Telegram Web Link
ወግ ብቻ
ሀገራት ባላቸው የኤችአይቪ/ኤድስ ስርጭት መጠንና ማህበረሰቡ ስለ መከላከያ መንገዶቹ ካለው ግንዛቤ አንጻር የሚለያዩ በመሆኑ፣ ሀገራት ኮንዶምን ለማስተዋወቅ በሚለቀቁ ማስታወቂያዎች ላይ፣ ከላይ የተዘረዘሩትን መሰረታዊ የማስታወቂያ ሞራላዊ መመዘኛዎች መሰረት በማድረግ፣ የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡ እንደ ፓኪስታን ያሉ ሀገራት ኮንዶምን ለማስተዋወቅ የሚሰሩ ማስታወቂያዎችን በቴሊቪዥንና ራዲዮ ጣቢያዎች…
የእነኚህን ማስታወቂያዎች ይዘትና አቀራረብ እንዲሁም በሀገራችን
የቴሌቪዥን ማሰራጫዎች የሚተላለፉ የተለያዩ ማስታወቂያዎች፣በዋናነት
የኮንዶም ማስታወቂያዎች ይዘትን አስመልክቶ፣ የሚከተሉትን ጥያቄዎች
መጠየቅ ምን ያህል ማስታወቂያዎቹ፣ ኢ-ስነምግባራዊ መሆናቸውን አስረጂ
ነው፡፡
ከባልነትና ከአባትነት ሚና ውጪ በበርካታ ሙያዊ ሚናዎች ከሚወከሉት
ወንዶች አንጻር የሴቶች ሚና ምን ያህል እናትነትና የቤት እመቤትነት ሆኖ፣
በማስታወቂያዎቹ ቀርቧል?
በማስታወቂያዎቹ የሴቶች ልጆች አስተዳደግን አስመልክቶ ያላቸው ሚና
የመንከባከብ ስለመሆኑ ወንዶች ለአስተዳደግ አስፈላጊ የሆኑ ወተትና መሰል
ነገሮችን በገንዘብ ሀይል የሚቀርቡ፣ በዚህም ሴቶቹ የራሳቸው የኢኮኖሚ
አቅም የሌላቸውና በባል ላይ ሙሉ ለሙሉ ጥገኛ ተደርገዋል?
የጥሩ ሴት መለኪያና መገለጫ ውጫዊ ውበት እንደሆነ፣ ውጫዊ ውበት
ማለት በአለምአቀፍ ሚዲያ የሚለቀቅን የሞዴሎች ምስል የሚመስል
ቅጥነት፣ አለባበስ ሜካፕ የያዘ እና ወጣትነት ብቻ ስለመሆኑ
በማስታወቂያዎቹ ተደጋግሞ ይተላለፋል?
በተለይ የኮንዶም ማስታወቂያዎቹ ምን ያህል ሴቶቹን የወንድን የወሲብ
ፍላጎት በእሱ ፍላጎትና ምርጫ ብቻ ሊያሟሉ የሚገባቸው፣ ከማን ጋር እና
መቼ ወሲብ መፈጸም እንዳለባቸው ወዘተ የመወሰን አቅም እንደሌላቸውና
የወንዱን ሙሉ ውሳኔ ተከትለው በተጠሩበት የሚሄዱ፣ ኮንዶም መጠቀም
አለመጠቀም ለወንዱ የተተወ ጉዳይ እንደሆነ በማስመሰል ያቀርባሉ?
በሀገራችን በየጊዜው በቴሌቪዥንና ሬዲዮ የሚለቀቁ የሰንሴሽን ኮንዶም
ማስታወቂያዎች፣ ይዘትና አቀራረብ፣ ከኢትዮጵያ የማስታወቂያ ህግና
አለምአቀፋዊ የማስታወቂያ መርሆዎች አንጻር ስንመለከት፤ እነኚህ የኮንዶም
ማስታወቂያዎች እያስተላለፉ ያለው መልእክት፣ አንድ ወንድ የአንዲትን ሴት
ውጫዊ ውበት ከወደደ፣ በቀጥታ ከእሷ ጋር የወሲብ ግንኙነት እንደሚኖረው
ነው፡፡ ይህም ልቅ ወሲብን የሚያበረታታና ሰዎች ስሜታዊ ሆነው ከማን ጋር
እና መቼ ወሲብ መፈጸም እንዳለባቸው ሳያስቡ ፤ በሁኔታዎች ብቻ ተገፋፍተው
እንዲወስኑ የሚገፋፋ ነው፡፡ ስለዚህም ከማህበረሰቡ ወግና ልማድ ጋር
ይጋጫል፡፡ የህብረተሰብ ጤና ፖሊሲና ህግጋትንም የሚቃረን ነው፡፡
ኤችአይቪን ከመከላከል አንጻር የወንድ ኮንዶም ያለው ውጤታማነት 85
በመቶ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር፤ ኮንዶምን ተጠቅመው ወሲብ ከፈጸሙ 100
ሰዎች 15ቱ በበሽታው ሊያዙ ይችላሉ፡፡ ከዚህም በላይ ኮንዶም የራሱ
የአጠቃቀም ህግጋት ያሉትና ወጥነት ባለው መንገድ ሁልጊዜ መጠቀምን
የግድ የሚል፣ ይህ ካልተተገበረ፣ የመከላከል አቅሙ ከ85 በመቶ በታችም
ዝቅ የሚል ስለሆነ፣ በወሲብ ምክንያት የሚተላለፉ በሽታዎችን ለመከላከል
ከኮንዶም በፊት የሚመከሩት መታቀብና ከአንድ ታማኝ ወዳጅ ጋር ረዥም ጊዜ
በታማኝነት መቆየት ናቸው፡፡ የመከላከያ መንገዶቹ በቅደም ተከተል A B C
ሆነው የተቀመጡ ሲሆኑ ከመከላከል ውጤታማነት አንጻር ቢቻል መጠቀም
ያለብን በ A እና B ያሉትን ነው፡፤. A-abstinence, B- be faithful and
C- use condom::
ስለዚህ ኮንዶም በመከላከል ረገድ በ3ኛ ደረጃ የሚመጣ ነው፡፡ የኮንዶም
ማስታወቂያዎቹ ግን ወሲብ መፈጸም፣ ውብ ሴትን ማየትን ብቻ የሚጠይቅ
አድርገው አቅልለው ማቅረባቸው ሳያንስ በመከላከል ረገድ ከኮንዶም በፊት
የሚመረጡት መታቀብና ታማኝነት መሆናቸውን አይገልጹም፡፡
በሌላ አነጋገር፤ መታቀብና ታማኝነት የሚሉትን ቀዳሚ የመከላከያ ዘዴዎች
ተመልካቹ እንዳይረዳቸው፣ በቂ መረጃ በማስታወቂያዎቹ አለመተላለፉ፣ ስለ
ኮንዶም የመከላከል አቅም ተጠቃሚው ላይ የተዛባ አመለካከት የሚፈጥር፤
ለኮንዶም ከፍተኛ ግምት መስጠትን የሚያነሳሳ ነው፡፡ በዚህ መልኩ፣ አንድን
ምርት፣ የሌለውን ጠቀሜታ እንዳለው አድርጎ ማስተዋወቅ፤ ስለ ምርቱ
በሚተላለፍ መልእክት ውስጥ አብሮ መገለጽ ያለባቸውን መረጃዎች
ባለመስጠት፣ እንደተገለጸው ጥቅሙ አንደኛ ደረጃ መሆኑን ለህዝቡ
ማስተላለፍ፣ ስለ ምርቱ ሀሰተኛና የተጋነነ መረጃ መስጠት በመሆኑ፣
በሀገራችን ህግ በግልጽ የተከለከለ፣ ህገወጥ፣ የማስታወቂያ መሰረታዊ
የስነምግባር መርሆዎች የጣሰ ተግባር ነው፡፡
ኮንዶም የመከላከል አቅሙ በአጠቃቀም ህጎቹ የሚወሰን መሆኑን
በመልእክቶቻቸው አለማካተታቸው፣ ኮንዶምን ወጥነት ባለው መልኩ
መጠቀም አስፈላጊ እንደሆነ አለመግለጻቸው፣ ለተመልካቹ ስለ ኮንዶም
የተጋነነ የመከላከል አቅም መረጃ እየሰጡ መሆኑን የሚያስረዳ ሲሆን በዚህም
ከመረጃ ሰጪነታቸው ይልቅ አብረው ማስተላለፍ ሲኖርባቸው፣ ባላካተቷቸው
ወሳኝ መልእክቶችና በሚያስተላልፉት ልቅ ወሲብን የማበረታታት አዝማሚያ፣
ለማህበረሰቡ ያላቸው ፋይዳ፣ ከመረጃ ሰጪነት ይልቅ ሀሰተኛ መረጃን
በመልቀቅ ከፍተኛ ጉዳትን ማድረስ ነው፡፡
ማስታወቂያዎቹ፣ አቀራረባቸው፣ መልእክታቸውን ለወንዱ የሚያስተላልፉና
ታሪኩ የሚነገርበት መንገድ /Storytelling/ ከወንድ አንጻር ሲሆን፣
የሚተዋወቀው የወንድ ኮንዶም መሆኑ፣ ተራኪው ወንድ መሆኑና የካሜራው
አቅጣጫ /Perspective angel/ ከወንዱ አንጻር መሆናቸው በአንድነት
ሲታይ፣ እነኚህ የኮንዶም ማስታወቂያዎች የሚያስተላልፉት መልእክት፣ ዋነኛ
ባለጉዳይ፣ ወንድ መሆኑን እንረዳለን፡፡ ይህ መልእክት የሚተላለፍበት አግባብ
ደግሞ በሴቷ መሳብን፣ ከተሳበ በኋላም ወሲብ ለመፈጸም መወሰንን፣
ድርጊቱን በኮንዶም መፈጸምን ሁሉ የወንዱ ብቸኛ ውሳኔ አድርጎ የሚያቀርብ
ነው፡፡ ሴቷ በዚህ ሂደት አንድም ሀሳብና ፈቃድ ስትሰጥ አይታይም፡፡
በሁሉም የሰንሴሽን ኮንዶም ማስታወቂያዎች እንደሚገለጽልን ከሆነ፤
ከተቃራኒ ጾታ ጋር በሚኖር ግንኙነት /ወሲብን / ጨምሮ፣ የሴቷ ሚና፣
በውጫዊ ውበቷ የፈለጋትን ወንድ ተከትሎ መሄድ ብቻ ነው፡፡ ከእነኚህ
ማስታወቂያዎች በመነሳት፣ አንድ ተመልካች ሊገነዘበው የሚችለው፣ ሴቶች
ከወንዶች ጋር ባላቸው የተቃራኒ ጾታ ግንኙነት፣ ምንም አይነት የመወሰን
ነጻነት፣ ችሎታና አቅም የሌላቸው እንደሆኑ፣ ከወንዶች ያነሱ ፍጡራን
መሆናቸውን ነው፡፡ ስነ-ተዋልዶንና ወሲብን አስመልክቶ፣ ጤናን ብሎም
አደገኛና አጋላጭ ከሆነ ተግባር ለመጠበቅ የሴቶቹ ሚና ወሳኝ እንዳልሆነና
ሁሉነገር በወንዱ ውሳኔ ስር ያለ አድርገው ያቀርባሉ፡፡ ሁሉም ሴቶች፤ ወንዱ
ከእነሱ ጋር ወሲብ እንደሚፈጽም መወሰኑ ብቻ ወሲብ ለመፈጸም
እንደሚያስገድዳቸውና ሊያስቀሩት እንደማይችሉት፣ የመምረጥ፣ በአካላቸው
ላይ የመወሰን አቅም እንደሌላቸው ምስኪን ተመልካቾች ተደርገው
ተቀምጠዋል፡፡ ጾታን መሰረት አድርጎ፣ ሴቶችን እንደ ሰው የመወሰን ነጻነት፣
አቅም የሌላቸው ተደርገው እንዲወሰዱ መልእክት የሚያስተላልፉ
ማስታወቂያዎች፣ ህገ ወጥ ስለመሆናቸው ከላይ በተጠቀሰው አዋጅ በግልጽ
ተድንግጓል፡፡
በሁሉም የኮንዶም ማስታወቂያዎች ላይ ሴቶቹ እጅግ ቀጭን፣ በውበት
ያማሩ፣ ውጫዊ ውበት ላይ የሚያተኩሩ፣ የሚሰሩት ስራም እንደ ካፌ
አስተናጋጅ አይነት አድርጎ የቀረበበት ነው፡፡ በእነኚህና በሀገራችን የቴሌቪዥን
ጣቢያዎች የሚተላለፉ በርካታ ማስታወቂያዎች ውስጥ የተካተቱ ሴቶች
በውጫዊ ውበታቸው ብቻ የሚገለጹ፣ ማህበረሰቡ ውስጥ ተቀባይነት
እንዲኖራቸው፣ የተሻለ ተደማጭነት እንዲያገኙ የሚያስገድድ ከውበት ውጪ
የሆነ ችሎታ እንደሌላቸው፣ ፍላጎታቸውና ዝንባሌአቸውም የቤት ውስጥ
እመቤትነትና ቤተሰብን መንከባከብ ብቻ ተደርጎ፤ ወጣት ሴቶች ተክለ
ሰውነታቸውን በሜካፕ በማሳመርና ቀጭን በመሆን፣ ወንድን ለመሳብ፣ ቀንና
ሌሊት የሚሰሩ አድርጎ ማቅረብ፣ የሴትን ውበት ከወጣትነት ብሎም
ከውጫዊ ገጽታ አንጻር ጋር ብቻ ያቆራኙም ናቸ
ወግ ብቻ
ሀገራት ባላቸው የኤችአይቪ/ኤድስ ስርጭት መጠንና ማህበረሰቡ ስለ መከላከያ መንገዶቹ ካለው ግንዛቤ አንጻር የሚለያዩ በመሆኑ፣ ሀገራት ኮንዶምን ለማስተዋወቅ በሚለቀቁ ማስታወቂያዎች ላይ፣ ከላይ የተዘረዘሩትን መሰረታዊ የማስታወቂያ ሞራላዊ መመዘኛዎች መሰረት በማድረግ፣ የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡ እንደ ፓኪስታን ያሉ ሀገራት ኮንዶምን ለማስተዋወቅ የሚሰሩ ማስታወቂያዎችን በቴሊቪዥንና ራዲዮ ጣቢያዎች…
ው፡፡
እነኚህ ማስታወቂያዎች፣ ወጥነትና ተመሳሳይነት ባለው
መልኩ፣የማህበረሰቡን እሴትና የሴቶችን ሰብአዊ ክብርና መብት የሚጻረሩ
በሆኑበት፣ እንደተፈለገ በየደቂቃው በየቴሌቪዥን ጣቢያዎች ሲተላለፉ
መመልከት፣ የቴሌቪዥን ጣቢያዎቹንም የኤዲቶሪያል ፖሊሲ ደካማነት
የሚያሳይ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለስልጣን፣ እነኚህ
ማስታወቂያዎች ከተመልካቹ በርካታ ቅሬታ እየቀረበባቸው ዝምታን
መምረጡም እጅግ አሳሳቢ ነው፡፡ የኤችአይቪ ቫይረስ ስርጭት እንደገና
በስፋት እየተስተዋለ በሚታይበት ሀገር፤ እነኚህ ማስታወቂያዎች
በሚያስተላልፉት ልቅ ወሲብን የሚያበረታታና ኮንዶምን አስተማማኝ
የመከላከያ መንገድ አድርጎ የማቅረብ የተሳሳተ አካሄድ እንዲቆም
አለማድረግ፣ ለዜጎች ጤና እና ደህንነት፣ ሀላፊነት የጎደለው ቸልተኝነት
እንደማሳየት የሚቆጠርም በመሆኑ፣ አፋጣኝ መፍትሄ የሚሻ ነው፡፡
ከአዘጋጁ፡- ጽሁፉ የጸሃፊዋን አመለካከት ብቻ የሚያንጸባርቅ መሆኑን ልንገለጽ
እንወዳለን፡፡

ምንጭ:- አዲስ አድማስ ጋዜጣ ቅዳሜ ጥቅምት 10 ቀን 2011
💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

እናንተም በሴንሴሽን ኮንዶም ማስታወቂያ እናም በሌሎች የቢራ መጠጥ ማስታወቂያዎች ላይ የታዘባችሁትን ብታካፍሉን ደስ ይለናል !!!!!!!
👇👇👇👇
@balmbaras
@wegoch
@wegoch
በሴንሴሽን ኮንዶም ማስታወቂያ እናም በሌሎች የቢራ ማስታወቂያዎች ላይ ትዝብታቹን ብታካፍሉን
👇👇👇
@balmbaras
@Lula_al_greeko
@wegoch
@wegoch
Marti Sol:👇👇👇


ለወጎች በኮንዶም እና ቢራ ማስታወቂያዎች የቀረበው ጽሑፍ ደግፋለው ምክንያቱም ስነምግባር የጎደለው እና ከባህል ያፈነገጠ ትውልድ ገዳይ ማስታወቂያዎች ናቸው ትውልዱ ከመጠጥ እና ወሲብ ውጪ ሌላ ምንም ህልም ወይም ደስታ እንደሌለው ተደርጎ መታየቱን ያሳያል ይሄ ደሞ ልክ አይመስለኝም።በተለይ በትምህርት ቤቶች እና የዩንቨርስቲ ግቢዎች ውስጥ የሚደረገው ኮንዶምን በነፃ የማደል ሁኔታ ወይም ሣጥኖች ውስጥ ማስቀመጡ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል ፤አንድ ተማሪ ከትምህርት ይልቅ ለስሜት ቅድሚያ እንዲሰጥና ላላስፈላጊ ወይም ልቅ ወሲብ እራሱን እንዲዳርግ ሁኔታዎች ስለተመቻቹለት አላማውን መሳቱና ለስሜቱ መውደቁ ከዛም አልፎ ለአስገድዶ መድፈር መነሳሳቱ አይቀርም ሴቷም ላልተፈለገ እርግዝና የመጋለጥ እድሏ ሰፊ ነው።ባለ ትዳሮችም ቢሆኑ ኮንዶምን ተማምነው ለትዳራቸው ታማኞች እንዳይሆኑ ያደርጋል ለዚህም የማስታወቂያ ስርዐታች ሊለወጥ ያስፈልጋል ምክንያቱም ሰዉ ራሱን ከመግዛት ይልቅ ለስሜቱ እንዲገዛ የሚያበረታታ ነው፤በሌላ በኩል የማስታወቂያ ዎቹ ገደብ ማጣት የሕጻናትን አይምሮ መመረዝና ስለማያውቁት ወይም ስለማይገባቸው ነገር ያለ እድሜያቸው ከአይምሮአቸው በላይ የሆነን ነገር እእንዲያስቡ እና ለማወቅ እንዲጥሩ ያደርጋል ያ ማለት ጠጪ እና ሴሰኛ ትውልድ እንዲፈጠር ያደርጋል ማለት ነው


ወግ ነኝ:👇👇👇

እውነቷን ነው
የኮንዶም ማስታወቂያ መብዛቱ ለእኔ ሚሰጠኝ ስሜት ዝሙት ማድረግ ትችላላችሁ ነገር ግን ልጅ እንዳይፈጠር ብቻ አደራ ብሎ መንግስት የተማፅኖ ድምፁን እያሰማ ይመስለኛል

በነገራችን ላይ ማስታወቂያው ያላሰበን ሁሉ አሳሳቢ ነው ከሚታዮት ጥንዶች አማላይነት ጀምሮ ሲቀጥል ከሚተላለፈው ትንታኔ(ድር እና ማግ ሚለው ልብ ይሏል) ከጀርባው የሚተላለፈው soundtrack ብቻ

ሰው አጋጣሚውን ባገኘ ቁጥር ድርያ ሚፈፅም ከእንስሳት ባህሪ ጋር ሚዋደድ ማንነት እንዳለው አድርገው ነው ሚስሉት

አንዳንዴ ሚሰሩት ሰዎች እራሱ አይሸክካቸውም እላለሁ ምንም እንጀራ ቢሆን ሰውን የክፋት ድርጊት ላይ ሚጥል ነገር ላይ መሰተፍ እንዴት የአይምሮ ሰላም ይሰጣቸዋል ብዬ አስባለው

አንድ ጥናት በቅርቡ ያነበብኩት ደግሞ ምን ይላል መሰለህ ከ35 በመቶ በላይ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ከ3 በላይ የወሲብ አጋር አላቸው የሚል ወደኋላ እንግመል ሽንት ለምናደርገው ጉዞ ትልቅ ማሳያ ነበር የሆነኝ

ጉዳዩ ከሚድያ የበላይ አካላትም ከፍ ይላል እንደ ሀገር በመንግስት ወጣቱን የሀሳብ መሀን ለማድረግ እየተሰራበት ነበር በፊት

ሆን ተብለው የተደረጉ ነበሩ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዙሪያ መጠጥቤቶች ዕፅ መነገጃዎች እና የድርያ መስኮች የነበሩት አሁን ግን ተስፉ አለኝ ቢያንስ ያለን እሱ ነው አሁን ይቀየራል ብዬ


ትዝብታቹን እየላካቹ ላላቹ በጣም እናመሰግናለን🙏🙏 ሌሎቻቹም ብትልኩልን ደስ ይለናል !!!

ሸጋ ምሽት!!!

@balmbaras
@Lula_al_greeko
@wegoch
@wegoch
Phoebe:👇👇👇👇
ሰላም ወጎች

ትክክል ናት! የኮንዶም እና የቢራ ማስታወቂያዎች ጉዳይ አሁን አሳሳቢ እና የሚመለከተው አካል መፍትሔ ሊያበጅለት የሚገባ ጉዳይ እንደሆነ ሁሉም ሰው ልብ ሊል ይገባል ። ከባህላችን ያፈነገጠ ከመሆኑ በተጨማሪ ትውልዱን የማበላሸት ትልቅ አቅም ያለው ነው። የኮንዶም ማስተዋወቂያቸው ተመልካቹን ለወሲብ የሚገፋፉ ሆነዋል። ሚዲያዎች (የቴሌቪዥን) ማስተዋወቂያዎች በሰው የሚፈጥሩት ተፅዕኖ እየታወቀ ችላ መባሉ መንግስትም ስለ ሚዲያ ያለ አቋም መውረድ ያሳያል። አሁን በቴሌቪዥኖቻችን የምናያቸው ማስተዋወቂያዎች ትውልዱን በመልካም ምግባር የሚያንፁ እና በእውቀት የሚገነቡ ከመሆን ይልቅ አዲሱን ትውልድ ሴሰኛ እና ጠጪ ለማድረግ አልመው የተነሱ መስለዋል። የማስተወቂያዎቹ አሰራር እና ሳቢነት ሁላ ከሌሎች የተለየ መሆን ብዙዎችን እያሳተ ነው። የቢራ ማስተዋወቂያዎች በሽልማት መጥለቅለቅ ሰዉ ተግቶ እንዲጠጣ ሱሰኛ ጠጪ ጊዜውን ገዳይ ትውልድ ከመፍጠር ያለፈ ትርፍ አይኖራቸውም። የኮንዶም ማስተዋቂያዎቹም ቢሆኑ ወጣቱ በፍቅር ታምኖ ተወስኖ እና ታቅቦ መልካም ትዳር ለመመስረት ከማለም ይልቅ እግረ መንገድ ለተመለከታት ሴት እንኳን "እንተዋወቅ" ብሎ በኮንዶም ፅፎ እንዲሴስን ከአስተዳደጉ ከእምነቱ ከባህሉ እንዲያፈነግጥ እያደረጉ ያሉ ፀረ ትውልድ ማስተዋወቂያዎች ናቸው። በአጠቃላይ መንግስት ትውልድ ከመጥፋቱ ይህ ነገር ግድ ቢለው ባይ ነኝ! ትውልድ ሊያንፁ በሚችሉ ማስታወቂያዎች ላይ ትኩረት ቢደረግ ብሎም እንዲህ ላሉ ማስተዋወቂያዎች ወሰን ቢደረግ ባይ ነኝ! ህብረተሰቡም የጉዳዩን አሳሳቢነት ተረድቶ ጫና ቢያረግ መልካም ነው ባይ ነኝ!
ፌበን ነኝ!

T҉ e҉ s҉ h҉ e҉  ......:👇👇👇👇

ስለ ሰንሴሽን ኮንዶም ደሞ በጣም ያዘንኩት

በቃ ወሲብን አሽሞንሙናችሁ አድርጉ ነው መልህክቱ

ድሮ ድሮ ወሲብ እንደነውር ነበር ሚታየው አሁን ግን አጣፍጣችሁ አድርጉ መባሉ ትንሽ የወረደ አሰራር መሆኑን ነው ሚያሳየን

ሲጀመር ወይ ማስታወቅያው ባይታይ ይሻላል

1 የ አሜሪካ ማስታወቅያ ነበር የኮንዶም ትንሽ ቆይቷል ካየውት እና በጣም ነበር ያስደነቁኝ

1 ነጭ ናት ልክ ከቤት ልትወጣ ስትል ዝናብ ጀመረ ....ተመልሳ ገባች እና ዣንጥላ ዘርግታ ዘና ብላ መንገዷን ቀጠለች ከዛ የኮንዶም ምስሉ መጣ።

ዝናቡ....ቫይረስ
ዣንጥላው....ኮንዶም

ነበር ሃሳቡ ቫይረሱን በ ኮንዶም ተከላከለች ማለት ነው።


አባት....ልጄ አዋሽ ምንድነው?

ልጅ....አባዬ አዋሽ ወይን ነው

አባት....ልጄ አክሱም ምንድነው?

ልጅ....አባዬ አክሱምም ወይን ነው

አባት...ልጄ ዋልያ ምንድነው?

ልጅ....አባዬ ዋልያ ቢራ ነው

አባት.....ልጄ ዳሽን ምንድነው?

ልጅ.....አባዬ ዳሽንም ቢራ ነው.

አባት....ልጄ ሜታ ምንድነው?

ልጅ......አባዬ ሜታም ቢራ ነው

አባት....ሀበሻ ምንድነው?

ልጅ....ሀበሻም ቢራ ነው

አባት.....ልጄ ጊዮርጊስ ምንድነው?

ልጅ......አባዬ ጊዮርጊስም ቢራ ነው😳

ጭብጥ፦ ቀጣይ ትውልድ ምናስተምረው ምንድነው? ወዴት እያመራን ነው?


ትዝብታቹን ለምትልኩልን እጅግ በጣም እናመሰግናለን 🙏🙏 ሌሎቻቹም ብትሳተፉ እና የናንተን ብናወቀው ደስ ይለናል!!! ሸጋ ቀን💚💛❤️💚💛❤️

@balmbaras
@Lula_al_greeko
@wegoch
@wegoch
☝️☝️☝️
ዛሬ ደሞ ስለዚህ ውብ ስዕል.....በደንብ አይታቹ ለናንተ የሰጣቹን ስሜት ስዕሉን የተረዳቹበትን ነገርብታጋሩን ደስ ደስ ይለናል!!! ሸጋ ጁምኣ💚💛❤️
👇👇👇
@balmbaras
@Lula_al_greeko
@wegoch
@wegoch
ወግ ብቻ
☝️☝️☝️ ዛሬ ደሞ ስለዚህ ውብ ስዕል.....በደንብ አይታቹ ለናንተ የሰጣቹን ስሜት ስዕሉን የተረዳቹበትን ነገርብታጋሩን ደስ ደስ ይለናል!!! ሸጋ ጁምኣ💚💛❤️ 👇👇👇 @balmbaras @Lula_al_greeko @wegoch @wegoch
Meazi:👇👇👇
Art men
Bezi se-el 1 se-ali aymerow west, behasabu beye gedgebaw lay hule menaw lay yaskemetewen tebeb masfer balebet bota mesal yakatewn tebebegna ayehubet

ይሄ ስዕል ባጭሩ ያለኛ ( ያለ አርቲስቱ) art ባዶ ነው፡፡ ትልቁ art ያለው እኛ ውስጥ ነው ይለናል::
By Pinel

ኪነ.አየለ ዳኒ:👇👇👇

እኔ ከዚህ ስእል የተረዳሁትን ባጭሩ ላካፍልህ...

፩ኛ, እኛ እራሱ በፈጣሪ እጅ የተሳልን ፣ የእሱ አሻራ ያለብን ፣ የእሱ ቀለማት የፈሰሱብን ስዕሎች መሆናችንን ነው እኛ መሳል ከመጀመራችን በፊት በመጀመርያ በፈጣሪ ምናብ ከዛም በፈጣሪ እጆች ተስለናል ያንን የሚያሳይ ይመስለኛል ሥዕሉ ።

ሌላው..

፪ኛ, በሥዕሉ ላይ እንደምንመለከተው የሰውዬው ምስል ጥላ ወይም ነፀብራቅ የስእል ቦርድ ወይም ሸራው ላይ ይታያል..እኛ የምንሰራው ስእል የእኛነታችን ወይም የስሜታችን ጥላ እንዳለበት ወይም የኛ ምናብ ነጸብራቅ መሆኑን እረዳለሁ እኔ ያንን ሥመለከት ።

ሌላው...

፫ኛ, ሥዕሉ እንደምናየው የብዙ ሕብረ ቀለማት ስብስብ ነው ። አንዱ ቀለም አንዱን ለመብለጥ የሚጣጣርበትም ሆነ አንዱ ባንዱ የተዋጠበት ሁኔታ አይታይም...በከለር ቢለያዩም ግን ሳይጣሉ ለሥዕሉ ውበትም ትርጉምም ሰጥተውታል ልክ እንደዚህ ሁሉ የኛም ልዩነት የውበታችን እንጂ የፀባችን መንስኤ ሊሆን እንደማይገባ ስዕሉ በጉልህ አሳይቶኛል ።

Fuad Jemal Sharif ®:👇👇👇

ስለ ስእሉ ያለኝ እይታ ፦ የሠው ልጅ ጥበብን ለማግኘት የትም መሄድ እንደሌለበትና ጥበብ የምትገኘው በዙሪያውና በአካለቱ እንደሆነ(ይህን የሚያሳብቀው በአካላቱና በዙሪያው ያሉት ቀለማት ናቸው።)ሌላው ደግሞ ራስ ቅሉ አካባቢ ምንም አይነት ቀለም አለመኖሩ ያመላከተኝ ጭንቅላት የጥበብ መፍለቂያ ከመሆን ይልቅ ያሉንን ጥበባት ማደራጃና ማጣመሪያ መሆኑን አይቻለሁ።።።
።።።።። ።።።።።።

☝️☝️☝️ ከተላኩልን በጥቂቱ ስለ ስዕሉ የአባላቶች ምልከታዎች ናቸው....የሌሎቻቹንም ምልከታዎች በጣም እንፈልገዋለን.....ምንም ይሁን ስዕሉን ስታዩት ለናተ የተሰማቹን ነገር አካፍሉን .......💚💛❤️ ምልከታቹን ላካፈላቹን በጣም እናመሰግናለን 💚💛❤️

👇👇👇
@balmbaras
@Lula_al_greeko
@wegoch
@wegoch
ወግ ብቻ
☝️☝️☝️ ዛሬ ደሞ ስለዚህ ውብ ስዕል.....በደንብ አይታቹ ለናንተ የሰጣቹን ስሜት ስዕሉን የተረዳቹበትን ነገርብታጋሩን ደስ ደስ ይለናል!!! ሸጋ ጁምኣ💚💛❤️ 👇👇👇 @balmbaras @Lula_al_greeko @wegoch @wegoch
Tezu :👇👇👇

እ. . ሸራውን ተመልክተከው ከሆነ የራሱን
ምስል ታያለህ . . ሰውየው ከቀለም ብዙ ነገር
ማስዋብ ችሎዋል ውብ ነገሮችንም ፈጥሮዋል
ግን እራሱን መሳል አልቻለም እራሱን ያየዋል
ግን አያሰፍረውም . .

ይህ የዓለም እውነት ነው ለብዝዎች እንደምቃለን
እኛን ማድመቅ አንችልም። እራሳችንን እናየዋለን
እኛን መሳል አንችልም. .

ከራስ ጋር ግጥምያ . . በመግባባት ውስጥ
አለመግባባት
. . . እኔ ያየሁት በዚህ መልኩ ነው . .

Robel Ye abraham:👇👇👇

እኔ በዚህ ስእል ላይ ያየሁት
ሰውየው ውስጡ እና ያለበት አካባቢው በውበት፣በጥበብ በተለያዩ ብርሀናዊ ቀለማት የተሞላ ሁኖ ሳለ ጭንቅላቱ ግን ጠቁሩዋል። እንደገና ደክሞና ዝሎ አንገቱን ደፍቱዋል። ይህም ጭንቅላቱ መጥቆሩ ዙሪያውን የከበበውን ውበት ማየት እንደተሳነው ውስጡን ማንነቱን ከማየት እንደገደበው ያሳያል። የስእል ሸራው ባዶ መሆኑ ውስጡን ማንነቱን ማየትስላልቻለ ምን ማበርከት፣መስጠት እንዳለበት የውስጥ ተሰጦው ባለማወቁ ማውጣት ተስኖታል። ብዙዎቻችን ያለንን ባለማዋቃችን የምንሰጠው አጥተናል። ሌላው ሸራው ላይ ጥላ ይታያል። ይህም ሰውየው ብርሀንን እየጋረደ ነው ብርሀንን ማስተላለፍ ተስኖት ጥላን ይለግሳል። ዛሬም በዙዎቻችን አውቀንም ሆነ ሳናውቅ የሰዎችን ብርሀን ጋርደን ጥቁር ጥላ የሆንንባቸው ብዙዎች ናቸው

ዮኒ:👇👇👇

እኔ የተረዳዉት ይህን ነዉ…እኛ ኢትዮጵያዊያን ባህላችን ፤ ቀለማችን ፤ ዉበታችን ጉራማይሌ ከመሆኑ የተነሳ ልዩነታችን ይበልጥ ያሳምረናል እናም ይበልጥ በአንድ ስንሆን እንጎላለን እንደምቃለን…እና ሳህሊዉ ከየቀለሙ እየቀነጫጨበ አሳመረን በሌላ መንገድ የአምላክ ልዩ ስራንም ያሳያል…ከየዓይነቱ የተቀነጫጨብን…

Bint Bin jabir:👇👇👇

ባሁን ግዜ እኛ ሰዎች የምንሰራው ስራ ታርጌቱ እንስትና አቅማችንና ጉልበታችንን በማይሆን ነገር ላይ እናባክናለን። የኋላ ኋላ ታርጌቱን ብናገኘው እንኳ አቅማችንና ወኔያችን ይጠፋል። ስራችንም ታርጌቱን ሳይመታ እንደባከነ ይቀራል።
We Don't have to miss the Target.
#ሐያት

በምስሉ ላይ እንደምትመለከተው

የመሳያ ቦርዱ ነጭ ነው ምንም አልተሳለበትም። በዛ ላይ ተገልብጧል።

ባጠቃላይ ነገር ተገለባብጦበታ ሰውዬው እንዴ እንደተሰማኝ ከሆነ።

Tammy:👇👇👇

Silu lay endemayew andi seali ke bord Ga hono andi sil lemesal eyasebe new beju kelem yizo malet new...ena bamirow eyaselasele ..Mn ayinet melk listew yetekemete yekome minkesakes..bicha misilew sil Mn ayinet melkt yasitelalif eyale yimesilegnal .
Yihe demo rasu sealiw yemifetirew gichit new meliso yesalew

Betty:👇👇👇

betam ds yemil seal nw bene eyeta seal malet yeweset semet nw, kelemu hiwet nw sheraw demo ye hiwet menged nw seraw bado nw seweyew demo azenual ya malet ye hiwet mengedun besheraw lay maskemet alchalem


በጣም እናመሰግናለን ምልከታቹን ላካፍላችሁን የቻናላችን ቤተሰቦች.....ሌሎቻቹንም እየጠበቅን ነው💚💛❤️
👇👇
@balmbaras
@Lula_al_greeko
@wegoch
@wegoch
# ጥቂት ስለ ዲዮጋን
ታላቁ እስክንድር ዲዮጋንን ከመውደዱና ከማድነቁ የተነሳ በተደጋጋሚ ይጎበኘው ነበር :: እስክንድር ዲዮጋንን ለመጀመርያ ጊዜ ለመጎብኘት አጃቢዎቹ ዘውትር ዲዮጋን ወደሚገኝበት አደባባይ በወሰዱት ጊዜ ዲዮጋን ከአደባባዩ ስር ተኝቶ ነበርና ወደ እርሱ ቀርቦ " እኔ ታላቁ እስክንድር ነኝ ! " ቢለው ዲዮጋንም በተኛበት ሆኖ አንጋጦ እየተመለከተው " እኔ ደግሞ ለማንም ግድ የሌለኝ ዲዮጋን ነኝ :: " በማለት መልሶለታል ::
*
በሌላ ቀን ታላቁ እስክንድር በጎዳና ላይ ከአጃቢዎቹ ጋር ሲያልፍ ዲዮጋን መንገድ ዳር ተኝቶ ፀሀይ ሲሞቅ አየው :: እስክንድር በዘመኑ ሁሉ የሚያደንቀውን ሰው መንገድ ላይ ተኝቶ ሲመለከተው ተደንቆ በፍጥነት ወደ እርሱ በመሄድ " የምትፈልገውን ንገረኝና ላድርግልህ " ቢለው ዲዮጋንም ቀና ብሎ " የምሞቃትን ፀሀይ ከልለኽኛልና ዘወር በልልኝ " ሲል መልሶለታል ::
*

ለዲዮጋን በሕይወት የሚያሳዝነው ነገር ቢኖር ሽማግሌ ማየት ነበር :: ለዚህም ለምን ? ተብሎ ሲጠየቅ " ሽማግሌ ወደዃላ እንጂ ወደፊት የሚያስበው ነገር የለም :: " በማለት መልሷል ::
***
ዲዮጋን በእነ ፕሌቶ ትምህርት እርባና ቢስነት ዘውትር ይሳለቅና ይወርፍ ነበር :: አንድ ቀን የደረቀ በለስ ከመንገድ ዳር ተቀምጦ ሲበላ ፕሌቶ አጠገቡ ደርሶ ሰላምታ ሰጠው :: ዲዮጋንም ጥቂት በለሶች አንስቶ እጁን እየዘረጋለት እንዲበላ ጋበዘው :: ፕሌቶም በለሱን ተቀብሎ በሙሉ በልቶ ሲጨርስ የተመለከተው ዲዮጋን " የምሰጥህን ነገር የምሰጥህ ለሌላውም እንድታካፍል እንጂ ሁሉንም ብቻህን እንድትበላ አይደለም :: " በማለት ጮኸበት ::
ምንጭ :- ጥበብ (ከጲላጦስ)
@yeyhudaanbesa
@wegoch
@wegoch
ወግ ብቻ
☝️☝️☝️ ዛሬ ደሞ ስለዚህ ውብ ስዕል.....በደንብ አይታቹ ለናንተ የሰጣቹን ስሜት ስዕሉን የተረዳቹበትን ነገርብታጋሩን ደስ ደስ ይለናል!!! ሸጋ ጁምኣ💚💛❤️ 👇👇👇 @balmbaras @Lula_al_greeko @wegoch @wegoch
ባሮክ:👇👇👇

እሱም አካባቢውም ውብ ድንቅ ሆኖ ሳለ ግን የአካባቢውንም ሆነ የራሱን ውበት መግለፅ (ማውጣት) እንደከበደን የሚገልፅ ይመስለኛል እንደኔ

Solomon:👇👇👇

ስለስዕሉ ከሌላው በተለየ እይታ ያለኝ ይመስለኛል ። ሁሉም ተሞልቶለት ነገር አይን ሳለው ማየት ያልተቻለው ሰው ይታየኛል ። ለአፍታ አካባቢውን ፣ ራሱን ፣ ሸራውን መመልከት ያቃተው ። ውሃን ፍለጋ በበረሃ ሲኳትን የዋለ በዚህም በጣም የተዳከመ ። አቅሪያባው የተቀመጡለትን ነገሮች ማስተዋል ያልቻለ ብዬ አስባለሁ።
ሰለሞን

፩ Ibrahim...:👇👇👇

ከስህሉ እንደተረዳሁት:-
-------
የሰውዬውን ማንነት ከያዘው ብሩሽና አጠገቡ ጋር ከተቀመጠው ነጭ ወረቀት ተነስተን ስንደመድም "ሰዓሊ" ይመስለናል..." ፣ ነገር ግን ከድርጊቱ አንፃር ማንነቱን ስንገልፅ ግርግዳ ቀቢ ወይም የቤት አሳማሪ ነው ልንለው እንችላለን።
---
ይህ የብዙዎቻችን ገፀባህሪ ነው።
የዛፍ ቅርንጫፍ ለመቁረጥ "የዳቦ ቆሎ መቁረጫ መቀስ" ይዘን እንወጣለን ፣ በእግር ኳስ ሜዳ በቴኒስ ኳስ እንደመጫ ነው።
---
እኔ ይህን ነው የተረዳሁት
ኢብራሂም


KB Kibr:👇👇👇

Tnsh yetesemagnin sle selu lbel

=and alemawekun yaweke tibebegna sew yitayegnal angetun medfatu wbetn ligelts techenko kezuriyaw libelt endemaychl besherawa manesm terdto yalen sew ayalew
Belela angl demo
=wbet malet yesew hasab yarefebet shera sayhon sew rasu wbet new yefetari yeEju sra endihum tefetrow


፼:👇👇👇

Sel sehilu ...yatesmachin belu...
.
Betbalnew mesrt .....1shera tegdebo tewtro bayisalem ...gen sehile nw enamnaln amenenem astyayat enstalen ....yameral betam yamirale .....yatsmgne gen 1...sehali bechinkilatu westi bezu ..webti ..kerbit ..melhate ..hebrt... Balchiew ...hasbochi ena nedfochi....yatkebebe...lemasfr gen yatchinke ..yimselale ...


Yatsemagn ..

ምልከታቹን ለላካችሁልን ሁላቹንም በጣም እናመሰግናለን 🙏💚💛❤️

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
የመን-የአረቦች ውድቀት ግልጽ ማሳያ!
-----
ይህቺ እናት በርሃብ በልጆቿ ፊት እንዲህ አርፋለች!! ከሞት ሁሉ ክፉው በርሃብ መሞት ነው! ከሞት ሁሉ ክፉው አባት ወይም እናት ሆነህ ልጆችህ በፊትህ በርሃብ ሲያልቁ ማየት ነው። የአረቡ አለም በጥጋብ ቁምጣን ሆዱን ሲታመም የየመን ህዝብ ይሄ አሰቃቂ እጣፋንታ
ተጋርጦበታል። አጉል አንጋራጭ ያገሬ ልጅ ሆይ፥ ለራሱ ያልሆነ ለኔ ይሆናል ብለህ አትቆላጭ!! ከጠኔ የከፋ ሰቆቃ የለም!!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
❤️ ስለ ፍቅር ፩❤️
/ ካህሊል ጂብራን /

💚💛❤️

" ፍቅር በዓይኑ ጥቅሻ በጠራችሁ ጊዜ መንገዶቹ ምን ያህል አስቸጋሪ እና አቀበት ቢሆኑም ተከተሉት...ክንፎቹ ሲያቅፏችሁም ተሸጎጡበት ። በላባዎቹ መሀል የተደበቁ ሰይፎች ቢያቆስሏችሁም ወደኋላ አታፈግፍጉ ...

ሲያነጋግራችሁም እመኑት ። ድምፁ የሰሜን ኃይለኛ ንፋስ የአትክልትን ስፍራ እንደሚያወድም ሁሉ ህልሞቻችሁን ቢበታትንባችሁም እሱን ከማመን አታመንቱ...

📖📖📖

ፍቅር ዘውድ የሚደፋላችሁን ያህል ይሰቅላችሁም ይሆናል ። የሚያሳድጋችሁንም ያህል ይከረክማችኋልም...እስከ ጫፍ ከፍ ብሎ በፀሃይ ውስጥ የሚወዛወዙትን እጅግ ለስላሳ ቅርንጫፎቻችሁን በፍቅር እንደሚደባብስ ሁሉ ፣ በመሬት ውስጥ ቁልቁል ወደ ስሮቻችሁ ወርዶም ተጠምጥሞ ከመሰረታቸው ይነቀንቃቸዋል...

📖📖📖

እንደ በቆሎ ክምር ወደ ራሱ ይሰበስባችኋል ። እርቃናችሁን ሊያስቀራችሁም ይወቃችኋል ። ከላፋችሁ ሊያላቅቃችሁም ይነፋችኋል ። ነጭ ዱቄት እስክትሆኑም ድረስ ይፈጫችኋል ። እስክትለወጡም ያቦካችኋል ። ከዚያ ለአምላክ ቅዱስ ድግስ የምትቆረሱ ቅዱስ ዳቦዎች ትሆኑ ዘንድ ወደ ተቀደሰው እሳቱ ውስጥ ይጨምራችኋል....

📖📖📖

ፍቅር እነዚህን ሁሉ ነገሮች የሚያደርግባችሁ ፣ የልባችሁን ምስጢራት እንድታውቁ እና በዚያ ዕውቀትም የህይወት ልብ አንድ ግማድ እንድትሆኑ ነው...

ይሁንና ፍርሃት አድሮባችሁ የፍቅርን ሰላም እና የፍቅርን ደስታ ብቻ የምትሹ ከሆነ፣ እርቃናችሁን ሸፍናችሁ ከፍቅር የመውቂያ ውድማ ወጥታችሁ ብትሄዱ ይሻላችኋል ። ወደዚያ የሄዳችሁበት ወቅቶች የማይፈራረቁበት ወቅት - አልባ ዓለም ውስጥም ትስቃላችሁ ። ነገር ግን ሳቃችሁን ሁሉ አትስቁትም ። ታላቅሳላችሁም፤ ግን እንባችሁን ሁሉ አታፈሱትም...

ይቀጥላል...

ምንጭ 👉 " የጥበብ መንገድ ፪ "
ደራሲ ካህሊል ጂብራን

@wegoch
@wegoch
ያጣኸውንና የናፈቀህን ነገር አብዝተው ከሰጡህ አትወደውም!
--------
ነጻነት እንደሰማይ ርቆን በጩኸታችን ብዛት ላንቃችን ተሰነጠቀ፥ እንዲህም አልን
"አምላካችን ሆይ የሰጠኸንን ነጻነት የሚቀሙን አፋኞች አጥፋ፥ አለም የደረሰበትን ሃሳብን
በነጻነት የመግለጽ መብት አጎናጽፈን"
ጩኸታችን ተሰምቶ ቆይቶ "ሰው ሆይ ነጻ ነህ" ሲልም መሪው አወጀ!! ላንቃ ሰንጣቂውም
የነጻነት እጦት ጩኸት ከስሩ ተመነገለ!!
-------
ግን ግን ብዙዎቻችን ድሮም ጩኸት አመላችን ቆይቷልና እሱን ራሱን እንጮህበት ይዘናል።
ምንም በለው ምን አብይ አህመድ የብዙ ነገሮች መልሴ ነው!!

ሸጋ ሸጊቱ ቀን💚💛❤️

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
“ሰላም ማደሪያዋ የያንዳንዳችን አእምሮ ነው!!”


“Try to be yourself,
Be the master of your soul,
Peace comes from within.”
ከላይ ያነበባችሁት እ.ኤ.አ በ2016 በጂብሰን አካዳሚ የአራተኛ ክፍል ተማሪዎች፣ በጃፓን ‹ሃይኩ› የግጥም ስልት ‹Peace› በሚል ርዕስ ባደረጉት
የግጥም ውድድር አንደኛ ወጥቶ የተሸለመ ግጥም ሲሆን የ10 ዓመት ህፃን የፃፈው ነው፡፡ ከአንድ ዓመት በፊትም (በ2015) በተመሳሳይ ርዕስ
የሚያስደንቅ ግጥም ፅፎ 1ኛ በመውጣት ተሸልሟል፡፡
*
ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ጎልማሳ ራሱን ሊያጠፋ ወደ ሱሉልታ ጫካዎች አቀና፡፡ ከዛፎቹ ባንደኛው ገመዱን አስተካክሎ ቋጠረበት፡፡ ለመሞት እንደተዘጋጀ እንጨት እየለቀሙ የሚተዳደሩ እናት ከሩቅ ሲመጡ ተመለከተ፡፡ ጠበቃቸውና አናገራቸው፡፡ “እማማ” “አቤት”
“ይህንን ይውሰዱ” አላቸው፤ ሰዓቱን፣ ቀለበቱንና ጥቂት ገንዘቦች!! እማማም
ፊቱንና ሁኔታውን በማየት ያሰበውን ተረዱና፤ “አልፈልግም” አሉት፤ ራሳቸውን እየነቀነቁ፡፡ “ለምን?” ጠየቃቸው፡፡
“ከሰላም አይበልጥብኝም” “ማለት?”
“አየህ ልጄ፤ የሰጠኸኝን ንብረት ባየሁ ቁጥር አንድ ተስፋ የቆረጠ፣ ህይወትን መጋፈጥ ያቃተው፣ ለጠላቶቹ የተንበረከከ ፈሪ ሰው እንዳጋጠመኝ አስታውሳለሁ፡፡ ይሄ ደግሞ ሰላሜን ያደፈርሳል” አሉትና ጥለውት ሄዱ። አጅሬም ተከተላቸው … “እማማ፤ ሰላም የት ትገኛለች?” በማለት ጠየቃቸው። ጭንቅላታቸውን በጣታቸው እየነካኩ መንገዳቸውን ቀጠሉ፡፡
*

ሰው ባለበት ሰላም፣ ሰው ባለበት ግጭት አለ፡፡ ሁለቱም የተፈጥሮ አካል
ናቸው፡፡ አንዳንዴ ተንኮልና ቅድስና ወይም ክፋትና ደግነት፣ አንዳንዴ
ሰብዓዊነትና አውሬነት ወይም ገሃነምና ገነት እንላቸዋለን፡፡ በሁለቱ
ተቃራኒዎች ፉክክር ህይወት ትሽከረከራለች፡፡ … ወደ ፊትና ወደ ኋላ፣ ወ ግራና ወደ ቀኝ!! … የኑሮ ጠመኔ በመንፈሳችን ሰሌዳ ላይ ፍቅርና ሰላምን፣ ጥላቻና ብቀላን ሲፅፍ፣ ሲሰርዝና ሲደልዝ ይውላል፡፡ የህሊና ዳስተራችን ደግሞ የመሰለውን እያጠፋ የመሰለውን ያቆያል፡፡ ወዳጄ፡- እኔና አንተ ጥሩ ሰዎች ስንሆን ቤተሰብ፣ ህብረተሰብ፣ አገርና ምድር ሰላም ይሆናሉ፤ጥሩ ካልሆንን ደግሞ ይታወካሉ፡፡ ውሃ የተሞላ ሳፋ፣ ኩሬ ወይም ባህር ላይ ትንሽ ጠጠር ብትጥል፣ እርጋታው ምን ያህል እንደሚናወጥ ታያለህ፡፡ የእያንዳንዳችን ባህሪም ለአጠቃላይ ሰላማችን፣ ልማትና ጥፋት የሚኖረው አስተዋፅኦ እንደዛ ነው፡፡ ሁላችን በአንድ፣ አንዱም በሁላችን
ውስጥ ተወልደን፣ አድገን፣ ተጋብተን፣ ተሳስረን … አገር ሆነናልና!! ወዳጄ፡- በዓለም በምንኖርበት ጊዜም ሆነ ከህይወት ተፋተን ወደ ነበርንበት ስንመለስ፣ አሻራችን እንደየ ሥራችን ስልጣኔያችን ላይ ታትሞ ይታያል፡ሂትለርና ሙሶሎኒ፣ ማርኮኒና ኤዲሰንን የምናውቀው ባሻራቸው ነው፡፡ ጋንዲና
ክርስቶስን ደስቶቭስኪና ማርክስን፣ ዳርዊንና ፍሮይድን እንዲሁም ሌሎች ብዙዎችን አላየናቸውም፡፡ ሁሌም ግን አብረውን ይኖራሉ፡፡ ኑሯችን ውስጥ አሻራቸው አለ፡፡ ቢል ጌትስና ማርክ ዘከርበርግ፣ ሃውኪንግና ቦብ ዲለን፣ እኔ፣
አንተ፣ እሱና እሷም ያው ነን፡፡ ስልጣኔ የሚገነባው በትውልድ ቅብብሎሽ ነው፡፡ ሰላም ደግሞ የቅብብሎሹ ድልድይ ነው፡፡ ድልድይ ከሌለ ታሪክ ይቋረጣል፡፡ አሻራ ይጠፋል፡፡ እስከ ዛሬ ድረስ “የአክሱም ሃውልት እንዴት ቆመ? … ላሊበላ እንዴት ታነፀ?” እያልን የምንጠይቀው ለዚህ ነው፡፡ ቅብብሎሹ ስለተቋረጠ ይመስለኛል፡፡ የቅብብሎሹ መቋረጥ በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂና በጥበብ ብቻ ሳይሆን ወጥ የሆነ፣ ተያያዥነት ያለው አሳማኝ የእምነት ታሪክም እንዳይሸጋገር ስላደረገ
እምነትም ከተረት፣ ከባህልና ከኑሮ ዘይቤነት አላለፈም። ለዚህ ነው የአምልኮትና የሃይማኖት ልዩነቶችንና ግጭቶችን የምናስተናግደው፡፡ ለምሳሌ ክርስትናን መሰረት ያደረጉ ትውፊቶች (Mytheology) “ሰው ከሞት ጋር አልተፈጠረም” ብለው ያስተምራሉ፡፡ አዳምና ሔዋን የእባብን ወሬ ሰምተው ተሳሳቱ፡፡ የሃሰት ወሬ ሞትና መከራን አመጣባቸው፡፡ ከገነት ተፈነገሉ ይላል፡፡ ሰው የሚሞተው በገዛ ጥፋቱ ነው ለማለት፡፡ የግሪክ ሚቲዮሎጂም፤ ሞት የመጣው ከሰው ጥፋት እንደሆነ ይተርካል … “… በወርቃማው ዘመን ዚየስ አምላክ፣ ለወዳጁ ኤፒሜቲየስ፣ ከሰዎች ውስጥ ቆንጆ ሴት መርጦ እንዲያገባት በስጦታ ሰጠው፡፡ … ውቧ ፓንዶራን። ፓንዶራ የአምላክ ሚስት በመሆኗ ሁሉ በጇ፣ ሁሉ በደጇ ሆኖ ስትኖር አንድ ቀን ተሳሳተች፡፡ አማልክቶቹ ማንም እንዳይነካው ብለው አደራ ያስቀመጡትን ሳጥን ስትፈለቅቅ በውስጡ የነበሩት ችግር፣ ህመም፣ ስቃይና የመሳሰሉት መከራዎች አፈተለኩ፡፡ የወርቃማው ሰው ዘመን አበቃ፡፡ ህይወትና ሞት ጎን ለጎን ተሰለፉ” ይላል። ባለቅኔያቸው ሄፂዖድም … በገነት የነበሩ አማልክት፣ ወርቃማውን የሰው ዘር፣ ህመምና ሞትን ሳያውቅ፣ እንደነሱ ሆኖ እንዲኖር፣ ቢያደርጉትም አላወቀ፣
የአደራ ህግን ስቶ፣ በመከራ ተዘፈቀ፡፡ …. በማለት ፅፏል፡፡ ዞሮ፣ ዞሮ በነዚህና በመሳሰሉ ሌሎች የእምነት ትርክቶች የ ‹ተረጋገጠው ዕውነት› ሰው ካላወቀ የራሱ ጠላት ይሆናል የሚል ነው፡፡
ወዳጄ፡- ከትዳርህ ወይ ከቤተሰብህ፣ ከጓደኛህ ወይ ከወዳጅህ ብትጣላ ትታረቃለህ፡፡ ከጎረቤትህ ባትግባባ፣ ከዕድርህ ባትስማማ ትሸመገላለህ፡ከአለቃህ ብትጋጭ ስርዓቱ ይዳኝሃል፣ አምላክህን ብታስቀይም ንስሃ ትገባለህ፡፡ ከራስህ ከተጣላህ ሰላምህን የት ታገኛለህ? ራስህን ከገደልከው ማንን ይቅርታ ትጠይቃለህ? “ከራሱ ጋር ሰላም የሌለው፣ ከሁሉም ጋር ጠበኛ ነው!!” ይላሉ ሊቃውንት፤ሰላም የነፍሳችን መዘውር መሆኗን ሲመክሩ፡፡ ወዳጄ፡- ህገ መንግስትም ሆነ ማህበራዊ ስርዓት ያስፈለገው ለሰላም ነው፡፡ የጦርነት ታሪክ ሲገለበጥ የሰላም ታሪክ ነው፡፡ የተባበሩት መንግስታት ታሪክ የሰላም ታሪክ ነው፡፡ የስልጣኔ ታሪክ የሰላም ታሪክ ነው። የመደብ ትግል፣ የብሔር ብሔረሰብ፣ የዘር፣ የጎሳና የጎጥ ውዝግብ ዞሮ ዞሮ መቋጫው ሰላም
ነው። ሰው ለሰላም ይዋጋል፣ ለሰላም ይገድላል፣ ለሰላም ይሞታል፡፡ ሁሉም
ግን ሰላም አይሰጡትም፡፡ ሰላም በመግደልና በመሞት አትገኝም፤ ሰላም
ማደሪያዋ የያንዳንዳችን አእምሮ ነው!!*** ወደ ጨዋታችን እንመለስ፡- እንጨት ሻጭዋ እማማ ቤት ድግስ አለ … ዛሬ፡የመጽሐፍ ምረቃ፡፡ የመጽሐፉ መግቢያ ሲነበብ … “በህይወት መሰላል እንወጣለን፣ እንወርዳለን፤ ነገር ግን ዕድሜያችንን በሙሉ የምንፈተንባቸውን … እኔ ማነኝ? … ሰላም እንዴት አገኛለሁ? እያልን ዘወትር የምንጠይቃቸውን ጥያቄዎች መመለስ አልቻልንም፡፡የመኖር በረከት የሆነችውን የህይወት ድር ለመበጠስ ግን አፍታ አይፈጅም፡፡ … ቤት ገንብተን፣ የኤሌክትሪክ መብራት
ለማስገባት የሚፈጅብን ጊዜ፣ ገንዘብ፣ የዲዛይንና የኢንስታሌሽን ግንባታ
ሂደትና ውጣ ውረድ ከባድ ነው፡፡ መብራቱን አጥፍተን ቤቱን ለማጨለም ግን ሰኮንድ ትበቃናለች። አንድ ቦታ መበጠስ ነው፡፡ በስንት መከራ የታነፀችን
ህይወትና ሰላም ለማጨለምም የዚህኑ ያህል ቀላል ነው፡፡” ይላል፡፡ … ከ15 ዓመታት በፊት እራሱን ሊያጠፋ የነበረው ጎልማሳ የፃፈውን መጽሐፍ እማማ ይመርቁለታል፡፡ መታሰቢያውን ለስማቸው፣ ሽያጩን ለኑሯቸው ‹ጀባ›
ብሏቸዋል፡፡ በነገራችን ላይ ‹ሠላም› የሚል ስም እወዳለሁ። አሁን ደግሞ የሠላም ሚኒስቴር ተጨመረልኝ፡፡ …. እሰይ!!
ሠላም!!

ሸጋ ቀን💚💛❤️!!!!!

ምንጭ :- አዲስ አድማስ ጋዜጣ ጥቅምት 18 ቀን 2011

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
"የማይረሱ ግን የማይወሱ ... ተራ ያልሆኑ ተረኞች"
.
1988
ፍቼ ከተማ አንድ እሁድ ረፋድ…ገብርኤል ቤተክርስቲያን መግቢያ የአንገት ልብሴን ተከናንቤ፤ ከእማዬ ኋላ ኋላ እየተከተልኩ፤ የሰንበቴ ቤት ዳቦዬን እየገመጥኩ ፤ ከቅዳሴ መልስ ወደ ቤት ስንሄድ … አንድ ከወገቡ በላይ የተራቆተ ፣ በቁምጣ የቆመ ያልተጎሳቆለ ደመግቡ ጎልማሳ ሰው፤ ድርስ ነፍሰጡር ሚስቱን አጠገቡ አድርጎ ሸሚዙን ፊትለፊቱ አንጥፎ አንገቱን ደፍቶ የሚለምን ፣ እጆቹን አመሳቅሎ የት ነበር ያደረጋቸው? በእግ ኳስ ጨዋታ የቅጣት ምት ሲመታ የተደረደሩት ተከላካዮች የሚያደርጉበት ቦታ ።ሲለምን ምን ነበር ያለው? "ከጅማ መጥተን ያረፍንበት ቤርጎ ተዘርፈን ወደ አገራችን ለመመለሻ አጣን እርዱን " እሷ ምንም አትናገርም። አንገቷን ደፍታለች። ብቻ አጠገባቸው ከተኮለኮሉት ነዳያን የበለጠ ብሮች እና ሳንቲሞች ፊታቸው ተበታትኖ ነበር፡፡ ምናቸው እንደገረመኝ አላውቅም መንገዴን ትቼ ለአፍታ ቆሜ አየኋቸው፡፡እማዬ አጠገቧ እንደሌለሁ ያስተዋለችው ከራቀች በኋላ ነበር፡፡ ተመልሳ መጥታ "አንቺ ወሬኛ" እያለች እጄን ጎትታ ልትሄድ ስትል ዞራ ያየሁትን አየች፡፡ ከሙዳየ ምፅዋት የተረፋትን ስሙኒ ከመሀረቧ ፈትታ ለገሰቻቸውና ይዛኝ ሄደች፡፡ እስከዛሬ አልረሳኋቸውም፡፡ እነዛ ባልና ሚስቶች አሁን የት ይሆኑ? ብሩ ሞልቶላቸው በሰላም አገራቸው ገብተው ይሆን? ወይስ የለመኑትም ድጋሚ ተዘርፎባቸው? ከዛ በኋላ ወዴት ሄዱ? የት ደረሱ? በሰላም ወልዳ ይሆን? ወንድ ይሆን ሴት የወለዱት? ልጃቸው ስንት አመት ይሆነው/ይሆናት ይሆን?
.
ሰባተኛ ክፍል ሳለሁ ሰልፍ አበላሸሽ ብሎ በጥፊ የመታኝ ርዕሰ መምህርስ? በእሱ ጥፊ ደንግጬ ሂሳብ ትምህርት የክፍል ስራ 3/10 እንዳገኘሁ ይገምት ይሆን? ጡረታ ወጣ? ከአገር ወጣ? ሞተ ወይስ አለ?
.
1997
በ3 ቁጥር አውቶቡስ ወደ ሜክሲኮ ስሄድ ከኋላዬ በእናትዋ እቅፍ ላይ ሆና ፀጉሬን እየጎተተች በብስጭቴ ስትዝናና የነበረች ሳቂታ ህፃንስ? ልደታጋ ወርደው ወዴት ሄዱ ቤተክርሰቲያን ተሳለሙ? ፍርድቤት ገብተው ችሎት ታደሙ? ልጅቷ አሁን ስንት አመት ይሆናት ይሆን? ትምህርት ቤት ገባች? ስንተኛ ክፍል ደርሳ ይሆን? ወንድም ወይ እህትስ ይኖራት ይሆን?
.
ሃይስኩል ተማሪ እያለሁ ደሞ ጋንዲ ሆስፒታል ሄጄ (እናቴ እዛ ትሰራ ነበርና እሷጋ ... በዛውም 7ኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን ምግብ ቤት ምሳ አትክልት ልጋበዝ ፤ የገብስ ሻይ ልጠጣ)ሆስፒታሉ በር ላይ ሚስቱ በምጥ ተይዛ ሆስፒታል የገባች ባል ፊቱን ወደ አጥሩ አዙሮ በድሮ ኖኪያ ስልክ ምን ነበር ያወራው? "120 ብር ብቻ ጎደለኝ ከነገ ወዲያ እመልስልሃለሁ ፤ እባክህ አበድረኝ፤ መድሃኒት መግዣ ጎድሎኝ ነው" እያለ የሚማፀነው ሰውዬ የት ደርሶ ይሆን? ብሩን አግኝቶ ይሆን? ፊቱን ያላየሁት፣ ፊቴንም ያላየኝ ድምፁን ብቻ የሰማሁት ፣እንባዬን ያመጣብኝ (ያኔ እኔም ተማሪ ከየት አባቴ ላምጣለት)
.
2005
ፒያሳ አቡነ ጴጥሮስ ሐውልትጋ በክረምት፣ በማታ ፣ ጎርፍ በሞላው መንገድ ስደናበር ፤ እጁን ዘርግቶ እጄን ይዞ ያሻገረኝ ረዥም ሰውዬ ስሙ ማን ይሆን? ልጆች አሉት? ታሞ ሳልጠይቀው ቀረሁ? ለቅሶ አልደረስኩትም? ሁሌም ለችግረኞች እጁን የሚዘረጋ ይሆን? ጌታ ይባርከው!
.
2006 በበጋ ወቅት… ወደ ፀሐይ መጥለቂያ ገደማ ፤ ቦሌ ወሎ ሰፈር
አይቤክስ ሆቴል አካባቢ ከስራ ወጥቼ ወደቤቴ ሳዘግም፤ የሚያውቋት አንድ ዘመዳቸውን መስያቸው "ሰናይት" ብለው አገላብጠው የሳሙኝ ጥቁር ጥለት ነጠላ ያዘቀዘቁ እናት፤ አሁን የት ይሆኑ? እኔስ ምናለ" ተመሳስዬብዎት ነው ሰናይት አይደለሁም" ብላቸው? ሰላምታቸው ደስ ብሎኝ፤ እንዳላሳፍራቸው፤ እንዳላስደነግጣቸው፤ ከዛ ሰናይትን የሆነ ቀን ሲያገኟት "ምነው ያኔ አግኝቼሽ" ብለው ሲከራከሩ ምን ትመልስላቸው ይሆን? ማን ሞቶ ይሆን ነጠላ ያዘቀዘቁት? ከኔ በኋላ ተሳስተው የሳሙትስ ሌላ ሰው ይኖር ይሆን? ሰናይት ግን ደህና ናት?
.
የዛሬ አመት አካባቢ የመገናኛ ታክሲ ሰልፍ ላይ ሆኜ "የካሳንቺስ ነው?" ብሎ ሲጠይቀኝ "አይ የመገናኛ ነው" ያልኩት ሰውዬስ? በኋላ ለካ እኔም ተሳስቼ ሰልፉ የካሳንቺስ ሆኖ ሲገኝ ... ስቼ ያሳሳትኩት ሰውዬ የት ደርሶ ይሆን? ታክሲ አገኘ? ካሳንቺስ ለምን ነበር የሚሄደው? አውቄ ያሳሳትኩት መስሎት ተቀይሞኝ ይሆን? ይቅርታ እሺ!
.
ትናንት
.
.
.
በጣም ብዙ መሰል ሁነቶች ...የጭንቅላቴ ውስጠኛው ግድግዳ ላይ ተለጥፈዋል ፤"በሚያስደነግጥ ሁኔታ ነው የምታስታውሺው" ያልከኝ ወዳጄ ይህንን
ስታነብ ምን ትል ይሆን?

By teym tsigereda

@wegoch
@paappii
Belay Bekele Weya

ከማፄሜ በፊት...
.
.
ልጅ እያለሁ የምማረው ለማወቅ ሳይሆን ከትምህርት ቤት እንዳልባረር ነበር፡፡ ወላጅ አምጣ እንዳልባል ነበር፡፡
ልጅ እያለሁ የሚያለቅሱና የሚያባብሉ ሰዎች ያስቁኝ ነበር።መሳቅ እችል ነበር።
ልጅ እያለሁ መንግስቱ ሀይለማርያም እና እጅጋየሁ ሽባባሁ(ጂጂ) የሚያረጁ አይመስለኝም ነበር።
ልጅ እያለሁ በተለያዩ ብሔረሰቦች አክሰንት (የቋንቋ ዘዬ) በሚቀለዱ ቀልዶች እስቅ ነበር። እቀልድም ነበር።የሚቀየመኝ ግን አልነበረም የሚስቅና የሚያስቀኝ እንጂ።
ልጅ እያለሁ አኩኩሉ ስጫወት ነጋ ሲሉኝ መንጋቱን አምን ነበር።
ልጅ እያለሁ ፦ ፎቶ የምነሳው ብልጭ የሚለውን ለማየት ነበር፡፡
ልጅ እያለሁ ፦ ሀድራ የምትባል ልጅ አፍቅሬ ነበር፡፡ ሙስሊም መሆኗን ክርስቲያን መሆኔን አላውቅም ነበር፡፡ ትምህርት ቤት እንጂ ብሔር እና ሀይማኖት ያለን አይመሥለኝም ነበር፡፡ እረ ፆታችን የተለያየ መሆኑን አላውቅም ነበር፡፡ ዝም ብሎ ፍቅር!!!
ልጅ እያለሁ ፣ አልፈኪ ሚባል ጓደኛ ነበረኝ ፡፡ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን ተሳልሜ ስገባ ተሳልሞ ይገባ ነበር፡፡ ሺህ ኦጀሌ መሥጂድ ስንገባ ተሳልሜ እገባ ነበር፡፡ ሀይማኖት እንዳለ አላውቅም ነበር፡፡ 
ልጅ እያለሁ ጥል እና ኩርፊያዬ ከቂም የራቀ ነበር። ምሳ እቃ እንጂ ቂም የሚቋጠር አይመስለኝም ነበር።
ልጅ እያለሁ ፦ የሚቆነጥጠኝ የሚቆጣኝ ሁሉ ወላጄ ይመስለኝ ነበር፡፡ ጎረቤት እንዳለ አላውቅም ነበር፡፡
ልጅ እያለሁ ፦ ባንዲራ ሲሰቀል አድጌ የማልገልፀው ስሜት ያቆመኝ ነበር፡፡
ልጅ እያለሁ ፦ ኢትዮጵያ ሀገር ሳይሆን አምላክ ትመሥለኝ ነበር፡፡
ልጅ እያለሁ ፣ ሰው ነበርኩ!!!
ሳድግ ነገሮች የተገላቢጦሽ ሆኑ። "ልጅነት" "ጅልነት" ሆነ!
@yeyhudaanbesa
@wegoch
Forwarded from Roger Mulugeta
Ethiopian App Store በቴሌግራም ደረጃቸውን የጠበቁ ጠቃሚ የሆኑ የሞባይል #አፕሊኬሽኖች (Mobile App)፤#ሶፍትዌሮች (Software)፤ #ጌሞች (Games) እና ወቅታዊ የቴክኖሎጂ መረጃዎች የሚያገኙበት ቻናል:: አሁኑኑ ይቀላቀሉ!

https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAEZAFZd8H5dwOnYJbQ
2024/09/29 15:22:04
Back to Top
HTML Embed Code: