ምናባዊ ወንጌል
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
እነሆ ጌታን ኢትዮጵያ ውስጥ አገኘሁት። ደቀመዛሙርቱም አብረውት ነበሩ። ብዙ ህዝብም ይከተለው ነበር። ከሚከተሉት
ህዝቦች መሀል አንድ ባለፀጋ ዘረኛ ወደ ጌታ ቀርቦ... "ጌታ ሆይ መንግስተ ሰማያት ለመግባት ምን ማድረግ አለብኝ?" ሲል ጠየቀው። እርሱም
"ትእዛዛቶችን ጠብቅ።" ብሎ መለሰለት። ባለፀጋው ዘረኛም "ትእዛዛትን ሁሉ ጠብቂያለሁ። አንዳችም የሻርኩት ትእዛዝ
የለም።ሁሉን ጠብቂያለሁ።"አለው። ጌታም "እንግዲያውስ ዘረኝነትህን ጥለህ ሀብትና ንብረትህን ይዘህ ተከተለኝ።"አለው።በዚህ ጊዜ ባለፀጋው ዘረኛ አፈገፈገ። ጌታም ወደ ደቀመዛሙርቱ ዞሮ እንዲህ አላቸው "እውነት እውነት እላችኋለሁ ዘረኛ መንግስተ ሰማያት ከሚገባ ዝሆን በትንኝ አይን ቢሾልክ ይቀላል!"
@wegoch
@wegoch
@lula_al_greeko

ቀን 12:45
አባቴ:-ሃሎ አዲሴ የት ነህ?
እኔ:- ሃሎ አባ 22 ነኝ
አባቴ:- በቃ ቶሎ ና እፈልግካለው
ከምሽቱ 2:30
ቤቱ ከሌላው ጊዜ በተለየ የደስታ የጀግንነት የኩራት የብድር በምድርነት መንፈስ ቤቱን ወብቆታል አባቴ ከተቀመጠበት ተነሳና "ትንሹና ዕድለኛው አዲሴ በአንተ ዘመን የደሜን እና የልፋቴን ዋጋ አየው" ብሎ በነዛ ፈርጣማ ክንዶቹና በየዋህ ልቡ አቅፎ ሳመኝ እህቶቼ ወንድሞቼ እና እናቴ በፍቅር ተሰብስበው ቤቱን በቢራና በጣፋጩ የእናቴ የጦም የምግብ ሙያዋ እየደመቁባት ነበር።
እንዴ ምን ተገኝ አባ? ስለው
" እነዚህ ሌቦች ወረበሎች የኔና የመሠል ጓደኞቼን ደም የመጠጡ ሀገሬን የማይገባትን ዋላ ቀርነትን ያወረሷትን ድህነትን ያጎናፀፏትን ርሃብን ስሟን ያረጉላት የቀን ጅቦችን ዛሬ በሠንሠለት ውስጥ አየዋቸው በሚዲያ የማትረቡ እንዳሉን በሚዲያ የስርቆት ተጠርጣሪ ሲባሉ ሰማን ታዲያ ለኔ #ለመቶ_አለቃ_ጉግሳ ከዚህ በላይ ምን ዳግም ውልደት አለ ምን አዲስ ማንነት አለ! " ብሎ እንደ አዲስ አቀፈኝ ደረቱ ባሩድ ባሩድ ሸተተኝ እጆቹ ጀግነነቱን ሰበኩኝ አውንም ጉልበቱ ጦር ሜዳ ያለ ይመስል ነበር
ለካ ሰሞኑ ሚዲያ ላይ የምሰማው የMetek እና የመሰሎቹ የመንግስት ድርጅቶች አመራሮች መያዝ ለኔ ለዚህ ትውልድ አባሉ ዋጋቸው ዜና ብቻ ነበር ለካ ለአባቴ ግን የዘመናት ትግሉ! የታፈነ ድምፁ! የታሰረ ሀቁ! ነበር ወይ ግን የመረዳት እና የመገኘት ጉዳይ ክፍተቱ ትልቅ መሆኑን ዛሬ በአባቴ በትንሹ የእራት ግብዣ ተረድቻለው
ኢትዮጵያዊነት ከሽለላ ውጪ ባዶ ለሚመስለን የኔ ትውልድ የአባቴን የእራት ግብዣ በተንቀሳቃሽ ስልኬ ብጋብዛቹ ምንኛ በተገረማቹ አባቴ ቢራውን እየተጎነጨ ፆም ሆነ እንጂ ደም አሳያቹ ነበር በግ ነበር የማርድላቹ አለ ወዲያው የ3:00 ሰዐት የኢቲቪ ዜና ጀምሮ አንዷ የሸገር ነዋሪ
"እንዴት መርከብ አውሮፕላን ጠፋ ይላል እንዴ ጭልፋ ድስት የጠፋ መሠላቸው እንዴ ሼም ነው።" ብላ እራታችን የህብረ ዜማ ሳቅ አደለችን ወይ ፈጣሪ ለካ
#ውድቀትን_ለድህነት_መነሻ_አርጎም_ሰርቶታል
#ሽንፈትን_ለአሸናፊነት_መነሻም_አርጓታል
ዛሬ ወዳጄ ቤት ቁጭ ብዬ ከዚህ በፊት አንድ ቦለቲከኛ ስለተናገሩት ያጫወተኝን ላጋራቹና ልሰናበት
* #ማረሚያ_ቤቱን_በንፅህና_እና_በጥራት_ያዙት_ነገ_እናንተም_ልትገቡበት_ትችላላቹና!! *
ይሄ ትንቢት እንጂ ወሬ ብቻ ነው እንጃ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
#ኢትዮጵያ_በአባቴ_ዐይነት_የሀገር_ፍቅር_ተከባ_ለዘላለም_ትኑር!!

:- #ተክለ_ዮሀንስ

በተመጣጣኝ ዋጋ የሚፈልጉትን ነገሮች ለገበያየት 👇
#አልባሳት
#ጫማዎች
#ኤሌክትሮኒክስ
#ሰዐቶች
#ቦርሳዎች.. 👇
@onlinesaleandbuystore
🛑የሌለን የለም ብቻ ነው!
JOIN ብለው ቤተሰብ ይሁኑ ።
👇👇👇
https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAEPkyxEP1snCoAkFGw

"ፍቅር በውስጥህ ቦታን ሲያገኝ የውበት መገለጫው
ትሆናለህ። ፍቅር የያዘው ሰው ውበት የሚንፀባረቅበት
መስታዋት ነው። ምክንያቱም ዉበትም ሆነ ነፀብራቁ
መነሻቸው ፍቅር ነውና...የሁለቱም ምንጭ ፍቅር
ነው።"ከሱፊዎች
ተራራዎችን ያነቃነቀውን ፍቅር እፈልገዋለሁ
ውቅያኖሳትን የከፈለውን ፍቅር እፈልገዋለሁ
ንፋሳትን ያርበደበደውን ፍቅር እፈልገዋለሁ
እንደ መብረቅ የሚጮኸውን ፍቅር እፈልገዋለሁ
ሙታንን ያስነሳውን ፍቅር እፈልገዋለሁ
ወደ መንፈሳዊ ፍንደቃ የሚያሻግረንን ፍቅር እፈልገዋለሁ
የአምላክ ቋንቋ (ዝምታ) የሆነውን ፍቅር እፈልገዋለሁ
ሩሚ
"ፍቅር ቤቱን የሰራበት ልብ እንዴት የታደለ ነው?
ምክንያቱም ከዓለም ጭንቀት ሁሉ መዳኛው ፍቅር ነውና።
ፍቅር ትዕግስትና ማመዛዘንን ወደምንምነት የሚቀይራቸው
የነጐድጓድ ኃይል ነው። አፍቃሪ ስለራሱ ደህንነት ማሰብ
አያውቅበትም፤ የትችት ተራራ ለእሱ ከገለባ ክምር የቀለለ
ነው። እንዲያውም ትችት የፍቅሩን ኃያልነት
የሚጨምርለት ጉልበቱ ነው" ይላሉ።ከሱፊው ጃሚ
ሸጋ ጁምኣ!!💚💛❤️💚💛❤️
@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ትሆናለህ። ፍቅር የያዘው ሰው ውበት የሚንፀባረቅበት
መስታዋት ነው። ምክንያቱም ዉበትም ሆነ ነፀብራቁ
መነሻቸው ፍቅር ነውና...የሁለቱም ምንጭ ፍቅር
ነው።"ከሱፊዎች
ተራራዎችን ያነቃነቀውን ፍቅር እፈልገዋለሁ
ውቅያኖሳትን የከፈለውን ፍቅር እፈልገዋለሁ
ንፋሳትን ያርበደበደውን ፍቅር እፈልገዋለሁ
እንደ መብረቅ የሚጮኸውን ፍቅር እፈልገዋለሁ
ሙታንን ያስነሳውን ፍቅር እፈልገዋለሁ
ወደ መንፈሳዊ ፍንደቃ የሚያሻግረንን ፍቅር እፈልገዋለሁ
የአምላክ ቋንቋ (ዝምታ) የሆነውን ፍቅር እፈልገዋለሁ
ሩሚ
"ፍቅር ቤቱን የሰራበት ልብ እንዴት የታደለ ነው?
ምክንያቱም ከዓለም ጭንቀት ሁሉ መዳኛው ፍቅር ነውና።
ፍቅር ትዕግስትና ማመዛዘንን ወደምንምነት የሚቀይራቸው
የነጐድጓድ ኃይል ነው። አፍቃሪ ስለራሱ ደህንነት ማሰብ
አያውቅበትም፤ የትችት ተራራ ለእሱ ከገለባ ክምር የቀለለ
ነው። እንዲያውም ትችት የፍቅሩን ኃያልነት
የሚጨምርለት ጉልበቱ ነው" ይላሉ።ከሱፊው ጃሚ
ሸጋ ጁምኣ!!💚💛❤️💚💛❤️
@balmbaras
@wegoch
@wegoch
እናቱን የሚወድ እናታችንን ይርዳልን
ወይንም ሼር ያድርግ ይሄንን መልክት
እናታችን ሙንተሃ ሸረፋ በጠና ታማብናለች ሁለቱም ኩላሊቶቿ አገልግሎት መስጠት አቁሟል። እናታችን ሙንተሃ ለ1 አመት ስድስት ወር ዲያለሲስ ስታደርግ ቆይታለች ነገር ግን አሁን ከአቅሟ በላይ በመሆኑ የእናንተን እርዳታ ትሻለች።
እናታችንን ለመርዳት የምትፈልጉ
የንግድ ባንክ ቁጥር 1000138716892
ሙንተሀ ሸረፋ
ላይ የቻላችሁትን አድርጉልን ይላሉ ቤተሰቦቿ።
አሁን በሞባይል ባን ኪንግ መላክ ትችላላችሁ።
ለትብብራችሁ እናመሰግናለን።

(የንግግር ህክምና)
አሁን አሁን ዓለምአቀፍ ተቀባይነትን እያገኙ ካሉ የህክምና መንገዶች አንዱ የንግግር ህክምና ነው:: የተለያዩ የአእምሮ ህመሞችን ለማከምም ሆነ አስቀድሞ ህመሞችን ለመከላከል የንግግር ህክምና
ተመራጭ ነው:: ይህ ህክምና በምእራቡ ዓለም ብዙዎን ጊዜ የሚሰጠው በስነአእምሮ ሙያተኞች ነው:: ይህ የህክምና አይነት አተገባበሩ የተለያየ ሲሆን እንደአሰጣጡ የተለያየ ስም ድንብና
ስነምግባሮች አሉት:: ለአብነትም የሚከተሉት ዋንኞቹ ናቸው:
1. Cognitive behavioral therapies (CBT)
2. Dialectic behavior therapy (DBT)
3. Psychodynamic therapies
4. Humanistic therapies
5. Other kinds of talking therapy
7. Group therapies
ይህ የህክምና ዘርፍ ዋንኛ ስርአቱ ህመምተኛው ችግሩን ስሜቱን ፍርሀቱን ድንጋጤውን የቀደመ ልምዶቹን ወዘተ ለአማካሪው እንዲናገር በማድረግ ያለፉና ወቅታዊ አእምሯዊ እና ስሜታዊ ብሎም አካላዊ ችግሮቹን በራሱ እንዲፈታ ማድረግ ነው:: በዚህ ህክምና ከሚፈቱ ችግሮች መካከል ጭንቀት ፍርሀት ሱስ
የስሜት መለዋወጥ እና ድብርት ዋንኞቹ ናቸው::ይህ ህክምና ለኛ ለኢትዮጵያውያን አዲስ አይደለም:: ጥንታዊ ነው:: ማህበረሰባችን በስልቦና ጠንካራ እንደመሆኑ ችግሮቹን ለመፍታት በህገልቦና ያጎለበታቸው የንግግር የህክምና መንገዶች አሉ:: ለአብነት የእናቶችን ቡና የመጠጣት ባህል ማንሳት እንችላለን:: እናቶቻችን ቡና ሲያጠጡ የኑሯቸውን ሁኔታ በግልፅ ይነጋገራሉ:: ይወያያሉ:: አሁን አሁን ይህን የእናቶቻችን እሴት ሀሜት ወዘተ እየተባለ እየተቀዛቀዘ ሊሄድ ችሏል:: ይሁን እንጂ እናቶቻችን በግልፅ በማውራታቸው ብሶታቸውን በመግለፃቸው ጭንቀትና ድብርት ብሎም
ፍርሀተን መቀነስ ይችሉ ነበር:: ይህን የእናቶቻችን እሴት Group therapies ከሚባለው ህክምና ጋር የሚመሳሰልበት አግባብም አለው:: ይህም ብቻ አይደለም ወደፊት በስፋት የምናወራበት ቢሆንም
የንስሀ አባትና ልጅ የመመካከር ግንኙነትም እንዲሁ ከዚህ ከንግግር ህክምና ጋር ብዙ የሚጋራው ነገር አለ:: የኛ ኢትዮጵያውያን የጉርብትና ህይወት በእጅጉ ጠቃሚ ነው:: በተለይ ጭንቀትና ድብርትና ከማስወገድ አንፃር:: ይህን የጉርብትና ህይወት በአንድም በሌላም መንገድ ማጎልበት አለብን:: ይህን የማህበራዊ ድረገፅንም ለዚሁ አገልግሎት ማዋል እንዳለብን ይሰማኛል:: ከዚህ በፊት በለጠፍኩት ማስታወሻ ድብርትና ጭንቀት ያለባችሁ እህት
ወንድሞች መነጋገር ሰው ማናገር የምትፈልጉ እህት ወንድሞች ልታዋሩኝ ትችላላችሁ ብዬ ነበር:: እሱን መሰረት አድርጋችሁ ለፃፋችሁልኝ አመሰግናለሁ:: ይህን ዓላማ የተረዳች አንድ እህታችንም
ይህን አገልግሎት መሳተፍ ትፈልጋለች:: እህታችን ትእግስት ትባላለች::
በስነልቦና ሳይንስ የመጀመርያ ዲግሪ ያላት ሲሆን በሁለተኛ ዲግሪ በማህበረሰባዊ ስነልቦና የማስተርስ ዲግሪ ባለቤት ስትሆን አሁንም ደግሞ ለተጨማሪ የማስተርስ ዲግሪ ክሊኒካል ሳይኮሎጂ በመማር ላይ ትገኛለች:: እርሷን በተለያዩ በሚያስጨንቃችሁ ጉዳይ ላይ ልታማክሯት ትችላላችሁ:: በጭንቀት በድብርት እና መሰል ህመሞች ማንም ራሱን ማጥፋት ማንም ራሱን መጉዳት የለበትም ብለን እናምናለን:: ሙሉ የህክምና እገዛ አንሰጣችሁም:: ችግራችሁን ግን ልንሰማችሁ እንችላለን:: እርሱም በራሱ በጎ ሚና አለው:: በመሆኑም በቅርባችሁ ላለ ሰው ስሜታችሁን አጋሩ:: አውሩ:: እንነጋገር:: ዝምታ ይገድላል::
# ራፋቶኤል

<<ዘውድ አለም ታደሰ>>
አንዳንዱ ስራ ፈት ደግሞ ሜቴኮች የበሉትን ብር ቀኑን ሙሉ ሲያካፍል ውሎ እንባ እየተናነቀው “ወይኔ! ይሄ ብርኮ ለኢትዮጵያ ህዝብ ቢከፋፈል ለእያንዳንዳችን አምስት ሺ ብር ደርሶን አመቱን ሙሉ ጠግበን እንበላ ነበር” ብሎ በተበላ ብር ይናደዳል። ሰዉ ጓያ መብላት ጀመረንዴ ጎበዝ? አንዳንዱማ የግል ጠብ ሁሉ አርጎታል። የሰላሳ ብር ቦንድ ገዝቶ “ሜቴኮች ገንዘቤን በልተው አይኖሯትም” ምናምን እያለ ይዝታል። ማይ ፍሬንድ ... የደሃ ደሃ የሚል መታወቂያ አውጥተህ ከሸማቾች ማህበር ጨው በዱቤ እየወሰድክ ገንዘባችን ምናምን ትላለህ
እንዴ? በዚህ አይነት ደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች ምን ይበሉ? ካልሆነ ሰላሳ ብርህን እንስጥህና ተፋታን! ኔቶርኩን አጨናነቅከውኮ!😂😂
@wegoch
@wegoch
@yeyhudaanbesa

አንቱ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)
------
አረጋዊው ዐብዱልሙጠሊብ በመካ ነዋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ስምና ዝና ነበረው፡፡
የመጨረሻ ልጁ የሆነው “ዐብዱላህ” የሚባል ሳተና አሚና የምትባለውን ኮረዳ ባገባ
በሶስት ወሩ ከዚህ ምድር ሲሰናበት በጣም አዘነ፡፡ ዐብዱላህን በእጅጉ ይወደው ስለነበረም
ከሃዘኑ መጽናናት አቃተው፡፡ ይሁን እንጂ ባሏ በሞተበት ወቅት የሁለት ወራት ቅሪት
የነበረችው አሚና ከሰባት ወራት በኋላ ወንድ ልጅ ስትገላገል የዐብዱል ሙጠሊብ ሐዘን
ጠፋ፡፡ የልጄን ምትክ አገኘሁ በማለት በደስታ ባህር ተዋጠ፡፡ አዋላጆቹ ልጁ በተወለደበት
ወቅት ያዩትን ተአምራት ሲነግሩትማ “ይህ ልጅ ካደገ በኋላ ምን እንደሚሆን ማየት አለብኝ”
የሚል ጉጉት በነፍሲያው ውስጥ ተፈጠረ፡፡
----
ጥቂት ወራት አለፉ፡፡ ዐብዱልሙጠሊብ በዘመኑ ደንብ መሰረት ድል ያለ ድግስ አዘጋጅቶ
በርካታ የመካ ነዋሪዎችን ጠራ፡፡ መብሉና መጠጡ ለህዝቡ እየታደለ ሁሉም ተደሰተ፡፡
በመጨረሻም ዐብዱልሙጠሊብ ለተሰብሳቢዎቹ እንዲህ ሲል ተናገረ፡፡
“ይህ ልጅ እስከ አሁን ድረስ በቤተሰቤ ውስጥ ከተወለዱት ህጻናት መካከል እጅግ በጣም
የተለየ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ስለዚህ በስራው የሰማይንም ሆነ የምድሩን ፍጡራን አስደስቶአቸው
ያመሰግኑት ዘንድ ስሙን “ሙሐመድ” (እጅግ የተመሰገነው) ብዬዋለሁ”፡፡
-----
በእውነትም ያ ልጅ በህይወት ሲሰነብት ተራ ልጅ እንዳልሆነ ታወቀ፡፡ “ጃሂሊያ” የሚባለውን
ከባድ ድንቁርና ከስሩ መንግሎ ለመጣል የለኮሰው ኢስላማዊ ርዕዮት የዓለምን ታሪክ ከስር
መሰረቱ ቀየረው፡፡ እነሆ ስሙ በመላው የዓለም ማዕዘን የሚታወቅ ሆኖ አስራ አራት ክፍለ
ዘመናትን ዘለቀ፡፡
----
ያ ህፃን የተወለደው በወርሃ ረቢዑል አወል በ12ኛ ምሽት ከሂጅራ በፊት በአርባኛው ዓመት
ዐረቦች "የዝሆን ዓመት" (ዓመል ፊል) እያሉ በሚጠሩት ዘመን ነበር።
----
እንኳን ለነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የልደት በዓል አደረሰን!! አደረሳችሁ!!
አላሁመ ሰልሊ ዐላ ሙሐመዲን
አሚና በመካ
ወለደችው ለካ
(የወሎ መንዙማ)
((( አፈንዲ ሙተቂ ))

Yohannese T Degu
እቺ ነች ኢትዮጵያ፥ እቺ ነች ሐገር
ከልደታ ክፍለ ከተማ ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ የሚደርስ ሰልፍ ተሰልፈህ፥ የጠዋት ፀሐይ ሞቀህ፥ የሰልፉ ጫፍ ትደርሳለህ፡፡ ታክሲ ይመጣል፥ እስካሁን ያልሾፍካቸው ነፍፍፍፍ ሰዎች ግርርርርር ብለው ይመጣሉ፡፡ ያን ፀሐይ ጠጥተህ፥ ተወርፈህ፥ ድጋሚ ራስህን ለፍልሚያ ታዘጋጃለህ፥ ከፊት ብትሆንም ተረጋግጠህ፥ ተራኩተህ ትገባለህ፥ ልጅ የያዘችውን ሴት አሽቀንጥሮ የገባው ወጠምሻ አጠገብህ ይቀመጣል፡፡
የቆመ መኪና ተደግፎ ጎማ ስር የሚሸና ቢጤውን እያየ "ይህ ህዝብ እኮ መቼም አይሰለጥንም" ይልሃል፡፡ ልጅ የያዘችው ሴት ቀጣይ ታክሲ እየጠበቀች ነው፡፡ እቺ ነች ኢትዮጵያ ጌታዬ!
*
ያን ረዥም ሰልፍ ተሰልፈህ፥ የተለያየ ዓይነት የልመና ስልት የሚከተሉ፥ ፈጠራ የታከለባቸው ምፅዋት ጠባቂዎች ኪሲህን ይጠይቁሀል፥ ለቻልከው ትሰጣለህ፥ ኪስህ ውስጥ ያለው ጨላ ሲሳሳ ባላየ ላሽ ትላለህ፡፡ አጠገብህ ተከናንቦ፥ ለስላሳ ዋሽንት ከፍቶ፥ ያደፈ የድሮሮሮ ብርድልሰብስ ለብሶ፥ ፊት ለፊቱ ፎጣ ዘርግቶ፥ ፊቱን ብርድ ልብስ ሸፍኖ፥ ሽርፍራፊ ሳንቲምና ብር ተዘርግቶ፥ ዋሽንቱ የሳባቸው እናት ይመጣሉ፡፡
አምስት ብር ይዘዋል፥ ፎጣው ላይ የሚዘረዘር ሳንቲም ያጣሉ፥ ይጠሩታል አይሰማም፡፡ በመቋሚያቸየተነሳች ልብሱን ከጭንቅላቱ ብድግ ያደርጋሉ፡፡ ኤድፎን ጆሮው ላይ አድርጎ፥ በሳምሰንግ ስልኩ ሜሴንጀር ላይ ቻት እያደራው ነው፡፡ ተገርመህ ሳታበቃ፥ ስልኩ ላይ ከንፈሯን አሞጥሙጣ ሰልፊ የተነሳች ቸከስ ታያለህ፡፡ ይሄን ስልክ ለመግዛት እቁብ እንደገባህ፥ በዚህ ወር እጣው ያንተ እንደሆነ ትዝ ይልሃል፡፡ እቺ ነች ኢትዮጵያ ጌታዬ!

አንድ ቀን አንድ ድሃ ሰው የወይን ዘለላዎችን ወደ ነብዩ መሀመድ(ሰ.ዐ.ወ.) አመጣና እንደገፀበረከት ሰጣቸው።
እሳቸውም አንዲቷን ፍሬ ቀጥፈው በሉ።
አንድ ደገሙ...
ሰለሱ...
.
.
እያሉ... እያሉ... ሁሉንም የወይን ፍሬ ተመግበው ጨረሱ።
ያ ያመጣላቸው ድሃ ሰውም ተደስቶና ረክቶ ሄደ።
.
.
አብረዋቸው ከነበሩት ሰዎች አንዱ ሰውም
" የአላህ መልክተኛ ኾይ(ሰ.ዐ.ወ) እንዴት ለኛ አንድ ፍሬ እንኳ ሳይሰጡን ሁሉንም ወይን ይበላሉ? " ብሎ ጠየቃቸው።
.
.
እሳቸውም...ፈገግ አሉና...
" እኔ ሁሉንም የወይን ፍሬዎች የበላሁት ፍሬዎቹ መራራ ስለነበሩ ነው።እነዚህን መራራ ፍሬዎች ከእናንተ ለአንዳችሁ ብሰጥና ብትበሏቸው ኖሮ በጣዕማቸው ምረት ፊታችሁን ታጠቁሩና የዛን የድሃ ስሜት ትጎዱት ነበር።
ስለዚህ እነዛን መራራ ፍሬዎች ብቻዬን በፈገግታ ተመግቤ ለመጨረስና ደሀውን ለማስደሰት ወሰንኩ" አሉ።
ለእስልምና ተከታዮች እንኳን ለመውሊድ በኣል አደረሳችሁ!!!💚💛❤️

ሁለገብነት
የነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ.) ታሪክ አንዳችን የህይወት
ገፅታ
ያላጓደለ
ምሉዕና ሁለገብ ነው ፡፡የግል ህይወታቸው ናፋቂ ልጅ
፣አዛኝ አባት ፣አፍቃሪ ባል ፣ታማኝ ጓደኛ ፣ቸር ጎረቤት
፣ታታሪ ሰራተኛ ፣በጎ አድራጊና ቅን አሳቢ እንደሆኑ
ይጠቁማል፡፡ በሌላ በኩል ከአላህ
የተጣለባቸውን ሀላፊነትና አደራ ለመወጣት ያደረጉትን
ጥሪ ፣እንቅስቃሴና የሌተ
ተቀን ትግል ፣ህዝቦቻቸውን ለማሳመን የተጠቀሙበትን ዘዴ
፣ የከፈሉተን መስዕዋትነት እና የመሳሰሉትን የሚያትት
ነው፡፡ በተጨማሪም የማህበረሰብ ግንባታ ፣የስነ-ልቦና
የአስተዳደር እና አመራር ጥበብ ፣የስነ-ምግባር ኩትኮታ
ስልት ፣የኢኮኖሚ ቀመርን የመሳሰሉትን
ያካተተ ነው ፡፡ ባጠቃላይ የታላቁ ነብይ (ሰ.ዐ.ወ.)ታሪክ
በአንድ
ህብረተሰብ
ውስጥ የሚንፀበራቁ የህይወት ዘርፎችን ሁሉ የሚዳስስ
ነው፡፡
ለዛም
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ.) በየትኛውም ዘመን ፣በየትኛው ቦታ
፣በየትኛው
የማህበረሰብ ክፍል ለሚገኝ ሁሉ የተሟላ ሞዴል የሆኑት !!!!
💚💛❤️💛❤️💚❤️💚
@balmbaras
@wegoch
@wegoch
የነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ.) ታሪክ አንዳችን የህይወት
ገፅታ
ያላጓደለ
ምሉዕና ሁለገብ ነው ፡፡የግል ህይወታቸው ናፋቂ ልጅ
፣አዛኝ አባት ፣አፍቃሪ ባል ፣ታማኝ ጓደኛ ፣ቸር ጎረቤት
፣ታታሪ ሰራተኛ ፣በጎ አድራጊና ቅን አሳቢ እንደሆኑ
ይጠቁማል፡፡ በሌላ በኩል ከአላህ
የተጣለባቸውን ሀላፊነትና አደራ ለመወጣት ያደረጉትን
ጥሪ ፣እንቅስቃሴና የሌተ
ተቀን ትግል ፣ህዝቦቻቸውን ለማሳመን የተጠቀሙበትን ዘዴ
፣ የከፈሉተን መስዕዋትነት እና የመሳሰሉትን የሚያትት
ነው፡፡ በተጨማሪም የማህበረሰብ ግንባታ ፣የስነ-ልቦና
የአስተዳደር እና አመራር ጥበብ ፣የስነ-ምግባር ኩትኮታ
ስልት ፣የኢኮኖሚ ቀመርን የመሳሰሉትን
ያካተተ ነው ፡፡ ባጠቃላይ የታላቁ ነብይ (ሰ.ዐ.ወ.)ታሪክ
በአንድ
ህብረተሰብ
ውስጥ የሚንፀበራቁ የህይወት ዘርፎችን ሁሉ የሚዳስስ
ነው፡፡
ለዛም
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ.) በየትኛውም ዘመን ፣በየትኛው ቦታ
፣በየትኛው
የማህበረሰብ ክፍል ለሚገኝ ሁሉ የተሟላ ሞዴል የሆኑት !!!!
💚💛❤️💛❤️💚❤️💚
@balmbaras
@wegoch
@wegoch
#የገባው_ዳናውን_ይመርምር
እንኳን ለ፻፬፱፫ የመውሊድ በዓል በሠላም አደረሳቹ
#አንድነታችን_ለጋራ_ቤታችን_ምሶሶ_ነው!
#ልዩነታችን_ለጋራ_ጎጆዋችን_ጌጥ_ነው!
ድህነት እና ፖለቲካችን የሠጡን ጥላቻ ይበቃናል ስፖርቱን ለተወለደበት ሠላም እንገዛለት
ሠላም ለኢትዮጵያ! ሠላም ለሕዝባችን!
#አላህ_ኢትዮጵያን_ይባርክ

ያ ሌት
የሆነ ባዕድ ነገር ወደ ሰውነቴ ውስጥ ዘልቆ የእግሬን ጅማቶች ሲበጣጥሳቸው ይሰማኛል። የአጥንቴ ህዋሳት(osteocytes) የድረሱልን ጥሪ እንዳስተላለፋ አዕምሮዬ ማሳወቅ ከጀመረ ሰነባብቶአል። አዕምሮዬ የመላው አካላቴ አጥንቶች ከመሰርሰራቸው ብሎም ከመሰባበራቸው በፊት ከገባሁበት የእንቅልፍ አዝቅት ውስጥ አስነሳኝ።
ወድያውኑ ከእንቅልፌ እንደተነሳው ከአልጋዬ ቀና ብዬ እግሬን ስዳስሰው የብርድ ልብስ ሽፋን ያልተዳረሰበት እንደ ድንግል መሬት ምንም ያልተነካ ሆኖ አገኘሁት። ከዚያም የስልኬን ባትሪ አብርቼ የብርድ ልብሴን ከወደቀበት አንስቼ እግሬን ላለብሰው ስል አንዳች ነገር አፉን በሀይል ከፍቶ ከቀዝቃዛው የአርክቲክ አህጉር እንደሚመጣ አጥንት ሰባሪ እጅግ ቀዝቃዛ አየር ወደ እኔ ያለ ርህራሄ እየተነፈሰ እንዳለ ተረዳሁ። ልቤ እንደ ዲጄ ደም በሀይል ማጫወት ጀምራለች(ወይ ከሮፍናን አልያ ከዲጄ ሼሪ አይታ ነው መሰለኝ) ። ትንሽ ለመረጋጋት በማሰብ የግንባታው ዘመን እንደረዘመው የህዳሴ ግድብ በረጅሙ ተነፈስኩ-ለ 9 ሴኮንዶች ። እንደምንም ብዬ ልክ እንደ ፖግቦ የፍፁም ቅጣት አመታት ባትሪ የያዘው እጄን እየተቀጠቀጥኩ በዝግታ ወደ ቀዝቃዛው አየር ተንፋሽ ነገር አበራሁ። ለካስ የቤቴ በር ሳይዘጋ ኖሯል።
"እንዴት በሩ ክፍቱን ሊያድር ቻለ?"- መ መልስ የለም።በሩ ክፍቱን በማደሩ የሌለ ደንግጬ ነበር ከሜቴክ የበላይ ሀላፊዎች በላይ(ሆ ምን ሆኜ ነው? ሀገርን ካወደሙ ሰዎች እኩል ራሴን ማወዳደር ባይገባኝም ግን ክው ብዬ ነበር።) ከድንጋጤዬ እንደወጣሁ በሩን በመዝጋት ፈንታ በሀሳብ ነጎድኩ።
"እንደው ፈጣሪ ሲጠብቀኝ እንጂ በሩ ቀዝቃዛ አየር ማስገባቱን ትቶ እንደ ድራገን እሳት የሚተፋ ቢሆንስ? አይ እኔ! መልካም ሰው በጠፋበት ዘመን ስለድራገን አስባለው"ብዬ የምፀት ሳቅ በራሴ ላይ ሳቅኩ። ቢሆንም ሳይተኛ ለሚጠብቀኝ አምላክ "ተመስገን" አልኩ።
በሩን በድጋሚ በደንብ እያየሁት ነው። ከበሩ የፊት ለፊት የብረት ጌጣጌጦች ከፊሉ የሉም። ተሰብረው ይሁን እኛ አናስፈልግም ብለው ይሁን አላውቅም(ምን ያህል እንደሚያሳምሩት ግን ባወቁ)። ከግማሽ በላይ የሚሆነው የበሩ የመስታወት ክፍል ተሰብሮ የበሩን ውበትና ግርማ ሞገስ ነጥቆታል። የተሰበረውን የመስታወት ክፍል ይሸፍን የነበረው ጨርቅም የለም። እንዲህ አይነቱ ነፋስ እንኳን ለጨርቁ ለመስታወትም ያሰጋል። ግን መስታወቱ አንድ ቢሆን ኖሮ እንኳን ቀዝቃዛ ነፋስን ይቅርና ሌላ ገንጣይ ሀይልን መቋቋም አያዳግተውም። ምናለ የጠፋው የመስታወት ክፍል የእርሱን ዋጋ በተረዳ አልኩ ባይሰማኝም። የበሩ እጀታ የለም። ያለ እጀታ በር እንዴት ይገጥማል? እጀታው ቢኖር ኖሮ ነፋስ ገብቶ አይሰረስረኝም ነበር።የእሱ አለመኖር የበሩን ግልጋሎት ይቀንሰዋል ። በሩ የተሰራበትን አላማ ከግብ እንዲመታ ከትናንሽ ብሎናችና ማቀፊያዎች እስከ ትላልቆቹ የብረት ጌጦች፣መስታወትና እጀታ እና ሌሎችም ለበር መስሪያነት የሚውሉ ጥሬ እቃዎች ድረስ ጥልቅ ወዳጅነት፣ አብሮነት ፣ፍቅር እና መተሳሰብ ሊኖር የግድ ይላል። መስታወቱና የብረት ላይ ጌጦቹ በሀይል ብዛት እንዳይጎዱ ማጠፊያውና እጀታው ፋይዳቸው የላቀ ነው። ትልቁ የበር እጀታ ከቦታው እንዳይነሳ ደግሞ የትናንሾቹ ብሎኖች ጥቅም በቃላት አይገለፅም። ስለዚህ እኚህ የበሩ አካላት ለበሩ በሁለት እግር መቆም በፍቅር ሊሰሩ ይገባል። አንደኛው ለሌላኛው መሰረት ነውና። አንዱ ያለ አንዱ ከምንም በታች ነውና።
ሳላስበው በተመስጦ በሀሳብ ነጉጄ ነበርና ሰዐቱ ሄዶ ሌሊት 8:27 መሆኑን አልተገነዘብኩም። ትንሽ ለመተኛት በማሰብ ከሄድኩበት ከሩቅ ምስራቅ ሀሳብ ተመልሼ በሬን ልዘጋ ተነሳሁ።"ምናለ እኛም እንደ ደህና በር በሆንን አንዳችን አንዳችን እየደገፍን ለዘላለም በቆምን" ብዬ እየተመኘሁ።
በUTOPIA
ህዳር አስር ሁለት ሺህ አስራ አንድ ዓመተ ምህረት
@wegoch
@wegoch
@gebriel_19

የህዳር ሰማይ ይታጠን !!! ያገሬ በራ
በሮች ሁሉ መኣዛ በሚያፈልቀው
የሉባንጃና የወይባ ማእጠንት
አብዝተው ይታወዱ። የኛም ነፍስያ
በውብና ሸጋ ሃሳቦች ትታጠን!!!
ሰላምና ፍቅር በጦቢያ ላይ ይስፈን!!!
💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️
ሸጋ ሸጊቱ ቀን!!!!!!💚💛❤️
@balmbaras
@wegoch
@wegoch
በሮች ሁሉ መኣዛ በሚያፈልቀው
የሉባንጃና የወይባ ማእጠንት
አብዝተው ይታወዱ። የኛም ነፍስያ
በውብና ሸጋ ሃሳቦች ትታጠን!!!
ሰላምና ፍቅር በጦቢያ ላይ ይስፈን!!!
💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️
ሸጋ ሸጊቱ ቀን!!!!!!💚💛❤️
@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ሰው ማህበራዊ እንስሳ ነው፣ ማስተንተን የጎደለው ስሜትና እምነት ሲጫነው ጭራሹን
እንስሳነቱ ያይላል!!
ቃል ቀድሞ ቢኖርም ሃይማኖት ከሰው ቀጥሎ ነው፥ ያለ ሰው መኖርና ህላዌ ሃይማኖት
ማደሪያ አልባ "ቃል" ነው!!
ሰው ለማመን፣ ለተስፋና ለፍርሃት ቅርብ ነው፥ "ነብሰ- ነጋዴዎች" ይሄን ያውቃሉና ቅርብና
ርብትብት ነብሱን እንዲህ ይበዱሏታል!! እሱም መበዱሉን ከመጽደቅ ይቆጥረዋልና
መረገጡን ይወዳል!!
ለማመን ማወቅ ግዴታ ባይሆንም ስታውቅ እንዴትም ቢሆን ለሌቦች አትመችም!!