Telegram Web Link
#ወግ_ብቻ
መንታ መልክ

📖📖📖

ሊዮናርዶ ዳቪንቺ የመጨረሻው ዕራት የሚለውን ሥዕሉን በሚሰራበት ወቅት አንድ ችግር ገጠመው። ከአሥር ዓመታት በላይ በፈጀው በዚህ የስዕል ሥራ ላይ ሁለት ሞዴል መሆን የሚችሉ ሰዎች ጠፉ። ኢየሱስን እና የአስቆሮቱ ይሁዳን...


ዳቪንቺ የካቶሊክ ቤተ-ክርስቲያን ኃላፊዎችን ጭቅጭቅ መታገስ ከአቅሙ በላይ ሆነበት። ስዕሉን እንዲጨርስ የተሰጠው ጊዜ እየተገባደደ ነው። ...የትም ፍጭው...አይነት መርህ።

🗒🗒🗒

ከእለታት በአንዱ ዳቪንቺ ሞዴል ፍለጋ ወደከተማ ወጣ። በአራት ማእዘን መተላለፊያዎች ጥግ ቆሞ ክርስቶስንም ይሁዳንም ወክሎ መሣል የሚችል ሞዴል አጣ። ከብዙ ፍለጋ በኋላ ድንገት አንድ ሰው ብቅ አለ ከገበያ መሃል...

የአጥንት አወራረዱ፣ የዓይኖቹ ውበት እና ጥልቀት፣ ቁመናው፣ የአፍንጫው አወራረድ፣ ፂሙ፣ ርጋታውና አትኩሮቱ ቁጭ ኢየሱስን። ወደ ስቱዲዮው ይዞት ገባ... ቀለሙን በጠበጠ፣ ሽርጡን ታጠቀ፣ ሰውየውን ከፊቱ አስቀመጠና ስሎ ጨረሰ።

🗒🗒🗒

አሁን የመንፈስ መረጋጋት እየተሰማው ነው። ነገር ግን አንድ ሰው መገኘት አለበት፤ ይሁዳን የሚመስል ። የአስቆሮቱ ይሁዳን ሰብዕና መወከል የሚችል ሰው በሀገሩ ጠፋ። አሥራ ሁለቱም ተስለዋል፤ የይሁዳ ቦታ ግን ባዶ ነው። የመጨረሻው እራት ከይሁዳ ውጪ ባዶ ነው። ኢየሱስን ወደ ደረቱ ቀርቦ የሚያነጋግረው ዮሐንስ አለ። ሌሎቹም እንዲሁ። ነገር ግን እጁን ወደ ወጪቱ ከመሲህ እጅ ጋር የሚያጠልቀው ይሁዳ ግን የለም፤ እርሱን የሚመስል ሞዴል አላገኘም ነበርና...እነሆ ሶስት ዓመት አለፈ። ይሁዳን ፍለጋ...

🗒🗒🗒

ከሶስት ዓመት በኋላ ከቀናት በአንደኛው ዳቪንቺ ወጪና ወራጁ በሚመላለስበት መንገድ መሃል አንድ ሰው አስተዋለ። ፊቱ በመጠጥ ብዛት የተመጠጠ፣ ዓይኖቹ ከጉድጓዳቸው ወጥተው ሊወድቁ የደረሱና ሁሉንም የሚመለከቱ መረጋጋት የተሳናቸው የሚመስሉ፣ ያለ ዕረፍት የሚንቀጠቀጡ ቅንድቦች ያሉት፤ መልከ-መልካም የነበረ የሚመስል የአካሉ ጉስቁልና የመንፈሱን መታወክ የሚሰብክ አንድ ሰውን ተመለከተ፤ ቀርቦም...

"እኔ ሰዓሊ ነኝ ለምስለው ስዕል ያንተ ገዕታ ያስፈልገኛልና ብስልህ ምን ይመስልሀል?" ሲል ጠየቀው ዳቪንቺ ሰውዬው በስላቅ እየሳቀና በጥርጣሬ እየተመለከተው "መልካም እኔ ምን ቸገረኝ ሳለኝ ነገር ግን ትከፍላለህ" አለው
ተስማምተው መንገዳቸውን ቀጠሉ....

🗒🗒🗒

እንዴት መቀመጥ እንዳለበት ለይሁዳ ስሜት በሚቀርብ ሁኔታ ሰውዬውን ካሰናዳ በኋላ ስዕሉን ጀመረ... ከሰዓታት በኋላም ስዕሉን ጨረሰ። የእፎይታ ስሜት የሰዓሊውን መላ አካል ወረረው። አሁን የሚጨቀጭቀው፣ የሚነዘንዘው አይኖርም።
የተሳለው ሰው ገንዘቡን ተቀብሎ ሊወጣ ካለ በኋላ ተመልሶ ስዕሉን ማየት እንደሚችል ጠየቀ።

🗒🗒🗒

ስዕሉን ወደሰውዬው አይኖች አዞረለት። እጁን አገጩ ላይ አስደግፎ ለበርካታ ሰዓታት ምስሉን ያስተውለው ገባ። እናም በጥርጣሬ አይነት አነጋገር "ይህን ስዕልከዚህ በፊት ሳላየው አልቀርም" አለ "በፍፁም አይተኸው አታውቅም ይህ ስዕል ገና አደባባይ ያልወጣ ያልታየ የራሴ ብቸኛ ስራ ነው" ሰውዬው አቋረጠው "ቢሆንም ይህንን ስራ ከዚህ በፊት በእርግጠኝነት አውቀዋለሁ"
"የት?" ዳቪንቺ ጠየቀ
"እዚሁ ከተማ ከዚህ በፊት አንድ ሰዓሊ ይመስለኛል ከሶስት ዓመት በፊት ክርስቶስን ትመስላለህ ብሎኝ ያውቃል ዛሬ ደሞ አንተ ይሁዳን ትመስላለህ አልከኝ" ብሎ "ወይ የሰው ልጅ" እያለ በመገረም በተሰጠው ዲናር ወይኑን ለመጎንጨት መንገዱን ጀመረ...

📖📖📖

ምንጭ 📖 የይሁዳ ድልድይ እና ሌሎችም ወጎች
ደራሲ ኤፍሬም ስዩም

፨ በኛ ሕይወት ውስጥም በየቀንና በየሰአቱ የሚቀያየርና የማይጨበጥ ስብዕና ያላቸው ሰዎች ስንት ይሆኑ...? ጥዋት እንደ ኢየሱስ በየዋህነት የሚቀርቡን ከሰአት እንደ ይሁዳ አስማምተው የሚሸጡን ስንት ይሆኑ?...ቤቱ ይቁጠራቸው...!
@wegoch
@wegoch
@wegoch
#የደሜ ዜመኞች

      ክፍል - ፪

ቀጥያለሁ......

team jungle boyz በትምህርት ቤታችን ታዋቂ ሆነናል
በስራችን ውስጥ የሌለ ተማሪ የለም ሁሉንም በኔትወርካችን ስር አድርገን ተደራሽነታችንን እስከ አስተማሪ ድረስ አድርሰነዋል በቃ ሁሉም ነገር ጭስ በጭስ ሆኑአል በኛ ምክንያት
አላማዬ መሉ በሙሉ ወደ ምፈልገው ቦታ ሄዶልኛል በዚ ዘመን ላለምነው አላማ መሳካት ያለምነው ነገር ሰውን ጎጂ መሆን አለበት
ሁሉም በር ካለምንም ልፋት ስለሚከፈትልን
ስለኛ ማያወራ ስለኛ ማያነሳ በኛ ስራ ማይቀና ሰው የለም
እኔም ከልጅነቴ ጀምሮ ሳየው የነበረው ነገር በተግባር በመፈጸሜ ከኔ በላይ የጀግንነት ስሜት የሚሰማው ሰው አልነበረም
በቃ ጀግና ነኝ....
ባለሁበት ትምህርት ቤት ውስጥ ካለው የተማሪ ብዛት 60% በላይ የሚህኑት ሴቶች ነበሩ በኔ የስራ አለም ውስጥ ፆታ ቀለም የሚባል ነገር የለም ሁሉንም ተደራሽ ማድረግ ነው ፍላጎቴ
ግን አብዛኛዎቹ ወንዶች በመሆናቸው ያን ያህል ተደራሽ እንዳሎንኩኝ ውስጤ በተደጋጋሚ ለጀግናው ስሜቴ ይነግረዋል
ሄዋንስ........  
ሄዋንን ወደኔ ለማምጣት ሌላ ብልህ  ሄዋን በጣም ታስፈልገኛለች እሷም ነይ ሳትባል ነው የመጣችው
ነገሩ ወዲህ ነው
አንድም ቀን ከጆሮዬ ኤርፎን ተለይቶኝ አያቅም #ኢስኮባር መጣ ኢስኮባር እንዲህ ሆነ ...
ኢስኮባር ነበር የሚሉኝ
ኢስኮባር ታዋቂ የኮሎምቢያ ሀሺሽ ነጋዴ ነው ኢስኮባር እሹ እራሱ አንድ መንግስት ነው ማለት ይቻላል
እኔም በሱ ስም በመጠራቴ ከፍ ያለ ስሜት ነበር የሚሰማኝ
አዎ ኢስኮባር ነበርኩ ትንሹ ኢስኮባር
አባቴ በአዝማሪነቱ የማያውቀው ሰው ያላካለለው ሀገር ያልዞረበት የባህል ቤት የለም
እኔም የማያውሸኝ ሰው በስራዬ ሙሉ የአዲስ አበባን ትምህርት ቤቶች እና ኩታራው የሚዝናናባቸውን ክለቦች በጠቅላላ ተቆጣጥሬ ነበር
የአዝማሪ ልጅ መሆኔን ለማሳወቅ ነው ሁሌ በሄድኩበት ሙዚቃ ማይለየኝ
በሄድኩበት ቦታ ሁሉ ሲሰማ የነበረው ሙዚቃ ይቀየራል ሁሉም ነገር ወደ ድሮ ይመለሳል
አንድም ሰው አያጉረመርምም
ፀጥ ረጭ ...... ኢስኮ ነኛ
ከአባቴ ቀጥሎ ያለኝ ነገር ሙዚቃ ነው አባቴም ከባቲ እና አምባሰል ካንቺሆዬን ትዝታ ቀጥሎ የምሰማው እሱ እራሱ አንዱ ሙዚቃዬ ነው
አባት አለሜ ለኔ የሰጠኝ ትልቁ ሀብት ሙዚቃ ነው
           ሙዚቃ ህይወቴ አለ ቴዲዬ ነፍሴ
ወደ ፊያሜታ ልመልሳችሁ (ማንም ሳይጠራት መጣች)
አንዳንዴ ፍቅርን ከየት እንደምናገኝ አናውቀውም ስንዳክር ለኛ ባልተሰራ ሰው ስነንደክም ቆይተን ባላሰብነው ሰአት የኛ ሰው ከጎናችንን እናገኘዋለን
የኔ ...... ባትሆንም የኔ ነበረች
ትዝ ይለኛል መማር ያለመደው ጎኔ ዛሬም በተለመደችው ቦታ ቁጭ ብያለሁ ለምን እንደሆነ ባላውቅም ብቻዬን ነበርኩኝ
                    ገና ስመጣ ወደዚች ምድር
                     አሳደገችኝ ቀብታ ፍቅር
                     በልጅነቴ ከእቅፋ ሰርቃ
                    ነፍሴን ወሰደች ያቺ ሙዚቃ
                                          ሳሚ ዳን ነው ብዙ አወጋዋችሁ እኔም የምፅፍበት ሉኬን ያበላሸውን ጠብታዬን ለፅዳ ድምጿን ጨመር አርጉት እኔም አንዴ ሰላም ያለው አየር ልውሰድ .......
ሰላም በሌለው ክፉ ትዝታ ውስጥ አፋኝ አየር እንጂ ንፁ ነገር የለም
ስቃይ ........
ለምን እንዲህ እንደሆንኩ አላቅም ጥግ ድረስ የልባችንን በራፍ ወገግ አርገን ስንከፍት የከፈትንለት ሰው ብቻውን መግባት ይፈራል መሰል ብዙ የልብ ምት አዋኪ ነገሮች ከልባችን ስር ይቀመጣሉ
ደም መዘዋወሩን አቁሞ በገባው ነገር ተደናግጥ እዛው ባለበት ይረጋል
ሌላ ደም ስለማይመጣ ልባችን ትቀዘቅዛል እራሷ ከፍታ ያስገባችውን አካል መልሳ ለማስወጣት ቅዝቃዜው ያስቸግራታል ለመሞቅ የትዝታዋን እሳት ስለለኩስ የረጋው ደም መፍላት ይጀምራል ይበልጥ ስቃይ
ትነቱ አእምሮ ጋ ሄዶ ይደልቀዋል ያኔ ያ ህመም ከህመሞች ሁሉ የባሰው ይሆናል
ምክንያቱም........
ማሰብ ቆሞ ልብ የምትሰጠንን ምስል ብቻ ማውጠንጠን ስለምንጀምር
ማሰብ ማቆም ነው የህመም ሁሉ ህመም
ልብ ሲተክዝ ሰወነት ይቆማል
ሰውነትም ሲቆም ማሰቡ የጠፋል
                 የኔ ሀሳብ ባንቺ ፍቅር ተመርዞ
                 ቢያስቸግረኝ ፍፁም ልቤን አስተክዞ
                ተረታሁኝ ባንቺ ፍቅር ተይዤ
                አሃ አሃ አሀሀሀሀሀሀሀሀሀሀ
               ቁጭ ብዬ ቀረሁልሽ ተክዤ
               አሃ አሃ አሀሀሀሀሀሀሀሀ
              ሀሳብ ብቻ በልቤ ውስጥ ተመርኩዤ
                                ግርማ ነጋሽ ቀጥሏል ከዚ ዜማ በላይ ሊገልፀኝ የሚችለው ነገር የለም
የልብ ስብራት እንደ ጉልበት ስለማይታሽ እንደ ፀባዩ መያዝ ነው
አቃተኝ እናነተዬ ደምና እንባ እየጠከስኩ ነው ምፅፈው አቅሙ አጥሮኛል እጄ ተንቀጥቅጦ ቃላቱን በአንዱ ቃል ላይ እየደረበ ነው
ስቃይ.....

                          እቀጥላለሁ
                   ብላቴናው በደም ቀለም
          
@wegoch
@wegoch
@wegoch
#ወግ_ብቻ
"የኮረና ቫይረስ በምግብ ይተላለፋል ወይ?"

Dr Solomon Kibret (ካሊፎርኒያ ዩኒቨርስቲ)

ጋዜጠኛ Tesfaye Woldesilassie ይህን ጥያቄ አብራርቸ እንድመልስ በጠየቀኝ መሰረት እንደሚከተለው አስረዳለሁ።

የኮረና ቫይረስ መተላለፊያ መንገዱ በትንፋሽና በንክኪ መሆኑ ይታወቃል። ለዚህም ነው ንክኪ መቀነስ፤ እጅን በሳሙና መታጠብና ማህበራዊ ፈቀቅታ የሚመከረው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚጠየቅ ጥያቄ ግን ምግብን በተመለከተ ሆኗል። "የኮረና ቫይረስ በምግብ ይተላለፋል ወይ?" ይህን ለመመለስ የተለያዩ ጥናቶችን ለመዳሰስ ሞክሪያለሁ።

የአሜሪካ የበሽታ መከላከል ማዕከል (CDC) ይህንን ጥያቄ በማስመልከት ማርች 17 በሰጠው መግለጫ; "There is no evidence that food has been associated with the transmission of the virus although more research is still required. Foodborne exposure to this virus is not known to be a route of transmission”

"እስካሁን ያለው መረጃ የሚያሳየው የኮረና ቫይረስ በምግብ ምክንያት አንደማይተላለፍ ነው። ቫይረሱ ከምግብ ጋር በመግባት የበሽታ መተላለፍ መንስኤ አይሆንም" በማለት መልስ ሰጥተዋል።

በቫንደርቢልት ዩኒቨርሲቲ የህክምና ፕሮፌሰር የሆኑት ዊልያም ሻፍነር ስለዚህ ጉዳይ ሲናገሩ "የኮሮና ቫይረስ የመተንፈሻ አካላትን የሚያጠቃ ነው እንጂ ሆድ ውስጥ ያሉ የምግብ መፍጫ አካላትን የሚያጠቃ አይደለም ስለሆነም በመተንፋሻ አካላት በኩል ዘልቆ ካልሆነ ከምግብ ጋር አብረን ስለተመገብነው በሽታው አይዘንም። ሆድ ውስጥ ቢገባ እንኳን የጨጓራ አሲድ ሲሳይ ይሆናል።" ይልቁንስ ይላሉ ፕሮፌሰር ዊልያም "ምግቡ ሲዘጋጅ ንክኪ ከተፈጠረ፤ ለምሳሌ በቫየረሱ የተያዘ ሰው ምግቡን ሲያዘጋጅ ቢያስነጥስበት ወይም እጁን ሳይታጠብ ካዘጋጀውና እኛም ምግቡን ወይም ምግቡ የታሸገበትን እቃ በእጃችን ነክተን ከዛም ከፊታችን ጋር ንክኪ ስናደርግ ቫይረሱን ቀጥታ ወደ መተንፈሻ አካላችን እንዲገባ እናመቻችለታለን። ይህ ንክኪ በተለይ በእጃችን በቀጥታ በመንካት የምንመገባቸው ምግቦችን (ምሳሌ፤ ፍራፍሬዎች፤ ሳንድዊች፤ ጥሬ ስጋ) ቫይረሱ ቀደም ሲል ምግቡን ከነካው ሰው ወደ እኛ እጅ በተወሰነ መልኩ (አነስተኛ እድል ቢኖረውም) የመተላለፍ እድሉን ሊፈጥር ይችል ይሆናል።"

ስለዚህ ምን ማድረግ አለብን?

መዘንጋት የለለብን ነገር ይህ ቫይረስ የሚተላለፈው በንክኪና በትንፋሽ መሆኑን ነው። ስለዚህ፤

1. ማንኛውም ምግብ የሚያዘጋጅ ሰው እጁን በሳሙና ታጥቦ [እና የፊት መሸፈኛ ማስክ አድርጎ] ምግብ ያዘጋጅ፤ አስታውሱ ምንጊዜም ምግብ ዝግጅት ከመጀመራችን በፊት እጃችንን በሳሙና በደንብ መታጠብ አለብን።
.
2. ከምግብ ተራ የገዛናቸውን ፍራፍሬዎችና አትክልት በተለያዩ ሰዎች ተነካክተው ስለሚሆን በሚፈስ ውሃ [running water] አጥበን እንጠቀም፤ [በሳሙና ወይም በኮምጣጤ ማጠብ አይገባም፤ ውሃ በቂ ነው](በእቃ ላይ የታቆረ ውሃን ሳያፈሱ ለብዙ ሰዓት ለማጠቢያነት መጠቀም ከማጠብ ተግባሩ ይልቅ ከአንዱ ወደ አንዱ የመበከል ሁኔታን ሊፈጥር ስለሚችል ምንጊዜም የሚወርድ ውሃን እንጠቀም]
.
3. ምግቡ የታሸገ ከሆነ የታሸገበትን ካርቶን/ወረቀት ካነሳን በኋላ በትክክል ማስወገድና ወዲያውኑ እጃችንን በሳሙና መታጠብ ይገባል [ለማስታወስ ያህል በቅርብ የተደረገ ጥናት ኮሮና ቫይረስ በካርቶን ላይ እስከ 24 ሰዓት መቆየት ይችላል]
.
4. ምግብን አብስሎ መመገብ የተለያዩ በሽታ አምጭ ተህዋስያንን ስለሚገልልን ልናዘወትረው ይገባል።
.
References:
1. Kutter JS, Spronken MI, Fraaij PL, Fouchier RA, Herfst S. 2018. Transmission routes of respiratory viruses among humans. Current opinion in virology 28:142-151.
2. NPR. How Safe Is It To Eat Takeout? April 8 2020; https://www.npr.org/…/822903…/how-safe-is-it-to-eat-take-out
3. US News. Coronavirus and Food Safety. March 31, 2020. https://health.usnews.com/…/art…/coronavirus-and-food-safety
4. FDA. Food Safety and the Coronavirus Disease 2019 (COVID-19). April 14, 2020.
@wegoch
@wegoch
@wegoch
ርቀት መጠበቅ ይወዳል ቤቱ፤
ከጥንት ነው ከመሰረቱ

( በእውቀቱ ስዩም)
አካላዊ መራራቅ የሚባለው ነገር ለብዙ ሰዎች ሲከብዳቸው ሳይ ይገርመኛል ! ለኔ ደግሞ አካላዊ ርቀት የሚባለው ነገር አብሮ አደጌ ነው!
የሆነ ጊዜ ላይ አያቴ በነበረው አስተዳደር ተማረረና ሸፈቶ ጫካ ገባ ፤ አልፎ አልፎ፤ ቀን በደመና ማታ በጨለማ ተሸሽጎ ይመጣና ቤቱ ያድራል ! ሁሌም ሲተኛ መውዜሩን እንደ አራስ ልጅ ታቅፎ ነው ! አንዴ ለቁርስ ልቀሰቅሰው አስቤ፤ የተከናነበውን ቡልኮ ብገፈው “ ይቺን ይወዳል ” ብሎ ፎክሮ በሰደፍ ለጥቂት ሳተኝ፤ እኔን የሳተኝ ሰደፉ ካጠገቤ የነበረውን ግድግዳ ነደለው ! የሚገርማችሁ ነገር ሰደፉ የነደለውን ቀዳዳ በተጠባባቂ መስኮትነት ሲያገለግለን መኖሩ ነው :: ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አያቴን ለመቀስቀስ ስፈልግ: ከቤት እወጣና -በረጅም አጣና በምኝታቤቱ መስኮት አሻግሬ ብብቱን እኮረኩረዋለሁ ፤ ልጅ እያለሁ ላጭር ጊዜ ካያቴ ጋር ኖርያለሁ! አያቴ ሁሌም ከአደን ሲመለስ ቆንጆ ቁርስ ይሰራለታል፤ መጀመርያ የገብስ ዳቦ በአጋዘን ወተት እያማገ ይበላል፤ ቀጥሎ የዥግራ መላላጫ ይመጣለታል ፤ በመጨረሻ እጁን ወደ ውጭ ሰደድ አድርጎ መስኮቱን ታክኮ ከበቀለው ቁጥቁዋጦ ውስጥ እንጆሪና ቀጋ ሸምጥጦ ይበላል ፤ ታድያ በየጣልቃው፤ ከጉሬዛ ፀጉር በተሰራ ናፕኪን አፉን መጥረግ አይዘነጋም ! እሱ ምግቡን በጨበጣ ሲያጠቃ ‘ እኔና ወንድሜ ባስር ሜትር ርቀት ላይ ቆመን በጉምዥት እናየዋለን ፤
አንድ ቀን ያያቴ የጭን ገረድ ፤” ልጆች እየተቁለጨለጩ ነው ምናል ትንሽ ቢያቀምሷቸው ?” አለቺው አያቴ አፉ ውስጥ የሚንጉዋለለውን ጉርሻ አጣድፎ ዋጠና እንዲህ አላት ;-“ ልጅ መቁለጭለጩን ሰማይ መብለጭለጩን አይተውም፤ ይልቅ ወሬውን ትተሽ ሽንብራ ቁይላቸው ” ያምስተኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ እንኮየ የምትባል የክፍላችን ቆንጆ ልጅ ወደድኩ! ስምንት ወራት ያክል በትጋት ካፈቀኳት በሁዋላ አንድ ቀን ስሸኛት ፤ ስፈራ ስቸር በጣቴ ከንፈሯን ነካሁት! ከዚያ ወደ ቤቴ ገሰገስሁ ! ከንፈሯን የነካሁበት ጣቴ እንዳይረክስ በመንገዴ ላይ ማንንም አልጨበጥሁም፤ ሊጨብጡኝ የሚቃጡትን ሁላ “ ይቅርታ አርጉልኝ፤ እከክ አለብኝ እያልሁ፤ ለእንኮየ ፍቅር ስል “ እከካም “ እየተባልሁ ቤቴ ደረስሁ ! እቤት ገብቼ በእንኮይ ከንፈር የተጠመቀ ጣቴን ጨመጨምኩት! አንድ ቀን እንኮየን አስቁሜ ስምንት ወር ሙሉ አፈቀርኩሽ አላማሽ ምንድነው አልኩዋት! እየተሽኮረመመች አደባባይ ላይ ከሚሆን ቤት ሄደን አይሻልም አለችኝ፤ ቤት ሄደን በባዶ ሆድህ አትችለውም ብላኝ ትንሽ ነገር ቀምሰን ስናበቃ፤ ተነስታ የሳሎኑን መስኮት መጋረጃ ዘጋች! ስንሳሳም ከውጭ ያለው ህብረተሰብ እንዳያይ አስባ ነው ብየ ገመትኩ፤ መሳሳቴን ያወቅሁት ታላቅ ወንድሙዋ ዶልቻ ከምኝታ ቤት ሲወጣ ሳይ ነው! ከዚያ በሁዋላ ያለው አይነሳ! ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ስስ ብልቴን ብቻ ሳይሆን ሸካራ ብልቴን ተመትቻለሁ ! በቅዱስ ሚካኤል ስእል ውስጥ እንዳለው ጠይም ሰይጣን ክንዴን ተንተርሼ ወድቂያለሁ ፤ ዶልቻ እንደ ልስን ጭቃ ‘ ደረቴ ላይ ጭድ እየነሰነሰ ደጋግሞ ረገጠኝ ፤ በመጨረሻ ቤቴ ደጃፍ ላይ አምጥቶ ሲጥለኝ “ ከእህቴ አርባ ክንድ ካልራቅህ የጋሽ አስፋውን ጋሪ ተከራይቼ ነው እምድጥህ “ ያለው አይረሳኝም!
ከዚያ ክፍል ቀየርኩ ! በማስከተል ትምርት ቤት ቀየርኩ ! በመጨረሻ ከተማ ቀየርሁ፤ የእንኮየን ወንድም ከብዙ ዘመን በሁዋላ ሚኒሶታ የሚባል ከተማ ያበሻ የሙዚቃ ፌስቲባል ላይ አገኘሁት ፤ በልጅነቴ ያደረሰብኝን ረስቶታል ፤ እኔ ግን ደረቴ ላይ የተመላለሰውን የጫማውን ቁጥር ሳይቀር አልረሳሁለትም! ያም ሆኖ አብሬው መጨፈር ጀመርሁ ! ዶልቻ ሁለቴ እስክስታ ይመታና ሶስት ጊዜ ዙርያ ገባውን ገልመጥ ገልመጥ እያለ በስጋት ይሾፋል ! ምክንያቱን ጠየኩት! ምላሹ ባጭሩ እንዲህ ነው! ሚስቱን በድሎ ፍርድ ቤት Restraining order አውጥቶበታል! ከቀድሞ ሚስቱ በተገኘችበት ቦታ ሁሉ በሶስት መቶ ጫማ እንዲርቅ ተወስኖበታል፤ ይህንን ርቀት ጥሶ ከተገኘ ይታሰራል !
“ ያቺ ሰላቢ እዚህ ከመጣች ደውላ ታሳፍሰኛለች “አለኝ
የዶልቻ የቀድሞ ሚስት መጥታ ፌስቲቫሉን እንድትቀላቀል በልቤ እየፀለይሁ ጭፈራየን ቀጠልኩ፤

@wegoch
@wegoch
#የደሜ ዜመኞች

ክፍል - ፫
ቀጥያሉ.....

ከታፈንኩበት አየር ተመልሻለሁ ትንጋዬንም ጠረግ ጠረግ አድርጌዋለሁ
ቅድም ከተሰቃየሁት በላይ ስቃይ መሰቃየት ልጀምር ነው መሰለኝ
ማብቂያ የሌለው ስቃይ የእቶን ቃጠሎ ከበርባሮስ በጠለቀ ፅልመት ውስጥ ነኝ
ፊያ.....
ኢስኮ ኢስኮ አለቺኝ ሰምቻታለሁ ግን እንደሌሎቹ ወይ ሰላም ለማለት ወይ እንደተለመደው .......
መጣራቱ ቆሞ ከአጠገቤ መታ ጀርባዬን ደለቀቺኝ
ምን አይነት ድፍረት ነው ደሜ ፈላ ብዙ ነገር ልናገር የተነሳሁት ልጅ አፌ ፀጥ ረጭ አለ
አነሳሴ አስደንግጡአት ነው መሰለ ትናንሽ እጆቹአን ቀሚሷ ላይ አርጋ አንገቱአን ደፋች
ያ የደለቀኝ ድፍረቷ የት ገባ
እእእእእእእእ ምድነው አልኳት
ቀና ብላ አየቺኝ ረጅሙ ፀጉሯ አንድ አይኗን እስከ ግማሽ ከንፈሯ ሸፍኖታል
የጎደለ የፊት ገፅታ ግን ምንኛ ታምራለች በአባባ ሞት
ፈጠን ብላ
እኔ ካንተ ጋ መቀላለቀል እፈልጋለሁ ምንም አታስብ ጭራሽ ሀሳብ አይግባህ የሰጠኸኝን ዛሬውኑ
አየር እንኳ አቶስድም ስታወራ ከንፈሯ ላይ የተጣበቀው ፀጉሯ ለማውራት ስላዳገታት ሙሉ ጸጉሯን በአለንጋ ጣቶቹአ ወደ ኀላ አሸሸችው
ያ ግማሽ ውበት አሁን በሙሉ ሆኖ ደሜን ያራውጠው ጀመር
እእእእእ በናትህ ኢስኮ ቃጭል ድምጿ ከሀሳቤ አነቃኝ
ምን አለ በደንብ በሀሳቤ ብከትሽ
ምንም ሳላቅማማ ከቀኑ የቢዝነስ ስራ የተረፈውን 5 ክርታስ ሰጠሁዋት
ዘላ ተጠመጠቺብኝ ትንፋሿ ይፋጃል ገና ከመመሰጤ ጥላኝ ሄደች ......
ከመሄዷ አይኔን አንከራተተችው ልፍለፋዋ ዝም ብሎ ይታወሰኝ ገባ
ለነገ የሰጠሁዋትን ትሽጥም አትሽጥም እሷን ማግኘት ለኔ ከብሩ በላይ አጓጊ ሆኑአል
አዳሬን ሙሉ እሷን ማሰብ ሆነ ከዚ በፊት ለብዙ ሴቶች እንዲ አይነት ስሜት ተሰምቶኝ ያውቃል ይሄም ስሜቴም ብዙ እንግዳ አሎነብኝም
መጣ መሄዷ ስለማይቀር......
                     ይገርማል ቁመናና ዛላ
                     ልዩ ነው የፀጉሯ ዘለላ
                    ጥርሶቿ አቀማመጣቸው
                    ይገርማል አቤት ንፃታቸው
                                       ጥልዬ ደሞ መቷል በተራው በጣም ይገልፃታል ይሄ ዜማ በሉ በምናባችሁ የኔ ፀጉረ ዘለላ ምን እንደምትመስል እየሳላችሁ ጠብቁኝ
እኔም እንደለመደብኝ ...........
አይነጋ የለ አዲሷ የቢዝነስ አጋሬ ስታቃዠኝ አድራ ከመኝታ ቤቴ ከምተገባው ጮራ ጋ ውብ ፊቷ ድቅን ይል ጀመረ
 ገና በጠዋቱ ....
አባቴ ተነስቶ ወዲ ወዲያ ይላል እንደለመደው ሬዲዮኗ ተከፍታ ጥዑም ዜማ እያደረሰችን ነው
                    ማለዳ ፀሀይ ስቶጣ ደማምቃ
                     ከእንቅልፌ ድንገት ባንኜ ስነቃ
                     ፈጣሪን በቀኝ አውለኝ እላለሁ
                     አምላኬን ስሙን ሳነሳ እውላለሁ
                                      ቴዎድሮስ ታደሰ ነው አባቴ ነፍሱ እስኪወጣ ነው ሚወደው
ዘፈኑ ለአመስጋኝ እንጂ ለኔ አይነቱ ተራሰው እንደማይሆን ባውቅም ቀኑን ሙሉ ምለሴ ላይ ዋለ
መማርን አላማ አድርጌ ወደ ምማርበት ቦታ ሄጄ አላውቅም
ዛሬም ማለዳ ከምላሴ ያቺ ውብ ደሞ ከጭንቅላቴ ተጣበቀው ዋሉ
ዛሬ ከመጣችልኝ ቀኔ ነው በቃ ምን አልባትም ዜማው ሳይረዳኝ አልቀረም መሰል
ፊያሜታ ከፊት ለፊቴ .........

                      እቀጥላለሁ
                  ብላቴናው በደም ብዕር

                  
@wegoch
@wegoch
@wegoch
★★ ሞቴን ቀማኝ…… #4★★
(የመጨረሻ ክፍል)

"እታባ ‘አባትህ ጥሩ ሰው ነው። አንዳች እክል ካልገጠመው በቀር እንዲህ አይጨክንብንም።‘ ትለኝ ነበር "

ያሬድ ለአየኸኝ እየነገረው ነው። ……የማንጎ ጭማቂ በማንኪያ ሊያጠጣው እየሞከረ…… ማብቂያ የሌለው ከሚመስል የሰዓታት ዝምታና ብቸኝነት በኋላ ከአባቱ አጠገብ ተቀምጦ ስለ እናቱና ስለራሱ ማውራት ሆኗል ልምዱ…… አየኸኝ ባይመልስለትም ልጁ አጠገቡ ተቀምጦ እየደባበሰ ያለማቋረጥ ሲያወራው ፊቱ ይፈግጋል። ………

"…… እኩያዬ እኮ ነው። …… ስላሸነፍኩት አባቱ ተደርቦ ገፈተረኝ እና እግሬ ወለም አለኝ።…… ከዛ አባቴን ካልወለድሽ ብዬ እህል አልቀምስም አልኳት።……" በትውስታው ፈገግ ብሎ ቀጠለ "…… አለቀሰች። ለመጀመሪያም ለመጨረሻም ጊዜ በአንተ ስትመረር የሰማሁት ያኔ ነው። …… አሳዘነችኝ። ……"

በሩ ላይ ቆሜ እሰማዋለሁ። ……

"በቃ እረፍ ትንሽ…… በወሬ አደከምሁህ" ብሎ ሊነሳ ሲል አየኸኝ ፊቱ ተከፋ……

"ትንሽዬ ተኛና ደግሞ አጫውትሃለሁ።" ብሎ የአባቱን እጅ ሳመው……

የተቀሩት ቀናት እንደዚህ አለፉ። ……

"ወንድሞች እንደነበሩህ ነግሮህ ነበር?" አልኩት የሆነ ቀን

"ምንም አልነገረኝም። ምንም አልጠየቅኩትም ነበር።" መለሰልኝ በጉጉት ። ያጫወተኝን በሙሉ ነገርኩት። ቃል ሳይተነፍስ ሰማኝ።

"ምስኪን አባቴን!" አለ ተነስቶ ወደ አባቱ ክፍል እየሄደ። ……

"የሰው ልጅ ተፈጥሮ ፈጣሪውን ነው የሚመስል፣ መልካም ነው። በህይወቱ በሚያልፋ ክፉና መልካም ተጎዳኝ ክስተቶች ክፉ ይሆናል እንጂ በተፈጥሮ የከፋ ሰው የለም።" ይለኝ ነበር አባዬ

ያሬድን አስቤ የገባኝ ይሄ ነው።በህይወቱ ያለፉ መከራዎች ሁሉ መንስኤ የአባቱ እናቱን ማስረገዝ እንደሆነ ነው የሚያምነው። …… ላለመማሩ እና የገጠር ወጣት ሆኖ ለመቅረቱ መንስኤ አባቱ እሱን አለመፈለጉ እንደሆነ… …… እሱ አቅሙ ደርሶ አርሶ መዝራት እስኪችል ከእናቱ ጋር በጥልቅ ድህነት ዘመናቸውን ገፍተዋል። …… ለሁሉም ምክንያት የሚያደርገው አባቱን ነው። ……

አባቱ ሊሞት መሆኑን ሲሰማ ምሬቱን ረሳው፣ ያለፈ መከራውን ተወው…… መከፋቱን ዘንግቶ ለአባቱ አለቀሰለት።……

ድምፁን የሰማሁ ስለመሰለኝ ተነስቼ ወደ አየኸኝ ክፍል ገባሁ። ያሬድ መሬቱ ላይ ተንበርክኮ ድምፅ አልባ ለቅሶ ሲያለቅስ ደረስኩ። …… ያንን ሞቴን የቀማኝን የአየኸኝ ለቅሶ የመሰለ መንሰቅሰቅ…… ያን እንባ የሚቀማ ለቅሶ የመሰለ ፍቅፍቅታ… … እራሱን አባቱን ይመስላል። …… አንጀት የሚያላውስ አይነት… …  የተፈጠረው ገባኝ። …… እሪ አልኩ። …… ድንኳን ተቀምጦ የቅርብ ወዳጁ እያለቀሰ እንደደረሰው ለቀስተኛ የኔን እሪታ ሲሰማ የሚይዘው አሳጣው። …… ኡኡ ብሎ አለቀሰ። …… በለቅሶና በእንባ ብዛት የራስን ሀዘን ያራግፉታል እንጂ ለአየኸኝ የነፍስ ስንቅ አይሆን ነገር ተላቀስነው……

ይህ የአየኸኝ ህይወት ፍፃሜ ነበር። የእኔ ህይወት ጅማሬ…… የያሬድም ሌላ የህይወት ምዕራፍ ጅማሬ…… ወዳጅ ነኝ ያለ በተሰበሰበበት ተቀበረ። ……
………
………
……
አየኸኝ ከሞተ ወዲያ አዲሳባ መቀመጡ ምንም ስላልተመቸኝ ወደ ቀዬዬ ከተመለስኩ ሰነባበትኩ። ያሬድም ጠበቃው የንብረት ክፍፍሉን ጉዳይ ፈር እስኪያሲዝ እናቱን ይዞ ሊመለስ ወደ ቀዬው ወረደ። ጠበቃው እንደነገሩኝ ከሆነ እውነት የማይመስል ንብረት ባለቤት ሆኛለሁ። በእርግጥ ምንም ላልነበራት ሴት ይሄ ሁሉ ምኗ ይሆናል?  ……

አዲስ ህይወት እጀምራለሁ? አዲስ አበባ እገባለሁ? የምጀምረው ህይወት ደስተኛ ያደርገኛል? አዲስ የኑሮ ልምድን ካልተለማመድኩ ይሄ ሁሉ ንብረት በዛች በእርምጃ በምትለካ ቀዬዬ ምን አደርግበታለሁ? …… የቱንም አውቆ መወሰን አቃተኝ እና ማሰቡንም ተውኩት።……
……
……

ጠበቃው ያዘመመች ጎጆዬ ድረስ ሲመጣ ወራት መንጎዳቸው ገባኝ። …… የነገረኝን የገንዘቤን መጠን የኔታ አላስቆጠሩኝም። … እንኳን ልሾፍረው አዲስ አበባ ስሄድ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳፈርኩበትን መኪና… … የመኪና ባለቤት መሆኔን ነገረኝ። ……
…… የአየኸኝ ኑዛዜ ያለውን ንብረት በሙሉ እኩል ካካፈለ በኋላ ቤቱንም እንድንካፈል ያዛል። ……

"ያሬድ ሊያማክርሽ ይፈልጋል ወደ አዲስ አበባ መሄድ አለብን!" አለኝ ጠበቃው… 

እዚህም ብቀመጥ የምፈትለው ጉዳይ ስላልነበረኝ ተስማማሁ። ……
……
……
………
ያሬድን ሳገኘው እንደ አብሮ አደግ ወዳጅ ተሰማኝ። በሰፊ እጆቹ አጀብ ደረቱ ላይ ቆየሁ። …… የምን እንደሆነ ያለየሁት ለቅሶ አለቀስኩ። አባበለኝ። …… እናቱ ተቆጥተው ለቅሶዬን አስቆሙኝ… …

"ምን አሰብሽ?" አለኝ በሁለተኛው ቀን ሲመሻሽ ገደማ

"ምን ላስብ?"

"የሌላው ንብረት በግልፅ ስለተካፈለ አስቸጋሪ አይደለም። ቤቱን እንዴት እናድርገው?" አለኝ

"ኸረ ሌላው ገንዘብ ይበቃኛል። ቤቱን ከእናትህ ጋር ኑሩበት። አይሸጥም።" መለስኩለት

"እንዲህ እንድትዪኝ አይደለም።" አለኝ ቅር እየተሰኘ

"ያለው መፍትሄ ምንድነው? ሸጦ መካፈል አይደል? ወይም አንዳችን የአንዳችንን ድርሻ ከፍሎ ቤቱን መጠቅለል? እኔ ካንተ ገንዘብ ተቀብዬ ቤቱን አልሸጥልህም። ተቃራኒውንም አላደርግም። ……"

"ሌላ መላ አይኖርም?" አሉ እናትየው የያሬድን አይን አይኖች እያዩ… … አስቀድመው የፈተሉት ወግ እንዳለ ያስታውቅባቸዋል።

"ምን አስባችሁ ነው?" አልኳቸው ተራ በተራ እያየኋቸው።

"ለምን አብረሽኝ አትኖሪም?" ሲል አይኖቹ አላዩኝም። ድምፁ ውስጥ ጥያቄ አይደለም ያለው… … ልመና ነበር። …… አብሮ መኖር…… አብሮ ከያሬድ ጋር መኖር……

"ባክሽ አትመለሽ?" አለ ቀጠለና… …

"በኔ ይሁንብሽ ልጄ… … ሞክረሽ ካልሆነ የፈለግሽው ይሆናል።" አሉኝ እናትየው

"እሺ!!" አልኩኝ በደመነፍስ ወዲያው ‘ምኑን?‘ ብባል መልሱን የማውቀው አይመስለኝም።

ያሬድ ከተቀመጠበት ተነስቶ እጆቼን እያገላበጠ ሳመኝ። እናትየው በእልልታ ቤቱን አቀወሱት። ይሄኔ እዚህ ቤት አብሮ ከመኖር ያለፈ የተጨዋወቱት ፈትል እንዳለ ገባኝ። ……
……
………
አሁን ጨርሰናል።
(ከበዛ ክብርና ነፍፍፍፍፍ ፍቅር ጋር!!!!!)

@wegoch
@wegoch
@paappii
#ስቅለት ወ ኮሮና

በእለተ ሀሙስ በፀሎተ ሀሙስ ከቤተክስቲያን መጥቼ በፆም የቆየ ሆዴን እንኳን ምግብ አልሰጠሁትም
እንዴት አንድ በሽታ ተፈርቶ ህጉ ተጥሶ እግሬን ሳልታጠብ በረከት ሳለገኝ መጣሁ እያልኩ እየተብሰለሰልኩኝ ነው
ዛሬ ይህ ስርዓት እንዴት ይቀራል ዶግማዋ ቀኖናዋ እንዴት ይሻራል
እረ ወዲያ......
ታጠቡ ታጠቡ ይሉናል ዛሬ እጠቡን ስንል ደሞ እምቢ
ከሳኒታይዘሩና ከሳሙናው በላይ የዛሬ ምንኛ ሚያነፃ በሆነልን ነበር
ማቆያ ገቡ የተባሉትን ሰዎች ሰብስቦ በዛሬው ስርአት በወይኑ እና በወይራው ቅጠል ቢታጠቡ አደለም ኮሮና ተብዬ ሌላም ነገር ብን ብሎ ነበር ሚጠፋው
ብቻዬን እንደ እብድ ስብሰለሰል የበሬ መንኳኳት ነው ያነቃኝ
ልጅ አቤሴሎም ና ጉልባን ብላ ቡናውም ደርሷል
የአከራዬ ልጅ ትለፈልፋለች
ወጣ አልኩና ወደ አከራዬ ቤት አቀናሁ
ምግብ ባልበላ አንጀቴ ኮሮና በሚባል ሰይጣን በጎደፈው ስርአት የተቃጠለው ቆሽቴ ላይ እንባ ሚያራጭ ሚጥሚታ የተቀላቀለበት ጉልባን ቀረበልኝ እሱን አይበላሁ ቡናዬን እየጠጣሁ ከአከራዬ ቤተሰቦች ጋ ወግ ያለው ጨዋታ ስንጫወት አመሸን
እኔም ስለደከመኝ ሰላም እደሩ ምኞቴን ተናግሬ ወደ ቀዝቃዛዋ ጎጆዬ ተመለስኩኝ
በሬን ዘግቼ አልጋዬ ላይ ተዘረጋሁ
ኮሮና ኮሮና ኮሮና ይህን ቃል ቀን በቀን ከመስማቴ የተነሳ ኮሮና ሲባል አቤት ማለት ጀምሬያለሁ ሁለተኛ የአለም ስም ሆኑአል
መሳሳም መተቃቀፍ አሁንስ ናፈቀኝ
ብሶቴን ማውጫ ገፄን ገንጥዬ መቸክቸክ ጀመርኩ

በጌቴ ሴማኒ
ይሁዳ ጌታን አሳልፎ ሲሰጥ ምልክት እንዲሆናቸው ዘንድ ጌታን አቅፎ ስሞታል
እኔም በዚ በዘመኔ ወደ ጌቴ ሰማኒ ሄጄ ሚመስለኝን እንዲህ አልኩ......
የአለም መከራ የሰው ሁሉ ሀጢያት ማብቂያ ሊያገኝ ሲል መሳሳምና መተቃቀፍ አለም ላይ ይቆማል
የአለም መዳኛ በመሳሙ ብቻ ተለይቶ ወቶ ስቃይን ስላየ ትንሳኤው እስኪሆን የዛ ዘመን ሰዎች መሳም መተቃቀፍ ያቆሙ ይመስለኛል
ለዛም ነው ትልቅ ደስታ ከፊታችን ሲመጣ ብዙ ፈተናዎች ሚገጥሙን
በዚ በኛ ዘመን ትንሳኤን ለማየት መሳሳሙ ቆሙአል
በጌቴ ሴማኒ ይሁዳ ጌታዬን ሲስመው ምልክት ሰቶአቸው ይገፉት ጀመረ ፈሪሳውያን በሰውኛ አቅማቸው
ጌታ መገፋት ሲጀምር የሰው ሁሉ ሀጢያት ከመዝገቡ ገፅ ይፋቅለት ስለጀመረ
አሁንም መሳሳም ያቆምነው መተቃቀፉ የቀረብን ጠግበን ማንጨርሰው ደስታ ከፊታችን እየመጣ ነው ብዬ አስብኩ
እነሱን አይመለከትም ወዲ ነው እናንተዬ
ይህን ካልኩ ይበቃኛል
መስገድም አቁሙ ሳይሉን በፊት ቶሎ ይህን ሳምንት በሰላም ያስጨርሰን
በሀሙስ ምሽት ለአርብ አጥቢያ ስለሆነ ተየፃፈው
                 መልካም ስቅለት
                    ብላቴናው
----Edited----
#ስቅለት ወ ኮሮና

በእለተ ሀሙስ በፀሎተ ሀሙስ ከቤተክስቲያን መጥቼ በፆም የቆየ ሆዴን እንኳን ምግብ አልሰጠሁትም
እንዴት አንድ በሽታ ተፈርቶ ህጉ ተጥሶ እግሬን ሳልታጠብ በረከት ሳለገኝ መጣሁ እያልኩ እየተብሰለሰልኩኝ ነው
ዛሬ ይህ ስርዓት እንዴት ይቀራል ዶግማዋ ቀኖናዋ እንዴት ይሻራል
እረ ወዲያ......
ታጠቡ ታጠቡ ይሉናል ዛሬ እጠቡን ስንል ደሞ እምቢ
ከሳኒታይዘሩና ከሳሙናው በላይ የዛሬ ምንኛ ሚያነፃ በሆነልን ነበር
ማቆያ ገቡ የተባሉትን ሰዎች ሰብስቦ በዛሬው ስርአት በወይኑ እና በወይራው ቅጠል ቢታጠቡ አደለም ኮሮና ተብዬ ሌላም ነገር ብን ብሎ ነበር ሚጠፋው
ብቻዬን እንደ እብድ ስብሰለሰል የበሬ መንኳኳት ነው ያነቃኝ
ልጅ አቤሴሎም ና ጉልባን ብላ ቡናውም ደርሷል
የአከራዬ ልጅ ትለፈልፋለች
ወጣ አልኩና ወደ አከራዬ ቤት አቀናሁ
ምግብ ባልበላ አንጀቴ ኮሮና በሚባል ሰይጣን በጎደፈው ስርአት የተቃጠለው ቆሽቴ ላይ እንባ ሚያራጭ ሚጥሚታ የተቀላቀለበት ጉልባን ቀረበልኝ እሱን አይበላሁ ቡናዬን እየጠጣሁ ከአከራዬ ቤተሰቦች ጋ ወግ ያለው ጨዋታ ስንጫወት አመሸን
እኔም ስለደከመኝ ሰላም እደሩ ምኞቴን ተናግሬ ወደ ቀዝቃዛዋ ጎጆዬ ተመለስኩኝ
በሬን ዘግቼ አልጋዬ ላይ ተዘረጋሁ
ኮሮና ኮሮና ኮሮና ይህን ቃል ቀን በቀን ከመስማቴ የተነሳ ኮሮና ሲባል አቤት ማለት ጀምሬያለሁ ሁለተኛ የአለም ስም ሆኑአል
መሳሳም መተቃቀፍ አሁንስ ናፈቀኝ
ብሶቴን ማውጫ ገፄን ገንጥዬ መቸክቸክ ጀመርኩ

በጌቴ ሴማኒ
ይሁዳ ጌታን አሳልፎ ሲሰጥ ምልክት እንዲሆናቸው ዘንድ ጌታን አቅፎ ስሞታል
እኔም በዚ በዘመኔ ወደ ጌቴ ሰማኒ ሄጄ ሚመስለኝን እንዲህ አልኩ......
የአለም መከራ የሰው ሁሉ ሀጢያት ማብቂያ ሊያገኝ ሲል መሳሳምና መተቃቀፍ አለም ላይ ይቆማል
የአለም መዳኛ በመሳሙ ብቻ ተለይቶ ወቶ ስቃይን ስላየ ትንሳኤው እስኪሆን የዛ ዘመን ሰዎች መሳም መተቃቀፍ ያቆሙ ይመስለኛል
ለዛም ነው ትልቅ ደስታ ከፊታችን ሲመጣ ብዙ ፈተናዎች ሚገጥሙን
በዚ በኛ ዘመን ትንሳኤን ለማየት መሳሳሙ ቆሙአል
በጌቴ ሴማኒ ይሁዳ ጌታዬን ሲስመው ምልክት ሰቶአቸው ይገፉት ጀመረ ፈሪሳውያን በሰውኛ አቅማቸው
ጌታ መገፋት ሲጀምር የሰው ሁሉ ሀጢያት ከመዝገቡ ገፅ ይፋቅለት ስለጀመረ
አሁንም መሳሳም ያቆምነው መተቃቀፉ የቀረብን ጠግበን ማንጨርሰው ደስታ ከፊታችን እየመጣ ነው ብዬ አስብኩ
እነሱን አይመለከትም ወዲ ነው እናንተዬ
ይህን ካልኩ ይበቃኛል
መስገድም አቁሙ ሳይሉን በፊት ቶሎ ይህን ሳምንት በሰላም ያስጨርሰን
በሀሙስ ምሽት ለአርብ አጥቢያ ስለሆነ ተየፃፈው
               መልካም የስቅለትበዓል
                    ብላቴናው
@wegoch
@wegoch
@wegoch
#የደሜ ዜመኞች

ክፍል - ፬
ቀጥያለሁ ......

የዛሬዋ ማለዳ ምንኛ ትለያለች ካየሁዋቸው ማለዳዎች ይቺ ለየት ሳትል አትቀርም
በማለዳ ዜማ ገና በማለደው እንደ ማለዳዋ ጮራ የፈካችው ልጅ ከፊት ለፊቴ ቆማለች
ዛሬም ያ እረጅም ፀጉር ይበልጥ አምሮበታል ከለበሰችው ጥቁር ጃኬት ጋ በቃ ዝም ነው
በዛች ትንሽ ንግግር ውስጥ እኔጋ ብዙ ስሜቶች ገብተዋል እኔም እንደመጣች ከእቅፌ አስገባሁዋት
ሌላ ስሜት ወደ ውስጤ ሲገባ ተሰማኝ
 እቅፍ አደረኩዋት
ጠረኗ ዛሬም አልተቀየረም እራሷ ተጠምጥማ ያሸተትኩትን ጠረን ዛሬ እኔ ተጠምጥሜባት መልሼ እያሸተትኩት ነው
በጣቶቹአ የያዘችውን ብር ከደረት ኪሰ ከተተችልኝ
መተቃቀፉ አበቃ     
ኤጭ.....
     እየው ኮሚሽኔ ከዛሬ ጀምሮ ይታሰብልኝ ደሞ ወደህ ነው ማታስብልኝ እኔ በአንድ ስራ ብቻ ትንሽ ነገር መውሰድ ስለማልፈልግ ነው እሺ ሙሉ ብሩን የሰጠሁህ
ያ የማውራት ፍጠነቱአ ዛሬም አልቆመም
አይኔ ከንፈሯ ላይ ነው
እና አጋሮች ሆነናላ ተስማምተናል አይደል 
አፌን ምን እንደለጎመኝ አላውቅም አይኔን ከከንፈሯ ነቅዬ አይኗ ላይ ተከልኩት ትክ ብዬ እያየሁዋት አንገቴን በአዎንታ ነቀነኩላት
በኔ ዝምታ ውስጥ ትልቅ ጩኸት አለ
መልሴ አስደሰታት መሰለኝ ደስ የሚል ትንሽዬ ፈገግታ ሰታኝ ቻው አለቺኝ
እቅፉአን ናፈኩት
ድንገት ከሄደችበት ተንደርድራ መታ ከንፈሯን ጉንጮቼ ላይ አሳረፈቻቸው
ኡፋ በአባባ ሞት
በዚች ማለዳ ውስጤን ያጠልቀለቀ ሀሴት ሲገባ ተሰማኝ
እርቃ ሳቴድ ታድያ ምሳ ልጋብዝሽ አልኩዋት
ቡና ይሁንልኝ ..... መለሰችልኝ
አቤት ፍጥነቷ
ፍጥነቷን ተጠቅማ ሳይሆን አይቀርም ከስሜቴ ዘላ እንዲህ በፍጥነት የገባችው
እጄ ከንፈሯ ያረፈበት ጉንጬ ላይ ነው አጣብቄው ቀርቻለው
ፍዝዝ ድንዝዝ ........
የልቤ በራፍ ሰተት ብሎ ሲከፈት ተሰማኝ በልቤ አዳራሽ እንድትገባ እኔም ፈቀድኩላት
በሩን ቶሎ አልዘጋሁትም
ምን ልበላችሁ በቃ ልዩ ሆነቺብኛ ምን አባቴ ላርግ
በፍላጎቴ ሰው ለመውደድ ስሞክር ታወቀኝ
ብዙ ጊዜ ፍቅር ሲይዘን ሁሌ ሳናስበውና ሳናስተውለው ስለሆነ ፍቅር እሱ እራሱ ሚታዘበን ይመስላል
እንዲህ ደሞ በፍላጎት ሲሆን በረከቱ እራሱ ሚበዛ ይመስለኛል
እናንተዬ ብዙ አሶራችሁኝ እኮ
እስቲ እቺን ጀባ ልበላችሁ እኔም ጠብታዎቼን ላፅዳ
                   የልቤን አዳራሽ መኖሪያ አርገዋለች
                  ወይስ የምሯን ነው ወይ ትቀልዳለች
                  ከልቤ አዳራሽ ውስጥ ሰተት ብላ ገብታ
                  ውስጥ የነበሩን በሙሉ አሶጥታ
                             መልካሙ ተበጀ ነው በፍላጎቴ አዳራሼን ከፍቼ ልቤን ልበላ ነው
ከትዝታዬ ተመልሻለሁ
ትንሽ የሙዚቃዋን ድምፅ ቀነስ አድርጉአት
ልቤም የአዳራሹን በር መክፈቱን እንጂ በየትኛው ቁልፍ ተዘግቶ ቁልፉን ከየት እንደጣለው ማያውቀው
ለዛም ነው በዘህ አሁን ባለሁበት ሁኔታ የልቤን አዳራሽ ከፍቼ ውስጡ ያለችውን ሰው ጎትቼ ማውጣት ያቃተኝ
ምክንያቱም ቁልፉ እኔጋ ስለሌ
አንዴ ከተዘጋ የልብን በር መክፈቻ ቁልፍ ማግኘት ይከብዳል
ቁልፉም አንዴ ብቻ ነው መሰል ለመክፈቻነት ሚያገለግለው
ለዛም ነው ብዙ ከፋቾች ወደ በራችን በር ሲመጡ በሩን መክፈት ሚከብዳቸው
የዘጋው መልሶ ከፍቶ ካልወጣ ከውጪ ሆኖ ማንም ሊከፍተው አይችልም
እሷም መልሳ እንዳቶጣ ከዚ ዘንድ የለችም
እሷ ግን የት ናት ወደትዝታዬ ስመለስ አወጋቹሀለሁ
   
                 
                እመለሳለሁ.....
            ብላቴናው በደም ቀለም
         
@wegoch
@wegoch
@wegoch
ታሪከ ብዙ በሆነችዉ መንደሬ ሳዘግም አለማየዉ ቤቱን ያቀፈዉ ዉሃ ልክ ለይ
ቁጭ ብሏል። የመንደራችን ቤቶች አጥር ስለሌላቸዉ የየቤቱ ዉሃ ልክ እንደ
ባለጌ ወንበር ቁጭ ብሎ መቆዘሚያ፤ መገርመሚያ ነዉ። "ምነዉ ብቻህን?" ሁሌም ብቻዉን እንደሚቀመጥ ባዉቅም እንደመግቢያ ጠየኩት፤ እስክደነግጥ ድረስ ትክ ብሎ ካየኝ በኃላ " ሰዉ ብቻዉን ሆኖ አያዉቅም!" አለ ክርር ባለ ድምፅ። በዝምታዬ እንዲያወራ ጋበዝኩት "አየህ የእኔም ያንተም ማንነት ከሌሎች ሰዎች ተዋጥቶ ነዉ እኛን የሰራን ፤የሌሎች ስብዕናን ቅንጥብጣቢ የተሸከምን ነን። እንዴት በለኝ?" ካልጠየኩት እንደማይቀጥል ከልምዴ ስለማዉቅ " እንዴት ?" አልኩት ፤ " አየህ ከሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት ዉስጥ እኛነታችን የሚዋቀረዉ ፤ ቀድማ ጭንቅላትህ ዉስጥ በተፈጠረች ትንሽዬ ጄኔቲክሳዊ እዉቀት ለይ ተንተርሰህ ከሰዎች ባህሪን በሶስት መንገድ ትቀዳለህ። የመጀመሪያዉ እንዳለ መቀበል ሲሆ ን ፤ልክ እንደመዉረስ በለዉ ። ሁለተኛዉ መቃወም ሲሆን ካየሀዉ ባህሪ ዉጭ የሆነ ተቃራኒ ባህሪን መከተል ነዉ። ሶስተኛዉ ደሞ ከመቀበልም ከመቃወምም ዉጭ በሆነ አማራጭ ማዝገም ነዉ።" ቀና ብሎ አይቶኝ ቀጠለ። "አየህ እኔ ዉስጥ በዚህ መልክ የተቀበልኳቸዉ የተደላደሉ የሌሎች ሰዎች ባህሪዎች አሉ። እኔ የጭምቷእናቴ፤ የኮስታራዉ አባቴ፣ የጉራማይሌ ቤተሰቤ ፤
የጉራማይሌ ጎረቤቴ ፤ የጉራማይሌ መንደሬ፣ የጉራማይሌ ሀገሬ ፣ የጉራማይሌ አለሜ... የነዚህ ሁሉ ድምር ነኝ። ብቻዬን ሆኜ አላዉቅም! ብቸኝነቴ ዉስጥ የተከተቱ ፤የትየለለሌ ሰዎች አሉ፤ህልቆ መሳፍርት የሆኑ ።ምናልባት ማዉቃቸዉ ምናልባትም ማላዉቃቸዉ፣ ምናልባት እያወቅኩ ማላዉቃቸዉ ፣ ምናልባት ሳላዉቅም ማዉቃቸዉ ... ብቻ እነሱ ሁሉ እኔ ዉስጥ ተከተዋል። 'እኔ' የሚባል ነገር ካለ ከነሱ የስብዕና ትብታብ ለይ ሰበዝ እየተመዘዘ ነዉ ፤ 'እኔ' 'እኔ' የሆንኩት።እና ሰዉ ብቻዉን ሆኖ አያዉቅም! " ለአንድ ጥያቄ እንዲህ ያለ ሰፊ መልስ ሲሰጠኝ አንዴ እያዛጋዉ፣ አንዴ መሬት አንዴ ሰማይ ሳይ ቆይቼ(ሰማይ ግን ለምን ሰማያዊ ሆነ? ጥቁር የሀዘን፤ ነጭ የደስታ ፤ ቀይ የመስዋዕትነት... ሰማያዊስ?) እንደ ጨረሰ ተነስቼ ሄድኩ። ምናባቱ ይለፋደዳል! ብሽቅ

@wegoch
@wegoch
@wegoch

#nicola nas
#የደሜ ዜመኞች

ክፍል - ፭
ቀጥያለሁ.....

ወደ ትዝታዬ ሚገፋኝ እህህህ ብሎ ሚሰማኝ ስለሆን አብራችሁኝ ፍሰሱ
ከዚ ዘንድ የሌለችው የኔ አለም ከየትኛው ቦታ ወደ የትኛው ሌላ አለም እንደገባች በደንብ አውቃለሁ
አዎ ከኔ አለም ወደ ሌላ አለም
እሷ ያለችበትን አለም ቶሎ መናገር አልፈልግም የሷን አለም መገኛውን ምነግራችሁ እኔም ወደዛ ለመሄድ መንገድ ስጀምር ነው
ለጊዜው ብዙ ምነግራችሁ ውብ ትዝታዎች አሉኝ
ወደ ትዝታዬ ተመልሻለሁ
ቅደም የተለያየንበት ቦታ ሁለታችንም እኩል ተገናኝተናል እሷም ወደ እኔ እኔም ወደ እሷ በፍቅር መላእክቶች ጠሪነት
ቁጥብ ፈገግታዋና ችኩልነቷ ተደምረው በቃ መፍዘዝ ሆኑአል ስራዬ
ወደ ቡናችን እንሂድ ፈጠን ብላ አነቃቺኝ
የቅደሚ እጄን ወደ ፊት ዘረጋሁላት ግድ የለም ቅደም ወደ ፊት ገፋችኝ
ታስገርመኝ ጀምሯል አይኔ አይኗ ላይ ነው
ጀርባዬን ትመታኛለች ከደረጃዎቹ ስንወርድ እጆቼን ትጎትተኛለች በቃ
ደስ የሚል ስቃይ.......
ባለፍንበት መንገድ ሁሉ ኢስኮና ፊያሜታ ሆኑአል ወሬው
እስከ ዚች ሰአት ድረስ ስሟን አልጠየኩዋትም ፊያሜታ መሆኑአን ያወኩት ጓደኛዬ ጠበቅ አርጋት የወንዱ ሁሉ አይን እሷ ላይ ብሎ የነገረኝ ሰአት ነው
ቡናችንን አዘን ቁጭ ብለን ደስ የሚል ጨዋታ ላይ ነን
ቆንጆ የቡና ሱሰኛ ናት ለነገሩ እኔም ካልጠጣሁ አይሆንልኝም
ስምሽ ግን ማነው በወሬያችን መሀል እንዳላወቀ ሆኜ ጥያቄዬን ወረወርኩላት
ፊያሜታ እባላለሁ ችኩል ብላ ተነስታ እጇን ዘረጋችልኝ
ምን አይነት እብደት ነው በጣም አሳቀቺኝ
ደስ አለኝ በቃ
እጄን ዘርግቼ ሰላምታዬን ስሰጣት መልሳ ከጎኔ ተቀመጠች
አይኖች ሁሉ ወደ እኛ ናቸው በቃ
የተማሪው አፍ በእኛ ወሬ ተጠምዶ ቡናው በስቅታ ነው የጨረስነው
እኔ ምልህ አይኗን ወደ አይኔ ተክላ እንዲህ ታዋቂ ነህ እንዴ ደሞ ተወዳጅ በዛ ላይ ቆንጆ
አቤት አቤት አረ አታሽኮርምሚኝ ጨዋታችን ሳቅ ብቻ ሆነ
ይልቅ አሁን ወደ ስራ በል ተነስ ተነስ የጠጣንበትን ሲኒ መልሰን ተነስተን ሄድን
ወደ ክፍሏ ይዛኝ ሄደች
ገባን በሩን ጥርቅም አደረገችው
ቡናው አስክሯት ነው መሰል ዝም ብላ ትስቃለች
ቁጥብ ፈገግታዋ ተቀይሮ እንዲህ ስትስቅ ሳያት ማላውቀው ስሜት ይነዝረኝ ጀመር
ዴስኮቹ ላይ ተቀመጥን በስራዬ ቀልጣፋና ፈጣን መሆኔን በባለፈው ስራዬ ተረድተሀል አይደል
ምንም እንደታስብ ጭራሽ በቃ 60% የትምህርት ቤቱን ሴት በእቅድህ አስገባልሀለሁ
በባለፈው የሰገሁሽ ሙሉ በሴቶች ነው ያለቀው ገርሞኝ ጥያቄዬን ወረወርኩላት
አዎና አለቺኝ.....
አንተ ከላይ አለክ ከበታችህ ብዙ ሰዎች እኔ ግን ከሁሉም በላይ አስፈልግሀለሁ በራስ መተማመኗ አስገረመኝ
ስለዚህ ሀሳብ አይግባህ ኢስኮዬ የሸሚዜን ኮሌታ ጨምድዳ ይዛ ይበልጥ ተጠጋችኝ ከመቀራረባችን የተነሳ በአይኗ ብሌን መልኬን አየሁት አይኗ ውብ ነው የሆነ ሀይል ያለው አካል
ትንፋሿ አጋለኝ ይበልጥ ተጠጋጋን አፍንጫዎቻችን እስኪነካኩ ድረስ መጠጋጋታችን አላቆመም ቀይ ፊቷ እዛው እያየሁት በርበሬ መሰለ እጆቼን ወደ አንገቷ ላኩት
እንቅ አደረኩዋት
አየር ሳንስብ ሁለታችንም አየር ተሰጣጠን ትንፋሽ የለም ቆዳዬን ትኩሱ ትንፋሿ ይገርፈው ጀመር
ያንን ከንፈር በቃ.......
እናንተዬ ኑ ተመለሱ በቃ ስቃዬን አበዛችሁት እኮ ትንሽ ዜማ እንስማ እንጂ እኔም ጠብታዎቼን እንደተለመደው ላፅዳ
                    ድንቅ ልጅ ድንቅ ነው ውበትሽ
                    ከዋክብት ናቸው አይኖችሽ
                   አቤት ቅርፀ ስራው የከናፍርሽ
                  ፈገግማ ስትይ ሌላ ነው ጥርስሽ
                          መሀሙድን ከፈትኩላችሁ
አዎና ማንም ምንም ብዬ ባልሰየምኩአት ልጅ የማላውቀው ስሜት ውስጥ ተወርውሬያለሁ
ማን ምን ብለን ሳንጠይቅ ሚሰማን ፍቅር ነው ሌላ ልዩ አለም ውስጥ ሚከተን በቃ እኔም እዛ ልዩ አለም ውስጥ ነበርኩኝ እንዲህ ትዝታን ብቻ ታቅፌ ከመቀመጤ በፊት
አሁንማ ልዩ አለም ውስጥ ሳልሆን ልዩ ስቃይ ውስጥ ነኝ
ወደ ትዝታዬ እመለሳለሁ ......

                 እቀጥላለሁ
        ብላቴናው በደም ቀለም
 
@Wegoch
@wegoch
@wegoch
የ Dereje Senay ባለቤት ደውላልኝ ስለነበር በዛውም ደረጄ የገዛት በግን ለማየት ቤቱ ሄጄ ነበር ። ደሬ ወገቡን ይዞ እየተንጎራደደ መንኮራኩር ሊያመጥቅ እንደተዘጋጀ ሳይንቲስት :) ትንሽ በተመስጦ ሲያብሰለስል ቆየና 

"ይገርምሀል ይሄ በግ እንደ ሌሎቹ በጎች ተራ በግ አይደለም...እንዲሁ ትኩር ብዬ ስመለከተው ትምህርቱን ሚኒስትሪ ተፈትኖ ያቆመ ይመስለኛል😃" አለኝ።

"ደሬ በጉ ነው የተማረው? " አልኩት የሰማሁትን ባለማመን 

"Yeah Definately !..." ...

"እያወራህ ያለኸው ነገር አልገባኝም "

"This is beyond Nature.. .ከተፈጥሮ ክንውኖች ውጭ የሆነ ክስተት ነው።...ለምን ይሄን እንዳልኩህ ታውቃለህ ?

ለበግ ሻጩ ቀለል አድርጌ ለበጉ 3000 ብር አይበቃውም ወይ? ብዬ ስጠይቀው በጉ ኮስተር ብሎ ገላመጠኝ....ሃሃሃ...በግ ሲገላመጥ ከዚህ ቀደም በዓለም ታይቶ ይታወቃል? ...ደግሞ መገላመጡስ ይሁን 3000 ብር ትንሽ ብር መሆኑን እንዴት ሊያውቅ ቻለ ?"

የደሬ ደህንነት ግራ አጋብቶኝ ትኩር ብዬ ሳየው ቆይቼ 

"እኔ ምልህ? ...ያ በዓል ሲደርስ አዕምሮዬን የሚያቀዣብረኝ በሽታ አለብኝ ያልከኝ ነገር አልተሻለህም ማለት ነው?" ...

"ያመኝ ነበር እንዴ?"

"አዎ ! ድብን አድርጎ ያምሀል ... ገንዘብ ስታወጣ የመርሳት ችግር እንዳለብህ ከዚህ ቀደም ነግረኸኛል "

"...እንዴት እንዲህ ትለኛለህ? " ቱግ ብሎ ጠየቀኝ።

"እና የተማረ በግ ገዛሁ ስትል ትንሽ አታፍርም ?...ጭራሽ ቁጥር የሚያውቅ በግ ገዛሁ እኮ ነው ያልከኝ! "

"ማ ...እኔ? ...

ሆ!...እኔ እኔና አንተ ከተገናኘንባት ቅፅበት አንስቶ ስለ በግ አውርቻለሁ ? "

ደሬ በሁኔታው ፈፅሞ አሳዘነኝ። እሱ ከቆመበት አለፍ ብላ የጠባብ ክፍላቸውን በር ደፍ ተደግፋ ወደ ቆመችው ምስኪን ባለቤቱ ተጠግቼ ...

"ደሬ ምን ሆኗል? " አልኳት.. .

"ቅድም ከ Assaye derbe ጋር በግ እንግዛ ብሎ ወትቶ ነበር ። በጉን ገዝተው ሲመለሱ አሳዬ ጠርቶኝ ባለቤትሽ ገብዘብ ካወጣ በኋላ ትክክል ስላልሆነ ገብቶ ይረፍ ብሎኝ ነበር ። ቢጨንቀኝ እኮ ላንተም ደውዬ ቤት እንድትመጣ ያደረኩህ ሚኪ?" ...እንባዎቿ በመንታ አይኖቿ በኩል ቁልቁል ተምዘገዘጉ ..

ባለቤቱ ስላሳዘነችኝ እቅፍ አድርጌ አፅናናኋት! ..." ደረጄ ድንገት የዛሬ ወጪውን ሲረሳው ወደ ቀድሞ ማንነቱ ሊመለስ ስለሚችል አትረበሺ ...ዛሬን አይተነው ...የሚብስበት ከሆነ ነገ ህክምና እንወስደዋለን። እኔም እኮ ሳዋራው የተማረ በግ ገዛሁ ምናምን እያለኝ ነበር ። አልኳት.. .

"የሚሻለው ይመስለኛል ። ግድ የለሽም ይሻለዋል.. .ቅድምም ሳዋራው እኮ ትንሽ የመርሳት በሽታው መለስ እያለለት ነበር" 

ዋሽተህ አስታርቅ በሚለው የአባቶች ብሂል ፈርቀዳጅነት  ተነሳስቼ ዋሽቼ ላፅናናት ሞከርኩ ።

"እርግጠኛ ነህ ተሽሎታል ?" 

"ተሽሎታል ። "

"እና ምን ሆኖ ነው ወገቡን ይዞ የሚንጎራደደው?"

"ድንገት አማራ ክልልን የደፈሩት የሱዳን ወታደሮች ጉዳይ አሳስቦት ይሆናል "

"ሚኪ እውነት ደረጄ ተሽሎታል ?" በስልምልም አይኖቿ እየተመለከተች ደግማ ጠየቀችኝ።

"ምን ሆነሻል ?...ተሽሎታል አልኩሽ እኮ.. .አሁን ማስታወስ ጀምሯል "...

"እየው ደግሞ ወደኛ እየመጣ ነው "

ዞር ስል ደሬ ወገቡን ሳይለቅ ቀጥ ብሎ ወደኛ አቅጣጫ መጥቶ ቆመ ። ቆሞ ለደቂቃዎች አሰበ ...

"እኔ ምልሽ? " አላት ባለቤቱን 

"ወዬ የኔ ጌታ "

"ሚኪ ምን ሆኖ ነው ዛሬ የቀረው?😃 እኔ የገዛሁትን በግ ላለማየት ምቀኝነት ይዞት ነው አይደል? "

ተሽሎታል ያልኩት ደሬ አጠገቤ ቆሞ ሚኪ ለምን አልመጣም ማለቱ አስደንግጦኝ አንገቴን ደፋሁ.. .

"ታድያ አሁን ህክምና መሄድ የለብንም ትላለህ? " ቀና ስል የደሬ ሚስት አይኖች በፍርሀት እየተቁለጨለጩ ነበር ...

"የበጉን ገመድ ፈተሽ ደሬን አስረን ነው ሆስፒታል መሄድ ያለብን "....

ሚስቱ ወደ ተገዛው በግ አቅጣጫ ተንደረደረች :)

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Mikael_Aschenaki
፣____የመንደር ወግ_____ ፤

"ሳቅ ብለን ፤ አብረን ሳቅ እንበል"
የመንደር ሎሬት የተከበሩ ጋሽ በረደድ
ጋሽ በረደድ ቤት መጥተዉ አስጠሩኝ። ስወጣ ከበር ተቀብለዉ ፤ ሊገዙ
እንዳሰቡት በግ ዙሪያዬን እየዞሩ ከቃኙኝ ቡኃላ ፤ ላቴን ማንሳት ሲቀራቸዉ "አይ
ቁመና!" አሉ። "ትንሽ ብልጠት ጎሎህ የዥል ገፅ ያዝክ እንጂ ቁመናስ ነበረ። በኛ ግዜ ብትኖር ፤ 'ክቡር ዘበኛ' ሰተት ነበር የምትል ፤ አይ መለሎ!" አሉ ፤
ፈገግታቸዉን እያሳዩኝ። "ሞዴል ሊያረጉኝ ነዉ እንዴ?" ግር ባለዉ ድምፅ፤ የግዴን ቀለድኩ። "አይ ድምጥ አሉ!" 'ፅ'ን ፊደል በ 'ጥ' እየተኩ " ድምጥህ ቁጭ የ'ምንሊክ ወሰናቸዉን'፤ እስኪ ደግመህ ጠይቀኝ?"
ደገምኩላቸዉ፤ "ደግ ዛዲያ ባረግህስ ምን ያንስሃል? አብሶ ፍራፍሬ ብታለማ ፤ ይህን የብቅል አዉራጅ ቁመናህን እየተጠቀምክ፤ ይህን ረጅም ክንድህን ከዛፍ ዛፍ እየወረወርክ፤ ይህን፡ቢዘፈንለት የማያንስዉ የእግር ቅልጥምህን እየሰነዘርክ... አረ እንዲያዉም ካሻህ በዚህ ቅልጥምህ ምድር ቆመህ የኮሪያ ካራቴ ሰንዝረክ ፍሬ እያረገፍክ... ፤ጥሩ ሞዴል አርሶ አደር ይወጣህ ነበር። " ኮስተር ብለዉ ሲመክሩኝ ሳቅ ያዘለ ገፄን የግድ አኮሳተርኩ። " አይ ገበሬ ለመሆን ሳይሆን ይሄ ጥሩጥሩ እየለበሱ በመድረክ ለይ ለሰዉ የሚታዩትን አላዩም?"ጠየኳቸዉ።
" ከንቱ !ልብስ የተሰጣበት አሸንጉሊት መሆን ኖሯል ምኞትህ? " ፊታቸዉን
አጨፍግገዉ ቀጠሉ "የአንተ መሻት ከሆኑት መሀል ፤ ባለፈዉ አንዱ በቴሌብዢን ሲያወራ ሰምቼዉ፤ እኔ የይች የደርጊቴን 9 ጣሳ ጠላ ጠጥቼ እንደነሱ ነገር አልስትም" ስስቅ አዩኝና "ሙት ! የይች የደርጊቴ ጎረቤት ፤ የባዚቴ ትንሹ አፍ ያልፈታዉ ልጅ ፤ እሱ ሲኮለታተፍ መስማት ጣዕም አለዉ። ያ አጊጦ መጥቶ ከተለፋደደዉ ይልቅ። "
እየተሳሳቅን ወደታች ወረድን፤ እሳቸዉም ወጉን ቀጠሉ "ይቺ መንደር ጥንት ጥንት ሳይዘሩባት ታበቅል ነበር። ሞሎቶልህ የተከልክ እንደሆን ፤ እሸት በቆሎ ብትተክል ገሚሱ እሸት ለይ ጤፍ ፣ ገሚሱ ለይ ስንዴ ፣ ገሚሱ ለይ ማሽላ ያዝል ነበር። የበቆሎዉ አገዳ ደግሞ እንደ ሸንኮራ ግጠህ ብትበላዉ ትችል ነበር። ዛዲያ ለከብቶቻችን ክብር ስለነበረን ለ'ነሱዉ እንተወዉ ነበር። አቤት ደጉ ዘመን!" በሀሳቡ የሰመጡ ከመሰሉ በኃላ ወጋቸዉን ቀጠሉ " ጓሮዬ ለይ ሽንኩርት አለማ ነበር። ዛዲያ የሽንኩርቱን ሽፍንፍን ልጬ ሳበቃ ዉስጡ ለይ አንዳንዴ ሎሚ ፤ አንዳንዴ መንደሪን አገኝ ነበር። ያሁን ልጆች እቃ ዉስጥ ደብቃቹ ስጦታ የምትሰጣጡበትን ዘዬ ምድሪቱ ነዉ ያመጣችዉ። " መገረሜ ምንም ሳይመስላቸዉ ቀጠሉ " ትልቀቱንስ ብትል ፤ አንዱ የሽንኩርት ራስ ከ ህፃን ልጅ ራስ ይገዝፍ ነበር።" "አረ ጋሽ በረደድ... " አልኩ የሚነግሩኝ ማመን ሲከብደኝ፤ "ይሄ ደንቆህ ነዉ? እንዲያዉም አያቴ ሲነግሩኝ፤ በነሱ ዘመን 'እንጀራ የወደብቅህ እንደሆን እንጎቻ ትመርቅልህ ነበር' ብለዉኛል"
" ማነች ምትመርቀዉ ?" እየሳቅኩ ጠየኳቸዉ
" ምድሪቱ ነቻ! ለምሽቴ ይህን ከነገርኳት ዕለት ጀምሮ ለብዙ ግዜ ምጣድ
ባሰማች ቁጥር እንጀራ ወደመሬት ትጥልና እንጎቻ ትጠብቅ ነበር። ዛዲያ አልሆን ሲላት ከነአያቴ ወረፈችኝ። እኔም ለስለስ ብዬ" ተይ አለሜ ጡር አትናገሪ ዘንድሮ እንጀራዉስ መች እንጀራ ሆነና ነዉ እንጎቻ የሚመረቀዉ? የፈረንጅ መዳበሪያ ነፋፍቶት መልከኛ ሆነ እንጂ ከጥንቱ እንደማይስተካከል ተዘንግቶሽ ነዉ?" አልኳት። " ዘወር ብለዉ አይተዉኝ ቀጠሉ "እሷ ታዲያ በጄ አላለችም። እንዲያዉም ሲብስባት 'ከነ አያቶት ይነፉ' አለችኝ።" ሳቄን እንደምንም ያዝኩት። "የሜዳ አህያ ይንፉትና!" አልቻልኩም በረጅሙ ሳቅኩ። "ጉድ እኮ ነዉ አግብቼ ምኖረዉ" አሉኝ ጥርሳቸዉን እያሳዩኝ። ትዝ ሲለኝ ጠየኳቸዉ ፤ " ለምን እንደፈለጉኝ አልነገሩኝም እኮ?" አልኩ፤ ያ ሁሉ ሙገሳቸዉ ትዝ ብሎኝ እየጓጓዉ
"ከዘኑዬ ቤት ፖፖዬ እንድታወርድልኝ ነበር።" አሉኝ እኔም እንደሚስታቸዉ በዉስጤ ተሳደብኩ "ጋሽ በረደድ ከነአያቶት ይነፉ!"
ይቀጥላል...
የሚቆም ታሪክ የለም...

@getem
@getem
@paappii

#nicola nas
Forwarded from Mykey (Mikiyas Liyew Mykey)
ንሴብሖ ለእግዚአብሔር ስቡሐ ዘተሰብሐ
መልካም በዓል!
ሚያዚያ 11/2012
@Mykeyonthestreet
ያለፈ የሚባል የለም፤ በዛሬ ዉስጥ የሚላወስ ትላንት እንጂ...
ዞሮ ዞሮ ከያለፈዉ የቀጠለ
****
ክፍል 2
*
"ሳቅ ብለን ፤ አብረን ሳቅ እንበል!"
የተከበሩ የመንደር ሎሬት ጋሽ በረደድ
... ያ ሁሉ ሙገሳ ፖፖዬ ለማዉረድ እንደነበር ስረዳ ነደድኩ። የሆነዉ ሆኖ ግን ከጋሽ በረደድ ጋር ወደ እትዬ ዘኑ ቤት መሄድ ቀጠልን። በመንገዳችን ለይም እትዬ አለሜ ማስክ አርገዉ ፤ ነጭ ጓንት አጥልቀዉ ጎመን ይቀነጥሳሉ። ዘበናይነታቸዉን አድንቄ ሳልጨርስ ፤ በቅንጠሳቸዉ መሀል አጠገባቸዉ ካኖሩት ብልቃጥ ወደ እጃቸዉ ይደፉና ያፋትጋሉ። ግር ብሎኝ ወደ እሳቸዉ አተኮርኩ።
አወቅኩት ፤ ሳኒታይዘር! ጋሽ በረደድም እንደኔ እያስተዋሏት ኖሮ " አንቺ አለሜ" ተጣሩ ። "እመት " አሉ ፤ እትዬ አለሜ።
"ባልተቤትሽ ባይረስ ሲያገሳ እንዲዉል ነዉ ይህን የምትቀቢለት?" አሉ፤
በእጃቸዉ በብልቃጥ ወደተቀመጠዉ ሳኒታይዘር እየጠቆሙ። "እርሶ እንደወዉ... ለራሶት ሊሞቱ አንድ ሀሙስ ነዉ የቀሮት፤ ምናለ ደግ ደጉን ቢያወሩ? " አለ እትዬ አለሜ " ወግጅ ፤ አንቺ ከገጠር ዘንቢልሽን ይዘሽ ፤ እደተንከረፈፍሽ ስትመጪ እኔ ገና ከ'ናቴ ጀርባ አልወረድኩም ነበር። ይሄ ተዘንግቶሽ ነዉ? " አሉ ወደ'ሷ እያዩ። "አዬ..." እትዬ አለሜ ሳቁ፤ "ባንቀልባ ታዝለዉ የነበረዉን ማስታወሶ ድንቅ ነዉ" አሽማጠጥዋቸዉ።
" ስማኝ ሸግዬ" ፈገግ ብለዉ ወደ'ኔ ዞሩ ፤ግን ዛሬ ሰዉ ሁሉ ለምንድነዉ
የሚያቆላምጠኝ? እትዬ አለሜ ቀጠሉ " አጤ ልብነ ድንግል ምድርን ጦር አዉርጅ እያለ ሲያስገርፍ ፤ ጋሽ በረደድ "ተዉ ምድሪቱ የተቆጣች እንደሆን ጉድ ይፈላል!" ብለዉ ይመክሩ እንደነበር ሰምተሃል?" ጭንቅላቴን በአሉታ ወዘወዝኩ። "ወመዘክር ተሰንዶ ተቀምጧል አሉ ፤ የእሳቸወ ምክሮች።" ማስካቸዉን አስተካክለዉ ቀጠሉ"ምክራቸዉ ደሞ መሬት ጠብ አይል ኖሮ እንዳሉት አህመድ
ከነጦረኞቹ መጥቶ ምድሪቱ ለይ ጉድ ፈላ።" አሉ "አስታዉስ እስኪ ይህን ታሪክ
አልነገሩህም?" ደግመዉ ጠየቁኝ፤ ደግሜ ጭንቅላቴን በአሉታ ወዘወዝኩ። "
እንግዲያዉስ አፄ ቴድሮስን አጉል ምክር መክረዉ ፤ በወኔ ሞልተዉ
ወደማይችሉት ባለጋራ እንደሰደዷቸዉም አልሰማህማ? " " ምን ትያለሽ አንቺ ሴት!" ጋሽ በረደድ ተቆጡ እትዬ አለሜ እንዳልሰሙ ሁሉ አይናቸዉን ከ'ኔ ለይ ሳይነቅሉ ቀጠሉ "ቅም አያቴ ለአያቴ ነግረዋቸዉ ፤ አያቴ ደግሞ ለ'ኔ ሲነግሩኝ 'ጋሽ በረደድ አጤ ቴዎድሮስን
በምላስ ደልለዉ ወደመቅደላ የሰደዷቸዉ ፤ ከአጤ ዩሀንስ ሰላሳ ጠገራ ብር
ተሰቷቸዉ ስለ ነበር ነዉ' ብለውኛል" አሉኝ ድምፃቸዉን ሆነ ብለዉ የሹክሹክታ
እያረጉት። "በል ና! ታሪክ ሲዛነቅ ቆሜ አላይም!" ጋሽ በረደድ እያካለቡ ወሰዱኝ፤ የእትዬ አለሜ ቀጭን ሳቅ'ም ሸኘን።
በመንገዳችን ላይም ንዴታቸዉ በእኔ ለይ እንዳይጎፈላ እየተጠነቀቅኩ ጠየቅኩ
"እኔ ምለዉ ጋሼ እርሶ ለምን አይጠነቀቁም? እትዬ አለሜን አሏያትም?" "ከአለሜ ጋር መንገዳችን ይለያያል እንጂ እኔም እጠነቀቃለዉ ። ሌት እንየተነሳዉ አየቱል ኩርሲይ ቀራና ዳዊት እደግማለዉ ። ዛዲያ አላሁና እግዜሩ ሲያብሩ ከጭንብልና ጓንት አይልቁም ትላለህ?" የብልጣብልጥ ፈገግታ አሳዩኝ። " እርሶ ጋር እራሳቸዉን አክስመዉ ነዉ የተዋሃዱት?" ሳቅ ብዬ ጠየቅኩ። "ምን አልክ አንተ አፈዛርጢ! ለዚህ ቂጣ ለቀደደዉ አፍህ ለከት አበጅለት እንጂ ፤ አጓጉል ከመለኮት ጋር የምትዳፈረዉን ነገር ያልሰማዉ እንዳይመስለህ " በቁጣ አጉረጠረጡብኝ፤ ኩም አልኩ።
አኳሃኔን አይተዉ ከአፍታ በኃላ እሳቸዉም በመጠኑ ለስለስ ብለዉ ቀጠሉ። "
እንዳንተ ያለዉ ከማስተዋል የራቀዉ፤ ብዙዉ ሰዉ 'ርስበ'ርስ የሚጋጩ
ይመስለዋል። ግን እንዲያ አይደለም። ካወቅክበት በነሱ ልፊያ ዉስጥ ልብህ
ይሰፋ እንደሆን እንጂ ፤ እግዜሩን ትተህ አላሁን ፤ አላሁን ትተህ እግዜሩን ማንሳት
ተላላነት ነዉ።" እኚህ ሰዉዬ ይፈላሰፋሉ ልበል ፤ ሀሳባቸዉ ባይዋጥልኝም ደነቀኝ። እሳቸዉም መገረሜን ከፊቴ ለይ አንብበዉ " ሌላ ቀን በሰፊዉ አወጋሃለዉ ። አሁን ዘኑዬ ጋር እንዝለቅና ፖፖዬ'ዬን አዉርድልኝ ።"
*

ቆሙ ያልናቸዉ ታሪኮች በዛሬ ግርዶሽ ዉስጥ የሚላወሱ እንጂ ሌላ ምንድናቸዉ?
ይቀጥላል....

@wegoch
@wegoch
@paappii

#nicola nas
"በመጨረሻ ሁላችንም ሰላም እንሆናለን። ፀሃይ ለሁላችሁም ብርሃኗን
ትፈነጥቃለች፤ ደመናውም ይገፈፋል"
የ100 ዓመቱ አዛውንት ካፒቴን ሙር
-------------
ካፒቴን ቶም ሙር ይባላሉ፤ እድሜያቸው 99 ዓመት የሞላ የቀድሞ የእንግሊዝ
ጦር አባልና የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ላይ የተሳተፉ አርበኛ ናቸው።
የአንድ መቶ ዓመት ዕድሜአቸውን ለማክበር የተወሰኑ ቀናቶች ሲቀሯቸው የኮሮና ቫይረስ ሃገራቸውንና ዓለምን መናጥ ጀመረ። ይሁን እንጂ ካፒቴኑ "የ100 ዓመት የልደት በዓሌን በማስመልከት የአትክልት ሥፍራዬን ስፋት አንድ መቶ እጥፍ እጓዛለሁ። እግረመንገዴንም ለእንግሊዝ የብሔራዊ ጤና አገልግሎት/NHS/ ሠራተኞች ድጋፍ የሚሆን 1,000 ፓውንድ እሰበስባለሁ" ብለው ጉዟቸውን
ጀመሩ። በካፒቴኑ በጎ ሃሳብ ልባቸው የተነካ ሰዎች ከመላው ዓለም እጃቸውን ዘረጉ። 1,000 ፓውንድ ለማሠብሠብ ያቀዱት ካፒቴን ጉዟቸውን ሲያጠናቅቁ 20 ሚሊዮን ፓውንድ ሠበሠቡ። መላው እንግሊዛዊ በሽማግሌው ካፒቴን ድርጊት ልቡ ተነካ። በ24 ሰዐት ውስጥ 500,000 የሚደርሱ ሰዎች የሃገሪቱ ከፍተኛ ማዕረግ የሆነውን Knighthood እንዲሰጣቸው ፔቲሽን ተፈራርመዋል።
መልካም ለመሆን ቅን መሆን ብቻ ይበቃል። ሌላው ያንን ተከትሎ የሚመጣ
ነው። 👏
----------
Capitain Moore said to everyone struggling during the
coronavirus pandemic that “at the end of the day we shall all
be ok. The sun will shine on you again and the clouds will go
away”.

ምንጭ: ።ዘ-ኢንዲፔንደንት

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Tilahun ango
''የባለቅኔው ኑዛዜ መግቢያ በጥቂቱ''
ሃሳብዎን በዚህ ይላኩልን! @Mykey21
@gebriel_19
@Nagayta
@Wegoch
@Wegoch
@Wegoch
#ወግ_ብቻ

ታክሲ ውስጥ ገብታ ልትቀመጥ ስትል ከወደኋላዋ ድምፅ ሰማሁ "ጡ.....ጥ"
ከሷ ፊት ስለተቀመጥኩ በመገረም ዞር ስል በሀፍረት ጥሬ አክላ አገኛታለሁ ያልኳት ባለድምፅ እኔ ላይ አፍጣ "ምነው? ስምህ ነው እንዴ?" አለችኝ ።
"ስም ያለው ሞኝ ነው" ደገመችኝ። (ገፅ 21)
ሰውና ጠመንጃ
ገበሬው ከሾፌሩ ግራሶ ተቀብሎ አልሰራ ያለውን ጠመንጃ እየጠራረገ ነው። የአፈሙዙ አቅጣጫ ወደሱ መሆኑ ያሳሰበው ሾፌር
" አፈሙዙን ወደዛ አዙር እንጂ "
" ምነው በሰራልኝና ባነበቀህ" (ገፅ 80)
"#ውልብታ" ከአለማየሁ ገላጋይ
@wegoch
@wegoch
@wegoch
#የደሜ ዜመኞች

ክፍል - ፮
ቀጥያለሁ....

በትዝታ ንጉደት ህመሜን ታማችሁ ኋላዬ ነውና አሁን ላለሁበት ምክንያት
አሁንም ከጎኔ ሁኑ በደም ዜማዬን እየሰማችሁ
ትዝታ ከፉ ነው መቼም ያሰቃያል የኔ ስቃይ ሲበዛ ከፍ ያለ ንዝረት በአካሌ ላይ ሀይለኛ ምት ያደርሳል ነርቬን ነክቶ የንዝረቱን መልስ በአፍንጫዬ ቀዳዳዎች ይመለሱልኛል መልሶቹም ጠብታዎቼ ናቸው ንዝረቱ ክፉ የሆነነ ህመም ውስጥ ስለሚከተኝ ፋታ ለመውሰድ ዜማን እከፍታለሁ ስቃዬም በረድ ሲል ዜማውን ቀነስ አድርጌ በትዝታዬ እጮሀለሁ
ወደ ትዝታዬ ተመልሻለሁ .....
ፍቅሯ በመቅሰፍቱ እየመታኝ ይገኛል ሁሉ ነገሬን ነጥቃ እሷ ዘንዳ አስቀምጣዋለች ስትመጣልኝ ነው እራሴን ማገኘው
ፊያሜታዬ ነፍሴ ሆናለች....
በቃ ከሚከተሉኝ ጓደኞቼ የበለጠ እሷን ከጎኔ አድርጌ መንቀሳቀስ ጀምሬያለሁ እኔ ካለሁ እሷ አለች ባለሁበት ቦታ ሁሉ ከጎኔ አድርጌ ይዣት መዞር ጀምሬያለሁ
ተማሪውም አውርቶ አውርቶ ሰለቸው መሰል አሁን ስለ እኔ እና ስለሷ መወራቱ ቆሟል ተለምደናል እኔ እና እሷም ተላምደናል
ብዙ ቀናቶች ሆኑን አሁንም ከኔ ዘንድ ነች
ፊያዬ እንዴት እንደሆነ ባልነገረቺኝ ሁኔታ ቢዝነሱን ተቆጣጥራዋለች
ሙሉ በሙሉ በሚቻል መልኩ ሴት ተማሪዎች በእቅዴ ውስጥ አስገብታልኛለች
ከኔ ጋ ከሚሰሩት ወንዶች ሁሉ ብዙ ገቢ ምታስገባልኝ እሷ ሆናለች
ካፒታሌም በደንብ ጨመር ብሏል ....
ለሷ ምቆርጥላትን ነገር ሙሉ ለሙሉ ትቼዋለሁ አሁን ላይ እኔ ማለት እሷ ስለሆነች የኔ የሆነው ሁሉ የሷ ሆኑአል በቃ
ምታመጣልኝን ገንዘብ ለራሷ እንድትጠቀመው ነግሬያታለሁ በቃ ግድ የለኝም ገንዘቡ አሁን ላይ ለኔ ምንም ነው እሷ ደሞ ብዙ ነገሬ ናት
ኑሮዬን ከቤተሰቤ ጋ ቢሆንም የራሴ የምላት ቆንጅዬ ቤት ነበረቺኝ ብዙ ነገሮቼን ማስቀምጠው በቤቴ ነው ምቆዝምባት ትንሽ መሸሸጊያ ቤት ነበረቺኝ
ፊያሜታዬን እዛ ይሻት ለመሄድ ወሰንኩ ቀኑን እኔ እና እሷ ብቻ እንድናሳልፈው ከሰዉ አይን እራቅ ብለን በትንሿ ቤቴ ትልቅ ፍቅር ውስጥ ለመግባት አሰብኩ
ከሷ ጋ.....
ወደ ማታ ደወልኩላት ዛሬ አኩርፋብኛለች ትንሽ ደብሮኝ ነው ኘለቺኝ
ቶሎ ለመናገር ወስኜ አፈነዳሁት ምንም ሳታቅማማ ተስማማች
ግን ምን አባህ አስበህ ነው ብላ በጣም አሳቀቺኝ ጥያቄው ስለገባኝ እኔም ያን ያህል መፍጠን እንደማልፈልግ ነግሬ ቃል ገብቼ ለነገው የፍቅር የድግስ ቀኔ ማሰብ ጀምርኩኝ
ምን ማድረግ እንዳለብኝ ባላውቅም ቤቴ ባለችበት ንፁህና ቆንጆ ስለሆነች ስለ ቤቴ ማሰቡ አላደከመኝም
ብቻ እስኪነጋ ቋምጫለሁ በእቅፌ እስካሞቃት ጓጉቻለሁ እኔ እና እሷ ብቻ
በቃ አይኔ ላይ ነው.....
ትንሽ ዜማ ልክፈት ወደ ንፁህ ቤት ከመግባቴ በፊት ትንሽ ጠብታዎቼን ላፅዳ
                  ትናንትናን ጥሶ ዛሬን ተንተርሶ
                  ነገንም ተውሶ አምናንም አድሶ
                  ይመጣል ትዝታሽ ጓዙን አግበስብሶ
አዎን በትናንት ጥሰት ውስጥ ዛሬን ተንተርሼ ትውስታ መመለሻዬን ዛሬ በትናንቱ ትዝታዬ ከትቼ ነገዬን ማስተካከል ስለምፈልግ ነው እንዲህ  በስቃይ ውስጥ ያለሁት
ትንሽ ትዝታዋን ስሻ ጓዙን ጠቅልሎ መቶ ያሰቃየኛል
በቃ ትዝታ ስቃይ ነው አቦ
እመለሳለሁ......

               እቀጥላለሁ....
     ብላቴናው በደም ቀለም

@wegoch
@wegoch
@wegoch
''የባለቅኔው ኑዛዜ''
ክፍል ፩
ፋሲካ ከበደ እንደፃፈው


@Wegoch
@Wegoch
@Wegoch
2024/09/25 12:21:38
Back to Top
HTML Embed Code: