Telegram Web Link
#ከግድግው_ባሻገር
በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተፃፈ
ክፍል ሶስት
“ስራሽን ማወቅ እችላለው?” ያልጠበቀችው ጥያቄ ስለነበር የግንባሯን ቆዳ ሸብሽባ አይኗን አፍጣ የንዴት ተመለከተችኝ፡፡
“ለምን ማወቅ ፈለክ?”
“አይ ያን ያህል አስፈልጎኝ አይደለም፡፡ ግን አንቺ እየተሰማሽ ያለውን ስሜት በጥልቀት ለመረዳት እና በምንነጋገርበት ሀሳብ ላይ የጋራ ነጥብ እንዲኖረን በማሰብ ነው፡፡ መናገር ካልፈለክሽ ግን አስገዳጅ አይደለም፡፡”
“ማሳጅ ቤት ነው ምሰራው፡፡ በማሳጅ ቤት ውስጥ በሴክስ ቢዝነስ እተዳደራለው፡፡” እምባዋ ግጥም አለ፡፡ እኔም ያልጠበኩት መልስ ነበር፡፡
“ማሳጅ ቤት ገብተህ ታውቃለህ?”
“እዚህ ሀገር አንድ ሁለቴ ቦስተን ገብቻለው፡፡ ነገር ግን ታይላንድ በነበርኩበት ወቅት በደንብ እገባ ነበር፡፡”
“ስለዚህ አንተ ዋነኛ ደንበኛ ነሀ የታይላንዱንማ ካወቅህ፡፡”
“አይ ታይላንድ እያለው በአብዛኛው የምጠቀመው የማሳጅ አይነት ታይ ካልቸራል ማሳጅ እና ፉት ማሳጅ ነው፡፡ በእርግጥ ሌሎች ከእኛ ወግ እና ስርዐት ያፈነገጡትን ባልጠቀማቸውም እንዳሉ ግን እውቀቱ አለኝ፡፡” ጭንቅላቷን ነቅነቅ አድርጋ በዝምታ ጠረጴዛው ላይ አይኖቿን ተከለች፡፡ በእጆቿ የማኪያቶውን ብርጭቆ ከማስቀመጫው ሳታነሳ ታሽከረክራለች፡፡ የፊትዋ ገፅታ ፍም እሳት ይመስላል፡፡
“ከማሳጅ ቤት ግድግዳ ባሻገር ሰው ይቸረቸራል፡፡ ትዳር ይፈርሳል፡፡ ሴት ክብር ታጣለች፤ ከእዛ ግድግዳ ባሻገር የሰው ብርሀን እየጨለመ ይመጣል…..” እንባዋን መሸከም ያቃቱት አይኖቿ ቁልቁል በጉንጯ ላይ መንታ እያደረገ እንባዋን ይወረውራል፡፡
“ዛሬ እንቅልፍ አልተኛውም፡፡ በጣም ስራ በዝቶብን ነበር፡፡ ማንነታቸውን ከማላውቃቸው 5 ወንዶች ጋር ወጥቻለው፡፡ ሁለቱ በእድሜ አርባዎች ውስጥ የሚገመቱ ናቸው፡፡ ቀለበት አድርገዋል፡፡ አንደኛው ሴክስ አድርጎ ሲጨርስ ገንዘብ ሊሰጠኝ የብር ዋሌቱን ሲያወጣው ሁለት የሚያማምሩ ልጆች ያሉበት ፎቶ ወደቀበት፡፡ ‘ልጆቼ ናቸው፡፡’ አለኝ በድፍረት፡፡ በእዛ ስረበሽ ቆየው በኋላ ላይ ከመጡት ወጣቶች መሀከል አንደኛው ከሌላ ጓደኛው ጋር እንደ መጣ አወቅሁ፡፡ አንደኛው ጓደኛው በሌላ ክፍል እየተሰራ ነበር፡፡ ይኼኛው ደግም ከእኔ ጋር፡፡ በጣም ትንሽ ልጅ እንደሆነ ገምቼ ነበር፡፡ መጨረሻ ላይ ብር ሲሰጠኝ ስንት አመቱ እንደሆነ ጠየኩት፡፡ 17 አመቱ ነበር፡፡ ጠጥቶ ስለነበር 2000 ብር እንደሚከፍለኝ እና ያለ ኮንዶም መውጣት እንደሚፈልግ ነግሮኝ ነበር፡፡”
“ምን አልሽው ታዲያ?”
“እሱ ቢያብድም እኔ አብሬ አላብድም፡፡ በደንብ እንደማስደስተው እና ያለ ኮንዶም ማድረግ እንደማልፈልግ ነግሬው ተስማምተን ነው ያደረግነው፡፡ እሱ ለሊት ከሰራኋቸው አምስተኛ ሰው ነበር፡፡ ከእሱ በኋላ ሌላ ሰው መስራት አልቻልኩም፡፡ በ17 አመቱ ራሱን አደጋ ውስጥ መጣሉን ሳስብ ስራው አቅለሸለሸኝ፡፡ በተዘጋ ግድግዳ የተሰባበረ ህይወት ነው ያለው፡፡ በስራው ጥሩ ገንዘብ አገኝበታለው፡፡ ሁሌም ህይወቴ ሙሉና ደስተኛ ሆኖ ግን አያውቅም፡፡ ወግ እና መዕረግ የእኔ ባዳ ናቸው፡፡” እንባዋ ዝም ብሎ መፍሰሱን ያየች የካፌው አስተናጋጅ ናብኪን አቀረበችላት፡፡
“አልቃሻ ሆንኩኝ እንዴ?” የውሸት ፈገግታ ለአስተናጋጇ አሳይታ አንድ ናብኪን አንስታ ፊቷን ጠራረገች፡፡
“ወንድሜ የኔ ጉድ ተነግሮ አያልቅም ቢቀርብህ ነው ሚሻለው፡፡” አይኖቼ አይኖቿ ላይ ናቸው፡፡ ድርቅ እንዳለ ሰው ትንፋሼም አይሰማም፡፡
“ደነገጥክ እንዴ? ወይስ ደበርኩክ? መልስ አልሰጥ አልክ..”
“ይቅርታ ዝም አልኩኝ? እንዴት ግን ወደዚህ ስራ ገባሽ?”
“ታሪኩ ብዙ ነው፡፡ ከአጎቴ ጋር ሳንጣላ የ12ኛ ክፍል ማትሪክ ሳይመጣልኝ በፊት ቲያትሪካል አርት መማር እፈልግ ነበር፡፡ ስለዚህ ግጥም እና ቲያትር እሰራ ነበር፡፡ ሀ…ሃ.ሃ…ሃ….ሃ…ነበር ብቻ፡፡ በኋላም ማትሪክ ስላልመጣልኝ ህልሜን ባላሳካም የውበት አጠባበቅ እና ማሳጅ ተማርኩኝ፡፡ አጎቴ የመሰለው ፀጉር ስራ ነበር፡፡ በጊዜው ከአጎቴ ጋር በጣም እንጣላ ነበር፡፡ እናም ልንመረቅ አካባቢ አንድ ጓደኛዬ ማሳጅ ስራ አትራፊ እና ብንሰራው የራሳችንን ህይወት የሚያስችለንን ነገር እንደምናገኝበት ነገረችኝ፡፡ ያኔ ይህን ስራ ሀ ብዬ ጀመርኩኝ፡፡ አስታውሳለው 22 ከሚገኝ አንድ ማሳጅ ቤት ነበር የጀመርኩት፡፡ አንድ ቀን ከሰዐት አካባቢ አንድ አረብ ሊሰራ መጥቶ እየሰራሁት ሴክስ እንድናረግ ጠየቀኝ፡፡ ደነገጥኩኝ፡፡ ማረግ እንደማልፈልግም አስረግጬ ነገርኩት፡፡ ወዲውም ከሻንጣ ውስጥ አንድ የታሸገ የ10,000 ብር እስር አወጣ፡፡…
የመጨረሻውን ክፍል ነገ ይጠብቁ፡፡
ይቀጥላል….
ስለሺ ሳልስ ዑመር
©SVC2017

@wegoch
@wegoch
@wegoch
Forwarded from Ribka Sisay
Forwarded from Ribka Sisay
#ከግድግው_ባሻገር
በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተፃፈ ክፍል አራት (የመጨረሻውን ክፍል) .........................................................
“የታሸገ የ10,000 ብር እስር አወጣ፡፡ በ10,000 የሚቆጠር ገንዘብ ቆጥሬ አላውቅም፡፡ ሴክስ ካረግን ይህንን ገንዘብ እንደሚሰጠኝና በሚሰራበት የሳውዲ ኤምባሲ ስራ እንደሚያስቀጥረኝ ነገረኝ፡፡ በዛን ቅፅፈት የአጎቴ ንትርክ ትዝ አለኝ፡፡ እንደማንኛውም ሴት ልጅ የተሻለ ህይወትን እፈልጋለው፡፡ ድህነቴ ግን ያንን ላይፍ እንድሆነው አልፈቀደልኝም፡፡ ትምህርት ደግም ስላልተሳካልኝ ከአጎቴም ሆነ ከአጎቴ ሚስት ጋር ትልቅ ቁርሾ ላይ ነን፡፡ እነኚህ ሁሉ ነገሮች ተደማምረው ለደቂቃዎች ክብሬን አጥቼ ህይወቴን የሚቀይረውን መንገድ ባመቻች የተሻለ ሆኖ ተሰማኝ፡፡ ወሰንኩኝ፡፡ አንዳንዴ መራራውን ፅዋ ጠጥተህ ህይወትን ማሸነፍ አለብህ፡፡ ያ ከሰዐት ሁለት የተደበላለቀ ስሜት የተሰማኝ ወቅት ነበር፡፡ ብዙ የሚመስል ብር እና ክብርን አጥቶ ከማያውቁት ሽማግሌ አረብ ጋር መተኛት፡፡”
“ቃል እንደገባው ታዲያ የኤምባሲውን ስራ አገኘልሽ?”
“የዛን ሰሞን በተደጋጋሚ ይመጣ ነበር፡፡ እንደ መጀመሪያው ቀን 10,000 ባይሆንም 1,000 ወይም 2,000 ብር ይሰጠኝ ነበር፡፡ እንደገናም በመኪና ከስራ ስወጣ ፒክ እያረገኝ አብረን ሺሻ ቤት እና መጠጥ ቤት እንዞር ነበር፡፡ በኋላ ግን ሳይነግረኝ ከሀገር ጠፋ፡፡ ብደውልም ስልኩ አይሰራም ነበር፡፡ ምንም ማረግ አልቻልኩም፡፡ ነገር ግን የሴክስ ቢዝነሱን አዋጪ የሆነ ስለመሰለኝ ተያያዝኩት፡፡ ከአጎቴም ጋር ተጣልቼ የራሴን ቤት ተከራይቼ መኖር ጀመርኩኝ፡፡ ይህ ደግሞ የማታም ሺፍት እየገባው እንድሰራ እድሉን አመቻቸልኝ፡፡”
እምባዋ በፊቷ ላይ ደርቆ ቁልቁል መስመር ሰርቷል፡፡ አይኖቿ ልክ እንደ ፀሐይ አድማሷን በምሽት ስትዘረጋ በሰማይ ላይ እንደምትለቀው ቀይ ቀለም ቀልተዋል፤ ከንፈሯ ዝናብ እንደናፈቁ የሰሀራ በረሀ ስንጥቅጥቅ መሬቶች ደርቀው ተሰነጣጥቀዋል፡፡
“ታዲያ በእዚህ ስራ የመቀጠል ሀሳብ አለሽ?”
“አሁንስ አንገሽግሾኛል፡፡ አንድም ቀን የሰላም እንቅልፍ ተኝቼ አላውቅም፡፡ ሁሌ ነጭናጫና በቀላሉ ተናዳጅ ሆኛለው፡፡ ለነገሮች ግደ የለሽ ቁብ የማይሰጠው ሆኛለው፡፡ በስራው ምክኒያት ሰውነቴም በጣም ተጎድቷል፡፡ ሁሌ ይደክመኛል፡፡ የምግብ ፍላጎቴም በጣም ወርዷል፡፡”
“እንደነገርሺኝ ያኔ ህልምሽ ቲያትሪካል አርት መማር ነበር፡፡ እንዴት ነው አሁንስ እሱ ነገር አለ ውስጥሽ?”
“ህልሜ አይደል እንዴ? መቼ ይጠፋና፤ ሁሌም አስባለው፡፡ አንድ ቀን ከዚህ ሰውበላ ከሆነ ስራ ተላቅቄ ትምህርቴን እንደምጀምር ተስፋ አለኝ፡፡ ሲከፋኝም ሆነ ውስጤ ሲሰማኝ ግጥም እፅፋለው፡፡”
“ቅርብ ጊዜ የፃፍሽው ግጥም ወይም ሌላ ፅሑፍ አለ?”
“አንድ ቀን ስራ ቦታ ግጥም ፅፌያለው ላንብብላቹ ብዬ ስለምኞቴ እና ስለወደፊት ቤቴ እና ኑሮዬ ግጥም አነበብኩላቸው፡፡ ከዛም ‘ምትበላው የላትም ምትከናነበው አማራት!’ ብለው ተረቱብኝ፡፡ ከዛን ቀን በኋላ አንድም ቀን ለሰው የምፅፋቸውን ነገሮች አንብቤያቸው አላውቅም፡፡”
“ግድ የለም እኔ ተረት አላውቅም ለኔ ልታነቢልኝ ትችያለሽ እንደነሱ አልተርትብሽም፡፡” ከግዚያት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ እውነተኛ ፈገግታ ፈገግ አለች፡፡ ፊቷም ከቅድሞ የተሻለ ገፅታ ነበረው፡፡
“ግጥም ትወዳለህ?” ቦርሳዋን በቀኝ እጇ እየከፈተች ጠየቀችኝ፡፡
“በጣም ነው ምወደው፡፡ ግን ገጣሚ አይደለሁም፡፡” ብጣሽ ወረቀት ከቦርሳዋ አውጥታ መፈታታት ጀመረች፡፡
“ትናንት በጣም በተከፋው ሰዐት የፃፍኩት ግጥም ነው ላንብብልህ?”
“እባክሽ! ግን ፍቃደኛ ከሆንሽ ልቀዳው እፈልጋለው፡፡”
“ምን በራዲዮ ልታስተላልፈው ነው እንዴ? መብትህ ነው፡፡” ፊቷ በፈገግታ ሲታጀብ፣ የተቋጠረ ግንባሯ ሲፍታታ፣ ጥርሶቿ እንደደረሰ የጥጥ ፍሬ ሲገሸለጥ፣ ጉንጮቿ በሳቅ ተወጥሮ እንደ በለስ ፍሬ ሲፈረጥም ውበቷ ከከሳው ህይወቷ አፈትልኮ ይወጣል፡፡
“ምን ይታወቃል የወደፊቷ እውቅ ገጣሚት አንቺ ብትሆኚስ? በይ ቀጥይ ጓጉቻለው እስካዳምጠው፡፡” የሞባይሌን መቅጃ አስተካክዬ ወደ እሷ ሸርተት አድርጌ አስቀመጥኩት፡፡
“እሺ ተስፋ ይሰኛል ርዕሱ…
የሚመጣው ሁሉ የሚገኘው ከፊት
ጨለማ ከሆነ ከለበሰ ፅልመት
አሁን ያየሁትን ነገር ባላየሁት ነበር
ባዘን ፋንታ ደስታ
ውጥረት ቀሎ ፋታ
ችግር አልፎ ምቾት
ውድቀት ቀርቶ ዕድገት
ይተካል ባይባል መሻል ነበረበት
ህይወት ትርጉም አልባ ተስፋ ባይኖር ኖሮ
ሰው የሚለው ፍጡር የደስ ደስ እንዲለው
ቆይታው እንዲያምር ጥረቱ ልፋቱ ልቆ እንዲሰምር
ተስማምቶና አብሮ በፍቅር እንዲኖር
መታገስ ያሻዋል በተስፋ መነፅር
የነገን እያየ የዛሬን እንዲኖር
ተስፋ ሀይል ነገር ህይወትን ቀማሚ
ሰውና ኑሮውን አንድ አርጎ አስማሚ
የዘንድሮውን አልፎ እንዲያስብ ለከርሞ
ተስፋ በጥበብህ ብልሀት ለግሰው
ቻል አርጎ እንዲኖር ‘ሰውን ልጅ አበርታው::
ይሔን ይመስላል እንግዲህ” ድስ ብሏታል፡፡ ያስታውቅባታል፡፡ ደስተኛ ነች፡፡
“በጣም ግሩም ግጥም! በጣም ሊጨበጨብልሽ ይገባል፡፡”
“ኸረ ባክህ? እንዲህማ አታካብደውም፡፡ ስምህ ማነው ግን? ሳንተዋወቅ ብዙ አወራን እኮ፤ አትፍረድብኝ ስራ ቦታ ስም ሳንጠይቅ ነው ወደ ስራ ምንገባው፡፡ በዛ ለምዶብኝ ነው፡፡” ከት ብለን ተሳሳቅን፡፡
“ስለሺ እባላለው፡፡ ሳልስ ብለሽ መጥራት ትችያለሽ፡፡”
“ኦኬ ሳልስ! ለየት ያለ ስም ነው፡፡ እኔ ፍሬዘር (ለባለ ታሪኳ ደህንነት የተለወጠ ስም) እባላለው፡፡”
“ስልክሽን ማግኘት እችላለው? ምን አልባት አንዳንድ ጊዜ ተገናኝተን ሻይ እንጠጣለን፡፡”
“ያንተን ስጠኝ እኔ ብዙ ስራ ላይ ስለምሆን ሲመቸኝ እኔ እደውላለው፡፡”
ስልኬን ወሰደች፡፡ ፍሬዘር አልፎ አልፎ በተለያዩ ቁጥሮች ትደውልልኛለች፡፡ ከዛን ቀን በኋላ ግን በአካል ተገናኝተን አናውቅም፡፡ በደወለችበት ስልኮች መልሼ ብደውልም አንዳቸውም አይሰሩም፡፡ አንዳንዴ በሞባይሌ የቀዳሁትን ግጥም ደግሜ ደጋግሜ አዳምጠዋለው፡፡ የፍሬዘር ህልም ትልቅ ነው፡፡ በተስፋ ሁሌም ህልሟ ጋር ለመድረስ ዛሬን ትኖራለች፡፡ ብዙ የፍሬዘር አይነት ህይወት የሚኖሩ ሴት እህቶቻችን በሀገራችን አሉ፡፡ ሁላችንም ከግድግዳው ባሻገር ያለውን ከባድ ህይወት ልንረዳና ልንረዳቸው ይገባል፡፡ ለፍሬዘር መልካሙን ሁሉ እመኝላታለው፡፡
እናንተም ይህንን ከግድግዳው ባሻገር የተሰኘውን ባለ አራት ክፍል ታሪክ ስላነበባቹ ከልብ አመሰግናለው፡፡ ህይወት ትቀጥላለች፡፡ እኔ ከፍሬዘር ብዙ ተምሬያለው፡፡ እናንተም ስሜቴን እንደምትጋሩ ተስፋ አደርጋለው፡፡
ስለሺ ሳልስ ዑመር ©SVC2017 @wegoch @wegoch
የማስተጋባት ክፉ ደዌ
.
ደብረ ሊባኖሳዊው ባለ ቅኔ ካህሊል ጅብራን እንዲህ ይላል:-"አንዱ ሰው በውስጡ ሁለት ሰዎችን ነው፤አንዱ በብርሃን ሲተኛ ሌላው በጨለማ ይነቃል" ይላል ይህቺን ይዘን ሌላ ከፈለጋችን እንጭለፍ። ሳንሞቀው የጠለቀው ፀሀያች አያ ሙሌ ሙሉ -ጌታ ተስፋዬ(አያዬ) ደግሞ " ለካ ሰው ጥንድ ነው የአንድ ራስ መንትያ
አንድ ነው ሲካፈል" ይለናል እያወዳደርኩ አይደለም። ግን ቢያንስ ያለንን እንወቅ። ማንም ማንንም አልቀደመም አልበለጠምም ራሱን እስካልቀደመ በቀር።ነገ ስም ያለው ተነስቶ ስለ አያ ሙሌ ቢያወራ አሽቃብጠን እና አለ ልክ አውርተን ዝም ነን። አድናቂ ከማድነቁ በፊት የሚያደንቀውን ሰው እና ግብሩን ቢያንስ በአረዳዳችን መጠን እንኳን እንወቀው ግድ የለም ጥበብ መንጋነት አትደግፍም። የሚገርመው ግን የሀገራችን የስነ ፅሁፍ አለም በመንጋ የሀሳብ ዳራ ተተብትቧል።አንድ ጫፍ ይዞ ስለ አንድ ሰው ብቻ መለፈፍ ታሪክ ገደላ ነው።
ምን አይነት የዘመኑ ዘዴ አለ መሰላችሁ የባዕድ ቋንቋ በንግግር መሃል መደብለቅ የአዋቂነት ልክ እንደሆነው ሁሉ በስነ ፅሁፍ ችሎታቸው ገዘፍ ያሉትን ስም እየጠቀሱ ገሳ መጠለል ደግሞ አዋቂነት ሆኗል።እኔ ግን አይመስለኝም። ቀድሞ ነገር የገባን ራሱ አልገባንም።የጥበብ ሰው ደግሞ ጣዎስ ወይም ኮፒ ማሽን አይደለም ከሌላው የሰማውን ለማሰማት በስማ በለው አይጋልብም።ኢትዮጵያዬ ሆይ ጥበበኞችን ስንጠራ ብቅ የሚሉትን አንድ በይልኝ እኛ ጥበበኞችን እንጂ የቡና ወረኞችን አልጠራንም።ለማንኛውም ይህን ያልኩት በማያቸው መደጋገሞች ነው። ስጋ ቤት ሲከፈት መደዳውን ስጋ ቤት መክፈት ንግድ ነው። ስጋ ቤት ሲከፈት ከጎኑ እንጀራ ቤት ፣ ቢላ መሞረጃ ቤት እና የመሳሰሉትን መክፈት ደግሞ ጥበብ ነው።
በረሃ ላይ ውሃ ፍለጋ አንዲት ቦታ ላይ ቆፍረህ ውሃ ስታገኝ ኩባያ ይዞ ከሚመጣው ሰው ይልቅ የተገኘውን ምንጭ ደግሞ ለመቆፈር የሚመጣው ይበዛል። የገጠመን ይህ ነው። ወይ ለመጠጣት ኩባያ ይዘህ ና ወይም ፈቅ ብለህ ቆፍር። ብዙዎቻችን ሰው ከሚተቸን ተኩሶ ቢገድለን እንመርጣለን እና በማወቅም ባለማወቅም የተቀየመ ካለ ይቅር ይበለኝ። እኔም ይቅርታን ጠይቄያለሁ። ቸር ሰንብቱማ
ያለንን እንወቅ!!
አድናቂነት በግርድፉ ሳይሆን ሰርፆ ይግባን!!
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
©ሲራክ
@wegoch
@wegoch
ሙትና ሐውልት
#አለማየሁ ገላጋይ

ፕሮፌሰር ጤና'ዳም ጥያቄ ምልክቱን መስለዋል(እሱ በድን ሲሆን እሳቸው ግን ፕሮፌሰር ናቸው) ከቢሮአቸው ከወዲያ ወዲህ ይላሉ፡፡ ሚዛናቸውን ለመጠበቅ እንዲረዳቸው እጃቸውን ወደ ኃላቸው ልከው አጣመሩ፡፡

ፕሮፌሰር የረበሻቸው በህይወታቸው ገጥሟቸው የማያውቅ ሁኔታ ስላፋጠጣቸው ነበር፡፡ ሁለት ሰዎች (አንድ ወጣትና አዛውንት አያቱ) በመኪና አደጋ ተጎድተው ከሞላ ጎደል የአንድ ሰው አካል ብቻ ቀርቷቸው መጡ፡፡ ለሁለቱ፡፡ ከሁለቱ ሰዎች የተገኘው አካል በዝርዝር (ማስታወሻቸውን ገለጡ) አዎ - ሁለት አይን (አንድ አንድ ማለት ነው) አሁንም ሁለት እግር፣ አንድ ልብና አንድ ሙሉ አንጎል (ልቡ የወጣቱ ሲሆን አንጎሉ የአዛውንቱ ነው፡፡) በዚህ ላይ የወጣቱ ቀሪ የላይኛው ማቀፊያ አካል ሊገጣጠም በማይችልበት ሁኔታ ተፈረካክሷል፡፡

ፕሮፌሰር ያስጨነቃቸው የቁስለኞቹ አካል ጉዳይ ሳይሆን የሀሳባቸው አለመገጣጠም ነበር፡፡ ወጣቱና አዛውንቱ የተለያየ የማይጣጣም አመለካከት አላቸው፡፡ ሁለቱም በቅዠት ላይ ሆነው ወጣቱ "ቴክኖሎጂ" ሲል "ባፍንጫክ ይትከላ'ባክ" ይላሉ፡፡ ይኸውም አደጋው ከመድረሱ በፊት ሲነጋገሩበት የነበረ ርዕሰ-ጉዳይ እንደሆነ ፕሮፌሰር ገምተዋል፡፡

"አካል የአንድ ሰው፤ ሐሳብ የሁለት ሰው እንዴት ይሆናል?" ፕሮፌሰር አሁንም ራሳቸውን ጠየቁ፡፡ በተደጋጋሚ የሁለት ሰዎች አካል በአደጋ ምክንያት የአንድ ሰው እየሆነ ይመጣል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ አብረው የሚውሉት በእድሜና በሀሳብ የተቀራረቡ ሰዎች በመሆናቸው አንድ አድርጎ በመተሳሰብ እንዲኖሩ ለሚደረገው ሳንካ አልተፈጠረባቸውም ነበር ፤ ከዛሬው ክስተት ሌላ፡፡ ወጣቱ ለዘመናዊ ትምህርት እውጭ ቆይቶ የመጣ ሲሆን አያቱ ግን ከእምነት ሌላ የማያውቁ ምስኪን በብህትውና የሚኖሩ አዛውንት ነበሩ፡፡

"ሁለቱንም ከማጣት አንድ ሆነው እንዲኖሩ ማድረግ ተገቢ ይመስለኛል" አሉ ፕሮፌሰር በሀሳባቸው ወሰኑም፡፡

ፕሮፌሰር ጫት ሳይቃም፣ ዕጣን ሳይጨስ፣ ሀድራው ሳይወርድ፤ እንደው በሌጣው በሚጠነቁሉበት ምናምን ነገር ላይ አንድ ዓይናቸውን አጨንቁረው፣ አቀርቅረው በመመልከት ትንሽ ከቆዩ በኃላ በሽተኞቹ ወደተኙበት ክፍል " ደፋ - ደፋ - ደፋ" እያሉ አመሩ፡፡ አመራር የሚጠብቁትም ሐኪሞች በአክብሮት ተቀበሉዋቸው፡፡

"እህሳ? ለውጥ አለ?"
ዶክተር ችግኝ ቀልጠፍ ብሎ "እርሶ የወሰኑበት ከሆነ......" አለ
"እኔ ወስኛለሁ"
" ጥሩ ሲበዛ እድለኞች ነን ለማለት እደፍራለሁ፤ ምክንያቱም የሁለቱም ጉዳተኞች አካል ከግማሽ በላይ ቢጎዳም የሁለቱም ምላስበጥሩ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ሐሳባቸውን ልንጠይቃቸው እንችላለን ብዬ አምናለሁ፡፡

"ምላስ ብቻ ምን ሊረባ?" አሉና ፕሮፌሰር ወደ ፊታቸው ዘንበል ስላሉ ለሚዛን መጠበቂያ እጃቸውን ወደኃላ አጣምረው "የወጣቱ አንጎልና የአዛውንቱ ልብ የለም -- አይደለም?"

" አዎ ግን ከእርሶ እኔ ባላውቅም ምላሶቻቸውን፣ የወጣቱን ከልቡ ጋር ፤ የአዛውንቱን ካንጎላቸው ጋር በጊዜያዊ መልክ አያይዘን አንድ የመሆናቸውን ሀሳብ ብንጠይቃቸው ተገቢ ይመስለኛል" አለ ዶክተር ችግኝ፡፡

" ጥሩ ሐሳብ ነው፣ አንዳንድ እጅ አላቸው አይደለም?"

" አዎ"
"እንግዲያው ከውሳኔያቸው ስር አስፈርመህ አምጣልኝ" አሉና "ደፋ ደፋ" እያሉ ወደ ቢሮአቸው ተመለሱ፡፡

★ ★ ★

ሁሉም ነገር ተሳካ - የመዋጮ ኑሮውም፡፡ ፕሮፌሰር በስራቸው ዘጠነኛ ኩራት ተሰማቸው፡፡ ምክያቱም ስምንቱን ኩራት አንድ ባንድ ከዚህ በፊት በሌሎች ላይ ኮርተዋልና፡፡ ትንሽም ቅር የሚያሰኘው የአሁኑ ድበላ በአካልም ሆነ በአስተሳሰብ እኩል አለመሆኑ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ ጉዳተኞቹን ሊያስማማቸው ያልቻለ የነበረው የምላስ ጉዳይ ነበር፤ ምክንያቱም የሁለቱም ምላስ ደህና ሲሆን <የኔ ይሁን፣ የኔ > የሚለው ክርክር ፕሮፌሰር ቢያስጨንቃቸውም በመጨረሻ ዘዴ ዘይደውለት በአንድ ጭንቅላት ሁለት ምላስ ተዋህዶ እንዲቀመጥ አድረገዋል፡፡ የመጨረሻ ሥራ የሚተዳደሩበትን ደንብ ማርቀቅና የሁለት አንድ የሆነ ስም እንዲኖራቸው ማድረግ ነበር፡፡ ይህም በዶክተር ችግኝ ተጠናቆ ቀረበ፡፡ "ሁሉም የጋራ ነው" ይላል ረቂቁ አፉን ሲከፍት "እግሮች የጋራ ናቸው፣ እጆች የጋራ ናቸው፣ ዓይኖች የጋራ ናቸው፣ ልብና አንጎልም የጋራ ናቸው፣ እንዲሁም ችግሮች የጋራ ናቸው.......... ደስታዎችም"

ስማቸውም <ሙትና ሐውልት> ተባለ

ሙትና ሐውልት ከተዋሄዱበት ከመውጣታቸው በፊት የመሄድ ጥምረት እንዲኖራቸው እንዲሁም የመብላት ልምምድን ተያያዙት፡፡ የሙት እግር <ነጠር> ሲል...... በመናዊነት፣ የሐውልት እግር ደግሞ <ኮሰስ> ይላል፡፡

<ነጠር - ጠር - ጠር፣ ኮሰስ - ስስ - ስስ፣ ነጠር - ጠር፣ ኮሰስ - ስስ፣ ነጠር -- ኮሰስ፣ ነጠኮስ፣ ነጠ - ኮስ፣ ነጠኮስ፣ ነጠኮስ> እያሉ ልምምዳቸውን በ <ነጠኮስ> ቅንጅት ጨረሱ፡፡ ከመዋሃጃው በደማቅ አሸኛኘት ወጡ፡፡

"ሙትዬ" አለ ሐውልት

"ሀውልትዬ" አለ ሙት

"ምነው አላምን አልኩ? ፍርሃት፣ ፍርሃት ይለኛል"

"ልብህ ስለሌለ ነዋ፣ ይልቅዬ እኔ ደስ ደስ ይለኛል፤ እመን እመን ይለኛል"

"አንጎልህ ስለሌለ ነዋ፣ አንጎል ፍርሃት ነው"

"አንጎል አለመኖሩ እንዴትጥሩ ነው ጃል"

"ልብ አለመኖሩስ፣ ዓለም ነው"

" በፊት አንስማማም ነበር - - - ሐውልትዬ"

"አሁን ተሰማማን - - ሙትዬ" አለና <ነጠኮስ> እያሉ መንገዳቸውን ተያያዙት፡፡

"ሁለት ልብ፣ ሁለት አንጎል እንዴት መጥፎ ነገር ነው ባክህ ......... ያጣላል"

"አንድ ልብ፣ አንድ አንጎል እንዴት ጥሩ ነው ............. ያፋቅራል"

"ሐውልትዬ"

"ሙትዬ"

"እኔ ምንህ ነኝ?"

"ሕይወቴ............ እኔስ ምንህ ነኝ?"

"ነፍሴ"


ልብና አንጎል፣ ነፍስና ሕይወት፣ አንድና አንድ ............... ሁለትና ሁለት ............... አራትና አራት ................... ብዙና ብ ዙ = #ሕዝብ!!!

@wegoch
@wegoch
@paappii
#ወግ_ብቻ
.
አንድ ወጣት መጥቶ << ጋሽ ስብሐት >> ይለዋል።
.
<<እ- ደህና ነህ?>> ይላል ስብሐት
.
<<ደህና ነኝ - ግን አውቀከኛል?>> ይጠይቃል ወጣቱ።
.
<<አውቄሃለሁ>>
.
<<በእውነት አውቀውኛል?>>
.
<<አውቄሃለሁ >>
.
<<አልመሰለኝም አውቀውኛል?>>
.
<<አውቄሃለሁ አልኩኮ>>
.
<<ያወቁኝ አልመሰለኝም ፤ አውቀውኛል ?>>
.
<<አዎ! >>
.
<<እሺ ማነኝ? >>
.
<<ችኮ መንቻኮ >>

@wegoch
@wegoch
#ወግ_ብቻ
.
ትንሽ ብታስብበት መብላት እጅግ የሚያሳፍር ተግባር ነው። ቄራ ውረድና አንድ ሰዓት ያህል አስተውል።
በሬውን አምገቱን ገዝግዘው ሲያርዱት ፣ ቆዳውን ሲገፉት ፣ ብልቱን ሲለያዩት ፈርሱን ሲጎለጉሉት ተመልከት።
ሆቴል ግባና አይንህን ጨፍነህ ህዝቡ ሲያኝክ ፣ አጥንት ሲቆረጣጥም ስማ። አክ! ምን አይነት መጨማለቅ! ይሄ ሁሉ ያቺን የግማት ስልቻ ለመሙላት! ቀበቶህን ባጣበቅክ ቁጥር ፈርስ እንደምትጨፈልቅ አስበህበታል? ልክ የጎለጎሉትን የበሬውን ፈርሰ የሚመስል።
ለመሆኑ በሬን ሲያርዱት በስመ አብ ብሎ ማረድ የጀመረው ቀልደኛ ቄስ መሆን አለበት እላለሁ። ቀልድ ካልሆነ እንዴት የአብን ፍጡር በአብ ስም ትገድለዋለህ??
.
ሌቱም አይነጋልኝ ገፅ 6 ደራሲ ስብሐት ገ/እግዚአብሔር
@wegoch
@wegoch
#ወግ_ብቻ
.
ሽማግሌው የከተማ አውቶብስ መጠበቂያ ስፍራ ቆመው አውቶብስ እየጠበቁ ነው። አከባቢው እንደሳቸው ሁሉ አውቶብስ የሚጠብቀውና በወጪ ወራጅ መንገደኛው ተጨናንቋል።
በይኽ መሃል በኪሳቸው ያለው ተንቀሳቃሽ ስልካቸው (ሞባይላቸው) መጮህ ጀመረ። ጥሪ ነበር። ሽማግሌው የስልካቸውን ጥሪ ቢሰሙትም በይኽ ግር ግር መኻል ስልክ ቢያነጋግሩ የቀማኞች ሲሳይ መሆናቸው ስለገባቸው ዝም አሉ።
የ "ሞባይሉ"ን ድምፅ የሰማው አንድ ጩሉሌ ሌባ ከኃላቸው አድፍጦ ሽማግሌው ስልካቸውን ከወሸቁበት ሲያወጡ መንትፎ ለመሮጥ ቋምጧል።
ሽማግሌው ግን የዋዛ አልነበሩም። ስልኩ ይጮኻል እሳቸው ግን እንኳንስ አውጥተው ሃሎ ሊሉ ድንግጥም አላሉ።
ይሄኔ ሌባው ወደ ሽማግሌው ብሎ " አባቴ ስልክዎ እየጮኸ ነው እኮ ያንሱት እንጂ"አላቸው። ውስጠ ዘ ው (ምስጢሩ) የገባቸው ጠንቃቃው ሽማግሌ ተወው ልጄ እኔ ኃላ ከምጮህ እሱ አሁን ይጩኽ "አሉት።
@wegoch
@wegoch
#Elssa_Mulugeta

አሁን ዛሬ ላይ ሆኜ በመደነቅ ልል የምችለው ነገር " ትናንት እንዴት ውብ ነበረ"
ን ነው ። በቀዝቃዛ ማታ እንደማገኝህ ሳስብ ጮቤ የምትረግጥ ነፍሴን ልክ
አጠገቤ ስትደርስ ምን ሆና ዝምታ እንደሚሸብባት ግራ ይገባኝ ነበር ።
ትናንት አጋጭተን ሳንጎነጭ ስለተውነው ፅዋ ይቅርታ ልጠይቅህ እፈልጋለሁ ።
ናፍቀኸኝ እንደነበር ስላልነገረህ አፌ ይቅርታ
በጣም ስለወደደችህ ልቤ ይቅርታ
እጆችህ እንዲዳብሱት መፈለጉን ስላላሳወቀህ ገላዬ ይቅርታ
ቻው ስትለኝ ያቀረረ እንባዬን ጨክነው ስላላፈሰሱ አይኖቼ ይቅርታ
ስታቅፈኝ ቀጥ ስለሚል ትንፋሼ ይቅርታ
የተሰበረ ጊዜያችን ውስጥ ያልፈሰሰ ትውስታ ለታቀፍኩኝ ለእኔ ስትል እኔን ይቅር
በለኝ ።

@wegoch
@wegoch
@paappii
ወጣትነት - ሞራል
________________

ከጥቂት ወራት በፊት የቁጠባ ባህል እንዲሰርፅብኝ በማሰብ አባቴ የሀገሪቷን እና የከተማይቱን እውነታ ተገንዘቢ በሚል ከቤት ይዞኝ ይወጣል። በዚህም ምክንያት ደላላዎች ጋር፣ የተለያዩ real state-ኦች እና ሰፈሮች እንዲሁም መኪና መሸጫዎች እንሄዳለን። ስለኑሮ ውድነት ባውቅም፣ የእውነት በቁጥሮች አስቤ ‘እኔ የት ጋር ነኝ?’፣ ‘አሁን ባለኝ አቅምና፣ ህይወቴ ሊይዘው በሚችለው አቅጣጫስ የወደፊት እውነታዬ ምን ሊመስል ይችላል?’ ብዬ አስቤ አላውቅም። ለቤት፣ ለመሬት፣ ለመኪና ብዙ ሚሊየን ብር እንደቀልድ ሲጠራ እውነት ያስደነግጣል። ግን ከእኔ መደንገጥ ባለፈ፣’ አብዛኛው ማህበረሰብ እነዚህን ነገሮች የመግዛት አቅሙ ምን ይመስላል?’ የሚለውን አለማሰብ አልቻልኩም። የተሻለ ሙያ ተብላ በህክምና ተመርቃ በወር ሰባት ሺህ እና ስምንት ሺህ ለምታገኘው እህቴ እና ጓደኞቿ፣ ከዛ ደሞ በጣም ያነሰ ለሚከፈላቸው ብዙሀን (አማካይ) የከተማው ሰዎች ቤት፣ መኪና እሩቅ ህልሞች ናቸው ወይ? ቤተሰቦቼ
የ200 እና 300 ብር ተቀጣሪ አስተማሪዎች ሆነው ፣ ቤት እና መኪና የሚጨበጡ ህልሞች የነበሩባቸው ጊዜ ከሁለት አስርት አመታት አያልፍም። ዛሬ ግን 120 ካሬ ሜትር ቤት አራትና አምስት ሚሊየን ብር ጥሪ ሲደረግበት፣ ይህንን ቤት afford ለማድረግ የአምስት ሺህ ብር ተቀጣሪ ሳይበላ ሳይጠጣ ገንዘቡን ለ80 አመት መቆጠብ እንዳለበት፣ ከአማካዩ ገቢ በጣም ከፍ ብለን እንኳን 50,000 ብር የሚከፈለውን ሰው ብናስብ ሙሉ ደሞዙን ቢቆጥብ 8 አመት እንደሚፈጅበት አስባለሁ። ያው በ8 አመት የቤቱ ዋጋ ምን ያክል ይጨምራል የሚለውን ግምት ውስጥ ሳናስገባ። ታዲያ እነዚህ መሰረታዊ ነገሮች ለብዙሀኑ ሩቅና የማይጨበጡ ህልሞች ከሆኑ፣ ለአብዛኛው ሰው የሚጨበጠው ህልም ምንድነው? አብዛኛው ሰው ነገውን በምን ሁኔታ ነው የሚያስበው? የማይጨበጡ ህልሞች ባሉበትስ የስራ፣ የእድገት፣ የመለወጥ ሞራላችን ምን ይመስላል? የሀገራችን ግለሰባዊ የኢኮኖሚ የእድገት መሰላል ግልፅ ባልሆነበት ሁኔታ፣ በተለይ ለተማረው ሰው ህልሙ ሀገርን ለቆ መውጣት ቢሆን አያስገርምም አይደል? ታዲያ እንዴት የሚጨበጡ ህልሞች፣ በግልፅ የሚታዩ እና የሚተገበሩ ግለሰባዊ የእድገት ደረጃዎች እንዲኖሩ ማድረግ ይቻላል? ምናልባትም እንደሀገር ያለን ትልቅ ሀብት የሰው ሀይል ነው፣ ግን የስራ፣ የመለወጥ፣ የእድገት ሞራል የሌለው ወጣት እንደ ሀብት ይቆጠራል፣ እንደ ሀብት ይሰራል?

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Hewan Hulet Shi
Forwarded from ቅንድል ኢትዮጵያ (Ermiyas Dejene)
ቅንድል-መፅሔት ቅፅ-፪ ቁጥር-፬.pdf
5.9 MB
#ቅንድል_ዲጂታል_መፅሔት

★ቅፅ-፪ ቁጥር-፬

በአውደ ብሩኀን ገፆች ከዶ/ር ኤሊያስ ገብሩጋ አስተማሪ ቆይታ

አጃኢብ ያስባሉ ባህሎች

ኢትዮጲያዊ ቅኖች የተመሰገኑበት፡፡

አሸላሚ የበዓል ውድድር የተካተተበት

አስደናቂ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ውጤት የተዳሰሰበት

ሌሎችም በርካታ መረጃዎች

ያንብቡትና ብዙ ያትርፉበት


የበፊት ዕትሞችን ለማግኘት ይሄን ይጫኑ

@KendelM
#ሃሳብዎን በነፃነት ይስጡ!


ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ከዚህ በታች የቀረቡት ቃለመጠይቆችን ከመስከረም 2012 ዓ.ም አንስቶ እስካሁን ባሉት ጊዜያት የተፈፀሙ ወይም የተከናወኑ ጉልህ አገራዊ ሁነቶች የሚመለከቱ ናቸው። ዓላማውም የቻናላችን አንባብያን የዓመቱ ምርጥ፣ ተወዳጅ፣አሳዛኝና አስደንጋጭ ክስተቶች በተመለከተ ሀሳባቹን ወይም አስተያየታቹን መሰብሰብ ነው።ምላሽ በመስጠት የተለመደውን ተሳትፏቹን እንጠብቃለን። እናመሰግናለን!🙏🙏


1 የዓመቱ ተፅዕኖ ፈጣሪ የክልል ፕሬዝዳንት
2 የዓመቱ ስኬታማ የመንግስት ተቋም
3 የዓመቱ አሳፋሪ የመንግስት ተቋም
4 የዓመቱ ተስፋ የሚጣልበት የዲሞክራሲ ተቋም
5 የዓመቱ አስደማሚ የመንግስት ስኬት
6 የዓመቱ ስኬታማ አገራዊ ንቅናቄ
7 የዓመቱ አስደንጋጭ ስኬት
8 የዓመቱ ተፅእኖ ፈጣሪ አክቲቪስት
9 የዓመቱ ምርጥ የፓለቲካ (የመንግስት ) መሪ
10 የዓመቱ ተወዳጅ የቴሌቪዥን ጣቢያ
11 የዓመቱ ተወዳጅ የሬድዮ ጣቢያ
12 የዓመቱ ምርጥ ኢ-ልቦለድ መጽሐፍ
13 የዓመቱ ተወዳጅ የኪነ ጥበብ ምሽት
14 የዓመቱ የሰላም የፍቅር አርዓያ
15 የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ድራማ
16 የዓመቱ ነጠላ ሙዚቃ
17 የዓመቱ ምርጥ የሙዚቃ አልበም
18 የዓመቱ ምርጥ ጋዜጠኛ
19 የዓመቱ አሳፋሪ የፓለቲካ ውዝግብ
20 የዓመቱ ምርጥ የበጎ አድራጎት ድጋፍ
21 ምርጥ ታሪካዊ ልብወለድ
22 ምርጥ የወግ መጽሐፍ
23 ምርጥ የፍልስፍና መጽሐፍ ―
24 ምርጥ የስነልቦና መጽሐፍ ―
25 ምርጥ የልብወለድ መጽሐፍ ―
26 ምርጥ የፖለቲካ መጽሐፍ―
27 ምርጥ የታሪክ መጽሐፍ ―
28 ምርጥ የሕይወት ታሪክ―
29 ምርጥ የግጥም መጽሐፍ ―
30 ምርጥ የትርጉም መጽሐፍ ―
31 ምርጥ የምርምር መጽሐፍ ―

# ማስታወሻ :- ስትልኩልን ስማቹን ፣ የምትኖሩበት ቦታ አብራቹ መላካቹን እንዳትረሱ 🙏🙏🙏

👇👇👇👇

@balmbaras
@Nagayta
ስም :- ባሮክ

አድራሻ:- ከመቂ


1 ዶክተር ደብረጽዮን
2 ቴሌ ና ግምሩክ
3 አዱገነትን ጨምሮ የኦሮሚያ አመራር
4 ወፍ የለም
5 የአባይ ሙሌት
6 የአባይ ሙሌት
7 የለም
8 አክቲቪስት ባይሆንም ዘመድኩን በቀለ
9 ወፍ የለም
10 Arts
11 ሸገር
12 የለም
13 የለም
14 ሙፍቲ ሀጂ ኡመር እድሪስ ኦባንግ ሜቶ
15 የእግር እሳት
16 ደሞ በአባይ-ቴዲሻ ና ሔዋን- ከምኔው
17 ዳዊት ፅጌ (የኔ ዜማ)
18 የለም
19 ምርጫው😀
20 የመቅዶንያ ና ሜሪጆይ🤔
21 ከእመጓ እስከ ሰበዝ
22 የበውቀቱ All
23 IDK
24 ሜሎሪና
25 ከእመጓ እስከ ሰበዝ
26 IDK
27 ማሊክ አምባር ከቀንበር እስከ መንበር
28 እረኛው ሃኪም
29 አዳምኤል
30 IDK
31 አንድሮ ሜዳ

ስሜ ማህደር አድማስ
አዲስ አበባ
👇👇

1.ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል
2. ኢትዩ-ቴሌኮም
3.አዲስ አበባ አስተዳደር
4.የለም
5.የአባይ ሙሌት
6.'' አባይ የኔ ነዉ ''
7.
8. ጀዋር ሙሀመድ
9. ዶ/ር ሊያ ከበደ
10. ፋና
11. ሸገር
12.
13.ጦቢያ ( ፍራሽ አዳሽ 2)
14. ኦቡዋንግ ሜቶ
15. የእግር እሳት
16. ቴዲ አፍሮ ' ደሞ ለአባይ '
17. ዳዊት ፅጌ ' የኔ ዜማ '
18. አስቴር በዳኔ
19. አዲስ አበባ የኛ ናት 😂
20. 'አንድ ሰዉ ለአንድ ቤተሰብ '
21. 'ምንትዋብ ' ህይወት ተፈራ
22. 'ነፀብራቅ' ሌሊሳ ግርማ
23.
24.
25. 'በሀሰተኛ ስም ' አለማየሁ ገላጋይ
26. 'ዳኛዉ ማነዉ ' ፕ/ር ታደለች ሀ/ሚካኤል
27.
28. ' እረኛዉ ሀኪም ' ፕ/ር ምትኩ በላቸዉ
29. 'ኣዳምኤል ' በእዉቀቱ ስዩም
30. ' ሆሞሬዮስ ' ዳግም ጥላሁን


Besrat Gezu ከ ሰሚት 👇👇

1 የዓመቱ ተፅዕኖ ፈጣሪ የክልል ፕሬዝዳንት
- የሲዳማ መሪ ደስታ ሌዳሞ
2 የዓመቱ ስኬታማ የመንግስት ተቋም
- አየር መንገድ
3 የዓመቱ አሳፋሪ የመንግስት ተቋም
- ኢትዮ ቴሌኮም
4 የዓመቱ ተስፋ የሚጣልበት የዲሞክራሲ ተቋም
- General Attorney
5 የዓመቱ አስደማሚ የመንግስት ስኬት
- First Round Dam Filling
6 የዓመቱ ስኬታማ አገራዊ ንቅናቄ
- Planting 5 Billion plants
7 የዓመቱ አስደንጋጭ ስኬት
- 🤷‍♂🤷‍♂
8 የዓመቱ ተፅእኖ ፈጣሪ አክቲቪስት
- ቢኖር ምን አስደበቀኝ
9 የዓመቱ ምርጥ የፓለቲካ (የመንግስት ) መሪ
- ዶ/ር ሊያ ታደሰ
10 የዓመቱ ተወዳጅ የቴሌቪዥን ጣቢያ
- ፋና
11 የዓመቱ ተወዳጅ የሬድዮ ጣቢያ
- ሸገር 102.1
12 የዓመቱ ምርጥ ኢ-ልቦለድ መጽሐፍ
- ሰበዝ
13 የዓመቱ ተወዳጅ የኪነ ጥበብ ምሽት
-
14 የዓመቱ የሰላም የፍቅር አርዓያ
- እኔ
15 የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ድራማ
- የእግር እሳት
16 የዓመቱ ነጠላ ሙዚቃ
- ኃይለየሱስ ፈይሳ - ፍቅር ተወደደ
- ትምኒት ወልዳይ - ቃህ
- ሄዋን //ወልድ - ከምኔው
17 የዓመቱ ምርጥ የሙዚቃ አልበም
- የዳዊት ፅጌ የኔ ዜማ
18 የዓመቱ ምርጥ ጋዜጠኛ
- ስሜነህ ባይፈርስ
19 የዓመቱ አሳፋሪ የፓለቲካ ውዝግብ
- የትግራይ ክልል የምርጫ ካላደረኩ አሻፈረኝ ማለት
20 የዓመቱ ምርጥ የበጎ አድራጎት ድጋፍ
- የ አዲስ አበባ የቤት እድሳት
21 ምርጥ ታሪካዊ ልብወለድ
-
22 ምርጥ የወግ መጽሐፍ
- ሰበዝ
23 ምርጥ የፍልስፍና መጽሐፍ ―
- መፅሐፈ ጨዋታ ስጋዊ ወመንፈሳዊ
24 ምርጥ የስነልቦና መጽሐፍ ―
-
25 ምርጥ የልብወለድ መጽሐፍ ―
-
26 ምርጥ የፖለቲካ መጽሐፍ―
-
27 ምርጥ የታሪክ መጽሐፍ ―
-
28 ምርጥ የሕይወት ታሪክ―
- የአስጌ የኢቲቪ ኢንተርቪው
29 ምርጥ የግጥም መጽሐፍ ―
-
30 ምርጥ የትርጉም መጽሐፍ ―
-
31 ምርጥ የምርምር መጽሐፍ ―


Biniam አርባምንጭ 👇👇

1,የአፋር ክልል ኘሬዝዳንት
2,Tele
3,ህወሃት
4,ኢዜማ
5,የአባይ ሙሌት
6,ስለ አባይ
7,የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ivory costn ያሸነፈበት
8,posetive ተፅእኖ አላየሁም nagative ከሆነ Ja war
9,Dr.abiy ahimed ali
10.Arts tv
11,yilefegn
12, ''
13, ''
14,ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድርስ
15, 9ኛው ሽ
16,ቴድ አፍሮ ደሞ በአባይ
17,የኔ ዜማ Dave
18, ኤልያስ መሠረት
19,የ ትግራይ ክልላዊ ምርጫ
20, ማዕድ ማጋራት (የ ኢትዮጵያ ህዘብ በ ሙሉ)
21,Yilefegn
22, ''
23,''
24, ''
25, ዴርቶጋዳ


ስም: ሱራፌል አሰፋ
አድራሻ: አዲስ አበባ (አዲሱ ገበያ)
👇👇👇


1. አቶ ሙስጠፌ መሀመድ
2. ኢትዮ ቴሌኮም
3. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
4. .........
5. ሸገርን ማስዋብና የአባይ ውሀ ሙሌት
6. ድምፃችን ለግድባችን
7. የአባይ ውሀ ሙሌት
8. .......
9. ዶ/ር ሊያ ታደሰ
10. Esat
11. ሸገር FM 102.1
12. .....
13. ......
14. ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ
15. የእግር እሳት
16. ቴዲ አፍሮ (ደሞ በአባይ)
17. ዳዊት ፅጌ (የኔ ዜማ)
18. ሲሳይ አጌና (ኢሳት ቲቪ)
19. ግድቡ ተሽጧል እና ኮንዶሚኒየሙ
20. ለኮሮና የተደረገው ርብርብ ከመላው ኢትዮጵያን
21. - 31 የለም


ስም፦ ስምረት (Ellameta)
አድራሻ ወሎ ደሴ

👇👇👇

1ሙስጠፌ የሶማሌው
2ኢትዮጵያ አየር መንገድ ና ቴሌ
3የአአ ከንቲባ ቤቶች አስተዳደር
4የፌደራል ፍርድቤት
5የህዳሴውን ግድብ ሙሌት ማስጀመር
6የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ
7የመጀመሪያው ዙር የግድቡ ሙሌት መጠናቀቅ
8ጀዋር መሀመድ
9ዶ/ር አብይ አህመድ አሊ
10 Art tv
11. ሸገር
12
13.የለም
14. ኡባንግ ሚቶ፣ ቀዳማዊ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እንድሪስ
15.ዘጠነኛው ሺ እና ቤቶች
16 ደሞ በአባይ(ቴዲ አፍሮ)
17.የኔ ዜማ የዳዊት ፅጌ
18.ተመስገን ደሳለኝ ፍትህ ጋዜጣ
19.የአርቲስት ሀጫሉ ግድያ
20.
21.የፍቅር ድንግልና(የጂጂእናት የፃፈችው)
22.እግረ መንገድ ስብሀት ገ/እግዚአብሔር
23.ጥበብ ከጵላጦስ ሀ/ጊዮርጊስ
24.ሜሎሪና ናሁሰናይ
25.ደህንነቱ ይስማዕክ ወርቁ
26.ዳኛው ማነው ታደለች ሀ/ሚካኤኣ
27.አዲስ አላነበብኩም
28.
29 .የራሴ
30.አልኬሚስት
31. ግራ አጋቢው ዘመን ትርጉም ነው
የእኔ መልስ ይሄንን ይመስላል

👇👇መልእክታቹን በዚህ ላኩልን

@balmbaras
@Nagayta
Forwarded from ሥዕል ብቻ ©
🌼ከአዲሱ አመት ጋር ፍክት ፍክትክት ይበሉልን🌼
🌼🌼🌼መልካም ዋዜማ🌼🌼🌼
#By_Ribka_Sisay🌼 ______________ @seiloch @seiloch @seiloch
ሃሳብ በሃሳብ …………!


ግሩፑን ለመቀላቀል

↓↓↓↓↓↓
https://www.tg-me.com/joinchat-Fez2QULOAgfN0GjJ8uG8aQ
አዲስ . . .
አዲስ ዓመት ላይ አዲስ በ"አ" ዓመት ደ'ሞ በ"ዓ" የሚፃፉበትን ሚስጥር ነጋሪ
ወይ ተናጋሪ (የአማርኛ not የግዕዝ) ባናገኝም... ብዙ ጊዜ አዲስ ሲባል ጥሩ
ነገር አመላካች ነው (ለከተማና ለአካባቢ እንዲሁም ለሥራ ሲሆን ብቻ
ቢያስበላም (ለወሲብ ጨምሮ (ሴት ስትሆን)))
እና... አንድ ጠቢብ ወዳጅ አንድ ወቅት እንዲህ ሲል ምክረ ሀሳቡን (በብስጭት
መልክ) አካፍሎን ነበር፣ እኔም በልቤ አኖርኩት፦
" ሰዎች 'አትጠጣ ጉበትህን ይጎዳዋል፣ አታጭስ ሳንባህን ይነካዋል፣ አትቃም
ጨጓራህን ይወጋዋል' እያሉ አዛ ያረጉናል። ቆይ እኔ የምለው ... ጨጓራ፣ ሳንባና
ጉበት እኔን አቅማቸው እስከፈቀደ ድረስ ተደስቼ እንድኖር እንዲያገለግሉኝ ነው
የተፈጠሩልኝ? ወይስ እኔ እነሱን ተሳቅቄና ተጠንቅቄ ተንከባክቤ እንዳኖራቸው
ነው የተፈጠርኩላቸው? "
እህእ!
በርካታ ሰዎች ስለሕሊና ሲያወሩ ተመሳሳይ (ወይም ተቃራኒ) አረዳድ
አይባቸዋለሁ። ሕሊናቸውን አዲስ እና ንፁህ አድርገው መኖር እንዳለባቸው
ስለሚያስቡ ፈፅሞ አይጠቀሙበትም። Hence ሕሊናቸው ንፁህ ነው¡ "ዜሮ
ዜሮ" ነው፣ የትም ያልተነዳ!
ቀጣዩ ዓመት ሕሊናችሁ እንዲያኖራችሁ እንጂ እንድታኖሩት አልተፈጠረምና፣
ሕሊናችሁን አፍግታችሁ፣ አልፍታችሁ፣ አሟጣችሁና አጨርጭሳችሁ
የምትጠቀሙበት ይሁንላችሁ!

@wegoch
@wegoch
@paappii

#gemechu merera fana
ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን ያሳለፉትን አመት ላየ የዘመን መለወጫ ዋዜማው
በድባቴ የሚያልፍ ይመስል ነበር ውጥንቅጡ የወጣውን አመት መዝጊያም ልክ እንደ አብዛኛው የአመቱ ክፍል
በድበርት የምናሳልፈው ይመስል ነበር፡፡
አዲስ አበባን ዞር ዞር ብላችሁ ስታዩ ግን ሁኔታው ተቃራኒ ነው፡፡ ቄንጠኛ ቡቲኮች ቢጫ እና ቢጫ መሳይ ልብሶቻቸውን በነቂስ አውጥተው ከአደይ አበባ ለመፎካከር እየሞከሩ ነው፡፡ የመንገድ ዳር ቸርቻሪዎች ከዘወትር እቃዎቻቸው መሃል እዚህም እዚያም ገዢ የማያጡበትን ቻይና ሰራሽ የፕላስቲክ አደይ አበባ ይዘው ውር ውር እያሉ ነው፡፡
በግ ተራው ከወትሮው ቢደምቅ እንጂ አልፈዘዘም፡፡ ለገበያ የወጣው ቄጠማ እና ችቦ ከሌላው ጊዜ ቢበዛ እንጂ ፈፅሞ አያንስም፡፡ ኢትዮጵያውያን በእጅጉ ያስከፋቸውን 2012 ገፍትረው ለማስወጣት የጓጉ ይመስል ዋዜማውን በልዩ ድምቀት ተያይዘውታል፡፡ 2013ን ‹‹ቶሎ ናልን እና ከዚህ መቅኖ ቢስ አመት ገላግለን›› በሚል ይማፀኑት በሚመስል አኳሃን በጉጉት ተወጥረዋል፡ ከእልቂቱም፣ ከበሽታውም፣ ከረሃቡም አትርፎ እዚህ አድርሶናልና፤ 2013ን የ2012 ተቃራኒ እንዲያደርግልን፣ አመቱን ሙሉ እንደ ዛሬ የዋዜማው ቀን በፌሽታ እና በተስፋ እንዲያከርመን እመኛለሁ፡፡
የከፋውን ጊዜ ታሪክ አድርጎ የተሻለውን ከፊታችን እንዲያደርግልን ፈጣሪን እማፀናለሁ፡፡ የሰላም እና አንድ የመሆን ምኞታችንን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ያሰምርልን ዘንድ የማምነውን አምላክ እለምናለሁ፡፡ መከራችንን ያለፈና ጊዜያዊ፣ ፌሽታንን የወደፊትና ዘላቂ ያደርግልን ዘንድ አጥብቄ እፀልያለሁ፡፡
መልካም አዲስ አመት!

@wegoch
@wegoch
@paappii

#hiwot emishaw
🌼🌼🌼መልካም አዲስ አመት 🌼🌼🌼
አዲሱ አመት የደስታ፣የፍቅር እና የሰላም ይሁንላችሁ ።
.
.
@wegoch
@wegoch
#ወግ_ብቻ
.
ሞኙ አህያ!

በአንድ ወቅት፤ ጨው እየሸጠ የሚኖር ሰው ነበር። በየቀኑ የጨው ከረጢት ወደ ገበያ የሚያወጣ አህያ ነበረው። ወደ ገበያ በሚወስደው መንገድ ላይ አንድ ትንሽ ወንዝ ማቋረጥ ይኖርባቸዋል። አንድ ቀን አህያው በድንገት ውሃ ውስጥ ወድቆ የጨው ከረጢቱ በውሃ ተነከረ። ከረጢቱ ውስጥ ያለው አብዛኛው ጨው ስለ ማሟ ለመሸከም ቀላል ሆነ። ሰውየው በተፈጠረው ነገር ቅር ቢሰኝም ወደ ገበያ ለመሄድ ቆርጧል። ከረጢቱ ክብደት ስላልነበረው አህያው ላይ ሲያስቀምጥው ከባድ ባለመሆኑ አህያው ተደነቀ። በዚህ ክስተት በጣም በመደሰት፤ አህያው በየቀኑ ተመሳሳይ ማታለያ ለመጫወት ወሰነ። ወንዙ ላይ ሲደርሱ፤ አህያው በመውደቅ ከረጢቱን ውሃ ውስጥ እንዲወድቅ ያደርጋል። ከዚያ አህያው ቀለል ያለ ከረጢት ተሸክሞ በደስታ ወደ ገበያው ይሄዳል። ሰውየው፤ አህያው እየሸወደው መሆኑን ስለተረዳ አንድ ትምህርት ለማስተማር ወሰነ። በሚቀጥለው ቀን፤ አህያውን በጨው ፋንታ በጥጥ በተሞላ ከረጢት ጫነበት። አህያውም በተመሳሳይ ለመሸወድ እና ለመጫወት ቢፈልግም እርጥበታማው ጥጥ ግን ለመሸከም በጣም ከባድ ነበር። ከዛም አህያው ወደ ገበያው ለመግባት ታገለ። አህያው ትምህርቱን ስለወሰደ፤ እንደገና ለመሸወድ አልሞከረም።

የታሪኩ ፍሬ ነገር!

ቀላል (አቋራጭ) መንገድ ለመያዝ አትሞክሩ። አቋራጭ ለተወሰነ ጊዜ ደስታን ቢያስገኝም ግን መጨረሻም እናንተ መሆን ወደ ምትፈልጉበት ቦታ አይወስዳችሁም። ቀላል አማራጭ ሲገጥማችሁ፤ አመስጋኝ በመሆን ጊዜውን በሚገባ ተጠቀሙበት። ያለአግባብ ለመጠቀም ስትሞኩሩ ግን ተመልሶ እናንተኑ ያጠቃችኋል።
@wegoch
@wegoch
@wegoch
2024/09/24 15:31:40
Back to Top
HTML Embed Code: