Telegram Web Link
ክፍል ሶስት

አፄ ቴዎድሮስ መቅደላ ላይ ካረፉ በኋላ ምን ተፈጠረ?👇

ከአጤ ቴዎድሮስ ሞት ኋላ ንጉሥ ነኝ ያሉት አጤ ዮሐንስ በደርቡሾች እጅ እስከሚወድቁበት ጊዜ ድረስ ለምኒልክ ከንጉሠነት ወደ ንጉሠ ነገሥትነት እንዳይሸጋገሩ ሁነኛ እንቅፋት ነበሩባቸው፡፡ ሆኖም አጤ ዮሐንስ መጋቢት ፩ መተማ ላይ በተጀመረው ጦርነት ምክንያት የአጤው ህይወት በማለፉ ለምኒልክ ለንጉሠ ነገሥትነታቸው ብዙ ተቀናቃኝ አልተነሳባቸውም፡፡
በሥርዓተ ንግሥ ጊዜ ግን ጳጳሳቱ #አቡነ_ጴጥሮስ እና #አቡነ_ማቴዎስ "በእኔ እጅ ነው ይነግሳሉ" እየተባባሉ ተጣሉ፡፡
#አቡነ_ጴጥሮስ የአጤ ዮሐንስ ጳጳስ ሲሆኑ "ቀድሞም የንጉሠ ነገሥቱ ጳጳስ እኔ ነኝና ዘውድ መድፋት የሚገባቸው በእኔ እጅ ነው!!" ሲሉ
#አቡነ_ማቲያስ ደግሞ የአጤ ምኒልክ ጳጳስ ሲሆኑ እሳቸውም "የንጉሠ ነገሥቱ ዕጣ ወደኔ ከደረሰ ምኒልክን የማነግስ እኔ ነኝ!!" አሉ
በስተመጨረሻም #በአቡነ_ቄርሎስ አማላጅነት አባ ማቴዎስ እንዲሆኑ ተወሰነ፡፡
የንግሡ በዐል በ1882 ጥቅምት ፳፭ ቀን በአዲስ አበባ እንዲሆን ተወሰነ፡፡ ለሊቱኑ ስርዐተ ንግሡ ተጀምሮ ዘጠኝ ሰዐት ሲሆን ጳጳሱ የወርቅ ሰይፍ ባርከው አስታጠቋቸው፡፡ ቅብዐ መንግስቱን ቀብተው የወርቁን ዘውድ ጳጳሱ ደፉላቸው፡፡ ቅዳሴውም ወደ ረፋዱ ገደማ አለቀ፡፡
ከስርዐተ ቅዳሴው በሁዋላ ዘውዳቸውን ደፍተው ካህናቱን ከፊትና ከኋላ እያጠኑ በራሶችና በደጃዝማቻቾች ታጅበው ከቤተክርስቲያን ብቅ አሉ፡፡ ህዝቡም "ሺ ዐመት ያንግሰዎ" እያለ ደስታውን በእልልታ ገለጠ፡፡ ከተዘጋጀላቸው ማረፊያ አልጋ ላይ ቁጭ ብለው፡፡
"ከእንግዲህ ንጉሥህ እኔ ነኝ ዕዳ ያለብህ ነፃ ብየሃለሁ፡፡ በዱር በገደልም ያለህ ምሬሃለሁ ግባ" የሚል አዋጅ አስነገሩ፡፡ ከዚህም ኋላ ወደ ቤተመንግስታቸው ሲገቡ 101 ጊዜ መድፍ ተተኮሰ፡፡

ዳግማዊ ምኒልክ ከማንኛውም የኢትዮጲያ ነገሥታት የተለየ የሚያደርጋቸው አንድ የንግሥ ነገር አለ፡፡ ማንኛውም ንጉሥ በሚነግስበት ጊዜ የበፊት ስሙን ለውጦ ሲነግስ ምኒልክ ግን ስማቸውን ሳይለውጡ እዛው በስማቸው ነገሡ፡፡

እድሜና ጤናውን ከቸረን ይቀጥላል

@wegoch @kinchebchabi
@ethio_art
‹‹ያ’ለምጣም ምኒልክ››
❇️💠❇️💠✳️💠✳️
---›
★ በአንድ ወቅት አጤ ምኒልክ ያማረ ሙሉ ልብስ አሰፉ። ሰፊው ጥሩ አድርጎ ስለሰፋላቸው ሲለብሱት እንደ ሕጻን ፈነደቁ። መስታወት ፊት እየተንጎራደዱ አይተው አልጠግብ አሉ። ከዚያ ሰፊውን እስቲ አንተ ደግሞ ልበሰው አሉት። ልብስ ሰፊው እሺ ብሎ ለብሶት መጣና በፊታቸው እጅ ነሣ። ልብሱ አምሮበት ነበር። እጅ ነስቶ ሲቆም አዩትና "አንተ ቀጣፊ እጅ የነሣኸው አውልቅ ብልህ ልታስኮንነኝ ነው? በል ለእኔ ሌላ ስፋልኝ" ብለው ከነልብሱ ሸኙት።
---›
★ ሁለት ሴቶች አጤው ፊት ለክስ መጡ (አንድ ደራሲ ወዳጄ ነው የነገረኝ) አንደኛዋ ሴት ክስዋን እንዲህ ስትል አሰማች ‹‹ጃንሆይ ይፍረዱልኝ ፣ ይህቺ ሴት ‹አንቺ ቱርክ› ብላ ሰድባኛለች›› አለች። ምኒልክ ወደተከሳሽዋ ዞረው ‹‹ቱርክ ብለሽ ሰድበሻታል?›› ብለው ጠየቋት። ተከሳሽዋም ‹‹አዎ ሰድቤያታለሁ ጃንሆይ›› አለች። ካሳ ለመካስ ስትጠየቅ ግን የለኝም ደሃ ነኝ አለች። እምዬ ምኒልክ እንዲህ የሚል ደብዳቤ አጻፉ ‹‹እገሊት እገሊትን ቱርክ ብላ ስለሰደበቻት ካሳ የሚሆን አምስት "ብር" (?) ከግምጃ ቤት ወጥቶ እንዲከፈልላት ይሁን››።
---›
★ አጤ ምኒልክ ከመኳንንቶቻቸው ጋር ግብር ሊበሉ ወደ አዳራሽ ሔዱ። ሊገቡ ሲሉ ግን ምኒልክ እንዲህ አሉ ‹‹አሁን እኛ ልንበላ ከገባን ባለሟሎቻችንና ፈረሰኞቻችን ሳይበሉ ከቆዩ ልባችን አያርፍም ፣ ስለዚህ እነርሱ ገብተው ይብሉና ከዚያ በኋላ እኛ ያለ ሃሳብ ስንጫወት እንቆያለን›› ስለዚህ እነርሱ ውጪ ቆመው አገልጋዮቻቸው ገብተው በሉ። (አንድ ድንቅ አባት የነገሩኝ)
---›
★ በአዝማሪ መመስገን የሰለቻቸው አጤ ምኒልክ አንዱን አዝማሪ እስቲ አሁን ደግሞ ስደበኝ አሉት። አዝማሪው እንዲህ አለ:-
‹‹ይገድሉኝም እንደሁ ይኸው ቆምኩልዎ፤
ያ'ለምጣም ምኒልክ ብዬ ሰደብኩዎ››፡፡
......ቅኔው ስለገባቸው የዋሁ ንጉሥ ልባቸው ተነክቶ አለቀሱ።
---›
እነዚህ በተባራሪ የሰማኋቸውና ያነበብኳቸው የንጉሡ የዋህ ገጽታ ናቸው። እምዬ ምኒልክ ሥራዬ ተብሎ ቢጠና ከዚህ በላይ የሚገኝባቸው የዋህ ንጉሥ ነበሩ።
★ አጤ ምኒልክ እምነታቸው ጽኑዕ ስለነበር ሲታመሙ የመጽሐፍ ቅዱስ ገጽ ቀድደው ይበሉ ነበር ይባላል። አንዳንድ ጸሐፊዎች ደግሞ የሚበሉት መጽሐፈ ነገሥትን ሲሆን ድል አድራጊነት እንዲሠጣቸው ነው ብለውም ጽፈዋል።
---›
ነሐሴ 12 የአጤ ምኒልክ እና የእቴጌ ጣይቱ የልደት ቀን ነው፤ እንኳን ተወለዱ !!!
---›
#ምንጭ:- (ከዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ገጽ)

@wegoch @kinchebchabi
@ethio_art
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ክፍል አራት

ምኒልክ የኢትዮጲያ ንጉሠ ነገሥት ከሆኑ በኋላ አስቸጋሪ ግን ኋላ ላይ የከሩበት ነገር ተፈጠረ ይህም የዐድዋ ጦርነት ነው፡፡ የውጫሌ ውል መዘዝ:-


<<ምኒሊክ ተወልዶ ባያነሣ ጋሻ
ግብሩ እንቀላል ነበር ይሄን ጊዜ አበሻ፤
*
ገበየሁ ቢሞት ተተካ ባልቻ
መድፍ አገላባጭ ብቻለብቻ፤
*
የአድዋ ሥላሴን ጠላት አረከሰው
ገበየሁ በሞቴ ግባና ቀድሰው፤>>

የአድዋ ድል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ክብር
ማኅተም፤ የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተጋድሎ
ቀንዲል ነው፡፡ የመላው ዓለም ተፈጥሮአዊ
ግብር እና ሰብአዊ ክብር የታደሠው፤
በእውነትና በፍትህ ህልውናና ምልዓት ላይ
የተሰካ ትልቅ ጥርስ የተነቀለው … በአድዋ
የታላቅ ህዝቦች ታላቅ ድል ነው፡፡
ከአዲስ አበባ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ስንሄድ
1066 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ታላቁ ጦርነት
የተደረገበትና ታላቁ ድል የተገኘበት ሥፍራ
አድዋ ከተማና የከተማው ግድም ገመገሞች
ይገኛሉ፡፡ በኢትዮጵያውያን አቡሻኽር (Julian
calendar) የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም፤
ወይም በአውሮጳውያን የዘመን አቆጣጠር
(Gregorian Calendar) February
(የካቲት) መጨረሻ እና March (መጋቢት)
መጀመሪያ ላይ 1896. ለጦርነቱ መነሻ
የሆነው ውል የተፈፀመው በዚሁ ዘመን
ከአዲስ አበባ በስተሰሜን 468 ኪሎ ሜትር
ርቀት ግድም ከውጫሌ ከተማ ግርጌ
ከአምባሰል ተራራ ሥር ወሎ ውስጥ ንጉሥ
ይስማ እየተባለ በሚጠራ ሥፍራ ነው፡፡
ሸልዶ ተራራ ወይም (ሶሎዳ ተራራ)፤
ማርያም ሸዊቶ፤ አዲ ተቡን፤ ረቢ አርእየኒ
(እግዚሃር አሳየኝ)… በመሠኘት የሚታወቁት
እነዚህ ገመገሞችና ተራራማ ሥፍራዎች
ዋነኞቹ የጦር ግንባሮች ናቸው፡፡ በመቶ ሺህ
የሚሠላ የኢትዮጵያ ገበሬ ሠራዊት ከአንድ
ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የአውሮጳ ቅኝ ገዢ
ወራሪዎችን ድባቅ ከመታና ረግጦ ካስወጣ
በኋላ ከምሽቱ አራት ሰዓት ግድም (የካቲት
23 ቀን) እንዳማርያም ላይ ተሰባስቦ በአንድ
እግሩ ቆሞ ቀኙን ለሰጠው አምላክ
ምሥጋና አቅርቧል፡፡ አባት ሆይ፤ ንቀውን
የመጡ የአገራችንን ድንበርና ልዕልና የደፈሩ
የአውሮጳ ኮሎኒያሊስት ወራሪዎችን
እንድናሸንፍ ስለረዳኸን
እናመሰግንሃለን ...
ሃያ ዘጠኝ ሺህ ፈረሰኞችን ጨምሮ ከመቶ
ሺህ እስከ መቶ ሃያ ሺህ የሚገመት አንድ
ሺህ ኪሎ ሜትር በባዶ እግሩ የተጓዘ
የኢትዮጵያ የገበሬ ሠራዊት በወታደራዊ
አካዳሚ የሠለጠነውን የአውሮጳ ወራሪ ጦር
የካቲት 23 ማለዳ አሥራ አንድ ሰዓት ግድም
ገጥሞ ከረፋዱ አራት ሰዓት ላይ ማሸነፉን
አረጋግጧል ይለናል የታሪክ ተመራማሪው
ጆርጅ በርክሌይ የአድዋ ጦርነትና ዳግማዊ
አፄ ምኒሊክ በተሰኘና ዳኘው ኃይለሥላሴ
ወደ አማርኛ በተረጐሙት መጽሐፉ ላይ፡፡
የኢትዮጵያ ገበሬ ሠራዊት ፈረሱ ላይ ሆኖ
የጋሻውን እምብርት መሬት ላይ እያጠቀሰ
ጐራዴውን አየር ውስጥ እየቀዘፈ ባበደ
መንፈስ (በተቆጣና በቆረጠ መንፈሥ)
በጀግንነት ተዋግቷል፡፡

ጦርነቱ በተጀመረ ከአምስት ሰዓት ባልበለጠ
ጊዜ ውስጥ ሃምሣ ስድስቱም የኢጣሊያ
መድፎች ሙሉ ለሙሉ ተማርከዋል፤ የቅኝ
ገዢውን ወራሪ ሠራዊት ከመሩት ጀኔራሎች
ጄኔራል አልቤርቶኒ ሲማረክ የሠራዊቱ ዋና
አዛዥ ጄኔራል ባራቴሪ ከጥቂት አጃቢዎቹና
በሽንፈት ከተበታተኑ የኢጣሊያ ወታደሮች ጋር
ሸሽቷል፡፡

ምኒልክ ለሙሴ ሽፍኔ በፃፉት ደብዳቤ እንዲህ አሉ
"....በጥጋባቸው አድዋ ላይ ተዋግተው ድል ሆኑ፡፡ እኔ ግን በድንቁርናቸው ብዛት የእነዚያን ሁሉ ክርስቲያን ደም በከንቱ መፍሰሱን እያየሁ ድል አረግኋቸው ብዬ ደስ አይለኝም...."

እድሜ ከጤና ከቸረን...
......ይቀጥላል

@wegoch @kinchebchabi
@ethio_art
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እኚህ የዘመን አቅላሚዎችን የሀገር ጀግኖቻችንን ልደት እናከር ዘንድ ስለበቃን ደስታችን የላቀ ነው

ክብር ለእነዚህ ታላላቅ ነፍስ ላላቸው ክቡራን
@ethio_art @wegoch
@kinchebchabi
የምኒሊኳ ቅዳሜ!!!
(የሺሀሳብ አበራ)

የዘመን ነዶው ሲተረተር ከነሀሴ 12 ቀን 1836 እስከ ነሀሴ 12 ቀን
2010ዓም 174 ዓመት ቢረዝምም ምኒሊክ እያደር ይቀርባል፡፡ይወለዳል፡፡እ
ያደር ይገናል፡፡ምኒሊክ በአድዋ ታድሷል፡፡
የምኒሊክ ትምክህት እና የነፍጠኝነት ጋብቻ አድዋን ወለደ፡፡
..............
ንጉሱ ገና የ 20 ዓመት ጎረምሳ ሆኖ የገናናውን የዳግማዊ
ቴዎድሮስ ልጅ ወይዘሮ አልጣሽን ቴዎድሮስን አገቡ፡፡ደጃዝማች የሚል
ማዕረግም ተደረጎታቸው፡፡ምርኮኛ ቢሆኑም መይሳው
ብልህነታቸውን አይተው በቤተመንግስታቸው አነገሷቸው፡፡
ደጃዝማች ምኒሊክ ግን ከቴዎድሮስ እልፍኝ ወጥቶ ሸፈተ፡፡
ባለቤቱን ትቶ ከቴዎድሮስ አምልጦ ራሱ ቴዎድሮስ ሆነ፡፡ ምኒሊክ
ያለቃ ፊት ሲጠይም እና ሲፈካ የሚሸበር እና የሚደሰት አጎብዳጅ
አልነበረም፡፡በራሱ የመመካት ደንዳና ትምክተኛነቱን ከአለቃው
ቴዎድሮስ በመሸሽ አሳየ፡፡ በቁርጥራጭ ጥቅማቅም ነገውን
የሚገብር፣ በማጎብደድ የሚችለውንም የማይችለውንም
በመሸከም ጀርባውን የሚያደክም.....ያላመነበትን ሁሉ
ለመሸከም ትምክህቱ አይፈቅድለትም ነበር፡፡ ራስን የመሆን
ትምክህት፡፡
....
ጣሊያን ዘመናዊ ጦር ታጥቆ በሰሜን ገባ፡፡ዳግማዊ ምኒሊክ
የጣሊያን ሰራዊት እንደ ፍልፈል መሬት እየጫረ ብለው ሰራዊቱን
ነፍሳት አድርገው ቆጠሩት፡፡ የምኒሊክ ወታደርም የጣሊያን
ሰራዊት እንደነፍሳት ቆጥሮ 70% በ 4 ሰዓታት ብቻ አጨደው፡፡
የመድፍ አፍ በምኒሊክ ሰራዊት ነፍጥ ተደፈነ፡፡ ከፍ ያለ
የእችላለሁ ትምክህት ጣሊያንን ውሃ ውሃ አሰኘው፡፡
..
በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት 70ሺ ገብረናል፡፡በጋሻ እና በጎራዴ
በፈረስ ተጉዘን በአድዋ ጦርነት ግን ከ 100 ሺ ወታደር ከ 5-7
ሺ ብቻ ህይዎት ከፍለናል፡፡ የማነስ ቁልቁለት ይሉት ነገር ይሄ
ነው፡፡ ትምክህት በነፍጥ ይጠበቃል፡፡ነፍጠኞቻችን 1888
የጣሊያን ወታደሮችን ማርከው ተንከባክበው ይዘው ከሁለት
አመት በኃላ በድርድር ለጣሊያን አስረከቡ፡፡ትምክህት ላነሰ ነገር
ለመጨነቅ ዕድል ይነፍጋል፡፡ሞርኮኛ እና ታሳሪ አይደበደብም፡፡
ዛሬ የራሱን ዜጎች በማነስ አብዶ እያሰረ ብልት የሚያኮላሽ
የሚያሰቃይ ቡድን ከየት መጣ?! አድዋ ድልን እንጂ ነፃነትን
አላወረሰንም፡፡የምኒሊኩ አድዋም በየዘመኑ ሂደት እየሸሸን ነው፡፡
....
ዳግማዊ ምኒሊክ ብዙ ሰርተው ጥቂት እንኳን አይናገሩም፡፡፡
አድዋ የነፃነት በዓል ሆኖ የተከበረው ከ 7 ዓመት በኃላ ነው፡፡
ምክንያቱም ለምኒሊክ አድዋ ትንሽ ድል ነው፡፡ሌላ ድል ና ሞገስ
ይናፍቃል፡፡በጦርነት ለሞቱት ወታደሮችም አዝነው ስለነበር
የአድዋ የድል በዓል ለመጀመሪያ ጊዜ የተከበረው ከ 7 ዓመት
በኃላ በ 1895 ዓም ነው፡፡
....
እምየ ምኒሊክ እሁድ 12:00 የካቲት 23 ለሚጀመረው ጦርነት
እስከ ሌሊቱ ስድስት ሰዓት አድዋ ስላሴ የንግስ በዓል
የሚያከብሩ ይመሰል ተረጋግተው ይፀልዮ ነበር፡፡ የፆሎት
መፅሃፋቸው 11:00 አስቀምጠው በቀጥታ ነፍጥ አነሱ፡፡ ምኒሊክ በደህናው
ቀን ፆሎተኛ፣በከፋው ቀን ነፍጠኛ የመሆን ሁለት ስሉ ባህሪ ነበራቸው፡፡ታላቁ
መፅሃፍ " እንደ እርግብ የዋህ፣እንደባብ ብልህ" እንዲል፡፡
የእብሪተኛው ወታደር አንገትም እንደ ጓሮ ጎመን በቀላሉ
ተቀነጠሰ፡፡ ከፍ ያለ ትምህክተኛነት እና ነፍጠኝነት በአድዋ ተራራ
ተጋብተው በምኒሊክ የጦር መሃንዲስነት ድል ና ነፃነትን ፈጠሩ፡፡
...
ዓለም ላይ በአግባቡ ከተያዙ ትምክህትን እና ነፍጠኛነትን
የመሰሉ ተፈጥሮአዊ ፀጋዎች የሉም፡፡ የሩሲያ ገናናነት፣የአሜሪካ
እጀ ረጅምነት፣የጃፖን ስልጣኔ፣የሰሜን ኮሪያ እና የኢራን አዲስ
ጉልበት መሰረቱ የተጋገረው ትምክህትን ባዘለ ነፍጠኝነት ነው፡፡
ትምክህተኛ ስትሆን የሚያስመካህን ድጋፍ ፍለጋ ትፈጥናለህ፡፡
እንቢ ባይነት የትምክህት ፍሬ ነው፡፡ የአለቃን ስሜት እያደመጡ
መብረክረክ ታላቁን የሰው ፍጡር ወደ እንስሳትነት ይደምራል፡፡
ዓለም የደፋሮች ብቻ ናት...አድዋም የድፍረት ውጤት ናት፡፡ምኒሊክም
የመድፈር አቀበት ነው፡፡
...
ብዙ አፍሪካውያን ከነጭ የተፈጠሩ ስለሚመስላቸው ለነጭ
ይሰግዳሉ፡፡አሊያም ያጎበድዳሉ፡፡ ይሄ በኛ በምኒሊክ በአድዋ
ተሽሯል፡፡ አድዋ ኢትዮጲያዊነት በምኒሊክ የተፈተለበት የጋራ
የማይቆሽሽ ሸማ ነው፡፡ የአፍሪቃም የነፃነት ጎህ ነው፡፡ የዓለም
ጥቁሮች ሁሉ የሰባዊነት መነሻ ነው፡፡ለዚህም ነው ክርስትና ያለ ኢየሱስ
ክርስቶስ፣እስልምና ያለ ነብዮ መሃመድ እንደማይሰበከው ሁሉ ኢትዮጲያን ያለ
ምኒሊክ ማንሳት ባዶ የሚሆነው ነው፡፡
...ምኒሊካዊነት ከፍ ይበልን!! አድዋም ይቅረበን!! መልካም ልደት ለጃንሆይ
ምኒሊክ!!

@ethio_art @wegoch
@kinchebchabi
Audio
🔈🔈🔈🔈

ከ 107 አመታት በፊት የተቀረፀው የአፄ ምኒልክ ድምፅ

ምንጭ ከስነጽሁፍ ዓለም

@wegoch @kinchebchabi
@ethio_art
Forwarded from Mykey (「Mikiyas Liyew Taddese)
“ኢትዮጵያ፤ ትወልዳለች እንጂ አታሳድግም”


ከዕለታት አንድ ቀን አንድ በኑሮው የደላው፤ ሀብቱ የተመቸው፣ እጅግ
ቀብራራ ሰው፣ ነበረ፡፡ የሰፈር ሰው ሁሉ ደግና ለተቸገረ ደራሽ ነው ይለዋል፡፡
ወደ ቤተ - ዕምነት ሄዶ ሰባኪው የሚሉትን ይሰማል፡፡
ሰባኪው - በሀልዮ በነቢር በገቢር የተሰራ ሐጢያትን እግዚሐር ይፍታን
ምዕመናን - አሜን!
ሰባኪው - ለተቸገረ እርዱ!
- በሽተኛ ጠይቁ!
- ለደሀ መጽውቱ!
- ሁለት ያለው አንዱን አንድ ለሌለው ይስጥ!
- የላይኛው ቤታችሁን እምድር ሳላችሁ አብጁ!
- ፁሙ! ፀልዩ!
- ትምህርታችሁን ይግለጥላችሁ!
ምዕመናን - አሜን!
ሰባኪ - ከእናንተ የተሻለ የሚኖር ማን አለ?
ምዕመናን - ማንም!
ሰባኪ - ከእናንተ መካከል ሳይበላ የሚያድር ማን አለ?
ምዕመናን - ማንም!
ሰባኪ - ትሰጡት አትጡ!
ምዕመናን - አሜን!
ሰባኪ - በየመንገዱ የወደቁትን ለማሰብ ልቦና ይስጣችሁ!
ምዕመናን - አሜን!
ሰባኪ - የሰማነውን በየልቦናችን ያሳድርብን!
ምዕመናን - አሜን! አሜን!
ሁሉም ወደ የቤታቸው ሄዱ፡፡ ያም ሀብታም ሰው ወደ ቤቱ ለመሄድ መንገድ
ጀመረ፡፡
ወደ ቤቱ መሄጃው ላይ አንድ ድልድይ አለ፡፡ እድልድዩ ላይ በግራና በቀኝ
በኩል ተቀምጠው የሚለምኑ ሁለት ዓይነ - ሥውር ለማኞች አሉ፡፡
መካከላቸው ሲደርስ ከኪሱ በርካታ ሳንቲሞች አወጣ!
ለማኞቹ - “ጌታዬ አትለፈን! ካለህ አይጉደልብህ! ትሰጠው አትጣ!
ትመፀውተው አትጣ! እጅህ እርጥብ ይሁን!” ይሉታል፡፡
ሀብታሙ ሰው ከኪሱ ያወጣቸውን ሳንቲሞች በሁለት እጆቹ ይዞ አንኳኳቸው፡፡
ሿ! ሿ! ሿ! አደረጋቸው፡፡ ሁለቱ ዐይነ - ስውር ለማኞች በጣም ጎመጁ፡፡
ከአሁን አሁን መጥቶ ይሰጠናል ብለው ሲጠብቁ, ሳንቲሞቹን መልሶ ኪሱ
ከቶ፤
“ተካፈሉ!” ብሎ ሄደ፡፡
በወዲህ ወገን ያለው ለማኝ; “ያኛው ተቀብሏል፤ ያካፍለኛል” አለ፡፡
በወዲያ በኩል ያለውም ለማኝ፤
“እሱ ተቀብሏል፣ ያካፍለኛል!” አለ፡፡
ሁለቱም ምንም ሲያጡ ተነስተው አንዱ; “ስጠኝ! የሰጠንን አካፍለኝ!
ሌላውም; “ላንተ ነው የሰጠህ አካፍለኝ!”
አንተ ወስደሃል … አንተ ወስደሃል” እየተባባሉ፤ ድብድብ ጀመሩ፡፡
ሀብታሙ ሰው; ከሩቅ ሆኖ ከት ብሎ ሳቀባቸውና ወደ ቤቱ ሄደ!
***
እኛ ኢትዮጵያውያን ደግ፣ እንግዳ ተቀባይ፣ ለተቸገረ ደራሽ፣ ተዛዛኝ …
እንባላለን፣ እንጂ ጭካኔያችን ለከት የለውም! ውስጣችን አልተፈተሸም፡፡
አልተመረመረም! በሰብአዊነት ሽፋን የምንኖር ኢ-ሰብአዊዎች ነን! ፈዋሽ
ሀኪም አልተገኘልንም እንጂ የውስጥ ደዌ አለብን - ጭካኔ! እንዋደዳለን
እንላለን እንጂ ውስጣችን በጭካኔ አባዜ የተሞላ ነው! የመሀይምነታችንና
የአረመኔነታችን (Barbarism) መጠን ገና አልታወቀም - አልተጠናንም!
እርግጥ ሁላችንም ላንሆን እንችላለን እንጂ የክፋታችን ልክ ይህ ወሰንህ፣
ይህ ዲካህ የሚባል አይደለም፡፡ አያምጣው እንጂ ክፉ ጊዜ ቢመጣ፣ እርስ
በርስ ሊያበላላን ይችላል! ነፃነት ይከብደናል! መከራ ከመልመዳችን የተነሳ
ነፃነት ሸክም ይሆንብናል፡፡ ድህነታችን የሀብት ብቻ ሳይሆን የአዕምሮም ነው!
የልቡናም ነው! ደግ ጊዜ ያምጣልን እያልን፣ ደጉን ጊዜ ገፍተን እንጥላለን!
ይሄ ኃይለኛ የልቡና ቀውስ ነው! አዎንታዊ ነገር የማይጥመን ከሆነ፣
አሉታዊው ነገር በደም ጎርፍ ያስተጣጥበናል!
ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን በቴያትሩ እንዳስቀመጠው፤
“ሞትን ለሚሻ ሞትን ነው መንፈግ! ህይወትንም አለመቸር! እማህል ቤት
ነው የሰው ልጅ ጥቅም የሚሰጥ! ሰው ሆኖ ካሹት፣ ጥቅም የማይሰጥ
የለም!” ይለናል፡፡ ለዚህ ፀሐፊ፣ የአበሻ ውስጠ ነገር ዱሮ ነው የገባው ማለት
ነው!
ያም ሆኖ “በርኩቻው ማህል ፀጥ ብለህ ለመጓዝ ሞክር” ይላል፤ የጥንቱ
የጠዋቱ የዴዚዴራታ ምክር! ምክሩ ከገባን ዓለም በውካታ የተሞላች ናት -
አንተ ግን ተረጋግተህ ተጓዝባት ማለት ነው፡፡ መረጋጋት፣ ማረጋጋት፣
ሁኔታዎችን በሰከነ ዐይን ማየት፤ የበሳል ሰው መርህ ነው፡፡ “በካፊያው
ከተረበሽክ የዶፉ ዝናብ ጊዜ ምን ይውጥሃል?” ይላሉ አበው፡፡ ህዝባችንን
ማሳወቅና ማስተማር፣ መሰረታዊ ጉዳያችን መሆን አለበት፡፡ በክፋት፣
በጭካኔና በአረመኔያዊነት (Barbarism) እና በህዝባዊ እምቢተኝነት (Civil
disabidience) መካከል፤ የገደል ያህል ልዩነት አለ፡፡ የፊተኛው የኃላ
ቀርነት፣ የኋለኛው የአዋቂነት አስተሳሰቦች ናቸው፡፡ በመሰይጠንና በመሰልጠን
መካከል ያለውን አደጋ እናስተውል፡፡ የዱሮ ፍልስፍናም ቢሆን “ህግ
የማይገዛውን ነፃነት፣ ኃይል ይገዛዋል” የሚለውን አባባልም እንደገና
ማውጠንጠን ግዴታ ሊሆን እንደሚችል አንዘንጋ፡፡ “ጥንቃቄ ሲጠብቅ ፍርሃት
ይሆናል” የሚለውንም አንርሳ፡፡ ዞሮ ዞሮ የሚመለከተውና ኋላፊነቱ
የሚሰማው ክፍል የሚያደርገውን ያውቃል ብለን እንገምታለን - “እኔ ተጎድቼ
ባመጣሁበት ውሰደው” ይላል ጮሌ ነጋዴ፡፡
ሀገራችን ሾተላይ ያለባት ይመስል ፅንስ ይጨነግፍባታል፡፡ ማስወረድ ልማድ
ሆኖባታል፡፡ አሮጊው እንቅፋት አዲስ እንቅፋት እየፈለፈለ ያሽመደምዳታል፡፡
“እኔ ስወለድ ነው የሳቅ ጀምበር የጠለቀችው” የሚል ኢትዮጵያዊ እንዳይበዛ፤
ልባም ልባሞቹ ሰዎች መመካከር አለባቸው፡፡ “ገዢ እንጂ መሪ
አያምርብንም” እንዳለው አፍሪካዊው ፀሐፊ፤ በግድ የገዢ ያለህ እያልን
እንዳንፀልይ ምህረቱን ይላክልን፡፡ ውድቀትን ማቀድ አልፎ አልፎ ያዋጣል
ብንልም፣ መነሻችን ጨለምተኝነት ከሆነ፣ ከ“ሁሉም ይውደም
ፍልስፍና” (nhilism) አባዜ አይተናነስም! “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል”
እንዳለችው እንስሳም፤ የአገር ጨለማን መባጀት ክፉ እርግማን ነው!
የየዓይነቱን እርግማን በበቂ አይተናልና አዲስ እርግማን ፍለጋ መባቸር ከንቱ
መላላጥ ነው፡፡ “ከመርገምት ሁሉ የከፋው መርገምት፤ ቋንቋ ለቋንቋ
መጠፋፋት ነው!” ይላል ገጣሚው፡፡ መግባባት እንዳይጠፋብን
አሳቢዎቻችንን (Thinkers) እናዳምጥ እንሰማማ!! እርስ በርስ እንናበብ፡፡
መናበባችንን ይባርክልን ዘንድ ቀና እንሁን፡፡ አገራችን ኢትዮጵያ ከእንግዲህ
“ትወልዳለች እንጂ አታሳድግም” መባሏ መቆም አለበት፡፡ የበቀሉ ዕድሎች
እንዳይጠወልጉ እንንከባከባቸው! እውቀታችንንና አቅማችንን ሁሉ
አፍንጫችን ሥር ባለው ጉዳይ ላይ ሳይሆን ትልቁን ስዕል አገርን (The
Bigger Picture) ማየት ላይ እናውለው፡፡ የግለሰቦችን ምንነት ከአጠቃላዩ
ህዝብ ህልውና ለይተን እንይ! ዛሬም ትምህርታችንን ይግለጥልን!!!


ምንጭ:- አዲስ አድማስ

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
Online market that will satisfy ur needs, find what u are looking for and order what u want👌join us now for ur better needs trust me.@shopi_nova Pls use our link and share it with friends those who wants any kind of online shoppings ¡¡Enjoy here with fair price thank you
📓አንድ ደብተር ለህፃናቶች ተስፋ ነው፡፡
📓አንድ ደብተር አንድ ሺነ ችግሮችን ይቀርፋል ፡፡
📓አንድ ሺ ደብተሮች አንድ ሚሊዮን ችግሮችን ይቀርፋሉ፡፡


📓እኛ የምንችለውን ያህል ደብተር በመግዛት እንጀራ ጋግረውና
እንጨት ተሸክመው ልጆቻቸውን የሚያስተምሩ ሚስኪን ወላጆችን በማገዝ ለኢትዮጵያ ተስፋ የሚሆኑ ልጆችን እናስተምር፡፡

📓እናም ውድ የቻነሎቻችን አባላት የቻላችሁትን ያህል የትምህርት ቁሳቁስ እንዲያበረክቱ በ አክበሮት እንጠይቃለን

"መረዳዳት የቀደመም ቋንቋችን ነው!!!"

ለበለጠ መረጃ ከታች ባሉት ስልኮች ይደዉሉ

+251912659753 @balmbaras
+251984740577 @gebriel_19

@getem
@wegoch
@seiloch
@Mykeypicture
መነበብ ያለበት ብቻ ሣይሆን የማስተማሪያ ማኗል ሆኖ ሊያገለግል የሚገባ ጽሁፍ !!
((Written by Bedilu wakijira (DR) ))
.
" የብሄር ብሄረሰብ ምሽግ ፈርሶ፣ ግልጽ አደባባይ ይገንባ !! "
.
ሀገራዊ የስነምግባር ዝቅጠት፣ ሥርዓተ አልበኝነት፣ የፍትህ ተቋማት አቅመ ቢስነት ??
.
ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተፈፀመ ያለውን ግፍ፣ በምንኖርበት የ21ኛው ክፍለ ዘመን
ስልጣኔ ታሪክ ውስጥ የሚፃፍበት ገጽ ከማይገኝላቸው ጥቂት እንስሳዊ ተግባራት አንዱ
ነው፡፡ በሊባኖስ ለስልጣንና ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ የበላይነት፣ እናቶችና ህፃናት ሳይቀሩ
በህንፃ ፍርስራሽ ውስጥ ከእነ ህይወታቸው ይቀበራሉ፡፡ በናይናማራ ሙስሊሞች
እርቃናቸውን እንደ ድንጋይ ተነጥፈው ተሽከርካሪ ይነዳባቸዋል፤ አካላቸው ይቆራረጣል፤
በረሀብ ይቀጣሉ፡፡ በኢትዮጵያ ዜጎች ከመንገድ ተይዘው ይቃጠላሉ፤ ተዘቅዝቀው
ይሰቀላሉ፤ ኮበሌዎች በቢላ ይቆራረጣሉ፤ ሚሊየኖች ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ
ከኖሩበት አካባቢ፣ ንብረታቸው እየተዘረፈ፣ ቤታቸው እየተቃጠለ፣ አካላቸው እየጎደለ
ይሰደዳሉ፡፡
የኢትዮጵያውያን ግፍና ኢ-ሰብአዊ ተግባር ከሌሎች በዓለማችን ከሚደረጉት ተመሳሳይ
ድርጊቶች የሚለየው ሀገራቱ በአምባገነን መሪዎች የሚመሩና መሪዎቻቸው የድርጊቱ
አስፈፃሚዎች ወይም ተባባሪዎች መሆናቸው ነው፡፡ ኢትዮጵያ ስለ ፍቅርና መደመር
የሚዘምር፣ ስለ ዲሞክራሲና ፍትህ መከበር ሙሉ ጊዜውን የሚሰራ፣ ሀገሪቱን
ከተዘፈቀችበት የጥፋት መቀመቅ ለማውጣት ቆርጦ የተነሳ መሪ ያላት፣ ግን ደግሞ ያለ
መሪ ብቻ ሳይሆን፣ ያለ ህሊና በደመነፍስ ብቻ በዱር የሚኖሩ እንስሶች በዝርያዎቻቸው
ላይ የማይፈጽሙት በደል የሚፈጸምባት ሀገር እየሆነች ነው፡፡
.
ይህቺ በሁለት እግር የሚራመዱ ፍጡራን፣ ከእንስሳዊ ደመነፍስ ሚዛን የወረደ ግፍና
ጭካኔ የሚፈጽሙባት ኢትዮጵያ፣ ያለፈው ግማሽ ምእተዓመት የደርግ አምባገነንነትና
የኢህአዴግ የጎሳ ፖለቲካ ውጤት ናት፡፡ እነዚህ ሁለት አምባገነን መንግስታት ገድለው
ይጥሉ – አስረው ያሰቃዩ ነበር። ህዝቡ ደግሞ ሲደፍር ያምጻል፤ ሲፈራ ተደብቆ
ያለቅሳል፡፡ በተለይ የሃያ ሰባት ዓመት የኢህአዴግ አምባገነን አገዛዝ፣ ኢትዮጵያውያንን
በጎሳ ሸንሽኖ ተፋቅረው እንዳይኖሩ፣ በጥላቻ የክልል ዋሻ ውስጥ ከትቷቸዋል፡፡ ኢህአዴግ
የደርግን አምባገነን መሪ በጣለበት ጠመንጃ፣ እኩልነትን፣ የፍትህ ተቋማትን፣
ተጠያቂነትን፣ ሰብአዊነትን፣ ሀይማኖታዊ ስነምግባርን፣ . . . ሀያ ሰባት ዓመት ጨፍጭፎ፣
በዘመኑ የተወለዱ ወጣቶችን፣ የጎሰኝነት መርዝ ፕሮፓጋንዳ እየጋተ ይህቺን ኢትዮጵያ
ፈጥሯል፡፡
.
ጎረቤቱ፣ አብሮ አደጉ ላይ እሳት የሚጭሩ ወጣትና እሳቱን የሚሞቅ ጎልማሳ ተፈጠረ፤
ዜጋን ዘቅዝቆ በአደባባይ የሚሰቅል፣ ሰቅሎ የሚፎክር ወጣት ተፈጠረ፡፡ ‹‹አትገድሉም››
ሳይሆን፣ ‹‹ሬሳውን በመኪና አትጎትቱም›› ብሎ የሚተኩስ ፖሊስ ተፈጠረ፡፡ ‹‹ብሔር-
ብሔረሰብ›› የተባለው ምሽግ ተፈጠረ። ይህ ምሽግ ጥይት አይበሳውም፤ ኒውክለር
አይደረምሰውም፡፡ የፍትህ ጨረር አይደርስበትም፤ ሰብአዊና ሀይማኖታዊ ስነምግባር
አያናውጠውም። የብሔር-ብሔረሰብ ምሽግ፣ ጥቂቶች ቢሆኑ እንኳ በስሙ ለሚፈጽሙት
ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ከለላ ይሆናቸዋል፡፡
.
በቤኒሻንጉል አንድ የ14 ዓመት ልጅ፣ ብልቱ ተቆርጦ፣ ተመትሮ ተገኘ፡፡ መንግስት
አሳከመው እንጂ አራጆቹን ለፍትህ አላቀረበም፤ ምክንያቱም ገዳይና ሟች ሰዎች
አይደሉም፤ ብሄር ብሔረሰብ ናቸው። ከሱማሌ ኦሮሞዎች ተፈናቀሉ፤ በአዋሳ ወጣቶች –
ወጣቶችን በእሳት አነደዱ፤ ጂጂጋ ሱቆች ተቃጠሉ፤ ቤተ ክርስቲያን ከእነ አገልጋዮቿ
ተቃጠለች፤ አዳማ . . . ሀረርጌ ፤ ሁሉም የተደረጉት በሰዎች አይደለም፤ ያጠቁትም
የተጠቁትም – ሁሉም ሰዎች አይደሉም፤ ብሔር ብሔረሰቦች ናቸው፡፡ በዛሬዋ ኢትዮጵያ
ብሄር ብሄረሰብ ከሆንክ፣ ህግ አይሰራም፤ ዳኝነት የለም። ዋናው ብሔር ብሔረሰብ መሆን
ነው። ብሔር ብሔረሰብ ስትሆን ቀድመህ ከገደልክ፣ ከዘረፍክና ካቃጠልክ፣ የብሄር
ብሄረሰብ ምሽግህ ከህግ ይከልልሀል፤ ከተቀደምክና ከተገደልክ፣ ከተዘረፍክ፣
ከተቃጠልክ መንግስት ሁኔታውን ያጠናልሀል፡፡
ኢትዮጵያ ከሶስት ወራት በፊት በአምባገነኑ የኢህአዴግ የአልሞትም መንፈራገጥ ወቅት
የነበረችበት አስፈሪ ሁኔታ፣ ዛሬ ካለችበት የተሻለ ነበር፡፡ ያኔ አምባገነኖችን ከስልጣን
ለመጣል፣ ያመፀ ህዝብ በአንድ በኩል፣ ስልጣንን የሙጥኝ ያለ፣ ህግን ለስልጣኑ
ማራዘሚያ በጭካኔ የሚጠቀም አምባገነን መንግስት በሌላ በኩል ተሰልፈው ነበር፡፡ ዛሬ
ህዝባዊው አመጽ፣ አውሬያዊ ጭካኔ በተሞሉ ቡድኖች ተተክቷል፤ አምባገነኑን መሪ
የተካው አዲሱ መሪ ደግሞ ህገ መንግስታዊ ጥርሱን፣ እንደ መቶ ዓመት ሽማግሌ፣ ሰው
ሰራሽ ጥርስ አውልቆ፣ ስልጣኔና እውቀት ያልገራውን፣ በጎሰኝነት አቅሉን የሳተ አውሬ
ሊማርክ ይታገላል። ይህ ሊሆን አይችልም፡፡ መንግስት የህግ ጥርሱን ማሳየት አለበት፤
ያለዚያ እንፈርሳለን፡፡
.
ቄሮ፣ ፋኖ፣ ዘርማ . . . በደልና የዲሞክራሲ እጦት የወለዳቸው ህዝባዊ አመጾች እንጂ
ቡድናዊ ነውጦች (ሞብ) አይደሉም፡፡ አንባገነንነትን ያንበረከኩትና ፍቅርና መደመርም
ያመጡት፣ የህዝብን ጥያቄ ይዘው በየመንገዱ እየተሰዉ፣ በየእስር ቤቱ እየተሰቃዩ እንጂ፣
ዜጎችን እያቃጠሉና እየሰቀሉ አይደለም፡፡ ቄሮ በጠራው ሰላማዊ የቤት መቀመጥ
አመጽና የመንገድ መዝጋት ነው አምባገነንነትን ድል ያደረገው፤ የተኛበት በግፍ ተገድሏል፤
ለዚያ እንኳን በበቀል ስሜት አልገደለም – አላቃጠለም – አልሰቀለም፡፡ ታዲያ የትግሉን
– የመስዋእትነቱ የመጀመሪያ ፍሬ – ‹‹የቲም ለማን›› የፍቅርና የመደመር መንገድ ላይ
የቆመ ቄሮ – ፋኖ – ዘርማ – እንዴት በእድሜያችን ያላየነውን ጭካኔ ይፈጽማል!?
አይፈጽምም፤ አልፈጸመምም ፡፡ ወንድሙ ለፍትህና ዲሞክራሲ መስዋእት ሆኖ ከጎኑ
ሲወድቅ በቁጭት እየቀበረ ለድል የበቃ ወጣት፣ ወንድሙን ዘቅዝቆ ሊሰቅል – በእሳት
ለኩሶ ሊያቃጥል አይችልም፤ ይህን ካደረገ ደግሞ ወንድሙ የተሰዋለትን፣ እሱ
የታገለለትን አላማ አያውቅም ማለት ነው፤ ድርጊቱ እየተፈጸመ ያለው የእነሱን ህዝባዊነት
እንደ በግ ለምድ ባጠለቁ፣ አውሬያዊ ስብእና ያላቸው ግለሰቦች ባደራጁት ነውጥ (ሞብ)
ነው፡፡ የምናያቸው ችግሮች እየተፈጸሙ ያሉት በቄሮ፣ ፋኖና ዘርማ . . . አይደለም ፤
እነዚህ የህዝባዊው አመጽ ጠንካራ ክንዶች ናቸው፡፡
.
አሁን ሀገራችን የምትገኝበት ፖለቲካዊ ሁኔታ ለህዝባዊ አመጽ የሚጋብዙ ምቹ ሁኔታዎች
የሉም፤ በአንጻሩ ደግሞ ለነውጥ (ሞብ) ሁሉም ተሟልተው የሚገኙበት፣ እጅግ ምቹ
ሁኔታ አለ። አብዛኛው ማህበረሰብ አሁን ባለው የ‹‹ቲም ለማ›› የተሀድሶና የለውጥ
አመራር ደስተኛ ነው፤ ይህ በየድጋፍ ሰልፉ ታይቷል፤ ባለፈው ግማሽ ምእተአመት፣ ይህን
ያህል ህዝባዊ ተቀባይነት ያለው መሪ አልታየም፡፡ በመሆኑም አሁን የሚታየው ነውጥ፣
ህዝባዊ አመጽ ተደርጎ ሊወሰድ አይችልም፡፡ አሁን ሀገራችን የምትገኝበት ሁኔታ ቀጥሎ
በተዘረዘሩት ሶስት ዋና ዋና ምክንያቶች (ቢያንስ በእኔ ማሰላሰል ነው፤ ሌሎችም ሊኖሩ
ይችላሉ) የተነሳ ለቡድን ነውጥ ምቹ ነው፡፡
.
የፍትህ ተቋማት አቅመ ቢስነት፤ የኢትዮጵያ የፍትህ ተቋማት፣ በተለይ ፖሊስና ፍርድ ቤት
ባለፉት 27 አመታት በደረሰባቸው ጠንካራ የኢህአዴግ አሉታዊ ተጽእኖ የተነሳ፣ አሁን
ሙሉ ለሙሉ ‹‹የሉም›› ከሚባልበት ደረጃ ደርሰዋል። የሲቪክ ማህበራት በነጻነት
እንዳይሰሩ ተደርጓል። ፖሊስም ሆነ ፍርድ ቤቶች የመንግስት ስልጣንና ጥቅም
ማስጠበቂያ መሳሪያዎች በመሆናቸው፣ የመንግስት ባለስልጣና
ት ፣ ካድሬዎች፣
የባለስልጣናት ዘመዶች ካልሆኑ በቀር፣ ዜጎች ‹‹ፖሊስ ይጠብቀናል፣ ፍርድ ቤት ፍትህ
ያስጠብቅልናል›› ብለው አይተማመኑም ። ላለመሰረቅ ሌባን በፖሊስ ማስያዝ ሳይሆን፣
ሌባን ጓደኛ ማድረግን፣ መበደልንና ግፍን በፍርድ ቤቶች ከመዋጋት ይልቅ ተለማምጦና
ተሽቆጥቁጦ መኖርን መርጧል። ማህበረሰቡ የፍትህ ተቋማት እንደማይጠብቁት፣
ነውጠኛውም፤ ተቋማቱ መንግስትን እንጂ ህዝብን እንደማይከላከሉ ያውቃል፡፡ በመሆኑም
ፖሊስ ከእነ ትጥቁ በቆመበት ዜጎች አሰቃቂ ጥቃት ይደርስባቸዋል ። ይህ የፍትህ
ተቋማት አለመኖር፣ በየሰዉ ነፍስ ያለው የአውሬነት ባህርይ ያለ ልጓም እንዲፈነጭና
ከሰብአዊነት እንዲርቅ አድርጎታል፡፡
.
የብሄርብሄረስብ ምሽግ፤ በደርግ ዘመን፣ (እንደ ዘመነ ኢህአዴግ በሰፋና በተንሰራፋ
መጠን ባይሆንም) ኢሰፓአኮና ኢሰፓ የግፈኞች ምሽግ ነበሩ፡፡ ይሁን እንጂ እንደ
ኢህአዴግ የብሄር ብሄረሰቦች ‹‹ምሽግ›› ከፍትሀዊ ተጠያቂነት የሚያስጥል ምሽግ
የለም። በዘመነ ደርግ በኢሰፓአኮና ኢሰፓ ምሽግ ውስጥ ተጠልለው ከፍትህ ለማምለጥ
የሚችሉት ጥቂት የፓርቲው አባላትና የአብዮቱ ልጆች ብቻ ነበሩ፡፡ የኢህአዴጉ የብሄር
ብሄረሰብ ምሽግ ግን፣ ግፈኝነትን፣ ህገወጥነትንና ኢ-ሰብአዊነትን ያልተጸየፈ ዜጋ ሁሉ
ይጠለልበታል። የደርግ ምሽግ ለራሱ ለደርግ መጠለያ የተሰራ ሲሆን፣ የኢህአዴግ ምሽግ
ግን ለሌሎች – ግፈኝነትን፣ ህገ-ወጥነትንና ኢ-ሰብአዊነትን ላልተጸየፉ ዜጎች የተሰራ
ነው፡፡ ኢህአዴግ ምሽግ አያስፈልገውም፤ የፍትህ ተቋማቱ ይጠብቁታል፡፡ ምሽጉ
የተሰራው ዜጎች በስማቸው በተሰራላቸው ምሽግ ገብተው እንዲታኮሱበት ነው፡፡
.
የኢትዮጵያ ህዝቦች ከደርግ ቀድመው በነበሩት ስርአቶች በማንነታቸው ሲያፍሩና
ሲሸማቀቁ መኖራቸው ስላንገበገባቸው ፤ በ1983 ኢህአዴግ የብሄር ብሄረሰቦችን
እኩልነት ሲያውጅ እያንዳንዱ ብሄረሰብ በየአደባባዩ ወጣ፡፡ ቀስ በቀስ . . ከ27 አመታት
በኋላ . . . ዛሬ ያ አደባባይ የግፈኞች መሸሸጊያ ምሽግ ሆነ፡፡ ኢህአዴግ የብሄረሰቦችን
መብትና ነጻነት፣ የክልሎችን እድገት ፍትሀዊ በሆነ መንገድ ማደላደል እንዴት ይቻላል?
የሚለው ጥያቄ ላይ ሳይሆን፣ ‹‹የብሄር ብሄረሰቦችን ፖለቲካ እንዴት አድርጌ በስልጣን
ላይ እቆይበታለሁ?›› የሚለው ጥያቄ ላይ አተኩሮ በመስራቱ፣ ለተቃወሙት ጋት፣ ለደገፉት
በክንድ እየሰጠ፣ ያንን የብሄር ብሄረሰቦች የእኩልነት አደባባይ፣ የግፈኛ ነውጠኞች ምሽግ
አደረገው፡፡ እዚህ ላይ ከአስር አመታት በፊት ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በሀላፊነት ላይ ስሰራ
ያጋጠመኝን አንድ ገጠመኝ ልግለጽ፤ ነጥቤን ያጎላልኛል፡፡
አንድ የዩኒቨርሲቲው ተማሪ፣ የተማሪዎች ሻይ ቤት የምትሰራ ወጣትን በአይኑ አፈቀራትና
ቀርቦ ጠየቃት። ‹‹እኔ አልወድህም›› አለችው፤ ፍቅሩ ባሰበት፤ ደግሞ ጠየቃት፡፡ ‹‹እምቢ››
ብላ ድርቅ አለች፡፡ አንድ ቀን ማታ ካፊቴሪያ ድረስ ሄዶ ደበደባት፡፡ ‹‹ወንጀል ፈጽመሀል፤
ደንብ ጥሰሀል›› ተብሎ፣ በግቢው ፖሊሶች ሲያዝ፣ ዘሎ የብሄር ብሄረሰብ ምሽጉ ውስጥ
ገባ፡፡ ‹‹በብሄረሰቤ ጠርታ አንቋሻ ሰድባኛለች፤ እኔስ እሺ ብሄር ብሄረሰቤ ምን በወጣው
አለ››፡፡ ፖሊሶች ከምሽጉ በር ተመለሱ፤ የተማሪው ብሄረሰብ አባል የሆኑ ተማሪዎች
ግቢው አልበቃቸው አለ፡፡ በተፈጠረው ረብሻ ተማሪዎች በጩቤ ቆሰሉ፤ ትምህርት
ለሳምንታት ቆመ። ዩኒቨርሲቲው በዚህ ረብሻ የተሳተፉና የተለያዩ ብረታብረቶችና
ጩቤዎች የተገኘባቸውን ተማሪዎችን ለዲስፕሊን ኮሚቴ አቅርቦ፣ በደንቡ መሰረት ለአንድ
አመት ከትምህርታቸው አገዳቸው፤ ይህንን የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ካጸደቀው በኋላ፣ የክልሉ
አስተዳደር፣ በዩኒቨርሲቲው ቦርድ ውስጥ ባስቀመጠው ሰው አማካይነት፣ ውሳኔው
ተግባራዊ እንዳይሆን አገደ፡፡ የቀረበው ምክንያት፣ ‹‹ከሁለቱ በስተቀር ወደ 29 የሚጠጉት
የአንድ ብሄረሰብ አባል በመሆናቸው፣ በብሄረሰቡ ላይ የተወሰደ ጥቃት ይመስላል››
የሚል ነበር፡፡ ያ ተንኮለኛ አፍቃሪ የተሸሸገበትን የብሄር ምሽግ፣ የክልሉ መንግስት
አጠናከረው፡፡ እና በዛሬዋ ኢትዮጵያ፤ ብቻህንም ሰራህ በቡድን ተደራጅተህ፣ የብሄር
ብሄረሰብ ምሽግህ ውስጥ ከገባህ ጠያቂ የለብህም፡፡
.
ሀገራዊ የስነምግባር ዝቅጠት፤ የእሳት ዳር ተረት እንደ ስነምግባር ማስተማሪያነት ጊዜው
አልፎበታል፤ የስነዜጋ ትምህርቱ እንጨት እንጨት የሚሉ የልማታዊ ፕሮፖጋንዳ
ታጭቆባቸዋል፤ ቲቪው የሚንቀሳቀስ ቶምና ጄሪ፣ ራዲዮው የሚናገር ቶምና ጄሪ፣ የህጻናት
መጻህፍቱ የሚነበብ ቶምና ጄሪ! . . . ልጆቻችን በየት በኩል ስነምግባር ይማራሉ!
ትምህርት ቤቶች ክፍል የሚቆጠርባቸው፣ ዩኒቨርሲቲዎች ዲግሪ የሚሰጥባቸው ቦታዎች
ሆነዋል። ሀገራችን ታታሪዎች ሳይሆኑ እራስ ወዳዶች፣ ሙሰኞች ተከብረው የሚኖሩባት
ሀገር ሆናለች። በደርግ ዘመን ፊናንስ ፖሊስ የሚባል ነበር፤ ኬላ ጠባቂ፣ ኮንትሮባንድ
ነጣቂ ፖሊስ፡፡ ደሞዛቸው 100 ብር አይዘልም ነበር፡፡ ግን እዚያ ለመቀጠር የነበረው
መዋደቅ አይጣል ነበር፤ ‹‹ለምን?›› ቢባል፣ ገንዘብ ተቀብለህ ታሳልፋለህ፤ የያዝከውን
ኮንትሮባንድ ለራህ ትወስዳለህ፡፡ ዛሬ ከ40 አመት በኋላ፣ የክልል ፕሬዚዳንቶችና የጦር
መሪዎች ናቸው ይህን ስራ የሚሰሩት፡፡ የኮርፖሬሽን ሀላፊ ሆኖ፣ ኮርፖሬሽኑን አክስሮ ያዘጋ
ሚኒስትር ይሆናል፤ ሚኒስትርነቱ ሲያቅተው ትንሽ ዘርፎ አምባሳደር ወይም የጠቅላይ
ሚኒስትር አማካሪ ይሆናል፡፡ ልጆቻችን በተረቱና በትምህርቱ ያጡትን፣ በየመስሪያ ቤቱ፣
በመንግስት መዋቅር አሰራር . . . ከህይወት ለመማር እንኳን እድል የላቸውም፡፡ እና
መንግስት እየሰረቀ አትስረቁ ይላል፤ ዜጎችን እየገደለ፣ በየእስር ቤቱ እያሰቃየ ተከባበሩ –
ተፋቀሩ ይላል፡፡ እያሸበረ አታሸብሩ ይላል፡፡ ማን ይሰማዋል?! ስርአተ አልበኝነት ነገሰ፡፡
ምን ይደረግ!
.
የመጀመሪያው አጣዳፊ ተግባር መንግስት ላይ ይወድቃል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
እጅግ በፍጥነት የፍትህ ተቋማትን በአዲስ መልክ አደራጅተው፣ ማህበረሰቡን ባሳተፈ
ቁርጠኝነት ተግባራቸውን እንዲያከናውኑ ማድረግ አለባቸው፡፡ ኢህአዴግ የገነባው የብሄር
ብሄረሰብ ምሽግ ፈርሶ፣ ግልጽ አደባባይ መሰራት አለበት፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ
የሚያስፈልገው አንዱ ብሄረሰብ ሌላውን በድሎ የሚደበቅበት ምሽግ ሳይሆን፣ አንዱ
ከሌላው ተቃቅፎ የሚታይበት- የሚኖርበት አደባባይ ነው። የአንድ ብሄረሰብ መብት
የሚከበረው፣ ልማቱ የሚደራጅለት እሱ በብሄር ተደራጅቶ፣ ‹‹መብቴ ይከበር›› ብሎ ሲነሳ
ሳይሆን፣ የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች በሙሉ፣ ‹‹መብቱ ይከበር›› ብለው ሲነሱ ብቻ ነው፤
ሁሉም ለአንዱ – አንዱ ለሁሉም ሊነሳ ይገባል፡፡
.
አገራዊ የስነምግባር ዝቅጠት በአጭር ጊዜ የሚቀረፍ ችግር አይደለም፤ ፍንጩን ለማየት
እንኳን ቢያንስ የአንድ ትውልድ ግማሽ እድሜ ይፈልጋል፡፡ ይህ ችግር በአብዛኛው
ከቤተሰብ ባህልና ከትምህርት ስርአት ጋር የተያያዘ በመሆኑ ረዥምና ተከታታይ፣ በእውቀት
ላይ የተመሰረተ ስራ ይፈልጋል፡፡ የብዙኃን መገናኛም በቤተሰብና በማህበረሰብ ባህልና
አስተሳሰብ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ስለሚያደርግ፣ በዘርፉ መሰረታዊ ለውጥ መደረግ
አለበት፡፡
በአጠቃላይ አሁን ያለውን ቀውስ ለመግታት መንግስት ሀላፊነትንና ተጠያቂነትን በብሄር
ብሄረሰብ ላይ ሳይሆን፣ በዜጎች – እንደ አንድ ሰብአዊ ፍጡር የሚያደላድል ስርአት
መገንባት አለበት፡፡ ለዚያ ግን ቀዳሚው የእያንዳንዱን ዜጋ ሀላፊነትና ተጠያቂነት
የሚያረጋግጡ ተቋማትን ማደራጀት ነው፡፡ ይህ ሲሆን እንደ ግለሰብ ሀላፊነታቸውን
የሚያውቁና የሚወጡ ዜጎች ልንቀርጽ እንችላለን። ሀላፊነቱን የሚያውቅና የሚወ

ግለሰብ ስናፈራ ብቻ ነው እንደ ማህበረሰብ መኖር መቀጠል የምንችለው፡፡
.
ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ትዝብት
ተከታታይ በየሀ የተማሪዎች ህብረት የሚቀርብ ህንፃዎቻችን ላይ የሚያተኩር ተከታታይ ፅሁፍ ነው፡፡

የታዘብነውንእንተርካለን፡፡
የታዘባችሁትን አድርሱን፡፡

በቅርብ ቀን!!!

@wegoch
@wegoch
Forwarded from Mykey (「Mikiyas Liyew Taddese)
ሰበር ዜና
(በላይ በቀለ ወያ)😂
።።።።
ሽሮ ሜዳ ተኩስ በተኩስ ሆናለች፡፡ ፖሊሶችም ወደ ኪዳነምህረት
የሚወስደውን መንገድ ተሸከርካሪዎች እንዳይገቡ አግደዋል፡፡
ተኩሱ የተጧጧፈበት ዋና ምክንያት ነገ ለሚከበረው የኪዳነ
ምህረት በአል የባህል ልብሶችን ፈጥኖ ለማድረስ እንደሆነ
ተገልፅዋል፡፡ መልካም በአል፡፡ለነገውም ለዛሬውም!!!

@lula_al_greeko
@wegoch
@wegoch
2024/09/30 11:39:16
Back to Top
HTML Embed Code: