#የሁለቱ_ሚኒስቴር_መስሪያ_ቤቶች_ፍጥጫ!!!
የኢትዮጵያ ሚስቶች የመከላከያ ሚኒስቴርን ተገን በማድረግ በባሎቻቸው ላይ ሊጥሉት ባሰቡት የሰዐትና የስልጣን ተዋረዳ እገዳን እንቃወማለን በማለት ነገ ሠላማዊ ሠልፍ እንደሚወጡ የኢትዮጵያ ባሎች ሚኒስቴር ፅፏል
በመጨመርም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሴቶች የሚኒስተርነት ይዞታ በመጨመሩ ሁሉም የኢትዮጵያ ሚስቶች ሚኒስቴር በድብቅ ስለደነገጋቸው እና ስለደረሰባቸው ሚስጥርም እንዲህ ሲል ተናግሯል
እኛ ባሎች ልንታፈንና ለተዘጋጀልን ወጥመድ ተጋላጭ መሆን የለብንም ሲል በደብዳቤው ላይ ገልጿል ቀጥሎም ሚስጥራዊ ወጥመዶችን በመግለፅ ቀጣይ ዕቅዱን እንዲህ ሲል ፅፏል :-
የሚስቶች ሚኒስቴር ድብቅ አጀንዳ በባሎች ላይ ስለሚወሰድ እገዳ
፩ ማንኛውም የውጪም ይሁን የሀገር ውስጥ ባል ከሚስቱ ፍቃድ ውጪ ከቤት እንዳይወጣ
፪ የትኛዋም ሚስት ቤት ውስጥ ያለው ስልጣን በሷ የበላይነት ማለትም ጠቅላይ ቤተሰብ መሪ እማወራ እንደምትሆን
፫ መዝናናት ያማረው ባል የሚስቶች ሚኒስቴር ባወጣው ሕግ መሰረት ማለትም ስለአልኮል መጠን፣ስለመዝናኛ ቤትና ቦታ ምርጫ፣ስለ ወጪ ፍጆታና ስለሚወስደው ሰዐት ከሕጉ ውጪ እንዳይሆን
፬ ማንኛውም ባል ከሚስቱ ጋር የአልጋ ላይ ጨዋታ ካማረው ከሳምንት በፊት ባለሶስት ገፅ ማመልከቻ ለሚስት ቤተሰቦች ማመልከት እንዳለበት
፭ በመጨረሻም ባሎች ከሚያገኙት ገቢ በየወሩ ሚስቶችን በውድ እና በድንቅ ቁሳቁስ የማስዋብ ግዴታ አለባቸው ይላል
ይሄን እና ያልደረስንባቸውን ሚስጥራዊ አዋጆችን ቀድመን ለማስቀረት ስንል የነገውን ሠላማዊ ሠልፍ አስበናል በመቀጠልም ከሠልፉ የማይገኝ ትርፍ ካለ ወደ ትጥቅ ትግሉ ለመግባት ዝግጅቶቻችንን ጨርሰናል ለዚህም የብዙ አገራት የባሎችን አዎንታ አግኝተናል ሲል በደብዳቤው ላይ ጠቅሷል
በመጨረሻም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ነገሩን በሠላማዊ መንገድ ለመፍታት በማሰብ እስከ ነገ ጠዋት ማንኛውም ባል ከሚስቱ ጋር ከሠላምታ ውጪ የተለየ እንቅስቃሴ ማለትም ከመጎራረስ እስከ መሳሳምን እንዳይፈፅም ጠቅሷል
#ድል_ዘመናትን_ሲረግጥና_ሲመራ_ለነበረው_የኢትዮጵያ_ባሎች
ግልባጭ ፎቶ ኮፒ
1ለጠቅላይ ሚኒስቴሩ ቢሮ
2 ለተወካዮች ምክር ቤት
3 ለማዘጋጃ ውል እና ማስረጃ ቢሮ
4 ለፌደራል ፖሊስ ቢሮ
***************************************
#ኢትዮጵያ_ለዘላለም_በባሎች_የበላይነት_ትኑር!!
***************************************
:-#ተክለ ዮሀንስ
@wegoch
@wegoch
@lula_al_greeko

በአንድ ወቅት፣አምና በሞት የተለየን ተወዳጁ ገጣሚ ሰለሞን ደሬሳ ቀጥሎ ያለውን ትንታኔ
ለያሬድ ጥበቡ አካፍሎት ነበር-ዜጋ መጽሔት በ1995( እንዳስነበበችን፡፡
….
መሸንሸን ከጀመርክ ሽንሸናው የሚያልቅበት ቦታ የለም፡፡ ሲጀመር የኢትዮጵያ መንግሥት
ኤርትራውያንን ያንን ያህል ሲዋጋ አጋሚዶ እንዳላቸው፣ አንድ ቀን ቁጭ ብሎ ሳያነጋግራቸው
ብዙ ጊዜ አለፈ፡፡ ምንድነው ችግራችሁ? ምንድነው ከሌላው ኢትዮጵያዊ የበለጠ
የተበደላችሁት? ተብለው ቢጠየቁ ኖሮ ምናልባት ለውጥ ያመጣ ነበር፡፡ እኔ የማውቀው
ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ጠርተው፣ ምንድነው የጎደላችሁ ሳይሏቸው፣ በማባበል ብቻ
(በመስማት ሳይሆን) ጊዜ የባከነ መሆኑን ነው፤ በማባበል ስልህ አዲስ አበባ
በተማርኩበት ትምሕርት ቤት ከመቶ ሃምሳው ባለዲግሪ ኤርትራውያን ነበሩ፡፡ ጭንቅላት
ከሌላው ኢትዮጵያዊ በልጠው አይደለም፡፡ ለማባበል ነበረ፡፡ እሱ ጥሩ፣ አልከፋም፡፡
…
አብዛኛዎቹ ብንከራከርም ልንለይ አንችልም፤ ኃይሉ የለንም ብለው ነበር የሚሉት፡፡
መጀመሪያ የኢትዮጵያዊነት ፓስፖርት ሰጪ ሆነው የተሾሙ አሉ፡፡ አንዳንዱ አሁን እኔ ከአንተ
ጋር ስለተነጋገርኩኝ ኦሮሞነቴንም አልቀበል ሊል ይችላል፡፡ ይህ እውነትነት ካለው እኔ
በአያቴ በኩል 45 ትውልድ ወደ ላይ እቆጥራለሁ፡፡ በእናቴ በኩል ደግሞ 19 እቆጥራለሁ፡፡
በእናቴ እናት በኩል ሌላ 19 እቆጥራለሁ፡፡ ለስሙ ስማቸው ኦሮሞ ነው፤ ካመንኩት፡፡ ግን
ጅል አይደለሁም፤ ይሄን ሁሉ እውነት ብዬ ብዬ አልቀበልም፡፡ ኦሮሞ ብንሆን ኦሮሞነትህን
የምፈቅድልህ እኔ ነኝ የሚል አለ፡፡ አሁን ደግሞ የሰው ስም ሳላነሳ አማራነትን የሚፈቅዱ
ተነስተዋል፤ በአማራው መሀከል ነገ ጎንደርና ሸዋ የተለየ እንደሆነ፣ ቋራና ምናምን ብሎ
የሚሰጥ ይነሳል፡፡ ኦሮሞው መሀከልም ወለጋና ኢሉባቦር የሚልም ይነሳል፡፡ መሸንሸን
ማለቂያ የለውም፤ እንደቦተተ ጨርቅ እስኪበታተን ድረስ፡፡
…
እኔ ብዙ ጊዜ ደጋግሜ እንዳልኩት ብዙ አገር ኖሬያለሁ፡፡ ከብዙ ሕዝብ ጋር ሰርቼአለሁ፡፡
ብዙ ነገር ደግሞ ዛሬ ተምሬያለሁ፡፡ በብዙ ሁኔታ ውስጥ አልፌ ሰውን አይቼዋለሁ፡፡
ኢትዮጵያዊ ስለሆንኩኝ ለመመፃደቅ አይደለም፡፡ ራሳችንን ለማመስገን ሳይሆን ዘር ቋንቋ
ሳይለይ ከዳር እስከ ዳር፣ እንደ ኢትዮጵያውያን ብሩህ አእምሮ ያለው ሕዝብ አጋጥሞኝ
አያውቅም፡፡ እንደ እሱ ባይሆን አያሳዝንም ነበር፡፡ የሚኖርበት ቦታ የማይስማማ ምድረ በዳ
ሆኖ ቢጠፋ፤ በጠቅላላው ደግሞ ክፉኛ ጨካኝ ሕዝብ ሆኖ ቢጠፋ አይገርምም፡፡ ኢትዮጵያ
ውስጥ፣ ወለጋ ውስጥ፣ ጎጃም ውስጥ፣ ጎንደር ውስጥ፣ ኤርትራ ውስጥ፣ ኢሉባቡር ውስጥ፣
ሸዋ ውስጥ፣ አሩሲ ውስጥ ያልኖርኩበት፣ በእግሬ ያልሄድኩበት ቦታና የሰው ቤት
አልነበረም፡፡ ሁልጊዜም የሚገርመኝ አክብሮ ለመከበር የኢትዮጵያ ሕዝብ ያለው ጥማት፣
ለልብ ሞቃትነት ያለው ችሎታ፣ ለአእምሮ ያለው ጥራት ሌላ ነው፡፡ ሁልጊዜ የምትጎል
የምትገርመኝ አንድ ነገር አለች፡፡ ‹‹ኢማጅኔሽን›› ሁልጊዜ ትጎድላለች፡፡ እና ጨክነን ከፎቅ
ላይ አንዘልም፡፡ እግዚአብሔር ከኋላ ሆኖ እንኳን ‹‹አትወድቅም፤ ምንም አትሆንም፤ ሂድ፤
ዝለል›› ቢለንም እንኳ የማንዘለው ኢማጅኔሽን ስለሚያጥረን ነው፡፡ ለምን እንዳጠረን
ምክንያቱ ረዥም ቢሆንም ባጭሩ ግን የአስተዳደር ነገር ይመስለኛል፡፡
((( እንዳለጌታ ከበደ )))
💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️
@balmbaras

ላንተ ዋጋ የሌለውና ርካሽ ነገር ሌሎች ጋር የህይወት ዋጋ ሊኖረው ይችላል።
እነዚህ ጫጩቶች ካጥለቀለቃቸው ጎርፍ በዚች ነጠላ ጫማ ላይ ለመትረፍ ራሳቸውን ባላንስ አድርገው ቆመዋል።
ህይወት ላንተ ዋጋ በማትሰጠው ነገር ሌሎችን ታስደስታለች!!!
ሸጋ ጁምኣ!!💚💛❤️💚💛❤️
@balmbaras
@wegoch
@wegoch
እነዚህ ጫጩቶች ካጥለቀለቃቸው ጎርፍ በዚች ነጠላ ጫማ ላይ ለመትረፍ ራሳቸውን ባላንስ አድርገው ቆመዋል።
ህይወት ላንተ ዋጋ በማትሰጠው ነገር ሌሎችን ታስደስታለች!!!
ሸጋ ጁምኣ!!💚💛❤️💚💛❤️
@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ብድር በምድር
.
(ፈይሠል አሚን)
.
የነዳጅ ነገር አሳሳቢ የሆነበት ዘመን ነበር፡፡‹‹የነዳጅ ዋጋ ወጋኝ እንደ ቀጋ!›› የሚል ተረት ፈልጌ ፈልጌ አጣሁ፡፡ጥበበኛ እናትና አባቶቻችን ምነው ነዳጅ ላይ ተረት አለመፍጠራቸው፡፡ሐገር ሰላም ነው ብለህ ሥራ ሠርተህ ወደ ቤትህ ልትመለስ መንገድ ስትጀምር የታክሲ ዋጋ፤የእንጀራ፤የዳቦ የሁሉ ነገር ዋጋ ጨምሮ ይጠብቅሃል፡፡
‹‹ምነው?›› ስትል ነዳጅ ጨምሮ ነው ትባላለህ፡፡ ሁሉም ነገር የነዳጅ አሽቃባጭ ነው፡፡ሲጨምር ይጨምራል፡፡
በዚያ ዘመን ሁሉ ነገር ከነዳጅ ጋር ሲጨምር፤በተለይ በታክሲ ዋጋ መጨማመር ምክንያት የኔም የደም ግፊት ሲጨምር ያበደርኳቸውን ሰዎች እንደ ጥላ እያሳደድኩ ብድሬን መቀበል ጀመርኩ፡፡ነዳጅ ሳይጨምር አበድሬ ሲመልሱ ከነዳጅ ዋጋ ጋር ጨምሬ እቀበላችኋለሁ፡፡
እትዬ አለማሽ የጌሾ ብቅል እገዛለሁ ብለው 200 ብር ተበድረው ነበር፡፡ታዲያ ያለብዎት 320 ብር ነው ብዬ ድርቅ አልኩ፡፡
‹‹እንዴት ሆኖ?!›› አሉ እንደልማዳቸው ወገባቸውን ይዘው፡፡
‹‹እንደሚያውቁት የርስዎ ጠላና ነዳጅ በመልክም በቁመናም አንድ ናቸው፡፡የአንድ እናት ልጆች ነው የሚመስሉት፡፡እና አሁን ነዳጅ ሲጨምር የጠላ ብቅልን ጨምሮ፤የጠላ ዋጋም ነዳጅን ተከትሎ ጨምሯል፡፡ ስለዚህ በጨመረበት ልክ አስልቼ 200 ብር የነበረው ወደ 320 ብር አድጓል ነው የምልዎት!!››
ወገባቸውን እንደያዙ ለደቂቃዎች ትክ ብለው ካፈጠጡብኝ በኋላ፡ -
‹‹ነው?!›› አሉ በኃይለ ቃል፡፡
‹‹አዎ!›› እኔም በኃይለ ቃል መለስኩ፡፡
‹‹ነው?!›› ደገሙ፡፡
‹‹አዎ! እንደውም በየቀኑ ሁሉ ነገር በሚጨምርበት ዘመን እኔን የመሰለ አበዳሪ ጎረቤት ሌላ ሦስት መቶ ብር ጨምረው ቢሰጡኝ ደስ ይለኛል!›› ብዬ ደረቴን ነፍቼ መለስኩላቸው፡፡
እየተናደዱ ከብብታቸው ሥር ያለውን ቀረጢት ሸምቀቆውን አላልተው ድፍን ሦስት መቶ ብርና የሃያ ብር ሳንቲም ሰጡኝ፡፡ ከናፍሮቻቸውን በጥርሳቸው ነከስ ነከስ እያደረጉ ‹‹ቆይ እሰራልሃለሁ!›› ብለው የጠላ ደንበኞቻቸውን ሊያስተናግዱ ወደ ቤታቸው አቀኑ፡፡
‹‹የእትዬ አለማሽን ጠላ ቤት በሰፈራችን ካሉት ጠላ ቤቶች ምን ለየት ያደርገዋል?›› የሚለውን ጥያቄ ማንሳት አስፈላጊ ነው፡፡
እንግዲህ ጠላ ቤታቸውን ለየት የሚያደርገው በሰፈራችን እምብርት ላይ መገኘቱ ብቻ አይደለም፤የዱቤ አገልግሎት መስጠታቸው ብቻም አይደለም፡፡ጠላ ቤታቸው ጠላ ቤት ብቻ አለመሆኑና እሳቸውም ጠላ ሻጭ ብቻ አለመሆናቸው እንጂ፡፡እትዬ አለማሽ የጠላ ደንበኞቻቸውን ለማርካት ከጠላ መጥመቅ የተረፈ ተሰጥኦቸውን በመጠቀም አጠር አጠር ያሉ ድራማዎችን፤ቤት የማይመቱና ቤት የሌላቸውን ግጥሞችን፤ባህላዊ ውዝዋዜዎችን ጠላ ከደንበኞቻቸው በላይ ሲጠጡ ደግሞ ዘመናዊ ዳንሶችንም ጭምር ለደንበኞቻቸው በማቅረባቸው በዱቤ የሚጠጡት የጠላ ተደራሲያንን ጨምሮ ደንበኞች ከቤቱ አይጠፉም፡፡እንደውም የወረዳችን የሴቶች ጉዳይ ‹‹ለሴቶች ተነሳሽነት በመፍጠር እና የሴቶችን ክብር በማላቅ›› በሚለው ዘርፉ የዓመቱ ምርጥ ሴት ብሎ ሸልሟቸው ነበር፡፡
ወደ ቀደመ ጉዳያችን ስንመለስ፡ -
አንድ ጊዜም እንደልማዴ ሌላ ሦስት መቶ ብር አበድሬያቸው ነዳጅ ያለ ልማዱ ዋጋው ዝቅ ማለቱ ተሰማ፡፡ታዲያ ወፎች ሳይንጫጩ ቤቴ መጥተው በሬን አንኳኩ፡፡
‹‹ስማ አንተ. . .ብድርህን ልመልስ ነው የመጣሁት!›› አሉኝ ከበሮ እንደሚመታ ሰው በሬን ደብድበው ከእንቅልፌ ከቀሰቀሱኝ በኋላ፡፡
‹‹ምነው ታዲያ አይነጋም እንዴ ወይስ ከሐገር ሊጠፉ ነው?›› አልኳቸው ዓይኔን እያሻሸሁ፡፡
‹‹ነዳጅ እንደሆነ እንደጫካ አውሬ ነው፤ በዚህ ስትለው በዚያ ይመጣብሃል፤ራቀኝ ስትለው ከሥርህ ይገኛል፡፡››
‹‹እሺ ስንት ነበር ያበደርከኝ?!›› እጃቸውን ወደ ፈረደበት ብብታቸው እየሰደዱ፡፡መቼም ይሄ ብብታቸው ግምጃ ቤት በሉት፡፡አንዳንዴ ጠላ እየሸጡ አንድ ደንበኛ ድንገት ‹‹እስቲ አለማሽ. . .እዚህ ጋር ጠላ ጨምሪልኝ. . ›› ካለ ጠላ ለመቅዳት እጃቸውን ወደ ብብታቸው ሊሰዱ ይችላሉ፤ልምድ ነዋ!!
ከሐሳቤ ተመልሼ ‹‹ሦስት መቶ ብር!›› አልኩኝ፡፡
‹‹ይሄው!›› አሉና ብዙ ሳንቲሞችና አንድ የብር ኖት መዳፌ ላይ አስቀመጡ፡፡ሳየው የብር ኖቱ ብብታቸው ውስጥ እስራት ተፈርዶበት የወጣ መቶ ብር ነው፡፡
ሳንቲሞቹን ልቆጥር ስሰናዳ ‹‹ሳንቲሞቹ ሃምሳ ብር ናቸው፤ምን ትቆጥረዋለህ?!›› አሉኝ፡፡
ብሩን ትክ ብዬ አየሁት፡፡ነጻ በመውጣቱ ተንበርክኮ ወደ ሰማይ እጁን ዘርግቶ የሚያመሰግን መሰለኝ፡፡እዚያ ድቅድቅ ውስጥ ስንት ዘመን አስረውት ይሆን? ብዬ ራሴን ጠየቅኩና ወደ እትዬ አለማሽ ዞርኩ፡፡
‹‹ይሄ ምንድነው?! አልኩ በኃይለ ቃል!
‹‹ያበደርከኝ ነዋ!›› አሉ እንደልማዳቸው ወገባቸውን ይዘው፡፡
‹‹ሦስት መቶ ብር አብድሬዎት. . .መቶ ሃምሳ ብር ብቻ ይመልሳሉ ታዲያ?››
‹‹ነዳጅ ቀነሰ እንግዲህ! ምን ታረጊዋለሽ ብሏል ጥላሁን››፤ብድር በምድር ማለት ይሄም አይደል?›› ብለው እየሳቁ ጣሪያ ላይ ያሰጡትን ብቅል በረጅም እንጨት ደባበሱት፡፡
የዚያ ሰሞን የቀሩኝን ብድሮች እያሳደድኩ ተቀብዬ፤የባንክ አካውንቴን እርቃኑን አስቀርቼ ቢያንስ በታክሲ ታሪፍ ከሚጨምረው ደም ግፊቴ ለመደበቅ ስል ሳይክል ገዛሁ፡፡
ሳይክሏ ያገለገለችና ዘመኗን ተሻግራ እኛ ዘመን ላይ የደረሰች ናት፡፡የሸጡልኝ አዛውንት እንደነገሩኝ በፋሽስት ወረራ ጊዜ የአንዱ ጣሊያናዊ ነበረች፡፡ሲወርድ ሲወራረድ መጥቶ እኔ እጅ ገባች፡፡
ወደ ሥራ ስሄድና ስመጣ በዚህች ሳይክል መጠቀም ጀመርኩ፡፡‹‹የእናት ሆድ ዥንጉርጉር›› እንዲሉ የኋላና የፊት ጎማዋ አይመሳሰሉም፡፡የፊቱ ትልቅ ሲሆን የኋላኛዋ ደግሞ ሰፌድ ነው የምታክለው፡፡እንደጅብ የሚያነክስ ሳይክል ስነዳ መንገድ ላይ የሚያዩኝ ቱሪስቶች የኢትዮጵያ ባህላዊ ሳይክል እየመሰላቸው ፎቶ ያነሱኛል፡፡
አንድ ጊዜ የአፍሪካ ሕብረት ጉባዔ የሚደረግ ሰሞን በአፍሪካ ሕብረት በኩል ሳልፍ የድርቅናዋ ብዛት ዋናው በር ጋር ስትደርስ ተበላሸች፡፡መንገድ መዝጋቴን ተመልክተው ጠባቂዎቹ ‹‹ተንቀሳቀስ!›› ብለው ሲጮሁብኝ ባልዲ የሚሞላ ላብ አላበኝ፡፡ለነገሩ እኔም ምናልባት ይህቺ ሳይክል የሐገሬን ገፅታ እንዳታጎድፍ ብዬ ፈርቼ ነበር፡፡
ኋላ አንዱን ጠባቂ አስተዛዝኜ ‹‹እባክህ ትንሽ ትገፋልኝ?›› አልኩት፤ቢጨንቀኝ ነው እንጂ ምኗ ይገፋል?
‹‹ግፋልኝ ወይስ ወርውርልኝ ነው ያልከኝ?›› አለ፡፡
ሰውነቱን አስተውዬ ሳየው በዚህ ግዙፍ ሰውነቱ ቢወረውራት የእትዬ አለማሽ ብቅል ከተሰጣበት ጣሪያ ላይ ያደርስልኝ ነበር፡፡
መቼም ሰው ሳይክል ሲነዳ ብዙ ነው ፍዳው፡፡
ይህቺም ሳይክል ከማን አንሳለሁ ብላ መኪናዎች እንደሚያደርጉት ፍሬን በጠሰች፡፡ብላት ብሰራት ላቆማት አልቻልኩም፡፡የቸርችል ጎዳናን ቁልቁለት ጠብቃ ፍሬን መበጠሷ ምን ይሉታል?
መብራት ጥሼ ማለፌን ያየ ትራፊክ ፊሽካ ቢነፋም ላቆማት ባለመቻሌ ከቸልችል ጎዳና ተስፈንጥሬ የብሔራዊ ትያትር አንበሳ አቆመኝ፡፡ከታሪካዊ እና ምስላዊ ግልጋሎቱ በተጨማሪ አንበሳው ከአደጋ እንደሚታደግም የገባኝ በሕይወት መትረፌን ሳይ ነው፡፡
መቼም ይሄ የእትዬ አለማሽ እርግማን ነው እንጂ እንዲህ የሚያምዘገዝገኝ፤ሳይክሏ እንደሆን ዕድሜ ጠገብ እንደመሆኗ እንዲህ እንደ ሮኬት የመምዘግዘግ አቅም አይኖራትም፡፡እዚያው እንደ መስታዎት ደቅቄ በተኛሁበት ‹‹ብድር በምድር›› ብዬ እትዬ አለማሽን የእርስዎነት ማዕረግ ነፍጌያቸው ‹‹ወይ አለማሽ የሥራሽን ይስጥሽ!!››› ብዬ ተራገምኩ፡፡
.
@huluezih

እኔ ሚገርመኝ የኛ ከተማ አክቲቪስት ነን ባዮች ልክ እንደዘንድሮ የቻይና ጫማ ናቸው ......ልትገዛቸው ዋጋቸው እርካሽ ነው እና ደሞ እንደ አየሩ ናቸው ከተማው ሲቀዘቅዝ አብረው ይቀዘቅዛሉ በተቃራኒው ከተማው ትንሽ ሲሞ ቅ እንደነሱ ሚያቃጥል ከየትም አይገኝም .
ደሞ በጣም ሚገርመኝ ልክ እንደ ጫማው እድሜያቸው በጣም አጭር ነው ሳምንት ሲረገጡ ይበታተናሉ ,ያልቃሉ ።
ወንድሜ ልምከርህ ሌላ ቦታ በዘነበ ዝናብ አንተ አትበስብስ .እኔ ሚያሳስበኝ ካንተ መበስበስ በላይ አንተ በስብሰህ ቅዝቃዜው ሲያሥቸግርህ እሱን ለማድረቅ ምትለኩሰው ክብሪት ምትማግደው እንጨት ስንት ቤት ሚሰራ መሰለህ ...ሞራል ካለህ እሱን ስታስ ብ ልታዝን ይገባል ።ወንድሜ በአክቲቪስት ስም ከመነገድህ በፊት ጥቂት የአለማችን ብሶት የወለዳቸውን ምርጥ አክቲቪሥቶች ወደዋላ ዘወር ብለህ Backgroung አጥና ....!!!
*they are finaicially matured.
*they have strong national feeling!!
*they have plenty of inforemation gate.
*they really know historical background of their nation.
በእርግጥ ልክ ነህ ሁሉ ነገር ከ0(zero) ነው ሚጀምረው ብለህ ሊሆን ይችላል ያ ማለት ግን -1(negative one ) ለማለት መሆን የለበትም ቢያንስ ማደግ አለበት ስትቆጥር ወደላይ ቢሆን ይመረጣል .በስተመጨረሻ ልልህ ምፈልገው ነገር ቢኖር "ለህይወትህ ዋጋ ስጥ "ለህይወትህ ዋጋ ስትሰጥ ለቤተሰብህ ,ለወንድምህ,ብሎም ለሀገርህ ዋጋ መስጠት ትጀምራለህ !""Be morally matured ""

ባንተ ላይ ያለኝ እምነት እያደር በሰባት እጥፍ ይጨምራል!!!!!
እውነት እልሃለሁ ቀይ ባህርን የተሻገረ ህዝብ ሙሴ ይወገር ብሎ ከመናገር ወደሃላ
አይልም!!!! አሁን ምድረ በዳ ላይ ስለሆንን አይገባንም ። ከነኣን ግን ከፊታችን ናትና ዛሬም
አንተን እናምናለን!!!
የምድረ በዳ ጩከት እንደማይበግርህ አምናለሁ ።
@balmbaras
@wegoch
@weoch

#እኔ_የማውቀው_ሀገሬን_ነው!!
በዚህ ሰዐት ፖለቲከኛ አሊያ አክቲቪስት ወይ ደግሞ ጦማሪ መሆን ካልፈለክ ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ ደግሞ አዲስ አበባ ውስጥ መኖር የለብህም በአሁን ጊዜ ሁሉም የፓለቲካ ተንታኝ ሁሉም አክቲቪስት ሁሉም የፈቀደውን ሀገራዊ ጉዳይ አራማጅ ሆኖ አርፎታል አስገራሚው ግን ሁሉም ልክ ነኝ ማለቱ ነው።
ሲጀመር የፓለቲካን አስቀያሚ ቡግራም ጨዋታ ለመጫወት ደም፣ግፍ እና ጭካኔን ገንዘብ ማድረግ ያስፈልጋል ጠዋት ለሠራከው ሃጢያት ከሰዐት የንስሃ አባትክ ጋር የሚያስኬድ ወንጀል አይደለም እና የሚያሰራክ
መቼ ዕለት ነው ያለ አግባብ ያሳቁኝ ጋሽ ባልቻ ትዝ አሉኝ እኔ እሳቸውን የማቃቸው መሠረተ ትምህርት ጠጅ የሚያስቆመኝ ከሆነ አልማርም ሲሉና እየሰከሩ ሲወድቁ ነው። ታዲያ ጋሽ ባልችዬ ባልኳቹ ዕለት "የመለስ ራዕይ እኮ ጦቢያን መገነጣጠል እና መበዝበዝ ነው" እያሉ እያ እኩያ ከዘራቸውን እየወዛወዙ ሲሟገቱ ሠማው አስተውሉ እንግዴ ካላቸው የዕድሜ ልምድ ዕውቀት ውጪ ጭረት ቢጤ ቀለም አልገበዩ ከማህበረሰቡ ከሚዲያው ቀሰሙ እንዳይባል ውሎ እና አዳራቸው ጠጅ ቤት ነው በነገራችን ላይ ዕውቀት #Formal እና #Informal ነው የሚገኘው ያው መደበኛ እና ያልሆነ ማለት ነው መደበኛው ትምህርት ቤት ገብቶ መማር ሲሆን ኢ-መደበኛው ደግሞ ከአካባቢያችን ከቤተሰባችን ከመሳሰሉት የሚገኝ ነው።
ስለሆነም ለጋሽ ባልቻ የጠጅ ቤት ዕውቀት ዋጋ የለኝም ሳይሆን ቦለቲከኛ የሚያረግ አሊያ ተንታኝ የሚያረግ ውሃ የሚያነሳ ዕውቀት አይኖርም ብዬ ነው።
እንደው ጎኔ ካሉት ጋሽ ባልቻ ጀመርኩ እንጂ ስንቱ የfacebook አርበኛ ነው ከመሬት ተነስቶ ለለጠፈው ፎቶ መቶ like ሲያገኝ ተቀባይነቱን በlikeሁ እየለካ ፓለቲከኛ፣አክቲቪስት፣ፖለቲካ ተንታኝ የሚሰራራው
እኔ የሚገባኝ አንድ ቁም ነገር ቢኖር በዚህ ሰዐት በየማህበራዊ ድረገፁ የሚቦተረፍ አረቂያም ሁሉ የካቲካላ ቤት አንጎበራም ዕውቀቱን የሚለጥፍ ተነስቶ ሊቅ ነኝ ሲለኝ ያንገሸግሸኛል
#ሁሉም_መሪ_ሁሉም_ተመሪ_መሆን_አይችልምና_ምረጡ_ወይምሩ!!!_ወይተመሩ!!!
የሆነ ወዳጄ በየሆነ ቀን እንዲህ ብሎኝ ነበር
"#ሁሉም_ለቤቱ_ፕሮፌሰር_ነው" ብሎኝ ነበር ቀላል ልክ ነህ ወዳጄ ሌባ የምትለው አቦይ ፀሀዬ እቤትህ መቶ አስቤዛክን የሚወስንልህ አይምሰል ጀግና ያረከው አብይም ሚስት የምትወጠውጠው ሽሮ ወጥ ላይ ቂቤ የሚጨምርልህ አይምሰል ቅድሚያ ቤትህን ምራ ቅድሚያ ጎጆ ላይ ስላሉት ችግሮች ተንትነህ እወቅ ሀገርህን የምገነባው ጎጆህን ስገነባ ነው።
የረባ ዕቁብ ሳይኖርህ የፖለቲካ ፓርቲ መታወቂያ አይኑርህ የባንክ አካውንት ሳይኖርህ በስምህ አራት የfacebook አካውንት አይኑርህ የንስሃ አባት ሳይኖርህ የፍልስፍና አባት አይኑርህ ሁዱ ሳይኖርህ ሌባ ብሎ የሚኮንን አፍ አይኑርህ ሚስትህን ማስደሰት ሳትችል ህዝብን አስደስታለው አትበል በቃ ሁላችንም ወደ እራሳችን እንመለስ ወደ ውስጣችን እንመልከት መድሃኒቱ ስለጠፋ የራስክ በሽታ እንጂ መድሃኒቱ ስለተደበቀ የኢትዮጵያ ፖለቲካ አትዳክር በቃ እንንቃ ማህበራዊ ህመማችንን እናክም ስለሚጠፋው ቅርስ፣ባህል፣ወግ፣ማንነትህ እንስራ እንመርምር ስለሰብሃዊነት እንስበክ ዛሬ እገሌ ንፁህ ነው እገሌ ሌባ ነው ብለ የምትዋጋበት ግለሰብ እርስ በርሱ አንተ ከወንድም ጋር በምታረገው ንክሻ እየተዝናና ውስኪውን ቺርስ እያረገ እየተዝናናብህ ነውና ንቃ በደንብ ንቃ እጅግ በጣም ንቃ!!!
አዲዮስ!!!
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
#ኢትዮጵያ_በክብር_ለዘላለም_ትኑር!!
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
:-#ተክለ_ዮሀንስ

ህገ-ወጥነትና ኢ-ስነምግባራዊነት
የተጫናቸው የ”ሰንሴሽን ኮንዶም”
ማስታወቂያዎች
Written by ሰብለ አሰፋ (ጠበቃና የህግ አማካሪ)
ማስታወቂያ ወይም ማስተዋወቅ “ad vertere” ከሚለው የላቲን ቃል የመጣ
ሲሆን ትርጉሙም፤ አእምሮን ወደ አንድ ምርት መሳብ/ሀሳብን ወደዚህ ምርት
መቀየር ማለት ነው፡፡ ይህ የአንድን ሰው አእምሮአዊ አስተሳሰብና እምነት ወደ
አንድ ምርት፣ አገልግሎት፣ ሀሳብ ለመሳብ ፤ ለማቅረብ ያለመ የማስተዋወቅ
ድርጊት በዋናነት ሁለት ሂደቶችን ያካትታል፡፡ እነኚህም አንድ ሰው፤ ስለዚህ
ነገር የሚያውቅበትን መንገድ መፍጠርና ስለዚህ ምርትም ሰውየውን
ማሳመንን ነው፡፡ ይህ በአቅራቢና በተጠቃሚ መካከል ያለ ትልቅ ሀይል ያለው
የመገናኛ መንገድ፣ ተጠቃሚዎች ስለ አንድ ምርት አገልግሎትና የጥራት
ደረጃ የሚኖራቸውን አመለካከት በእጅጉ የሚወስን በመሆኑም፣
ማስታወቂያዎች፣ ስነ-ምግባራዊና ህጋዊ በሆነ መንገድ ካልተሰሩ ከፍተኛ
ጉዳት ያስከትላሉ፡፡
ከአገልግሎቱ ባህሪ አንጻር የተለያዩ አምራቾች ለገበያ የሚያቀርቧቸውን
ኮንዶም አይነቶች ተጠቃሚ ለመጨመር የሚጠቀሙበት የማስታወቂያ
ይዘትና አቀራረብ፣ ያልተፈለገ ባህሪን የሚያበረታታና በዚህም ማህበረሰቡ
ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትል በመቻሉ፣ ኮንዶምን የማስተዋወቅ አግባብነት
በአለምአቀፍ ደረጃ አጠያያቂና አነጋጋሪ ነው፡፡ በአለምአቀፍ ደረጃ የኮንዶም
ማስታወቂያዎች፣ በአድማጭ ተመልካቹ ላይ ሊያስከትሉ ስለሚችሉት ውጤት
አንድ አጠቃላይ ግንዛቤ አለ፡፡ ይህም በወሲብ አማካኝነት የሚተላለፉ
በሽታዎች በተለይ ስለ ኤችአይቪ/ኤድስ እና ስለ መከላከያ መንገዶቻቸው በቂ
መረጃና ግንዛቤ በሌለበት ማህበረሰብ ውስጥ ኮንዶምን ለማስተዋወቅ
የሚሰራጩ ማስታወቂያዎች፣ከጥቅማቸው ጉዳታቸው የሚያመዝን መሆኑ
ነው፡፡ ከዚህ አንጻር መንግስታት የኮንዶም ማስታወቂያዎች ይዘት፣ አቀራረብና
ስርጭት ላይ ቁጥጥር ያደርጋሉ፡፡
ይሁን እንጂ የኮንዶም ማስታወቂያዎች ሊያስከትሉት የሚችሉትን አሉታዊ
ውጤት ለማስቀረት ሀገራት መውሰድ ያለባቸው ትክክለኛ እርምጃ ምንድን
ነው የሚለው አነጋጋሪ ነው፡፡ ቁጥጥሩ ማስታወቂያዎቹን ሙሉ ለሙሉ
እንዳይተላለፉ ማገድን መጨመር አለበት? ወይስ የይዘትና አቀራረብ
እንዲሁም የሚተላለፉበትን ሰአት ብቻ መቆጣጠር? በተለይ በአንዳንድ
ሀገራት ከሚታየው ሰፊ የበሽታው ስርጭት እንዲሁም ስለ ኮንዶም ካለ ሰፊ
የግንዛቤ እጥረት አንጻር፣ የኮንዶም ማስታወቂያን ሙሉ ለሙሉ ማገድ
ለማህበረሰቡ የሚጠቅም ትክክለኛ እርምጃ ይሆናል፤ የሚሉት አከራካሪ
ነጥቦች ናቸው፡፡
የኮንዶም ማስታወቂያዎች ሙሉ ለሙሉ ባልተከለከሉባቸው ሀገራት፣ ከምርቱ
ባህሪና አገልግሎት አኳያ ሊያስከትሉ የሚችሉትን አሉታዊ ውጤት መቀነስ፣
መከላከልን በሚያረጋግጥ መልኩ እንዲሰሩ ለማስቻል ማስታወቂያዎቹ
ሊመዘኑበት የሚገባ የሞራል/ግብረ ገባዊ መርሆዎች በአለም አቀፍ ደረጃ
ዳብሯል፡፡ የእነኚህ መርሆዎች በአንድ ማስታወቂያ ይዘት ወይም አቀራረብ
አለመከበር ሊያስከትል የሚችለው ህጋዊ ውጤትም በየሀገራቱ ህግ
ተደንግጎ ይገኛል፡፡
በአለምአቀፍ ደረጃ የማስታወቂያዎችን ይዘትና አቀራረብ አግባብነት
ከሚለኩ መርሆዎች ዋነኞቹ የሚከተሉት ናቸው፡-
1. እውነተኝነት- አንድ ማስታወቂያ የሚያስተላልፈው መልእክት፣
ስለሚያስተዋውቀው ነገር ትክክለኛ ባህሪና የጥራት ደረጃን የሚያመላክት
መሆን አለበት፡፡ ከዚህ ደንብ ጋር በተያያዘ Puffery ወይም ስለ አንድ ምርት
የተጋነነ መረጃ መስጠት ተቀባይነት የላቸውም በተባሉ በርካታ
ማስታወቂያዎች የሚስተዋል ዋነኛ ችግር ነው፡፡
ባህል፣ ልማድና ወግን ያገናዘቡ/ያከበሩ መሆን፡- የአንድ ማስታወቂያ ይዘትም
ሆነ አቀራረብ የሚሰራጭበትን ሀገር ባህል፣ ልማድና ወግ ያገናዘበ መሆን
አለበት፡፡ ይህም በዋናነት ተጠቃሚውን ወደ አልተፈለገና ማህበረሰባዊ
ተቀባይነት ወደ ሌለው ባህሪና ድርጊት የማምራት አሉታዊ ውጤት
እንዳይኖረው የሚያስችል ነው፡፡
የሰውን ልጅ ሰብአዊ ክብር ማንነት የማይነኩ መሆን አለባቸው፡- በዚህ ስነ
ምግባራዊ ደንብ ስር ለዚህ ጽሁፍ አግባብ ያለው እና በአለምአቀፍ ደረጃ
የተወገዘው ሴቶችን በተወሰነ፣ ባነሰ ሚና፣ በተወሰኑ ድርጊቶች ገድቦ
የማቅረብ ተግባር ነው። /Stereotyping of women/ ይህ የማስታወቂያ
ይዘትና አቀራረብ፣ ለምሳሌ ሴቶች በማህበረሰቡ ዘንድ ሊኖራቸው
ስለሚገባው ሚና እና ሊሰጣቸው ስለሚገባ ቦታ አሉታዊ መልእክትን
ለአድማጭ ተመልካች የሚያስተላልፍና በማህበረሰቡ ውስጥ ሊኖር
የሚገባን ፍትሐዊና ጾታን መሰረት ያደረገ፣ አድልዎ የሌለበት የሰዎች ግንኙነት
እንዳይኖር ከፍ ያለ ሚና ሊጫወት በመቻሉ በአለም አቀፍ ደረጃ የተወገዘ
ነው፡፡
መሰል ማስታወቂያዎች ሴቶችን አስመልክቶ የሚያስተላልፉት
መልእክት፤ትክክለኛነት የጎደለውና ሴቶችን በተሳሳተና አንድ ወጥ በሆነ
መገለጫ የሚያስቀምጥ ነው፡፡ ይህም ጾታቸው ሴት የሆኑና በመላው አለም፣
በአንድ ሀገር፣ በተለያየ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ሁሉ፣ ሴት በመሆናቸው ብቻ
በዝንባሌ፣ በትምህርት፣ በኑሮ፣ በስራ ደረጃ፣ በአመለካከት ወዘተ-- ተመሳሳይ
እንደሆኑ አድርጎ ያለ አግባብ የማስቀመጥ አካሄድ ነው፡፡ ሴቶች በጾታ
ቢመሳሰሉም፣ አንዳቸውን ከአንዳቸው ለመለየት የሚያስችሉ በርካታ
መገለጫዎች ያሏቸው በመሆኑ፣ አንድና ወጥ የሆነ የሴት ሚና፣ ደረጃና
ማንነት አለመኖሩን ማህበረሰቡ እንዳይገነዘብ የሚያደርግ የተሳሳተ መረጃን
መስጠት፣ የማስታወቂያዎች ኢ-ስነምግባራዊነት መገለጫ ተደርገው
ከተፈረጁት አንዱ ነው፡፡
ይቀጥላል ...........

ሀገራት ባላቸው የኤችአይቪ/ኤድስ ስርጭት መጠንና ማህበረሰቡ ስለ
መከላከያ መንገዶቹ ካለው ግንዛቤ አንጻር የሚለያዩ በመሆኑ፣ ሀገራት
ኮንዶምን ለማስተዋወቅ በሚለቀቁ ማስታወቂያዎች ላይ፣ ከላይ የተዘረዘሩትን
መሰረታዊ የማስታወቂያ ሞራላዊ መመዘኛዎች መሰረት በማድረግ፣ የተለያዩ
እርምጃዎችን እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡ እንደ ፓኪስታን ያሉ ሀገራት ኮንዶምን
ለማስተዋወቅ የሚሰሩ ማስታወቂያዎችን በቴሊቪዥንና ራዲዮ ጣቢያዎች
ማሰራጨትን ሙሉ ለሙሉ ከልክለዋል፡፡ ሌሎች ሀገራት ለምሳሌ ህንድ
የኮንዶም ማስታወቂያዎቹ ከጠዋቱ 12 ሰአት እስከ ምሽቱ 4 ሰአት
እንዳይተላለፉ በማገድ፣ ይዘታቸው በስፋት ማህበረሰቡ በእነኚህ ሚዲያዎች
የሚለቀቁ ፕሮግራሞችና ማስታወቂያዎችን ሊያይ በሚችልባቸው ሰአታት
እንዳይሰራጩ ማድረግ ችለዋል፡፡
በሌላ በኩል፤ እዚሁ አህጉራችን አፍሪካ ያሉትን ሀገራት ለምሳሌ ኬንያና
ናይጄሪያን ስንመለከት፤ የኮንዶም ማስታወቂያን ይዘትና አቀራረብ በቅርበት
የሚከታተል ኮሚሽን ያቋቋሙ ሲሆን በዚህም ለሀዝብ መሰራጨታቸው
ከመረጃ ሰጪነታቸው ጉዳታቸው ያመዝናል የሚባሉ እና አድማጭ
ተመልካቹም ቅሬታ የሚያቀርብባቸውን ማስታወቂያዎች፣ ሰፊ ስርጭት
ከማግኘታቸው በፊት የማስቆም አካሄድን ይከተላሉ። በተጨማሪም ናይጄሪያ፣
የማስታወቂያ ህጓን በማሻሻል፣ማንኛውም የኮንዶም ማስታወቂያ ሊኖረው
ስለሚገባ ይዘት የደነገገች ሲሆን ይህ በአስገዳጅነት መካተት ያለበት
መልእክት፡-
‹ የኮንዶም የመከላከል ውጤታማነት 100 ፐርሰንት አይደለም፡፡ ለመከላከል
ዋነኛ ተመራጭ መንገዶች መታቀብ፣ ከአንድ ፍቅረኛ ጋር ታማኝ ሆኖ ለረዥም
ጊዜ መዝለቅ ነው፡፡› የሚል ነው፡፡
ይህ የናይጄሪያ ህግ፤ የኮንዶም ማስታወቂያዎች በትምህርት ቤት፣አምልኮ
ስፍራ መዝናኛ ቦታ ወዘተ-- አካባቢ ለህዝብ እይታ መቅረብ፣ መለቀቅ
እንደሌለባቸውም ይደነግጋል፡፡ በሀገራችን ኢትዮጵያ ከላይ የተጠቀሱትን
አለምአቀፋዊ ማስታወቂያን የተመለከቱ ስነምግባራዊ መርሆዎች መነሻ
በማድረግ፣ አንድ ማስታወቂያ ሊያሟላው ስለሚገባ ስነምግባራዊና ህጋዊ
መስፈርቶች ዝርዝር ነጥቦችን የያዘ የማስታወቂያ አዋጅ ቁጥር 759 በ2004
ዓ.ም ወጥቷል፡፡ በዚህ አዋጅ መሰረት፤ የተለያዩ መስፈርቶች የተቀመጡ
ሲሆን በዋናነት ማስታወቂያዎቹ በሚኖራቸው ይዘትና በአቀራረባቸው፣
ማናቸውንም ህጎችንና የማህበረሰቡን ስነምግባር፣ የማህበረሰቡን እሴትና
ባህል መጻረር የለባቸውም፡፡ ስለሚያስተዋውቁት ምርት የሚያስተላልፉት
መረጃም፣ ትክክለኛ መረጃ የሚሰጥ መሆን አለበት፡፡ /አንቀጸ 6/
በተጨማሪም አዋጁ በአንቀጽ 7፣ አንድ የማስታወቂያ ይዘት ወይም
አቀራረብ፣ መልካም ስነምግባርን ወይም ህግን የሚጻረር ነው የሚል
ድምዳሜ ላይ የሚያደርሱ ዝርዝር መመዘኛዎችን ያስቀመጠ ሲሆን አንድ
ማስታወቂያ በይዘቱም ሆነ በአቀራረቡ ጾታን አስመልክቶ፣ የሰው ልጅን
ሰብእና፣ ነጻነት፣ እኩልነት የሚጻረር ምስል፣ አነጋገር ንጽጽር ከያዘ፣ ለመልካም
ጸባይ ተቃራኒ የሆነ መልእክት፣ ምስል ወይም አቀራረብን ካካተተ unlawful
or immoral advertisement ተደርጎ ይወሰዳል ብሎ በግልጽ
አስቀምጧል፡፡
በሀገራችን በተደጋጋሚ የሚተላለፉ የሰንሴሽን ኮንዶም ማስታወቂያዎችን
ይዘትና አቀራረብ፣ ከላይ ከተጠቀሱት ህግና ስነምግባራዊ መርሆዎች አንጻር
መፈተሽ፣ የዚህ አጭር ጽሁፍ ዋነኛ አላማ ሲሆን ለአንባቢው ግልጽ
ለማድረግ፣ 3 የኮንዶም ማስታወቂያዎች ይዘትና አቀራረብ በማሳያነት
የሚዳሰሱ ይሆናል፡፡
የማስታወቂያዎቹ ይዘት-
ማስታወቂያ 1፡- አንዲት ሞዴል የፋሽን ትርኢት እያቀረበች ሳለ፣ በቁንጅናዋ
የተሳበ ወንድ ትእይንቱን ከሌሎች በርካታ ሰዎች ጋር ተሰብስቦ እየተከታተለ
መሆኑን ሁሉ ዘንግቶ፣ ለዚህች ሞዴል ረዥም ጭብጨባ ያሰማል፡፡ ይህን
አይነት የአድናቆት ስሜት ወንዱ ለሞዴሏ ውበት ከተሰማው የሚከተለው
ተፈጥሮአዊ ውጤት (Natural and automatic consequence) ወንዱን
ከዚህች ሞዴል ጋር ወሲብ ለመፈጸም የሚዳርግ እንደሆነ ተደርጎ እንዲወሰድ
በሚያስችል መልኩ፣ ይህን ትእይንት/የወንዱን በውበቷ ተማርኮ ስሜታዊ
መሆንን ተከትሎ፣ ማስታወቂያው ለጥንቃቄው ኮንዶም እንዲጠቀም ወንዱን
ይመክራል፡፡
ማስታወቂያ 2፡- በአንድ ካፌ ውስጥ በቡድን እየተዝናኑ ከነበሩ ወንዶች
አንዱ፣ አንገቱን ቀና ሲያደርግ፣ ብቻዋን ካፌ ውስጥ የተቀመጠች ቆንጆ
ወጣት ያያል ፤ ከኪሱ ኮንዶም አውጥቶ፣ ስልክ ቁጥሩን ጽፎበት በአስተናጋጅ
አማካኝነትሊልክላት ሲሞክር፣ ከካፌው መውጣቷን ያስተውላል፤ ይህን
ተከትሎ ሌላኛው ደኛው ለአስተናጋጇ ተመሳሳይ ፍላጎት ያድርበትና፣ ኮንዶም
ላይ ስልክ ቁጥሩን ጽፎ ሲሰጣት፣ በድርጊቱ ተስማምታ ስትቀበል ይታያል፡፡
ማስታወቂያ 3፡- በአሁን ሰአት በቴሌቪዥን ጣቢያዎቻችን በየደቂቃው
እየተላለፈ ያለው ማስታወቂያ አጭር መልእክቱ፤ ሴቷ ጥልፍ ጠልፋ አሳምራ
የሰጠችውን ነጠላ፣ አሳምሮ ቋጨው አይነት መልእክት አለው፡፡ እንግዲህ
እኔ እንደገባኝ የማስታወቂያው መልእክት፤ ከሴቷ ጋር ወሲብ እንዲፈጽም
ከእሷ ያገኘውን ፈቃደኝነት ተከትሎ፣ ይህንን በሰንሴሽን ኮንዶም በመፈጸም
ድርጊቱን የተሻለ አደረገው ነው፡፡
ይቀጥላል .............

ጌታቸው ረዳን ባሰብነው ጊዜ መጨረሻየን አሳምረው ብለን ጸልየናል!!!!
በራያ አላማጣዎች ታሪክ የጎበዝ ተማሪ ተቀዳሚ አርአያ ከነበሩት ሳተና ቀለሜዎች መሃከል
አንዱ ጌታቸው ረዳ ነበር ። ውሸት ምን ያደርጋል ??? እሱን አይተውና ሰምተው ወደ
ትምህርት አለም የጎረፉና የተሳካላቸው የአላማጣ ልጆች ብዙ ነበሩ ። ታዲያ ምን ዋጋ
አለው???? የተማርከው ትምህርት ለወለደህና ላሳደግህ ህዝብ ጠቀሜታ ላይ ካልዋለ ፤
የወጣህበትን ማህበረሰብ ችግር ለመፍታት የማያግዝ ከሆነ ትምህርት ከጸጋነቱ ይልቅ
ሸክምነቱ ይልቃል ። ጌታቸው ረዳ ዛሬ ላይ በማርና በወተት እየፈተፈተ ያሳደገውን የራያ
ህዝብ አደራ በልቷል ። ዛሬ ላይ ጌታቸው ረዳ ራያዊ ማንነቴ ይከበርልኝ ሲል አደባባይ ላይ
የወጣው የራያ አላማጣ ህዝብ በጥይት እንዲለቀም ከጠላቶቻችን ጋር አብሮ በመቆም
ስሙን ጠርታ የማትጠግበውን አላማጣ አንገቷን አስደፋት ። በራያ አላማጣ ልጆች
አንደበት ሲጠራ አፋቸው ሙልት የሚባልለት ጌታቸው ረዳ ማንነቱን ክዶ አላማጣ በጥይት
አረር እንድትቆላ ማድረጉን ባየን ጊዜ መጨረሻየን አሳምረው ብለን ፈጣሪን መማጸን ይዘናል
። የአላማጣ እናቶችን እንባ ይገድባል የተባለው ጌታቸው ረዳ ከአስለቃሾች ጎን ቁሞ ታሪኩን
አበላሸ ። የራያ ገበሬዎች ዛሬ ዛሬ በየእርሻዎቻቸው ማማ ላይ ቆመው ሲያንጎራጉሩ እንዲህ
ማለት ጀምረዋል ፤
መማር ጥሩ ነበር ላገር የሚበጅ ፤
ጌታቸው ረዳ አበላሸው እንጅ ።