Telegram Web Link
አንዳንድ ቀን ይበለኝ የደስታዬ ጠላት እኔ ነኝ እላለሁ ።የማፈቅራት ልጅ ነበረች ፤ ቅብጥ
ያለች ፤ ጨዋታ አዋቂ ነፍሷ በጥንጥ ነገር የሚደሰት ። ቁም ነገሬ ለምለው ነገር ያላት
ቸልታ ነገ ለምመሰርተው ኑሮ ተፅዕኖ እንዳለው እጠረጥራለሁ ። ጥርጣርዬ ግንኙነታችን
ወደ ትዳር እንዳያድግ አገደኝ ።
መልክ አይቼ፤ ዳሌ አይቼ ፤ ሳቄን ብዬ እንዴት ኑሮ እመሰርታለሁ ብዬ ነው የተውኳት።
አብረን ሆነን ስኮምክ እንደትንሽ ልጅ አፏን ከፍታ ደረቴ ላይ ተለጥፋ ታሽካካዋለች ፤ አሳሳቋ
የድብርት ፤ኩርፍያን ይገነብራል።
እኔ ጅንኑ ከእሷ ጋ ስሆን ነፃነቷን ታፈናጥርብኛለች ፤ እላፋታለሁ ፤ ተው እያለችኝ ለልፊያ
እራሷን ታዘጋጃለች ፤ ስታገላት እየሳቀች በሳቋ መሃል "ጅል ነህ እንዴ"? ትለኛለች
ጅል ላልሆነ ሰው ጅል ሲባል የበለጠ ያስቃል የበለጠ ያጃጅላል።
ኩርፊያዋ አይቆይም ፤ ረስታው ታወራኛለች እያወራች መሃል ላይ "ኤጭ ለካ አኩርፌ ነበር
በቃ ምስኪን ስለሆንኩ ትጫወትብኛለህ ኣ"? ትለኛለች አንገቷ ስር ሽጉጥ ብዬ ስስማት
"እሰ..ይ" ትለኛለች ።
እንስቃለን ።
ቁጠባ፤ እቅድ ፤ ነገር ማወሳሰብ ጠላቷ ነው አትችልበትም ። ጫማሽን እንሽጠው እና
እንጠጣበት ብላት አረ ? ጥሩ ሃሳብ ከማለት ውጪ አትግደረደርም ።
አውጥቼ ፤ አውርጄ ፤ ብልጣ ብልጥነቴን ተጠቅሜ ተውኳት።
ሌላ ጠበስኩ
አገባሁ።
ጨዋ ፤ ጠንካራ ፤ነብሴ ከነብሷ የማይናበብ
ሰው ስለወደደልኝ ፤ ጨዋ ነች ብዬ ስላሰብኩ አገባኋት ።
ባለ መነፅር ፤ እርግት ያለች ፤ ለእያንዳንዱ ነገር ማብራሪያ ያላት ጎበዝ ታታሪ ነች ሚስቴ ።
ደስ አለኝ ራሷን የቻለች ልጅ፤ ትጉህ ሰራተኛ እና የሚጠቅማት ላይ የምትመሰጥ በመሆኗ
ነው የመርጥኳት ።
ነገር ግን
ድሮ ቀልድ እችል እንደነበረ ሁላ ነው ያጠፋችብኝ ። ኑሮዬ ሎጂክ ሆነ ። እሷ ጋ ሁሉ ነገር
ቁምነገር ነው። ልለውጣት ብሞክር ብጣጣር ከሆነችው ነገር ፈቀቅ አልል አለች ።
ረጅም ማሽካካት ፤ ልግጫ ፤ ልፍያ ፤ ቀልድ ድራሹ ጠፋ ።
ከስራ መልስ ሌላ ስራ ነው። እራት ይቀርባል ፤ እንበላለን። ቀስ ብለን ልክ እንደ ምግብ
ተሰናድተን ልክ ለደሞዝ እንደሚሰራ ስራ አንዳንዴ እንዋሰባለን።
ወሲባችን ልፍያ የለው ፤ ግፍያ የለው ፤ ችኮላ የለው፤ መላላስ የለው ፤ መቀባጠር የለው ፤
ሁካታ የለው፤ ቅድመ ወሲብ እና ድህረ ወሲብ በወሲቡ ዙርያ ቀደዳ የለ፤ ሁሉ ነገር እሷ ጋ
ቁምነገር ነው ።
ቁጥብ ያለ ነው ሁሉ ነገሯ ።
በቃ ኑሮን ካለ እቅዴ ኮስተር ብሎ ከሚኖሩት ውስጥ ተቀላቀልኩ ። ጭምትር ማለቷን
ላላቅቃት ሞከርኩ ። በሙከራዎቼ መንፈሳዊ ጥቅሶች ፤ ባህል፤ እሴት፤ ወግ እየሞጀረች
ኩም ታደርገኛለች ።
ዝግጁ ያልሆነን ሰው እና ፍቃድ የሌለው ፍጡርን እንደ መቀየር ከባድ ነገር የለም ።
ብዙ ጭቅጭቅ የለ ፤ ብዙ ንዝንዝ የለ ። የማሽን ኑሮ እየኖርኩ ነው።
አንዳንዴ
ምን አለ የድሮ ፍቅረኛዬን ባገባት ኖሮ እላለሁ። እሺ ይሁን እጣ ፈንታችን አልገጠመም ።
ያን የመሰለ ማሽካካት ፤ልፊያ ፤ልግጫ ፤ ቡረቃ አይቼው ባልነበር ፤ ዛሬ እንደዚህ መች
አይኔ ላይ ውል ይለኝ ነበር?!
እጦትን ከሚያጎሉ ነገሮች አንደኛው አግኝቶ ማጣት ነው ።
ቁም ነገረኛዋን ሚስቴን ማግባቴ ትክክል ነኝ አይደለሁም አላቅም።
ኑሮዬ ስራ ሲሆን የድሮ ኑሮዬ ንፍቅ ይናፍቀኛል።
ሚስቴ ጋ ከጓደኛ ጋ መሰብሰብ ፤ ማምሸት መቀምቀም ምቾት አይሰጣትም በዚህም
ምክንያት በአጋጣሚ ካልሆነ አላመሽም አልሰበሰብም አልቀመቅምም።
ጥንካሬዋ እና ጉበዝናዋ የኑሮ ሸክሜን ስታቀልልኝ አይ እሰይ እንኳን ያገባኋት እላለሁ።
ነፃ መሆን ፤መፍታታት ፤መሽካካት ነፃ አበላለግ ከአጋሬ ጋ ሲያምረኝ የትላንቷ እጮኛዬ
ትናፍቀኛለች ።
ማስታወሻ
እጅግ የበዛ እጅግ እንዳነሰ ያህል ነው ።


@getem
@getem
@paappii

#Adhanom Mitiku
ልጅነት...
*
በልጅነታችን ሁላችንም ለወላጆቻችን ጨዋ ነበርን። ሼባዎቹ ጠጅ ቤት በተጣሉ ቁጥር
<<ከእገሌ ልጅ ጋር አትዋል!!>> የሚል ሀርድ ይበጨቁብናል። ጥሎብን ደግሞ
የተከለከልነውን ጓደኝነት ነፍሳችን አጥብቃ ትሻለች። በልጅነቴ ኩኩሻ ከተባለ ልጅ ጋር
እንዳልውል ማዕቀብ ተጥሎብኛል። እሱም እንደኔው ከእኔ ጋር እንዳይውል ማስጠንቀቂያ
ተሰጥቶታል። በእዚህ ምክንያት ለአባቶቻችን <<ጦጣው>> የሚል የጋራ ቅጽል ስም
አውጥተንላቸው በድብቅ እንገናኝ ነበር።
አንድ ቀን ጨፌ ኳስ ልጫወት የጨርቅ ኳሴን ታቅፌ በበራቸው ላይ እያለፍኩ ሳለ
ከግቢያቸው ውስጥ የኩኩሻን ድምጽ የሰማኹ መሰለኝ።
<<ኩኩሻ!>> ብዬ ተጣራሁ።
ከግቢው ውስጥ <<እ!>> የሚል ድምጽ ሰማሁ።
<<ኳስ አትጫወትም? ጨፌ እየሄድኩ ነው!>>
መልስ ሳጣ በድጋሚ <<ምነው? ጦጣው አለ እንዴ?>> ብዬ ጠየቅኹ።
ይሄኔ ከግቢው ውስጥ <<ኧረ አለሁ..አለሁ...ግባ!>> የሚል የአባትየውን ጎርናና ድምጽ
ተሰማ።
ከእዚያ በኋላ እንዴት ነፍሴ እስክትወጣ በርሬ ቤት እንደገባሁ እኔና እግሬ ብቻ ነን
የምናውቀው። ሁለቱ ሼባዎች እስኪታረቁ ድረስ የእኔና የኩኩሻ ጓደኝነትም ተቋርጦ ቆየ።
**

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Tilahun girma ango
አክስቶቼ እና ላሞቻቸው
-----
ጸሐፊ: አፈንዲ ሙተቂ
------
ስለሁለት አክስቶቼ ላወጋችሁ ነው። አሚና ኢብራሂም (በቀኝ) እና ሐኒፋ ሼኽ ሙሐመድ ረሺድ ይባላሉ፡፡ “ሐኒፋ” የአባቴ እህት ስትሆን መላው ዘመዶቿ እና የሰፈሩ ህዝብ “አዴ” እያለ ነው የሚጠራት፡፡ ከዚህ ቀደም “ኦነግ እና ኢህአዴግ በአንድ ቀን ጦርነት” በሚል ርዕስ በጻፍኩት ጽሑፍ ያወጋኋችሁ ጦርነት የተጀመረው በርሷ ግቢ ውስጥ ነው፡፡ አሚና ኢብራሂምም የስጋ ዘመዴ ናት፡፡ ይሁንና አያቴ (ሼኽ ሙሐመድ ረሺድ) ያገቧት የመጨረሻ ሚስት እርሷ በመሆኗ የሼኽ ሙሐመድ ረሺድ ልጆች “አዮ አሚና” እያሉ ነው የሚጠሯት፡፡ እኛም የአባቶቻችንን ልማድ በመከተል “አዮ አሚና” እያልን እንጠራታለን፡፡

እነዚህ አክስቶቼ ልጅ በነበርኩበት ዘመን በርካታ ከብቶች ነበሯቸው፡፡ በግቢዎቻቸው ጥግም ለከብቶች የተሰሩ ሰፋፊ በረቶች ነበሯቸው፡፡ ባለፈው በጥቅምት ወር 2008 ስዘይራቸው ግን የሁለቱም በረት በቦታው አልነበረም፡፡ “ከብቶቹ ወዴት ጠፉ?” ብዬ ስጠይቃቸው ልዩ ልዩ ምክንያቶችን ዘረዘሩልኝ፡፡ ዋነኛው ምክንያታቸው “ድሮ የግጦሽ ስፍራ የነበሩት መስኮች በሙሉ ወደ እርሻ ማሳነት ተቀይረዋል፤ ስለዚህ ከብቶቹን ለማብላት ወደ ሩቅ ስፍራዎች መሰማራት ግድ ይላል፤ አሁን ባለው ሁኔታ ግን ያንን ማድረግ አንችልም፤ በመሆኑም ከብቶቹን ለመሸጥ ተገደድናል” የሚል ነው፡፡ ምክንያታቸው አሳማኝ ቢሆንም ከሁለቱ ቤቶች እንደ ድሮው ትኩስ ወተት በ“ቀቤ” ለመጠጣት ባለመቻሌ አዘንኩ! እስቲ ስለነዚያ ከብቶች ያለኝን ትዝታ በትንሹ ላውጋችሁ፡፡
*
በዚያ ዘመን በሰፈሩ የሚኖረው እያንዳንዱ ቤተሰብ ጥቂት የማይባሉ ከብቶች ነበሩት፡፡ በዘመኑ ወግ መሰረት ሴት ከብቶች (ላም እና ጊደር ) እና ጥጆች ባለቤትነታቸው የእመወራዎች ነው፡፡ ከነዚያ እመራዎች ሁሉ በከብቶች ብዛት የምትበልጠው ደግሞ “አዮ አሚና” ነበረች፡፡ በበረቷ ከሚያድሩት ላሞች መካከል በአንድ ጊዜ የሚታለቡት ብቻ አስራ አምስት ያህል ይሆናሉ፡፡ በመሆኑም ከቤቷ ወተት፣ ቅቤ እና እርጎ ጠፍተው አያውቁም፡፡ አያቴን ሊዘይሩ ለሚመጡ እንግዶች የሚቀርበው “ሆጃ” የሚፈላው በአብዛኛው ከርሷ ቤት በሚታለበው ወተት ነበር፡፡ ልጆች በቤታቸው እንጀራ እና ቂጣ ብቻ አግኝተው ማባያ ሲያጡ ወደርሷ ይመጡና ወተትና እርጎ ይጠይቃሉ፡፡ ለልጃገረዶችም ጸጉራቸውን የሚሰሩበትን ቅቤ ትሰጣቸው ነበር፡፡

በዘመኑ ወግ መሰረት ከብቶችን በስም እየለዩ መጥራት የተለመደ ነው፡፡ ታዲያ ለከብቶች የሚሰጠው ስም በአብዛኛው የከብቱን ቀለም እና ቁመና የተከተለ ነው፡፡ የ“አዮ አሚና” ስም አሰያየም ግን ከዘመኑ ልማድ ወጣ ያለ ነው፡፡ “መጋል” እና “ጉራቻ” ከተሰኙት ሁለት ላሞች በስተቀር ሌሎቹ ከብቶች ለየት ባሉ ስሞች ነበር የሚጠሩት፡፡ ለምሳሌ “ደንገሹ”፣ “ኩሜ”፣ “ባቲ”፣ "መገርቱ" ፣ “ሂና” “ኩሊ”፣ “ኩሪ”፣ "ዱኮ" ወዘተ…. በመሳሰሉ ስሞች የሚጠሩ ከብቶች ነበሯት፡፡ ስያሜዎቹን እንዴት እንደምታወጣቸው አላውቅም፡፡ ታዲያ አዮ አሚና ከብቶቿን ስታነጋግራቸው ዋዛ እንዳትመስላችሁ!! እያንዳንዱን ከብት እያከከችው እንደ ሰው ልጅ ታዋራው ነበር፡፡
*
የአዴ (ሐኒፋ ሼኽ ሙሐመድ ረሺድ) ከብቶች በብዛት የአሚናን ያህል አይደሉም፡፡ ይሁንና ከሰፈሩ ከብቶች ሁሉ ለኔ በጣም የሚታወሱኝ እነርሱ ነበሩ፡፡ ምክንያቱም ነፍስ ካወቅኩ በኋላ ወደሰፈሩ በምሄድበት ወቅት የማርፈው እርሷ ዘንድ ስለሆነ ነው፡፡

ከነዚያ ከብቶች መካከል በጣም ቁጡዋ “ዳለቲ” ትባላለች፡፡ “ዳለቲ” ቀንድ የላትም፡፡ ሆኖም በድቡልቡል ጭንቅላቷ በቴስታ “ገጭ” እያደረገችን ከመሬት ላይ ትፈጠፍጠን ነበር፡፡ ከልጅነት እስከ ጉልምስና ዘመኗ ድረስ የምታውቃት አክስቴ እንኳ ቀኑ ሲመሽ ዳለቲን ይዛ በማደሪያ ስፍራዋ ላይ አስራ አታውቅም፡፡ “ዳለቲ” የማትነካቸው ሁለት ልጆችን ብቻ ነው፡፡ አንደኛው ሙሐመድ አሕመድ (ነጋሺ) የሚባለው የራሷ (የአክስቴ) ልጅ ሲሆን ሌላኛው “ናጂ በደው” ይባላል፡፡ ስለዚህ ዳለቲን ለማሰር ከተፈለገ እነዚያ ልጆች የግድ መገኘት ነበረባቸው፡፡
“ዳለቲ”ን የወደለቻት “ጋሬ” የምትባል ላም ናት፡፡ ይህቺ ጋሬ “ጄብሎ” የተሰኘ ሌላ ላምም ወልዳለች፡፡ ታዲያ ይህቺ “ጄብሎ” በውጊያ እናቷን ታሸንፋታለች፡፡ አክስቴ የቡና አተላ (ረጃ) እና ድርቆሽ ለጋሬ በምትሰጥበት ጊዜ “ጄብሎ” እያባረረቻት ትነጥቃለች፡፡ ሆኖም “ጄብሎ” ምንም ቀንድ ያልነበራትን ዳለቲን አትችላትም፡፡ በመሆኑም ዳለቲ ከእናቷ አፍ ድርቆሹን የነጠቀችውን “ጄብሎ”ን ታባርርና ለራሷ መብላት ትጀምራለች፡፡ ይሄኔ ግን የድርቆሹ የመጀመሪያ ባለቤት የሆነችው “ጋሬ” ከተፍ ትላለች! ምክንያቱም እርሷ ጄብሎን ባትችላትም ቀንዳ አልባ ለሆነችው ዳለቲ ትበረታለችና! እናም ከጅምሩ ለርሷ የተሰጠውን ድርቆሽ ያስመለሰችው “ጋሬ” ዘና ብላ መመገብ ትጀምራለች፡፡ ይሁንና ምንም ያህል ሳይቆይ “ጄብሎ” እንደገና ከተፍ ትልና እንደለመደችው “ጋሬ”ን በማባረር ድርቆሹን መብላት ትጀምራለች፡፡ አንድ ጊዜ ያህል ዋጥ ካደረገች በኋላ ግን “ዳለቲ” ከተፍ ትልና ድርቆሹን ትነጥቃታለች፡፡ “ዳለቲ” መብላት ስትጀምር ደግሞ እንደገና “ጋሬ” ትመጣለች፡፡ እንደገና “ጄብሎ”፤ እንደገና “ዳለቲ”፤ እንደገና “ጋሬ”!
አክስቴ ለሶስቱ ከብቶች በተለያየ ቦታ ድርቆሽ ብታስቀምጥላቸው እንኳ ላሞቹ ጥላቸውን አይተውም፡፡ አንደኛው ከብት ለርሱ የተሰጠውን ከማላመጥ ይልቅ ሌላኛውን ነጥቆ መብላቱ ያስደስተዋል፡፡ ስለዚህ አክስቴ የከብቶቹን ጥል ለማስቀረት ሌላ ዘዴ ፈጠረች፡፡ ላሞቹ ከማደሪያቸው ሳይፈቱ ድርቆሽና ውሃቸውን መስጠት!! በዚህ ዘዴ ሁሉም ተስተካከለ፡፡ ሆኖም አንዳንዴ አክስቴ በቤቷ በሌለችበት ጊዜ የአክስቴ ልጆች የሶስቱን ከብቶች ጥል ለማየት ሲሉ ብቻ መመሪያውን እየጣሱ ከብቶቹን ይፈቷቸው ነበር፡፡ እናም ጋሬ፣ ዳለቲ እና ጄብሎ ለረጃ እና ለድርቆሽ ሲሉ እየተቁነጠነጡ ውጊያ ይገጥማሉ፡፡

ይህ የሶስቱ ላሞች ጥል ለረጅም ጊዜ ሲገርመኝ ነበር፡፡ አንዱ ከብት አንደኛውን ብቻ ይችለዋል፤ ሌላኛውን ለማባረር ግን ወኔ የለውም፡፡፡ ይህ ሊሆን የቻለው እንዴት ነው…? ሁለቱንም ላሞች የወለደችው “ጋሬ” ሌሎቹን ማሸነፍ ያልቻለችበት ምክንያትስ ምንድነው…? ቀንድ ያላት “ጄብሎ” ቀንድ አልባዋን “ዳለቲ”ን የምትፈራበት ምክንያትስ ምንድን ነበር….?

መልሱን በጭራሽ አላውቀውም!! ይሁንና በኋለኛው ህይወቴ ተመሳሳይ አጋጣሚዎችን በማይበት ጊዜ ሁሉ የነዚያ ከብቶች ጥል ወደ አዕምሮዬ ይመጣል፡፡
*
የአዴ” (አክስቴ) ከብቶች የሚጠሩባቸው ስሞች ከአዮ አሚናም ይበልጥ ያስገርማሉ፡፡ ለምሳሌ ከላይ የጠቀስኳት “ጋሬ”ን እና “ጋሬ” የወለደቻቸውን ብቻ በስም ላስተዋውቃችሁ፡፡

በሀረርጌ ኦሮሞ ባህል መሰረት “ጋሬ” የሚባለው ሰውነቱ በጥቁር ወይም ቀይ ቆዳ ተሸፍኖ በጭንቅላቱ ላይ ብቻ ነጭ የሆነ ከብት ነው፡፡ “ጋሬ” ግን ሙሉ በሙሉ ቀይ ነበረች፡፡ በዚህ ረገድ ከሌሎች ጋሬዎች ሁሉ የተለየችው እርሷ ብቻ ነበረች፡፡ አክስቴ ለምን ከህዝቡ ልማድ ውጪ ለላሚቱ “ጋሬ” የሚል ስም እንዳወጣች ስጠይቃት “ጋሬ የእናቷ ስም ነበር፤ እናቷን በጣም እወዳት ነበር፤ ብዙ ወተት ያለስስት የሰጠችኝ ላም ናት፤ ነገር ግን የአባ ጎርባ በሽታ ገደለብኝ፤ ስለዚህ እርሷን ለማስታወስ ብዬ ለልጇ “ጋሬ” የሚል ስም አወጣሁ” አለችኝ፡፡
(ከላይ ካለው ጽሑፍ የቀጠለ)
----
“ጋሬ” የወለደቻት የመጀመሪያ ከብት “ቤጆ” ትባላለች፡፡ “ፔጆ 404” የምትባለው የቤት መኪና “ፋሽን” በነበረችበት ዘመን ስለተወለደች ነው እንዲህ ተብላ የተጠራችው፡፡ ሁለተኛዋ ቀንድ አልባዋ “ዳለቲ” ናት፡፡ ይህችኛዋ በቀለሟ “ዳለቻ” ስለነበረች ነው እንዲያ የተባለችው፡፡ ሶስተኛዋ “ጄብሎ” ናት፡፡ አክስቴ ስሙን ከየት እንዳመጣችው አላውቅም፡፡ ሆኖም ወደ ከተማ መጥታ “ጀብሎ” የሚባሉ ሲጋራ አዟሪዎችን ካየች በኋላ ስሙን ለከብቷ እንዳወጣችው እጠረጥራለሁ፡፡ አራተኛው “ሌንጮ” ይባላል፡፡ ይህኛው ወይፈን ነው፡፡ “ሌንጮ” በልጅነቱ የተለየ ስም የነበረው አይመስለኝም፡፡ በሂደት ግን የሰፈሩን በሬዎች እየገጠመ ስላሸነፋቸው “ሌንጮ” የሚለውን ስም አግኝቷል (“ሌንጮ” በአማርኛ “አንበሳው” እንደማለት ነው)፡፡

አምስተኛዋ “ዲምቱ” ትባላለች፡፡ “ቀዮ” እንደማለት ነው፡፡ ይህቺኛዋ “ኦነግ እና ኢህአዴግ በአንድ ቀን ጦርነት” በሚል ርዕስ በተጻፈው ተከታታይ ጽሑፍ ውስጥ ያስተዋወቅኳችሁ ላም ናት፡፡ በዕለቱ በግቢው ከነበሩት ከብቶች መካከል በጥይት ተመትታ ለመሞት የበቃችው እርሷ ብቻ ናት፡፡ ስድስተኛዋ አንዲት ብስል ቀይ ጥጃ ናት፡፡ ይህቺኛዋ “ደሃቦ” የሚል ስም የነበራት ሲሆን ስሙን የሰጣት ደግሞ በወቅቱ ከብቶቹን ያግድ የነበረው “ሙሐመድ አሕመድ” (ነጋሺ) የተባለው የአክስቴ ልጅ ነው፡፡ ሆኖም በዚህ ስም ላይ ከባድ ውዝግብ ተቀስቅሷል፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡
ስያሜው በቅድሚያ የተሰጠው ከቢር ያሕያ የተባለ የአክስቴ ጎረቤት ለወለዳት አንዲት ቀይ ልጅ ነው፡፡ መሐመድ አሕመድ ግን ስሙ በጣም ደስ አሰኘውና በዚያው ሰሞን “ጋሬ” ለወለደቻት ጥጃ ሸለማት፡፡ የከቢር ያሕያ ሚስት ይህንን ስትሰማ ተቆጣች!! “እንዴት በልጄ ስም ከብቱን ይጠራል?” በማለት መንደሩን ቀወጠችው፡፡ መሐመድ አሕመድ ጥጃዋን በዚያ ስም መጥራቱን እንዲተው ቢነገረው “እምቢ” አለ፡፡ አክስቴ ብትለምነው፣ ብታስፈራራው፣ ብትገርፈው ልጁ በእምቢታው ጸና፡፡ የከቢር ያህያ ሚስት አክስቴ “ሆን ብላ ያደረገችው ነው” ባይ ሆነች፡፡ አክስቴ ሐቁን ብታስረዳት በጭራሽ አልሰማ አለች፡፡ በመጨረሻም ሽማግሌዎች በነገሩ ገብተው መሐመድን ገሰጹት፡፡ መሐመድም ለጊዜው ግሳጼውን የተቀበለ መሰለ፡፡ ነገር ግን በዚያ ስም ፍቅር ስለተለከፈ አንድ መላ ፈጠረ፡፡ ደሃቦን በአማርኛ መንዝሮ “ወርቄ” በሚል ስልት ጥጃዋን መጥራት ጀመረ፡፡ አማርኛ የማትሰማው የከቢር ያህያ ሚስትም ከቁጣዋ ረገብ አለች፡፡ መሐመድ አሕመድም ለ“ደሃቦ” የነበረውን ፍቅር በ“ወርቄ” በኩል ተወጣ (“ደሃብ” በዐረብኛ ወርቅ ማለት ነው፤ ሶማሊዎች ስሙን ሲያቆላምጡት “ደሃቦ” ይላሉ”)፡፡
-----
እነዚያ በፍቅር እያናወዙ ጎረቤት የሚያጣሉ ከብቶች ዛሬ የሉም፡፡ ወተት “በሽበሽ” የነበረበትን ያንን ደግ ዘመን አልፈን የገጠሩ ህዝብም እንደ ከተሜው ገበያ እየሄደ ወተት በኩባያ ከሚገዛበት ዘመን ላይ ደረስን፡፡ ይህም እንግዲህ ኑሮ ነውና “አልሓምዱሊላህ” እንላለን፡፡

በነገራችን ላይ "አዮ አሚና" አሁን በሕይወት የለችም። ይህንን ጽሑፍ ከጻፍኩ በኋላ በጥር ወር 2010 አርፋለች። አላህ ይርሓማት። "አዴ" ግን ዛሬም አለች። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ድሬ ዳዋ ከከተመው ልጇ ዘንድ እየኖረች ነው። ረጅም ዕድሜ ይስጣት።
እኛንም ቸር ያቆየን!
-----
አፈንዲ ሙተቂ
ጥቅምት 30/2008 ተጻፈ።
ገለምሶ- ምዕራብ ሀረርጌ

@wegoch
@wegoch
@paappii
አታምጣው ስለው አምጥቶ ቆለለው #6

“ማት? አንተ እኔን ብትሆን ምን ታደርግ ነበር ?" አልኩት ወንድሜን የሆነውን አንድ በአንድ ከነገርኩት በኋላ።

"እኔ አንቺን ልሆን አልችልም! ኸረ ማንም አንቺን ሊሆን አይችልም! እህቴ ማንም ያንቺ ልብ የለውምኮ!! ግን አያድርገውና ባንቺ ቦታ ብሆን ታውቂኛለሽ እዛው አንድ አይኑን በቦክስ ጠብቼው ሁለት ስንቅ ታመላልሺ ነበር።" አለኝ እየሳቀ።

"ማት የምሬን ጨንቆኝኮ ነው!"

"እህቴ ? " አለኝ ..... አለው የሆነ የሚያየኝ አስተያየት .... የስስት ዓይነት! በስሜ ጠርቶኝ አያውቅም። 'እህቴ' ነው የሚለኝ።

"ያለሽ እውነቱን ነው። ካንቺ የተሻለ ምክንያታዊ ሆኖ የሚወስን ሰው እኔም በአቅራቢያዬ አላውቅም! የሆነማኮ እነእማዬ ከእኔ ተደብቃው ያስተማሩሽ ጉብዝና አለ"

"አያድርገውና ብትሞትስ?" አልኩት

"ብትሞት ነው ወይስ ብትድን ይበልጥ ያስፈራሽ?"

"ማለት? "

"ማለትማ ገብቶሻል! ቅድም ከባባ ጋር ስትሆኚ የነበረውን አይቻለሁ። ውስጡ ካለነው በአንድ ጣት የማንሞላ ሰዎችሽ ውጪ ማንም እንዳይገባበት ደራርበሽ ያጠርሽውን አጥር ዘው ብሎ ገብቶብሻል። ያን አጥርሽን ሲያልፉ .... ስስት አታውቂም ነፍስሽንም : ያለሽንም ትሰጫለሽ! ከዛ ሲሄድብሽ ያለውን መሰበር ትፈሪዋለሽ!"

እሱ ክሽን አድርጎ በቃላት ሲያስቀምጠው የሆነ ያሳከከኝን ቦታ በትክክል ያገኘው 'አዎ !...እሱጋ' የሚያስብል አይነት ስሜት ተሰማኝ። የገለፀበት መንገድ ገርሞኝ

"አይገርምም! ፈሪ አድርጎኛል!" አልኩኝ

"እሱ ነው ፈሪ ያደረገሽ? እሱም በግድ አጥርሽን አልፎ አይደለም ውስጥ ያገኘሽው? ስታውቂው ውጣልኝ የማትዪበት ደረጃ ደርሶ አይደለም የተቀበልሽው? አስቢው እህቴ? መቼ ነው ከቤተሰብ ውጪ ለመጨረሻ ጊዜ ጓደኛ ኖሮሽ የሚያውቀው? ከአቢ በኋላ ሁሌም እንዲህ ነበርሽ። "

አቢ የአባዬ ታናሽ እህት የአክስቴ ልጅ ናት። እሷ እኛ ቤት ከመምጣቷ በፊት ምን ዓይነት ልጅ እንደነበርኩ አላስታውስም። አክስቴ በልጅነቷ ከትዳር ውጪ ነበር የወለደቻት። ጣሊያን ቪዛ አጊንታ ስትሄድ አቢ እኛ ቤት ስትመጣ 14 ዓመቴ ነው። በወራት ነበር የምትበልጠኝ። እህትም ጓደኛም አገኘሁ። እኔ የምማርበት ትምህርት ቤት ገባች። ለአራት ዓመት ከእርሷ ተለይቼ የሄድኩበትን ቦታ፣ ከእርሷ ተለይቼ የበላሁትን ምግብ፣ ሰምቼ ወይ አድርጌ እሷ የማታውቀው ነገር አላስታውስም። ውጤት አምጥተን የተለያየ ዩንቨርስቲ ሲደርሰን አይኖቼ እስኪፈርጡ አለቀስኩ። በዚህ መሃል እናቷ መጣች። እናቷ ስትመጣ በተደጋጋሚ ከእናቷ ጋር ለብቻ ማሳለፍ ሲጀምሩ የምሰራው ጠፋኝ። እሷ ሳትኖር ምንድነበር የማደርገው? ማሰብ አቃተኝ። የሆነ ቀን ግራ ሲገባኝ እማዬጋ ሱቅ ሄጄ ዋልኩ። ስመለስ አቢ አልነበረችም። ሻንጣዋን ይዛ ሄዳለች። ቻው እንኳን አላለችኝም። አባዬና ማት ሳሎን ቁጭ ብለው ነበር።

"አቢስ?" አልኩኝ

"አቢ ከእናቷ ጋር ሄዳለች!" አለኝ አባዬ

"ልታድር? " አልኩኝ ማደሯ እየከፋኝ

"አይደለም ልጄ! ተመልሳ አትመጣም! ከእናቷ ጋር ወደውጪ ሄዳለች። ዛሬ ነው በረራቸው !" አለኝ ምንም እንዳልሆነ ቀለል አድርጎ።

ያውቁ ነበር እንደምትሄድ። ራሷ ትንገራት ብለው ነበር ዝም ያሉኝ። እሷ ልትነግረኝም ..... ቻው ልትለኝም ግድ አልሰጣትም። ማልቀስ እየፈለግኩ ግን አላለቀስኩም። ዝም አልኩኝ። ለቀናት ዝም አልኩኝ። ለእኔ ብዙ ነገሬ ናት ብዬ ለማስባት ሴት ለሷ ምኗም አልነበርኩም ብዬ ሳስብ ልቤን ክብድ ይለኛል። እኔና እሷ የምንቀመጥበት የነበረ ካፌ ብቻዬን ቁጭ ብዬ 'የምሯን ነው ግን? አብረን የሳቅነውን፣ ያለቀስነውን፣ አብረን የሰራነውን ተንኮል፣ የተማከርነውን ....የምሯን ረስታው ነው?' እላለሁ። ከወር በኋላ ደውላ

"ቻው ያላልኩሽ ፈርቼሽ ነው!" ከማለት የተሻለ ማብራሪያ እንኳን አልሰጠችኝም። በቃ ህይወቷን ቀጠለች። እኔ ግን ጎደለችብኝ። የሆነ ቀን ከቤት ደወልኩላት። ከኢትዮጵያ ጣሊያን! በቅጡ ሰላም እንኳን ሳትለኝ "ፌቪዬ ልወጣ ስል ነው የደወልሽው እደውልልሻለሁ!" ብላ ዘጋችው። የእኔ በህይወቷ መጉደል ቁርስ የመዝለል ያህል እንኳን ሳይከብዳት ህይወቷን ቀጠለች:: ..... ጠበቅኳት። የሆነ ቀን 'ናፈቅሽኝ' ትለኛለች ብዬ ...... የሆነ ቀን የሄደችበት ሀገር የገጠማትን ልታወራኝ መልሳ ትደውላለች ብዬ ........ ጊቢ ሸበላ ወንድ አይቼ እንደው ደውላ ታበሽቀኛለች ብዬ ....... ቢያንስ ለልደቴ እንኳን አትረሳኝም ብዬ ......... ከዓመታት በኋላ ወደሀገር ቤት እስከተመለሰችበት ጊዜ ድረስ አልደወለችም። .....

"የህይወት አንዱ አካል ነው። ሰዎች ወደ ህይወትሽ ይመጣሉ ይሄዳሉ። የሆነው መንገድሽ ላይ መቀበልንም መሸኘትንም መልመድ የለብሽም?" አለኝ ማት በሀሳብ መጋለቤን እያስተዋለ። ስልኬ ሲጠራ አየውና በጥያቄ አየኝ

"ባክህ ባለመኪናው ነው። የገጫት!" አልኩት ግሩም የሚለውን ሲያይ ሌላ ነገር አስቦ እንደሆነ እየገባኝ።

"እኔ ተናግሪያለሁ!" አለኝ በተንኮል። ስልኩን አነሳሁትና ግሩም ሊያገኘኝ እንደሚፈልግ ነግሮኝ ልጄ ከትምህርት ቤት ከተመለሰች በኃላ ባባን ለሷ ትቼው ልንገኛኝ ተቀጣጥረን ዘጋሁት።

"አባቷ ምንም አድርጎ ቢሆን እውነቱን እንዳለ ማወቅ አለባት። ሳይዘገይ ብታውቅ ደግሞ ጥሩ ይመስለኛል።" አለ ማት ግሩም ስለአሸናፊ ሊነግረኝ በአካል ቢሆን ይሻላል እንዳለኝ ስነግረው።

"አውቃለሁ። ግን..."

"አንቺ አለሽላት ምንም አትሆንም! እያወቅሽ እንዳልነገርሻት ከምታውቅ እውነቱ ምንም ያህል ከባድ ቢሆን እሱን ብታውቅ ይሻላል። "

ማት ቤቴን ለቆ ከወጣ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ባባ ከእንቅልፉ ነቅቶ አጠገቤ መጣ። አይኖቹን እያሻሸ በቅጡ ሳይገልጥ የተቀመጥኩበት ሶፋ ላይ እግሮቹን አውጥቶ ጭንቅላቱን ጭኔ ላይ አስደግፎ ተጋደመ። ልምድ እንደሆነ ነገር ........ ብዙ ጊዜ አድርጎት እንደሚያውቅ ነገር.......ለቀናት ሳይሆን ብዙ ጊዜ እንደሚያውቀኝ ነገር። ሳላስበው ፈገግ አልኩ።

ሊሄድብኝ እንደሚችል እያወቅኩም ቢሆን ያለስስት ልወደው፣ ልጠብቀው፣ የእኔ እስከማይሆን ቀን ድረስ የእኔ ላደርገው ለራሴ ቃል ገባሁ። ቀኑ ደርሶ ትቶኝ ሲሄድ አምኜ እቀበላለሁ! አልኩ። ልጄ ስትመጣ እዛው እግሬ ላይ እሱ እንቅልፍ ወስዶት በተቀመጥኩበት ሶፋውን ደገፍ ብዬ ሸለብ አድርጎኝ ነበር።

"ነፍስ አጥፍቶ ነው!" አለኝ ግሩም አንዱ ካፌ በተቀመጥንበት ሊነግረኝ ሲታሽ ቆይቶ!

"አሸናፊ በሌላ በምንም ሊታሰር ይችላል። ነፍስ ማጥፋት? በፍፁም!" አልኩኝ የሰማሁትን እንኳን ለማብሰልሰል ሰከንድ ሳልወስድ እርግጠኛ ሆኜ :: መደንገጥ ነበር የነበረብኝ አይደል? እንደዛ አይደለም የተሰማኝ

"እኔ እንጃ! ሰዎች እኮ ይቀየራሉ! አንቺ የምታውቂው ሰው ላይሆን ይችላል አሁን"አለኝ

"ትናንት ያየሁት አሸናፊ ምንም አልተቀየረም! የዛሬ 15 ዓመት የማውቀው አሸናፊ ነው።" ካልኩት በኋላ ነው ዓይኖቹን አፍጥጦ በመገረም ሲያየኝ ስለእኔና ስለአሸናፊ የሚያውቀው ነገር እንደሌለ ያስታወስኩት።

"የልጄ አባት ነው!" ካልኩት በኋላ ለማስረዳት ብዙ እንደሚፈጅ ሲገባኝ ተውኩት። እሱም አልጠየቀኝም። "እሺ ስንት ዓመት ነው የተፈረደበት? "

"አስራ አራት"

"በፍፁም እርግጠኛ ሆኜ የምነግርህ አሸናፊ እንኳን ሰው ለመግደል ለጥፊ እጁን አያነሳም።"

"እኔ ስለማላውቀው ምንም ልልሽ አልችልም ሰዎች ግን አይደለም በ15 ዓመት በ15 ቀን ሊቀይራቸው የሚችል አጋጣሚ ይፈጠራል።"

"ሟች ምን አይነት ሰው ነው? መረጃ አለህ?"
"አብሮት ማሳደጊያ ያደገ ጓደኛው የነበረ ሰው እንደነበር ? ከሀገር ውጪ ነበር መሰለኝ ለእረፍት በመጣበት ነው የተገደለው።"

"ገደለው?" አልኩኝ ሳላስበው።

"ምነው ታውቂዋለሽ?"

"አዎ! ማለቴ አላውቀውም ግን አሸናፊ ሲያወራ ሰምቻለሁ:: እርግጠኛ ነኝ እሱ ነው!! " አልኩኝ ደሜ ቀዝቅዞ

ይቀጥላል እኮ ....

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Meri feleke
የአብዮት ፍሬ ነኝ!

ብዙ ነገሮች ይናፍቁኛል። ብዙ ነገሮች በትዝታ ይመልሱኛል። በዚህች አጭር የእድሜ ልዩነት ይሄን ሁሉ ለውጥ ካየው በኔ ልጅ ዘመን ነገሮች ምን ያህል እንደሚለወጡ ሳስብ እንደ መደንገጥም እላለሁ።

ለውጥ 1

የድሮ መምህራኖች ማለት ...

አብዮት ፍሬ ነው የተማርኩት ። ይቅርታ አብዮት ፍሬ ነው ያደግሁት ...ሰላሳ አባትና ሰላሳ እናቶች ነበሩኝ።

የድሮ መምህራን እንደ ልጅ ይሳሱልሀል...እግር በእግር ይከታተሉሀል...ያፎካክሩሀል...ይመክሩሀል።

አይረሳኝም

መምህርት ብርቱኬ እኛ ከበናቸው.. .ግርማ ሞገሳቸው መቼም የእቴጌ መነን ነው። ኩርት ያሉ ቀብራራ...ሲኮሳተሩ ምድር ሆይ መቼ ነው የምትውጭኝ እንላላን....ሲንከባከቡን ደግሞ የእናታችንን ስም ለጊዜው እንዘነጋለን።

ታሪክ ሲተርኩልን በምናባችን እንጋልባላን...ከሚኒልክ ጋር እንዘምታላን...ጥልያንን አሳሩን እናበላዋለን መቼም !

የአድዋን ታሪክ ያፅፉናል...(ንግስታችንን ከበናል ... የባህርዛፉ ውዝዋዜ ራሱን የቻለ ዜማ ነው) .... አጤ ሚኒልክም...

አጤ ሚኒልክም (እንፅፋለን)...በመሀል የመምህራችን ንግግር አምልጧት የነበረችው ማርቲ ጔደኛችን ኤጭ!  አለች ጮክ ብላ ።

ኤጭ?????!

በስመአብ !

መብረቅ የወረደብን ያህል ክው አልን። ማርቲ በቃ ዛሬ እንደበርበሬ ልትደለዝ ነው ብለን ስናስብ መምህራችን ነገሩን ወደ ቀልድ ቀየሩት

"በባዶ ቤት ያንጫጫሽ! "

አጤ ምኒልክ አልኩሽ እኮ.. ..ሳቅ ተጥለቀለቀ....

አሁን ያሉትን መምህራን አሰብኳቸው።

ኤጭ ለማለት አትሳቀቅም...አብረውህ ይቅማሉ...አብረውህ ይጠጣሉ...ፌስቡክ ቲክቶክ ላይ አብረውህ ይለፋደዳሉ...ግርማ ሞገስ የላቸውም።

ለውጥ 2

አምስተኛ ክፍል ስገባ አብዮት ፍሬ ውስጥ እናቴ የለሽም። ከ 1-4 ክፍል ነበር ያኔ የምታስታምር...ዛሬ ሀይስኩሉን ትሾፍረዋለች።

መንጠራ ትምህርት ቤት ሳለው የመምህር ልጅ የሚል አክብሮት ይቸረኛል። በእረፍት ሰዓት እንደ ንጉስ ከቆምኩበት ሆኜ ጮርናቄና ብርቱካን ይመጣልኛል። የትኛውም ልብ አለኝ የሚል ውሪ ቀና ብሎ አያየኝም።

አብዮት ፍሬ ስገባ ብቸኛ ነበርኩና በአይን ከማውቃቸው የምዳሰ ሰፈር ጀለሶቼ ጋር ተቀላቀልኩ።

አንዳንድ ግብረ ገብ ያልሆነ ነገራቸው ግን አማረረኝ። አንዱ ደህና ኩርኩም አልሶኝ ዞር ስል ከየት መጣ ያልተባለ ሌላ ኩርኩም አናቴን ይፈልሰኛል።

ጭራሽ ደግሞ የሆነች ጌምህን ካላመጣህ ብለው ወጠሩኝ።

ያቺ ጌም ያን ጊዜ ከ I phone 13 በላይ ክብር ነበራት ።

26 ነፍስን የሚያስቱ ጨዋታዎች ነበሯት። በተለይ የአውሮፕላን ውድድሩ ይምጣብኝ 😍

ያቺን ጌም ይዣት ክፍል መጣሁ (ይዣት ባልመጣ እንደ ፊኛ ነፍተው ይጠልዙኛላ)

ምድረ ውሪ ከሌላ ፕላኔት እንደመጣ ፍጥረት ከበቡኝ።

ጭዌው ተጀመረ.. .ጌሟ ስትከፈት የሆነ ሰቅጣጭ ድምፅ ደግሞ አላት ...

ዲምዲሪሪሪንንንንንን...

ደግሞ ለክፋቱ ሂሳብ መምህራችን ጋሽ በሌ ከተፍ !

ጋሽ በሌ አበዱ ...

ጭራሽ ጌም ይዛችሁ ክፍል ውስጥ? (ይታያችሁ የዛሬ ተማሪ እኮ ብሉቱዝ ኤርፎኑን ሰክቶ ፖርን ፊልሙን ይለባልባል🙄)

ጌሙ የማነው?

ከዚህች ጥያቄ በኋላ ውሪው ሀዋሪያት ጌታን በከዱበት ፍጥነት ከዱኝ። በተለይ ዮሀንስ ሶስት ጊዜ ጮሆ ሸመጠጠኝ። ይሁዳው ቦጌ በጣቱ ጠቆመኝ።

ቲቸር ወላጅ ካላመጣህ አትገባም አሉኝ።

አቤት ድንጋጤ!

አባቴ ተጠርቶ ጌም ይዤ ክፍል እንደገባሁ ሲነገረው አሰብኩት ። አንበርክኮ በዛ የአዞ ቆዳ ቀበቶው ሲያርገፈግፈኝ ሳልሁት (ቀበቶዋ ደግሞ አስጨናቂ ሳህለ ሚካኤል የሚል ጥሁፍ ተነቅሶባታል ።) እውነትም አስጨናቂ...

ያኔ እኔ ታማሚ ነኝ ብዬ አወጅኩ። ትምህርት ቤት ቅርት!

ሀኪም ዘንድ ሂድ እንቢ

ፀበል ሂድ ኸረ ምን በወጣኝ! ...እናቴ ተሸበረች...

ከሶስት ቀን በኋላ በራችን ተቆረቆረ ።

ጋሼ ሄዶ ሲከፍተው ጋሽ በሌ!

የኔ እየሱስ የጠፋሁባቸውን በግ ለመፈለግ መጡ።

ሚኪ ትንሽ አጥፍቶ ተቆጥቼው ነበር አሉ...

አስቡት ጌምን ለዛውም ጩኸቱ ከመድፍ የሚልቅ ጌም ይዤ ክፍል መግባት ትንሽ ጥፋት ሲሆን 😑

ደንግጦ ቀርቶ ነው ብለው ቤተሰቦቼን አረጋጉልኝ ። ጥፋቴን እንኳ ሹክ አላሉም እኮ.. .ነገሮች ተድበሰበሱልኝ።

ከቀበቶ ውርጅብኝ አርነት ወጣሁ። በነጋታው ክፍል ስደርስ ከነዛ ቦዘኔ ውሪዎች አርቀው እዮብ የሚባል ጎበዝ ተማሪ ዘንድ አስቀመጡኝ።

ተመልከት የድሮ መምህር ጓደኛ ሰውን ምን ያህል ሊቀይር እንደሚችል የገባቸው ነበሩ።

እጅ ፅሁፌ ሲታይ ደብተሬ ላይ ዶሮዎች ፓርቲ ያዘጋጁ ይመስል ነበር ። እዮቤን እያየሁ እጄን ገራሁ !

የደብተሬ ልባድ የእብድ ቡትቶ ይመስላል ።

በጊዜ ሂደት ደብተሬን በወጉ መሸከፍ ጀመርኩ። ጭራሽ የመጀመርያው ገፅ ላይ ያለ ተሰጦዬ አበባ ሳልኩበት። አሁን ላይ ሆኜ ያን አበባ ሳየው ሳማም እንደመምሰል ይላል 😄

የዛሬን ተማሪ አሰብኩት.. .

ወላጅ ሲባል ገና ሪሲኒንግ አስቦ ይዞ ከተፍ ይላል

የዛሬን ወላጅ አሰብኩት ...

የተማሪ ነፃነት...መብት ምናምን በሚል ማልያ መምህሩን ለመክሰስ ሲሯሯጥ...

የዛሬን መምህር አሰብኩት ...

የበደለውን ተማሪ ከማስተማር ይልቅ ለመጣል ሲጋጋጥ.. .

ይቀጥላል! 

@wegoch
@wegoch
@wegoch
አክስቶቼ እና ላሞቻቸው
-----
ጸሐፊ: አፈንዲ ሙተቂ
------
ስለሁለት አክስቶቼ ላወጋችሁ ነው። አሚና ኢብራሂም (በቀኝ) እና ሐኒፋ ሼኽ ሙሐመድ ረሺድ ይባላሉ፡፡ “ሐኒፋ” የአባቴ እህት ስትሆን መላው ዘመዶቿ እና የሰፈሩ ህዝብ “አዴ” እያለ ነው የሚጠራት፡፡ ከዚህ ቀደም “ኦነግ እና ኢህአዴግ በአንድ ቀን ጦርነት” በሚል ርዕስ በጻፍኩት ጽሑፍ ያወጋኋችሁ ጦርነት የተጀመረው በርሷ ግቢ ውስጥ ነው፡፡ አሚና ኢብራሂምም የስጋ ዘመዴ ናት፡፡ ይሁንና አያቴ (ሼኽ ሙሐመድ ረሺድ) ያገቧት የመጨረሻ ሚስት እርሷ በመሆኗ የሼኽ ሙሐመድ ረሺድ ልጆች “አዮ አሚና” እያሉ ነው የሚጠሯት፡፡ እኛም የአባቶቻችንን ልማድ በመከተል “አዮ አሚና” እያልን እንጠራታለን፡፡

እነዚህ አክስቶቼ ልጅ በነበርኩበት ዘመን በርካታ ከብቶች ነበሯቸው፡፡ በግቢዎቻቸው ጥግም ለከብቶች የተሰሩ ሰፋፊ በረቶች ነበሯቸው፡፡ ባለፈው በጥቅምት ወር 2008 ስዘይራቸው ግን የሁለቱም በረት በቦታው አልነበረም፡፡ “ከብቶቹ ወዴት ጠፉ?” ብዬ ስጠይቃቸው ልዩ ልዩ ምክንያቶችን ዘረዘሩልኝ፡፡ ዋነኛው ምክንያታቸው “ድሮ የግጦሽ ስፍራ የነበሩት መስኮች በሙሉ ወደ እርሻ ማሳነት ተቀይረዋል፤ ስለዚህ ከብቶቹን ለማብላት ወደ ሩቅ ስፍራዎች መሰማራት ግድ ይላል፤ አሁን ባለው ሁኔታ ግን ያንን ማድረግ አንችልም፤ በመሆኑም ከብቶቹን ለመሸጥ ተገደድናል” የሚል ነው፡፡ ምክንያታቸው አሳማኝ ቢሆንም ከሁለቱ ቤቶች እንደ ድሮው ትኩስ ወተት በ“ቀቤ” ለመጠጣት ባለመቻሌ አዘንኩ! እስቲ ስለነዚያ ከብቶች ያለኝን ትዝታ በትንሹ ላውጋችሁ፡፡
*
በዚያ ዘመን በሰፈሩ የሚኖረው እያንዳንዱ ቤተሰብ ጥቂት የማይባሉ ከብቶች ነበሩት፡፡ በዘመኑ ወግ መሰረት ሴት ከብቶች (ላም እና ጊደር ) እና ጥጆች ባለቤትነታቸው የእመወራዎች ነው፡፡ ከነዚያ እመራዎች ሁሉ በከብቶች ብዛት የምትበልጠው ደግሞ “አዮ አሚና” ነበረች፡፡ በበረቷ ከሚያድሩት ላሞች መካከል በአንድ ጊዜ የሚታለቡት ብቻ አስራ አምስት ያህል ይሆናሉ፡፡ በመሆኑም ከቤቷ ወተት፣ ቅቤ እና እርጎ ጠፍተው አያውቁም፡፡ አያቴን ሊዘይሩ ለሚመጡ እንግዶች የሚቀርበው “ሆጃ” የሚፈላው በአብዛኛው ከርሷ ቤት በሚታለበው ወተት ነበር፡፡ ልጆች በቤታቸው እንጀራ እና ቂጣ ብቻ አግኝተው ማባያ ሲያጡ ወደርሷ ይመጡና ወተትና እርጎ ይጠይቃሉ፡፡ ለልጃገረዶችም ጸጉራቸውን የሚሰሩበትን ቅቤ ትሰጣቸው ነበር፡፡

በዘመኑ ወግ መሰረት ከብቶችን በስም እየለዩ መጥራት የተለመደ ነው፡፡ ታዲያ ለከብቶች የሚሰጠው ስም በአብዛኛው የከብቱን ቀለም እና ቁመና የተከተለ ነው፡፡ የ“አዮ አሚና” ስም አሰያየም ግን ከዘመኑ ልማድ ወጣ ያለ ነው፡፡ “መጋል” እና “ጉራቻ” ከተሰኙት ሁለት ላሞች በስተቀር ሌሎቹ ከብቶች ለየት ባሉ ስሞች ነበር የሚጠሩት፡፡ ለምሳሌ “ደንገሹ”፣ “ኩሜ”፣ “ባቲ”፣ "መገርቱ" ፣ “ሂና” “ኩሊ”፣ “ኩሪ”፣ "ዱኮ" ወዘተ…. በመሳሰሉ ስሞች የሚጠሩ ከብቶች ነበሯት፡፡ ስያሜዎቹን እንዴት እንደምታወጣቸው አላውቅም፡፡ ታዲያ አዮ አሚና ከብቶቿን ስታነጋግራቸው ዋዛ እንዳትመስላችሁ!! እያንዳንዱን ከብት እያከከችው እንደ ሰው ልጅ ታዋራው ነበር፡፡
*
የአዴ (ሐኒፋ ሼኽ ሙሐመድ ረሺድ) ከብቶች በብዛት የአሚናን ያህል አይደሉም፡፡ ይሁንና ከሰፈሩ ከብቶች ሁሉ ለኔ በጣም የሚታወሱኝ እነርሱ ነበሩ፡፡ ምክንያቱም ነፍስ ካወቅኩ በኋላ ወደሰፈሩ በምሄድበት ወቅት የማርፈው እርሷ ዘንድ ስለሆነ ነው፡፡

ከነዚያ ከብቶች መካከል በጣም ቁጡዋ “ዳለቲ” ትባላለች፡፡ “ዳለቲ” ቀንድ የላትም፡፡ ሆኖም በድቡልቡል ጭንቅላቷ በቴስታ “ገጭ” እያደረገችን ከመሬት ላይ ትፈጠፍጠን ነበር፡፡ ከልጅነት እስከ ጉልምስና ዘመኗ ድረስ የምታውቃት አክስቴ እንኳ ቀኑ ሲመሽ ዳለቲን ይዛ በማደሪያ ስፍራዋ ላይ አስራ አታውቅም፡፡ “ዳለቲ” የማትነካቸው ሁለት ልጆችን ብቻ ነው፡፡ አንደኛው ሙሐመድ አሕመድ (ነጋሺ) የሚባለው የራሷ (የአክስቴ) ልጅ ሲሆን ሌላኛው “ናጂ በደው” ይባላል፡፡ ስለዚህ ዳለቲን ለማሰር ከተፈለገ እነዚያ ልጆች የግድ መገኘት ነበረባቸው፡፡
“ዳለቲ”ን የወደለቻት “ጋሬ” የምትባል ላም ናት፡፡ ይህቺ ጋሬ “ጄብሎ” የተሰኘ ሌላ ላምም ወልዳለች፡፡ ታዲያ ይህቺ “ጄብሎ” በውጊያ እናቷን ታሸንፋታለች፡፡ አክስቴ የቡና አተላ (ረጃ) እና ድርቆሽ ለጋሬ በምትሰጥበት ጊዜ “ጄብሎ” እያባረረቻት ትነጥቃለች፡፡ ሆኖም “ጄብሎ” ምንም ቀንድ ያልነበራትን ዳለቲን አትችላትም፡፡ በመሆኑም ዳለቲ ከእናቷ አፍ ድርቆሹን የነጠቀችውን “ጄብሎ”ን ታባርርና ለራሷ መብላት ትጀምራለች፡፡ ይሄኔ ግን የድርቆሹ የመጀመሪያ ባለቤት የሆነችው “ጋሬ” ከተፍ ትላለች! ምክንያቱም እርሷ ጄብሎን ባትችላትም ቀንዳ አልባ ለሆነችው ዳለቲ ትበረታለችና! እናም ከጅምሩ ለርሷ የተሰጠውን ድርቆሽ ያስመለሰችው “ጋሬ” ዘና ብላ መመገብ ትጀምራለች፡፡ ይሁንና ምንም ያህል ሳይቆይ “ጄብሎ” እንደገና ከተፍ ትልና እንደለመደችው “ጋሬ”ን በማባረር ድርቆሹን መብላት ትጀምራለች፡፡ አንድ ጊዜ ያህል ዋጥ ካደረገች በኋላ ግን “ዳለቲ” ከተፍ ትልና ድርቆሹን ትነጥቃታለች፡፡ “ዳለቲ” መብላት ስትጀምር ደግሞ እንደገና “ጋሬ” ትመጣለች፡፡ እንደገና “ጄብሎ”፤ እንደገና “ዳለቲ”፤ እንደገና “ጋሬ”!
አክስቴ ለሶስቱ ከብቶች በተለያየ ቦታ ድርቆሽ ብታስቀምጥላቸው እንኳ ላሞቹ ጥላቸውን አይተውም፡፡ አንደኛው ከብት ለርሱ የተሰጠውን ከማላመጥ ይልቅ ሌላኛውን ነጥቆ መብላቱ ያስደስተዋል፡፡ ስለዚህ አክስቴ የከብቶቹን ጥል ለማስቀረት ሌላ ዘዴ ፈጠረች፡፡ ላሞቹ ከማደሪያቸው ሳይፈቱ ድርቆሽና ውሃቸውን መስጠት!! በዚህ ዘዴ ሁሉም ተስተካከለ፡፡ ሆኖም አንዳንዴ አክስቴ በቤቷ በሌለችበት ጊዜ የአክስቴ ልጆች የሶስቱን ከብቶች ጥል ለማየት ሲሉ ብቻ መመሪያውን እየጣሱ ከብቶቹን ይፈቷቸው ነበር፡፡ እናም ጋሬ፣ ዳለቲ እና ጄብሎ ለረጃ እና ለድርቆሽ ሲሉ እየተቁነጠነጡ ውጊያ ይገጥማሉ፡፡

ይህ የሶስቱ ላሞች ጥል ለረጅም ጊዜ ሲገርመኝ ነበር፡፡ አንዱ ከብት አንደኛውን ብቻ ይችለዋል፤ ሌላኛውን ለማባረር ግን ወኔ የለውም፡፡፡ ይህ ሊሆን የቻለው እንዴት ነው…? ሁለቱንም ላሞች የወለደችው “ጋሬ” ሌሎቹን ማሸነፍ ያልቻለችበት ምክንያትስ ምንድነው…? ቀንድ ያላት “ጄብሎ” ቀንድ አልባዋን “ዳለቲ”ን የምትፈራበት ምክንያትስ ምንድን ነበር….?

መልሱን በጭራሽ አላውቀውም!! ይሁንና በኋለኛው ህይወቴ ተመሳሳይ አጋጣሚዎችን በማይበት ጊዜ ሁሉ የነዚያ ከብቶች ጥል ወደ አዕምሮዬ ይመጣል፡፡
*
የአዴ” (አክስቴ) ከብቶች የሚጠሩባቸው ስሞች ከአዮ አሚናም ይበልጥ ያስገርማሉ፡፡ ለምሳሌ ከላይ የጠቀስኳት “ጋሬ”ን እና “ጋሬ” የወለደቻቸውን ብቻ በስም ላስተዋውቃችሁ፡፡

በሀረርጌ ኦሮሞ ባህል መሰረት “ጋሬ” የሚባለው ሰውነቱ በጥቁር ወይም ቀይ ቆዳ ተሸፍኖ በጭንቅላቱ ላይ ብቻ ነጭ የሆነ ከብት ነው፡፡ “ጋሬ” ግን ሙሉ በሙሉ ቀይ ነበረች፡፡ በዚህ ረገድ ከሌሎች ጋሬዎች ሁሉ የተለየችው እርሷ ብቻ ነበረች፡፡ አክስቴ ለምን ከህዝቡ ልማድ ውጪ ለላሚቱ “ጋሬ” የሚል ስም እንዳወጣች ስጠይቃት “ጋሬ የእናቷ ስም ነበር፤ እናቷን በጣም እወዳት ነበር፤ ብዙ ወተት ያለስስት የሰጠችኝ ላም ናት፤ ነገር ግን የአባ ጎርባ በሽታ ገደለብኝ፤ ስለዚህ እርሷን ለማስታወስ ብዬ ለልጇ “ጋሬ” የሚል ስም አወጣሁ” አለችኝ፡፡
(ከላይ ካለው ጽሑፍ የቀጠለ)
----
“ጋሬ” የወለደቻት የመጀመሪያ ከብት “ቤጆ” ትባላለች፡፡ “ፔጆ 404” የምትባለው የቤት መኪና “ፋሽን” በነበረችበት ዘመን ስለተወለደች ነው እንዲህ ተብላ የተጠራችው፡፡ ሁለተኛዋ ቀንድ አልባዋ “ዳለቲ” ናት፡፡ ይህችኛዋ በቀለሟ “ዳለቻ” ስለነበረች ነው እንዲያ የተባለችው፡፡ ሶስተኛዋ “ጄብሎ” ናት፡፡ አክስቴ ስሙን ከየት እንዳመጣችው አላውቅም፡፡ ሆኖም ወደ ከተማ መጥታ “ጀብሎ” የሚባሉ ሲጋራ አዟሪዎችን ካየች በኋላ ስሙን ለከብቷ እንዳወጣችው እጠረጥራለሁ፡፡ አራተኛው “ሌንጮ” ይባላል፡፡ ይህኛው ወይፈን ነው፡፡ “ሌንጮ” በልጅነቱ የተለየ ስም የነበረው አይመስለኝም፡፡ በሂደት ግን የሰፈሩን በሬዎች እየገጠመ ስላሸነፋቸው “ሌንጮ” የሚለውን ስም አግኝቷል (“ሌንጮ” በአማርኛ “አንበሳው” እንደማለት ነው)፡፡

አምስተኛዋ “ዲምቱ” ትባላለች፡፡ “ቀዮ” እንደማለት ነው፡፡ ይህቺኛዋ “ኦነግ እና ኢህአዴግ በአንድ ቀን ጦርነት” በሚል ርዕስ በተጻፈው ተከታታይ ጽሑፍ ውስጥ ያስተዋወቅኳችሁ ላም ናት፡፡ በዕለቱ በግቢው ከነበሩት ከብቶች መካከል በጥይት ተመትታ ለመሞት የበቃችው እርሷ ብቻ ናት፡፡ ስድስተኛዋ አንዲት ብስል ቀይ ጥጃ ናት፡፡ ይህቺኛዋ “ደሃቦ” የሚል ስም የነበራት ሲሆን ስሙን የሰጣት ደግሞ በወቅቱ ከብቶቹን ያግድ የነበረው “ሙሐመድ አሕመድ” (ነጋሺ) የተባለው የአክስቴ ልጅ ነው፡፡ ሆኖም በዚህ ስም ላይ ከባድ ውዝግብ ተቀስቅሷል፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡
ስያሜው በቅድሚያ የተሰጠው ከቢር ያሕያ የተባለ የአክስቴ ጎረቤት ለወለዳት አንዲት ቀይ ልጅ ነው፡፡ መሐመድ አሕመድ ግን ስሙ በጣም ደስ አሰኘውና በዚያው ሰሞን “ጋሬ” ለወለደቻት ጥጃ ሸለማት፡፡ የከቢር ያሕያ ሚስት ይህንን ስትሰማ ተቆጣች!! “እንዴት በልጄ ስም ከብቱን ይጠራል?” በማለት መንደሩን ቀወጠችው፡፡ መሐመድ አሕመድ ጥጃዋን በዚያ ስም መጥራቱን እንዲተው ቢነገረው “እምቢ” አለ፡፡ አክስቴ ብትለምነው፣ ብታስፈራራው፣ ብትገርፈው ልጁ በእምቢታው ጸና፡፡ የከቢር ያህያ ሚስት አክስቴ “ሆን ብላ ያደረገችው ነው” ባይ ሆነች፡፡ አክስቴ ሐቁን ብታስረዳት በጭራሽ አልሰማ አለች፡፡ በመጨረሻም ሽማግሌዎች በነገሩ ገብተው መሐመድን ገሰጹት፡፡ መሐመድም ለጊዜው ግሳጼውን የተቀበለ መሰለ፡፡ ነገር ግን በዚያ ስም ፍቅር ስለተለከፈ አንድ መላ ፈጠረ፡፡ ደሃቦን በአማርኛ መንዝሮ “ወርቄ” በሚል ስልት ጥጃዋን መጥራት ጀመረ፡፡ አማርኛ የማትሰማው የከቢር ያህያ ሚስትም ከቁጣዋ ረገብ አለች፡፡ መሐመድ አሕመድም ለ“ደሃቦ” የነበረውን ፍቅር በ“ወርቄ” በኩል ተወጣ (“ደሃብ” በዐረብኛ ወርቅ ማለት ነው፤ ሶማሊዎች ስሙን ሲያቆላምጡት “ደሃቦ” ይላሉ”)፡፡
-----
እነዚያ በፍቅር እያናወዙ ጎረቤት የሚያጣሉ ከብቶች ዛሬ የሉም፡፡ ወተት “በሽበሽ” የነበረበትን ያንን ደግ ዘመን አልፈን የገጠሩ ህዝብም እንደ ከተሜው ገበያ እየሄደ ወተት በኩባያ ከሚገዛበት ዘመን ላይ ደረስን፡፡ ይህም እንግዲህ ኑሮ ነውና “አልሓምዱሊላህ” እንላለን፡፡

በነገራችን ላይ "አዮ አሚና" አሁን በሕይወት የለችም። ይህንን ጽሑፍ ከጻፍኩ በኋላ በጥር ወር 2010 አርፋለች። አላህ ይርሓማት። "አዴ" ግን ዛሬም አለች። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ድሬ ዳዋ ከከተመው ልጇ ዘንድ እየኖረች ነው። ረጅም ዕድሜ ይስጣት።
እኛንም ቸር ያቆየን!
-----
አፈንዲ ሙተቂ
ጥቅምት 30/2008 ተጻፈ።
ገለምሶ- ምዕራብ ሀረርጌ

@wegoch
@wegoch
@paappii
.. አስደሳች ጨዋታዎች

(ከተስፋዬ ገብረአብ )
-------
ተስፋዬ ገብረ-አብ “በጋዜጠኛው ማስታወሻ” በርካታ ፖለቲካ-ነክ ወጎችን አውግቶናል፡፡ እኔ እዚህ የምጽፍላችሁ ግን ፖለቲካውን ሳይሆን ተደጋግመው ቢነገሩ የማይሰለቹ ሌሎች ጨዋታዎቹን ነው፡፡ (እኒህን ጨዋታዎች የቀዳሁት ከዚያው መጽሐፍ ነው)፡፡

===አቶ ፍሬው ለምለም እና የቼክ እደላው===

አቶ ፍሬው ለምለም ደግ አዛውንት ነበሩ፡፡ የብሄራዊ ሎተሪ ተጠባባቂ ስራ አስኪያጅ ሆነው የተመደቡ ሰሞን እንደ አንበጣ ወረርናቸው፡፡ የመንግሥትና የኢህአዴግ ሚዲያዎች ሁሉ ማስታወቂያ ይሰጡአቸው ዘንድ የሽያጭ ወኪሎቻቸውን ላኩባቸው፡፡ ከቴሌቪዥን፣ ከሬድዮ፣ ከአዲስ ዘመንና ከበሪሳ ጋዜጦች ለመጡት ሁሉ ይሉኝታ ይዞአቸው ቼክ ፈረሙ፡፡ ቀጥሎም “አብዮታዊ ዲሞክራሲ” ጋዜጣ መጣ፡፡ እምቢ ማለት አልቻሉም፡፡ የሾማቸው ኢህአዴግ ነውና ቼክ ፈረሙ፡፡ ከ“ማህቶት” ጋዜጣ ለመጣው ግን ላለመስጠት አንገራግረው ነበር፡፡ “በአማራው ክልል ዋና የሎተሪ ደንበኞች ዘንድ እንደርሳለን” እያለ ሲለፈልፍባቸው ለመገላገል ብለው ቼኩን ፈረሙ፡፡ በነጋታው የኦሮሚያ ጋዜጣ ወኪል መጣ፡፡ “ለአማራው ፈርመህ ለኦሮሞ ያልፈረምከው ነፍጠኛ ስለሆንክ ነው” እንዳይባሉ ቼክ ፈረሙ፡፡ ከደቡብና ከትግራይ መጡባቸው፡፡ ከነገር ለመሸሽና ላለመነካካት ሲሉ ፈረሙላቸው፡፡ በመጨረሻም እኛ ሄድን-ከእፎይታ መጽሔት፡፡ ዐርብ ጠዋት የሽያጭ ሰራተኛውን አስከትዬ ከቢሮአቸው ስገባ ግስላ ሆነው ጠበቁኝ፡፡

“ምን ፈለጋችሁ እናንተ ደ’ሞ?!” ሲሉ ጮኹ፡፡ “አታፍሩም እንዴ? ፍሬው ለምለም እንደ ጠበል ጠዲቅ ገንዘብ እየመዠረጠ ይሰጣል ያላችሁ ማን ነው? ምንጣፉንም ጠቅልሉትና ውሰዱታ! ጠረጴዛውንም ጫኑ! እሱ ነው የቀራችሁ:: ነውር አይደለም እንዴ?”
ካረጋጋናቸው በኋላ ሳምንቱን በሙሉ የደረሰባቸውን አጫውተውን ሲያበቁ እንዲህ አሉ፡፡
“እስኪ ይሁን እንግዲህ… ዳግመኛ አትምጡብኝ እንጂ ለዛሬው ባዶ እጃችሁን አልመልሳችሁም”::

===መለስ እና ደበበ እሸቱ===

እውቁ ተዋናይ ደበበ እሸቱ በምርጫ-97 ተወዳድሮ እንደነበር ይታወሳል፡፡ እናም ጠ/ሚ/ መለስ እንዲህ ተጠይቀው ነበር አሉ፡፡

ጋዜጠኛ፡ ኢህአዴግ በምርጫው ድራማ ሰርቷል ይባላል፡፡ እውነት በምርጫው ድራማ ተሰርቶ ነበር እንዴ?
ጠ/ሚ/ መለስ፡ የተሰራ ድራማ የለም፡፡ ምናልባት በምርጫው ደበበ እሸቱ ስለተሳተፈ ድራማ የመሰላቸው ካሉ ተሳስተዋል”፡፡

(ሆኖም ይህቺ የድረ-ገጾች ፈጠራ ናት ይለናል- ተስፋዬ ገብረ አብ)

===ስብሐትና ቦነስ===

ለጋሽ ስብሐት ገብረ እግዚአብሄር ለስድስት ዓመታት ያህል አለቃው ሆኜ ብንሰራም በአንዳንድ ነገሮች ላይ እርሱ ነበር የሚያዘኝ፡፡ አንድ ቀን እንዲህ ሲል ጠይቆኛል፡፡
“ላማክርህ ነበር የመጣሁት”
“እሺ ጋሽ ስብሐት ምን ነበር?”
“ገንዘብ ቸግሮኛል”
ዝም አልኩ፡፡ ምክንያቱም የመጪዎቹን ሁለት ወራት ደመወዙን ከወዲሁ ወስዶ ነበርና ምን እንደማደርግ ግራ ሊገባኝ ጀምሮ ነበር፡፡ እሱም ይህንን ተገንዝቦ ኖሮ ፈጥኖ ንግግሩን ቀጠለ፡፡
“ደመወዜን ቀድመህ ስጠኝ ልልህ አልችልም፡፡ ወስጄዋለሁና፡፡ አሁን ሳስብበት ቆየሁና አንድ ሌላ ዘዴ መጣልኝ፡፡
“ምን ዘዴ አገኘህ ጋሽ ስብሐት?”
“ታታሪ ሰራተኛ በሚል ለምን ቦነስ አትሰጠኝም?”

===ፈረሰኛው ባህሩ===

የግንቦት ሀያ አንደኛ ዓመት በዓል እየተከበረ ነው፡፡ ብዙ ህዝብ በመስቀል አደባባይ ታድሞአል፡፡ ሁሉም እንደ አቅሙ ሸልሏል፡፡ ከዚያ ህዝብ መሀል አንድ ፈረሰኛ አባት ትኩረቴን ሳቡት፡፡ ፈረሳቸው ተንቆጥቁጧል፡፡ እሳቸውም ፈረሳቸውን መስለዋል፡፡ እኒህ ሽማግሌ ያቅራራሉ፡፡ ጃሎታውን ያስነኩታል፡፡ ምናልባት ደርግ ብዙ ጋሻ መሬት የወረሰባቸው ይሆን? ወደርሳቸው ቀርቤ ምክንያቱን ብጠይቅ የተሻለ ነው በማለት ለቃለ መጠይቅ ጋበዝኳቸው፡፡
“አባት ስምዎትን ማን ልበል?”
“ባህሩ ከበደ”
“አቶ ባህሩ ዛሬ እንዲህ አምረው በሰንጋ ፈረስዎ እየጋለቡ ወደዚህ አደባባይ የመጡት ለምንድነው?”
“እኔ ከኃይለ ስላሴ ዘመን ጀምሮ፣ በደርግም ጭምር፣ አሁን ወያኔ ከመጣ ወዲህም ሰልፍ የሚባል አምልጦኝ አያውቅም፤ ሰልፍ አለ ከተባለ የክት ልብሴን ለብሼ ሰንጋ ፈረሴን ጭኜ ከተፍ ነው”

===ወይዘሮ ኢትዮጵያ===

ደርባን በምትባል ከተማ ላይ የተዋወቅኩት ኤርትራዊ ጋዜጠኛ ያጫወተኝ ነው፡፡
ኤርትራ የነጻነት በዓሏን እያከበረች ነው። ህዝቡ በሳባ ስታድየም ታድሟል። ወታደሮች የሰልፍ ትርኢት ያሳያሉ። እናቶች ሹሩባ ተሰርተው በእልልታና በእስክስታ ክብረ በዓሉን አድምቀውታል። ኤርትራዊው ጋዜጠኛም የአንድ ደማም ኤርትራዊት እናት የእስክስታ አወራረድ ስለማረከው ለቃለ መጠይቅ ጋበዛቸው።
“እናት! እንኳን ደስ አለዎት”
“እንኳን አብሮ ደስ አለን፡፡ ኤርትራ ሀገራችን ከኢትዮጵያ አገዛዝ ነጻ በመውጣቷ ደስ ብሎናል፡፡ የዛሬዋ ዕለት የልደት ቀናችን ናት”
“ስምዎትን ማን ልበል?”
“ወይዘሮ ኢትዮጵያ እባላለሁ”
-------
(ተስፋዬ ገብረ አብ፣ የጋዜጠኛው ማስታወሻ፣ 2001/2009 G.C.)

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Afendi mutaki
እማሆይ ረታ ነጠረች_ ቅዱስ_አርዮስ
<unknown>
እማሆይ ረታ ነጠረች

ተራኪ
ቅዱስ አርዮስ ና ዳናዊት

ፅሁፍ አርዮሱ


@wegoch
@wegoch
@paappii
አታምጣው ስለው አምጥቶ ቆለለው #7

“ምን አድርጎት ነው የገደለው?” ነበር ያለችኝ።

በየትኛው ቃል፣ በየትኛው ዓረፍተ ነገር፣ በየትኛው ሰዓት፣ የት ቦታ ፣ እንዴት እንደምነግራት ስጨነቅ እና ሳምጥ ቀናት ካለፉ በኋላ ለልጄ ስለአባቷ ስነግራት!! ያልጠበቅኩት ምላሽ ስለነበር ፈራኋት። ምናልባት በጣም ደንግጣ ይሆን ምንም ዓይነት መረበሽ ያላሳየችኝ?

“የእኔ ልጅ ሁሉንም በአንዴ ስደራርብሽ ይበዛብሽል። ሌላ ጊዜ ደግሞ ነገሮችን በሰከነ ጭንቅላት ሆነን እነግርሻለሁ። አንድ ነገር ግን በእርግጠኝነት ልንገርሽ አባትሽ መጥፎ ሰው አይደለም!” አልኳት

“እማ እኔ እንደምታስቢው ህፃን ልጅ አይደለሁም! ስለአባቴ እውነቱን የነገርሽኝ ትችለዋለች ብለሽ ስላመንሽብኝ አይደል? ከነገርሽኝ አይቀር ሁሉንም ማወቅ እፈልጋለሁ። እና ደግሞ እንኳንም ነገርሽኝ!” ብላ ጉንጬን ሳመችኝ። ከኔ በተሻለ ነገሩን በእርጋታ የተቀበለችበት መንገድ ጤነኝነት እስከማይመስለኝ ድረስ ተገረምኩ። ዝም ማለቴን ስታይ ቀጠል አድርጋ

“ቆይ በህይወቴ ሁሉ ጭራሽ ያልነበረ አባቴ ድንገት እስር ቤት እንደሆነ ከማወቅ ያውም ሰው ገድሎ፣ እናቴን ትቶ ሌላ አግብቶ የወለደው ወንድም እንዳለኝ ከማወቅ የባሰ አለው? የለውም እኮ እማ! ንገሪኝ ሁሉንም!!” እውነቷን ነው የባሰ የለውም!

“የለውም!” አልኳት እንዲህ መብሰሏ እየገረመኝ

“ንገሪኛ! ምን አድርጎት ነው የገደለው?”

“የአባትሽን ህይወት ያበላሸበት ሰው ነው። የእሱን ብቻም አይደለም። የባባን እናትም ህይወት ያበላሸ ሰው ነው። አባትሽ ያልኖረውን ህይወት ስኬታማ ሆኖ በመበቀል የሚያምን ሰው ነበር። በትምህርቱም ጎበዝ ተማሪ ነበር። ጥሩ ውጤት አምጥቶ ተምሮ ስራ ይዞ አግብቶ ወልዶ የሚኖርለት ቤተሰብ እንዲኖረው ነበር ምኞቱ። ስሙን ረስቼዋለሁ ……… ሟች ….. አብሯቸው ማሳደጊያ የነበረ ልጅ ነበር። በባህሪው ባለጌ በጉልበት የሚያምን ነበር። የባባን እናት ፍቅረኛዬ ካልሆንሽ ብሎ ያስቸግራት ነበር። የሆነ ቀን አባትሽ ‘ተዋት አትፈልግህም!’ ስላለው ይጣላሉ። ይደባደባሉ። የዛን እለት ማታ አባትሽ ወደማደሪያው ሲመለስ ሎከሩ ውስጥ መጠኑ ብዙ የሆነ አደንዛዥ እፅ በጥቆማ ተገኝቶበት ተከሰሰ። የአስራሁለተኛ ክፍል ትምህርቱን ሊጨርስ አንድ ዓመት ነበር የቀረው። ከዛ በፊት በጥሩ ስነምግባር : ልጆችን በማስጠናት : በቅን ልብ የሚታወቅ ልጅ በመሆኑ ቅጣቱ ቀሎለት 1 ዓመት ነበር የተፈረደበት። ከዛ ግን ህይወት ከቆመችበት አልቀጠለችለትም። እሱ ባልነበረበት ጊዜ ይሄው ልጅ የባባን እናት አታሎ ከጊቢ ውጪ አስጠርቶ ደፈራት። ለማንም መንገር ፈርታ ለአባትሽ የተፈጠረውን ነግራው ማሳደጊያውን ጥላ ጠፍታ አረብ ሀገር ሄደች። አባትሽ ከራሱ መታሰርና ህይወቱ እንደቀድሞ ካለመሆኑ በላይ እርሷን ሊጠብቃት ያለመቻሉ እኔ እስከማውቀው ድረስ ይጠዘጥዘው ነበር። አቅመ ቢስነት ይሰማው ነበር።”

“አባቴና እሷ ያኔ ፍቅረኛሞች ነበሩ? “

“እሱ እንደነገረኝ ከሆነ አልነበሩም። እንደእህትና ወንድም ነበር የሚጠባበቁት። ካምፑ ውስጥ ከነበሩ ልጆች በሙሉ ሁለቱ በተለየ ይቀራረቡና ይጠባበቁ ነበር። እንደታናሽ እህቱ ይሳሳላት እንደነበር ነው የነገረኝ።”

“እሺ ከዛስ?”

“ከዛ አባትሽ ቅጣቱን ጨርሶ ሲወጣ እሷም የለችም። ልጁም በህገወጥ መንገድ ከሀገር ወጥቷል። ከመታሰሩ በላይ ከፍተኛው ቅጣት ወደማሳደጊያ ጣቢያው መመለስ እንዳይችል የተጣለበት ማዕቀብ ነበር። ከዛ ጊቢ ውጪ ሰውም ህይወትም አልነበረውም። የትም ሆኖ ትምህርቱን መቀጠል አይችልም ነበር። ስራ እንኳን ለመቀጠር ተያዥ የሚሆነው ሰው የለውም ነበር። ብቻ እስር ቤት በነበረበት ጊዜ ተምሮ በነበረው የእጅ ሙያ አንድ ፈርኒቸር ቤት ስራ እስኪያገኝ ድረስ ብዙ አስከፊ ህይወት አሳልፏል።”

“እና ሰውየውን በመግደሉ ልክ ነው ብለሽ ነው የምታስቢው?” አለችኝ

“ልክ ነው ብዬ አላስብም ። አንዳንዴ ግን ሰዎች ሁሉ ልክ ያልሆነ ነገር እናደርጋለን። አባትሽ ያደረገው ልክ ባይሆንም። ያደረገበትን ምክንያት ግን በመጠኑም ቢሆን እረዳለሁ።”

“ትጠይዋለሽ? ማለቴ አባቴን ትጠይዋለሽ? ሰው በመግደሉ ሳይሆን አንቺን ባደረገሽ ነገር?”

“አልጠላውም የእኔ ልጅ!! ግን ተቀይሜዋለሁ። በጣም ብዙ ተቀይሜዋለሁ። ጥላቻ ሳይሆን መከፋት! ቅያሜ ነው ያለኝ!! ብዙ ቅያሜ!!”

“ይቅርታ ቢልሽስ?”

“ከይቅርታው ይልቅ ያደረገበትን ምክንያት መረዳት ብችል ምናልባት ቅያሜዬን እተወው ይሆናል። አላውቅም! እስከማውቀው ድረስ አባትሽ ያለበቂ ምክንያት ማንንም ሰው ቢሆን የሚጎዳ ነገር የሚያደርግ ሰው አልነበረም! ቢያንስ እኔ እንደዛ ነው የማስበው!”

“ስታገኚው አልጠየቅሽውም?”

“ከእኔ ጥያቄ የሚበልጥ መጎዳት ውስጥ ስለነበር መታገስን መረጥኩ የእኔ ልጅ!”

“አትናደጂም?” አለችኝ የእሷ እድሜ በማይመስል ጠንካራ ድምፀት

“በምኑ?”

“ደግነትሽን እንደጂልነት ሲቆጥሩብሽ? ምንም አድርጎሽ ቢሆን እንደምትረጂው ስለሚያውቅ ለምን ትቶሽ እንደሄደ እንኳን ምክንያቱን ሳይነግርሽ ጥሩነትሽን ይጠቀምበታል። እንቢ እንደማትዪው ያውቃል። ምክንያቱም ክፉ ልብ የለሽም አይደል?” ይሄን ያለችበት መንገድ ጉዳዩ ስለእኔ ብቻ እንዳልሆነ ገባኝ። የሆነ እያለፈችበት ያለ ነገር አለ ማለት ነው። የሆነችው ነገር። ንግግሯ የ15 ዓመት ልጅ ንግግር አይደለም።

“እንደዛ እንዲሰማሽ ያደረገሽ ሰው አለ? መልካምነትሽን እንደጅልነት የቆጠረብሽ ሰው አለ? ደግ ሆነሽለት ብልጥ ሆኖ የተጠቀመብሽ ዓይነት ስሜት እንዲሰማሽ ያደረገሽ ሰው አለ?”

“ብዙ ጊዜ። ጓደኞቼ የምላቸው የሆነ ነገር ከእኔ ሲፈልጉ የሚወዱኝ ይመስላሉ። እያወቅሁ የፈለጉትን የምችለው ከሆነ አድርግላቸዋለሁ። እነሱ ግን የሚመስላቸው የሸወዱኝ ነው።”

“ወይኔ ጉዴ!! መቼ ነው እንደዚህ ያደግሽው? በ15 ዓመት እንዲህ አይበሰልምኮ የእኔ ልጅ?”

“ያንቺ ልጅ አይደለሁ?”

“የውልሽ የእኔ ልጅ! ጥሩ መሆን፣ ለሰዎች ሁሉ ቅን ነገር ማድረግ፣ የቻልሽውን ሁሉ መርዳት ጥሩ ነገር ነው። የሰው ልጅ ሁሉ የሚያጭደው የዘራውን ነውና የዘራሽው ደግነት ባላሰብሽው መንገድ ጎተራሽን ሞልቶ ታገኚዋለሽ!! ያ ማለት ግን ቅን ልብሽን ተጠቅመው ባገኙት አጋጣሚ ሊጠቀሙብሽ ለሚፈልጉ ብልጥ ነን ብለው ለሚያስቡ ከንቱዎች ሁሌ መጠቀሚያ መሆን አለብሽ ማለት አይደለም። ዝምታ የሚገባው ብልህ ሰው ብቻ ነው። አንዳንዱ ሰው ከንቱነቱ ሊነገረው ይገባል። ለራስሽ ቁሚ! ‘እስከዛሬ ዝም ያልኩህ እንደእኔ ጥሩነት እንጂ እንዳንተ ከንቱነት አይደለም’ ማለት አለብሽ” ስላት ድክም ብላ ትስቃለች። ለዛሬ ንግግራችንን የጨረስን መሰለኝ። ውስጤ ሽጉጥ ብላ

“እወድሻለሁ እኮ! ምርጥዬ እናት ነሽ! እንዳንቺ ዓይነት እናት ባትኖረኝ እኔም ከከንቱዎቹ አንዷ እሆን ነበር።” አለችኝ

በሳል እንደሆነች ድሮም አውቃለሁ። ዛሬ ግን ከአዕምሮዬ በላይ ሆነችብኝ። እኔ በሷ እድሜ አባዬ እና እማዬ ሲጨቃጨቁ ሰምቼ እናትና አባቴ ተጣሉ ብዬ እንደ ተዓምር ለማቲና ለአቢ እያለቀስኩ መናገሬን አስታውሳለሁ። በእኛ ፊት አያደርጉትም እንጂ ለብቻቸው ሲሆኑ እንደማንኛውም ባለትዳር የሚጨቃጨቁበት ጉዳይ ሊኖራቸው እንደሚችል የገባኝ መቼ እንደሆነ እንኳን እንጃ ...... እሷ ከእኔ ተሽላ በእርጋታ ነገሮችን የተቀበለችበት መንገድ እየቆየ 'ሆ'ያስብለኝ ገባ።
ለተወሰኑ ቀናት ነገሮች እንደዛው ባሉበት ቀጠሉ። ልጄ ምንም እንኳን ስለአባቷ ያለውን ነገር ብትቀበልም ለጊዜው ልታገኘው እንደማትፈልግ አስረግጣ ነገረችኝ። እኔ ግን ላገኘው እፈልጋለሁ!! አሁንም የቀረኝ ነገር እንዳለ ነው የሚሰማኝ!! ባገኘው ፣ የሄለንን ያህል እንኳን ወዶኝ ባይሆን አብረን ያሳለፍነው ጊዜ በልቡ ውስጥ የሆነ ቦታ እንደነበረው ማወቅ ከሆነ መታሰሬ የሚፈታኝ ነገር ይመስለኛል። ለልጄ ያልኳት ከልቤ ነው። ይቅርታ እንዲለኝ አይደለም መሻቴ ምክንያቱ እኔን ትቶ ለመሄድ ውሃ ያነሳ እንደነበር ነው ማወቅ የምፈልገው። በሌላ ቋንቋ እሱጋ የነበረኝን ዋጋ ነው ማወቅ የፈለግኩት።

በቻልኩት አጋጣሚ እና ጊዜ የባባን እናት እየሄድኩ አያታለሁ። ምንም ለውጥ የላትም። እነግሩም የህክምና ወጪዋን እየሸፈኑ ቢሆንም ከዛ ባለፈ የተነጋገርነው ነገር የለም። ምንም ከመወሰኔ በፊት ሄለን ብትነቃ ውሳኔውን ለሷ ለመስጠት ፈልጌ ይመስለኛል በዝምታ ቀናት ያስቆጠርኩት።

አሸናፊ ለባባ ስለእናቱ እንዳልነግረው ቢነግረኝም ያን ማድረጉ ልክ መስሎ ስላልታየኝ ለባባ በእድሜው ሊገባው በሚችል መልኩ እናቱ ለጊዜው መታመሟን ነግሬው የተወሰነ ቀንም ይዤው ሄጄ አሳይቼዋለሁ። ምናልባት እሷ ብታልፍ እንኳን ዋሽቼው ልጄ አላደርገውም። እናቱ እንደሞተች አውቆ ከልጄ ለይቼ የማላየው እናቱ እንደሆንኩ አሳየዋለሁ። እናት እሆነዋለሁ!! የማትዋሸው እናት!! መጀመሪያ የወሰድኩት ቀን እንድትነቃለት ስሟን እየጠራ ሲያለቅስ እንደህፃን አብሬው አልቅሻለሁ!! የዛን ቀን እንቅልፉን ተኝቶ ሁሉ እየቃዠ ይጠራት ነበር። አልጋዬ ላይ አምጥቼው አጠገቤ አስተኝቼው በጭንቀት እና በላብ የተጠመቀ ትንሽዬ ፊቱን እያየሁት ለረዥም ሰዓት እንቅልፍ አልወሰደኝም። እቅፌ ውስጥ ሲሆን እንደምጠብቀው ልቡ ነግሮት ነው መሰለኝ ለጥ ብሎ ተኛ!!

ከተከታዮቹ ቀን በአንዱ ከስራ ተመልሼ ከልጄ እና ከባባ ጋር መክሰሳችንን እየበላን በሬ ተንኳኳ። የግሩም እናት ነበሩ። ከመጀመሪያው ቀን በኋላ አይቻቸው ስለማላውቅ እየገረመኝ ወደውስጥ እንዲገቡ ጋበዛኳቸው።

"ላናግርሽ ፈልጌ ነበር። በልጆቹ ፊት ባይሆን ጥሩ ነው!" አሉኝ ወንበሩ ላይ እየተቀመጡ። ልጄ እኔ ምንም ከማለቴ በፊት ባባን ይዛው ወደክፍሏ ሄደች።

"ምንድነው ሀሳብሽ? ውሳኔሽን ማወቅ እፈልጋለሁ! ልጄ ከዛ ቀን በኋላ ተረጋግቶ ምንም ነገር ማድረግ አልቻለም! ስራውን እንኳን በትክክል እየሰራ አይደለም! እሱ ዓመት ሙሉ ዝም ብትዪም እንደማይጠይቅሽ ስለማውቅ ነው ራሴ የመጣሁት! እየሆነ ያለው ነገር ምንም አልገባኝም! 'እሷ ለራሷም አልተረጋጋችም!' ይለኛል እሱ። መቼ ነው የምትረጋጊው? አንቺ እስክትረጋጊ ከዛሬ ነገ ፖሊስ መጥቶ በሬን አንኳኳ : ልጄን ወሰደብኝ እያልኩ መሳቀቅ ገደለኝ" አሉኝ ያነገቱትን ቦርሳ እንኳን ከትከሻቸው ሳያወርዱ

ይቀጥላል .......

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Meri feleke
አታምጣ ስለው አምጥቶ ቆለለው #8
«ስትነቃ ውሳኔሽን ባትቀበልስ” አለኝ ማት። የግሩምን ጉዳይ በሽምግልና እንዲያልቅ መወሰኔን ስነግረው።
"አስቤዋለሁ ማትዬ ... ይህቺ ሴት ሱቅ ውስጥ ተቀጥራ ነበር የምትሰራው። የቤት ኪራይ ከፍላ ...ልጇን አሳድጋ ... የትምህርት ቤት ከፍላ .... ምን ዓይነት ህይወት የነበራት ይመስልሃል? ይህቺ ሴት አንድ ቀን የምትጎርሰው ብታጣ ሄዳ የምትጠጋበት ዘመድ እንኳን የላትም። ታዲያ ለዝህች ሴት የገጫትን ሰው በእስር ከማስቀጣት እና ለልጇ የወደፊት ህይወት ዋስትና የሚሆናት ተቀማጭ ገንዘብ ከማግኘት የቱ ይበልጥባታል?"
"እሺ ካሳው ምን ያህል ብር እንዲሆን ነው ያሰብሽው?"
"ለዛ ነው እኮ የፈለግኩህ! ጉዳዩን በቁም ነገር እንዲይዙት እፈልጋለሁ። የሽምግልና ሂደቱ በትክክል ይደረጋል። ሰዎቹ ሀብታም ነገር ናቸው። ጥሩ ሰዎችም ይመስላሉ! እናትየው ልጇ አይታሰርባት እንጂ ምንም ያህል ብንላት አታመነታም! ብቻ ለባባ የወደፊት ዋስትና የሚሆን ገንዘብ መጠን መሆን አለበት። ሽምግልናውን የሚይዙልን ሰዎች አዘጋጅልኝ! "
"እንደገባኝ ከሆነ ያሰብሽው ገንዘብ ትንሽ አይደለም። ባይስማሙስ? "
"ምንም ቢሆን በልጄ ጉዳይ እንደማልቀልድ ማወቅ አለባቸው።" ባባን 'ልጄ!' ብዬ መጥራቴን ያስተዋልኩት ማት ያንን የስስት ፈገግታውን ፈገግ ሲል ነው።
"እሺ መች እንዲሆን ነው ያሰብሽው?"
"ነገሩን እያሰነዳዳን ትንሽ እንቆይ። ማትዬ ትንሽ ልጠብቃት። ምንም እንኳን አሸናፊ ሃላፊነቱን ቢሰጠኝም፣ እሷም ስሜን ስትፅፍ አምናብኝ ቢሆንም ህይወቱ የሷ ነው። የሷ የወደፊት ነው። ምንም የሚያስቸኩለን ነገር የለም! ልጠብቃት!"
"እሺ አያድርገውና ብትሞትስ?"
"ውሳኔዬን የፈራሁት እሱን ሳስብ ነው። ያሰብኩት ገንዘቡ ለባባዬ እንዲቀመጥለት ነው። ራሱን ሲችል የሆነ ነገር ለመጀመር ይረዳዋል። እናቱን አይመልስለት ይሆናል። ቢያንስ ግን ለሆነ ነገር ይጠቅመዋል። ግሩም ቢታሰርም እናቱን አይመልስለትም። ግን ትልቅ ሆኖ ከገንዘቡ ይልቅ እናቴን ያሳጣኝ ሰው ቢቀጣልኝ ነበር የምፈልገው ቢለኝስ? ይቅር ባይለኝስ? ቢጠላኝስ?"
"እህቴ ያንቺ ልጅ ሆኖ አድጎ እንደሱ ይላል ብዬ አላስብም! ካንቺ ጋር አይደለም አድጎ አንድ ቀን አድሮ ያንቺ ልብ የማይጋባበትኮ አይኖርም! ትልቅ ሲሆን እንዳንቺ ይቅር ባይ፣ እንዳንቺ ጠቢብ፣ እንዳንቺ መልካም ነው የሚሆነው።"
"ሁሉም ልጆችኮ በእናታቸው አይወጡም!"
"ሁሉም ልጆች ግን እንዳንቺ ፍቅሯ የዓለምን ክፋት ሁሉ የሚያስረሳ እናት የላቸውም።"
"ባክህ እናት ሁሉ ለልጇ እንደዛ ናት።"
"ለልጇ አዎ! በዙሪያዋ ላሉ በሙሉ ግን አይደለችም። ልጆችሽ ለእነርሱ የምታደርጊውንና የምትሆኚውን ብቻ እያዩኮ አይደለም የሚያድጉት። በእያንዳንዷ ቀንሽ ለሌሎች የምታደርጊውን እና የምትሰጪውን ፍቅር ያያሉ። እነርሱም ሲያድጉ በደም ለተጋመዳቸው ብቻ ሳይሆን ለሰው ልጅ ሁሉ ቅንና ፍቅር ሰጪ መሆን ትክክለኛው መንገድ መሆኑን ያውቃሉ። በልጅሽ ውስጥ ራስሽን አታዪም? "
"እኔእንጃ ማት አንዳንዴ እኔ እንደምትሏት ዓይነት ቅን ሰው ከሆንኩ፣ ሁሌ እንደምትለኝ ገራሚ ልብ ካለኝ ለምንድነው አምላክ ደስተኛ ሆኜ እንድኖር ያልፈቀደው?" አልኩት
ማለት የፈለግኩት የነበረው ግን ለመጀመሪያም ለመጨረሻም ጊዜ የወደድኩት ሰው ትቶኝ ሲሄድ ጥፋቴ ምን ነበር? ሙሉ ልቤን ሰጥቼ ፍርክስክስ ያለ ልብ መቀበል ፍራቻ ወንድ መልመድ ሸሽቼ ልጄን ብቻዬን ሳሳድግ የየትኛው ጥፋቴ መከር ነበር?
"የምትፈልጊውን አምላክሽን ለምነሽው ታውቂያለሽ?"
"አምላክ እኮ ነው። የሚያስፈልገኝን ከእኔ በላይ የሚያውቅ፣"
"እራሱ አምላክ ነው 'ጠይቁ ይሰጣችኋል አንኳኩ ይከፈትላችኋል' ያለው። ሳንጠይቀው በፊት የምንጠይቀውን ስለማያውቅ አይደለም። አምላክ የነፃነት አምላክ ስለሆነ በፈቃዳችን ነው የሚያደርግልን። ፈቃዳችንን ይፈልጋል። ባይሆን ኖሮ ስንቱን ልበ ድንጋይ እያጋጨ አይመልሰውም ነበር? ምክንያቱም ልኩና የሚያስፈልገው መልካም መሆን ስለሆነ! ግን ለምርጫችን ይተወናል። አምባገነን አይደለማ!"
"እንዴ? የምንፈልገውና የምንጠይቀው ሁሉኮ ልክ አይደለም። አንዳንዴ የማይበጀንን እንጠይቃለን። እርሱ ግን የቱ እንደሚበጀን ያውቃል።"
"እኔ የማምነው ለምሳሌ 'አምላኬ ሆይ ደስተኛ አድርገኝ!' ብለሽ ስትለምኚ ምናልባት ያንቺ ልመና ገንዘብ ሊሆን ቢችል እርሱ ደስታሽ ልጅጋ ከሆነ ያለው ልጅ ይሰጥሻል። የለመንሽው ደስታን ነውና ደስታሽን ታገኛለሽ። እኔ እንደዛ ነው የማስበው!"
"እና ስላልጠየቅሽ ነው ያልተሰጠሽ ነው የምትለኝ?"
"ያንቺ ከዛም ያልፋል እህቴ!" ሳቅ እያለ "አምጥቶ አልጋሽ ላይ ቢያስተኛልሽም ራሱ 'የእግዜር እንግዳ' ነው ብለሽ አልጋሽን ለቀሽለት ትሄጃለሽ! ቢሰጥሽም ለመቀበል ዝግጁ አይደለሽም።"
"ባል ነው የምፈልገው ወጣኝ?" አልኩት ፈገግ ብዬ። ሁሌም ሳልናገር በፊት ያሰብኩት እንዴት እንደሚገባው ግርም ይለኛል።
"እኔስ እንግዳ ተቀባይ ነሽ አልኩ እንጂ ባል ትፈልጊያለሽ ወጣኝ? እኔ የምለው እማዬ ባባን እንዳላመጣሽው ነገረችኝ ለማን ትተሽው ነው ስራ የገባሽው?" አለኝ። ስራ ስገባ እነእማዬጋ እየተውኩት ነበር የምሄደው።
"የምታይልን ልጅ ቀጠርኩ" ስለው የሆነ የምስራች የነገርኩት ነበር የሚመስለው። ደስ አለው።
"ምነው? ምንድነው የሚያስፈነድቅህ?"
"እህቴ ሰራተኛ ኖራት!" ብሎ አሁንም ይፍነከነካል።
"ታዲያ ምኑ ነው የሚገርመው?"
"እስከዛሬ ሰው ሳያስፈልግሽ ቀርቶ ነበር ሰው ያልኖረሽ? 'እኔ የማንን ጎፈሬ ሳበጥር ነው ሰራተኛ የምቀጥረው?' ያልሽንን አምነንሽ ዝም ያልን ነው የሚመስልሽ? አዲስ ሰው ወደ ህይወትሽ በምንም መልኩ እንዲገባ ስለማትፈልጊ ነው። ይሄንንማ ለእማዬ እስክነግራት...."
"ኸረ አይደለም! ደግሞ እማዬም እንደዛ ነው የምታስበው?" የምርም በዚህ መንገድ አስቤው አላውቅም!!
"አንቺ ብቻ ነሽ እንደዛ የማታስቢው" አለኝ አሁንም ፈገግታው ፊቱ ላይ እየተርመሰመሰ። ቀጠል አድርጎ "ግሩም ምን አለ?"
"ስለምኑ?" ድንብር አልኩ።
"ስለሽምግልናው ነዋ!"
"ደስ ነው ያለው!! ቅጣቱን አይደል በገንዘብ የቀየርንለት? ለምን ካሳውን እንደመረጥኩ ስነግረው 'እንኳን በሞትና በህይወት መሃከል ለመሆኗ ምክንያት ሆኜ፣ እንዲሁም ልንረዳት የሚገባት ሴት ናት!' አለኝ"
"ቆይ ቆይ ከዚህ ሌላ ምን አወራችሁ?"
"ምንም!" አልኩኝ ፍርጥም ብዬ
"አላውቅሽም እና ነው? ሌላ ነገርማ አለ! ምን አለ ስልሽ እንደፌንጣ አትዘዪም ነበር።"
"እራት ልጋብዝሽ!" አለኝ።
"እና?"
" ለምን? ስለው ላመሰግንሽ አለኝ! እስከአሁን ያመሰገንከኝ በቂ ነው እራቱ አስፈላጊ አይደለም አልኩት ..." ተናግሬ ሳልጨርስ ማት በሳቅ ይንፈቀፈቅ ጀመር።
"እንዴት ያለሽው ገልቱ ነሽ?" እያለ በሳቅ ይፈርሳል ። የማይሆን ነገር ስናደርግ ገልቱ ብቸኛዋ የአባዬ ስድብ ናት። እራት ልጋብዝሽ ማለት 'ላውቅሽ እፈልጋለሁ!' ማለት እንደሆነ ጠፍቶኝ አልነበረም። አፌ ላይ የመጣልኝ ለምን? የሚል ጥያቄ ነበር። እሱም እንደማቲ 'ምኗ ገልቱ ናት?' ብሎ መሰለኝ ላመሰግንሽ! ያለኝ!! ማት መሳቁን አላቆመም!!
"ማቲዬ በእማዬ ሞት እረፍ!"
"እሺ ይቅርታ!" ለመኮሳተር ይሞክርና ደግሞ ይስቃል። "እህቴ ይቅርታ አለመሳቅ ከባድ ነው። ለምን? ምን የሚሉት ጥያቄ ነው?" ይደክማል። "ቆይ አንቺ ከአሼ በኃላ ጭራሽ ዴት አድርገሽ አታውቂም? እንዴ (እንደማስታወስ እያለ) ማነው ይሄ ቢጫ መኪና የሚነዳው ቢጫው ሰውዬ ..." ይስቃል
"ድንገት ከመሬት ተነስቶ እራት ልጋብዝሽ ብሎኝ ግን አይደለም ዴት የተደራረግነው?"
"ደብዳቤ ይፃፍ? የልብ ስዕልስ ይጨምርበት? መንገድ ላይ እየጠበቀ ሳታዪው ከጀርባሽ እየተከተለ ለአንድ ዓመት ይሸኝሽ? አንቺን ለማየት ደሞዙን 30 ቦታ ከፍሎ በየቀኑ ባንክ እየመጣ አስር አስር ብር በየቀኑ ሴቭ ያድርግ? "
(ቢጫ ሰውዬ ያለው 'አዲስ' እንደዛ ነበር ያደረገው። በመጨረሻ እሺ ብዬው ሁለት እራት እንኳን በስርዓቱ ሳንበላ ነው የተለያየነው።)
"For God sake ዴት ለማድረግ እየደረሰች ያለች ልጅ ባደረሽበት እድሜ እንደኮረዳ መሽኮርመም? እህቴ! ትልልቅ ሰዎች እንደዚህ ነው የሚያደርጉት በአዋቂ ደንብ ተገናኝተው ይነጋገራሉ። ይተዋወቃሉ። አብሮ የሚያስኬድ ነገር ካላቸው ይቀጥላሉ ካልሆነ ተነጋግረው መንገዳቸውን ይለያሉ!"
"እኔ ይሄ ጠፍቶኝ ነው? "
"ጠፍቶሽማ ነው!" ይንፈቀፈቃል። "ትልልቅ ሰዎች ሌላ የሚያደርጉት ምን መሰለሽ? አንደኛው እስኪደውል አይጠባበቁም! ደውዪና እራቱን መች እናድርገው ?በይው።"
"አላደርገውም! በፍፁም!"
"እህቴ? " አለኝ ሳቁን ጨርሶ እየተኮሳተረ አንድ አንዴ አንዳንዴ ሲያዝንልኝ በሚያወራበት ፊቱ «ብቻሽን ዘመንሽን ሁሉ ትኖሪያለሽ? የሰው ልጅ ደግሞ ቀርበሽ ሳታውቂው ወጥ ውስጥ ያለጨው እንደሚቀመሰው ቅምስ አድርገሽ አታውቂውም! እድሉን ስጪውና ሞክሪው!"
"ብወደውና ልቤን ቢሰብረውስ?"
"የፍቅር ቀመሩኮ ያ ነው እህቴ! ስትወጂ ሊሰብረው እንደሚችል እያወቅሽ አምነሽ ልብሽን ትሰጫለሽ! አንዳንዱ ይጠብቅልሻል። አንዳንዱ ደግሞ እንደፈራሽው ሰብሮ ይመልስልሻል። ደፍረሽ ካልሞከርሽው ግን ልብሽን እንደእንቁ ሊጠብቅልሽ የሚችለውንም ገፋሽው ማለት አይደል?"
"እሺ ይሁን እንበልና ብወደውኮ የባባን እናት የገጫትን ሰው ማለት ነው። አይበለውና ባትተርፍ እናቱን የቀማውን ሰው ዴት ማድረጌን ሲያውቅ ባባ ምን ይለኛል? "
"ታወሳስቢው የለ እንዴ?" አለኝ ግርም ብሎት እያፈጠጠ። ......
ይቀጥላል.....

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Meri feleke
የአብዮት ፍሬ ነኝ 2

ዱርዬ ነው ፊቱ !

ብዙ አይነት ፈተና አውቃለሁ። የአምስተኛ ክፍል የሁለተኛዋ ክፍለ ጊዜ ፈተና ግን እንዴት ይገለፃል?

ሁለተኛ ክፍለ ጊዜ የእረፍት መንደርደሪያ ናት። የየሺ ጮርናቄ የሚጠበሰው በሁለተኛዋ ክፍለ ጊዜ ነው።

የጮርናቄ ሽታ ከሸክላ ጥብስ ሽታ በላይ ያማልላል...ከጭቅና ጥብስ በላይ ያነሆልላል። ምድረ ውሪ ነፍሳችን ዝቅ የምትልለት ውብ መዓዛ! በዛ ሰዓት ከገነት ፍሬ በላይ ለጮርናቄ ሽታ እንንበረከካለን። ከፈጣሪ አልቀን ለፓስቲ እንሰግዳለን። 

ወንድማችን ፓስቲ ሆይ

በሰማይ የምትኖር ብለን ለመፀለይ አይሸመቅቀንም 😋 እንደውም ማንም ሰባኪ መጥቶ ገነት ምን ትመስላለች ቢለን...ሰማዩም ...ምድሩም...ዛፉም...ድንጋዩም.. .ሳሩም ጮርናቄ የሆነ ቦታ ብለን የምንመልስ ይመስለኛል። 

ያቺ ሰዓት የቤት ልጆች ከፍንዳታ ልጆች ተለይተን የምንቁለጨለጭባት ክፉ ትውስታችን ናት።

አንድ ብር ከስሙኒ ማግኘት ተዓምር ነው...ምትሀት ነው...ድግምት መተት ነው ለኛ !

እነ ፍንዴክሶቹ እስጢፎና ቦጌ ለዚህ የታደሉ ናቸው ። በሁለተኛው ክፍለ ጊዜ አስፈሪው ሂሳብ መምህራችን ቢከሰቱ እንኳ እነ እስጢፎ በመስኮት ከመዝለል አይመለሱም። 

እኛ ሆዳችን እየተላወሰ ጂኦሜትሪ ምናምን እንማራለን ። የሌላውን ባላውቅም እኔ ግን በዛች ፔሬድ ትምህርት አይገባኝም።

እንኳን ጂኦሜትሪ ቀላሉ አማርኛ እንኳ ለኔ ፊዚክስ ይሆንብኛል። በሁለተኛው ክፍለ ጊዜ አንድ የአማርኛ መምህር የቆጡን አወርድ ብላ ቢጀምሩ የብብቷን ፓስቲ ጣለች ከማለት አልመለስም 😄

የሆነውም ሆኖ ግን ዱርዬ ነው ፊቱ የዋህ ነው ልቡ ይሉት ዘፈን የገባኝ ያን ጊዜ ነው። 

ቸካዮቹ እነ አቤኒ (የሀብታም ልጅ ነው እኮ)

ጮርናቄ ገዝተው አካፍሉን ስንላቸው ፓስቲውን በርገድ ያደርጉና ምራቃቸውን እንትፍ ይሉበታል። ወሽመጥህ አብሮ ቁርጥ ይላል ።

እስጢፎ ግን የዋህ ነው...ከገዛት ፓስቲ ውስጥ አርባ አራቱንም ታቦት ጠርተን ቢሆን ያካፍለናል። ያቺን አንድ ጉርሻ ማን ወንድ አላምጦ ይውጣታል? እንደ ጫት ተርዚና ወጥረን ደቂቃዎችን እንቆያለን ። 

እንደውም ከኔ ጋር ከሚለምነው ቢኒያም ጋር አንድ ቀን ተጣልተናል።

ቢና ፓስቲዋን አንዴ ቆርሶ ውጧታል። እረፍት ጨርሰን ስንገባም ያላምጣል። ከኛ ተደብቆ ኪሱ ውስጥ ይዞ ይሆናል ብዬ በረበርኩት ወፍ የለም። 

ቀስ ብዬ ስሾፍ እጁን የትም ሳይሰድ አፉ ግን ያላምጣል። ከቆይታ በኋላ አንድ ነገር ገባኝ።

ቢኒ ጮርናቄዋን በእረፍት ሰዓት ቢውጣትም...መልሶ መላልሶ እያጋሳ እንደ ፈረስ መኖ እያመነዠካት ነበር።

ስነቃበት ደነገጠም ...አፈረም...እኔና ጓደኞቼ ደግሞ ዜብራው እያልን ሙድ ያዝንበት.. .እንደ ፈረስ አሽካካንበት.. .

ከዛች ቅፅበት በኋላ ቢኒ እኔን ሲያየኝ ብዙ አልመቸውም 😂

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Mikael Aschenaki
በር ላይ እንደመግቢያ የሚያገለግለው ፓስታ ፣ መኮሮኒ፣ ሩዝ ... ደረቅ ምግብ ፣ የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ፣ አልባስ ይሆናል ! ቀን 23/4/2014 በብሔራዊ ቴአትር ቤት ይቀርባል ! በለቱ ከጠዋት ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር በር ላይ ደም የሚሰጥ ይሆናል ። ቴአትሩ የሚቀርብበት ሰዓት 11:30 ይጀምራል

@wegoch
አታምጣው ስለው አምጥቶ ቆለለው #9

“በቅርብ ጊዜ …. ማለቴ አናቴ በነጭ ፀጉር ከመከደኑ በፊት ዝግጁ የምትሆኚ ይመስልሻል?”አለኝ ግሩም ፈገግ እያለ።

ማት እንዳለኝ ራሴው ነኝ የደወልኩለት። አዋቂዎች ያደርጉታል እንደተባልኩት የእራቱን ሀሳብ ተቀብያለሁ አልኩት። ስለብዙ ነገሮች ስናወራ ቆይተን።

"ግሩም አሁን ባለሁበት ሁኔታ ካንተጋ ለመሆን ዝግጁ አይደለሁም!" ብዬው ነው

"አናቴ በነጭ ፀጉር ከመከደኑ በፊት ዝግጁ የምትሆኚ ይመስልሻል?" የሚለኝ

"እንደማየው ከሆነ ካሁኑ ነጭ ፀጉር ጀምሮሃል! ሙሉ አናትህን እስኪከድነው ያለው ጊዜ ዝግጁ ለመሆን ያንሰኛል!" አልኩት እሱ በጀመረው ጨዋታ

"የእውነት ዝግጁ ስላልሆንሽ ነው ወይስ እንደአንዳንድ ሴቶች ደጅ በማስጠናት ምን ያህል ርቀት እንደምሄድ ልትፈትኚኝ ነው?"

"አይ እኔስ የእውነቴን ነው። ግን እንዳልካቸው ሴቶች ቢሆንስ?" አልኩት

"አታስዋሺኝ እኔ ትዕግስቱ የለኝም። ቀጥተኛ ሰው ነኝ! የተሰማኝን ፊትለፊት እናገራለሁ። ይሄ የልጅ አባሮሽ ጨዋታ እድሜዬም ባህሪዬም ነው ብዬ አላስብም። ለአባባል ነው እንጂ ጠብቀኝም ብትዪኝ ፀጉሬ ነጭ እስኪሆን አልጠብቅሽም አልዋሽሽም!" አለኝ እየሳቀ

"ሀቀኝነትህ ደስ ይላል"

"እኔ ስለሆንኩ ነው ወይስ ባጠቃላይ ማንንም ቢሆን ለመቀበል ዝግጁ አይደለሽም?"

"ለማንም ቢሆን ዝግጁ አይደለሁም! አንተ መሆንህ ደግሞ ይባስ ፈታኝ ይሆንብኛል።"

ለማውራት የሚከብድ ሰው ስላልሆነ ወይም ምክንያቴን ማወቅ ይገባዋል ብዬ እኔእንጃ ጥቃቅን ነገሮች ሲቀሩ ብዙውን ነገር ስለአሸናፊ አወራሁት። በዝምታ ሲሰማኝ ከቆየ በኋላ

"የሆነ ሰው በጥይት ተመቶ ቢቆስል ቁስሉ እያንገበገበው መጀመሪያ የሚያደርገው ሀኪምጋ መሄድ አይደል? ቁስሌ ሲነካ ስለሚያመኝ ብሎ የሚደማ ቁስሉን አቅፎ እቤቱ አይቀመጥም! ሀኪሙ ቀዶም ይስፋው፣ ምንም ያድርገው ግን አምኖ ቁስሉን ይሰጠዋል። ያኔ የሚፈጀውን ጊዜ ፈጅቶ ቁስሉን ያድንለታል። ያው ጠባሳው ሙሉ ለሙሉ ባይጠፋም!" አለ ትከሻውን እየሰበቀ።

"አይገናኝም! ሀኪሙ እንደሚያድነው ቀድሞ ነገር ያውቃል። ከርሱ ቁስል ሌላ ብዙ ቁስሎች እንዳዳነ ስለሚያውቅ ነው አምኖ የሚሰጠው!" አልኩት

"ያን ለማወቅ የሀኪሙን ፋይል ያገላብጣል? ያለፈ ታሪኩን ያጠናል? በፍፁም! የለበሰውን ነጭ ጋውንና ማዕረጉን አይቶ ያምነዋል። ምናልባት ሀኪሙምኮ የሆነ ቀን ተሳስቶ በሙያው ህይወት የሚቀጥፍ ስህተት ሰርቶ ያውቅ ይሆናል።"

"እና ሀኪሙን ነኝ እያልከኝ ነው?"

"አቁሳይ እንዳለ ሁላ ሀኪምም አለ እያልኩሽ ነው!"

ኑሮዬ ያለፉትን 15 ዓመታት (ከሆስፒታል ስልክ እስከተደወለልኝ ቀን ድረስ) ጠዋት ከእንቅልፌ ስነቃ ምን እንደሚመስል የማውቀው ፣ የታቀደ ቀን ያለኝ ፣ ተመሳሳይ እና በአብዛኛው ተደጋጋሚ ነበር።

ያልተለመደ፣ አዲስ፣ አድቬንቸር ያለበት ቀን አልወድም። አልሞክርም። አዲስ ነገር ስለምጠላ አይደለም። የምሞክረው አዲስ ነገር ያለኝንም ረጭ ያለ ቀን ይዞብኝ ሄዶ የተሻለ ፍለጋ ያለኝን እንዳላጣ ስለምፈራ እንጂ። ስለዚህ ባለኝ ቀን አርፌ እውላለሁ። አዲስን ነገር በመሞከር ውስጥ የተሻለ ነገር ሊኖር እንደሚችልም ጠፍቶኝ አይደለም። የመሆን አጋጣሚው 0.00002 % ቢሆንም የባሰውን የምጋፈጥበት ዝግጁነት የለኝም! ስለዚህ ጨው የሌለበት አልጫ አልጫ የሚል ቀኔን እያመሰገንኩ እሰለቅጣለሁ።

"እንደውም ሀሳቤን ቀይሬያለሁ! ፀጉሬ እስኪሸብት እጠብቅሻለሁ" ብሎኝ ነበር ግሩም እየሳቀ የዛን ማታ ወደቤቴ ሲሸኘኝ። ራይድ ጠርቶ ነበር የሸኘኝ።

"እስከመቼ ነው መኪና የማትይዘው?" ስለው

"እሷ እስክትነቃ! ነቅታ ጥፋትህ አይደለም ካለችኝ የዛኑ ቀን ካለሽበት መጥቼ ወደምትፈልጊበት እሸኝሻለሁ።"

"ካልነቃችስ?"

"አላውቅም! ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድብኝ አላውቅም! ጊዜ እፈልጋለሁ" ነበር ያለኝ።

ከግሩም ጋር እራት መብላቴ ስለግሩም ያለኝን ነገር አይደለም የቀየረው። ባልገባኝ ምክንያት በዙሪያዬ ያሉትን ነገሮች የማይበትን መነፅር እንደቀየረው ገባኝ። እና ለማድረግ የማልደፍረውን ነገር ደፈርኩ። አቢጋ ደወልኩ! እስከዛሬ ያልነገርኳትን ቻው እንኳን ሳትለኝ መሄዷ እንዴት እንዳስከፋኝ፣ በህይወቷ እንዳልነበርኩ ስትረሳኝ የተሰማኝን መታመም ልነግራት እንጂ ልወቅሳት አይደለም።

'ህይወት የቅፅበቶች ጥርቅም ናት' ትላለች እማዬ። ቤተሰቦቼ በጣም ለጥቃቅን ነገሮች ትኩረት የሚሰጡ፣ ትንንሽ ለውጦችን ትኩረት ሰጥተው የሚከታተኩ ዓይነት ናቸው። ደስታም ይሁን ሀዘን። ለምሳሌ እማዬ ሰራተኛ መቅጠሬን ከዩንቨርስቲ የመመረቄን ያህል እኩል እንደትልቅ ክስተት እንደምትደሰትበት ፣ ከግሩም ጋር እራት መብላቴን ስነግረው ማት ስራ ቦታ መጥቶ የተሰማኝን ስሜት እንደሚያረጋግጠው ፣ 'ባባ ፖፖ ላይ ተቀምጦ ነው የሚሸናው' ስላቸው አባዬ እቤት ድረስ መጥቶ 'ወንዶቹ እንዴት እንደሚሸኑ ላሳይልሽ' እንዳለኝ አይነት .....ህይወት የትልቅ ክስተቶች ጥርቅም አይደለችም! ልክ ስለሰው ያለንን ነገር በጥሩም ይሁን በመጥፎ ለመቀየር አንድ ሰው እንጂ የሰው ልጅ ሁሉ እንደማያስፈልገው ....... በአንድ ሰው ምክንያት መላ የሰው ዘርን እንቀየማለን፣ እንፈራለን፣ እንጠላለን እንጠራጠራለን እንደዛው በአንድ ሰው ምክንያት ደግሞ መላ ህይወትን እንወዳለን ለመኖር እንጓጓለን ፍጥረትን ሁሉ እንወዳለን እንደዛ .....
የሚገርመው ያ አንድ ሰው ባደረጋት አንዲት ስህተት ወይም አንዲት መልካምነት ይሆናል እንደዛ ዓለማችን የሚገለባበጠው

"ይቅርታ አድርጊልኝ ፌቪዬ እንደዛ እንዲሰማሽ እንዳደረግኩ በጭራሽ አላውቅም! ልጆች ነበርንኮ!" አለችኝ አቢ ፀጥ ብላ ከሰማችኝ በኃላ .... ከዚህ ሁሉ ዓመት በኋላ ዛሬ የሆነ ያህል እያንዳንዱን ነገር ማስታወሴ የገረማት ትመስላለች። እንዳሰብኩትም የሆነ ሸክም ከላዬ ላይ የቀለለኝ ስሜት ተሰማኝ።

እንዲህ ነውኮ አይደል? የተቀየማችሁት ሰው፣ በእሱ ምክንያት እንቅልፍ ያጣችሁለት ሰው፣ ህመማችሁን ለዓመታት ያስታመማችሁበትን ቁስል የሰጣችሁ ሰው ጭራሽ መከፋታችሁንም ላያውቀው ሲችል? ልክ እሱ ከእናንተ ህይወት ሲወጣ ረስቷችሁ ህይወቱን እንደኖረው እናንተም ረስታችሁት የኖራችሁ ሲመስለው? ለልጄ የመከርኳትን ምክር ለራሴ መተግበር ነበረብኝ።

"አቢዬ ቂም አልያዝኩብሽም። ካልነገርኩሽ አይወጣልኝም ብዬ ስላሰብኩ ነው የነገርኩሽ። ከሰሞኑ የገባኝ እኔ ያለስስት እንደእህቴ ሊወድሽ የሚችል ትልቅ ልብ ስለነበረኝ እንጂ የወደድኩሽ አንቺ ስለሚገባሽ አልነበረም። ያኔ ቢገባኝ ደስ ይለኝ የነበረው ልቤ ፍቅሩን የተሳሳተ ቦታ ማፍሰሱ እንጂ መውደዱ ስህተት እንዳልነበር ባውቅ ነበር።" አልኳት። ስልኩን ዘግቼው አስብ የነበረውም ያንን ነው። በህይወቴ ውስጥ በብዙ ወድጃቸው በተመሳሳይ ሁኔታ በአካል አጊንተው እንኳን ሊሰናበቱኝ ላልፈለጉ ሁለት ሰዎች መውደዴ ስህተት ይመስል ራሴን ስቀጣ የኖርኩርኩት እኔ! ረስተውኝ ስለኖሩ መታመሜን እንደመሸነፍ ቆጥሬው በራሴ የምበሳጨው እኔው!

ደስ የሚል ስሜት ሲሰማኝ ከረምኩ። ቀኖቼ የተለመዱት ቢሆንም ስሜቴ ግን ይለይ ነበር:: (እንደዋዛ ቀናት ወራትን ተክተው በአንዱ ጠዋት ከሆስፒታል ተደውሎ ሄለን መንቃቷ እስከተነገረኝ ሰዓት።) የሚሰማኝን ስሜት መለየት ቸገረኝ። የሆነ ደስ የሚል ስሜት ከዛ ደግሞ የሆነ የተወናበደ ልቤን ክብድ የሚለው ስሜት ከዛ ደግሞ የመከፋትም ስሜት በአንድ ጉዳይ ሁሉም ስሜት። ለደቂቃዎች ስልኬን እንኳን ከጆሮዬ ሳላወርደው ቆየሁ። ድንዝዝ ያለ ስሜት .........
ከተቀመጥኩበት ሳልነሳ ማት እና ግሩምጋ ደወልኩ።
"እግዚአብሄር ይመስገን!" ካለኝ በኋላ ወዲያው "መጣሁ!" አለኝ ማት ሳልነግረው ይገባው የለ? ግሩም ፈነጠዘ። ሆስፒታል ስደርስ ነቅታ ሰውነቷ ላይ ተሰካክተው የነበሩት ማሽኖች ተቀንሰው ቅልል ብሏታል።

"ልጄስ?" ነው ያለችኝ ገና ስታየኝ መልኬን ታውቀዋለች ማለት ነው? ወይስ ገምታ ነው ብዬ እያሰብኩ

"ትምህርት ቤት ነው!" አልኳት ባባ ትምህርት ከጀመረ ሁለት ሳምንቱ ነበር። ዶክተሩ 'ከዚህ በኃላ ልትነቃ የምትችልበት እድል እየጠበበ ነው።'ያለኝ ጊዜ ነው ትምህርት ቤት ግማሽ ሴሚስተር ላይ ያስመዘገብኩት። ዝም አለች። ከዛ ደጋግሜ "እንዴት ነሽ አሁን?" የምላት እኔ ሆንኩ። ማት እና ግሩም ሲገቡ ማናቸው በሚል ስታያቸው ማንነታቸውን ነገርኳት።

"ቤተክርስቲያን እየሄድኩ ነበር።" አለች ለግሩም በሚመስል አነጋገር።

"ይቅርታ በፍፁም አላየሁሽም ነበር!" አላት ቀጥሎ ከአፏ የሚወጣውን ለመስማት መጓጓቱ እያስታወቀበት።

"ከእጄ ላይ ሳንቲም ወድቆ እሱን ላነሳ ነበር!የመኪና መንገዱ መሃል መድረሴንም አላስተዋልኩትም ነበር።" አለች አሁንም ግሩምን እያየች .......ያቺ ያነሳኋት የአንድ ብር ሳንቲም ትዝ አለችኝ የዛን ቀን የቦርሳዬ ትንሽዬ ኪስ ውስጥ እንደከተትኩት ነው።

"የምሰራበት የነበረበት ሱቅ ባለቤት ስራ ልቀይር ነው ብሎ ሱቁን ዘግቶት ነበር። ስራ እየፈለግኩ እጄ ላይ የቀረው አንድ ብር ብቻ ነበር።" እንደነገሩ ቀለል አድርጋ እያወራችው ግን የሚጋባ መከፋት ነበረው ድምፅዋ

"በአንድ ብር ምን አደርግበታለሁ? ልጆች ሆነን ማሳደጊያ እማሆይ ወይኗ የምንላቸው እናት ነበሩ መፅሃፍ ቅዱስ የሚያነቡልን ስለአንዲት ሴት ያነበቡልንን ሁሌ የማስታውሰው ነበር:: በሀገሩ የሚበላ ጠፍቶ ድርቅ በነበረበት ዘመን የቀራትን ትንሽዬ ዱቄት በውሃ ለውሳ ጋግራ ለነብዩ ስላበላች ሴት ..... ቃል በቃል አላስታውሰውም!ያላትን ለእግዚአብሔር አገልጋይ ሰጥታ እጇን አጣጥፋ ሞቷን ስለጠበቀች ሴት ........ ያለሽን የመጨረሻ እንጥፍጣፊ አልሰሰትሽምና ብሎ አምላክ ስለባረካት ሴት ....." ብላ ዝም አለች። የሁላችንንም ፊት ተራ በተራ ካየች በኃላ

"አላዋቂ ናት ብላችሁ ታስቡ ይሆናል። የማደርገውን ሳጣ ያስታወስኩት ይሄን ታሪክ ነበር። በዛ ለሊት ተነስቼ ቤተክርስቲያን የምሄደው ያቺን የቀረችኝን አንድ ብር ለቤተክርስቲያን ሰጥቼ ልጄንም እኔንም እንደፈለግክ አድርገን ልለው ነበር። ከዛ ውጪ ምን ማድረግ እንደነበረብኝ አላውቅም ነበር። የማውቀው፣ ቸገረኝ የምለው ዘመድም ጓደኛም የለኝም ነበር።" ብላ አሁንም ዝም አለች። ማንም ምንም ለማለት አቅሙም ቃሉም አልነበረውም። ጉንጭሽ ላይ ካልተደፋሁ ብሎ መጣሁ መጣሁ የሚል እንባዬን መታገል ጀመርኩ። "አይዞሽ፣ እኔን!" ልላት እፈልጋለሁኮ ግን ቃል ከአፌ ከመውጣቱ በፊት እንባዬ እንደሚቀድም ስለገባኝ የባሰ ሆድ ላስብሳት አልፈለግኩም። ከሆነ ደቂቃ በኋላ

"አይዞሽ! ከአሁን በኋላ ቤተሰብ አለሽ! " አላት ማት እሷ ወደ እኔ አየች። ያን እንዳረጋግጥላት ይሁን አልገባኝም። የምለው ግራ ገባኝ እና እጇን ያዝኳት

"ከፈለግሽ ባባን በኋላ ከትምህርት ቤት ሲወጣ ላመጣው እችላለሁ!" ስላት ሳግ እያነቃት

"እሺ!" አለችኝ። ባባን እንደምትወስድብኝ ሳስብ የሆነ አንጀት የሚቆርጥ ህመም አለው ግን የመተው ዓይነት ህመም አይደለም...... ይከፋኛል ብዬ ያሰብኩትን ያህል አይደለም:: ልክ የሆነ ስሜት ሳይሆነው ልክ የሆነ ነገር ....... የሆነ በህመም ውስጥ ፈውስ ያለበት ነገር......

ይቀጥላል.......

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Meri feleke
ደጋግመን በጣም ብዙ ጊዜ ተያይተናል።
'የሆነ ቦታ የማውቅህ መሠለኝ ፡ መልክህ አዲስ አይደለም' ብዬ ራሴው ወሬ ጀመርኩኝ።
ሙሉ መልኩን ሳላይ ፡ ማስክ አድርጓል ኮ
ይጠብቅ የነበረው አጋጣሚ ይመስል ፡
"አይገርምም? እኔም እያልኩኝ ነበር በውስጤ ፡ የት ነው የማውቃት? እያልኩ" አለኝ።
እዚህ አከባቢ ነህ?
አይ ፡ አይደለሁም።
እሺ እዚህ አከባቢ ነሽ? ምናልባት መንገድ ላይ ተያይተን ከሆነ?
ኧረ አይደለሁም።
(መንገድ ላይስ ብንተያይ አሁን ማን ይሙት እንዲህ አስታውሰው ያስታውሰኝ ይመስል ?
አልኩኝ በሆዴ።)
እዚህ ሀገር ነበርክ?
ኧረ በጭራሽ።
እዚህ ሀገር ሄደሽ ታውቂያለሽ?
አላውቅም ኧረ።
እዚህ አከባቢ ይሆን የማውቅሽ?
ወደዛም ሄጄ አላውቅም።
ok ፡ እከሌ የሚባል ወንድም አለህ?
ወንድም የለኝም ፡ እም ፡ ለቤተሰቤ ከሦስት ሴቶች በኋላ የተገኘሁ ብቸኛ ወንድ ልጅ ነኝ።
ምናልባት የሆነች የማውቃት እከሌ የምትባል ልጅ አለች፡ እሷን መስለሽኝ ይሆን ?
እኔ እንጃ ፡ እንደዛ የምትባል ሴት በእርግጥ አላውቅም። ምናልባት መልኬን እሷን መስሎህ
ይሆን?።
እንደዚህ የሚባል መስሪያቤት ትመጣ ነበር? ምናልባት እዛ ብዙ ሰው ስለሚመጣ እዛ
አይቼህ ከሆነ።
ኧረ እኔ የተሰማራሁት በዚህ ስራ መስክ ነው፡ ወደዛ አከባቢ መጥቼ እንኳን አላውቅም።
.
.
.
.
በመሀል ሰው መጣ እና ፡ እሱም ወደ ውጭ ወጣ ፡ ጥያቄዎቻችንን በእንጥልጥል ተውነው
፡ ምናምን።
ከነበርኩበት ለመሄድ ተነስቼ ወጣሁ ። ከርቀት ለየሁት ፡ የጊቢው በር አከባቢ ከሰዎች ጋር
ቆሞ ሲያወራ ተመለከትኩት። እሱም አይቶኝ እንደነበር የገባኝ፡ አይኖቻችን ሲገጣጠሙ
ፈገግ ብሎ ሲመለከተኝ ማስተዋሌ ነው። እያወራሁ የነበረውን ስልክ ዘግቼ ወደሱ አመራሁ
"ልትሄጂ ነው እንዴ?" ሲለኝ አዎን ፡ግን ነገ እመለሳለሁ አልኩት። ወደእኔ ቀረብ ብሎ
እንደሚተዋወቅ ሰው እቅፍ አድርጎኝ ፡ እከሌ እባላለሁ ሲለኝ ስሜን ብቻ ነግሬው ነገ
እመለሳለሁ ብዬው ተለየሁት። ትንሽ ተደነባብሬ ፣ ተንተባትቤ ስሜንም በአግባቡ
አልነገርኩትም መሠለኝ።
ቆይ ነገ ታምሜ ባልሄድስ?
እሱ አሞት ነገ ባይመጣስ?
ድንገተኛ ለቅሶ ያጋጥመው ይሆን?
በተለየ ነገር መንገድ ይዘጋ እና መምጣት አይችል ይሆን?
የምሄድበት ምክንያት ሌሊቱን አልቆ ብቀርስ?
ምናምን ምናምን እያልኩ ሀሳብ ገብቶኝ አደርኩኝ።
ሰው እንዴት ስልክ አይለዋወጥም? መች ነው ፋራ የሆንኩት?

መልካም ቀን ቤተሰብ

@wegoch
@wegoch
@paappii

#ጠርሲደ ከበደ
2024/09/23 08:27:11
Back to Top
HTML Embed Code: