Telegram Web Link
Finally 🙏
ፈጣሪ ታላቅ ነው።
አዕጋረ ፀሓይ ዛሬ ሕትመቷን ጨርሳ ለስርጭት ጃዕፋር መፅሀፍት ተልካለች። በቅርቡም በመላው አዲስ አበባ እና ክልል ከተሞች ትዘልቃለች።
በሂደቱ ሁሉ ከጎናችን ለነበራችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው።
መልካም ንባብ

ደራሲ ሚካኤል አስጨናቂ
1892 ላይ ስታንፎርድ ዩንቨርስቲ ይማር የነበረ የ18 አመት ወጣት ለትምህረቱ የሚከፍለው ገንዘብ ይቸገራል። ገንዘብ የሚጠይቀው ሰውም አልነበረውም። በዚህ ሃሳብ እያለ ከጓደኛውጋ ይማከራል ... 'ለምን የሙዚቃ ኮንሰርት አዘጋጅተን ገንዘብ አንሰበስብም?'

ሁለቱ ወጣቶች ወደ አንድ Ignacy J.Paderewski የሚባል ታዋቂ ፒያኒስትጋ ይሄዱና ማናጀሩን ያገኛሉ። ማናጀሩም $2000 ክፈሉና እንደፈቀዳችሁ አላቸው። ወጣቶቹ ሙዚቃቸውን እያጠኑ እና እየተለማመዱ ለሙዚቃ ፕሮግራማቸው ይዘጋጁ ጀመረ

ያ የተባለው ሙዚቃቸውን የሚያቀርቡበት ቀን ደረሰ። ብዙ ትኬት ስላልተሸጠ ባጠቃላይ ያገኙት ገቢ 1600 ዶላር ብቻ ሆነ። ያቺን ያገኟትን ገንዘብ ይዘው ወደ Paderewski ይሄዱና እንዳሰብነው አልሆነልንም። ስለዚህ የምንመልስልህ ያገኘነውን ሙሉ 1600 እና ወደፊት ልታወጣው የምትችለው የአራትመቶ ዶላር ደረቅ ቼክ ነው ይቅርታ አሉት።

ሰውየው ግን ጭራሽ ተቆጥቶ ቼኩን ቀደደ እና ገንዘቡን አልቀበልም አላቸው። ይህ ገንዘብ ለአንዳንድ ወጪ ያወጣችሁትን ይሸፍንላችኋል። የቀረውን ለራሳችሁ ተጠቀሙት አላቸው።

ወጣቶቹ ተደንቀው አመስግነውት ወጡ። ስለተደረገላቸው መልካምነት እጅግ ተደሰቱ።

የማያውቃቸውን ሰዎች ለምን በዚህ መጠን ሊረዳቸው ፈለገ? ከእነሱ ምንንም ሳይጠብቅ ለምን ይሄንን ቸርነት አደረገላቸው? አንዳንዶቻችን "ይህንን ሰው በዚህ በተቸገረው ነገር ብረዳው ለኔ ምን እጠቀማለሁ?" ብለን እናስባለን። አንዳንድ ብሩህ ልብ ያላቸው ደሞ "ይህንን ሰው በዚህ በተቸገረበት ሰአት የአቅሜን ባልረዳው ምን ይሆናል?" ብለው ስለ እዛ ሰው ያስባሉ

ከጊዜያት በኋላ ይህ ፒያኒስት የ ፖላንድ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነ። የተወደደ ገዢ ሆኖ በሚመራበት ዘመኑ የአለም ጦርነት ተጀመረ እና 1.5 ሚሊየን ፖላንዳውያን ተራቡ። እሱም እርዱኝ ብሎ አለማትን መለመን ጀመረ።

ወደ አሜሪካን መልዕክት ላከ። በሰአቱ የአሜሪካ ፕሬዚደንት የነበሩት Herbert Hoover ወዲያው እርዳታ አደረጉለት። በዚህም የፖላንዱ ጠቅላይ ሚንስትር ተደስቶ ይህንን ሰው በአካል ያለበት ሄጄ አመሰግነዋለሁ ብሎ አሜሪካ መጥቶ እጅ ነሳ። 'ለህዝቤ እና ለእኔ ላደረግህልን በጎነት አመሰግናለሁ' አለ የፖላንዱ ጠቅላይ ሚንስትር።

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ግን 'ለምን ታመሰግነኛለህ?' አለው

'ከብዙ አመታት በፊት ሁለት ተማሪዎችን ለትምህርት የሚከፍሉት ሲቸገሩ በጎ ፈቃድ ያደረግህላቸው ትዝ አለህ? አንዱ ወጣት እኔ ነበርኩ'

By Mastewal Aseffa

@wegoch
@wegoch
@paappii
Forwarded from ሥዕል ብቻ © (Leul M.)
Exhibition titled, “መልክ”
By Surafel Alemneh

Artawi Gallery
opened for public.

The galley opened  until 20 July 2024 starting from 2 PM - 6 PM bole, around British international school or 250m in from Yod Abyssinia, Kkare Homes, 2nd Floor


@seiloch
መናፍስት አማረኛ አወራ ?
                          በግዕዝ ሙላት

ሰማዬ ጋር የክዋክብት መብራት የአራስ ህፃን አይን መስለው ቡዝዝ ብለው በየፈርጡ ተኮልኩለዋል ። ጨለማው ከሰማዬ ብርሃን ገዝፎ መጠነኛ ንፋስ የግቢውን ዛፎች ያስደንሳቸዋል !ቅጠሎች ደሞ ሰክረዋል መሰል እዬተንገደገዱ ይወድቃሉ (የንፋሱን ውስኪ ገልብጠው)።

እዬለፈለፍኩ ነው? ግን እያወራሁ አይደለም? የተፈጥሮ የድምፅ ፀጥታ ከራሴ ጋር ሊያመካክረኝ ዝግ ስብሰባ ይዟል። ቆይ... ቆይ... ቆይ...ሲጀምር... ለምንድነው? ከራሴ ጋር ምማከረው?... እንደዛ ሲባልስ... ደባል ስዕብና በውስጤ አለ ወይስ የለም  ? ሲጀምርስ ምክክርን ከዚህ ምን አመጣው ? ብሽቅ!(አለ ያነኛው )

አንዳንዴ በቀን ኑሮ ውስጥ ያሉ ትዕይንቶች ለስዕብናችን የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ(political speech ሆነ መሰል ?😏ለምን የድመቱን ድርሻ አይወስዱም ምን አገባኝ? አይጥ!) (አለ ይሄኛው)

ሲጀምርስ ፖለቲካን እዚህ ምን አመጣው? አያችሁ ይሄ ነው ስዕብና ማለት ዝም ብሎ መዘባረቅ። ስዕብና ፀንቶ የሚኖር ሀውልት አይደለም! በሁኔታው ሁሉ ይቀያየራል። ለዛም ይመስለኛል ህፃን ልጅ ልጅ ሳለ ንፁህ ይሆንና የኋለኛው ማንነቱ በአረመኔነት የሚቀዬረው ።
(በሚያዬው ትዕይንት እና ገቢር መጠን...ስል ገና)
" እና እኛ ምን አገባን?' ቅማላም' ቁጭ በል" አለኝ ያነኛው(የትኛው?)

<እኔ>
ሰአቱ ስንት እንደሆነ አላቅም.. እርግጥ ነው መብራት ስለጠፋ (መጀመሪያውንም ስለሌለ)  ብቻ ስልኬም ባትሪው ዘግቷል ።ይመስለኛል ይሄን የተፈጥሮ ፀጥታ  እንዳዳምጥ ያደረገኝ ሰው የፈጠራቸው ነገሮች በቴክኒካል ችግር መደበቃቸውን ነው(ባትሪ መዝጋቱን ማለቴ ነው)።የሚገርመው ግን ተፈጥሮ የምትባለው ሴት ግን (ሁሉንም ከሴት እናገናኜዋለን!) ቴክኒካል ችግር የለባትም! አሁን አሁን የአዬር ብክለት ሚባለው ነገር ትልልቅ ትሪሊዮነሮችን ባለሀብት በገነቡት እንዱስትሪ በሚለቀቀው ጋዝ ተበከለና መልሰው በበከሉት አዬር ያገኙትን ትርፍ መልሰው የአዬር ብክለትን ለማስተካከል ይደክሙበታል።...ቆሻሻ አለ ጋሽነት። (ጋሽነት የሰፈራችን ሰው ነው ልጁ በጣም አስቸጋሪ ስለሆነ ልጁ ጋር ያለውን ፍቅር ለመግለፅ የሚጠቀምባት ቃል ናት!ቆሻሻ አለ ጋሽነት( አለ ተኝቶ የነበረው እኔ?)

<ያነኛው እኔ>
በቃ ሰው እንዲህ ነው ዝም ብሎ መባከን መባከን መባከን(አልጨረሰም ገና) ..."አንተ ልጅ ተመለስ ተው" አለ የሆነ ድምፅ ከጨለማው መሃል' እማዬ ድረሽልኝ' ምንድነው የሰማሁት(በአካል የሚታዬው አፌተናገረ)...መናፍስት ?... አይ አይ መናፍስት አማረኛ አይችሉም! ...እና ማነው ያወራው?...ፀጥ አልኩ ሁሉም ነገር ፀጥ አለ ድጋሚ..."ለምን ዝም አልክ" አለ ያ ድምፅ...'ኧረ ደገመው' አልኩና ጆሮዬን የት ጋር ድምፁ እንደመጣ አጣራው ከውስጥህ ነኝ ያለሁት አለኝ የሆነ ድምፅ!.. ግን የሆድ ድምፅ ይመስላል (እ? እንዴት ራሴው አውርቼ ራሴው ፈራሁ አንዳንዴ ከሰውነታችን የሚወጡ ትርጉም የለሽ ድምፆች የሆነ ቅፅፈት ትርጉም ይኖራቸዋል ልክ እንደዚሁ ) በድጋሚ የሚናገረው ድምፅ ተሰማኝ የራሴው ስዕብና ነው ላምን አልቻልኩም "ኧረ ቤስሚያም"አሉ አባ ጎርብጥ

<ወዲህኛው እኔ>
ነግሬቹሃለሁ ሁላችንም በሁኔታዎች የሚቀያዬር ስዕብና ነው ያለን..."መጣሁልህ አንተ ፈሳም" አለኝ ሌላ ድምፅ ከዛፉ ስር "እማዬ ድረሽ መናፍስት አማረኛ አወራ?"....እዬሮጥኩ ወደ ቤቴ....

@geez_mulat

@wegoch
@wegoch
@wegoch
..."አባዬ" (ልጅ)

..."አቤት" (አባት)

..."በግ አስተኝተን፡ አርደን፡ ደሙን አፍሥሰን፡ በጥብስ እና በቅቅል አርገን ስንበላው ነፍሱን በማጥፋታችን ሀጥያት አይሆንብንም?"(ልጅ)

..."ምን ስትል አሰብከው ልጄ? እረ አይሆንብንም።" (አባት)

..."እንዴ አባዬ እየገደልን አደለ እንዴ፡ እንዴት ሀጥያት አይሆንብንም?" (ልጅ)

..."ምን መሰለህ ልጄ... እንዴት ላስረዳህ?... ሞት እኮ በር እንጂ መጨረሻ አይደለም፡ በጉን ስንበላው በኛ ውስጥ መኖሩ ይቀጥላል እንጂ ጨርሶ አይሞትም" (አባት)

..."እረ እረ አባዬ ደሞ እንደዚ አለ እንዴ?" (ልጅ)

...."አዎ! እውነት ስልህ ፥ ያው የበላነው ተስማምቶን ሀይል እና ጉልበት አግኝተን፡ አካላዊ እድገት እያመጣን አይደል የምንኖረው ፡ ያ ታድያ እኮ በኛ ኖረ ማለት ነው ልጄ" (አባት)

..."እሺ እና ጋሽ ጀንበሬ እንደውም ባለፈው በለሊት ወደስራ ሲሄዱ ጅብ የበላቸው ጅብ ሆነው እየኖሩ ነው ማለት ነው አባዬ?" (ልጅ)

..."ወይ ጉድ ዛሬ እንደው ምን ጉድ ውስጥ ነው የገባሁት...ማነሽ 'አልማዝ ነይ እስኪ ይሄን ልጅ ወደዛ ወስደሽ ገላግይኝ'...አልሞት አልኩህ?" (አባት)

..."ምን አልክ አባዬ?" (ልጅ)

..."ምንም ወዲህ ነው የእራት ሰዓት ደርሷል እናትህን ወስደሽ አብይው እያልኳት ነው....'አንቺ አልማዝ ነይ እኮ ነው ምልሽ'. ..አትሰማኝም እንዴ?" (አባት)

..."እና ንገረኛ አባቴ ጋሽ ጀንበሬ ጅብ ሆነዋል ማለት ነው? የባቢ አባት ጅብ ናቸው ማለት ነው?" (ልጅ)

..."ሆሆ! ደሞ ነገ ት/ት ቤት ሄደህ 'የባቢ አባት ጅብ ሆኑ እንጂ አልሞቱም ብሏል አባዬ' ልትል ነው ሆሆ! ደሞ ከጎረቤቶቼ አቆራርጠኛ! በል በል የለም ያልኩህን እርሳው በቃ እንደውም ሀጥያት ነው ከንግዲህ በግ የሚባል አናርድም።. ..ግልግል እንደውም ተወዷል...ሆ! በገዛ እጄ...ቆይ እዛ ት/ት ቤት ምን ስትማሩ ነው የምትውሉት?" (አባት)

..." እርሳው? አባዬ ደሞ አንዴ ነግረኸኝ እንዴት ነው ምረሳው?...ደሞ ት/ት ቤት ሳይሆን አንተ እኮ ነህ የነገርከኝ በግን ስንበላው እኛን እንደሚሆን...ት/ት ቤት ምን አጠፉ....ህእ!" (ልጅ)

..."ማ? እኔ አልወጣኝም! አይወጣኝምም!. ..ምን ይላል ይሄ...በል ጥፋ ከዚ. ..ድራሽ አባክ ይጥፋና...አትሄድም!".....

By Mikiyas Beshada Kebede

@wegoch
@wegoch
@paappii
Forwarded from ግጥም ብቻ 📘 (Leul M.)
#ወደ_ግጥም__ወደ_ነብይ
ፈግታን ስለቸረን መነሱ ___ ስላስጠለለን ዋርካነቱ
ስለ አፅናኝ ጨዋታዎቹ ___ ሕይወት ስለሚያሞቁ ግጥሞቹ
ቅንነቱን ለማቀንቀን ___ አባትነቱን ለማወደስ
ስለ ግጥም _ _ _ ደግሞም ስለ ነብይ
ቅዳሜ እንሰበሰባለን። ፈንድቃ ቤተ ጥበብ [ ፈንድቃ የጥበባትና ባህል ማዕከል:Fendika Art & Cultural Center ]

• ውብ ግጥሞች ልዩ
• ልዩ የሙዚቃ ጨዋታዎች
• ነገረ ነብይ
• የጥበብ ቅማ ቅመም

የምትወዷቸው የምንወዳቸው ሁሉ አሉ። ስለ ግጥም _ ስለነብይ።

ከ8:00 ቀደም ብላችሁ ኑ።
ቡናውም ጨዋታውም ወዳጅ ትውውቁም እንዳይቀርባችሁ።

ቅዳሜ ሀምሌ 6 2016 ዓ.ም 😍🙏🙏🙏😍

@getem
@getem
Notcoin🪙 በአዲስ አሰራር መቷል! ገብታችሁ ስሩበት


https://www.tg-me.com/notcoin_bot?start=er_36367900
አባት ልጁን ለማግኘት ወደ ክፍሉ ጎራ ይላል፤ ልጁ ግን የለም። እንደለመደው አምሽቶ ሊመጣ እንደሆነ እያሰበ ክፍሉን ለቆ ሊወጣ ሲል የሆነ ነገር አስተዋለ።

አዎ ክፍሉ እንደወትሮው አልተዝረከረከም፤ በሚገባ ተፀድቶ ተስተካክሏል። አልጋውም በስርዓት ተነጥፏል፤ ወለሉ ሸልፉ ምኑ ሁሉ በወግ በወግ ሆኗል።

ግራ በመጋባት ክፍሉን እየቃኘ በመሃል ማጥኛ ጠረጴዛው ላይ ደብዳቤ ያገኛል፤ ከላይ ለ አባዬ ይላል በትልቁ።
ከፍቶ ማንበብ ጀመረ..

“ አባዬ ከትሬሲ ጋ ተያይዘን ጠፍተናል..አውቃለሁ እድሜዋ ከእኔ በ30 እንደሚበልጥ ፤ ቢሆንም እኔ ግን በጣም እወዳታለሁ። ለመጥፋት የወሰንነው እንዳረገዘችና ልጁ የኔ እንደሆነ ስትነግረኝ ነው።
ምንም ገንዘብ ስላልነበረን ከዋሌትህ ልሰርቅ ተገድጃለሁ።

ጥሩ ገንዘብ መስራት የጀመርን ጊዜ፤ የኤች አይ ቪ በሽታዋን ሆስፒታል እየሄድን ክትትል ማድረግ እንጀምራለን። ደሞ ብዙ ልጆችንም የመውለድ እቅድ አለን ፣ ጊዜው ሲደርስ ተሰብስበን መጥተን የምናይህም ይሆናል።

ቆይ ቆይ አባዬ የውሸቴን ነው ተረጋጋ፤ እዚሁ ሰፈር ነው ያለሁት የትም አሌድኩም። የኔ ፍላጎት ከፈተና ውጤቴ በላይ አስፈሪ ነገሮች እንዳሉ ለማስታወስ ነው ፤ ልታየው ከፈለክ ሌላኛው ጠረጴዛ ላይ አለልህ።
ስትረጋጋ ደውልልኝ ”

@wegoch
@wegoch
@paappii
ፀጉር ቆራጩ ደምበኛውን ያዝናናል ብሎ ያሰባቸውን ነገሮች በማጫወት ላይ ነው።
“ያ ይታይሃል?...አስፖልቱ ዳር የተቀመጠው ልጅ..?”
“አዎ”
“ከምታስበው በላይ ጅል ነው”
“እንዴት? ”
“ቆይ ላሳይህ” አለና ፤ወጣ ብሎ ልጁን ጠርቶ ወደ ውስጥ አስገባው።
“ተመልከት እንግዲህ..”

ከኪሱ አንድ የአምስት ብርና አንድ የአስር ብር ኖት አወጥቶ ሁለቱንም መሬት ላይ ጣላቸው ከዛ ልጁን “ ከሁለቱ ትልቁን ብር አንስተህ ሂድ” አለው። ይሄኔ ያ ልጅ አምስቷን ብር ብድግ አርጎ ወደ መጣበት ይመለሳል።
“አየህ ይሄን ደደብ?...በዚ እድሜው አምስት ብርና አስር ብርን መለዬት አይችልም!!”
“በጣም ሚገርም ነው” አለ ፀጉሩን ሊቆረጥ የመጣው ሰውዬ ባዬው ነገር የእውነትም ተገርሞ።

አስተናግዶት ከጨረሰ በኋላ ተሰነባብተው ተለያዩ። ይሁን እንጂ ያ ሰውዬ ቅድም ባየው ነገር ተገርሞ ብቻ ሊቀር ስላልፈለገ ልጁ ወዳለበት ሄዶ ያሳሰበውን ነገር ጠየቀው
“እውነት አንተ..አስር ብር እና አምስት' ብርን መለየት አትችልም?”
“አዪዪ..” አለ ልጁ
“አዪዪ..10 ብሩን ያነሳሁ ቀንማ ጨዋታው ያበቃል”

by Yosef Gezahegn

@wegoch
@wegoch
@paappii
ሥዕል ለወዳጅ ዘመዶ ስጦታ ማበርከት የምትፈልጉ በ+251984740577 ይደውሉ።


ወይም @gebriel_19 ላይ  ፎቶ  በመላክ በ ተመጣጣኝ ዋጋ  ማዘዝ ይችላሉ!



@seiloch
@seiloch
ብርቅዬ ጎደኞቻችን

———
አብዛኞቻችን ከህይወት ዘመናችን አካል ከሆኑት ውስጥ የት/ቤት ጎደኞቻችን እና ትዝታችዎቻችን በእጅጉ ከምንናፍቃቸው እንዲሁም ወደኋላ ተመልሰን የመኖር ምርጫ ቢሰጠን በድጋሚ ያን ህይወት ለመኖር የምንመኘው እና የምንጎጎለት አንዳንዴም እንደእኔ ያለ የኋላውን ናፋቂ የሆነ ሰው በፈረንጆቹ ፊልም ውስጥ የሚያየውን በእነሱ አፍ  time travel  ወደኛ ስናመጣው ጊዜን ወደፊት እና ወደኋላ መመለሻ machine ለመስራት መመኘቱ አይቀርም ትግበራ ላይ ባንገባም (እውቀታችን ቢገድበንም) እና ስመለስ ወደእኛ አለም  የት/ት ቤት ህይወታችን ወርቃማው አስደሳቹ የህይወት ዘመናችን አካል ነው ብል ማጋነን አይሆንብኝም።የት/ት ቤት ትዝታዎቻችንን ስናነሳ ደሞ የሀይስኩል ህይወታችንን ሳናነሳ ማለፍ የሚታሰብ አይደለም የአብዛኞቻችን አስደሳች ሮማንቲክ አስቂኝ ህይወት ያሳለፍነው እዛ ውስጥ ነው ። ያ  ጊዜ ለብዝዎቻችን መፈንዳት የጀመርንበት (like volcano )ሴት መጥበስ ,መጀንጀን ትምህርቱን ከነጭራሹ መርሳት  ,ቤተሰብ ትልቅ ሰው መስማት ያቆምንበት እንደልባችን የምንሆንበት ከጎደኞቻችን ጋር ጥዋት ወተን ማታ ለማደር ወደቤት የምንገባበት አፍላ እድሜ። በዛ የጡዘት ጊዜ አይደለም ቁምነገረኛ ልጅ መሆን ቀርቶ ጥሩውን ከመጥፎ በቅጡ መለየት የምንቸገርበት እድሜ ነው ።ታዲያ እንዲህ ስል የሁሉንም የት/ት ቤት ህይወት የሚያጠቃልል አይደለም ሁላችንም አሉን ለየት ያሉ  ከልጅነት የምናቃቸው አንዳንዴም የቅርብ ጎደኞቻችን የሆኑ አሉን።  ከላይ የጠቀስኩትን life የማያቁት ከእድሜያቸው በላይ የበሰሉ አሁን ላይ ሆነው የወደፊታቸውን ዛሬ የሚቀርፁ,ሚያልሙ ትልቅ የማይዳሰስ የማይጨበጥ ለኛ ሲነግሩን እንድናሾፍባቸው የሚያደርጉን  ቁም ነገር የሚያበዙ በአብዛኛው ነገራቸው ለየት ያሉ ከኛ በተቃራኒ የቋሙ ውስጣቸው ሌላ ትልቅ ሰው አለ እስከምንል ንግግራቸው እና ሀሳባቸው የሚያስደንቀን እኛም የእነሱ አለም ገብቶንሞ ሆነ ሳይገባን እንዲሳካላቸው የምንመኝላቸው አሉን ብርቅዬ ጎደኞች ከዘፋኞች መሃል ያሉ ዘማሪዎች ከወረኞች መሃል ያሉ ዝምተኞች ከተደባዳቢዎች መሃል ያሉ አስታራቂዎች አሉን በትምህርት ብቻ ዕውቀታቸው ያለተገደበ ከኛ መሃል ምሁሮች አሉን። ታዲያ ይሄ ሁሉ ነገር እንዳነሳ ያስገደደኝ አንድ ነገር ነበር ተዕለታት በአንዱ ቀን ማታ ላይ ከቤተሰቦቼ ጋር ተሰብስበን  ቁጭ በልንበት ልጄ ለመዝናኛ የሚሆን ነገር ለመክፈት ከቻናል ቻናል ይቀያይራል በድንገት ግን አንድ  ከዚ ቀደም የማውቀውን ሰው በቲቪ መስኮት አየሁት በፍጥነት እንዲመልሰው ወደቻናሉ ልጄን አዘዝኩት ትዕዛዝ ይሁን ቁጣ አላቀውም እሱም ደንግጦል መለሰው እንዳልኩት አየሁት በድጋሚ ልቤ ደነገጠ የማውቀው ስሜት ተሰማኝ ልዩ ታሪክ አለኝ ከሱ ጋር ግን አልመጣል አለኝ ተብሰለሰልኩ አዕምሮዬን አስጨነቁት ጎልማሳውን ሰው ለማስታወስ የአዕምሮዬን የትውስታ ፋይሎች አገላበጥኩ ደከምኩ ከብዙ ድካም በኋላ የሆነ ሰው ያፋልጉኝ ማስታወቂያ ተለጥፏለት ሲገኝ እንዳለው ስሜት ተሰማኝ ተደሰትኩ አመሰገንኩ ወደራሴ ስመለስ  ቆሜ ነበር እና ተረጋግቼ ቁጭ አልኩ ሳቅኩ ከልቤ ተገረምኩ የደስታም እንባ አነባው ይሄ ሁሉ ሲከሰት ለካ እረስቻቸዋለው ቤተሰቦቼን ቁጭ ብለው እንደቲያትር ታዳሚ ይመለከቱኛል ከዛም ትወናው  አለቀ መሰለኝ ሚስቴ ልጆቼን ወደክፍላቸው አስገብታ ልታወራኝ መጣች መቼም ልጆጄ ዛሬ እንቅልፍ የላቸውም ምን እንደተፈጠረ ሲያሰላስሉ ሲጠይቁ እና ሲመልሱ ነው ሚያደሪት ።ወደሷ ስለመስ በአግርሞት እና በነዛ ስስ አይኖቾ በስስት እያየቺኝ ስፖንጅ በሚመስሉ እጆቾ እየዳበሰቺኝ ምን እንደተፈጠረ ጠየቀቺኝ ምኑን ብዬ ምን ልበልሽ ከየትኛው ልጀምርልሽ አልኳት አይን አይኖን እያየዋት እኔም በተራዬ ።ደስ ካለ የሷ ምላሽ ነበር  በሀሳብ ብዙ አመታት ተመልሼ ጀመረኩት ትረካውን አንድም ለሶ አንድሜ ለራሴ ።

ይቀጥላል part 2

@wegoch
@wegoch
@paappii
በውስጣችን ያለውን ሰውዬ እንዴት ተው እንበለው ?
(ሚካኤል አ )
እነሆ ለብርሀን ጨለማ ፣ ለወንድ ሴትን ፣ ለክፋት ደግነትን ተቃርኖ አድርጎ ሲፈጥር እንዴት ባንድ ገላ ውስጥ ሁለት ማንነት አብሮ ማቆየት ቻለበት ስል አስባለሁ !
ከዚህ ቀደም ሚካኤል አስጨናቂ (እኔ) ተቤራ በተሰኝ መፅሀፉ "ወይ ለከ!" በሚለው የአጭር ልበ ወለድ ክፍል ያነሳት እንስት ሁሌ ወደ አዕምሮዬ ትመጣለች ።
ያቺ ሴት ሰዎች በተለምዶ ሴተኛ አዳሪ የሚሏት ካራክተር ነች ።
ልቧ ሩህሩህ ፣ እምነቷ ፅኑ ነው ።
አታውቅም አይሏት ማንበብና መፃፍ ፣ መስማትም ትችላለች ። አንድ ጊዜ ዋነኛው ገፀ ባህሪይ ሊታዘባት ለገብርኤል ዕለት ሻማ ስታበራ አያት ።
የሱ አይደለም የሚገርመው ፣ የበዓል ዝክር አቀረበች ። ቡናው እጣኑ ፏ ብሎ ጠባቧ ቤት ድባቧ ፈካ ።
ያኔ “ይህን ለምን እንዳደረገች “ ጠየቃት ።
ያቺ ሩህሩህ እርግብ ። “ገብርእኤልን እወደዋለሁ ። ጠባቂ መልዓኬ” ነው አለችው ።
እሰየው አበጀች!
ቀጣይ ንግግሯ ግን መንፈስን በሁለት ገመድ የሚወጥር ፣ ግርምትን የሚጭር ነበር ።
“ አባቴ ዛሬም አንዱን ክልፍልፍ ያመጠልኛል ። መቼም ፆም አያሳድረኝ” አለች ።
አሁን ይህች ሴት እንዲህ ያለው እምነት እያላት ፣ እንዲህ ያለው ቀናኢነት እና የዋህነት እያላት ገላን ለዝሙት መስዋዕትነት ማቅረብ ሀጥያት መሆኑን እንዴት ሳታገናዝብ ቀረች ?🤔
ገብርኤልን ለዝሙቴ ተባባሪ አድርገኝ ብሎ በየዋህነት መለመንን ምን ይሉታል ?
ዋናው ገፀ ባህሪ ገረመችውም ፣ ስጋዋ ደግሞ አሳዘነችው ።
ዝም አለ ፣ ፅሞና ።
ዘመዴ እስቲ ሌላ ጨዋታ ላቀብልህ ደግሞ !
የዘመነ መሳፍንቱን ደጃች ማሩ ታውቃቸዋለህ አይደል ?
መቼም እኒህ ባላባት ዝክር አውጥተው ፣ እግዜርን ተለማምነው ፣ ለሀይማኖታቸው ቀንተው በቃኝ አይሉም ። አቤት እግዚሀርን ሲወዱት !
ለአንገት ሰይፍ መዘው ንሰሃ አባታቸው “ውጉዝ ከማሪዎስ” ካሉ ንዴት እና ደምፍላታቸውን ዋጥ አድርገው ሰይፋቸውን ወደ አፎታቸው ለመመለስ አይግደረደሩም ።
እናም አንደዜ ረዥም ፀሎት ይዘው አሽከራቸው ከጠሎት አናጥቧቸው እንዲህ አላቸው !
"ጌታዬ አስቸኳይ ጉዳይ አለን "
“እህ ምን ሆናችሁ ?”
“ስለ አያል ጉዳይ ነበር “
“አያል ምን ሆነ ?”
አሽከሩ እጅ ነስቶ ለጥ ማለት እየቀረው
“ጊታዬ እሱን አስሮ መግረፍና ማሰቃየት ደከመን አላቸው ። አንድ ነገር ይበሉት “
“ለዚህ ነው ፀሎቴን ያቋረጥከኝ ? አመዳም ወግድልኝ “ ብለው ተመናቅረው ሎሊያቸውን አባረሩት ።
ያ ሎሌ በልቡ እንዲህ ያለ ይመስለኛል ።
“እኒህ ምስጉን ትልቅ ፀሎተኛ መሪ እንዴት የአንድ ነፍስ ስቃይን እንዲህ በቀላሉ ንቀው ይተውታል ?”
(በነገራችን ላይ ደጃች ማሩ ደጃች ኃይሉን (የመይሳው ካሳን አባት) በክህደት ለረዥም ጊዜ ግዞተኛ አድርገውት መቆየታቸው በታሪክ ይወራል ። ይሄም ራሱን የቻለ ብዙ ጥያቄ የሚያስነሳ የክፉ ባህሪያቸው ምሳሌ ነው ። ክህደት !
በሌላ በኩል ደጃች ይማም በጎንደር ቅኔ ቤት ተማሪዎች ላይ በፈፀሙት ግፍ ምርር ብለው በሀዘኔታ ሲያነቡም ተስተውለዋል ። ሁለት ሰው ማለት ይሄ አይደለምን ?
ይሄን ሁሉ የምዘበዝበው ልጅ ሆነን ለፍስለታ ጾም ያጋጠመኝ ነገር ትዝ ብሎኝ ነው ።
ሁሌ መልክምነትን የሚያስተምረን ፣ በዛ ዕድሜ ካለን ልጆች በመልካምነት እና ዕውቀት አርአያ የምናደርገው ስንሻውን ነበር ።
ብዙ ልጆች አብረነው ፍልሰታ ፆምን እናስቀሳለን ።
ቄስ አምሀ ባዛ ስርቅርቅ ድምፃቸው አሀዱ ብለው አስጀምረው በሰላም ግቡ እስኪባል ድረስ በፍፁም መንፈሳዊነት እና ስክነት እናሳልፋለን ።
መቼም የቅዳሴ መዓዛው እና ጣዕሙን ያላጣጣመ ሰው ምንኛ ቀረበት ። የመቅደሱ እጣን ያን ሁሉ ፀሎት ቀጥ አድርጎ ወደ ሰማይ ሲያሳርግ በምናቤ ይታየኛል ።
የገነት መዓዛ !
ቅዳሴው ተፈፅሞ ወደ ቤት ስንሄድ ግን ስንሻው አድርጎ በመጣው ኤርገንዶ ጫማ ምትክ ዘናጭ እስኒከር አድርጎ አየሁት ።
ይሄ ልጅ መላዕክት ቀናነቱን አይተው ጫማ ገዝተው አምጥተውለት ይሆን ? ለማለት እየዳዳኝ
“እስኒከሩ?” አልኩት ።
“ አዎ ካንዱ ነፈዝ ላፍ አደረግሁት 😃"አለኝ
አጠገቤ የቆመው ያ የሰው መልዓኩ ስንሻው መሆኑን ተጠራጥሬ ትክ ብዬ አየሁት ።
በውስጣችን ሌላ ሰው እንዳለ ያሰብኩት ለዛን ቀን ይመስለኛል ።
በቃ የልጅ ልቤ በድንጋጤ አታሙዋን ደቃች ።
ዛሬም ድረስ ራሴንም ይሁን ሌላውንም ሰው እፈራለሁ ።
ውስጣችን ያለውን ሰውዬ መቼም አላምነውም 🙂


@wegoch
@wegoch
@wegoch
የመጨረሻው ቀን August 14 ነው። እድላችሁን ሞክሩ🙌
https://www.tg-me.com/dogshouse_bot/join?startapp=2H-hloxORHKMqDS8Gwvfbw
የሔዋን እናት... !

(ኤልቫን እንድታሸንፍልን የቋጠርንበት አንድ ዘመን🥰)

ዝም ብዬ ስለ ሲፋን ሐሰን እያሰብኩ... ድንገት ኤልቫን (ሔዋን) አብይለገሠ ትዝ አለችኝ። ያቺ ለቱርክ ትሮጥ የነበረችው፣ ልክ እንደ ሲፋን ቀጭን አንጀት የራቃት (አንጀት የምትበላ) ግን ጎበዝ፣ አይበገሬ፣ ፈገግተኛ አትሌት ነበረችንኮ። ብዙ ሰው እንደሚያስታውሳት አስባለሁ።

ያቺ ኤልቫንም እንደ ሲፋን ብዙ ድንቅ የሚባሉ የሩጫ ድሎች ነበሯት። በሆነ ወቅት የግማሽ ማራቶን ወርቅ ሜዳሊያን ወስዳ፣ እና የ5ሺ ይሁን የ3ሺ ሪከርዱን ሰብራ ሁሉ ነበረ። ልክ እንደ ሲፋን በየውድድሩ አትጠፋም ነበር ኤልቫንም!

ታዲያ ኤልቫን የደብረብርሃን ልጅ ናት። ያኔ.. የዛሬ 20 ዓመት አካባቢ ማለት ነው.. የንግድ ባንክ ነገረፈጅ ሆኜ የሰሜን ሸዋ፣ የመራቤቴ፣ የፍቼ፣ ወዘተ አካባቢዎች ጉዳዮችን በኃላፊነት ወስጄ ፍርድቤቶች እቀርብ ነበረ።

በዚያም ወቅት ብዙ ጉዳዮች በእንጥልጥል ላይ በመሆናቸው ለእነሱ በቶሎ እልባት እንድሰጥ ተብሎ (እና ተስማምቼ)፣ አለቆቼ አዲሳባ ሆነው፣ እኔ ደሞ ደብረብርሃን ላይ የማስተባበሪያ ቅርንጫፍ ቢሮ ተከፍቶልኝ፣ ለ11 ወራት ገደማ ለቆየ ጊዜ ሠርቼያለሁ።

በዚያ ወቅት፣ ያው ወጣትነትም አለ። ጭፈራውም። የጓደኞች መዓትም አለ። ብሩም ይመጣል። ይጠፋል። የሚገርም ዓለም ውስጥ ነበርን ከነጓደኞቼ። አንዳንድ ድሮ ሎውስኩል አብረን የተማርን ጓደኞቼም በደብረብርሃን በሚገኘው የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛው ፍርድቤት በዳኝነት ያገለግሉ ነበሩ። የሚገርም ጊዜን አሳልፈናል አብረን።

ታዲያ አንዳንዴ ኪሳችን የሚሞላውን ያህል፣ ስለማንሠርቅ ደግሞ፣ የዚያኑ ያህል በወሩ መጨረሻ ገደማ ደግሞ ኩ ኪሳችንን ድርቅ ይመታዋል። አንደኛችን ሌላኛችንን እስቲ ትንሽ ሳንቲም ይኖርሃል? የምንልበት ወሽመጥ ይቆረጥብናል። ምክንያቱም እንተዋወቃለና😀😊

እና በአንድ በጠብሽ በተወገርንበት አንዱ ክፉ ሰሞናችን፣ እግዜሩ አትሌት ኤልቫን ለገሠን በእጃችን ላይ ጣለልን። እንዴት? በየት በየት በኩል? ቀላል ነው። አስረዳለሁ።

የኤልቫን ወላጅ እናት የደብረብርሃን ከተማ ነዋሪ ነበሩ። ነዋሪ ብቻ ሳይሆኑ በከፍተኛው ፍርድቤት የመዝገቤት ሠራተኛ፣ እና የችሎት አስተናባሪ ሆነው ይሠሩ ነበረ። አሁን ስማቸው ተዘነጋኝ። ስማቸውን ስለረሳሁ በጣም ራሴን ወቀስኩ። አልዛይመሬን😊!!

እና ለቱርክ የምትሮጠዋ ኢትዮጵያዊት ቀጭኔ ተምዘግዛጊ አትሌት፣ ኤልቫን፣ የሆነ ዓለማቀፍ ውድድር ባሸነፈች ቁጥር፣ በቃ ለእናቷ ጫን ያለ ብር ትልክላቸው ነበር። እና ከመጠን በላይ ደስተኛ ነበሩ።

ደሞ እኛ ፍርድቤት አካባቢ ያለነው፣ የኤልቫን እናት መሆናቸውን ስለምናውቅ፣ ኢትዮጵያውያንን ቀድማ ወርቃችንን በመንጠቋ ቆሽታችን ቢያርር ራሱ፣ እናቷን ግን በማግስቱ ስናገኛቸው "እንኳን ደስ አለዎት! ጀግና ልጅ አለችዎት!..." እያልን የእናትነት ደስታቸውን ለመቋደስ (በአራዳ ቋንቋ እናትየውን ለማመቻቸት) እንጣጣር ነበር።

በሆነ ለደመወዝ በቀረበ አንዱ ሰሞናችን ታዲያ፣ ከየት እንበደር? እያልን መላ እየዘየድን እያለ... በድንገት አንድ የአትሌቲክስ ድል በጓደኛችን ቤት ቲቪ ላይ ተሰማ። ለቱርክ የምትሮጠው ትውልደ ኢትዮጵያዊት ኤልቫን አንደኛ ወጥታለች፣ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ደሞ ሁለተኛና ሶስተኛ ሆነው ጨርሰዋል። ያንን እንዳየን እኔና ዳኛው ጓደኛዬ (ስሙን ልጥራው ይሆን?) በደስታ እርስበርስ ተያየን!😀 ቆይ ሰው ሀገሩ ወርቅ ተነጥቃ ምን ፈገግታ ያለዋውጠዋል?

በማግሥቱ ይሁን በሳልስቱ "አንተ ጠይቃቸው፣ የለም አንተ ጠይቃቸው" ተባብለን ለኤልቫን እናት ሞቅ ያለ እንኳን ደስ ያለዎት መልዕክታችንን ካሰማን በኋላ... ፀጉራችንን እያከክን (አንደኛችን)... "ከሰሞኑ ደመወዝ ሲወጣ የሚመለስ ትንሽ ብር ይኖርዎት ይሆን... የኤልቫን እናት?" የምትለዋን ወሳኝ ጥያቄ እንደምንም አምጠን ተነፈስናት😀😀😀!

መልሳቸው ከጀት የፈጠነ እሺታ ነበር! እንዴታ! ደሞ ምን ችግር አለ? ስጦታ አልጠየቃችሁኝ? ያውም ብድር? ደሞ ልጄ ልካልኛለች ቤትሽን አሳድሺ ብላ! አይዟችሁ፣ ሲቸግራችሁ እናታችሁ ነኝ፣ ጠይቁኝ፣ አትፍሩ...!?" ተብለን በነፍስ ወከፍ በጠየቅነው ልክ ብድር ተለቀቀብን😊😀😀! አቤት ደስታ? አቤት ፌሽታ?! ከማጣት በኋላ የምትገኝ ሲሣይ... አቤት በረከቷ?!🥰😊😀

ታዲያ ሁሌ ስለ ኤልቫን ሳስብ... በእናቷ በኩል... ደብረብርሃን ላይ.. ለጠብሽ ሰሞናችን እንደ አንዳች ሲሣይ ከሠማይ ወርዳ የደረሰችልንን እያሰብኩ... ሁሌ ፈገግ እላለሁ!

ደሞ ጓደኞቼም ቀልደኞች ናቸው... አንዳንዴ ኧረ ሰሞኑን ድርቅ መታን እኮ... አሁንስ ሰበብ አጣን... ያቺ ኤልቫን ለገሠ ከሰሞኑ አንድ ውድድር አሸንፋ ይሆን? እንባባላለን። ሣቅ በሣቅ። ኧረ አልሰማሁም፣ አልሰማሁም ይላል ሌላው ሰው። ከዚያ ይቺ ጦልጧላ ማሸነፍ አቅቷት ነው አሁን? የማንን ጎፈሬ ስታበጥር ነው..? እኛ እሺ ምን እንሁን?? 😀😀😀 ሌላ ሳቅ! ብዙ ሳቆች!

ጊዜዎችህ፣ ዘመኖችህ፣ ወራቶችህ፣ የፍፍስሃና የሃዘን ሰዓቶችህ፣ የጠብሽና የሃላል ቅፅበቶችህ ሁሉ አብሯቸው የተያያዘ አንዳች የሰው ታሪክ አላቸው። በዐድሜህ ሁሉ የሆነ አብሮህ የሚደሰት፣ አብሮህ የሚከፋ፣ አብሮህ ምች የሚመታ፣ አብሮህ ከሲሣይህ የሚቋደስ አንድ ሰው፣ ብዙ ጓደኛ፣ ብዙ ሰዎች አሉ።

ይህ ነገር በተለይ ለእኛ ኢትዮጵያውያን በብዛት ተለይቶ የተሰጠን ትልቅ የጋራ ህይወት፣ ትልቅ የተባረከ ዕፁብድንቅ ሥጦታ ይመስለኛል።

ከሃገርህ ርቀህ ብዙውን ጊዜ፣ አጣህም አገኘህም፣ ተደሰትክም ከፋህም፣ ጨነቀህም አለፈልህም... ብዙ ጊዜ በብቻህ ጀልባ ላይ ነህ። ወቅቶችህ አኗኗሪ፣ ትዝታ ፈጣሪ፣ አዳማቂ ሰው የላቸውም። ሰው አልባ ህይወት፣ ትንፋሽ የለሽ ዕድሜ ይሆንብኛል።

እና ሳልወድ በግድ የድሮውን መከራና ደስታ እናፍቃለሁ። ሳልወድ በግድ በድሮ ትዝታዎች ውስጥ ስመላለስ አገኘዋለሁ ራሴን።

አሁንም ወደ ኋላ በትዝታ የመለሰኝ መነሻ ሃሳብ... የሲፋን ለኔዘርላንዶች መሮጥ ነበር። በሷ የተነሳ የጥንቷ የጠዋቷ ኤልቫን አብይለገሠ እና የደብረብርሃኗ ደግ፣ ደስተኛ፣ ትሁት እናቷ ትዝ አሉኝ! ጓደኞቼ ትዝ አሉኝ። ቀኖቻችን ትዝ አሉኝ።

ያ ሁሉ ወጣትነት። ተስፈኝነት። ሃቀኝነት። የጋራ ደስታችን። የጋራ ድብርታችን። የጋራ ጎጇችን። የጋራ ሀገራችን። የጋራ ዓለማችን። የጋራ ላይፋችን። ብዙ ወርቃማ ትዝታዎች ተግተልትለው ወሰዱኝ በሃሳብ።

የደብረብርሃን የኤልቫን እናት በዕድሜ፣ በጤና አሁንም እንደሚኖሩ ከልቤ ተስፋ አደርጋለሁ። ስለ ደግነታቸው፣ በአካል የራቀቻቸውን ልጃቸውን ድል በሰሙ ቁጥር፣ ደስታቸውን የሚጋራቸው ወገን ሲያገኙ... ከዓይኖቻቸው የሚፈልቁት የደስታ ጮራዎች አሁን ፊቴ ላይ ድቅን ይሉብኛል። ባሉበት መልካሙን ሁሉ እመኝላቸዋለሁ።

ለሁሉም። ለሁላችንም። የሰው ሃገር ባንዲራ ይዘው እንዲሮጡ ህይወትና ዕጣፈንታ ያስገደደቻቸውን የእናት ኢትዮጵያ አፈር ያበቀለቻቸውን ውድ ልጆቻችንን ሁሉ... ለእነሱም። ፈጣሪ መንገዳችንን እንዲያቀናልን። መልካሙን ሁሉ እንዲያመጣልን ምኞቴ ነው።

ፈጣሪ እናት ሀገራችንን፣ ሕዝባችንን፣ አብዝቶ ይባርክ!

በረካ ሁኑ! ♥️

መልካም ጊዜ!!🙏

by assaf Hailu

@wegoch
@wegoch
@paappii
ወግ ብቻ pinned «⌚️ በቀጣይ List የሚደረጉ ፕሮጀክቶች 👇👇👇 ትንሽ ጊዜ ነው ያላችሁ! #LOST_DOGS https://www.tg-me.com/lost_dogs_bot/lodoapp?startapp=ref-u_454803628__s_573809 1, MAJOR https://www.tg-me.com/major/start?startapp=454803628 2, BLUM🤢 https://www.tg-me.com/blum/app?startapp=ref_4AQg09PDzR 2,CATS 🐈 t.me…»
"እማዬኮ ሔዱ"
.
.
ባውሮፕላን ሔዱ። ጎረቤቶቻቸው አዋጥተው በአውሮፕላን አበረሯቸው።
ፎቶ እንኳ እንደሌለን ያወቅኩት ሲሔዱ ነበር። ሙሉ ጊቢውን ጠየቅኩ ማንም የለውም።
"ሳላገኘው ልሔድ ነው?" እያሉ ሳለ ትናንት ከአዲስ አበባ መጣሁ።
"እማዬ ማናቸው?"
የዩቲዩብ ትምህርቶቼን የሚከታተል ድምጻቸውን ሳይሰማ አይቀርም።
..
"ለምን ሔዱ?"
.
ምክንያታቸውን ሲናገሩ...
"ደከመኝ! የሽንት ውሀ ማንጠልጠል እያቃተኝ መጣ"
" ደጁ ላይ አስቀምጡልኝ ብለው አላቀብሎትም ያለ ሰው አለ? መሔድ ደስ ካላሎት ለምን አይቀሩም ?"
🥺 " ላዬ ላይ ሲያመልጠኝስ? ምን ታደርጋላችሁ?"
.
እማዬ ለምን በዚህ መሆን ፈለጉ?
.
1. ሀሜት አለ።
አራት አመት ገደማ ሆኗቸዋል ድሬዳዋ ከገቡ። የወሎ ሰው ናቸው።
ተመልሶ ወደ ልጆቻቸው መሔድ ደስ አላላቸውም። ስጋ እንደ ባዳ እንደማይደላ ደመነፍሳቸው ነግሯቸዋል። ዘመድ ስጋን እንጂ ስነልቦናን አይረዳም።
.
ባዳ መሀል ሀሜት አለ። ሀሜትኮ ንሰሀ ነው አይምሮን ያጸዳል። ቅርጥፍ አድርጎ ማማት ያልቻለ ሰው paranoid የመሆን እድሉ ሰፊ ነው። በአጭሩ ሀሜት #የአይምሮ_ሰገራ ይመስላል። ቆሻሻ ነው ግን መውጣት አለበት ልክ እንደ አር። አማናዊው ሰገራ በባለቤቱ ግፊት በምጥ ይወጣል! የአይምሮ ሰገራ ለማውጣት ግን #ባዳ ይፈልጋል።
.
#ባል ባዳ ነው። ለዛ ነው ሚስቱን #የሚበዳው። ባዳው ባል ከሚስቴ ጋር ይሕ #ስጋዬ ነው ይህ #ስራዬ ነው #ሳይል በሀሜት ከተንበለበለ አይምሮው ጤነኛ ይሆናል! ረጅም ይኖራል። "ሴትንኳ ስራዋ ነው" 🤭 አላልኩም ስርአት!!! ሚስትም ከጎረቤት ማማት ትታ ከባሏ ጋር በማማት ከተባበረች #እባብ ፈጣሪን የሚያሳማው ባዳ አያገኝም።
..
2. ትዕዛዝ አለ።
.
ዘመድ እንደባዳ እርጅናን አያከብርም። አሮጊቷን አንቺ ሲል ያቀረበ ይመስላል። ፍቅር ክብርን የሚበልጥ የሚመስለው ይኖራል። በፍቅር እንደልብ መታዘዝ የለም በክብር እንጂ። አልገባንም ከምናፈቅረው ለምናከብረው እንታዘዛለን። ከእናት በላይ ለአባት እንደማለት።
.
የምናፈቅረው ላይ የምናከብረው ነገር ከተገኘ አቤት መታደላችን።
.
#እማዬ ይከበራሉ። #ደም ለማየት ወራት የቀሯትን የደረሰች ልጅ ሲልኩ በሞገስ ነበር። ማንም የእርጅና ዘውዳቸውን እያየ ይታዘዝላቸዋል። ምናልባትምኮ ልጅቱን ከ 20 ሜትር የጠሯት አንድ እርምጃ ርቀት ላይ ያለች ከሰል እንድታቀብላቸው ነው። ፊቷን ቅጭም እንዳደረገች አቤት ሳትል ታቀብላቸዋለች። እግረመንገድ ለሚያወሯት ዝብዛብ አትመልስም! አቀብላቸው ስትመለስ እየተጉመጠመጠች ነው።
"አንቺ አስቀያሚ ስለምወድሽ ነውኮ!" ምናምን ይላሉ። "ኧረ ጎረመሰች" ይላሉ።
ሌላ ትእዛዝ እንዳይደግሟት እየጸለየች አጎንብሳ ትፈተለካለች። የልጅ ልጃቸው ብትሆንስ?😁
(አንድ የልጅነት ጓደኛዬ አጨባሽ አያቱ በመላክ አማረውት "ጂፓሱ ሸርተት ብሎ በወደቀባቸው" ይለኝ ነበር)
.
.
3. ሰላምታ ያገኛሉ።

ኦኦ እማዬ ሰላምታ ነፍሳቸው ነው። ማንም ሰላም ሳይል አያመልጣትም! በጊቢው 12 ተከራይ አለ። ከአንዱ ቤት ቢያንስ 2 ሰላምታ አያጡም። ሀያአራት ደና አደርክ እና ደና አመሸህ። አንዳንዴም እድል ከቀናም ስምንት ደናእደሩ ይደርሳቸዋል።
.
በሳቸው እድሜ ይሔ ቀላል ሀብት እንይመስልህ። ደሞ ትንሽ ስኳርና ሌላም በሽታ አላቸው/አለባቸው። ስለዚህ በትንሹ ሁለት ረዘም አድርጎ ጤናቸውን ጠያቂ ይገኛል። እግረመንገድህን ስለጤናህ ተመክረህ ታልፋለህ። ምናልባት ከትናንት ወዲያ አንዷ ጎረቤትህ እናትህ ከሪፍትቫሊ #የገዛችውን(ማነው ያገኘችውን! No ያመጣችውን! ይሔም አይሆንም ብቻ whatever u call it) የዲግሪ ወሬ ሰምተዋል።
"እንኳን ደስ አላት...ምን ተማረች...አንተን የመሰለ አድራሳ ምነው እስካሁን...😁" ብዙ ወሬ! ቲክቶክና ፌስቡክ የማይጠቀሙ ሰዎች መሰንበቻ የሚሆን ወሬና ጨዋታቸውን ከየት ያመጣሉ? እንደዚህ ነዋ የሚሸቃቅሉት። በስጋቸው መሀል ይሔም የለም።
.
.
5. ከሰል ይሸጣሉ።

ይሔ ደሞ እንድሜ ለመብራትሀይል መላ ሰፈሩን ወደሳቸው ይነዳዋል።
በህጻን አዋቂው "እማዬ የሉም" መባል ቀላል አይምሰላችሁ። በቀደም በመልክ የማያውቀኝ አንዱ
"የበሀይሉ መጸሀፍ አለ?" ሲሉት ጃፈር ጎን ቆሜ የተሰማኝን ሙቀት አልረሳም። 😊
ጃፊ በአይኑ አይኔን እያጠቀሰ "አልቃለች..." ሲልማ እዛው ገልቤ ልመታ ምንም አልቀረኝ።😁
እማዬ...
"ዝርዝር ይዛችሗል?
ማነው ስምህ አንተ? አባትህ ይቅማል? በል ቀጣይ ስትመጣ ፌስታል ይዘህ ከመጣህ ለበጎቻችሁ የተረፈ ሰላጣና ድንች አዘጋጅልሀለሁ። ምነው አጠርክብኝ ደሞ"
" ኧረ እናቴ ላጭታኝ ነው"
" በልሺ ሒድ አጭበርባሪ ቁመትህን የማላውቅ መስሎህ ነው አ?" (ይቺ ሁለት መስመር እንኳ ነገር አማረልኝ ብዬ ልቦለድ ሳደርጋት ነው። እማዬ አይሞጣሞጡም። አይናፋር አሮጊት ናቸው)
.
ልጆቻቸው ጋር ሲሔዱ ቅላታቸውን እና ክብራቸውን የሚፈታተን ከሰል መሸጥ አይችሉም። ከሰል መሸጥ እናት ማውረድ መስሏቸው። የዋህነታችን!
.
.
6. ትረባ
ትረባ አስለምጃቸው ነበር። የተለመደ ሰላምታቸው ሲያሰለቸኝ የፈጠርኩት መላ ናት። ለተፈሳው ለተገሳሁ ሁሉ ሊመክሩኝ ሲሞክሩ ቤት ገብቼ መሀል ጣት እስከማውጣት ስፈተን ትረባ አስለመድኳቸው።
.
"ምንስለሆኑ ነው እርሶ ሚካኤልን የማያስገቡት" ሙስሊም ናቸውና ይቀኑ ይሆናል ነጭ የለበሱ ጎረቤቶቻቸው ግቢውን አስታቅፈዋቸው ሲጠፉ። ሳቁ አይገልጸውም ፈነዱ! የወለቀ ሶስት ጥርሳቸው ፊት ሻሻቸውን ሳይጎትቱ። ተመልሰው ለመጡ አንጋሽ ጎረቤቶቻቸው እያወሯት ሰላምታቸውን አረዘሙ።
.
በቀደም ከውጪ ሲገቡ አይቼ..
"ከየት ነው?" ስላቸው ገቡልኝ
" ወክ ወጥቼ። ጠበስኩኮ!" 😂😂
ኦቲስቲኩ በሀይሉ ከውስጤ ምን ይላል...
"እንዴ በስተርጅና" ግም!
አፌ " መቼ ነው የሚያስተዋውቁን?"
አፋቸውን አፍነው 🤭 " በል አልችልህም ውጣልኝ"
.
ከሗላዬ...
"ሰላም ይመልስህ በል! ደና እደር..."
መቼም አመል ቶሎ አይለቅ።
.
እኚ ናቸው የሔዱት።

#በሃይሉ_ሙሉጌታ

@wegoch
‹‹አልተበላሸም››


÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷
1989 ዓ.ም.



አስራ ስድስት ዓመቷ ነበር፡፡ የአስረኛ ክፍል ተማሪ ነበረች፡፡ ድርስ ነፍሠ ጡር ነበረች፡፡



የልጇ አባት (የልጅሽ አባት ሲባል ደስ አይላትም፡፡ ያስረገዘኝ  ወንድ በሉ ትላለች) የሰባት ወር ቦይፍሬንዷ ነበር፡፡ ማርገዟን እንደሰማ ብን ብሎ ጠፋ፡፡



ለመጀመሪያ ጊዜ ያፈቀረችው ወንድ ነበር፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ የሳማት፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰውነቷን የሰጠችው፡፡ 



ከብዙ ማባበል በኋላ ስትለምደውና ስትወደው በአንዱ ቀን እንዲህ አላት፤
‹‹አጎቴ ተከራይቶ የሚኖርበት ቤት እዚሁ ቤላ ጋር ነው፡፡ ለስራ ሐረር ሲሄድ ቁልፍ ሰጥቶኛል፡፡ ለምን እዚያ ሄደን በነጻነት ስናወራ አንውልም?››

‹‹አጎቴ ቤት ልወስድሽና ድንግልናሽን ልወሰደው ›› የሚል ወንድ የለ መቼስ፡፡ 



እጁን ይዛ ተከተለችው፡፡  የአጎቱ አንድ ክፍል ቤት በአግባቡ ከተነጠፈ ፍራሽ፣ ከብዙ መፅሐፍትና ከትልቅ ቴፕና አጠገቡ ከተዘረገፉ ካሴቶች በስተቀር ዐይን የሚገባ ነገር አልነበራትም፡፡



ፍራሹ ላይ አደላድሎ እንዳስቀመጣት ሰንደል ለኮሰ፡፡

‹‹ዘና እንድንል ነው፡፡ በዚያ ላይ ቤቱ ተዘግቶ ስለዋለ ይናፈስ ብዬ ነው›› ብሎ፡፡ 

‹‹ሰንደል በየት ሃገር ነው የታፈነ ቤት የሚያናፍሰው..?ይልቅ ለምን መስኮቷን አትከፍታትም?›› አላለችውም፡፡


‹‹አጎቴ ሙዚቃ በሃይል ይወዳል፡፡ የወጣ ካሴት አያመልጠውም፡፡ ቆይ ሰሞኑን የወጣ የፍቅራዲስ ካሴት አለ፡፡ እሱን ልክፈተው ለሙድ›› አላት ቀጥሎ፡፡
ለሙድ፡፡



ምንም አላለችውም፡፡


ከዚያ….



ፍቅርአዲስ ቤቱን በአስረቅራቂ ድምፅዋ ስትሞላው የእሱ ከንፈሮች አንገቷ ላይ ነበሩ፡፡


ሰላማዊት ተነክታ የማታውቀው ቦታ ስትነካ ፍቅርአዲስ አትርሳኝ እያለች በሚያባብል ድምፅዋ ታለቃቅስ ነበር፡፡

ፍቅርአዲስ ፣
‹‹ሄደሃል አሉ ብዙ ርቀህ እንደኔ ሆነህ አንተም ናፍቀህ
ምናለ ሆዴ ብትመጣልኝ ብታስብልኝ››  ብላ ስትለማመጥ
‹‹እንዲመችሽ ጃኬትሽን አውልቂው›› ብሎ እየተለማመጣት ነበር፡፡

በስልምልም ዐይኖቹ ሲለማመናት፣ በምትወደው ድምፁ ሲያባብላት ታዘዘችለት፡፡



በዚያ ላይ ቀኑን ሙሉ እህል አልበላችም ነበር፡፡ ከምሳ በፊት አስፎርፏት ስትወጣ ምሳቃዋን ረስታ፡፡
ሲገቡ ከሱቅ ካስመጣላት ሙቅ ሚሪንዳ በቀር ሆዷ ባዶ ነበር፡፡ 
እንደማቅለሽለሽ እያላት ነበር፡፡

እስከዛሬ ድረስ ሙቅ ለስላሳ አልጠጣም ብላ ስትከላከል ብዙ ሰዎች ‹‹ብርድ አይደል…ምን ማለትሽ ነው?›› ሲሏት አታብራራም፡፡ ግን ካልቀዘቀዘ ለስላሳ፣ በተለይ ሚሪንዳ አትነካም፡፡


እስከዛሬ ድረስ ፍቅርአዲስን ስትሰማ ዐይኖቿ በእምባ ይሞላሉ፡፡  ምን ሆንሽ ብሎ የሚጠይቃት ሲኖር መልሷ አንድ ነው፡፡

‹‹ድምጽዋ ደስ ስለሚለኝ ነው››
ግን ውሸቷን ነው፡፡ ፍቅርአዲስ በአትርሳኝ ሙዚቃ አጃቢነት በአንዲት ቀን አስረግዞ የረሳት የመጀመሪያ ቦይፍሬንዷን ስለምታስታውሳት ነው፡፡ ድምፅዋ ሃዘን የሃዘን በረዶ ያወርድባታል፡፡



ከሶስት ወራት በኋላ የኮከበ ፅባህን ግምብ ተደግፈው እያወሩ ‹‹አርግዣለሁ›› ስትለው አመዱ የጨሰው ሳሙኤል ብን ብሎ ጠፋ፡፡

ምስጢረኛ ጓደኞቿ ‹‹ድሮስ ከቅምቢቢት ዱርዬ ምን ይጠበቃል?›› ብለው አብረዋት አለቀሱ፡፡

አማራጭ ስላልነበራት ቤት ሄዳ የሆነችውን ስትናገር አባቷ ያለችውን የሰሙበትን ጆሯቸውን ማስቆረጥ ቢችሉ ደስ ይላቸው ነበር፡፡ እናቷም ከአንግዲህ ዐይኔ እንዳያይሽ አለቻት፡፡



ልብሷን ሸክፋ ወደ ብቸኛ መሸሸጊያዋ - ወደምትወዳት አክስቷ- ከመሄዷ በፊት ግን እናቷ ለሚቀጥሉት ሃያ አመታት ላትዘነጋው የወሰነችውን ነገር ተናገረቻት፡፡

‹‹ሕይወትሽን ጨርሰሽ አበላሽተሽዋል፡፡ ከእንግዲህ የትም አትደርሺም›› ብላ፡፡



እርግዝናዋ የኮከበጽባህ ትምህርት ቤት ርእሰ ሃሜት ሆኖ ቢከርምም በአክስቷ ፍቅርና ማበረታቻ ተደግፋ አስረኛ ክፍልን ከገፋ ሆዷ ጋር አገባደደችና ሰኔ 12/1989 ልጇን ወለደች፡፡


ሚካኤሏ አለቻት፡፡ የሰኔ ሚካኤል ልጅ ስለሆነች፡፡

አክስቷ ጥላ፣ አክስቷ ግድግዳና ማገር ሆናላት ሚካኤላን ከልጆቿ ጋር ስታሳድግላት መራር የእናቷን የእርግማን ቃል እንደምታመክን ቃል አስገብታት ነበር፡፡


‹‹ዛሬ ተሳስተሻል ማለት እስከወዲያኛው ሕይወትሽ ተበላሽቷል ማለት አይደለም፡፡ ይሄን እውነት ኖረሽ ካሳየሽኝ ልፋቴን ካስሽው ማለት ነው›› ብላ  የልጅነትእኩያ ልጇን ከጎኗ፣ የሰላማዊትን ጨቅላ በእቅፏ አድርጋ ስትመክራት ጉልበት ሆናት ነበር፡፡






ጥር 2016

የአርባ አራት ዐመቷ ሰላማዊት ከሃያ ስድስት ዐመት እኩያ ልጇ ሚካኤሏ ጋር እስክስታ ትወርዳለች፡፡
የሚካኤሏ ሰርግ ነው፡፡

በቅርበት የማያውቃቸው ሰው ሁሉ ደጋግሞ እንዲህ ይላል፡፡

ቀልዳችሁን ነው…እናቷ ልትሆን አትችልም፡፡ ታናሽ እህቷ ናት!
አይሆንም!
እውይ ደስ ሲሉ!
ታድለው!

ትንሽ ቆይቶ፣
ጭፈራው አድክሟት በሚዜና አጃቢዎቿ ታጅባ ከአዲሱ ባሏ ጋር የምትጨፍረውን ሙሽራ ልጇን እያየች ቁጭ ያለችው የሙሽሪት እናት ሙቅ ሚሪንዳዋን እየጠጣች ለራሷ-
‹‹ምንም የተበላሸ ነገር የለም፡፡ ሁሉም ነገር ግሩም ነው›› አለችና፤

ወዲያው በሰዎች ምርጫ ሙዚቃ ወደሚያጫውተው ዲጄ ለመሄድ ወሰነች፡፡


‹‹የፍቅርአዲስ ዘፈን ይኖረው ይሆን?›› ብላ እያሰበች፡፡

By Hiwot Emishaw

@wegoch
@wegoch
@paappii
ብ-ት-ን-ት-ን
-----------------------



ወላጆቼና አያቴ የጎረቤቶቻቸው ቤት ዘወትር በቦምብ እየተደበደበ፣ ጥይት እንደ ወፍ በጣራቸው ላይ እየበረረ ከዚህ ቦታ ሽሹ ብላቸውም አንገታችን ይታረዳል አሉ፡፡



ይሄ የወንድማማቾች ጦርነት ከተጀመረ አንስቶ ነጋ ጠባ ቀብር ላይ ናቸው፡፡ ባለፉት ጥቂት ወራት ማህበርተኞቻቸውን፣ አብሮ አደጎቻቸውን፣ ጎረቤቶቻቸውን፣ ዘመድ ወዳጆቻቸውን በየተራ፣ በሰልፍ ቀብረዋል፡፡ 



ትላንት ማታ ራሱ ወይዘሮ ታየች- የእማዬ የሴት ማህበር አጣጭ፣ የስንት ዘመን ባልንጀራና የታናሽ እህቴ የክርስትና እናት በሯ ላይ ተገድላ ተገኘች፡፡  ተባራሪ ጥይት ነው አሉ፡፡



‹‹በፈጠራችሁ ተለመኑኝ! አሁንም ከዚህ ሳይብስ ከዚህ እንሂድ›› ብዬ ተለማመጥኳቸው፡፡ ዛሬ ልመናዬ ውሃ ቢያነሳ ብዬ የደብራችንን ቄስ ለምኜ ይዤ መጥቻለሁ፡፡ አጠገቤ ቆመዋል፡፡



ካልሄድን ብዬ ልማለድ ስመጣ ይሄ አራተኛዬ ጊዜዬ ነው፡፡ ብዙ ሳትርቅ የምትገኘው ከተማ ውስጥ አነስተኛ አንድ ክፍል ቤት ተከራይቼ እኖራለሁ፡፡ ደልቃቃ ቤት አይደለችም ግን ቢያንስ ከጦር ሜዳው ሩቅ ናት፡፡



‹‹ልጄ! ቤታችን እዚህ ነው፡፡ ቀያችን ይሄ ነው፡፡ የት ነው ጥለነው የምንሄደው…?ለማን ጥለነው ነው የምንሄደው…? ጎጇችን ምን ይሆናል…እንስሶቻችንስ ማን ይይዝልናል?››  ብለው እንደ ሁልጊዜው አፍ አፌን አሉኝ፡፡




ቄሱ እምብዛም አላገዙኝም፡፡ ‘አረ እባክዎ እርዱኝ ! ›› ብዬ ብጠይቃቸው ይባስ ብለው፤
‹‹ተያቸው በቃ!  እንደ ፈቀዳቸው ይሁኑ፡፡ እዚሁ ይቆዩ›› አሉ፡፡
‹‹አባ! እዚህ ቆይተው ይሙቱ ነው የሚሉት?›› ብዬ እንደ መጮህ አደረገኝ፡፡ እማዬ አፍታም ሳትቆይ ቄሱን ልቆጣ በመድፈሬ ክፉኛ ተቆጣችኝ፡፡



ወዲያው ደግሞ ሁሉ ነገር ሰላም ይመስል ራት ሰርታ አብልታን ‹‹በይ አንቺ ነገ በጠዋት ወደ ሃገርሽ…ነገር ሳይጋጋል›› አለችኝ፡፡


እኔ እንድሄድ ይፈልጋሉ፡፡ እኔ እንዳልጎዳ ይፈልጋሉ፡፡


የአብዛኞቹ ከመንደሩ ወጥተው ከተማ የሚገኙ እኩዮቼ እጣ ፈንታ እንደሚደርሰኝ አውቀው ነበር፡፡ አንዱን ቀን ተደውሎ ቤታችሁ ጋዬ፣ እናት አባትሽ፣ አያትሽ ተገደሉ እንደምባል አውቀው ነበር፡፡


የእኔም ቤተሰቦች ተራ አሃዝ እንደሚሆኑ ልቦናዬ ያውቀው ነበር፡፡



ለመጨረሻ ልመናዬ ከመጣሁ ሳምንት እንኳን ሳይሞላኝ እንደማይቀርልኝ ያወቅሁትን መርዶ ተረዳሁ፡፡  ቤታችሁ በመትረየስ ተመቷል አሉኝ፡፡ እናትሽም.፣ አባትሽም፣ አያትሽም ሞተዋል አሉኝ፡፡



ከቀናት  ለቅሶ በኋላ ነገር ተረጋግቷል ሲባል እኔና ታላቅ ወንድሜ አውቶቢስ ይዘን ወደ ድሮ ቤታችን ተጓዝን፡፡


አይ ቤታችን እቴ! ቤታችን ወደነበረበት ባዶ ሜዳ ብል ይቀላል፡፡

ማልቀሱንስ ሳለቅስ ነው የከረምኩት፡፡



ነገር ግን እማዬ አባዬ እንደነገሩ አጣጥሮላት እንደ ጭስ ቤት የምትጠቀምበት ቦታ ላይ ያ የምወደውን ምስር ወጥ የምትሰራበት ሸክላ ድስት ብትንትን ብሎ ሳየው ግን ለአባባይ እስካስቸግር ማንባት ጀመርኩ፡፡



እኔ ልበታተንልሽ አባዬ፡፡  እኔ ብትንትን ልበል የኔ ዓለም፡፡

@wegoch
@wegoch
@paappii

By Hiwot emishaw
2024/09/21 10:48:39
Back to Top
HTML Embed Code: