ልጠይቀው እኔም እፈልግ ነበር ግን ከየት ላግኘው ከነመፈጠሩም ማን ይሁን ምን አላውቀውም አለች አሉ

@wegoch
@wegoch
@yeyhudaanbesa
መቻቻል? ????????????????


ይህንን ህያው ፍቅር መቻቻል ብሎ መጥራት ድንቁርና
ነው ። እኛ ጋር መዋደድ ፤ መፋቀር ፤ ሰው መሆን ነው
ስንቃችን! !! መቻቻል የሚባል የዱርዬ ቋንቋንህን ወደዚያ
ውሰድልኝ! !!


ሸብርቅርቅ ያለች ቅዳሜ ትሁንላቹ!!!💚💛❤️
@balmbaras
@wegoch
@wegoch
የማያስተኛ ነገር ነግረውን ተኝተው
አደሩ!

ከዚህ በፊት ብዙ ጊዜ ብለነዋል፤ ማንም ስላልሰማን ደግመን እንለዋለን ይላል - አንድ የጥንት ታሪክ ፀሐፊ፡፡ የእኛም እንደዚያው ነው፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ሁለት ደገኛ ገበሬዎች አብረው ይኖሩ ነበር፡፡ ሳር ቤት ነው ያላቸው፡፡ ደሳሳ ጎጆዎች ናቸው፡፡ በድንገት አንድ ቀን የአንደኛው ገበሬ ቤት ተለወጠ፡፡ ቆርቆሮ ቤት ሆነ፡፡ ጎረቤትየው ደነገጠና፤ “ወዳጄ፤ እንዴት ይሄ ቤትህ ሊለወጥ ቻለ? ምን ተዓምር ተገኘና ነው?”
ገበሬው፤ “አየህ በሬዎቼን ሸጥኳቸውና ታች ቆላ ወርጄ ብረታ ብረት ገዛሁ፡፡ ከዚያ ደጋ አምጥቼ ለቀጥቃጩ፣ ለባለእጁ፣ ማረሻ ለሚፈልገው ገበሬ ሸጥኩ፡፡ ብዙ ብር አገኘሁ፡፡ ቤቴን ለወጥኩ፡፡ አጥሬን ለወጥኩ፡፡ ራሴን ለወጥኩ!” “በቃ፤ እኔም እንዳንተ አደርጋለሁ” አለና ሄዶ በሬዎቹን ሸጠ፡፡ ከዚያም ገበያ ገብቶ ማጭድ፣ አካፋ፣ ዶማ፣ ማረፊያ፣ ገሶ … ብቻ አለ የሚባል የብረት ግብዓት ገዝቶ፣ ተሸክሞ፣ ወደ ደጋ ዳገቱን ተያያዘው፡፡ ሆኖም ያን ሁሉ ብረት አቅሙ አልችል አለና ዳገቱ ወገብ ላይ ተዝለፍልፎ ወደቀ፡፡ የመንደሩ ሰው በዚያ ሲያልፍ አየውና፤
“አያ እገሌ ምን ሆነህ ነው?”
“ያ ጎረቤቴ ገበሬ ጉድ አርጎኝ ነው!”
“ምን አደረገህ?”
“ንግድ ጀምሬያለሁ ብሎ የንግዱን ጠባይ ነገረኝ፡፡ ባለኝ መሰረት ንግድ
ውስጥ ገባሁ” “ታዲያ እሱ ምን በደለህና ነው ጉድ አደረገኝ የምትለው?”
“ትርፉን ነግሮ መከራውን ሳይነግረኝ!”
***
አያሌ ትርፍ ያስገኛሉ የተባሉ ነገሮች መከራ እንዳላቸው መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡ ቀላል የሚመስሉ ግን ውስብስብ የሆኑ፣ ውስብስብ ሆነው የባሰ የሚወሳሰቡ፣ ሳንማርባቸው ያለፉ፣ ተምረንባቸው የተረሱ፣ ጨርሶ ያላጠናናቸው ብዙ ብዙ ቁምነገሮች አሉ፡፡ “ከበሮ በሰው እጅ ያምር ሲይዙት ይደናገር!” የሚባለው ተረት፣ ለተሿሚዎቹ ሁሉ የማስጠንቀቂያ ደወል ነው! በተለይ ሴት ተሿሚዎች መብዛታቸው አኩሪ የመሆኑን ያህል ኃላፊነታቸውን መወጣታቸው፣ ከሙስና የፀዱ መሆናቸው፣ የፆታ እኩልነትን ማበልፀጋቸው፣ ለበርካታ ሴቶች አርአያ መሆናቸው፣ ከወንዶች ይልቅ ዝርዝር ጉዳይ ላይ የማተኮር ክህሎታቸው (Meticulousness) እጅግ የላቁ
ያደርጋቸዋል! ይሄ ቢሳካልን ላሜ ወለደች ነው! ይህን ዕድል እንደ ሌሎች ያመለጡን ዕድሎች እንዳይሆን መትጋት ያስፈልጋል፡፡ የእናቶች ፀጋ በእጃችን
ነው፡፡ የህፃናት ፀጋ በእጃችን ነው፡የትምህርት ፀጋ በእጃችን ነው!የሚያስጎመጅ ዕድል ባያመልጠን መልካም ነው! የዲሞክራሲ፣ የፍትህ፣ የተስፋ፣ የራዕይ ጊዜ እየጀመረ ነውና እንጠቀምበት! ለብዙ ዓመታት የጮህንለት የሴቶች አጀንዳ መልካም ጉዞ ይጓዝ ዘንድ የወንዶችም የሴቶችም
ጥያቄ አድርገን እንየው፡፡ አለበለዚያ “የማያስተኛ ነገር ነግረውን ተኝተው
አደሩ” ይሆንብናል!!

ምንጭ :- አዲስ አድማስ ጋዜጣ ጥቅምት 24 ቀን 2011

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
አረብ ገንዳ በልቤ ውስጥ!
(የመን የጉድ ዘመን ማሳያ)
-------
የመኖች መልካሞች ናቸው። ሲሰጡ አይሰስቱም። ከአረቡ አለም መልካም ህዝቦች
እንደነሱ የለም። አበሻ ከአረብ ጋር ዝምድናና የጋራ ታሪክ ቢኖረው ከየመን ህዝቦች ጋር
ያለውን ያክል ከማንም የለው። የመን ግዛታችን ነበረች ስንል የመናውያን እኛ ነን እያልን
ነው።
ራያ ቆቦና ደሴ አረብ ገንዳ የሚባሉ ሰፈሮች የነዚሁ መልካም ህዝቦች ዝርያዎች
የሚኖሩባቸው ናቸው። ከራያ ቆቦ እስከ ደሴ፥ አረብ-ገንዳ ሰፈሮች ሃበሻንና የመናውያንን
አቅልጠው ሰርተዋል። የመኖች ሃበሾች፥ ሃበሾችም የመኖች ሆነዋል።
እናማ የመኖች እንዲህ መኣት ሲወርድባቸው ዝምምም ብሎ ማየት ከመበደል እኩል ሆኖ
ተሰማኝ። 13 ሚሊዮን የመናውያን በጠኔ ተመትተው ሞታቸውን ይጠብቃሉ። እነዚህን ደግ
ህዝቦች፥ እነዚህን ጊዜ የከፋባቸው የኛን ህዝቦች እንዴት ዝም እንበላቸው?
በመከራው ጊዜ "we are the world" ብለው የደረሱልን አሜሪካውያንና አውሮፓውያን
እንደነበሩ አንረሳውምና ደሃ በርሃብ የምትሞትን ነብስ ቢታደግ ነውር ይሆናልን?
አለም የለም!
የመን የጉድ ዘመን ማሳያ!!

@wegoch
@wegoch
የዜሮ_እና_መቶ ወግ

(ስዩም ተሾመ)

#መቶ፡ “ው…ይ ዜሮ ደሞ ሙዝ…ዝ ስትል አይጣል! የለህም…ባዶ ነህ… ምንም ነህ! ለምን ድርቅ ትላለህ?”
#ዜሮ፡ “አይ መቶ! እሺ እኔ ከሌለውና ‘ምንም’ ከሆንኩ፣ አንተ ራስህ የለህም’ኮ። እንዴት ነው የምታስበው? እኔን በጥላቻና ፍርሃት ለማጥፋት ስትጥር ራስህን ታጠፋለህ’ዴ?! ያንተ ህልውና’ኮ በእኔ መኖር ላይ የተመሰረተ ነው። አንተ ግን ዝ…ም ብለህ ትጮኻለህ! የሆንክ ባዶ ነገር…”
#መቶ፡ “‘እ…ኔን ነው?…እንዴት ባክሽ? …ኧረ እስኪ እንዴት ነው የእኔ ህልውና ባንቺ መኖር የሚወሰነው?… ዶጮ ራስ!”
#ዜሮ: “‘እኔ ዶጮ ራስ’? አንተ አለህ አይደል ‘ዶማ ራስ!?’ …በቃ “መቶ” ስትባል ‘ምሉዕ’ የሆንክ ይመስልሃል? ያለኔ’ኮ “100” መሆንህ ቀርቶ “1” ነነገር
#መቶ: “እንዲያም ሆኖ’ኮ ግን ቁጥር የሚጀምረው ከኔ ነው። በገሃድ ያለ ነገር “1” ብሎ እንጂ “0” ተብሎ አይቆጠርም። አየሽ እንዴት ያላቺ መኖር እንደምችል? ሃሃሃ…ደቃቃ ነገር ነሽ…ላጥፋሽ እንዴ?… ‘እፍፍፍ’!”
#ዜሮ፡ “ኤጭ…እሳቤህ ሁሉ ቁንፅል ነው። የእውነትን ጠምዝዘህ ባንተ ፍላጐት አቅጣጫ እንዲሄድ የምታደርግ ይመስልሃል። የሆንክ ጉልበታም ነገር ነህ! እውነት በእውቀት እንጂ በጉልበት አይገዛም!
#መቶ: “ኧረ ይሄን ሁኹትና ብጥብጥ የሚያስነሳ ንግግርሽን ተይ!…”
#ዜሮ: “እኔ ከሌለው አንተ “1” ብቻ ትሆናለህ። ይሄን ትክዳለህ?”
#መቶ:- “ይሁና…’1’ቁጥር ሆኜ’ኮ እኖራለሁ። አንቺ ግን ከሌለሽ የለሽም…በቃ አለቀ… ሃሃሃ”
#ዜሮ: “እሺ ይሁንልህ፣ እኔ የለሁም።  አንተ ብቻህን ከሆንክ’ኮ ቁጥርና መቁጠር አይኖሩም። አንተ ብቻህን ነሃ!  እንዳንተ አይነት ጡንቻ ራስ “እኔ በራሴ ‘ሙሉ’ ነኝ” ብሎ የሚለፍፍ ሁሉ “ሙሉ” የሚለው ነገር በራሱ “ምንም” ማለት እንደሆነ ሊያውቅ ይገባል።
#መቶ: “እሺ…አንቺ እንዳልሽው መቶ ቀርቶ አንድ ልሁን። አንድም ሆኜ ግን በገሃድ ያለ ነገር ሁሉ “አንድ” እንጂ “ዜሮ” አይባልም። አየሽ… እኔ የመኖር መለያ፣ አንቺ ደግሞ ያለመኖር መለያ ነሽ። እኸ! ልዩነቱ ገባሽ?” 
#ዜሮ፡ “አለመኖር ከሌለ መኖር ፋይዳ የለውም! የሚቆጠር ሳይኖር መቁጠር አይቻልም፣ አንድ ብቻውን ቁጥር አይሆን’ማ! ቁጥር የሚኖረው አማራጭ ሲኖር ነው። አማራጭ በሌለበት ምርጫ የለም። “እኔ ብቻ” በማለት አለመኖርህን መሰከርክ እንጂ መኖርህን አላረጋገጥክም። ደደብ ነገር ነህ’ዴ?! “አለሁ” ስትል የለህም’ኮ!!!”
መቶ፡ “ኧ…?”
ዜሮ፡ “‘100’ ያለ ‘0’ አንድ ‘1’ ነው። 1 ምርጫና አማራጭ የለውም። ምርጫና አማራጭ ካለ 100% ድጋፍ ወይም ተቃውሞ አይኖረውም። አማራጭ ባለበት “100% ድጋፍ አገኘሁ” ማለት ምርጫው ነፃ እንዳልነበር ከመመስከር ያለፈ ትርጉም አይኖረውም። 
**
ሰኔ 15, 2007 ዓ.ም
@yeyhudaanbesa
@wegoch
@wegoch
የመን ፣የጉድ ዘመን ማሳያ!!!

እዚህ ደርሰናል። ደሃ አትሁን ፥ አይጨልምብህ እንጂ ጥጋበኛው አለም ላንተ ሞትና ዋይታ ደንታ አይደለም።😭😭😭😭😭

@wegoch
@wegoch
///አንብብ ትለኛለች////
ቀስ ቀስ እያለች አንብብ ትለኛለች።


……ራት ተመግበን እንደጨረስን ፈጥና ሰሀኖቹን አነሳስታ ወደ መኝታ ወደ አልጋ ይዛ ታፋጥነኛለች። "ወደ አልጋ እሚያፋጥናት ምንድን ነው?" ብሎ እየጠየቀ ሲጥ ሲጥ በእዝነ ልቦናው እየዋለለ እሚያቃጭልበት አይጠፋም። ምክንያቱም ራት ከተበላ በሁዋላ ወደ አልጋው የሚያሯርጣት በቃ የአልጋ ውስጥ ጨዋታ በሚለው ዝግመተ ለውጥ ማለሚያው ተጀቡኗልና። ……ራት እየበላን ሳለን ቦዘዝ ብለው በሚያስለመልሙኝ ዐይኖቿ እያየችኝ አልጋዋን ሁሌ ታልማለች። በዐይኖቿ ደሞ አልማለሁ። በቦዘዙት ዐይኖቿ ራት ተመግበን… እቃዎችን እያነሳሳን… ወደ እቃ ቤትእየተከታተልን ስናመላልስ… ትከሻ ለትከሻ ስንነካ እንደተጫረ ክርቢት
ብርሀን ለጥርሶቻችን ሲለኩሱ… በጥቅሻ ስትስመኝ… እቃ ቤት ሆና አንድ ብርጭቆ ቀዝቃዛ ውሀ እየተጎነጨች ከጉሮሮዋ ሲወርድ ሰውነቴን ሲለሰልሰኝ……ፀጉሯን ነስነስ አድርጋ ተመልሳ እያጣደፈች
ይዛኝ ስትነጉድ ወደ መኝታ ቤት …የአልጋውን አነጣጠፍ የትራሶቹ አደራደር…ከሸልፉ መፅሀፍት ተኮልኩለው… ጭል ጭል እንደሚል ኩራዝ ብርሀን የሚለግሰው የራስጌ መብራት…ሸክ ሸክ የምትለው ሰዓት…… ለስለስ ካለው የቴዲ አፍሮ ሙዚቃ እያጀበ ከአልጋው ስትሰፍር አልማለሁ።

……በሳልሳ አለስልሳ እያስለመለመች…እያሻፈደች… በለሆሳስ ወደ አልጋው ከደረቴ እየወረወረች አንብብ ትለኛለች። ይሔው ወደ አልጋ አሯሩጣ አንብብ ትለኛለች። እያስለመለመች አንብብ ትለኛለች። እያሻፈደች አንብብ ትለኛለች። ፀጉሬን እየደባበሰች አንብብ ትለኛለች። አንገቴን እየሳመች አንብብ ትለኛለች። ወደ ደረቷ እየሳበች አንብብ ትለኛለች።
……ትንፋሼ ቁርጥ ቁርጥ እያለ እሽ እላታለሁ። ከአንጋለለችኝን ተነስቼ ላነብላት ስል ከላዬ ላይ ሆና አንብብ ትለኘለች። የቢጃማዬን ቁልፍ እየፈታች ደረቴን እየሳመች አሁንም እየደጋገመች አንብብ ትለኛለች። ……በዚህ ሙቀት በዚህ መዳበስ ስለምን ግጥም አንብብ ትለኛለች እያልኩ አስባለሁ። የረጠበው ቡናማ ከንፈሯ አፌን እየሳመ ግጥም
አንብብ ትለኛለች። ……የማንን ግጥም እላታለሁ። ከናፍሬን እየመጠጥኩ። ከላዬ ላይ ሰፍራ እየደባበሰች አንብብ ትለኛለች።
…የናፈቅሽኝ እለት
ንፍቅ ያልሽኝ እለት ትገኛለሽ ብዬ…
በፍለጋ ጉዞ ምድርን አካልዬ፤
ስማስን በዱሩ፣ ሳስስ በባህሩ…
በሜዳ ገደሉ ሲመሽ እየነጋ ሲነጋ ቢመሽም
ያለሽበት የለም አንቺ አልተገኘሽም!
አየሽ… እንደ ዘንዶ ስሳብ… እንደጥንቼል ስዘል… እንደ አሞራ ስበር ቤ ውስጥ እንዳለሽ ልብ አላልኩም ነበር።( ግጥም:– መስፍን
ወንድወሰን )

እያልኩ አነብላታለሁ…ገልበጥ አድረጋ ከላይዋ ላይ አድርጋ ግጥም
ትለኛለች። ከደረቷ ለጥፋ አንብብ ትለኛለች። ስቅታዋ አይሎ አንብብ
ትለኛለች።
ግጥም ትለኛለች።

በጆሮዬ አንብብ ትለኛለች።
እጠጋታለሁ የሚሞቅ ትፋሼ ከጆሮዋ ለግቼ
……
እኔና አንቺ!
በጥምር ነፍሳችን ፣ አረፍ ስንልበት ጨለማው ወገገ፤
ፈጣሪ ተገርሞ ለደስታ ፍቺ አዲስ ቃል ፈለገ።
እኔና አንቺን እኮ!
አበቦቹ ያጅቡናል፣
ፍራፍሬው ይከበናል፤
ሕይወት ጉንጯ ሲንቆረቆር ይሰማናል።
ወፎቹ!
እኔና አንቺን አይተው ተቃቅፈው በረሩ፤
ከጨረቃ ታርቀው በምሽት በረሩ።
ኮከቦቹ!
" ጨረቃ ወለደች! " እየተባባሉ፤
ከእኛ ተጠግተው ብርሀን ተሞሉ።
በቀቀኖች እንኳን!
ከፃድቃን ቃል ውጭ መድገም የማይችሉ፤
ከእኛ ሳቅ በሁዋላ " ድምፅ ሰማን! " አሉ።
‘ ባክሽ እንዳይገርምሽ!
በእኛ ሲከፋፈት ~ የምድር የሰማይ በር፣
እንዲህ ቀልቡን ሲሰጥ ~ የአዕዋፍ የአራዊተ ዘር ፣
ሁሉን ይሸምታል ~ ፍቅር ሲዘረዘር።
( ግጥም: – በረከት በላይነህ)
አነብላታለሁ።
እየተኛች ግጥም ትለኘለች።
ቀስስ እያልክ አንብብ ትለኛለች።
አሁንም አንብብ ግጥም ትለኛለች።
ደሞ ደሞ አንብብ ትለኛለች።
አነብላታለሁ።

@wegoch
@wegoch
@lula_al_greeko
ኑ! ሀገሬን እናዋልዳት


አዋላጇ ጠፍታ ልጁም በእግሩ መጥቶ
እናቲቱ ሞተች ልጅዬውም ሞቶ
የሚል የልቅሶ ግጥም አለ። ነፍሰ ጡር እናት ስትወልድ ልጁ በእግሩ ከመጣ አደጋ ነው ይባላል። ጎበዝ አዋላጅ አግኝታ ልጁ በአናቱ እንዲመጣ ልታግዛት ይገባል። ያ ካልሆነ ግን ባልተስተካከለ መንገድ የመጣውን ልጅ ለመውለድ የምታምጠው እናት፣ ለረዥም ጊዜ በማማጧ የተነሣ ደክማ ለሞት ትዳረጋለች። ልጇም የመሞት ዕጣ ፈንታ ይገጥመዋል። መውለድ ደስታ የሚሆነው ልጁ በሰላም ተወልዶ፣ ለእናቱ ጤናና ደስታ ካመጣ ነው። መውለድ ካልተስተካከለ ማርገዝ ብቻውን ድካም ነው። ለዚህ ነው ነፍሰ ጡሮች በሕክምና እርዳታ ሲታገዙ ቆይተው፣ በሕክምና እርዳታ እንዲወልዱ የሚመከረው
ሀገር ለውጥን ልትወልድ የምትችለው የለውጥን ጽንስ በጤናማ መልኩ አርግዛ በጤናማ መልኩ እንድትወልድ የሚረዷትን ሐኪሞች ካገኘች ነው። ጽንሱ ጤናማ መሆኑን በየጊዜው የሚከታተሉ፤ ችግር ሲፈጠር ወዲያው መፍትሔ የሚሰጡ። ስትወልድም ልጁም እናቲቱም ጤንነታቸው በተጠበቀበት መንገድ እንድትወልድ የሚረዱ አዋላጅ ሐኪሞች ያስፈልጓታል። ይህ ሲጠፋ ልጁም እናቲቱም ለሞት ይዳረጋሉ።
ኢትዮጵያ ብዙ ጊዜ ለውጥን ፀንሳ ታውቃለች። ብዙ ጊዜ የማታገኘው ጎበዝ አዋላጅ ሐኪም ነው። በዚህ ምክንያትም ብዙ ጊዜ ልጇ ሞቶባታል። ያውም በእርሷም ላይ ከባድ አደጋ አድርሶ። ማኅፀኗን ጎድቷት ስለሚሄድ፣ ሌላ ልጅ ለመጸነስ ዘመናትን እንዲፈጅባት አድርጎ።
የቅርቡ ታሪካችንን እንኳን ብንመለከተው፣የልጅ ኢያሱን ዘመን ፀንሳ ነበር። ነገር ግን ካለፉት ዘመናት በተለየ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሀገሪቱ ሂደት ባለቤት እንዲሆን ከዘመኑ በቀደመ ሐሳብ የተነሣውን ወጣቱ ንጉሥ ሐሳቡን የሚያዋልድለትና ፅንሱ በእግሩ መጥቶ እናቱንም ራሱንም እንዳይገድል የሚያደርግ ሐኪም አጥቶ፣ ሀገሪቱ ያንን ዕድል አመከነችው። የተገኙት አዋላጆች ሳይሆኑ አምካኞች ነበሩ። ልክ ፈርዖን በግብጽ፣እሥራኤላውያን ላይ አሠማርቷቸው እንደነበሩት የአዋላጅ አምካኞች።
በ1953 ዓ.ም ኢትዮጵያ እንደገና ሌላ የለውጥ ልጅ ፀንሳ ነበር። ነባሩ ንጉሣዊ ሥርዓት ከመሠረቱ ሳይናጋ ነገር ግን ዘመኑ የሚጠይቀውን ሥርዓታዊ ለውጥ ለመውለድ ፀንሳ ነበር። አዋላጅ ግን አላገኘችም። ያንን ሐሳብ በሚገባ ፀንሳ በሚገባ እንድትወልድ የሚያደርጉ አዋላጆች ብታገኝ ኖሮ፣የጥንቱን ከዘመኑ ያጣጣመ ሥርዓት ገንብታ ለመጓዝ ትችል ነበር። ግን ምን ዋጋ አለው፤ ጨነገፈ።
በ1966 ዓ.ም ሌላ የለውጥ ልጅ ፀነሰች። ሀገሪቱን ወደተሻለ ሥርዓት ሊወስድ የሚችል ተስፋ የሰነቀ ልጅ። ምን ዋጋ አለው። አዋላጆች አላገኘችም። ልጁን ጤናማ ሆኖ እንዲወለድ ከማገዝ ይልቅ አዋላጆቹ እርስ በርሳቸው ሲጨፋጨፉና ሲቧቀሱ፣ ልጁ ‹ታሪክ የጣለብንን ኃላፊነት ለመወጣት› ብለው በተነሡ የወታደር አጨናጋፊዎች እጅ ወደቀ። አንዲት የገጠር ሴት ለመውለድ ደርሳ አዋላጅ ጠራች። የቀን ጎደሎ ሆኖባት የማይችል ሰው እጅ ወደቀችና እርሷም ልጇም ሞቱ። አልቃሽ፡-
እንዲህ ያል ክፉ ቀን ክፉ ሰው ላይ ጥሏት
እንኳን ልጅ ልታገኝ እርሷንም ገደሏት፤
ብላ ገጠመች ይባላል። ኢትዮጵያም በ66 እንዲህ ነው የሆነቺው። ሐኪሞች ልጆቿ፤ የራስዋን ልጅ ማዋለድና ማሳደግ ሲገባቸው፣ የማደጎ ልጅ ከሶቪየት አምጥተው ልጅሽ ይሄ ነው አሏት። በማኅፀንዋ የተፀነሰውን የራስዋን ልጅ ገድለው የሰው ልጅ አሳቀፏት። የአዋላጆቹ ጠብም ልጇን እንዴት እናዋልዳት? መሆኑ ቀርቶ፣የትኛውን ልጅ ትታቀፍ? የሚለው ላይ ሆነ። እንኳን አዲስ ልጅ ልትወልድ እርሷም በወሊድ ምክንያት በተከሠተ ሕመም ለዘመናት ትሰቃይ ጀመር።
ያ ዘመን አልፎ 1983 ዓ.ም መጣ። ሁሉንም ያሳተፈ፤ የኅብረተሰብም የሐሳብም ብዝኃነትን የተቀበለ፤ ሀገሪቱ ስትመኘው የኖረቺውን ልጅ ልትወልድ የምትችልበት ዕድል ገጠማት። አሁንም ግን አዋላጆች ጠፉ። ያንን ለውጥ በፖለቲካ ብስለት፣ በዕውቀትና በትዕግሥት፣ በአመራርና በጥበብ አዋልደው፣ሀገሬ ዴሞክራሲና ዕድገትን ከነ ቃጭሉ ዱብ እንድታደርግ የሚያስችሉ አዋላጆች ጠፉ። ሁሉም የራሱን ብቻ ሲሰማና ‹ልጁ እንዲፀነስ የታገልኩት እኔ ነኝና እኔ ብቻ ልወስን› ሲል ሀገሬ ልጇን አጣችው። እርሷ ለመፅነስ እንጂ ለመውለድ ሳትታደል ቀረች።
ከሕዝቡ አብራክ ተከፍሎ በኢትዮጵያ ማኅፀን የተፀነሰውን ያንኑ ልጇን ተባብሮ ከማዋለድና እርሱኑ ተከባክቦ ከማሳደግ ይልቅ አሁንም ኮሚኒዝሙን፣ ማኦኢዝሙን፣ ዴሞክራሲውን፣ ቀያይጠንን እንደ አሻንጉሊት ሰፍተን፣ ‹ልጅሽ ይሄ ነው› አልናት። የብሔረሰቦችን ጥያቄ ልንግባባበትና ሀገር ልንመሠርትበት በምንችለው መንገድ መፍትሔውን መውለድ ሲገባን፣ ዘወትር የሚያጣላንንና የሚያበጣብጠንን የማደጎ ልጅ አመጣን። ከራሳችን አብራክ በራሳችን ማኅፀን ለኛ የሚሆን የፌዴራሊዝም ልጅ ልንወልድ ሲገባን የማደጎ ልጅ አመጣን። ይኼው አሁን በሂደት ልጁ የኛ ልጅ አለመሆኑን፤ ኢትዮጵያ የወለደችው ልጅ አለመሆኑን እየነገረን ነው። ከኛ ፍላጎት፣ ባህል፣ አስተሳሰብና ታሪክ ጋር መኖር አቅቶታል። የገዛ ልጃችን ዕዳ ነው የሆነብን። ሀገሬ ልጅ አልወጣላትም።
በ1997 ዓ.ም ሀገሬ ሌላ ልጅ ፀንሳ ነበር። ዴሞክራሲን። የአስተሳሰብ ብዙኅነትን ልትወልድ ነበር። እኛም ትወልዳለች ብለን የገንፎውንና የአጥሚቱን እህል አዘጋጅተን ነበር። ግን ምን ያደርጋል፤ ሐኪም አላገኘችም። ‹እኔ ብቻ› የሚል ሐኪም ገጥሟት፤ የዛሬውን እንጂ የነገውን የማያይ ስግብግብ አዋላጅ ገጥሟት፤ ምንጊዜም በሆስፒታሉ ውስጥ ‹ብቸኛው ስፔሻሊስት ሐኪም› እየተባለ መኖር የሚወድ ራስ ወዳድ ሐኪም ገጥሟት፤ ጊዜያዊ ችግሮችን ለዘላቂው ጥቅም ሲል መታገሥ የማይችል ሐኪም ገጥሟት፤ ወይ ‹ሁሉን ማግኘት አለያም ሁሉን ማጣት› የሚባል የማዋለጃ መሣሪያ የያዘ ሐኪም ገጥሟት ሀገሬ ልጇ ሞተባት።

እርሷም ትፀንሳለች እኛም እንፈጫለን
ለልቅሶ ነው እንጂ ለእልልታ አልታደልን፤

አለ አሉ፤ ኀዘን የጎዳው ባል። ሚስቱ በፀነሰች ቁጥር ለአራሷ የሚሆን እህል በቤቱ ይፈጫል። ነገር ግን ወለደች ተብሎ እልል ሳይባል፣ ሞተባት ተብሎ ይለቀሳል። ይሄ ነበር ባልን እንዲህ እንዲያንጎራጉር ያደረገው። ሀገሬም እንዲህ ነው የሆነቺው።
አሁንም ሀገሬ ፀንሳለች። እኛም ሊያግባባንና ሊያስማማን የሚችል ሥርዓተ መንግሥት፤ የብዙኃኑን ውክልና የሚያረጋግጥ ዴሞክራሲያዊ ሂደት፤ የትብብር መነሻ የሚሆን፣ ከአጥር ይልቅ ድልድይ የሚገነባ ፌዴራሊዝም፣ ሰብኣዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን የሚያከብርና የሚጠብቅ የፖለቲካ ምኅዳር ትወልዳለች ብለን ተስፋ እያደረግን ነው። ይህ እንዲሆን ግን ማዋለድ ያስፈልጋል። ኃይልና ጉልበትን፣ ዘረኝነትና ጽንፈኝነትን፣ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀልና እኔ ብቻ ዐውቅላችኋለሁን፣ እኔን ምን አገባኝና እኔ የለሁበትምን፣ አግላይነትንና ጠቅላይነትን፣ ጥገናዊነትንና ጊዜያዊነትን ትተን ሀገሬ ለሁላችንም የሚሆን፣ ሁላችንም እልል ብለን የምንቀበለው፤ ሁላችንም የአራስ ጥሪ የምናመጣለት፣ ሁላችንም በመወለዱ ገንፎ የምንበላበት፣ ሁላችንም ልደቱን የምናከብርለት፣ ከሩቅ ያሉት እንደ ሰብአ ሰገል ገሥግሠው፣ ከቅርብ ያሉት እንደ እረኞቹ ነቅተው ሄደው የሚያመሰግኑት ልጅ እንዲወለድልን ማዋለድ አለብን። ምሁራኑ፣ የፖለቲካው ልሂቃን፣ ደጋፊዎች፣ ተቃዋሚዎች፣ የእምነት መሪዎች፣ የሚዲያ ተዋንያን፣ ነጋድያን፣ ወጣቶችና ሴቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ወታደራዊ አለቆች፤ ሀገራችን የፀነሰቺውን ልጅ በሰላም እንድትገላገል እንርዳት። አንዱ እግሩን፣ አንዱ እጁን፣ አንዱ ጆሮውን፣ አንዱ ጭንቅላቱን እየሳበ፣ ለራሱ ብቻ የሚጠቅመውን የየራሱን ልጅ ለ
ማዋለድ ቢጥር ልጁ ይሞታል እንጂ ልጅ አይሆንም። ሀገሬም ፀንሳ በወለደች ቁጥር እየተጎዳች፣ እየደከመች ትሄዳለች።

እናት በተደጋጋሚ ልጆች ሞተውባት በስተመጨረሻ ተወልዶ የሚያድግላትን ልጅ ‹ማስረሻ› ትለዋለች። ያለፈውን መከራና ስቃይ ሁሉ የሚያስረሳ ማለቷ ነው። ሀገሬ ማስረሻ የሆነ ልጅ ትፈልጋለች። እልህና ኃይለኝነት አልጠቀመንም። ዘረኝነትና መከፋፈል አልፈየደልንም፣ ጥላቻና ሽኩቻ አላሳደገንም፤ ግዴለሽነትና ራስ ወዳድነት አላራመደንም። አሁን ሰከን ብሎ፤ ከስሜታዊነትም ወጥቶ፣ሀገሬ የፀነሰቺውን ልጅ እንዴት በሰላም ልትገላገል እንደምትችል መነጋገር፣ መመካከርና መተባበር ያስፈልጋል። ኑ! ሀገሬን እናዋልዳት፤ ኑ፡፡ እስከ መቼ ልጅ ይሙትባት?
((በ ዳንኤል ክብረት))

@yeyhudaanbesa
@wegoch
@wegoch
በልጅነት ስንኞች ውስጥ
( ናትናኤል ጌቱ )
ልጅ እያለሁ ብዙ ግጥሞች ፅፌ ነበር ። በወቅቱ አንዳንዶቹን ምን ለማለት ፈልጌ እንደፃፍኳቸውም አላውቅም ነበር ። ( የምንፅፈው ለማወቅ ነው እንጂ ስለምናውቅ አይደለም እንዲል ጠቢብ ) ከእድሜ ከፍ ያለን ነገር ጥበብ ሹክ ሳትል አትቀርም ። ከፍ ካልኩ በኋላ ታድያ የልጅነት ስንኞቼን እያየሁ ተገርሜያለሁ ።
ያኔ ስፅፈው ያልገባኝ ግጥም እነሆ ህይወት ትርጉሙን አስረድታኝ አሳይታኛለች ። የቅርፃቸውና የቃላት አመራረጥ ውበታቸውን በበሰለ አካሄድ ደስ ያለኝ ጊዜ አድሳቸዋለሁ ። ከነዚያ በወቅቱ ካልተረዳኋቸው ስንኞች ግን ያለ ምንም ማሻሻያ ይህቺን ጋበዝኩ ።

የሰውና የዶሮ ህይወት

ያስቀናኛል ዶሮ ፣ ኑሮና ህይወቱ
ሁለቴ ተወልዶ ፣ አንድ ጊዜ መሞቱ
እኔስ ለሰው ልዘን ፣ ሰው መሆን ከንቱነት
አንዴ ይወለዳል ፣ እልፍ ሞት ለመሞት

እየሞትን ነው…

@wegoch
@wegoch
@lula_al_greeko
2024/09/29 09:32:50
Back to Top
HTML Embed Code: