Telegram Web Link
"በፈጠረህ ይዤሀለሁ ትልቁ...በፈጠረህ....የምትወዳት ከሆነ 'በ ዳኋት' አትበለኝ በቃ።"
"እኔ እኮ እንዲህ አይነት ነገር መስማት ትወዳለህ ብዬ ነው ስከንፍ ወዳንተ የመጣሁት።"
"እውነት ነው እወዳለሁ። የምትወዳት ከሆነ ግን 'ተኛን' ወይ 'ወሲብ ፈፀምን' በለኝ። ያው ያደግነው ከሬዲዮ ስር አይደል?! ንግግርህ አዕምሮዬ ላይ ቁልጭ ያለ ምስል መፍጠሩ አይቀርም። ያን ቃል በተጠቀምክ ቁጥር ሲገባ ና ሲወጣ ሁሉ ይታዬኛል..."

"ህክምና ያስፈልግሀል አንተ!"

"ተው አልኩህ...አልሰማ አልከኝ...ምን ልበልህ?...በዛ ላይ ብዙዬ እኮ የሁለታችንም አብሮአደግ ነች። ለሌላ ሴት የምትጠቀመውን ቃል ለሷም ስትጠቀመው ደስ አይልም።"
"ይቅርታ ግን እንደዚህ ተደስቼ ስለማላውቅ እኮ ነው። እንዲያውም ይሔንን ደስታ በግዕዝኛ ነበር... 'ፍስሀ...ሀሴት...ስርፀት' ምናምን በሚሉ ቃላቶች እየታጀቡ መግለፅ!"
"ኧረ ተረጋጋ"
"የምሬን ነው። ታውቃለሀ ከሷ በፊት ሴክስ እንደ ሴክስ አዝናንቶኝ እንደማያውቅ?"

"ምን ማለት ነው እሱ ደሞ?"

"በቃ መዋሰቡ አልነበረም የደስታዬ ምንጭ! ምኗን ስነካት ምን እንደምትሆን እያዬሁ በመገረም ብቻ ነበር ሌቱን የምገፋው። ልክ ቲቪ የመጣልን ሰሞን ሪሞቱን አንስተን አንዱን አንዱን እየነካካን ምኑ ምን እንደሆነ ለመረዳት ስንሞክር እንደነበረው ማለት ነው!"
"እእእ ገባኝ። ህእ!...ባይዘዌ...የመጀመሪያ ቀን ቀዩን ተጭነህ ስዊችድ ኦፍ ሲሆንብህ ደንግጠህ ከአክስታችን ቤት ያደርከውን ዛሬም ድረስ ባስታወስኩት ቁጥር ነው የምስቀው!"
"ሂሂ እጄ የማያርፈውን?...በዛ ሳምንት ብቻ አራቴ ነው ያበላሸሁት...ቡኃላ እንደዛ ሊሰለቸኝ ያን ያህል ሙጥኝ ማለቴ ይገርመኛል!"

"ለምንድን ነው ግን እንደዛ የሆንከው?"

"ምን የሆንኩት?"
"ማለቴ..ሁሌም የሆነን ነገር ስታገኝ ለመጎርጎር የምትጣደፈው? ሬዲዮኗንም እንዲሁ ነካክተህ ነካክተህ ሲበቃህ ጣልካት። ቲቪውንም እንደዛው። በቃ አንድን ነገር የምትወደው እስክታውቀው ብቻ ነዋ?!"
"ሂሂሂ ...... ብዙዬንም ነካክተህ ትጥላታለህ እያልከኝ ነዋ አንተ ሴታሴት?"

"ጂሰስ!!...የመስማት ነው የመረዳት ችግር ያለብህ?"
"ትንሹዬ...ካወቅኩት ቡኃላ ያልተውኩት አንድ አንተ ብቻ ነህ። 'ንዲህ አይነት ድብብቆሽ እኔ ላይ ደስ አይልም።"
"ስለምን መደባበቅ ነው የምታወራው?"

"ጠይቀሀት ነበራ ብዙዬን?"

"እንዴ? በጣም ድሮ እኮ ነው። የታችኛው ፀጉር ራሱ..."
"ጭገር?!"
"ስነስርዓት ይኑርህ እስኪ..."
"እሽ ምን እንበለው?"
"በቃ ተግባባን አይደል? የግድ እስከ አያቱ ድረስ መጠራት አለበት?"
"ቀጥል እሺ!"
"ብቻ እሱን ነገር ራሱ ገና አላበቀልኩም ነበር! እሺ ብትለኝ ምን ላደርጋት አስቤ እንደነበር እንኳን አላውቅም። ካጠገቤ ስላገኘኋት ብቻ ነው የጠዬቅኳት።"
"እንግዲያውስ ይቁረጥልህ ከእንግዲህ ስለሷ እንዳታስብ። አንዴ ተባድ ተናል እኛ!"
"አባቴ ይሙት ካሁን ቡኃላ ይሔን ቃል ከተጠቀምከው...."
"በድ ቻታለሁ.....ብ ድትድት አድርጌያታለሁ ምን ታመጣለህ እስኪ?!"

"አይይይይይይ እ!....ጌታን የምታሳዝን ሰው ነህ!!"

"እንዴዴ?....ምን እየሆንክ ነው?...ኧረ...ኧረ ውሀ መቋጠር ምናምን!! ልታለቅስ ነው? እና መጀመሪያውኑ እንደምትወዳት በግልፅ አትናገርም ነበር እንዴ?"
"አልወዳትም። አንተን ይንሳኝ አልወዳትም.....ኧህህህህህ!....ሁለት በጣም የምትቀርቡኝን ሰዎች አ'ምሮዬ ውስጥ እንደዛ ላስባችሁ ስለማልፈልግ ብቻ ነው...ok?! እንደ አባዬ እና እማዬ እናንተም አድርጋችሁት የማታውቁ እንዲመስለኝ ብቻ ነው ማሰብ የምፈልገው። የምለው ገብቶሀላ?"
"ማለት?! አባዬ እና እማዬም እኮ ይባ..!"
"እንዳትጨርሰው!"
"እሺ በቃ ይቅርታ!....ሆሆሆ!...ቆይ አንተ ግን እስከመቼ ነው እንደዚህ ከተግባሩ በላይ ቃሉን እየፈራህ የምትኖረው?"

"የሌለ ችግር ፈጥረህ አታውራ!"

"ኧረ ተው? መናገር የፈለግከውን ሁሉ እየተናገርኩልህ፤ መብላት የፈለግከውን 'አምሮኛል' እያልኩልህ ማደግህን ረሳኸው?...መልስልኝ እስኪ?!...ቆይ የምታስበውን ነገር 'እንዲህ አስቤያለሁ' ብሎ መናገር ለምንድን ነው ወንጀል የሚመስልህ? በተግባር እንዳንተ ክፉ የለም። አሁን ራሱ እድሉን ብታገኝ ብዙዬን ከኔ ነጥቀህ ታገባታለህ። ለአፍህ ግን የማይከብደው ነገር የለም።"

"ሁሉም እንዳንተ አይደለም ትልቁ። እንዲያውም እኔ ባንተ ቦታ ብሆንና የፍቅር ጥያቄ ጠይቀሀት እንደምታውቅ ብሰማ ኑሮ ከአጠገቧ ድርሽ አልልም ነበር። እንኳን ልጠይቃት!!"

"አታካብድ...ከበዳ...አይይይይ እ!....ግብረ ስጋ ግኑኝነት ከፈፀምን ቡኃላ ነው የነገረችኝ!"

"ሲጀመር እኔ እንደምወዳ...ማነው እንደጠየቅኳት የማያውቅ አንድም የሰፈር ሰው የለም።"
"አንድ እኔ አለሁ አልኩህ እንግዲህ..."
"ለማመን ይከብደኛል እሱን!"
"ያንተ ማመን እና አለማመን ምንም ትርጉም የለውም ትንሹ። ህይወት ለማመን በሚከብዱ ገጠመኞች የተሞላች ነች። እኔ ግን ህሊናዬ ንፁህ ነው።"
"ህሊናቸው ንፁህ በሆኑ እና ባልሆኑ ሰዎች መሀል ያለው ልዩነት ምን እንደሆነ ታውቃለህ?"
"ምን?"
"ንፁህ የሆኑት ሁሌም እንደቆሸሹ ነው የሚያስቡት። የቆሸሹት ደግሞ ፃድቅ እንደሆኑ!"

"ብ ዳታም ፓስተር! ከነ እውቀትህ ገደል ግባ እሺ። አሁንስ ይሔ ሾካካነትህ በጣም ነው ምርር ያለኝ!! እንዲያውም ለአንድ ለሁለት ሳምንት ላገኝህ አልፈልግም። ቻው!"

"ግዴለም አታስብ!!...ለሁለት ሳምንት ብቻ ሳይሆን ለሁለት አመት ያህል አታገኘኝም። ክፍለሀገር ስራ ልጀምር ነው።"
"ማ...ማለት...ክፍለሀገር የት?"
"ጂማ ዩንቨርስቲ!"
"አንተተተተተ ውሻ!!! አውቀሀለሁ ውሻ ነህ ማሪያምን!!"

"ምንድን ነው የሚያስጮህህ? እስኪ ተረጋጋና አውራኝ?"
"እጄን ምታ? እስኪ 'አባቴ ይሙት...ብዙዬ ጅማ ስራ መጀመሯን አላውቅም' በለኝ!!"
"በእየሱስ ስም?! የምርህን ነው?..."

"ሌላ ምንም አትበል። አላውቅም ነበር ብለህ አንዴ ብቻ ማልልኝ። ከዛ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከህይወትህ ወጥቼ እሔድልሀለሁ።"

"ለኔም እኮ ማወራረድ ከበደኝ የሰማሁትን ነገር!"
"ማልልኝ አልኩህ!!".
"እሺ አትጩህ! ይሔው በአባቴም በእናቴም ስም እምላለሁ አላውቅም ነበር።.....እህህህህህ...ምንድን ነው እንደዚህ የምታፈጥብኝ? ጌታን አላውቅም አልኩህ......እንዴዴዴዴ ኧረ አይንህን ንቀል ሰውዬ!!.......እንደዛ ከተሰማህ ወይ ስራው ያምልጠኝ በቃ...መቅረትም እኮ እችላለሁ..."

"አያይ...አያስፈልግም እሱማ።....እንደው ነገሩን ተራ መገጣጠም ነው ብዬ ለማመን ትንሽ ስለከበደኝ ብቻ ነው!!"

"ያንተ ማመንና አለማመን ምን ትርጉም አለው ትልቁ? ህይወት እንደሁ ለማመን በሚከብዱ ገጠመኞች የተሞላች ነች። እኔ ግን ህሊናዬ ንፁህ ነው።"

"👀"

(ርዕስ:- ቃዬል እና ቃዬል)

@wegoch
@wegoch
@paappii

By mickel Azmeraw
ኤየር ባስ 380 የተባለው ግዙፍ አይሮፕላን በመቶዎች የሚቆጠር ተሳፋሪዎችን ጭኖ በ800 ኪሎ ሜትር በሰአት ፍጥነት 30,000 ጫማ ከፍታ ላይ እየበረረ ነው

ከየት መጣ በሚያስብል ፍጥነት ደግሞ የተዋጊ ጄት ከጎኑ ተከሰተ - ከትልቁ አውሮፕላን ትይዩ ሆኖ በመገናኛ ሬዲዮ የትልቁን አይሮፕላን ፓይለት አገኘው

"ኤየር ባስ 380 መንዳት ድብርትን የሚያጭር ይመስለኛል"

የትልቁ አውሮፕላን ፓይለት አልመለሰለትም

"እስኪ አሁን የማደርገውን አዝናኝ ትርኢት ተመልከት” ብሎ የሚያበረውን ጄት በጀርባው በመገልበጥ በብርሃን ፍጥነት ወደ ሰማይ ሽቅብ ወጥቶ እየተገለባበጠ ወደ ምድር ተምዘግዝጎ በድጋሚ በቄንጠኛ ሁኔታ ፍጥነቱን ጨምሮ ወደ ላይ ተምዘግዝጎ ከትልቁ አውሮፕላን ጎን ቆመ

"እንዴት ነበር ትርኢቱ?" በድጋሚ በሬድዮ ጠየቀው

"በጣም አስደናቂ ነበር! እስኪ የእኔን ደግሞ ላሳይህ" ብሎት ሬድዮኑን ዘጋው

የጄቱ አብራሪ ቢጠብቅ ቢጠብቅ ምንም የለም

ከ15 ደቂቃ በኃላ የትልቁ አውሮፕላን አብራሪ ተመልሶ መጥቶ "እንዴት አየኸው?" ብሎ ጠየቀው

"ምኑን? ምን አደረግክ?" የጄቱ አብራሪ ጠየቀው

"ከወንበሬ ተነስቼ እግሮቼን አፍታትቼ ወደ አውሮፕላኑ የኃላ ክፍል ሄጄ ተሳፋሪዎቹን ሰላም ብዬ ሽንት ቤት ተጠቀምኩኝ:: በዚያውም ደግሞ ቡና እና የቸኮሌት ኬክ ይዤ ተመለስኩኝ" 🤷🏽‍♂️🤷🏽‍♂️

👇🏾

ወጣት እያለህ ፍጥነት: ስሜት: ለመታየት መቅበዝበዝ እና ተቀባይነት ለማግኘት መጋጋጥ ያለ ነው

እድሜህ ሲገፋ እና ህይወት ሲገባህ ግን ምቾት: ሰላም እና እርግት ስክን ማለት ትልቁ መገለጫህ ሊሆን ይገባል

@wegoch
@wegoch
@paappii

By zemelak endris
የነዳጅ ነገር

ወገን ሰሞኑን መገናኛ አካባቢ ሄዳችዃል? ድልድዩ ስር ክራር ይዘው የሚለምኑ ባለተሰጥኦ ለማኞች አልበዙባችሁም? የኑሮ ውድነቱና የነዳጅ ዋጋው በዚሁ ከቀጠለ ዋሽንትና ከበሮ ይዘን የምንቀላቀላቸው ብዙ ወገኖች እንኖራለንና የሙዚቃ መሳሪያ ገዝቶ መዘጋጀቱ ይበጃል።

እኛ ስንቀላቀላቸው ልመናው በሙሉ ባንድ ይታጀባል። ቢያንስ ቢያንስ ምፅዋት ሰጪ "እስኪ ያሁኗን ልመና ድምፅህን ወረድ አደርገህ ድገምልኝ፤ በሙዚቃ መሳሪያ ብቻ ለምነኝ" እያለ ዘና ብሎ መመፅወት አለበት። 32 ቁጥር አውቶቡስን የሚጠብቁ የኮተቤ ነዋሪዎችም ባሷ እስክትመጣ ነገር እየበሉ በባንድ የታጀበውን ልመና እየሰሙ ቢቆዩ ይመርጣሉ።

I came from the future ብዬ አልሰክሳችሁም ከላይ የፃፍኩት ቀልድ አይደለም በቅርቡ በሰፊው የምንመለከተውና ብዙሃኑ ህዝብ ደግሞ የተመለከተው እውነታ ነው። የነገውን የኢትዮጵያ ገበያ ለመገመት Time traveller መሆን አይጠበቅንም። ከባዱ ነገር ኑሮ ከበደኝ እንኳን ብትል የሚሰማህ የለም። ከወራት በፊት መንግስት ለነዳጅ እሰጥ የነበረው ድጎማ ካዝናዬን ስለጎዳው አቁሜያለሁ ሲል ኢኮኖሚስቱ ሙሼ ሰሙ መንግስት ድጎማ ማድረግ ከበደኝ ካለ ህዝብስ በምን አቅሙ ሊሸከመው ይችላል ብሎ ጠይቆ ነበር። መልስ የሰጠው የለም። መንግስት ዝርዝር ሳይዝ ነው የሚንቀሳቀሰው መሰለኝ ብዙ ጊዜ መልስ አይሰጥም።

ወዳጆች ከዚህ ቀደም እንዳልኳቹህ ኑሮ ውድነቱ በዚህ ስለሚቀጥል ግሮሰሪ ገብቶ ከለር ፕሪንት አላቹህ ብሎ የሚጠይቅ ተማሪ፣ ወደገበያ ሲሄድ ወታደራዊ አሸኛኘት የሚደረግለት ሸማች፣ ሽንኩርት ገዝቶ ወደቤቱ ሲገባ የታየ አባወራ "የሽንኩርቱ ጌታ" ተብሎ ሲዘፈንለት መስማታችን አይቀርም። እኔ ለቅድመ ዝግጅት 1 ኪሎ ሩዝ ምን ያህል ፍሬ እንዳለው ጎግልን መረጃ እየጠየቅኩ ነው። ከዛ ቆጥረህ ትቅላለህ፤ 12 ፍሬ ለቁርስ 12 ፍሬ ለምሳ ለመተኛት እንኳን መመገብ አያስፈልግም።

@wegoch
@wegoch
@paappii

By yihune Ephrem
ደባሌ ነች። የስራ ባልደረባዬም ነች። አብረን ነው የምንውለው። አብረን ነው የምናመሸው። የምንለያዬው....ለመኝታ ብቻ ነው። "አትሰለችህም ወይ?" ይለኛል ጓደኛዬ። ስንተኛም የማንለያይበትን መንገድ ለማግኘት እየጣርኩ እንደሆነ አያውቅም።

እንደምወዳት እኮ ልነግራት ነበር። ግን ድንገት ስለምትፈልገው የወንድ አይነት ስታብራራ ሰምቼ ጉሮሮዬ ተዘጋብኝ። ፀጥ አልኩ። ውሸት ምን ያደርጋል? መስፈርቷ ውስጥ በከፊል እንኳን የለሁም። ድሮ ድሮ ኮራጅ ተማሪዎች ጎበዝ ተማሪ ሲያጡ ከሰነፉ ላይ ይኮርጁ ነበር...እሱ "True" ሲል እነሱ "False" እያሉ...እሷም መስፈርቷን ያወጣችው እንዲህ እያደረገች ሳይሆን አይቀርም....እኔ ስስ ስሆንባት "ደንዳና"...እኔ ፀይም ስሆንባት "ደማቅ ቀይ" እያለች!

አንዳንዴ እንደዚህ ነው...የማይፈልጉት ነገር መሆንህን የሚሳውቁህ ስለሚፈልጉት ነገር እያወሩ ነው።

ስለዚህ በዝምታ መውደዴን ቀጠልኩ። መውደዴን ያልተውኩት ሞኝ ስለሆንኩ አይደለም። መውደዴን ያልተውኩት እሷ ያስቀመጠችውን መስፈርት የሚያሟላ አንድም ወንድ እንደማታገኝ ስለማውቅ ነው።
አውቃለሁ አለም እንደኔ ባሉ መካከለኛ ሰወች የተሞላች እንደሆነች። አውቃለሁ ህይወት ኮርኩማ ኮርኩማ ስታንዳርዷን እንደምታወርድባት። ከኔ የሚጠበቀው ያ ቀን እስኪመጣ ድረስ ከስሯ ሳልጠፋ መቆዬት ብቻ ነው።

የሴት ጓደኛም የላትም። ረጅም ስለሆነች ከነሱ ጋ ስትቆም ቀውላላ ያስመስሏታል። ስለዚህ እኔ እኩያዋ ጋ መሔድን ትመርጣለች። "እንደዚህ ረጅም ሴት ወይ ከአማልክቱ ወገን ነች...ወይ በስህተት ሴት ሁና የተፈጠረች ወንድ ነች!" ይላል ጓደኛዬ። እስማማለሁ በአባባሉ። በስህተት ሴት ሁና የተፈጠረች ወንድ እንዳልሆነችም አውቃለሁ።

ማታ ማታ የሆነ ቲቪ ሸው እናያለን። ትንሽ እንዳዬን እናቋርጠውና "Grey Anatomy" የሚለውን ተከታታይ ድራማ ለአስረኛ ጊዜ እንጀምረዋለን። ወይ "Friends" እናያለን። ጓደኛማቾቹ ሲሳሳሙ ዞር ብዬ አያታለሁ። እሷ ግን አታዬኝም። መልሼ እዞራለሁ።

ታዲያ ሁኔታችንን ሁሉ የሚገርመው የስራ ባልደረባችን "እንደኛ ባለትዳር ለመባል እኮ በሶስት ወር አንዴ ሴክስ ማድረግ ነው የቀራችሁ" እያለ ሙድ ይይዛል። ቀልዱ ቀልድ ነው እኔ ግን.... "ሜሪ" ብዬ ለሌላ ነገር በጠራኋት ቁጥር...በዛው "ሜሪ ሚ?" ብዬ ልንበረከክላት የሚያምረኝ ቀን ጥቂት አይደለም።

እሱም ነው ትልቁ ፍርሀቴ። የሆነ ቀን ኩሽና ውስጥ፣ ወይ ፊልም ስናይ፣ ወይ የሆነ ሒሳብ ሳስረዳት፣ ወይ ስለምናዬው ድራማ ስታብራራልኝ...ድንገት ደፍሬ እስማታለሁ። ከዛ ትክ ብላ ታዬኝና ተነስታ ወደ ከፍሏ ትገባለች። ዘግታኝ ልትውል ነው ብዬ ስጨናነቅ ተመልሶ በሯ ይከፈታል። ከዛ እንደገና ልትስመኝ ነው ብዬ መጓጓት ስጀምር በአንደኛው እጇ ሻንጣዋንም ይዛ እየወጣች ነው። በስማም!!.....ላብ በላብ ሁኜ ከእንቅልፌ እነሳለሁ። "ህልም እልም" "ህልም እልም" ብዬ አማትቤ እተኛለሁ።

ተይዣለሁ። ተይዣለሁ በጣም። በርግጥ እስከ ምን ድረስ እንደተያዝኩ ያወቅኩት አንድ ቀን አሟት ቀርታ ቢሮ ብቻዬን የሔድኩ ዕለት ነው።  "አንቺ ስትሔጅ ስንቶች ተጋለጡ" የሚለው የአብርሽ ግጥም እንዳዲስ ትርጉም ሲሰጠኝ ዋለ!
ከቤት እስከ ቢሮው ያለው መንገድ ለካስ እንደዚህ ሩቅ ነበር?! ምን ብርታት ሰጥቶን ነው በ'ግራችን ስንመላለስበት የከረምነው?
ለካስ ስራዬን እጠላዋለሁ!! አለቃዬስ ምንድን ነው እንዲህ የሚያስጮኸው? ቢሯችን ለምንድን ነው ሆስፒታል ሆስፒታል የሚሸተው? ሰራተኛው ሁሉ ለምንድን ነው የማያስቅ ቀልድ የሚቀልደው?
ከተማው ላይስ መቼ ነው ሰው እንደዚህ የበዛው? ሮፍናንን ማነው ዘፋኝ ያደረገው? ፀሀዩዋ እንዴት እንዴት ነው የሚሰራራት?

የምወደው ነገር ሁሉ አስጠላኝ። የምጠላውን ሁሉ ማጥፋት አማረኝ። ይሔን ሁሉ ሁኘ ምርር ብሎኝ ሰዓቱን ሳዬው ደግሞ ገና አራት ተኩል እያለ ነው። በርግጥ ሀያ ደቃቃ ይቀረዋል ለተኩልም። ራሴን አመመኝ። ስራውን ትቼው ወደቤት ተመለስኩ።

በሩን ከፍቼ ስገባ...!

ሜሮን በድንጋጤ ከላዩዋ ላይ ያለውን ወንድ ገፍትራው ተነስታ ቆመች። አይኔን ማዬት ከብዷት ተሸማቅቃ አንገቷን ሰበረች። እኔም የሰማኒያ ሚስቴ ስትማግጥብኝ የያዝኳት ያህል ግርጥት ብዬ ዝም አልኩ። ከተወሰነ መፋጠጥ ቡኃላ ነበር ሚስቴ አለመሆኗ ትዝ ያለኝ። ብንን ብዬ ይቅርታ ጠይቄያቸው ተመልሼ ልወጣ ስል ሩጣ እጄን ያዘችው።  "ምነው?" አልኩ ድምፄ እንዳይንቀጠቀጥ እየተጠነቀቅኩ።

"ጊዜ ማሳለፊያ መስሎህ እንዳትቀዬመኝ" ብላ ጀመረች!...እጆቿን እያፍተለተለች...."ያው ነገሩ ትንሽ ሲሪዬስ እስኪሆን ደብቄህ ነው እንጂ...ስመኘው የኖርኩትን ልጅ'ኮ  አግኝቸዋለሁ!" አለችና በፈገግታ አዬችኝ። ከልቧ ደስ እንዳላት ታስታውቃለች። ሁኔታዋም ለሚወዳት ልጅ ሳይሆን ለታላቅ ወንድሟ እንደምትነግር...ሀፍረት እና ኩራት የተቀላቀለበት ነው። አይኖቿ የደስታ እንባ አቅርረዋል። እርግጠኛ ሆናለች። የኔም አይኖች ረጠቡ።
አንዳንዴ ደግሞ እንደዚህ ይሆናል....የምስራቻቸው ውስጥ መርዶህን ትሰማለህ!

By michel Azmeraw

@wegoch
@wegoch
@paappii
“እኔኮ አፌ እንጂ ልቤ ንጹሕ ነው…” የምንል ብዙዎች ነን —ጀብድ እንደኾነ ነገር፤ መርዘኛ ምላስ ከክፉ ልብ ይቀልል ይመስል ነገር።

“እኔ ሲፈጥረኝም መደባበቅ አላውቅም፣ ሲፈጥረኝም ግልጽ ግልጹን ነው የማወራው” እያልን ሰው የምናቆስል አለን። ግልጽነትን መረን ከመኾን ለመለየት ዕድሜና ብስለት ያልሰጠን —ስናሳዝን።

ሰው ግን በልቡ ከሞላው በቀር በአፉ ሊወጣ የሚችል ምንም ነገር የለም —ሐቅ ነው። እርግጥ ነው አንዳንዴ ሰው በብስጭት ከአፉ ያልተገቡ ቃላት ሊወጡ ይችላሉ። ደጋግሞ ደጋግሞ የታቀደ በሚመስል መልኩ ሰውን የሚሰብር ሰው ግን “እኔም ሰው ነኝ” ብሎ ሊመሳሰል አይችልም።

“ይቅርታ” ማጣፊያው ሲያጥረን የምንመዘው ራስን የመከላከያ መሣሪያ አይደለም። “ይቅርታ” ማለት ድጋሚ ያንን ጥፋት ላለማድረግ መወሰን እንጂ፤ “የቀደመ ጥፋቴን እርሱልኝ” የሚል የብልጣ ብልጦች ይግባኝ ሊኾን አይገባም። ብዙዎች ግን ያለ ምንም ማመዛዘን ከአፋቸው አጥንትን የሚሰብር ቃል እያወጡ ደግመው ደግመው “ይቅርታ” በማለት የቃሉን ጉልበት ይፈትናሉ።

ይቅርታ” ማለት ግን “ቀጣይ በደንብ አስቤ አወራለኹ” ማለት ጭምር ነው። ይቅርታ ማለት ግን “ቀጣይ በቂ መረጃ ሳይኖረኝ አላወራም” ማለት ጭምር ነው። ይቅርታ ማለት ግን “የማወራው ነገር የሚያመጣውን ቅጣትና ወቀሳ ሙሉ ለሙሉ እቀበላለኹ” ማለት ነው። ካልኾነ ግን “ይቅርታ” የፍቅር መግለጫ፣ የሕግ ፍጻሜ የኾነውን ያሕል … የመሠሪዎች መሹለኪያ የማርያም መንገድ ኾኖ ይቀጥላል።
————————————

@wegoch
@wegoch
@paappii

By Henock Bekele
ፍቅር ይሞታል
*

ፍቅር እንደ ሰው ልጅ ይጸነሳል፣ ይወለዳል፣ ያድጋል፣ ይሞታል። በህይወት ውስጥ ይኼን ዑደት ከውኖት ያልፋል። ምናልባት መች እንደሚሞት ማን እንደሚገድለው ይሆናል ማይታወቀው። ከመሞት እጣ ፈንታው ግን አፈንግጦ ነጻ መውጣት አይችልም።

ልብ የፍቅርን ዘር በጉያው ሸጉጦ ሊያጸድቅ ይነሳል። ዘር ሁሉ ማረፊያው የተለያየ ስፍራ እንደሆነ ሁሉ ፍቅርን የተሸከመ የልብ ማህጸንም መክተሚያው ይለያያል።

በመንገድ ላይ የተበተነ ዘር አፈር እንኳ በቅጡ ሳይለብስ በእንጭጩ በወፍ አፍ እድገቱን እንደሚቀጭ ሁሉ፤ አንዳንድ ፍቅርም ገና እንዳልተወለደ ጽንስ በልብ ማህጸን ውስጥ ሳያቆጠቁጥ አፈር ድሜ ይበላል። ሳይዙት ይተናል። ሳይጨብጡት ይበተናል።

አንዳንድ ፍቅር የታጨው ሳይጀምር ለማለቅ ነው። ሳይወለድ እንደመውረድ። ልብህ ለሽንፈት ዘነፍ ማለት በጀመረበት ወቅት ብዙ ምክንያቶች የእድገት ጸር ወፍ ሁነው ይለቃቅሙታል። ድንገት አይተኃት ልብህ እየተንፈራገጠች ወደ መውደድ ባህር ልትደፍቅህ ስታብሰለስል...

ምታፈቅረው ሰው፣ ባል፣ ትዳር፣ ልጆች እንዳሏት ትሰማና አንጀትህ ቁርጥ ሊል ይችላል።
ነገ ከነገ ወዲያ ሀገር ለቃ ልትከንፍ ክንፏን እያርገበገበች ያለች፤ አሊያም አንዳች እርጉም ህመም ከጥቂት ቀናት በኋላ ይዟት ወደ ሞት ደጃፍ ሊያሸከትፍ መሆኑን አውቀህ ... ላለመጎዳት፣ በተስፋ ጉም ላለመጨበጥ፣ በማጣት ሰደድ ላለመንደድ በእንጭጩ ልትደፈጥጠው ትችላለህ።

ጽንሰቱን አጽድቆ ለውልደት የሚንደረደር ፍቅርም በጭንጫ መሀል እንደተዘራ ዘር ጥልቅ መሬት በማጣቱ ምክንያት ... ፀሐይ እሳት ሚተፋ ጥርሷን አግጥጣ የወጣች ጊዜ እንደደረቀ ሁሉ፤ በቅጡ ሳያቆጠቁጥም ሆነ ለማደግ በሚፍጨረጨርበት ወቅት ... ልበ መሬቱ ጥልቅ መሆን አቅቶት ስረ እምነቱ ስር መስደድ ሲሳነው ... እንደ ቅናት እና ጥርጣሬ ያሉ አጠውላጊ ፀሐዮች በእሳት አናትህን እየደቁ የፍቅርህን እድገት ገትተው ለሞት ይዳርጉታል።

"ከብዙ ሴቶች ጋር ያለህ ቅርበት ደስ አይልም" በሚል ... ርካሽ ቅናት በተጠናወተው መንፈስ ልታለመልም ያቀድከውን ፍቅር አድርቃ ልትርቅህ ትንደረደራለች። እንደ ሂሳብ ድምር አንተን አንድ አለኝ ብላ ጥግ ላይ አኑራህ፤ "የተሻለ ሰው በህይወቴ ሊመጣ ይችል ይሆናል" በሚል ኦና የተስፋ ጥርጣሬ እየወላወለች መሀል ቤት አንሳፋህ ግራ ስታጋባህ ከርማ ... አደገ እያልክ አንተ ደስታህን ስትምግ፤ ድንገት ተፈትልካ... ከስርህ አፈንግጣ ስርህን አድርቃ ትሸሻለች።

እሾህ መሀል ወድቆ እድገቱን እያናረ ... ራሱን ለትልቅ ምርት ሊያጭ ሲያኮበኩብ በእሾኹ ታንቆ እንደሚከስም ዘር፤ አንዳንድ ፍቅሮችም በጥሩ ሁኔታ እያደጉ ሂደው ... ጥሩ መንገድ አበጅተው ተጉዘው ... ለፍሬ ሊበቁ፣ ሊደነቁ፣ ሊመሰገኑ ነው ሲባል፤ ድምጹን አጥፍቶ በውስጣቸው ሲያደባ የነበረ ያልታወቀ አመለ እሾህ ደርሶ ወጥቶ እንቅ አድርጎ እዛው አኮስምኖ ለሞት አፍ ይገብራቸዋል።

ስንት አመት ተጠናንተህ ኑረህ... ለሰርግ ስትዘገጃጅ፤ ራስክን ለትዳር ተቋም ስታደረጅ፤ ከዓመታት በፊት የሰራኸው ስህተት ልጅ ሆኖ መጥቶ እንደ እሾህ አንቆ የፍቅርህን ግንድ አጥመልምሎ ይደፋዋል።

ከዛሬ ነገ ቀለበት ልሰርላት እያልክ ያደገ ፍቅርህን እስከ እርጅና ለማጽናት እየታተርክ ባለህበት ወቅት፤ ሀብት የሚያንገበግባቸው ቤተሰቦቿ... እልፍ አስገዳጅ ምክንያቶችን ደርድረው ውዷን ፍቅርህን እንደ ባሪያ ለራሳቸው ጥቅም ይሸጡብህና ተስፋ ላይ ያነጽከውን ቤት ብን አድርገው ከነፍቅርህ ያቀጭጩታል።

ለትዳር በቅተህ እስከ እርጅና ዘመንህ... መልካም መሬትን ተጣብቆ ለፍሬ እንደበቃ ዘር ፍቅርህን አጽድቀህ ጣፋጭ ፍሬዎቹን እየተመገብክ ይሆናል። ግን ህይወት ፍቅርን ለዘላለም የሚያኖር የዋህ ልብ አትሻምና ውድህን በሞት ትነጥቅኃለች። አንተ መውደድህን በልብህ አጽድቀህ እጅ ባለመስጠት ልትሟገታት ትፍጨረጨራለህ፤ እልዃ እስከ ጥግ ነውና አንተን ከነፍቅርህ ትደመስሳለች። ትገድላለች!

ፍቅር መሞቻው... እንደ ሰው ልጅ የመሞቻ ቀን አይታወቅም፤ ግን ከመሞት አያመልጥም። ሲጸነስ፣ በጽንስ ውስጥ፣ እንደተወለደ፣ ተወልዶ ጥቂት ኖሮ፣ እያደገ፣ በደንብ አድጎ፣ ጎርምሶ፣ ጎልምሶ፣ ለእርጅና በቅቶ ... ብቻ የሆነ የኑረት ኡደት ውስጥ ለሞት ተላልፎ ይሰጣል። ፍቅርም እንደ ሰው ልጅ ይሞታል። በሰው ልጅ ልብ ውስጥ ፍጹም ሆኖ ለመኖር እየታገለም ቢሆን... አብሮ ካኗሪው ጋር በአፈር ይቀበራል።

#ኤልዳን
@eldan29

@wegoch
@wegoch
@paappii
ሌባዋ ሴት ነበረች!
(አሌክስ አብርሃም)

ስልክ ምናምን እያልን ስለመሰረቅ ስናወራ ወዳጀ ዴቭ ትዝ አለኝ!" መገናኛ የገጠመውን እየነገረኝ ነው ...

" አንተ ስልክ ትላለህ እንዴ! የኔን ልንገርሃ ...መገናኛ ልክ ታክሲ ውስጥ ልገባ ስል የሆነ ፈጣን እጅ ኪሴ ውስጥ ዘው አለና ወዲያው ወጣ ፤ ዞር ስል ብዙ ሰው አለ ፣የማን እጅ እንደሆነ አላወኩም ...ግን ሳስበው ሳስበው ሴት ሳትሆን አትቀርም..."

"እንዴ ! ካላየኻት ሴት መሆኗን እንዴት አወክ?"
"የእጇ ልስላሴ ....በስማም! እንደዛ አይነት ፈጣንና ለስላሳ እጅ አጋጥሞኝ አያውቅም"
"እጁ ገብቶ የወጣው ኪስህ ውስጥ፤ ልስላሴውን እንዴት ...'ሴንስ' አደረከው ?"
"ባክህ ኪሴ ቀዳዳ ነበር ፣ በዛ ላይ ፖንት አለበስኩም! አፈፍእኮነው ያደረገችኝ እንትኔን ፣ማርያምን! ከመደንገጤ የተነሳ እጀን ልኬ ሁሉ መኖሩን ቸክ አደረኩ፤ መገናኛ ምኑ ይታመናል?!ሆሆ!"

ቆይቶ ዴቭ ከፍቅረኛው ጋር ተጣላና ሌላ ሴት ጋር ጀመረ ... እና ኤክሱ ብስጭት ብላ ምን አለች? ..."ደግሞ ከሌባ ለተረፈ እንትኑ!" ውይ ሴቶች 😀

@wegoch
@wegoch
@paappii
ፖሊማጅ!
(አሌክስ አብርሃም)

ከአመታት በፊት ሽመልስ ሀብቴ አካባቢ እኖር ነበር! አንድ ቀን ቤተሰቦቸን ለመጠየቅ ወደክፍለሐገር ልሄድ ተነሳሁ! በሌሊት የልብስ 'ባጌን' በጀርባየ አዝየ ወደአውቶብስ ተራ የሚሄድ ታክሲ ለመያዝ ጠደፍ ጠደፍ ስል የገነት ሆቴል የግንብ አጥር ስር የተቀመጡ ሁለት ፖሊሶች አጋጠሙኝ፤ አንዱ ክላሽንኮቩን ታፋው ላይ አጋድሟል ፣ሌላኛው ዝነኛውን ጥቁር ዱላ ይዟል! ብርድና የጧት ጨለማ ስለነበር ተጀቡነው መልካቸው እንኳን በወጉ አይታይም! ቦታዋ ጨለም ካለ ተደጋጋሚ ስርቆት የሚፈፀምባት በመሆኗ ፖሊስ በማየቴ ውስጤ ዘና አለ! "ሄይ ወደየት ነው?" አለኝ አንዱ ፖሊስ ...ርምጃየን ገታ አድርጌ "ወደአውቶብስ ተራ" አልኩ!

"ና ጠጋ በል እስቲ ...መታወቂያ ይዘሀል?" ጠጋ ብየ መታወቂያ ለማውጣት ስንደፋደፍ "ያ ምንድነው?" አለኝ በጅንስ ሱሪየ ላይ ቅርፁ ጎልቶ ወደሚታየው ስልኬ በጥቁር ዱላው እየጠቆመ
"ስልክ" አልኩ
"እስቲ አምጣው " ብሎ እጁን ዘረጋ ...ሰጠሁት፤ ሳምሰንግ ጋላክሲ ኖት 6 (በወቅቱ የመጨረሻው የሳምሰንግ ዘመናዊ ስልክ የነበረ ነው)! እያገላበጡ ለሁለት ሲያዩት ቆዩና ...."እና የት እየሄድክ ነው? "
"ወደክፍለ ሀገር "
"የት"
"ደሴ"
"ይሄን ስልክ ይዘህ ደሴ?" ሁለቱም ተሳሳቁ! አሳሳቃቸው አላማረኝም!
"ስትመለስ ጣቢያ መጥተህ ውሰድ " አለኝ ባለዱላው መጀመሪያ ቀልድ ነበር የመሠለኝ... ጥቁር ዱላውን አመቻችቶ "ምን ይገትርሀል ሂዳ ፤ ወይሰ እንሸኝህ?" ሲለኝና ከኋላችን የአንዲት ፒካፕ መኪና መብራት ሲያርፍብን አንድ ሆነ! እዛው ሰፈር የሚያውቀኝ 'ታዋቂ ሰው' ነው ...(እግዜር ልኮት ይሁን እድሌ ጎትቶት እንጃ) መስተዋቱን ዝቅ አድርጎ አንድ ነገር ብቻ አለ "ደህናደራችሁ? ቤተሰብ ነው! " ሞቅ ያለ ሰላምታ ተለዋውጠው .... ስልኬን በ"ስታይል" መለሱልኝና አጭር ምክር መከሩኝ ..."ለወደፊቱ ውድ እቃ ይዘህ ሌሊት ብቻህን አትሂድ ...ማጅራት መችዎች ሊጎዱህ ይችላሉ" አለና ከኋላየ ወደቆመችው መኪና እያዩ ስልኬን ላተረፋት ሰው ምን ቢሉት ጥሩ ነው ? " ምከረው! " 😀 አመስግኘ መንገዴን ቀጠልኩ! ከብዙ ግርምትና እስካሁን ልመልሰው ካልቻልኩት የዕምነት መፈራረስ ጋር!

ፖሊማጅ "ፖሊስ" እና "ማጅራት መች" ከሚሉት ቃላት አዳቅየ የፈጠርኩት አዲስ ቃል ነው! ማጅራት መች ፖሊስ እንደማለት! "ምላጭ ከለገመ በምን ይበጣል...ውሃ ካነቀ በምን ይዋጣል" እንዲሉ! ማጅራት ከሚመታ ፖሊስ ይጠብቀን🙏

@wegoch
@wegoch
@paappii
ከአንዲት የባላገር ጎጆ በዚህ ሰዓት የሚወጣ ድምፅ-

[ ለመተኛት እያኮበኮቡ ነው ፣ ከመደቡ ፈቅ ብላ እግሯን በቆሮቆንዳ እየታጠበች ነው። ዴስ ብሏታል። የአቡዬ ዕለት ነበር...]

' ምነው ከረምሽሳ አመጭም እንዴ? ' አላት በጀርባው ተንጋሎ;

' ጨርሻለሁማ! ልለቃለቅ ብዬ ነው ' አለችው። በኩራዙ ብርሃን ብቅ የምትል ፈገግታ እያሳየችው;

' ትመጪ እንደው ነይ ' ፊቱን ከስክሶ;

ሄደችለት;

የአቡዬ ምሽት ነው። የረጠበ እግሯ በቅጡ አልደረቀም ነበር። ገና ከመደቡ እንደወጣች። ተፈናጠጠባት። የረሀብ አንጀት ያዘለ ህጣን ይመስል ነበር። መንሰፍሰፉ!

ከደቂቃዎች ትንቅንቅ በኋላ-

' አንቺዬ '

' ወዬ '

' ዛሬ ጣፈጥሽኝና እ '

' አመዳም ሌላ ቀንስ ? '

' እሱስ ሁሌ! የዛሬው ባሰ ማለቴ ይ '

' ምን ተገኝቶ ? ' አለችው። ለምን እንደተለየበት አሳምራ ታውቃለች።

' ስሜን ደጋግመሽ ጠራሽ እኮ '

' ኤዲያ ቀጣፊ '

' አቡዬን! ጋሹ ጋሻዬ ጋሻ ምን ያላልሽኝ አለና '

' ሆሆይ ጋሻዬ ጋሹ ' አለችው በስሱ እየሳቀች;

' አንችው መልሶ እንደ መነሳት አለብኝ '

' ኧረ ኤዲያ! ስጠራህ? '

' አቡዬን ስልሽ! የሞተው ተነሳ! '

[ መተሻሸት ጀመሩ እየደጋገመች ጠራችው ' ጋሹ' እያለች ]

@wegoch
@wegoch
@paappii

By Noah z adwa
ተማሪ ሆነን ነውስ:: ጏደኛችንን ሳራን የወደደው የሰፈራችን ልጅ እኩያችን ቢሆን ነው ከትምህርት ቤት ወደቤት ለምሳ ስንሄድ እየተከተለ ያወራናል:: እንድንጀነጅንለት መሆኑ ነው::

ልክ ለቤታችን ትንሽ ደቂቃ ሲቀረን ያለ ዳቦ ቤት ጋር ስንደርስ ዳቦ ልጋብዛችሁ? አለን :: እኔና ጏደኛዬ ተያየን!! እሺ አልኩ ፈጠን ብዬ....::

ለምትሸጠው ልጅ ሳንቲሞች ከኪሱ አውጥቶ ዘረገፈላት እና 2 ዳቦ አቀበለችን:: እቤት ማን እንደገዛልን እንዳንጠየቅ እዛው ዳቦ ቤቱ ጋር ሆነን ደረቅ ዳቦውን ቅርጥፍ አርገን በላን::

ከብዙ ዓመታት በኃላ መች ለታ ዝንጥ ብዬ ከስራ ስመለስ መንገድ ላይ ተገናኘን:: ባላየ አለፍኩት :: ትንሽ እንዳለፍኩ...::

"ዳቦ እያበላሁ አሳድጌ....." ሲል ሰማሁት😂

@wegoch
@wegoch
@paappii

By Ma Hi
ወጣቱ በጣም ኳስ ይወዳል። አንድ ቀን ምግብ ሲያመጣልኝ ጆሮው ላይ ማድመጫ ተክሎ ሬድዮ እያዳመጠ ነበር።

''ምን እየሰማህ ነው'' አልኩት

''ኳስ ጨዋታ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ'' አለኝ።

''አ የዛሬን አያድርገውና እኔም የአርሰናል ደጋፊ ነበርኩ'' አልኩት።

ለካ እሱም አርሰናልን ልቡ እስከሚጠፋ የሚደግፍ ሰው ነው። ከዛ ቀን በኃላ ሁሉም ነገር ቀርቶ ወዳጆች ሆንን። ብቻውን የሆነ እለትና አርሰናል የሚጫወት ከሆነ በሬን ይከፍታል። በር ላይ ይቆምና አንዱን የጆሮ ማዳመጫ አውጥቶ እኔ እንዳዳምጥ ይሰጠኛል።

ሁለታችንም '' ብስራት '' የሚባል የኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ በአማርኛ የሚያስተላልፈውን ግጥሚያ እናዳምጣለን። የጋዜጠኞቹ አቀራረብ በጣም የሚያስደንቅ ነው። የሁለታችንንም ልብ ጉሮሯችን ስር ገብቶ እንዲቀረቀር የሚያደርግ ዘገባ ነው የሚያስተላልፉት። እኔ ና ጠባቂዬም አርሰናል ሲያሸንፍ ተደስተን ሲሸነፍ ተኳርፈን እንለያያለን። አንዳንድ ጊዜ ካልተመቸው ሌሊትም ቢሆን በር ከፍቶ '' አርሰናል በዚህ ውጤት አሸንፏል '' ይለኛል።

ይህን ሲያደርግ አለቃው እንዳይጠረጥረው ድምጹን ከፍ አድርጎ '' አንኳኳህ መሰለኝ '' ይለኛል። እኔም አንዳንድ ቀን ለመተግባበር '' አዎ ሆዴን ጎርብጦኛል ሽንት ቤት መሄድ እፈልጋለሁ'' እላለሁ። ለማስመሰልም ሽንት ቤት እሄዳለሁ። አንዳንድ ቀን ''ውጤት እነግርሃለሁ '' ብሎ ቃል ገብቶ ይጠፋል። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ለምን እንደሚጠፋ ገባኝ። የሚጠፋው አርሰናል ሲሸነፍ ብቻ ነው።

የዚህ ጠባቂ ድርጊት የሚያሳየው የሰው ልጅ የማንነቱ መገለጫዎች ብዙ መሆናቸውን ነው። ለኔ በሰዎች መሃከል ዘርን አቋርጦ የሚሄዱ ተመሳሳይነቶች በዘር ላይ ከተመሰረቱ ተመሳሳይነቶች የሚበዙ መሆናቸውን ስለማውቅ በጠባቂዬ ድርጊት አልተገረምኩም።

- የታፋኙ ማስታወሻ ( አንዳርጋቸው ጽጌ ) ከገጽ 111 - 112 የተወሰደ ——————————————————————

@wegoch
@wegoch
@paappii
"የማይረሱ ግን የማይወሱ ... ተራ ያልሆኑ ተረኞች"
.
1988
ፍቼ ከተማ አንድ እሁድ ረፋድ…ገብርኤል ቤተክርስቲያን መግቢያ የአንገት ልብሴን ተከናንቤ፤ ከእማዬ ኋላ ኋላ እየተከተልኩ፤ የሰንበቴ ቤት ዳቦዬን እየገመጥኩ ፤ ከቅዳሴ መልስ ወደ ቤት ስንሄድ … አንድ ከወገቡ በላይ የተራቆተ ፣ በቁምጣ የቆመ ያልተጎሳቆለ ደመግቡ ጎልማሳ ሰው፤ ድርስ ነፍሰጡር ሚስቱን አጠገቡ አድርጎ ሸሚዙን ፊትለፊቱ አንጥፎ አንገቱን ደፍቶ የሚለምን ፣ እጆቹን አመሳቅሎ የት ነበር ያደረጋቸው? በእግር ኳስ ጨዋታ የቅጣት ምት ሲመታ የተደረደሩት ተከላካዮች የሚያደርጉበት ቦታ። ሲለምን ምን ነበር ያለው? "ከጅማ መጥተን ያረፍንበት ቤርጎ ተዘርፈን ወደ አገራችን ለመመለሻ አጣን እርዱን " እሷ ምንም አትናገርም። አንገቷን ደፍታለች። ብቻ አጠገባቸው ከተኮለኮሉት ነዳያን የበለጠ ብሮች እና ሳንቲሞች ፊታቸው ተበታትኖ ነበር፡፡ ምናቸው እንደገረመኝ አላውቅም መንገዴን ትቼ ለአፍታ ቆሜ አየኋቸው፡፡እማዬ አጠገቧ እንደሌለሁ ያስተዋለችው ከራቀች በኋላ ነበር፡፡ ተመልሳ መጥታ "አንቺ ወሬኛ" እያለች እጄን ጎትታ ልትሄድ ስትል ዞራ ያየሁትን አየች፡፡ ከሙዳየ ምፅዋት የተረፋትን ስሙኒ ከመሀረቧ ፈትታ ለገሰቻቸውና ይዛኝ ሄደች፡፡ እስከዛሬ አልረሳኋቸውም፡፡ እነዛ ባልና ሚስቶች አሁን የት ይሆኑ? ብሩ ሞልቶላቸው በሰላም አገራቸው ገብተው ይሆን? ወይስ የለመኑትም ድጋሚ ተዘርፎባቸው? ከዛ በኋላ ወዴት ሄዱ? የት ደረሱ? በሰላም ወልዳ ይሆን? ወንድ ይሆን ሴት የወለዱት? ልጃቸው ስንት አመት ይሆነው/ይሆናት ይሆን?
.
ሰባተኛ ክፍል ሳለሁ ሰልፍ አበላሸሽ ብሎ በጥፊ የመታኝ ርዕሰ መምህርስ? በእሱ ጥፊ ደንግጬ ሂሳብ ትምህርት የክፍል ስራ 3/10 እንዳገኘሁ ይገምት ይሆን? ጡረታ ወጣ? ከአገር ወጣ? ሞተ ወይስ አለ?
.
1997
በ3 ቁጥር አውቶቡስ ወደ ሜክሲኮ ስሄድ ከኋላዬ በእናትዋ እቅፍ ላይ ሆና ፀጉሬን እየጎተተች በብስጭቴ ስትዝናና የነበረች ሳቂታ ህፃንስ? ልደታጋ ወርደው ወዴት ሄዱ ቤተክርሰቲያን ተሳለሙ? ፍርድቤት ገብተው ችሎት ታደሙ? ልጅቷ አሁን ስንት አመት ይሆናት ይሆን? ትምህርት ቤት ገባች? ስንተኛ ክፍል ደርሳ ይሆን? ወንድም ወይ እህትስ ይኖራት ይሆን?
.
ሃይስኩል ተማሪ እያለሁ ደሞ ጋንዲ ሆስፒታል ሄጄ (እናቴ እዛ ትሰራ ነበርና እሷጋ ... በዛውም 7ኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን ምግብ ቤት ምሳ አትክልት ልጋበዝ ፤ የገብስ ሻይ ልጠጣ)ሆስፒታሉ በር ላይ ሚስቱ በምጥ ተይዛ ሆስፒታል የገባች ባል ፊቱን ወደ አጥሩ አዙሮ በድሮ ኖኪያ ስልክ ምን ነበር ያወራው? "120 ብር ብቻ ጎደለኝ ከነገ ወዲያ እመልስልሃለሁ ፤ እባክህ አበድረኝ፤ መድሃኒት መግዣ ጎድሎኝ ነው" እያለ የሚማፀነው ሰውዬ የት ደርሶ ይሆን? ብሩን አግኝቶ ይሆን? ፊቱን ያላየሁት፣ ፊቴንም ያላየኝ ድምፁን ብቻ የሰማሁት ፣እንባዬን ያመጣብኝ (ያኔ እኔም ተማሪ ከየት አባቴ ላምጣለት)
.
2005
ፒያሳ አቡነ ጴጥሮስ ሐውልትጋ በክረምት፣ በማታ ፣ ጎርፍ በሞላው መንገድ ስደናበር ፤ እጁን ዘርግቶ እጄን ይዞ ያሻገረኝ ረዥም ሰውዬ ስሙ ማን ይሆን? ልጆች አሉት? ታሞ ሳልጠይቀው ቀረሁ? ለቅሶ አልደረስኩትም? ሁሌም ለችግረኞች እጁን የሚዘረጋ ይሆን? ጌታ ይባርከው!
.
2006 በበጋ ወቅት… ወደ ፀሐይ መጥለቂያ ገደማ ፤ ቦሌ ወሎ ሰፈር
አይቤክስ ሆቴል አካባቢ ከስራ ወጥቼ ወደቤቴ ሳዘግም፤ የሚያውቋት አንድ ዘመዳቸውን መስያቸው "ሰናይት" ብለው አገላብጠው የሳሙኝ ጥቁር ጥለት ነጠላ ያዘቀዘቁ እናት፤ አሁን የት ይሆኑ? እኔስ ምናለ" ተመሳስዬብዎት ነው ሰናይት አይደለሁም" ብላቸው? ሰላምታቸው ደስ ብሎኝ፤ እንዳላሳፍራቸው፤ እንዳላስደነግጣቸው፤ ከዛ ሰናይትን የሆነ ቀን ሲያገኟት "ምነው ያኔ አግኝቼሽ" ብለው ሲከራከሩ ምን ትመልስላቸው ይሆን? ማን ሞቶ ይሆን ነጠላ ያዘቀዘቁት? ከኔ በኋላ ተሳስተው የሳሙትስ ሌላ ሰው ይኖር ይሆን? ሰናይት ግን ደህና ናት?
.
የዛሬ አመት አካባቢ የመገናኛ ታክሲ ሰልፍ ላይ ሆኜ "የካሳንቺስ ነው?" ብሎ ሲጠይቀኝ "አይ የመገናኛ ነው" ያልኩት ሰውዬስ? በኋላ ለካ እኔም ተሳስቼ ሰልፉ የካሳንቺስ ሆኖ ሲገኝ ... ስቼ ያሳሳትኩት ሰውዬ የት ደርሶ ይሆን? ታክሲ አገኘ? ካሳንቺስ ለምን ነበር የሚሄደው? አውቄ ያሳሳትኩት መስሎት ተቀይሞኝ ይሆን? ይቅርታ እሺ!
.
ትናንት
.
.
.
በጣም ብዙ መሰል ሁነቶች ...የጭንቅላቴ ውስጠኛው ግድግዳ ላይ ተለጥፈዋል ፤"በሚያስደነግጥ ሁኔታ ነው የምታስታውሺው" ያልከኝ ወዳጄ ይህንን
ስታነብ ምን ትል ይሆን?

By teym tsigereda

@wegoch
@paappii
ከቤሩት እስከ እየሩሳሌም

(በሰዎች ልብ ውስጥ ያለውን ዘልቆ ያነበበ ደራሲ)

የዚህ መፅሐፍ ደራሲ (ቶማስ ፍሬድማን) በመካከለኛው ምሥራቅ በተከናወኑ አሉ የተባሉ ታሪካዊ ክስተቶች ሁሉ ውስጥ ከ10 ዓመት በላይ የኖረ አሜሪካን ጂዊሽ ጋዜጠኛ ነው።

ከጥቂት ዓመታት በፊት ይሄንን "From Beirut to Jerusalem" የተሰኘ እጅግ ድንቅ መፅሐፉን ካገኘሁ በኋላ የዚህ ደራሲ ሥራዎች አሳዳጅ ሆኜ ቀረሁ። ሁሉም መፅሐፎቹ አሉኝ። ፍሬድማንን አንዴ ካነበብከው፣ በትረካዎቹ ተለክፈህ የመቅረት ዕድልህ ከአስር አስር ነው።

"The Lexus and the Olive Tree" የተሰኘውና ፑሊትዘርን ጨምሮ ለበርካታ ዓለማቀፍ ሽልማቶች ያበቃው መፅሐፍ። "The World is Flat" የተሰኘው መፅሐፉ። እና ከእርሱ ቀጥሎ ያሳተመው "Hot, Flat and Crowded" የተሰኘ መፅሐፉ። ሁሉም እጅግ ድንቅ ናቸው።

"ዊት" አለው። ከሁሉ የህይወትና የዕውቀት ተሞክሮ የተቀዳ ምጡቅ ዕውቀት። እና ያንን እያዋዛ፣ እያጫወተ የመናገር ልዩ ተሰጥዖ። ከልጅነቴ ያዳበርኩት ነው ይላል ስለራሱ ሲናገር።

ፍሬድማንን ስታነብ የልብወለድ ድርሰት የምታነብ እንጂ በዕለት ጦርነቶች በሚታመስ ክፍለ ዓለም የተኖረን ዕውነተኛ የህይወት ገጠመኝ የሚፅፍልህ አይመስልም። ፍሬድማንን ሳነብ በዓሉ ግርማ ነው የሚመጣብኝ። ኦሮማይን ይዞ። የቀይ ኮከብ ጥሪን ይዞ። ሀዲስን ይዞ። ይሄ ፍሬድማን ጉድ ነው።
በነገራችን ላይ ያጋጣሚ ጉዳይ ሆኖ ሌላ ከዚህኛው ፍሬድማን በፊት የማውቀው ሌላ ፍሬድማንም አለ። የህግና ኢኮነሚክስ ፕሮፌሰር ነው። ዴቪድ ፍሬድማን ነው እሱ።

ዴቪድ ፍሬድማንም እጅግ "ዊቲ"፣ እጅግ አዋቂ፣ እጅግ ቀልደኛ፣ ህግን የመሠለ ደረቅ ጉዳይ አስገራሚ ለዛና ውበት አላብሶ የሚተርክ፣ ፕሮፌሽናል ተሆኖም ለካ እንዲህ ዘና ብሎ መፃፍ ይቻላል! ብዬ እጅግ እንድደነቅ ያደረገኝን ዓይን-ገላጭ መፅሐፍ የፃፈ ሰው ነው። እና በአጋጣሚ ሆኖ ስመ ሞክሼው ቶማስ ፍሬድማን ደሞ ከእርሱም የባሰ ጉደኛ ደራሲ ሆኖ አገኘሁት።

በግሌ ምርጫ፣ ይሄን ከቤሩት እስከ እየሩሳሌም የሚል መፅሐፉን የሚያህል በውብ አተራረክ፣ በጥልቅ ዕውቀትና በቀጥታ የዓይን እማኝነቶች የተደገፈ ድንቅ ድርሳን በመካከለኛው ምሥራቅ ጉዳዮች ላይ ዳግመኛ መፃፍ ይችላል ወይ? ብዬ እስክደመም ድረስ የመሰጠኝ መፅሐፉ ነው።

ይህ ከቤሩት እስከ እየሩሳሌም የተሰኘው የቶማስ ፍሬድማን መፅሐፍ በእርግጥ በቅርብ ዓመታት ደግሞ "update" አድርጎ ቢያወጣውም፣ ከታተመ ቢያንስ ሶስት አሰርት ዓመታትን ያስቆጠረ መፅሐፍ ነው። ስለሆነም የቅርብ ጊዜ መረጃዎችንና ክስተቶችን አልያዘም። ነገር ግን የእስራኤልና ፍልስጥኤምን (አጠቃላይ የአረቦችና እስራኤልን) ጉዳይ ለማወቅ የሚሻ ሁሉ የግድ ማንበብ ያለበት ድንቅ ድርሳን ነው።

የመፅሐፉ ጥቅጥቅ ያለ ወደ 600 ገፅ የሚጠጋ የገፅ ብዛት ትዕግሥትን የሚፈታተን መስሎ ቢታይም፣ እንደ ኦሮማይ የመሠለ አጓጊ ድርሰትም ይመስላል። ሳይታወቅህ ላፍ ይላል። ከሚያውቅ ጋር ነው መጫወት - እንዲል ያገራችን ሰው። ፍሬድማን ሳያሰለችህ የልብ የልቡን፣ matter የሚያደርገውን፣ ለነገም ለሁልጊዜም ነገሮችን በትክክል ልታይበት በምትችልበት መልኩ፣ መንገርን ያውቅበታል። ተክኖበታል።

ጦርነትና ግጭት፣ ፍንዳታና ሥጋት፣ ጥቃትና ጉዳት... የዕለት ተዕለት ቀለብ በሆኑበት እንደ መካከለኛው ምሥራቅ ባለ የዓለም ክፍል ላይ ስትገኝ፣ ምን ያህል ተማስ ሆብስ የተባለው ፈላስፋ "ሌቪያታን" በሚለው መፅሐፉ የገለፀው "state of nature" የሚባለው የሰው ልጅ የእርስበርስ ጥርጣሬ የነገሰበት፣ አንዱ ከሌላው ጥቃት ተሰነዘረብኝ እያለ በሥጋት የሚያድርበት፣ ህይወት አስመራሪ፣ አረመኔያዊ፣ ሽሚያ፣ አስቀያሚና አጭር የሆነችበትን የሰው ልጅ ህይወት ሲያብራራ - ሆብስ የሚናገረው ቲዎሪ ሳይሆን በትክክል የሆነንና ወደፊትም የሚሆንን ነገር ተመልክቶ ተንብዮ የፃፈ ነው የሚመስልህ - እያለ ይገረማል ባጋጠመው አስመራሪ የህይወት ምስስሎሽ።

አንድ ዕለት በአንድ ምግብ ቤት ምግብ አዝዞ እስኪመጣለት እየጠበቀ በረንዳው ላይ ቁጭ ባለበት አካባቢው ድንገት በተኩስ መናወጥ ይጀምራል። ጩኸቶች ከዘዚህም ከዚያም ይሰማሉ። የፍንዳታ ጭሶች ከሩቅ ይታያሉ። ነዋሪዎቹ ግን ምንም አዲስ ነገር እንዳልተፈጠረ እንደ "normal" ነገር የሚታየውን ግርግር ለምደውታል። አይደናበሩም። አይሯሯጡም።

በመንገዱ እየሄደች ያለች እናት ህፃን ልጇን ይበልጥ ወደራሷ ጥብቅ አድርጋ መንገዷን ትቀጥላለች። ፍሬድማን በዚህ ሲገረም የምግብ ቤቱ አስተናጋጅ መሀመድ መጣ ወደበረንዳው ፈገግታ ባልተለየው ትሁት ፊት ተሞልቶ። ምርጫውን ሊጠይቀው፦ "ቁርሱ ደርሷል ሚስተር... አሁኑኑ ይምጣልህ? ወይስ ተኩሱ ሲበርድ ቢመጣልህ ይሻልሀል?"።

ማመን አቃተኝ ይላል። ግርግሩ ሳይበግራቸው ቁርሳቸውን በትኩስ ሻይ የሚያወራርዱ ደንበኞች ሁሉ አሉ ይላል። ይገረማል። አይይ.. ትንሽ ይቆየኝ። አመሠግናለሁ። ይህን ከማለቴ አንድ ሮኬት መጥቶ አካባቢው ላይ እንደ ነጎድጓዳማ መብረቅ ወርዶ ተከሰከሰ። ሁሉም ወደ ውስጥ ሩጫና ነፍስ አድን ግርግር ሆነ። ከግማሽ ሰዓት በኋላ ሁሉም ፀጥ።

ከዚያ አስተናጋጁ ወደ ፍሬድማን መጣ። ከነፈገግታው። "አሁን ይቅረብልህ አይደል?"። መሀመድ የሚኖረው የዕለቱን ነው። የሰዓቷን ነው። የደቂቃዋን ነው። ስለሌላ ነገር የሚያስብበት ቅንጦቱ የለውም። አስቦም የሚቀይረው ነገር የለም። የነዳጅ ዋጋ 0.50 ሣንቲም ጨመረብን ብለው ለተቃውሞ ሰልፍ የሚወጡት፣ ከስድስት ወራት አስቀድመው የገና በዓል ጌጣጌጥ የሚገዙት፣ ያገሬ ሰዎች ሳልወድ አሳቁኝ። አሳቀቁኝ። ይላል ፍሬድማን።

ስለ ፍልስጥኤም ነፃአውጪ ድርጅትና ስለ እስራኤል መከላከያ ሠራዊት እያነፃፀረ ሲናገር ፍሬድማን፦

"ያሲር አራፋትና ኤሪየል ሻሮን ያው የሚዋደዱ
ሰዎች አይደሉም፣ የገና ስጦታ አይሰጣጡም፣
የሚለዋወጡት ነገር ቢኖር ተኩስ ነው፣ ያሲር
አራፋት ከሻሮን የሚቀበለው የአየር ጥቃትና
የጓዶቹን አስከሬን ነው፣ ሻሮንም ከአራፋት
የሚቀበለው አጥፍቶ ጠፊ ቦምበኞችንና
ተወንጫፊ ሮኬቶችን ነው፣

"በመሐላቸው ምንም ዓይነት ሮማንቲክ
ነገር የሌለን ሰዎች ነው አሜሪካና አውሮፓ
በቴሌቪዥን ካሜራ ፊት እያጨባበጠ
የሚደሰተው፣ ፋንታሲ ነው፣ እውነታው የዳንቴ
አሌገሪን ትራጀዲክ ኮሜዲ የመሠለ ዘግናኝና
አጓጊ ነው፣ አስፈሪና የተለመደ ነው፣ ሞትና
ህይወት፣ ስቃይና ፈገግታ ነው፣ ይሄንን
ተቃርኖአዊ ህይወት በድርሰት ካልሆነ በቀር
በእውን ከዚህ ሥፍራ በቀር የትም አታገኘውም!"

አንድ በሰሜን እስራኤል (በጎላን በዌስትባንክ በሊባኖስ ወዘተ) ዕድሜውን ሙሉ ከፍልስጥኤሞች ጋር ሲዋጋ ያሳለፈ የእስራኤል ሜጀር ጀነራልን አባባል ይጠቅሰዋል ፍሬድማን አንድ ምዕራፉ ላይ፦

"ይኸው አርባ ዓመት አለፈን፣ በግሌ ከጠየቅከኝ ፍልስጥዔሞቹን አልወዳቸውም፣ እነሱም አይወዱኝም፣ ግን በአንድ አልጋ ላይ አርባ ዓመት ሙሉ አብረን አለን፣ በመሐላችን ፍቅር የለም፣ ሴክስ የለም፣ አብሮ የሚያቆየን ሀባ የጋራ ነገር የለም፣ እና በኔ ቦታ ብትሆን ምንድነው የምትፈልገው? ግልፅ ነው፣ ፍቺ (ዲቮርስ) እፈልጋለሁ!"

እነዚህ ለዓመታት ሲታኮሱና ሲጠላሉ እርስበርስ ሲጠራጠሩ የኖሩ ሁለት ህዝቦች፣ ምናልባት የሚያስፈልጋቸው ጥሩ ፍቺ ይሆን ይሆናል። ግን ያንን ጥሩ ፍቺም ማምጣት ነው ያልተቻለው። ተፋተውም አምባጓሮው የሚቀጥልበት ዕድል ከፍ ያለ ነው።

በዚያ ላይ ደሞ - ይላል ፍሬድማን - የፍቺውንም ሆነ የጋብቻውን ስምምነት የማይፈልጉ ብዙ ዓይነት ሰዎች በሁለቱም በኩል አሉ። የእስራኤል ለዘብተኛ መሪዎች ከያሲር አራፋት (ፒኤልኦ) ጋር እርቀሠላም ሊፈራረሙ ጫፍ ሲደርሱ፣ ሞሳድ ይሄድና በዮርዳኖስ ያገኘውን የሀማስ ከፍተኛ አመራር ይገድላል። ሀማስ ደሞ እስራኤል ላይ ሮኬት አዝንቦ ሰላማዊ እስራኤሎችን ይገድላል። ነገሩ ይቀጣጠልና የሰውም የሠላም ስሜት ተቀይሮ ሁሉም ወደግጭት ይገባል። የሠላም ፊርማው በዚያው ይቀራል።

ደሞ ሌላ አደራዳሪ፣ ሌላ አስማሚ ይመጣና፣ እስራኤልና ፍልስጥኤም የመጨረሻውን ሠላም የሚያመጣ ስምምነት ሊፈራረሙ ነው ይባላል። ይሄን ሲሰማ ሀማስ ይመጣና ያለ የሌለ መቅሰፍቱን በእስራኤሎች ላይ ያወርደዋል። አይዲኤፍ ደሞ ጋዛን ይወርና በፍልስጥኤሞች ላይ መቅሰፍቱን ያወርዳል። ስምምነቱ ተዳፍኖ ይቀራል።

ደሞ ሌላ። ደሞ ሌላ። በጣም የሚገርመው ሁለቱ ደሞ ፀጥ ብለው የሚስማሙ ሲመስል ሌሎች አደፍራሾች ደሞ ብቅ ይላሉ። አንዴ ሁለቱ የሠላም ሰነድ ሊፈራረሙ ነበር። ዓለም ሁሉ እያጨበጨበ ነው። በመሐል የያክ አክራሪ እስራኤላዊ ባሩክ ጎልድስታይን እስካፍንጫው ታጥቆ በሄብሮን መስጊድ በሠላም በሚሰግዱ ፍልስጥዔሞች ላይ የጥይት እሩምታውን ያዘንብባቸዋል። ሁሉም ፍልስጥዔም እሳት ጎርሶ ከየቤቱ ጋዝ የተሞላ ጠርሙስ እያነደደ በእስራኤሎች ላይ ያፈነዳል። የሠላሙ ተስፋ ተዳፍኖ ይቀራል።
በዚህ ሥፍራ ሁሌም ሠላም የለም። እርቅም አይፈለግም። አደፍራሽም ፈፅሞ አይጠፋም። እስራኤሎችም፣ ፍልስጥኤሞችም፣ ጆርዳኖችም ሠላምን ይናፍቃሉ። ሌሎችም እነ ኢራንና ሶርያ፣ ሊባኖስና ግብፅ የሠላምን ዓየር በረዥሙ ስበው ማጣጣምን ይመኛሉ። በመሬት ላይ የሆነውና የሚታየው ግን ከዚህ ተቃራኒው ነው።

ፍቺ የሌለበት የጋራ የፀብና የጦርነት ህይወት ብቸኛውና መፍትሄም ያልተገኘለት የአኗኗር መንገድ ሆኗል። እነዚህ ህዝቦች እርስበርስ እየተፋተጉ ከግማሽ ክፍለዘመን በላይ አሳልፈዋል። በማይበርድ ጦርነት ውስጥ ተጥደው ፍዳውን እያወራረዱ ናቸው።

በጣም በቅርበት ተጠግቼ ሁሉንም አይቼያለሁ። በሁሉም ሰው ፊት ላይ መሰላቸትን አነባለሁ። ግን መፍትሄው እንዴት እንደሚመጣ ያወቀ የለም። ማንም አያውቅም። በዚህ ስለምንም ነገር እርግጠኛ በማትሆንበትና የዕለት-የዕለቱን ብቻ እያሰብክ በምታድርበት የምድሪቱ ሥፍራ ላይ ነገና ከነገወዲያ ስለሚሆነው ነገር በእርግጠኝነት መናገር የሚችል የለም።

በአንድ ወቅት ስፅፍ በእኔ ዕድሜ በእስራኤልና ፍልስጥኤም መሐል እርቀሠላምና ስምምነት ነግሦ ከማይ፣ ከምላሴ ፀጉር በቅሎ ባይ ብዬ መመኘትን እመርጣለሁ፣ ባጭር አነጋገር የማይሆን ምድራዊ ቅዠት ነው - ብዬ ነበር።

ፕሬዚደንት ክሊንተን አራፋትንና ራቢንን ባፈራረማቸው ዕለት እኔን በእንግድነት ጋብዞኝ ነበር። እና ፀጉርህ በቀለ ወይ? ይኸው ምንትሆን እንግዲህ ተፈራረሙ - አለኝ። ተሳሳቅን። እና ፈጣሪ እንዲያፀናላቸው እመኛለሁ አልኩት። ያፀናላቸው ግን አልመሠለኝም።

አሁን ላይ እንደ ቀድሞው ፈፅሜ ጭፍን መሆን አልፈልግም። በሰው ልጅ ያልተገደበ አቅም አምናለሁ። ኦፕቲሚዝም አለኝ። ሁለቱ ህዝቦች ዛሬም በእኔ ጊዜ ባይሆን፣ ወደፊት በፍቅር ተቀራርበው፣ ለፍቅርና ለአብሮነት እጅ ሰጥተው፣ ተፋተውም ይሁን ተጋብተው፣ በሠላምና በጉርብትና መኖሩን የሚመርጡበት ቀን እንደሚመጣ እርግጠኛ ሆኜ እናገራለሁ።

መቼ ነው ያ ቀን? - አታስዋሸኝ። የዚህ ጥያቄ መልስ ዛሬ ላይ ማናችንም ጋር እንደሌለ አሳምረን እናውቃለን። ዛሬ ላይ ሆኜ አንድ ነገር በእርግጠኝነት የምነግርህ ነገር ግን አለ። ሁለቱም ሕዝቦች በቅቷቸዋል። ታክቷቸዋል። እና ሁለቱም ወደወደፊቱ የሚያደርሳቸውን የሠላም ትኬት ቆርጠዋል። መቼ ነው ደፍረው የሚሳፈሩበት?

እሱን ለማየት በትዕግሥት መጠበቅ ያለብን ይመስለኛል። በእኔ ዘመን ያን ጉዞ ለማየት ባልታደል፣ ይህን የፃፍኩትን ቃል በጉልምስና ዘመናቸው ቁጭ ብለው የሚያነቡ ልጆቼ በዘመናቸው ለማየት እንዲታደሉ ከልቤ እመኛለሁ።

ቶማስ ፍሬድማን። በመረጃዎች፣ በክስተቶች፣ በዕውቀቶች የተሞላ ርቱዕ ደራሲ ነው። ይህ መፅሐፉ በብዙዎች ሲደነቅ የሚኖር የሰው ልጆች ትራጀዲና ተስፋ አንድላይ ተሰፍተው በማራኪ ብዕር የቀረቡበት ሀቀኛ መፅሐፍ ነው። ያገኘው ቢያነበው ዘና ብሎ እጅግ ብዙ ያተርፍበታል።

ሠላም ለዓለም ይሁን!🙏🙏

@wegoch
@wegoch
@paappii

By Assaf Hailu
........ ይዘባር(ረ)ቃሉ ........

         ‹ከጊዜያት ባንዱ›……. የሚለው አገላለፅን ተጠቅመን የኋሊት እንዳንቃኘው የተምታታ ስፍር ይሆንብናል (‹ጊዜ›)፡፡ ጭል ጭል ከምትል እና ደብዛዛ እሳት ከምትተፋ አምፖላችን በታች፣ ከተጋጋጠ ጠረጴዛችን ፊት ለፊት እግሩ በሚንጥ ወንበራችን ተቀምጠን አምሽተን ይሆናል (በእኛ የጊዜ ሚዛን)፡፡ ፀሃይም እደኛ አይነት ቤት ያመሸች መስሎን ይሁን ሌላ….. እኛም ተከትለን እንወጣለን፡፡ አንድ ምሽት ብለን የሰፈርነው ቆይታችን ለካ በዐለም የጊዜ ሚዛን አስ ደቂቃ ብቻ ነው፡፡ ወደ ድንኳናችን (የምድር አይደለም! ከበረሃ ምናባችን እያፈራረቅን የምንተክለው ነው) ሀሳብ ስንጥል፣ ሀሳብ ስናነሳ አሁንም ‹10 ደቂቃ› የሚል ስም የሰጠነውን የጊዜ ውል ያህል እንቆያለን፡፡ እንደ ቤ/ክ መጋረጃ የገብርኤል ሰይፍ (ጦር?) ያልቀደደው መጋረጃችንን ወደ አንድ እናንሸራትትና ለ1 ደቂቃ ብቻ (ባልነው) በብርሃን ጮራ ስንጫወት እንቆያለን፡፡ ከበራችን አካላችንን ስናሻግር እና ከዐለም ስንቀላቀልስ?....... 10ሩ ደቂቃ ለካ 3 ቀን ነበር! ለየቅል የሆነ ሚዛን………. ከዴሞክራሲ ወዲህ ከብዙኃኑ በተቃራኒ መቆም ትርፉ፣ ትርፍ ማጣት ሆኗል፡፡ አሁንም ግን ፈለግነውም፣ አልፈለግነውም…..... ገባንም፣ አልገባንም…… ከጊዜ ሆነ ከዐለም መታረቅ አልተቻለንም፡፡   ከነዚህ ቀናቶች (በዚህ እንስማማና) ስዋልል፣ በገዛ ምናቤ…… ቀንበር ከጫንቃው ያረፈ ደመና ሰማይ እያረሰ ወደ ምዕራብ ያዘግማል፡፡ ጉልበቱ ሲበዛበት ሌቱን ማሳለፊያ ጎሕ ይቀዳል፡፡ ሲሻው በዚህ ደግሞ ምድር ዳምኖ ሽቅብ ያዘንባል፡፡ ነገሩ እስኪምታታኝ፣ አቅሌን እስኪመታኝ የተፈጥሮ ህግ ሲዛነፍ፣ ልማድ ተሸራርፎ ከማይነሳበት ሲያርፍ አስተውላለሁ፡፡ (ትቢያ ይጫነው ይሆን ይሄም? ማለት ከአጥንቶች ጋር ለምፅዓት ሊሰበሰብ? እንጃ!) ብቻ ጊዜም እንደ ፈትል ውሉ ተዘባርቆ አልፈታ ይለኛል፡፡ በራሱ የመተርኩት አጭር ስለው ተለጥጦ ጥጉ እና ቅጡን ያጣል (ይዝረከረካል!)፡፡ ስንዝር የመሰለኝ በብዙ ተመንዝሮ ዘላለም ያህላል፡፡ አጭር ያልኩትማ……. በዐለም ስፍር ርዝመቱ ከሁሉ ይጋጫል፡፡ በእርግጥ ይሄ ሁሉ ዝብርቅርቅ ውበቱ አጀብ ነው፡፡ ግና ውበት፣ ልክነት አይሆንም፡፡ ውበት አፈንጋጭ እና ልዩ እንጂ ተለምዷዊ አይደለምና…….



By Lewi @Lee_wrld777


@wegoch
@wegoch
@wegoch;
“ማንም ስለ እናንተ ግድ የለውም” | ጥቂት የግል ምልከታ
.

ሼክስፒር «ዓለም የቴአትር መድረክ ናት፣ ተዋናዮቹም እኛው ነን» ያለው “እኛን” ሳያይ መኾኑ ይገርማል። በስመአብ —አደገኛ ቴአትረኞች ነን። የተካንን አስመሳዮች፣ “ቪሊያን” ካራክተሮች ነን። በተለይ እንደ ልብ መተጣጠፍ፣ መለጠጥ፣ መለወጥ፣ መቀየጥ የሚቻልበት የማኀበራዊ ሚዲያ ሜዳ ይኽን አመሳሶነታችንን ጎልቶ ያወጣዋል። ማናችንም ከዚህ ፍርድ አንተርፍም።

ትንሽ ጨከን ብለን መነጋገር ካለብን በተለይ ሰዎች ራሳቸውን ሲያጠፉ ወይም በሌላ ምክንያት ሲሞቱ የምናሳየው ባሕርይ በአጥንታችን ውስጥ ያለውን ዘግናኝነት ያጋልጣል። ያመመን እናስመስላለን እንጂ ያን ያሕልም አያመንም። ሰውን በአፍጢሙ ለመድፋት በምላሱና በግብሩ የተሰለፈ ኹሉ ልክ «እገሌ ሞተ …» ሲባል የተጠና ሙሾ አውራጅ ኾኖ ብቅ ይላል። ትንሽ ወቀሳ ካደረግኹት ይቅርታ!

የኾነ ሰው ሲሞት እየጠበቁ “ጓደኛዬ አልደረስኩልኽም/ሽም …” የሚሉ፣ የተላላኩትን መልዕክት የሚለጥፉ፣ በድንገተኛ ኀዘን የደቀቁ የሚመስሉ ትዕንግርቶች እዚኽም እዚያም ብቅ ብቅ ይላሉ። ይኽ የሚያሳየው ቀሽም ጓደኛ መኾናቸውን መኾኑ ግን አይገለጥላቸውም። “እናውራ…”፣ “በሕይወት እያለን እንዋደድ …”፣ “ሲከፋችኹ አለኹላችኹ አውሩኝ… ” ምናምን ምናምን የሚል የተሰላ ሽሙጥ መሳይ እዝነታቸውን ለአደባባይ ያበቃሉ።

እነዚኽ ሰዎች ኀዘናቸው ለይምሰል መኾኑን ለማወቅ ጎበዝ ታዛቢ መኾን አያስፈልግም። ድርጊታቸውን ብቻ ማየት በቂ ነው። እነዚኹ ሰዎች በነጋታው ኹሉን ነገር ረስተው በሁካታና ቱማታ፣ በሳቅና ቀልድ፣ በብሽሽቅና በስድድብ ውስጥ ተጠምደው ይታያሉ። ከመቼው ከእንባ ወደ ፌዝ እንደተከረበቱ እንጃ!

የግል ሐሳቤ ትርጉም ካለው ይኽንን እላለኹ!

ለሰው አደገኛ ተስፋ አትስጡ! ላትኖሩ “አለኹልኽ” አትበሉ። ላታዳምጡ “ንገረኝ” አትበሉ! መሸከም የማትችሉትን “እንሸከማለን” አትበሉ! የማንንም ሕመም የማስታመም ግዴታም የለባችኹም። ከማስመሰል “ጆሮ ዳባ” ማለት ሰውን ያተርፋል።

ለሰው “ያልፋል!” ብቻ ሳይኾን “ላያልፍ ይችላል፣ ባያልፍም ግን መኖር ትችላለኽ” በሉ። ለደከማቸው እውነቱን ንገሯቸው! አንዳንዴ የሠሚም ጆሮ ይዝላል … አንዳንዴ ማንም ላይሰማኽ ይችላል። በጣም የቅርብ ጓደኛኽ ቀርቶ እናትህ እንኳ ስላንተ ግድ ላይሰጣት ይችላል። ሕይወት ይኽንንም ችሎ መኖር ነው። በቃ እንዲኽም ከባድ ነው።

ኹሉም ነገር በንግግር አይፈታም። አንዳንዱ ችግር አንተ ጋር ብቻ የሚቀር ነው። እናትኽ፣ አባትኽ፣ ወንድምኽ፣ ጓደኛኽ፣ ፍቅረኛኽ የማይራመዱልህ መንገድ ሊኖር ይችላል። ኹሉም በራሱ ዓለም ውስጥ የተጠመደ ነው። ለራሳችኹ ራሳችኹ ብቻ አዳኝ ኾናችኹ የምትቀሩበት ጊዜ አለ። ለብዙዎች ስታትስቲክስና የከርሞ ዜና ብቻ ናችኹ።

የአንድ ሰው ራስ ማጥፋት “የአንድ ሰው ጉዳይ” ሳይሆን ከሥር ያለውን መዋቅራዊ ችግር የሚያሳይ ትንሽዬ ምልክት (tip of the iceberg) ነው። የሰዎች ራስ ማጥፋት ጥላ (shadow) ነው። ጥላውን የጣለው ቅርጽ (shape) ላይ አተኩሩ። ሴተኛ አዳሪነት፣ አስገድዶ መድፈር፣ ተስፋ ማጣት ኹሉ ጥላ ናቸው …ወደ አንድ ትልቅ ምስል ይጠቁማሉ። ኹሌ ነገሩን ዜናና ሰሞነኛ ወሬ ማድረግ ምንም አይፈይድም። በዚህ መንገድ ሊሞቱ ያሉ ተሰልፈዋል። ገና ለብዙዎች ተመሳሳይ እንባ ልናለቅስ ጊዜ እየጠበቅን ነው። ምክንያቱም ብዙ ፈሪዎች ለመሞት የመጨሻዋን ድፍረት በጽዋቸው ውስጥ እያጠራቀሙ ነው።

Dostoevsky በ “The Karamazov Brothers.” መጽሐፉ ላይ አንዲት መሥመር አለች…
“Adelaida Ivanovna muisov's action was similarly no Doubt, an echo of other people's Ideas”

ለቀደመው አረፈድን ካላችኹ ለሚቀጥሉት ድረሱላቸው። ከንግግር በላይ ግን ተግባሩ ላይ አተኩሩ። ሰው በስውር የነገራችኹን በሰው ፊት አትግለጡ። የመጣው ማዕበል ከ“ቴራፒ” ወይም ንግግር ይበልጣል። ብቻውን መኾንን ያልተማረ፣ ለብቻው ዋጥ አድርጎ መቻልን ያልሠለጠነ ሰው እንደ ምዕራባውያን በትንሽ ዱላ የሚሰበር፣ በትንሽ ወሬ የሚፈራርስ ሴንሰቲቭ ልፍስፍስ …ትውልድ ይፈጥራል። ይኽን መዋቅራዊ ችግር እስካልፈታን “አውሩኝ…” እያሉ የሰውን ሕመም ጥም ማርኪያ ማድረግ በቦሃ ላይ ቆረቆር ዓይነት ነገር ነው።

P.s:- ሳቃችሁን ከሰው ጋር አድርጉ ለቅሷችሁ ግን ከጸሎት ቦታችሁ አይለፍ!

———-
Sorry for the incoherence — T.P

@wegoch
@wegoch
@paappii

By Henock Bekele
አባቴ ድሃ ታግሎ ኗሪ ነበር ። ነፍስ እስካውቅ የሆነ ኮት ነበረው ፤ ዘወትር ነበር የሚያደርገው ፤ እሱን ኮት ሳይለብስ ከመንገድ ባገኘው የማልፈው ሁላ ነው የሚመስለኝ ።

ረጋ አባባሉ የሞላለት ያስመስለዋል ።
በትንሽ በትልቁ አይናደድም ፤ በትንሽ በትልቁ አይመክረኝም ። ከሰው ጋ ሲጣላ አጋጥሞኝ አያውቅም ።

ሰላማዊ ሰው ነው ፤ ሁሉንም ሰው በሙሉ ስም ነው የሚጠራው እኔንም ጭምር ። እናቴን ግን ያቆላምጣታል ። እሷ ጋ ሲደርስ የሚሆነው መሆን ለየት ይላል ፤ ይቀልዳል ፣ ያሾፍባታል ግንባሯን ይስማታል ።

አጠገባችን ላሉ እጅግ ከእኛ የበለጠ ደሃ ለነበሩት እማማ አዛሉ እና ከእኛ ቤት ፊት ለፊት ሰፊ ትልቅ ግቢ ላላቸው ለዲታው ጋሽ ይልማ የሚሰጠው ሰላምታም ተመሳሳይ ነው።

አባቴ ችግር ሲያወራ አይቼው አላውቅም ፤ ዝም ብሎ የቻለውን ያደርጋል ፤ ምን አልባት ለእኔ ማውራት አያበድረኝ ፣ አይሞላልኝ ብሎ ይሆናል እንዳልል ስራ ላለው ለታላቅ ወንድሜም እንኳን አያወራም ።

ስራ በያዝኩ በሶስተኛ ወሬ በአንዴ አራት ሙሉ ልብስ ገዛሁለት ። ደስ አለው በጣም ።
እጄን ይዞ
አትጣ
ሞገስ ልበስ
የአንተ የሆነ ሁሉ ይባረክልህ ብሎ መረቀኝ

በአራተኛው ቀን ........ከገዛህልኝ ሁለቱን ሙሉ ልብስ ለወዳጄ እና ለበሪሁን መስጠት ፈልጌ ነበር አለኝ (ወዳጄ እና በሪሁን ወንድሞቹ ናቸው)

ቅር ይልህ ይሆን ብሎ አይን አይኔን አየኝ

አጠያየቁ አስተያየቱ የሆነ የሚያሳዝን ነው ፤ አንጀቴን በላው

ከእነሱ ጋ በጋራ መዘነጥ ፈልጎ ከእነሱ ተለይቶ ላለመድመቅ ነው መሰለኝ

ሌላ ቃል ስላጣው አይ ጋሼ ብዬ እጁን ሳምኩት!!!

By Adhanom Mitiku

@wegoch
@wegoch
@paappii
#መርሳት እና ማበድ
…….መርሳት እውነትም ፀጋ ነው፡፡ ማን ነበር ይህን ያለው? ያለበድነውም ስለምንረሳ ነው ሁላ ብሏል፡፡ እና እኔ አብጃለሁማለት ነው? ይሄን የመሰለ ፀጋ ለፍጥረት የት ነበርኩኝ? በየትኛውም የህይወቴ ክፍል ነገሮችን ከተፈጠረ በኋላ በቀላሉ ረስቼ ማለፍ አይቻለኝም፡፡ ከመለያየት ወዲህ ማንም ቢሆን ትዝታ እያመሰው የሚቆይበት የጊዜ ልክ አለ፡፡ ለኔ ሲሆን ግን ይሄ ተለጥጦ ከዘለዓለም እኩል ረዝሟል፡፡ እንደ ገዛ ስሜ፣ ኑሮዬ፣ ልጅነቴ ያሉ የግል መረጃዎቼ ሳይሰረዙና ጨርሶ ላይሻሩከሚቀመጡበት የአዕምሮዬ ቋት እሷና ያሳለፍነው ሁሉ ተፅፏል፡፡ ስለፈለኩ አልረሳውም፣ ስላልፈለኩ ደሞ አለማስታወስ አልችልም፡፡
ለስንተኛ ግዜ እንደሆነ እንጃ ብቻ ሁሌ እንደማደርገው ለመጨረሻ ግዜ ተገናኝተን ከተለያየንበት ካፌ እየወጣሁ ነው፡፡ ከሳምንት፣ ሳምንት ‹እንለያይ› ብላ አፍ አውጥታ ከጠየቀችኝ ስፍራ ማመን ቢሳነኝ ከእውነት ልሟገት እሄዳለሁ፡፡ ቅዱስ ሚሉት ሀሙስ እረክሶብኝ ጠላሁት፡፡ ምነው እሮብ ብሎ አርብ ቢሆን? ለነገሩ ሊሄድ ለወሰነ ቀን ቢሻር ምን ገዶት? በርግጥ ከጥያቄዋ ወዲህ ተነስቼ የሄድኩት እኔ ነኝ፡፡ በድን አካሌን እየጎተትኩ ለዚያውም፡፡ ቀልቤና ደመ ነፍሴ፣ ሙሉ እኔነቴማ እዚያው ወንበር ላይ ስንት ሳምንታቸው! መሄድ እና መንገድ ስል ይሄ የምንረግጠውን ምድር ሳይሆን የረቀቀውን የልብ ላይ ፍኖት ማለቴ ነውው፡ ወደኔ የሚያመጣትን ስታ መሸሽ ከጀመረች ከርማለች፡፡ አለማየት ደጉ ስንቱን ጋርዶ ገላግሎኝ እንጂ ከዛች እርኩስ ሀሙስ በፊት ስንቴ እከስም ነበር፡፡ ደውዬላት ሺህ ግዜ ስልኳ ከጠራ በኋላ ተይዟል ብሎኛል፡፡ ሺህ ግዜ ሺህ ምክንያት ፈጥሬላት ሺህ ግዜ አልፌዋለሁ፡፡ ካልደወልኩ ቀኑ የማያልቅላት ተገልብጣ ጥሪዬን ሆን ብላ መዝጋት ስትጀምር አንድም አልጠረጠርኩም፡፡ ቀጥሪያት መምጣት ካቆመች ወራት ሄደዋል፡፡ ስትፈልግ ብቻ ከግማሽ ሰዓት ላነሱ ደቂቃዎች ታገኛለች፡፡ እኔ ሞኙ ያቺም ግማሽ ሰዓት ዐለሜ ናት! እሷ ናታ! ምን ብዬ አማርራለሁ?
ከሁሉም የሚገርመኝ የአክስቷ ልጆች፣ ጎረቤቶቿ እና የጎረቤቶቿ ልጆች መብዛታቸው፡፡ ደሞ ሴት ዘመድና ጎረቤት የላትም እንዴ? ወንድ ላይ ተንጠልጥላ ባየኋት ቁጥር አንዳች ስጋዊና ቤተሰባዊ መስር አጠገቧ ካለ ሰው ጋር ተዘረጋለች፡፡ እኔ እንኳን ምክንያ ደርድራ እንዲሁም ከዐይኔ በላይ አምናታለሁ፡፡ አፍቃሪነት ይሄ መሰለኝ፡፡ 6ኛ ምናምን የሚሉት ስሜታችን እውነቱን ከአጋጣሚ እየገለጠልን ተፈቃሪን ላለማጣት እውነተን የመግፋት ነገር……. የሆነ የሆነውን ሽሮ የሌለን መልካምነት ከገዛ ልብ እያደሉ የመልካምነት ኒሻን ለማያፈቅር የመስጠት አይነት፡፡ ልክ እኔ እንዳደረኩት! ይሁዳነቷን ገና ስማ ስላልሸጠችኝ የአለማመኔ ነገር…… ምናልባትኮ እሷ ሳትነግረኝ መንገድ እንደጀመረች ሁሉ እኔም እንዳደርገው እየተበቀች ይሆናል፡፡ እኔ እና እሷ ግን የተለያየን ነን፡፡ እኔ አፍቃሪ፣ እሷ ይሁዲ!
ብቻ ከሁሉም እየገረመኝ ያለው ነገር ንዴቴ ችሎ ለሷ ያለኝን ፍቅር ማክሰም ያለመቻሉ ነገር ነው፡፡ ለዚህም ይመስላል ያወቅኩትን እውነት ተቀብዬ መዋጥ የተሳነኝ፡፡ ከእውነት መታገል ደሞ የማበድ ጠርዝን ይዞ መራመድ ነው፡፡ በዚያ ላይ መርሳት የሚሳነው አቅሉን ከመሳት ብዙ አይርቅም፡፡ በርግጥ አላበድኩም! ባለፍንበት ሳልፍ የነገርኳትን ቀልዶች እንዳለች ሁሉ ደግሜያቸው በሀይል ስቄያለሁ፡፡ ሰፈር የምንቀመጥበት ቦታ ሆኜ ብትኖር የምነግራትን እንዳለች ሁሉ ደአውርቻለሁ፡፡ ከምናዘወትረው ካፌ እየሄድኩኝ ሁለት ኬክ አዝዣለሁ፡፡ ከተለያየንበት ወንበር ሀሙስን እየጠበቅኩኝ በሌለችበት ለምኛታለሁ፡፡ ግን አላበድኩም! ምክንያቱም አውቃታለሁ፡፡ ድሮ ገና ያፈቀርኩት የሆነ እሷነቷ ነበር፡፡ የእውነተኛ ነፍሷ አማናዊ የማንነቷ ተቀፅላ የሆነ እሷነት! ዛሬ ባይመልሳት የምናደርገውን መላልሼ ሳደርግ የሆነ ቀን አለስልሶ ወደኔ ያመጣት ይሆናል፡፡ የሆነ ቀን…… ዛሬ ወይንም ነገ ያልሆነ የሆነ ቀን!

By Lewi @lee_wrld777

@wegoch
@wegoch
@paappii
[…ማኀበራዊ ዝ-ሙ-ት አዳሪነት…]

—መግቢያ—

የአንዳችን ትራጀዲ ለአንዳችን ኮሜዲ ነው። አንተ ትስቅ ዘንድ እኔ ማልቀስ አለብኝ። የዘለለት ስቃይኽና መከራኽ ለአንዳንዶች ስሙ «ፖለቲካ» ነው —ይዝናኑበታል፣ ይተነትኑታል፣ ይነግዱታል፣ ይበሉበታል። መጣላትም ለትርፍ ነው፣ መታረቅም ለትርፍ ነው። እንባም ጥበብ ነው፣ ኀዘንም ሒሳብ ነው።

መንገዱ ይለያይ ይኾናል እንጂ ማኀበራዊ ዝ-ሙ-ት አዳሪነት ውስጥ ነን። አንዳንዱ ገላውን ይሸጣል፣ አንዳንዱ ዕውቀቱን ይሸጣል፣ አንዳንዱ ክፋቱን ይሸጣል። አንዳንዱ በክርስቶስ ስም ይነግዳል፣ አንዳንዱ በሰይጣን ስም ያተርፋል። አንዳንዱ መናፍቃን እያለ ይበለጽጋል፣ አንዳንዱ አሕዛብ እያለ ይከበራል። እምነትና ተስፋ በገበያው ዋጋ ይመነዘራሉ … ፍቅር ግን አልፎበታልና ወደዚያ ይጣላል።

— አንድ ታሪክ እዚኽጋ…—

እናት ልጇ የት ይግባ የት ሳይታወቅ ድንገት በወጣበት ጠፍቶ ይቀራል። ወሬ ስታፈላልግ መንግሥት አሥሮታል ትባላለች። የቀበሌው ሊቀመንበር ጋር አቤት ትላለች። ቀበቶውን እያላላ «ያው መቼም አሠራሩን ታውቂዋለሽ» አላት። ደነገጠች። «መፍትሔው የወረዳው ሊቀመንበር ጋ ነው፣ እርሱ ጋር መቅረብ ከፈለግሽ ለአልጋ ተስማሚኝ» አላት —አማራጭ አልነበራትም። ከነድንጋጤዋ ተስማማች።

የወረዳው ሊቀመንበር ጋ ቀረበች። እርሱም እንደ በፊቱ «የአውራጃው ገዢ ጋ እንዳደርስሽ አብረን እንተኛ» አላት። ድንጋጤዋ አኹንም አለ። ቢኾንም ጥቂት ለምዳዋለች።

የአውራጃው ገዢ ጋ ቀረበች። ተኛችው። እርሱ ወደ ሀገረ-ገዢው ላካት —እዚያም ተኛች። ልጇን ፍለጋ በየቦታው መውደቅን ሥራ አለችው —በቃ ለመደችው። ተዋረዱን እያለች እያለች ንጉሡ ጋር ደረሰች። ንጉሡ ፊት ቀርባ እጅ እንደነሣች ምንም ሳይላት ልብሷን ማውለቅ ጀመረች —እንደቀደሙት መስሏት ። በሀገሩ እንዲህ ያለ ግፍ እንዳለ ያልጠረጠረው ደግ ንጉሥ ተደናግጦ

«ምን ኾነሻል? ልብስሽን ለምን ታወልቂያለሽ?» ሲላት እዚያው ስቅስቅ ብላ ማልቀስ ጀመረች።

«ምነው?»

«ንጉሥ ሆይ ምነው አልወደዱኝም? ልጄን አስፈታ ዘንድ ምኔን ልስጥዎት? እባክዎት»

— መውጪያ —

አስገድዶ መድፈር ግዴታ እጅ መያዝ፣ አንገት ማነቅ፣ በኃይል ጭን መክፈት ብቻ አይደለም። እንዲኽ በአቅም ማጣት የተስማማናቸው፣ ሳንወድ በግድ «እሺ» ብለን ከአልጋ የወደቅንላቸው፣ ከአልጋ የጣልንባቸው፣ የቅድስና ስም የሰጠናቸው ኃጢአቶች አሉን። መቃወም፣ ማፍረስ ፣ demythologize ማድረግ ያለብን እርም አለ —ማኀበራዊ ዝ-ሙ-ት አዳሪነት

By henock Bekele

@wegoch
@wegoch
@paappii
2024/09/21 18:02:07
Back to Top
HTML Embed Code: